Wednesday, November 26, 2014

የሃና ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረትን የሚሻ ነው

Read in PDF

በቅርቡ የተከሠተው አስደንጋጭም ዘግናኝም ከሰብኣዊ ፍጡር ፈጽሞ የማይጠበቀውና በሀገራችን የሥነምግባር ዝቅጠት የቱን ያህል እየወረደ መምጣቱን የሚያመለክተው የ16 ዓመቷ ተማሪ የሐና ላላንጎ በአምስት ጎረምሶች በተደጋጋሚ መደፈርና ታዳጊዋን ለኅልፈተ ሕይወት ማዳረጉ የማንኛውንም ሰብኣዊ ፍጡር ልብ ያደማና ወደየት እያመራን ነው ያሰኘ ክሥተት ሆኗል፡፡ በታዳጊዋ ላይ የደረሰው ይህ ዘግናኝ ድርጊት መልካም የሚባሉ ኢትዮጵያዊ እሴቶች ምን ያህል እየተሸረሸሩና በሴቶች ላይ እየተፈጸመ  ያለው ጾታዊ ጥቃት ምን ያህል በዓይነትም በመጠንም በአፈጻጸምም እየከፋ መሄዱን አመላካች ነው፡፡ እህታችን ሀና ከትምህርት ቤትዋ ወደ መኖሪያ ቤትዋ ለመሄድ ከተሳፈረችበት ታክሲ ታግታ ህይወትዋ እስኪጠፋ ድረስ የአስገድዶ መደፈር ወንጀል የተፈጸመባት መኆኑን ማወቅና ማሰብ ለማንም ህሊና ላለው ፍጡር በጣም የሚያስደነግጥ የሚያሳዝንና የሚያሥቆጣም እውነት ነው፡፡
ሀና ለምን ተደፈረች? ምን አይነት ሰብዓዊ ፍጡር ነው የ16 ዓመት ልጅን እንደ እንስሳ ተሰብስቦ የሚደፍረው? ሀገሪቱ የነበሯት እና ህብረተሰቡ በተለምዶ የሚቀበላቸው የሥነ ምግባር ህጎች የት ሄዱ? ሰብዓዊነቱስ እንዴት ጠፋ? የክርስቲያን ደሴት በምትባል ሀገር፣ ክርስቲያን ታዳጊ ወጣት፣ ምናልባትም “ክርስቲያን” ነን በሚሉ ሰዎች እንዴት ልትደፈር ቻለች?  እነዚህ ጥያቄዎች የግድ መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች ናቸው። አሁንም ቢሆን ስለ ሀና መደፈር እና ሞት ግልጽ ያለው እውነት አለመውጣቱና የወንጀሉ መፈጸሚያ ቦታ ነው የተባለው ሺሻ ቤት አለመዘጋቱ ከፍተኛ ግርምትን የሚፈጥር ጉዳይ ሆኗል። ሺሻ ቤቱን ለመዝጋትና የሺሻ ቤቱን ባለቤት በወንጀል ለመጠየቅ መንግስት ከዚህ በላይ ምን ይፈልግ ነበር? የሚያሰኝም ሆኗል። ህብረተሰቡም እንዲህ ያለው ወንጀል ፈጽሞ ፈጽሞ እንዳይደገም ከከንፈር መምጠጥ ባለፈ እያደረገ ያለው ነገር ባለመኖሩ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው። 

ቤተክርስቲያን በዚህ ጉዳይ ላይ እስከዛሬ ድረስ ምንም አለማለትዋ በእውነት በጣም የሚያሳፍር ነው። በትንሹም በትልቁም ጉዳይ በማስታወቂያ ፖስተር ሀገር የሚያጥለቀልቁት የፕሮቴስታንቶቹ  ፓስተሮችም ምንም ሲሉ አልተሰማም። ግለሰቦች በፌስ ቡክ ከሚያደርጉት ጠንካራ እንቅስቃሴ በመለስ ሚዲያውም ቢሆን ከፍ ባለ ቸልተኝነት ተይዟል። በእኛዎቹ ሚዲያዎች ለአንድ ወር ሙሉ በሀና ጉዳይ ተዘገበ የሚባለው ነገር ጋዜጠኞቻችን የእንግሊዝ የሶስተኛ ዲቪዝዮን ኳስን ለመዘገብ የሚያደርጉትን ያህል  እንኳ ትኩረት የተደረገበት አይደለም። ምን እየሆንን ነው? የሀና ጉዳይ ማኅበረሰባችን የደረሰበትን የሥነምግባር ውድቀት ደረጃ የሚያሳይ ነው። በጣም ያሳዝናል። በተለያዩ ሁኔታዎች ስለድርጊቱ የተዘገበውን ስንመለከትና ስንገመግም ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂዎቹ የሃይማኖት ተቋማትና መንግሥት መሆናቸው አይቀርም፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያን ሕዝብ ባህል መልካም ጠባይ ጥሩ የሚባል አኗኗሩን በመቅረጽ ረገድ የተጫወተችው ሚና በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ የዚያኑ ያህል ለአንዳንድ ጎጂና ልማዳዊ ድርጊቶች መስፋፋት ተጠያቂ መሆኗ ሳይዘነጋ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኗ ሕዝቡ በክርስቶስ ወንጌል የታደሰ ሕይወት እንዳይኖረውና በልማዳዊውና ሰውን ለእውነተኛ ለውጥ በማያዘጋጀው ልማዳዊ ትምህርትና ተረታ ተረት ተብትባ መያዟ ለዘመኑ አለመመጠኑንና ለብዙ ምግባረ ብልሹ ሕይወቶች የሚያጋልጡ አስነዋሪ ልምምዶች ሰፊ በር ለተከፈተለት ለወጣቱ ትውልድ የሚረዳ አለመሆኑ ቤተክርስቲያኗ ዘመኑን እየዋጀች ላለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኗ ያለፈ ታሪኳንና በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ላይ ቆሞ ያልተጣራውን ትምህርቷን እንዳለ እንዲቀጥል የምታደርገው ከንቱ ድካም የተሳካ ካለመሆኑም በላይ በርካታ ተከታዮቿን በየጊዜው እያሳጣት ይገኛል፡፡ ቤተክርስቲያኗ የሀገሪቱን መንፈሳዊና ሞራላዊ ሥነምግባሮችን ስትቀርጽ የኖረችና እንደመሆኗ እንዲህ ያለው የውሾች ተግባር ሲፈጸም መስማት ትልቅ ውድቀት ነውና በአንድም በሌላም መንገድ ተጠያቂ መሆኗ አይቀርም፡፡
ለዚህ መፍትሔ ሊሆን የሚችለው ሕዝበ ክርስቲያኑ በወንጌል ቃል እውነተኛ የሕይወት ተሐድሶ እንዲያመጣ ማድረግ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኗ ግን እስካሁን ድረስ ለስብከተ ወንጌል የሰጠችው ትኩረት እጅግ አናሳ ከመሆኑም በላይ ወንጌል ብላ የምትሰብከው ወንጌል አለመሆኑና በሰው ሕይወት ላይ ትክክለኛውን የሕይወት ተሐድሶ የማያመጣ ሞራላዊ ትምህርት ብቻ መሆኑ በገሃድ የሚታይ ሐቅ ነው፡፡ ስለዚህ ሰውን ከተሰቀለለት አዳኙ ጋር በማገናኘት የሕይወት ለውጥ እንዲያመጣ ማድረግ ይጠበቅባታል። አሊያ እንደዚህ ያሉና ከዚህ የከፉ ዜናዎችን መስማታችን ይቀጥላል፡፡

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳትሆን የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትም እየደረሰ ላለው ለእንደዚህ ዓይነቱ ዘግናኝ ድርጊት ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ከጥቂቶች በቀር ዛሬ ብዙኃኑ ወንጌልን መስበክ ትተዋል፡፡ ይልቁንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወንጌልን ሳይሆን ብልጽግናን፣ የተቀሰለውንና ዳግም የሚመጣውን ክርስቶስን ሳይሆን ምድራዊ ኑሮን እያሻሻለ እዚህ ዓለም ላይ እያንደላቀቀ የሚያኖረውን “ክርስቶስን” እየሰበኩ ያሉ በርካቶች ሰውን ወደ ክርስቶስ ሳይሆን ወደተንደላቀቀ ምድራዊ ኑሮ እየጋበዙት ስለሆነና ትበለጽጋለህ በሚል ስብከት የእርሱን ኪስ የማራቆቱን ሥራ ስለቀጠሉበት ዛሬ በብዙዎቹ ዘንድ የእውነተኛው ክርስትና መልክ ጠፍቷል፡፡ በቦታውም ምድራዊነትና ዓለማዊነት ተንሰራፍቷል፡፡ በዚህ መንገድ እየተሰበከ ያለው የብልጽግና ወንጌልም ሰውን እንዲህ ላለው ልቅና መረን ለወጣ ምግባረ ብልሹነት ላለማጋለጡ ምንም ዋስትና የለም፡፡ እዚህ ላይ ሕዝባችን ሠርቶ መለወጥና መበልጸግ ያለበት በመሆኑ ላይ ምንም ጥያቄ የለንም፡፡ ነገር ግን የተሰቀለውን ክርስቶስንና የመስቀሉን መንገድ ወደጎን በመተውና ለዚህ ዓለም በሚመች ዓለማዊ ኑሮ ውስጥ በመዘፈቅ የሚሆን አይደለም፡፡ ስለዚህ ወንጌላውያን መጠሪያቸው ያደረጉትን ወንጌልን ከጣሉበት ሊያነሡ፣ የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ ሊሰብኩ፣ ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲሆንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥነ ምግባርን ተግተው ሊያስተምሩ ይገባል፡፡ አሊያ ሊያፈሩ የሚችሉት ሐናን በአሰቃቂ ሁኔታ የደፈሩትን ጎረምሶች የመሰለ ትውልድ ይሆናል፡፡
በታዳጊ ሐና ላይ ለደረሰው ለዚህ አሠቃቂና አስነዋሪ ድርጊት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በላይ በዋናነት መንግሥት ተጠያቂ ነው፡፡ መንግሥት ለዜጎቹ ጥበቃና ዋስትና መስጠት አለበት፡፡ በተለይም እንዲህ ዓይነቱ አስነዋሪ ድርጊት በሚፈጸምባቸው በት/ቤቶች አካባቢ ለዚህ ችግር የሚያጋልጡ መጠጥ፣ ሺሻና ጫት ቤቶችን መዝጋት ሲገባው እንዲህ ያሉ ችግሮች ሲፈጠሩ ብቻ ጥቂት እንቅስቃሴ አድርጎ በኋላ ተወት ማድረጉ ለችግሩ መባባስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ዛሬ ወደ ሚዲያ ያልወጡና የዚህ ችግር ሰለባ የሆኑ እጅግ በርካቶች መኖራቸው አይካድም፡፡ እነዚህ ምግባረ ብልሹነት የሚስፋፋባቸው ቦታዎች ከትምህርት ቤት አካባቢ እንዲወገዱ ማድረግ መሠረታዊው ነገር መሆን አለበት፡፡ በሐና ላይ ይህን ዘግናኝ ድርጊት የፈጸሙትን ወንጀለኞችም ሌላውን ሊያስተምር የሚችል ቅጣት መቅጣት ተገቢነት ይኖረዋል፡፡ ችግሩ በታዳጊ ሴቶች ላይ ብቻም ሳይሆን በወንዶችም ላይ እየደረሰ ስለሆነ በተለይ በግብረ ሰዶማውያንና በግብረ ሰዶም ላይ መንግሥት አቋሙን ማለሳለስ የለበትም፡፡ ሕግኑ ማጥበቅ እንጂ ማላለት እንደዚህ ላሉት ወንጀሎች በር የሚከፍት በመሆኑ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንና መልካም ስነ ምግባራችን ተጠብቆ እንዲቀጥል ማድረግ ከሁሉም ይጠበቃል እንላለን፡፡         

15 comments:

 1. በጣም በጣም በጣም ያሳዝናል። ይህ ግፍ ነው። ዝም ሊባል አይገባውም

  ReplyDelete
 2. what a shameful act. i do really sorry for this. so sorry

  ReplyDelete
 3. ብላችሁ ነው??
  1--ኦርቶዶክስን ካለወቀሳችሁ መቼም አይሆንላችሁ፡፡መጀመሪያ ነገር ይሄ ወንጌልን የመስበክና ያለመስበክ ችግር ነው ብሎ ለመደምደም መፋጠን ትክክል አይደለም፡፡ስንትና ስንት በወንጌሉ ተመራመሩ የምንላቸው የካቶሊክ መነኮሳት ከህጻናት ጋር ግብረሰዶም ፈጸሙ ሲባል በተደጋጋሚ ሰምተናል፡፡ፕሮቴስታንትም በወንጌል እየማለ ነው አሜሪካና አውሮፓ ላይ በየአዳራሹ ተመሳሳይ ጾታ ቃልኪዳን አጋብቶ መዳር የጀመረው፡፡
  2--እናንተ ተረት-ተረት የምትሉዋቸው የቅዱሳን ገድላትና ድርሳናት አንድ ህጻን ለ5 ሆኖ ስለመድፈር ሳይሆን ጭራሹን ዓለምን ንቆ፣ከፍትወት ርቆ መኖርን የሚሰብኩ ናቸው፡፡ወደግራም ወደቀኝም ብትተረጉሟቸው ሀና ላይ ለደረሰው ሰቆቃ ገድላቱ፣ተአምራቱ፣ድርሳናቱ ተጠያቂ የሚሆኑበት እድል የለም፡፡
  3--ኦርዶክሳዊነት ከነስብከቱና ትውፊቱ በገነነበት የሀገሪቱ ማእከላዊና ሰሜናዊ ክፍል እንዲህ አይነት ወንጀል ሲፈጸም አልተመለከትንም፡፡እረ ቤ/ክ ከጋብቻ በፊት ፈቃደሥጋን መፈጸምም ሆነ ከአንድ በላይ ማግባትን/ዝሙት መፈጸምን/ ከማውገዝ አልሰነፈችም፡፡ልጆቿ በሥርዓተ - ተክሊል ብቻ ተወስነው ትዳራቸውን የሰመረ እንዲያደርጉ ከመወትወት አልቦዘነችም፡፡
  4--እንዲህ የሴት መብት ተጠበቀ ተብሎ ብዙ ከመወራቱ በፊት በነበረው ጊዜ ይህን የመሰለ ሰቆቃ ያልሰማነው ሕዝቡ ለእናንተ ተረት በሚመስለው ለእኛ ግን አርአያ - ቅዱሳንን ለመከተል ያገዘን ዜና - ቅዱሳን የሕዝቡን ሞራል በመቅረጽ ረገድ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ስለነበረው ነው፡፡ከሁሉም ይጠበቃል የምትሉት ኢ/ዊ እሴትና መልካም ሥነ - ምግባር ዋና ቀራጺዋ ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ መሆኗን አትርሱ!!
  5--ስለዚህ ጥቃቅን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ባያችሁ ቁጥር አጓጉል ቅድስት ቤ/ክ ላይ እጃችሁን በመቀሰር የተጠርጣሪዎችን ድርጊት ከማለባበስ ከመሞከር እንደ ቀደምት ኦርቶዶክሳውያን አሰረ - ቅዱሳንን ተከትለን በምግባር እንጽና በሉ፡፡ወይም ፕሮቴስታንቲዝም በስፋት አጥለቅልቆት አርአያነት ያለውና ከእኛ የተሻለ ሞራላዊ ማኅበረሰብ የገነባ ሀገር አሳዩንና እንመናችሁ!!
  6--ተውኝማ!! በዛሬው ስልጡን ዓለም ትውልድን ክፉና ደግ አድርጎ በመቅረጽ በኩል ሃይማኖት ያለው ተጽእኖ ብዙ ጊዜ ጉልህ ሆኖ አልታይህ ይለኛል፡፡በጥቅሉ ሃይማኖት በተማረውና በከተሜው የማኅበረሰብ ክፍል ያለው ተጽእኖ የይስሙላ እና የታይታ ብቻ ይሆንብኛል፡፡ሁለቱን ኃይላት በእምነት ጥብቀት ረገድ እጠረጥራቸዋለሁ፤አላምናቸውም፡፡ከእምነት ይልቅ ለአመክንዮ ነው የምንንበረከከው፡፡ለዚህ ይመስለኛል የሚምታታብን--የሰላማ ጸሐፍት በመ/ቅዱስም ሆነ በቤተ - ፕሮቴስታንት ከሚነገሩት ተአምራት የተለየ የሎጂክ ሚዛን በመጠቀም የገድልና ድርሳንን ተአምራት በሎጂክ ለመተንተን እንደሚሞክሩት--ነቃሁ የሚለው ትውልድ እንዲያ ይሆንብኛል፡፡ከእምነት ይልቅ ሎጂክ በ‘ይሆናል አይሆንም’ የጥርጣሬ ትንተና ድክመትን ለመሸፈን ብዙ ቀዳዳ አለው!!
  7--ለማንኛውም፡- ሃይማኖት ባያገናኘን እንኳ ሰብአዊነት ሊያስተሳስረን ይገባል!!የሐናን መጠቃት ለማውገዝ የግድ በአንድ ሃይማኖታዊ ቦታ መሰባሰብ አይጠበቅብንም--ሰው መሆናችን በቂ ነው!!ስለሆነም ከዘወትራዊ ዐላማችሁ ተነስታችሁ ወንጌሉን ተርጉማ ያቆየቻችሁን ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክንን በኢ-ወንጌላዊነት አጓጉል ለመኮነን ከሄዳችሁበት መንገድ በመለስ ያለውን ጥሪያችሁን በበጎ ነው የምቀበለው፡፡አማንያን መሆን ቢያቅተን እንኳ ከሰብአዊነት አንውረድ!!ሰው እንሁን!!
  እስኪ የልጅቷን ነፍስ ይማር!!ለቋሚዎችም ልብ ይስጠን!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hiruy thank you so much for addressing my thoughts!!! May God bless you!!!

   Delete
 4. ወንድሜ አዎ የምትሉትን እንረዳለን እኛን የቀደመውን ተረታ ተረት ብላችሁ የራሳችሁን ተረት ልትግቱን መሞከራችሁ ግን ከናንተ ቀድመን እንገነዘባለን ለዚህም አንድ ማሳያ ላንሳ አባቶቻችን የሰሩልንን ጸሎት ትተን የእንናንተን ተንስኡ እንድንጸልይ መሞከራችሁን እናውቃለን፡፡ እንዲየው ለነገሩ አልኩኝ እንጂ እናንተም ከዚህ የኃጢዓት ጭቃ ያልወጣችሁ ተሳዳቢዎችና አላዋቂ ሆናችሁ ሳለ እኛን ስለ ጌታ ለመንገር ምን ብቃትና እውቀትና ቅድስና አላችሁ፡፡ ሰውስ ከማን እንዲማር ትጠብቃላችሁ፡፡ እናንተስ ምን ሰራችሁ፡፡

  ReplyDelete
 5. የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳትሆን የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትም እየደረሰ ላለው ለእንደዚህ ዓይነቱ ዘግናኝ ድርጊት ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ከጥቂቶች በቀር ዛሬ ብዙኃኑ ወንጌልን መስበክ ትተዋል፡፡ .. ከጥቂቶች???

  ReplyDelete
 6. በሀና እምባ ለምን ሠይጣ መጣ? የትኛውም ወንጀል ሀጢያት ነው።ወንጀል በነፍስም በስጋም ያሥጠይቃል። እህታችን ሀና የደረሰባት አሳዛኝና ልብን የሚሰብር ወ
  ንጀል ነው።ይህ የእንስሳነት ድርጊት በማንም የተወገዘ
  ነው። የሐይማኖት ተቋማት ድርጊቱን ከማቃወምና
  መንግስት ወንጀለኞችን እንዲቀጣ ከመጠየቅ ውጭ ሌላ
  ምንማድረግ ይችላሉ?ነገር ግን የአባ ሰላቢ ብሎግና
  ጀሌዎቹ እዚህም እዚያም ሲረግጡ ይታያሉ።ዛሬ ደግሞ
  በሀና ሽፍና የተለመደውን አባታቸውን የዲያብሎስን
  የከሣሽነት ካርድ መዘው ብቅ ብለዋል። ይሁዳ አምላኩን
  አሳልፎ ለመስጠት የተነሣው ለድሆች አዛኝ መስሎ ነበር።
  አባ ሠላቢዎችም ለሀና ያዘኑ በመምሰል የለመዱትን
  ቤተክርስቲያንን መተቸትና መክሰስ ቀጥለዋል።እኔ
  ስለሌሎች የእምነት ድርጅቶች መናገር አልፈልግም።ነገር
  ግን ክርስቶሥ በደሙ በመሰረታት ቤተክርስቲያን ላይ ይህ
  ብሎግና ጀሌዎቹ ለሠነዘሩት ትችትና ክህደት ግን ጥቂት
  ማለት ተገቢ ነው ክርስቶሥ በሥጋ በዚህ አለም በተመላለሰበት ዘመን አይሁድና ፈርሳዊያን ለኢየሱስ
  ክርስቶሥ የአብርሀም ልጆች ነን አሉት ።ጌታ ኢየሱስም
  አላቸው "የአብርሀም ልጆች ብትሆኑስ የአብርሀም እምነትና
  ሥራ በኖራችሁ ነበር" አላቸው። አባ ሠላቢዎች የኦርቶዶክስ
  ተዋህዶ እምነትና ሥራ እንዲሁም የአምልኮ ሥርዓት
  ሳይኖራቸውና ሳይተገብሩ ቤተክርስቲያንን በመጥራት ልጆቿ ለመምሠል ይሞክራሉ።አይሁድ ክርስቶስን
  በመስቀል ላይ ሠቅለው ከመግደላቸው በፊት ነቢያቱን
  ሲቃወሙ ሲያሳድዱና ሲገሉ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ
  ይመሠክራል።ዛሬ ሠላቢዎችና አጋሮቻቸው ኦርቶዶክስ
  ተዋህዶን ያሣድዷት ይቃወሟትና ይገሏታል።ይህ ሁሉ
  የጠላት የውጊያ ቀስት የሚወረወርባት ለእውነት በመቆሟ
  ነው።እስቲ በጥቂቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቷን
  እንመልከት። አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ።ከባኸሪ
  አባቱ ከአብና ከባኸሪ ህይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ሣየለይ
  በአምላክነት ትክክል ምንም ያልጎደለበት ፍፁም አምላክ
  ነው ብላ አምና የተቀበለችና የምታስተምር ናት።ልጆቿንም
  ፈጣሪየቸውን እንዲፈሩና ሀጢያትን እዳይሰሩ ታስተምራለች። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት መጽሐፍ
  ቅዱስን የያዘቸው እውነትን ለመመስከርና ከአባቶቿ
  እንደተማረችው እራስን ዝቅ በማድረግ ትህትናንና መልካም
  ምግባርን በመልበስ ለመዳንና ለሕይወት ነው። ወንጌልን
  የምታስተምረው በመሸንገልና በማቫበል እንዲሁም በከንቱ
  የቃላት ውጊያ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ አስተማሪነትና
  ገላጭነት የእግዚአብሔርን ቃል አለም እንዲሰማና አምኖ
  እንዲድን በመገሠፅ ነው።በሥነምግባር ትምህርቷም
  ክርስቲያኖችን ለሀጢየትና ለፈተና ከሚያጋልጡ
  እንቅሥቃሴወችና አዋዋሎች እንዲታቀቡ
  ታሥተምራለች።ለምሣሌ የተቃራኒ ጾታዎች ቅርርብ
  እንዴትና ምን መምሠል እንዳለበት፣ በእንዴት ባሉ
  ቦታዎች መገኘትና አለመገኘት እንዳለባቸው እንዲሁም
  ከማን ጋር መዋልና መቀራረብ እደሚገባቸውና ሌሎችንም
  በመልካም ሥነምግባር ሊታነፁባቸውና እራሳቸውን
  ከጥቃትና ከፈተና ነፃ የሚያደርጉበትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ
  የሥነምግባር ትምህርቶችን ትሰጣለች።ትምህርቷን
  ተቀብሎ መተግበር የእያንዳዱ የመብት ግዴታ እንጂ
  የቤተክርስቲያን ችግር አይደለም።ለመዳን የተጠሩት
  ብዙዎች ሆነው ሳለ የመጡት ግን ጥቂቶች ናቸውና
  ክርስቶስ አልጠራቸውም ተብሎ ሊወቀሥና ሊተች ነው?እረ
  በፍፁም ጥሪውን ተቀብሎ መምጣትና የመዳንን ተግባር
  መፈፀም የተጠሪው ምርጫና ውሳኔ ነው።እንደዚሁም ሁሉ
  ቤተክርስቲያን እውነትን እየመሰከረች አለም ክፉ ተግባሩን
  እንዲተው ትመከር ታሥተምራለች እንዲሁም ትገሥፃለች
  ይኸንን ሠምቶ መፈፀም ግን የሰሚዎቹ ምርጫና ውሳኔ
  ነው።መጽሐፍ ቅዱሥ እንዲህ ይላል"እሳትና ውሀ
  ቀርቦልሀል ወደ ወደድከውና ወደ ፈቀድከው እጅህን ላክ"
  ሲል የምርጫንና የነፃ ፈቃድን ውሣኔ ለሠውለጅ መሠጠቱን ይነግረናል።ሥለዚ ቤተክርሥቲያን መልካሙ ምግባረ ይሄ
  ነው ይሄንም ብትፈጽሙ የመዳንን አክሊል ትሸለማላችሁ
  ነገር ግን ክፉዉን ሥራና ምግባርን የምትመርጡና
  የምተሠሩ ከሆነ ግን ፍርድ ይጠብቃችኇል እሡም
  የሀጢያት ፍርድ የዘላለም ሞት ነው እያለች እሥከ ምፃት
  ታሥትምርና ትገሥፃለች።አባ ሠላቢዎችና ጀሌዎቻቸው
  እንዲሁም መሠሎቻቸው ግን መጽሐፍ ቅዱስን የተሸከሙት ወደ እውነት ቀርበው ለመዳንና በክርስትና ለመኖር ሳይሆን
  ለጥፋታቸወና ለማታለያነትይዘውታል። መጽሐፍ ቅዱስ
  "ሠይጣን የብርሀን መላዕክት ለመምሠል እራሡን
  ይለውጣል" ይላል። እራሱንም የሚለውጠው እሡ
  የእግዚአብሔር መላዕክ ሆኖ ሳየሆን መስሎ
  የእግዚአብሔር የሆኑትን ለማጥመድና ከእውነት
  ስፍራ አውጥቶ ለመጣል ነው።እደዚሁ አባ ሠላቢዎችና
  መሠሎቻቸው መጽሐፍ ቅዱሥን ታቅፈው በግብዝነት
  ለመታየት የሚሞክሩት እውነትን አውቀው የክርስቶስ
  የወንጌል ፍቅር ልባቸውን ፈንቅሏቸው ህይወት
  ለማግኘትና ለመዳን ሳይሆን ከክፉዉ የተማሩትን
  የማስመሠል ተንኮል መሠረት አድርገው እውነተኞችን የክርሥቶሥ ወንጌል ሰባክያንን በመምሠል በቃላት ውጊያ
  እውነተኛ አገልጋዬችን ለመቃወምና በክርስቶስ ያመኑትን
  ለመዋጋትና ለማታለል እንጅ አምነው የቃሉ ሙላት
  በውስጣቸው ኖሮና ሚሥጢሩ ተገልፆላቸው ለመዳን
  አይደለም።ማንነታቸውና አላማቸውም በተግባራቸውና
  በምግባራቸው የተገለፀና የታወቀ ነው።ይኸውም ሁሌም
  እውነትን መቃወም ከሳሽነት፣የዘረኝነት አሥተሣሠብንና
  ዘረኝነትን በክርሥትና ሥም በማንፀባረቅ የክርስቶሥን
  ህዝቦቸ መለያየት እና ሌሎች የክፋት ተግዳሮችን
  በመፈፀም ነው።ሁልጊዜም በቁራ ጩኸታቸው አለም
  እራሱን እንዲፈትሽና በተሠበረ ልብ እንደባቶቹ እኔ
  ምናምንቴ ነኝ እያለ ራሱን ዝቅ በማድረግ የእግዚአብሔር
  መንግሥትን እንዲያገኝ ሳይሆን በሚያባብል የቃላት ውጊያ
  አለሙ ክርሥቶሥን ሳያምንና በእውነተኛው የክርሥትና
  መንገድ ሳይቆሙ እኔ በክርስቶስ ፀድቂያለሁኝና ንሥሀ
  አያሥፈልገኝም ፆም አያሥፈልግምና ሌሎች የእምነት
  ሥራዎችን መተግበርና ሥርዓትና ህግ እንዲሁም የቅዱሳን
  ምልጃ አያሥፈልጉም ብለው እዲስቱ ያደርጋሉ።ኢየሱስ
  ኢየሱስ በማለት መዳን እንደማይቻል ሁሉ በክርስቶስ
  ፀድቂለሁ በማለትም መፅደቅም ፃድቅ ነኝ ማለትም
  አይቻልም።ዛሬ ለአለማችን በክፋ የሥነምግባር ዝቅጠት
  መገኘት ምክንያቱ የአባ ሠላቢዎችና ጀሌዎቻቸው
  ትውልዱ ፈጣሪውን ፈርቶ በእምነት ከእኔ ወንድሜ
  ይበልጣል ብሎ እንዳያስብ የእምነት ፍሬወችን ሳይዝ
  በክፉ መንፈስ ሙላት ተሸብቦ እንዲያብጥና እራሱን
  ባላገኘው ደረጃ እንዲሠቅል በሚያደርጉት የቁራ
  ጩኸታቸው ነው።ዛሬ በነ አባ ሠላቢና ጀሌወቻቸው ልብና
  አይምሮ ሀጢያትን ከመለማመዳቸው የተነሳ ፅድቅ
  አድርገውት ይገኛሉ።

  ReplyDelete
 7. ተናግረህ ሞተሃል፡፡ የክርስቲያን ደሴት ምናምን እያላችሁ በየአደባባዩ የምትቀባጥሩት እንደዚህ አይነት ማህበረ ሰብ እየጠፈጠረ ባለበት አገር ነዉና ወንጌል ይሰበክ ገድል መተረክ ይብቃ ስለተባለ ለምን ከፋህ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውነት እንናገርDecember 11, 2014 at 6:07 PM

   ወንጌል ያለ ገድል አልተሰበከም ወንድሜ።ክርስቶስን ወንጌል(ክርስቶስን) በብዙ መከራ ወይም ተጋድሎ ለእናንተ እንናገራለን እንደተባለ አትዘንጋ።ስለዚህ ቤተክርስቲያን ወንጌልን ስታስተምር የቅዱሳኑን የእምነት ጽናት ተጋድሎ ልጆቿ በእምነት ጸንተው እንዲቆሙና ፈተናን ሁሉ ስለክርስቶስ በእምነት ተጋድሎ ተግበው መጋደል እንዳለባቸው የቅዱሳኑን የእምነት ጽናት በጋደሎ ትነግር ታዘክራለች።በመጽሐፍ ቅዱስ "እሩጫየን ጨርሻለሁ መልካሙን ገድልም ተጋድያለሁ የክብር አክሊልም ተዘጋጅቶልኛል" ሲል የእምነት ገድል እንዳለ ይናገራል። መናፍቃንና ፕሮንቴንታሶች በክርስቶስ በማመን የሚፈፀሙትን የእምነት ተግባሮችን ወይም ሥራዎችን የሚቃወሙት የሠውንና የእግዚአብሔርን ነገር ሥለ ማያሥተውሉና ሥለማይረዱ ነው።ወንድሜም ሆንክ እህቴ የክርስቲያን ደሴት ምናምን ትላላችሁ ብለህ(ሽ) ያጣጣልኸው(ሽው) ባዶ አላዋቂና እምነት አልባነታችሁን ያመለክታል።ታዲያ የቢልግህራም ወይሥ የቦንኬ ሀገር ነው የክርስቲያን ደሴት?የሐጢያትና የአህዛም መፍለቂያና መፈጠሪያ የነቦንኬ የነቢልግራህም የነፓስተር ቾዎ እና የመሠሎቻቸው ሀገር አይደለምን?እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ እውነት ያናግራችሁ።

   Delete
  2. አገርህ ከነቦንኬ ሀገር በሚመጣ ስንዴና ርዳታ ህዝቦቿን እንደምትመግብ ዘነጋኸዉ እንዴ? በአሁኑ ወቅት ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ወደ አሜሪካ የመኼድ እድል ቢያገኝ የሚያቅማማ የሚኖር ይመስልሃል? ተረት ከመተረክ እዉነቱን መናገር አይሻልምን? ሃና አሜሪካ ብትሆን ተጠልፋ በአምስት ሰዎች ትደፈር ነበር ብለህ ትገምታለህ?

   Delete
  3. ስንዴ መለመንን ከምግባር ምን አገናኘው??ለማንኛውም የአሜሪካው መፍቀሬ ፕሮቴስታንት ወንድማችን የአሜሪካንን ጉድ በዚህ http://en.wikipedia.org/wiki/Rape_statistics በኩል ግባና እየው፡፡ “A 2011 report on prison rape by the BJS stated that "in 2008 there were at least 69,800 inmates who were raped under conditions involving force or threat of force, and more than 216,600 total victims of sexual abuse, in America’s prisons, jails, and juvenile detention centers."[265]
   The majority of rapes in the United States go unreported. The FBI recorded 85,593 rapes in 2010, while the Centers for Disease Control counted nearly 1.3 million incidents in that same year.[266]
   Data on the prevalence of rape vary greatly depending on what definition of rape is used. According to the National Violence Against Women Survey, 1 in 6 U.S. women and 1 in 33 U.S. men has experienced an attempted or completed rape in her or his lifetime.[267] A 2007 study by the National Institute of Justice found that 19.0% of college women and 6.1% of college men experienced either rape or attempted rape since entering college.”
   ሲል ታገኝዋለህ፡፡በበላህበት አትጩህ፡፡መጋቢዎችህም ይታዘቡሃል፡፡ወንድ ከሴት ሲደፈርባት የሚውለው አሜሪካ ገበናም የላት፡፡ከፈለክ ጎግልን አስሰው፡፡ተታለህ አታታለን፡፡

   Delete
  4. ይኼ ጎንበስ ጎንበስ እቃ ለማንሳት ነዉ አሉ፡፡ አንተ አገርህ የክርሲቲያን ደሴት ነች ብለህ የምታምን ከሆነ ለምን ያንን በማስረጃ አስደግፈህ አትነግረንም? መጽሐፍ ቅዱስ
   መዝሙረ ዳዊት
   37፥25 ላይ "ጐለመስሁ አረጀሁም ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።"ይላል፡፡ የአንተ አገር አንተ እንደምትለዉ የክርስቲያን ደሴት ከሆነች ለምን የአለም ጭራ ሆነች? አሜሪካም እኮ ከሌሎች አገሮች ለሄዱ ስደተኞች ማረፊያ በመሆኗ የገጠማት ተግዳሮት እንጅ በገንዘባቸዉ ላይ ሳይቀር We Trust in God ብለዉ ለአለም እዉነተኛ ክርሲቲያን መሆናቸዉን የሰበኩ ህዝቦች ናቸዉ፡፡ እዉነተኛ ክርስትና ያለዉ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ብቻ ነዉ ብለህ የምታስብ ከሆነ እሱ ያንተ ችግር ነዉ፡፡

   Delete
 8. ውድ anonymous በመጀመሪያ ስለመብል አይደለም ጽሑፉ የተጻፈው። የአሥተያየት መልሱን የፃፍኩት የክርስቶስን ወንጌል የሰበኩትን የቅዱሳኑን የእምነት ጽናት ተጋድሎን ለሚያጣጥለውና የክርስቲያን ደሴት ምናምን ትላላችሁ ተብሎ ያላዋቂ ከስተያየት ነው። ውድ anonymous ሥለሚጠፋና ቆሻሻ ሆኖ ሥለሚወጣ መብል ከምትዘባርቅ የጻፍኩትን ሀሳብ ተረድተህ የራስህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ ካለህ ባቀረብክ ነበር። ነገር ግን ፍየል ወዲያ ቅጠል ወዲህ ሆነና ሌላ መቀባጠር ጀመርህ። በእርግጥ ከዋናው ፅንሰሐሳብ በመውጣት ለማምለጥ መሞከርና ማምታታት የዲያቢሎስና የመናፍቃን መገለጫ ነው። ይህን የሚያደርጉትም ሠይጣን እውነትን እዳይረዱና እንዳያሥተውሉ ልባቸውን እያወከ አምሯቸውን በብዙ ነገሮች ወጥሮ አስጨንቆ ከዋናው መስመር እዲወጡ ሥለሚያደርጋቸው ነው። ውድ anonymous አንተ ሀገሬ ከቦንኬ አገር የመጣ ስንዴ እንደምትቀበል ተናግረሀል። አገሬ ሥንዴ ከቦንኬ አገር ሥለተቀበለች ቦንኬም ሀገሩም የጥሩ ሥነምግባር መገለጫም ሆነ የክርሥትና ምድር መሆን አይችሉም አይደሉምም። እንዳንተ አገላለጽማ ከሆነ ዮሴፍ በግብፅ ሳለ የግብፅ ምድር በምግ ተንበሻብሸው ነበርና ፈርኦንና ሀገሩ እግዚአብሔርን ያመልኩ ነበርን? እረ በፍፁም አልነበሩም። እንዲያውም ጣወት አምላኪዎች እስራኤላዊያኑንም በግፍ ይረግጧቸውና ወንድ ልጂ ከተፀነሠም እንዳይወለድ ይገሉ የነበሩ ናቸው። ታዲያ ቦንኬ የመላባችሁን የሁከት መንፈስ ምንነት መግለፅና መተርጎም የማይችል ምድራዊ ሀብት እሡና ሀገሩ ሥላካበቱ ከዛም ሥንዴ ሥለሠጡ ክርሥቲያንና የክርሥትና ደሴት መሆን ይችላሉን? እረ በእንዲህ አይነት የወረደ በሆድ አደር አሥተሳሰብ አይሆንም። ውድ anonymous ሰው ሁሉ አሜሪካ ቢሔድ ይመርጣል ላልከው ይሄን በምን ያክል እሥታቲክሥ እንዳጠናኸው የምታውቀው አንተ ብትሆንም ሠው ሁሉ አሜሪካ ለመሄድ የመረጠው ክርስትናን ፍለጋ ሳይሆን በአንድ እውነታ ነው እሱም
  ምድራዊ ምግብ ፍለጋ ነው። ገንዘብና የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ደግሞ አሜሪካ ብቻ ሳይሆን አረብ ሀገርም ይሠደዳሉ። ውድ anonymous ሌላው በደም መጣጮች የተቀጠፈችውን እህታችንን ሀናን አንስተሀል። ሀናን የቀጠፏት ሠዎች በምድር ባይቀጡ እንሿን በሠማይ የሀና ደም እንደ አቤል ደም በእግዚአብሔር ፊት አቤት እያለች ትጮሀለችና ዘማዊዎቹ በእግዚአብሔር ፍርድ ይቀጣሉ። እኛም ሥለሀና አቤት እንላለን ምድራዊ ንጉስ ባይሠማ ሠማያዊው ንጉሥ እንዲሠማና ለሀና ገነትን እንዲሰጥልንና ዐማዊዎችንም ከዝሙት ወንጀል እንዲገላግላቸው። ሀና አሜሪካ ብትሆን ተጠልፋ ለአምስት ትደፈር ነበር ብለህ ትገምታለህ ብለህ የግምት ጥያቄ አንተሀል። አንተ የት እንደምትኖር አላውቅም። አሜሪካ ነህ እንዳልልም አሜሪካ በየዕለቱ ምን እንደሚካሄድ የምታውቅም የምትሠማም አትመሥልም። ጠልፎም ሆነ አሥገድዶ ለአንድም ይሁን ለአሥር መድፈር ሁሉም ሀጢያትና ወንጀል ናቸው። በአንድና በብዙ መደፈር ልዮነት አላቸው ከተባለም በብዙ የተደፈረችውን ሕይወቷን እሥከመቅጠፍ የሚያደርሥ ወንጀል መሆኑ ነው። እናም ውድ anonymous አሜሪካ የብዙ ወንጀሎች መተግበሪያ ብዙ ሕይወቶች የሚጠፉባት ምድር ናት። አልሠማህም ወይም ከአሜሪካ የራቅ ሆነህ ነው እንጅ ሶስት ወጣት ታዳጊ ሴቶችን አባታቸው ወይም አያታቸው የሚሆን ግለሠብ ጠልፎ የቤቱ ቤዝመንት ቆልፎ ሁሉንም አስገድዶ የደፈረና ያሥረገዘ አንዷ እዛው የወለደች በመጨረሻ በፖሊስ ክትትል ሠውየው እሥር ቤት ልጆቹ ከደረሠባቸው መደፈር ጋር ነፃ ወጥተው ከቤተሠቦቻቸው እንደተቀላቀሉ አታውቅምን? አሜሪካ ህጋቸው የጠነከረ ቢሆንም ብዙ የሥነምግባር ወንጀሎች አሥገድዶ መድፈርን ጨምሮ የሚፈፀምባት ምድር ናት። ውድ anonymous በጨለምተኝነት ከመወንጀልና ከመፃፍ ወጥተህ በሚዛናዊነት ብትፅፍ መልካም ነው። ሥንዴ ሰባ ሰሰጡህ ማንነትህንና ንፁህ እምነትህን አሥጥለው በእነሱ ምድራዊ ፍልስፍና አውረውህ እንደሆነ ካላወቅህ እኔ ዛሬ ላሳውቅህ። እስቲ አንተ ለነሡ የሠጠሀቸው እነሱም ካንተ የወሠዱትን ንገረኝ? ምን እውነት ቢኖርህ ምን የፈጠራ ችሎታ ቢኖርህ አንተን ከሥር አድርገው አጎብዳጅ ሆነህ ያሉህን ብቻ የምትቀበል ነው የሚያደርጉህ። ውድ anonymous እራስህን ሆነህ ብትገኝ መልካም ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሚዛናዊ ለመሆን ሞክረህ ለሰጠኸዉ አስተያየት ምስጋናዬ የላቀ ነዉ፡፡ የምትኖርበትን አላዉቅም ላልከዉ የምኖረዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ በአንድ መርህ እንስማማ፡፡ እኛ ኢትዮጵያዉያን እዉነተኛ ክርስቲያኖች ነን አገራችንም የክርሲቲያን ደሴት ነች ብለን የምናምን ከሆነ መገለጫዎቹ መታየት አለባቸዉ፡፡ የክርስቲያን ደሴት ማት ምን ማለት ነዉ? አስተዳረደራችን ነዉ? ኑሮአችን ነዉ? ምኑ ነዉ እንደዚያ ያስባለን? እንደዚያ ከሆነ
   1. የአዲስ አበባን መንገዶች በሌሊት የሚያጨናንቁት ሴተኛ አዳሪዎች የየት አገር ዜጎች ናቸዉ?
   2. በየማረሚያ ቤቱ የታጎሩት ወንጀለኞች ከየት የመጡ ናቸዉ?
   3. አገራችን በሰባዊ መብት አያያዝ ከአለም ስንተኛ ደረጃ ነች?
   4. ለምን ስንዴ ለማኞች ሆነን ቀረን(ለምን እግዚአብሔር ምድራችንን አልባረከም)?
   5. በየጠንቋይ ቤቱና ቃልቻ ቤቱ የሚሰለፈዉ ሰዉ የእኛ ዜጋ አይደለም ወይ? ወዘተ………………
   አገሪቱ የክርስቲያን ደሴት ነች ማለት ብቻዉን ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡ ያሉት ሁኔታዎች ያንን ያሳያሉ ወይ ሲባል ግን ሀቁ ሌላ ነዉ፡፡ አንተም ብትሆን ቢያንስ በነበረን ወግና ባህል መሰረት አንድ ወንድ የነካትን ሴት ሌላዉ ሲነካ ትርጉሙ ምን ሊመስል እንደሚችል ማሰብ አያቅትህም፡፡ ቁም ነገሩ የክርስቲያን ደሴት እየተባለች በምትሞካሽ ሀገር ይህ እንዴት ሊፈጠር ቻለ የሚለዉ የሚያስቆጭ ጥያቄ ነዉ፡፡ እናም ትዉልዱ መረን እየለቀቀ ስለሆነ ቤተክርሲቲያን ወንጌል መስበክ አለባት፡፡ በግዕዝ የሚደገሙ አወልዕድ መጻህፍት የትዉልዱን ልብ ወደ እግዚአብሔር ሊመልሱ አይችሉም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ መሰበክ አለበት የሚለዉ የግል አቋሜ ነዉ፡፡ ከዚህ ዉጭ እግዚአብሔር አንድ ነዉ መጽሐፍ ቅዱስም ዩንቨርሳል ነዉ፡፡ በቤተ እምነት ተከልለን የምንሰራዉ ግድግዳ አይደለም ቁምነገሩ፡፡ የየትኛዉም ቤተዕመነት አባል ልትሆን ትችላለህ፡፡ ሃይማት ሳይሆን ወሳኙ ነገር በግልህ ያለህ መሰጠት ነዉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ዘመኑን እንድንዋጅ የሚያስተምረን ስለሆነ አንንቃና ያለንበትን ሁኔታ በእግዚአብሔር ቃል እዉነት እንመርምር መልዕክቴ ነዉ፡፡ ነጻና ፍትሃዊ ነዉ ብለህ አስበህ ለሰጠኸዉ አስተያየት ግን ምስጋናዬ ከልቤ ነዉ፡፡

   Delete