Tuesday, December 23, 2014

መዳን የሚገኘው እንዲህ ነው

“ወበከመ ሙሴ ሰቀሎ ለአርዌ ምድር በገዳም ከማሁ ሀለዎ ለወልደ እጓለ እመ ሕያው ይሰቀል፡፡ ከመ ኵሉ ዘአምነ ቦቱ ኢይትኀጐል አላ ይሕየው ሕይወተ ዘለዓለም፡፡ እስመ ከመዝ አፍቀሮ እግዚአብሔር ለዓለም እስከ ወልዶ ዋሕደ መጠወ ወወሀበ ቤዛ ኵሉ፡፡ ከመ ኵሉ ዘየአምነ ቦቱ ኢይትኀጐል አላ ይሕየው ሕይወተ ዘለዓለም፡፡ …”

“ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።” (ዮሐ. 3፥14-18)

ይህ የወንጌል ክፍል መድኀኒተ ነፍስ ለሚያስፈልጋቸው ኀጢአተኞች የመዳንን መንገድ የሚያብራራ ሲሆን፣ ቃሉን የተናገረው ራሱ መድኀኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረውም በሌሊት ወደ እርሱ መጥቶ ላነጋገረው ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ ለነበረው ለኒቆዲሞስ ሲሆን፣ ዘላለማዊና ሕያው በሆነው ቃሉ በኩል እስከ ኅልቀተ ዓለም ድረስ ደግሞ ለሰው ልጆች ሁሉ እየተናገረ ነው፡፡ በሌላም ምዕራፍ እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።” (ዮሐ. 5፥24-25)፡፡

ከላይ በመግቢያው በተጠቀሰው የወንጌል ክፍል ጌታ የተናገራቸውና ከመዳን ጋር የተያያዙት ሦስት አንኳር ነጥቦች የሚያስተላልፉትን ሰማያዊ መልእክት ቀጥሎ እንመልከት፡፡


1. የሰው ልጅ መሰቀል አለበት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ የወንጌል ክፍል የተናገረው የመጀመሪያ ነገር የሰው ልጅ ክርስቶስ መሰቀል አለበት የሚል ነው፡፡ ለምንድነው የሚሰቀለው? ካልተሰቀለስ መዳን በሌላ መንገድ አይገኝም ወይ? ቢባል፥ መልሱ አዎን ነው፡፡ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰቀለው፥ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” ነው፡፡ ሰው ሊጠፋ የነበረው በኀጢአቱ ምክንያት ነው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች በኀጢአት ከወደቁ ጊዜ አንሥቶ ሰው የኀጢአቱን ውጤት ሞትን ከመቀበል በቀር በራሱ በኩል ተስፋ ቢስ ነበረ፡፡ ስለዚህ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምንበት ሰው እንዳይጠፋና የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው መሰቀሉ የግድ መሆኑን ተናገረ፡፡

ለመዳናችን የእርሱ መሰቀል ዋሳኝ ነገር የሆነው በእርሱ መሰቀል የኀጢአታችን ዕዳ መከፈል ስላለበት ነው፡፡ እርሱ ካልተሰቀለ ዕዳችን አይከፈልም፤ በኀጢአታችን ተጠያቂ እንሆናለን፤ የዘላለምን ሕይወት አናገኝም፤ ወይም እንጠፋለን፣ ማለት ከእግዚአብሔር ተለይተን በዘላለም ሥቃይ ውስጥ እንኖራለን፡፡ ስለዚህ ይህ ሁሉ በሰው ላይ እንዳይደርስ የሰው ልጅ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ ይገባዋል አለ፡፡

ለእኛ መዳን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀል የግድ በመሆኑ ነቢዩ ኢሳይያስ አስቀድሞ “እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።” ብሎ እንደ መሰከረ (ኢሳ. 53፥6)፥ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም “… እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በዕንጨት ላይ ተሸከመ” እንዳለ (1ጴጥ. 2፥24) የኀጢአታችን ዕዳ የተከፈለው በእርሱ ሥቃይና ሞት ነው፡፡ ኀጢአታችን የተወገደው በዚህ መንገድ ነው፡፡ ያስወገደውም መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ የመዳኛው መንገድ እርሱ ብቻ ሆነ፡፡ ከእርሱ በቀር ስለ ኀጢአታችን የተሰቀለልንና የሞተልን ስለሌለ ልንድን የምንችለው በእርሱ የመስቀል ላይ ሥራ ብቻ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእኛን ኀጢአተኛነትና የምንድነው በኢየሱስ ክርስቶስ የቤዛነት ሥራ በኩል ብቻ መሆኑን ነው የሚመሰክረው፤ እንዲህ ሲል፦ “ሁሉ ኀጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ፡፡” (ሮሜ 3፥23-24)፡፡ ደግሞም መዳንም በሌላ በማንም የለም ይላል (ሐ.ሥ. 4፥12)፡፡ ስለዚህ ሰዎች ሁሉ ይድኑበት ዘንድ የተሰቀለው ክርስቶስ ብቻ መሰበክ አለበት፡፡

2. እግዚአብሔር ዓለሙን እንዲሁ ወዷል
በዚህ  የወንጌል ክፍል የምንማረው ሌላው ነጥብ እግዚአብሔር ዓለሙን እንዲሁ የወደደ መሆኑን ነው፡፡ ዓለሙን ስለ ወደደም አንድያ ልጁን ስለ ሰዎች መዳን ይሞት ዘንድ አሳልፎ ሰጠው፡፡ በእግዚአብሔር የተወደደው ዓለም ግን አስቀድሞ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ፍቅር የሆነው እግዚአብሔር የሚወደድ ነገር የሌለውን ኀጢአተኛ ዓለም፥ ማለትም እኛን እንዲሁ ወደደን፡፡ “በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና። ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኀጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” (1ዮሐ. 4፥9-10)፡፡ “ነገር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል” (ሮሜ 5፥8)፡፡

ፍቅር የሆነው እግዚአብሔር የወደደን በኀጢአት የደከምን ደካሞች ሳለን፣ ገና ኀጢአተኞች ሳለን፣ ገናም ጠላቶቹ ሳለን መሆኑ የጠረጋገጠ እውነት ነው (ሮሜ 5፥6፡8፡10)፡፡ በዚህ ሁኔታ የወደደን መሆኑ መቼም ቢሆን እንደማይጠላን ትልቅ ዋስትና ይሰጠናል፡፡ ደግሞም ቃሉ “የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው” ሲል ፍቅረ እግዚአብሔር በምንም ቢሆን የማይለወጥ ጽኑዕ እና ኀያል መሆኑን አረጋግጧል (ዮሐ. 13፥1)፡፡ እግዚአብሔርን እንድንወደው ያደረገው እርሱ አስቀድሞ እኛን የወደደበት አስደናቂና ታላቅ ፍቅሩ ነው (1ዮሐ. 4፥19)፡፡ ጠላቶቹ ሳለን አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ደርሶ የገለጸልን ፍቅሩ እጅግ ታላቅና ጽኑ በመሆኑ፥ ወደ እርሱ ልንቀርብ እንጂ ወደ ኋላ ልናፈገፍግ፣ እርሱን እስከ መጨረሽ ልንከተለው እንጂ በምንም ድካም ውስጥ ብንሆን ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም፡፡ ብንወድቅ እንነሣለን፡፡ ብንዝል እንበረታለን፡፡ ብንሳሳት እንመለሳለን፡፡ ምክንያቱም “እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል፤ አምነንማል።” (1ዮሐ. 4፥16)፡፡  

3. ያመነ ይድናል ያላመነ ይፈረድበታል
መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ የሚያምን ሰው ይድን ዘንድ እርሱ መሰቀል አለበት ብሎ ተናግሯል፡፡ እግዚአብሔርም አንድያ ልጁን አሳልፎ የሰጠው በእርሱ የሚያምን የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፡፡ እግዚአብሔር እንዲሁ ወዶን አንድያ ልጁ እንዲሰቀል ካደረገና ሰው የሚድንበትን ሥራ ካከናወነ፥ ከሰው የሚጠበቀው ታዲያ ምንድነው? ስለ እርሱ መዳን የተከናወነለትን ይህን የቤዛነት ሥራ አምኖ መቀበልና የዘላለማዊ ሕይወት ባለቤት መሆን ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የዘላለም ሕይወት ባለቤት መሆን የሚቻልበት መንገድ ከቶ የለም፡፡ ስለዚህ በእርሱ የሚያምን ይድናል፤ የዘላለም ሕይወትንም ያገኛል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” እንዲሁም “በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል።” አለ፡፡ (ዮሐ. 10፥9)፡፡ በሌሎችም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መዳን የሚገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑ ተጽፏል (ዮሐ. 3፥36፤ ሐ.ሥ. 4፥12፤ ሮሜ 3፥21-24)፡፡
 
መዳን የሚገኘው በኢየሱስ ክርስቶስና በቤዛነት ሥራው በማመን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔርም ሰው እንዲያደርገው የሚፈልገው ዋናና መሠረታዊ ነገር በልጁ በክርስቶስን እንድናምን ነው፡፡ “ትእዛዚቱም ይህች ናት፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ፥ ትእዛዝንም እንደ ሰጠን እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ።” (1ዮሐ. 3፥23)፡፡ ጌታችንም የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? ሲሉ አይሁድ ላቀረቡለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ “ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።” (ዮሐ. 6፥29)፡፡ ሰው የሚድነውና የዘላለም ሕይወት ባለቤት የሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመኑ ብቻ ነው የሚለው እውነተኛ ምስክር ከሆነና “በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም” (ሮሜ 8፥1) ከተባለ፥ በሰው የሚፈረድበትና ወደዘላለም ኵነኔ የሚሄደውም በኢየሱስ ክርስቶስና በቤዛነት ሥራው ባለማመን ምክንያት በሚቈጠር ኀጢአት መሆኑ አይጠረጠርም፡፡ ጌታችን ኢየሡስ ክርስቶስ እርሱ ከሄደ በኋላ መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ሰዎችን ስለ ኀጢአት እንደሚወቅሥ ሲናገር ኀጢአት ሲል የጠራው በእርሱ አለማመን መሆኑን “ስለ ኀጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤” በማለት ገልጿል (ዮሐ. 16፥8)፡፡ በርግጥም ሰው የሚኰነነው የኀጢአት ዕዳውን ሊከፍልልት በመጣውና ሞቶና ተነሥቶ ባዳነው በኢየሱስ ክርስቶስ ባለማመኑ ምክንያት ነው፡፡ ለዚህ ነው “በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።” ተብሎ የተጻፈው (ዮሐ. 3፥18)፡፡

ማጠቃለያ
እንድን ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀሉ የግድ ስለሆነ ኀጢአታችንን ተሸክሞ የእኛን የኀጢአት ቅጣት ተቀብሏል፡፡ እግዚአብሔርም አንድያ ልጁን አሳልፎ የሰጠው በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኝ ነው፡፡ ነቢያትም በእርሱ የሚያምን ሁሉ የኀጢአቱን ስርየት እንደሚቀበል መመስከራቸውን ሐዋርያት ጽፈዋል (ሐ.ሥ. 10፥43)፡፡ ስለዚህ ይህን እውነት ያልተረዳን፣ ማለት ክርስቶስ የሞተው ለእያንዳንዳችን መሆኑን ተገንዝበን ወደእርሱ በእምነት ያልቀረብን  ካለን፣ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” (ማቴ. 11፥28) ለሚለው ሰማያዊ ጥሪ አሁኑኑ በየግላችን ምላሽ በመስጠት ወደ እርሱ በእምነት እንቅረብ፡፡ በየግላችንም ራሳችንንም በፍቅር ለእርሱ እናስገዛ፡፡ ስለ እኔ ሞተሃል፤ ዕዳዬንም ከፍለሃልና አመሰግንሃለሁ በማለት የተቤዠንን መድኀኔ ዓለም ክርስቶስን እናምልከው፡፡ የመልክአ መድኀኔ ዓለም ደራሲ እንዲህ እንዳለ፦
“ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢረከቡ ተፍጻሜተ
መላእክተ ሰማይ ወምድር እለ ለመዱ ስብሐተ
መድኀኔ ዓለም ተወከፍ እንተ አቅረብኩ ንስቲተ
ዘሰተይከ በእንቲኣየ ከርቤ ወሐሞተ
በሞተ ዚኣከ ከመ ትቅትል ሞተ፡፡
ትርጉም፦ ምስጋና ማቅረብ የለመዱ ሰማያውያን መላእክት
መደምደሚያ ላላገኙለት ስምህ ሰላምታ አቀርባለሁ፡፡
በሞትህ ሞትን ታጠፋ ዘንድ
ስለ እኔ ከርቤና ሐሞት የጠጣህ መድኀኔዓለም ክርስቶስ ሆይ
እኔም ያቀረብሁልህን ጥቂት ምስጋና ተቀበል፡፡

(ይህን አንብቦ የጨረሰ አንዳንዱ ሰው ሥራስ ለመዳን አያስፈልግም ማለትህ ነወይ? ሲል መጠየቁ አይቀርም፡፡ ለዚህ ምላሹ ሰው የሚድነው ከላይ እንደ ተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ በመሞቱና ከሙታን ተለይቶ በመነሣቱ በፈጸመለት ቤዛነት ብቻ ነው፡፡ ይህን ያመነ ሰው ይድናል፤ ያመነበት እምነት ሕያው በመሆኑ እምነቱ በሥራ ይገለጣል (ያዕ. 2፥14-26)፡፡ መታዘዝ ወይም መልካም ሥራ በራሱ የሚመጣ ወይም ለብቻው የሚገኝ ሳይሆን ከእምነት የሚነሣ ነው (ሮሜ 1፥5)፡፡ ስለዚህ መዳንን በእምነት የተቀበለና የዳነ ሰው ድኅነትን የተቀበለ መሆኑ የሚታወቀው በተለወጠ ሕይወት ሲመላለስና ምግባሩ የቀና ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ እምነት መጽደቂያ ምግባር ደግሞ በእምነት መጽደቅን መመስከሪያ ወይም መግለጫ ነው)።   

ከመምህር አዲስ

16 comments:

 1. የያዕቆብ መልእክት 2
  17 እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።

  18 ነገር ግን አንድ ሰው። አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።

  19 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።

  20 አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?

  21 አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?

  22 እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?

  23 መጽሐፍም። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።

  ReplyDelete
 2. አዎን እንዲህ ነው

  ReplyDelete
 3. May the Lord Jesus bless you. Thank you for sharing God's Word.

  ReplyDelete
 4. kalehiwe yasemalin

  ReplyDelete
 5. ሐዋርያት የሰበኩት አዳኙ ኢየሱስ ብቻ ነው የኦርቶዶክስ ህዝብ ግን ብዙ አዳኞችን ይከተላል


  ReplyDelete
  Replies
  1. ውድ anonymus ለመሆኑ አዳኝነትን አንተ እንዴት ይሆን አንተ የተማርከው? የኢየሱስ አዳኝነትና የኢየሱስ አገልጋይ የሆኑት የቅዱሳንና የመላዕክት አዳኝነት ልዩነቱና አንድነቱ እንዴት ነው የምትገልፀው። ለመሆኑ "የእግዚአብሔር መላዕክ በሚፈሩት ዙሪያ የሺ የሰፍራል ያድናቸውማል" ይላል ። ለአንተ ለመሆኑ የመላእክት አዳኝነት መነገሩ ምን ይሆን? ደርሶ ጻድቅና ፍፁም መምሰል ከየት የመጣ ነው። የእግዚአብሔር ቃል "የጻድቅ ሰው ነፍስ በስራዋ
   ሀይልን ታደርጋለች" ይላል። ለመሆኑ ለአንተ የጻድቅ ሰው ነፍስ ሐይልን ታደርጋለች ማለት ምን ማለት ነው? ሰይፍ ጎራዴ ፤ ጂዶ ካራቴ፤ ቦክስ ሪሲሊንግ፤ጫማ ጥፊ ቃሪያ ጥፊ ማለት ነውን ለአንተ ወንድም anonymous። "ሐዋሪያት የሰበኩት አዳኙ ኢየሱስ ብቻ ነው የአርቶዶክስ ህዝብ ግን ብዙ አዳኞችን ይከተላሉ " ሲል ውድ anonymous ያላዋቂ ክስ ይከሳል። የክርስቶስ አዳኝነት እኮ በአምላክነቱ ነው። እንዲሁም እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ስራውን ደግሞ በቅዱሳኑ በኩል መስራት ይችላል። ለምሳሌ ጴጥሮስና ዮሐንስ ለፀሎት በዘጠኝ ሰዓት ወደ መቅደስ ሲሔዱ በደጂ ሆኖ ይለምን የነበረውን ጴጥሮስ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሳና ተመላለስ በሎ
   እንዳዳ ነው በሐዋርያት ስራ ላይ ተገልጿል። እዚህ ጋ ሐዋርያቱ ምጽዋትን ይለምን ለነበረው ኢየሱስ ክርስቶስን አንዲያድነው ለምን አይደለም ያሉት። ነገር ግን ሐዋርያው ጴጥሮስ ብርና ወርቅ የለኝም ያመኝን ግን እሰጥሀለሁ ብሎ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ጠርቶ ተነሳና ተመላለስ ብሎ እጁን ይዞ አነሳውና ከሽባነቱ ፈወሰው። ያለውም ሀብት የኢሱ ሀብት የማዳን(የመፈወስ) ሀብት መሆኑን አረጋገጠ። ስለሆነም እኛ ኦርቶዶክሳውያን ቅዱሳኑን አድኑን ስንል ይህ የእግዚአብሔር ሀብት እንዳላቸው ስለምናምን ነው። ሐዋርያው ጴጥሮስ ሌላማ ድንቅ ስራ ሰርቷል። ይኸውም ሐናንያምና ሰጲራ መሬታቸውን ሸጠው ከሽያጩ አስቀርተው ሐናንያም በሐዋሪያው ጴጥሮስ ፊት ባቀረበ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ሐናንያምን መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከሽያጩ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን ስለምን ሞላ?……? እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም አለው ሐናንያም ወደደ ወደያው ወድቆ ሞተ። ሚስቱም በመጣች ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ስለመሬቱ ሽያጭ ዋጋ ጠየቃት። እሷም ዋሸች ቅዱስ ጴጥሮስም አላት "የጌታን መንፈስ ትፈታኑ ዘንድ ስለምን ተስማማችሁ? እነሆ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው አንችንም ያወጡሻል አላት።" ወዲያውም ከሐዋርያው እግር ሥር ወድቃ ሞተች። እዚህ ጋር መታወቅ ያለበት ሐዋርያው ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ወይም እግዚአብሔር ሆኖ አይደለም ነገር ግን የእግዚአብሔ እውቀት የመንፈስ ቅዱስ ፀጋና ሐይል በእሱ ውስጥ ስላለ ነው። እናም እደግመዋለሁ እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ቅዱሳ በእግዚአብሔር ፀጋ የከበሩና ማዳን እንደሚችሉ እግዚአብሔርም በመስቀለ ላይ ከፈፀመው የማዳን ቤዛነት ውጭ ልዩ ልዩ የማዳን ስራውን በቅዱሳኑ በኩል እንደሚፈጽም ስለምናምን ነው ቅዱሳንን አድኑን፣ አማልዱን፣ ጠብቁን፣ ፈውሱን የምንለው። መቸም የፊደል አርበኛው anonymous እና መሠሎቹ የለመዱትን የአላዋቂነት የክህደት ዘፈን አሁን ሞተዋል የሚለውን ያለመረዳት ዘፈናቸውን መልቀቃቸው አየቀርም። ግን መልሱ አለ። ይኸውም እግዚአብሔር የህያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አይደለም። እሱ እራሱ እኔ የአብርሀም፣የያዕቆብ የኢሳቅ አምላክ ነኝ ብሏልና። ውድ anonymous እውነትን መቃወሙን ትተህ እውነትን ታውቅ ዘንድ እንደ ልዲያ ልቤን ክፈተው በል።

   Delete

 6. Who is mahibere kidusan to receive? Mahibere kidusan real name is mahibere seytan.

  ReplyDelete
 7. ሰለ ጌታችን ኢየሱሰ ሲሰበክ ባለብዙ አማልክቶቹ ይረበሻሉ። ወንድማችን አንተ ያሰተማርከን ግን ትክክለኛ ወነገል ሰለሆነ በርታ! እንላለን። ያ የተረት ተረት ዘመን ሰም ጆሮ አጥቷልና።

  ReplyDelete
 8. ወንድሞች ሆይ ሁላችን አስተማሪዎች አንሁን በቃል የማይሠናከል የለምናDecember 25, 2014 at 8:40 PM

  ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በህቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንሿን ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሾልከው ያገባሉ ………(2ኛጴጥ 2፤ 1…)
  ይኸንን የሐዋሪያውን የቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ለአስተያየቴ መግቢያነት የተጠቀምኩት እራሱን መምህር አዲስ ብሎ የሠየመውን ግለሰብ ማንነትና በቃላት ውጊያ የታጨቀውን የጽሑፉን ምንነትና አላማ ይገልፀዋል ብየ በማመኔ ነው ። ሙሉውን የቃሉን መልእክት በማንበብ በእግዚአብሔር መንፈስ አንባቢ ሊመረምረው ይገባል። እኔ በግሌ መምህር አዲስ ባዩን የምገልፀው ሐሰተኛ የሐሰት መምህር ብየ ነው። የሐሰት መምህሩ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን ሐሰተኛ ጽሑፋን እውነተኛ ለማስመሰል ተጠቅሟል። የጠቀሳቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን ግን የተፃፉበትን ሚስጢርና ትርጉማቸውን በመንፈስ ቅዱስ አስተማሪነትና ገላጭነት ተረድቷቸው በማበብራራት አይደለም። ደረቅ የሆነ የማምታቻና የክህደት ማራመጃ ለማድረግ ዝምብሎ ለሐጢያታችን መወገጃ ፣ ለሞታችን መወገጃና ለመዳናችን የእግዚአብሔር ልጅ መሞት ግድ ነበር ብሎ የሐሰት መምህሩ አስቀምጧል። አዎ ግድ ነበር ግን ስለየትኛው ሐጢያት ነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ሞት በፈቃዱ የሞተው? ስለቀደመው በአዳምና በሔዋን ምክንያት አለሙን ሁሉ ከእግዚአብሔር ለለየው ሐጢያት ወይስ የክርስቶስ የመስቀል ላይ አለሙን የማዳን ስራ ከተከናወነ በኋላ ስለሚፈፀም የሐጢያት ሥራ ነው? እነዚህ ጥያቄዎች በግልጽ ነጥረው መመለስ አለባቸው። ጌታችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀላይ ተሰቅሎ ያዳነንና ሸክማችንን ያሥወገደልን በአዳምና በሔዋን ምክንያት ከተፈረደብን የሐጢያትና የሞት እዳ ነው። ነገር ግን ክርስቶስ የቀደመውን በአዳምና በሔዋን ምክንያት የተፈረደብንን የሞት ፍርድ በሞቱ አስወግዶ አርነት ካወጣን በኋላ ግን ለሚፈፀም የአለማመንና የሐጢያት ትግበራ ሁሉ በንስሐ ካልተመለስን ተጠያቂዎች እንሆናለ። ለመሆኑ ክርስቶስ ስለበደላችን ለመስቀል ሞት የታዘዘ ሆኖ የተቤዠንና ከበደላችን ነፃ እንዳወጣን በአሁኑ ዘመን ለማን ነው የሚሰበከው? ክርስቶስ ስለ ሐጢያቴ ሞቶልኛል በማለትስ ብቻ የዘላለም ሕይወት ይገኛልን? አቶ የሐሰት መምህር ምን ይሆን መልሰወት ለነዚህ ጥያቄዎች መልስዎት። ለማንኛውም አሁኑ ዘመን ስለክርስቶስ የማያውቅ አለ ለማለት ከባድ ቢሆንም ከክርስትና እምነት ውጭ ለአሉት ክርስቶስ ወደዚህ አም መጥቶ ከድንግል ማርያም እንደተወለደ፣ በምድር ላይም ያደረጋቸውን የማስተማርና የመፈወስ እንዲሁ የሠራቸውን ታምራቶችና ሰለእያንዳዳችን ስለቀደመው ሐጢያታችን በመስቀል ተሰቅሎ ሞቶ እንዳዳነን መመስከርና የተመሰከረለትም የተደረገለትን አምኖ የክርስቶስን አዳኝነት መቀበል አለበት። የክርስቶስን አዳኝነት ካልተቀበለ(ካላመነ) አሁን ተፈርዶበታል። የተፈረደበት ስለ ጽድቅ ወይም ስለሐጢያት አይደለም በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ባለማመኑ ነው። ክርስቶስ የሞተው የኔን የውርስ ሐጢያት ለማስወገድ ነው ብሎ አምኖ ባለመቀበሉ ነው። በክርስትና ስም ላሉት ክርስቶስን እናውቃለን ሞቶልናል ለሚሉትስ ክርስቶሶ ሞቶልሀልና ሐጢያት የለብህም ሞቶልኛል በይ(በል) በማለት የእምነት ፍሬ ሳይሰሩ፣ በንስሀ ወደ እግዚአብሔር ሳይቀርቡ፣ ሐጢያታቸውን ሳይናዘዙ ካለምንም ምግባርና ምንም አይነት የእውነት ሳይኖራቸው በከንቱ እንዲታበዩ በማድረግ አይደለም። የክርስቶስን አምላክነት የማያምኑ በፍጡር አንጻር የሚገልጡት አንዴ የቃሉን ትርጉ ባለመረዳት ፈራጅነቱን አማላጂ እያሉ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ከፍ ዝቅ የሚያደርጉ እኔና አብ አንድ ነን አብ ያለው የኔ ነው እኔን ያየ አብን አይቷል ብሎ ክርስቶስ የተናገረውን ባለማመን ከአብ ለሚያሳንሱ ከምንም በፊት ኢየሱስ አምላክ፣ ፈራጅ፣ ከአብ ጋር የተካከለ በምንም የማያንስና ሰው በመሆኑ ከአምላክነቱ ምንም ያልጎደለበት ፍፁም አምላክ መሆኑን ማመን አለባቸው። ሌላው የሐሰት መምህሩ አስገራሚ ው ነገር ለመዳን ክርስቶስ ብቻ መሰበክ አለበት ይላል። ምን ማለት ነው? በግርድፉ ሲታይ መልካም ይመስላል ግን እንዴት ነው ክርስቶስ የሚሰበከው? ሞቶልሻል ሞቶልሀል በማለት ብቻ ነው እንዴ? እረ በፍፁም አይደለም። የክርስቶስን ወንጌል በእውነት፣ በፅናትና ባለመጠራጠር ማስተማርና መመስከር ክርስቲያኖች ከሐጢያት እንዲርቁና የእምነት ፍሬ እንዲያፈሩ ምሳሌ በመሆን ነው ። የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖኞቻችሁን አስቡ የእምነታቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው እንደተባለ። ሌላው የሐሰት መምህሩ አስገራሚ የተድበሰበሰ ማደናገሪያ ስራንና መዳንን የገለፀበት መንገድ ነው። "ሰው የሚድነው ከላይ እንደተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ በመሞቱና ከሙታን ተለይቶ በመነሳቱ በፈፀመለት ቤዛነት ብቻነው "ይላል። ይኸን ያመነ ይድናል ከዛ በኋላ እምነቱ ሕያው ስለሆነ እምነቱ በስራ ይገለጣል ይላል። ላይላዩን ለተመለከተው እውነት ይመስላል ነገር ግን ስሕተት ነው። እንደሱ አባባል ኢየሱስ በሞቱ የፈፀመለትን ቤዛነት ያመነ የተፈፀመለትን የሞት ቤዛነት በመሞት በሥራ መግለፅና የእምነቱን ሕያውነትም ማስመስከር አለበት ማለት ነው። የሐሰተኛው ስሕተት ክፉ ፍልስፍና ነው። የክርስቶስን የመስቀል ቤዛነትና መነሳት ማመን ማለት በአዳምና በሔዋን ምክንያት በሞት ተይዘን የነበርነውን በሞቱ ሞታችንን አስወገደ በትንሳየውም ሞተን በስብሰን አለመቅረታችንን በቀኝም ሆነ በግራ ለመቆም መነሳታችንን ማመን ነው። ይኸን ያመነ እግዚአብሔር እንደግዚአብሔርነቱ በማመን የጽድቅ ፍሬ ማፍራትና መፈፀም ነው። የፅድቅ ፍሬ ደግሞ የእምነት ሥራ ነው። አብርሀም አመነ ፅድቅም ሆኖ ተቆጠረለት እምነቱም በሥራ ተገለፀ ተብሎ ተፅፏል። አብርሀም አምላኩ እግዚአብሔር የተናገረውን ልጁን የመሰዋት ትዛዝ በሥራ የፈፀመ በመሆኑ ነው አብርሀም አመነ የተባለው። እንደሁም እምነት ያለሥራ ሥራ ያለ አኛ አምነት የሞተ ነው ተብሎ ተፅፏል። ይህም ማለት እምነትና ሥራ የማይነጣጠሉ በአንድ ላይ የሚሔዱ ናቸው። በአጠቃላይ የሐሰት መምህሩ በቃላት ውጊያ እዚህም እዛም እየረገጡ ሐሰተኛ ትምህርታቸውን በሐሰተኛው ብሎግ አውጥተዋል። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እውነቱን የሺ የግለጥላቸው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Fere kerseki new eyaworah yalehew! Lebehen atadenden. Pls

   Delete
  2. አቶ ምኑነው ፍሬከርስኪ? ልብህን ማደንድ ማለት ምንማለት? እውነት መናገርና ስለእውነት መጽናት ነውን? አስበውል

   Delete
 9. ስለ ቅዱሳን ተናገርከዉ እዉነት ቢሆንም እነሱን ባለስልጣን ማድረግም ሆነ ይህንን አደረጉልኝ ብሎ እልልታ ማቅለጥ ከባድ ወንጀል ነዉ።ባዕደ አምላኪነት ነዉ። እነ ጴጥሮስን ካነሳህ ዘንድ ለነሱ ሊሰግዱ ሲመጡ እየጮሁ ጨርቃቸዉን መቅደዳቸዉን፣ ክብር ሁሉ ለጌታ ብቻ እንደሆነ መመስከራቸዉን ምነዉ ደበቅህ? ደግሞ በየአዉደምህረቱ ታምራቱ ሚነገረዉ ለጌታ ነዉ ወይስ ለመላኩ ወይም ለቅዱሱ ነዉ? ይህንን በልባችሁ መላኩነንና ቅዱሱን አንግሳችሁ ጌታን በገዛ ቤቱ ባዕድ ማድረግ ክርስቲያንነት አይደለም። እያወቃችሁ ማዉገርገር ምን ማለት ነዉ? ጌታ
  ያስባችሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Amen amen amen!

   Delete
  2. "የምታነበውን ታስተውለዋለህን?መአላውቀውም ማን አስተማረኝና?"
   ለመግቢያነት የተጠቀምኩበት የእግዚአብሔር ቃል በሐዋሪያው በቅዱስ ፊሊጶስና በሰረገላ ሆኖ ይጏዝ በነበረው በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ መካከል የተደረገን የመጠይቅና ጥያቂያዊ መልስ ንግግር ነበር። ይሔን የእግዚአበሔርን ቃል የማወቅንና የቃሉን ትርጉምና ሚስጢር ለማስተዋል መደረግ ያለበትን መንገድ እንዴት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ለመዳን ሳይሆን ጠፍተው ለማጥፍት፣ ከእውነት እርቀው በእውነት ስፍራ ያሉትን ከእውነት ለማውጣት፣ ለታይታና ለማስመሳያነት ለተሸከሙት እራሳቸውን አንዴ ፕሮቴስታን ሌላ ጊዜ ተሐድሶ እያሉ ተወናብደው ለሚያወናብዱት መናፍቃን ትክክለኛ መልክት ስለሆነ ነው። " ማን አስተምሮኝ!" መናፍቃን ሳይሆኑ ነን፣ ሳይሾሙ ተሾምን፣ ሳይማሩ አስተማሪነን፣ ሳይቀቡ ተቀባን የሚሉ ስላነበቡ ወይም ማንበብ ስለቻሉ ብቻ አወቅን መጠቅን የሚሉ ግብዞች ናቸው። ወንድሜ anonymous ስለ ቅዱሳን የተናገርኩትን ትክክል ቢሆንም አልህና "እነሱን ባለስልጣን ማድረግም ሆነ ይህንን አድርጉልኝ ብሎ እልልታ ማቅለጥ ከባድ ወንጀል ነው። ባዕድ አምላኪነት ነው" ብለህ ያው ባዶ አሉባልታንና ክስን አስቀምጠሀል። አንተና መሰሎችህ መናፍቃንን ያልገባችሁና ያልተረዳችሁት ቅዱሳኑ ሲከበሩና ሲመሰገኑ ማንና የማን እንደሆኑ ባለመረዳታችሁ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ወንጀል የሚለው ቃል በክርስትና ውስጥ የት ቦታ እንዳለ አላውቅም። ወንጀል የሚለው ቃል አገልግሎቱ ከምድራዊ ህግ ጋር የሚጠቀስ እንጂ በሐይማኖት ውስጥ እንዴት እንዳገባሀው አንተው ታውቀዋለህ። ይህም ሆኖ ያመነበትን ማክበርም ሆነ ስልጣን አላቸው ማለት ወንጀል አይደለም። ክብርም ስልጣንም የላቸውም ካልክ ማሳመኛህን ማቅረብ ነው። እኔ ግን አንተ ለምን ተከበሩ ለምን ለመፈወስና እኛን ለመርዳት ስልጣን አላቸው አላችሁ ብለህ በየትኛው ህገመንግስት እንደረቀቀ ባላውቅም ወንጀል ነው ብለሀል። ነገር ግን እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ የመፍረድ ስልጣን እንደዲህ " በአስራ ሁለት ወንበር ላይ ቁጭ ብላችሁ ትፈርዳላችሁ" ሲል። እንግዲህ እሱንም ወንጀል አደረግህ በላዋ። ይቅር ይበልህ። ሌላ የተናገርከው " ባዕድ አምላኪነት ነው " የሚል ነው። አንተና መሰሎችህ ስታችሁ የምታስቱት የበዐድ አምልኮን ምንነትና ትርጉ ስለማትረዱት ነው። በዐድ አምልኮ በአዲስ ኪዳን የተጀመረ ሳይሆን ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ የነበረና የተከለከለ ነው። በአድ አምልኮ ማለት የእግዚአብሔር ስም የሌለበት፣ ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው በአጠቃላይ እግዚአብሔር በማይከብርበት ነገር ሁሉ ማመንና የአመኑበትንም እንደፈጣሪና አምላክ አድርጎ ማምለክ ጣወት አምላኪ ይባላል። ነገር ግን እግዚአብሔር የሚጠራበት፣ ስሙ ያለበት፣ የሚከብርበት ስራውን የሚያከናውንበትን እነዚህ ከእግዚአብሔር ናቸው ብሎ ማክበርና ማመስገን ግን ጣወት አምላኪነት አይደለም። ማምለክ ማክበር ሲባልም አምላክ ናችሁ በማለት የአምላክነትንና የፈጣሪነትን ቦታ ሰጥቶ አለመሆኑ በግልፅ ሊታወቅ ይገባል። እልልታ ታቀልጣላችሁ ላልከው ለምን እልል አንልም የእግዚአብሔር ስራና ማዳን በመላእክትና በቅዱሳኑ በኩል ሲገለጥ። ለምን እልል አንልም እግዚአብሔር ድንቅ ስራዎችንና ታምራተን ያደርጉ ዘንድ መላእክትንና ቅዱሳኑ እንደሾማቸው ሲገለጥ። ደግሞስ"እኔ አማልእክት አልሿችሁ" ተብሎ ተጽፏል እኮ። ያም ማለት በፀጋ የተሾሙ አማልእክት። ሙሴን እግዚአብሔር የፈርኦን ገዢ አድርጌ ሾምኩህ ብሎታል እኮ። ሌላው " እነ ጴጥሮስን ካነሳህ ዘንድ ለነሱ ሊሰግዱ ሲመጡ እየጮሁ ጨርቃቸውን መቅደዳቸውን፣ ክብር ሁሉ ለጌታ ብቻ እንደሆነ መመስከራቸውን ምነው ደበቅህ?" በማለት ጠይቀሀል። አንተም ሆንክ መሰሎችህ መናፍቃን ማወቅና ማስተዋል ያለባችሁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና አማኞች ምንም የተደበቀና የሚደብቁት እንደሌለ ነው። ያመኑበትን እምነታቸውን ካለ ሀፍረትና ፍርሀት በግልጥ ይተገብራሉ። ለሁሉም ጫፉን ይዘኸዋል ወይም ተነግሮሀል እንጅ ሙሉ መልእክቱን አላየኸውም ምክንያቱም አንተ የፃፍከውና የመጽሐፉ ቃል ስለማይመሳሰል ነው። ሙሉ ቃሉን በሐዋሪያት ስራ ምዕራፍ 14 ከቁጥር 8 እስከ 18 አንብብና ተረዳ። በአጭሩ ግን በልስጥራ እግሩ የሰለለ በእናቱም ማኀፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ ከቶም ሄዶ የማያውቅ አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር። ይህም ሰው ጳውሎስ የሚናገረውን ይሰማ እንደነበርና ቅዱስ ጳውሎስም ትኩር ብሎ ተመልክቶት ለመዳን እምነት እንዳለው ባወቀ ጊዜ በታላቅ ድምፅ ቀጥ ብለህ በእቅርህ ቁም እንዳለውና ሰውየውም ተነስቶ በተመላለሰ ጊዜ ህዝቡ ቅዱስ ጳውለስ ያደረገውን ባዮ ጊዜ አማልክት በሰዎች ተመስለው መጥተዋል በማለት በሊቃኦንያ ቋንቋ እንደተናገሩና ለቅዱስ ጳውሎስና ለበርናባስም የተለያዮ ስሞች እንሰጧቸው ይናገራል። ከዛም በከተማው ፊት ቤተ መቅደስ ያለው የድያ ካህን ኮርማዎችንና የአበባ አክሊሎችን ወደ ደጃፍ አምጥቶ ከህዝቡ ጋር ሊሰዋላቸው በወደደ ጊዜ በርናባስና ቅዱስ ጳውሎስ ሰሙ ና ልብሳቸውን ቀደው በህዝቡ መካከል እየጮሁ እሮጡ……እንዳይሰውላቸውም በጭንቅ አስተዋቸው ይላል። አንግዲ አንተ ሊሰግዱ ሲመጡ ያልከውን ከየት አመጣኸው። መሠዋትና ስግደትስ እንዴት አንድ ይሆናሉ። የሐዋሪያት ሥራ ምዕራፍ 14 ከቁጥር 8 እሥከ 18 ባለው ቃል ውስጥ ስለስግደት የሚገልጥ የለም። መስዋቱንም እንሿን በግድ አስተዋቸው ነው የሚለው። ስለሆነም ቤተ ክርስቲያን መስዋትን አትሰዋም። ልጆቿም እንዲሁ። አንተ ግን ስለቅዱሳንና መላእክት የተናገርከው እውነት ቢሆንም ብለህ የአመንክ መስለህ ወዲያው ክህደትህንና ሰይጣናዊ ክስኸን ተግባራዊ አደረግህ። እውነት መሆኑን ካወቅህ የእግዚአብሔር ሐይል አላቸውና ማዳን መፈወስይችለሉና እኔንም ያድኑኝ ይፈውሱኛል በል። እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል ተብሏልና ቅዱሳኑ ሲከብሩ እግዚአብሔር እንደሚከብር አውቀህ በፊደልና በአፍ ሳይሆን በተግባር አክብራቸው። አለበለዚያ እንደ ሳኦል ቅዱሳኑን የምታሳድድና የምትንቅ ከሆነ "ሳኦል ለምን ታሳድደኛለህ የመውጊያወን ቀስት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሀል" ይልሀል። ደግሞስ ክርስቶስ ተናግሮ የማያደርግ ደካማ አስመስላችሁ ጉባኤ ሊያውክ የመጣ መንፈስ አለ አሁን ይወጣል እያሉ አገልጋይ ተብዬዎቻችሁ እያጓሩ መልስ ሲያጡ እጅ ለእጅ ተያያዙ በማለት አዳራሹ ሁሉ በጩኸት ሲናጋ ያ ጉባዬ ሊያውክ የመጣ ሳይሆን አይቀርም ይባላል። እግዚአብሔር የተናገረውን የሚያደርግ ሐያል አምላክ እንጂ እንደናንተ እጅ ለእጅ ካልበያያዛችሁ አይልምም ደካማም አይደለም ይቅር ይበላችሁ። በእዬ አዳራሻችሁ ያለውን ጉድ የማይታወቅ አይምሰልህ።

   Delete
  3. አሜኑ አላነሰም እንዴ አተanonymous። መመርመር የለም ዝምብሎ መወዛወዝ። አቋም የለም ያም ትክክል ነው ይሄም ትክክል ነው እያልክ እንደነዱህ መነዳት። አሁን በእውነት አሜን አስተያየት ነው እንዴ? ለማንኛውም በአዳራሾቻችሁ ፓስተሩ ጉባኤው እንዲሞቅ ኦርጋኑን ከጩኸቱ ጋር ምታው እንደምትሉት አሜኑ አንሶበት የክህደቱ ፀሐፊ አልተደሰተምና አሜኑን ጨምርባት።

   Delete