Sunday, November 30, 2014

ማኅበረ ቅዱሳንን ክርስቲያናዊ ብራዘር ሁድ የሚያሰኙ ማስረጃዎችና መመሳሰሎች!ምንጭ፡- ደጀ ብርሃን
ሙስሊም ብራዘር ሁድ ወይም የሙስሊም ወንድማማቾች ማኅበር የተባለው ድርጅት 1928 / በግብጽ ተመሠረተ። ከሰማንያ ዐመታት በኋላ በጄኔራል አልሲሲ መንግሥት በአሸባሪነት ተፈርጆ ድምጥማጡ እስኪጠፋ ድረስ 70 ሀገሮች ውስጥ ቅርንጫፎቹን ከፍቶ በዘመናዊና ሃይማኖታዊ ትምህርት ቤቶች፤ በገበያ ማዕከላት፤ በንግድ ሱቆች፤ በማከፋፈያ ድርጅቶች፤ በሚዲያ ተቋማት ወዘተ የሀብት ማግበስበሻ መንገዶች እየተሳተፈ ክንዱን በማፈርጠም ለእንቅስቃሴው የሚጠቅመውን የገንዘብ ምንጭ ሲፈጥር ቆይቷል። ይህ የግብጹ ሙስሊም ብራዘር ሁድ በዐረብ ሀገራት ውስጥ ተመሳሳይ የሙስሊም ወንድማማች ማኅበራትን በማደራጀትና በማሰልጠን መንግሥታቱን ሲያስጨንቅ የቆየ ሲሆን አሁንም እያስጨነቀ ይገኛል።

የሙስሊም ብራዘር ሁድ ለተባለው ሃይማኖታዊ-ፖለቲካዊ ድርጅት ዋነኛ ተቀባይነት ማግኘት ዋናው ምክንያት የሆነው በእስላሙ ሕብረተሰብ ውስጥ ቶሎ ሰርጾ እንዲገባ የሚያካሂደው ሃይማኖታዊ አስተምህሮቱና  ለዚህ እምነት መክፈል የሚገባውን ዋጋ ሁሉ በመክፈል ከአላህ ዘንድ የሚከፈለውን ምንዳ ለመቀበል ቶሎ መሽቀዳደም ተገቢ መሆኑን አበክሮ በመስበኩ የተነሳ ነው።

1/
የሙስሊም ብራዘር ሁድ መዋቅራዊ እንቅስቃሴ 

 
ሙስሊም ብራዘር ሁድ መዋቅሩ በሀገሪቱ የመንግሥት ሲቪላዊ መዋቅር ደረጃ የተዘረጋ ነው። ይህም ከማዕከላዊ ቢሮው ተነስቶ አባል በሆኑ በእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ በሰንሰለት የተያያዘ ነው። ቤተሰባዊውን የአባልነት ማኅበር «ኡስራ» ይሉታል። አንድ «ኡስራ» አምስት አባላት ሲኖሩት ከአምስት በላይ ከሆነ በሁለተኛ የኡስራ ስያሜ ደረጃ ይዋቀራል። በቤተሰቡ ያሉትን ኡስራዎች የሚመራ ደግሞ የቤተሰቡ አባል የሆነ በእስልምና ሃይማኖቱ የበሰለና የብራዘር ሁድ አስተምህሮት በደንብ የገባውን ሰው የቤተሰቡ ጉባዔ ይመርጠውና «ናቂብ» ተብሎ ይሰየማል። ይህ «ናቂብ» የተባለው ሰው የቤተሰቡ አባላት በእስልምናው ደንብ ዘወትር ስለመንቀሳቀሱ ይቆጣጠረዋል፤ ያስተምረዋል፤ ይነግረዋል። ያልተመለሰውን በማኅበረሰቡ ደረጃ ለተቀመጠውና ከፍ ላለው ሃይማኖታዊ መሪ ያቀርበዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ስለእስልምናው የሚደረግ እርምጃ በመሆኑ በደስታ ከሚቀበል በስተቀር ማንም በተቃውሞ አያንገራግርም፤ ሊያንገራግርም አይችልም። ምክንያቱም ጸረ እስልምና እንደሆኑ ራሳቸውን አስገዝተዋልና። በዚህ ዓይነት አደረጃጀት የሙስሊም ወንድማማቾች ማኅበር ከላይ ወደታችና ከታች ወደላይ የተሳሰረ መዋቅር አለው።

2/   የገንዘብ ምንጮቹን ማሳደግ

ገንዘብ የዚህ ዓለም እንቅስቃሴ የደም ሥር ነው። አባላት ለመመልመል፤ እንቅስቃሴውን ለማስፋፋት፤ የሽብር ተግባሩን ለመፈጸም፤ ለመደለል፤ ለመሰለል፤ ሃይማኖታዊ ዶክትሪኑን ለማስተማር  እጅግ ጠቃሚ ነገር መሆኑን ጠንቅቆ የተረዳው ብራዘር ሁድ የገንዘብ አቅሙን ለሀገር ውስጥና ድንበር ዘለል ተግባሩ ያውለው ዘንድ ተግቶ ይሰራል።

የእስላም ወንድማማቾች ማኅበር ሁለት ዓይነት የገንዘብ ምንጮች አሉት። አንዱ በውጪ ሀገራት ካሉ አባላቱ በመዋጮ የሚሰበሰብ እንዲሁም ብዙ ሃብት ካላቸው የድርጅቱ ደጋፊ ሚሊየነሮች  የሚደረግለት የገንዘብ ፈሰስና በእስላማዊ መንግሥታት ስር ከተሸሸጉ ባለስልጣናት የሚዋጣለት ገንዘብ ነው።  ሁለተኛው ደግሞ በተራድዖ ስም ከውጭ የሚያሰባስበውን ገንዘብ ወደልማት ካዝና በመቀየር በአካባቢ ልማት፤ በትምህርት ቤቶችና መድራሳ ማቋቋም፤ ሥራ አጥ ህብረተሰብን በማደራጀት፤ የራስ አገዝ እንቅስቃሴን በመመሥረት የሚሳተፍ ሲሆን ለዚህም ሀገር በቀል የእርዳታ ስልት በመቀየስ መዋጮውን ቅርጹን ለውጦ ያግበሰብሳል። ይህም፤

/ ከአባልነት መዋጮ
/ ከንግድ ድርጅቶቹና ከሚዲያ ተቋማቱ የሚገኝ ገቢ ነው።

ይህንን ገንዘብ በተለያየ የገንዘብ ማስቀመጫ ስልቶችና በብዙ የሂሳብ አካውንቶች ቋት ውስጥ በተለያየ ስም በማስቀመጥ ለሚፈልገው ዓላማ በፈለገበት ሰዓት ማንም ሳያውቅበት ያውለው ነበር። በተለይም የእስልምና ባንኮች ተመራጭ መንገዶቹ ነበሩ።

3/
በመንግስታዊ ተቋማት ውስጥ ሰርጎ መግባት

ብራዘር ሁድ አባላቱን ሲመለምል ነጻና ገለልተኛ የሆኑትን ብቻ አይደለም። ከሚኒስትሮች እስከፍርድ ቤቶች፤ ከመከላከያ እስከ ፖሊስ መምሪያዎች፤ ከድርጅት ሥራ አስኪያጆች እስከ አስተዳደር ኃላፊዎች ድረስ በአባልነት መልምሎ፤ አሰልጥኖና ሃይማኖታዊ ትጥቅ አስታጥቆ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነበር። እነዚህ የመንግሥታዊ አካላት ክፍሎች ድርጅታቸው ለሚነሳበት ተቃውሞና ኅልውናውን ፈታኝ ለሆኑ ችግሮች የግብዓት ምንጭ ሆነው ያገለግላሉ። አስፈላጊ በሆነ የመረጃ፤ የፋይናንስና የአፈና ሥራው በትጋት ይሰራሉ።
ይህ ድርጅት እንደሃይማኖታዊ ተቋም አራማጅነት ተነስቶ ወደፖለቲካዊ ሥልጣን መቆናጠጥ እርምጃው ለማደግ መሠረት አድርጎ የሚነሳው የእስልምና ሃይማኖትን ነው። ይህም ብራዘር ሁድን መቃወም እስልምናን እንደመቃወም እንዲቆጠር በሕብረተሰቡ ዘንድ የኅልውናውን ስዕል በማስቀመጥ እንዳይነካ ወይም እንዳይጠፋ ረድቶታል። የእስልምናውን አስተምህሮ መነሻ በማድረጉ የማይነቃነቅ ፖለቲካዊ ግብ ለማስረጽ ያገዘው ሲሆን የዚህም መገለጫው በአልሲሲ መንግሥት ላይ በአንድ ጊዜ እስከ 33 ሚሊዮን ተቃዋሚ ሰልፈኞችን በመላ ሀገሪቱ ማንቀሳቀስ የሚችል ድርጅት አድርጎታል።
 
ይሁን እንጂ የጀነራል አልሲሲ መንግሥት እርምጃ ስልታዊ በመሆኑ በአንድ ቀን ብቻ ከሁለት ሺህ በላይ ከፍተኛና ዝቅተኛ አመራሩንና የሃይማኖታዊ ተፍሲር መምህራኖቹን ለቃቅሞ ወደማጎሪያ ካምፕ በመክተቱ ድርጅቱ 85 ዓመት እድሜው አይቶት የማያውቀውን ውድቀት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያስተናግድ አድርጎታል። በአልሲሲ መንግሥት የተተገበረው «ወፎቹ እንዲበተኑ ቅርንጫፉን መቁረጥ» የሚለው አባባል ብቻ ሳይሆን ግንዱን መንቀል በመሆኑ የብራዘር ሁድ ዋና መሪ መሐመድ ሙርሲን ጨምሮ ከፍተኛውን የሹራ ካውንስል ሳይቀር ከስር ገርስሶታል። በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቱም የሞትና የእስራት ፍርድ ተከናንበዋል። አልሲሲ በቲቪ ቀርበው "ብራዘር ሁድን ከስረ መሠረቱ ነቅለን ካላጠፋን ሰላም የለንም" በማለት ድራሹን አጥተውታል። ዛሬም ድረስ የተቃውሞ ሰልፎች ያሉ ቢሆንም በሃይማኖት ካባ ስር በተሸፈነው ድርጅት በኩል የአእምሮ አጠባ ተደርጎ የተታለለው ሕብረተሰብ እንጂ ብራዘር ሁድ እንደተቋም በግብጽ ታሪክ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል። ማለት ግን ብራዘር ሁድን የሚደግፍ፤ የሚጠባበቅና እንዲያንሰራራ የሚፈልግ የለም ማለት አይደለም።

4/
ማኅበረ ቅዱሳን እንደክርስቲያን ብራዘር ሁድ ስንል ምን ማለታችን ነው?

1/
ተቋማዊ አደረጃጀቱ ከመንግሥትም፤ ከቤተ ክህነትም ቁጥጥር ነጻ መሆኑ
2/
የራሱን አባላት የሚመለምልና የሚያደራጅ መሆኑ
3/
የራሱ የሆነ የገቢ ምንጭ ያለውና የንግድ ተቋማትን የሚያንቀሳቅስ መሆኑ
4/
ከአባላቱ ልዩ ልዩ መዋጮዎችና የስጦታ ገቢዎችን በመሰብሰብ በልማት ውስጥ እየተንቀሳቀሰ እንዳለ የማሳየት ብልሃት ያለው መሆኑ
5/
በመንግሥት ተቋማትና መሥሪያ ቤቶች፤ ፍርድ ቤቶች፤ ፖሊስ መምሪያዎች፤ በኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ስውር መዋቅር ያለው መሆኑ
6/
በቤተ ክርስቲያኒቱ ላዕላይ መዋቅርና እስከ አጥቢያ ድረስ በተዘረጋው አስተዳደር የራሱ አደረጃጀት የዘረጋ መሆኑ
7/
በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ውስጥ የራሱን ጳጳሳት በመመልመል ማስሾም የቻለ መሆኑ
9/
ከሀገር ውጭ ዓለም አቀፍ ቢሮዎችን ከፍቶ የሚንቀሳቀስና አባላት ያሉት መሆኑ
10/
ከዓለም አቀፍ የገቢ ፈጠራው ውስጥ በልማት ሰበብ የሚያጋብስ መሆኑ
11/
የመረጃ፡ የስለላና የትንተና መዋቅር ያለው መሆኑ
12/
የቤተ ክርስቲያኒቱን አደረጃጀቶች ለራሱ ዓላማ የመጠቀም አቅም ያለው መሆኑ
(
ሰንበት /ቤቶችን፤ የጥምቀት ተመላሽና የጽዋ ማኅበራትን)
14/
የግለሰቦችን ስም በማጥፋት ወይም ራሳቸውን በማጥፋት፡በማባረር፡በመደብደብ ወይም ግለታሪካቸውን ለራሱ ዓላማ ጠምዝዞ በማዋል እርምጃ መውሰድና ማስወሰድ የቻለ መሆኑ
15/
ስሙን ለማግነን፤ ክብሩን ለማስጠበቅ የሚያስችል በራሱ የሚመራ እንዲሁም በፖለቲካ የተቃውሞው ጎራ የተሰለፉ ደጋፊዎችና በስውር መረብ የሚንቀሳቀስ የሚዲያ ተቋም ያለው መሆኑ፤
ማኅበረ ቅዱሳንን ክርስቲያናዊ ብራዘር ሁድ እንድንለው ያስችለናል።

እስካሁንም ማንም ምላሽ ሊሰጥበት ያልቻለው ዋናው ነጥብ ማኅበረ ቅዱሳን ከመንግሥት እይታ ውጪ መሆን ባይችልም ከመንግሥት ቁጥጥር ውጪ የሆነ ክርስቲያናዊ ማኅበር መሆኑ ሲሆን እንደክርስቲያናዊ ተቋምነቱ  ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱ በማኅበሩ ላይ ቁጥጥርና ክትትል የማድረግ ችሎታ አንዳችም አቅም የሌላት በመሆኑ ያሳዝናል:: በመንግሥትም፤ በቤተ ክህነቱም ማንም ጠያቂ የሌለው ሆኖ መቆየቱን ለማመን ያለመፈልግ ዝንባሌ መኖሩም ያስገርማል::  ማኅበሩ እንደምክንያት ሁልጊዜ የሚያቀርበው ሲኖዶስ በሰጠኝ ደንብ እመራለሁ ቢልም እውነታው ግን ብራዘር ሁድ በሆኑ ጳጳሳት አባላቱ በኩል የሚመቸውን ደንብ አስጸድቆ ያለጠያቂ በነጻነት ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የገቢ አቅሙን እያሳደገ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን አባላት ለራሱ አባላት እየመለመለ፤በቤተ ክርስቲያኒቱ ቁመናና መልክ የራሱን አደረጃጀት፤ መዋቅርና እንቅስቃሴ እያከናወነ ያለ ማኅበር መሆኑ የማይካድ እውነታ ነው። ለምሳሌ የማኅበሩ ብራዘር ሁድ አባላት ጳጳሳቱ አባ ማቴዎስ፡አባ ቀውስጦስ፡ አባ ቄርሎስ፡ አባ ያሬድ፡አባ አብርሃም፡አባ ሳሙኤል፡ በአባ ማቴዎስ አደራዳሪነት የትግሬን መንግስት በጋራ መዋጋት በሚል ፈሊጥ ከማኅበሩ እግር ላይ ወድቀው የታረቁት አባ ፋኑኤል ተጠቃሾች ናቸው:: አባ ገብርኤል ግን ከአቶ ኢያሱነታቸው ጀምሮ የተጠጋቸው የውግዘት በሽታ  መቼም አይለቃቸውም::

5/
ለመሆኑ አሁን ያለው ማኅበረ ቅዱሳን አደረጃጀት፤   

የሰንበት /ቤት ስብስብ ነው? እርዳታ ድርጅት ነው? የልማት ተቋም ነው? የበጎ አድራጎት ማኅበር ነው? ራሱን ከሰንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ውጪ አስደርጓል። በዋና ሥራ አስኪያጅ ሥር የሚተዳደር ነገር ግን የቤተ ክህነቱ መምሪያ ያልሆነ መምሪያ ነው?
በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ሥፍራው ከየት ነው? በምንስ እንመድበው? ማኅበሩ በምን ሂሳብ እንደተቋቋመና በምን አደረጃጀት ኅልውና እንዳገኘ አይታወቅም::

እስከሚገባን ድረስ እንቅስቃሴውንና ያለውን አደረጃጀት ተመልክተን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳናዊ ብራዘር ሁድ ብንለው ተግባሩ ያረጋግጣል።
በሌላ መልኩ መንግሥት በኢትዮጵያ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ እንዲህ ዓይነት ማኅበር ከእስልምና ምክር ቤቱ ውጪ እንዲቋቋም ይፈቅዳል ወይ ብለን እንጠይቃለን? መልስ የሚያሻው ጥያቄ ነው።

24 comments:

 1. What a person with devil spirit you are? you see, all what you have written do not have spiritual sense. I know that you want to benefit from such allegation.

  Try to think again and again if you want to be a spiritual person. But you do not want to be like that. Wow...???

  ReplyDelete
 2. So funny! Protestant Brotherhoods

  ReplyDelete
 3. mederajret mebit mehonun atawukim.....adir bay....senef....wushet ... geta yigesitsih....

  ReplyDelete
 4. tiru yemiseru ehetochina wendemoch yalubeten mahiber endezih lemefereji memoker tegebi ayidelem lemanegnawum lebona yistachihu

  ReplyDelete
 5. I will never trust what you guys saying.... Thanks to the last meeting i saw how Government and Thehadiso trying to destroy the church and Mahibere Kidusan. How dare you are comparing Muslim Brother with Christian Organization? At least, they have done something tangible. Why you guy think us like moron? Silent means we are watching which side is telling the truth and analyzing the motive. Your motive is heading to the wrong direction. I don't know what to call it.... Political intention with Thehadiso? Now, Our eyes are opened. You haven't mentioned one word from Bible and the meeting... This tells us the source is the same and same as we have seen in the last meeting. They called it Spritual meeting but the whole talking was Politics. It was full of Politics, Thehadiso, Protestant and a group of people with some intention..... Shame on the Government and Fellow Christians... I am silent Christian and observed this... I will not tolerate this kind of intervention. Sty out of our Church...

  ReplyDelete
 6. መጀመሪያ የምንጩ ስም ቢስተካከል ደጀ ፅልመት ወይም ፀረ ብርሀን ተብሎ። በመቀፀል ከመሬት ተነስቶ ስም ማውጣት ከተቻለ እናንተንስ ማን እንበላችሁ? የተሀድሶ ብራዘርሁድ? ወይስ የአልቃይዳ? ቂቂቂቂ ሬሳ የሆነ ፅሁፍ ነው።

  ReplyDelete
 7. ቃየሎች
  ለእንደናንተ አይነቱ የጥፋት መልክተኛ አይደለም ቤተክርስቲያንና ማህበረ ቅዱሳን እኔም መልስም አስተያየትም መሥጠት ተገቢም አሥፈላጊም አይደለም።ምክንያቱም እናንተ ከጥፋት ውጭ ምንም አይነት ነገር ለመማርም ሆነ መለወጥ ስለማትችሉና ለመልካም ነገር ልባችሁ የተከፈተ አይደለምና ነው።እግዚአብሔር ሰውን በመፍጠሩ እንደ ተፀፀተ ይነግረናል።የተፀፀተው ሰውን በፈጠረበት ሁኔታ ሳይሆን ሰው የተባልነው ከተፈጠርንበት አላማ ወጥተን ጠላት ዲያብሎሥ ከሚሠራው ጥፋት እጅግ በፈጠነ ለጥፋትና ለተንኮል የፈጠንና የተጋን በመሆናችን ነው።አምላክን ፍቅር ሥቦት ወደዚህ አለም መጥቶ ለመሥቀል ሞት የታዘዘው በእኛ ክፉ ስራ እንጂ እሡ እግዚአብሔርማ ምን ሀጢያትና ጉድለት ይገኝበታል።ሙሠኛ፣ ዘማዊ፣ዘረኛ፣ነፍስ ገዳይ፣አሸባሪ፣ተላላኪ ሌላም ሌላም ተቀፅላ እየሠጣችሁ ትንሽ ትልቅ ሳትሉ የጥፋት በትራችሁንና ሠይፋችሁን በንፁሐን ላይ ለመሠንዘርና ለማሥወርወር ያላደረጋችሁት ሙከራ የለም።ደሚገርመው ምግባረ ክፉነን በሥም ይደግፋ ሆነና አባ ሰላማ ብላችሁ እራሳችሁን ሠይማችኇል።ለመሆኑ ክርስትና ማለት ለእናንተ የዋጃችሁን አምላክ መቃወም፣የንፁሐንን ደም ማፍሰስ፣እውነትን ማሳደድ፣በአጠቃላይ በክፉ መንፈስ እየተነዱወንጀልን ማራመድ ነውን? እረ ክርስትና ማለት በክርስቶስ አምኖ ሥለእውነት መቆምና መመሥከር ፣ጠላትን መውደድ፣በአጠቃላይ የመንፈስ ቅዱስን ፍሬ ማከናወን ነው።ቃየል ወንድሙን አቤልን የገደለው እንደ አቤል በእግዚአብሔር ባለማመኑና በክፉ ቅናት በመቃጠሉ ነበር።ዛሬም እናንተ በቃየል ጎዳና የምትሔዱ የክርስቶ የሆኑትን የምትገሉና በሀሠት መንፈስ የምትከሱ ቃየሎች ናችሁ።በሙስሊም ወንድማማቾች በኩል ተጠማዠዛችሁ የመጣችሁበት የማመሳሰል ተግባር በጣም ምን ያህል ለመዳን የማትፈልጉ ለጥፋትና ተንኮል የተጋችሁ መሆናችሁን ነው።በእርግጥ ስለሙስሊም ወንድማማቾች የጻፋችሁት ምን ያክል እውነት እንደሆነ ለመቀበል አዳጋች ነው።ምክንያቱ ከባህሪያች ሥነሣ እውነት ሥለማትናገሩና ሥለማትፅፉ ነው።ለምሳሌ ሙስሊም ወንድማማቾችንና ማህበረ ቅዱሳንን ለማመሳሰል የሞከራችሁበት ማህበር በምትለው ለየትኛውም ሥብሥብ መግለጫነት የምታገለግለዋን ቃል ነው።የሚገርመው ግን ሁለቱ በአላማ በየትኛውም መለኪያ ወይም መመዘኛ ሊነፃፀሩ አይችሉም ።ሙስሊም ብራዘር ሁድ ለምድራዊ ሥልጣን የሚታገል የፖለቲካ ድርጅት ወይም ማህበር አኛ አናንተ በማህበርሠለሠላችሁት መሆኑ ለማንም የተደበቀ አይደለም።ማህበረ ቅዱሳን የቅዱሳን አባቶችን አሰረ ፍኖት ተከትሎ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ከአባቶች መመሪያን በመቀበል ለማገዝና ለማሥፍት ግቡም የእግዚአብሔር መንግስት ሠዎች እንዲያገኙ የተቋቋመ መንፈሳዊ ማህበር ነው።ማህበሩ አባላት አሉት፣ማህራዊ አገልግሎቶችን ይሰጣል፣ አባላትን ይመለምላል ምናምን የምትሉት ቅናትና የናንተ የጥፋት መተግበሪያ በራችሁ በእግዚአብሔር ሀይል ሥለ ተዘጋባችሁ ተናዳችሁ እንጂ አንድ አካል ወይም ግለሠብ ማህበር ሊሆንም ተብሎ ሊጠራም አይችልም።መንግስትን ያጭበረበርንና ያታለልን መሥሏችሁ ትርኪምርኪ ታናፍሡና ፅፋችሁ ትበትናላችሁ።መንግስት ማንኛውም መንፈሳዊም ይሆን ፖለቲካዊ ማህበር ወይም ተቋም ያመነበትን እምነትና አሥተሣሠብ የሌላውን ተቋም ሳያውክ በሠላማዊ መንገድ የማራመድ መብትን ሠጥቷል።ሥለዚህ የሙስሊም እምነት ተከታይ ወንድሞቻችንም አምነታቸውን በሠላማዊ መንገድ ለመደገፍ ይህን መብት ማድረግ እንደሚችሉ መንግሥት የሠጠው መብት ነው።ደግሞ መንግሥት በምነት ተቋማትን ለአማንያኑ የተወ መሆኑም መታወቅ አለበት።ለማንኛውም የእናንተን ተንኮልና የቁራ ጬኸት መንግሥት የሚሠማበት ጀሮ የለውም።እናንተ ተዋህዶንና የክርስቶሥ የሆኑትን ለማዳከምና ለማጥፍት መሆኑ ይታወቃልና ተዋጊው እግዚአብሔርም ሥለ ቤተክርስቲያንና ሥለ አገልጋዮቹ እንዲሁም ህዝቦቹ ይዋጋልና አይሆንላችሁም።የማሳችሁትም ጉድጏድ የናንተው መቀበሪያ መሆኑ አይቀርም በንሥሀ ካልበመለሣችሁ።

  ReplyDelete
 8. አባ ሰላማዎች ከማቅ በአስተምህሮ እንጅ በርዕዮተ ዓለም አቋም ምክንያት አለመግባታችሁን አልተረዳሁም ነበር። ለመሆኑ ማቅን አንድጊዜ የሽዋ ሌላ ጊዜ የጎንደር የፖለቲካ አቀንቃኝ ነው እያላችሁ ስትኮንኑ እኖተ ኦነግን ዎይንስ ሕወሀትን ወክላችሁ እየሟገታችሁ ነውን? ታሳፍራላችሁ። አሁን አሁን በብሎጋችሁ የምታዎጡት ጽሑፍ እንደኔ እይታ ዎይንም ጸረ ተዋሕዶ ከዚያም ከራቀ ጸረሀገር ብቻ ሁኗል። ማቅን በወንጌል አመለካካቱ እዲድግ ብትፈታተኑት ትደነቁ ነበር። አሁን ግን ስናያችሁ በአደረጃጀቱ የቀናችሁ መሰለኝ። በየትኞውም መመዘኛ ማቅን ከብራዘር ሁድ ጋር ማነጻጸር ስላሞችን ለማስደሰት ካልሆነ በቀር ሌላ ምንም አይነት ፋይዳ የለውም።
  እባካችሁ የሚነጽ ነገር አቅርቡ።

  ReplyDelete
 9. If you consider Mahibere Kidusan as Muslim brotherhood what name shall we give to you? Since you are working for the devil spirit, let me give you a good name, ISIS or Alshebab, or BINALADEN OR DIREECTLY deveil.

  ReplyDelete
 10. Have you ever heard of the name Christ? May the lord have mercy on your soul. - please read Ephesians 6.

  ReplyDelete
 11. Why you guys didn't publish my comment? This by itself tells me who you are? and your intention. Thank you for letting me know that. I will support Mahibere Kidusan. They seemed that they are a true Organization with good intention.

  ReplyDelete
 12. ክፉትና ጥፋት የሠፈረባችሁ የክፉ አገልጋዮች ናችሁ።

  ReplyDelete
 13. meaningless as usual

  ReplyDelete
 14. የዋህ ከሐዲ!
  ታውቆብሻል አንቺ የሚሉ ለመንግስት ተቆርቋሪ ፡ እርር ድብን በይ !

  ReplyDelete
 15. Yehenene maheber lematefat yethalathehuten hulu taderegalathu wegeyawe gen ke menefes kedus ga selemihounebathu atethelutem lebouna yesetathu

  ReplyDelete
 16. Oh Mahber Kedusan is realy follows a right way.

  ReplyDelete
 17. ይህ የዲያብሎስ ልብ፤ አእምሮ እና አንደበት (ምላስ) የሆነ መጦመርያ ብሎግ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ ሆኖ በበጎች በረት ገብቶ በገሃድ እንደሚበጠብጥ ሁሉ በዚህም በዋና ገጹ ስር ሌሎች ድረ ገጾች ብሎ ስንደና እንክርዳዱን በመቀላቀል
  የዘረዘራቸዉን ድረ ገጾች ማየት በቂ ማስረጃ ነዉ፡፡ የእርሱ ያልሆኑትን እና የሚቃወማቸዉን ሳይቀር እንደ ተጨማሪ ምንጭ የጠቀሳቸዉ ለምንድን ነዉ? ንጹህ ኦርቶዶክስ ተዋሂዶአዊ መስሎ ለመታየት የዋህ በጎችን ለማጭበርበር ብቻ ነወ፡፡ የራሱ የሆነ ምንም ነገር የሌለዉ ባዶ ስብስብ ከመሆኑም በላይ በቤ/ክናችን ላይ ሲመቸዉም ዉስጥ በመመሸግ አደገኛ ጥገኛ ቨይረስ ሆኖ የቤ/ክንን ንጹህ ደም እየመጠጠ ቤ/ክን አርጅታለች እንደገና እናድሳት እያለ በህቡእ እና በገሃድ እየጨፈረ ነወ፡፡ ለመሳሌ መርዙን ከሚጭባቸዉ ድረ ገጾች መካከል ተሃድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሂዶ፤ ደጀ ብርሃን፤ ጮራ፤ የሚባሉ የተሃድሶ መናቃን ጭፍሮች በ/ክንን የሚሳደቡባቸዉ የአዉሬ አፎች የሆኑ ድረ ገጾች ይጠቀሳሉ፡፡

  ReplyDelete
 18. መቼም ቢሆን አትድኑ

  ReplyDelete
 19. Mahbere kidusan is not 'kidus', true statement about the association.

  ReplyDelete
 20. What a well written comparison!!! Great work and government has an excellent plan to deal with this evil mahibere once and for all. Hailemariam doesn't have patience like meles.

  ReplyDelete
 21. Mahibere kidusan will demolish EPRDF AND take over the leadership. You stupid Tigrewoch and oromowoch. MK has over 25 million memebers. We are more powerful than ever.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማሙሽዬ ምን አይነት ኅጻን ነህ? ተራ የተራ ተራ ነህ

   Delete
 22. አረ ባክችሁ ልለምናችሁ እንናነተ አባ ጥፋቶች፤ ንቁ ተመለሱ ከእወነት ጋር ተባበሩ እውነት ማሸነፍ ወይም ማጥፋት ስለማይቻል፡፡ እስኪ አስተያየቶችን ተመልከቱ የሰጣችሁተን መረጃ አንብቦ የደገፋችሁ ማን ነው፡፡ ከምትከተሉት ሰይጣን ውጫ ማንም፡፡ ማትመለሱ ከሆነ ቅጥል በሉ እንጂ እውነት እውነት ነው በሱ ላይ ልታመጡት የምትችሉ ለውጥ የለም፡፡

  ReplyDelete