Sunday, December 21, 2014

የማኅበረ ቅዱሳንና የተላላኪ ጳጳሳቱ ስውር አጀንዳ ሲጋለጥከመርጌታ ልሳነ ወርቅ

በጥቅምቱ የሲኖዶስ ስብሰባ ማኅበረ ቅዱሳንን አስመልክቶ በማኅበሩ የውስጥ አርበኛ ጳጳሳትና በቅዱስ ፓትርያሪኩ መካከል ብዙ አስገራሚ ውይይቶችና የጦፉ ክርክሮች እንደተስተናገዱ ይታወሳል። ከብዙ ንትርክና ትርምስ በኋላም ማኅበሩ በሕገ ቤተ ክርስቲያን መመራት፤ በቤተ ክህነቱ ሞዴላሞዴሎች መጠቀም አለበት የሚለው ሀሳብ በመላው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ስምምነት ላይ ተደርሶ መወሰኑ የሚታወቅ ነው።ይሁን እንጂ ውሳኔውን ተከትሎ ማኅበሩና የማኅበሩ የውስጥ አርበኛ ጳጳሳት ቅሬታ ውስጥ ስለገቡ ቅዱስ ሲኖዶስ እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ሀሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ተጠቅመው ማኅበሩ ከቤተ ክርስቲያንዋ ሕግ ውጭ የሚመራ፤ አሥራት በኩራቷን በሕገ ወጥነት የሚሰበስብ መሆኑንና የመሳሰለውን ድርጊቱን በአጋለጡት ካህናት ላይ የበቀል እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቁ። ሆኖም ቅዱስ ፓትርያሪኩ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪዎችና ኃላፊዎች በስብሰባ ላይ የመሰላቸውን ሀሳብ የመስጠት መብታቸው ሲሆን ሀሳባችሁን በነጻነት የመግለጽ መብታችሁን ለምን ተጠቀማችሁ ማለት አግባብ አይደለም በማለት ውድቅ ማድረጋቸው ታውቋል።

ይኽ በማኅበሩና በማኅበሩ የውስጥ አርበኛ ጳጳሳት የቀረበው የበቀል እርምጃ በቅዱስ ፓትርያሪኩ ተቀባይነት ስለአላገኘ አባ ሉቃስና አባ ማቴዎስ ጉዳዩን ከጫፍ ለማድረስ ሥውር ደባ ሠሩ። አስገራሚው ነገር ይኽ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነ እንኳ ቢሆን ተፈጻሚነት ሊኖረው የሚገባው በዋና ፀሐፊው በኩል ሲሆን አባ ማቴዎስ በጣልቃ ገቢነትና በማይመለከታቸው ተግባር የበቀሉን እርምጃ ተፈጻሚነት እንዲኖረው በቀጥታ ለአባ ቀለምንጦስ የአዲስ አባባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጻፉ። ሆኖም ይኽ ሕገ ወጥ ተግባር ወዲያውኑ ስለተደረሰበት የበቀል ምኞቱ ሳይፈጸም ከሸፈ።

ሌላው አባ ማቴዎስንና አባ ሉቃስን ትልቅ ትዝብት ላይ የጣላቸው በእውነት ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ክብር መነካት ተቆርቁረው አለመሆኑ ነው። ቢሆን እንኳ በማኅበሩ በኩል የቅዱስ ፓትርያሪኩ መዘለፍ ለምን አልተሰማቸውም ነበር? የቅዱስ ፓትርያሪኩ መዘለፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብር መስሎ ካልታያቸው ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም የተሰነዘረው የካህናቱ ሀሳብ በምን ዓይነት መመዘኛ ታይቶ ነው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ተነካ የተባለው? ይሁንና በጉዳዩ በስተጀርባ ያለው ድብቁ አጀንዳ መሆኑን በተለያየ ጊዜ በማኅበሩ በኩል ሲገለጽ የቆየና አሁንም ሂደቱ በውስጥ አርበኛ ጳጳሳቱ የሚካሔደውን እንቅስቃሴ በግልጽ ያሳያል።

እነዚህ ጳጳሳት የተቀመጡበት ኃላፊነትና የቤተ ክርስቲያን የአባትነት አስተውሎት ቢኖራቸው ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያንዋ ላይ ስለአደረሰው በደል ሥሜታቸውን የገለጹትን ካህናት በሸለሙ ነበር። ምክንያቱም ብዙዎች በጥቅምና በይሉኝታ ታሥረው እውነትን ለመናገር ድፍረት በአጡበት መድረክ እነዚህ ካህናት እውነቱን በአደባባይ መመሥከራቸው ተአማንነት ነውና። እንኳን በቤተ ክርስቲያን መድረክ በአለም እንኳ ይበል የሚያሰኝና ሽልማት የሚያስገኝ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ይኽ ሀሳባቸው ትክክለኛ በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ አምኖበት ውሳኔ የሰጠበት ስለሆነ ይኽ በራሱ የካህናቱ ሀሳብ ትክክለኛነትን ያስረዳል። ሊቃውንቱን ሲያስለቅስ፤ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች ሲያሳድድ፤ የቤተ ክርስቲያንን አንጡራ ሀብት(አሥራት በኩራት) ሲዘርፍ የኖረውን ማኅበር እንዲታረምና እንዲስተካከል በድፍረት መቃወም እውነተኞች ያሰኛቸዋል እንጂ አማሳኞች አያሰኛቸውም ነበር። በሲኖዶስ ደረጃ የቅጣት ውሳኔ የሚያሰጥ ስህተታቸው ምን ላይ ነበር የሚለውን እንድንጠይቅ ተገደናል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከአባቶቻችን ሐዋርያት ጀምሮ መደበኛ ሥራው ሃይማኖትን ማስፋፋትና ለቤተ ክርስቲያን ልማትና እድገት በስፋት መወያየትና ውሳኔ ማሳለፍ ነው። በአሁኑ ሰዓት አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የበዙበት፤ ብዙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ወደ ባዕድ እምነት እየተሰደዱ ባሉበት ጊዜ ጥያቄ አነሳችሁ ተብሎ በግለሰቦች ላይ የበቀል እርምጃ ማካሔድ ኢክርስቲያናዊ እና ኢዲሞክራሲያዊ ነው። በአጭር ቋንቋ ሲቀመጥ አምባ ገነንነት (Dictatorship)ማለት ነው። የአለም ህብረተሰብ ሀሳብን በነጻ የመግለጽን (freedom of speech) በሚያስተጋባበት ዘመን ላይ የነጻነት ባለቤት ከሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምባ ገነናዊ ሥርዓት ማየት እጅግ ያሳዝናል። ቤተ ክርስቲያናችንም የምታስተምረው እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት በሉ ነው። ከዚህ የተለየ የክፉ ነውና። ስለሆነም ኦርቶዶክሳውያን ካህናትና ምዕመናን ቤተ ክርስቲያናችን ወዴት እያመራች እንደሆነ ማስተዋልና እጆቻችንን ወደ ጌታ ማንሳት ይገባናል።

በመሆኑም ከዚህ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን የዘለፉ ካህናት ይቀጡ ከሚለው ጀርባ ያለውን ግልጽ የማኅበሩና የተላላኪዎቹ ጳጳሳት አጀንዳ እንዲሁም የአጀንዳው ትግበራ ፖለቲካዊና ፀረ-ሃይማኖታዊ ተውኔቱን በዝርዝር ስንመለከት፦

·        የተቃውሞ ሀሳባቸውን በሰጡት ካህናት ላይ የበቀል እርምጃ እንዲወሰድ የተፈለገበት ዋና ምክንያት

1)    ለድብቁ አጀንዳ የአዲስ ፓትርያሪክ ናፍቆትና መንገድ ለመጥረግ

ቀደም ሲል በጥቅምት 26/2007 ዓ/ም በአንድ አድርገን ድህረ-ገጽ ታደሰ ወርቁ የተባለው የማኅበሩ ሊቀ መንበር የነበረው ግለሰብ ድብቁን አጀንዳ በግልጽ አስነብቦን አልፏል። ጊዜው ማኅበሩ ክፉኛ የተጋለጠበትና ቅዱስ ሲኖዶስ በማኅበሩ ላይ የመታረም ውሳኔን ያሳለፈበት ስለነበረ የጽሑፉ ፍሬ ሀሳብ በንዴት መንፈስ ምሥጢርን ያፈተለከ ይመስላል። ምክንያቱም ጽሑፉ ድብቁን ምሥጢር ይፋ ከማድረግና የሚያስከትለውን ውጤት ከአለማስተዋል አንጻር የፀሐፊውን ጤንነት ጥያቄ ውስጥ አስገብቶ የነበረ ጽሑፍ መሆኑን ብዙዎች ታዝበዋል። ጽሑፉ የማኅበሩ አጀንዳና የፕትርክና ሥልጣን ህልማቸው ከንቱ የሆነባቸው ጳጳሳት ተልዕኮ የተንፀባረቀበት ሲሆን አጭርና መደምደሚያ ሀሳቡ ግን ኦርቶዶክሳዊ ፓትርያሪክ ያስፈልገናል የሚል ነው። ይኽ ጽሑፍ የማኅበሩን ህልምና በሃይማኖትም የመረዳት ዓቅሙን በድንገት ያፈረጠ ጽሑፍ ነው።

ይኽም ማለት ማኅበሩ እንደ አባ ማቴዎስ ለማኅበሩ ጥቅም ብቻ የሚሠራ ፓትርያሪክ የሚፈልግ መሆኑን ነው። ፍላጎቱም አሁን የተንፀባረቀ ሳይሆን ቀደም ሲል ማኅበሩ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ለራሱ ዓላማ የሚመቹ አገልጋዮችን ማለትም ከዲያቆን እስከ ፓትርያሪክ ለራሱ ሲያመቻች የኖረ መሆኑ የአደባባይ ምሥጢር ነው። አባ ማቴዎስም ይኽንን ተስፋ ስለአደረጉ የቤተ ክርስቲያን ሰላምና መለኮታዊ አደራዋ ሳይታያቸው የፕትርክና ህልማቸውን አንግበው፤ ሰፈርተኝነትንና ማኅበሩን ተንተርሰው፤ ኃላፊነታቸውን ዘንግተው ቤተ ክርስቲያንዋን ሲያምሱ ዓመታት ተቆጠሩ።

በሌላው መልኩ ሲታይ ማኅበሩ የእርሱ አባል ያልሆነ ሁሉ ተሐድሶ ተብሎ እንደሚፈረጅ የምናውቀው ታሪክ ነው። አሁን ደግሞ በሥርዓትና በሕግ ተመራ የሚለው ፓትርያሪክ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም የሚል ነው። በማኅበሩ ልሳን ኦርቶዶክሳዊ ማለት የማኅበሩን ፖለቲካና የንግድ ተግባሩን መፈፀምና ማስፈፀም ነው። የኦርቶዶክስን ትርጉም ከመስጠት አንጻር ማኅበሩ በሃይማኖት ያለው እውቀትና አመለካከቱ ምን ያህል የዘቀጠ፤ ስንቱን ያሳሳተና ለተሳሳቱትም ምክንያት መሆኑን ያሳያል።

“ኦርቶዶክሳዊ ፓትርያሪክ እንፈልጋለን” የሚለው አባባል የእድሜ ባለጸጋ፤ በቅድስና የከበሩ፤ የመልካም አስተዳደር ብቸኛ አስተማሪና አራማጅ የሆኑትን ፓትርያሪክ ማትያስን መቃወም ብቻ አይደለም። ይልቁንም ቤተ ክርስቲያንዋን ማቃለል ሃይማኖቱንም መናቅ ነው። ምክንያቱም በማኅበሩ ሚዛን ኦርቶዶክሳዊ ማለት ሕገወጥነት፤ ለሕግ አለመገዛት፤ በሃይማኖትና በቤተ ክርስቲያን ስም መነገድ ስለሆነ። በእርግጥም ከውጭ የተቃዋሚ ኃይላት ጋር ያለው የማኅበሩ ጽንፈኝነትና ፖለቲካዊ አሠራሩ የፖለቲካ ድርጅት እንጂ የቤተ ክርስቲያን ልጅነት የሌለው መሆኑን ማየት ከጀመርን ቆይተናል።

2)    ሽንፈትና ስውር ደባው የተጋለጠበት ማኅበር እንዲካስ

ሕገወጥነት አሠራሩ እንዳይጋለጥበት ብዙዎችን በገንዘብ አፋቸውን ሸብቦ የኖረው ማቅ ስውር ደባው ሲጋለጥ የደረሰበት ኪሣራ ቀላል አልነበረም። በአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በከፍተኛ ውይይት የዳበረውንና ማኅበሩ በሕግ ይመራ የሚለውን አጀንዳ በሲኖዶስ ስብሰባ ለመቀልበስና ከተሰነዘረበት ተቃውሞ ለማምለጥ ማኅበሩ ያላደረገው ጥረት አልነበረም። በእውነትና ለእውነት የቆሙት ፓትርያርክ ማትያስ ግን ከእውነት ጋር በቆራጥ አቋም ስለጸኑ ውሳኔው ሳይቀለበስ ጸንቷል።

በዚህ አጋጣሚ የመጋለጥና የሽንፈት ኪሣራ የደረሰበት ማኅበሩ ብቻ ሳይሆን ሀሳቤን ያስፈጽሙልኛል በማለት በጥቅም በመደለልና በነውራቸው በማስፈራራት ያስቀመጣቸው ጳጳሳትም ጭምር ናቸው። ስለዚህም ማኅበሩ እንዲካስና እነርሱም ተልዕኮአቸውን ለመወጣት የመጀመሪያ ሥራቸው አድርገው የያዙት ይኽንን የተቃውሞ ሀሳብ በአደባባይ ግልጽ ያደረጉትን ካህናት መበቀል ነው። ይኽን ከአነሳን ዘንዳ እነዚህ በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ያሉትን የማኅበሩ ተወካዮች (አባ ማቴዎስና አባ ሉቃስ)ዋና ምክንያት መግለጽ ግድ ይለናል።

-   አባ ማቴዎስ ስለማኅበሩ ሲነሳ ልዩ ሥሜት ያላቸው መሆኑ ቀደም ሲል በፓትርያሪኩ ላይ በሠነዘሩት የጽርፈት ቃል ለማወቅ ተችሏል። አባ ማቴዎስ ከማኅበሩ ጋር የገቡት ቃል ኪዳን እንዳይፈርስባቸውና ማኅበሩ በየትኛውም ሕገወጥ ሥራው መነካት እንደሌለበት ሲሟገቱ እንዲህ ነበር ያሉት፦ “ማኅበረ ቅዱሳንን መንካት ካላቆሙ እርስዎም እንደ አባ ጳውሎስ ይሞታሉ”። አባ ማቴዎስ የአንድን ቅዱስ አባት ሞት መመኘት ምን ያህል ሥልጣኑን ቢፈልጉ ነው? እንዲህ ዓይነቱን የወረደ ቃልስ ከአንድ ሊቀ ጳጳስ መስማት ምን ጊዜ ላይ ብንደርስ ነው? እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ!!!

የአባ ማቴዎስ የአመራር ችሎታና ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለማኅበሩ የገቡት ቃል ኪዳን ምን ደረጃ ላይ እንዳለ በዚህ ማወቅ ተችሏል። በመሆኑም “ኦርቶዶክሳዊ ፓትርያሪክ እንፈልጋለን” የሚለው የማኅበሩ ዓላማ ይሳካልኛል ብለው መጠበቃቸው ያሉበትን ኃላፊነት ዘንግተው የአንድ ማኅበር ጠበቃ ለመሆን ተገደዋል።
                                
-   አባ ሉቃስ ከማኅበሩ ጋር ያላቸው ንክኪ እንደ አባ ማቴዎስ ተመሳሳይ ሲሆን ልዩ የሚያደርገውና በተለይም ማኅበሩን የተቃወሙትን ካህናት ለበቀል የተነሱበት ምክንያት የሚከተለው ነው። ከአጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ከመደረጉ በፊት ተቃዋሚዎቹ ካህናት አባ ሉቃስን ጨምሮ ከቅዱስ ፓትርያሪኩና ከጥቂት ጳጳሳት ጋር ስብሰባ አድርገው ነበር። በዚህን ጊዜ ከካህናቱ መካከል አባ ሉቃስን ከልጅነት ጀምሮ የሚያውቋቸው ነበሩ። አባ ሉቃስ የማኅበሩ ጉዳይ ሲነሳ በንዴት ብድግ አሉና በቃ አሁን በዚህ ጉዳይ አንወያይም። ጸሎት ይደረግና ስብሰባው ይዘጋ አሉ። ይኽንን ከሰሙ ካህናት አንዱ “ቄስ ሐጎስ ይተዉ እንጂ ሁሉንም ነገር እኮ እናውቃለን አሉ” ይኽም ማለት አባ ሉቃስ መርጌታ ሐጎስ እየተባሉ ትዳር መሥርተው፤ ልጆች ወልደው ይኖሩ እንደነበር መናገራቸው ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አባ ሉቃስ ከማይወጡበት የበቀል አዘቅት ውስጥ ገቡ።

ይኽንን ያሉትን ካህን ይቀጡልኝ፤ አዋርደውኛል ብለው ግለሰቡን ለይተው ለቅዱስ ሲኖዶስ ቢያቀርቡ በአማረባቸው ነበር። ጉዳዩ ፀሐይ የሞቀውና ሰው ያወቀው ስለሆነ ማንሳት አልፈለጉም። ነገር ግን በዚህ ፋንታ በቅዱስ ሲኖዶስ ሉዓላዊነት አሳብቦ የራሳቸውን በቀል መወጣትን መረጡ። 

·        በማኅበሩ የተንኮል መረብ ምክንያት በተላላኪ ጳጳሳቱና በቅዱስ ፓትርያሪኩ መካከል ያለመግባባት ችግር በቤተ ክርስቲያንዋ እድገትና ልማት እንዲሁም መልካም አስተዳደር ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ

ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንዋ ሁለንተናዊ አሠራር መመሪያና እቅድ አውጭ መሆኑ ሲታወቅ ነገር ግን ለቤተ ክርስቲያንዋ ሐዋርያዊ ተልዕኮ መስፋፋትና ልማት የሚያስብበትን ጊዜ በማኅበሩ በኩል ለሚመጣው ተንኮሳ መፍትሔ በማፈላለግ ብቻ ጊዜውን ያባክናል። ጊዜውን የማባከኑ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በሚፈጠረው አለመግባባት የሚመጣው ልዩነት ሌላው የሥራ መሠናክል ነው። ለዚህም ይመስላል ማኅበሩ አንዱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አልፎ ቀጣዩ እስክደርስ አዲስ አጀንዳ በማሰናዳት ይፋጠናል። ተላላኪዎቹ ጳጳሳትም ይኽንኑ የማኅበሩን አጀንዳ ለማስፈጸም ውስጥ ለውስጥ አድማውን ሲያቀጣጥሉ ይቆያሉ። ለዚህ ለማኅበሩ መሠርይ ተግባር እንግዳ የሆኑ አብዛኛዎቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከቅንነትና ከየዋህነት አንጻር ብቻ በመመልከት የተንኮሉ ሰላባ ይሆናሉ።

የሲኖዶሱ ጉባኤም አዳዲስ ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን ሳይመለከት ጊዜውን በኪሣራ ደምሮ፤ ዓመቱን አስቆጥሮ ያልፋል። በውኑ ይኽ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለሲኖዶስ አባላቱ ይታያቸው ይሆን? የቤተ ክርስቲያንዋን ችግር ተመልክተው የተሰማቸውን ሀሳብ በነጻነት የሚሰጡ ግለቦችን መኮነን ወይስ የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም ማስቀደም?

በአሁኑ ሰዓት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያሪክነት ቤተ ክርስቲያን ሰላም አገኘች፤ ወደ ልማትና ወደ ሐዋርያዊ ተልዕኮዋ ፊቷን መለሰች ተብሎ በሚነገርበት ወቅት ምክንያት አልባ ውንጅላው ከማኅበሩ ብቻ መሰንዘሩ ችግሩ የራሱ የማኅበሩ መሆኑን ያሳያል። የቅዱስነታቸው መንፈሳዊ አባትነት፤ ለሰላም ያላቸው ቆራጥ አቋምና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ያላቸው ዓላማ በወዳጆች ብቻ ሳይሆን በጠላትም እየተመሠከረላቸው ነው። አልመው የተነሱበትንም የመልካም አስተዳደር ራዕይ ሁሉም በጉጉት የሚጠብቀው ሲሆን እንቅፋቱ ግን ብዙዎቹን እያሳዘነ ነው።

በእርግጥም ከላይ ያስቀመጥነው የማኅበሩና የተላላኪዎቹ ጳጳሳት ምክንያታቸው የታወቀ ነው። ማኅበሩም ለራሱ የሚመቸውን ፓትርያሪክ ይፈልጋል። ይኽን ተስፋ ያደረጉ ተላላኪ ጳጳሳቱም እግረ መንገዳቸውን የፕርትክናውን እንጄራ ለማብሰል ራሳቸውን ለዚህ እኩይ ሥራ አስገዝተዋል። እዚህ ላይ ማኅበሩ የሚያሽሞነሙናቸው አባ ማቴዎስ ፕትርክናን በምን ሚዛን ተመኙት? መቼም ወደ ጵጵስናው ማዕረግ የደረስኩኝ ያለምንም ሚዛን ከመሆኑም በላይ እንከኔ እየታወቀ ስለሆነ ይኽም ይቻላል ብለው በማመን ይሆን? መልሱን ለራሳቸውና ለማኅበሩ እተዋለሁ። አስፈላጊ ከሆነም ለጵጵስናው እንኳ ብቁ የማይሆኑበት ምክንያትን ወደፊት ማቅረብ ይቻላል።

·        በአሁኑ ሰዓት ግለሰቦችን መነሻ አድርጎ ትንኮሳው ያስፈለገበት ዐቢይ ምክንያት

በአሁኑ ሰዓት ቤተ ክርስቲያን እንድትተገበር ቅዱስ ሲኖዶስ ያስቀመጠላት እጅግ ብዙ ፕሮጀክቶች እያሉ የሰላም ማደፍረሻ የሆነው ትንኮሳ ያስፈለገበት ምክንያት ሳይታለም የተፈታ ነው። ይኽም የውጭ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች የሚጠቀሙትን ዘዴ በመከተል ሕዝቡ ለምርጫ በሚዘጋጅበት፤ ፖለቲከኞችም የራሳቸውን ሚና በሚጫወቱበት በአሁኑ ሰዓት ቤተ ክርስቲያንዋን ከተቃዋሚዎች ጎራ ለማሰለፍ የታለመ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል። በተለይም ምርጫው የሚካሔደው በግንቦት ሲሆን የሲኖዶስም የርክበ ካህናት ስብሰባ በግንቦት መሆኑ አመጽ ለመቀስቀስ የጥምረት እቅድ ያለ አስመስሎታል። አልተሳካለትም እንጂ ከዚህ ቀደም በ2006 ዓ/ም ማኅበሩ በዕለተ ስቅለት የአመጽ ሰልፍ መጥራቱ አይዘነጋም። ያለው መንግስት ተመረጠ አልተመረጠ ጉዳዬ ባይሆንም ሁከትን ለማጋጋል ቤተክርስቲያንን እንደመሳሪያ መጠቀምን ግን እቃወማለሁ። ቤተክርስቲያን የተቀላቀለችው ሁከት በቀላሉ እንደማይበርድ የታወቀ ነው።

ለሁለቱ የማኅበሩ የውስጥ አርበኛ ጳጳሳት ያለኝን አጭር መልእክት ሳቀርብ በታላቅ አክብሮት ነው።

ü የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም በማስቀደም ኃላፊነታችውን እንድትወጡ ነው።

ü መንጋውን ትመሩ ዘንድ የተቀበላችሁት የመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን ለአንድ ነጋዴ ማኅበር ሳይሆን መለኮታዊ ተቋም ለሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለሆነ መንጋውን እንድትመለከቱ ነው።

ü ዘመኑ እግዚአብሔር አእምሮ የሰጠው የሰው ልጅ ቀርቶ ጉዑዛን ፍጥረታት የሚናገሩበት የቴክኖሎጂ ዘመን ነው። በመሆኑም ሰውን የመናገር ነጻነትን ማሳጣት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ወንጀል ስለሆነ ከዚህ ይልቅ ለሚሻለው መንፈሳዊ ሥራ እንድትሠሩ ነው።

ü ከእውነት ጋር መወገንና ለእውነት መስራት ዋጋው ሰማያዊ ነውና የሥጋ፤ የሀገር ወገናዊነትን ትታችሁ በእግዚአብሔር ልጅነት እንድትሠሩ ነው።

የቤተ ክርስቲያን አምላክ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅ!!!

10 comments:

 1. እውነትን እውነት ሐሰትን ሐሰትDecember 22, 2014 at 9:44 AM

  እውነቱን ሐሰት ነጩን ጥቁር ለምትሉ ለናንተ ወዮላችሁ!
  አቶ ልሳነወረቅ እኔ እንሿን ልሳነ አጋንንት እያልኩኝ ነው የምገልጽወትና የምጠራወት። መቸም ልሳነወርቅ የሚለውን ስሙን እውነተኞች ሲጠሩበት ሠምተው ወደውትና ተውሰውት ነው እንጅ ለእርስዎ እንደማይገባና ሥምወ እንዳልሆነ ልቦናና ሕሊና
  ካለወት እነሱ ያውቁታል። እኔ ይገባወታል ባልኩት ልሳነ አጋንንት መጠሪያነት እርስዎን እየገለጽኩኝ ነው አስተያየቴን የማሠፍረው። በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ ነውና አቶ ልሳነ አጋንንት እዚህም እዚያም እየዘባረቁና እየተደናበሩ በውሸት ላይ ውሸትን እያመቁ አለማዊ ነውወትና የዚህ አለም ገዠን የንፁሐኑን ደም ማፍሰሻ የጥፋት ጦሮች የሆኑትን የፈጠራ አሉባልታዎችን ወርውረዋል። ደግሞ ሙህር ለመምሰልም አንድ ሁለት የእንግሊዘኛ ቃላትም ወርውረዋል። ለነገሩ የክርስቶስ አገልጋይነትና የክርስቶስ መንግስት ወራሽነት መመዘኛውም ሆነ መለኪያው ምድራዊ የሆነው የዚህ አለም ጥበብና እውቀት ሳይሆን በሞኝነትና በመንፈስ ቅዱስ የሆነው እምነትና አገልግሎት ነው። ደስ የሚለው በፍርድ ቀን ምን ተማርህ የትምህርት ደረጃህስ ምን ነበር ሳይሆን ፅድቅ ሰርተሀል ወይስ ሐጢያት፣ በቅንነትና በእውነት ፈርደሀል ወይስ ፍርድ አጉድለሀል መሆኑ ነው። አቶ ልሳነ አጋንት የክርስቶስ ተቃዋሚ እሱም አባትህና የመሠሎችህ አባት የሆነው የሐሰት ባለቤት ዳቢሎስ ሐሰትን እያራገበና እያሰፍ እውነትንና የእውነት ምስክሮችን ማሳደድና በወንድማማቾች ይኸውም በክርስቶስ አገልጋዮች መካከል ጥልን በመፍጠር መለያየት ማድረግ አላማው ነውና አንተና መሰሎችህም የሱ ሰራዊቶች ናችሁና የሱኑ ሥራ በመተግበር ላይ ናችሁ። አቶ ልሳ አጋንንት ይገርማል ቃላቶችን አልተነተኗቸውም እንጂ ጽፈዋቸዋል። ለነገሩ ሲራገብ ሰሟቸው እንጅ አያውቋቸውም። "ኢክርስቲያናዊና ኢዲሞክራሲያዊ በአጭር ቋንቋ Dictatorship and freedom of speach" ነው ያሉት የኛ ሙሁር አቶ ልሳነ አጋንንት። ምን ማለት ናቸው እነዚ ቃላቶች? በክርስትናስ እንዴት ነው የሚታዮት? ለምን አልተነተኗቸውነበር? ጉድወትና ማንነታችሁን ስለሚያጋልጥ እንደሆነ ይገባኛል። ኢክርስቲያናዊ ማለት ለርስዎ ለሚረግሟቸው፣ በሐሰት ለሚወነጂሏቸው የክፉዎች ቋንቋ እንዳምላካቸው የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው በማለት ዝም ማለታቸው ነውን? ለእርስዎ ተሳዳቢነት፣ ከህደትና ተጠራጣሪነት፣ ምንፍቅና፣ ሐሰተኛ ከሳሽነትና ሌሎች የመንፈስ ፍሬ ያልሆኑት ባዕድ ቋንቋዎች ናቸዉን ክርስቲያናዊ የሚባሉትን? ዲሞክራሲስ ለርስዎ ካለመረጃ ሰዎችን መወንጀል፣ አፍ ስለተከፈተ ዝምብሎ ማውራት፣ መሳደብ፣ ከመንግስት ተቋማት የተገኘን የትምህርት ማስረጃ የውሸት ብሎ ማናናቅ፣ አልቃይዳ አልሸባብ እያሉ የንፁሐኑ ደም ለማፍሰስ በውሸት መዘባረቅ፣ በአጠቃላይ ወንጀልን መተግበር ነውን? የመናገር ነፃነት ማለት አቶ ልሳነ አጋንንት የውሸት መረጃና ሐሰተኛ አሉባልታን መንዛትና የግለሰብንም ሆነ የአንድ ማህበርን ሠባዊና ድርጅታዊ መብትን ማቆሸሽ ነውን?

  ReplyDelete
 2. aba selamawoch eyandandachihu jerbachihu lay binebeb tehadiso ena mezbari yemilc silemayrefa yetsafachihut neger ayidenkegnm mikinyatum kezinb mar aygegnimina

  ReplyDelete
 3. Meri balege Lisane mot,mahberu asgededo genzeb siqebel ayiche semeche alawuqem,and sew asratun lefelegew mestet yichilal,Mahberu yemiseraw yasdesetew meemen asratun befeqadu des bilot esetalehu bil ante men agebah?

  ReplyDelete
 4. We know what you want. your father, Satan gave you the mission of destabilizing, shedding the blood of innocent Christians, dividing the church and teaching heresy. thus why one of your top leader said to the Patriarch"we will die together". the aim is to make the church battle field. Our Fathers are wise. they will not go to such extent. previously they passed the decision that the idol monument you erected in front of the church and the posters you posted in the church compounds are anti-Christ, illegal, foolish and extravagant act. no need of forcing to dismantle or discard them. it is enough for us to know your work. here also no need of punishing the arrogant people. they do not need to be corrected. they do not want it. they knew the truth but denied to follow the path of truth. they are the servants of the worldly kingdom, the servants of money, and the servants of the father of false. they cannot serve two kings at a time. why we worry to force them? we already knew them well,Thanks to the God of our Fathers!

  ReplyDelete
 5. Mahibere kidusan is the same as muslim brotherhood of egypt. Please don't post any mahibere kidusan videos here. Mahibere kidusan is a political organization trying to fulfill it's political agenda under the uumbrella of the ethiopian orthodox tewahido chumurch.

  ReplyDelete
 6. የዚእን ማሀበረ እርኩሳን ወሬ ብታቆሙ! ባጣም ሰልችቶናል እኮ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እርኩስ ባዩ አንተ ማንነህና ነው? አንተን ፈራጅስ አድርጎ የሾመህ ማነው? ብርሀኑን ጨለማ የምትለ አንተ፣ የተቀደሰውን እርኩስ የምትል አንተ፣ ስልጣን ያላቸውን የምትሳደብ አንተ የክፉ አገልጋይ "በመዳራት እርኩሰት ይከተሏቸዋል" እንደተባለ በክህደት መመሳሰል ተባባሪ የሆነህ በሐሰት ትወነጅላለህ። ይህ ደግሞ መልካም አይደለም የሚፈጥን ጥፋት በራስህ ላይ ታመጣለህና።

   Delete
 7. endaw be ewnet Fitsum wushet be menager/be mesbek yetim ayderesim-aba selamawoch ebakachiu we all know who you are?

  ReplyDelete
 8. betcerstyan hulem yemtegodaw endenant ayntu tehadso new yegermal democerasy en betekrrstyann leu hulm alamachu maheberun lematfa new gen egzabher yetekelw ayenkelmen mastewalun yestachu end yehuda genzb amelaky atehn mergetannet tergmu yeh new?

  ReplyDelete