Sunday, November 9, 2014

ስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ አርባ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን በኮለምበስ ኦሓዮ አካሄደ።

Read in PDF

በጥሩ መንፈስ የተጠናቀቀ ነው የተባለው ጉባኤ በርካታ ካህናት እና ምእመናን የተገኙበት ጉባኤ ነበር ይባል እንጂ ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች አነጋጋሪ ነበሩ።
  የመጀመሪያው የቅዱስ ፓትርያርኩ 25ኛ ዓመት በዓል አከባርን የተመለከተ ሲሆን በጥቅምት ውስጥ ሊከናወን ቀጠሮ ተይዞበት እያለ ይህን ጉዳይ እንዲያስፈጽሙ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ምንም እንቅሥቃሴ ሳያደርጉ ቆይተው በመጨረሻ ፕሮግራሙ ተሰርዟል ብለው አስታወቀዋል። ምክንያታቸው ምን እንደሆነ ሲጠየቁ የተድበሰበሰና ተንኮልን ያዘለ ሆኖ ተገኝቷል። ሲኖዶሱ ውስጥ የጠራ አላማ የሌላቸው ሰዎች አሁንም እየተሽሎከለኩ መሆኑን ግንዝቤ ተይዞበታል። ይህ ጉዳይ ብዙ ሰዎችን አሳዝኗል።

   ሁለተኛው ጉዳይ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በአንድ ሕግ የሚመሩበትን ቃለ አዋዲ ማጽደቅ የሚል ነበር። ይህ ከፍተኛ ክርክር የተካሄደበት እና ብዙ ተቃዉሞ የገጠመው አጀንዳ ነበር። ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የየራሳቸው መተዳደሪያ ደንብ ያላቸው ሲሆን የካህናትና የምእመናን ግንኙነት ጤናማ እንዳይሆን አድርጎ ይኖራል። ቦርድ ሐሳቡን የማይደግፈውን ካህን ከአገልግሎት ማባረር ልማድ ሲሆን የተባረረው ካህንም የሚከተሉትን ሰዎች ይዞ ሌላ ቤተ ክርስቲያን መክፈት የተለመደ ነው። የሲኖዶሱንም ሥልጣን የማያከብሩ አብያተ ክርስቲያናት አሉ ነገር ግን በሲኖዶስ ሥር ነን እያሉ ሽፋን ያገኛሉ። 
ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ አቋም ይዘው ተከራክረዋል። ይህን አንድ ወጥ የሆነ ሕግ የማይቀበል ቤተ ክርስቲያን ቢኖር ከሲኖዶሱ መውጣትና ወደ ፈለገው መሄድ ይችላል ብለዋል። ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ ሥርዓት እና ሕግ ያስፈልጋል ያሉት ብጹእነታቸው በሥርዓት የሚያምኑትን ለሥልጣን ተገዢ የሆኑትን ብቻ ማገልገል ይኖርብናል የሚል ጠንካራ አቋም ይዘዋል። የዲሲዎቹ ቦርዶች ግን ካህናቱን ጥፋተኛ በማድረግ ችግር ፈጣሪ ስለሆኑ እንጂ ሕጋችን ችግር የለውም ብለው ለመክሰስ ሞክረዋል። ከብዙ ክርክር በኋላ በቋሚ ሲኖዶስ እንደገና ተጠንቶ ወደ አብያተ ክርስቲያናት እንዲላክና እንዲጸድቅ ተወስኗል።
  ሦስተኛው የዳላስ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ትልቅ መዋያያ ሆኖ ነበር። በኦክላንድ በተካሄደው ጉባኤ ሁሉም አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት እውቅና እንዲያገኙ ተብሎ በተወሰነው መሠረት የዳላስ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንም እውቅና አግኝቷል። ነገር ግን መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ አንዷለም ዳግማዊ የደብሩን ካህናት እና ዲያቆናት በማሳደም አስችኳይ የተቃዉሞ ደብዳቤ የላከ ሲሆን በስልክም ለነ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እየደወለ አቡነ ዮሐንስ አስወስነው ቢመጡ አብረናቸው አንቀድስም ቤተ መቅደሱንም እንዘጋለን ሲል ዝቷል። ይህ የአድማ ደብዳቤ ዶክተር ነጋን ጨምሮ በጥቂቶች ደጋፍ ያገኘ ሲሆን አብዛኛዎቹ ተሳታፊዎች ተቃውመውታል። በመጨረሻም የሚካኤል ቦርድ አባል የሆነው አቶ ላቀው ከፈለገ ሕይወት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ጋር ችግር የለብንም ነገር ግን ካህናቱን የሚያነጋግር ሽማግሌ ይላክልን ሰላማችን እንዳይደፈርስ እንፈራለን በማለት ጥያቄ በማቅረቡ ቅ/ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኑ ተቀባይነት አግኝቶ ቅሬታ አለን የሚሉ የሚካኤልን ካህናት ግን አቡነ ሳዊሮስ አቡነ ሚካኤልና አቡነ ሰላማ እንዲያነጋግሩ ተመድበዋል። ፈለገ ሕይወት ኢየሱስ የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ወደ ሲኖዶሱ ከመግባቱ በፊት የተመሠረተ መሆኑ በጉባኤው ተነግሯል።
 ከዚህ በተጨማሪ የካህናት ስልጠና በየስድስት ወሩ እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን የዚህም አስፈጻሚ የስያትሉ አባ ገብረ ስላሴ ሆነው ተመድበዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በዜጎች ላይ የሚያካሂደው እሥራት እና ወከባ እየጨመረ በመሄዱ የተቃዉሞ መግለጫ እንዲሰጥ ተወስኗል። ፍርድ ሲጓደል ደሀ ሲበደል ቤተ ክርስቲያን ዓይኔን ግንባር ያድርገው ማለቷ ያሳዝናል። ጌታ ኢየሱስና ሐዋርያቱ ቢሆኑ ዝም አይሉም ነበር። በነርሱ ወንበር ላይ የተቀመጡት አባቶችም  ትክክል ያልሆነ ነገር ሲፈጸም ተግሣጽ ቢያደርጉ ኃላፊነታቸውን ተወጡ ማለት ነውና ሊበረታቱ የጋባቸዋል።      

8 comments:

 1. ወይ ጉድ አንዷለም ዳግማዊን መጋቤ ሃይማኖት ከማለት መጋቤ ተንኰል ቢባል ከናዝሬት ጅምሮ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ሁሉም ይስማማል

  ReplyDelete
 2. hahahha, lol - so funny news. Lemin tikelidalachihu. "Sidetegna sinodos". Ayy Ethiopia besimish yemayibela yemayichekachek yelem mechem.

  ReplyDelete
 3. Esti ketesasatikugn arimugn. Gin koy yeSinodos sibseba sibal yePapasat meslogn neber. Miemenan ena Kahnat alubet ende? Kesinodos sibseba befit yeKahinat ena yeMiemenan teklala gubaie ayderegim ende?

  ReplyDelete
 4. Thank you Dr. Kesis Andualem for being a voice this synod needs. Bringing out the truth that others haven't seen.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Can u produce a shred of evidence that he is a doctor? U must? What schoo? Where? When?

   Delete
 5. አንዱዓለም ዶክተር አይደለም ገና ነው አለጨረሰም ይህ ሰው ሲያትል ገብርኤል መጥቶ የአቡነ ዜና ማርቆስን ምስል እየተሳለማችሁ ግቡ እያለ ህዝቡን የስህተት ትምህርት የሚያስተምር ሰው ያላወቀው መሰሪ ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. Were you there? Please listen the sermon again. He said how Abune Zena is Kedus. He told us how lucky we are to have his body in front of our church. And just to say good morning, good day. Also it is a choice.

   Delete