Friday, October 31, 2014

ከቅዱስ ሲኖዶስ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የተዘረጋው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ በሙሉ ድምጽ ጸደቀ።

Read in PDF

 • ·        ቅድስት  ቤተ  ክርስቲያን  እንኳን  ደስ  አለሽ!  
 • ·        ብፁዕ  ወቅዱስ  አባታችን  እንኳን  ደስ  አለዎት!  
 • ·        ብፁዓን  ሊቃነ  ጳጳሳት  እንኳን  ደስ  አላችሁ!  

   በቅዱስ  ፓትርያሪኩ   ብርቱ  አሳሳቢነትና  ጠንካራ  አቋም  የቀረበውና   የቅዱስ  ሲኖዶስ   ምልዓተ  ጉባኤ  በሰፊው  የተወያየበት  ሕገ  ቤተ  ክርስቲያን   ማሻሻያ   በሙሉ  ድምጽ   ጸደቀ።  ሕገ  ቤተ ክርስቲያኑ  አንድ  ወጥ  የሆነና  ከቅዱስ  ሲኖዶስ  እስከ  አጥቢያ  ቤተ   ክርስቲያን  የተዘረጋ መዋቅራዊ  አሠራርን  ያካተተ  መሆኑ ታውቋል።  
ሕጉ  እንዳይጸድቅ  የነበሩ አንድ   አንድ  እንቅፋቶች  ሁሉ ታልፈው በስተመጨረሻ ግን መሳካቱ አልቀረም  ከብዙ  ውጣ  ውረድና  የጊዜ   መባከን  በኋላም  በቅዱስ  ፓትርያሪኩ  ጽኑዕ  አቋምና  በሊቃነ  ጳጳሳቱ  ጥልቅ  ውይይት  ሕገ   ቤተ  ክርስቲያኑ  በትላንትናው  ቀን  በሙሉ  ድምጽ  ሊጸድቅ ችሏል።   

በዘንድሮው  የቅዱስ  ሲኖዶስ  ጉባኤ  ከተለመደው  ውጭ  በቅዱስ  ፓትርያሪኩና  በተወሰኑ ሊቃነ  ጳጳሳቱ   መካከል  ክርክርና  ውጥረት  ሰፍኖ  የነበረው  በማኅበሩ  (ማቅ)  ጉዳይ  መሆኑ  ይታወቃል።   ይኽም  ቅዱስ  ፓትርያሪኩ  የቤተ  ክርስቲያን  ሕግና  ሥርዓት  ይከበር  በሚለው  አቋማቸው   ሲሆን  በማቅ  በኩል  ግን  እንዳፈነገጠ  ለመቀጠል  በተለመደው  ሥልቱ  አባቶችን   በመከፋፈል  የሐሰት  ወሬዎችን  በመንዛት  የአልሞት  ባይ ተጋዳይነት  ሥራውን  አጧጥፎ   ነበር።  ማኅበረ ቅዱሳን እንደሚለውም  ቅዱስ  ፓትርያሪኩ   በሌሎች  ምክርና   ባላመኑበት  ጉዳይ  ሳይሆን  ከመሠረቱ  አምነው  የተነሱበትና  አቋም  የያዙበት  በመሆኑ   በድል  ሊወጡት  ችለዋል።  አንድ  ለዕልፍ  ሆነው  ለድል  እንዲበቁ  ያስገደዳቸው  አባታዊ   አቋማቸው  የዳዊትንና  የጎልያድን  ፍጥጫ  ያስተውሰናል።  ጎልያድ  ባካበተው  የጦር   ልምዱና  ሥልቱ  ቢንጎራደድም፤   ከእውነተኛ  ጋር  የሚቆመውን  እግዚአብሔርን   ቢገዳደርም  ድሉ  ግን  የብላቴናው  ዳዊት  ሆነ።   ምሥጢሩም  የእግዚአብሔር  እጅ   ከእርሱ  ጋር  መሆኑ  ነበር።     መቼም  በማቅ  ሰፈር  የእግዚአብሔርን  እጅ  ከመቀበልና  ለእውነት  ከመሸነፍ  ይልቅ   አዳዲስ  ውሸቶችን  መፈብረክ  የተለመደ  ነው።  የሌለ  ታሪክ  በመፍጠር  አባ  እገሌ   እንዲህ  አሉ፤  አባ  እገሌ  እንዲያ  አሉ  እያሉ  አባቶችን  ቢለያዩም፤  አባቶች  ሊቃነ   ጳጳሳቱና  ፓትርያሪኩ  ግን  በአንድ  ድምጽ:    

 • ·        ማቅ  ወደ  ነበረበት  የሰንበት  ትምህርት  ቤት  ማደራጃ  ሥር  ሆኖ  እንዲሠራ  
 • ·        በሕገ  ወጥነት  የቤተ  ክርስቲያንን  መዝረፍ  ቀርቶ  በቤተ  ክህነቱ  ሞዴላሞዴሎች   እንዲጠቀም  
 • ·        ተጠርነቱ  ለሰንበት  ትምህርት  ቤት  ማደራጃ  እንዲሆን  
 • ·        ንደማንኛውም  ማኅበር  የቤተ  ክርስቲያንዋን  ሕግና  ሥርዓት  አክብሮ   እንዲተዳደር  ሲሆን  ነገር  ግን  ሕገ  ወጥ  ሥራውን  የማያቆም  ከሆነ  እስከ   ማሰናበት  ድረስ  ሥልጣኑ  የቅዱስ  ሲኖዶስ  መሆኑን  ወስኗል።    

የቅዱስ ፓትርያሪኩ አቡነ ማትያስ አጠቃላይ ሀሳብ ፍላጎትና ከመጀመሪያው ጀምሮ የነበራቸው  አቋምም  ይኽ  መሆኑን እያወቀ  ማኅበሩን  ሊያፈርሱ   ነው  በሚል ስልት የሐሰት  መረጃ  በመስጠትና እና በጭፍን ደጋፊዎቹ አማካኝነት በማስወራት  የተወሰኑ ህብረተሰብ ክፎሎችን ያሳሳተ  ቢሆንም  አድማውና  የሐሰት   ቅንብሩ   ግን   ወሬ   ሆኖ   ቀርቷል።
ማቅ በስመአብ እንደተባለ ሰይጣን አጥብቆ የሚፈራውና የሚያስደነግጠው ህግና ሥርዓት አክብረህ ሥራ የሚለውን ትዕዛዝ ላለመቀበል በበርካታ የሀሰት ወሬዎች ሲያስወራ የነበረው መሯሯጥ ሲከሽፍበት የሆነው ሁሉ የሆነው   በእግዚአብሔር  እጅ  መሆኑን  አምኖ  መቀበል  ይገባው  ነበር።  ከአለፈውም  ስህተቱ  ተምሮ  ከአሁኑ  ራሱን  ማስተካከል፤   አባቶች  ላይ  የሚሰነዝረውንም  ጽርፈት  ባቆመ  ነበር።   ይሁን  እንጂ  የጊዮርጊስን  ግብር  የበላ………...  እንደሚባለው  ታርሞ  ከመመለስ  ይልቅ   አሁንም  ቅዱስ  ፓትርያሪኩን  መንቀፉንና  ከአፈርኩ አይመልሰኝ እያሰኘው ያለውን የሐሰት  ወሬውን  ቀጥሎበታል።    
  ቀደም  ሲል  የቅዱስ  ፓትርያሪኩን  ,ሕግና  ሥርዓት  ይጠበቅ.  የሚል  አቋማቸውን  ጥላሸት   እየቀባ  ,ማኅበሩን  ሊያፈርሱ  ነው፤  ቅዱስ  ሲኖዶስ  ገሰጻቸው….  ወዘተ  በማለት  ቆይቶ   አሁን  ደግሞ  ቅዱስ  ፓትርያሪኩ  ከቅዱስ  ሲኖዶስ  አባላት  ጋር  አንድ  ሆኑ  ይለናል።  
ቅድምም  ለቅሶ  አሁም  ለቅሶ!  ታዲያ  ለማቅ  የሚመቸው  የትኛው  ነው?  አቤቱ  ዓይነ   ልቡናውን  አብራለት………….!!!!       በመሠረቱ  ቀድሞም  ቢሆን  ቅዱስ  ፓትርያሪኩና  ሊቃነ  ጳጳሳቱ  የሀሳብ  ልዩነት   እንጂ   በጠብ  ወይም  በዓላማ  አልተለያዩም።   በሀሳብ  ልዩነት  ተወያይቶ  ጠቃሚውን   ሀሰብ   ጨምቆ  ለውሳኔ  ማቅረብ  የብስለት  እንጂ  የመንደር  አምባጓሮ  አልነበረም።  ስለዚህ  ማቅ   ገመዱ  አጥሮበትም   አለመማሩ  ቀኑን  እያሳጠረ  መሆኑን  ያሳያል።  
ስለዚህም  በቅን   ለሚያገለግሉ  ለማኅበሩ  አባላት  መልእክት  አለን!     መልእክት  ቤተ  ክርስቲያናቸውን  በቅን  ለሚያገለግሉ  የማኅበሩ  አባላት     በጥቂት  ጥቅመኞች  በማህበሩ የተለያየ ሚዲያዎች የሚሠራጨው  የሐሰት  ወሬ፤  አባቶችን   ያለማክበርና  ለቤተ  ክርስቲያን  ሕግ  አለመገዛት  የማኅበሩን  ቅን  አገልጋይ  አባላትን   ይወክላል  ብለን  አናምንም።  ወይም  በቤተ  ክርስቲያን  ጥላ  ሥር  ያሉ  የቤተ  ክርስቲያን   ልጆች  ይኽን  የመረዳትና  የማስተዋል  አቅም  ያንሳቸዋል  ለማለትም  ይከብደናል።  ሆኖም   በይሉኝታና  በዝምታ  መመልከቱ   ደግሞ   በራስም  ሆነ  በቤተ  ክርስቲያን  ላይ   ጉዳት   ማስከተሉ  አከራካሪ  አይሆንም።  እስከአሁን  በተሔደበት  መንገድ  ምን  ተገኘ?  ቤተ   ክርስቲያን  ቀብታ  ያከበረቻቸውን  አባቶች  በሥርዓት  ተመሩ  ስለአሉን  ብቻ  መንቀፍና   ማዋረድ  ያስገኘው  በረከት  ወይስ  መርገም?  በአባቶች  ቀሚስ  ሥር  ተደብቆ  አባቶችን   ሰድቦ  ማሰደብ  ወደከፍታ  አወጣን  ወይስ  ቁልቁል  አወረደን?   መልሱን  ለእናንተና   ማስተዋልና  እውቀትን  ሊሰጣችሁ  ለሚችለው  መንፈስ  ቅዱስ  እንተዋለን።  ስለዚህ   ወደጥንቱ  ጅማሬያችሁ  እንድትመለሱ  የዘወትር  ጸሎታችን  ነው።        
በእውነቱ  ነኝ!  
ከቤተ ክህነት

18 comments:

 1. እኔን የገረመኝ ደላላ ሁሉ የዚህ ጉዳይ ተዋናይ መሆኑ ነው በተለይ ግርማ ቀሬ ጨምሮ ሌሎችም
  እናንተም ተአማኒነት አጣችሁ ህገ ቤ/ክ የማቅን ስፍራ የሚውስን ሳይሆን አጠቃላይ መዋቅራዊ አደረጃጀት ነው::በዚህም ከሁለቱም ወገን ይልቅ ቤተ ክርስቲያን ተጠቅማለች

  ReplyDelete
 2. Kale hiwate yaseman

  ReplyDelete
 3. ወይ ማቅ ምን ይሻልሻል ግን ውሸት እኮ ሆነ ቀለብሽ።ብራቮ አባ ሰላማ እንዲህ እውነቱን ስትነግሩን ደስ ይላል።

  ReplyDelete
 4. ያንተ ያለህ ግራ ቀኙን አመዛዝነህ እባክህ ፍጠን ለፍርድህ!!

  ReplyDelete
 5. wushet komo sihed ezih blog lay ayehut !!! Gud bel Gonder ale sewuyew !!!

  ReplyDelete
 6. abatochin Yemisadeb man endehone libachihu yawukewal. Midre menafkan atdikemu MK ayfersim!!! Mekabru derese, tebetene wezete bemalet sitfualilu yeneberachihut enante alneberachihu?

  ReplyDelete
 7. ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያናቸውንና ሀገራቸውን ኢትዮጵያን የሚወዱ አባላት እስካሉት ድረስ እግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎናቸው ነው። ማኅበረ ቅዱሳንና የነ አባ ማትያስ መንግሥት ''ኦርቶዶክሱንና ዐምሐራውን አከርካሪውን ሰብረነዋል'' እያሉ ቢደነፉም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ ኦርቶዶክስም ሆነች ዐምሐራው ተሰብረው አይቀሩም። ይነሣሉ ። የዘረኞችና የበታኞች ሴራ ይከሽፋል !! ለዚህ የጥፋት ሴራ ማኅበረ ቅዱሳን አልተባበርም በማለቱ ስለሆነ አሁን በጠላት ቅኝ ገዥነት የተፈረጀው ተልዕኮውን ስንጠራጠር የነብርን ወገኖች ሁሉ ከማኅበሩ ጎን እንድንቆም ሁነናል። እንደ ዐይን ብሌናችን እንጠብቀው አለን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማሞ ችግርህ የዘር ነው አይደል? ማቅንና አማራን አንድ አድርገህ አታውራ። ማቅ ያልሆንንና ማቅን የምንቃወም በርካታ አማራዎች አለን። ዘረኝነትን የምትቃወም መስለህ ዘረኛ መሆንህን ነው ያረጋገጥክልን። ማቅ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰራው ወንጀል ብዙ መሆኑን ለማወቅ የተለየ ሊቅነት አይፈልግም። እስኪ ከመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት አብዛኛዎቹ ለምን የሚቃወሙት ይመስልሃል? ከኔ ሀሳብ ውጭ ቤተክርሰቲያን መመራት አለባት ስለሚል እኮ ነው። ስማ ወንጌል ድንጋይ አይደለም በኢንጅነሪንግ እውቀት የምትፈለጥ ቁጥር አይደለችም በአካውንታት እውቀት እየተደመረች የምትቀነስ ህግ አይደለችም በጠበቃ እውቀት የምትተነትን። ወንጌል በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈች በእግዚአብሔር መንፈስ ምትብራራ እና በእግዚአብሔር መንፈስ የምትገለጥ ነች።ወንጌል ለማንም ቢሆን በዲግሪ አትገባም። መንፈስ ቅዱስ ሊገልጥልህ ያስፈልጋል። የማቅ ችግር ይሄ ነው። ወንጌልን በዩንቨርሲቲ ዲግሪ በኩል ሊያብራራ ይፈልጋል። ለዚህ ነው ከጥቂት እበላ ባዮች በቀር ከአብዛኛዎቹ የቤተክርቲያኒቱ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችም ሆነ ሊቃውንት ጋር መስማማት ያቃተው። በአማራነት ተከልለህ ሆዳችንን ለማባባት አትሞክር።ማቅን አሁንም እንቃወማለን። እዛው በጠበልህ።

   Delete
 8. I wandered! You guys how much you tyre to make your devils staff.true, but no one be dam in your wrong and false propaganda. Its better to come the truth you guys. Every one gets their price from God. Before the forgiveness time pass you better to back or accept the truth. Mahibere kidusan is doing the right faith that they recieve from God.

  ReplyDelete
 9. ምንይሻል ይሆን የጳጳሳቱን ነገር ?ሲሾሙ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ ነበር ቃል የገቡት ኣሁን ግን እየታየ ያለው ዘረኛና ጎ ጠኛ ከሆነው በ1968 ዓ/ም በብጹእ ወቅዱስ ኣቡነ ቴዎፍሎስ የፈረሰዉን ካህናትን በቶፋነት ቀጥሮ ማሰራትን መልሶ ለማቋቋም እየጣረ ያለዉን ማህበር ወግነው ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ሽንጣቸዉን ገትረው እየተሟገቱ ነው ያሉ በኣሁኑ ሰኣት ልጆቻችን እያሉ የሚጠሩት ካህናቱን ማለትም መምህራኑን ቀሳውስቱን ዲያቆናቱን መነኮሳቱን መዘምራኑን ሳይሆን የማቅ ኣባላትን ብቻን ነው ኣሁን ካህናቱ መውሰድ ያለባቸው እርምጃ መነጋገር ኣለባቸው ምክንያቱም ልጄ ብሎ የማይጠራን ኣባት ኣባት ብሎ መጥራትን በጣም ይቸግራል ለማንኛዉም የእንጀራ ኣባቶቻቸው ለበላተኛ ኣሳልፈው ከመስጠታቸው በፊት ካህናቱ ቤተ ክርስቲያናቸውን ራሳቸውንም ለመጠበቅ መንቀሳቀስና መነጋገር ኣለባቸው ኣባሰላማም ካህናቱ እንዲነቁና ራሳቸውን እንዲጠብቁ እንዲደራጁ ቅስቀሳ ብታደርጉ መልካም ነው እላሎህ መድህን ነኝ ከእውነቱ ሰፈር

  ReplyDelete
 10. Lemen slerasachue church atesefum.yeker yebelachue

  ReplyDelete
 11. ahya yeahya lij meslohal wagahn tagegnaleh mk

  ReplyDelete
 12. ኦኬ! አሁን ገባኝ ለእኔ ለካስ ይህ ብሎግ ቤተ ክህነት ውስጥና የአማሲያኖቹ ነው። ይገርማል አች የቅዱሳን ደምና አፅም የፀናሽ ቤተ ክርስቲያን ስታሳዝኝ። ማህተም ቅዱሳን ጎሊያድ እነሱ ቅዱስ ዳዊት። ቸር አምላክ እስከመቼ?

  ReplyDelete
 13. yerasua arobat yesewu tamasilalech alu, churchachihun titachihu lemin wede orthodox betekiristian metachihu? ai pente ai tehadisso protestant, enawkalen, alamachihu siwur aidelem, minim enkuan yebeg lemid bitlebsu shitachihu yebeg aidelem. yemenafik shitawu keruk yastewukal.

  ReplyDelete
 14. Stop,... Stop lie.... Fake news.

  ReplyDelete
 15. could u posted the new hege betekerestiyan????? !!!pls

  ReplyDelete