Tuesday, November 4, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን ለአቡነ ቀሌምንጦስ መልካም የሥራ ዘመን የተመኘው ለምን ይሆን?

Read in PDF

በዘንድሮው የጥቅምት ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ከተወሰኑት ውሳኔዎች አንዱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ እንዲሆኑ መወሰኑ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ የሆነችው ሐራ ከዚህ ቀደም «ብአዴን እና ደህንነቱ» እያለች ስማቸውን እንዳላጠፋች ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስን እንኳን ደስ አለዎት ለማለት የቀደማት የለም፡፡ ይህን ያደረገችው ስለቀድሞ ዘለፋዋ ይቅርታ ጠይቃ ሳይሆን አይኗን በጨው አጥባ ነው “ለብፁዕነታቸው ውጤታማ የሥራ ዘመን እንመኝላቸዋለን፡፡” ስትል ከሰሞኑ የጻፈችው፡፡ ከዚህ ቀደም January 21, 2013 ባወጣነው ዘገባ እንዲህ ብለን ነበር፣ ማኅበረ ቅዱሳን “የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሊቀጳጳስ በሆኑት በብፁእ አቡነ ቀሌምንጦስ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈተ ሲሆን፣ በብሎጎቹ ላይ «ብአዴን እና ደህንነቱ» እያለ ስማቸውን በማጥፋቱ ብፁእነታቸው ማቅን «እኛ እኮ ከእኛ ጋር ተባብሮ ለቤተ ክርስቲያን ይሰራል ብለን ነው አርፎ የማይቀመጥ ከሆነ ሁለት መስመር ደብዳቤ ጽፈን እናዘጋዋለን» ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ከዚህ ቀደም ማቅ የመምሪያው ሃላፊ ከነበሩት ከአባ ሠረቀ ብርሃን ጋር ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ገብቶ በነበረ ጊዜ አቡነ ቀሌምንጦስ ከማቅ ጎን ቆመው ለማቅ ከፍተኛ ድጋፍ የሰጡ ሲሆን ያኔ ማቅን በሚገባ ባለማወቅና ለቤተ ክርስቲያን የቆመ መስሏቸው ያን ድጋፍ እንዳደረጉ እየተናገሩ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ አባ ሠረቀ ብርሃንን «እኛ እኮ የእርስዎን ትግል ሳናውቀው ነው ከማቅ ጎን የቆምነው» ብለው ባለፈው በሆነው ነገር ሁሉ መጸጸታቸውን ምንጮች ይናገራሉ፡፡”

ከሰሞኑ ሐራ ከዚህ ቀደም ያለችውን እንዳላለች ቆጥራ (ለነገሩ “ብአዴንና ደኅንነቱ” ብላ የጻፈችውን ከብሎጉ ላይ አንስታለች) ለብፁዕነታቸው መልካም የሥራ ዘመን መመኘቷ ለምን ይሆን? የሚል ጥያቄ ማንሣታችን አልቀረም፡፡ የማቅ ልሳን ሐራ እንዲህ ያለችው የብፁዕነታቸው መሾም አስደስቷት እንዳልሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ምንም ቢሆን ማቅ እንዳሻው እንዲፈነጭና በልቡ የያዘውን ቤተክርስቲያኗን የመቆጣጠርና ወደቤተ መንግሥቱ የሚያደርገውን ግሥጋሤ እንዳፋጠኑለትና ሳይታሰብ ግን አካሄዱን እንዳስነቁበት እንደ አባ እስጢፋኖስ መንገዱን አልጋ በአልጋ እንደማያደርጉለት ያውቃልና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚፈልገውን እንደቀድሞው አገኛለሁ ብሎ እንዲህ እንዳላለም ይታወቃል፡፡ ታዲያ ለምንድነው እንዲህ ያለው? ስለ ሁለት ነገሮች ነው የሚል እምነት አለን፡፡
የመጀመሪያው አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ከአባ እስጢፋኖስ ጋር በመሆን ለራሱ ባመቻቸውና በከሸፈው ሕግ መሠረት እንዲሠሩ ለመጠምዘዝ ሲሆን፣ ሐራ በመልካም ምኞት ዘገባዋ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ብዙ ሥራዎች እንደተሠሩና ለውጦችም እንደተመዘገቡ አድርጋ አቅርባለች፡፡ እውነታው ግን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ከፍተኛ ለሆነ ሙስናዊ አሰራር የተጋለጠውን የቀሲስ በላይ መኮንንን አስተዳደር እድሜ ለማራዘም ፈልጎ ያቀረበው ፕሮፓጋንዳ ከመሆን አያልፍም፡፡ በቀሲስ በላይ ሥራ አስኪያጅነት የተፈናቀሉትንና በቀለጠው የዝውውር ገበያው ለብዙ ውጣውረድና እንግልት የተዳረጉትን ግን ማኅበረ ቅዱሳን ሰምቶ እንዳልሰማ አይቶ እንዳላየ ማለፉ አስገራሚ ነው፡፡ ከበርካታ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት ሠራተኞች ጋር ያጋጨውም ይኸው እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ሐራ ግን ይህን ሐቅ ወደጎን ትታ ብዙ ጥፋትና ሙስና እየተፈጸመ ባለበት በዚህ ወቅት ብዙ ድል እንደተመዘገበ ማተቷ ማቅን ትልቅ ትዝብት ላይ የሚጥለው ሆኗል፡፡
ሁለተኛው ምክንያቱ ደግሞ የሚከተለው ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ስማቸውን በቀይ ቀለም ከትቦ ለብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ መልካም ምኞቱን የገለጸው ብፁዕነታቸው የከምባታ ሐዲያ ጉራጌና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብቻ ሳይሆኑ የሰንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የበላይ ላፊም በመሆናቸው ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ በዚሁ የጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ወደቀደመ ስፍራው ወደ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እንዲመለስ ስለተወሰነ ቀድሞ በማኅበሩና በአቡነ ቀሌምንጦስ መካከል የነበረውን ውጥረት ለማርገብ አስቀድሞ እጅ መንሣቱ ሳይሆን አይቀርም የሚል ጥርጣሬ አሳድሯል፡፡ ለማንኛውም ማኅበረ ቅዱሳን እንዲያው ደርሶ እጅ ከመንሣቱ በፊት ከዚህ ቀደም በብሎጎቹ «ብአዴን እና ደህንነቱ» ሲል የብፁዕነታቸውን ስም ሌላ መልክ ለመስጠት መሞከሩን በሆነ መንገድ ቢያወራርደው ሳይሻለው አይቀርም፡፡

10 comments:

 1. ሐሳባችሁ ስላልተሳካ ከነግብረ አበሮቻችሁ ቦታችሁን ፈልጉ፡፡ ቤተከርስቲያን ለእናንተ ቦታ የላትም፡፡ እውነት ምንጊዜም ያሸንፋል፡፡ በንስሐ ለመመለስ ያብቃችሁ፡፡

  ReplyDelete
 2. That is all you have plaintiffs? Why you are not take off the truth person name aba Selma and use some other political party name and register. Really, you are moral demolished. You are empty, fruitless and the career of bad sprit. You are digging to many holes to bare the truth, but all the holes will be you cave if you didn't not use the forgiveness of God and back to the truth. Everything you as the case why mehabere k idusan said congratulation for the orthodox father Abun Kelemintos are non sense. Anyone who puts himself in mistakenly and he/she believes as worshipping God that is not work at all. So stop against our faith and its servant. Before I close my comments I want tell you something. I am not the member of mehabere k idusan, but you try to connect every one with mehabere kidusan. That is completely wrong. You said other orthodox tewahedo church organizations members don't want to mention their organization, but they are saying, I am mehabire kidusan. You are lying too much. You are false plaintiff. I pray for you guys may God broke you heart and bring you back to the truth.

  ReplyDelete
 3. ማንም አመነም አላመነም ማኅበረ ቅዱሳን መንፈሳዊ ማኅበር አይደለም። መንፈሳዊ ማኅበር ማለት ምን ማለት ነው? ትህትና ያለው፣ የማይዘልፍ፤ በደልና ኃጢአትን የማይቆጥር፤ ክርስቲያናዊ ስነምግባር ያለው፤ በመልካም ስራው ለሌሎች አርአያ መሆን የቻለ፤ በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የተመሰከረለት ማለት ይመስለኛል። ማኅበረ ቅዱሳን ከነዚህ ውስጥ አንዱንም አያሟላም። ማኅበረ ቅዱሳን የስለላ ክፍል እንዳለው የመሰከበት የራሱ አባል ዳንኤል ክብረት ነው። ማኅበረ ቅዱሳን አቋሙን የማይደግፉ ሰዎችን ስም በማጥፋትና በማሳደድ የሚያክለው የለም። ማኅበረ ቅዱሳን የተቃወሙትን በማስደንደብ፤ ከስራ በማፈናቀል የሚወዳደረው የለም። ጽጌ ጽጦታውን ደብረ ሊባኖስ ገዳም አስደብድቦ ገደል የጣለው ማኅበረ ቅዱሳን ነው። ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤልን ቤተ ክህነቱ በራፍ ላይ በፖሊስ ያስቀጠቀጠው ማኅበረ ቅዱሳን ነው። ቀሲስ ትዝታው ሳሙኤልን ቅድስት ማርያም ግቢ ውስጥ በዱርዬ ያስመታው፤ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁንን መርካቶ ተክለሃይማኖት በጥፊ ያስደበደበው ማኅበረ ቅዱሳን ነው። በቤተ ክህነቱ ዘንድ ማኅበረ ቅዱሳን እንደሚፈራው መቼ ፌዴራል ፖሊስ ይፈራል??? ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የእውነት ወንጌል እንዳይናገሩ፤ የተሳሳተውን እንዲታረም እንዳያወጡ ሲያስፈራራ የኖረው ማኅበረ ቅዱሳን ነው። ነፍሳቸውን ይማርና እነ መጋቤ ብሉይ ሠይፈ ሥላሴ፤ እነ አቡነ መርሐ ክርስቶስ በዚህ ማኅበር ስማቸው ጠፍቷል። ከሀዲዎች ናቸው ያላቸውን ሰዎች ሰብስቦ አፍንጫና ጆአቸውን በሰይፍ እየቆረጠ ከጉድጓድ ከትቶ በራሳቸው ላይ ከብት እየነዳ አይሞቱ ሞት ስለተፈጸመባቸው ደቂቀ እስጢፋኖስና ይህንን በማድረጉ ደጉ ንጉስ ዘርዓ ያዕቆብ እያለ ዘወትር አውርቶ የማይጠግበው ይህ ማኅበረ ቅዱሳን ነው። ሰይጣን አመነኮሱ እያለ ስለተክለሃይማኖት አውርቶ የማይሰለቸው ይኸው ማኅበረ ቅዱሳን ነው። አባ ዘጋስጫ ባንዴ ዘጠኝ ቅርጫት እህል የሚበሉ ጻድቅ ነበሩ እያለ ተረት የሚያወራው ይኼው ማኅበረ ቅዱሳን ነው። ራዕየ ማርያም በተባለ የተረት መጽሐፉ ሲዖልን የሞላው ጋላ፤ ሻንቅላ፤ ኩናማና ፈላሻ ነው የሚለውን ይህ ዘረኛና ስም አጥፊ መጽሐፍ እሳት እንዳይገባ የሚከራከርለት ይኼው ማኅበረ ቅዱሳን ነው። ስለማኅበረ ቅዱሳን ስንቱ ተወርቶ? ስንቱ ተነግሮ? ማኅበረ ቅዱሳን ሰይጣን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተከለው የጥፋትና እውነት እንዳይገለጥ መጋረጃ የሆነ የጥፋት ኃይል ነው። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን በእውነትና የሰላም ጌታ በሆነው በሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እጅ በቅርቡ ይነቀላል። አስተውሉ! የግፉና የዐመጻው ጽዋ ስለሞላ እንደትንቢት ቁጠሩልኝ፤ ማኅበሩ በቅርቡ ይነቀላል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ewunet new..yeewunet amilak kebetekirstian yinkelachew..!!

   Delete
  2. የክርስቶስ በዚህ አለም በተመላለሰ ጊዜ ከሳሾቹ ብዙ የሐሰት ክሶችን ሲያቀርቡበት ነበር። ቅድሥት ቤተክርሥቲያናችን የክርሥቶሥ በመሆኗ ከውሥጥ እንክርዳዶች ከውጭ
   አህዛብ ይከሷታል ይፈታተኗታል። ዛሬም
   መናፍቃንና ምድራዊያን የክርሥቶሥን
   ቤተክርሥቲያንን በማገልገልና እውነተኛውን
   ክርቶሥንና የእሱን ወንጌል በማሥተማር
   የተጉትን እውነተኛ አባቶችን ወንጌል
   ሠባኪያንን፣ካህናትን፣ዲያቆናትን፣ማኀበራትንና
   ዘማሪያንናን፡ እንዲሁም የቤተክርሥቲያን ልጆች
   ምእመናን በሀሠት ይከሣሉ ያውካሉ፣እገግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ የሠራቸውን ተምራትና ገድላት የተመዘገቡባቸው መፅሐፍትን የእግዚአብሔርንና የሠውን አሠራ ባለመረዳት ሚሥጢርና ምሣሊያዊ መልክቶችን ባለመረዳት ይቃወማሉ በድፍረትም የተረት መፅሐፍ እያሉም ያቃልሉ።እግዚአብሔር የሠራቸው ሥራዎች ለሁሉም ይዳረሥ ዘንድ በተዘጋጀው መፅሐፍ ቅዱስ ውሥጥ ከሌለ በማለት እግዚአብሔር ን ሥራ የማይሠራ በማሥመሠል የተሠሩትንና እየሠራቸው ያሉትንም ይቃወማሉ ። በቤተክርሥቲያን ልጅነታቸው ቤተክርሥቲያንን እግዚአብሔር በሠጣቸው ጉልበት፣እውቀትና ገንዘብ በማገልገልና ከአባቶች እግር ሥር ቁጭ
   ብለው የተማሩትን የክርሥቶሥ ወንጌል
   ሳይበርዙና ምድራዊ ፍልሥፍና ሣይጨምሩ
   በእውነት በእግዚአብሔር አውደምህረት በቃል
   ሣይሆን በተግባር የአባቶቸ እግር በቆመበት
   ለመቆም እኔ ማን ነኝ በማለት የክርሥቶሥን
   ወንጌል ከሚያሥተምሩ የቤተክርሥቲን
   መኀበራት አንዱ ማኀበረ ቅዱሣን ነው።
   ከሳሽና ትንቢት ተናጋሪ ሆይ ጠላት
   የክርሥቶሥ የሆኑትን ሁሉና ቤተክርሥቲያንን
   በሀሠት ይከሣል፣ ይቃወማል፣ በመምሠልና
   በማሥመሠል ይዋጋል፣ ያሣድዳል፣ ይራገማል፣
   ይሣደባል፣ ሌላም ሌላም ይላል ያደርጋልም።
   ቤበክርሥቲንም ልጆቿም በአለም ዘንድ ይህ
   እንዳለና እደሚደርሥባቸው ያውቃሉ።
   ምክንያቱም በአለም ሣላችሁ መከራ አለባችሁ
   ተብሏልና። ነገር ግን ሁሉን በሚችል
   በእግዚአብሔር ቤተክርሥቲን ከልጆቿ ጋር
   በአሸናፊነት ትኖራለች እሥከ ምፃት።ማኀበረ
   ቅዱሳንንም እግዚአብሔር ለቤተክርሥቲያን
   መሥርቶታልና ጠላት ዲያብሎሥ አጥብቆ
   ይጠላዋል ይቃወመዋል የሀሠት ክሶችን
   ያውጅበታል እያሣደዱት አሣዳጅ ይሉታል የርግማን መዐት ያወርዱበታል ሌላም ክፍትና
   ተንኮሎችን ያሴሩበታል ። ማኀበሩ ግን
   የቆመለትን አላማ ክርሥቶሥን ከማገልገልና
   ቤተክርሥቲያንን በሚያሥፈልጋት ከማገዝና
   የእውነት ተቀዋሚዎችን መናፍቃንን ከነ ክፉ
   ሥራቸው ከማጋለጥ ውጭ አምላካቸው
   ክርሥቶሥ በከሣሾቹ ፊት ዝም እንዳለ ከሱ
   ተምረዋልና ለቤተክርሥቲያን ጠላቶች ያለም
   ቋንቋ ዝም ብሏል።
   ውድ ትንቢት ተናጋሪ፦ ማኀበሩ መንፈሣዊ
   አይደለም ብለህ ዋሽተሀል። ለመሆኑ ለአንተ
   ውሸት መፃፍና እርግማን ነው መንፈሳዊነት?
   እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ይበላችሁ
   ልባችሁንም ወደእውነትይመልሠው።ማኀበሩ
   አባቶችን አክብሮ ቤተክርሥቲያን በሠጠችው
   መመሪያ የሚንቀሣቀሥ፣ አባላት የሚያዋጡትን
   ገንዘብ ለፈረሡ አድባራትመጠገኛና ለመንፈሳዊ
   አገልግሎቶች የሚያሥፈልጉ ቁሣቁሶች ችግር
   ላለባቸው አቢያተ ቤተክርሥቲያን ማቅረቢያነትና
   ሌሎች መንፈሣዊ አገልግሎቶች ከማዋል
   ውጭ ለግል መበልፀጊያም ሆነ ለአለማዊ
   ተግባ የማይሠበሥብ፣የሠራቸው ሥራዎቹም
   በእውነተኟቹ የቤተክርሥቲያን አባቶችና
   አገልጋዮች እንዲሁም ልጆቿ የተመሠከሩና
   የሚታዮ እየታዮም ያሉ ፣ ሌሎች ብዙ መንፈሣዊ
   ተግባሮች የሚያከናውን ማኀበር ነው። በርግጥ
   ክፉ አምኖ ሥለ ክርሥቶሥ እንደማይመሰክር
   እንዲሁ የዚህ አለም ገዠ አገልጋዮች
   የሀሠተኞው ክርሥቶሥ አቀንቃኞች መናፍቃን
   የዋጃቸውን ክርሥቶሥን አሥቀድመው
   ክደዋልና የማህበሩንም መንፈሣዊነትና
   አገልግሎት አይመሠክሩ ሊመሠክሩም
   አይችሉም። ምክንያቱም የማኀበሩ ተግባር
   ከአለማዊያን ተግባርና አላማ የተለየ ለእውነትና
   ለእግዚአብሔር መንግሥ ት የቆመና የሚተጋ
   ነውና። ወድ ትንቢተኛ፦ የግለሠቦች ሥም እየጠቀሥክ ማኀበሩ እንዲህ አደረጋቸው
   አሥደረጋቸው የሚል ሀሠተኛ ፅሑፍ
   ፅፈሐል።ምንም እንሿን የገለፅሀቸውን
   ግለሠቦች ሁሉንም በላውቃቸው አድ ሁለቱን ግነ
   በአካልም አውቃቸዋለሁ።አንደኛው እዚህ እኔ
   ከምኖርበት እሥቴት ይኖራል። ለሁሉም ግን
   ማህበሩ በግለሠቦቹ ላይ ምንም አይነት የአካል
   ጥቃት እንዲደረግባቸው አላደረገም። የማህበሩ
   ተልኮም ሆነ አላማ ሠይጣናዊ ተግበር ሣይሆን
   ሠማያዊ ነው። ለምሣሌ ተክለሐይማኖት
   ተደበደቡ ያልካቸውን ብንመለከት በቅዱሡ
   ሥም በሚጠራው በእግዚአብሔር
   አውደምህረት ሳይጠሩ፣ ሳይሠየሙ፣ ሳይጋበዙና
   ሣይበቁ በማናለብኝነት ባለቤት እንደሌለው በሩ
   እንደተከፈተ ቤት በድፍረት በትቢት ካልወጣን
   በማለታቸው ከማኀበሩ ግንኙነት የሌላቸው ነገር
   ግን እንደማኀበሩ ለቤተክርሥቲያናቸውና
   ለእምነታቸው ቀናይ የሆኑት የቤተክርሥቲያኒቷ
   ልጆች እነትዝታውን እናንተ ለዚህ አትበቁም
   ሥላሏቸው ነው። ከምርትነሽ ውጭ
   የእነትዝታው ቡድኖች ፃድቁን ሲያጥላሉና
   ሲያናንቁ የነበሩ ናቸው። መፅሐፍ ቅዱስ ፃድቃንን
   የሚጠሉ ይፀፀታሉ የሚለውን አሥተውለው
   እንሿን ንሥሀ አልገቡም። ካላመኑበት ደግሞ
   መሔድ ለምን አስፈለጋቸው? ሁከት ለማሥነሳ
   አይደለምን? የሱ ባልሆነቦታሥ መሔድና ሁከት
   እንዲነሣ ማድረግ የዚህ አለም ገዠ በግባር
   አይደለምን? ለምሣሌ ትዝታው ሣይማር
   ፣እግዘአብሔር ሣይቀባው ካላሥበማርኩኝ ብሎ
   ሥህተትን የሚያሥተምር አይደለምን?
   በእግዚአብሔር ዉሥጥ ደሠ የሚልና የማየይል
   ያለ ይመሥል ይህ ቃል ደሥ ይለኛል እያለ
   የእግዚአብሔርን ቃል ጥሩና መጥፎ አድርጎ
   በሠዎች አምሮ ለማሥረፅ እየሠራ አይደለምን?
   ይህሥ ምንፍቅና አይደለምን?እግዚአብሔር
   ልቡን ይመልሠው። ማኀበረ ቅዱሣን ምንፍቅና
   ይዋጋል በቤተክርሥቲያን እንዳይኖር ምንፍቅና
   አራማጆችን ያጋልጣል።ተጠራጣሪዎችን
   ከጥርጥር እንዲወጡ ያሥተምራል ይነግራል።
   ሥለዚ ተባረሩ ተሠደዱ ያልካቸው መናፍቅ
   ከሆኑና አንመለሥም ካሉ ከክርሥቶሥም
   ከቤተክርሥቲያንም ጋር ህብረት የላቸውምና
   በማህበሩ ሣይሆን በቤተክርሥቲያኗ አባቶች
   ውሣኔ መናፍቃኑን ያመናችሁበት እራሣችሁን
   ችላችሁ አራምዱ ብለው ከቤተክርሥቲያን
   የሥወጧቸዋል። አመንክም አላመንክም እውነቱ
   ይሔ ነው። ውድ ትንቢት ተንባይ፦ ሥለትንቢት ሢነገር ሠምተሀል መሠለኝ እንጅ ትንቢት ምን
   እንደሆነ የተረዳህ የተገነዘብህ አይመሥለኝም።
   ለዚህም ነው የእውነት ጠላቶችና ገንዘብ
   ወዳጆች በማኀበረ ቅዱሳን ላይ ያወጁትን
   የውሸት አሉባልታ ቀርበህ አይተህ ሣትመረምርና
   ሣትገነዘብ የምታራግበው። ለሁሉም ትንቢት
   ሢነገር ቦታውና ጊዜው በግልፅ ይነገራል።
   ይኼም ደግሞ እውነተኛነቱ በመፈፀሙ
   ይረጋገጣል። ውድ ትንቢት ተናጋሪ አንተ ግን
   በቅርብ ብለሀል። ቅርብ ሥንት ጊዜ ነው?
   እግዚአብሔር ይመልሥህ።
   በመጨረሻ እውነትን የተናገራችሁን ሁሉና
   ተሣሥታችኃል ያላችሁን ሁሉ ማኀበረ ቅዱሣን
   ትሉታላችሁና እኔ የማኀበሩ አባል አይደለሁም። ማንነቴ ከፈለገችሁ በየትኛውም መንገድ መግለፅ እችላለሁ።

   ክርስቶስ አርነት አውጥቷችኃልና ዳግም በባርነት አትያዙ።

   Delete
  3. የኛ ነቢይ! ከተናገርከዉ ዉስጥ ስንት እዉነት አለ? የዘረኝነት መርዝህን በመርጨት የቤተክርስቲያንን ልጆች ለመበተን አልመህ ከመጻፍህ ዉጭ አንድም እዉነት ሳትቀላቅል ነዉ የምትለፈልፈዉ፡፡ አንተ የተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልጅ (የእምነቱ ተከታይ) ካልሆንክ ሲጀመር እዉነቱን በመናገር የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ መንቀፍ ትችል ነበር፤ ነገር ግን ማታለልን መረጥክ፡፡ አይ ክርስቲያን! ለምን ቤተክርስቲያንን ነቀፍክ አልልህም፤ ይህ ፈጣሪ የሰጠህ ነጻ ፈቃድ ስለሆነ፡፡ ነገር ግን ለምን በቤተክርስቲያን ዉስጥ ያለህ ለመምሰል ትሞክራለህ? በመዋሸት ነዉ እምነትህን የምትገልጸዉ? አለማፈርህ ደግሞ የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ለመምሰል ስትሞክር፡፡

   Delete
 4. yewega biresa yetewega ayresa

  ReplyDelete
 5. ምንም እንኳን ብሎጉና ማህበሩ ቢለያዩም እንደኔ ከጽሑፋችሁ የተረዳሁት ማህበሩ ቢመኝም ትክክለኛ ይሆናል፡፡ መመኘቱ ተገቢ የሚሆነው እንደናተ መናፍቅ ስላልሆነ

  ReplyDelete
 6. yihe yetelat were new. sile maninetachew bemeyazegaghut andi guzho bemesatef ena bemeserut sira maweki yichalal. manim fistusm yelem.
  lenante gin lib yistachew.

  ReplyDelete