Sunday, December 7, 2014

በቀጨኔ መድኀኔ ዓለምና በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የተጀመረው የቤተክርስቲያንን ገንዘብ ከሙሰኞች የመጠበቅ ተጋድሎ በቢሮ ሠራተኞችና በካህናት መካከል ውጥረት አንግሧል፡፡

ባለፈው ጊዜ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጠራራ ፀሐይ እየተፈጸመ ያለውን ሙስና የተመለከተ ጽሑፍ ልከን በዚሁ ድረገጽ ላይ እንዲነበብ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ በሁለት ደብሮች ውስጥ እየታየ ያለውን ጥቂት መሻሻል ለመጥቀስ ወደድን፡፡ መሻሻሉ የታየው ባለፈው ባቀረብነው ጽሑፍ ለውጥ ተገኝቶ ይሆን ወይም በቅዱስ ፓትርያርኩ ትእዛዝ ወይም በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ትእዛዝ የተከናወነ ይሆን ባይታወቅም አንዳንድ ወገኖች ግን ከካህናቱ በቀረበ አቤቱታ መነሻነት በፓትርያርኩ ትእዛዝ የተፈጸመ ነው ይላሉ፡፡ ለማንኛውም ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ከሰሞኑ የባሕርይ  ለውጥ ማሳየት ጀምረዋል፡፡ እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት እርሳቸው በሀገረ ስብከቱ ውስጥ እየተፈጸመ ባለው ሙስና ውስጥ ዋና ተዋናይ መሆናቸውን ጠቅሰን ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ አንዳንድ እርምጃዎችን እየወሰዱና ለውጦች እየታዩ መሆናቸው ስላስደሰተን ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ እየሠሩ ስላለው መልካም ጅምር ይበርቱ ልንል ወደድን፡፡ ቀድሞም ቢሆን የሥራ አስኪያጁን ስም በከንቱ ለማጥፋት ብለን ሳይሆን እውነቱን ለመግለጥ በመሆኑ ሲያጠፉ ወቀስናቸው፡፡ አሁን ሲያለሙ ደግሞ ልናበረታታቸው ይገባል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም የቆሮንቶስን ሰዎች በአንድ ምዕራፍ ውስጥ ሲያመሰግናቸው፣ ደግሞም የማመሰግናችሁ አይደለም ሲላቸው እናነባለን፡፡ እንዴት? ቢባል ሰው ሊመሰገን የሚችልበት አጋጣሚ እንደሚኖር ሁሉ የሚወቀስበት ተግባርም ሊፈጽም የሚችል ፍጡር ነውና፡፡ በመሆኑም ቆሮንቶሳውያንን አስቀድሞ “ወአእኵተክሙ አኀውየ እስመ ዘልፈ ትዜከሩኒ ወዘከመ መሐርኩክሙ ትትሐረሙ ከማሁ ተዐቀቡ፡፡” ትርጉም፡- “ወንድሞች ሆይ፥ በሁሉ ስለምታስቡኝና አሳልፌ እንደ ሰጠኋችሁ ወግን ፈጽማችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።” አላቸው (1ቆሮ. 11፥2)፡፡ እዚያው ምዕራፍ ላይ መልሶ “ወዘኒ ዘነገርኩክሙ አኮ ዘንዕድኩክሙ እስመ ኢተሐውሩ ለእንተ ትኄይስ ዘእንበለ ዳዕሙ ውስተ ዘይተሐት” ትርጉም፡- “ነገር ግን በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚከፋ እንጂ ለሚሻል ስላልሆነ ይህን ትእዛዝ ስሰጥ የማመሰግናችሁ አይደለም” አለ (1ቆሮ. 11፥17)፡፡ ልክ እንደዚሁ እኛም ከዚህ በፊት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በሀገረ ስብከቱ እየተፈጸሙ ባለው ሙስና ዋና ተዋናይ መሆናቸውን ጠቅሰን ወቅሰናቸው እውነትንም ገልጠን ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ አንዳንድ እርምጃዎችን እየወሰዱና ለውጦች እየታዩ መሆናቸው ስላስደሰተን ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን እየሠሩ ስላለው መልካም ጅምር ልናመሰግናቸውና ይበርቱ ልንላቸው ወደድን፡፡ ቀድሞውንም ቢሆን የሥራ አስኪያጁን ስም በከንቱ ለማጥፋት ብለን ሳይሆን እውነቱን ለመግለጥ በመሆኑ ሲያጠፉ ወቀስናቸው፡፡ አሁን ሲያለሙ ደግሞ ልናበረታታቸው ይገባል፡፡ እርሳቸውም ነገሩን በዚህ መልክ ይረዱልናል ብለን ተስፋ እንደርጋለን፡፡  

ለውጡ የታየው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ሲሆን ለዓመታት በገዳሙ ውስጥ ሲፈጸም የቆየውን ሙስና እርቃኑን ያሳየውን ሥራ ማየት የቻልነው ከቅዱስ ፓትርያርኩ ወደፓትርያርኩ ረዳት ሊቀጳጳሱ አቡነ ቀሌምንጦስ ከእርሳቸው ወደ ቀሲስ በላይ በተላለፈው ትእዛዝ ቀሲስ በላይ በገዳሙ ውስጥ በቢሮ ሠራተኞችና በካህናቱ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት በአካል ተገኝተው ጉዳዩን ለማጣራት የሄዱበት መንገድና ያቀረቡት መፍትሔ ከፍተኛ ውጤት ስላስገኘ ነው፡፡ ዛሬ ለሥራቸው ይበል ለማለትና ለማድነቅ እንዲሁም ይኸው አሠራር ሙስናው በተንሰራፋባቸው ሌሎች አድባራት እንዲሠራበት እንዲያደርጉ ጥቆማ ለመስጠት ነው ይህን ጽሑፍ ይዘን የተመለስነው፡፡ ለውጡ እዚሁ ብቻ ከቀረና ብልሹ አሠራሩ በሌሎቹ አድባራትና ገዳማት ከቀጠለ ውጤቱ ተመልሶ እዚያው መሆን ነውና፡፡
በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ውስጥ በቢሮ ሰራተኞችና በካህናቱ መካከል ውዝግብ የተፈጠረው “የገዳሙ ገንዘብ እየተዘረፈ ነውና ገንዘቡን ሲዘረፍ ዝም ብለን አናይም፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር መስፈን አለበት” ባሉት ካህናትና “አላሰራ ብለውናልና ወደሌላ ደብር ይቀየሩልን” በሚሉት የቢሮ ሰራተኞች መካከል ነው፡፡ የቢሮ ሰራተኞቹ ማልደው ወደሀገረ ስብከት አቤት ማለታቸው ሲታወቅ ካህናቱ ደግሞ ከሁለት ተከፍለው ግማሾቹ ወደ ሀገረ ስብከት ግማሾቹ ደግሞ ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ አቤት ብለዋል፡፡ ወደፓትርያርኩ እንዳይገቡ ግን በተለይ በንቡረ እድ ኤልያስ በኩል ክልከላ ተደርጎባቸው የነበረ ቢሆንም የኋላ ኋላ መግባታቸውና ማልደው የተነሡትን የቢሮ ሰራተኞቹን መቅደማቸው አልቀረም፡፡ ንቡረ እድ የተማሩ ሆነው ሳለ እንዲህ ላለው መልካም ነገር ቀና አለመሆናቸው በእጅጉ ያሳዝነናል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩን በብዙ ሁኔታ የሚጠቅሙ ቢሆኑም በሌላ አቅጣጫ እያደረጉ ያለው ነገር ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዳይሆኑ የሚያጓትትና በብዙዎች ዘንድ ፓትርያርኩን የሚያስወቅስ እንዳይሆን ሥጋት አለን፡፡
ወደዋናው ጉዳይ ስንመለስ በሁለቱም ወገኖች በኩል የቀረበ አቤቱታ ቢኖርም ወደፓትርያርኩ የገቡት ካህናት በአቤቱታተቸው መሠረት ማጣራት እንዲደረግና አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው በፓትርያርኩ ትእዛዝ በመሰጠቱ ምክንያት ከሊቀጳጳሱ ወደ ቀሲስ በላይ በተላለፈው ትእዛዝ መሰረት ራሳቸው ቀሲስ በላይ በገዳሙ በአካል በመገኘት የችግሩን መንስኤ ከመረመሩ በኋላ ምክንያት የሆነው የሙዳየ መጽዋት ቆጠራ ራሳቸው ካህናቱ ባዋቀሩት ኮሚቴ አማካይነት እንዲከናወን በተወሰነው መሠረት ከኅዳር ማርያም የሚገባው የገንዘብና የዓይነት ስጦታ ከዚህ ቀደም በገዳሙ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ትልቅ ውጤት አስገኝቷል፡፡ ይህም ከዚህ ቀደም በደብሩ ገብቷል ከተባለው ትልቅ ገንዘብ ጋር ሲነጻጸር ከሁለት እጥፍ በላይ ነው፡፡ ከገንዘቡ ይልቅ በተጨማሪ የቢሮ ሠራተኞች ገንዘብ ያጋብሱበታል በሚባለው የጧፍና የንዋየ ቅድሳት ሽያጭ ላይም ተመሳሳይ እርምጃ በመወሰዱ የቤተክርሰስቲያን ገንዘብ ከአማሳኞች እጅ ሊጠበቅ ችሏል፡፡ በየወሩና በክብረ በዓላት መጠኑ የማይታወቅ ገንዘብና በስጦታ ከሚገባው ንዋየ ቅድሳት ሽያጭ ያለተቆጣጣሪ ሲመዘብሩ የቆዩት የቢሮ ሰራተኞች በዚህ ደስ አልተሰኙም፡፡ ደስ አለመሰኘታቸውን በተደጋጋሚ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለቆጠራው የመጡ ልኡካን ላይ ቁልፍ ይዘው በመጥፋታቸውና እንቅፋት በመፍጠራቸው አስመስከረዋል፡፡ በዚህ መንገድ ደስ ባይሰኙም የኅዳር ማርያም ገቢ ግን ከእነርሱ ምዝበራ ስላመለጠ ይህ ዓይነቱ ትግልና ውጤቱ ብዙዎቹን ደብሮች እያነቃቃ ነው፡፡ ምንም እንኳ መዝባሪ በሆኑ በብዙዎች አለቆች ፀሐፊዎች ሂሳብ ሹሞችና በአጠቃላይም የቢሮ ሰራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን ቢፈጥርም በተገኘው ውጤት በሙስና የተማረሩ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ግን እጅግ ተደሰተዋል፡፡
ከመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እንቅስቃሴ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ በቀጨኔ መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን በቢሮ ሰራተኞችና በካህናቱ መካከል ተመሳሳይ ውዝግብ ተፈጥሮ በካህናቱ አሸናፊነት አስደናቂ ውጤት የታየ ሲሆን በዚህ ውዝግብ ውስጥ አንዱ የቢሮ ሰራተኛ አንዱ ደግሞ የቤተ መቅደስ አገልጋይ በሆኑ ወንድማማቾች መካከል ጠብና መለያየት ጭምር እንደተፈጠረ እናውቃለን፡፡ ይህም ሁኔታ ሙስናን ከቤተክርስቲያን ለማስቀረት በሚደረገው ተጋድሎ የአንድ አባትና እናት ልጆችን ሳይቀር እስከማለያየት መድረሱ የቤተክርስቲያንን ገንዘብና ንብረት ከሙሰኞች እጅ ለማዳን የተጀመረው ተጋድሎ ምን ያህል እየጠነከረና በታማኞችና በዘራፊዎች መካከል ውጥረቱን ምን ያህል እያነገሠው እንደመጣ አመላካች ሆኗል፡፡ እንዲህ ባለው ተጋድሎ በተጠቀሱት በሁለቱ ደብሮች ዘንድ ውጤት እያሳየ ያለው ሙስናን የማስወገድ እንቅስቃሴ በሌሎችም ደብሮች እንዲቀጥል የብዙዎች ተስፋና ፍላጎት ነው፡፡ ሌሎቹ አድባራትና ገዳማት ከሁለቱ ደብሮች ተሞክሮ መማር ያለባቸው የቤተክርስቲያንን ገንዘብና ንብረት ከመዝባሪዎች ለመታደግና በዚህ አቅጣጫ ዘወትር በመጥፎ እየተነሣ ያለውን የቤተ ክርስቲያንን ስም ለመጠበቅ ተጋድሎ ማድረግ ያለባቸው ራሳቸው ካህናቱና ዲያቆናቱ መዘምራኑም ናቸው እንጂ ሌላ አካል አይደለም፡፡ እነርሱ መብታቸውን ለማስከበር ከተንቀሳቀሱ ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆኑ ሌሎቹ ረዳት ሊቀጳጳሱ ለመፍትሔ እንደሚንቀሳቀሱ እሙን ነው፡፡ ባለቤት ካልጮኸ ግን ጎረቤት አይደርስምና፡፡    
ለሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ የምናስተላልፈው መልእክት ሥራ አስኪያጅነትዎ በሚሰጥዎ ሥልጣን በመጠቀም በእነዚህ ደብሮች ያሳዩትን ትጋትና ችግሮቹን ለመፍታት የሄዱበትን መንገድ በእዚህ ብቻ ወስነውት እንዳይቀሩ አደራ እንላለን፡፡ በተለይም በጠራራ ፀሐይ እጅግ ከበድ ያለ የሙስና ወንጀል የሚፈጸምባቸውን አድባራት በተለይም ጎፋ ገብርኤልንና ብሔረ ጽጌ ማርያምን በአፋጣኝ እንዲመለከቱና አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡ ጥሪያችንን ማስተላለፍ እንወዳለን፡፡ እንዲህም ስንል በሁለቱ ደብሮች የተደረገውን ዓይነት ማስተካከያ ለመውሰድ የየደብሮቹን ጥሪ ከመጠበቅና ችግር ሲፈጠርና ሁከት ሲበዛ ለመገላገል ከመሄድ ሁሉም የሚመራበትን ሥርዓት መዘርጋቱ አማራጭ የለውምና ሥርዓት ወይም ሲስተም መዘርጋቱ ላይ ትኩረት ቢደረግ ችግሩን ለመፍታት አማራጭ የሌለው መንገድ ከመሆኑም በላይ ቀሲስ በላይን እጅግ የሚያስመሰግናቸው ሥራ ሆኖ ይኖራል የሚል እምነት አለን፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረስብከት አድባራትና ገዳማት የምንገኝ ግፉዓን

13 comments:

 1. ምነው ገርጂ ጊዮርጊስን ብትመለከቱት፣ መቃብር ቦታ ሳይቀር ሸጠው መኪና የሚሸላለሙበት ሙስና አይበቃልም ማለት ነው፡፡
  እኛ እንደሰማነው ሌብነቱ ሁሉ ምርቃትነና መልካም ስራ እንዲመስል እነ ንቡረ እድ ኤልያስና ዜና ቤተ ክርስቲያን አዘጋጆችም የድራማው ተዋናዮች መሆናቸውን እናውቃለን፡፡

  ReplyDelete
 2. ለእንደናንተ አይነቱ የጥፋት መልክተኛ አይደለም
  ቤተክርስቲያንና ማህበረ ቅዱሳን እኔም መልስም
  አስተያየትም መሥጠት ተገቢም አሥፈላጊም
  አይደለም።ምክንያቱም እናንተ ከጥፋት ውጭ
  ምንም አይነት ነገር ለመማርም ሆነ መለወጥ
  ስለማትችሉና ለመልካም ነገር ልባችሁ የተከፈተ
  አይደለምና ነው።እግዚአብሔር ሰውን በመፍጠሩ
  እንደ ተፀፀተ ይነግረናል።የተፀፀተው ሰውን
  በፈጠረበት ሁኔታ ሳይሆን ሰው የተባልነው
  ከተፈጠርንበት አላማ ወጥተን ጠላት ዲያብሎሥ
  ከሚሠራው ጥፋት እጅግ በፈጠነ ለጥፋትና ለተንኮል
  የፈጠንና የተጋን በመሆናችን ነው።አምላክን ፍቅር
  ሥቦት ወደዚህ አለም መጥቶ ለመሥቀል ሞት
  የታዘዘው በእኛ ክፉ ስራ እንጂ እሡ እግዚአብሔርማ
  ምን ሀጢያትና ጉድለት ይገኝበታል።ሙሠኛ፣
  ዘማዊ፣ዘረኛ፣ነፍስ ገዳይ፣አሸባሪ፣ተላላኪ ሌላም
  ሌላም ተቀፅላ እየሠጣችሁ ትንሽ ትልቅ ሳትሉ
  የጥፋት በትራችሁንና ሠይፋችሁን በንፁሐን ላይ
  ለመሠንዘርና ለማሥወርወር ያላደረጋችሁት ሙከራ
  የለም።ደሚገርመው ምግባረ ክፉነን በሥም ይደግፋ
  ሆነና አባ ሰላማ ብላችሁ እራሳችሁን
  ሠይማችኇል።ለመሆኑ ክርስትና ማለት ለእናንተ
  የዋጃችሁን አምላክ መቃወም፣የንፁሐንን ደም
  ማፍሰስ፣እውነትን ማሳደድ፣በአጠቃላይ በክፉ
  መንፈስ እየተነዱወንጀልን ማራመድ ነውን? እረ
  ክርስትና ማለት በክርስቶስ አምኖ ሥለእውነት
  መቆምና መመሥከር ፣ጠላትን
  መውደድ፣በአጠቃላይ የመንፈስ ቅዱስን ፍሬ
  ማከናወን ነው።ቃየል ወንድሙን አቤልን የገደለው
  እንደ አቤል በእግዚአብሔር ባለማመኑና በክፉ ቅናት
  በመቃጠሉ ነበር።ዛሬም እናንተ በቃየል ጎዳና
  የምትሔዱ የክርስቶ የሆኑትን የምትገሉና በሀሠት
  መንፈስ የምትከሱ ቃየሎች ናችሁ።በሙስሊም
  ወንድማማቾች በኩል ተጠማዠዛችሁ የመጣችሁበት
  የማመሳሰል ተግባር በጣም ምን ያህል ለመዳን
  የማትፈልጉ ለጥፋትና ተንኮል የተጋችሁ መሆናችሁን
  ነው።በእርግጥ ስለሙስሊም ወንድማማቾች
  የጻፋችሁት ምን ያክል እውነት እንደሆነ ለመቀበል
  አዳጋች ነው።ምክንያቱ ከባህሪያች ሥነሣ እውነት
  ሥለማትናገሩና ሥለማትፅፉ ነው።ለምሳሌ
  ሙስሊም ወንድማማቾችንና ማህበረ ቅዱሳንን
  ለማመሳሰል የሞከራችሁበት ማህበር በምትለው
  ለየትኛውም ሥብሥብ መግለጫነት
  የምታገለግለዋን ቃል ነው።የሚገርመው ግን ሁለቱ
  በአላማ በየትኛውም መለኪያ ወይም መመዘኛ
  ሊነፃፀሩ አይችሉም ።ሙስሊም ብራዘር ሁድ
  ለምድራዊ ሥልጣን የሚታገል የፖለቲካ ድርጅት
  ወይም ማህበር አኛ አናንተ በማህበርሠለሠላችሁት
  መሆኑ ለማንም የተደበቀ አይደለም።ማህበረ
  ቅዱሳን የቅዱሳን አባቶችን አሰረ ፍኖት ተከትሎ
  የቤተክርስቲያን አገልግሎት ከአባቶች መመሪያን
  በመቀበል ለማገዝና ለማሥፍት ግቡም
  የእግዚአብሔር መንግስት ሠዎች እንዲያገኙ
  የተቋቋመ መንፈሳዊ ማህበር ነው።ማህበሩ አባላት
  አሉት፣ማህራዊ አገልግሎቶችን ይሰጣል፣ አባላትን
  ይመለምላል ምናምን የምትሉት ቅናትና የናንተ
  የጥፋት መተግበሪያ በራችሁ በእግዚአብሔር ሀይል
  ሥለ ተዘጋባችሁ ተናዳችሁ እንጂ አንድ አካል
  ወይም ግለሠብ ማህበር ሊሆንም ተብሎ ሊጠራም
  አይችልም።መንግስትን ያጭበረበርንና ያታለልን
  መሥሏችሁ ትርኪምርኪ ታናፍሡና ፅፋችሁ
  ትበትናላችሁ።መንግስት ማንኛውም መንፈሳዊም
  ይሆን ፖለቲካዊ ማህበር ወይም ተቋም ያመነበትን
  እምነትና አሥተሣሠብ የሌላውን ተቋም ሳያውክ
  በሠላማዊ መንገድ የማራመድ መብትን
  ሠጥቷል።ሥለዚህ የሙስሊም እምነት ተከታይ
  ወንድሞቻችንም አምነታቸውን በሠላማዊ መንገድ
  ለመደገፍ ይህን መብት ማድረግ እንደሚችሉ
  መንግሥት የሠጠው መብት ነው።ደግሞ መንግሥት
  በምነት ተቋማትን ለአማንያኑ የተወ መሆኑም
  መታወቅ አለበት።ለማንኛውም የእናንተን ተንኮልና
  የቁራ ጬኸት መንግሥት የሚሠማበት ጀሮ
  የለውም።እናንተ ተዋህዶንና የክርስቶሥ የሆኑትን
  ለማዳከምና ለማጥፍት መሆኑ ይታወቃልና ተዋጊው
  እግዚአብሔርም ሥለ ቤተክርስቲያንና ሥለ
  አገልጋዮቹ እንዲሁም ህዝቦቹ ይዋጋልና
  አይሆንላችሁም።የማሳችሁትም ጉድጏድ የናንተው
  መቀበሪያ መሆኑ አይቀርም በንሥሀ
  ካልበመለሣችሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የአስተያየቱ ፀሐፊ ባለቤትDecember 9, 2014 at 5:33 PM

   ዉድ አናነመሥ ሆይ ይሔን አስበያየት በኮፒ ፔስተ ገልብጠህ(ሽ) ለዚህ ጽሑፍ አሥተያት መሥጫ ላይ መለጠፍህ(ሽ) ለምን እንደሆነ አልገባኝም። ይሔን የአሥተያየት በዚህ ብሎግ ላይ ለወጣ የጥፍት ጽሑፍ ተዋህዶ በሚል የስም ፕሮፍይል የሠጠሁት አስተያየት ነው።ለምን ለዚህ ጽሑፍ አስያየት እነደተጠቀማችሁበት ብትገልጡልኝ?ለዚህኛው የወተት ዝምብ ለሆነው የአባ ሠላቢዎችና አማሣኞች የአሥመሣይነታቸው ጽሑፍም "ዝም አልልም" በሚል የሥም ፕሮፋይል ሥር አሥተያየቴን ለለጊወኖች ሠጥቻለሁኝ።

   Delete
 3. "ንቡረ እድ የተማሩ ሆነው ሳለ እንዲህ ላለው መልካም ነገር ቀና አለመሆናቸው በእጅጉ ያሳዝነናል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩን በብዙ ሁኔታ የሚጠቅሙ ቢሆኑም በሌላ አቅጣጫ እያደረጉ ያለው ነገር ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዳይሆኑ የሚያጓትትና በብዙዎች ዘንድ ፓትርያርኩን የሚያስወቅስ እንዳይሆን ሥጋት አለን፡፡" This is the most funny statement:) An absolute confirmation that the article is writter by ንቡረ እድ himself.

  ReplyDelete
 4. ዝም አልልምDecember 8, 2014 at 9:19 PM

  ጳውሎስንም አውቀዋለሁ ኢየሱስንም አውቀዋለሁ እናንተ ግን ማን ናችሁ?
  ይሄን የግብር አባታችሁን ምስክርነት ሀይለቃል የተጠቀምኩበትኝ እናንተን በደንብ አድርጎ ሥለሚገልጥ ነው።የግብር አባታችሁ ዳቢሎሥ ይህን ምሥክርነት የተናገረው የሐዋሪያው ጳውሎስ ጨርቅ አጋንትን ሲያሥወጣና በሽተኞችን ሲፈውሥ ያዪት አህዛብ ገንዘብን ለመሰብሠብ ሲሉ የሐዋሪያውን ጨርቅ ቀደው በአጋንት በተያዙት ላይ ባደረጉ ጊዜ ዳቢሎስ ተናገራቸው እናንተ ማን ናችሁ ብሎ።እናንተም አለማዊና የአለምን ነገር የምትወዱ የአባታችሁንም የዳቢሎሥን ተግባር የምትሠሩ ሆናችሁ ሳለ ክርስቶስ በደሙ ስለመሠረታት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀሳብና ትችት የምትሠጡ ማን ናችሁ።አንደበታችሁን ሳትገሩ ከሚጋልባችሁ ከዳቢሎሥ በረቀቀ የሥድብ ውርጅብኝና ክስ ንፁሐንን ስትደበደቡና አሁንም ክፉ ሥራችሁን በመተግበር ላይ ያላችሁ እንደሆነ ይታወቃል።እናንተ በውስጣችሁ ምንም አይነት የእምነት ፍሬና ሥራ የሌለባችሁ ሐሳባችሁ ምድራዊ እንደሆነ ግልጽ ነው።ደሞ እናንተን ብሎ ነቃፊና ምክር ሰጭ።መጀመሪያ እራሳችሁን አጥሩና እውነትን ተቀበሉ አሉባልታንና ሐሰተኛ ውንጀላችሁን አቁሙ።የተማሩ ገለመሌ እያላችሁ የምትቀባጥሩበትን ማማለያ አይሉት መደለያ የመንፈሳዊነትንና እውነተኛ አገልጋይነትን በመንፈስ ቅዱስ ሐይል ካልተመራ ና ካልተባረከ በሥተቀር ብቻውን ሊያንፀባርቅም ሆነ ሊገልፅ አይችልም።እውቀት በእምነት በመንፈስ ቅዱስ ካልታነፀና ካልተመራ ከንቱ ነው።ብዙ ብሮፌሰሮች ሳይንቲስቶች ይገኛሉ።ነገር ግን ይህ አለማዊ እውቀታቸው የመንፈሳዊነት መለኪየ አየሆንም።ለክፉ ስራችሁና ለክህደታቸሁ መግቢያና መሥፈፀሚያ ለማግኘት በእባብ ገላችሁ ትሽሎከለካላችሁ።ሆኖም እግዚአብሔር ቤቱን በሚንበለበል የእሳት ሠይፍ አጥሯታልና አይሆንላችሁም።

  ReplyDelete
 5. xba selamawoch enamesegenalen chetacenene selecoculene. thank you very much.

  ReplyDelete
 6. You are not authorized to speak about EOTC about St. Mary Church. You do not know St Mary. You have been supporting these people when they opposed the reform in Addis Ababa Curches.!
  First repent and belive in the cred of the Holy Orthodox Church!

  ReplyDelete
 7. ገርጂ ጊዮርጊስን ለምን ዘነጋችሁት ያልከው ሰውዬ እውነት ብለሀል፡፡ ዋናው የሙስና ቤት ሆኗል፡፡ ከየትኛውም ደብር የበለጠው ዘረፋ ያለው ገርጂ ጊዮርጊስ ነው ፡፡ንቡረ እድ ኤልያስማ የምስጥር ቤቱ ነው፡፡ ለምን ብትሉ የእለት ገንዘብ ተቀባይ፣ ሂሳብ ሰራተኛ ሆነው ቀደም ብሎ የተቀጠሩት፣የሚስቱና የእሱ ዘመዶች ናቸው ፡፡ አለቃና ጸሀፊ ቦታው ላይ ሲመደብም ከእነሱ ምስጢረኛ ሆኖ ለንቡረ እዱ ገንዘብ ያቀባብላል፡፡ አሁንማ የደብሩን ይዞታ በሙሉ ለ20 ለ10 አመታት እያሉ በዘመዶቻቸውና በወዳጆቻቸው ተከፋፍለውታል፡፡

  ReplyDelete
 8. ምነው ምነው ዛሬ ማቅን ሳትጠሩት?

  ReplyDelete
 9. What abt Merkato Debre hail St.Raguel church?????

  ReplyDelete
 10. Please read what is happening in Atlanta on http://www.mahtote-berhan.com/
  There is a bishop and his relative that are giving the congregation hell.

  ReplyDelete
 11. በእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ስላሴ ያለውንስ ጉድ ማን ይመልከተው ይሆን? የቤተ ክርስቲያኒቱን መሬት ለግል ባለሀብት እየቸበቸቡ ቤተ ክርስቲያኒቱንና ማህበረ ካህናቱን ራቆታቸውን ሲያስቀሩ እነሱ ግን የቪላ ቤትና የቤተ መኪና ባለቤት ሆኑ። እረ ግፍ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈጸመው ግፍ ማብቂያው መቼ ይሆን?

  ReplyDelete