Monday, November 17, 2014

ግብረ ሰዶማዊነትና የእኛ ዘመን አገልጋዮች

 ምንጭ፡-ደጀ ብርሃን
(ግብረ ሰዶማዊነት በአስደንጋጭ ሁኔታ በሀገራችን እየተስፋፋ ይገኛል። በኅጻናት መብት ረገጣ ዙሪያ የሚሰሩ ሰዎች እንደሚናገሩት በአዲስ አበባ ከተማ ወደ ሆስፒታል ተደፍረው ከሚመጡ ኅጻናት መካከል የወንዱ ቁጥር ከሴቶቹ እኩል እየሆነ ነው። ይህ ወሬ ለክርስቲያኖች ሩቅ ነው ብለን ስናስብ የነበረ ቢሆንም በቤተክርስቲያን በግልጽ የሚሰማ ጉዳይ ሆኗል። እነ አባ እገሌ እነ ዲያቆን እገሌ እየተባለም የሚጠሩ ሰዎችን መስማት እንግዳ መሆኑ አብቅቷል። ይህ በሀገር ውስጥም በውጭም ባለችው ቤተክርስቲያን እኩል የሚሰማ እና የሚያስደነግጥ ጉዳይ እየሆነ ነው። በፕሮቴስታንቱም አለም ቢሆን ያለው ችግር ተመሳሳይ ነው።
በቤተክርስቲያናችን እንዲህ ያለ ችግር መስማታችን የበለጠ ልባችንን ያደማዋል። እንደዚህ አይነቱ ወሬ የመጨረሻው ዘመን ላይ ለመሆናችን ትክክለኛው ማሳያ ነው። በአሜሪካ እና በአውሮፓ መብት ሆኖ የጸደቀው እና በአደባባይ እስከ ማጋባት የደረሰው ግብረ ሰዶማዊነትን በመቃወም ቤተክርስቲያን የበኩልዋን ድርሻ ስላልተወጣች ነው። በኛም ሀገር ዝም ከተባለ እና ስለ እነ እገሌ እንዴት ይወራል? በማለት በዝምታ የሚታለፍ ከሆነ የሚያስከትለው ችግር እየከፋ ይመጣል። ለዛሬው በደጀ ብርሃን ብሎግ ላይ የወጣውን ይህንን ጽሁፍ እንድታነቡት እንጋብዛለን።)
    ( ከአቤኔዘር ተክሉ )
       
 ስለግብረ ሰዶማዊነት በሁለት የተለያዩ ክፍሎች መጻፌና በሁለቱ ክፍሎችም ለጊዜው የነበረኝን ሃሳብ ማጠቃለሌን አልዘነጋውም፡፡ ነገር ግን አሁንም ግብረ ሰዶማዊነት የቤተ ክርስቲያንን ቅድስና ከማርከስ፤ ምድራችንን ለከፋ ጉስቁልናና ርኩሰት አሳልፎ ከመስጠት ያላቆመ ፍጹም ወደመስፋፋት የሄደ ክፉ ርኩሰት ነውና ዳግም ይህንን ርዕስ ማንሳት አስፈልጎኛል፡፡ ለዚህ እውነታ ብዙ የቅርብ ጊዜ ማሳያ ብቻ ማንሳቱ በቂ ይመስለኛል፡፡
    ድርጊቱ የተፈጸመው በምስራቁ የሃገራችን ክፍል ነው፡፡ የሠላሳ ሁለት አመት አጐት የአራት አመት የወንድም ልጁን በእረኝነት ሥፍራ በመሄድ ጫት እንዲቅም ያግባባዋል፡፡ ህጻኑ እንቢ ቢልም ያስገድደዋል፡፡ ጫት እንዲቅም ካስገደደው በኋላ ልጁ ራሱን መቆጣጠር ሲያቅተው ልጁን የግብረ ሰዶም ጥቃት ይፈጽምበታል፡፡ የልጁ የሰገራ ማውጫ ሙሉ ለሙሉ ይቀዳዳል፡፡ ከሆዱ የወጣው የውስጠኛው የሰገራው ክፍል ሙሉ ለሙሉ የልጁን ጠረን ይለውጠዋል፡፡ ልጁ ፍጹም ራሱን ስቶ ሲወድቅ ከወደቀበት ቦታ ተሸክሞት ከወላጆቹ ጓሮ አምጥቶ ጥሎት ይሰወራል፡፡ ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የልጁ ህይወት ያልፋል፡፡


    ሌላም ብንጨምር፦ አንድ “ስመ ገናና” አገልጋይ እንዲህ ያለ ነውር እንደሚፈጽም በምስክር ይረጋገጥና ብዙዎች ተረባርበው ሊመክሩት ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ከማስመሰልና የሽንገላ እሺታ ከማሳየት በቀር ከነገሩ ሳይታቀብ ይቀራል፡፡ በኋላ ይባስ ብሎ በአቋም፤ የሠራው ትክክል እንደሆነና ይቅርታ መጠየቅ እንደማያስፈልግ ከብዙ ደጋፊዎቹ ጋር በግልጥ በአቋሙ ይጸናል፡፡ ወንድሞቹን ይቅርታ ሳይጠይቅ በግልጥ ለሠራውና ሌሎችን ላሰናከለበት ኃጢአቱ ንስሐ ሳይገባ እንደዋዛ ዛሬም አለ፡፡ በድርጊቱ የተጠቁት ወንድሞች ግን “እንዲህ ያለ ነገር እያደረገ በአንድ የኃይማኖት ጥላ ሥር አንቀመጥም” በማለት ወደሌላ የእምነት ተቋም ራሳቸውን አገለሉ፡፡ (ርቀው ወደሌላ የኃይማኖት ተቋም እንዳይሄዱ ብዙ ርብርብ ቢደረግም አልተሳካም፡፡)
    በመንግስትም ደረጃ በዘንድሮው የይቅርታ መመሪያ ውስጥ ይቅርታ ከሚያሰጡ ወንጀሎች መካከል ግብረ ሰዶማዊነትም እንዲካተት ጥረቶች “መደረጋቸውና መሳካቱንም” ጭምጭምታዎች ይሰማሉ፡፡ ጉዟችን ወዴት ይሆን? እንዲህስ እስከምን ድረስ ነው የምንጓዘው?
      ግብረ ሰዶማዊነት እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት ሙሉ ለሙሉ በመቃረን የሚፈጸም ርኩሰት ነው፡፡ ቃሉም “ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው”(ሮሜ.1፥24) እንዲል ቅዱሱን የእግዚአብሔር ፍጥረት በመቃረናችን ምክንያት የገዛ ኃጢአታችን “ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ እንደሰጠን” ትልቅ ምስክር ነው፡፡(ሮሜ.1፥26)
   ጥቂት የማይባሉ አገልጋዮች “ለአገልግሎት” ወደክፍለ አገር ወይም ወደውጪ አገር ሲወጡና ጨርሰው ሲመለሱ ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ሹልክ ብለው ለሴሰኝነትና ለዝሙት እንደሚገባበዙ ፀሐይ የሞቀው እውነት ሆኗል፡፡   በአቶ አስማማው ኃይሉ በተጻፈውና “ኢህአሠ” በተባለው ቅጽ አንድ መጽሐፍ ላይ ከትግል መልስ ደራሲው አንድ ታጋይ ነገረኝ ብሎ ሲጽፍ ፤ ታጋዩ ማደሪያ አገኘሁ ብሎ ወደ አንድ ቤተ ክርስቲያን ሊጠለል ጎራ ባለበት ወቅት ሌሊቱን ሙሉ  የገጠመው ሌላ ትግል ይኸው ከግብረ ሰዶማውያን ጋር ያደረገው ያለመደፈር ትግል እንደነበር በግልጥ አስቀምጦታል፡፡ በእርግጥ ዛሬ በገዳም ካሉት ጥቂት የማይባሉ መነኰሳትና መነኰሳይያት፤ እንዲሁም  በወንዶችም ሆነ በሴቶችም ዘማሪዎቻችን መንደርም የምንሰማው ነገር ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነው፡፡ (እንደአገር ስናስብ ደግሞ በካርዲናሎቹና በፓስተሮቹም መካከል አጸያፊ የርኩሰት ነገር ጆሯችን ከመስማት አልታከተም!!)     
     ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያሉ ኃጢአተኞችን በግልጥ ከመቃወም እየደከመች የመጣች ይመስላል፡፡ ምክንያቱም የግብረ ሰዶማውያን “አገልጋዮችን” የጨለማ ሥራን ከመግለጥ (ኤፌ.5፥11)፤ ሌሎች ሰዎችም ከክፋታቸው እንዳይተባበሩ ከማስጠንቀቅና መክራ እንዲመለሱ ከማድረግ ድምጿን አሰልላለች፡፡ ስለዚህም ሌሎች ብዙዎች ግብረ ሰዶማውያኑን  “በርቱ፤ እኛም ከጎናችሁ ነን” ከማለት አልፈው ለግብረ ሰዶማውያኑ ድጋፍ ሲሰጡና ሲሟገቱላቸው በአይናችን እያየን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ኩልልና ጥርት ያለ የተቃውሞ ድምጿን ልታሰማ ግድ የሚላት ጊዜ አሁንና አሁን ነው፡፡ ከረፈደ በኋላ መሯሯጥ ድካም እንጂ ሚዛን የሚደፋ ትውልድ የማዳን ሥራ አይሠራም፡፡  
    የሰዶም ሰዎች ያደርጉት የነበረው የክፋት ድርጊታቸውን እንደመልካም ከመቁጠር አልፈው እነርሱ የሚያደርጉትን ነውር የማያደርጉትን ሰዎች ይቃወሙ፤ የእነርሱን ነውር እንዲቀበሉ ያደርጉም ነበር፡፡ በአገሪቱ ካሉት ሰዎች ሁሉ ጋር ነውራቸውን ከፈጸሙ በኋላ  እንግዳ ሰዎች በመካከላቸው በተገኙ ጊዜ ከእንግዶቹ ጋር ሊፈጽሙ (በሎጥ ቤት የመጡትን መላዕክት ሲያዩ ወደአዲስ መጎምጀት መጥተዋልና!) የኃይልን መንገድ እንደተጠቀሙ፤ ጻድቁንም ሎጥ እንደተጋፉትና በሩን ሊሰብሩ እንደተገዳደሩ ታላቁ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡(ዘፍ.19፥5-9) ሰው ለእግዚአብሔር ባህርይና ለተፈጥሮ እውነት መገዛት ሲሳነው የኃጢአት መሻቱ ድንበር አልባ ይሆናል፡፡ ሁሉንም ርኩሰት ከመፈጸም የሚያግደውም የለም፡፡
   ዛሬ ላይ ድሆች ሃገራትን ለመርዳት የሚዘረጉ ብዙ የእርዳታ እጆች ስውር አጀንዳቸው ግብረ ሰዶምና ሰዶማዊነት ለመሆኑ ብዙ ማስተንተኛ ማቅረብ አያስፈልግም፡፡ ግብረ ሰዶምን በግልጥ የተቃወመች ብቸኛይቱ አፍሪካዊት ሃገር ይህንን በግልጥ አይታዋለችና፡፡ እኛ “ከቃል ባልዘለለ” ክርስትናችን በከንቱ ስንመካ ከአገራችን ቀድማ ግብረ ሰዶማዊነትን በግልጥ አለም አቀፍ በሆነ ዕይታ ህግን አስደግፋ ተቃውሞ ያሰማችው አፍሪካዊት አገር ኡጋንዳ ናት፡፡ በእርግጥ የእኛ ወንጀል ህግ “ግብረ ሰዶማዊነት ወንጀል ነው” ይላል፤ ግን የአገሪቱን ትልልቅ ከተሞች ጎዳና እያጥለቀለቁ ያሉትና ቁጥራቸው የማይናቅ አገልጋዮችን እንደወረርሽኝ በሽታ እየወረሱት ያሉት “ሴት እንተኛ አዳሪዎች” ብቻ ሳይሆኑ ግብረ ሰዶማውያኑም ጭምር ናቸው፡፡ ህጉ ቢኖርም ለነዚህ ምድርን ለሚያረክሱ “ወገኖች” ግን ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆኖ ተቀምጧል፡፡
   የኡጋንዳ መሪዎች ያንን የመሰለ ቁርጥ ያለ አቋማቸውን በግብረ ሰዶማዊነት ላይ ሲያሰሙ፤ ሰለጠን ያሉቱ ምዕራባውያን የኡጋንዳን ድርጊት “የሰይጣን ድርጊት” አድርገው ለማቅረብ ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡ (እግዚአብሔርስ ይቅር ሰይጣን እንኳ እንዴት ታዝቦን ይሆን?!)  የእኛ አገልጋዮች ግን ዛሬም ግብረ ሰዶማዊነትን በመካከላችን ያሽሞነሙኑታል፡፡ ከዓመታት በፊት ግብረ ሰዶማውያኑም አለም አቀፍ ስብሰባ አፍንጫችን ስር ባለችው አዲስ አበባ አድርገው አባላታቸውን መልምለው ሲሄዱ እንኳ ዝም ጭጭ ሆኗል ክርስትናችን፡፡ እንኪያስ ወርቁ ለምን ይሆን የደበሰው?
   ግብረ ሰዶማውያንን ለመቃወም የአገልጋዮች “ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ” ማለት ከበለጠብን እንኪያ እኛስ ከእነርሱ በምን እንሻላለን? መንፈሳዊነት መለኪያው የአገልግሎት ስኬት ሳይሆን የህይወት ጥራት ነው፡፡ ጌታ ጥራት ከሌለው ሸንጋይ መንጋ ጋር ህብረት እንደሌለውና ጥራት ካለው ጥቂት አማኝ ጋር ብቻ ህብረት እንዳለው በጌዴዎንና በሐዋርያት ህይወት አይተናል፡፡ ምክራችን፣ ጩኸታችን፣ ተግሳጻችን፣  ቁጣችን … “ምክር ለምኔ” ያሉ ግብረ ሰዶማውያን አገልጋዮች በንስሐ ተመልሰው የበደሏቸውንና ያሰናከሏቸውን ወንድሞች ይቅርታ በመጠየቅ እንዲመለሱ ነው እንጂ በመካከላችን ተቀምጠው ሌሎችን ለማጥቃት እንዲያደቡ አይደለም፡፡
    የእግዚአብሔርን ምህረት የሚያሸንፍ ወይም የሚበልጥ ኃጢአት የለም፡፡  እንዲህ የምንለው ግን በንስሐ ለሚመለሱ እንጂ ልብን ለሚያደነድኑ አመጸኞች አይደለም፡፡ ጌታ ለምድሪቱ ምህረትና የንስሐን ልብ ያውርድላት፡፡ አሜን፡፡

17 comments:

 1. gude gude gude are min yisalenal? geta hoy kezihe kefu zemen seweren.

  ReplyDelete
 2. ስመ ገናና ኢየሱስ ብቻ ነው። መንገደኛውን ሁሉ ስፀ ገናና እያላችሁ ተግሳጽ እንኳ ለመስጠት ድፍረት ታጣላችሁ

  ReplyDelete
 3. ኃጥያትን ብንሸፍናት አትከለል። ትታያለች እኔስ የሚሻለው ህዝበ ክርስቲያኑ ዓለሙ የደገፈውን ዝም ብሎ መደገፍ አብሮ መጥፋት ነውና መምህረኖቹ እባካችሁ በዓለሙ የተወደደውን እንጠላ እንጠየፈው ዘንድ ገስጹን። አለም ከግብር የወጣውን ወሲብ በግልጥ እንደ መብት እንድንቀበል ሲነግረን ከነሱ ይሻላል ብለን ወንድ ከሴትም አንሰስን። ዝሙት በሁሉም መልኩ ጥፋት ነው።

  ReplyDelete
 4. betam yigermal. ene degimo yihe gud le protestant ena le tehadiso bicha yimesilegn neber. andi ken andi yetehadiso ageligayi andun yetehadiso sebaki sidefirew be'ayine ayiche yigalet bil endet hono enwaredalen tebalena teshefafino kere. belelam gizie andi yepente paster kelela paster gar tegnitew sibaligu agegnehuachew. andit ye tehadiso zemari endihu kelelawa zemari gar. endihum andi ye pente zemari kelelawa zemari gar yazhuachew. yih hulu me'at sayameta megalet alebachew biye bizu dekemihu gin begenzeb bizat negerun adibesibisewut keru. ye orthodoxunis alisemahum neber. enesua enkua endezih yadergalu biye alitebikim neber

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰዉዬዉ ለመሆኑ አነተ ምን ስታደርግ እነዚህን ሁሉ ለማየት ዕድል አገኘህ የሚገርም ዉሸት ነዉ ትዝብትም ያስከትላል አንድም አንተን እነዚህ ሁሉ ሰዎች ለምስክርነት ይጠሩሃል ወይም አንተዉ ራስህ ነህ ሁሉንም የምታደርገዉና የምታስደርገዉ ማለት ነዉ በሕጋዊ ጋብቻ ዉስጥ እንኩዋን ያሉ ጥንዶች ይህን ጉዳይ በሰዉ ፊት አያደርጉትምና' ሌላዉ ደገሞ ስለስም መጥራት የሚያወሩት ምን እንዲፈይድ ነዉ ከባድ ሐጢያተ መሆኑን ማስተማርና ለንስሐ መጋበዝ ነዉ እንጂ እንኩዋን ሰባኪ ትላልቅ አባቶች ላይ ሲለቀለቅ የኖረዉ ምን ለዉጥ አመጣ ስም መጥራት የበቀለኝነት አንዱ ገጸታ ነዉ ገንቢም አይደለም

   Delete
 5. ጐበዝ እናንተ አካባቢ በዚህ መንፈስ እየተያዘ አለ ይባላል ግለጡት

  ReplyDelete
 6. በመጀመሪያ ማናችሁም አሥተያየት ሠጭዎች ልትገነዘቡት የሚገባ ነገር ያለ ይመሥለኛል። ይኸውም በዚህ ፅሑፍ ላይ ከመረጃ አቀራረብ ጀምሮ ሌሎችንም መለኪያዎች በመጨመር በንፁህ አድሎ በሌለበት ህሊና መዝናችሁ አሥተያየት ሥጡ።
  ምንም እንሿን ግብሮሰዶ የዛሬ ችግር ባይሆንም በአሁኑ ጊዜ በየትኛውም አለም የሚገኝ ችግርና ክፉ የሠይጣን መንፈስ ድርጊት ነው። በመየትኛውም መንገድ ግብረሰዶማዊነት ተቀባይነት የለውም። ነገር ግን የዚህ ፅሑፍ ታማኒነትና የአባ ከሳሽ ይቅርታ ይደረግልኝና አባ ሰላማ ብየ መጥራ አይገባኝም ምክንያቱም ስሙና ተግባሩ አብረዉ ሥለማይሄዱ ነውና ብሎጉ ይንጽሑፍ ማውጣቱ ለምን አላማ ነው? መቸም ለትምህርትና ለተግሳጽ እንደማትሉኝ እተማመናለሁ። አንድ ትውልድ ለማሥተማር አንድ ፁሑፍ በእውነተኛ መረጃዎች የተደገፈ መሆንና ተጠያቂነትን የአካተተ መሆን አለበት ብየ አምናለሁ። ይህ ፅሑፍ ግን ግብረሰዶማዊነትን መቃወሙ ተገቢ ቢሆንም በውሥጡ እንደማሥረጃ የተጠቀመባቸው ግን ታማኒነትንና እውነታን አያመላክቱም። በትና መፅሐፍ አንድ ታጋይ እንደነገረኝ ብሎ እንደምድራውያን የፖለቲካ ታጋዮች ሕቡ የሆ የሥም አገላለጽን ተጠቅሞ እና አንድ ትልቅ አገልጋይ ግብረሠዶምን ፈፅሞ ይቅርታም አልጠየቀ ይባሥ ብሎ ተግባሩን ትክክል ነው ብሎ በአደባባይ ይከራከራል በማለት እንደመረጃ መጠቀም አንድን የምነት ተቋም በዘቀጠ ጥላቻ ለመወንጀል ካልሆነ በሥተቀር ተራ ተረታተረት ነው። የታጋዮን ትተን የአገልጋይ ተብሎ በህቡ ትልቅ ተብሎ የተጠቀሠውን ብንመለከት ለምን ፀሐፊው ሥሙን አልገለፀውም? እንዳይገለል አዝኖለት ነው? አይመሥለኝም። ምክንያቱም ክፉ ሥራው ትክክል ነው ብሎ በግልፅ ይከራከራል ሲል ገልጾታልና ነው። የሚገርመውና የጽሑፉን አላማ የሚያሣየው ትልቅ አገልጋይ በተባለው አገልጋየ የተጠቁት እሱን አናይም ብለው ወደ ሌላ እምነት ሔዱ በማለት ተረት ያወራል። አንድ ሠው እምነትን መርምሮ ያልገባውን ጠይቆ ይወሥናል እንጂ የአንድን ግለሠብ ድርጊት የእምነቱ አካል አድጎ መወሠንና መለየት ባዶነት እንጂ እውቀት አይደለም። ደሞሥ ግለሠቦቹ ድርጊቱ ከተፈፀመባቸው ማጋለጥና ግለሠቡን ወደ ሕግ መውሠድ እንጂ ሀይማኖት መቀየር በግብረሠዶም ለመጠቃታቸው ማረጋገጫ አይሆንም። ለመሆኑ የግለሠቡን ሥም መጥቀሥ ለምን ፀሐፊው ፈራ? ለኔ እውነተኛ ሥላልሆነና በህግ እንደሚያሥጠይቀው ሥለሚያውቅ ነው። ለሁሉም አላማችሁ እውሸትን ለማንገሥ ነፁሐንን ለመክሥሥ በዚህም ክርሥቲያኖችን ለማሥኮብለል ነውና አይሆንላችሁም። ደግሞ እግዚአብሔር ያልተከለው አይፀናምና አንዳንድ በአለም ወሬ የሚሸነፉትን ልታገኙ ትችሉ ይሆናል። ይሄን ባዶ ክሥ በመለጠፍ መፅደቅ አይቻልም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. we heard a lot of things here in addis specially the so called one ``preacher`` if u gays have the evidence please let us know.

   Delete
  2. በኛ ሀገር ደረጃ ስም ጠቅሶ መጻፍ ከባድ ይመስለኛል። ስሙ የተጻበት ሰው የሚደርስበት መገለል ከባድ ነው። ጸሀፊው ስም አለመጥቀሱ ትክክል ይመስለኛል። በተረፈ ሰዶማውያን በኛ ቤተክርስቲያን ለመኖራቸው ለማጣራት በቅርብ የሚያውቁትን አገልጋይ መጠየቅ ነው። ጆሮዎትን እስከሚያምዎት ድረስ ሊነግርዎት ይችላል። ምናልባትም በጣም የሚያደንቁት ሰው የችግሩ ሰለባ ይሆን ይሆናል። ጌታ ይድረስልን

   Delete
  3. ምን ማለትሕ ነው ። ስዶማዊ ኣገልጋይ የለም ከሆነ ኣስተያየትሕ ስሕተት ነው። ኣንተም በሁሉ ስፍራ ኣለ ብለሃልና። ታድያ ማዘን ለማን ነው፣ ለተጎዱት ቢሆን ጥሩ ይመስለኛል። ያንተ ኣስትያየት ግን ሰዶማውያንን ኣገልጋዮት ኣትንኩብኝ ይመስላል። ማን ያውቃል ኣንተም ኣንደኛው ትሖን ይሆናል ጌታ ይመርምርህ

   Delete
 7. አንዳንዱ ሰው ምን እንደሚያስብ ራሱ ለማወቅ ይቸግራል። ችግሩ አይኑን አፍጦ እያለ እንኳ ስለቤተክርስቲያናችን እንሸፋፍነው ባይ ነው። ሌላው ደግሞ የችግሩ ሰለባ የሚያውቀው ሰው ስለሆነ ብቻ ደርሶ ጽድቅ ሊያደርገው ይሯሯጣል። ግን ትክክለኛው መንገድ ነገሮችን እንደ እግዚአብሔር ቃል ማየት ነው። ቃሉ ኃጢአት ያለውን ነገር ሀጢአት ብሎ መጥራት ያስፈልጋል። የተጻፈውን ነገር ሀጢአትን ሀጢአት በሚል ድፍረት ስለሆነ ጸሀፊው ሊደነቅ ይገባል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. በጣም ይገርማል እንዴት ሰው በአደባባይ እንዲህ ያለ ውሸት ይጽፋል ?በመጀመሪያ ደረጃ የእናንተ ችግር ምቀኝነት ነው፡፡ ይህንን ደግሞ በቅርበት የምናውቃችሁ ምስክሮች ነን ለምንድነው የፈጠራ ወሬ እያወራችሁ ሕዝቡን ግራ የምታጋቡት? ሠይጣንን ለማገልገል ቆርጣችሁ የወጣችሁ ክፉ አገልጋዮች ናችሁ፡፡ ምንም ዓይነት መንፈሳዊነት የማይታይባችሁ ለበቀል የወጣችሁ የቃየል ልጆች ናችሁ፡፡ ምናልባት እንደዚህ አባቶችንና ወንድሞችን ስማቸውን በአደባባይ ስታጠፉ ጥቂት ሰው ልታሰናክሉ ትችሉ ይሆናል ነገር ግን ሁሉን የሚያውቅ አምላክ በእውነት ይፈርዳልና አይሳካላችሁም፡፡እናንተ ብሎ ቤተክርስቲያንን አዳሽ በቅድሚያ ራሳችሁ ታደሱ ፡፡ ልቦና ይስታችሁ፡፡

   Delete
  2. አባ ሰላማዎች ይህች አስተያየት ቃል በቃል እሰማት ስለነበር ሰፈርዋን አውቃታለሁ እና ምላሽ ለመላክ ተገደደድኩ። እዚህ አዲስ አበባ ከተማ የተቋቋመ አንድ የሰዶማውያን "ፓርቲ" አለ። የፓርቲው አባላት አገልጋያችን የሚሉት ሰው ተሳሳተ ከሚሉ ኢየሱስ ተሳሳተ ማለት የሚቀናቸው ጨለማ ለባሽ የጨለማ መንገደኞች ናቸው። ሰውየው ልብ ገዝቶ ሰዶማዊነቱን አምኖ ከእግዚአብሔር ለመታረቅ የነበረውን ፍላጎት እንኳ በጭፍንነታቸው ያስተዉት እነዚህ "ተከታዮቹ" ናቸው። ኢየሱስን ስለማያውቁትና እርሱም ስለማያውቃቸው ነገሩን በእግዚአብሔር ቃል ፈትነው ትክክለኛውን ነገር ተቀብሎ ማስተካከያ ከማድረግ ይልቅ ምቀኝነት ምናምን የሚል የልጅ ተረት እያወሩ እራሳቸውን ምክንያታዊ ለማድረግ ይፈልጋሉ። ካፈርኩ አይመልሰኝ እያላችሁ ባቋቋማችሁት የውሸት ፋብሪካ የተለያየ ውሸት እየፈበረካችሁ ከመንዘላል እና ቀኑን ሙሉ እርሱን እያወሩ ከመዋል ከእግዚአብሔር ታርቃችሁ ከተያዛችሁበት ሰዶማዊ መንፈስ ነጻ ብትወጡ ይጠቅማችኋል። ዝም ስትባሉ ትክክል የሆናችሁ እየመሰላችሁ ተቸግራችኋል። ሰዶማዊ አገልጋያችሁን ታቅፋችሁ ክርስቶስን በማያስከብር እና ጌታም በተለየው ጉዞ መቀጠል ትችላላችሁ። ቢቀና ቢቀና ግን በሰዶማዊ አይቀናም ባይሆን ይታዘንለታል እንጂ። እና እነ ማሞ እና እነ ሚሚ እባካችሁ በቃ ተውናችሁ እኮ የማያሳድግ የማያበስል የማያጸድቅ ወተታችሁን እየተጋታችሁ መኖር ከተባለ መኖር ትችላላችሁ። እየነካካችሁን ግን እውነቱን በአደባባይ ጸሀይ እንድናሞቀው አታድርጉን። ይህ ምን ማለት እንደሆነ ሰዶማዊው "አገልጋያችሁ" ይገባዋል። ከጭፍሮቹ የተሻለ ማስተዋል እንዳለው ቢያንስ ይህ አስተያየት ሰጪ ያውቀዋል። በተረፈ እንደምናደራችሁም የት ዋላችሁም ስትባሉ አትደንግጡ ከእናንተ በቀር እና እናንተ ስም ጠፋ ቅብርጥሶ እያላችሁ ካወራችሁለት ሰው በቀር ጉዳዩን ብዙ ሰው አያውቀውም። ግን ነገሩን በውሸት በመከላከል ማስተካከል አይቻልም። መቸም ቢሆን ማስተካከያው ትክክለኛው መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር በእውነት መታረቅ ነው። ሰውያችሁም ገደሉን ቀበሩኝ እያለ አፈር ለአፈር ከሚንከባለል መንፈሱ እና ኅሊናው የሚነግሩትን እውነት ተቀብሎ በትክክለኛ ንስሀ ቢመለስ ይበጀዋል። አያሳዝናችሁም ወይ? እየዋሻችሁ እያታለላችሁ ሰውን በሀሰት እያነሳላችሁ አንደበቱ ልቡ የማይመሰክርለትን ነገር እያወራላችሁ ህሊናውን አቆሽሾ መንፈሱን አዋርዶ አብሮዋችሁ ሲቀመጥ አታዝኑለትም ወይ? መንፈስ ቅዱስ ያልነገረውን ጌታ እንዲህ ይላል ሲላችሁ ምን ይሰማችኋል? ሌላውን ትታችሁ ከእውነት መጣላት የሚያስከትለው የመንፈስ ኪሳራ የሚገባችሁ ከሆነ ብታስቡለት እና ወደ ትክክለኛው መፍትሔ ብታስጠጉት ጥሩ ነው። አሁንም እናንተ አላሰባችሁለትም። ያቀፋችሁት እየመሰላችሁ ኅሊናውን እየጠቀጠቃችሁት ነው። ትንሽም ቢሆን ቁራጭ መንፈሳዊነት እና እግዚአብሐየርን የሚፈራ ልብ ካላችሁ ብትረዱት ጥሩ ነው። በተረፈ አንድ ነገር ውሸት ነው ተብሎ ወሬ ስለተወራ ብቻ ውሸት እንደማይሆን ያለፉት ስድስት ወራት ሊያስተምሩዋችሁ ይገባል። በጣም የማዝነው የማታውቁት የማትወዱት የማታስቡለት እና በጌታ መንገድ መሄዱን የምትቃመሙ ሰዎች ተሰብስባችሁ እንደምታስቡለት እና እንደምትቆረቆሩለት ሲሰማችሁ ነው። ቢገባችሁ ለማንኛችንም ውርደቱ ውርደታችን ነው። ስለማይገባችሁ ግን ምቀኝነት በቀል ምናምን የሚል የልጅ ወሬ ታወራላችሁ። አለመብሰልና አለመተከል የሚያስከትለው ችግር ይሄ ነው። ጌታን ካወቃችሁት ማንም በማንም ውድቀት ደስ ሊሰኝ እንደማይችል ይገባችሁ ነበር። ነገር ግን ደግሞ ማንም በውሸት ጻድቅ መባሉም ለእግዚአብሔር መንግስት ሥራ እንደማይጠቅምም ማወቅ ይኖርባችኋል። ዋሹልኝ ሳትባሉ መዋሸት እንደጀመራችሁ አውቃለሁ። እሱም ውሸታችሁ ጥቂት ሰዎችን እንዳተረፈለት አውቆ ተሳሳተ። ሰው እንጂ ጌታ ግን ለመለየቱ መጠየቅ እንኳ አያስፈልግም። ቢያንስ አሁንም ቢሆን ቀኑን የሚጨርሰው ከህሊናው እየተሟገተ መሆኑ ግልጽ ነው። እባካችሁ ቢያንስ በእግዚአብሔር ፊት አንወሻሽ። እውነት መናገር ካልቻላችሁ ዝም ማለትም እኮ ይቻላል። ሁሉን የሚያውቅ ጌታ በእነውነት ይፈርዳል የተባለው ግን ትክክል ነው። ግን ከፍርዱ በፊት ምህረቱን መለመን አይሻልም? ከፈረደ በማን ላይ እንደሚፈርድ ግልጽ ነውና። ጌታ እውነተኛውን ማስተዋል ይስጣችሁ። ለእውነትና ለጽድቅ ጠበቃ ወደ መሆን ያድርሳችሁ። ከስሜታዊነት ነጻ ያውጣችሁ።

   Delete
  3. wnedeme sedomawinten lemekaweme tehadeso mehon ayasfelegim eko. hatiyat mehonun keteteraterke min litdereg tichelaehe. eslam enkuwa yimikawemewen lemekawem lemin yichegerehal. satetadesu minamin malet kentu negeger new. geber sedome hatiyat new malte weset kehone engidehe min yederegal? enastewel

   Delete
 8. የኡጋንዳ መሪዎች ያንን የመሰለ ቁርጥ ያለ አቋማቸውን በግብረ ሰዶማዊነት ላይ ሲያሰሙ፤ ሰለጠን ያሉቱ ምዕራባውያን የኡጋንዳን ድርጊት “የሰይጣን ድርጊት” አድርገው ለማቅረብ ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡ (እግዚአብሔርስ ይቅር ሰይጣን እንኳ እንዴት ታዝቦን ይሆን?!)

  የሰላማ ብሎግ ጸሐፊዎች ያልተገነዘባችሁት ወይንም ለመደበቅ የፈለጋችሁት ነገር አለ፡፡- ምዕራባውያን የቸእናንተ እምነት መሥራቾችና መሲሆቻችሁ መሆናቸውን፡፡ ስታንቆለጳጵሷቸው የነበሩት ምዕራባውያን ከፓስተሮቻቸው ጀምሮ እስከ ታላላቅ መሪዎቻቸው ድረስ ግብረ ሰዶምን መፈጸም ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ በሃገራቱ በሕግ እንዲፈቀድ በማድረግ ወራዳነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ይህ አልበቃ ብሏቸው በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ስብሰባዎች ግብረ ሰዶም እንዲፈቀድ ጥረት እያደረጉ እንደነበረና አሁንም በማድረግ ላይ መሆናቸውን እናውቃለን፡፡ የግብረ ሰዶም ታሪክ ከሰዶምና ገሞራ የጀመረ ቢሆንም እንዲያንሰራራ ያደረገው የፕሮቴስታንት መስፋፋት መሆኑን አንባቢው ልብ ይበል፡፡ በሃገራችን ኢትዮጵያ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት ርዝራዦች በየከተማው ሲያስፋፉት የቆዩት ይሄንን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሰገሰጉ የተሃድሶ መናፍቃን ሰለባዎች የዚህ ገፈታ ቀማሾች ናቸው፡፡ በሁለት ቢላዋ ሚበሉ ዲያቆንና ቄስ መሳዮች እወነተኛ አባቶቻችንን ለማሰደብ ይህንን ተግባር እፈጸሙ መሆን ሁሉም ያውቀዋል፡፡
  በተለያዩ አድባራትና ቤተ ክኅነት መዋቅር ውስጥ የምናገኛቸው አነዚህ መናፍቃን የኑፋቄ ወላጆቻቸው ምዕራባውያን ያወረሷቸውን ተረክበው በሰዶም መንገድ አየበረሩ ይገኘኛሉ፡፡ ታዲያ የኑፋቄ ብሎግ ጸሐፊው ይህንን መጻፉ ለምን ይመስላችኋል፡፡ ምዕመናን ምስጢሩን ሲረዱ ከፊታቸው እንዳይደርሱ ስለሚያደርጓቸው እንዲሁም ውርደት ያሳፍራልና ይህንን ለመሸፋፈን እስቅሞ ለመከላለክ ተብሎ የተፈጸመ ደባ ነው፡፡ እናንተ ትደብቁት ባለቤቱ እግዚአብሔር ይገልጠዋልና አይምሰላችሁ፡፡
  ምዕመናን ሆይ የመናፍቃን የንፍሃቱ ውርጭ እንዳያጠወልገን መንቃት ይገባናል፡፡ እንርሱንም ልብ ይስጣቸውና ወደ ቀደመ ቤታቸው ለመመለስ ያብቃቸው፡፡

  ReplyDelete
 9. Wedate wedate....bemejjemeriya tininish wendochun yemidefruteko menekosatu nachewo.bizuwochenm lezihech keysi hatiyat asalefew yesetwachew enersu nachew.

  ReplyDelete