Thursday, January 29, 2015

አስተያየት መቀበል የተሳናቸው ጳጳሳት መጨረሻቸው ምን ይሆናል?የዘንድሮው የጥቅምት ወር ሲኖዶስ ከወሰናቸው ውሳኔዎች መካከል አንዱ በተራ ቁጥር 19 ላይ ተይዞ በነበረው አጀንዳ ውስጥ በሥርዋፅ የገባውና ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በቅርቡ ያሳተመው “ስማችሁ የለም” የሚለው መጽሐፍ ጉዳይ እንደሚገኝበት በቅርብ ጊዜ ከወጣ አንድ ጽሑፍ ላይ ሳነብ እጅግ ነው የተገረምኩት፡፡ ሲኖዶሱ እጅግ ወርዶና ተዋርዶ “ ‘ስማችሁ የለም’ የሚለው በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተጻፈው መጽሐፍ በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶና ተመርምሮ መልስ እንዲዘጋጅለት ሲል በአንድ ድምጽ ተስማምቶ ወስኗል፡፡” ሲል የቃለ ጉባኤው ውሳኔ ያስረዳል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር ማለት እንዳለብኝ በጣም ተሰምቶኛል፡፡ ለግንዛቤ እንዲረዳ “ስማችሁ የለም” በሚል ርእስ የቀረበውን የዲ/ን ዳንኤል ክብረትን ጽሑፍ ቀጥሎ ላቅርብ፡፡ ከዚያ ወደ ጽሑፌ አገባለሁ፡፡ስማችሁ የለም
በሰማያዊው ዙፋን ዘንድ አንድ ውሳኔ ተላለፈ፡፡ «እነዚህ የኢትዮጵያ ሰዎች ሃይማኖተኞች ናቸው፡፡ ስለዚህም ዓለም ከማለፉ በፊት አስቀድመው ተጠርተው ዋጋቸውን ሊቀበሉ ይገባል» የሚል፡፡ አንድ ሊቀ መልአክ እልፍ አእላፍ መላእክትን አስከትሎ ከሰማይ ሲወርድ ታየ፡፡ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሰዎችንም ሁሉ ለሰማያዊ ፍርድ ሰበሰባቸው፡፡

ወዲያውኑ በመንግሥተ ሰማያት በር ላይ ሁለት ዓይነት ሰልፎች ታዩ፡፡ አንደኛው ሰልፍ ረዥም፤ ሌላኛው ሰልፍ ግን አጭር ነበር፡፡ ረዥሙ ሰልፍ ባለበት ቦታ ገበሬዎች፣ ወዛደሮች፣ የዕለት ሥራ ሠራተኞች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ ሕፃናት፣ ሊስትሮዎች፣ የቤት ሠራተኞች፣ ሾፌሮች፣ መሐንዲሶች፣ ሐኪሞች፣ አስተማሪዎች፤ ማን ያልተሰለፈ አለ፡፡ ከጥቂቶቹ በቀር ብዙዎቹ መንግሥተ ሰማያት የመግቢያ ካርድ ማግኘት ቻሉ፡፡

ይህንን ሁኔታ ሲመለከቱ በአጭሩ ሰልፍ በኩል የተሰለፉት የልብ ልብ ተሰማቸው፡፡ መጀመርያውኑ ለብቻቸው ሰልፍ የሠሩት ከሕዝብ ጋር ላለመደባለቅ እና ላለመምታታት ብለው ነበር፡፡ እንዴት ሲያስተምሩት፣ ሲያስመልኩት፣ ሲያስሰግዱት፣ ሲያሳልሙት፣ ከኖሩት ሕዝብ ጋር አብረው ይሰለፋሉ? መጀመርያ ነገር እነርሱ ያስተማሩት ሕዝብ መንግሥተ ሰማያት ከገባ እነርሱ የማይገቡበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ወደፊትም ቢሆን በመንግሥተ ሰማያት ለየት ያለ የክብር ቦታ ሊጠብቃቸው ስለሚችል ለየት ብለው መሰለፋቸው ተገቢ ነው፡፡ ይህንን እያሰቡ እና እያወሩ እያለ አንድ መልአክ ወደ እነርሱ ሰልፍ መጣ፡፡

ተሰላፊዎቹ በኩራት ገልመጥ ገልመጥ አሉ፡፡ እንዲያውም «ከመካከላችን ማን ይሆን ቀድሞ የሚገባው» የሚለው ነገር ሊያጨቃጭቃቸው ነበር፡፡ አንዳንዶች በተከታዮቻቸው ብዛት፣ አንዳንዶች በነበራቸው መንፈሳዊ ሥልጣን፣ አንዳንዶች ባገኙት የካሴት እና የመጽሐፍ ገቢ፣ ሌሎችም በሕዝቡ ዘንድ በነበራቸው ተደናቂነት፣ የቀሩትም ደግሞ በንግግር እና በድምጽ ችሎታቸው እየተማመኑ እኔ እበልጣለሁ እኔ እቀድማለሁ ሲባባሉ መልአኩ «እናንተ እነማን ናችሁየሚል ያልተጠበቀ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡

Sunday, January 25, 2015

የተሐድሶ እንቅስቃሴ በሚያስገርም ፍጥነት እየሄደ ነው።

Read in PDF


እኔው ነኝ
  ከዛሬ አራት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ያለውን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ያለበትን ደረጃ በጽሑፍ አቅርቤ እንደነበረ ይታወሳል። በዚያ ጽሑፌ ማህበረ ቅዱሳንና የተሐድሶ አንቀሳቃሾችን "ሁለቱ ኃያላን‚ በማለት ገልጫቸው ነበር አሁን ግን ኃያልነቱን ለተሐድሶዎች ብሰጥ የተሳሳትሁ አልሆንም። ከአራት ዓመት በኋላ ያለው እይታዬን ደግሞ እነሆ!  ሁለቱ እንደ እስማኤልና ይስሐቅ ወይም እንደ ኤሳውና ያዕቆብ እርስ በርስ የሚገፋፉ ናቸው። ተሐድሶዎች ማህበረ ቅዱሳንን የባሪያቱ ልጅ ይሏቸዋል። እስማኤልና ይስሐቅ ከአንድ አባት እንደተወለዱ ሁሉ ማህበረ ቅዱሳንና ተሐድሶዎችም ከአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የተወለዱ ናችው። ሁለቱ በአንድ ባል ከሚተዳደሩ፣ በአንድ ቤት ከሚኖሩ ሁለት እናት እንደተወለዱ ሁሉ ማህበረ ቅዱሳንና ተሐድሶዎችም ባንድ ጌታ ከተሰጡ በአንድ ሐሳብ ላይ ከሚያጠነጥኑ ከብሉይ ኪዳን እና ከሐዲስ ኪዳን የተወለዱ
ማህበረ ቅዱሳን ከብሉይ ኪዳን ተሐድሶዎች ከሐዲስ ኪዳን ተወልደዋል። ይህን ያልኩበት ምክንያት ማህበረ ቅዱሳን እንደ ፈሪሳውያን ወግ አጥባቂ ሲሆኑ ታቦትና የብሉይ ኪዳን ሕጎችን እንደ ወር አበባና የአመጋገብ ሥራት የመሳሰሉትን ልክ እንደ አይሁድ ስለሚከተሉ ነው። ተሐድሶዎች ግን ብሉይ በሐዲስ ስለተተካ የአይሁድን ሕግ የመከተል ግዴታ የለብንም ኃጢአትን ማድረግ የለብንም እንጂ የአይሁድን ልማድ ለመከተል አንገደድም ይላሉ። በዚህም ምክንያት ማህበረ ቅዱሳን ተሐድሶዎችን ያሳድዳሉ። በገላትያ ም 4፥22 ላይ ባርያይቱ አጋር በብሉይ ኪዳን የተመሰለች ሲሆን ልጇ እስማኤል የአሳዳጆች ምሳሌ ሆኖ ቀርቧል። ሳራ ደግሞ የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ ስትሆን በስተርጅና የወለደችው ልጇ ይስሐቅም የስደተኞች ምሳሌ ሆኗል። ስለዚህ ማህበረ ቅዱሳን የባሪያይቱ ልጅ፣ ተሐድሶዎች የጭዋይቱ ልጅ ይባላሉ። ተሐድሶዎች ኦርቶዶክስ በስተርጅና የወለደቻቸው የተስፋው ቃል ልጆች ናቸው። 

Thursday, January 22, 2015

ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶን ከመቀበል ይልቅ ለማጥናት ኮሚቴ የማቋቋሟ አንድምታ

በእግዚአብሔር መንግሥትና በሰይጣን መንግሥት መካከል ያለው ትግል ከጥንት እስከ ዛሬ እንደቀጠለ ነው። ሰይጣን የእግዚአብሔርን ዕቅድና ዓላማ ሊያበላሽ በተንኮልና በማስፈራራት ሲሠራ ኖሯል። የቱንም ያህል ቢፍጨረጨር ግን እግዚአብሔር ያቀደውን ከመፈጸም አላገደውም። ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ ሰይጣን የሚጠቀምበት ስልት አንድ ዓይነት መሆኑ ነው። በብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ነቢያት የእግዚአብሔርን ቃል ወደሕዝቡ ሲያመጡና ፍርዱን ሲገልጡ ሕዝቡም ንስሐ እንዲገቡ ሲናገሩ ይህ እንዲሆን የማይፈልገው ሰይጣን ነቢያትን የሚያሳድዱ ሰዎችን በተለይም ነቢያት ነን የሚሉ ሐሰተኛ ነቢያትንና መምለክያነ ጣኦት የሆኑ ነገሥትን ጭምር በእውነተኞቹ ነቢያት ላይ ያስነሣና ያሳድዳቸው ያስደበድባቸው ያስገድላቸውም ነበር። በዚህ ውስጥ የእግዚአብሔር ዕቅድ መፈጸሙ ግን አልቀረም። ይሁን እንጂ የነቢያቱን ድምፅ ያልሰሙት የተነገረው ፍርድ ደርሶባቸው ለምርኮና ለብዝበዛ ተዳርገዋል። ብሉይ ኪዳን ይህን በመሰለ ታሪክ ተሞልቷል።


በሐዲስ ኪዳን ዘመንም ሰይጣን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በተከታዮቹ ሐዋርያት ላይ ተመሳሳይ ስልት ነው የተጠቀመው፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆንና በምድረ እስራኤል እየተመላለሰ ማስተማሩና ብዙ ተከታይ ማፍራቱ ያበሳጨው የእግዚአብሔር መንግሥት ጠላት ሰይጣን የሃይማኖት ሰዎችን በመቀስቀስ መድኃኒታችን እንዲያዝና እንዲሰቀል አደረገ፡፡ እርሱ ቢሞት እንቅስቃሴው ይቆማል ብሎ ነበር፡፡ ለጊዜው እርሱ ተይዞ ሲሰቀልና ደቀመዛሙርቱም ሲበተኑ ሰይጣን ድል የደረገ መሰለው፡፡ ነገር ግን ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ሰይጣን ያሰበው አልሆነም፡፡ እንዲያውም ባሰበት፡፡ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት የሃይማኖት ሰዎች ነን በሚሉ ጻፎች ፈሪሳውያንና ሊቃነ ካህናት ብዙ ዛቻና ማስፈራሪያ፣ እስርና ስደት እስከ ሞት የደረሰ መከራም ደርሶባቸዋል። ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ዕቅድ ከመፈጸም ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ድኅነተ ነፍሳቸውን ማግኘታቸው ወንጌል መሰበኩ ቤተ ክርስቲያን (ምእመናን) እየበዙ መሄዳቸው፣ ቤተክርስቲያን በዓለም ሁሉ መስፋፋቷ አልቀረም፡፡ ዛሬ ግን ክርስቶስን የምታሳድድ እውነተኛውና መጽሐፍ ቅዱሳዊው የክርስትና ሕይወት የተለያትና በልማዳዊ ሥርዐት የምትመራ ሃይማኖታዊ ተቋም የሆነች “ቤተክርስቲያን” መሆኗ በእጅጉ ያሳዝናል፡፡ ስለዚህ ሰይጣን ቤተክርስቲያንን ለማሳደድ እየተጠቀመ ያለው ቤተክርስቲያን ነኝ የምትል ሃይማኖታዊ ተቋምን መሆኑ ያስገርማል፡፡

Saturday, January 17, 2015

የክርስቶስ ሰምራ ክንፎች

Read in PDF

እኔ ካነበብኋቸው መጻሕፍት እንደተረዳሁት ባገራችን በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክንፍ አውጥተው የሚበሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ። እነርሱም አንደኛ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሁለተኛይቱ ክርስቶስ ሰምራ ናቸው። ሁለቱም የቡልጋ ተወላጆች የነበሩ ሲሆን በሥጋም ዘመድ መሆናቸውን ገድላቸው ይናገራል። ክንፉ የዘር ይሆን የታምር ለተመራማሪዎች ትቼዋለሁ።

 የተክለ ሃይማኖት  ስድስት ክንፎች አበቃቀል ሁለት ዓይነት ታሪክ ያላቸው ሲሆን አንደኛው ሰባት ዓመት ቁመው በመጸለያቸው እግራቸው ስለተቆረጠ ክንፍ ተሸለሙ ይላል። ሁለተኛው ግን ደብረ ዳሞ ላይ ሰይጣን ገፍቶ ሊጥላቸው ሲሞክር ክንፍ ተሰጧቸው ስለበረሩ ሳይወድቁ ቀርተዋል የሚል ነው። እዚህ ላይ ጥያቄ አለኝ የተክለሃይማኖት ክንፎች መቼ በቀሉ? ትክክለኛውን ታሪክ አጥርታችሁ ንገሩኝ? ሁለተኛው ጥያቄዬ የተክለ ሃይማኖት አጥንት ከተቀበረበት ወጥቶ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ተቀምጧል ክንፎቻቸው የት ሄዱ? እነዚህን ጥያቄዎች ዳንኤል ክብረት ቢመልስልኝ ካልተቻለ ግን ማንኛውም ሊቀ ሊቃውንት ይመልስልኝ። እኔ ግን ወደ ክርስቶስ ሰምራ ክንፎች ትንታኔ ላቅና። በመጀመሪያ ስለክንፎቿ የሚተርከውን ክፍል በግእዝ ልጻፍላችሁና ከዚያ በአማርኛ ልተርጉምላችሁ እናንተ ግን ምዕራፍና ቁጥሩን ከመጽሐፈ ገድሉ በማንበብ የበለጠ እንድትረዱልኝ እጠይቃለሁ።
 "ወሶቤሃ ሠረፁ ላዕለ ሥጋሃ ስድስቱ አክናፍ ሠለስቱ በየማና ወሠለስቱ በጸጋማ። ወሶበ ሰፍሐት ዘይንእስ ክነፊሃ በጽሐ እስከ ደብረ ዳጋ። ወለእለ ይልሕቁሰ አክናፊሃ ኢያእመረት ብጽሐቶሙ። ወበኅሊናሃሰ ሐለየት እንዘ ትብል አይቴ ያበጽሑኒ እሙንቱ አክናፍ። ወእንዘ ትሄሊ ከመዝ አውስአ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይቤላ ምንተ ትሄልዪ ክርስቶስ ሰምራ ፍቅርትየ። ወትቤሎ ትሄሊ አመትከ እንዘ ትብል አይቴ ያበጽሑኒ እሙንቱ አክናፍየ። ወይቤላ ሶበሰ ፈቀድኩ በሥልጣነ መለኮትየ እምጽንፍ እስከ ጽንፍ እምአብጽሑኪ ክልኤቱ እምኔሆሙ። ወባሕቱ ለክብረ ዚአኪ ረሰይኩ ለኪ እሎንተ ስድስተ አክናፈ ከመ አርባዕቱ እንስሳ መናብርትየ። ወእሙንቱሰ አክናፍ ምሉዓን አዕይንት ወኍላቈሆሙ ዐሠርቱ ምዕት ወሥዑል ውስቴቶሙ ሥዕለ ኪሩቤል። ወሶበ ከሠተ ዓይኖ አሐዱ እምኔሆሙ አብርሃ ኩሎ ዓለመ ከመ ፀሐይ። ርእዩኬ አበውየ ወአኃውየ ዘመጠነዝ ጸጋ ዘአሰርገዋ በአክናፈ ስብሐት ከመ አርባዕቱ እስንስሳ መናብርት።” ገድለ ክርስቶስ ሰምራ ዘጥር ም 1፥64-74።

Tuesday, January 13, 2015

ይድረስ ለወንድሜ ለዳንኤል ክብረት

Read in PDF

እኔ ስሜ እገሌ እባላለሁ የተወለድሁት በጎጃም ክፍለ ሀገር ነው። እንደ ማነኛውም የቤተ ክርስቲያን ልጅ ገና የሰባት ዓመት ልጅ ሆኜ ነበር ቆሎ ት/ ቤት የገባሁት። በልጅነቴ የሀገሬ ቤተ ክርስቲያን መርጌታ ከሆኑት ከዬኔታ ሞገሴ ፍቅር እያገኘሁ አደግሁ። እናት እና አባቴ ጥሩ አሳዳጊዎች ነበሩ፣ ነገር ግን ባሀገሩ ባህል ትምህርት እንዲገባው በሚለው አስተሳሰብ ለምኜ እየበላሁ እንድማር ተገደድሁ። አባቴ በግ እንድጠብቅለት ነበር የሚፈልገው፣ እናቴም እንዲሁ። የኔታ ግን ቤተ ሰቦቼን እየመከሩ እንድማር አደረጉ። ቀን ፊደል አቡጊዳ፣ መልክተ ዮሐንስ ወንጌለ ዮሐንስ ከዚያም ዳዊት ጾመ ድጓ እየተማርሁ፣ ማታ ደግሞ የዘወትር ጸሎት፣ ውዳሴ ማርያም፣ አንቀጸ ብርሃን፣ መልክአ ማርያም መልክአ ኢየሱስ፣ ት/ኅቡአት፣ ውዳሴ ማርያም ዜማ፣ መስተጋብዕ፣ አርባዕት፣ አርያም፣ ክስተት፣ ሰለስት፣ ስብሐተ ነግሕ። ተማርሁ እነዚህ ሁሉ የቃል ትምህርት ናቸው ሌት ያለ መብራት ስለምንማራቸው በቃል የምንይዛቸው ናቸው።
 ይህ በእንዲህ እንዳለ እነዚህን ትምህርቶች አጠናቅቄ ገና ሳልጨርስ ከብፁእ አቡነ መቃርዮስ የምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዲቁና ተቀበልሁ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን ካጠናቀቅሁ በኋላ የኔታ መርቀዉኝ ጉልበት ስሜ ተሰናብቼ ቅኔ ቤት ገባሁ። ቅኔው ወዲያው ነበር የገባኝ። ሦስት ቦታዎች ላይ ከጉባኤ ቃና እስከ መወድስ ያሉትን ሞልቼ አራተኛው ቦታ ላይ አስነጋሪ ሆንሁ። በቅኔ አዋቂነቴ ባካባቢው ሊቃውንት ዘንድ አድናቆትን አትርፌ ነበር። የኔን ቅኔ ለመስማት የማያሰፈስፍ ሊቅ አልነበረም።

Friday, January 9, 2015

ዕጹብ የገና ስጦታ፡- ‹‹ሰላም በምድር ይሁን፣ ለሰው ልጆችም በጎ ፈቃድ!››በዲ/ን ተረፈ ወርቁ
የሰላም ጉዳይ፣ የሰላም ወሬ የፍጥረት ሁሉ ናፍቆት ነው ብል ብዙም ያጋነንኩ አይመስለኝም፡፡ ሰላም ማለት የግጭት፣ የብጥብጥ፣ አሊያም የጦርነት አለመኖር ብቻ አይደለም ይላሉ የሥነ ልቦና ምሁራን፡፡ ሰላም በጦርነት፣ በጫጫታ፣ በኹከት፣ በመናወጥና በማይመች ሁኔታ ውስጥም ሆኖ እርጋታን፣ ውሳጣዊ ጸጥታን መላበስም ጭምር ነው ሲሉ መንፈሳዊ አንድምታ ያለው ትርጓሜ ይሰጡታል፡፡
በእርግጥም በነጋ ጠባ፣ የጦርነትና የእልቂት፣ የሥቃይ፣ የጩኸትና የጣር ድምጽ በሚሰማባት ዓለማችን፣ የሽብር ሥጋት ክፉኛ በሚንጣት ምድር ላይ እየኖርን ውስጣዊ የሆነ በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆንም የማይናወጥና የማይደፈርስ ሰላም ይኖርን ዘንድ የግድ ይላል፡፡
እንዲህ ዓይነቱ ሰላም ምንጩ ከላይ፣ መገኛውም ሰማያዊና መለኮታዊ ነው ሲሉ የሃይማኖት ሊቃውንትና ምሁራን ከቅዱሳት መጽሐፍት ጠቅስው ያስረዳሉ፣ ይተነትናሉ፡፡ ዓለማውያኑንም ሆኑ በፈጣሪ መኖር የሚያምኑ ምሁራን ስለ ሰላም ምንጭ ያላቸው ትንታኔ ቢለያይም በአንድ ነገር አጥብቀው ይስማማሉ፡፡ እርሱም ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ አስፈላጊና መሰረታዊ መሆኑን!!

Tuesday, January 6, 2015

“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።” ሉቃ. 2፥11እንኳን ለጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ እንላለን፡፡ ይህን የደስታ መግለጫ መልእክት ለውድ የአባ ሰላማ ብሎግ አንባቢዎች ስናስተላልፍ መልእክታችን በባህላዊ መንገድ ለሚከበረው የገና በዓል እንኳን አደረሳችሁ ከማለት ያለፈ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡ መልእክታችን እንኳን ክርስቶስ ተወለደላችሁ፡፡ ክርስቶስ በመወለዱ እንኳን ደስ አላችሁ ወደሚለው ያዘነበለ ነው፡፡

እንደ ክርስቲያን በዚህ በዓለ ልደት የደስታችን ምክንያቱ የክርስቶስ መወለድ እንጂ ሌላ ሊሆን አይገባውም፡፡ ክርስቶስ በተስፋ ሲጠበቅ የነበረው ሕዝቡን ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው መድኃኒት መሆኑ በመልአኩ በኩል በዚያች ሌሊት መንጋቸውን ሲጠብቁ ለነበሩ እረኞች ተበሥሯል፡፡ ብሥራቱ ለእረኞቹ የጠላለፈ ቢሆንም ለእነርሱ ብቻ ሳይሆን ለሕዝቡ ሁሉ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤” እንዳለ መልአኩ፡፡
የተወለደው ክርስቶስ ጌታ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው የሚያድን፣ ሰውንና እግዚአብሔርን በሞቱ የሚያስታርቅ፣ በኃጢአት ምክንያት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የገባውን ጥል የሚያስወግድ ብቸኛ ሊቀ ካህናትና መሥዋዕት ነው፡፡ በዓለ ልደቱን በየዓመቱ ስናከብር ይህን እውነት ማእከል አድርገን ካልሆነ ግን እንደ ከሰርን ነው የሚቆጠረው፡፡ ስለዚህ በበዓለ ልደቱ የተነገረው የምሥራች ወደ ውስጣችን ዘልቆ ሊገባ፣ የተወለደው ክርስቶስ መድኃኒታችን፣ ጌታችንና አምልካችን መሆኑን ማወቅ ብቻ ሳይሆን ማመን ይገባናል፡፡ በእርሱ መምጣትና ሰው ሆኖ መወለድ የልብ ዕረፍትና ሰላም ሊሰማንም ይገባል፡፡ እነዚህ ነገሮች ለእያንዳንዳችን ካልደረሱልንና “የክርስቶስ በዓለ ልደት” በሚል ብቻ በዓሉን በመብልና በመጠጥ ፌሽታ ብቻ የምናከብር ከሆነ ግን የክርስቶስ መወለድ ለእኛ ምንም ትርጉም አይኖረውም፡፡ መልአኩ ካበሠረን ብሥራት በእጅጉ ተራርቀናልና ስለዚህ ልናስብበት ይገባል፡፡

Monday, January 5, 2015

አቡነ ቀለሜንጦስ በውጥረት ላይ ናቸውበቅርቡ የቅዱስ ፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በመሆን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አባ ቀለሜንጦስ ብልሹ አሠራርንና ዘረኝነትን ያስወግዳሉ ተብለው በቅዱስ ፓትርያርኩ አቅራቢነት ከቅዱስ ሲኖዶስ ኃላፊነት ቢሰጣቸውም አስተዳደራቸው ግን ገና ከጅምሩ ከዚህ በፊቱ ባልተናነሰ ዘረኝነት ውስጥ የተዘፈቀ እየሆነ ነው የሚል ትችት እየተሰነዘረባቸው ይገኛል።
ይህንን የሚሉ ሰዎች ለማስረጃነት ከሚያቀርቡት አንዱ የሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ዋና ጸሀፊ ለነበረው ዲያቆን ሩፋኤል የማነብርሃን ያደረጉት ነገር ነው። ይህ ግለሰብ በዘረፋ እና ንዋየ ቅድሳትን በማተራመስ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሲሆን ተነቃብኝ ብሎ የቤት እቃውን ሸጦ ወደ አሜሪካ ሊሄድ ሲል የካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ አድርገው በመሾማቸው ጉዞውን ሰርዞ ተደላድሎ ተቀምጧል።
አመጸኛውና መዝባሪው ዳቆን ሩፋኤል በሄደበት ቦታ ሁሉ ከህዝበ ክርስቲያኑ እና ከማህበረ ካህናቱ ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት የሚኖር ሰው ነው። የሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ካህናትና ምዕመናንም የቅዱስ ፓትርያርኩንና የሀግገረ ስብከቱን ቢሮ በተቃውሞ እያጨናነቁት ሳለ ዲያቆኑ ግን መልካም እንደሰራ ተደርጎ ለአስተዳዳሪነት መሾሙ አባ ቀለምንጦስን ዘረኛ የሚለውን ስም ሊያሰጣቸው ችሏል።
ከዚህም ጋራ ተያይዞ የሥጋ ዘመዳቸውን ሳሕለ ማርያምን የሀገረ ስብከቱ ዋና አስተዳዳሪ አድርገው በመሾማቸው የጳጳስ ወገንተኛ ናቸው እየተባለ ስማቸው እየተነሳ ይገኛል። ትችቱንም የሚያቀርቡት በአብ ዛኛው የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ልዩ ልዩ ሠራተኞች ናቸው።

Friday, January 2, 2015

አባ ሰላማ አገልግሎት ከጀመረች 4 ዓመት ሆናት

የአባ ሰላማ ብሎግ ከተጀመረች እነሆ 4 ዓመት ሆናት። በዚህ 4 ዓመት ውስጥ ወደ 3 ሚሊዮን ጎብኝዎች ሲኖሯት ብዙ እውቀትና መረጃዎች ያስጨበጠች ስለመሆኗ አንጠራጠርም። የደረሱን አስተያየቶች እንዳመለከቱን  በርካታ አንባቢዎቻችም ብዙ ቁም ነገር እንደጨበጡ  የገለጹልን ሲሆን ገንቢ የሆኑ አስተያየቶችንም ተቀብለናል። ስለነበረው ሰፊ ተሳትፎ፤ አስተያየት እና ምክር እጅግ እናመሰግናለን።  በአንጻሩ ደግሞ ከተወሰኑ አንባቢዎች የደረሱን አስተያየቶች በህዝባችን ዘንድ የእውቀት ማነስ እና ያለመረዳት ችግር እንዳለም አስገንዝበውናል። ጭፍን ያለ ደጋፊነት፣ ጋጠ ወጥ የሆነ ስድብ፣ ለማወቅ እና ለመረዳት አለመፈለግ ችግር አሁንም እንዳለ ለማስተዋል ችለናል።  በተለይ በተወሰኑ አንባቢዎች ዘንድ ኃላነት ያላቸው ሰዎች ያለባቸውን  ተጠያቂነት ያለመረዳት ችግር በስፋት ይስተዋላል።  
በአባ ሰላማ ብሎግ ላይ ማንኛውም ሰው በመረጃ የተደገፈና እውነተኛ ሐሳቡን መግለጥ እንደሚችል እሁንም ልናስታውስ እንወዳለን። ነገር ግን ባለፉት 4 ዓመታት እንዳደረግነው የመረጃዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥና እውነተኛ መረጃ ያላቸውን ጽሁፎች ብቻ ለማስተናገድ የተቻለንን ሁሉ ስናደርግ ቆይተናል አሁንም እናደርጋለን።  ባለፉት 4 ዓመታት ውስጥ አባ ሰላማ በብዙ ሃሳቦች ዙሪያ አንባቢያንን ያወያየች ሲሆን ድምጽ ለሌላቸውም ድምጽ ሆና ቆይታለች። በተለይ ግን በመሪዎቻችን እና ኃላፊነት ባላቸው ሰዎች ዘንድ ተጠያቂነት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስታደርግ ቆይታለች። በትክክለኛ መረጃ የተደገፈ እስከሆነ ድረስ በአገራችን እና በቤተ ክርስቲያናችን እየተፈቸመ ያለውን ነውር፣ በደል፤ አመጻና የክፋት አሰራር ሁሉ ከማጋለጥ ወደኃላ እንደማንል ልናረጋግጥላችሁ እንችላለን። ይህንን ስናደርግ ግን የሁሉንም የሰው ክፋት እንገልጣለን ማለት ሳይሆን በሃላፊነት ደረጃ የተቀመጠ ሰው ሓላፊነቱን ረስቶ ስናገኘውና የተዋረደ ስራ ሲሰራ ስናገኘው ልናልፈው አንችልም ለማለት ነው። ታዋቂና ሃላፊነት ያለው ሰው ተጠያቂነት እንዳለበት ማስገንዘብ ስም ማጥፋት አይደለም። ስም ማጥፋት የሚባለው ሰው ያላደረገውን አደረገ ብለን ስንጽፍ እንጂ እርሱ በድፍረት ያደረገውን ኃጢዓት እኛም በድፍረት ብንገልጠው ስም ማጥፋት ሊሆን አይችልም።  መጽሐፍ ቅዱስም ከጨለማ ስራ ጋር አትተባበሩ ይልቁንም ግለጹት በማለት ይደግፈናል። ሐላፊነት ያለበትን ሰው ገመና መሸፈን የመጽሐፍ ቅዱስ ባህል አይደለም።  ይልቁንም ሌሎችን የማዳንና የማስጠንቀቅ ስራ የመጽሐፍ ቅዱስ አሰራር እንደሆነ ግልጽ ነው።  የእነ ዳዊት ኃጢአት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈው ገመናን መሸፈን ትክክል ስላልሆነ ነው። የቅዱሳን ሁሉ ኃጢዓት በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል እግዚአብሔርም ገመናቸውን አልሸፈነም። የመጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛና እውነተኛነት የተረጋገጠው የኃጢዓተኞችን በደል በመግለጡ ብቻ ሳይሆን የቅዱሳኑንም ኃጢያት በማጋለጡ ነው። ስለዚህ እኛ የምንከተለው የሐበሻን ባህል ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስን ባህል ነው። አገራችን የመጽሐፍ ቅዱስን ባህል ብትከተል አመጽ እና በደል እንዲህ እየሰፋ ባልሄደም ነበር። ስለዚህ እውነቱን ተገጋግረን ከማስመሰል ህይወት እንውጣና ተጠያቂነት እንዲኖር ሁላችንም ልንሰራ ይገባል።  የተዋረደውን እንደከበረ፤ የከበረውን እንደተዋረደ አድርገን ማየታችንን እናቁም። ብዙ ጊዜ ገመናን መሸፈን ነገር ሲነሳ የኖህን ገመና የሸፈኑት ሴምና ያፌት ይጠቀሳሉ። ይህ ግን ኖህ አንዴ ብቻ ያደረገው በመሆኑ ሊሸፈን ይገባል። ሁሌ የሚሰክርና እራቁቱን የሚሆን ቢሆን ኖሮ ግን ሊሸፈን አይገባውም ነበር። ስለዚህ በሀገራችንም ሀጢያት እና በደልን በቋሚነት ይዘው ጻድቅ ለመምሰል የሚሞክሩ ሰዎችን እናጋልጣለን እንጂ በስህተት ወድቀው በንስሃ የተመለሱትን  ማለት ስህተታቸውን ቋሚ አድርገው ያልያዙትን ሰዎች የማጋለጥ አላማ የለንም። ስለዚህ ይህን ተግባራችንን ከትክክለኛ ማስረጃ መቀጠሉ አስፈላጊ ይሆናል ማለት ነው።

ክርስቶስን የምታሳድድ ቤተክርስቲያን እንዴት ቤተክርስቲያን ትሆናለች?

Read In PDF 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ክርስቶስ እየተሰበከባት ይገኛል፡፡ የዚያኑ ያህል ክርስቶስንም የማሳደድ ሥራ በተረፈ አይሁድ ማኅበረ ቅዱሳን በትጋት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ይህ ፀረ ክርስቶስና ፀረ ወንጌል ነገር እያካሄደ ያለው ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት ያላቆዩትንና እርሱ ከየገድላገድሉ የሰበሰበውንና ከወንጌል የሚቃረነውን “እንክርዳድ ሃይማኖቱን” እርሱ ተሐድሶ መናፍቃን የሚል ስም ካወጣላቸው የቤተክርስቲያንሊቃውንት ለመጠበቅና “እግዚአብሔርን ለማገልገል” ነው፡፡ ማቅ ይህን መልካም ስም የሰጠውን እኩይ ተግባር እየፈጸመ ያለው ከቤተክህነት እየጎረሱ ወደእርሱ በሚውጡ ግብረ በላዎቹትከሻ ላይ ተንጠላጥሎና በየሰበካ ጉባኤው በሰገሰጋቸው ቅጥረኞቹ በኩል ነው፡፡ ማቅ ለሃይማኖቴ ቀንቼ ነው ይህን እያደረግሁ ያለሁት ቢልም፣ ሥራው ክርስቶስን ማሳደድ ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስለተከታዮቹ አስቀድሞ ሃይማኖተኞች ነን ከሚሉ እግዚአብሔርን ሳያውቁ እግዚአዘብሔርን እናገለግላለን ከሚሉ ሰዎች ስደት እንደሚገጥማቸው እንዲህ ሲል ነግሯቸው ነበር፡፡“እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው። ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ እኔ እንደ ነገርኋችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። ከእንናንተም ጋር ስለ ነበርሁ በመጀመሪያ ይህን አልነገርኋችሁም።”(ዮሐ. 16፥1-4)፡፡ሳውል ለሃይማኖቱ ቀንቶና እግዚአብሔርን ያገለገለ መስሎት የክርስቶስን ተከታዮች ሲያሳድድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና አላገኘም፡፡ እንዲያውም የክርስቶስን ተከታዮች ማሳደዱ ክርስቶስን እንደማሳደድ ተቆጥሮበት “ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ?” የሚል የወቀሳ ቃል ያዘለ ጥያቄ ነበር የቀረበለት፡፡ የማቅ ድርጊትም ተመሳሳይ ነው፡፡ ማቅ ከዚህ ቀደም በርካቶችን ከእናት ቤተክርስቲያናቸው ሲያሳድድ ግዳይ እንደጣለና እግዚአብሔርን እንዳገለገለ ነው የሚቆጥረው፡፡ አሁንም በዚህ እኩይ ተግባሩ ገፍቶበታል፡፡