Wednesday, October 29, 2014

የሲኖዶሱ ስብሰባ እና የማቅ ዘገባዎች

read in PDF

ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በሐሰትም የሚናገር አያመልጥም. (ምሳ.19:5) 
ሰሞኑን ማቅ ስለገባበት ለሕግ ተገዛ አጣብቂኝ አስመልክቶ በሐራ ብሎግ ስለሚናፈሰው የሐሰት ወሬ አንድ ለማለት ፈለግን። ቅዱስ ሲኖዶስ 3ኛውን ዓመታዊ ስብሰባ ከማድረጉ ቀደም ብሎ የጠቅላላ ሰበካ ጉባኤ ስብሰባ እንደነበር ይታወቃል። በዚህ ጉባኤ ላይ ማቅ ሕገ ወጥነቱ በሰፊው የተነሳ ሲሆን ከቅዱስ ፓትርያሪኩ ጀምሮ በብዙዎቹ የጉባኤው  ተሳታፊዎች ጠንካራ ተቃውሞ የደረሰው መሆኑ ታውቋል። ይኽንን ተከትሎ ማቅ ጉዳዩ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንዲነሳለትና የጳጳሳቱን ድጋፍ አግኝቶ በቀላሉ ለማምለጥ እንድችል ያላደረገው ጥረት የለም። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉት አባቶች እንደሚናገሩት በብዙ የሚቆጠር ብር ለእያንዳንዱ ሊቀ ጳጳስ በመበተንና እንዲሁም በተለያየ መንገድ ድጋፋቸውን ለመሰብሰብ አጥብቆ መሯሯጡ የአደባባይ ምሥጢር ነበረ።  
ይኽ በእንዲህ እንዳለ በሐራ ተዋሕዶ በኩል ማቅ የሚያወናጭፈው የሐሰት ወሬ ግን ቀደም ሲል ከነበረው በዓይነቱም ሆነ በይዘቱ እጅግ የከረፋ ሆኗል። ነገሩን በውል ስናየው ከወንጀሉ ለማምለጥ በሚያደርገው ጥረት የአንባቢ ግንዛቤ መኖሩን  እንኳ ዘንግቶታል። ወይም የተፈለገውን ያክል ብዋሽ ሥራዬ ስለሆነ ልቀይረው አልችልም የሚል ይመስላል። በእኛ ዘንድ እውነቱ ግን ,ያዳቆነው.....ሳያቀስ አይቀርም. እንደሚባለው ከጅምሩ የተዋሐደው የሐሰት መንፈስ ወደዳር እያወጣው መሆኑ ነው። የቆየውን ወደኋላ እንተወውና አሁን ሰሞኑን ,ሐራ ተዋሕዶ. ብሎግ የተለጠፈውን ውሸት እንመለከት፦ 

ቅዱስ ፓትርያሪኩ በቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ተገሰጹቅዱስ ፓትርያሪኩ ባደረጉት ጥፋት ይቅርታ ጠየቁቅዱስ ሶኖዶስ ያዘጋጀው አጀንዳ ሃያ ሁለት ነው።የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ 14 አጀንዳ ተይዟል። 
ይህ የሐሰት መረጃ እስከተለጠፈበት ጊዜ ድረስ የማቅ ጉዳይ ቅዱስ ሲኖዶሱ ያልተወያየበት ሲሆን የሌለ ውሸት በመፍጠር ያልተደረገን ታሪክ በሐሰት አስነብቦናል። ምክንያቱም ቅዱስ ፓትርያሪኩ አልተገሰጹም። ምን ስለአደረጉ? ሕጋዊ አሠራር ይስፈን፤ ማቅ ከሕገ ወጥነት ወጥቶ በሕግ ይተዳደር ስለአሉ? ቅዱስ ፓትርያሪኩ ይቅርታም አልጠየቁም። በመሠረቱ ይቅርታ ይጠይቁ ብሎ የቀረበ የሲኖዶስ አካልም አልነበረም። ፀሐይ የሞቀውና ሰው ያወቀው እውነቱ ግን በቅዱስ ፓትርያሪኩ እግር ላይ ወድቀው ይቅርታ የጠየቁት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ናቸው። ይኽም ማቅን አስመልክቶ በአደረጉት ከመሥመር የወጣ ንግግራቸው ተጸጽተው እንደሆነ ታውቋል። 
ማቅ ውሸቱን እውነት ለማስመሰል የሁለት ሁለትን አጀንዳ የሁለት ሰባት ነው ብሎ በመለጠፍ አንባቢውን ሁሉ ለማደናገር ሞክሯል። እንደ ገሳጭ አስመስሎ ያቀረበው የአቡነ ሉቃስ ፎቶም በሁለት ስድስት ጉባኤ ላይ የነበረ ፎቶ ነው።እንዲህ ዓይነቱ ውሸታም ማኅበር ነው ለቤተ ክርስቲያን እሠራለሁ በማለት ቤተ ክርስቲያንዋን የሚያምሰው። በቅንነት የዚህ ማኅበር አባል ሆናችው ወገኖቻችን የውሸቱ ሰለባ እንዳትሆኑ፥ ከእውነት አምላክ ጋር እንዳትጣሉ ወደራሳችሁ ተመለሱ። እስከዛሬ ማቅ የዋሸውን ሁሉ በዚህ ማረጋገጥ ስለምትችሉ የሐራን ብሎግ ከፍታችሁ እንድታነቡ በአጽንዖት እንጋብዛችኋለን። በጥቂት ጥቅመኞችና ፖለቲከኞች እየተመራችሁ ቤተ ክርስቲያናችሁን እንዳትበድሉ፤ እግዚአብሔር የቀባቸውን አባቶች በማከፋፈልና በማጣላት የሰይጣንን ሥራ ከመሥራት ምርጫችሁን አስተካክሉ እንላለን። 
በሌላ አንጻር ማቅ ይህን ያህል የማጭበርበር ሥራ ለመሥራት የተገደደው ከቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት መካከል ያሉ ቅምጦቹ አዲሱን አጀንዳ ያልሰጡት መሆኑን  ያሳያል። ምንም እንኳ ቅምጦቹ ውስጥ ለውስጥ ህሊናቸውን ሸጠው አለንልህ ብሉትም የፓትርያሪኩ ጠንካራ አቋም ሳያስፈራቸው አልቀረም። ቀድሞ ፓትርያሪኩ ዝምተኛ ናቸው፤ በአቋም
የመሥራት ድፍረት አይኖራቸውም የሚለው የአንዳንዶች ግምት አሁን ባለው የፓትርያሪኩ እውነተኛና ጠንካራ አቋም ዋጋ አጥቷል።  
ማቅ በሚያናፍሰው የሐሰት ወሬው የቅዱስ ፓትርያሪኩን መሠረታዊ አቋም ለመቀልበስ፤ በሌሎችም ዘንድ የተሳሳተ መረጃ ለመስጠት እየሞከረ ነው። እንዳንድ የዋሀን ሰዎችም ይኽንን የሐሰት ወሬ ይዘው ቅዱስ ፓትርያሪኩ ማቅን ሊያፈርሱ ነው የሚለውን ሲያናፍሱ ተሰምተዋል። እውነቱ ግን የቅዱስ ፓትርያሪኩ አቋም ሕጋዊ አሠራር ይስፈን ነው። ማቅ በሕገ ወጥነት በቤተ ክርስቲያንዋ እምነትና ንብረት ላይ እያደረሰ ያለውን በደል ያቁም፣ በሕግ ከለላነት ይኑር ነው። ይኽ የቅዱስ ፓትርያሪኩ ሀሳብ አሁን በብዙዎቹ ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱ ተረጋግጧል።  
እኝህን አባት (ቅዱስ ፓትርያሪኩን)ሕግ ይከበር፤ ሥርዓት ይጠበቅ የሚለው ጠንካራ አቋማቸው እስከአሁን ከአየናቸው አባቶች ሁሉ ልዩ ያደርጋቸዋል። በገንዘብ፤ በቅድስና የማይታሙ ለእውነትና በእውነት መቆማቸው ይበል የሚያሰኝ ሲሆን ለማቅና ለቲፎዞዎቹ ግን አልተዋጠላቸውም። በሕግና በሥርዓት እንሥራ የሚለውን አባት ከማክበር ይልቅ የአባትነት ሚናውን ጥሎ እንደ ቦይ ውኃ የሚዋልለውን አባት ማለት ለሐሰተኛው ማቅ ሐይማኖቱ ነው።  
ብዙ አባቶችን ጠጋ ብለን ስለቤተ ክርስቲያናችን ስናወያይ ችግሯን ከመተረክ በቀር የችግሩ መፍትሔን የመጠቆም እብዛም አይታይም። በእርግጥ ማቅ ከቤተ ክርስቲያናችን ችግር አንድ መሆኑ ሲታወቅ አባቶች በአንድነት ሥርዓት ማስያዝና ለችግሩ መፍትሔን ማበጀት ይገባ ነበር። የቤተ ክርስቲያንን ችግር ወደጎን ትቶ ለአንድ ማኅበር መወገን ግን በአባትነት ቤተ ክርስቲያንዋን ለወከሉ ወገኖች እጅግ አሳፋሪ ነው። ማኅበሩ ታርሞ በሕግና በሥርዓት የሚሔድበት ቀን ሲመጣ የሚታዘባቸው ወላወዮችን ነው እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ሕግ አቋም ይዞ የሚታገለውን አባት እንዳልሆነ ይታወቃል። 
ማቅ በሐራ ተዋሕዶ ድህረ ገጹ ,አማሳኞች. የሚለውን ቃል በተደጋጋሚ ይጠቀማል። እነዚህም በማቅ ,አማሳኞች. የሚባሉት ታላላቅ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ በሕግና በሥርዓት እንመራ የሚሉ እንደሆኑ ይነገራል። ታዲያ ,አማሳኝ. ማነው? በሕግና በሥርዓት እንስራ የሚሉት አባቶች ናቸው ወይስ ሕግና ሥርዓት አያስፈልገኝም፤ ሀብቷን ያለአግባብ እዘርፋለሁ የሚለው ማኅበር ነው? መልሱን ለአንባቢያን እንተዋለን። 
ማቅ ቤተ ክርስቲያን በሥርዓትና በሕግ ትመራ የሚሉትን ,አማሰኞች. ሲል የእርሱ አባል ያልሆኑትን ሊቃውንት ደግሞ ,መናፍቅ. ይላቸዋል። መናፍቅ ማነው? መንፈሳዊ አባቱን የማይሰማ፤ የሚያዋርድ ወይስ ለመንፈሳዊ አባቱ የሚታዘዝ? የቤተ ክርስቲያንዋን አስተምህሮና ቀኖና አፋልሶ ለራሱ ንግድና ፖለቲካ ቤተ  ክርስቲያንን  የሚያምስ ማኅበር ግብሩ መናፍቅ ያሰኘዋል። መናፍቅ ማለት ያለውን እውነት የማይቀበል፤ የራሱን ለመተካት እውነትን ጥላሸት የሚቀባ ማለት ነው። ስለዚህ ,መናፍቅ. የሚለውን ይኽን ትርጉም የሚወክል ከማቅ በቀር ሌላ ማነው? 
አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንደ ልጅነታችን በእግረ መስቀላችሁ  ሥር ሆነን፤ እንደ ቤተ ክርስቲያን አባልነታችን ደግሞ ጽኑ አቋም ይዘን የምንማፀናችሁ አንድ ነገር ብቻ ነው። ከመንፈስ ቅዱስ የተቀበላችሁትን የቤተ ክርስቲያን አደራና አባታዊ ሚዛናችሁን ትጠብቁ ዘንድ ነው። ማኅበሩም እንደ ልጅነቱ ለሕግና ለሥርዓት ይገዛ። ለአባቶቹም ይታዘዝ። ቤተ ክርስቲያን አትታመስ። የእርስበርስ መከፋፈልና ውጊያ ይብቃን። ኃይላችንና አንድነታችን ይጽና ስንል ተማኅፀኖአችንን እናቀርባለን።  
በእውነቱ ነኝ!

25 comments:

 1. Wendem ya anten anebeben anetsatsern,gen antem eko ke ebesu bask enji alteshalkem,bizu birr le pappassat betenu setu yalkew.sent setu?le man setu?,meche setu?yemilewun eskaltenagerk deres yantem bere weled hone eko

  ReplyDelete
 2. non sense as usual.....you will never get anything out of it... you stupid tehadiso.....

  ReplyDelete
 3. እጅግ አስቀያሚ ዉሸታሞች..... እዛው የለመድከው አዳራሽ ከመዝለልንና ውሸት ከማውራት ንስሀ ግባ

  ReplyDelete
 4. ''እግዚአብሔር የቀባቸውን አባቶች በማከፋፈልና በማጣላት የሰይጣንን ሥራ ከመሥራት ምርጫችሁን አስተካክሉ እንላለን።'' .......SO what were you doing untill now.... this blogs is dedicated to dissmantle our forfathers .... and now you wanted to believe that you are trying make peace... that is bullshit we already knew everything abot you, do everything you could but we believe God is with us...and you will eat your ''tasty'' shame sooner...until then....we will never give up for your tehadiso rumors.......ንቁም በበዕላዌነ እስከንክቦ ለአምላክነ!!!!!!!!

  ReplyDelete
 5. OOPS .... Did u got noyhing to comment...? hahaha.... ውሸታችሁን የምትደጋግሙት እውነት እንዲመስል ነው እንዴ.? ደግሞ የሚያሳዝነው የማይገባችሁን ስም ''Aba Selama'' መያዛችሁ ነው....እውነቱ ...ድንቄም እውነቱ....እኔ ግን ሃሰቱ ብየሃለሁ....

  ReplyDelete
 6. Mk lie to God and public. I will file law suit they violated copyright and photo shop in pateriarc image.

  ReplyDelete
 7. kikikiki miskin menafk. Mechem tesfa atikortum aydel? Yeqoye foto kweqitawi zegeba lay makatet benanite bet wushet mehonu new. Maferiya, silegazetegninet min tawukuna!!

  ReplyDelete
 8. be wishetu negn maletih new? libona yistachihu kemalet lela min enibel?

  ReplyDelete
 9. ዓለም በሙሉ ዓለምን ለማሳለፍ ይሯሯጣል ሁሉም ዓለም ዳዓሽ ሆኗል።
  የእኛዎቹስ ይህን ቢተገብሩ ምን ይጐልባቸዋል (ዘመነ መንሱት) በመሆኑ

  ReplyDelete
 10. ማቅ ዋሻ ዘረ ዋሾ አታላይ እና ክፉ ነው ጌታ ይገስጸው

  ReplyDelete
  Replies
  1. Either u people believe that there is God and understand that there is a consequence for your actions when you say right is wrong vs wrong is right. I. e. Day is Night where as Night is day. Which means if some numbers of illiterate theological ignorants following M.K. at the end you people R going to be doomed!!!!

   Delete
  2. akatelachu aydel ente agannitoch

   Delete
 11. Ortodx satebereze lezelalem rebute ye mahebere kedusanen 1% aleserathehum zem lematefatena lemasadede anedejuthe lebuna yesetathu

  ReplyDelete
 12. እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ:: ከእውነት ጋር ተጣልታችሁ እውነትን ስትዋጉና ስትቃውሙ ትኖራላችሁ እናንት በአባ ሰላማ ስም የተሸፈናችሁ::

  ReplyDelete
 13. ልኡል እግዚአብሄር ልቦና ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 14. yeMK yezemenat gifina bedel yeejachewun yagegnutal..beteretna..simbematifat andim qen silewegel sataweru bewengel teshefinachihu ewunetun kidachihu besimet yenorachihubetin zemen fetari sint gize tagesachihu?...menfesawi neger kemesirat befit enanite meserat alebachihu...wedelibachihu bitimelesu badonetachihun tagegnutalachihu...Amilak yikir yibelachihu!! Abaselamawoch beritu!!

  ReplyDelete
 15. maqe eko yemiwasewe yetefetrowe hono new. yetegelete yewengel enean ye ewnet telat new. biwash min yidenkal? baheriwe newa

  ReplyDelete
 16. Aba selama inkwan des alesh.Yesinodosu andinet tetebeke.Sinodosu yebelay akal hone

  ReplyDelete
 17. Aba Matias said that mk never paid tax, this is violation will be handled by Revenue office. If mk not paid tax, revenue office must close mk immediately with out any preconditions. That means public finance violation. Not a joke, revenue office will be take action as soon as possible. Most papas have wife and houses never pay tax simply stealing public money in the church. Those mk, gangs, come to the church to collect easy money. The master key point is revenue office must responsible for all this financial games.

  ReplyDelete
 18. yetlikun abat sim yizachihu!! please, wey wede betekirtastiay gibu wey wutu! yalebeleziya andegrachu wedebetu and egrachu wede lela ayhun. hassetegnoch mehonachu sew hulu awkuachuahual! Hara is the best blog!!!

  ReplyDelete
 19. What about now? Where is your truth? Fools! Don't waste your time.

  ReplyDelete