Tuesday, December 29, 2015

ቤተ ክርስቲያኗ አዲስ ልታቋቁም ባቀደችው የቴሌቪዥን ጣቢያ ገና ከጅምሩ ሊፈጸምበት የነበረው ሙስና መክሸፉ ተሰማቅዱስ ሲኖዶስ በዘንድሮው የጥቅምት ስብሳባ ላይ እንዳስታወቀው ቤተክርስቲያኒቱ የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ስርጭት ማለትም የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት ልትጀምር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለዚህም በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበው ጥናት ላይ መሠረት በማድረግ የአንድ ዓመት በጀት 12 ሚሊየን ብር ቅዱስ ሲኖዶስ አጽድቋል፡፡ ይህን ፕሮጀክት የሚመራ ቦርድ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰየመ ሲሆን የቦርዱ ሰብሳቢ የስብከተ ወንጌል መምሪያ የበላይ ሃላፊ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ሐሳቡ በመጀመሪያ የመነጨውና እንቅስቃሴው የተጀመረው ጉዳዩ ግድ ከሚለው የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሲሆን፣ የሰውን ሐሣብ በመንጠቅና የራስ አስመስሎ በማቅረብ በተግባር የተመሰከረላቸውና የሰዎችን ድርሰት በራሳቸው ስም በማሳተም ጭምር ቅሌት ውስጥ የገቡትና እስካሁን በሲኖዶስ ተጠያቂ ያልሆኑት አባ ሳሙኤል ይህን የስብከተ ወንጌልን ፕሮጀክት በመንጠቅ በሌላቸው ውክልና የራሳቸው አስመስለው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ሐሳቡን ራሳቸው ያመነጩትና የጀመሩት ያህል በመቁጠር ስለጉዳዩ የማቅ ልሳናት ሆነው እያገለገሉ ባሉት እንደ አዲስ አድማስ ባሉ ጋዜጦች ላይ ጉዳዩን የተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ እንደነበር የጥቅምት 20/2008 አዲስ አድማስ ጋዜጣን መመልከት ይቻላል፡፡
ይሁን እንጂ አባ ሳሙኤል ከቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሁም ከቦርዱ እውቅና ውጪ በስልት መንቀሳቀሳቸው ስለተደረሰበት የጉዳዩ ተዋናዮች ለነበሩት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መጻፉን ከቤተክህነት አካባቢ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሊቋቋም የታቀደው የቴሌቪዥን ጣቢያ እስራኤል አገር ሲሆን፣ ባለፈው ሰሞን አባ ሳሙኤል ከዚህ ጋር ባልተያያዘ ለህክምና በሚል ፓትርያርኩን ፈቃድ ጠይቀውና ደብዳቤ አጽፈው፣ በጎን ደግሞ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ የአቡነ ማርቆስን ውክልና ወስደው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል  ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አባ ሃይለማርያም የፈረሙበትን ደብዳቤ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ለመዋዋል ሙከራ አደርገው ነበር፡፡ ይህ የሆነው አባ ማቴዎስ ከሲኖዶሱ ስብሰባ በኋላ እምብዛም በቢሮ የማይገኙ በመሆናቸው ነው ተብሏል፡፡ 

Monday, December 28, 2015

ማኅበረ ቅዱሳን መንፈሳውያን ኮሌጆች ላይ በከፈተው የጽሑፍ ዘመቻ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ነውራሱን ብቻ ትክክልና የቤተክርስቲያን ጠበቃ አድርጎ የሚመለከተውና ሌላውንና የእርሱን ተረት አልከተልም ያለውን፣ በአሰራር እንኳን ለእርሱ አልመች ያለውን ሁሉ መክሰስና ስሙን ማጥፋት ልማዱ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያወጣ ባለው ስምአ ጽድቅ ጋዜጣ ላይ ሶስቱን አንጋፋ መንፈሳዊ ኮሌጆች ማለትም የቅድስት ሥላሴ፣ የመቀሌው ከሳቴ ብርሃንና ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስን የመናፍቃን መፈልፈያ ሆነዋል በማለቱ ተቃውሞ እየገጠመው ነው፡፡
ዛሬ ማኅበረ ቅዱሳን አለአቅሙ ሊዘልፋቸው የተነሳው እነዚህ ሦስቱ ኮሌጆች ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው የሚንቀሳቀሱና የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት የቤተክርስቲያኒቱን ራዕይ ያሳካሉ የተባሉ ኮሌጆች ናቸው፡፡ ኮሌጆቹን የመሠረትዋቸው ሰዎችን እንኳን ብንመለከት ለትምህርትና ለለውጥ ከፍተኛ ትኩረት የሰጡ አባቶች ፍሬ መሆናቸውን እገነዘባለን፡፡ ለምሣሌ የቅድስት ሥላሴ ደግሞ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ቴዎፍሎስ፣ የከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ መሥራች ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ፣ የሰዋሰው ብርሃን ደግሞ የአጼ ኃ/ሥላሴ ምስረታ ውጤት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ትምህርት ቤት እስከ ሚኒስቴር ደረጃ የደረሱ ደቀመዛሙርት ወጥተውባቸዋል፡፡ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን እንኳን ብንመለከት የቅ/ሥላሴ ኮሌጅ እንደ አይን ብሌን የሚያሳሳ ኮሌጅ እንደሆነ ታሪክ ያስረዳል፡፡ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ይቅርና አሁን በሕይወት ያሉም የሌሉም አባቶች ሊቃውንት ወጥቶውበታል፡፡ ለመጥቀስ ያህል፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ ፕሮፌሠር ሉሌ፣ ዶ/ር ሐዲስ፣ ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፣ አቶ እሱባለው፣ አቶ አእምሮ ወንድምአገኘሁ፣ አቶ ገ/ክርስቶስ መኮንን፣ ዶ/ር ምክረ ሥላሴ ገ/አማኑኤል፣ ዶ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ ዶ/ር ስርግው ሐብለ ሥላሴ፣ ዶ/ር አምሳሉ አክሊሉ፣ ፕ/ር ታደሰ ታምራት በመጀመሪያ የዚህ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ በየተሰማሩበት መስክ በቤተክርስቲያንና በአገር ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመጣ የተንቀሳቀሱና በጎ አሻራቸውን ያሳረፉ ታላላቅ ሰዎች ናቸው፡፡

Friday, December 25, 2015

ማሙዬ በፎርጂድ ዲግሪ መቀጠሩ በመረጋገጡ ታሰረበአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ የቆየውና ባልዋለበት ሙያ መጋቤ አእላፍ የሚል ማዕረግ የተሸከመው ማሙዬ እንደ ባልንጀራው ታዴዎስ በፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ ቅሌት ሰሞኑን ለእስር መዳረጉ ተሰማ፡፡ ማሙዬ በሂዩማን ሪሶርስ ማኔጅመንት ከአልፋ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪ እንዳለው ተደርጎ በአባ እስጢፋኖስ ጊዜ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በነበራቸው የውስጥ ስምምነት የማቅን ተልእኮ ይፈጽማሉ ተብለው ከታሰቡትና በሀገረ ስብከቱ ቦታ ከተሰጣቸው ሰዎች አንዱ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ አባ እስጢፋኖስ ሀገረ ስብከቱን ለማቅ ለማስረከብ ውስጥ ለውስጥ ሲሰሩ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ማሙዬ በደብረ ብርሃን ሥራ አስኪያጅ ሆኖ እያለ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬምን ከፖሊሶች ጋር ተመሳጥሮ በመኪና ሲሄዱ መሳሪያና የጥንቆላ መጽሐፍ ይዘዋል ብሎ ሊያሳስራቸው ሲሞክር ጉዳዩ ውሸት ስለሆነ ስራ አስኪያጅነቱ ተባርሮ የነበረ ቢሆንም የማቅ አባል ስለሆነና በመሰሪነቱ ለማቅ ስለሚጠቅም ግን አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀጠር መቻሉን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 

Saturday, December 19, 2015

ግጭትና ጦርነት የማያስተምራት አገር

ስለራሳችን እንዲህ እንናገራለን ፦
-      እንግዳ ተቀባይ ሕዝቦች ነን ፤
-      ብዙ ብሔር ብሔረሶችና ሕዝቦች ተዋደው የሚኖሩባት አገር አለን ፤
-      ለቁጥር የሚታክት “ክርስቲያን” ፣ እልፍ አዕላፍ ገዳም ፣ መድረክ የሚያጨናንቁ አገልጋይ ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናትና ዘማርያን አሉን ፤
-      ከእኛ ወዲህ ማን አለ አማኝ? ከእኛ በላይ ጸዳቂ ፤ ታማኝ አገር ወዳድ ወዴት አለ?! …
ስንታይ ግን፦
-      “ባዕድ እንግዳ” ለመቀበል ሆዳችንን እንደአገር ስናሰፋ ፥ ከጎረቤትና ከወገናችን ጋር ግን “ጠብ ያለሽ በዳቦ” በሚል መንፈስ የተያዝን ፤
-      አገልጋዮቻችን ጸንሰው ወልደው ፣ አሳድገው የሰጡን አንዱ መልክ ዘረኝነትና ልዩነት ነው ፤
-      ከእኛ በላይ ሁሌም ሰው የለም ብንልም ዘወትር ግን እየኖርን ያለነው ከሰው በታች ጅራት ሆነን ነው …
     ሰሞኑን በከፊል የአገራችን ክፍል ብጥብጥና ሁከት ፤ ደም ማፍሰስና ግድያ ነግሶ ነበር፡፡ ይህን ሁሉ አድራጊው ሌላ ወራሪ ወይም እንግዳ አሸባሪ መጥቶብን አይደለም ፤ ሟችም እኛው፥ ገዳይም ያው እኛው ኢትዮጲያውያን ፤ ንብረት አውዳሚም፥ ንብረት የሚወድምበትም ያው የአንድ አገር ዜጎች ፤ የአንድ ርስት ወሰንተኞች ፤ የአንድ ወንዝ ጠጪዎች እኛው ነን፡፡
 
      እስኪ አስተውሉ፥ አንድ መቶ ዓመታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በእኛና እኛ መካከል የተደረጉ ጦርነቶችን ብናነሳ፦ በ1909 ዓ.ም በራስ ተፈሪና በንጉሥ ሚካኤል መካከል በሰገሌ ፣ በ1922 ዓ.ም በራስ ተፈሪና በራስ ጕግሳ በአንቺም ወይም በበጌምድር ፣ ከ1966-1983 ዓ.ም ወታደራዊው መንግሥት ደርግና ኢሕአዴግ በተለያየ ቦታ ያደረጉት አስቀያሚ ጦርነት ፣ በ1994 ዓ.ም ሁለቱ “ወንድማማች” ኢትዮጲያና ኤርትራ ያደረጉትን ጦርነት (ወታደራዊው መንግሥት በአንድ ጉድጓድ የፈጃቸው የንጉሡ ዘመን መሪዎችና ሌሎችም ሳይካተቱ) ይህን ሁሉ ስናነሳ ምን ይታወሰናል?!

     በእውኑ እኛ ነን ተቻችሎ አዳሪ? እኛ ነን ለእግዚአብሔር ቀናተኞች? ከእኛ በላይ አማኝ ፤ ከእኛም ወዲያ ክርስቲያን የሚባልልን በእውነት እኛ ነን?! እኔ የፖለቲካ ተንታኝ አይደለሁም፥ ዳሩ ይህን አምናለሁ ፤ ማርቲን ሉተር ኪንግ ፣ ማኅተመ ጋንዲ ፣ ታዋቂው የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ጦር ሳይመዙ ፣ የጥይት ባሩድ ሳያጤሱ ለሕዝቦቻቸው ነጻነትን ያጎናጸፉ ምርጥ የነጻነት ታጋይ ተምሳሌቶች ናቸው፡፡ እኒህ መሪዎች ከሕዝባቸው እኩል መከራ ተቀብለዋል ፣ ተርበዋል ተጠምተዋል ፣ በእስር በግርፋት ተሰቃይተዋል ፤ በፍጻሜው ግን ዘረኞችን ድል አድርገዋል፡፡

Tuesday, December 15, 2015

ከጥቅምቱ ሲኖዶስ ውሳኔዎች አንዳንዶቹ እንደ ገና ሊጤኑ ይገባልRead in PDF
ከዘሩባቤል
በቅድሚያ የጳጳሳት ጉባኤ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ በግብረ ሐዋርያት እንደ ተጻፈው ሐዋርያትን አብነት አድርጎ የሚሰበሰብና ለቤተክርስቲያን (ለተቋሙ ወይም ለምድራዊ ድርጅቱ ሳይሆን ለማኅበረ ምእመናኑ) እድገትና መስፋፋት በዓለም ላይ ለሚኖራትም በጎ ተጽዕኖ የሚበጁ ውሳኔዎችን በመወሰን እንደ እግዚአብሔር ቃል መሠረት ቢሠራ “እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናል” እስከማለት የደረሰ ሥልጣን እንዳለው መረዳቱ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ይህን ሥልጣኑን ከዚህ ውጪ የሚጠቀምበት ከሆነና ለእግዚአብሔር ክብር ሳይሆን ለራስ ወይም ለአንድ ማኅበር ክብር፣ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ሳይሆን ለራስ ወይም ለአንድ ማኅበር ጥቅም የሚበጁ ውሳኔዎችን የሚወስን ከሆነ ግን በውሳኔዎቹ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተባባሪ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ውሳኔዎቹ የሰዎቹ ብቻ ይሆናል፡፡ ውሳኔዎቹም የወረቀት ላይ ነብር ከመሆን አያልፉም፣ በሰውም በእግዚአብሔርም ፊት ክብደታቸው ይቀንሳል፣ ተቀባይነትም ያጣሉ፡፡ ባለፈው ጊዜ እንኳን ዲ/ን ዳንኤል ክብረት “ስማችሁ የለም” በሚል ርእስ ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ እኛ ተነክተናልና መጽሐፉ በሊቃውንት ጉባኤ ይታይና ውሳኔ ያግኝ ተብሎ ከተወሰነ በኋላ ውሳኔው በገዛ እጁ ቀሊል ሆኖ ስለተገኘ  የትም እንዳልደረሰ ማየት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ውሳኔው አጀንዳውን ያነሱት ጳጳሳት ለራሳቸው ክብር ከመጨነቅና ጉልበታቸውን ለማሳየት ከመፈለግ የወሰኑት እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ከማሰብ የቀረበና በሲኖዶስ መታየት የነበረበት ጉዳይ ባለመሆኑ ነው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስለኢየሱስ “አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ ምስክርነትን በሰጠ ጊዜ ኢየሱስ ይህን ሰማያዊ አባቴ እንጂ ሥጋና ደም አልገለጠልህም ብሎ ብፁዕ መሆኑንና በእርሱ ምስክርነት ላይ ቤተክርስቲያን እንደምትመሠረት ተናገረለት (ማቴዎስ 16፡16-19)፡፡ እዚያው ምዕራፍ ላይ ዝቅ ብሎ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ እንደሚቀበልና እንደሚገደል በሦስተኛውም ቀን እንደሚነሣ ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠላቸው ጊዜ ከሰማያዊው አባት የሰማውና ብፁዕ ነህ የተባለው ጴጥሮስ፣  እዚህ ላይ ከሰይጣን ሰምቶ ጌታን ወደ እርሱ ወስዶ “አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም” ብሎ ሊገሥጸው ሲጀምር ኢየሱስ ዘወር አለና ጴጥሮስን “ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።” (ማቴዎስ 16፡21-23)፡፡ 

Monday, December 14, 2015

ውግዘትና የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት - ክፍል ስምንት


Read in PDF 
በዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ
ካለፈው የቀጠለ
3.  ድህረ ውግዘት ልናደርገው የሚገባን ጥንቃ
3.1.አውግዞ መለየት በቂ አይደለም

“ኤጲስ ቆጶስ ሆይ የበደለውን አውግዘህ ብትለየው በውጭ አትተወው፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መልሰው እንጂ፡፡ የጠፋውንም ፈልግ፡፡ ስለኃጢአቱ ብዛት እድናለሁብሎ ተስፋ የማያደርገውን በሁሉ ጠፍቶ ይቀር ዘንድ አትተወው፡፡ እንዲህም ኤጲስ ቆጶስ የኃጥኡን ኃጢአት ሊሸከም ይገባዋል፡፡ እርሱም ፈጽሞ እንደበደለ
ያድርግለት፡፡ የበደለውንም “አንተ ተመለስ እኔም ስለእኔና ስለሁሉ በሞተው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምሳል ስለአንተ ሞትን እቀበላለሁ ይበለው፡፡”

(ፍትሐ ነገስት አን.5 ቁ.122)

    ኃጢአትን በግልጥ በመሥራቱና ብዙዎችን ስለማሰናከሉ የተወገዘ ሰው፤ ፈጽሞ ሊጣልና ሊወረውር አይገባውም፡፡ ምንም እንኳ ቃሉ “እንደአረመኔና እንደቀራጭ ይሁንልህ”(ማቴ.18፥17) ቢልም፤ “ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ቢፈረድም” (1ቆሮ.5፥5) አውግዘን የለየውን “ወንድም” ዳግም ልንፈልገው፤ ከደጅ ወደ ቤቱ ልንመልሰው “የቀጣንህ ቅጣት ይበቃሐልና ፤ ከልክ ባለፈ ሐዘን አትዋጥ ይልቅ ተመለስና ተጽናና … በክርስቶስ ፊት ይቅር ብለንሐል፡፡”(2ቆሮ.2፥6-11)
   ጌታ ኢየሱስ በዱርና በጫካ የጠፋውን፤ የባዘነውን በግ አዳምን ሲፈልገው (ሉቃ 15፥3-7)ብዙ ዋጋ ከፍሎ ነው፡፡ “ኤጲስ ቆጶሳት ሆይ መድኃኒታችንን ንጉሳችንን አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አብነት ልታደርጉት ይገባችኋል፡፡ ጉበኞችም ልትሆኑ ይገባችኋል፡፡ እርሱንም ምሰሉት የምትራሩ ሰላምንም የምትፈልጉ ትሆኑ ዘንድ፡፡ … ኃጥእ ፩ ጊዜ ወይም ፪ ጊዜ ቢበድል ንቀህ ከአንድነት አትለየው፤ በምግብ ጊዜ ከእርሱ ጋር ተባበር አንጂ፡፡ንስሐውንም ተቀበል ፡፡ተጸጽቶ ወደአባቱ በተመለሰው ልጅ አምሳል (ሉቃ.15፥17-24) ልብስ አልብሳቸው፡፡ በጥምቀት ፈንታ እጅ በማኖር ባርካቸው፡፡ ንስሐ የሚገቡ ሰዎች በእጃችን በመባረክ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ያገኛሉና፡፡ ወደ ቀደመ ቦታቸውም መልሳቸው፡፡      (ፍትሐ ነገስት አን.5 ቁ.126፤132)
     እንግዲህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትና የቤተ ክርስተያናችን ቀኖና ይህ ነው፡፡ አውግዞ መለየት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ መልሶ ማየትና መፈለግ፤ እድል መስጠት ይህን ሁሉ አድርገን በተመለሰ ጊዜ ይቅር ልንለው ይገባናል፡፡(ሉቃ.17፥3)

Tuesday, December 8, 2015

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሃይማኖት አልባውን ዘሪሁን ሙላቱን አባረረሃይማኖት የለሽ በመሆኑ የሚታወቀውና በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ጥናትና ምርምር ሥራ ላይ የተመደበው ዘሪሁን ሙላቱ ከሥራ ተባረረ፡፡ ላለፉት 4 ወራት በሥራ ላይ የቆየው ዘሪሁን የተባረረው ከ10 ገፅ በላይ የተሣሣተ መረጃ አዘጋጅቶ የኮሌጁ የበላይ ኀላፊ አቡነ ጢሞቴዎስና መምህር ግርማ ባቱ ኮሌጁን ለመናፍቃን አሳልፈው ሊሰጡ ነው በሚል ለአቡነ ማቴዎስ እና ለአቡነ ሉቃስ የተሳሳተና ስም የሚያጠፋ መረጃ በመስጠቱ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ እንደ ቸሬ አበበ የኮሌጁን ዌብሣይት ለግል ጥቅሙ በማዋል “ኦርቶዶክስ መልስ አላት” የሚለውን ሲዲ የኮሌጁ ልሳን አስመስሎ በዚያ ላይ ሲያስተዋውቅ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኦርቶዶክስ መልስ አላት የተሰኘው ሲዲ ዘሪሁን የእግዚአብሔርን ቃል እያጣመመና እየሸቃቀጠ ያቀረበበት ሲዲ ሲሆን ቤተክርስቲያኒቱ ሳትወክለው የቤተ ክርስቲያኗ ትምህርት አስመስሎ በማቅረብ ሕዝብን ሲያሳስትበት እንደ ነበረ የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ዘሪሁን ኮሌጁንና ቤተክርስቲያንን የማይወክሉ ፅሁፎች በዌብሳይቱ ያወጣ የነበረ ሲሆን በዚህ ድርጊቱ የኮሌጁን ክብርና ምስጢር አልጠበቀም፡፡ በዚህ ድርጊቱ “ዘዳግም ቸሬ” ተብሎአል ቸሬ አበበ የተባረረበት አንዱ ምክንያት ይህ ነውና፡፡

Thursday, December 3, 2015

ውግዘትና የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት - ክፍል ሰባት


Read in PDF 
በዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ
ካለፈው የቀጠለ
2.   በውግዘት ጊዜ ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄ
     ነገሩ በምስክር ተረጋግጦ፤ ትምህርቱ ወይም ድርጊቱ ብዙዎችን ያሰናከለና እያሰናከለም ያለ እንደሆነ ቀድሞ በሚገባ ተጢኖ፥ ከተደመደመ በኋላ ወደውግዘት መሄድ የሚገባ ነገር ነው፡፡ በዚህ ጊዜ፦
2.1. በንጹህ ህሊና መዳኘት

   የንጹህ ህሊና መገኛ መሠረቱ ዕውቀትና የራስ ጥበብ ሳይሆን ዛሬም ትኩስ ሆኖ በሰማያት ያለው የክርስቶስ ደም ነው፡፡ (ዕብ.9፥10 ፤ 14 ፤ 1ጴጥ.3፥21) በንጹና መልካም ህሊና ለመዳኘት በደሙ ህያውነት ቀድሞ መመላለስ ያሻል፡፡ የክርስቶስ ደሙ ለህይወታችን ምን ያህል እንደሚያስፈልግ በሚገባ ከተረዳን፤ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለተወጋዡም ያስፈልገዋልና በውግዘት ጊዜ ክርስቶስንና ቤተ ክርስቲያንን ብቻ እንድናስብና በእግዚአብሔር ፍርሃት ውስጥ እንድንኖር ያደርገናል፡፡ ስለዚህ ምስክሮችን በቃሉ መሠረትነትና ሚዛንነት ላይ በማስቀመጥ በንጹህ ህሊና መዳኘት ያስችለናል፡፡
    በክርስቶስ ደም የተወቀረ ንጹህ ህሊና ከእግዚአብሔር ውጪ የሚፈራው ምንም ነገር የለውም፡፡  
v አድሎአዊነት ንጹህ ህሊናን ያሳጣል፡፡
v አድሎአዊነት ፍርድን ያዛባል፡፡
v አድሎአዊነት ደምን በእጅ ያስጨብጣል፡፡
v አድሎአዊነት ፍርድን በራስ ያስመልሳል፡፡
     ስለዚህ በማውገዝ ጊዜ በንጹህ ህሊና መሆን ከክፉ ጥፋት ያድናል፡፡ የጌታን ትምህርትና ቀኖናን እንጂ የሰዎችን ስሜት አለመከተል ከብዙ ነገር ይጠብቀናል፡፡ ይህን በተመለከተ በአንድ ወቅት ፓትርያርክ አቡነ ጳወሎስ በጻፉት ደብዳቤ እንዲህ ብለው ነበር፦

Monday, November 30, 2015

የቀድሞው ፲ አለቃ ተክላይ የአሁኑ ጳጳስ አባ ድሜጥሮስ ማናቸው?በቀደመው ዘመን ወደጵጵስና የሚመጡ መነኮሳት በአብዛኛው በዕውቀታቸውም በኑሯቸውም የተመሰከረላቸው ከእነርሱም ብዙዎቹ ጵጵስናን የሚሸሹና በግድ ተለምነው የሚገቡበት መንፈሳዊ ሃላፊነት ነበር፡፡ ዛሬ ግን የተገላቢጦሽ ሆኖ ዕውቀቱም ሆነ ኑሮው የማይጠየቅበት፣ በፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ ይህንንና ያንን ተምረዋል የዚህ መምህር ናቸው እየተባለ በሕይወት ታሪካቸው ውስጥ እየተካተተ የሚቀርብበትና የሌላቸውን ሰብእና እንዲያገኙ ተደርጎ የሚገቡበት፣ ተለምነውና የግድ ተብለው ሳይሆን ለምነውና ጉቦ ሰጥተው ጭምር የሚገቡበት፣ ከዚያ በኋላ ማንኛውንም ወንጀልና ኃጢአት ቢሰሩ የማይከሰሱበትና ከህግ በላይ የሚሆኑበት ሃይማኖትን ቢጥሱ ኑፋቄን ቢዘሩ የማይጠየቁበት፣ በአንጻሩ ግን ያሻቸውን የሚያደርጉበት ትልቁ ሥልጣን ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ዛሬ ጵጵስና የቀደመ ክብሩን ያጣበትና የቀለለበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ አባ ድሜጥሮስም ዘመኑ ያፈራቸው ጳጳስ ናቸው፡፡ ለመሆኑ እርሳቸው ማናቸው ለሚል ጠያቂ መልሱ እነሆ፦      
በቀድሞው ስሙ ፲ አለቃ ተክላይ ግዛቸው ይባላል፣ ኤርትራዊ ሆኖ የደርግ ወታደር ነበር፡፡ ከብላቴ አምልጦ ወደ ዝዋይ ገዳም ሊገባ ሲል አቡነ ጎርጎርዮስ “አንተ ዘረኛ መሆንህን ሰምቻለሁና ልጆቼን ታበላሽብኛለህ” ብለው አባረውት እንደነበር አቡነ ዲዮስቆሮስ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ስለኤርትራዊነቱ አሁን የቤተ ክህነቱ ልዩ ጽ/ቤት ሠራተኛ መጋቤ ሠናያት አሰፋ በሚገባ ያውቃሉ፡፡ በዱባይ ደግሞ እነ አቶ በርሄ ይመሰክራሉ፡፡ ከአቡነ ጎርጎርዮስ ሞት በኋላ ግን ወደ ዝዋይ ገዳም ተመልሶ በመግባት መነኮሰና አባ ፅጌ ተባለ፡፡

Saturday, November 28, 2015

እነማን ጳጳስ ይሆኑ ይሆን?ጵጵስና ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የተሰጠ የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ነው። ልብ እንበል! የግለ ሰብእ ሥልጣን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያን ነው። ስለዚህ ከቤተ ክርስቲያን ዓላማ ውጭ ለሌላ ነገር ሊሠራ አይችልም። ለተቀደሰ ነገር ብቻ እንዲሆን የተሰጠው የህ የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ንብረት ለሌላ ጉዳይ ሆኖ ሌላ ነገር ሲሠራበት ቢገኝ ከባድ ወንጀል ነው። ለምሳሌ የግል ጥቅም፣ የዘረኝነት አገልግሎት፣ የፖለቲካ ወገንተኝነት፣ ወይም የዝሙትና የዚህ ዓለም ርኩሰት በጵጵስና ደረጃ ቢገኙ በጌታ መንግሥት ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን መታወቅ አለበት። ዛሬ ግን ጵጵስና ቆብና ቀሚስ ብቻ ከሆነ ብዙ ዘመናት አልፈዋል።
በዛሬው ጊዜ የጵጵስና ሹመት እየተፈለገ ያለው ለእግዚአብሔር መንግሥት አገልግሎት አይደለም ማለት ይቻላል።  በዚህ ዘመን በቤተ ክህነትም ሆነ በቤተ መንግሥት የሚሾሙ ሰዎች ሦስት ሰዎች ብቻ ናቸው። እነርሱንም እንደሚከተለው ላስተዋውቃችሁ።

Thursday, November 26, 2015

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ እና ስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊው ከሰባክያን ጋር ተወያዩ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና አዲስ የተሾመው የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል መመሪያ ኃላፊ መላከ ሰላም ዳዊት በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ አድባራትና ገዳማት ውስጥ ከሚያገለግሉ ሰባክያን ጋር ተወያዩ፡፡ ትናንት በ15/3/2008 ዓ.ም. በተደረገው ውይይት ላይ አዲሱ የመምሪያው ኃላፊ ወደ ፊት በመመሪያው ሊደረግ የታቀደውን በ13 ነጥቦች ሥር ያቀረበ ሲሆን ካቀረባቸው መሠረታዊ ነጥቦች መካከል፡-
·        እገሌ መናፍቅ ነው ለማለት እኛ ምንም መብት የለንምና እንዲህ ዓይነቱ በማስረጃ ያልተደገፈና ከበስተ ጀርባው ሌላ ድብቅ ዓላማ ያለው ውንጀላና ክስ ተቀባይነት ማጣት አለበት፡፡
·        ሰባኪው ኃላፊነት ተሰጥቶት እያለ በቡድንና በማህበር የተደራጁ ሕገወጦች ከመድረክ የሚያስወርዱበት ሁኔታ ይታያልና ይህን አሠራር እናስቆማለን፡፡ ይህን የሚያደርጉ ሰዎች ከዕውቀት ማነስ ስለሆነ የእውቀት ማበልፀጊያ የሚሆን ነገር ልንመሰርት ይገባል፡፡
·        ከሰባኬ ወንጌልነት ተነስተው አለቃ የሚሆኑ በጣም ውሱን ስለሆኑ በዚህ ያላለፉ ሕዝቡን በቅርብ ስለማያውቁ የችግር ፈጣሪዎች አካል ሆነዋልና ይህ ክፍተት እንዲሞላ መሥራት ያስፈልጋል፡፡
·        ጣልቃ ገቦች ለግል ጥቅማቸው እኔ ነኝ ባለቤት ስለሚሉ በየቀኑ የሚፈለፈሉ ማህበራት እውነተኞችን አንገት እያስደፉ ነው፡፡ በዚሁ ውስጥ መደበኛውን ሰባኪ ገፍትረው ጉባኤ እናዘጋጅ የሚሉ ቡድኖች፣ እገሌ የተባለውን ሰባኪ፣ ዘማሪ አንፈልግም፡፡ ከዚህ ማህበር እገሌ የሚባል ሰባኪ ይምጣልን እያሉ ወንጌሉን ገደል እየሰደዱት ነው በማለት መላከ ሰላም ዳዊት ይህንና ይህን የመሳሰለውን ወቅቱን ያገናዘቡ ሐሳቦችን አቅርቧል፡፡

Tuesday, November 24, 2015

ውግዘትና የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት - ክፍል ስድስት


Read in PDF 
በዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ
ካለፈው የቀጠለ
ስለውግዘት ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

   ቤተ ክርስቲያን በውግዘት የካደን ከሃዲና ኃጢአተኛውን ለመለየት የመጨረሻውና አማራጭ የሌለው መንገድ ነው፡፡ይህ ተግባር እጅግ ከባድ፤ የተጋ የጸሎት ጉልበትና የወንጌል ልብ የሚጠይቅ ነው፡፡ መናፍቃንንና ከሃዲያንን ብቻ ሳይሆን ነውራቸው ተገልጦ ብዙዎችን ያሳቱ ኃጥአንንም የምናወግዝ ከሆነ የተከፈለላቸውን ሰማያዊ ዋጋ በማሰብና የሟቹን ሞት የማይፈቅደውን የጌታን መንፈስ ባለማሳዘን በሚያስተውል ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡
    በዛሬ ዘመን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚመክሩና የሚገስጹ የሚያቀኑም ልቦች ጠፍተው “ሆ” ብለው የሚያወግዙና የሚቆጡ፤ የሚንጫጩና መንፈስን የሚያውኩ፤ በአላዋቂነት ድፍረት ከመደብደብ የማይመለሱ ሥጋዊ(ፍጥረታዊ) ሰዎች የበዙበት ነው፡፡ እነዚህን ልቦችና አንደበቶች ጸጥ አሰኝቶ፤ ገትቶ ወደእውነት ለመድረስ የሚከፈለው ዋጋ እንዲህ በቀላል የሚመዘን አይደለም፡፡ ይህንን በመያዝ ስለውግዘት ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎችን በሦስት ከፍለን ብናይ፦

1.     ከውግዘት በፊት
2.    በውግዘት ጊዜ
3.    ከውግዘት በኋላ፡፡

1.    ከውግዘት በፊት ልናደርግ የሚገባው ጥንቃቄ


      መጽሐፍ “ጥንቃቄ ይጠብቃል፤ ማስተዋል ይጋርዳል” (ምሳ.2፥11) እንዲል ከምንም ነገር በፊት ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ከፍ ያለ ዋጋ አለው፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታና በግድየለሽነት መሥራት ፍጹም ያስረግማልና፡፡(ኤር.48፥10) ስለዚህ ቤትን በጥበብ ልንሠራ፣ በማተዋልም ልናጸና ይገባናል፡፡ (ምሳ.24፥3) ጥንቃቄዎች ግን ከመንፈስ ቅዱስ ሀሳብና ከቃሉ በራቀ መልኩ መሆን የለባቸውም፡፡ የምንጠነቀቀውም “ሰዎችን ላለማጣት” ሳይሆን ለእግዚአብሔር እውነት በመወገን ፍጹማን ምስክሮች ለመሆን ነው፡፡
     ሰዎች ያለምስክር ንጹህ ሆነው ሳለ በሐሰት እንዳይነቀፉና እንዳይወገዙ አብዝቶ መጠንቀቅ ያሻል፡፡ “ለፍርድ የተዘጋጀ ኤጲስ ቆጶስ በአንዱ ላይ ስንኳ በሐሰት ቢፈርድ በፈረደው ፍርድ በራሱ ላይ ይፈረድበታል” እንዲል፡፡(ፍትሐ ነገስት አን.5 ቁ.183 ገጽ.65) በተለይ ብዙ ሰዎች ስለኃይማኖት በመቅናትና መቆርቆር ስሜት በመነሳሳት ብቻ ፍጹም ወደሆነ ሥጋዊ ስሜት በመግባት የሌሎችን ስም ሲያጠፉ፣ደብድበው ጉዳት ሲያደርሱ፣አምጸው ሰው ሲያሳድዱ ፈጣሪን የማገልገል ያህል ቢረኩም በፍቅርና በእውነት በሚከብረው አምላክ ፊት ግን ይህ ድርጊታቸው ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ስለዚህ ለማውገዝ ሥጋዊ ኃይልን መጠቀም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ፍጹም ተቃራኒ መሆናችንን ልንዘነጋ አይገባንም፡፡

Monday, November 23, 2015

አክራሪውና ጽንፈኛው ማኅበረ ቅዱሳን በጎንደር የአብነት ትምህርት ተማሪዎች ከበጎ አድራጊዎች እርዳታ እንዳያገኙ አደረገበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከእኔ በቀር ማንም መኖር የለበትም የሚል አካሄድን በመከተሉና ሌሎች የአክራሪነት መገለጫዎችን በተደጋጋሚ ማሳየቱን መሠረት በማድረግ በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አክራሪና ጽንፈኛ ተብሎ የተፈረጀው ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነቱ ከአዲስ አበባ የሄዱ ኦርቶዶክሳውያን በጎ አድራጊዎች የነገ የቤተክርስቲያን ተረካቢ ለሆኑት የአብነት ተማሪዎች እርዳታ እንዳይሰጡ ሃይማኖትን ሽፋን አድርጎ ለአመፅ ባደራጃቸው ወሮበሎች በኩል መከልከሉ ተሰምቷል፡፡ ማቅ በአመፅ መንገድ ይህን የበጎ አድራጎት ሥራ የከለከለውና የአብነት ተማሪዎች ድጋፍ እንዳያገኙ ያደረገው በሕገወጥ መንገድ ሲሆን ሊቀጳጳሱና ሥራ አስኪያጁ የፈቀዱትን በጎን አመፅ በመቀስቀስ ማስተጓጎል እንደቻለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጎ አድራጊዎቹ በጎንደር ግምጃ ቤት ማርያም ላሉ 50 ተማሪዎች በነፍስ ወከፍ 1 ኩንታል ጤፍና አንድ ኩንታል ስንዴ እንዲሁም የቁሳቁስ ድጋፍ ሊያደርጉ ተዘጋጅተው የነበረ ቢሆንም በግብሩ እኩይ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን “የተሐድሶ እርዳታ ነው” በሚል እርዳታው እንዳይሠጥ ተማሪዎቹም እንዳይቀበሉ አስከልክሏል፡፡
በጎ አድራጊዎቹ ቀደም ብለው የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ በብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ እና ሥራ አስኪያጁ ሐሳቡን ሲሰሙ እጅግ ደስ ተሰኝተው በጎ ዓላማ ነውና ልትረዱ ትችላላችሁ በማለት ግዢው ሊፈጸም በዝግጅት ላይ እንዳሉ ከየት መጡ የማይባሉ የከተማው የማህበረ ቅዱሳን አባላት ተቃውሞ በማድረግ በተማሪዎቹ ላይ ጨክነውባቸዋል፡፡ ተማሪዎቹና አስተባባሪዎቹ ይሰጠን ቢሉም እርዳታውን ብትቀበሉ ከዚህ የአብነት ት/ቤት ትባረራላችሁ ብለው አስፈራርተው እንዳይቀበሉ አድርገዋል፡፡ በጎ አድራጊዎቹም ላይ ጥቃት ለማድረስ ያረፉበትን ሆቴል ከበውና እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግና ወደአዲስ አበባ ለመመለስ ሲሉም ጥቃት ለማድረስ ጥረት አድርገው የነበረ ቢሆንም በጸጥታ ኃይሎች በኩል ጥበቃ ስለተደረገላቸው ምንም ማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ 

Friday, November 20, 2015

የኅዳር ሚካኤል በዓል የማን በዓል ነበር?


 Read in PDF
የኅዳር ሚካኤል በዓል የሚከበረው ምንን በማስመልከት ነው? ብለው ቢጠይቁ ወይም በዕለቱ ወደ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሄደው በዓሉን የተመለከተ ትምህርት ሲሰጥ ቢሰሙ ሚካኤል ህዝበ እስራኤልን ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣበት ቀን ተብሎ ሲነገር ይሰሙ ይሆናል፡፡ ድርሳነ ሚካኤልን ቢያነቡም ተመሳሳይ ነገር ነው የሚገጥምዎት፡፡ ነገር ግን እውነቱ ያ ነወይ? እስራኤልን የመራው ማነው? የኅዳር ሚካኤል በዓልስ በምን ምክንያት ነው መከበር የጀመረው? ስለዚህ ጉዳይ በዕለቱ ከሚተረከው ውጪ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ምን ይላሉ? ጉዳዩ በመጽሐፍ ቅዱስ ሲፈተሽስ እውነቱ የቱ ነው? እስኪ ለሁሉም ቀጥሎ የቀረበውን ጽሑፍ ይመልከቱ፡፡   
“ቦኑ ኢትክል አድኅኖ እዴየ ወቦኑ ዘኢይሰምዕ በእዝንየ አክብሩ በዓልየ ወሑሩ በሕግየ ትበልዑ ከራሜ ከራሜ ከራሜ እም በረከትየ ወእም ፍሬ ተግባርየ ይቤ ሚካኤል” (የመስከረም ሚካኤል ዚቅ)።
ትርጓሜ “ሚካኤል አለ፤ በውኑ እጄ ማዳን አትችልምን? በጆሮዬስ የማልሰማ ነኝን? በዓሌን አክብሩ፤ ሕጌንም ጠብቁ፤ ከሥራዬ ፍሬ፣ ከበረከቴም የከረመ የከረመውን ትበላላችሁ።”
“ቦኑ ኢትክል አድኅኖ እዴየ ወቦኑ ዘኢይሰምዕ በእዝንየ አክብሩ ሰንበትየ ወሑር በሕግየ ትበልዑ ከራሜ ከራሜ ከራሜ እም በረከትየ ወእም ፍሬ ተግባርየ ይቤ ቅዱሰ እስራኤል” (መጽሐፈ ድጓ 1959፣ ገጽ 58)።
ትርጓሜ፣ “የእስራኤል ቅዱስ (እግዚአብሔር) አለ፤ በውኑ እጄ ማዳን አትችልምን? በጆሮዬስ የማልሰማ ነኝን? ሰንበቴን አክብሩ፤ ሕጌንም ጠብቁ፤ ከሥራዬ ፍሬ፣ ከበረከቴም የከረመ የከረመውን ትበላላችሁ።”

Thursday, November 19, 2015

እውነተኛ ደስታ ያለው በፍቅር ለሌሎች በመኖር ውስጥ ነው!!በዲ/ን ኒቆዲሞስ  nikodimos.wise7@gmail.com
ለዚህ ለዛሬው ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ በቀድሞው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት በነበሩት በመ/አ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት በሰላምና በአረንዴ ልማት ጉዳይ ላይ በተጠራ ስብሰባ ላይ ያገኘሁት ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው እጅግ ባለ ጠጋና የተሳካለት የሚባል፣ በበርካታ የንግድ ሥራዎች ላይ የተሰማራ፣ በጎልማሳ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ የአምስት ልጆች አባትና የቤተሰብ ሓላፊ ነው፡፡ ታዲያ ስብሰባው እስኪጀመር ከዚህ ሰው ጋራ በሕይወት ዙርያ ላይ አንዳንድ ቁም ነገሮችን አንሥተን ጨዋታ ጀመርን፡፡
በጨዋታችን መካከልም ይህ ሰው በሥራ አጋጣሚ አብሮት ይሠራ የነበረው ወዳጁ መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እንደካደውና በጊዜው እጅግ መራርና ሊቀበለው ያዳገተው ይህ መጥፎ አጋጣሚም ለሕይወት የነበረውን ምልከታ እንዴት ሊያስቀይረው እንደቻለም እንዲህ ሲል አወጋኝ፡፡

Monday, November 16, 2015

ተሃድሶ የእምነት መግለጫዉን ይፋ አደረገ

ወደ እግዚአብሔር ቃልና ወደ ፈቃዱ ልንመለስና ሕይወታችንንና አገልግሎታችንን እንደ ቃሉ ልንቃኝና ልናርም ይገባል የሚል የለውጥ ጥያቄ በማንሣታቸውና ወንጌልን በማስተማራቸው ምክንያት የማያምኑትን እንደሚያምኑና ማንነታቸው ያልሆነውን መገለጫቸው እንደሆነ ተደርጎ ስማቸውን በማጥፋትና በመክሰስ ከእናት ቤተክርስቲያናቸው በግፍ የተገፉትና አሁንም በየሥፍራው በመከራ የሚገኙትን የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑትን የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ማንነታቸውንና እምነታቸውን የሚገልጥ የእምነት መግለጫ ታትሞ በይፋ ተመረቀ፡፡ ጥቅምት 14/2008 ዓ.ም ከቀትር በኋላ እጅግ በደመቀ ሁኔታ በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዐት ላይ ካህናት፣ ሰባክያን፣ ዘማርያንና ምእመናን የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም በጉባኤው ታድመዋል፡፡

የምረቃ ስነ ሥርዐቱ በካህናት አባቶች ጸሎት የተከፈተ ሲሆን በጉባኤው ላይ የቀረቡት ዋና ዋናዎቹ መርሐ ግብሮች መነባንብ፣ የእምነት መግለጫን ታሪካዊ አመጣጥና ይዘትን የሚያሳይ ትምህርት፣ ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ የእምነት መግለጫ በሚል ርእስ ስለተዘጋጀው የእምነት መግለጫ ይዘት ዳሰሳና እኛ የምናምነው እንዲህ ነው በማለት ይህን የእምነት መግለጫ ስላዘጋጁቱ የስነ መለኮት ምሁራንና ከልዩ ልዩ ሥፍራ የተውጣጡ ወገኖች ማንነታቸውን የሚገልጥ ሰነድና እምነታቸውን በጽሑፍ አዘጋጅተው ለማሳተም ያነሣሣቸውን ዓላማ የሚገልጥ ጽሑፍ ይገኙበታል፡፡
ባለ 42 ገጹ “ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ የእምነት መግለጫ” ስድስት ዐበይት ክፍላት እና 32 ንኡሳት አርእስት አሉት፡፡

Saturday, November 14, 2015

ምህረተአብ በአሜሪካ እንዳያስተምር ታገደ

Read in PDF

መንደርተኛው እና ተረት ተራቹ አልቦ እውቀት ወምግባር የሆነው ምህረተአብ አሰፋ “አገለግላሁ”  ብሎ በመጣባት አሜሪካ ምንም አይነት “አገልግሎት” እንዳይሰጥ በብጹዕ አቡነ ዘካሪያስ በተጻፈ ደብዳቤ ታገደ፡፡ በብጹእነታቸው የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው ግለሰቡ ወደ አሜሪካ ሲመጣ ያለ ቤተክህነትና ሀገረ ስብከት ፈቃድ ነው፡፡ 


ስለዚህ እንደእርሱ ያለ “ሌሎችን ሃይማኖትና ሥርዓት አፈለሱ ብሎ የሚወቅስ ይህንንም ለመግታት እታገላለሁ የሚል አንድ ሰባኬ ወንጌል ፍጹም እውነተኛነቱ የሚመዘነው እርሱ ራሱ በአግባቡ መሄድ ሲችል ነው፡፡” የሚለው የእግድ ደብዳቤው እራሱ ራሱ ግን ህግና ሥርዓት አፍርሶ አስተምራለሁ ማለቱን “ሥርዓትን የጣሰ እና እንዲሁም ሊታለፍ የማይችል ከባድ ጥፋት ሆኖ አገኝተነዋል፡፡” ይላል፡፡ 

በደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ባልተፈታው ችግር ምክንያት ካህናቱ ደመወዝ የሚከፍላቸው አጡ

Read in PDF

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ስንዘግብ እንደነበረው በደብሩ ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስናና ብልሹ አሰራር በአንድ ወገን ለመሸፋፈን በሌላው ወገን ደግሞ ይህን ለማጋለጥና ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት በተፈጠረው ችግር ሳቢያ ተጠቂዎቹ የደብሩ ካህናት ሆነዋል፡፡ የደብሩ ካህናት ሙዳየ ምጽዋት ባለመቆጠሩ ምክንያት ደሞዝ አልተከፈላቸውም፤ ሙዳየ ምጽዋቱ እንዳይቆጠር አለቃውን አናስገባም በሚሉ ሙሰኞችና እነርሱ ባሳደሟቸው ክፍሎች በተደረገው አመፅ ምክንያት መሆኑን ማወቅ ተችሏል፡፡ ደመወዝ ባለመከፈሉ ምክንያት የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያና የቤት ኪራይ መክፈል ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ችግር በመጋለጣቸው በትናትናው ዕለት ተሰብስበው መጥተው በሀገረ ስብከቱ መፍትሄ እንዲሰጣቸው አቤት ብለዋል፡፡ ችግሩን ለኩሰው ያሉትና በዝርፊያ የበለፀጉት የተደላደለ ኑሮ ሲኑ ካህኑ በረሃብ ላይ ነው፡፡
ቀደም ሲል በካቻማሊ ተጭነው ወደ ሀገረ ስብከቱ እና ጠቅላይ ቤተክህነት በመሄድ አለቃው ይነሱልን ቢሉም አጣሪ ልከን ችግሩን አውቀን ነው አለቃውን የምናነሳው ተብለዋል፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በዚህ ጥያቄ ላይ ወሳኝ ነገር ያስተላለፈ ሲሆን ይኸውም በህገወጦች አድማ አለቃ አይነሣም በማለት ለደብሩ አለቃ ገብተው እንዲሠሩ መመሪያ ተሰጥቶአል፡፡ አለቃውም ገብተው መሥራት ጀምረዋል፡፡ ይህ ጥሩ እርምጃ ነው፡፡ አለቃው መነሣት ያለባቸው በህገወጥ ድርጊት ሳይሆን በቦታው ላይ በመደባቸው በሀገረ ስብከቱ አሰራር ብቻ መሆኑ መረጋገጡ በህገወጥ መንገድ መጓዝ ለሚፈልጉ ህገወጦች ትልቅ ማስተማሪያ ነው፡፡

Thursday, November 12, 2015

የማኅበረ ቅዱሳን /ማቅ/ የዘረኝነትና የፖለቲካ ሥራ አፍ አውጥቶ ሲናገርባለፉት ዓመታት በነመልአከ መንክራት ኃይሌ ላይ በብስራተ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በሰሩት የልማት ሥራ፣ የአካባቢው ሕዝብ ይሁን የሰበካ ጉባኤ መኪና ሸልሟቸዋል (ሰጥቷቸዋል)፡፡ ምንም እንኳን ሽልማቱ ለሠሩት ሥራ ተመጣጣኝ ነው? ወይስ ከመጠን በላይ ነው? ወይስ ያንሳል? የሚለው ግን በቂ ጥናት የሚፈልግ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡
አንድ ነገር ማለት ግን ይቻላል መልአከ መንክራት ለቤተክርስቲያን ያደረጉት (የሰሩት) ሥራ በዓይን የሚታይ በእጅ የሚዳሰስ መሆኑን መመስከር ይቻላል፡፡ በተለይ በብስራተ ገብርኤል የተሰራው ሥራ ቦታው ለልማት ምቹና አውላላ ሜዳ ላይ ያለ በመሆኑ ለብዙ ዘመናት ያለ ልማትና ያለጥቅም የከብቶች መዋያ ሆኖ ይኖር ነበር፡፡ መንግሥት ለልማት ሊወስደው ሲል መልአከ መንክራት ኃይሌ ወጥተው ወርደው ከመንግሥት ጋር በመግባባትና የቤተ ክርስቲያንዋን ልዕልና በማስጠበቅ አጥርዋ እንዳይደፈር በማድረግ ቤተ ክርስቲያንን አስከብረዋል፡፡ ሲቀጥልም በተመለሰው ቦታ ላይ በብዙ ሚሊዮን የሚገኝ ልማት ተሰርቷል፡፡ 

Monday, November 9, 2015

የውጩ ሲኖዶስ በወንጌል ጉዳይ ላይ የተሻለ አቋም እየያዘ ነው፤ አዳዲስ ጳጳሳትንም ሊሾም ነው።

Read in PDF

በብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የሚመራው ስደተኛው ሲኖዶስ 42ኛ ሲኖዶሳዊ ጉባኤውን በኮሎምበስ ኦሐዮ ከጥቅምት 24 እስከ 26 2008 ዓ.ም ድረስ አካሂዷል። ሊሞቱ ነው እየተባለ ሁልጊዜ የሚወራባቸው ብፁእ አቡነ መልከ ጼዴቅ ገና እንደ ወጣት ሰው በማሰብ በመከራከር በማመን እና በማሳመን ሲኖዶሱን መርተዋል ቅዱስ ፓትርያርኩም በተሻለ ጤንነት ሆነው ጉባኤውን ተካፍለዋል። ጉባኤው በሰላም እና በአንድነት መንፈስ የተጠናቀቀ ሲሆን ጥሩ የሚባሉ አቋሞችን ይዞ ታይቷል።
 የአሜሪካ አብያተ ክርስቲያናት በሦስት የተከፈሉ መሆናቸው ይታወቃል። እነርሱም በአገር ቤቱ ሲኖዶስ የሚመሩ፣ በውጩ ሲኖዶስ የሚመሩና ገለልተኛ ማለት ከሁሉም ሲኖዶስ የወጡ ናቸው። ይሁን እንጂ የየራሳቸው ሕግ ያላቸው በመሆናቸው ለየትኛውም ሲኖዶስ መመሪያ አይገዙም። ሲኖዶሱ አንድ ወጥ የሆነ ሕግ ለሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ለማቅረብ ካሰበ ረጅም ጊዜ ቢፈጅም በቅርቡ ተፈጻሚ እንዲሆን ተስማምቷል።

 የኦርቶዶክስ አባል ቁጥር እየቀነሰ የሄደበትን ምክንያት አጀንዳ አድርጎ በተወያየበት ጊዜ የሚከተሉትን ምክንያቶች ጠቁሟል። አንደኛ መንግሥት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እያደረገ ያለው ተጽእኖ ነው ብሏል። ሁለተኛ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተስፋፋው ሙስና ዘረኝነትና በልሹ አስተዳደር የሚለውን ምክንያት አምኖብታል። ሦስተኛ ወደ አረብ አገር የሚሄዱ ሰዎች በድኅነት ምክንያት እምነታቸውን ስለሚቀይሩ ነው ብሏል። አራተኛውና የመጨረሻው ምክንያት ግን የቤተ ክርስቲያንን አይናማ ሊቃውንት መናፍቃን እያልን በማሳደዳችን፤እና  ለሕዝቡ ትክክለኛውን ትምህርት ባለማስተማራችን ነው በሚሉት ምክንያቶች አምኖበታል። 

Sunday, November 8, 2015

ወገን እማማ ኢትዮጵያ ተርባለች … የድረሱልኝ ጥሪዋንም እያሰማች ነው?! የ፲፱፻፷፮ቱ እና የ፸፯ቱ ዓይነት የረሃብ እልቂት ከመድረሱ በፊት ለወገኖቻችን እንድረስላቸው! ከፍል- ፪በዲ/ን ኒቆዲሞስ      (ምንጭ- ከሰንደቅ ጋዜጣ መጠነኛ ማስተካከያ ተደርጎበት የተወሰደ፡፡)
በአገራችን በኢትዮጵያ የተከሰተውን የረሃብ አደጋ አስመልክቶ ከሰሞኑን በመጀመሪያ ክፍል ያስነበብኩትን ጽሑፍ ባወጣሁ ማግሥት በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነች አንዲት ወዳጄ የRFI.fr ድረ-ገጽ ‹‹Sever Drought Threatens Millions of Ethiopia›› በሚል ርዕስ በአገራችን ስለተከሰተው ረሃብ በሰፊው የሚያትት ጽሑፍ ላከችልኝ፡፡ ይህ የrfi.fr ድረ ገጽ ያስነበበው ጽሑፍ እንደሚያትተው የኤሊኒኖ ክስተት በምሥራቅ አፍሪካና በኤዥያ በሚገኙ አገራት ባስከተለው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት አገራችን በድርቁ በከፍተኛ ኹኔታ ተጠቂ መሆኗን ዘግቦአል፡፡
ይህ ዘገባም ጨምሮ አገራችን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ1984-85 በርካታዎች ከቀዬአቸው በተፈናቀሉበትና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ካለቁበት የረሃብ ክስተት ጀምሮ አገሪቱ በምግብ እህል ራስን የመቻል ጥያቄ ውስጥ የወደቀች አገር መሆኗን በመግለጽ፤ የዘንድሮ በዝናም እጥረት ምክንያት የተከሰተው የድርቅም ከምሥራቅ አፋር ክልል እስከ ደቡብ ሶማሊያ ያለውን ሰፊ ቦታ እንደሚሸፍንና ረሃቡ በእነዚህ ቦታዎች ላይም ከፍተኛ የሆነ ማኅበራዊና ሰብአዊ ቀውስ እያደረሰ እንዳለ ይገልጻል፡፡

Saturday, November 7, 2015

የሰማዕቱ የአባ እስጢፋኖስ ስም ሲነሣ የዘርዓ ያዕቆብ መንፈስ ይጮሃል፤ ይታወካል Read in PDF
ሰሞኑን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ወደ ትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ መቼም ቅዱስ ፓትርያርኩ የአትዮጵያ ፓትርያርክ እስከ ሆኑ ድረስ ከአሜሪካ አስከ አውሮፓ፣ ከአረብ እስከ ሱዳን በአገር ውስጥ ከአፋር እስከ ጋምቤላ እየሄዱ ነው፡፡ ወደእነዚሁ አገራት ሲሄዱ ማለትም ከሙስሊም እስከ ፕሮቴስታንት አገራት ሲሄዱ ማቅ የተባለው ጨለምተኛ ቡድን ምንም ብሎ አያውቅም፡፡ ከሰሞኑ ግን መንፈሱን የሚረብሸው አእምሮውንም የሚያውክ ነገር እየተሰማው ነው፡፡ ይኸውም የረበሸው የፓትርያርኩ የአዲግራት ጉዞ ነው፡፡
አዲግራት ትግራይ ውስጥ የሚገኝ የሰማዕቱ የአባ እስጢፋኖስ አገር ነው፡፡ አባ እስጢፋኖስ ደግሞ ለአብና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር ለማንም አልሰግድም በሥላሴ ላይ አራተኛ አልጨምርም ብሎ ከአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጋር በመጣላቱ ከነተከታዮቹ ከ15 ሺህ በላይ መነኮሳት ካህናትና ምእመናን ሰማዕት ሆነዋል፡፡ የዘርዓ ያዕቆብ የመንፈስ ልጅ የሆነው ማቅ ቅዱስ ፓትርያርኩ እስከ አሁን በዓለም ላይ ካደረጉት ጉዞ መታገስ ያልቻለውና መንፈሱን በጣም የረበሸው የአዲግራቱ ጉዞአቸው ነው፡፡ አዲግራት ከዓለም የተለየች አገር ይመስል በፓትርያርኩና በሊቃነ ጳጳሳቱ ጉዞ ላይ አብዝቶ ሲጮኸ እና ሲያወግዝ ሰንብቷል፡፡ እርግጥ ማቅ የፓትርያርኩና የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ የአዲግራት ጉዞ ካላስጮኸውና ካላንፈራፈረው ነበር የሚገርመውና የሚደንቀው፡፡ የግብር አባቱ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ያፈሰሰው የቅዱሳኑ የደቂቀ እስጢፋኖስ ደም በእግዚአብሔር ፊት እየጮኸ ያውከዋል፡፡ ለዚህም ነው የሰሞኑ የአዲግራት የፓትርያርኩ ጉብኝት ለማቅ የሆድ ቁርጠት የሆነበት፡፡ 

Friday, November 6, 2015

ወገን እማማ ኢትዮጵያ ተርባለች … የድረሱልኝ ጥሪዋንም እያሰማች ነው?! የ፲፱፻፷፮ቱ እና የ፸፯ቱ ዓይነት የረሃብ እልቂት ከመድረሱ በፊት ለወገኖቻችን እንድረስላቸው! ከፍል- ፩በዲ/ን ኒቆዲሞስ      (ምንጭ- ከሰንደቅ ጋዜጣ መጠነኛ ማስተካከያ ተደርጎበት የተወሰደ፡፡)
እኛ ኢትዮጵያውያን ለረሃብ ክሥተት በፍጹም እንግዶች አይደለንም፡፡ ጠኔ-ችጋር ደግሞ ደጋግሞ የጎበኘን፣ ረሃብ ስማችንን ያጎደፈብን፣ በሃፍረት አንገታችንን ያስደፋን፣ ቅስማችንን የሰበረን፣ ታሪካችንን ያጠለሸብን፣ የእልቂት፣ የፍጅት፣ የደም ምድር- ‹‹አኬል ዳማ›› በሚል የሚያሰቅቅ ስያሜ የተጠራን፣ መላው ዓለም በኀዘን ከንፈሩን የመጠጠልንና እንባ የተራጨልን ምስኪን ሕዝቦች ነን፡፡
እስቲ ለዛሬው በዝናም እጥረት ምክንያት በአገራችን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ሚሊዮኖች ወገኖቻችን ለረሃብ ስለተጋለጡበትና ቤተኛው ስላደረገን የድርቅ/የረሃብ ጉዳይ ላይ አብረን በአንድነት ሆነን ትንሽ እንቆዝም ዘንድ በተከታታይ ላስነብባችሁ ወዳሰብኩት ጽሑፍ የሚያንደረድረኝንና ዛሬም ድረስ ሳስታውስው እጅጉን በሚያሳቅቀኝ አንድ ገጠመኜ ልጀምር፡፡
በደቡብ አፍሪካ የአርትና የባህል ሚ/ር፣ ማንዴላና የትግል ጓዶቻቸው ለ፳፯ ዓመታት በተጋዙበትና በዩኔስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት በተመዘገበው በሮቢን ደሴት የነጻነት ሙዚየምና እና በኔልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን ትብብርና የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጠውን ‹‹የአፍሪካ ቅርስና ቱሪዝም ጥናት የድኅረ ምረቃ/የፖስት ግራጁየት የትምህርት ፕሮግራም›› ነጻ የስኮላር ሺፕ ዕድል አግኝቼ ከፍተኛ ትምህርቴን በተከታተልኩባት በኬፕታውን ከተማ በሮቢን ደሴት ሙዚየም የሆነ ገጠመኜ ነው፡፡

Wednesday, November 4, 2015

የጥቅምቱ ሲኖዶስ ውሳኔዎች እና አንዳንድ ክስተቶች ምን ይመስላሉ?ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የሲኖዶስ ስብሰባ ልዩ ትኩረት የሚስብ ስብሰባ እየሆነ መጥቷል፡፡ ለሳቢነቱ በማቅና በወንጌል እንቅስቃሴ መካከል ያለው ፍትጊያ ተጠቃሽ ነው፡፡ የዘንድሮው የጥቅምት ሲኖዶስም በጉጉት ሲጠበቅ ነበር፡፡ ብዙዎች በጉጉት ይጠብቁት የነበረው ግን ያለ ምክንያት አልነበረም፡፡ ማቅ በየቦታው ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይበልጣል በሚለው አቋሙ ብዙ ሰዎች ሊወገዙ ነው ብሎ ከ6 ወር ላላነሠ ጊዜ ሲያወራና ሲያስወራ ፀረ ወንጌል እንቅስቃሴውን የሚያሳልጡለትን ቡድኖች ሲያደራጅ ከርሞአል፡፡ በየፌስ ቡኩ እና በተለይም ሐራ በተባለው ብሎጉ የተቻለውን የማደናገሪያ ጽሑፍ ሲለጥፍ ነበር የከረመው፡፡ ፀረ ወንጌል አቋም ያላቸው በዘንድሮ ጥቅምት ይለያል እስከ ማለት የደረሰበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡
በሠበካ መንፈሳዊ አጠቃላይ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ አጠንክረው “ሕዝቡ ወደሌላ እምነት እየፈለሰ ነው፤ ባዶአችንን ከመቅረታችን በፊት ለተደራጀ ድንበር የለሽ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንነሳ” ብለው ቤተ ክርስቲያኗ አሁን ያለችበትን ተጨባጭ እውነት በገሃድ አሳዩ፡፡ ይህም ማቅና ያደራጃቸው ቡድኖች ብዙ ሲለፉለት የነበረው የጥቅምቱ ሲኖዶስ የመክፈቻ ፀሎት ላይም ከዚህ በፊት በመናጆነት ወጥተው ተሃድሶን እናወግዛለን የሚሉ ወጣቶች ወደ ቦታው ዝር ሳይሉ ቀርተዋል፡፡ እነዚህን ወጣቶች ሲያስተባብር የነበረው የግቢ ገብርኤል ሰንበት ተማሪ ሄኖክ አሥራት በሲቪል ሰርቪሱ ውይይት ላይ የቡድኑን ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት አሁን ብዙ ተምሬአለሁ ስላለ ወጣቶችን በማያውቁት መንገድ ለጥፋት ማሰለፉን የተወ መስሏል፡፡

Tuesday, November 3, 2015

በስካር አውደ ምሕረት ላይ በወጣ የክፍለ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት የሰው ኀይል አስተዳደር ጉባኤ ታጠፈ

Read in PDF

ባለፈው አርብ በደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ይሰጥ የነበረውን መደበኛ ትምህርት ለማስተጓጎል በዓላማ መጥቶ በስካር መንፈስ ወደ አውደ ምሕረቱ የወጣው ቄስ ሙሴ ዘነበ የተባለው የነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት የሰው ኀይል አስተዳደር ጊዜውን በሞቅታ በሚነዳው አንደበቱና ምንም ፍሬ ነገር በሌለው እዚህና እዚያ በሚረግጠው “ስብከቱ” ብዙ ምእመናንን ማሳዘኑንና ብዙዎች ትምህርቱን አቋርጠው መሄዳቸወን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ ቃለ እግዚአብሔርን ተርበውና ተጠምተው የመጡት ምእመናን የፈለጉትን ሳያገኙ የግለሰቡን እንቶ ፈንቶ ወሬ በግድ ሰምተው ለመሄድ የተገደዱ ሲሆን፣ ይህንንስ አንሰማም ያሉ በርካታ ምእመናንም የሰውዬውን ሁኔታ በማየት ጉባኤውን አቋርጠው ሄደዋል፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ሥራ አስኪያጁ መድረኩ ላይ የወጣው በደብሩ ውስጥ ያለውን ጤናማ የወንጌል አገልግሎት ለማፍረስ ተልእኮ ተሰጥቶት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቄስ ሙሴ ዘነበ  የተወለደው ሳሪስ አቦ አካባቢ ሲሆን ይህ ነው የሚባል የቤተክርስቲያን ዕውቀት ሳይኖረው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ ቤተክህነት የሰው ኀይል አስተዳደር ሆኗል፡፡ ከሳሪስ አቦ ከደጀሰላም ጀምሮ በሰካራምነቱ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ባህርዩ እስካሁን አብሮት እንደቀጠለ ነው፡፡ እሱ በሚመራው ወረዳ ቤተክህነት ውስጥ ብዙዎች ወንዶችንና ሴቶችን በጉቦ ቀጥሯል፡፡ ከተራ ዲያቆን ጀምሮ “ልትቀየሩ ነው ልትታገዱ ነው” እያለ በማስፈራራት ጉቦ የሚቀበል ሙሰኛ ነው፡፡ በተለይም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በሊቀማእምራን የማነ ስም በርካታ ወንጀሎችን እየፈጸመ ነው፡፡ ስለዚህ ሥራ አስኪያጁ እንደ ሙሴ ባሉ ሙሰኞች አስተዳደራቸው ላይ ጥላ እንዳያጠላ የብዙዎች ሥጋት ነው፡፡ 

Sunday, November 1, 2015

ዘከመ ርኢነ ሰማዕተ ንከውን

Read in PDF


መጽሐፍ ያየነውን እንመሰክራለን ይላል፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ ያየነውን መመስከር የሰማነውን መናገር ሃይማኖታዊ ግዴታችን ነው፡፡ ስለሆነም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ያየነውንና የተመለከትነውን በታሪክ የምናውቀውን ለመመስከር ተነሥተናል፡፡ እንደሚታወቀው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን ያልተለመደ ክስተት አስተናግዷል፤ ያልተለመደ የጸባይና የባሕርይ ለውጥም አምጥቷል፡፡ ቅን ህሊና ላለውና ታሪክን ለማይረሳ ሰው የትናትናዎቹ ጥቅምትና ግንቦት ወሮች በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ሥር ላሉ ሠራተኞች ለሆኑ ካህናት ትልቅ ሕመምና ሰቀቀን ነበሩ፡፡ እነዚህ ሁለት ወሮች ጥቅምትና ግንቦት የሲኖዶስ ስብሰባ የሚካሄድባቸው ወሮች በመሆናቸው ሥራ አስኪያጁ ይቀየራል ጳጳሳቱ አይሰሙም አይከታተሉም ተብሎ የአንዱን እንጀራ ቀምቶ ለሌላው በመስጠት ሊቃውንቱን በማፈናቀልና ከሥራ ውጪ በማድረግ፣ የክህነቱና የሥራ ደረጃው ለጨረታ የሚቀርብበት ወቅት ነበር፡፡ ብዙ የአብያተ ክርስቲያናቱ ሠራተኞች በዚህ ወቅት ወይም በጥቅምትና በግንቦት ወሮች የቅርብ ዘመድ እንኳን ቢሞትባቸው የዓመት ፈቃድ (ዕረፍት) ወስደው ክፍለ ሀገር ለመሄድ ፈቃድ የማይጠይቁበት ወቅት ነበር፡፡
በተለይ በመጋቤ ሐዲስ ይልማና በቀሲስ በላይ የተፈጸመውን ግፍና በደል ታሪክ ሊረሳው ከአእምሮም ሊጠፋ የማይችል ነው፡፡ ምክንያቱም ትልቅ ኃላፊነትና ሥልጣን ተሰጥቷቸው እያለ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በገንዘብ በመቀየር የሰንቶችን ርስትና ሥራ በመቀማት ገንዘብ ላለው በመሸጥ የብዙዎችን ጉሮሮ ዘግተዋል፡፡ የሾሟቸው ጳጳሳት ለሰባት ቀን ስብሰባ ገብተው እስኪመለሱ ድረስ ለአንድ ሳምንት እንኳን መጠበቅ አቅቷቸው ቤቱን ወና በማድረግ እጅግ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ቤተክርስቲያኗን ጎድተዋታል፡፡ በተለይ መጋቤ ሐዲስ ይልማ የፈጸሙት ግፍና በደል በጣም ስላሳፈራቸው ከእንግዲህ ወዲህ በየትኛው ዓይኔ ነው ካህናቱን የማያቸው? በማለት የፖለቲካ ጥገኝነት በሚመስል መልኩ ከአገር ተሰደው የቤተክርስቲያንን ሀብት በመዝረፍ ኮብልለዋል፡፡ እርሳቸው የሸጧቸው ሠራተኞች ግን እስካሁን ድረስ ወደ ቀድሞ ስራቸው ለመመለስ አስቸጋሪ ሆኖባቸው ለማስተካከል አስቸግሯል፡፡

Friday, October 30, 2015

አባ ሳሙኤል በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ በርካታ ችግሮችን እየፈጠሩ ነውበጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ዋዜማ ላይ በድርሰት ስርቆት እስከተጋለጡበት “ግብረ መንፈስ ቅዱስ” መጽሐፍ ድረስ በሰው መጽሐፍ ራሳቸውን ጸሀፊ ለማሰኘትና የሌላቸውን ማንነት ለመገንባት ያልተሳካ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የቆዩት አባ ሳሙኤል በግብረ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ግን የፈጸሙት አሳፋሪ ድርጊት መጋለጡን ተከትሎ ሌሎች መሰሪና አሳፋሪ ሥራዎቻቸው መጋለጥ ቀጥለዋል፡፡ ከግብረ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ጋር ጋር በተያያዘ ለማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ከማኅበሩ ግልጽ አመራሮች መካከል አንዱ ቀርቦ የተጠየቀ ሲሆን ስለ መጽሐፉ በአባ ሰላማ ድረገጽ የቀረበው ትክክል መሆኑን አምኗል፡፡ መጽሐፉን እነርሱም ሽጡ ተብለው እንደተረከቡና መጽሐፉ ችግሮች ስላሉበት ሳንሸጥ መጋዘን በማስገባት ክፍያውን ግን ፈጽመንላቸዋል ብሏል፡፡
ይህም የሚያሳየው ማቅ ለሃይማኖት ሳይሆን ለግል ጥቅሙ የቆመ ድርጅት መሆኑን ነው፡፡ ምክንያቱም ለሃይማኖቱ ተቆርቋሪ ቢሆን ኖሮ አባ ሰላማ እስኪያጋልጥ ድረስ የአባ ሳሙኤልን ሃይማኖታዊ ሕጸጽና ቅስጣ ድርሰት በቸልታ ማየት እንዳልነበረበትና ጉዳዩን ለሚመለከተው የቤተክርስቲያን አካል አቤት ማለት እንደነበረበት ማንም የሚናገረው እውነት ነው፡፡ ማቅ ግን ለፖለቲካው ሲል እንዲህ አላደረገም፡፡ ለዚህም እንዲህ ባደርግ በአባ ሳሙኤል በኩል የሚፈጸምልኝ ጉዳይ ሊበላሽ ይችላል ብሎ ቅድሚያ ለዚያ ሰጥቶም እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ ሌላውን አለስሙ ስም ለመስጠት አለቅጥ የሚጣደፈውና ማንም የማይቀድመው ማቅ በዚህ ጉዳይ ላይ ያሳየው ዳተኛነትና ቸልተኛነት ሰዎች እንዲወገዙ ጥያቄ የሚያቀርበው በሃይማኖታቸው ላይ ሕጸጽ ስለተገኘ ሳይሆን ለእርሱ አልመች ስላሉትና ስለተቀናቀኑት ነው ለሚለው የብዙዎች እምነት ትልቅ ማጠናከሪያ ሆኗል፡፡ 

ውሸት ቢሮጥ እውነትን አይቀድምም “አሪፍ ለወሬ አይቸኩልም” ይላሉ የአራዳ ልጆች፡፡ መጽሐፍም “ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤” ይላል፡፡ (ያዕቆብ 1፥19)፡፡ በዚህ የማይመራው የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን ሐራ እውነትን ለማድበስበስና ብዙዎችን በወሬ ለመፍታት ያልተደረገውን ተደረገ የተደረገውን ደግሞ አልተደረገም በማለት ሐሰቱንና የልቡን ተምኔት ሁሉ “ሰበር ዜና” እያለ ማቅረቡን ቀጥሏል፡፡ ሰበር ዜናፈቃድ የሌላቸው የኢ..ኤስ ፕሮግራሞች በቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ተወሰነ፤ 24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት ይጀመራል” በሚል ርእስ ሰሞኑን ያናፈሰው ወሬ የተዛባና ሐሰት የተቀላቀለበት መሆኑን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ በሐራ ዘገባ ሐሰትነት ያዘኑት ምንጮች ሐራ እንዲህ የምታደርገው ሰውን በወሬ ለመፍታት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሲኖዶሱ በሰበካ አጠቃላይ ጉባኤ በተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ተመስርቶና በሌሎች የራሱ ጉዳዮችም ላይ አጀንዳውን እንደሚያረቅ እየታወቀ በአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ያልተነሣውንና በመግለጫው ላይ ያልተነሣውን የተሐድሶን ጉዳይ ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል በስርዋጽ አስገብቶ እንዲያነበው በማስደረግ ሸፍጥ ተፈጽሟል፡፡

(ዳንኤል በት/ቤት እያለ የማቅ ደጋፊ በኋላ ደግሞ ተቃዋሚ የነበረ ቢሆንም ከዚህ ቀደም በፈረንሣይ ኤምባሲ እርዳታ አባ ጳውሎስ የተወለዱበት መደራ አባ ገሪማ ገዳም ሙዚየምን ለማሠራት በገዳሙ ስም ገንዘብ ተቀብሎ የነበረ ቢሆንም ኤምባሲው ገዳሙን ሲጠይቅ ገንዘቡ እንዳልደረሰው በመግለጹ ዳንኤል ከሥራ ታግዶና ወደ ውጪም እንዳይወጣ ጭምር ተፅፎበት ነበር፡፡ እሱም ከላይ የተገለጸውን ችግር የሠሩብኝ ማቆች ናቸው ይል ነበር፡፡ ጉዳዩ በምን እንደተዘጋ ሳይታወቅ አሁን የአቡነ ገሪማ ምክትል ሆኖ እየሠራ ይገኛል፡፡ በ34ኛው የሠበካ ጉባኤ የመዝጊያው የአቋም መግለጫ ላይ ከስብሰባው መንፈስ ውጪ በሥርዋፅ የገባ “ተሃድሶ” የሚል ቃልና ሐሳብ መነበቡ ዳንኤል እነ አቡነ ማቴዎስን ለማስደሰት ያደረገው እንደሆነ ታውቋል፡፡ ምክንያቱም ከፈጸመው የሌብነት እገዳ በኋላ መልሰው ያስገቡት እሳቸው በመሆናቸው ለውለታቸውና በቀጣይም ለማቅ አጋር ሆኖ መቀጠል እንደሚፈልግ ለማሳየት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡)