Monday, October 20, 2014

ሰበር ዜና፡-ማኅበረ ቅዱሳን ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተገንጥሎ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ለመመሥረት እየሠራ እንደሆነ ማስረጃ እንዳላቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አስታወቁ፡፡

ምንጭ፡-http://www.tehadeso.com/

 •  READ IN PDF
 • ማኅበረ ቅዱሳን ገንዘብ የሚሰበስበው በሕገ ወጥ መንገድ ነው፡፡ 
 •   ወይ ከቤተ ክርስቲያን ወይ ከመንግሥት ካልሆናችሁ ለሳራችሁም አዳጋ ነው፡፡
 •   የሀገረ ሰብከት ሥራ አስኪጆች ስለማኅበረ ቅዱሳን በሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ሪፖርት የሚያቀርቡት የማስታወቂያ ሥራ እንዲሠሩለት ስለተከፈላቸው ነው፡፡
 •   ከማኅበረ ቅዱሳን የምትቀበሉት ገንዘብ “እርጥባን” ነው፡፡
 •   ቤተ ክርስቲያን አባላት ትመዘግባለች፤ ማኅበረ ቅዱሳንም አባላትን ይመዘግባል፤ ቤተ ክርስቲያን ከምእመናን ዐስራት ትቀበላለች፤ ማኅበረ ቅዱሳንም ከአባላቱ ፐርሰንት ይቀበላል፤ ስለዚህ ሁለት የተለያዩ ቤተ ክርስቲያኖች ተፈጠሩ ማለት አይደለምን?
 •   በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ሰብስቦ የሠሩትን ሥራ ሪፖርት መቀበል ወንጀል ነው፡፡
 • በማኅበረ ቅዱሳን አመራር አባላት ተጸልዮብኛል፡፡
 • ማኅበረ ቅዱሳን በአሜሪካ ሌላ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊመሠርት እየሠራ እንደሆነ ማስረጃ ደርሶኛል፡፡  (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ)

33ተኛው መደበኛ አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ አስገራሚና አሳዛኝ ክስተቶችን በማስተናገድ ተጠናቀቀ፡፡ ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ/ም ተጀምሮ ጥቅምት  8 ቀን የተጠናቀቀው 33ተኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከፍተኛ መከፋፈል የታየበት መሆኑን ምንጮች አረጋገጠዋል፤  ማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል! ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተለይ ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ በመግቢያ ንግግራቸው ያሰሙት አባታዊ መመሪያ ውይይት እንዳይደረግበት አቡነ ማቴዎስ ስብሰባውን በተራ ነገሮች ሳይቀር በማጓተት ከፍተኛ መሰናክል ሆነው ቆይተዋል፤ በመጨረሻው ቀን “ውይይት ሳይደረግ ስብሰባው አይዘጋም” የሚል አቋም የያዙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በስብሰባው ላይ ሁሉንም ያስገረመ፤ የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊዎችንንና አባላቱን አፍ ያስያዘ ( ዝም ያሰኘ) አስደናቂ ንግግር አድርገዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  እንዳሉት “ማኅበረ ቅዱሳን ገንዘብ የሚሰበስበው በሕገ ወጥ መንገድ ነው”፤ ስለዚህ በየስድስት ወሩ ቀድሞ ለሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አሁን ደግሞ ለጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት ለቤተ ክህነት አቀርባለሁ የሚለውን ተራ ነገር መቀበል አይገባም፤ ምክንያቱም ምንጩ ባልታወቀ ወይም በሕግ ካልተፈቀደ ምንጭ ገንዘብ ሰብስቦ የሠሩትን ሥራ ሪፖርት መቀበል ሕገ ወጥ የገንዘብ ምንጭን ተጠቅሞ መሥራትን ማበረታታት ስለሆነ ነው” ብለዋል፡፡  

ዶ/ር ሙሉጌታ (በቅስናው ስለማናምን ቀሲስ የሚለውን አልጨመርንም) ተነሥቶ በሚያባብል ቃል ትሑት በመምሰል ጉባኤውን አቅጣጫ ለማሳት ሙከራ አድረጎ አልተሳካለትም፤ ፓትርያርኩ ንግግሩን እንዲያቆም ጠይቀው “ቅዱስ አባታችን ጠርተው ሳያነጋግሩን ለምን በዚህ ስብሰባ ላይ ይወቅሱናል?” ሲል ላቀረበው ተራ ጥያቄ ፓትርያርኩ ለመመለስ በሚያሳዝንና በሚገርም መልኩ ተናግረዋል፡፡ ማሳዘኑ  የማኅበረ ቅዱሳን  አመራር አባላት አቡነ ጳውሎስ እንደሞቱ እኒህ አባትም ቢሞቱላቸው የሚፈልጉ መሆኑን በፊታቸው መናገራቸውን ፓትርያርኩ ለጉባኤ ማረጋገጣቸው ነው፤ በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ አስተዳዳሪ አስቀድሞ ፍንጭ የተሰጠውን ይህን ሐሜት ቅዱስ ፓትርያርኩ እውነት መሆኑን “ተጸልዮብኛል” ሲሉ ነበር ያረጋገጡት፡፡ “ተጸልዮብኛል” ማለት እንድሞት ጸሎት ተደርጎበኛል ማለት ነው፡፡ አስገራሚው ነገር ደግሞ ፓትርያርኩ መልስ ሲሰጡ ስለ ማኅበሩ ሕገወጥ አሠራር ያላቸው ግንዛቤና አሳባቸውን በጣም በግልፅና በድፍረት ማቅረባቸው ነው፡፡ ብዙ ተሳታፊዎች ፓትርያርኩ መንፈስ ቅዱስ ያናገራቸው መሆኑን እንደሚምኑ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ተቃዋሚዎችና የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ጥንካሬ ሳይሆን መከፋፈልና መዳከም የሚፈልጉ ግን አብደዋል እያሉ ሲሳለቁባቸው ነበር፡፡ የፓትርያርኩ ንግግር ጊዜውን ጠብቆ መገለጡ ግን አይቀርም፡፡
ዶ/ር ሙሉጌታ አንተ ስለሌለህ ነው እንጂ ቢያንስ ሦስት ጊዜ አነጋግሬያቸው አለሁ፤ አንድ ቀን ከተወያየን በኋላ አሳባቸውን እንደማልቀበላቸው ስገልጽላቸው የቀድሞው ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ከእኛ ጋር ሲዋጉ እግዚአብሔር ወሰዳቸው፤ እግዚአብሔር ምናለ እኒህንም ቢወስዳቸው ብለው ጸልየውብኛል፤ “ተጸልዮብኛል” ብለዋል፤ አስከትለውም  “ነገሩን ከቁም ነገር ቆጥሬው ሳይሆን እንዳነጋገርኋቸው ለመግለጥ ነው” ሲሉ  ምን ያህል የማኅበሩ አመራር አባላት የአባቶቻቸውን ሞት የሚመኙ አስቸጋሪዎች እንደሆኑ አሳይተዋል፡፡
ጉባኤው ይህን ሲሰማ በጣም ነበር ያዘነው፤አንዳንድ ግብረ-በሎችም ለማኅበረ ቅዱሳን  ወግነው ሲሞግቱ ቆይተው የማኅበሩ ክፋት በዚህ መልኩ ሲገለጥ ደንግጠው ዝም ብለዋል፡፡ ማኅበሩ ነፍሰ ገዳይ ነው ሲሉ የብዙ ሰዎች ደም ከማኅበሩ እንደሚፈለግ ብዙ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሲናገሩት የቆዩት ነገር በፓትርያርኩ በዚህ መልኩ መገለጡ በእርግጥም ማኅበሩ ክፉ መሆኑን አሳይቷል፡፡
 ከሳምንት በፊት በተደረገው የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያዎች ኀላፊዎችና ምክትል ኀላፊዎች ስብሰባ ላይ አቡነ ማቴዎስ “አቡነ ጳውሎስን የገደሏቸው አሁን እርስዎን የሚያማክሩ ሰዎች ናቸው” ሲሉ ለተናገሩት ቃል እነ አባ ሰረቀ “አቡነ ጳውሎስን የገደላቸው ማኅበረ ቅዱሳን ነው” ሲሉ ተከራክረው ነበር፡፡ በዕለቱ ስበሰባውን የተከታተሉት አንዳንድ ሰዎች  “አቡነ ጳውሎስን የገደላቸው ማነው? ማኅበረ ቅዱሳን? ወይስ ሌላ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ነገሩ ምን ያህል ውስብስብ ችግር በቤተ ክህነት እየተፈጠረ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን ግብረ በሎች የሆኑ የሀገረ ስብከቶች ሥራ አስኪያጆች “በየ ሀገረ ስብከቱ ማኅበረ ቅዱሳን የሠራውን  ሥራ ሪፖርት አቅርበናል፤ እናንተ ለምን ትቃወማላችሁ? ሲሉ ላቀረቡት ጥያቄም ፓትርያርኩ “እናንተ ሪፖርት የምታቀርቡላቸው ስለከፈሏችሁ ነው፤ የማስታወቂያ ሥራ እንድትሠሩላቸው ከፈሉአችሁ፤ የማስታወቂያ ሥራ ታውቃላችሁ፤ አንድን ምርት ለማስተዋወቅ ገንዘብ የተከፈለው ድርጅት አጋንኖ ጭምር ምርቱን ያስተዋውቃል፤ እናንተም ስለተቀበላችሁት ብር ለማኅበሩ በዚህ መድረግ ታስዋውቃላችሁ አንጂ ሪፖርቱ ቤተ ክርስቲያንን የሚወክል አይደለም” ሲሉ ተቃውመዋል፡፡
ማኅበሩ ጥፋት ካለበት እራት እንዲጋብዝ ለምን ፈቀዳችሁለት? እናንተም አብራችሁ አጥፋ እያላችሁን ነውን? ሲል አንድ ተሳታፊ ላቀረበው ጥያቄ ደግሞ “የራሳችሁ ገንዘብ ነው፤ ከእናንተ ወስዶ ነው ለእናንተ የሚሰጣችሁ፤ ማኅበሩ ከየት አመጣው? በቤተ ክርስቲያን ስም በሕገ ወጥ መንገድ ከምእመናን የሰበሰበው አይደለምን? ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ንግግራቸውን ለሰማውና ሁኔታውን በአካል ለታዘበ ሰው ነገሩ በጣም የሚገርም ክስተት ነበር፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች በግልጥ ታውቀዋል፡፡ 
የሁሉም ተሳታፊ ቅስም የተሰበረውና ሁሉም የማኅበሩ ደጋፊ አንገቱን የደፋው ግን “ማኅበረ ቅዱሳን ሌላ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ ሊያቋቁም እየሠራ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ እንደረሳቸው በገለጡበት ወቅት ነበር፤ በመክፈቻ ንግግራቸው “እኔ የተመረጥሁት አንዲትን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ለመምራት ነው፤ ሁለት ቤተ ክርስቲን የለቺም” ሲሉ የተናገሩበት ምክንያት ለካስ ይህ ማስረጃ ስለደረሳቸው ነበር፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊዎች እባካችሁ ቆም ብላችሁ አስቡ! ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያንን አዳጋ ላይ ሳይጥላት በጊዜ ሃይ በሉት፡፡ ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያንን ሊከፍላት ነው በማለት ለቤተ ክርስቲያን እድገት የሚሠራ ነገር ግን ደካማ የተሐድሶ እንቅስቃሴን ለቤተ ክርስቲያን አደጋ አስመስሎ እንደጭራቅ አግዝፎና አክፍቶ ሲሰብክ የኖረው ለካስ ይህን ደባ ደብቆ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲንን ከዚህ አይነት አዳጋ ያድልን፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በቁጥጥር ሥር ሊውል ይገባል የሚል እምነት ያላቸውና ይህንኑ ደጋግመው ሲያሰሙ የነበሩት ቅዱስ ፓትርያርኩ በዚህ አቋማቸው ተግተው ከቀጠሉ በእርግጥ ማኅበረ ቅዱሳን ወይ በህግ ይገዛል ወይ ከቤ ክርስቲያን ጀርባ ላይ ወርዶ ወደ አጼ ሚኒሊክ ሰፈር ይገባል፡፡
ሌላው አስገራሚ ድራማ ደግሞ የማህበሩ ደጋፊዎች አባልነትም ሆነ ተሳታፊነት ሳይኖራቸው ሾልከው በመግባት ፓትርያርኩን ለማሳቀቅ በሲኖዶስ የተወሰነን ውሳኔ እንቀበላለን፤ ፖፕ አይሳሳትም በማለት የፓትርያርክን ውሳኔ የምትተገብር ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ናት፤ እርስዎ ይህን ያህል ስልጣን የለዎትም፤ ሲኖዶሱ የሚወስነው ማስፈጸም ነው እንጂ እንደካቶሊክ ፖፕ ስልጣን አለኝ ብለው ይህን ያህል ሊሠሩ አይገባም በማለት ፓትርያርኩ ማኅበርን ለመቆጣጠር የሚበቃ ስልጣን እንደሌላቸው የሚያስመስል እንደሌላቸው በመንገር መንፈስ መመሪያ ሊሰጥ የሞከረውን ሙከራ አንድ የሊቃውንት ጉባኤ አባል የመለሰበት መንገድ ነበር፡፡ ሊቁ እንዳለው ዲዲስቅልያ “ወይፍርህዎ ለሊቀ ጳጳስ ከመ እግዚአብሔር” ማለትም ሊቀ ጳጳሱን (ፓትርያርክ ማለት ነው) እንደ እግዘኢበሔር ይፍሩት ማለት ያክብሩት ይላል አንተ ዲድስቅልያውን ሽረህ ይህን ትምህርትና ተቃውሞ በድፍረት በፓትርያርኩ ላይ ለመናገር ለምን ደፈርህ? ኦርቶዶክሳዊ መሆንህ ራሱ አጠራጣሪ ነው፤ ጀርባህ ሊጠና ይገባል” ሲል አሳፍሮታል፡፡
ይህ ሙግት የተነሣው አባ ሠረቀ ብርሃን የዚህች ቤተ ክርስቲያን አባት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ናቸው፤ ለዚህች ቤተ ክርስቲያን እርሳቸው የክርስቶስ ወኪል ናቸው፤ ሊሰሙ ይገባል” ሲሉ ላቀረቡት አሳብ ማኅበሩ ባሳየው ተቃውሞ ይህ አይነት ትምህርት የካቶሊክ ነው በማለት በለመደው መልኩ እርሱ የሚናገረው ብቻ ኦርቶዶክስ ሌላው የሚናገረው ወይ ካቶሊክ ወይም ፕሮቴስታንት ነው እያለ የሚያስፈራራበትን ስልት ተጠቅሞ በዚህ ጉባኤም ተመሳሳይ ሥራ ሊሠራ በመሞከሩ ነው፡፡
 በጉባኤው ላይ የነበረውን መከፋፈል አንድ ተሳታፊ እንዲህ በማለት ነበር የገለጠው፡፡ “እኔ በዚህ ጉባኤ ሁለት ጊዜያት በጣም አሳዛኝ የሆኑ ነገሮችን ሰምቼ በጣም አዝናለሁ፤ አንዱ በሁለት ሺ ዓ/ም በጂማ የደረሰውን ጥፍጨፋ ሰምተን ተላቅሰን የተለያየንበት ስብሰባ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ዛሬ በማኅበረ ቅዱሳን ምክንያት ይህ ጉባኤ ያሳየውን መከፋፈል ሳይ ነው” ብሏል፡፡ እውነት ነው መከፋፈሉ በጣም በግልጥ ታይቷል፡፡ ሆኖም ግን ፓትርያርኩ በግልጥ እንደተናገሩት መድኃኒቱ መነጋገር እንጂ ዝም ማለት አይደለም፡፡ መወያየት መድኃኒት ነው፤ በዚህ ስብሰባ ማን ግብረ-በላ የማኅበረ ቅዱሳን አባል ማን የቤተ ክርስቲን ልጅ እንደሆነ ተገልጧል፡፡
ከዚህ በኋላ የቤተ ክርስቲን ልጅና የማኅበር ልጅ የሚያደርጉት ትግል ይቀጥላል፡፡ የማኅበሩ ልጅ ነኝ እያሉ እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነት ተቆጥሮ የሚነገረው ተረት ከዚህ በኋላ ወደ ለየለት ክርክርና መፎካከር ተሸጋግሯል፤ የቤተ ክርስቲን ልጆች ከሰማኒያ ሰባት ዓመተ ምህረት ጀምሮ ማኅበሩ ድብቅ ዓላማ አለው፤ ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያንን ይከፋፍላል ሲሉ ሲናገሩት የነበረው ትንቢት የደረሰ ይመስላል፡፡
ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የዚህ ሁሉ ችግር ምክንያቱ ቤተ ክህነትም ሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ከወንጌል ይልቅ ለተረትና ለግል ፍላጎት ሲሯሯጡ ቤተ ክርስቲያን እየተዳከመች መምጣቷ ነው ብላ ታምናለች፡፡ ይህን ለመቅረፍ በጉባኤው ላይ ሲሰማ እንደነበረው መጠነ ሰፊ የስብከተ ወንጌል ሥራ መሠራት አለበት፤ ሥራ የፈታ ካህን ጦርነት ያውጃል፤ መቅደሱን የወንጌል መስበኪያ ሳይሆን የጦርነት አውድማ ያደርጋል፤ እየታየ ያለውም ይህ ነው፡፡ ወንጌልን እንስበክ፤ ሕዝቡን በወንጌል እንምራው፤ ያን ጊዜ የሕዝቡ አይን ሲገለጥ ሕዝቡ የክርስቶስ የሆኑትን የማወቅ እድል ያገኛል፡፡ አሁን ግን ሕዝቡን በድንግዝግዝታ ውስጥ ይዞ ከሕዝቡ በሚሰበሰበው ገንዘብና ስልጣን ላይ ጦርነት በመክፈት ምእመናንን ማሳዘን ተገቢ አይደለም፡፡
·        እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን!
·        ማኅበሩንም ያስተግሥልን!
·        ለአባቶችም ልብ ይስጥልን!
·        ለቅዱስ አባታችን ጥንካሬን፣ ብልሐትንና ትግሥትን ይስጥልን!

38 comments:

 1. የመንግስትን አስተሳሰብ ማስፈጸም አለብኝ ቢሉ አይሻልም፡፡ ማህበሩ ከቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው መመሪያ መሰረትና ወቀቱ በሚጠይቀው አሰራር ገንዘብ መሰብሰብ የጀመረው ዘንድሮ አይደለም ስንት አመት እንደሰራ ይገንዘቡት፡፡ ህገወት ነው ማለታቸው ሊያስከስሳቸው እንደሚችልም ማወቅ አለባቸው፡፡ ለምን ቢባል ቅዱስ ሲኖዶሱን ነውና እየተናገሩት ያሉት፡፡ እነሱ የሚሰጣቸውን ለኢትዮጵያ ህዝበ ምእመን ሪፖርት አያደርጉ አይጠየቁ እንደፈለጋቸው ሲሆኑበት ይታያሉ ያንንም እያደረጉ ሰው መስጠቱን አላቆመም፡፡ ምእመኑኮ ለቤተክርስቲያን የሚያስገባውን ብር ቢጠይቅ የማህበሩን ያክል ያውም በጎ አድራጊዎችና ከደሞዛቸው የሚደረግ አስተዋጽኦ የሰራውን ያክል ሲሰራ አይታይም፡፡ እስቲ ያለውን የቤተክርስቲያንዋን ገቢ ለማህበሩ ግለጡና በዚህ ምን ልንሰራ እንችላለን ብላችሁ ጥይቁዋቸው፡፡ በአንድ ጊዜ ቤተክርቲያናችንን ቀዳሚ የሚያደርግ ነገርን ሳዩዋችሁ ነበር ነገር ግን መዝረፍ ተለምዶ ማን ቁጥጥርን ይፈልጋል ምድረ አስተዳዳሪ ጉዱ ይፈላ ነበር፡፡ ይህንንም የጻፋችሁት ብትሆኑ መናፍቅ ናችሁና ስለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምንም ልታወሩ አይገባችሁም እንላለን፡፡ አላማችሁ ቤተክርስቲያን በመናፍቅ እጅ እንድትሆን ነው ይህ እንዲሆን ማህበሩ መፍረስ አለበት ይህ ደግሞ የሚሆነው እግዚአብሔር ከሌለ ብቻ ነውየመንግስትን አስተሳሰብ ማስፈጸም አለብኝ ቢሉ አይሻልም፡፡ ማህበሩ ከቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው መመሪያ መሰረትና ወቀቱ በሚጠይቀው አሰራር ገንዘብ መሰብሰብ የጀመረው ዘንድሮ አይደለም ስንት አመት እንደሰራ ይገንዘቡት፡፡ ህገወት ነው ማለታቸው ሊያስከስሳቸው እንደሚችልም ማወቅ አለባቸው፡፡ ለምን ቢባል ቅዱስ ሲኖዶሱን ነውና እየተናገሩት ያሉት፡፡ እነሱ የሚሰጣቸውን ለኢትዮጵያ ህዝበ ምእመን ሪፖርት አያደርጉ አይጠየቁ እንደፈለጋቸው ሲሆኑበት ይታያሉ ያንንም እያደረጉ ሰው መስጠቱን አላቆመም፡፡ ምእመኑኮ ለቤተክርስቲያን የሚያስገባውን ብር ቢጠይቅ የማህበሩን ያክል ያውም በጎ አድራጊዎችና ከደሞዛቸው የሚደረግ አስተዋጽኦ የሰራውን ያክል ሲሰራ አይታይም፡፡ እስቲ ያለውን የቤተክርስቲያንዋን ገቢ ለማህበሩ ግለጡና በዚህ ምን ልንሰራ እንችላለን ብላችሁ ጥይቁዋቸው፡፡ በአንድ ጊዜ ቤተክርቲያናችንን ቀዳሚ የሚያደርግ ነገርን ሳዩዋችሁ ነበር ነገር ግን መዝረፍ ተለምዶ ማን ቁጥጥርን ይፈልጋል ምድረ አስተዳዳሪ ጉዱ ይፈላ ነበር፡፡ ይህንንም የጻፋችሁት ብትሆኑ መናፍቅ ናችሁና ስለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምንም ልታወሩ አይገባችሁም እንላለን፡፡ አላማችሁ ቤተክርስቲያን በመናፍቅ እጅ እንድትሆን ነው ይህ እንዲሆን ማህበሩ መፍረስ አለበት ይህ ደግሞ የሚሆነው እግዚአብሔር ከሌለ ብቻ ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ:- (1) ፓትርያርኩን ሾሞ ያስቀመጣታቸው ሲኖዶስ መሆኑን ረሳኸውን??
   (2) ቅዱስ ሲኖዶስ ፓትርያርኩንና ቤተክሕነቱን አትስሙአቸው ብሎአችኋልን??
   (3) ከአባላቶቼ 60 በመቶ ኢህአዴግ ናቸው እያለ የሚያስፈራራው ማቅ አይደለምን??
   (4) ይሄ ማኅበር ሁሉን ካልጠቀለልኩ እያለ በካሕናቱ በጥርጣሬ የሚታይ ከመሆን በቀር እንደልጅነቱ በልጅ መንፈስ ከአባቶች ተስማምቶ ሰርቶ በ22 አመታት በአስተዳደሩ ዘርፍ ምን አበረከትልን??
   (5) ስለ ቤተክሕነት አስተዳደር ድክመት ዘወትር በማውራት ራሱን ትልቅ የሚያደርግ አይደለምን??
   (6) አባቶችን ሰድቦ ለሰዳቢ አልሰጠምን??
   (7) በገሀድ የገሰጹትን በስውር አልዘለፈምን??
   (8) ማቅን ተችቶ ስሙ በበጎ ተነስቶ የሚያውቅ ተመልክተሀል??
   (9) ጥያቄ ባነሱበት ላይ ሁሉ ታርጋ እየለጠፈ አንገት አላስደፋምን??
   (10) በጳጳሳት ቀሚስ ስር ተደብቆ ፓትርያርኮቻችን ላይ ምላሱን ሲያወጣ አልኖረምን??
   ማዕተብ ያደረገ ኦርቶዶክሳዊ ሁሉ የማቅ ደጋፊ አይምሰልህ::እኛ ከቅ/ፓትርያርኩ ጋር እየተነታረከ በሲኖዶስ የሚያስፈራራ የትልቅ ህጻን አንፈልግም::እሳቸውን ካላከበራችሁ የፈለጋችሁበት መድረስ ትችላላችሁ::ያለ ጳጳስም ኖረናል እንኳንም ያለ ጨቅላ ማኅበር::
   እናንተን ብሎ ፓትርያርክ ከሳሽ!!የመምሪያነት አቅምና የቤተክርስቲያን ውክልና ሳይኖራችሁ የትኛውም የመንግሥት ፍርድ ቤት መቆም እንደማትችሉ እያወቃችሁ አጓጉል አቧራ አታስነሱ::አሁን ባለው ሁኔታ ማኅበሩን ሊቆጣጠርና ከቤተክርስቲያን እንዳያፈነግጥ ሊያደርገው የሚችል ሕግ ሊቆምለት ግድ ነው:: ገለልተኛ ሚዲያ እንኳ እንድናጣ አድርጎ በግድ የተሐድሶዎችን ሪፖርት እንድናነብ ያደረገን ማቅ ነው::ደግ ደጉን ብቻ እያወራህ አታሞኘን፡፡በጊዜ አደብ የሚያስገዛ ሕግ ካልቆመለት ለ2 ብቻ ሳይሆን ለ4ትም ይከፍለናል፡፡ማቅ ቢሳካለት ኖሮ እኮ አቡነ ጳውሎስን ገና ዱሮ አውርዷቸዋል፡፡አሁንም አቅም ስለሌለው እንጅ ቢሳካለት አቡነ ማትያስን ቢያወርዳቸው ደስ ይለዋል፡፡
   ስለዚህ ቀሲስ ዶክተርም ሆንክ ዲያቆን ዶክተር ገና ለገና የተራቀቀ ጭንቅላት አለኝ እያልክ ባማረ ቋንቋና በውብ አቀራረብ የተደበቀ እብሪትህን በመሰወር ማኅበር ተከልለህ ቅዱስ አባታችንን እንድታሳንስ አንፈቅድልህም፡፡
   እኔ ተሐድሶ አልወድምም አልደግፍምም፣የማቅን በእንግሊዝኛ ተናጋሪነት ያበጠ ትምክህታዊ አካሄድም አልወድም፣የቤተክሕነቱ ሙስናም ያናድደኛል፡፡ነገር ግን ተቋሙን እንደተቋምና አባቶችን እንደ አባትነታቸው ማንም ውርጋጥ በተቆርቋሪነት ሥም ሲያዋርዳቸው ማየት አልፈልግም፡፡ ተሐድሶን እንዋጋለን እያልን ውጭ ውጩን ስንታገል ራሱ ማቅ የአባትና ልጅ መከባበርንና የትህትና ቋንቋችንን በርዞ ድንቅ ትውፊታችንን እየሸረሸረብን ነው፡፡ማኅበሩ ተስተካክሎ መቆም አለበት፡፡
   ወገን ተሐድሶ መዋጋችንን ሳናቋርጥ ይሄን ማኅበርም ልንፈትሸው ይገባል፡፡

   Delete
 2. ወሳኝ የሆኑትን ጉዳዮች ትቶ በጥቃቅን ነገሮች ላይ ማተኮር
  ፓትርያርኩ መስከረም ፳፯ ቀን ጉባዔውን ሲከፍቱ ቀጥለው የተዘረዘሩትን አንገብጋቢ የሆኑ የቤተ ክርስቲያኗን ችግሮችን ዘርዝረዋል
   የምእመናን በቁጥር መቀነስ
   የቤተ ክርስቲያን ሃብት መቀነስና አብያተ ክርስቲያናት መዘጋት
   የቤተ ክርስቲያን እሴቶች ለኢትዮጵያ የሚያበረክቱት ጠቀሜታ መቀነስ
   መዋቅር ዘርግተው ለራሳቸው ጥቅም የሚሯሯጡ ሃላፊዎች መበራከት
   ከቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እጅግ የላቀ መንፈሳዊ ተግባር መጥፋት
   በቤተ ክርስቲያን ስም የሚደራጁ ማኅበራትና ግለሰቦች መዋቅርን አለመከተል
   ማኅበራትና ግለሰቦች ንብረት ማፍራት ላይ መጠመድና አባቶችን መከፋፈል

  በእውነቱ ከሆነ እነዚህ ጉዳዮች እጅግ አሳሳቢዎች ናቸው.: ቶሎ መፍትሄ ካልተሰጣቸው ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር የተጣለባትን አደራ በተገቢው መጠን ልትወጣ አትችልም:: ዳሩ ግን ከጊዜና ከአቅም ውሱንነት የተነሳ እንዲሁም ከመረጃና ማስረጃ እጥረት የተነሳ ሁሉም ችግሮች በአንድ ጊዜ እኩል ትኩረት አያገኙም:: ለአጀንዳዎች ቅደም ተከተል ሰጥቶ መወያየት የሚያስፈልገውም ለዚህ ነው:: አስተዋይና አዋቂ መሪ የሚያስፈልገውም ለዚህ ነው:: ጥሩ መሪ ሁሉንም ችግሮች የሚፈታ ማለት ሳይሆን ወሳኝና አንገብጋቢ የሆኑትን ለይቶ በማውጣት መፍትሄ የሚሰጥ ማለት ነው:: ፓትርያርኩ ችግሮችን ቢዘረዝሩም ካለው ጊዜ አንጻር ትኩረት ሊሰጧቸው የሚገቡ ጉዳዮች መለየት ነበረባቸው:: የምእመናን ቁጥር መቀነስና የአብያተ ክርስቲያናት መዘጋት እንዲሁም የሙስና መስፋፋት ከማኅበራት ጥቃቅን ችግሮች ጋር እንዴት እኩል ይታያል?

  የሚገርመው ግን ረጅም ጊዜ የወሰዱ ጠንካራ ንግግሮች የተካሄዱት ከማኅበራትም በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ብቻ ነበር:: የተወሰኑ የደብር አለቆች (አብዛኛው ችግር ከነሱ ሥራ ጋር እንደሚያያዝ ስላወቁ) የተወረወረውን ‘ጦር’ አቅጣጫ ቀየሩለት:: ፓትርያርኩም ጉባዔው በማስተዋልና በመንፈሳዊነት መወያየት እንደሚያስፈልግ ከማሳሰብ ይልቅ ለጀሮ በሚሰቀጥጡ ስድብ ነክ ንግግሮች የተደሰቱ መስለው ታይተዋል:: መሪ የሌለው ስብሰባ ሆኖ የተነሳበትን «አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግ» መሪ ቃል ሳይመራበት ቀረ:: የአቋም መግለጫ የወጣው ቤተ ክርስቲያኒቷን እያንገላታት ስላለው ስለሙስናና አድሎአዊ አሠራር ወይም ስለምእመናን መባዘንና አብያተ ክርስቲያናት መዘጋት ሳይሆን ስለአንድ ማኅበር ‘ሃብታም’ መሆን ነው:: በመሆኑም የእለቱ ጉባዔ መነሻውና መድረሻው ያልተጣጣሙ ሆነው ቀርቷል:: ይህም ከአመራር ብቃት ማነስ ወይም ከልዩ ዓላማ መኖር ጋር ሊያያዝ ይችላል:: ሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉባዔያት የሚጠሩትና የሚመሩት እንዲህ ከሆነ እጅግ አሳዛኝና ፈታኝም ነው:: ብፁዕነታቸው ትልቁን ጉዳይ ከትንሹ ለይተው ካላወያዩና ከሚመለካተቸው አካላት ጋር አብረው ካልሰሩ የራሳቸውን ወይም የሌሎችን አካላት ፍላጎት ከመከተል የሚያግዳቸው አይኖርም::
  ስሜትን መሠረት ያደረጉ ስሜት ቀስቃሽ ንግግሮች
  ንዴትን: ብስጭትን: ቅሬታን: ተስፋ መቁረጥን: ድካምን: ደስታን ወይም ስኬትን መነሻ ያደረገ ንግግር ሁሉ ስሜታዊ ነው:: አይደለም በመንፈሳዊ ህይወት በዓለማዊ አሠራርም ስሜታዊነት ጥቅም የለውም:: ጥሩ መሪ ማለትም ስሜትን ተቆጣጥሮ ሠራተኞችን ወይም አገልጋዮችን በማስተባበር ዓላማን ማሳካት የሚችል ነው:: ቅዱስ ፓትርያርኩ በልምድ ማጣትም ሆነ በብሶት ወይም በሌላ ምክንያት ስሜትን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ንግግሮችን ከላይ በተጠቀሱት ታላላቅ ጉባዔያት ደጋግመው ተናግረዋል:: ለምሳሌ ያህል ቀጥለው የተዘረዘሩት የፓትርያርኩ ንግግሮች አብይ ናቸው
   የሚሰማኝ ስላጣሁ ከበታች የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት ጋር መወያየት አስፈለገኝ ወደፊትም ዓመቱን ሙሉ አደርገዋለሁ
   ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ ነው የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ሃብት ቀምቷል
   ይህ ማኅበር በቁጥጥር ሥር እንዲውል አሳስባለሁ
   እኔ ይኽን ጉዳይ ከራሴ አወርዳለኹ፤ የቤተ ክርስቲያናችን ገንዘቧ፣ ክብሯ ተወስዷል
   ቤተ ክርስቲያን ከቅኝ ተገዥነት ትውጣ፤ ካህናቱ ከመከራ ይውጡ
   ይህችን ቤተ ክርስቲያን ለመጠበቅ፤ አንዷን ቅድስት፣ ኦርቶዶክሳዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን ልመራ እንጂ ኹለት ቤተ ክርስቲያን የለችም
   እኔ ብቻዬን የምሠራው ነገር የለም፤ በዚኽ መግለጫ እንድትሠሩበት ነው የምነግራችኹ
   በህግና በሥርዓት የማይመራ ማኅበር አሸባሪ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው
   አባ ማትያስ አላበደም፤ መልእክቴን እያስተላለፍኹ ነው ያለኹት፤ መልእክቴን በጸጋ ተቀበሉ ብዬ እማፀናችኋለኹ

  እዚህ ላይ መነሳት የሚገባው ነገር ቢኖር ከዚህ በላይ ለተጠቀሱት ከባድ ንግግሮች የቀረበ መረጃም ሆነ ማስረጃ አለመኖሩ ነው:: እንዴትና በምን ሁኔታና ምክንያት ነው ጠቅላይ ቤተ ክህነትና ቅዱስ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን ሃሳብ የማይጋሩ? ማኅበሩስ የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ሃብት የቀማው እንዴት ነው? ካህናትንስ እንዴትና በምን ሥልጣን ነው በገዥነት የያዛቸው? ለነዚህና ለሌሎችም ትችቶች መረጃም ሆነ ማስረጃ አልቀረበባቸውም:: ይህ ሆኖ ሳለ እንዴት ተደርጎ ነው የፓትርያርኩ ፍላጎት የሚፈጸመው? «ሃሳቤን በጸጋ ተቀበሉት» ማለታቸውም መረጃና ማስረጃ እንደሌላቸው ጠቋሚ ነው:: አሳማኝ መረጃና ማስረጃ ካለ መለማመጥም ሆነ መለመን አያስፈልግም:: ሁሉም አካል ለእውነት ተገዥ መሆን አለበትና:: የቀረቡት ንግግሮች መሠረታቸው በውል ባይታወቅም ከስሜት ግን የጸዱ አይደሉም:: ስሜት ደግሞ አይደለም ለፓትርያርክ ለተራ ክርስቲያንም የተመቸ ወይም የሚጠበቅ አይደለም:: ስሜት የጎበኛቸው ንግግሮች የሰውን እንጅ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለማያስቀድሙ በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች መካከል ክፍፍልን ያመጣሉ:: እልህን ከዚያም ቂምን ከዚያም መጠቃቃትን ይጋብዛሉና::


  ReplyDelete
  Replies
  1. you say right!

   Delete
  2. Good bless you...these bloggers might learn something from this article if they have heart

   Delete
 3. ማጠቃለያ
  ከንግግራቸው እንደምንረዳው ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር መልካም ግንኙነት እንደሌላቸውና በዚህም የተነሳ መንፈሳቸው እንደተረበሸ ነው:: በዚህ ሁኔታ ያለ መሪ አይደለም አዲስ ውጤት ሊያመጣ ያለውን ሊንድ ይችላል:: ብፁዕነታቸው በተመረጡበት ወቅት ቤተ ክርስቲያኒቷ ያጣችውን ክብርና አንድነት እንዲሁም ተሰሚነት ለመመለስ ከሁሉም አካላት ጋር እንደሚሰሩ ቃል ገብተው ነበር:: ይህ ግን እስካሁን ሲደረግ ወይም ለመደረግ ሲሞከር አልታየም:: ይባስ ብሎ ጉባዔያት መረጃና ማስረጃ የሌላቸው ተራ ሊባሉ የሚችሉ ክሶችን በማስተናገድ ላይ ይገኛሉ:: ከጥቂት ታዳሚዎች በስተቀር አብዛኞቹ ግራ ከመጋባትና ከመለያየት ባለፈ እየቀረቡ ባሉ ንግግሮች ተጠቃሚዎች ሊሆኑ አይችሉም:: ይህም የቤተ ክርስቲያኒቱን አገልግሎት በእጅጉ ይጎዳል::

  ይቅር የማይሉና እርቅን የማያውቁ ባለሥልጣናት እንዴት ወንጌልን ሊሰብኩ ይችላሉ? ያጠፋ አካል ካለ ጥፋቱ በተጨባጭ ተነግሮት ይመከራል: አስተዳደራዊ ርምጃ ይወሰዳል እንጅ በመድረክ የስድብ ናዳ ይወረድበታል? የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዴት ይካሄድበታል? ከላይ ያሉት አባቶች በእንደዚህ ያሉ ነገሮች የሚጠመዱ ከሆነ ምእመናን ማንን አርአያ ሊያደርጉ ይችላሉ??? ምናልባትም የምእመናን ቁጥር መቀነስ አንዱና ትልቁ ምክንያት ይህ የበላይ አካላት አላስፈላጊ ግብግብ ይመስለኛል:: ብፁዕነታቸው ለራሳቸውና ለንግግራቸው ይበልጥ በመጠንቀቅ የአባትነት ሚናቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል:: የይቅርታ: የእርቅ: የአንድነትና የሰላም አርአያ ሆነው መቀጠል ይጠበቅባቸዋል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን የሚፈልጉት ፍጹም መንፈሳዊ አባት እንጅ በሥልጣኑና በኃይሉ የሚመካ መሪ አይደለም::
  ማጠቃለያ
  ከንግግራቸው እንደምንረዳው ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር መልካም ግንኙነት እንደሌላቸውና በዚህም የተነሳ መንፈሳቸው እንደተረበሸ ነው:: በዚህ ሁኔታ ያለ መሪ አይደለም አዲስ ውጤት ሊያመጣ ያለውን ሊንድ ይችላል:: ብፁዕነታቸው በተመረጡበት ወቅት ቤተ ክርስቲያኒቷ ያጣችውን ክብርና አንድነት እንዲሁም ተሰሚነት ለመመለስ ከሁሉም አካላት ጋር እንደሚሰሩ ቃል ገብተው ነበር:: ይህ ግን እስካሁን ሲደረግ ወይም ለመደረግ ሲሞከር አልታየም:: ይባስ ብሎ ጉባዔያት መረጃና ማስረጃ የሌላቸው ተራ ሊባሉ የሚችሉ ክሶችን በማስተናገድ ላይ ይገኛሉ:: ከጥቂት ታዳሚዎች በስተቀር አብዛኞቹ ግራ ከመጋባትና ከመለያየት ባለፈ እየቀረቡ ባሉ ንግግሮች ተጠቃሚዎች ሊሆኑ አይችሉም:: ይህም የቤተ ክርስቲያኒቱን አገልግሎት በእጅጉ ይጎዳል::

  ይቅር የማይሉና እርቅን የማያውቁ ባለሥልጣናት እንዴት ወንጌልን ሊሰብኩ ይችላሉ? ያጠፋ አካል ካለ ጥፋቱ በተጨባጭ ተነግሮት ይመከራል: አስተዳደራዊ ርምጃ ይወሰዳል እንጅ በመድረክ የስድብ ናዳ ይወረድበታል? የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዴት ይካሄድበታል? ከላይ ያሉት አባቶች በእንደዚህ ያሉ ነገሮች የሚጠመዱ ከሆነ ምእመናን ማንን አርአያ ሊያደርጉ ይችላሉ??? ምናልባትም የምእመናን ቁጥር መቀነስ አንዱና ትልቁ ምክንያት ይህ የበላይ አካላት አላስፈላጊ ግብግብ ይመስለኛል:: ብፁዕነታቸው ለራሳቸውና ለንግግራቸው ይበልጥ በመጠንቀቅ የአባትነት ሚናቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል:: የይቅርታ: የእርቅ: የአንድነትና የሰላም አርአያ ሆነው መቀጠል ይጠበቅባቸዋል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን የሚፈልጉት ፍጹም መንፈሳዊ አባት እንጅ በሥልጣኑና በኃይሉ የሚመካ መሪ አይደለም::

  ReplyDelete
 4. You are talking, but Jesus is doing. You are accused the the truth, and the people who are telling the truth. The orthodox church has the truth. The truth is Jesus. Machinery kidusan has Jesus. They always teach about Jesus and his people. But aba selama and tehadeso are empty because the are layer. The argument you posted on the website is nothing make sense. It is out of the sprit of Jesus. Anyway, whatever you guys said God always with the right people. Of course, it is a time to wake up for all orthodox faith believers because the devils are crying around the church, and that is you. I want give you an advice, take off the mask that you are doing the devil's staff in the name of Jesus. If you do no, you can ask and know the truth.Jesus is not full.

  ReplyDelete
 5. እውነቱ እንዲህ ነው፡፡ በእምነት መፅናትን፤ በእምነት መራመድን፤በእምነት መኖርን፤ሀገር መውደድን፤ለሎች እምነቶች ክብር መስጠትን፤ ለእውነት መስራትን፤ድህነትን ተጸይፎ ወደነበርነበት የጥነቱ ክብር እንመለስ ዘነድ ማንነት ማወቁ ላይ፤ በወጣትነት እድሜያችን በሱስ እነዳነጠመድ ፤ በባህል ወረራ ማንነታችንን እንዳናጣ ፤ በቅጡ እነበላ ዘንድ፤በወጉም እንለብስ ዘንድ አረስንቱን ወዘተ… ብለን እናልፈው ዘንድ ግድነውና ወዘተ ብለን እንለፈው፡፡
  ክፍተታችንን ሞልተው ጠማማነታችንን አርቀው ለዚህ ቀን ያበቁን ቁርጥ የተወህዶ ልጆች ፤የቅድሲቲቱ ቤተክርስትያናችን ለክፉ ቀን ደራሾች እነዚህ ዛሬ አነ አማን ነጸር የሚያብጠለጥሏቸው ማሕበረ ቅዱሳን ናቸው፡፡
  የማህበሩን ቅን አገልግሎትም ለቤተክርሰትያኒቱም ይሁን ለሀገረችን እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አይደለም የተወህዶ ልጆች በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉም የሌሉም የሌላ እምነት ተከታይ የሆኑ ወንድሞች በግልፅ ያወቁታል፡፡ዓለምም ያውቀዋል፡፡ሁሉም ይረዳዋል፡፡
  የማህበረ ቅዱሳን ወንድሞች ፀብ ያላቸው በእምነት ስም ካባ ለብስው በቤተክርስትያኒቱ ስም በሚነግዱት፤ እራሰቸው ሳይታደሱ ቤተክርስቲየያንን እነድሳለን ብለው ሌተ ከቀን በሚያሴሩ ማንነተቸውን በልተረዱ የቤተክርስትያን ጠላቶች እና በመሳሰሉት ላይ ቢሆን አንጂ ከራሳቸው ይልቅ ለሌሎች ቅድሚያን የሚሰጡ በትህትናና በፍቅር የታነፁ ናቸው ብል ተግባረቸውን የሚያወቁ ሁሉ ይጋሩኛል፡፡
  ሌብነትን፤ለሀገርና ለወገን ማሰብን ወደጎን በማድረግ በልመና ምእመኑን አስመርረው የሚሰበስቡትን ገንዘብና ሃብት ለግል ጥቅም የሚያወሉትን ግለኛ ጥቅመኞችን መቃወም በመንግስት በኩልም ይሁን በእውነተኛ የቤተክርስትያኒቱ አባቶችና አገልጋዮች ዘንድ ተቀባይነት ያለው በእግዚአብሄርም ዘነድ የተወደደ እነጂ የሚየስነቅፍ ወደ ጥላቻም የሚሰድ ተግባር አልነበረም፡፡
  እውነት በትዘገይ እነጂ መገለጧ አይቀሬ ነው፡፡ ነገር በማወሳሰብና እውነተኛ ጎዳናላይ ያለ ሕገዊ ሆኖ የሃገሪቱን ህግና ደንቦች ፤የቤተክርስትኒቱንም ዶግማና ቀኖና፤መመሪየያዎችና ደንቦች አክብሮና ታዞ የሚሰራን የቤተክርስትያን እውነተኛ ልጅ እደግ ይሉት እንደሆን እንጂ ከፊቴ እነደላይህ ቢሉት የሚሰማማ ፀባይ እይደለም፡፡
  መንግስትም ይሁን እውነተኞቹ የቤተክርስትየያኒቱ አባቶችና አገልጋዮች ምዕመኑም ቢሆኑ ማህበረ ቅዱሳንን በትክክል ያውቁታል፡፡ ማንም ተነስቶ ያ እንዲህ ነው ያም እነድያነው ስላለቸው በትጉህ የንብ መንጋዎች ቀፎ ላይ ከማሩ ለመጠቀም መሀሩን ለመሰባሰብ ቢሀሆን እንጂ የማሪቱ ባለቤት ዳግመኛ ማር እንደትሰጥ በቀፎው ስር አሳት አያነዱም፡፡ እነድያ ከሆነ ግን ግዜ ለኩሉ ነውና ያስተዛዝባል፡፡ ለሞት እነኳን ቢያደርስ ክርስትና መሰረቱ ሰለእውነት መሞት ጸጋው ነውና በክብር እንቀበላለን እንጂ በዋዛ ፈዛዛም ሊታለፍ የሚችልም አይደለም እውነት ምህዳሯን ትስታለችና ነው፡፡ ስለዚህ የገሬ መንግስት መረጃዎችን አጥርቶ እነደያይ፤ የጉዳዩ በለቤት የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስም የዚህ ክፉ ደባ ትዋኔ ምንጩ ከየት ሊሆን እነደሚችል አጥርቶ በማየት እነደሰው ሣየሆን እነደ እግዚዘበሄር መንግድ እነዲፈርድ ፤ ህዝበ ክርስትያኑም ቢሆን ቤተክርስትያኑን በትጋት እነዲመለከታት በፀሎቱም እነዲተጋ አኔ የሚሰማኝ እወነቱ አነዲህ ነው እላለሁ፡፡ ይህን ሳልል ባልፈው የመከሩን የገሰፁን በእምነት ጎዳና የመሩን የአውነተኛይቱ ቤተክርስትያን የተዋህዶ ልጆች አባት፤ በአነድነት በሶስትነቱ የሚመሰገን የማያንቀላፈው ሎላዊ እረኛችን እግዚአቢሄር በእውነት አደባባይ ላይ የሚፈረደኝ ይመስለኛልና ነው፡፡
  እግዚአቢሄር አገረችን ከክፉ መካሪዎች፤አባቶችን ከልጆች፤መንግስትን ከህዝብ ከሚያቃቅሩ የእውነት አስመሳይ ሌቦችና ከሃዲዎች ይጠብቃት ! አሜን!!!

  ReplyDelete
 6. ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የዚህ ሁሉ ችግር ምክንያቱ ቤተ ክህነትም ሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ከወንጌል ይልቅ ለተረትና ለግል ፍላጎት ሲሯሯጡ ቤተ ክርስቲያን እየተዳከመች መምጣቷ ነው ብላ ታምናለች
  ይህ ጽሑፍ የአባ ሰላማ አይደለም ማለት ነው፤ እንደዚ ኮፒ እያደረጋችሁ ውሸት ከምትቀባበሉ የእውነት አይን እንዲኖራችሁ ለምን አትለምኑም

  ReplyDelete
  Replies
  1. they said the source is tehadedo blog. donot uunderstand this?

   Delete
  2. አይ ሞኞ አታነብም እንዴ ምንጭ እኮ ጠቅሰዋል። ምን ያለኸው ሞኝ ነህ ጃል።

   Delete
 7. The pateriarc is real boss in our church. He can be demolish mk with our pre condition. Mk the criminal you have out of game. The time is over. Go to your real place to hell. F........ Mk

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ጅል መናፍቅ ዝም ብለህ አትርተርተር….

   Delete
  2. Ante kentu! ye kentu kentu! min lematref newu yefelekewu? an how these is the games that beyond yuor scope.frist try to wake up!

   Delete
 8. zegebaw tiru new gin gudayu ketehadso gar lmamesasel atmokr wet reach stun asmesay werenga

  ReplyDelete
 9. እጅግ የሚያኮራ ንግግር በዚህ እስከ ሰማእትነት ድረስ ቢቀበሉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅድስና ታከብርዎታለች ቅዱስነትዎ ይበርቱ እሱ ራሱ እውነት የሆነ፣ የእውነት አምላክ፣ እውነተኛ አምላክ ከርስዎ ጋር ይሁን፣ ያበርታዎት፡፡ ይህን ሥራ ሲፈጸሙ ከ100 ሺ በላይ ወጣት ምእመናንን ከተሳሳተ መንገድ ይታደጋሉ፣ በርካት ደጋፊዎችን ያድናሉ፣ በመቶ ሚሊየን የሚቆጠር አለአግባብ የሚባክን የቤተ ክርስቲያን ጥሬ ገንዘብ፣ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት በየአጥቢያው፣ ሀገረ ስብከት፣ እና መንበረ ፓትርያርክ ያስገባሉ፡፡ ከሁሉ በላይ የቤተ ክርስቲያን የቅድስና፣ የአንድነትና የሃዋርያዊነት ክብር ይጠብቃሉ፡፡

  ReplyDelete
 10. Abetu enzihen siryesededu yebetecrstiyanachenen cancer mk yemibaluten serachewn endetaderklen be enateh bedengle mariyam temasnen.ebhal.

  ReplyDelete
  Replies
  1. libona yistyih! gudguag wust indale sewu iyitah tebab newu!

   Delete
 11. The one calls his name tehadeso is jocking, but the orthodox church and the true orthodox church evangelicals (preachers) including mahibere kidusan teaches every minute Jesus. But you tehadeso, you put yourself in the higher level, and now you are trying to be above Jesus. That's why you try to change the truth by the false history. Jesus made everything new; nothing is new bellow the heaven. Tehadeso never has the faith in Jesus, so you don't have the faith of orthodox. You are just blaming, attack, arguing the orthodox and it's believers. They are not coming to your circle; why you are not their religion and faith for them.the reason is clear , you faith is not true because you are leading by the devils sprit.so never get the truth from devils. You might think you are following Jesus, but not. Calling his name, its not work because the devils know who is Jesus.but they don't have faith in Jesus.

  ReplyDelete
 12. አልፎ አልፎ ግር ግር አስፈላጊ ነው ግን የብዙዎችን ሓሳብ የሚበትን እንዲሁም ሥር የሰደደ የጥላቻ ወሬ
  መንዛት ኅሊናን ከመሳትና አእምሮን ከማጣት ያስቆጥራልከግለ ሰብ ጀምሮ እስከ ማኅበረ ሰብእ ያለ ወገን
  መንፈስ ቅዱስ ሲርቀው ጠባቂ መላኩ ሲለየው ሰላምን ስምምነትን ያጣል በመጨረሻም እንደ አኪጦፌል ይሆናል።
  ስንኳንስ በመንፈሳዊ አስተዳደር በሥጋዊም ቢሆን አግባቢ ንግግርና አስማሚ ሥርዓት ያስፍልጋል እናም ግራም ቀኙም ሁላችንም ሊያስቡበትና ልናስብበት ተገቢ ከመሆኑም ባሻገር መሥመሩን የለቀቀ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። ወዴት እንደሚያመራ (ነገር ፈጣሪውን እሾህ አጣሪውን) እርሱ ይወቀው።

  ReplyDelete
 13. አልፎ አልፎ ግር ግር አስፈላጊ ነው ግን የብዙዎችን ሓሳብ የሚበትን እንዲሁም ሥር የሰደደ የጥላቻ ወሬ
  መንዛት ኅሊናን ከመሳትና አእምሮን ከማጣት ያስቆጥራል ከግለ ሰብ ጀምሮ እስከ ማኅበረ ሰብእ ያለ ወገን
  መንፈስ ቅዱስ ሲርቀው ጠባቂ መላኩ ሲለየው ሰላምን ስምምነትን ያጣል በመጨረሻም እንደ አኪጦፌል ይሆናል።
  ስንኳንስ በመንፈሳዊ አስተዳደር በሥጋዊም ቢሆን አግባቢ ንግግርና አስማሚ ሥርዓት ያስፍልጋል እናም ግራም ቀኙም ሁላችንም ሊያስቡበትና (ልናስብበት) ተገቢ ከመሆኑም ባሻገር መሥመሩን የለቀቀ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። ወዴት እንደሚያመራ (ነገር ፈጣሪውን እሾህ አጣሪውን) እርሱ ይወቀው!

  ReplyDelete
 14. maqe teferse teferese teferese

  ReplyDelete
 15. Aba selama Hara zetewahidon anbibesh kitil bey ingdih.Betekirstiyan yemitmerawu Besinodos inji beand gileseb aydelem.Bekale Awadiyachin Patriyark yesine migbar gudlet kalebet Besinodos wusane indemiweged yazal.Lemehonu beand sewu hasab memerat lehilinachihu inkwan tikikle newu tilalachihu?Maferiyawoch

  ReplyDelete
 16. ----ye gebeya gir gir le ketafi bejew -----

  ReplyDelete
 17. በእግዚአብሄር ቤት ዉስጥ፣የእግዚአብሄርን ሀይል ና ጸጋ ረስተዉ፡ ዲያቢሎስ አለምን እያሳያቸዉ፣ ስንት አባቶች ጠፉ፡፡ከ 10ቱ ትእዛዛት አንዱ አትስረቅ፡ እንዴት ተረሳ፤
  መንፈሳዊ ክፉ ዘር በቤተክርስቲያን ዉስጥ፡- ያስቆሮቶስ ይሁዳ፡ ለምን ይሄን ለጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የቀረበዉን ሽቶ ሸጠን ለድሆች አንሰጥም አለ፡፡ ለ ድሆች ተገዶላቸዉ ሳይሆን ሌባ ስለነበር ነዉ፡፡በመንፈሳዊ ቤትም ሌብነት አለ፡፡ መንፈሳዊ ክፉዘር፡፡ ይሁዳ፡ ከጌታዉ ጋር እራት እየበሉ ከጌታችን ከመዲሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ እጅ ቁራሽ ከተቀበለ ቡሃላ ያን ግዜ ሰይጣን ገባበት፡፡ ተመልከቱ ከጌታ በረከት እነጂ፤ጸጋ እንጂ..እንዴት ሰይጣን ይገባል፡፡ ይሔዉ በእኛ ዘመን ተከሰተ፡፡እግዚአብሄር ከ እኛ ጋር ይሁን፡፡ ቤቱን ለማንም ወሮበላ አያስደፍርም፡፡ አባቶች እባካችሁ ለፈጣሪ በርከክ በሉ፡፡ ሀይሉን አትርሱ፡፡ዲያቢሎስ አለም እያሳያችሁ አትጥፉ፡፡ በእሱ እኛ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን ተብሎ የተስፋ ቃል ተሰጥቶናል፡፡ ፈራሹን አትመለክቱ፡፡ ክብር ለዘለአለም ለእሱ ይሁን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 18. ፓትርያርኩ ትላንት ስለ ማኅበረ ቅዱሳንን ያሉትን ዛሬ ሻሩት!
  ( ማየት ያለብዎት አስገራሚ ቪድዮ)
  ፓትርያርኩን ግን እንዲህ የሚያሽከረክራቸው ማነው? እሳቸውን ቅኝ የገዛ አካል እንዳለ ግን በሚገባ እየተስተዋለ ነው:: አባታችንን መውቀስ አቁመን ልናዝንላቸው ይገባል:: በርግጥም አባታችን ቀውስ ውስጥ መውደቃቸው ግልጽ እየሆነ ነው:: ይሄ ሁሉ አቋንም 360 ዲግሪ መቀየር ምንጩ ምንድነው? ከበስተጀርባቸው የተጫናቸው ኃይል ምንድነው? እውን አባ ማቲያስ ነጻ ናቸውን? —
  https://www.facebook.com/video.php?v=1489732551304824&set=vb.100008042808114&type=2&theater

  ReplyDelete
 19. ተመስገን ፣ተመስገን ፣ተመስገን አሁንም ተመስገን የማህበረ ቅዱሳን ጠባቂ የድንግል ማርያም ልጅ ጌታዬ መድሃኒአለም አብዝቼ አመሰግንሃለሁለ፤፡ የዲያቢሎስና የእናንተ ቀስት ያልቃል እንጂ ማህበረ ቅዱሳን ምንም አይሆንም እንደውም ባህር ዛፍ ሲነካ እነደሚበዛ ሁላ ገና እንበዛልን. አባታችን አባ ማትያስ ለመናፍቅና ለ ተሃድሶያውያን መሳሪያ እየሆኑ እነደሆነ እንደው ይታወቆታል…. እግዚአብሄር ያስቦት የትንቢት መፈጸሚያ ከመሆን ሁላችንንም ያድነን.

  ReplyDelete
 20. በየዓመቱ የሚካሔደው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የመክፈቻ ቃለ ምዕዳን ተጀመረ ፡፡

  የጥቅምት መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሀገር አቀፍ የአጠቃላይ መንፈሳዊ የሰበካ ጉባኤን ተከትሎ በምልዓተ ጉባኤው መክፈቻ ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ ያቀረቡት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ እንደሚከተለው በጽሑፍና በድምጽ ወምስል ያቀረብን ሲሆን፣ በጉባኤው የሚወሰኑ ውሳኔዎችንም ተከታትለን እንደምናቀርብ ለመግለጽ እንወዳለን ፡፡


  የጥቅምት 2007 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የመክፈቻ መልእክት

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

  ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!

  ታላቋና መተኪያ የማይገኝላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በውስጥም ሆነ በውጭ የተጋረጡባት ግልጽና አደገኛ ፈተናዎች እንዳሉ መገንዘብ አለብን ፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ከሚታዩ ፈተናዎች አንዱና ዋነኛው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናን ወደ ሌላ እምነት እየፈለሱ ከመሆናቸው ሌላ፤
  • በቤተ ክርስቲያን ስም ሀብትን የሚሰበስቡ ማኅበራት በእነርሱ የምትተዳደር ቤተ ክርስቲያን ሳትኖር የቤተ ክርስቲያን ብቸኛ መብት የሆነውን ከምእመናን ገንዘብና ንብረት የመሰብሰብ ሥልጣንን ወደራሳቸው በማዞር ገንዘብና ንብረት ከምእመናን መሰብሰብ መልመዳቸው፤
  • በዚህም ምክንያት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁለት የተለያዩ ዓሥራትና በኩራት ሰብሳቢዎች እየተፈጠሩ መምጣታቸው፤
  • በቤተ ክርስቲያን እየተፈጠረ ያለው ሁለተኛ ባለሀብት ማኅበር በሂደት ቤተ ክርስቲያንን ወደ ሁለት የመክፈል አዝማሚያ እንዳለው ግልጽ ማስረጃ መገኘቱ፤
  • ማኅበራቱ በመንግሥትና በቤተ ክርስቲያን የማይታወቅ ሀብት የሚሰበስቡ በመሆናቸው ገንዘቡ በሚያስከትለው ሌላ ጉዳት ቤተ ክርስቲያን በአክራሪነት የምትፈረጅበት አጋጣሚ መከሠቱ፤
  • ማኅበራት በሌላቸው ሥልጣን በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ሥራ በቀጥታ ጣልቃ እየገቡ የሰላም ጠንቅ ሆነው መገኘታቸው፤
  • ችግሩን በቀላሉ ለማስተካከል ቢሞከር እንኳ ማኅበራቱ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የሚሰጣቸውን መመሪያ ለመቀበል ፈቃደኝነቱና ቅንነቱ ፈጽሞ የሌላቸው ሆነው መገኘታቸው አስቸኳይ መፍትሔ የሚሻ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግር ሆኖ ተገኝቶአል ፡፡


  ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!  ‹‹በይሉኝታ የራስ ዓሊ ቤት ተፈታ›› እንደተባለው እውነቱን እንነጋገር ከተባለ በሃይማኖታችን ትውፊት ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ጸበልን ቀምሶ የሚኖር የጽዋ ማኅበር ካልሆነ በቀር በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ቤተ ክርስቲያንን አህሎ የተደራጀና ቤተ ክርስቲያን አከል የሆነ ገንዘብ ሰብሳቢ ማኅበር ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ፡፡
  ስለሆነም በማኅበራት ጉዳይ ላይ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሕጋዊና ዘላቂ መፍትሔ ማስቀመጡ ቤተ ክርስቲያንን የመታደግ ጉዳይ መሆኑን በአጽንዖት ሳንጠቁም አናልፍም ፡፡

  በመጨረሻም


  ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ግልጽ በሆነ ሁኔታ እያልን ያለነው በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ያልታቀፈና ለቤተ ክርስቲያን የማይታዘዝ ማኅበር በቤተ ክርስቲያን ስም ተደራጅቶ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ለቤተ ክርስቲያን ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ የሚያስከትለው ጉዳት ከባድ ስለሆነ፣ በሕግ ማስተካከል አለብን የሚሉትን ነው ፡፡

  እግዚአብሔር አምላክ ጉባኤያችንን ይባርክ፤ ይቀድስ፤ አሜን ፡፡  አባ ማትያስ ቀዳማዊ
  ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
  ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም፤ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
  ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም
  አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

  ReplyDelete
 21. አዎ እኛም ማኅበረ ቅዱሳን ነን:: ማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚደረግ ትንኮሳ ሁሉ ቤተ ክርስትያን ላይ የሚደረግ የጥፋት አዋጅ ነው:: የሃሰት ክስ ይቁም::እግዚአብሔር ያያል:: በስጋም ያስቀጣል:: በሃይማኖትም ሃጥያት ነው::
  " እውነት አርነት ታወጣሃለች"

  ReplyDelete
 22. ማህበሩም፣ መናፍቁም፣ ተሐድሶም ተያይዘችሁ ገደል ግቡ ቤተክርስቲያንን አታምሱ ክብራችሁን አዝላችሁ ዙሩ!!!!!

  ReplyDelete
 23. ልካችሁን የሚያውቀው ማኅበረ ቅዱሳንን መጣል ለእናንተ ደስታ ነው፡፡ ግን ሁሉ በእግዚአብሔር እንጅ በሰው ሀሳብ ስለማይሆን ፍላጎታችሁ ከንቱ ነው፡፡የምንፍቅና ዘራችሁን ለመዝራት እየቋመጣችሁ እንደሆነ እናውቃለን በቤተ-ክርስቲያን ስም ኦርቶዶክሳዊያንን ለማሳት የምጽፉትና የምትወተውቱትን ውትወታ የሚገፋችሁ የምትኖሩበት ረብጣ እንዳይቋረጥባችሁ ነው፡፡ኑሯችሁን ይኖሩላችኋል እናንተ ደግሞ ዓላማቸውን ለማሳካት ቤተ-ክርስቲያንን መቀኝና በግራ ግዕዝ እየጠቀሳችሁ ልታጠፏት ብትሞክሩም የሲኦል ደጆች አይሏትምና በከንቱ አትድከሙ፡፡ሰው ለያዘው የዕምነት አቋም መጽናት አንድ ነገር ነው ነገር ግን ትንሽ እምነት አለን እንኳን ካላችሁ ሀሰት የሆነ በሬ ወለደ ጽሁፍ ስትጽፋ አታፍሩም፡፡ ለነገሩ ብታፍሩ ነው የሚገርመው ፡፡የሌባ አይነ ደረቅ ልብ ያደርቅ ነው የሚባለው፡፡

  ReplyDelete
 24. እውነቱ እንዲህ ነው፡፡ በእምነት መፅናትን፤ በእምነት መራመድን፤በእምነት መኖርን፤ሀገር መውደድን፤ለሎች እምነቶች ክብር መስጠትን፤ ለእውነት መስራትን፤ድህነትን ተጸይፎ ወደነበርነበት የጥነቱ ክብር እንመለስ ዘነድ ማንነት ማወቁ ላይ፤ በወጣትነት እድሜያችን በሱስ እነዳነጠመድ ፤ በባህል ወረራ ማንነታችንን እንዳናጣ ፤ በቅጡ እነበላ ዘንድ፤በወጉም እንለብስ ዘንድ አረስንቱን ወዘተ… ብለን እናልፈው ዘንድ ግድነውና ወዘተ ብለን እንለፈው፡፡
  ክፍተታችንን ሞልተው ጠማማነታችንን አርቀው ለዚህ ቀን ያበቁን ቁርጥ የተወህዶ ልጆች ፤የቅድሲቲቱ ቤተክርስትያናችን ለክፉ ቀን ደራሾች እነዚህ ዛሬ አነ አማን ነጸር የሚያብጠለጥሏቸው ማሕበረ ቅዱሳን ናቸው፡፡
  የማህበሩን ቅን አገልግሎትም ለቤተክርሰትያኒቱም ይሁን ለሀገረችን እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አይደለም የተወህዶ ልጆች በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉም የሌሉም የሌላ እምነት ተከታይ የሆኑ ወንድሞች በግልፅ ያወቁታል፡፡ዓለምም ያውቀዋል፡፡ሁሉም ይረዳዋል፡፡
  የማህበረ ቅዱሳን ወንድሞች ፀብ ያላቸው በእምነት ስም ካባ ለብስው በቤተክርስትያኒቱ ስም በሚነግዱት፤ እራሰቸው ሳይታደሱ ቤተክርስቲየያንን እነድሳለን ብለው ሌተ ከቀን በሚያሴሩ ማንነተቸውን በልተረዱ የቤተክርስትያን ጠላቶች እና በመሳሰሉት ላይ ቢሆን አንጂ ከራሳቸው ይልቅ ለሌሎች ቅድሚያን የሚሰጡ በትህትናና በፍቅር የታነፁ ናቸው ብል ተግባረቸውን የሚያወቁ ሁሉ ይጋሩኛል፡፡
  ሌብነትን፤ለሀገርና ለወገን ማሰብን ወደጎን በማድረግ በልመና ምእመኑን አስመርረው የሚሰበስቡትን ገንዘብና ሃብት ለግል ጥቅም የሚያወሉትን ግለኛ ጥቅመኞችን መቃወም በመንግስት በኩልም ይሁን በእውነተኛ የቤተክርስትያኒቱ አባቶችና አገልጋዮች ዘንድ ተቀባይነት ያለው በእግዚአብሄርም ዘነድ የተወደደ እነጂ የሚየስነቅፍ ወደ ጥላቻም የሚሰድ ተግባር አልነበረም፡፡
  እውነት በትዘገይ እነጂ መገለጧ አይቀሬ ነው፡፡ ነገር በማወሳሰብና እውነተኛ ጎዳናላይ ያለ ሕገዊ ሆኖ የሃገሪቱን ህግና ደንቦች ፤የቤተክርስትኒቱንም ዶግማና ቀኖና፤መመሪየያዎችና ደንቦች አክብሮና ታዞ የሚሰራን የቤተክርስትያን እውነተኛ ልጅ እደግ ይሉት እንደሆን እንጂ ከፊቴ እነደላይህ ቢሉት የሚሰማማ ፀባይ እይደለም፡፡
  መንግስትም ይሁን እውነተኞቹ የቤተክርስትየያኒቱ አባቶችና አገልጋዮች ምዕመኑም ቢሆኑ ማህበረ ቅዱሳንን በትክክል ያውቁታል፡፡ ማንም ተነስቶ ያ እንዲህ ነው ያም እነድያነው ስላለቸው በትጉህ የንብ መንጋዎች ቀፎ ላይ ከማሩ ለመጠቀም መሀሩን ለመሰባሰብ ቢሀሆን እንጂ የማሪቱ ባለቤት ዳግመኛ ማር እንደትሰጥ በቀፎው ስር አሳት አያነዱም፡፡ እነድያ ከሆነ ግን ግዜ ለኩሉ ነውና ያስተዛዝባል፡፡ ለሞት እነኳን ቢያደርስ ክርስትና መሰረቱ ሰለእውነት መሞት ጸጋው ነውና በክብር እንቀበላለን እንጂ በዋዛ ፈዛዛም ሊታለፍ የሚችልም አይደለም እውነት ምህዳሯን ትስታለችና ነው፡፡ ስለዚህ የገሬ መንግስት መረጃዎችን አጥርቶ እነደያይ፤ የጉዳዩ በለቤት የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስም የዚህ ክፉ ደባ ትዋኔ ምንጩ ከየት ሊሆን እነደሚችል አጥርቶ በማየት እነደሰው ሣየሆን እነደ እግዚዘበሄር መንግድ እነዲፈርድ ፤ ህዝበ ክርስትያኑም ቢሆን ቤተክርስትያኑን በትጋት እነዲመለከታት በፀሎቱም እነዲተጋ አኔ የሚሰማኝ እወነቱ አነዲህ ነው እላለሁ፡፡ ይህን ሳልል ባልፈው የመከሩን የገሰፁን በእምነት ጎዳና የመሩን የአውነተኛይቱ ቤተክርስትያን የተዋህዶ ልጆች አባት፤ በአነድነት በሶስትነቱ የሚመሰገን የማያንቀላፈው ሎላዊ እረኛችን እግዚአቢሄር በእውነት አደባባይ ላይ የሚፈረደኝ ይመስለኛልና ነው፡፡
  እግዚአቢሄር አገረችን ከክፉ መካሪዎች፤አባቶችን ከልጆች፤መንግስትን ከህዝብ ከሚያቃቅሩ የእውነት አስመሳይ ሌቦችና ከሃዲዎች ይጠብቃት ! አሜን!!!

  ReplyDelete
 25. May the Lord forgive all of you and bring you to understanding.

  ReplyDelete
 26. ከማቅ ድሮስ ቢሆን ምን ኢጠበቃል? እኔ ቅዱስ ነኝያለው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ራሱን ቅዱስና ጻድቅ አድርጎ ከኮፈሰ ቡድን ምን ድህና ነግር ሊገኝ ይችላል? ከፍ ብሎ እንደ ተገለጸው በአሜሪካን አገር ማቅ እናገለግላለን በሚሉበት ቤተ ክርስቲያን ከቅዳሴ አገልግሎት በኋላ ሙዳየ ምጽዋት ተዙሮ ከተሰበሰበ በኋላ እንደገና ሌላ ሙዳየ ምጸዋት መዞር ይጀምራል፤ ይህን ያስተዋሉ ሰዎች ሙዳየ ምጸዋት እኮ ዞሯል ብለው ሲናገሩ አዟሪዎች ምን ቢሉ ጥሩ ነው? ይህ ደግሞ ለማህበረ ቅዱሳን ነው ብለው እርፍ፤ ይህን ጉዳቸውን ለመደበቅ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በአቋማቸው ጸንተው የደረሳቸውን መረጃ ይፋ አውጥተው ማቅን ቢያጋልጡ ታመው ነው አሏቸው። የተለከፈውስ ማን እንደሆን አሁን አሁን ፍንትው ብሎ እየታየ ነው። የእውነትን ጭላንጭል ያሳየን አምላክ ክብሩ ይስፋ።

  ReplyDelete
 27. አባታችን አቡነ ሺኖዳ የተናገሩትን የቡራኬ ቃል ወንድሜ ዲ.ዳንኤል እይታ ላይ አንብቤ ነበር፡፡ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ያገለግሉ ነበር፡፡ እናንተም ለእግዚአብሔር ስትሉ አገልግሉ፡፡ የሚለው ቃል ትዝ አለኝ፡፡ በረከታቸው አይለየን፡፡ ለመሆኑ እኚህ አቡነ ማቲያስ የሚባሉት ችግራቸው ገንዘብ ነውን? እኚህስ አባት የሚያገለግሉት ገንዘብንና የመንግስትን ዓላማ ነውን? እንዳለ ሪፖርቱ ስለገንዘብ አሰባሰብ ነው የሚያወራው በገንዘብ ተጀምሮ በገንዘብ የሚያልቅ ሪፖርት ደግሞ የመንግስትም ወሬ ስልችቶናል፡፡ አይ ይሁዳ እይቆጨውም ጥሩ ተከታየችን አፍርቶብን ነው ያለፈው!! ይሁዳ ጌታ ባርኮ የሰጠውን ህብስትና ወይን ከእጁ ሲቀበል ሰይጣን ገባበት ይለናል የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ነው አባታችንም ልባቸው የገንዘብ ጥማት ስለነበር ልክ ፓትራይራክ አባትነትን ሲቀበሉ የሚያስቡት ሁሉ ስለገንዘብ ሆነ፡፡ ምን ያድርጉት ከጌታ የተቀበሉት ክህነት ሰይጣን አሳደረባቸው፡፡ ደግሞ የእርሳቸው ሕይወት ደግሞ በማህበረ ቅዱሳን ምኞትና ጸሎት ከሆነም የሚኖረው ኧረ እኔም እንደዚህ አይነቱን አባት በእኔ ትውልድ ከማይ ወይ እንደይሁዳ ታንቀው በሞቱ የሚል ፀሎት ብጸልይ ማን ይከለክለኛል፡፡ ምክንያቱም ይሁዳ ንስሀ ከመግባት ይልቅ ታንቆ አይደል የሞተው፡፡ግን የእርሳቸው ሕይወት በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለሆነ ያለው የእግዚአብሔር ፈቃድ ደግሞ ሁልጊዜ ማስተዋልና ጥበብን መስጠን የሚችል ጌታ ስለሆነ በውስጣቸው የገባውን በስጋቸውና በደማቸው የተዋሀደው የገንዘብ ጥማት ቀይሮ የእግዚአብሔርን ቃል በስጋቸውና በደማቸው ገብቶ ጌታን የሚያዩበት አይን እንዲሰጣቸው ፀሎቴ ነው፡፡ ማህበረ ቅዱሳንን በክፉ ያዩበትን አይናቸውን አንስቶ የጌታን ቃል እንዲያዩ ያድርግልን፡፡ የሰማዩን ጌታ ያላዩ አይኖች ሁልጊዜ የሚናገረው የምድራዊን ንጉስ ሀሳብ አስፈፃሚ ነው የሚሆኑት፡፡ በቤተልሄም የተወለደውን ጌታ ለማየት ብዙ ሄሮድሶች ይገጥሙናል፡፡ ምክንያቱም ስለተወለደው ህፃኑ ጌታ ለማየት በመጀመሪያ ካርታውን በደንብ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ከዚያም ብዙ ሄሮድሶች ቢገጥሙንም ቀና ማለት እንድንችል የአባቶቻችንን አምላክ ይረዳናል ከዚያም ኮከቡን ማየት እንጀምራለን፡፡ ኮኮቡን ያየ ደግሞ የሰማዩን ጌታ የይሁዳ አንበሳ ኢየሱስ ክርስቶስን ማየት አያቅተውም፡፡ አለበለዚያ ግን ሁልጊዜ የሄሮድስ ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነን ነው የምንቀረው፡፡ እኔ ደግሞ ምን ይሁን መረጃቸው ብዬ እንዴት ቸኩዬ እንደከፈትኩት፡፡ አይ አባቴ እንደዚህ ሆነው አረፉት በገንዘብ ተጀምሮ በገንዘብ የሚያልቅ ሪፖርት ደግሞ ይዘው ማህበረ ቅዱሳንን ለመክሰስ መነሳቶ በእውነት አሳፋሪ ነው፡፡ እኔ የማህበረ ቅዱሳንን ዓላማና መሬት ወርዶ እየተሰራ ያለውንም ሆነ እያየሁት ያለውን ነገር ትምህርታቸውንም ሁሉ እኔ ያለምንም ጥርጥር የምቀበለው ነው፡፡ ስለገንዘብና ስለውስጥ አስራራቸው ያለውን ድክመትና ጥንካሬ ስለማላውቅ መናገር አልፈቅድም፡፡ ድክመት ካለ ድክመቱን አልደግፍም፣ ጥንካሬ ካለ ደግሞ እደግፋለሁኝ፡፡ ግን ለዚህ ብሎግ አቅራቢ የምገልጸው ነገር ማህበረ ቅዱሳን የሚሰሩት ለቤተክርስቲያን ትንሳኤ ነው ይህንንም ለመረዳት ግድ ውስጥ መገኘት የለብኝም ትምህርታቸውን መከታተልና የሚጨበጥ ነገር ያሚያሳዩት ለእኔ በቂ ነው፡፡ ምክንያቱም ጌታም ከፍሬዎቻቸው ታውቃላችሁ ነው የተባልነውና፡፡ ይህ ማለት ድካም አይኖርም ማለት አይደለም ድክመታቸው ግን ግለሰባያዊ እንጂ ሐይማኖታዊ አይደለም፡፡ ሻማ እራሱ እየቀለጠም አይደል ብርህን የሚሰጠው፡፡ ቢችሉ ፋኖስ/አምፖል ቢሆኑ አንጠላም እየበሩ ቢያበሩልን፡፡ ካልቻሉ የራሳቸው ችግር ነው፡፡ ግን ብርሀናቸውን ግን እፈልገዋለሁኝ፡፡ እና አባሰላማ ብሎግና አቡነ ማቲያስ የማህበረ ቅዱሳን አምላክ በተዋህዶ የከበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሆነና ዓላማቸውም ትንሳኤ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እስከሆነ ድረስ ተገንጥሎ ሌላ ቤተክርስቲያን እየሰራ ነው የሚለውን አነጋገር በእኔ እይታ የምቀበለው አይደለም፡፡ ነገር ግን የእናንተንና የአሁንን በአቡነ ማቲያስ እየተመራ ያለው ቤተክህነት እንደዚህ እንደዘረዘሩት ከሆነ ዓላማው መባል ያለበት ቤተክርስቲያንን የከፈላችሁት በራሳችሁ አመራር እየመራችሁ ያላችሁ የእንግዳ ትምህርት የምታስተምሩ እናንተ ስለሆናችሁ የራሳችሁን ዓላማ ለማህበሩ የምትሰጡ ተኩላዎች ናችሁ፡፡ የተኩላውን ድምጽ ለመሰማት የሚችል ህሊና የለኝምና፡፡ ትንሳኤ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብያለሁኝ፡፡ ሙሉጌጥ/ወለተስላሴ ነኝ

  ReplyDelete
 28. ayisakalachihum arifachiw tekemetu

  ReplyDelete
 29. wnedeme betam medanyalem lebona yestek yemetastewlbet aymero yadelk yelekunes lesew ymetekm neger betastemer yeshalal

  ReplyDelete