Sunday, November 2, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን ሶስተኛው ሲኖዶስ

Read in PDF

ቅዱስ ፓትርያርኩ በ33ተኛው አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ማኅበረ ቅዱሳን ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተገንጥሎ የራሱን ቤተክርስቲያን ለመክፈት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጠዋል። ቅዱስነታቸው መረጃ አለኝ በማለት የገለጡት እውነት ተግባራዊ ከሆነ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሦስት ሲኖዶሶች ሊኖሯት ነው ማለት ነው። ይህ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱ ህጋዊ ተጠሪ እኔ ነኝ እያሉ የሚወዛገቡትን የአገር ቤቱንና የውጪውን ሲኖዶስ የሚያስቆጣ ይሆናል። በእኛ እምነት ግን ማኅበሩ አሁንም ቢሆን ሦስተኛ ሲኖዶስ ነው የሚል አቋም ነው ያለን። ይህን በጥቂት ማስረጃዎች እናሳይ

አንዲት ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ከሚያሰኝዋት ነገሮች አንዱ አስራት በኩራት መቀበልዋ ነው። ማቅ ይኸው ድፍን ሃያ ዓመት አስራትና በኩራት እየተቀበለች ኖራለች። እንዲሁም ተሳስተሻል የሚሉዋትን ሁሉ ለራስዋ ባዘጋጀችው ልዩ ዶክትሪን አማካይነት “ተሀድሶ መናፍቅ” እያለች ነው። የተለየ የአባላት ምዝገባ የተለየ በአባልነት የመጠመቂያ ትምህርትም አላት። ቤተክርስቲያኒቱንና ጳጳሳቱን የምትፈልጋቸው የምታከብራቸው የምታሞግሳቸው እና የምትባርካቸው ከእርስዋ ጋር እስከተሞዳሞዱ ድረስ ብቻ ነው።

እርስዋን ለተቃወመ ሁሉ የሚሆን “በልዩ መገለጥ” የሚቀርብ የነውር ማስረጃ ትፈለስፋለች። ወደዱኝ ብላ ስታንቆለጳጵሳቸው የነበሩትን ሁሉ ተቃወሙኝ ብላ ሙሰኛ፣ ዘረኛ፣ እበላ ባይ፣ ተሀድሶ፣ ቅብርጥሶ ስትል ሀፍረትም የለባት። ማቅን የማይቀበል ጳጳስ ሁሉ ለማሳደድ እንደ ሂዝቦላ ባደራጀቻቸው ሀገር በቀል መሳሪያ የሚጠቀሙ ድንጋይ ወርዋሪና ተሳዳቢ አባላትዋን በተመደቡበት ሀገረ ስብከት ሁሉ ታሰማራለች። በማኅበርዋ ደጅ አንድ ሰው ለቤተክርስቲያን ጠቃሚነቱ የሚነገረው እና የሚታወጀው ከማህበርዋ ጋር እስከተሞዳሞደ ድረስ ብቻ ነው። የማኅበሩ አባል አልሆንም ቤተክርስቲያንን ግን በሚያስፈልገኝ ሁሉ አግዛለሁ ያለ ሰው አለቀለት። ቤተክርስቲያንን ለማገዝ ብቸኛው መፍትሄ ማቅ መሆን ብቻ ነው ተብሎ ስለሚታመን እንዲህ ያለውን ሰው በህቡዕ ብሎጎችዋ ትተገትጋለች የስም ማጥፋት ዘመቻ ደግሞ በስፋት ታደርጋለች።
እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስንመለከት ቅዱስ አባታችን ማቅ ሶስተኛ ሲኖዶስ መመስረትዋንና መሆንዋንም እስከዛሬ እንዴት አላወቁም? ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን። ማቅ ከተቋቋመ በኋላ ቤተክርስቲያን ለዘመናት ተቀብላ ስታስተምራቸው የነበሩ ትምህርቶችን ለመቀየር ተገድዳለች። ማቅ በርካታ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ኦርቶዶክሳዊ አባቶች ያስተማሯቸውን ትምህርቶች ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ አይደሉም እያለችና ተረታ ተረቶችን እያስተማረች ልዩነቶችን እየዘራች ትገኛለች፡፡ ለምሳሌ የኢዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናትና መካከለኛ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስም የኦርቶዶክስ አባቶችም በየመጻሕፍቶቻቸው ቢመሰክሩም ማቅ ግን አትቀበለውም፡፡ ይህን እውነተኛ ሐዋርያዊ ትምህርት ኑፋቄ አድርጋ ነው የምትቀበለው፡፡ በዚህ ምትክ “ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም” የሚለውን አዲስ ትምህርት በሕዝቡ መካካል ዘርታለች፡፡ ይህ ነገር ስህተት ነው ቤተክርስቲያን እንዲህ አትልም፤ መጽሀፍቶችዋም እንዲህ አይሉም ያለውን የቤተክርስቲያን ልጅ ሁሉ መናፍቅ ተሃድሶ የነ እንቶኔ ተላላኪ በማለት እያሳደደችና አዲስ ገብ ትምህርትዋን እያጸናች ነው። ምነው ቢሉ ማቅ ሦስተኛ ሲኖዶስ ስለሆነች የማቅ ውሳኔ የሲኖዶስ ውሳኔ ተደርጎ መወሰድ አለበት ብላ ታምናለችና።
ምን ይህ ብቻ ይህን የእርሷን አዲስ ወንጌል ለማስፋፋት በምታደርገው ጥረት እውነተኛውን ወንጌል የሚሰብኩትን መምህራን “የምን ኢየሱስን ብቻ ሌሎችንም ስበኩ እንጂ” እያለች በማስፈራራትም በማሳደድም ክርስቶስን ስትቃወም የኖረች ናት፡፡ የለም እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን በሚለው የወንጌል አቋም የጸኑትን ኑፋቄ ተገኝቶባቸዋል በሚል እጅግ በርካቶችን ከቤተክርስቲያን እንዲባረሩ አድርጋለች፡፡
ማቅ ራሷን 3ተኛው ሲኖዶስ አድርጋ ስለምትመለከት የቤተክርስቲያንን ሥርዓት በራሷ ሥልጣን እስከማሻሻል የደረሰች ናት፡፡ ቤተክርስቲያናችን በቀኖና የወሰነቻቸው አጽዋማት ሰባት ናቸው፡፡ የጌታ ስደት የሚታሰብበት ወርሃ ጽጌ በልማድ የጽጌ ጾም እየተባለ የመጠራቱን ጫፍ ይዛ በልማድ የጽጌ ጾም ከተባለ አይቀር ብላ ልማድን በማጽናት ልማዷ 8ኛው ጾም መሆን አለበት ስትል ማወጃ የሚታወስ ነው፡፡ ተሳትሻል ስህተትሽን አርሚ ብትባልም ለአፏ አርማለሁ ካለች ወዲያ ሳታርመው እስካሁን አለች፡፡ አንዳንድ  የትምህርቷ ተከታዮችም ጽጌን ስምነተኛ ጾም አድርገው እየጾመጹት ይገኛሉ፡፡ እርሷ 3ተኛ ሲኖዶስ ናታ! የሲኖዶስ ውሳኔ እንዴት ይቀለበሳል? በዚህ ላይ የቀራትና ወርኃ ጽጌን ጾም አይደለም የሚያሰኝባት ቅዳሴው ከሮብና ከአርብ በቀር በጧት መቀደሱ ነውና እርሱንም እድሜ ከሰጣት ወደሰዓት ቅዳሴ ማስለወጧ አይቀርም፡፡ 3ኛዋ ሲኖዶስ ናታ
ማቅን 3ተኛው ሲኖዶስ ከሚያሰኟት መካከል ሌላው ነጥብ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች መካከል የመለመለቻቸውን ተከታዮቿን ራሳቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ብለው እንዲጠሩ ማድረጓ ነው፡፡ የማቅ አባልት አውቀውም ሆነ ሳያውቁ አንዳንዶችም በቅንነት ራሳቸውን እኔ ማኅበረ ቅዱሳን ነኝ ማለት ይቀናቸዋል፡፡ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ አያሌ ማኅበራት ቢኖሩም በእነዚያ ማኅበራት ውስጥ ያሉ ሁሉ ራሳቸውን የሚጠሩት እኔ የዚህ ማኅበር ተከታይ ነኝ ብለው አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሌላ ድብቅ ዓላማ የላቸውምና ነው፡፡ ማቅ ጋ ሲመጣ ግን እኔ ማህበረ ቅዱሳን ነኝ ማለት የግድ ነው፡፡ ማቅ ራሷን 3ኛው ሲኖዶስ አድርጋ ስለምትመለከት ነው ተከታዮቿን በገሃድ ራሳቸውን እኔ ማኅበረ ቅዳስን ነኝ እንዲሉ፣ በሌሎችም እነርሱ እኮ ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው እንዲባሉ ላለፉት 23 ያህል ዓመታት ስትሰራ የቆየችው፡፡
ይህ ብቻ አይደለም ማቅ 3ተኛ ሲኖዶስ የመሆን ህልሟን ለማሳከት የራሷን የአስኳላ ተማሪዎችና ተመራቂዎች የክብር ቀሳውስት ዲያቆናትና ባለማዕረጎች አድርጋ በሥልጣነ ክህነትና በማዕረግ ስም አጥለቅልቃለች፡፡  እድሜ ለእኒያ በነውራቸው ይዛቸው ለምታስፈራራቸው፣ እንዲሁም በቤተክርስቲያን ስም ከሰበሰበው ገንዘብ ላይ እርጥባን ለሚጥልላቸው ተላላኪ ጳጳሳቷ፡፡ ምን ይህ ብቻ 3ተኛ ሲኖዶስነቷን ለማጠናከር እንዲረዳት ከቆሎ ትምህርተ ቤት እስከ ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ድረስ የሠገሰገቻቸው ተማሪዎቿ ተረት ሲሰለቻቸውና እውነትን ሲለዩ ይለዩአታል እንጂ የነገ የሲኖዶስ አባላቷ እንዲሆኑ ያቀደቻቸው ናቸው፡፡
ራሷን ሶስተኛ ሲኖዶስ አድርጋ የምትመለከተውና ሁሉም አይቅርብኝ የምትለው ማቅ 3ተኛዋ ሲኖዶስ  አድርጋ ስለምትመለከት ጊዜዋ እስኪደርስ ራሷ ከሳሽና ዳኛ ሆና በተሰየመችበት ሲኖዶስ ላይ በአብዛኛው እውነተኛ ትምህርት ያስተማሩትን መናፍቅ ተሀድሶ አሰኝታ እንዲወገዙ አድርጋለች፡፡ እርሷ ያቀረበቻቸውንና ሲኖዶሱ ምንም አላገኘሁባቸውም ነጻ ናቸው ያላቸውን የቤተክርስቲያን መምህራንና ዘማርያን ግን 3ተኛ ሲኖዶስ ነኝ የምትለዋ ማቅ ባይሰምርላትም ሲኖዶስ ያላወገዘውን ሁሉ ውጉዝ እያለች ትገኛለች፡፡ የሲኖዶስ ግብር እንዲህ ባይሆንም ወግ ወጉን ይዛለችና ከዚህ በላይ 3ተኛ ሲኖዶስ ከየት ሊመጣ ነው?
ማቅ ራሷን 3ተኛዋ ሲኖዶስ አድርጋ ስለምታይ ማንም እንዲያርማት አትሻም፣ ራሷ 3ተኛዋ ሲኖዶስ ናታ! የፈጸመቻቸውን ስህተቶች እንድታርም የተሰጣትን መመሪያ እንድም ጊዜ አክብራና ታርማ አታውቅም፡፡ ራሷን እንደ ሦስተኛው ሲኖዶስ ስለምትቆጥር የሊቃውንት ጉባኤን ተግባር የሚያከናውን ስሙ የኤዲቶሪያል ቦርድ የተባለ አካል ሰይማ ትምህርቴ ሁሉ በእርሱ እየተመረመ ነው የሚወጣውና ልሳሳት አልችልም ባይ ናት፡፡ ከህትመት ውጤቶቿ እስከ ቴሌቪዥን ፕሮግራሟ ድረስ “በማኅበረ ቅዱሳን ኤዲቶሪያል ቦርድ የተፈቀደ” የሚል ሕጋዊ ማረጋገጫ ትሰጣለች፡፡ ታዲያ የእርሷን ኤዲቶሪያል ቦርድ ማን ሊያርመው? ቤተክርስቲያናችን ስምንት አጽዋማት ናቸው ያሏት ብትል ትክክል ናት፡፡ ምክንያቱም በሊቃውንት ጉባኤዋ የተፈቀደ ነዋ፡፡
እነዚህን እና እነዚህን የሚመስሉ ነገሮችን የምትፈጽመዋ ማቅ ሶስተኛ ሲኖዶስነትዋን በድርጊት ካወጀች አመታት ተቆጥረዋል። ምናልባት አሁን የሚቀረው በይፋ መግለጡ ይሆናል።
ከዲያቆን መሸሻ

14 comments:

 1. I wonder you plaintiff! Everything you through all your false accusations on mehabere kidusan didn't make any goal, and now you appear with another false accusations. Of course accusations is on of the behavior and character of devils. The devils are plaintiff the faith,religion and innocent people. Mehabere k idusan always teaches about Jesus and also the true decibels of Jesus. You are really one of the devils tool to accuse innocent organization. You are definitely plaintiff, and all plaintiffs will be failed.

  ReplyDelete
 2. አሜን አሜን አሜን ደስ ብሎናል።የቅድስት ቤተ ከርስትያናችን ህግና ሥርዓት መጠበቅ አለበት። ሦስተኛው የማቅ ስኖዶስ ከአሁኑ መገታት መገደብ አለበት። እዉነቱ ይህ ነው።
  የማቅ ክፉ ስራው አሁንም አላቆመም። ለምስክርነት እድሆነን በሐራ ድህረ ገጽ ላይ ለእዉነት ቆመው ስለ እውነት የተናገሩት አባቶች መጥፎ ስም በመስጠት ለጥፎዋል። ለመሆኑ የማቅ ድህረ ገጽ የስም ማጥፋት ዘመቻ በአባቶች ላይ እያደረገ ነው። ስማ ማጥፋት ክርስትያናው ህይወት ምግባር አደለም። ይህ የመሰለ ነው የማቅ ሥርዓት አፍራሽነት ቤተ ክርስቲያንን ለማደስ የምያደርገው የእለት ተእለት ተግባሩ ነው።
  ለመሆኑ እነዚህ እነዚህ ማቅን እንደ ሀይማኖት የምያመልኩት ሊቃነ ጳጳስት ማስትዋል ኖሮዋቸው እንድህ አይነቱ የማቅ ድብቅ አላማ ምን ያህል ቅድስት ቤተ ከርስትያነችንን እየጎዳት እንዳለ ማወቅ እደንደት ተሳናቸው? የማቅ ክምር ገንዘብ አይኖቻቸውን አሳዉሮ ከልዑል እግዚአብሔር ይልቅ ማቅ አምነው ወደ ዘላለማዊ ሞት መሄድ ምን ያህል ከባድ ነው።ለእግዚአብሔርና ለህዝበ ከርስትያኑ ሳይመቹ በአውደ ምህረት ላይ እንደት አደረገው አይኖቻቸውን በጨው አጥበው ይቆማሉ? ያሳዝና ያስለቅሳል ። ዛሬ በዚህ በዘመናች እንድህ አይነት አባቶች መታየታቸው ሞት ነው። ሰው እንደት አድረጎ ነው ከእግዚአብሔር ይልቅ ለማህበረ ገንዘብ ሟች የምሆነው። እውነት ነው ሀብት ስበዛ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ያስረሳል። ማቅ ሆይ በቅዱሳን ስም ህዝብን ማታለል አበቃ ሁሉ በአሁን ሰዓት በወንጌል ነቅቶዋል ሞኝ የለም። ወንጌል ወንጌል ወንጌል በአለም ላይ በግልጽ እየተሰበከ እነተነገረ እየተሳማ እየተነበበ እየተደመጠ ስለሆነ በሞኝነት መጓዝ ቀርቶዋል።
  ከሰላም ከሩ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቅብጥርጥርርርርር በምርቃና ነው ወይስ በልሳን የጻፍከው ቂቂቂ አይ ጥርሴ ሞኙ ይህስ ያሳዝናል እንጅ አያስቅም

   Delete
 3. አይ መሸሻ! መሸሻ ቢስ ነገር ነህ ይህን የመሰለ ዝቃጭ አሉባልታ በመፃፍ ጊዜ የምታጠፋው ምን ያህል ሥራ ፈት ብትሆን ነው እባክህ? ለነገሩ ይህን በመፃፍህ ቀጣሪዎችህ ይከፍሉሀል አይደል! እንዳንተ አሉባልታ ከሆነ የአንተ ቀጣሪዎች/ተሐድሶ መናፍቃን/ ደግሞ አራተኛ ሲኖዶስ ይባሉልህ?
  እስቲ ልብ ይስጥህ ሰው ለመሆን ፀልይ! ብራቦ ማቅ በርቺ ጠላቶችሽ ከውስጥም ከውጭም ሆነው ቢያዋክቡሽም የእግዚአብሔር ርዳታ እንዳልተለየሽ እያየን ነው

  ReplyDelete
 4. በሳቅ ሞትን! ተሃድሶ እያደር እየከረፋ እያቅለሸለሸ መጣ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የተቀደሰውን ለውሾች(ተሃድሶዎች) ከመስጠት ይጠብቀን፡፡ የቤተክርስቲያናችንን ሰላም አንድነት ያጽናልን፡፡ የተሃድሶውን የቦንኬ መንፈስ(አውሬውን) ከላያችን ያርቅልን፡፡ ልቦና ይስጠን ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 5. ከዲያቆን መሸሻ, Ene man bileh teyik.................sim yaleh neger gen bigbar yeleleh , mengedih yetefabih, be sidib yekosheshik, ye enat tut nekash, leba, esist.............maninetih yetefabih, medireshahin ena meneshahin yematawuk deha neh......................

  ReplyDelete
 6. tifatih sinegerh atarmima, tiferaleha..............post endayidereg tichit tiferaleha........

  ReplyDelete
 7. መኅበሩ መጀመሪያም አባላትን ሲመዘግብ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ አባልነትን የመጀመሪያ መስፈርት አድርጎ ነው፤.... በራሴ ፈቃድ ለአገልግሎት የምከፍለው ምጽዋትና መዋጮ ለምን ያንገበግባችኋል......
  ...........ጾም......ስንጾምስ ለምን ይደብራች ኋል.... አምላክ ጽናቱን በሰጠንና አብዝተን በጾምን ምንኛ ደስ ባለን.....በመሰረቱ ጾምን መቃወም ኦርቶዶክሳዊነትን መቃወም ነው! እዚህ የሰው ቤት ከመበጥበጥ የማይጾሙ ሰዎች የተሰበሰቡበት አዳራሽ መሄድና አለመጾም ትችላለህ! ”“ዲያቆን”“ መሸሻ በበጎች መሀል የተወተፍክ ተኩላ እንደሆንክ እንኳን ሙሉ ጽሑፍሕ ፊደላትህም ያሳብቁብሃል.... ተሃድሶም ነህ.....ከዚያ ፕሮቴስታንት ትሆናለህ.......

  ReplyDelete
 8. አማርኛ መፃፍ የሚችል የቤ/ክርስቲያን ልጅ ማ/ቅዱሳን ብሎ ይፅፋል ልበ ሙሉና የማኅበሩን አገልግሎት የሚያውቅ ደግሞ በልበ ሙሉነት ማኅበረ ቅዱሳን ብሎ ይፅፋል! ለነገሩ መጽሐፉ ፡- ከፍሬያቸው ታውቋእዋላችሁ ስለሚል እናንተም በክህደት ትምህርታችሁ በርቱ ነገር ግን ታላቁን አባት አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃንን ለቀቅ አርጉና ታላቁ ዴማስ ብሎግ ብትሉት ስራችሁን የተሳካ ያደርግላችኋልና አስተያየቴን ታናሽነቴን ገልጬ ፃፍኩላችሁ፡፡ አማርኛ መፃፍ የሚችል የቤ/ክርስቲያን ልጅ ማ/ቅዱሳን ብሎ ይፅፋል ልበ ሙሉና የማኅበሩን አገልግሎት የሚያውቅ ደግሞ በልበ ሙሉነት ማኅበረ ቅዱሳን ብሎ ይፅፋል! ለነገሩ መጽሐፉ ፡- ከፍሬያቸው ታውቋእዋላችሁ ስለሚል እናንተም በክህደት ትምህርታችሁ በርቱ ነገር ግን ታላቁን አባት አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃንን ለቀቅ አርጉና ታላቁ ዴማስ ብሎግ ብትሉት ስራችሁን የተሳካ ያደርግላችኋልና አስተያየቴን ታናሽነቴን ገልጬ ፃፍኩላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 9. Doma Yibezal malet new ende endet new asrate yikebelale malet please you are mistaken

  ReplyDelete
 10. In revelation 4, it states

  In the center and around the throne, there were four living creatures covered with eyes in front and in back. 7 The first creature resembled a lion, the second was like a calf, the third had a face like that of a human being, and the fourth looked like an eagle in flight. 8 The four living creatures, each of them with six wings, were covered with eyes inside and out. Day and night they do not stop exclaiming: “Holy, holy, holy is the Lord God almighty, who was, and who is, and who is to come.”
  CAN SOMEONE TELLS ME WHY THE MAHBERE KIDUSAN SYMBOL HAS THOSE 4 LIVING CREATURES CRRYING THE SYMBOL. THERE MUST BE GOOD REASON

  ReplyDelete
 11. Mk ..mahber tesadabiwoch.. mahbere yewengel
  telatoch..mahbere Erikusan mahbere asadaajjoch...yemilwo seyame hulu lezihech woshetam mahber yemsgana new.egziabher aferso yesrachu.

  ReplyDelete
 12. ለመሆኑ ማቅን የማይደገፍ ሁሉ ተሐድሶ ተብሎ በአባለቱ ዛሬ እየገነገረ ነው። ማቅ እኮ ነው ቤተ ከርስትያን ለማደስ እየታገለ ነው። ሥርዓተ ቤተ ክርስትያን ሳይጠብቅ ተቆርቋር መስሎ በገንዘቡ በስፋት ይነግዳል። ለብቻው አስራት እየተቀበለ የራሱ ድብቅ ጳጳሳት ያለው ህግን በራሱ ግዜ አያወጣ የኦርቶዶክስ ቤተ ከርስትያናችንን ህግ ወደ ታች ረግጦ የራሱን በአደባባይ እየበተ ይገኛል።የእርሱ አድሱ መዋቅር በየደብሩ 20 ካህናት ብቻ ለማድረግ ምክንያቱም የራሱ የሆኑትን ድበቅ ካህናት ብቻ ለመሰግሰግ ሞክሮ ነበር ነገር ግን በእውነተኞች የቅድስት ቤተ ከርስትያናችን አባቶችና ልጆች በልዑል እግዚአብሔር ድል ተመቶዋል። አሁንም ድል ብደረግም ማቅ አላቀላፋም ግዜና ቦታ እየጠበቀ ነው። ተሐድስ እያሉ ለላውን ህብዝ ለማደናገር መሞከር ባዶነት ነው። ህዝባችን ነቅተወቀል ከእንዳንድ የነዋይ ረሀብተኞች አባቶች በስተቀር። ለዚህም ነው የእምነታችን ተከታዮች አባለት እለት ተዕለት ቁጥር እየቀነሰ የሚሄደው። እግዚአብሄር አምላክ ዝም አይልም ..........ስለ ክብሩ እርሱ ይዋጋል። የማቅ እድሜው እራሱን በራሱ ያሳጠረበት ወቅት ስለሆነ .......ሁሉን ግዜው ይፈተዋል።

  ReplyDelete
 13. OMG- i am not member of MK but your thoughts are totally False

  ReplyDelete