Thursday, November 6, 2014

ማኅበረ ቅዱሳንና ተላላኪዎቹ ጳጳሳት የቤተክርስቲያንን ችግር ሆነው የሚቀጥሉት እስከ መቼ ነው?

Read in PDF

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ መታመሷን ቀጥላለች፡፡ የሲኖዶስ ስብሰባ በመጣ ቁጥር ማኅበረ ቅዱሳን አጀንዳ ሆኖ መቅረቡ በጣም አነጋጋሪ ነው፡፡ ልዩ ልዩ ውሳኔዎች ቢወሰኑም ከቤተክርስቲያን ጥቅም አንጻር ሳይሆን የማኅበሩን ጥቅም የሚነካ መስሎ ከታየ በልዩ ልዩ መልክ ተፈጻሚ እንዳይሆን እጀ ሰፊውና እጀ ረጅሙ ማኅበረ ቅዱሳን ልዩ ልዩ የማዳከም ሥራዎችን በመሥራት ውሳኔዎቹ የወረቀት ላይ ነብር ሆነው ብቻ እንዲቀመጡ ያደርጋል፡፡ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ጊዜዎች በማኅበረ ላይ የወሰነቻቸው ውሳኔዎችም ሳይፈጸሙ እንደገና ሌሎች ውሳኔዎች እየተላለፉ ከ2007ቱ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ደርሰናል፡፡ 
አሁንም የቀድሞው የማኅበሩ ተጠሪነት ጉዳይ ላይ የተላለፈው የሲኖዶስ ውሳኔ ተሽሮ ወደቀድሞው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እንዲመለስና ተጠሪነቱ ለእርሱ እንዲሆን ወስኗል፡፡ ሲኖዶሱ ይህን ውሳኔ ሲወስን ምክንያቱ ምን ይሆን? ቀድሞ ከዚያ እንዲወጣና ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ቤተክህነት እንዲሆን ሲወስን ማኅበረ ቅዱሳን ትልቅ ማኅበር ስለሆነ በአንድ መምሪያ ሥር መሆኑ አይመጥነውም ተብሎ ነበር፡፡ አሁን ታዲያ ወደቀድሞው መምሪያ ሲወርድ ምን ምክንያት ተሰጥቶ ይሆን? ትልቅ የተባለው ማቅ ትንሽ ሆኖ ስለተገኘ ይሆን በመምሪያ ሥር ነው መሆን ያለበት ተብሎ እንደ ገና ወደ ቀድሞው ቦታው የተመለሰው? ወይስ ሌላ ምክንያት ይቀርብ ይሆን? ይህ ሲኖዶሱን የሕጻናተ አእምሮ ስብስብ የሚያሰኝና የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎችም ክብደት የሌላቸው ተራና ምክንያታዊ ያልሆኑ እንደሚያደርጋቸው ምንም አጠራጣሪ አይደለም፡፡ 

ይህ ሁሉ የሚያሳየው ሲኖዶሱ ማለት አብዛኛው የሲኖዶስ አባላት የማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪዎች ሆነው መቀጠላቸውን ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንም ጡንቻውን ማፈርጠሙንና ሲኖዶሱን ለማሽከርከር እየሞከረ ያለው እርሱ መሆኑን ነው የሚያሳያው፡፡ በዘንድሮው የጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የታየውም ይኸው ነው፡፡ የማቅ ተላላኪ ጳጳሳትም የራሳቸው አጀንዳና አቋም የሌላቸው ማቅ የጫናቸውን የሚያራግፉ ሆነው ነው የተስተዋሉት፡፡ አንዳንዶቹም ጠዋት ላይ ደኅና ሆነው ከሰዓት በኋላ ሌላ ሆነው የተስተዋሉበትም አጋጣሚ ብዙ እንደሆነ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ጠዋት ደህና ሆነው የቆዩት ማቅ የጫናቸው ነገር ስለሌለ ሲሆን ከሰዓት የተለወጡት ደግሞ ማቅ ሞልቷቸው ስለገቡ ነው የሚል ትልቅ እምነት አለ፡፡ ግን ይህ ጉዳይ በዚህ መልክ የሚቀጥለው እስከመቼ ይሆን? ለግል ጥቅማቸው እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ለአፍታም ቢሆን የማያስቡት የማቅ ተላላኪ ጳጳሳት ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም ሥራ ሳይሠሩ በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ከባድ ሸክምና ዕዳ ሆነው የሚቀጥሉትስ እስከ መቼ ነው? መንጋውን ሳይሆን ራሳቸውን አሰማርተው በምእመናን ሀብትና ንብረት የሚንደላቀቁትና መንኩሰናል ለዓለም ሞተናል ብለው በተግባር ግን ከዓለማዊ ሰው እጅግ ከፍ ባለና በናጠጠ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙት ቤተክርስቲያንን እየበዘበዙና እያስበዘበዙ የሚኖሩት እስከ መቼ ነው? ሕዝቡስ በብዙ ነውርና ሙስና ውስጥ ተዘፍቀው የሚገኙትን ጳጳሳት የሚታገሳቸው እስከ መቼ ነው? ወደሕዝቡ ከመቅረብና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሕዝቡን ከማገልገል ይልቅ እንደክት ልብስ ለበዓል ብቻ ብቅ እያሉ አገልግለው ሳይሆን ተገልግለው የሚኖሩት እስከ መቼ ነው? ብዙ ነውርና ወንጀል ግፍም ፈጽመው ነገር ግን ከሕገ ቤተክርስቲያንም ሆነ ከሕገ መንግሥት በላይ ሆነው የሚኖሩትስ እስከ መቼ ነው? እስካሁን ብዙ ወንጀል ፈጽሞ የተጠየቀ ጳጳስ ስለሌለ ሌሎች ጳጳስ ለመሆን እየተጋደሉ ያሉት በሕግ ያለመጠየቅ መብታቸውን ለማስከበርና ከሕግ በላይ ሆነው እንዳሻቸው ለመሆን አይደለም ወይ? ግን ይህ ሁሉ እስከ መቼ ነው የሚቀጥለው? እንዲህ ሲባል ግን ይህ ገለጻ ሁሉንም ጳጳሳት እንደማይወክል ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል፡፡ ሆኖም በጳጳሳቱ መካከል ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ለመቆም ምክንያት የሆናቸውን ጉዳይ መቃኘቱ መልካም ነው፡፡
ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በተያያዘ ከቅንነት የመነጨ አመለካከት ያላቸው አንዳንድ ጳጳሳት ማኅበረ ቅዱሳን ምንም ችግር የለበትም ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ እነዚህ ጳጳሳት ለቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ቅናት ያላቸው አብዛኛዎቹ የአብነት መምህራን ሆነው ያሳለፉ ሲሆኑ በእድሜያቸውም ከፍ ያሉ ናቸው፡፡ ለእነርሱ የማቅ ጥፋት ጎልቶ አይታያቸውም፡፡
ሌሎቹ ደግሞ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል ፈሊጥ ማህበሩ ሰፊ ድጋፍ አለው ብለው ስለሚያስቡና ብዙ ብርም ስላለው እርሱን ጋሻና መከታ በማድረግ ማኅበሩን መቃወም አይሆንላቸውም፡፡ እንዲያውም ማኅበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ውሳኔ እንኳን ቢሆን ከመወሰን ወደኋላ አይሉም፡፡ እነዚህ ጥቅመኞች በአቡነ ጳውሎስ ዘመን በርካታ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳና የማኅበረ ቅዱሳንን ጥቅም የሚያስከብር ውሳኔ ሲያሳልፉ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡
በሶስተኛው ጎራ የሚመደቡት ጳጳሳት ደግሞ በግልጽ የአንኮበርን ፖለቲካ የሚያቀነቅኑና መንግሥት ከሸዋ ፕትርክናም ከሸዋ መውጣት የለበትም የሚሉ ናቸው፡፡ እኒህ ጳጳሳት የማቅ 90 ከመቶ የሚሆነው ስብስብ የሸዋ ተወላጆች ስለሆኑ ይህን ሕልም በማኅበሩ በኩል ለማሳከት ደፋ ቃነ የሚሉና በአቡነ ማቴዎስ የሚመሩ ናቸው፡፡ ይህ ዝም ብሎ የሚወራ ሳይሆን ብዙ ማሳያዎች ሊቀርቡበት የሚል ነው፡፡ ለምሳሌ የመጀመሪያው ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ግብጽ ላይ ሲሾሙ አብረው ከሄዱ የሸዋ መኳንንት መካከል ልዑል አስራተ ካሳ እና መርስኤ ሐዘን ወልደ ቂርቆስ ካይሮ ላይ የፈረሙት ሰነድ ይህን የሚያስረዳ ነው፡፡ በሰነዱ ላይ “ከአባ ባስልዮስ በኋላ ፓትርያርክ መሆን ያለበት የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ነው” ብለው ነበር፡፡ ይህን የሸዋ ፖለቲካ የሚያራምዱ ጳጳሳት ህልማቸውን እውን ለማድረግ ማቅን የግድ ይደግፉታል፡፡
የሚገርመው ከአሁኑ የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ከአቡነ ማቴዎስ በፊት የነበሩት የኢየሩሳሌሙ አቡነ ማቴዎስ በቅጽል ስማቸው “ገበርተ ዓመፃ” ይባላሉ፤ የዐመፃ ልጅ እንደ ማለት ነው፣ እኚህ ጳጳስ ደብረ ሊባኖስ ውስጥ መነኮሳት ከሆኑ አባትና እናት መወለዳቸው ይነገራል፡፡ እርሳቸው በሕይወት እያሉ የአንኮበርን ፖለቲካ ለማራመድ ወደኋላ የማይሉና የፓትርያርክ አክሊልና ልብስ አዘጋጅተው የተቀመጡ ነበሩ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንም እኚህን አባት ፓትርያርክ ለማድረግ ያላደረገው ጥረት አልነበረም፡፡ ምኞቱ በጳጳሱ ሞት ምኞት ሆነ ቀረ እንጂ፡፡ የማኅበሩ ሰው የሖነው ዶ/ር መርሻ አለኸኝ የፊቼ ተወላጅ ሲሆን ባዘጋጀው “ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን” በተሰኘው መጽሐፉ ላይ መታሰቢያነቱን ለአቡነ ማቴዎስ ሲሰጥ የነበረውን ምኞት አልደበቀም “ብዙ ያስተምሩናል ብዙ ይመክሩናል ስንል … በድንገት በሞት ለተለዩን ለብፁዕ አቡነ ማቴዎስ” ይላል፡፡
ሟቹ አቡነ ማቴዎስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን ብዙ ጊዜ ይቃወሙ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ በአንድ ወቅት እንዲያውም “አንተ ገዳም ሳትኖር ከአሜሪካ እዚህ መጥተህ ፓትርያርክ ሆንክ” ብለው አቡነ ጳውሎስን በነገር ሊወጉ ሲሞክሩ አቡነ ጳውሎስም ቀበል አድርገው “ገዳምን ባንወለድበትም አድገንበታል” በማለት አባ ማቴዎስ ከመነኮሳት በገዳም ውስጥ የተወለዱ መሆናቸውን የሚጠቁም ምላሽ እንደሰጧቸው ይነገራል፡፡ ስማቸውን የወረሱት የአሁኑ አባ ማቴዎስም ያንኑ ታሪክ ለመድገም ከማኅበሩ ጋር እጅና ጓንት ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
በአሁኑ ጊዜ የማኅበሩን አመራር አባላት ብዛት ከሸዋ ወደ ጎንደር የቀየሩት አመራሮችና አባላት ፍላጎት ፓትርያርክ መርቆሬዎስን ለማምጣት ሲሆን መንፈሳዊ መሰል መልእክታቸውን በሐመር ፖለቲካዊ ዓላማቸውን ደግሞ  በአዲስ ጉዳይ በሎሚና በፋክት መጽሔቶች ላይ በግልጽ የሚያስተላልፉ ከዚህም በላይ የመጽሔቱን አክስዮን በመግዛት ጭምር ሲሰሩ የነበሩ እንደሆኑ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ በሀገሪቱ ላይ ሁከት እንዲፈጠር ጭምር በጽሑፍ ሲቀሰቅሱ የነበሩ የማኅበሩ አባላት በጎንደር ተወላጆች ጳጳሳት ጀርባ ሆነው ቤተክርስቲያኒቱን ለመክፈል የሚጥሩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ አዲስ ጉዳይ ላይ ባለአክስዮን የሆነው ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ የማኅበሩ የኮሚዩኒኬሽንና ሚድያ ክፍል ሃላፊ ሲሆን የዋልድባን ጉዳይ ለግጭት መንስኤ አድርጎ በማቅረብ ቅስቀሳ ሲያደርግ ነበር፡፡ በተለይ ምላጭ ቢያብጥ በሚል ርእስ ግልጽ ቅስቀሳዊ ጽሁፍ አቅርቧል፡፡ ከዚህ ቀደም ይኸው ዲያቆን “በዓላት” በተሰኘው መጽሐፉ ሕዝቡን በበዓላት ብዛት አስሮ ያየዘውንና ሰርቶ እንዳይለወጥ ያደረገውን ልማዳዊ ድርጊት እንዳይለቅ በሃይማኖት ሽፋን ፖለቲካዊ አቋሙን አንጸበርቋል፡፡ “በዓላት በገበሬዎች ኮንፍራንስ በሚዲያ ልፈፋ አይቀነስም” በማለት ሕዝቡ ከልማድ እንዳይወጣና ኋላ ቀር እንዲሆን ሰብኳል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ብርሃኑ አድማስ መንግሥት በመጽሔቱ ላይ ክስ መመሥረቱንና ያደረገውንም አውቆ ለንደን ሄዶ ቀርቷል፡፡ ምናለ ሁለቱንም ከሚያጣቅስ አንዱን ቢይዝ? እርሱን የመሰሉ የማህበሩ ሰዎች ብዙዎቹ በሁለት ኮፍያ የሚጠቀሙ ናቸው፡፡
ከላይ ከተመለከትናቸው ጳጳሳት በተጨማሪ ሌሎቹ የማኅበሩ ደጋፊ ጳጳሳት እጅግ አስነዋሪ ተግባር ላይ የወደቁ፣ የቆብ ውስጥ ሚስት የነበራቸው፣ ልጆች የወለዱ፣ የሀብት መጠናቸው ከፍ ያለ ሲሆኑ እነዚህን ደካማ ጎናቸውን በመጠቀምና መረጃ ይዤባችኋለሁ፣ ካልደገፋችሁኝ ለሕዝብ ይፋ አደርገዋለሁ በማለት የሚያስፈራራቸው ናቸው፡፡ እንደ አባ ሉቃስ ራሺያ ለትምህርት በሄዱ ጊዜ ለምደውታል ተብለው የሚታሙበትን ግብረሰዶማዊነታቸውን ማኅበሩ እንደ መያዣ በመያዝ እንዲደግፉት ያደርጋል፡፡ ይህም ሐራ የተባለው የማቅ ብሎግ ተራ በተራ ፎቷቸውን ያወጣቸው የፓትርያርኩ ተቃዋሚዎች ይህ ችግራቸው እንዳይጋለጥባቸው የሚሰጉ የማኅበሩ አግብርት ናቸው፡፡
አንዳንድ የፕትርክናው ሥልጣን ያመለጣቸው ጳጳሳት ደግሞ በፊት አቡነ ጳውሎስን አሁን አቡነ ማትያስን ማኅበሩ ያስወግድልን እንጂ ማኅበሩን ቅድሚያ የምናፈርሰው እኛ ነን የሚሉ፣ የማኅበሩን ክፋት ቢያውቁም እንደ መወጣጫ ሊጠቀሙበት የሚፈልጉ አሉ፡፡ ሌሎች ጳጳሳት ደግሞ ማኅበር አያስፈልግም ለቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ነው የሚያስፈልጋት ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን ይፍረስ የሚል አቋም የነበራቸው፣ ከጀርባቸው ምንም ነገር ያልተገኘባቸው፣ በይሉኝታም ሆነ በጥቅም የማይደለሉ ለቤተክርስቲያን ብቻ የሚያስቡ አባቶች ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ የሚጠቀሱት ታላቁ አባት ብፁዕ አቡነ መርሐክርስቶስ ነበሩ፡፡ የማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ ለሲኖዶስ ቀርቦ ሲጸድቅና ሁሉም ሁሉም ሲፈርም እርሳቸው ግን “አሁን ገና የቤተክርስቲያን ዓይን ጠፋ” በማለት ተናግረው እንደበር ይወሳል፡፡ ይኸው ከ10 ዓመታት በኋላ  ያሉት ነገር ደረሰ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሁን ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ነገሩ የገባቸው አባት ናቸው፡፡ ከላይ የዘረዘርናቸውን የማኅበሩን ደጋፊ ጳጳሳትን በደንብ የለዩ ይመስላል፡፡ የግል የሥነምግባር ችግር ያለባቸውን፣ በዘረፋ የተሰማሩትን፣ የልጆች አባት የሆኑትን፣ በሰዶማዊነት የሚጠረጠሩትን፣ የአንኮበር ፖለቲካን የሚያራምዱትን፣ ከፖለቲከኞች ጋር የተጋቡትን ሁሉ ጊዜ ወስደው በሲኖዶሱ ላይ ሁከት የሚፈጥሩትን  ሁሉ የያዛቸው ይሉኝታ መሆኑን በሲኖዶሱ ስብሰባ መጀመሪያ ላይ ማንሣት ተገቢ ነው፡፡ “በይሉኝታ የራስ ዓሊ ቤት ተፈታ” እንደተባለው በይሉኝታ ካልሆነ በቀር ማኅበሩን የምንይዝበት ህግ አጥተን አይደለም በማለት ከቤተ ክርስቲያኒቱ ይልቅ ይሉኝታ በማኅበሩ ላይ የያዛቸውን ጳጳሳት አስተውሉ ከምን አንጻር እንደሚደግፉ፡፡
ፓትርያርክ ማትያስ ጠንካራ ባሕርያቸው ያለ ይሉኝታ ነገሩን ማንሳታቸው ጀርባቸው ላይ ምንም እንደሌለ ያመለክታል፡፡ ይህ ጠባያቸው ገና ፓትርያርክ ከመሆናቸው በፊት ደርግ በአገሪቱ ላይ ያደረሰውን ግፍ አይተው ከኢየሩሳሌም ወደ አሜሪካ ሔደው በስደት ላይ ያለውን ሕዝብ ሲያጽናኑ ሰዎች በፖለቲካ ምክንያት ሲረብሿቸው እኔ ትቼላችሁ አንዱ ገዳም ነው የምቀመጠው ምንም የሚቀርብኝ የለም በማለት ያለ ይሉኝታ ሲናገሩ የሰሙ አቶ በላይ ግደይ በ1990 ዓ.ም. ባሳተሙት “ኢትዮጵያ ሀገሬና ትዝታዬ” በተባለው መጽሐፋቸው ላይ አድንቀው መስክረውላቸዋል፡፡ ስለዚህ አቡነ ማትያስ በማኅበሩ ላይ ያዙት አቋም አባ ማቴዎስና ሐራ ብሎግ እንደሚያወሩት አይደለም፡፡ የማቅን እኩይ ዓላማ መሠረት በማድረግ ቤተክርስቲያንን ለመታደግ ፓትርያርኩ እየወሰዱ ያለውን አቋም መደገፍ አስፈላጊ ነው፡፡

23 comments:

 1. Long live to aba matiyas

  ReplyDelete
 2. አባ ሰላማ ነገርካቸው ነው የሚባለው! ዳሩ ግን ኃጢአኛ የሚሰማው ዐመጽን ብቻ ነው። ኧረ አባ ማቴዎስም ሴት ሲያንጎዳጉድ በቅርብ የሚያውቀውና ጓደኛው የነበረ ሰው ተገኝቷል። አሁን ደርሶ ጻድቅ ቢመስልም ማንነቱ በደንብ ይታወቃል። በለፈለፉ በአፉ ይጠፉ እንዲሉ ሰውየው በቅርቡ ትኩሱ መረጃ የት? መቼና ከማን ጋር እንደነበር በማስረጃ አስደግፎ ኢንተርኔት ላይ በቅርቡ ይመጣል።

  ReplyDelete
 3. amen long live to aba Matias..lewengel yeminoru tamagn abat!!

  ReplyDelete
 4. errrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrr. weyne aba selamawoch tebesachachu ende? gena enante taleksalachu mahibere kidusan gn bete krstiyanachn ktehadso menafkan ena kemusegnoch ytebkal.
  degmo ene betam yegeremegn tnant lemahiberu abatoch ysedbal, yawardal blachu endaltsafachuln zare enante rasachu abatochn mezlef teyayazachut.... mn tegegnto yhon?
  yezeregnnetu guday yaw yetelemede propogandachu new. wshetegnoch bematawkut guday eyegebachu bete krstiyann atrebshuat. yemahibere kidusan abalat bezeregnnet lemekfel aychalachum. mknyatum bemahiberu wst yaltekelakel bher yelemna.
  enante gn gena taleksalchu..........errrrrrrrrrrrrrr..........................

  ReplyDelete
 5. Huletegna Edil enesetachihualen Mokiru.....mechem telat telat newu atarifum ahun 1 le 0 teshenefachihual

  ReplyDelete
 6. አባ ሰላማ ብሎግ፡- አልሆን ቢል የጦር መሣሪያሽን ለመቀየር መሞከርሽ ነው አይደል፡፡ የሰይጣን ጦር መሣሪያዎች ቢለዋወጡም በጾምና ጸሎት የማይከሽፍ የለም፡፡ ምንም እንኳን ለታሪክ ቦታ ባለመስጠትሽ /አያስፈልግም በማለትሽ / የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ስለማታስታውሽ ካለፈው አለመማርሽ አዲስ ነገር ባለመሆኑ አይደንቅም

  ReplyDelete
 7. አሁንም እዉነት እንደምታሸንፍ አታዉቁምን? ነገር ግን ክርስቲያን በፈተና ያልፍ ዘንድ አለዉና አሁንም ከበፊት ይልቅ የከፋ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፈታችሁ፡፡ ለክርስቲያኖች ፈተና ለሆናችሁ ለእናንተ ወዮ፡፡ እዉነትን በሀሰት ለመሸፈን ትተጋላችሁና ወዮ፡፡ አምላክ ልብን እና ኩላሊትን የሚመረምር እንደሆነ ልብ ባለማለት ከስጋዊ ምኞታችሁ የተነሳ ለተቅበዘበዘችሁ ለእናንተ ወዮ፡፡

  ReplyDelete
 8. ትዋሻላችሁ፣ ትከሣላችሁ፣ ለማሣደድ ትታትራላችሁ፣ ሌላም ብዙ ጥፋቶች ታደርጋላችሁ። ምነው የሀሠት ወንጌል ሥብከታችሁን የሚያደምጥአጣችሁ እንዴ? በውሸትና ንፁሐንን በመክሠሥ ክርሥቶሥን ማገልገልና መፅደቅ አይቻልም። አባቶችን በረከሠው አንደበታችሁና በጎለደፈው ብዕራችሁ በሀሠት ብትወነጅሏቸውም ለነሡ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገሥና ክብር ለእናንተ ግን እዳና ሞት ነው። እየፃፋችሁት ያለው ሀሠተኛ ፅሑፍ ሁሉ ነገ በህግም ያሥጠይቃችል። እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ።

  ReplyDelete
 9. ውሸት ነው ይህችኛዋን ክስ ደግሞ የግብር አባታችሁ ዲያቢሎስም አያውቃትም :: ይገርማል::
  እናንተም ልዩነታችሁ የሃይማኖት ነው: :ለምን የፖለቲካና የዘር ማስመሰል ፈለግህ ጻሃፊ ሆይ ?የመንግሥትን ድጋፍ በማግኘት ስውር አላማህን ለማስፈጸም:: እኔ ስለቅዱሳን የምትጽፉትን ሳየው እነማን እደሆናችሁ ተረድቻለሁ:: በቃ ከማህበሩ ጋር ጦርነቱ ተሃድሶዊ አጀንዳችሁን ስላከሸፈባችሁ ነው::
  ይህንን ያደረገ እና ቤተክርስቲያንን የሚጠብቅ ደግሞ እግዚአብሄር ነው::
  የውሸትን ክስ የሃይማኖት ሰው ነኝ ባይ ሲጠቀምበት እንዴት ያሳዝናል:: ልቦናህን ያብራለህ : ለንሰሃ ህይወት ያብቃህ :፡

  ReplyDelete
 10. that is not your business!!!!! you are not orthodox

  ReplyDelete
 11. Please go and fool your foolish followers. What did you do for the church? Something tangible. If you have a credible source and concern then show us. Blah blah blah...

  Actually, this year meeting gave us who is behind our church working to destroy our church. Thanks to You Tube and those foolish politician.

  Please pray

  ReplyDelete
 12. Afe sikefet thenekelate yetayale yelalu abew yetafathehuten metethet ayasefelegem lebuna yestathu leneseha mute yabekathu egeziyu

  ReplyDelete
 13. የአባ ሰላማ ጦማሪ ሆይ እየዋሸህ የምትቀጥለው እስከመቼ ነው???

  ReplyDelete
 14. እዉነት ያሸንፋል!!

  ReplyDelete
 15. እኛ እዉነተኛዉን ወንጌላችንን መሰበክ እንቀጥላለን፣ የሀሰት አባቱና ተረታተረታሙ የእርኩሳኑ መሰብሰቢያዉ በተረቱ ይግፋበት እዉነቱ ሲያሸንፍ ቀብሩን እንደርሳለንና።

  ReplyDelete
 16. What is real ?May be death.ግራም ቀኙም የሚሉት የሞተ ሞተ ሳይሆን አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆነ።አንተስ ከየትነህ ካላችሁ እኔማ ጲላጦስ ብሆን ይከፋብኝ ይሆን እንጃ! What is truth.
  John.18.38 ማነኛውም አሳቢ የራሱ ሓሳብ እንዳይናድበት ጥግንግን መረጃ ከማቅረብ በስተቀር ወደ ዕውነት እልፍ አይልም እናም መጻጻፉ መልካም ነው ይበል! ይሁን እንጂ ጽድቅና ሐሰትን ዕውነትና ውሸትን ከማነጻጻር የዘለለ መፍትኄም የለ፤ ሳሚ ወልደ ጌራ (ይቀልየከ ልብከ) እያንዳንዱን ኅሊናው ይመሰክረዋል ይመሰክርለታል ይመሰክርበታል ዳሩ ግን ለማደር ለመዋል ትግል ያስፈልጋል።

  ReplyDelete
 17. kkkkkkkkk belela yelachum selabewoch wustwa eyarerech tirswa yesekal malet manewwwwwwwwww???????? ererrrrr teken deben ...setasazenu 1 neger lengerachuh tekekelegna ena ewunetegna emnet benorachuh nuro sele beharr atanesum neber daru gen men yehonal .................. 0000 ..... selehone tekekelegna mereja metsaf alechalachuhem amlak wede lebonach YEMELESACHUH ye wushet eyenorachuh ye ewunet temotalachuh be ewunet lemenor ye esraeal amlak yerdachuh.

  ReplyDelete
 18. ለአውሬው የሥድ አፍ በሰጠው
  እናንት ሥነምግባር የጎደላችሁ፡ የእፉኝት ልጆች፡ በእውነተኛው የተዋህዶ አባት ሥም ተሸፍናች፡ የተዋህደን አገልጋዮች፡ የምትዋጉ፡ በዚህ ከግብር አባታችሁ ዳቢሎሥ በከረፋ ምግባራችሁ ማን እንደሆናችሁ ተጋለጣችሁ። ብላችሁ ደግሞ በየትኛው የሀይማኖት ተቋም በውሥጥ በማይታ የዘቀጠ የሥድብና የሥም ማጥፋት ዘመቻ ተሠማራችሁ? ከሣሽነት፣ ሥም አጥፊነት፣ ዘረኝነት፣ በውሸት መሥካሪነት፣ ክፋት፣ አሉባልታ፣ አለምንና ገንዘብን መመኘት፣ ደም አፋሳሽነት፣ ሌብነት፣ ጥርጥር፣ መናፍቅነት፣ ሁከት ቀሥቃሽነት፣ ወዘተ፡ ክፉ ተግባራት ሁሉ የሀሠተኛው መሲህ የዳቢሎሥና የግብር አበሮች እንጂ የእውነተኛው ክርሥቶሥ ለሆነተችው ክርሥትናና አማኞቿ መገለጫ አይደለም። የጀመራችሁት ሥም አጥፊነት መብት አይደለም። መብት ያመኑበትን ሀሣብ በራሥ ቦታ ሆኑ መተግበር እንጅ ሠዎች ባልዋሉበት ተግባር መወንጀልና ሥም ማጥፋት አይደለም። ይሄም ክፉ ተግባራችሁ በምድራዊ ህግም በእግዚአብሔርም ያሥጠይቃችኇል። በክፋታችሁ አለማዊነታችሁን እያረጋጣችሁ አለም ለእናንተ የተመቸች ሥትሆን የክርሥቶሥ ለሆኑት ግን የማትመች ናት። ምክንያቱም በአለም ሣላችህ መከራ አለበችህ ተብሎ በመፅሐፍ ቅዱሥ በነግሯልና ነው። ነገር ግን መከራውም አለሙም ያልፋል። በክፉ ስራችሁ የክርሥቶሥ መሆን፣ ወደእውነት መቅረብ፣ መፅደቅ፣ የመንፈስ ቅዱሥን ፀጋ ማግኘት አትችሉም። እናንተ ከመልካም ይልቅ መርዝ የሞላበት አፋችሁን የእግዚአብሔር በሆኑት ኦርቶዶክሣውያ ትከፍታላችሁ። እነሡ ግን ክርሥቶሥ በከሣሾቹ ፊት ዝም እንዳለ ዝም ብለው ወደ ላይ ይጮሀሉ።

  ReplyDelete
 19. yes yes yes we are true orthodox church children you believe or not.
  MK is truly no orthodox, MK not obey the church rule and law, Not respect our church top leader. MK trying to build own private hidden political agenda in the church. so who is tehadiso ? bros....go read MK blog what they are writing ...............dude do waste your time, every Orthodox members are clearly understand about MK........good luck...no more

  ReplyDelete
 20. አያችሁ አባሰላቢዎች አላማችሁ ምን ያህል ርካሽ እንደሆነ ይህ ፅሁፋችሁ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ማ/ቅን በማብጠልጠል ስትንፈራገጡ ሰነበታችሁና ሲኖዶሱ እንደተመኛችሁት ሳይወስን ሲቀር ሊቃነ ጳጳሳቱን መዝለፍና ያለስማቸው ስም መለጠፍ ተያያዛችሁት። አሁን ድጋፋችሁ ለአቡነ ማትያስ ብቻ ሆነ እሳቸወንም ወዳችሁቸው ሳይሆን ማ/ቅን ስለተዋጉ። በአጭሩ የእናንተ አላማ ተደጋግሞ እንደተገለፀው መጀመሪያ መላወሻ ያሳጣችሁን ማ/ቅን ማዳከም ቢቻል ማጥፋት/የማይቻል ቢሆንም/ ቀጥሎ ጳጳሳቱን ፓትርያርኩን ጨምሮ በማንቃሽሸ ሲኖዶስ እንዳይኖር ማድረግ ከዚያ ቤተክርስቲያኒቱን በተሀድሶ ፕሮቴስታንት ቅኝት እንደፈለጋችሁ መዘወር።
  እውነት እንላችሀለን ይህ መቸም የማይተገበር የቀን ቅዠት ነው። ይህን እኩይ ቤተክርስቲያናችንን የማፍረስ ተልእኮ ለማሳካት ከአጥቢያ እስከ ጠቅላይ ቤተክህነት እስከ ሲኖዶስም ጭምር እንደተሰገሰጋችሁ እናውቃለን። ብዙ ጥፋት እያደረሳችሁ እንደሆነም እንረዳለን ግን ከናንተ ትግል የኛ ይበልጣል ከናንተ ክፋት የኛ እውነተኛ ተቆርቃሪነት ይልቃልና እናንተጋር ካለው ክፉ መንፈስ እኛ ጋር ያለው የቅዱሳን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ይበልጣልና እናሸንፋችሁለን። ፃእ መንፈሰ ረኩስ

  ReplyDelete
 21. "ማኅበረ ቅዱሳንና ተላላኪዎቹ ጳጳሳት የቤተክርስቲያንን ችግር ሆነው የሚቀጥሉት እስከ መቼ ነው?"
  እናንተ ሃይማኖት አልባ መናፍቃን ከቤተክርስቲያኗ ተነቅላችሁ ወደ አዳራሻችሁ እስትጠቃለሉ ድረስ እና ከዛ በኋላም።

  ReplyDelete
 22. ay aba selam eski chaweta keyere Mk ande be egezabehar charente adego bezeto le hezeb christian terefal selezi lala neger keyer.God bless Mk.

  ReplyDelete
 23. Mk yemechershawo zemen endederese yemiyasayen talak Miller yehone mahber new.sikelew awgezew Gidelew debdebew....kemil kedabilos yetegegne..kerstos bezih zemen bihone yemetawo mk zekzeka neber yemteseklew.mk wef awgez mahber.Dennett yemngeste semayat kulf bejachu aydelem enjji begenzeb neber yemetasgebut.

  ReplyDelete