Wednesday, November 19, 2014

የእግዚአብሔርን ዝማሬዎች ለሌላ የሰጡ “ዘማሪዎች” ምን ይባሉ?

read in PDF

ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሣሣኝ ከሳምንታት በፊት አባ ሰላማ ላይ የወጣውና በዘማሪ ታዴዎስ ዝማሬዎች ላይ የቀረበው መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጎ የተሰጠው እጅግ መልካምና ሚዛናዊ ሒስ ሲሆን እኔም ታዴዎስን ጨምሮ የእግዚአብሔርን ዝማሬዎች ለሌላ በመስጠት እግዚአብሔርን እያሳዘኑ የሚገኙ የጥቂት ዘማሪዎችን ዝማሬዎች ይዘት በመጠኑ ለመዳደስ ነው፡፡ ከእነዚህ ዘማሪዎች መካከል የታዴዎስን የአዜብ ከበደንና የእንግዳወርቅ በቀለን አንዳንድ ዝማሬዎችን እንመልከት፡፡

ዘማሪ ታዴዎስ
ይህ ዘማሪ የአንኮበርን ፖለቲካ ያራምዳሉ ከሚባሉት የማቅ ክንፎች አንዱ እንደሆነ ከሚዘምርላቸው “ቅዱሳን” አንጻር መመልከት ይቻላል፡፡ መዝሙሩ በአብዛኛው በሸዋ የተወለዱና “ቅዱሳን” የተባሉ ሰዎችን የሚያሞጋግስና የሚያመልክ ነው፡፡ ታዴዎስ ከዘመረላቸው የሸዋ “ቅዱሳን” መካከል እጨጌ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ አንዱ ናቸው፡፡ ስለእርሳቸው ሲዘመር ምንጭ አድርጎ የተጠቀመው ገድለ ተክለሃይማኖትን ሲሆን ገድሉ ፈጽሞ ተኣማኒ ያልሆነውንና እንደ ዮሐንስ አድማሱ ያሉ ሊቃውንት በግጥማቸው “ሰይጣን ሠለጠነ” ብለው የተሳለቁበትን፣ ብዙዎችም ተረት ተረት የሚሉትን የፈጠራ ድርሰት ነው፡፡ የዮሐንስ አድማሱ ግጥም እነሆ!
ሰይጣን ሰለጠን፣
ቀንዶቹን ነቃቅሎ
ጭራውንም ቆርጦ
ከሰው ልጆች ጋር አንድነት ተቀምጦ
ሊኖር ነው ጨምቶ
ከሰው ልጆች ጋር ሊጋባ ተጫጭቶ።
ሰይጣን ሰለጠነ፤
ዘመናዊ ሆነ
ፊደል ቆጠረና ዳዊትም ደገመ
በስመ አብ ብሎ ውዳሴ ማርያምን
አንቀጸ ብርሃን መልካመልኩን ሁሉ
አጠና ፈጠመ።
ከዚህም በኋላ ጾም ጸሎት ጀመረ
በመጨረሻውም አቡን ተክሌ አጥምቀው
ክርስትና አነሱት።
ግና ተቸገረ
እንዲያው በየዕለቱ
ጨርሶ አላወቀም ለማን እንደሆነ ጾምና ጸሎቱ
ቢጨንቀው ጊዜና ቆይቶ ሰንብቶ
ክርስቲያን የሆነ አንድ ሰው አግኝቶ
ተወዳጀውና ብሶቱን ነገረው ሁሉንም ዘርዝሮ፣
በጣፈጠ ቋንቋ በውነት አሳምሮ።
አትቸገርአለው ክርስቲያን ወዳጁ አጽንናው መልሶ
ሰይጣኑ ካሰበው አለመጠን ብሶ፣
ይህስ ቀላል ነገር ችግርም የለው
እንደኛው ክርስቲያን ሆንክ ማለት ነው።

እንደሚታወቀው ገድለ ተክለ ሃይማኖት ላይ ያለው የፈጠራ ታሪክ አባ ተክሌ ዲያብሎስን ገርዘው አጥምቀው አመንኩሰው ክርስቶስ ኀረዮ የሚል ስመ ጥምቀት እንደሰጡት ይተርካል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ሰይጣንና ሰራዊቱ የዘላለም እሳት የተዘጋጀላቸውና ወደመዳን የማይመጡና ለፍርድ ቀን የተጠበቁ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል፡፡ ዘማሪ ታዴዎስ ግን ይህን እውነት እንኳ መገንዘብ ተስኖት ይሁን ወይም ሆነ ብሎ ሕዝብን ለማሳሳትና ጊዜያዊ ትርፍ ለማግኘት ሲል “መነነ ተክለ ሃይማኖት” በተሰኘው “መዝሙሩ” ውስጥ ይህን አሳፋሪና ሐሠተኛ ታሪክ አውስቷል፡፡
መነነ ተክለ ሃይማኖት መነነ
አሰረ ወንጌል ዴገነ …
ወበጸሎቱ ዓለምን አዳነ
በተክልዬ ገዳም ዲያብሎስ ታሰረ     
ድንጋይም ፈለጠ እንጨትም ቆረጠ …” እያለ ይቀጥላል
ይገርማል! ዓለም የሚድነው በክርስቶስ ሞት ብቻና ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የተክልዬ ጸሎት ዓለምን አዳነ ተብሎ ሊነገር አይችልም፡፡ የቅዱሳን ጸሎት በሥራዋ ኃይልን የምታደርግ መሆኗ እውነት ሲሆን፣ ይህም ቅዱሳን በአጸደ ሥጋ እስካሉ ድረስ የሚሆን ነው፡፡ ከሞቱ በኋላ ይህን ማድረግ አይችሉም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በግልጽ የምናነበው  የቅዱሳን ምልጃ በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ያቀረቡትን ምልጃ ነውና፡፡ እርሱም ቢሆን ዓለምን ለማዳን የሚጠቅም አልነበረምና ክርስቶስ መምጣት አስፈለገው፡፡ እንኳን ጸሎታቸው የነቢያት ደም ዓለምን ለማዳን እንዳልጠቀመ አይቶ ጌታ ሰው ሆኖ መምጣቱን መጽሐፈ ቅዳሴ ጠቅሶታል፡፡ ስለዚህ የተክልዬ ጸሎት ዓለምን አዳነ ተብሎ ሊገር አይገባም፡፡ ታዴዎስ ይህን ዝማሬ የዘመረው ቅድስት ሥላሴ ገብቶ ቲኦሎጂ ሳይማር በፊት ነውና ለ5 ዓመታት በቅድስት ስላሴ ኮሌጅ ቆይታ ካደረገና ከተመረቀ በኋላ ስለዚህ ጉዳይ ያለው አመለካከት ምን ይሆን? በዚህና በመሳሰሉት “መዝሙሮች” ተጸጽቶና አፍሮባቸው ይሆን? ወይስ አጽንቶት ቀጥሎበታል? ይህን መስማትና ማወቅ ያጓጓል፡፡

ሌላዋ ዘማሪት አዜብ ከበደ ናት፡፡ ይህች ዘማሪት የክርስቶስን አዳኝነት ከሌሎች “አዳኞች” ጋር ደብላ ያቀረበች ከጽንፈኛ “ዘማሪያት” ጎራ የምትመደብ  ናት፡፡ አንዱ ዝማሬዋ “አድነኝ ክርስቶስ አድነኝ፤
      ከመከራ ሕይወት ሰውረኝ” የሚል ሲሆን፣
ይህን በዘመረችበት አፏ ምንም ሳትሰቀቅ አድኚኝ ማርያም፣ አድነኝ ጊዮርጊስ … እያለች ዘምራለች፡፡ ለመሆኑ ስንት አዳኝ ነው ያላት? የአንዱ አዳኝነትስ አይበቃም ነበር ወይ? የክርስቶስ አዳኝነት አልበቃ ብሏት ነው አድኚኝ ማርያም ያለችው? የማርያምስ አላረካት ብሎ ነው ጊዮርጊስ አድነኝ ያለችው? ይህ የብዙዎች ችግር ነው፡፡ እንኳን እርሷ መጽሐፈ ሰዓታትም በዚህ ዓይነቱ ስሕተት የተሞላ መጽሐፍ ነው፡፡ እውነተኛ ምስጋና የቀረበበት መጽሐፍ የመሆኑን ያህል ፈጣሪን ብቻ ሳይሆን ፍጡራንን ሁሉ በ “ለምኑልን” (ሰአሉ ለነ) ስም አዳኝ አድርጎ ያቀርባል፡፡ የክርስቶስ አዳኝነት አላረካ ያላቸውና ሌሎችን አድኑኝ ብለው የሚማጸኑ ሰዎች ምንኛ አሳዛኞች ናቸው? እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን፡፡

በመጨረሻ የምጠቅሰው እንግዳ ወርቅ በቀለ ሲሆን፣ ይህ ሰው ከሚዘምራቸው መዝሙሮች በመነሣት “ኦንሊ ማርያም (Only Mary)” የሚል ቅጽል ስም የወጣለት መሆኑን ማስታወስ እወዳለሁ፡፡ ይህ የእግዚአብሔርን ቃል ጭምር በመዳፈር የሚታወቅ “ዘማሪ” “ቆይቼ እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኸቴንም ሰማኝ።” የሚለውን ቃል ለውጦ ለፈረደባት ኪዳነ ምህረት ሰጥቶ አገርን ጉድ አሰኝቷል፡፡ “ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን …” በማለት፡፡ እስኪ አሁን ይህ ቃለ እግዚአብሔር ለኪዳነ ምህረት እንዴት ሆኖ ነው የሚስማማት? ምናለ የማይሆናትን ከሚሰጣት በልኳ ቢሰፋላት? ሕያው እግዚአብሔር ክብሬን ለሌላ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም ብሏል እኮ? ይህ አምላካዊ ማስጠንቀቂያ ለእንግዳወርቅ ምንም አይደል መሰል የእግዚአብሔርን ለኪዳነ ምህረት ሰጠ፡፡ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው፤ ማስተዋልንም ይሰጠው፡፡

በመጨረሻም “ዘማሪ” እንግዳ ወርቅና የግብር ባልንጀራው “ዘማሪ” ምንዳዬ ብርሃኑ ላይ የተባለውን ልጥቀሰና ላብቃ፡፡ ሁለቱ በሚያወጧቸው “መዝሙሮች” ውስጥ የማርያምን አብዝተው የጌታን አሳንሰው ማውጣት ልማዳቸው ነው፡፡ ማለት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ስለፍጡራን በርካታ “መዝሙሮችን” ይዘምሩና ስለጌታ እንደነገሩ አንድ ሁለት ጣል ያደርጉበታል፡፡ ይህን በተመለከተ ዘማሪ ቴዎድሮስ ዮሴፍ እንዲህ አለ አሉ፡፡ ይኸውም በተአምረ ማርያም ውስጥ ያለውን አምስቱ ሀዘናት የተባለውን ጥያቄና መልስ ለውጦ የተናገረው ነው፡፡ ጌታ እመቤታችንን በእኔ ምክንያት ካገኙሽ ሀዘኖች የትኛው ሀዘን ይበልጣል ብሎ ጠየቃት፡፡ እሷም ስትመልስ በአንተ ምክንያት ካገኙኝ ሀዘኖች ከፍተኛው ምንዳዬና እንግዳ ወርቅ በየካሴቶቻቸው 2 የአንተን 8 የእኔን መዝሙር መዘመራቸው ነው፡፡ እሱም ከቶ አላውቃቸውም አላት ብሏል፡፡ ታዲያ ከታዴዎስ እስከ አዜብ ከእንግዳ ወርቅ ወርቅ እስከ ምንዳዬ ያሉትን ፍጡር አወዳሽ “መዘምራንን” ምን እንበላቸው?  ዘፋኝ ቢባሉ ምን ይላል?

መሪጌታ ገብሬ


19 comments:

 1. I absolutely agree.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለእውነት እንቁምNovember 20, 2014 at 8:19 PM

   ባትስማ ነበር የሚገርመው።ሰይጣን ሰይጣንን ሰይጣንን ብሎ ክፉ ስራውን ለመቃወምና ለመለየት አይሻምና ነው። አንተም በመርጌታነት ሽፋን የተለበጠውን የአቶ ሐሰተኛ ከሳሽነህ ግብሩን የእግዚአብሔርንና የሠውን አሠራር ባለማወቅ የተጻፈን የእግዚአብሔር የሆኑት ጻድቃን ለምን ክብራቸው፣በእግዚአብሔር ፀጋና ሀይል የሠሯቸው ሥራዎች በመዝሙገርና በመፅሐፍ ተዘከረ ጥላቻን ብትደግፍና ብትሥማማ ህብረትህ ከአቶ ከሳሽነህ ግብሩ ነውና አያሥደንቅም።በመጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስ አስር ዲናር ስላቀረበችው ሴት እንዲህ ብሏል"ወንጌል በሚነገርበት ሁሉ ይኸች ሴት ያደረገችው ይነገራል"። ሥለሆነም ኤልሳቤት"የጌታየ እናት ወደኔ ትመጭ ዘንድ እንዴት ይሆናል" ብላ እንዳመሰገነቻት የተዋህዶ ዘማሪያንና አማኞች ለእመቤታችን ድንግል ማርያም የተሠጣት ቃልኪዳኖችና ያደረገቻቸውን ታምራቶች በማንሳት ይዘምራሉ።የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ነው ተብሏልና ለእግዚአብሔር ተለይተው ጃንደረቦች ለሆኑት ቅዱሳንም የተዋህዶ መዘምራንና አማኞቿ ክብራቸውንና የእምነት ተጋድሏቸው በመመስከር ይዘምራሉ።ኤልሳ የአባቱን የኤልያስን መንፈስ ሲጠይቅ መጎናፀፊያውን ነበር ኤልያሥ ለኤልሳ የሠጠው።ኤልሳም መጎናፀፊያውን በደስታ ነበር የተቀበለው።ምክንያቱም የአባቱ የኤልያስ መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ ነውና ከሰውነቱ አልፎም በመጎናፀፊያው ተርፏልና በእምነት ተቀበለ በመጎናፀፊያው ባህርን ከፈለ።ሥለዚ እኛም በቅዱሳኑ በኩል እግዚአብሔር እንደሚባርከን፣እንደሚፈውሰንና፣ጠላታችንን እንደሚጥልልንና ችግሮቻችንን ሁሉ እደሚፈታል በማመን ቅዱሳኑን በፀሎት፣በመዝሙር፣በምስጋና እንጠራ ለን እናከብራለን። ደቀመዝሙር ከመምህሩ አይበልጥምና የሚያገለግልም ክብር ይገባዋልና።"እንግዲህ ሥለዚህ ነገር ምን እንላለን?እግዚአብሔር ያከበራቸውን ማን ይቃወማቸዋል?"ሥለሆነም እናክብራቸው።ማክበር ደግሞ በተግባር እንጅ በወሬ አይደለም።ከሳሽነህ ግብሩና አባ ሠላቢዎች እንዲሁም ቲፎዞዎቻቸው ብሎም አሠሪዎቻቸው ወደልባችሁ ተመለሱ "እግዚአብሔር በፀጻድቁ እንደተመሰገነ እወቁ"።እናም ጻድቃን ቅዱሳንን እኛ ኦርቶዶክስ ተዋህዶአዊያን ሥናከብራቸውና ሥናመሠግናቸው እግዚአብሔርን በአምላክነቱ ይብራል፤ይመሠገናልና ይህንን እወቁ።

   Delete
 2. መሪገታ ሰዎቹ እኮ ለእንጀራ ነዉ እንጂ አሁን አጥተዉት ነዉ ብለዉ ነዉ? እኔስ ነፍሴን እንዲህ ከምሸጠዉና በመንፈስ ቅዱስ ከምቀልድ ሌባ መሆን የሻለኛል፡፡የሃጢያት ቆንጆ ባይኖረዉም በመንፈስ ቅዱስ የሚያፌዝ (ዘማሪ ነን ባዮቹ የጌታን መወድስ ለሌለ በመስጠታቸዉ የመንፈስ ቅዱስን በረከት ማክፋፋታቸዉ ስለሆነ) ይቅርታ ስለሌለዉ ማለቴ ነዉ፡፡ ይህ ምን ይባላል? ባገራችን ራሱን የገደለ ፍትሃት የለዉምና ይቅርታ እንኩዋን ይደረገላቸዉ ለማለት ይከብደኛል፡፡

  ReplyDelete
 3. አባ ሰላማዎች ለወንጌል አገልግሎት የተቃጠላችሁ መስሎኝ ሁሌም ባይሆን በአብዛኛው እደግፋችሁ ነበር። እንዲህ ዓይነት ዘር ተኮርና በጣም የወረደ አንድን ዘር የሚያጥላላ ጽሁፍ በዚህ ሰሞን ደጋገማችሁን። ይህንን ብሔር በሀገሩ ላይ ሰደተኛ ከሆነ 23 ዓመታት አሰቆጠረ እኮ። አሁንም አሳዳጁ ሚኒሊክ ቤተመንግስት አለ። ማሳደዱን ለመንግስት ትታችሁ እናንተ ወንጌሉን ብትይዙ አይሻልም።

  ReplyDelete
 4. zefen hatyat ew..zefagnm ye egiziabihern mengist ayiwersm..neger gin zefagn neseha bigeba amilak bemihiret yikebelewal...enezih zemari tebiyewoch gin yeneseha lib ayinorachewum..miknyatum beelih menfes eyebasu yemihedu..lememar yalitezegaju..enjerachew kasset yehone dekamoch nachew...yikir yibelachew...tseliyulachew...!!

  ReplyDelete
 5. አውሬው የሚውጠውን ፍለጋ እንደሚያገሳ አንበሳ በዙሪያችሁ ይጮለልና ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ!
  ክፉ የዚህ አለም ገዠ ነውና በማረካቸው ከመልካም ይልቅ አመፃንና ተነኮልን በሞላባቸው
  እውነትን ፈልገው ወደ እውነት እንዳይቀርቡ በአዚም
  ባወራቸው ማንነታቸውንና አርነታቸውን ቀብሮ የሐጢያት ባሮች አድርጎ ረግጦ በያዛቸው የጥፍት
  ሠራዊቶቹ አማካኝነት በእውነት ቦታ የቆሙበትን
  ለመጣል ሌት ተቀን በክሥ፣በስም ማጥፋት፣
  የእግዚአብሔር መንግስትን የሚያውጆትን ፖለተክኛና
  ዘረኛ በማለት፣በእግዚአብሔር መንፈስ የሚነገረውን
  የእውነት ወንጌል በማጥላላት፣የምዕመናንን ልብንና
  መንፈስን ማርኮ ህሊናን ቀሥቅሶ አምላካቸውን
  እግዚአብሔርንና የሱ የሆኑትን ቅዱሳኑን የሚያዮበት
  የእውነት መዝሙሮችንና ዘማሪወቿን በማንቋሸሽ፣ሌሎችንም የአባታቸውን የዲያብሎስን የውጊያ ፍላፃዎችን በመወርወር በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና አማኞቿ ዙሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተነገረው በዙሪያቸው የሚውጥቱን ፍለጋ ያንቧርቃሎ።ዛሬ ደግሞ አውሬው የሚውጠውን ፍለጋ ውጊያውን በተዋህዶ መዝሙራትና ዘማሪወቿ ላይ አድርጏል።በመጀመሪያ አንድ ሠው በእራሱ ቤት ውሥጥ ሥላለው ሊያወራ ይችላል አኛ አንጅ የጎረቤቱ ቤት የውሥጥ ይዞታ ባለቤቱ ካላአበራራለትና ካላሣወቀው በሥተቀር ቤት ውሥጥ የገባ ቢሆንም እንሿን ምንም አይነት ነገር አሟልቶ መናገር እንደማይችለው ሁሉ የአንድን እምነት ተቋምም የእምነት አፈፃፀምም ለአማኛቿ እንጅ ለሌሎች የተገለፀ ሥለአይደለ ምንም መናገር አይችሉምም አይመለከታቸውም ብየ አሥባለሁኝ።አውሬው ድሮ የግዕዝ ቋንቋን፣ከበሮውን፣ፀናፅልንና መቋሚያን፣እንዲሁም የኦርቶዶክሥ እምነት መንፈሳዊ መገልገያ የሆኑትን የአገልግሎት መሳሪያዎች ሁሉ ሲያጥላሉና በክፉ ሲገልጿቸው ነበር። ዛሬ ግን የግዕዝ ቋንቋውንም፣ ፀናፅልና መቋሚያውን፣ከበሮውንና ሽብሸባውን ለመዳንና ለእውነት ሳይሆን ለማታለያና አሥመሣይነት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።ለመሆኑ ለእግዚአብሔር የሚዘመረው ለአምላክነቱና በአምላክነቱም በሠማይም በምድርም ሥለሚሠራው የአምላክነት ሥራው መሆኑን ለቅዱሳን የሚቀርበው ዝማሬና ምስጋና ደግሞ ለክርሥቶሥ ተለይተው እግዚአብሔር በነሡ የሠራውን ሥራ በማዘከርና የተሠጣቸውን ክብርና ቃልኪዳን በማሠብ የፀጋ ምሥጋናና ዝማሬ እንጂ አምላክ ናቸው ተብሎ አይደለም።ነገር ግን ከሳሽ ጠይቆ ከመረዳትና እውነቱ ከማወቅ ይልቅ የተለመደውን የከሳሽነትና የአላዋቂነቱን ተግባሩን በትጋት እያከናወነ ይገኛል።ለመሆኑ እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል
  ማለት ምንማለት ነው ከሳሽ? መቀበልንስ በእምነት እንዴት ነው ተግባራዊ የሚደረገው?በመዝለፍ፣ሙታን በማለት፣በስጋ መለኪያ እንደኛ ናቸው በማለት እረ በጭራሽ።የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ነው ማለትሥ ምንማለት ነው? በመዝሙር፣ በእግዚአብሔር የተከበራችሁ ሀይሉንና ፀጋውን ያበዛላችሁ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በእናንተ አድሮ ሥራውን የሠራባችሁና የሠራችሁ ክብርና ምስጋና ይገባችኃል በማለተ ማዘከር አይደለምን? ሳኦል የተብሎ ይጠራ የነበረው ሐዋሪያዊው ቅዱስ ጳውሎስ በናዝሬት ጎዳና ክርሥቲያኖችን ያሳድድ በነበረበት ጊዜ ክርስቶስ ሥለምን ታሳድደኛለህ የመውጊያውን ቀስት በትቃወም ለአንተ ይብስብሀል ባለው ጊዜ አንተ ማንነህ ብሎ ሲጠይቀው አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ እየሱስ ነኝ ነው ያለው። ዛሬም ጻድቃንን የሚጠሉ ይፀፀታሉ እንደተባለው የክርስቶስ የሆኑትን ለምን አከበራችሁ፣ ለምን በመዝሙር አዘከራችሁ በማለት ተከባሪዎችንም አክባሪወችን ማሳደድና መጥላት ክርስቶስን መጥላትና ማሳደድ ነውና በድርጊታቸው መፀፀታቸው አይቀርም።ምክንያቱም ቅዱሳን ሥለ ቅድስናቸውና ስለክብራቸው ሲመሠገኑ ከእነሱ ጋር ያለው እግዚአብሔር ነውና የሚከብረው። ሌላው አስገራሚው ዘመቻ በእግዚአብሔር ፀጋና ሐይል ጻድቁ አቡነ ተክለሐይማኖት የሠሯቸው ታምራቶችና ድንቅ ስራዎች መናቅና ሐሰተኛ ለማሥመሠል የሚደረገው ዘመቻ ነው። ለመሆኑ ሠይጣንን አሳምነው አጥምቀውክርስቲያን አደረጉ ማለት በቁሙ አካል የለሹን ክፉውን መንፈስ የዚህ ዓለም ገዠ የባለው ነውን? እረ በፍፁም አይደለም። ሰይጣንን አሳምነው አጥምቀው አመለኮሱ የተባለው ስጋ ለባሽ የሆነው ሠው በዳቢሎሥ ጦር ተወግቶ ሠይጣን ክፉ ስራ ያሰራ የነበረውን እግዚአብሔር በሠጣቸው ሀይልና ፀጋ የሠይጣንን መንፈስ አሥወጥተው እውነትን እሱም ክርሥቶሥን እንዲያምን አድርገው አመለኩሱት ማለት ነው እንጂ ክፉወች እንደሚያናፍሱት ሰይጣን የተባለውን ሥጋ የለሽ ክፉ መንፈስ አይደለም። ይኸን ማድረግ አይችሉም ከሆነ በመፅሐፍ እምነት ይኑራችሁ እንጂ እኔ ከማደርገው በላ ተው ተደርጋላችሁ ተብሏልና በእምነታቸው ፍፁምነት አድርገውታል። በዚህ በአባ ሠላቢ ብሎግ ላይ መጋቢ ዲያቆን ነኝ እያላችሁ በዳቢሎሥ መነሳት መነፈስ እየተጋለባችሁ ፊደል ስለተገጣጠመላችሁ የሞትለጥፉ እውነትን የምትዋጉ ወተቱን የምታጠቁሩ የራሳችሁ የሆነ ቤት የሌላችሁ የእውነትን ቤት ለማዳከም የምትናውዙ መሆናችሁ ተውቋልና እውነተኞቹን ልታሸንፉ አትችሉም።ምክንያቱም ተዋጊው እግዚአብሔር ስለእነሱ ይዋጋልና።

  ReplyDelete
  Replies
  1. yegeremall .....menew tadyaa zemarii tewodrosenn zemmee alutee meregetaa......ende zemarii tewodross selemebetachen,sele melakete yemezemeree ylelemm...new weyes fertewetee new......yiegermall....yegell kimee semeselebeweteee.......lemanegnaweme egzabhere feredune yesete.

   Delete
 6. እሱም ከቶ አላውቃቸውም አላት ብሏል፡፡

  ReplyDelete
 7. እሱም ከቶ አላውቃቸውም አላት ብሏል፡፡

  ReplyDelete
 8. መጽሐፍ ቅዱሱንም እንየው፡፡ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር በተባለው መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን….ርግቤ…ሱላማጢስ….ወዳጄ….ውበቴ በሚሉ ቃላት ተውቦ በሴት አንቀጽ(ጾታ) የቀረበው መዝሙር እንዴትም ቢተረጎም ምስጋናውና ውዳሴው ለእግዚአብሄር የቀረበ ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ሊቃውንቱም (ቅ/ያሬድን ጨምሮ) የሚተረጉሙት አንድም ለወንጌል፣አንድም ለቤ/ክ፣አንድም ለእመቤታችን የቀረበ ውዳሴ ነው እያሉ ነው፡፡እርግጥ የእናንተን ትርጉም አናውቀውም፡፡ግን ለእግዚአብሄር ብቻ የቀረበ መዝሙር ነው እንደማትሉን ተስፋ እናደርጋለን፡፡እ/ር በሴት አንቀጽ ሲመሰገን አይተን ስለማናውቅ፡፡ለቤ/ክ ነው ካላችሁም ዞሮ ዞሮ ምስጋና የሚቀርበው ለእ/ር ብቻ ነው የሚለው መከራከሪያ መፍረሱ አይቀርም፡፡

  ReplyDelete
 9. ስለ እመቤታችን የምስጋና(የመዝሙራት) ምንጮች
  ሀ. ትንቢት፡ ቤ/ክ ዳዊት በመዝ 44 ቁ 16….ለልጅ ልጅ ስምሽን ያሳስባሉ…ሲል የተናገረው ትንቢት እመቤታችን በሉቃ 1 ቁ 48….እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል…ስትል በተናገረችው ቃል ፍጻሜ አግኝቱዋል ብላ ታስተምራለች፡፡የምድራዊቷን ቅ/ኤልሳቤጥ እና የሰማያውይውን ቅ/ገብርኤል ምስጋናም እንዳትረሳው፡፡ይሄው እኛም ለፈጽሞ ትንቢት ሰአሊ ለነ ቅድስት እያልን ስሙዋን እንጠራለን-ለትውልድ እናሳስባለ፡፡የለም፡፡ የዳዊት ትንቢት ለኢየሩሳሌም የተነገረ ነው የሚል ካለም ጌታ ተመላለሰባት ተብሎ ከምትወደሰው ግኡዝ ምድር ጌታን ወልዳ፣ተሰዳ፣አጥብታ፣ከቀራንዮ እስከ ጰራቅሊጦስ ያልተለየቸው ወላዲተ አምላክ ምስጋናም ሲያንሳት ነዋ እንላለን!!
  ለ. ቀደምት አበው፡እነ ቅ/ኤፍሬም፣እነ አባ ህርያቆስ፣እነ ቅ/ያሬድ፣እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣እነ ዮሐንስ አፈወርቅ እረ ስንቱ…..አወድሰዋት፣ቅድስናዋን አማላጅነቱዋን ተናግረው አይጠግቡም፡፡እነዚህ ቅዱሳን ስለ ብሉይና ሐዲስ ያላቸው እውቀት ደግሞ አይጠረጠርም፡፡በምስጋናዋ የሚደረድሩት የነቢያት ትንቢትና አምሳል፣የሐዋርያት ስብከት ምጥቀታቸውን ያሳያል፡፡ትምህርቱን ፈጥረው፣አመንጭተው ሳይሆን ከሐዋርያት ሲወርድ ሲዋረድ እናዳገኙም እናውቃለ፡፡እኛም የእነሱ ልጆች ስለሆንን አርዓያነታቸውን ተከትለን ...ተፈስሂ ኦ ማርያም እም ወአመት-እናትነትን ከአገልጋይነት ያስተባበርሽው ብቸኛዋ እመቤት ሆይ ደስ ይበልሽ… እያልን በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንላታለን፡፡እናወድሳታለን፡፡ሆኖም አናመልካትም!!

  ሐ. ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ እውቅና ከምትሰጣቸው ጉባኤያት መካከል በ431 ዓ.ም 200 ሊቃውንት ተሰብስበው ሁለት አካል፣ ሁለት ባህርይ ባዩን ንስጥሮስን ያወገዙበት ጉባኤ-ኤፌሶን አንዱ ነው፡፡በዚህ ጉባኤ ላይ ንስጥሮስ እመቤታችን የወለደችው መለኮትነት የሌለው ወልድን ብቻ (እሩቅ ብእሲ) እንጅ መለኮት የተዋሀደው ስጋን አይደለም በማለቱ “ታዲያ ሰብዐ ሰገል አምኃ አቅርበው የአምልኮ ስግደት የሰገዱት ለሩቅ ብእሲ ነው እንዴ” ተብሎ ተረታ፡፡የእመቤታችን ወላዲተ-አምላክነትም በጉባኤው ዳግም በአጽንኦት ተነገረ፡፡በመጨረሻም በውሳኔው አንቀጸሃይማኖት “….የእውነተኛ ብርሃን እናት ሆይ እናከብርሻለን፣መጥቶ ነፍሳችንን ያዳነውን የዓለምን ሁሉ መድኃኒት ስለወለድሽልን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆይ እናመሰግንሻለን….” ሲሉ የቀደሙ አባቶችን ትምህርት አጽንተው ከ1500 አመት በፊት በዶግማ ደንግገውልናል!!ዶግማ ደግሞ አይሻሻልም፣አይጨመርበትም፣አይቀነስበትም!!ስለሆነም በመላው ዓለም ይሄን ጉባኤ በሚቀበሉ የምእራብና የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ከሉተራውያን በቀር እመቤታችንን ‘ሰአሊ ለነ ቅድስት’ ሳይል የሚውል ክርስቲያን የለም!!በነገራችን ላይ ደቀመዛሙርቱ እንጅ ሉተር የእመቤታችንን ምስጋና አይቃወምም ነበር፡፡

  ReplyDelete
 10. እመቤታችን ቤዛ፣መድኃኒት መባሏ ያንገበግባችኋል፡፡ሊቃውንት …በስመ ሀዳሪ ይጼዋእ ማኅደር… ይላሉ፡፡ቤት በነዋሪው ይጠራል እንደማለት ነው፡፡እመቤታችንን መድኃኒት ቤዛ ስንላትም እንደዛ ነው፡፡የጌታ ማደሪያ ስለሆነች!!እንደዛ ባይሆንና እሱዋ ቤዛና መድኃኒት ነች ብለን ብናምን ለምን ከጌታ ለምኝልን ማለት አስፈለገ!!ምክንያቱም እሷ መድኃኒት ከሆነች አድኝን እንጅ አማልጅን ማለት አያስፈልገንም፡፡ከዚህ በፊት ጌታን በመርፌ ውስጥ እንዳለ መድኃኒት እመቤታችንን እንደሃኪም፣ጌታን እንደፍሬ እመቤታችንን እንደፍሬው ተሸካሚ ተክል እያደረግን የእሷ መድኃኒት መባል በዛ መልኩ እንደሚገለጽ ተናግረናል፡፡ከፈለጋችሁም ይሄን አንብቡት፡፡የፍጡር መድኃኒት መባል በእሷ አልተጀመረም፡፡ መሳ 3 ቁ 9 እንዲህ ይላል…የእ/ኤል ልጆች ወደ እ/ር ጮሁ፤እ/ርም የሚያድናቸውን “አዳኝ” የካሌብን ታናሽ ወንድሙን ጎቶንያልን አስነሳላቸው፡፡እንጨምር፡- አብድዩ ቁ 21….በዔሳውም ተራራ ላይ ይፈርዱ ዘንድ “አዳኞች” ወደ ጽዮን ተራራ ላይ ይወጣሉ፤መንግሥቱም ለእ/ር ይሆናል፡፡ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች አዳኝ ሲባሉ የመዳን ምክንያት ሆኑ መባላቸው ነው የሚገባን እንጅ እ/ርን ተክተው የማዳን ስራ ይሰራሉ ማለት አይደለም፡፡እኛ እመቤታችንን ቤዛዊተ ዓለም እግዝእትነ ወመድኃኒትነ ስንላትም እንደሱ ማለታችን ነው፡፡በነህ 9 ቁ 27 እና በ2ኛ ነገሥት 13 ቁ 5 እ/ኤልን የሚታደጉ ታዳጊዎች፣አዳኞች ተብለው የተጠቀሱ ግለሰቦች አሉ፡፡እሱን አንብቡት፡፡

  ReplyDelete
 11. Wey Wey Wey!!!!! Tekleyen minew?! tew tew tew!!!!
  Tekleye tselotachew Hayal sile hone sile alem sitseliyu tselotachew semto Geta Ammanuel alem yimiral, yadinal

  ReplyDelete
 12. የማህበረ ቅዱሳን እና የዚህ ድህረ ገጽ ጻሐፍት ልዩነት ቁልጭ ያለ የሃይማኖት ልዩ ነት ሆኖ ሳለ:: በሃሰት የፖለቲካ እና የዘር ወይም ያስተዳደር ልዩነት ለማስመሰል የመፈለግ ሁኔታ ይታያል:: ቢሆንም በዚህ ጹሑፍ የቀረበው ትልቅ የሃይማኖት ልዩነት ነው::ዋሽቶ ፖለቲከኞቹን ምድራውያዊያንን ማታለል :: ግን ባለቤቱን እግዚአብሄርን ከቶ መዋሸት ይቻላል ብላችሁነው:: ይህ ብሎግ የሰይጣን እንጂ የክርስቶስ ቢሆን ለምን ዙሪያ ጥምጥም ይጓዛል::ደግሞ እያወቀ ሸዋ አንኮበር እያለ ይቀባጥራል:: ከሃይማኖት እና ከእግዚአብሄር ፈቀቅ ብላችሁል እና ብትመለሱ ይሻላችሁል

  ReplyDelete
 13. IS this Aba Selama blog Tehadiso? Because you hate yeMariam misgana, you disrespect the saints of God, but your blog name is "Aba Selama"
  Do you know Aba Selama is also a holy saint? St Aba Selama they are equal to Tekle Haymanot, and St Giyorgis. IF you disrespect 1 saint, you disrespect all the saints. So by disrespecting St Giyorgis and denying that he can not save you, and calling the holy book Gedle Tekle Haymont fiction, you have disrespected St Aba Selama the very saint your blog is named after.
  I pray that they will pray for your soul!
  One day Mariam the Queen of Heaven will show you that she can save or destroy you, one day Tekle Haymanot will show you their holy book is not fiction, and St. Giyorgis will show you his power!! Beware!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. No creature (fitur) can create nor destroy? If you claim they have the power to destroy are you also claiming they have the power to create? Lotu sebhat. This is pure blasphemy. But we ask the saints to pray and intercede for us. That is the teaching of orthodoxy since the early century. Nothing more or less so let's keep it at that. God said he's a jealous God in multiple places so God's attributes are his. Also the saints in heaven are pure. They pray for the wicked, the sinners, and all those that rebel against God. They pray for the salvation of the world not for destruction. Even Jesus asks us to pray for those that persecute us so don't give Mother Mary this false deed like she wants to destroy sinners.

   Delete