Friday, January 2, 2015

አባ ሰላማ አገልግሎት ከጀመረች 4 ዓመት ሆናት

የአባ ሰላማ ብሎግ ከተጀመረች እነሆ 4 ዓመት ሆናት። በዚህ 4 ዓመት ውስጥ ወደ 3 ሚሊዮን ጎብኝዎች ሲኖሯት ብዙ እውቀትና መረጃዎች ያስጨበጠች ስለመሆኗ አንጠራጠርም። የደረሱን አስተያየቶች እንዳመለከቱን  በርካታ አንባቢዎቻችም ብዙ ቁም ነገር እንደጨበጡ  የገለጹልን ሲሆን ገንቢ የሆኑ አስተያየቶችንም ተቀብለናል። ስለነበረው ሰፊ ተሳትፎ፤ አስተያየት እና ምክር እጅግ እናመሰግናለን።  በአንጻሩ ደግሞ ከተወሰኑ አንባቢዎች የደረሱን አስተያየቶች በህዝባችን ዘንድ የእውቀት ማነስ እና ያለመረዳት ችግር እንዳለም አስገንዝበውናል። ጭፍን ያለ ደጋፊነት፣ ጋጠ ወጥ የሆነ ስድብ፣ ለማወቅ እና ለመረዳት አለመፈለግ ችግር አሁንም እንዳለ ለማስተዋል ችለናል።  በተለይ በተወሰኑ አንባቢዎች ዘንድ ኃላነት ያላቸው ሰዎች ያለባቸውን  ተጠያቂነት ያለመረዳት ችግር በስፋት ይስተዋላል።  
በአባ ሰላማ ብሎግ ላይ ማንኛውም ሰው በመረጃ የተደገፈና እውነተኛ ሐሳቡን መግለጥ እንደሚችል እሁንም ልናስታውስ እንወዳለን። ነገር ግን ባለፉት 4 ዓመታት እንዳደረግነው የመረጃዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥና እውነተኛ መረጃ ያላቸውን ጽሁፎች ብቻ ለማስተናገድ የተቻለንን ሁሉ ስናደርግ ቆይተናል አሁንም እናደርጋለን።  ባለፉት 4 ዓመታት ውስጥ አባ ሰላማ በብዙ ሃሳቦች ዙሪያ አንባቢያንን ያወያየች ሲሆን ድምጽ ለሌላቸውም ድምጽ ሆና ቆይታለች። በተለይ ግን በመሪዎቻችን እና ኃላፊነት ባላቸው ሰዎች ዘንድ ተጠያቂነት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስታደርግ ቆይታለች። በትክክለኛ መረጃ የተደገፈ እስከሆነ ድረስ በአገራችን እና በቤተ ክርስቲያናችን እየተፈቸመ ያለውን ነውር፣ በደል፤ አመጻና የክፋት አሰራር ሁሉ ከማጋለጥ ወደኃላ እንደማንል ልናረጋግጥላችሁ እንችላለን። ይህንን ስናደርግ ግን የሁሉንም የሰው ክፋት እንገልጣለን ማለት ሳይሆን በሃላፊነት ደረጃ የተቀመጠ ሰው ሓላፊነቱን ረስቶ ስናገኘውና የተዋረደ ስራ ሲሰራ ስናገኘው ልናልፈው አንችልም ለማለት ነው። ታዋቂና ሃላፊነት ያለው ሰው ተጠያቂነት እንዳለበት ማስገንዘብ ስም ማጥፋት አይደለም። ስም ማጥፋት የሚባለው ሰው ያላደረገውን አደረገ ብለን ስንጽፍ እንጂ እርሱ በድፍረት ያደረገውን ኃጢዓት እኛም በድፍረት ብንገልጠው ስም ማጥፋት ሊሆን አይችልም።  መጽሐፍ ቅዱስም ከጨለማ ስራ ጋር አትተባበሩ ይልቁንም ግለጹት በማለት ይደግፈናል። ሐላፊነት ያለበትን ሰው ገመና መሸፈን የመጽሐፍ ቅዱስ ባህል አይደለም።  ይልቁንም ሌሎችን የማዳንና የማስጠንቀቅ ስራ የመጽሐፍ ቅዱስ አሰራር እንደሆነ ግልጽ ነው።  የእነ ዳዊት ኃጢአት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈው ገመናን መሸፈን ትክክል ስላልሆነ ነው። የቅዱሳን ሁሉ ኃጢዓት በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል እግዚአብሔርም ገመናቸውን አልሸፈነም። የመጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛና እውነተኛነት የተረጋገጠው የኃጢዓተኞችን በደል በመግለጡ ብቻ ሳይሆን የቅዱሳኑንም ኃጢያት በማጋለጡ ነው። ስለዚህ እኛ የምንከተለው የሐበሻን ባህል ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስን ባህል ነው። አገራችን የመጽሐፍ ቅዱስን ባህል ብትከተል አመጽ እና በደል እንዲህ እየሰፋ ባልሄደም ነበር። ስለዚህ እውነቱን ተገጋግረን ከማስመሰል ህይወት እንውጣና ተጠያቂነት እንዲኖር ሁላችንም ልንሰራ ይገባል።  የተዋረደውን እንደከበረ፤ የከበረውን እንደተዋረደ አድርገን ማየታችንን እናቁም። ብዙ ጊዜ ገመናን መሸፈን ነገር ሲነሳ የኖህን ገመና የሸፈኑት ሴምና ያፌት ይጠቀሳሉ። ይህ ግን ኖህ አንዴ ብቻ ያደረገው በመሆኑ ሊሸፈን ይገባል። ሁሌ የሚሰክርና እራቁቱን የሚሆን ቢሆን ኖሮ ግን ሊሸፈን አይገባውም ነበር። ስለዚህ በሀገራችንም ሀጢያት እና በደልን በቋሚነት ይዘው ጻድቅ ለመምሰል የሚሞክሩ ሰዎችን እናጋልጣለን እንጂ በስህተት ወድቀው በንስሃ የተመለሱትን  ማለት ስህተታቸውን ቋሚ አድርገው ያልያዙትን ሰዎች የማጋለጥ አላማ የለንም። ስለዚህ ይህን ተግባራችንን ከትክክለኛ ማስረጃ መቀጠሉ አስፈላጊ ይሆናል ማለት ነው።

15 comments:

 1. አራት አመት ሙሉ የክህደት ትምህርት ሰጣችሁ !! እንኳን ደስ አላችሁ!!

  ReplyDelete
 2. እውነት ትፀናለችJanuary 2, 2015 at 7:58 PM

  አባ ተሳዳቢ በአራት አመት በአለማዊ ህግ ስንት ወንጀሎችን በእግዚአብሔር ሕግ ደግሞ ስንት ሐጢያቶች፣ ስንት የስድብ አፍ ጽሑፎች፣ ስንት የሐሰት ትምህርቶች፣ስት የንፁሐንን ደም አፍስሱልን የሐሰት የቅስቀሳ ጽሑፎች ወዘተ አስተናግደናል? በነዚህ የክፍት ተግዳሮታችንስ ምን ያኸል አሳዳሪዎቻችንን መናፍቅ ፕሮቴስታንቶችንና አባታቸውን ሰይጣንን ደስ አሰኝተናል? ምህራባዊያኑና በአገር ውስጥ ያሉ አሠማሪዎቻችን የሚለቁልን የተልከኳቸው ማስፈፀሚ ግቡን መቶላቸዋልን?ለነገስ ብዙ ገንዘብ ፈንድ እናገኝ ዘንድ ምን አይነት በሬ ወለደ ክህደቶችን በእቅድ እናቅርብላቸው? ለማለት ይመስለኛ የዚህ ጽሑፍ መልዕክታችሁ። በቁጥር የገለፃችሁት የጎብኝ ቁጥር ከእውነት የራቀ ሐሰተኛ ናችሁና ሐሰት ነው። ለዚህ አንዱ ማረጋገጫ ጎብኝ ከማጣታችሁ የተነሳ ጽሑፎችን የምትለጥፉት እንደ ኢትዮጽያን ሪቪው አይነት ዊብ ሳይቶች ላይ አይደለምን? እኔም ሐሰተኛና የክህደት ጽሑፎቻችሁን የማያቸው በዚሁ ዊብ ሳይት ላይ ነው። አወናባጆች ናችሁና በጠቀስኩት ዊብ ሳይት ካወጣችሁትና አስተያየተች ሲመጡ የእናንተው ጭንብል ለበስ ብሎግ ተብየ ላይ ታወጣላችሁ። እኔ በግሌ ለክህደታችሁ መቃወመያ የሚሆን ለማስፈር እንጂ ከናንተ ከጥፍት ውጭ ምንም እውነታ እንደማይገኝ አውቃለሁ። ዳቢሎስን ተቃወሙት በብሏልና የእናንተን ሰይጣናዊ ጽሑፎች የመራ የመቃወመው ቀርበው ሳይረዱ በውጭ ሆነው ለሚወናበዱት በእናንተ ሐሰተኛ አሉባልታና የስህተት ትምህርት እንዳይጠቁ ለማስገንዘብ ይረዳቸው ዘንድ እንጂ እናንተ ወደ እውነት ትመለሳላችሁ ብየ አይደለም። ምክንያቱም አንድ ጊዜ ለጥፋት ተወስናችኋልና ነው።

  ReplyDelete

 3. «ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች። ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ።
  ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ። የባለቤቱም ባሮች ቀርበው። ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት። እርሱም፦ ጠላት ይህን አደረገ አላቸው። ባሮቹም። እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን? አሉት።
  እርሱ ግን፦ እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም።
  ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን። እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ» ማቴ 13፤ 24-30
  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሠረቷ በክርስቶስ አዳኝነት ላይ የቆመ ነበር። ነገር ግን ጠላት በዚያ መሠረት ላይ ሌላ ሊመሠርት ሌሊት መጣና ብዙ የድነት መንገድ መኖሩን በመናገር የራሱን ዘር ዘራ። ልጆቿ ጥዋት ተነስተው ይህንን የጥፋት ዘር የሆነውን እንክርዳድ ከስንዴው ጋር አብረው በቅሎ ተመለከቱ። የዘሩ መከር ደርሶ ወደ ጎተራ ከመሰብሰቡ በፊት ቀኑ ዛሬ መሆኑን የሚናገሩ የልጆችን ድምፅ በመከልከል እንክርዳዱ ባለበት እንዲቆይ ጠላት ብዙ ታገለ። ውጊያውን ከፈጸመባቸው መካከል አባ ሰላማ ብሎግ ከላይ በምስል ያስቀመጣቸውና ሌሎችም ሊቃውንት ነበሩ። «ከተመሠረተው በቀር ሌላ አንመስርት» በማለት የተናገሩት እነዚያ ሊቃውንት ያኔ ብዙ መከራን ቢቀበሉም ዛሬ ሚሊዮኖች መልካም ዘርን አፍርተዋል። ያ መልካም ዘር ማፍራቱን አላቆመም፤ አያቆምም። ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አንስቶ እስከ ታላቁ የሲኖዶስ ጉባዔ አባላት ድረስ «የተሐድሶ»ን ዓላማ የተቀበሉና የደገፉ ሚሊዮኖች መኖራቸው ደስ የሚያሰኝ ነው። አንዳንዶች ቤተ ክርስቲያንን ለባዕድ ወረራ አሳልፎ የመስጠት ዘመቻ እንደሆነ አድርገው የሀሰት መለከት ቢነፉም «ከክርስቶስ በቀር ሌላ አዳኝ የለም፤ ለዘላለማዊ ሕይወት ዋስትና ያለ ክርስቶስ ሌላ ቃል ኪዳን ለማንም አልተሰጠም» የሚለው እውነት የወንጌል እውነት በመሆኑ በመጨረሻም አሸናፊ መሆኑ አያጠራጥርም። «ተሐድሶ» እምነትን ማደስ አይደለም። ተሐድሶ የተሳሳተውን የማስተካከል፤ የተጣመመውን የማረም፤ ስርዋጽ የገቡ እንክርዳድ ትምህርቶችን የመንቀል ዓላማ ያለውና በእስትንፋሰ እግዚአብሔር ላይ የመቆም ግብ ያዘለ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምስጢረ ሥላሴና በምስጢረ ሥጋዌ ላይ ያላት የአበው አስተምህሮ እንደ ምንጭ ውሃ የጠራ ንጹህ ነው። ሐዋርያት ባስተማሩት የወንጌል ቃል ላይ ተመስርታ መልስ መስጠት የምትችል ኩሩ ቤተ ክርስቲያን ናት። ከማንም የምትበደረው አስተምህሮ የለም። ነገር ግን መሠረቱንና የህንጻውን እድገት የሚንድ እንግዳና ወፍ ዘራሽ ትምህርት በኋላ ዘመን ጠላት እንክርዳድ ዘርቶባታል። ለምሳሌ ያህል «ዓለም ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አይድንም» የሚለው አስተምህሮ የድንግል ማርያምን ክብርና ብጽዕና የሚናገር ሳይሆን «ዓለም ድኅነት ስላልተፈጸመለት የርሷ አማላጅነት የግድ ነው» ከሚል ምንፍቅና የመጣ ትምህርት ነው። « ያመነ፤ የተጠመቀ ይድናል» የሚለውን ቃል ከመጻረር ወዲያ እንክርዳድ ዘር ይኖር ይሆን?
  «ማርያም ታማልዳለች» ማለት አንድ ነገር ነው። «ያለማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም» ማለት ደግሞ ሌላ ነገር ነው። ይህንና ይህን የመሳሰለ ብዙ ትልቅ ነገር አለ።
  ጽላትና ስለጽላት ያለው መጽሐፍ ቅዱሳዊው አስተምህሮ እንዳለ ሆኖ ጽላትን በገንዘብ መሸጥና መግዛት የእንክርዳዱ ዘር ውጤት ካልሆነ ምን ሊባል ይሆን? መቼም ሙሴ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጽላት ገዛ ካልተባለ በስተቀር በህጋዊ ደረሰኝ ከሚሸጠው ባሻገር በስርቆትና በኩብለላ ስለሚዘዋወረው ጉዳይ ዝም ማለት በራሱ በጠላት አዚም መደንዘዝ ነው።
  ይህንና ይህን የመሳሰሉ ሺህ እንክርዳዶችን መንቀስ ይቻላል። ተሐድሶ ማለት ምርጡን የስንዴ ዘር ትቶ እንክርዳዱን በመንቀል ንጹህ ማንነት መልሶ መያዝ ማለት እንጂ መሠረቱን ማፍረስ ማለት ባለመሆኑ «አባ ሰላማ» ብሎግና ሌሎች ጦማሪያን፤ ጸሐፊያን ሁሉም በያሉበት የሚያደርጉት መንፈሳዊ ተጋድሎ እግዚአብሔር የተናገረው የሚፈጸምበት ቀን የመድረሱ ምልክት በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ ነው።
  40 ዓመት ሙሉ በምድረ በዳ የመራቸው የእግዚአብሔር ድምጽ እየሰሙ፤ ያደረገላቸውን እያዩ፤ የተመረጡና የተለዩ ሆነው ሳለ ከቃሉ ወጥተው የራሳቸውን መሻት እያቀላቀሉ ስላስቸገሩት በበረሃ ቀርተዋል። ምን ጊዜም እልከኛ ልብ አጥፊ ነው።
  «ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት፥ አባቶቻችሁ እኔን የፈተኑበት የመረመሩበትም አርባ ዓመትም ሥራዬን ያዩበት በምድረ በዳ በፈተና ቀን በማስመረር እንደ ሆነ፥ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ» ዕብ3፤8
  አባ ሰላማዎች እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጣችሁ። በናንተ ያለው የእግዚአብሔር ኃይል አሸናፊ ነው።

  ReplyDelete
 4. I am one of Ethiopian single mom from Canada. My x boyfriend moved to Atlanta, became as priest. Is that posdible? I have one boy and two girls with him. He is Mk. His name is YAKOB.

  ReplyDelete
 5. 4 የጥፋት፣የሐሰት፣የውንጀላ፣ የክስ፣ የኑፋቄ፣ የስድብ፣ የዘለፋ፣ የአመፅ፣የቅሰጣ፣አመታት አቤት! ከንቱ እድሜ፣ የባከነ ጊዜ፣
  እናንተ ማንን ፈርታችሁ። ገና ትቀጥላላችሁ። ሰው እግዚአብሔርን መፍራት ካቆመ ከጥፋት ጎዳናው በቀላሉ እንደማይመለስ የታወቀ ነው። እስቲ ፈጣሪ ሰው ሆናችሁ እንድታልፉ በቸርነቱ ይርዳችሁ። ሌላ ምን ይባላል።

  ReplyDelete
 6. መናፍቃንና አባ ሰላማ ምን አገናኛቸው?January 6, 2015 at 12:32 AM

  አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ!
  አባ ስላማ የመናፍቃን ብሎግ ነው!!!!!!!!!!!!!!!
  ይህ ብሎግ የሉተራውያን (የመናፍቃን) ስለሆነ መቼም ቢሆን እውነት መጠበቅ የለብንም፡፡ ከኩርንችት በለስ አይጠበቅምና፡፡ መናፍቃን የራሳቸው ማንነት ስለሌላቸው እንዲሁም በስማቸው ስለሚፍሩበት በቅዱስ አባታችን ስም ተደብቀው መርዝ መረጨታቸውን ይቀጥላሉ፡፡የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ ነገር ግን ውስታቸው ነጣቂ ተኩላዎች ተጠበቁ እንዳለ ጌታ በወንጌል ስንዴውእና ዕንክርዳዱ እስከ ምፅዓት ድረስ አብረው እነዲኖሩ ጌታ ራሱ ይፈቅዳልና፡፡ ጌታችን መድሀኒታችንና አምላካችን እየሱስ ክርሰቶስ በማቴዎስ ወንጌል የሚከተለውን ለሀዋሪያት እንዳስተማራቸው ልብ ልንል ያስፈልጋል፡፡
  መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች። ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ። ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ። የባለቤቱም ባሮች ቀርበው። ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት ተገኘ? አሉት። እርሱም፦ ጠላት ይህን አደረገ አላቸው። ባሮቹም። እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን? አሉት። እርሱ ግን፦ እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም።
  ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን። እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ» ማቴ 13፤ 24-30
  አባ ሰላማ (ፍሬ ምናጦስ ከሳቴ ብርሃን) የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ መሆናቸውን እራሳቸው መናፍቃን እ ይመሰክራሉ፡፡ለመሆኑ መናፍቃንና አባ ሰላማ ምንና ምን ናቸው?

  ReplyDelete
 7. “በቅሎ አባትሽ ማነው ቢሏት ፈረስ አጎቴ ነው አለች”
  1. አለቃ ታየና መሠረት ስብሐትለአብ በይፋዊ ፕሮቴስታንትነታቸው በግልጽ በጉባኤ ተወግዘው የተለዩ ሰዎች ናቸው፡፡ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ “ሊቃውንት” የሚለው ቅጽል ቀርቶ “ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” የሚለው ቃልም አይነካካቸውም፡፡መቃብራቸውም የተፈጸመው ከአጸደ-ቤተክርስቲያን ውጭ ነው፡፡ስለዚህ እነሱ ጋር ያላችሁን የመንፈስ ቁርኝት አጽድቀንላችኋል፡፡ባይሆን ተሐድሶ ምናምን እያላችሁ ቃላት ከማሽሞንሞን እንደነሱ በገሀድ ካምፑን ተቀላቅልችሁ ውጊያውን በገሐድ ብታደርጉት ጥሩ ነው--ብሎግ ላይ አሸምቆ ነገረ-ዘርቅ እየቀላቀሉ አጓጉል ቆንጻይ ከመሆን!!
  2. ሁለቱ ሊቃውንት ግን እናንተ አባቶቻችን ትላላችሁ እንጅ እነሱ ቢያገኟችሁ ልጆቻችን የሚሏችሁ አይመስለኝም፡፡አለቃ ኪዳነወልድ እና መጋቤብሉይ ሰይፈሥላሴ ዮሐንስ እስከ መጨረሻው በኦርቶዶክሳዊት ሃይማት ጸንተው በክብር የተሸኙ ናቸው፡፡የጻፏቸው መጻሕፍትና በየጽሁፎቻቸው የሚጠቅሷቸው መጻሕፍት ምስክሮች ናቸው፡፡ተናጋሪዎቹ ቢሞቱም ቃላቸው አይሞትም፡፡ሕያው ነው፡፡የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቀንዲልነታቸውን ይመሰክራል፡፡ለዛ ነው የበቅሎዋን ተረት የምንተርትባችሁ!!
  3. እናንተ ግን እስከመቼ በኣባት እጦት እንደምትባዝኑ አላውቅም፡፡አንድ ጊዜ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን፣ሌላ ጊዜ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌን፣እንደገና እነ አቡነ መልከጼዴቅንና አቡነ ቴዎፍሎስን፣ቆይታችሁ አቡነ ጎርጎርዮስንና አቡነ ጳውሎስን፣አሁን ደግሞ ሰይፈንና ኪዳነወልድ ክፍሌን፣….ትባዝናላችሁ፡፡ከበረቱ የወጣ መንጋ ይሄው ነው!!ገና ትባዝናላችሁ!!አውሮፓ ላይ ራሷን ለዘመናዊነት ሽጣ እርቃኗን የቀረችው ቤተ-ፕሮቴስታንት ኢትዮጵያ ላይ ያንን አጓጉል የሊበራሊዝም ፍልስፍና የተጀቦነ በራዥና ከላሽ አደንዛዥ አስተምህሮ ዘርታ ስታበቃ ምድሪቱን ለሙት ፍልስፍና እንድታጋልጥ አንፈቅድም--እዛው!!
  4. አባት ፈልጉ--ከኢ/ያ ሳይሆን--ከእዛው ከአውሮፓና አሜሪካ!!ኋላቀር አባት ምን በወጣችሁ!!እናንተ እኮ ዘመናውያን ናችሁ!!ምን በወጣችሁ የሺህ አመታት ታሪክ ካላት ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ጋር የሚያታግላችሁ!!አዲስ ቤት ሥሩና ልክ ከሙስሊም ወንድሞቻችን ጋር እንደኖርነው ማኅበራዊ ኑሯችንን አንድ ላይ፤ቤተ-አምልኮአችንን ግን ለየብቻ አድርገን በመቻቻል እንኖራለን!!ከዚህ ውጭ “የኢኦተቤክ ተሐድሶ” የምትሉትን ምውት ፍልስፍና በዐውደምሕረታችን እንናገር ብትሉ ጉዳዩ በቃላት መቃወም ብቻ አይቆምም!!በመቋሚያም ይታገዛል እንጅ!!ያንጊዜ ደግሞ ዓለማዊውም ሕግ ከእኛ ጎን እንደሚቆም ካለፉት ዓመታት ተሞክሮዎች ትገነዘባላችሁ ብየ አስባለሁ!!ከተሞክሮው ካልተማራችሁም ከመከራው ትማራላችሁ--እንደነ ፅጌ ስጦታው!!

  ReplyDelete
 8. Ellllllllllllllll, Temesgen Getta!!!!!
  Enkuan Des Alachehu. Genna bezu Amet yihonachehual. Egziabeher Awaki newu.

  ReplyDelete
 9. ከሳሽ የተከሳሽን ልብ ቢያውቀው ፍርድ ቤት አይሄድም ነበ

  ReplyDelete
 10. ሻማ ይዘውልን ያበሉን ሻማው ሲያልቅ እኛን በሉን

  ReplyDelete