Thursday, November 13, 2014

ቤተ ሙስና የሆነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአቡነ ቀሌምንጦስ ይለወጥ ይሆን? ወይስ…

Read in PDF

በአገራችን ተወዳዳሪ ያልተገኘለትና ጠያቂም ተጠያቂም የሌለበት ቤተ ሙስና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በዚያ፣ ለቤተክርስቲያን እድገት ሳይሆን በቤተክህነት ትምህርት ብዙ ደክመው ሥራ ፍለጋ ደጅ ከሚጠኑና በልዩ ልዩ ምክንያት (ደኅና አድርገው ለመብላትም ጭምር ሊሆን ይችላል ምክንያቱ) ወደተሻለ ደብር መዛወር ከሚፈልጉ ሥራ ፈላጊዎች ወንድሞቻቸው ላይ ጉቦ በመቀበል ለመበልጸግ ተግተው የሚሠሩ ጥቂት ስግብግብ ሹማምንት አሉ፡፡ 
ሥራ ፍለጋ ደጅ በመጥናት ላይ ያሉና በር ከፍቶ የሚያስገባቸው እንኳን ስላላገኙ በሀገረ ስብከቱ በር ላይ በሥራ ቀናት የሚኮለኮሉ፣ በቤተክህነት ትምህርት ብዙ ደክመው ቤተክህነቱ ያልተቀበላቸው ተምረው እንዳልተማሩ የሆኑ ሊቃውንት ጊዜ በሰጣቸው ጨዋዎች እየተጉላሉ በዚያ አሉ፡፡ በችሎታቸው ሳይሆን በጉቦ ጥሩ ገቢ ባለበት ደብር ውስጥ ዳጎስ ያለውን ገቢ በሚያስገባ ጥሩ የሥራ መደብ ለመመደብ በበሩ ሳይሆን በጓሮ በር የሚገቡ ወደፊት ለመዝረፍ ዛሬ ጉቦ የሚሰጡ ከንቱዎችም በዚያ አሉ፡፡ ደግሞም እንደ ሎጥ በዐመፀኞች መካከል ጻድቅ ነፍሳቸውን አስጨንቀው የሚኖሩ እንደ ሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ እንደ ቀሲስ ኃይሉ ያሉ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረባቸው ጥቂት ታማኞችም በዚያ አሉ፡፡

እነሆ በየጊዜው የሲኖዶስ ስብሰባ በመጣ ቁጥር ታዲያ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ላይ የይነሣልን ጩኸት  ይበረታል፣ ትርምስም ይፈጠራል፣ ሥራ አስኪያጁም ላለመነሣት የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል፣ እርሱ ብቻ ሳይሆን በሙስናው ሰንሰለት ውስጥ ያሉት ሁሉ ቀምሶ የሚያቀምሳቸው፣ በልቶ የሚያበላቸው ሥራ አስኪያጅ እንዳይነሳባቸው የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ ሥራ አስኪያጁ ይህን የሚያደርገው ምናልባት ጉቦ በልቶባቸው ያልፈጸማቸው ዝውውሮችና ምደባዎች ስላሉ ይሆናል፡፡ ደግሞስ የምልጃ (ጉቦ) እንጀራ አይጠገብ አይደል! ሥራ አስኪያጁም ሆነ ሌላው ባለሥልጣን ደመወዙን ካስረሳውና በሙስናና በዝርፊያ ሀብት ከሚያካብትበት የገቢ ምንጩ ላይ ሲነቀል እንዴት ዝም ይላል? እኛም የቤተክርስቲያናችን በሙስና መንቀዝ፣ ጥቂቶች በመማለጃ (በጉቦ) ገንዘብ ይከብሩ ዘንድ የብዙኃኑ አገልጋዮቿ መንገላታትና ሰሚ ማጣት ይቆጨናልና ዝም ማለት አንችልም፡፡ 
ነቢዩ ኢሳይያስ “ወኢያረምም በእንተ ጽዮን ወኢየኀድግ በእንተ ኢየሩሳሌም እስከ ትወፅእ ጽድቅየ ከመ ብርሃን፣ እስመ ትወፅእ ጽድቅየ ወተኀቱ መድኀኒትየ ከመ ማኅቶት” ትርጉም፦ “ስለ ጽዮን ዝም አልልም፥ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፥ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።” (ኢሳ. ፷፪፥፩) እንዳለና ለሀገረ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም እንደተቆረቆረ እኛም በአንዳንድ ኅሊና ቢስ ግለሰቦች እየደረሰ ያለው ብዙ ጥፋት ውድቀቷን እያፋጠነው ነውና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ዝም ማለት አንችልም፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ታሪክ እንዳስተዋልነው የሚሾመው ሥራ አስኪያጅ ሁሉ የቤተክርስቲያንን ገንዘብ ሙልጭ አድርጎ ይበላና በጩኸት ብዛት ተነሥቶ ተጠያቂ ሳይሆን ወደሌላ ክፍል ይዛወራል፡፡ ሌላው ተረኛ ደግሞ ተመሳሳይ ተግባር ፈጽሞ ዘወር ይል ዘንድ ይሾማል፡፡ ነገሩ ሁሉ “ጉልቻ ቢለዋወጥ ..” ሆኗል፡፡ ይህ ክፉ ልማድ የሚቀጥለው እስከ መቼ እንደሆነ ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡

በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ቀሲስ በላይ መኰንን ከመቼውም ጊዜ የከፋ ሙስና እየፈጸሙ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ ተገልጿል፡፡ እኚህ ሰው በመማለጃ ወይም በጉቦ የተፈጸመ ሕገወጥ ዝውውር በማካሄዳቸው አለአግባብ ከቦታቸው የተነሡ፣ ዝቅተኛ ገቢ ወዳላቸው የተዛወሩና አየር ላይ የተንሳፈፉ ሰዎችን ለእንግልት ሲዳርጉና ሲያስለቅሱ፣ መማለጃ ሰጥተው በዚያ ቦታ የገቡትን ደግሞ በገንዘብ ረገድ ተጠቃሚ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በዚህ መንገድ የሚገኝ ገንዘብ የአመፅ ትርፍና ትልቅ ጉዳት መሆኑ ሳይዘነጋ ማለት ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ መሾማቸውን ተከትሎ ምን የሚስተካከል ነገር ይኖር ይሆን? የሚለው ጥያቄ በሙስና ሰንሰለቱ ውስጥ ለሚገኙት ሙሰኞች ለጊዜውም ቢሆን ሥጋት መሆኑን ጨምሮ የሁሉም ሰው ጥያቄ ሆኗል፡፡ ይሁንና ቀሲስ በላይ ገና ለገና ልነሣ እችላለሁ በሚል ስጋትና አቡነ ቀሌምንጦስ መሾማቸውን ተከትሎ የተለያዩ ወሬዎችን እያስወሩ መሆናቸው ቤተክህነት አካባቢ ይሰማል፡፡ ሰውዬው የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል መሆናቸውን መከታ በማድረግ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ስም እየጠሩ ማንም አይነካኝም በሚልና በተለይ የአቶ ኩማ ድሪባንና የአቶ አባዱላ ገመዳን ሥልጣን ሽፋን በማድረግ ከቦታዬ መነሣት የለብኝም የሚል አቋም የያዙ ይመስላል፡፡ እንዲህ እያስወሩ ያለው ዝውውር በመፈጸምና ነቅሎ በመትከል ስም በያዙት ሙስናዊ መንገድ መማለጃ የበሉባቸው የሥራ መደቦች ስላሉ ቢያንስ እንኳን ያንን ሳያስፈጽሙ እንዳይወርዱ ነው ተብሎ በብዙ ተገምቷል፡፡ ጉቦ ሰጥተው ዝውውሩን ወይም ሕገ ወጥ ምደባውን የሚጠባበቁ አንዳንድ ሰዎች እንዳሉ ከራሳቸው አንደበት ተሰምቷልና፡፡
ቀሲስ በላይ መኰንን የሙስናውን ሥራ የሚሠሩት በውስጥና በውጭ ጉቦ አቀባባዮችና ተቀራማቾች በኩል እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ በውጪ በኩል ካሉት መማለጃ አቀባባዮች መካከል አንዱ የደብረ ከዋክብት ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሰባኪ የሆነው ያሬድ ሲሆን ከውስጥ አቀባባዮችና ተጋሪዎች ደግሞ በሀገረ ስብከቱ ሕግ ክፍል ኃላፊ የሆነው ታዴዎስና ምክትል አስተዳደር የሆነው ጌታሁን ናቸው፡፡ ቀሲስ በላይ በሙስና መጨማለቅ ብቻ ሳይሆን ዘመዶቻቸውን በሕገወጥ መንገድ ሥራ በመስጠትና ሕገወጥ አሰራር እንዲሰፍን በማድረግም ድርብርብ ሙስና በመፈጸም ይታወቃሉ፡፡ እኚህ የሕግ ምሩቅና የምክር ቤት አባል የሆኑ ሰው ከተማሩት የሕግ ትምህርትና የሕዝብ ተወካይ ከመሆናቸው አንጻር ሕጋዊ አሰራርን ከማስፈን ይልቅ ሕገወጥነትን ማስፋፋታቸው ተምረው እንዳልተማሩ፣ የሕዝብ ተወካይ ሆነው እንዳልሆኑ እንዲቆጠሩ አድርጓቸዋል፡፡ እንደእርሳቸው ዘመናዊ የሕግ ትምህርት ሳይኖራቸው ከቤተክርስቲያን በተማሩትና ባካበቱት ዕውቀትና ልምድ ቤተ ሙስና በሆነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ሕግን በማስፈን ትልቅ ሥራ በሠሩትና ከፍጻሜ እንዳያደርሱት ግን በአቡነ ጳውሎስ ዘንድ ነገር ተሠርቶባቸው ከሥራ አስኪያጅነታቸው እንዲነሡ በተደረጉት በንቡረ እድ ገብረ ማርያም አማካይነት የተሠራው ሥራ ግን እስካሁን ድረስ በታላቅ ምሳሌነቱና የሙስናውን ምንጭ ማድረቅ እንደሚቻል ትልቅ ተስፋ በመፈንጠቁ ይጠቀሳል፡፡
ቀሲስ በላይ በሥራ አስኪያጅነታቸው በመማለጃ ከመሥራት አንሥቶ የስጋ ዘመዶቻቸውን እስከመጥቀም የደረሰ ልዩ ልዩ ሙስናዊ ተግባራትን በመፈጸም ወደር አልተገኘላቸውም ስንል ከሜዳ ተነሥተን አይደለም ማስረጃዎች አሉን፡፡ ለምሳሌ ያህል አውጉስታ ማርያም ላይ ቀሲስ በላይ አዛውረው ያመጧቸውና አስተዳዳሪ ያደረጓቸው የሥጋ ዘመዳቸው መጋቤ ሰላም ዓለማየሁ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ አላስበላ ሲላቸውና ሙዳየ ምጽዋት በትክክል ይቆጠርና ገቢ ይደረግ በማለቱ አፍርሰውት በአሁኑ ጊዜ ደብሩን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ያለሰበካ ጉባኤና ያለተቆጣጣሪ እየተመዘበረ የሚገኝ ብቸኛ ደብር እንዲሆንና እንዲባል አድርገውታል፡፡ ልብ እንበል፣ አስተዳዳሪው በሕዝብ የተመረጠውንና ሕዝብ የጣለበትን ኃላፊነት ተረድቶ ልሥራ ያለውን ሰበካ ጉባኤ ነው በማን አለብኝነትና ከበላይ ባለሥልጣናት ጋር በመመሳጠር አፍርሰው ያለተቆጣጣሪ የቤተክርስቲያኒቱን ገቢና እየተሠራ ላለው ሕንጻ ማሠሪያ የሚገባውን ገንዘብ በከፍተኛ መጠን እየመዘበሩና እንደስማቸው “ዓለማቸውን እየቀጩ” የሚገኙት፡፡ ግለሰቡ የሚቃወሟቸውንና በሕጋዊ መንገድ ይሠራ የሚሉትን ሠራተኞች ከቀሲስ በላይ ጋር በመመሳጠር እንዲታገዱና እንዲንሳፈፉ በማድረግ የጠበባቸው የሚመስለውን የሙስናውን ሜዳ እያስፉት ነው፡፡ የቀሲስ በላይ አስተዳደር ግን ይህን እያየና እየሰማ ዝምታን መርጧል፡፡ ምክንያቱም የሙስናው ሰንሰለት አናት ላይ ያለውና ዋናው የጥቅሙ ተጋሪ ነውና፡፡ እነዚህ ሙሰኞች መቼ ይሆን ታዲያ ለፍርድ የሚቀርቡት?
ቀሲስ በላይ ሥራ አስኪያጅ ከሆኑ ጀምሮ ሕጋዊው አሰራር በሕገወጥ አሰራር ተተክቷል፡፡ ቀድሞ በንቡረ እድ ገብረ ማርያም ሥራ አስኪያጅነት ጊዜ መሥመር የያዘው አንዱ ጉዳይ ሠራተኞች ማስታወቂያ ወጥቶና ተወዳድረው እንዲቀጠሩ የወጣው ሕግ በቀሲስ በላይ ጊዜ ተጥሷል፡፡ ስለዚህ በእርሳቸው ዘመን መማለጃ ሰጥቶ እንጂ በዕውቀቱ ተወዳድሮ የተቀጠረ አንድም ሰራተኛ የለም፡፡ እውን ከአንድ የሕግ ምሩቅ ካህን ይህ ይጠበቃልን?
ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ማኅበሩ ከዚህ ቀደም ቀሲስ በላይ ወደ ሰዋስወ ብርሃን ተዛውረው በሄዱ ጊዜ በሐራ ብሎጉ ላይ ተሐድሶ መናፍቅ ብሎ ስማቸውን በተሐድሶነት ለመፈረጅ የቀደመው አልነበረም፡፡ ዛሬ ግን እንዲህ ያለውን ሙስና እየፈጸሙ እያየና እየሰማ እንዳላየና እንዳልሰማ ሆኖ በዝምታ ማለፍን ነው የመረጠው፡፡ ይህም የሚያሳየው በቀሲስ በላይና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ያልተጠበቀና ድንገተኛ የሆነ ሰላም መስፈኑን ነው፡፡ ከእርሳቸው ይልቅ ማቅ በአሁኑ ጊዜ ሙስና ነክ ቀረርቶውን እያሰማ ያለው፣ ክፉ ሥራውን እየገለጡ ባሉት አንዳንድ የደብር አለቆች ላይ ነው፡፡ ማቅ የደብር አለቆቹን ሙሰኞች እያለ ስማቸውን በማጥፋት ሥራ የተጠመደው ሙስና አስጨንቆት ሳይሆን አለቆቹ እንደነበር ጅራት ስለያዙት ነው፡፡ ሙስና ቢያሳስበው ኖሮማ የእነርሱ አለቃ ቀሲስ በላይ ላይ አንድ ነገር ማለት በቻለ ነበር፡፡ እየተፈጸመ ያለውን ሙስና እያየ ምንም ትንፍሽ አለማለቱ ማኅበሩ ለግል ጥቅሙ እንጂ ለቤተክርስቲያን ጥቅምና እድገት እንዳልቆመ፣ የግለሰቦችን ስም የሚያጠፋውም የግል ጥቅሙን ሲነኩበት እንጂ የቤተክርስቲያን ጥቅምና ህልውና ስለተነካ እንዳልሆነ ያሳያል፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን መንደር ቤተክርስቲያን ውስጥ ሙስና መፈጸም ወንጀል መሆን የሚጀምረው አንዳንድ ሙሰኞች በቀጥታ ሙስናን ስለ ፈጸሙ ሳይሆን ሙስናን ፈጽመው የማኅበረ ቅዱሳን ተጻራሪ ሆነው ሲቆሙ እንደሆነ እየታየ ነው፡፡ ሙስናን እንዳሻቸው ፈጽመው እንደ ቀሲስ በላይ ወደውት ሳይሆን ሸንግለውት በምስጢር ከጉያው የተሸጎጡን ሙሰኞች ግን ማቅ ሊሸፍናቸው ይሞክራል፤ ወይም አያጋልጣቸውም፡፡ ይህም የሚያሳየው ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ ከሙስና ያልጸዳ ማኅበር መሆኑን ነው፡፡ ሙሰኞች ሙስና ፈጽመው ከማቅ ጋር ከአንገት በላይ ፍቅር ስለሆኑ ብቻ እንዴት ዝም ይላል? ማቅ እንደ ማኅበር እንዲህ ቢያስብ እንኳን ይህን የሚቃወሙና ለቤተክርስቲያን በትክክል የሚቆረቆሩ የአመራር አበላትም ሆኑ ተራ አባላት እንዴት ይጠፋሉ?
ቤተ ሙስና የሆነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በርካታ ሙሰኞች ተከብረው የሚኖሩበት ቤት የመሆኑን ያህል  እንደ ዋና ጸሐፊው እንደ ቀሲስ ኃይሉ ያሉ እውነተኛና ታማኝ የሆኑ አንዳንድ አገልጋዮችም ያሉበት ቤት መሆኑ ይገርማል፡፡ ቀሲስ ኃይሉ ከቤተክርስቲያን ትምህርት ባሻገር የ2 ዲግሪ ባለቤት ሲሆኑ፣ ወደእርሳቸው የተመራውን ፋይል ሕጋዊና ትክክለኛ እስከሆነ ድረስ ይዋል ይደር ሳይሉ ወዲያው የሚፈጽሙ ሐቀኛ ጸሓፊ መሆናቸው በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ይታወቃል፡፡ ሐቀኛነታቸው እዚህ የጀመረ ሳይሆን የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል ጸሐፊም በነበሩ ጊዜ የሚታይና ፐርሰንት በአግባቡ በመክፈልና በታማኝነት በመሥራት የተመሰከረላቸው አገልጋይ ናቸው፡፡ ቀድሞም ሆነ አሁን በሙሰኞችና በአመፀኞች መካከል ሲኖሩ እንደሎጥ ነፍሳቸውን እያስጨነቁ የሚኖሩ መሆናቸው በብዙዎች ዘንድ ይታወቃል፡፡ በበጎ ሥራቸው ክፉ ሥራቸውን እየገለጡባቸው መሆኑ የተሰማቸው ሙሰኞች ግን እኛን ካልመሰሉ በሚል “እንደሞኝ” ነው የሚያዩአቸው፣ እርሳቸው ግን ፈጣሪያቸውን የሚፈሩ፣ ቤተክርስቲያንን በቅንነት የሚያገለግሉና ለኅሊናቸው ተገዝተው የሚኖሩ ታላቅ ሰው ናቸው፡፡ እንደ እርሳቸው ያሉትን ሰዎች ወደበለጠው ሥልጣን ማምጣት ቢቻል በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ትልቅ ለውጥ መምጣት በተቻለ ነበር፡፡ ነገር ግን ቤቱ ያለ ሕገሙስና የማይንቀሳቀስ ስለሆነ ታማኝና ሕጋዊ ሰው አይፈለግም፡፡ ከዚህ ቀደም እንደ ታየውም እንደ ንቡረእድ ገብረ ማርያም ነገር ይሠራበትና የጀመረው መልካም ሥራና ያስመዘገበው አመርቂ ውጤት ሥር ሳይሰድ በሙሰኞች አመፅና ሴራ በአጭሩ እንዲቀጭና እንዲጨናገፍ ይሆናል፡፡
አሁን እየተጠበቀ ያለው ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ቀሲስ በላይንና በእርሳቸው የተዘረጋውን የሙስና ሰንሰለት ምን ያደርጉት ይሆን? ይበጣጥሱታል ወይስ … የሚለው ነው፡፡ ቀሲስ በላይን ከቦታቸው ማንሳትና በሌላ መተካት አንድ ነገር ቢሆንም ብቻውን ግን መፍትሔ አያመጣም፡፡ ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም እንደሚባለው ነው የሚሆነው፡፡ መፍትሔው ሙስናዊ ሰንሰለቱን መበጣጠስና የሚከፈለውን መሥዋዕትነት በመክፈል ሕጋዊ አሰራርን ማስፈን ነው፡፡ ንቡረ እድ ገብረ ማርያም የጀመሩትን ሁሉን ወደ ሕግ መሥመር የማስገባት ሥራ ወደ ቦታው መመለስ ዋናውና የመጀመሪያው መፍትሔ ነው፡፡ ለዚህም ምናልባት ንቡረ እድ ገብረ ማርያምን ወደሥራ አስኪያጅነታቸው መልሶ የጀመሩትን ሥራ እንዲቀጥሉ ማስቻል አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በሙስናዊው መሥመር ውስጥ የሚገኙ ከጸሐፊ እስከ አለቃ፣ ሥራ አስኪያጅ ለመሆን ከሚቋምጡ ዘመዶቻቸውን ወደፈለጉበት ደብር ልከው ማስቀጠር እስከለመዱት አንዳንድ ጳጳሳት ድረስ ይህ እንዲሆን ፈጽሞ እንደማይፈለግ ግን ይታወቃል፡፡
ሌላው መደረግ ያለበት ለሙስና በር የከፈቱና ሙስና እየተሠራባቸው ያሉ አሠራሮችን ለሙስና ዕድል በማይሰጡ ሕጋዊ አሰራሮች መለወጥ ነው፡፡ ለምሳሌ የሙዳየ ምጽዋት ቆጠራን፣ የሠራተኛ ቅጥርን፣ እድገትንና ዝውውርን ሕጋዊ አሰራር እንዲከተል ማድረግ፣ ሥልጣንን ከግለሰቦች እጅ አውጥቶ በኮሚቴና ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መንገድ እንዲሠራ ማድረግ፣ ኮሚቴውም የሚገመገምበትንና የሚጠየቅበትን ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ቤቱ ሙስናን የለመደ ከመሆኑ አንጻር በሙስናው ሊዘፈቅ ይችላልና በኮሚቴው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ካለ የሚቀርብበትንና አፋጣኝ መፍትሔ የሚሰጥበትን ሁኔታ ማመቻቸትና መፍጠር ይገባል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን በሙስና ስማቸው እየተነሣ ያሉ ባለሥልጣናት እንደ ከዚህ ቀደሙ የድርሻቸውን ይዘው ያለ ተጠያቂነት ወደጠቅላይ ቤተክህነት አንዱ ክፍል ከማዛወር ይልቅ በሕግ የሚጠየቁበት ሥርዓት መዘርጋት አለበት፡፡ አሊያ ጠቅላይ ቤተክህነቱ የሙሰኞች ዋሻ ሆኖ መቅረቱ ነው፡፡
ሙስና እንዳይፈጸም ማስተማርና ምሳሌ መሆን የሚገባት ቤተክርስቲያን በሙስና ተነክራና ተዘፍቃ ትገኛለች፡፡ ይህም በዓለም ላሉት ሰዎች እጅግ መጥፎ የሆነ ምሳሌ ነው፡፡ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሓስ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በፈጸሙት ርኩሰት ምክንያት ክብር ከእስራኤል እንደለቀቀና ኢየሩሳሌም ለጥፋት፣ ሕዝቡ ለሽንፈት፣ የእግዚአብሔር ታቦት ለምርኮ፣ አፍኒንና ፊንሓስ ለሞት፣ ልጆቹን እንደሚገባ ያልገሰጻቸው ኤሊም በድንጋጤ ለድንገተኛ ሞት እንደተዳረገ ሁሉ ዛሬም ካህናት እየፈጸሙት ባለው ዝርፊያ፣ ቅሚያ፣ ሙስና፣ ፍትሕን ማጓደል ዐመፅና ሌሎችም በደሎችና ኃጢአቶች ምክንያት የእግዚአብሔር ጽዋ ሲሞላ በልዩ ልዩ መልክ የሚገለጥ ጥፋትና የክብር መልቀቅ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እንደሚመጣ ለመናገር ነቢይ መሆን አያስፈልግም፡፡ እርግጥ ዛሬ ካለችው ቤተ ክርስቲያናችን የእግዚአብሔር ክብር ከለቀቀ ሰነባብቷል፡፡ የቤተክርስቲያናችንና የአገልጋዮቿ ተሰሚነት እየቀነሰ መጥቷል፡፡ እጅግ በርካታ ተከታዮቿ ወደሌሎች እየፈለሱ ነው፡፡ በካህናቱ ወገን ሙስናውና ግፉ በርትቷል፡፡ ቢጮሁ ሰሚ የለም፡፡ እውነተኞች የሚገፉባት ሐሰተኞች ክብር የሚያገኙባት ቤት ሆናለች፡፡
ይህን ሁሉ ነገር ጠላት ዲያብሎስ ያመጣብን ፈተና ነው በማለት ራሳችንን ከመሸንገል ይልቅ በጥፋታችንና በበደላችን ይልቁንም በካህናቶቻችን በደል የደረሰብንና የእግዚአብሔር ክብር መልቀቅ (ኢካቦድ የመሆኑ) መገለጫ መሆኑን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ንስሐ ሊገባና ራሱን ሊያስተካክል ይገባል፡፡ መጽሐፍ እንደሚል “ዘይሰርቅኒ ኢይስርቅ እንከ ለይትገበር ወይፃሙ እንከ በእደዊሁ ለሠናይ በዘይረድኦ ለነዳይ” ትርጉም “የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።” (ኤፌ. 4፥28)፡፡ በግፍና በዐመፅ ሥራ የተጨማለቀም “ወደሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያነጽሐነ እምኩሉ ኃጣውኢነ” ትርጉም “የልጁም የኢየሱስ ክርስቶሰ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” እንደተባለው (፩ዮሐ. ፩፥፯) በመንጽሒ ደሙ እጁን ሊያጥብና ሊያነጻ ይገባል፡፡ የጨው ገደል ሲናድ ሞኝ ይስቃል ብልኅ ግን ያለቅሳል እንደሚባለውም ዛሬ እየሆነ ያለው ነገር ካልታየንና በንስሐ በማልቀስ መፍትሔ ካላፈላለግን  የቤተክርስቲያኗን ውድቀት እያፋጠንነው ነው፡፡ ስለዚህ ብልሆች  እንጂ ሞኞች አንሁን፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን    

9 comments:

 1. hello abaselamawoch...yene comment enkua tabote tsion ke axum teserekech minamn..yemil yeminafes were ale..tsafulin..I know tabote tsion alech /neberech bbbbbbbbbiye/ alamnm...but alemenoruan lememesker lela zede jemirew kehone neberech gin t eserekech bilew were tejemiro yihon? lenegeru eko bitinors serken new alu yametanat yelechm enji bitinor lebinet adele...?

  ReplyDelete
 2. በመጀመሪያ ይህን ሥነ ጽሑፍ አቅራቢ እናመሰግናለን።እናም የሚሠራው ግፍ እጅግ ዘግናኝ በመሆኑ እናዝናለን። አንድ ጊዜ ጳጳሳት በሌላ ጊዜ ማኅበሩ እየተባለ መፍትኄ ሊመጣ አይችልም፤ ሁሉም ልብ ያልገዙ በጥቅም ገበያ የሚናውዙ በሆናቸው (ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ)ነውና ቀና ብለው ሊመለከቱ አይችሉም
  ስለሆነም ከላይ ዕርማት መስጠት ከሥር መንግሎ መጣል ወደሚቻለው ፈጣሪ ማመልከት ይበጃል።
  ማመልከቻውም እንደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሳይሆን ባጭሩ (አቤቱ ፈጣሪ ከባዱን ሸክም አስወግድልን)ነው
  ፍጡር ከማመለክ ፈጣሪን ማምለክና ፈጣን ምላሽ መቀበል ይሻላል።

  ReplyDelete
 3. ዛሬም ክፋት ክሥ ውንጀላ ተንኮል ሀጢያት
  እውነት ሐሰት ሐሰትንም እውነት ጥቁሩንም ነጭ ለማለትና ለማድረግ ሀፍረትና ይሉኝታ የሌላችሁ ባዶ ጋኖች ናችሁ። ለምን ሥለራሳችሁና ስለቀጣሪዎቻችሁ ስለ ኘሮቲያንቲዝም ለምን አትፅፉም አታወሩም። በወንድሞች መካከል ጥል ወይም ጠብን የሚዘራ በጥብቅ የተጠላ ነውና እናንተም ክፉዎች ሆናችሁ የክፋት ማሥፈፀሚያ መሳሪያዎች ናችሁና በተዋህዶ ወንድሞች መካከል ጠብን ለመዝራት ትሯሯጣላችሁ። ነገር ግን እግዚአብሔር አለና ከእውነት ጋር ነውና እውነተኞች በእግዚአብሔር ቸርነት በመንፈስ ቅዱስ ፀጋና ሐይል ድል እያደረጉ የእናንተን ክፉ ተግባር እያጋለጡ ተዋህዶ የክርሥቶሥ መሆኗን በትጋት በፅናት ያውጃሉ። እናንተ ግን ዛሬም ክሥን ክፋትን ጠብን ሀሠበንና አመፃንና ታውጃላችሁ። የኦርቶዶክሥ አባቶችና ልጆቿ ሥለራሣቸው ሥለቤተክርሥቲያናቸው ስለወገኖቻቸውና ሥለሀገራቸው ይፀልያሉ። የቤተክርስቲያን አገልጋዬችን መንፈሳዊ አገልግሎትን የሚመዝነው እግዚአብሔር ሲሆን ከሱ በታች በአገልግሎት የሚመስሏቸው እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች ናቸው። እናንተ የምትመዝኑበተ የእውቀት መለኪያ በመንፈስቅዱሥ ሲታነፅ እንጂ ብቻውን አለማዊው እውቀት ለህይወት አያበቃም። በአባቶቻችን የትምህርት ደረጃቸውም ሆነ ብቃታቸው ኦርቶዶክሳዊያን የምንኮራበትና የምንኮራባቸው ሲሆን ለእደናንተ አይነቶች ክፉዎችና መሠሪዎች ግን ከባዶነታችሁ የተነሣ የልዮነትና የጥላቻ መፍጠሪያነት ለመጠቀም ትሞክራላችሁ። ነገር ግን ኦርቶዶክሣዊያን አገልጊዮች ከአለማዊው ዕውቀትና ማህረግ ይልቅ የመንፈስ ቅዱስን ፀጋና ጥበብ ያሥቀድማሉና የእናንተን መሠሪ ተግዳሮት ቦታም አይሠጡትም። በእግዚአብሔር ዘንድ የአገልጋዮች ልዩነት የለም ምክንያቱም በመፅሐፍ በእናንተ መካከል የበላይ የለም፡የእናንተ የበላይ ለመሆን የሚፈልግ ቢኖር የእናንተ ባሪያና አገልጋይ ይሁን የሚል አለና ይህንም ሥለሚያውቁ የእናንተን ተንኮል አይሠሙም።

  ReplyDelete
 4. Abwselamawoch Yehagere sibket gubegnoch bemagaletachu lamesegnachihu wededku gin atadalu .kesis belay azuro yemimeleketibet anget yelelew azure ymiyasibbet aemro yellow kil zerafi bicha sayhon Wishetam new gin bemiktilnet yetemedebew Hailemariam abrhas AKEBAYNA TEKEBAY MHONU SATAWKU KERTACHIHU NEW YAH LEBANON ADDIS ABABA SIGEBA AND NEVADA KONGONA KELEMU YELEKEKE KISS BICHA IPHONE SURINAME NEW KISS MABZATU TIRGUMU AHUN NEW YEGEBAN .KEURAEL.KELIDETA .KMERKATO MIKAEL ZERFO ZAREFO ZARE YEMEKINA ASMECHINA SHAT SIHON AHUN DEGMO SEW BMISHETIBET YEDIS ABEBEBA HGERESIBKET GEBEYA .SEW BEMESHET LAY YALE LEBA NWE YIH SEW YEBELAY GENZBE AKEBAY NEW LMASMESEL LITALU YICHILALU .SILKIH ATADALU!!!!

  ReplyDelete
 5. your are pure protestant but hidden inside orthodoxy tewahedo church and please this is not your business. you also are clean? ask yourself first and do not confusion others we know clear who are you.

  ReplyDelete
 6. አአ ሀገረ ስብከት የሙስና ቤት ከሆነ መሰነባበቱ እውነት ነው። ከሲስ በላይን ግን በሙስናቸው ብቻ አይመስለኝም የምትዘልፋቸው። ምን አልባት ከሰሞኑ ተሀድሶን ተቃውመው ይሆን? ማቅ ደግሞ ምን ያድርጋችሁ? የዘረዘራችሁት የሀገረ ስብከቱ ችግር እንዲቀረፍ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል መመሪያ አዘጋጅቶ አስረከበ። የፓትርያርኩን አይንና ልብ ለግዜውም ቢሆን ማሳወር የቻሉ ሙሰኞችና የናንተ ብጤ ተሀድሶ መናፍቃን ተግባራዊ እንዳይሆን አምርረው ታገሉ። የኔ ወንድም ማቅ እኮ ሲኖዶስ አይደለም። መስራት የሚችለውና የማይችለው አለ። አትጠራጠር ሙሰኞችንና መናፍቃንን ከመቃወም መቸም ወደሃላ አይልም።

  ReplyDelete
 7. በደ/ኦሞ: በሀ/ስብከቱ እና በማኅበረ ቅዱሳን መተባበር ከ16 ሺሕ በላይ ምእመናን ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ተጨመሩ፤ ‹‹ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ደስታ ነው›› /ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ/
  እናንተ አውሩ ___________የሚሰራ ይስራ ___________

  ReplyDelete
 8. አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሌቦች ዋሻ ነው

  ReplyDelete
 9. እውነቱን እውነት ሀሰቱንም ሀሰት ማለትን ልመዱ እስኪ ሁሌ ውሸት ጥላቻ….ካልቀላቀላችሁ መልእክት ያስተላለፋችሁ አይመስላችሁም? ከእስከ አሁኑ በአንጻራዊ የተሻለ የሚባል ዘግባችሁ አበላሻችሁት፡፡
  ከላይ ከቤተክህነቱ ጀምሮ በአአ ሀገረ ስብከት ያለው ሙስና ወደር የሌለው ግፍ መሆኑን መናገራችሁ ትክክል ነው፡፡ አዲስ ነገር ግን አይደለም ፤ለዘመናት የተንሰራፋ እንጂ፡፡ ይሄንንም ለማስተካከል ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይገባል፡፡
  ታድያ ማኅበረ ቅዱሳን ይሄንን ለማስተካከል ነበር እኮ ‘’የሰው ሀይል እና የገንዘብ አስተዳደር መመርያ’’ በብጹ አቡነ እስጢፋኖስ አባታዊ መመርያ መስረት ያዘጋጀው….’’ህጋዊ አሰራር’’ ወዳላችሁት እንዲመጣ….. የ’’ማቅ’’ ተቃዋሚዎች ያላችኃቸው ወዳጆቻችሁ ግን ለተቃውሞ ሰላማዊ ስልፍ ወጡ::…..ስብሰባ ጠሩ….እንደ ዮሴፍ ወንድሞች እናጥፋው እንግደለው…ብለው ጮሁ፡፡ እናንተም አብራችሁ…. ታድያ ማኅበረ ቅዱሳን እናንተ የምትሉትን ግለሰብ ከመቃወም ይልቅ አሰራርን (ሲስተሙን) ለማስተካከል መጣሩ ቢያስመሰግነው እንጂ ያስወቅሰው ነበር??? እስኪ እናንተ ምን ሰራችሁ???????? የማያንጽ….የማይረባ የአሉባልታ ወሬ….መለያየት ስድብ…አድመኝነት…ኑፋቄ….ብቻ…..የማን ለጆች ናችሁ??? የግብር አባታችሁ…… እስኪ መልሱልን፡፡

  ReplyDelete