Wednesday, October 22, 2014

አባ መቃርዮስ በሲሞን መሰርይ መንገድ

Read in PDF

·         ያረጁ ታቦታትን በአዲስ ለውጡ እያሉ ለማስለወጫ 10 ሺህ ብር ይጠይቃሉ
·         የማዕረግ ስም ለመስጠት 700 ብር ያስከፍላሉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ በብዙ ችግሮች ውስጥ የተጠላለፈችበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ የችግሩ መንስኤዎች ደግሞ በግንባር ቀደምነት የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎችና ኃላፊዎች ለመሆናቸው አንድና ሁለት የለውም፡፡ በተለይም አንዳንድ ብፁዓን አባቶች እጅግ በሚያሳዝንና ለተቀመጡበት ቦታ እንኳን በማይመጥን የተለያዩ የቅድስና ችግሮች ውስጥ ተዘፍቀው የሚገኙበት ጊዜ ላይ ያለነው፡፡ ዛሬ የምንቃኘው የቀድሞው አባ ገብረ ዋህድ የአሁኑ የአዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑትን የአባ መቃርዮስን ሲሞናዊ መንገድ ይሆናል፡፡
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ካሉት አብያተክርስቲያናት ሁሉ ከምትለይባቸው ነገሮች መካከል አንዱ የታቦት ባለቤት መሆኗ ነው፡፡ ኦሪትና ወንጌልን ላለዩ ለብዙዎች ይህ የኩራት ምንጭ ሲሆንላቸው፣ ኦሪት ለወንጌል ጥላና ምሳሌ መሆኗን የተረዱ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና ምእመናን ደግሞ ማፈሪያና አንገት መድፊያ ነው፡፡ ምክንያቱም ታቦት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያገለግል የነበረና ለእስራኤል ብቻ የተሰጠ ንዋየ ቅዱሳት በመሆኑና በአዲስ ኪዳን አገልግሎት ውስጥ ግን ስፍራ የሌለው በመሆኑ ነው፡፡ የዚህ ጽሁፍ ዓላማ በታቦት ስም ቤተክርስቲያኒቱ የምትጠቀምበትን ንዋየ ቅድሳት ጉዳይ ማብራራት ባለመሆኑ እርሱን ለጊዜው እንለፈውና በታቦት ቅያሬ ስም በአባ መቃርዮስ እየተፈጸመ ያለውን ግብረ ሲሞን እንግለጽ፡፡ 


በግብረ ሐዋርያት እንደተጻፈው ሲሞን አስቀድሞ ጠንቋይ የነበረና በፊልጶስ የወንጌል አገልግሎት አምኖ ተጠምቆ ከእነርሱ ጋር ሲተባበር የነበረ ሰው ነበር፡፡ በኋላ እጅ በመጫን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ሲሰጥ አይቶ እርሱም እጁን የሚጭንበት ሁሉ ይህን ጸጋ እንዲቀበል ማድረግ ይችል ዘንድ ጸጋውን በገንዘብ ለመግዛት ከጀለ፡፡ በዚህ ጊዜ “ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። ልብህ በእግዚአብሔር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም። እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንሰሐ ግባ፥ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ወደ እግዚአብሔር ለምን፤ በመራራ መርዝና በዓመፅ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና። አለው፡፡ (የሐዋርያት ስራ 8፡20-23)፡፡ መቼም ሲሞን ይህን ጸጋ በገንዘብ ለመግዛት የፈለገው እጁን የሚጭንበት ሰው የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ እንዲቀበል ለመድረግና ይህን በጸጋ የሚሆን አገልግሎት እንደገቢ ምንጭ ሊጠቀምበት ፍለጎ ይሆናል፡፡የአባ መቃርዮስ አሰራርም ከሲሞን አሰራር ጋር ይመሳሰላል፡፡ እርሳቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ ባላቸው ሥልጣን ተጠቅመው ያረጁ ታቦታትን በአዳዲስ እንዲተኩ በማድረግ ይህን እንደ ገቢ ምንጭ መጠቀማቸው ነው በሲሞን መንገድ ላይ ነው ያሉት ያሰኛቸው፡፡ ቤተክርስቲያኗ ታቦቷን በእደ ጥብብ ባለሙያዎች ካስቀረጸችና በጳጳስ ከተባረከ በኋላ በድጋሚ የምትባርክበት ሁኔታ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ታቦት አረጀ ተብሎ በሌላ ይተካ የሚል ነገር ግን የለም፡፡ በፍትሐ ነገሥት ላይ “ወለእመ ተሰብረ ምሥዋዕ አው ፈለሰ ይቀድሱ ዳግመ” ትርጉም “መሠውያው (ታቦቱ) ቢሰበር ወይም ቢፈልስ (ቢማረክ) ዳግመኛ ይቀድሱት”  ተብሎ ተደንግጓል፡፡ (አንጽ 1 ቁጥር 6)፡፡ አባ መቃርዮስ ግን አረጀ ብለው ነው በታቦት ቅያሬ ስም የቤተክርስቲያንን ገንዘብ እየመዘበሩ ያሉት፡፡ ለነገሩ መጽሐፍ ቅዱስ የኦሪቱን አንዱን ታቦት ከግራር እንጨት እንዲሠራ አዝዞ የነበረውን ውዳሴ ማርያም ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደተሠራ ይናገር ነበር፡፡ የእኛዎቹ በርካታ ታቦቶች ግን ከምን ዕንጨት ቢሰሩ ነው ያረጁት? ነው ወይስ አባ መቃርዮስ ለጥቅማቸው የዘየዱት መላ ይሆን?
አባ መቃርዮስ ይህን ሲሞናዊ ግብር የሚፈጽሙት በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ ባሉ አድባራትና ገዳማት ውስጥ መቅደስ ውስጥ እየገቡ መንበር በመግለጥ “ይህ ጽላት አርጅቷልና ቀይሩ” በማለት ላረጀው ጽላት 10 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ያስገድዳሉ፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እስካሁን 38 ያህል ጽላቶችን በዚህ መንገድ እንዲቀየሩ ያደረጉ ሲሆን ከዚህም 380,000.00 ብር ለግላቸው እንዳገኙ ስሌቱ ያስረዳል፡፡ ከዚህ አንጻር ይህን ታቦት የመቀየር ሥራ እንደ አንድ የገቢ ምንጭ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ በመንበረ ጵጵስናቸው አርጅተዋል ተብለው ከአገልግሎት የታገዱ 15 የሚጠጉ ጽላቶች በቢሮአቸው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ከታቦት ቅያሪ ብር 10 ሺህ ከሚያገኙት በተጨማሪ ለማዕረግ ስያሜ 700 ብር ያስከፍላሉ ተብሏል፡፡ ይህን ያስከፈሉበትን ሞዴል 30 ደረሰኝም አባሪ ሆኖ ቀርቧል፡፡ ቀድሞ በዕውቀትና በችሎታ ይሰጥ የነበረው ልዩ ልዩ የማዕረግ ስም ዛሬ በገንዘብ የሚገዛባት ቤተክርስቲያን መሆኗ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ባልዋሉበትና ባልደከሙበትና ባልሆኑትም “ሊቀ ምንተስ መላከ ምንተስ” የሚባሉ የዕውቀትና የሙያ ሳይሆን እንደማኅበረ ቅዱሳን ቀሳውስት የክብር ማዕረግ በገንዘብ የሚገዛባት ቤተክርስቲያን እንደነ አባ መቃርዮስ ላሉ ጳጳሳት የገቢ ምንጭ ሲሆን የቤተክርስቲያኒቱን ክብር የሚነካ ጥራትና ደረጃዋን  እጅግ እያወረደና እያሽቆለቆለ የሚገኝ ኃላፊነት የጎደላቸውና ለጥቅማቸው ያደሩ ጳጳሳት በቤተክርስቲያኒቱ ላይ እያደረሱ ያለው ጥፋት አንዱ መገለጫ ነው፡፡ ለማዕረግ ይህን ያህል ያስከፈሉ ጳጳሳት ለዲቁናና ለቅስናስ ስንት አስከፍለው ይሆን?
ከላይ ከተገለጹት በተጨማሪ ሌላም ገንዘብና ሀብት የሚያካብቱበት ስልት አላቸው፡፡ አባ መቃርዮስ እንደማንኛውም ጳጳስ ከደመወዛቸው በተጨማሪ ለኑሯቸው ከበቂ በላይ የሆነ መኪናን ጨምሮ ብዙ ጥቅማጥቅሞችን ከቤተክርስቲያኒቱ የሚያገኙ ቢሆንም ያ አልበቃ ብሏቸው መኪናዬ አርጅቷልና ግዙልኝ በሚል በያንዳንዱ ደብር ላይ ከ2 ሺህ እስከ 12 ሺህ እንዲያዋጡ እያስገደዱ ይገኛሉ፡፡ ለዚህም ተገደው እያንዳንዳቸው 12 ሺህ ብር የከፈሉትን የጎልጎታ መድኃኔ ዓለምንና ደብረ መንክራት ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያኖችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ቅርስን በተመለከተ በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ ካህናቱ ውድ የሚሏቸውንና ለማንም የማያሳዩትን የብራና መጻህፍት አባ መቃርዮስ ጥብቅ ግንኙነት ካላቸው የጀርመን ዜግነት ካላቸው ግለሰቦች ጋር በመነጋገር ካህናቱን እያስገደዱ ያሳዩአቸዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ አባ መቃርዮስ ሁለት ጊዜ ጀርመን ደርሰው መጥተዋል፡፡ ምን ሰጥተዋቸው ይሆን? አረጁ የተባሉትና በአዳዲስ እንዲተኩ የተደረጉት ታቦቶች ከቅርስነታቸው አንጻር በዋጋቸው ከአዳዲሶቹ እንደሚበልጡ የሚጠበቅ ነውና መድረሻቸው የት ይሆን?
አባ መቃርዮስ በልዩ ልዩ መንገድ የሚመዘብሩትን ሀብትና ንብረት በቀላልና በተሳለጠ መንገድ ለማከናወን በተቻላቸው መጠን በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ ሙስናዊ ሰንሰለቶችን የዘረጉ ሲሆን ሾፌራቸውን የሀገረ ስብከቱ ዕቃ ግዢ ክፍል አድርገውታል፡፡ ሥራ አስኪያጅ ያደረጉት ደግሞ ዘመዳቸውን ነው፡፡ የሥራ አስኪያጁ ሚስት ደግሞ ገንዘብ ቤት ናት፡፡ ይህ ብልሹ አሰራርን የሚወልድ ሙስናዊ ሰንሰለት ካልተበጣጠሠ በቀር የቤተክርስቲያንን ሀብትና ንብረት ለመመዝበር ሰፊ በር ይከፍታል፡፡ አባ መቃርዮስ እስካሁን ባካበቱት የግል ሀብት 3 ቪላ ቤቶችን እንደገነቡ ምንጮቻችን ያስረዳሉ፡፡
ይህ ሁሉ ዘርፈ ብዙ ችግርና እጅግ አደገኛ ተግባር እየተከናወነበት የሚገኘው ሀገረ ስብከት ኣጣሪ ቢመደብለትም ሰሚ  አላገኘም፡፡ በጳጳሱ ላይ ለሚቀርቡ ክሶች በቂ ማስረጃዎች ቢገኙም ቤተክህነቱ ዝምታን ነው የመረጠው፡፡ በአሁኑ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የክልሉ ተወላጆች ተገኝተው እየጮኹ የነበረ ቢሆንም ሰሚ አላገኙም፡፡ የቅርስ ባላደራ ነኝ ተውፊት ጠባቂ ነኝ የሚለው ማኅበረ ቅዱሳንም ጉዳዩን እያወቀ ለዚያውም አሮጌ ጽላት ወደቢሮ አዲስ ጽላት ወደመንበር ጠርቦ ለማስገባት 10 ሺህ ብር በሕጋዊ ደረሰኝ እየተሰበሰበ በመጨረሻ ለሊቀጳጳሱ ተመላሽ እየሆነ ባለበት ሁኔታ ሌሎችን ወንጌል ሰበኩ ብሎ በተሐድሶ ስም የሚከሰውን ያህል በሙስና የተዘፈቁትን የእርሱን ወዳጆች እኔን እስካልነኩኝ ምን ቸገረኝ በሚል መንፈስ በዝምታ እንደሚያልፋቸው በተደጋጋሚ የሚታይ እውነታ ነው፡፡
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ከተጋረጡባት ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ችግሮች አውጥቶ ተሐድሶዋን እውን ያደርግልን፡፡
  

21 comments:

 1. አምላክ አያረጅም አይቀየርም።ለጣኦታት ከሆኔ ግን የምያመልኩትም እንደዝዉ ዋዛ ፌዛዛ ናቸዉ።

  ReplyDelete
 2. አሮጌ ነው ይቀየር? ጉድ በል ጎንደር

  ReplyDelete
  Replies
  1. What do you mean, when you said "guode bele Goddard?" Are you joking? If it is joking, that is okay. Because it is the character of the devils.

   Delete
 3. ማቅ ሲነካ ነው ያዙኝ ለቀቁኝ የሚለው

  ReplyDelete
  Replies
  1. Non. Do you no empty jar, that is you. You just stepped on the on the innocent shoulder with false accusations. Why you aren't try to learn the bible.?

   Delete
 4. shame on aba selama website.wesate hateyte nawe atewashuuuuuuuuuuuu

  ReplyDelete
 5. እንደተለመደው….ፍሬን የበጠሰ ጽሑፍ….ከሰላማ ብሎግ!!
  (ሀ) ክንብንቤን አውርጄ ስመ - ክርስቶስ የሰፈረበትን የቃልኪዳኑን ታቦት በአስተብርኮ በማክበር ልጀምር!!
  1-በመጀመሪያ …ታቦት ለብሉይ ኪዳን እንጅ ለሐዲስ ኪዳን አያገለገልም… የሚል ጥቅስ ብትሰጡን መልካም ነበር፡፡ምክንያቱም እኛ በሐዲስ ያልተሻሩ ሁሉ በብሉይም እንደጸኑ ይቀጥላሉ ብለን እናምናለን፡፡ስለዚህ በሐዲስ የእንስሳት ደም እየተሰዋ ፍጡር ከፈጣሪው ይገናኝበት የነበረውን ታቦት መሥዋዕቱን በሐዲስ ኪዳኑ በግ መስዋዕት በጌታችን በኢሱስ ክርስቶስ ቀይረን ብሉዩን ከሐዲስ አስማምተን እየሄድን ነው፡፡በዚህ ድርጊታችን በምዕራባውያን አፍዝ አደንግዝ ፈዞ የራሱ ለሆነው ሁሉ ከውጭ ማስረጃን ለማግኘት ከሚባዝነው በማንነት ቀውስ ውስጥ የወደቀ ፕሮቴስታንት መራሽ ተውልድ ውጭ ከማንኛውም ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ወቀሳ ደርሶብን አያውቅም፡፡
  2 - ደግሞም ታቦት በሀዲሱ ያልተሸሩት 10ቱ ቃላት የተጻፉበት፣የጌታቻን የኢሱስ ክርስቶስ ዘለዓለማዊ ሥም አልፋ ወኦ(ሜጋ) የሰፈረበት በመሆኑ ብንሰግድና ብንንበረከክለት …ወበእንተዝ አዕበዮ እግዚአብሄር ጥቀ ወፀገዎ ስመ ዘየዐቢ እምኩሉ ሥም ከመ ለሥሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኩሉ ብርክ…ትርጉም ….ስለዚህም ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰግድ ዘንድ እግዚአብሄር ፈጽሞ አከበረው፤ከሥም ሁሉ የበለጠ ሥምን ሰጠው…የሚለውን የሐዋርያው ጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 2 ቁ 9--10 ያነበበ ሰው ታቦትን ለማክበር ባይታደል እንኳ የሚያከብሩትን ሰዎች የሚነቅፍበት አንደበት እንደሌለው ሊረዳ ይገባ ነበር፡፡
  3 - የጽሑፉ ማጠንጠኛ ሆኖ የቀረበው የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ቁ 23 የሚናገረው ስለሥልጣነ - ክሕነት እንጅ ከክሕነት ወይም ከጉባኤ ክትትል በኋላ ስለሚመጣው ማዕረግ አይደለም፡፡ስለዚህ ጥቅሱ የጽሑፉን ሀሳብ አይደግፍም--ሐሜቱን ጥቅስ ለመቀባት ካልተፈለገ በቀር!!ትንሽ ላብራራው!!ሥልጣነ ክሕነት የምንለው ዲቁና፣ቅስና(ምንኩስና) እና ጵጵስና የመሳሰሉ ካሕኑ ምስጢራተ ቤ/ክ ለመፈጸም ማለትም ለመቀደስ፣ለማቁረብ፣ለማጥመቅ፣ለመናዘዝ፣ክሕነት ለመስጠትና ለመሳሰሉት የሚያበቁ በነፍሐተ መንፈስቅዱስ የሚገኙ ጸጋዎችን ነው፡፡ምስጢረ - ክሕነት በራሱ ከ7ቱ ምስጢራተ ቤ/ክ አንዱ ነው፡፡በሌላ በኩል ቅጽል ስያሜዎች የምንላቸው ከክሕነት በፊትም ሆነ በኋላ በአገልግሎትና በትምሕርት ብቃት የሚገኙ ብዙ ጊዜ ክብርንና ሹመትን ወይም ተሰያሚው ለተሰየመበት ደብር ያለንን ክብር ለመግለጽ በትውፊታዊ መልኩ ከታላላቅ አበው ወይም ከማኅበረ ካሕናት የሚሰጡ ስያሜዎች ናቸው፡፡ለምሳሌ፡- መጋቤ/ምስጢር(ቅኔ መምህር ማለት ነው)፣መጋቤ ሐዲስ፣ሊቀ ትጉሃን፣በኩረ ምዕመናን፣ሊቀ ጠበብት፣ንቡረ ዕድ(አክሱም ጽዮን ላይ በአስተዳዳሪነት ለተሾመ ሁሉ የሚሰጥ)፣ወዘተ ስያሜዎች በአደባባይ ከፍ ብሎ ለመጠራት የሚጠቅሙ ስያሜዎች እንጅ እንደ ዲቁናና ቅስና ምስጢረ ክሕነት መፈጸሚያ አይደሉም፡፡ስለሆነም እንዲህ አይነት ስያሜዎች ሲሰጡ ድርጊቱን ሲሞናዊ ለማለት መሯሯጥ ግነት ይመስለኛል፡፡
  4 - ታቦት ለእስራኤል ብቻ ነው የተሠጠው የሚለው የጽሑፉ መንፈስ በጣ…..ም አስገርሞኛል፡፡ይቺን በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 15 ቁ 22 ጀምሮ ያለች ሙስሊሞች ኢሳ (ኢየሱስ) የተላከው “ለእስራኤል ብቻ ነው” ሲሉ የሚያቀርቧት መከራከሪያ አስታውሶኛል፡፡ቃል በቃል ላቅርባት፡- “እነሆም፥ ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ። ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል ብላ ጮኸች። እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው። በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት እያሉ ለመኑት። እርሱም መልሶ። ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።” እነፊደላዊ እንግዲህ በእናንተ ታቦት የተሰጠው ለእስራኤል ብቻ ነው የሚል መከራከሪያ ከሄድን …ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም… ያለው ኢሱስም በናዝሬት መንደሮች ተወስኖ መቅረቱ ነው፣10ቱ ቃላትም ላይመለከቱን ነው፣የዳዊት እነዛ ሁሉ ስለ እስራኤል እና ቤተ እስራኤል ብቻ የተነገሩ ትንቢቶች ለእኛ በክርስቶስ ላመንን ሁሉ ይፈጸማሉ የሚለው ተስፋ ገደል መግባቱ ነው፡፡አይይይ!! እረ መቼ ይሆን አእምሯችሁ ከአውሮፓዊ ሚሽነሪ አስተሳሰብ ቅኝ ግዛት ወጥቶ ማሰብ የሚጀምረው!!አይይይ!!!

  ReplyDelete
 6. እንደተለመደው….ፍሬን የበጠሰ ጽሑፍ….ከሰላማ ብሎግ!!
  (ለ) እሺ ጉዳዩን እንይላችሁ--በቅዱስነታቸው ላይ ያቀረባችሁትን የክስ መዝገብ!!
  ዘገባችሁ ቀድሞ ለደመደመ አእምሯችሁ ድጋፍ በመፈለግ ብቻ ስለተጻፈ እንከኑ ብዙ ነው፡፡
  እንከን 1፡- ያቀረባችሁት ሰነድ የ1999 ዓ.ም እና 2005 ዓ.ም መሆኑ ሳያንስ እሱም በጣም የደበዘዘ እና የላሸቀ መሆኑ ሲታይ የደረሰኙ ሕጋዊነት ላይ ጥያቄ ልናነሳ ግድ ነው፡፡ትክክለኛነቱን እጠራጠራለሁ!!እናም…በፎረንሲክ እንዲጣራ ትዕዛዝ ሰጥተናል…እላለሁ እንደ ዳኛ!!
  እንከን 2፡- ማንም ጤናማ አእምሮ ያለው ሰው ሊያስበው እንደሚችል ጉቦ (በእናንተ አነጋገር ሲሞናዊነት) በደረሰኝ ሲሰበሰብ አይተን አናውቅም፡፡ስለዚህ አሁንም የደረሰኙ ትክክለኛነት መጠርጠሩ ግድ ነው!!እናም…ደረሰኙ ተአማኒነትና ተቀባይነት የሚሰጠው ሆኖ አልተገኘም…ብያለሁ በራሴ ችሎት!!
  እንከን 3፡- በገጠሪቷ የኢኦተቤክ አነጋገር ታቦት እና ቤ/ክ እርስ በርስ ተለዋጭ እየሆኑ የሚነገሩ ቃላት ናቸው፡፡ማለትም አንድ ሰው የእከሌ ታቦት ሲል የእከሌ ቤ/ክ እያለ ነው፣ታቦታችን ማለትም ቤ/ክናችን ማለት ነው፡፡ስለዚህ ፊደላዊ አንዳትሆኑ እፈራለሁ፡፡እናም… ከአካባቢው ወግና ልማድ አንጻር የከሳሾችን ሰነድ ትክክለኛ ነው ብሎ ለመቀበል አልተቻለም…በይኛለሁ!!
  እንከን 4፡- እናንተን ይቅር ይበላችሁና አሮጌ ታቦት በአዲስ ለመቀየር 10 ሺህ ብር ተከፈለ አላችሁን፡፡ነገር ግን ያቀረባችሁት ደረሰኝ ..አሮጌውን በአዲሱ ለመቀየር.. አይልም፡፡እንግዲህ በእናንተ አስተሳሰብ አዲስ ከተባለ የግድ አሮጌ አለ!!ወይ ውስጥ አዋቂነት!!አይይይ!!ለማንኛውም አንባቢ ተረዳ!! (1) ታቦታት በምንም መልኩ በዘመናት የሚቀየሩ አይደሉም፣(2) ሌቦች እንኳ ለመመዝበር የሚሞክሩት ብዙ ጊዜ የጥንት የተባለውን ነው--እንኳን ጳጳሱ ሌባው ራሱ ታቦት በጊዜያት እንደማይቀያር ስለሚያውቅ፣(3) ሌባ የሚሸጠው እያሉ የሚያሳንሱትንም አትስማቸው--ጌታችንም በ30 ብር ተሸጧላ!!፣(4) አዲስ ታቦት ማለት ገና ለተቋቋመ ህንጻ ቤ/ክ መንበር የተዘጋጀ ማለት ሊሆን ይችላል፣ወይም (5) በነባር ቤ/ክ ድርብ የሚሆን!!ስለዚህ ነገሮችን ፈልጠን ልናይ ግድ ነው!!(6) በዚህ ላይ ሁልጊዜም በየብሎጎቹ የሚቀርቡ ወሬዎች የግራ ቀኝ ማስረጃ ሳይሰማባቸው ለአንድ ቡድን ዐላማ ማስፈጸሚያ ብቻ የሚነዙ መሆናቸውን እያየን በንስር ዐይን ልናይ ይገባናል!!እናም…ከሳሽ ያቀረበው ማስረጃ ክሱን የሚያስረዳ ሆኖ አልተገኘም…አልተቀበልነውም!!
  እንከን 5፡- ቤ/ክ ውብ ዶግማና ቀኖናዋ እንደተጠበቀ ሆኖ አስተዳደሯ ግን እኛ በምንፈልገው ደረጃ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ሆኖም ከቤተ - ፕሮቴስታንት ሲነጻጸር እኛ ቤት ያለው አስተዳደር እጅጉን የላቀ ነው--የገዘፈ!!የእናንተ እኮ የኢንተርፕርነሮች (በክርስቶስ ሥም ራሳቸውን ያደነደኑ ወፍራም ፓስተሮቼን ማለቴ ነው) መፈልፈያ፣የቅዥታሞች ማደናገሪያ (ነቢይ ነን የሚሉት ማለቴ ነው)፣የልሳናሞች መናኽሪያ (በልሳን እናወራለን የሚሉ)፣የዳንኪረኞች መፈንጪያ (የመዝሙር ኮንሰርት አቅራቢዎች)፣የዘቀጡ የናይጄሪያ ፓስተሮች መፈንጪያ፣ወዘተ….ነው!!ስለሆነም ምን ቅር ቢለንም ወደ እናንተ አያምረንም!!በፕሮቴስታንት ተመርቶ ሞራላዊ ተምሳሌትነት ያለው ትውልድ የቀረጸ አፍሪካዊም ሆነ አውሮፓዊ ወይም አሜሪካዊ ሀገር መች አለና--በሰብአዊ መብት ሰበብ ወንድና ወንድ እያጋባ ክርስትናን በስመ ዘመናዊነት ከማዝቀጥ በቀር!!እናም…….
  ….ከሳሽ ያቀረበው ክስ የክስ ምክንያት ስለሌለው፣በበቂ ማስረጃ ያልተደገፈ ስለሆነ፣ክሱን ለማቅረብ የሚያስችል ከኢኦተቤክ የተሰጠ ውክልና ወይም በጉዳዩ መብትና ጥቅም ያለው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ከተከሳሽ ስላልቀረበ መዝገቡን ዘግተን ተከሳሽን በነጻ አሰናብተናል፤ተከሳሽ ለደረሰበት መጉላላት ወጭና ኪሳራ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው….
  ማረሚያ ቤት ከሳሽ ክሳቸውን በሚያሰሙበት ወቅት ችሎት ላይ ተከሳሽን ባልተገቡ ቃላት በመዝለፍ የችሎቱንና የተከሳሽን ክብር ስለነኩ የተፈረደባቸውን የ6 ወራት እስራ ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ታዟል!!ይጻፍ!!
  መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ!!
  “ጓ” ጠረጴዛውን በመዶሻ!!
  የዳኛ ሕሩይ (ደብተራ) ፊርማ ……

  ReplyDelete
 7. እንደተለመደው….ፍሬን የበጠሰ ጽሑፍ….ከሰላማ ብሎግ!!
  (ለ) እሺ ጉዳዩን እንይላችሁ--በቅዱስነታቸው ላይ ያቀረባችሁትን የክስ መዝገብ!!
  ዘገባችሁ ቀድሞ ለደመደመ አእምሯችሁ ድጋፍ በመፈለግ ብቻ ስለተጻፈ እንከኑ ብዙ ነው፡፡
  እንከን 1፡- ያቀረባችሁት ሰነድ የ1999 ዓ.ም እና 2005 ዓ.ም መሆኑ ሳያንስ እሱም በጣም የደበዘዘ እና የላሸቀ መሆኑ ሲታይ የደረሰኙ ሕጋዊነት ላይ ጥያቄ ልናነሳ ግድ ነው፡፡ትክክለኛነቱን እጠራጠራለሁ!!እናም…በፎረንሲክ እንዲጣራ ትዕዛዝ ሰጥተናል…እላለሁ እንደ ዳኛ!!
  እንከን 2፡- ማንም ጤናማ አእምሮ ያለው ሰው ሊያስበው እንደሚችል ጉቦ (በእናንተ አነጋገር ሲሞናዊነት) በደረሰኝ ሲሰበሰብ አይተን አናውቅም፡፡ስለዚህ አሁንም የደረሰኙ ትክክለኛነት መጠርጠሩ ግድ ነው!!እናም…ደረሰኙ ተአማኒነትና ተቀባይነት የሚሰጠው ሆኖ አልተገኘም…ብያለሁ በራሴ ችሎት!!
  እንከን 3፡- በገጠሪቷ የኢኦተቤክ አነጋገር ታቦት እና ቤ/ክ እርስ በርስ ተለዋጭ እየሆኑ የሚነገሩ ቃላት ናቸው፡፡ማለትም አንድ ሰው የእከሌ ታቦት ሲል የእከሌ ቤ/ክ እያለ ነው፣ታቦታችን ማለትም ቤ/ክናችን ማለት ነው፡፡ስለዚህ ፊደላዊ አንዳትሆኑ እፈራለሁ፡፡እናም… ከአካባቢው ወግና ልማድ አንጻር የከሳሾችን ሰነድ ትክክለኛ ነው ብሎ ለመቀበል አልተቻለም…በይኛለሁ!!
  እንከን 4፡- እናንተን ይቅር ይበላችሁና አሮጌ ታቦት በአዲስ ለመቀየር 10 ሺህ ብር ተከፈለ አላችሁን፡፡ነገር ግን ያቀረባችሁት ደረሰኝ ..አሮጌውን በአዲሱ ለመቀየር.. አይልም፡፡እንግዲህ በእናንተ አስተሳሰብ አዲስ ከተባለ የግድ አሮጌ አለ!!ወይ ውስጥ አዋቂነት!!አይይይ!!ለማንኛውም አንባቢ ተረዳ!! (1) ታቦታት በምንም መልኩ በዘመናት የሚቀየሩ አይደሉም፣(2) ሌቦች እንኳ ለመመዝበር የሚሞክሩት ብዙ ጊዜ የጥንት የተባለውን ነው--እንኳን ጳጳሱ ሌባው ራሱ ታቦት በጊዜያት እንደማይቀያር ስለሚያውቅ፣(3) ሌባ የሚሸጠው እያሉ የሚያሳንሱትንም አትስማቸው--ጌታችንም በ30 ብር ተሸጧላ!!፣(4) አዲስ ታቦት ማለት ገና ለተቋቋመ ህንጻ ቤ/ክ መንበር የተዘጋጀ ማለት ሊሆን ይችላል፣ወይም (5) በነባር ቤ/ክ ድርብ የሚሆን!!ስለዚህ ነገሮችን ፈልጠን ልናይ ግድ ነው!!(6) በዚህ ላይ ሁልጊዜም በየብሎጎቹ የሚቀርቡ ወሬዎች የግራ ቀኝ ማስረጃ ሳይሰማባቸው ለአንድ ቡድን ዐላማ ማስፈጸሚያ ብቻ የሚነዙ መሆናቸውን እያየን በንስር ዐይን ልናይ ይገባናል!!እናም…ከሳሽ ያቀረበው ማስረጃ ክሱን የሚያስረዳ ሆኖ አልተገኘም…አልተቀበልነውም!!
  እንከን 5፡- ቤ/ክ ውብ ዶግማና ቀኖናዋ እንደተጠበቀ ሆኖ አስተዳደሯ ግን እኛ በምንፈልገው ደረጃ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ሆኖም ከቤተ - ፕሮቴስታንት ሲነጻጸር እኛ ቤት ያለው አስተዳደር እጅጉን የላቀ ነው--የገዘፈ!!የእናንተ እኮ የኢንተርፕርነሮች (በክርስቶስ ሥም ራሳቸውን ያደነደኑ ወፍራም ፓስተሮቼን ማለቴ ነው) መፈልፈያ፣የቅዥታሞች ማደናገሪያ (ነቢይ ነን የሚሉት ማለቴ ነው)፣የልሳናሞች መናኽሪያ (በልሳን እናወራለን የሚሉ)፣የዳንኪረኞች መፈንጪያ (የመዝሙር ኮንሰርት አቅራቢዎች)፣የዘቀጡ የናይጄሪያ ፓስተሮች መፈንጪያ፣ወዘተ….ነው!!ስለሆነም ምን ቅር ቢለንም ወደ እናንተ አያምረንም!!በፕሮቴስታንት ተመርቶ ሞራላዊ ተምሳሌትነት ያለው ትውልድ የቀረጸ አፍሪካዊም ሆነ አውሮፓዊ ወይም አሜሪካዊ ሀገር መች አለና--በሰብአዊ መብት ሰበብ ወንድና ወንድ እያጋባ ክርስትናን በስመ ዘመናዊነት ከማዝቀጥ በቀር!!እናም…….
  ….ከሳሽ ያቀረበው ክስ የክስ ምክንያት ስለሌለው፣በበቂ ማስረጃ ያልተደገፈ ስለሆነ፣ክሱን ለማቅረብ የሚያስችል ከኢኦተቤክ የተሰጠ ውክልና ወይም በጉዳዩ መብትና ጥቅም ያለው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ከተከሳሽ ስላልቀረበ መዝገቡን ዘግተን ተከሳሽን በነጻ አሰናብተናል፤ተከሳሽ ለደረሰበት መጉላላት ወጭና ኪሳራ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው….
  ማረሚያ ቤት ከሳሽ ክሳቸውን በሚያሰሙበት ወቅት ችሎት ላይ ተከሳሽን ባልተገቡ ቃላት በመዝለፍ የችሎቱንና የተከሳሽን ክብር ስለነኩ የተፈረደባቸውን የ6 ወራት እስራ ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ታዟል!!ይጻፍ!!
  መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ!!
  “ጓ” ጠረጴዛውን በመዶሻ!!
  የዳኛ ሕሩይ (ደብተራ) ፊርማ ……

  ReplyDelete
  Replies
  1. This is very nice. Hiruy, you have a lot of knowledge in depth. I learned a lot through reading you article. Thank you!!

   Delete
 8. ታቦት የሚሉት ቀልድ መሆኑን በዚህ ይታወቃል። በካርኒ የሚሸጥ ታቦት ተሸክመው ህዝብ ሲያሰግዱ ያሳዝናል። ህዝቡማ ልቡ ታውሮ ማስተዋል ተስኖታል። የታቦትና የጽሌው ቃል ኪዳን ለእስራኤላውያን ነበር። ለዚያውም ለ12 ነገድ አንድ ብቻ። እነዚህ ግን ራሳቸው ጠርበው በካርኒ እየገዙ በየሰፈሩ ተክለው ይሰግዳሉ፤ ያሰግዳሉ። ይባስ ብሎ አባ መቃርዮስ እንደአላቂ እቃ አሮጌውን እየሰበሰበ በገንዘብ ይለውጣል። የሚገርምና የሚያሳዝን ነገር ነው።

  ReplyDelete
 9. የዘመናችን የቤተ ክር..አላፊዎች ዲቁናው ሳይገባቸው ወደ ቅስናው ቅስናውን ሳይረዱት ወደ ጵጵስና
  ጵጵስናውን ሳይገነዘቡት ወደ ብትርክና ይሸጋገሩና ያዘው ልቀቀው ይላሉ፡ በያዘው ልቀቀውና ገንዘብን በማጋብስ አገር አይቀና ሰላም አይመጣ እንዲያው እስከዚያው አለሁ ለማለት እንጂ።

  ReplyDelete
 10. የዘመናችን የቤተ ክር..አላፊዎች ዲቁናው ሳይገባቸው ወደ ቅስናው ቅስናውን ሳይረዱት ወደ ጵጵስና
  ጵጵስናውን ሳይገነዘቡት ወደ ብትርክና ይሸጋገሩና ያዘው ልቀቀው ይላሉ፡ በያዘው ልቀቀውና ገንዘብን በማጋብስ አገር አይቀና ሰላም አይመጣ እንዲያው እስከዚያው አለሁ ለማለት እንጂ።

  ReplyDelete
 11. አምላክ አያረጅም
  ኦሪት ለወንጌል ጥላና ምሳሌ መሆኗን የተረዱ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና ምእመናን ደግሞ ማፈሪያና አንገት መድፊያ ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. That is true, God never get old. Also everything belongs to him never get old. Aba selam groups and their followers are layers. They always accuse the innocent people and pure and true faith. They never have the word of God. The spray the toxic staffs that they get or receive from devils to kill the people who has faith in Jesus. Let me tell you one thing, why you guys don't stop suing the church of Jesus? I do understand, because you are moving in devils sprit. Devils are always fighting the truth.

   Delete
 12. አባሰላማ መናፈቅ የማያገባውን የሚያወራ ወሬኛ

  ReplyDelete
 13. Are you kidding? Aba Abraham was sold 259000 U SA dollar, when he was USA.Buyer was naive mk elements.

  ReplyDelete
 14. enihen abat enante wushoch ketelachihachew, he is doing great

  ReplyDelete
 15. yegermal!!!!ye aba mekaryos mezbera be abune argawi beal magest sigalet!!! Merega ena Maserga yekerbebet guday haset belo makreb ke diablos ke abatachu yeweresachut selehone aygermenm!! ESKE MECHI NEW HEZEBU YEMNATALEW YE ADIGRAT HIZB ENA KAHINAT EYALEKESU NEW BE HAYMANOTACHWE? AHUNEM YE TABOTU SHIYACHI YEKUM!! HULACHIN KE ADIGRAT KAHINAT ENA MEMENAN ENMAR!!! MEKARIYOS + DIYBLOS= ARIOS!!! SELAMA BE MEREGA SELEKERBLEN ENAMESEGNALEN KETLUBET!!!!

  ReplyDelete
 16. Pastor With Full Blown AIDS Confesses To Sleeping With Many Church Members
  By Liya Ahmed 10/10/2014 08:41:00 // News
  220 Google +0 0 0

  Juan Demetrius McFarland Juan Demetrius McFarland

  Former Montgomery, Ala., pastor, Juan Demetrius McFarland, who had led his church for 23 years, walked up to the pulpit and told his congregation that he has full-blown AIDS and that he had slept with church members who never knew his health status.

  “He confessed to the entire membership and then to the city of Montgomery, because as soon as he got done confessing, it went all over Montgomery anyway,” Deacon Nathan Williams Jr. told WSFA 12 News. “So it’s nothing we [are] making up. It’s coming out of his mouth.”

  According to the news station, McFarland’s announcement has continued to shake the Shiloh Missionary Baptist Church to its foundation. Church members told the news station that they were stunned to learn, from McFarland’s admission, that he found out he was HIV-positive in 2003 and has had AIDS since 2008. But that wasn’t all. According to the news station, McFarland also acknowledged that he had used drugs and misused church funds.

  According to WSFA, “McFarland was removed as church pastor on Oct. 5.”

  Several members of the church told the news station that the revelation not only has stunned the church but also has several women concerned for their safety.

  “I know a young lady who is a member of the church who says she has slept with him and that she didn’t want this to go public, and she running out now trying to find out if there is anything wrong with her,” a church member, who didn’t want to be named, told the news station. “And my heart goes out to her because she’s been a wonderful church member, and then for something like this to happen. The fact that he didn’t tell them at all, that’s a crime in itself.”

  Very sad.

  ReplyDelete