Sunday, December 28, 2014

“ታላቅ ዜና” “ተሐድሶ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲጠና ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑ ተሰማ፡፡”

ተሐድሶ ለቤተ ክርስቲያን እድገት፣ ለእግዚአብሔር ቃል ቅዱስ ወንጌል መስፋፋት፣ ለሐሰት ትምህርት ከቤተ ክርስቲያን መወገድ፣ ቤተ ክርስቲያን ቸል ያለችውን ወንጌል መልሳ እንድታነሣና ራሷን በመለኮታዊ ኀይል እንድታስታጥቅ የሚያግዝ አገልግሎት ነው፤ ሆኖም ግን ብዙ ሰዎች የሚያስተምሩት የሐሰት ትምህርት ጥያቄ ላይ ስለሚወድቅባቸው ተሐድሶን አይወድዱም፡፡
የቤተ ክርስቲያን መሪ ነኝme የሚለው ቅዱስ ሲኖዶስም የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ከመስማትና ራሱን በእግዚአብሔር ቃል ከመመርመር ይልቅ ተሐድሶን የመናፍቃን ትምህርት (እንቅስቃሴ) በማለት ሲያወግዝና የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ሲያባርር ኖሮአል፤ ዛሬም በዚህ ኢክርስቲያናዊ ተግባሩ ቀጥሎ በዚህ ዓመት በጥቅምት ወር ባደረገው ጉባኤ በተራ ቁጥር 19 በያዘው አጀንዳው “ስለ መናፍቃንና ስለ ተሐድሶ” ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ማረጋገጥ ችለናል፡፡ የውሳኔውን ሙሉ ቃልና ማብራሪያ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡
24/2/2007 ዓ/ም
“ስለ መናፍቃንና ስለተሐድሶ እንቅስቃሴ በተመለከተ በተራ ቁጥር 19 የተያዘ አጀንዳ ነው፡፡ መናፍቃን ሁልጊዜ (1) ስልታቸውንና አካሄዳቸውን  እየቀያየሩ (2) ሲፈልጉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ነን፤ (3) ቤተ ክርስቲያንን እንወድዳታለን፤ (4) አባቶችን እናከብራለን በማለት (5) የቤተ ክርስቲንን እንጀራ እየበሉ (6) ስውር ዓላማቸውን እያካሄዱ (7) ሕዝበ ክርስቲያኑን በመከፋፈልና (8) መሠሪ ተግባራቸውን በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየፈጸሙ የሚገኙ መሆናቸው (9) በሁሉም አህጉረ ስብከት ያሉ አባቶች የብፁዕ አቡነ ሄኖክን የአቤቱታ ደብዳቤ መሠረት በማድረግ ችግራቸውን በሰፊው በጉባኤው ላይ አቅርበዋል፡፡
በመሆኑም የመናፍቃንና የተሐድሶ መገኛ ምንጫቸው ከየት እንደሆነ ጉባኤው በመወያየት (10) ደቀ መዛሙርቱ ከየአህጉረ ስብከቱ ሲላኩ ጤናማ እንደሆኑ፣ ነገር ግን ተመርቀው ሲመለሱ ከነችግራቸው ሌላ ሰው ሆነውና መስለው ይመለሳሉ፤ (11) ለዚህ የችግሩ ምንጮች ኮሌጆች እንደሆኑ ያመለክታል፡፡ ምክንያቱም መንፈሳውያን ልጆች ተልከው መናፍቃን ሆነው ሲመለሱ እያንዳንዱን ኮሌጅ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባዋል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ኮሌጅ ሊፈተሹና (አንድና ብዙ በቃለ ጉባኤው አልተጠበቀም) ሊመረመሩ ይገባል በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሰፊው ከተወያየ በኋላ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ 


ውሳኔ
ኮሌጆች ሲከፈቱ በመጀመሪያ ደረጃ እነማን እንደሚማሩባቸውና መምህራኖቹ እነማን እንደሆኑ፣ የሚያስተምሩባቸውም መጻሕፍት ሊታወቁና በካሪኩለሙ (ሥርዐተ ትምህርት ማለት ነው) ሊቀረጹ ይገባል በማለት ጉባኤው በሰፊው ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን ነጥቦች ጉባኤው አስቀምጧል፡፡
1.      የመምህራኖች ክህሎትና የሃይማኖታቸው ጉዳይ
2.     የኮሌጆቻችን የትምህርት ካሪኩለም አቀራረጽ
3.     የመጻሕፍቱ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ታይተውና ተፈትሸው ሊሠራባቸው ይገባል በማለት ጉባኤው በአጽንኦት ተነጋግሮበታል፡፡
(12)  እንዲሁም ከኮሌጆች ተምረው በየአህጉረ ስብከቱ የተላኩት ደቀመዛሙርት የኑፋቄ ትምህርታቸው በአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እየተመረመሩና አግባብ አግባብ ሆኖ ካላገኘው ባለው መረጃ መሠረት እገዳ እንዲደረግና ከስሕተታቸው የሚመለሱትንም ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እየሰጠ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዶግማና ቀኖና እንዲጠበቅ እንዲያደርግ ሆኖ ከኮሌጆችና ከሀገረ ስብከት አስተዳደር አቅም በላይ የሆነውን ችግር በደረጃው ለበላይ መ/ቤት አቅርቦ ማስወሰን እንዳለበት ጉባኤው ተስማምቷል፡፡
እንዲሁም ይህ ጉዳይ ብዙ ጊዜ ሊሰጠው ስለማይገባ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ካሉት መምሪያዎች ውስጥ፡-
1.      የስብከተ ወንጌል መምሪያ
2.     የትምህርት ማሰልጠኛ መምሪያ
3.     የሰንበት ት/ቤት መምሪያ
4.     የሊቃውንት ጉባኤ መምሪያ
5.     የቅርሳቅርስ መምሪያ በመቀናጀት ተጠሪነታቸው ለሥራ አስኪያጁ ሆኖ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ (ሀገረ ስብከታቸውም ተጠቅሷል) በተገኙበት ከላይ በተጠቀሱት መምሪያዎች ውስጥ (13) በቂ ክህሎትና ችሎታ ያላቸው ምሁራን ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጀምሮ እስከ አህጉረ ስብከት ድረስ ያለውን የመናፍቃንና የተሐድሶ እንቅስቃሴን ጥልቅ በሆነ መልኩ ሰፊ መረጃ በማሰባሰብ አጥንተው ለግንቦቱ ርክበ ካህናት እንዲያቀርቡ፣ ችንዲሁም “ስማችሁ የለም” የሚለው በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተጻፈው መጽሐፍ በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶና ተመርምሮ መልስ እንዲዘጋጅለት ሲል በአንድ ድምጽ ተስማምቶ ወስኗል፡፡” ይላል፡፡ የዚህ ቃለ ጉባኤ አሳብ ሲተነተን የሚከተሉን ነጥቦች ይዞ እናገነዋለን፡፡ ከላይ ከ1-13 በቅንፍ ውስጥ ሆነው የገቡ ቁጥሮች ከቃለ ጉባኤው ትኩረት የተሰጣቸውን ነጥቦች ያመለክታሉ፡፡

(1)   ስልታቸውንና አካሄዳቸውን  እየቀያየሩ፡-  ከዚህ ቃለ ጉባኤ የምንረዳው የመጀመሪያው ነጥብ ሲኖዶሱ ተሐድሶ ስልቱንና አካሄዱን የሚቀያይር መሆኑን መረዳቱ ነው፡፡ በመሠረቱ ጌታ “እንደ እባብ ብልሆች፣ እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ” ሲል ያስተማረውን መሠረት በማድረግ ስልትን በየጊዜው መቀያየር መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያ ነው፤ ዋናው ነገር ስልቱ ሳይሆን የሚተላለፈው መልእክት ነው፤ የማይለወጥ ወንጌል እንጂ የማይለወጥ ስልት የለንም፡፡ ስለዚህ ማንም ሰው ሊረዳው የሚገባው ነገር ቢኖር ተሐድሶ በየትኛውም ጊዜ በየትኛውም ስልት የሚያስተምረው ወንጌል አንድ ነው፤ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትንሣኤን የሚሰጥ ሕያው ወንጌል ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ወንጌል እንጂ አንድ ስልት የለንም፤ ይህን የምናደርግበት ዋና ምክንያትም ማኅበረ ሰብ በየጊዜው በተለያዩ ምክንያቶች አስተሳሰቡንና አኗኗሩን ስለሚቀይር በተለያዩ ስልቶች ወንጌልን ማድረስና ሕይወቱን ማዳን የግድ ስለሚሆን ነው፡፡ አገልግሎቱ ሕያው ነው፤ በማኅበረ ሰቡ ውስጥ ያለውን ለውጥ ያውቃል፤ ቤተ ክህነቱም ሆነ ሲኖዶሱ ስለሞተ ሁል ጊዜ አንድ ስልት የሚከተል ከሆነ ጊዜውን ያልዋጀና ሕዝብን መታደግ የሚችል አቅም የሌለው ተቋም ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ አይነት አካል ሁልጊዜ አንድ ስልት ቢከተል፣ ሌሎችም አንድ አይነት ስልት ብቻ ይጠቀማሉ ብሎ ቢገምትና ቢሸውድ አይገርምም፤ ምእመናን ወደ ተለያየ እምነት እንዲበተኑ ያደረገውም ይህ እንቅልፍ በቤተ ክህነትና በሲኖዶስ ላይ ወድቆ ለረጅም ጊዜ ስለኖረ ነው፤ አሁን የመንቃት ጊዜ ነው፤ እንንቃና ቤተ ክርስቲያናችንን እንጠብቅ፤ ወንጌልን በመስበክ ፍልሰትን እንግታ የተሐድሶ አቋም ነው፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ተሐድሶ በትግሉ ይቀጥላል፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፡፡

(2)   ሲፈልጉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ነን፡- “የቤተ ክርስቲን ልጆች ነን” እያሉ የሚለው ሁለተኛው ነጥብ ነው፤ የተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጆች የቤተ ክርቲን ልጆች ነን ማለታቸው እውነት ነው፤ ይህን የምንለውም ለቃል ብቻ ወይም በከንቱ አይደለም፤ ለቤተ ክርስቲያን ትንሣኤ የምንታገል እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን ነው እንጂ፡፡ ልጆች ለመሆን ትምህርቷን መማራችን፣ በሥርዐቷ መጠመቃችን፣እርሷን ማገልገላችን፣ ከምንም በላይ በወንጌል ትንሣኤ እንድታገኝና መታደስዋ እንዲፈጥን መጋደላችን ማረጋገጫችን ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ ማረጋገጫ አንፈልግም፤ ከዚህ የተሻለም የቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ማረጋገጫ የሚሆን ነገር አይኖርም፡፡

(3)   ቤተ ክርስቲያንን እንወድዳታለን፡- እኛ የተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጆች በእርግጥም ቤተ ክርስቲያንን እንወድዳታለን፤ ቤተ ክርስቲያንን ካልወደድን ለምን እንወገዛለን? ለምን እንራባለን? የሐሰት ትምህርት ቤተ ክርስቲያንን ሲወርራት፣ ትምህርቷን ከወንጌል መሠረት ሲያስለቅቅ፣ ምእመናን ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብን ክብርና አምልኮ ለፍጡራን ሲሰጡ ፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ መርገምን የሚያስከትል ተግባር ሲፈጸም ዝም ማለት አንችልምን?  የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደተጻፈ እኛስ ውግዘቱንም፣ መራብና መጠማቱንማ፣ ስም ማጥፋትና መሰደዱንም፣ ታግሰን ወንጌልን በመስበክ እንተጋለን፤ ይህን የምናደርገው ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን ስለምወድድ እንጂ ሌላ ጥቅም ስላለን አይደለም፤ ከሥራ የሚባረር ማነው? የሚሰደድ ማነው? እንደሌሎች ዝም ብለን መቀመጥ ወይም ቤተ ክርስቲያን ከወንጌል ወጥታ የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡራን ስታቀርብ ዝም ማለት አንችልም፤ የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ግድ ይለናልና፡፡ ለዚህ ሁሉ ችግር መፍትሔው ወንጌል ነው፤ ይህን ደግመን ደጋግመን እንናገራለን፡፡
(4)   አባቶችን እናከብራለን በማለት፡- አባቶችን እናከብራለን ማለታችን የቃል ብቻ አይደለም፤ አባቶች ለወንጌል የሚሠሩ ከሆነ በወንጌል አገልግሎት የሚተጉ እጥፍ ድርብ ክብር ሊሰጣቸው ስለሚገባ፣ ለወንጌል ባይተጉም ታላላቆችንና አባቶችን የማክበር መጽሐፍ ቅዱሳዊና ባህላዊ ሕጎችን በክርስቲናዊ መስፈርት እየለካን በእርግጥ አባቶችን እናከብራለን፤ ይህን አባቶች ሊጠራጠሩና የተሐድሶ ጠላቶች በሆኑ ሰዎች ሐሰተኛ ወሬ ሊሳሳቱ አይገባም ብለን እናምናለን፤ እኛ እግዚአብሔር የሚፈልገውን በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መሠረት እናደርጋለን እንጂ አንዳች ነገር አንቀንስም፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይም ከራሳችን የሆነ አንዳች ነገር አንጨምርም፡፡
(5)   የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉ፡-  እንጀራ የእግዚአብሔር ነው፤ ቤተ ክርስቲያን የራሷ የሆነ እንጀራ የላትም፤ ይህ አይነት አነጋግርም ከማያምኑ ሰዎች እንጂ ከሲኖዶስ አባላት ከጳጳሳት የሚጠበቅ አይደለም፡፡ ከዚህም በላይ ቤተ ክርስቲያንን በእውነተኛው ወንጌል የሚያገለግሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ከቤተ ክርስቲያን እጅ የእግዚአብሔርን እንጀራ ይበሉ ዘንድ “ለሚሠራ ደመወዙ ይገባዋል” ያለው የወንጌል ቃል ይፈቅድለታል፤ አባቶች እውነተኛ መንፈሳዊ አባትነታቸውን ስላጡ የእንጀራ አባቶች ሆነዋል፤ ስለዚህም የእኛን እንጀራ እየበላችሁ እኛ የማንፈልገውን አትስበኩ ይሉን ጀመሩ፡፡ ይህን ስንናገር አባቶችን እናከብራለን እያላችሁ ይህን ትናገራላችሁን? የሚል ሰው ይኖር ይሆናል፡፡ ለአባቶች ያለን ክብር ወንጌልን እንድለውጥ አያስገድደንም፤ የምንበላው እንጀራ የምጋደልለት የወንጌል ፍሬ እንጂ አንድም ሰው ይህ እንጀራ የእኔ ነው ብሎ ሌላውን ሊነቅፍበት የሚገባ አይደለም፡፡ አባቶች አርሰው፣ ነግደው ወይም ሌላ ሥራ ሰርተው ያመጡት ገንዘብ የለም፤ የወንጌልን እውነት እያጣመሙ ምእመናንን ከእውነተኛው የወንጌል እምነት እያስወጡ ያሉ የሐስት አስተማሪዎችን እየቀለቡ ለወንጌል እውነት እየተጋደሉ ያሉ እውነተኞችን የተሐድሶ አገልጋዮች መዝለፍ ተገቢ ነው ብለን አናምንም፤ አባቶች ይህ አቋማቸው ቤተ ክርስቲያንን የሚጎዳና የቤተ ክርስቲያንን ተሐድሶ የሚያዘገይ ስለሆነ ሊያስተካክሉ ይገባል፡፡
(6)  ስውር ዓላማቸውን እያካሄዱ፡- ተሐድሶ ስውር አላማ አይደለም፤ አገልግሎቱ ስውር የሆነበት ምክንያት የተሐድሶ አገልግሎት አራማጆች እንደክፉ አድራጊዎች ተቆጥረው መሰደድ ስለበዛባቸው እንጂ፡፡ አባቶች ለወንጌል ቢደሉ፣ ቤተ ክርስቲያንን ከሐሰት ትምህርት ነጻ ለማድረግ ቢሠሩ ተሐድሶ ስውር ሊሆን አይችልም፤ የተሐድሶ አራማጆችም በግልጽ መሥራት በቻልን ነበር፤ በግልፅ የተሐድሶ ጥያቄ ያቀረቡ መናፍቃን እየተባሉ ሲፈረጁና ሲሰደዱ እያየን እንዴት አላማችንን ልንገልጽ እንችላለን? ይህ የብልህ ሰው ስልት አይደለም፤ እናንተ አባቶች ከእግዚአብሔር ይልቅ ለሰው እያደላችሁ እንደሆነና የእግዚአብሔርን አሳብ እይተቃወማችሁ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ተሐድሶ ግልጥ እንቅስቃሴ ነው፤ የማይታወቅና ለእናንተም የተሰወረ ነው ብለን አናምንም፤ ማናው ነጥብ ተሐድሶ እንደ ክፉ አድራጊ ተቆጥሮ በመሰደድና በመወገዝ ላይ ያለ ቢሆንም የእግዚአብሔር አሳብ ስለሆነ እየሰፋና እየበዛ ያለ አገልግሎት ነው፤ ገማልል እንዳለው ከሰው ከሆነ ይጠፋል፤ ከእግዚአብሔር ከሆነ ከአሳቡ ጋር የሚዋጉት ይጠፋሉ እንጂ ሊጠፋ አይችልም፤ እኛም በዚህ እምነት ሆነን እያገለገልን ነው፡፡
(7)   ሕዝበ ክርስቲያኑን በመከፋፈልና መሠሪ ተግባራቸውን በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየፈጸሙ የሚገኙ መሆናቸው፡- ሕዝብን የመከፋፈል መሠሪ ተግባር የሚሠራው ተሐድሶ ሳይሆን የተሐድሶ ጠላቶች ናቸው፤ እኛ ወንጌልን እንሰብካለን፤ የወንጌል ጠላቶች በሕዝብ መካከል ጸረ-ወንጌል የሆነ ስብከትን ያሰራጫሉ፤ ይህም በሕዝብ መካከል መከፋፈልን ይፈጥራል፤ ለወንጌል የሚያደሉ እውነተኞች ከእኛ ጋር ይቆማሉ፤ ከእግዚአብሔርም ጋር ይተባበራሉ፡፡ ጸረ-ወንጌል ስብከትን የተከተሉ ደግሞ በተሐድሶ ላይ ስደትንና ተቃውሞን ያመጣሉ፡፡ ወንጌልን መስበክ ልዩነትን ይፈጥራል፤ ክርስቶስም ወንጌል በአባትና በልጅ፣ በእናትና በልጅ፣ በቤተ ሰብ መካከል መለያየትን እንደሚያመጣ በግልጽ ስላስተማረ ይህ በወንጌል ያልተነገረ አይደለም፡፡ ይልቁንስ አባቶች በኀላፊነታቸው መሠረት እውነተኛው እንዳይሰደድ፣ ሐሰተኛው ቤተ ክርስቲያንን በጸረ- ወንጌል ሐሰተኛ ትምህርቱ እንዳይጎዳት መከላከል ይገባቸዋል እንጂ እውነተኞችን በማሳደድ ቤተ ክርስቲያን የሐሰተኛ ትምህርት መፈንጫ ማድረግ አይገባቸውም ብለን እናምናለን፡፡ ይህን ኀላፊነታቸውን ሳይወጡ ቀርተው ወንጌልን የሚሰብኩ ሰዎችን በሕዝብ መካከል መከፋፈልን የሚፈጥሩ በማለት መክሰስ ከአባትነታቸው የሚጠበቅ ተግባር አይደለም፡፡
(8)   በሁሉም አህጉረ ስብከት ያሉ አባቶች የብፁዕ አቡነ ሄኖክን የአቤቱታ ደብዳቤ መሠረት በማድረግ ችግራቸውን በሰፊው በጉባኤው ላይ አቅርበዋል፡፡ ከዚህ ቃለ ጉባኤ የተረዳነው አንድ ታላቅ ነገር ቢኖር ተሐድሶ በሁሉም አህጉረ ሰብከት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተስፋፋ መሆኑ ነው፤ ይህን እኛ በሥራው ላይ ያለን አገልጋዮች እናውቀዋለን፤ አባቶች ነገሩን የተረዱበት መንገድ ግን ልዩ ነው፤ ይህም ተሐድሶን እንደመልካም ነገር ከመቁጠር ይልቅ እንደችግር ማየታቸው ነው፡፡ አባቶች በዚህ ቃለጉባኤ ላይ እንዳሰፈሩት አቡነ ሄኖክ ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት ተሐድሶ በሁሉም አህጉረ ስብከት ያለ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ በእኛ እምነት አባቶች ይህን እንደመልካም እድል እንጂ እንደችግር ሊያዩት አይገባም ነበር፤ እነርሱ በጀት በጅተው፣ እቅድ አውጥተው ሊያመጡት የሚገባ ለውጥ ሲሆን እኛ ታግለን፣ በተለይ ደግሞ ከእኛ በፊት የነበሩ የወንጌል አገልጋዮች በብዙ መከራ ውስጥ አልፈው እዚህ ሲያደርሱት እንደገና በችግር መልክ ማየትና ተቃውሞ መፍጠር ግን አሳዛኝ ነገር ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ አባቶች ይህን ለቤተ ክርስቲያን የመጣ መልካም እድል በእግዚአብሔር ቃል መሠረት በመርመርና በመምራት ወደ ተሻለ ደረጃ ሊያደርሱት ይገባል፤ ይህ እድል ለቤተ ክርስቲያን ሊያመልጣት አይገባም፡፡
(9)  የተሐድሶ ምንጮች ኮሌጆች ናቸው፡- ተሐድሶ ከትምህርት ተቋማት መምጣቱ የሚጠበቅና መሆን ያለበትም ነው፤ በቃለ ጉባኤው የተገለጠበት መንገድ ግን ከአባቶች የሚጠበቅ አይደለም፤ አባቶች እናዳሉት ደቀ መዛሙርቱ ከየአህጉረ ስብከቱ ሲላኩ ጤናማ እንደሆኑ፣ ነገር ግን ተመርቀው ሲመለሱ ከነችግራቸው ሌላ ሰው ሆነውና መስለው ይመለሳሉ፤ ለዚህ የችግሩ ምንጮች ኮሌጆች እንደሆኑ ያመለክታል፡፡ ምክንያቱም መንፈሳውያን ልጆች ተልከው መናፍቃን ሆነው ሲመለሱ እያንዳንዱን ኮሌጅ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባዋል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ኮሌጆች  ሊፈተሹና  ሊመረመሩ ይገባል”፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው? “ጤናማ” ማለት ያለተማረና መጽሐፍ ቅዱስ የማያነብብ ነው፤ ትምህርት ቤት ገብቶ ምንም አይነት ለውጥ ሳይታይበት የሚመለስ ተማሪ ኦርቶዶክሳዊ ነው፤ ከሀገረ ስብከት ያጠናውን ተረት በእግዚአብሔር ቃል ሳይመረምር ተመልሶ ከአምስት ዓመት በኋላ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የተመደበለትን 960 ብር ደመቀዝ ብሎ ይዞ የሚመለስ ተማሪ ኦርቶዶክሳዊ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ያነበቡ፣ በሕይወተቸው ክርስቶስን አውቀው የተለወጡ፣ ወንጌልን በግልጽና በድፍረት መስበክ የጀመሩ፣ ሐሰተኛ ትምህርትን በእግዚአብሔር ቃል መዝነው የጣሉ፣ ለእውነት ራሳቸውን የሰጡ፣ የተማሩትን ነገረ መለኮት ከሕይወታቸው ጋር ያዋሐዱና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመኖር የመሰኑና በእግዚአብሔር ቃል የተለወጡ ተማሪዎች ተሳስተዋል፤ መናፍቃን ሆነዋል፡፡ እንዳይለወጡ ከፈለጉ ለምን ይልኳቸዋል? ለመደንቆር አራት ኪሎ መምጣት ለምን ያስፈልጋል? ለምንስ የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ለወንጌል አገልግሎት ሊውል ሲገባው የእግዚአብሔር ገንዘብ በከንቱ ይባክናል? በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ ኮሌጆች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ለውጥ ማምጣት ስለጀመረ ኮሌጆች የችግር ምንጮች ናቸው ተብለው መከሰሳቸው ነው፡፡ ቤተ ክርስቲን ወዴት እየሄደች ነው? የሚመክር አባት እንድ እንኳን የለም እንዴ? ኮሌጆች ለምን ያስተምራሉ? በኮሌጆች ውስጥ እኮ መጽሐፍ ቅዱስ ይነበባል፤ መጽሐፍ ቅዱስ አንብቦ የማይለወጥ ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ አንብቦ ለቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ የማይመኝ ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ አንብቦ በቤተ ክርስቲናችን ውስጥ የገባውን የሐሰት ትምህርት መለየትና ይህን የስሕተት ትምህርት ለማስወገድ የማይታገል ማነው? ወይ በቁርጡ መጽሐፍ ቅዱስ እንድታነብቡ አንፈልግም በሉንና ሙሉ በሙሉ በቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ላይ ተስፋ እንቁረጥ፡፡ ምን እያላችሁ ነው? ለውጥ እንዲመጣ ካልፈለጋችሁ ለምን ኮሌጆችን ከፈታችሁ? ለውጥ እንዲመጣ የምትፈልጉ ከሆነ እናንተ የምትፈልጉት ለውጥ ምን አይነት ለውጥ ነው? በእግዚአብሔር ቃል የሚመጣ ለውጥንስ ለምን ትቃወማላችሁ? ንስሓ! ንስሓ! ንስሓ! አባቶች አስተውሉ! እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያናችን የላከውን የተሐድሶ ጥሪ አትቃወሙ፤ ክብራችሁ አይደለም፤ ወንጌልን ተቃውማችሁ በምን ልትከብሩ ትፈልጋላችሁ? በእግዚአብሔር ፍቅር፣ በቤተ ክርስቲያን ስም እንለምናችኋለን ይህ አቋም አይበጅም፡፡
(10) ኮሌጆች፣ መምህራንና የሚያስተምሩባቸው መጻሕፍት ሊጠኑ ይገባል፡፡ አቅም ካለ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያስተዳድራቸውን የትምህርት ተቋማት የመቆጣጠርና አጥፍተው ከተገኙ ማስተካከል መብት አለው፤ ከዚህም የተነሣ ይጠኑ ብሎ መወሰኑን በመርህ ደረጃ አንቃወምም፡፡ ጉዳዩ ያተኮረው ተሐድሶን ለመዋጋትና ለማጥፋት ከመሆኑ አንጻር ግን ኢክርስቲያናዊና ኢመንፈሳዊ  ውሳኔ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ውሳኔው በተሐድሶ ላይ ምንም አይነት ተጽእኖ ሊኖረው አይችልም፤ ተሐድሶ እግዚአብሔር ስለተበቀው እንጂ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ቃል መሠረት መርምራ ድጋፍ ስላደረገችለት ከዚህ የደረሰ አገልግሎት አይደለም፤ እንደሌሎች ማኅበራትም የንግድ ተቋማት የሉትም፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ከየመምሪዎች የተውጣጡና አቅም ያላቸው ምሁራን ያጥኑት ብሎ ቢወስንም ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ ምንም አይነት እውቀት የሌላቸው፣ የነገረ መለኮት ትምህርት ምን እንደሆነ የማያውቁና የእግዚአብሔርን አሳብ ዘወትር በመቃወም የሚታወቁ ሰዎች እንዲያጠኑት ብሎ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በቁጥር 1483/84/07 በቀን 11/03/2007 ዓ/ም በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡ የተመደቡት ምሁራን ተብዮችም ሊቀ አእላፍ ያዛለም ገሠሠ (የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ ነገር ግን የመጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርትም ሆነ የዘመናዊ ነገረ መለኮት ትምህርት የሌለው ደብተራ ወይም የዜማ ባለሙያ ብቻ)፣ ሰሎሞን ቶልቻ (በነገረ መለኮት ትምህርት በዲፕሎማ ያውም በማታው መርሀ ግብር ተምሮ ነገረ መለኮቱ ሳይገባው የወጣ ከዚህም በላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ መደበኛ ትምህርት ነፍጹም የሌለው ነው፤ እንዲህ አይነቱ ሰው በቤተ ክህንት ቋንቋ “ድንግል በክልኤ” ይባላል፤ ትርጉሙም በሁለቱም ማለትም በዘመናዊም በቤተ ክርስቲን ትምህርትም የሌለበት ድንግል ማለት ነው፡፡)፣ ኀይለ ጊዮርጊስ ዳኘ (የታወቀ የማቅ ሠራተኛና በቅርቡ በወንጀል ተክስሶ የተፈታ፣ በሁለቱም ትምህርት የሌለው አሳዳጅ)፣ ርእሰ ደብር በሪሁን አርአያ (በተመሳሳይ ሁኔታ ኮሌጅንና የተሐድሶን ጥያቄ ለማጥናት አይደለም ኮሌጅ ገብቶ ለመማር እንኳን የማይበቃ ሰው) እንዲሁም ይቅርባይ እንዳለ (ይህም ወጣትና ቴዎሎጂያን ቢሆንም እምነት የማይጣልበት አቋም የለሽ ሰው) ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች እንዲያጠኑ በሲኖዶስ የተመረጡ አይደሉም፤ አቡነ ማቴዎስ ግን የማኅበሩን ጥቅም ይጠብቃሉ፤ ብለው ስላሰቡና የአጼ ዘርአ ያዕቆብን ወንጌል በማስቀጠል የክርስቶስን ወንጌል የሚሰብኩ ሰዎችን ያሳድዱልኛል ብለው ስላመኑ የሾሟቸው ናቸው፡፡ ለሁሉም እግዚአብሔር ተሐድሶን ይጠብቃል፤ የተሐድሶ አገልግሎት ገና ይሰፋል! እግዚአብሔር በሀገሪቱ ሁሉ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ቤት ተሀድሶን ያስነሣል፤ እኛም ቤተ ክርስቲያን በወንጌል ታድሳ በኀይል ስትነሣ እናያለን፤ ጌታ ያደርገዋል! እናምናለን፤ አሜን፡፡

ማስገንዘቢያ፡- ቃለ ጉባኤውን ቃል በቃል ጽፈን ስላቀረብን ስካን ማድረግን ለጊዜው አልፈለግንም፤ የሚፈልጉ ካሉ ግን ወደ ፊት ስካን አድርገን ለማቅረብ እንችላለን፡፡

19 comments:

 1. እልልልልልልልልል

  ReplyDelete
 2. ቅዱስ ሲኖዶስ ከየመምሪዎች የተውጣጡና አቅም ያላቸው ምሁራን ያጥኑት ብሎ ቢወስንም ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ ምንም አይነት እውቀት የሌላቸው፣ የነገረ መለኮት ትምህርት ምን እንደሆነ የማያውቁና የእግዚአብሔርን አሳብ ዘወትር በመቃወም የሚታወቁ ሰዎች እንዲያጠኑት ብሎ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በቁጥር 1483/84/07 በቀን 11/03/2007 ዓ/ም በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡ የተመደቡት ምሁራን ተብዮችም ሊቀ አእላፍ ያዛለም ገሠሠ (የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ ነገር ግን የመጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርትም ሆነ የዘመናዊ ነገረ መለኮት ትምህርት የሌለው ደብተራ ወይም የዜማ ባለሙያ ብቻ)፣ ሰሎሞን ቶልቻ (በነገረ መለኮት ትምህርት በዲፕሎማ ያውም በማታው መርሀ ግብር ተምሮ ነገረ መለኮቱ ሳይገባው የወጣ ከዚህም በላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ መደበኛ ትምህርት ነፍጹም የሌለው ነው፤ እንዲህ አይነቱ ሰው በቤተ ክህንት ቋንቋ “ድንግል በክልኤ” ይባላል፤ ትርጉሙም በሁለቱም ማለትም በዘመናዊም በቤተ ክርስቲን ትምህርትም የሌለበት ድንግል ማለት ነው፡፡)፣ ኀይለ ጊዮርጊስ ዳኘ (የታወቀ የማቅ ሠራተኛና በቅርቡ በወንጀል ተክስሶ የተፈታ፣ በሁለቱም ትምህርት የሌለው አሳዳጅ)፣ ርእሰ ደብር በሪሁን አርአያ (በተመሳሳይ ሁኔታ ኮሌጅንና የተሐድሶን ጥያቄ ለማጥናት አይደለም ኮሌጅ ገብቶ ለመማር እንኳን የማይበቃ ሰው) እንዲሁም ይቅርባይ እንዳለ (ይህም ወጣትና ቴዎሎጂያን ቢሆንም እምነት የማይጣልበት አቋም የለሽ ሰው) ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች እንዲያጠኑ በሲኖዶስ የተመረጡ አይደሉም፤ አቡነ ማቴዎስ ግን የማኅበሩን ጥቅም ይጠብቃሉ፤ ብለው ስላሰቡና የአጼ ዘርአ ያዕቆብን ወንጌል በማስቀጠል የክርስቶስን ወንጌል የሚሰብኩ ሰዎችን ያሳድዱልኛል ብለው ስላመኑ የሾሟቸው ናቸው፡፡ ለሁሉም እግዚአብሔር ተሐድሶን ይጠብቃል፤ የተሐድሶ አገልግሎት ገና ይሰፋል! እግዚአብሔር በሀገሪቱ ሁሉ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ቤት ተሀድሶን ያስነሣል፤ እኛም ቤተ ክርስቲያን በወንጌል ታድሳ በኀይል ስትነሣ እናያለን፤ ጌታ ያደርገዋል! እናምናለን፤ አሜን፡፡
  ሃሃሃሃሃሃሃሃ ለመጀመሪያዎቸሁ አረፍተ ነገሮች
  አሜን ለመጨረሻዎቹ አረፍተ ነገሮች
  ጌታይረዳናል ቤተክርስቲያን ትታደሳለች።

  ReplyDelete
 3. ተሃድሶ ለኦርቶዶክስ

  ReplyDelete
 4. ወኀልቀ በከንቱ መዋዕሊሆሙ፤ወኀለፈ በጉጉዐ አመቲሆሙ…ቀበሮ የበሬ እንት ይወድቅልኛል ብላ…!!
  1. እንደ ድሮ የሽግግር ወቅት ፕሬሶች ርእስ በማጮህ ብቻ አንባቢ ለመሳብ ካልሆነ በቀር ርእሳችሁና ይዘቱ በፍጹም እንደማይገናኝ ገሀድ ነው!!ተአምረ ብኪ--ታውቆብሻል!!አትልፉ!!በአቡነ ማትያስ አስተዳደር ውስጥ እናንተ የምትሉት አይነት በምዕራባዊ መንፈስ የተጀቦነ አጓጉል ጥራዝ ነጠቅ ተሐድሶ አይሞከርም፡፡ሳትጠሩ ራሳችሁን ደርሳችሁ የፓትርያርኩ አፈ ቀላጤ ለማድረግ ብትጣጣሩም እውቅና አንሰጣችሁም፡፡በፍጹም!!እርግጥ አንዳንድ የማኅበረቅዱሳን አካሄድ የሚያስቀይማቸው ወንድሞቻችን መተንፈሻ ሲያጡ ሃይማኖታችሁን ሳይደግፉ ለእልህ መወጫ ያህል ሲጠቀሙባችሁ አይተናል፡፡እሱ ደግሞ መዋቅሩ በቅጥ ሆኖ ማኅበሩ በትክክል ወደ ሥርዓት ሲገባ ቅርጹን ስለሚይዝ አያስጨንቀንም፡፡ያን ለማድረግ ደግሞ በቤቷ ያደግነው አንሰንፍም!!የአቡነ ማትያስና የማኅበረቅዱሳን ልዩነት የአካሄድ እንጅ የሃይማኖትና የዐላማ እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡እናንተም አትስቱትም!!ያን ከፍጻሜ አድርሶ ቤተክርስቲያንን ካጓጉል ቡድናዊነት ለማውጣትና አማናዊ የምዕመንና የካሕናት ኅብረት የሚገለጽባት ለማድረግ ከቶ መች እንተኛና!!ግበረ በላማ አንሆንም!!
  2. በኮሌጆቻችን የሚካሄዱ እንደ አንጻራዊ ትምህርተ - መለኮት አይነት ትምህርቶች እምብዛም በእውቀት ሳይጎለምሱ የሚመጡ አንዳንድ ደቀመዛሙርትን እንደሚያዋልሉ ባንስተውም እስካሁን የሚባል የሚወራውን ያህል በእናንተ መንገድ ሲነጉዱ ስላላየን እናንተ “የእኛ” ያላችሁትን ሁሉ አንሰጣችሁም፡፡እነሱ ወትሮም አሁንም እዚህ ናቸው፡፡አብረን ነን፡፡ከኛ እንጅ ከእናንተ የሚቆሙ አይደሉም፡፡አትፎክሩ!!ንግሥናችሁ ከብሎግ አልፎ መሬት እንዳይወርድ እኮ ነው ይሄ ሁሉ ድካማችን!!አየነው እኮ!!ፕሮቴስታንት ከቶ ለዓለም የሞራል እሴት ምን የረባ ፋይዳ አመጣና የምንከተለው??!!የሥጋ ፈቃድን እየተከተለ መጽሐፍ ሲበርዝ ለሚውል ድኩም አውሮፓ መራሽ፣መርህ አልባ የሉተር ፍልስፍና እንዴት ተደርጎ እጅ ሊሰጥ??!!እኮ እንዴት??!!ዛሬ የያዘውን ነገ ለሚጥል መሰረት አልባ እንኳንስ እኛ የቅድስት ተዋሕዶ ልጆች በሳይንሱ የመጠቀችው ካቴሊካዊት ቤተክርስቲያንም ነቅላችኋለች!!ድሮ “…በእንግሊዝኛ እና በኢንተርኔት ክብረ ቅዱሳን አይነገርም፤ፈረንጅ ሁሉ ጴንጤ ነው፤ምልጃ ብሎ አስተምህሮ በየትም ዓለም የሌለ ኋላቀር ትምህርት ነው …” እያላችሁ ቀሰጣችሁ፡፡ “የዓለም መጽሐፍቅዱስ ብዛት 66 ብቻ ነው” እያላችሁ አታለላችሁ፡፡ዓለም የፕሮቴስታንት ብቻ ትመስል!!የሐዋርያት ሥራ በራሱ ገድል መሆኑ እየታወቀ፣ሐዋርያው ጳውሎስ በእብራውያን 11 ጊዜ አጠረኝ እስከማለት ድረስ ገድለ አበውን ሲዘክርና በዚሁ መልእክቱ በምዕራፍ 13 ቁ 7 ዋኖቻችንን እንድናስብ እያሳሰበን “ሥመ - ቅዱሳንን አታንሱ” ብላችሁ የተሞላችሁትን ለፈፋችሁ፡፡እሱ ጊዜ አሁን አልፏል፡፡አዲስ ትውልድ በሁሉም አቅጣጫ እየተፈጠረ ነው፡፡ይሕ ትውልድ ደግሞ ምዕራባዊውን ፕሮቴስታንት ከካቶሊኩ፣ምስራቃዊውን ኦርቶዶክስ ከኦሪየንታሉ ለመለየት እንዲችል ሆኖ በመረጃ ከመረጃ የተሰራ ነው!!ስለዚህ ሚሽነሪ ፈረንጆች በስመ “ፈረንጅ አዋቂ ነው” ብሂል የሚቀስጡበት ጊዜ አለፈ!!አለፈ!!ቻው!!ቻው!!
  3. በነገራችን ላይ፡- ያወራችሁት ምስጢር አይደለም፡፡ወሬውም ለእናንተ ሳይሆን በእናንተ ነው!!ስለማታስተውሉ እንጅ የቀደመ 2004 ዓ.ም የግንቦት ውግዘታችሁን አጠናክሮ ከያላችሁበት ህዋሳታችሁን የሚመነግል ነው--እቅዱ፡፡የ33ኛው የጠ/ሰ/ጉባኤ የአቋም መግለጫ ዝርዝር ማስፈጸሚያ እኮ ነው ይሄ፡፡ “ደንቆሮ የሰማ እለት ያብዳል!!” ካላያችሁት እዩት!! ይሄው በhttp://www.addisababa.eotc.org.et/site/ በኩል…“፫.፮.የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ ስለመቆጣጠር
  ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው ውሳኔ መሠረት የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ የሚያራምዱ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከተወገዙና ከተለዩ በኋላ የተዳከሙ ቢመስልም ውስጥ ለውስጥ እንቅስቃሴው ቤተ ክርስቲያንን እየጎዳ ያለ መሆኑን ጉባኤው ከምዕራብ ወለጋና ከቄለም ወለጋ አህጉረ ስብከት ከቀረበው ዘገባዎች ተገንዝቧል፡፡ ስለዚህ በቤተ ክርስቲያንና በአገልግሎቷ ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ያለውን የተሐድሶ እንቅስቃሴና የሌሎችንም መናፍቃን ተጽእኖ ለመቋቋም ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋትና ምእመናን በእምነታቸው ጸንተው እንዲኖሩ በማስተማር ተግተን እንሠራለን…አራ ነጥብ!!”
  ስሙኝ እማ!!አስተዳደር እንጅ ሃይማኖት እኮ አይታደስም!!ፈጽሞ አንድ ጊዜ ተሰጥቷላ!!ለማንኛውም ፈንድ የሚያረጋችሁ አካል ካለ ለፈንድ ማስለቀቂያ ያህል የሚሆን ሪፖርት ይሆን እንደሆነ እንጅ ይሕ ዜና ታላቅ፤ሳይሆን ውዱቅ ነው!!ዜና ውዱቅ፣እለ ውዱቃን፣ዘወድቀ ማዕከለ - ተዐይን!!
  መቼም ሃይማኖት ባያገናኘንም ለዘወትር ትብብራችሁ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት፣በኦርቶዶክሳዊት ሥርዓት ምስጋናየን አልነፍጋችሁም!!አመሰግናለሁ!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ሰው እስቲ ፈጣሪ እድሜ ይስጥህ

   Delete
 5. የተገላቢጦሽ(የሐ ሥ 24/5---7 ረከብናሁ ለዝ ብእሲ ይነብብ ጽርፈተ ወይገብር ማዕሌተ ወየሀውክ ኩሎ
  በኩሉ በሐውርት ወይሜህር ካህደ ዘሕዝበ ናዝራውያን ጳውሎስ ትክክለኛውን ቢያስተምር ጠላት ይቀባል
  ጥላት እንደሚባለው መናፍቅ ከሀዲ ተባለ ከዚያ በኋላ ካናጉንስጢስ እስከ ጳጳስ ስም እንዳይሰጣቸው በመፍራት ከውነት እየራቁ በዕብለት እየዘቀጡ ይኖራሉ (እንዲህ ያለ ዘመን የተገላቢጦሽ
  አህያ ወደሊጥ ውሻ ወደግጦሽ) እናም የውነት ሰዎች እንደ ጳውሎስ ፈጣሪ ከጐን አለሁ የሚል ጥሪ ካላሰማ በስተቀር ያስቸግራል።

  ReplyDelete
 6. ተረት ተረቱ ተነቃባችሁ! እድሜ ለተሃድሶ ።ዳግም በደብተራ አሸንክታብ አንታለልም!!።አንቀበላችሁም........ ወንጌል ብቻ።።።።!

  ReplyDelete
 7. ተረት ተረቱ ተነቃባችሁ! እድሜ ለተሃድሶ ።ዳግም በደብተራ አሸንክታብ አንታለልም!!።አንቀበላችሁም........ ወንጌል ብቻ።።።።!

  ReplyDelete
 8. ተረት ተረቱ ተነቃባችሁ! እድሜ ለተሃድሶ ።ዳግም በደብተራ አሸንክታብ አንታለልም!!።አንቀበላችሁም........ ወንጌል ብቻ።።።።!

  ReplyDelete
 9. ደቀ መዛሙርቱ ከየአህጉረ ስብከቱ ሲላኩ ጤናማ እንደሆኑ፣ ነገር ግን ተመርቀው ሲመለሱ ከነችግራቸው ሌላ ሰው ሆነውና መስለው ይመለሳሉ፤ ለዚህ የችግሩ ምንጮች ኮሌጆች እንደሆኑ ያመለክታል፡፡ ምክንያቱም መንፈሳውያን ልጆች ተልከው መናፍቃን ሆነው ሲመለሱ እያንዳንዱን ኮሌጅ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባዋል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ኮሌጆች ሊፈተሹና ሊመረመሩ ይገባል፡፡
  አቤት አቤት አቤት……………..!
  በቃ የሲኖዶሱ አመለካከት ይኼዉ ነዉ ማት ነዉ? መማር መናፍቅ የሚደርግ ከሆነ በቃ ቤተክርስቲያን በአብነት ተማሪዎች ብቻ ትመራ ማለት ነዋ? በጣም ያሳዝናል አንድ ርምጃ ወደፊት ሁለት ወደኋላ እየሄድን ፍጻሜያችን ምን ይሆን? ታምረ ማርያምን አስደግመን ከመመለስ ገላግለዉ መጽሐፍ ቅዱስ በመስበክ አጥሩን የሰበሩት የወንጌል ሰባኪዎች መናፍቅ እየተባሉ ታዲያ እኛ ማንን እንከተል ጎበዝ?

  ReplyDelete
 10. Pls listen the following panel discussion about 'Memeher' Girma by calling 7124325221 code 2484446# and record # 2005# and 2009#.

  ReplyDelete
 11. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስና መልካም ትምህርቱ እንዳይነገር ምእመናን ሳይቀር እያወቁ እንዳላዋቂ የዕብለት
  ተባባሪዎች ናቸው። ጽድቅን እናውቃለን የሚሉ ግን ናሁ ኩሉ ዓለም ተለወ ድኅሬሁ እያሉ የጽድቅ እንቅፋትና መሰናክል መሆን ከጀመሩ ዘመናትን አስቆጥረዋል።ሆኖም የተሐድሶ አባላት ስህተትን ለማረም
  የሚያደርጉት ያላሠለሰ ጥረት ከማስገረምም አልፎ ይበል ያሰኛል(አዋቆች ካልሰጡት ማረሚያና አራሚ፤
  ንፍጥ ይለቀልቃል አላዋቂ ሳሚ) የመንደር አባባል ዕንኳ የሚሰማ ቢገኝ ይህም ምናልባት ነው።

  ReplyDelete
 12. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስና መልካም ትምህርቱ እንዳይነገር ምእመናን ሳይቀር እያወቁ እንዳላዋቂ የዕብለት
  ተባባሪዎች ናቸው። ጽድቅን እናውቃለን የሚሉ ግን ናሁ ኩሉ ዓለም ተለወ ድኅሬሁ እያሉ የጽድቅ እንቅፋትና መሰናክል መሆን ከጀመሩ ዘመናትን አስቆጥረዋል።ሆኖም የተሐድሶ አባላት ስህተትን ለማረም
  የሚያደርጉት ያላሠለሰ ጥረት ከማስገረምም አልፎ ይበል ያሰኛል(አዋቆች ካልሰጡት ማረሚያና አራሚ፤
  ንፍጥ ይለቀልቃል አላዋቂ ሳሚ) የመንደሩን አባባል ዕንኳ የሚሰማ ቢገኝ ይህም ምናልባት ነው።

  ReplyDelete
 13. tenekabehe tehadesu men tehone engedihe

  ReplyDelete
 14. ሚዛን እየጠበቃችሁ ብትፅፉ መልካም ነዉ ።

  ReplyDelete
 15. Menafek malet tirgumu eyetezaba new.pls tikikelgna tergumu negerugne.

  ReplyDelete
 16. ከአንድ ሁለቱ አስተያየቶች ውጭ ሌሎቹ አንድ አይነት ዘፈን የሚዘዘፍኑ አበዛኛዎቹም የራሳቸውን አመለካከት ሳይሆን የፀሐፊውን ፅሑፍ እንዳለ የገለበጡ ናቸው። ለሁሉም ቤተክርስቲያን አትታደስ አንድ ጊዜ ክርስቶስ አዲስ
  አድርጏታልና። እናንተ አላማችሁ ሐሰተኛው ክርስቶስን በቤተክርስቲያን ለማንገስና የውሸት ትምህርታችሁን
  ለማስገባት መሆኑ የታወቀ ግልፅ ነው። ደግሞ የተወችውን
  ወንጌል ይማልልኛል። የልደት የጥምቀት የስቅለት
  የመስቀል በአላቶቿ እንሿን በጥቂቱ የክርስቶስ ወንጌልን
  እንደያዘችና እንደምትፈፅም ይገልፃሉ። እናንተን ከቤተክርስቲያን ከነ ክህደታችሁ ለማስወጣት ጥናት እንዲደረግ መወሰኑ ተገቢና በፍጥነት መከናወን አለበት። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መልካሙን ስንዴ ዘርቶ ሳለ ጠላት በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቷልና እናንተም ጠላት የዘራችሁ የቤተክርስቲያን እንክርዳዶች ናችሁና ከየተቋማቱ መወገድ አለባችሁ፡

  ReplyDelete
 17. Edmeeeee Ltehadesooooooooooooooo

  ReplyDelete