Tuesday, January 13, 2015

ይድረስ ለወንድሜ ለዳንኤል ክብረት

Read in PDF

እኔ ስሜ እገሌ እባላለሁ የተወለድሁት በጎጃም ክፍለ ሀገር ነው። እንደ ማነኛውም የቤተ ክርስቲያን ልጅ ገና የሰባት ዓመት ልጅ ሆኜ ነበር ቆሎ ት/ ቤት የገባሁት። በልጅነቴ የሀገሬ ቤተ ክርስቲያን መርጌታ ከሆኑት ከዬኔታ ሞገሴ ፍቅር እያገኘሁ አደግሁ። እናት እና አባቴ ጥሩ አሳዳጊዎች ነበሩ፣ ነገር ግን ባሀገሩ ባህል ትምህርት እንዲገባው በሚለው አስተሳሰብ ለምኜ እየበላሁ እንድማር ተገደድሁ። አባቴ በግ እንድጠብቅለት ነበር የሚፈልገው፣ እናቴም እንዲሁ። የኔታ ግን ቤተ ሰቦቼን እየመከሩ እንድማር አደረጉ። ቀን ፊደል አቡጊዳ፣ መልክተ ዮሐንስ ወንጌለ ዮሐንስ ከዚያም ዳዊት ጾመ ድጓ እየተማርሁ፣ ማታ ደግሞ የዘወትር ጸሎት፣ ውዳሴ ማርያም፣ አንቀጸ ብርሃን፣ መልክአ ማርያም መልክአ ኢየሱስ፣ ት/ኅቡአት፣ ውዳሴ ማርያም ዜማ፣ መስተጋብዕ፣ አርባዕት፣ አርያም፣ ክስተት፣ ሰለስት፣ ስብሐተ ነግሕ። ተማርሁ እነዚህ ሁሉ የቃል ትምህርት ናቸው ሌት ያለ መብራት ስለምንማራቸው በቃል የምንይዛቸው ናቸው።
 ይህ በእንዲህ እንዳለ እነዚህን ትምህርቶች አጠናቅቄ ገና ሳልጨርስ ከብፁእ አቡነ መቃርዮስ የምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዲቁና ተቀበልሁ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን ካጠናቀቅሁ በኋላ የኔታ መርቀዉኝ ጉልበት ስሜ ተሰናብቼ ቅኔ ቤት ገባሁ። ቅኔው ወዲያው ነበር የገባኝ። ሦስት ቦታዎች ላይ ከጉባኤ ቃና እስከ መወድስ ያሉትን ሞልቼ አራተኛው ቦታ ላይ አስነጋሪ ሆንሁ። በቅኔ አዋቂነቴ ባካባቢው ሊቃውንት ዘንድ አድናቆትን አትርፌ ነበር። የኔን ቅኔ ለመስማት የማያሰፈስፍ ሊቅ አልነበረም።

 ከቅኔ ቤት እንደተመልስሁ ወደ ዜማ ቤት ገብቼ አስቀድሜ የተማርኳቸውን የቃል ትምህርቶች እንደ ገና አጥንቼ ድጓ የተባለውን ረጅም ትምህርት ተማርሁ። አከታትየም ወደ አቋቋም ቤት ገባሁና መዝሙር፣ ክብረ በዓል፣ ወርኀ- በዓል፣ ጾም ቀለም፣ ለእመ ኮነ፣ አጠናቀቅሁ። ከዚያም ዝማሬ እና መዋስዕት ተምሬ መሪጌታ ሆኜ ተሾምኩ። በዚህ ጊዜ ጎርምሼ ነበር። እናትና አባቴ ሊድሩኝ እንደሆነ ስሰማ መጽሐፍ ሳልማር አልታሰርም ብዬ ወደ ሽዋ ተሻገርሁ። በአታ ገዳም አራት ኪሎ ገብቼ ብሉይ ኪዳንን ተማርሁ፣ ጎን ለጎንም ሐዲስ ኪዳንን አጠናሁ። የትምህርት ጥማቴ እየጨመረ ሲመጣ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብቼ በአራት ዓመቱ ሴሚናር ኮርስ መውሰድ ጀምርኩ። በዚያን ጊዜ አንድ የማህበረ ቅዱሳን አባል በጣም ወዳጅ ሆኖ ቀረበኝ፣ እኔም በጣም ወደድሁት፣ በትርፍ ሰዓቴ ውዳሴ ማርያም አንድምታ አስተምረው ጀምርሁ። እርሱ ግን ታቦት እየቀረጸ ይሸጥ እንደነበር ስላወቅሁ በተለይም ያቡነ ጎርጎርዮስ ታቦት ቀርጾ ሳየው ተቆጣሁ፣ በሲኖዶስ ያልተወሰነ ነገር እንዴት ላንድ ግለሰብ ታቦት ትቀርጻለህ? ብዬ ተቃወምሁት። ወጥመድ ውስጥ የገባሁበት ቀን ይህ ቀን!!!
 ይህ ወዳጄ ከኮልፌ እየተነሣ ወደ ማህበረ ቅዱሳን ቢሮ አምስት ኪሎ ሲመላለስ ነገር እንደሚያመጣብኝ አልጠበቅሁም ነበር። ወዲያውም በማላውቀው ሁኔታ መናፍቅ ተብየ ተከሰስሁ፤ አንተም ዳንኤል ክብረት የስማ ጽድቅ ጋዜጣ አዘጋጅ በነበርህበት ጊዜ እኔን ሳታውቀኝ ስሜን ጠቅሰህ በጋዜጣ መናፍቅ ነው ብለህ አወጅህ። ከዚያ ሰዓት ጀምሮ ሕይወቴ አደጋ ላይ ወደቀች፣ በቆሎ ትምህርት ቤት ውሻ ሲያባርረኝ፣ ባለጌ ሲገፋኝ፣ ቁንጫና ትኋን፣ ሲፈራረቅብኝ፣ ረሃብና ጥም ሲያሰቃየኝ ያደግሁ ሰው ነኝ። ተመርቄ እረፍት አገኛለሁ ስል ዕዳ አመጣህብኝ። ስማ ጽድቅን ያነበቡ ሁሉ ምራቅ ይተፉብኝ ጀመር፣ ከጓደኞቼ አብሮኝ የሚቆም ጠፋ፣ ስበላ ብቻየን፣ ስሄድ ብቻየን ሆነ ኑሮዬ፤ በመጨረሻም የቤተ ክህነቱን ባለሥልጣናት አሳምናችሁ ኖሯል ያለምንም ፍርድ ከት/ቤቱ ተባረርሁ። ዳንኤል አስበው እስኪ እንደ ድሮዬ ለምኜ አልበላ? የማፍርበት ዕድሜ ላይ ነው ያለሁት። በቤተ ክርስቲያን ያደግሁ እንደመሆኔ ደሞዝ መቀበል ሲገባኝ ያንተ ጋዜጣ ዋጋዬን አሰጥቶኛል።
  ምን ላድርግ ብዬ አሰብሁ፣ ሰዎችም አላስጠጋ አሉኝ፣ እሙንቱሰ ይጸልዑኒ በከንቱ እነርሱ ግን በከንቱ ጠሉኝ እንደተባለው ባልተጨበጠ ወሬ ተጠላሁ። ረሐቡም እየጸናብኝ ማደሪያም እየቸገረኝ ሲመጣ ስማአ ጽድቅን ጨምሮ ሌሎች ጋዜጦችን ማዞር ጀመርሁ። ስሜን ያጠፋችውን ጋዜጣ እየሸጥሁ ምሳዬን መብላት ችዬ ነበር። ማታ ማታ ያልሸጥኋቸውን ጋዜጦች በረንዳ ላይ አንጥፌ እተኛለሁ። ካልተቀደዱ በማግስቱ እሸጣቸዋለሁ። ማን ይረዳኛል? ዳንኤል? በዚያን ጊዜ አንተና ጓደኞችህ አምስት ኪሎ በሚገኘው የማህበረ ቅዱሳን ሆቴል አልጫና ቀይ ወጥ እየቀላቀላችሁ ትበሉ ነበር። እኔ ሳለቅስ እናንተ ትስቁ ነበር። ጌታ በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ይህን ነገር እንዴት ያየው ይሆን?
   ከላይ የተቀስኋቸውን የትምህርት ዓይነቶች ተንከራትቼ ተምሬ የበረንዳ አዳሪ ስሆን እንኳንስ ሊማሯቸው ስማቸውንና ቅደም ተከተላቸውን እንኳ የማያውቁ ሰዎች የቤተ ክርስቲያን ሰው በመምሰል እያሳዳዱን እንጀራ ይበሉብናል። ዳኛው ማን ይሆን? እያልሁ ሳዝን በከንቱ መገፋቴን ያዩ አንድ አስተዋይ ሰው ወደ ሀገረ ስብከቱ አስተዳዳሪ አቀረቡኝ። እኒያ አስተዳዳሪ እኔን ሲያዩ ያነቡትን እንባ አልረሳውም። ዓይኖቼ ወደ ውስጥ ገብተው አንጀቴ ታጥፎ በየወንበሩ ክልትው ስል ያየ እንዴት አያለቅስ? ቤተ ክርስቲያን ሃያ ዓመት ሙሉ አስተምራ ባንድ ጋዜጣ ምክንያት አውጥታ ስትጠለኝ እንዴት አያስለቅስ? ጌታ በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ይህን ነገር እንዴት ያየው ይሆን?
 ወደ ሀገሬ እንዳልገባ ስሜን በቤተ ክርስቲያን እሁድ ቀን ባንድ ቄስ አማካኝነት አቆሽሻችኋል። ቤተ ሰቦቼ ከዚያ ቄስ ጋር ደም ሊቃቡ ይችሉ ነበር። ጊዜ ይፍታው ብለው ዝም አሉ እንጂ። ዳንኤል ብዙ ለመማር ብዙ ለማደግ ያሰብሁትን ሰው የንጀራ ጉዳይ ብቻ እንዲያሳስበኝ አደረግኸኝ። ዋና ጸሎቴ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቼ በተማርሁት እያገለገልሁ እንጀራ የምበላበትን መንገድ ብቻ ማግኘት ነበር። እንዴት እንደጎደሃኝ አስበው። አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስሄድ የሚያስገባኝ ባለመኖሩ አምሳ ሳንቲም ለዘበኛ እየከፈልሁ እገባ ነበር። ስብከተ ወንጌል ክፍሉ ብር ያለኝ መስሎት እጅ እጄን እያየ ለረጅም ጊዜ አሰቃየኝ። በስንት መከራ አንድ ቤተ ክርስቲያን በሦስት መቶ ብር ተመደብሁ። የሥቃዬ ዘመን አበቃ ብየ ስጠበቅ በተመድብሁ ባመቴ ስሜን በጋዜጣ እንደ ገና አወጣኸው። ስማ ጽድቅ ጋዜጣን ማየት አልወድም እንደ ተናዳፊ ዕባብ ያህል ስለምፈራው ነው። ስማ ጽድቅ ጋዜጣ ሲዞር ሳይ እራሴን ያዞረኝ ነበር።
  አንድ ቀን አንድ ጓደኛዬ የማታ ፕሮግራም ጋብዤው መጥቶ አስተምሮ ከጨረሰ በኋላ እስከሚሳፈርበት ፌርማታ ድረስ ልሸኘው ተከተልሁት። ዳንኤል ክብረት አለቀቀህም? አይደል? አለኝ ለመሆኑ ያውቀሃል? ሲል ቀጠለ። ምን ነው ደግሞ ምን አመጣ? አልሁት። ስምህን ስማ ጽድቅ ጋዜጣ ላይ አላየኸውም? እንዴ መናፍቅ ብለው አውጥተዋል እኮ! ሲለኝ? ከቆምሁበት ላይ ተዝለፍልፌ ወደቅሁ። ጓደኛዬም እኔን ተሸክሞ ወደ ቤቴ ተመለሰ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለሁለት ወር ያህል ታምሜ ተኛሁ። በዚያን ወቅት እውቀቴ እንጂ እምነቴ ደካማ ነበር። የሰንበት ተማሪዎች ስማ ጽድቀን አንብበው ኖሯል ምንም ሳይጠይቁኝ አባረሩኝ፣ ለአንድ ዓመት ያህል ሳስተምራቸው ያደንቁኝ የነበሩት ሁሉ ስማ ጽድቅን ሲያነቡ ይደቀድቁኝ ጀምር። ስማ ጽድቅ ስላነበቡ እንጂ እኔ ምን እንዳልሁ መረጃ አላገኙም። ዳንኤል መናፍቅ ነው ስላለ ብቻ መናፍቅ ነው ተባልሁ። ጌታ በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ይህን ነገር እንዴት ያየው ይሆን?
  ከቤተ ክርስቲያን ወጥቼ የት ልሂድ? ሌላ ቤተ ክርስቲያን አላውቅ? ሁሉንም ትቼ የቀን ሥራ እየሰራሁ ዘመናዊ ትምህርት ልማር አልሁና ወደ አቃቂ ሄጄ ስሚንቶ ማቡካት ጀመርሁ። ከዚያም የማታ እየተማርሁ ባጭር ጊዜ አንደኛ እየወጣሁ ሰበተኛ ክፍልን አጠናቀቅሁ። እግዚአብሔር ግን አልተወኝም፣ ታምሜ እንዳልሞት፣ እንዳልድን ሆንሁ። አይ ያ ጊዜ አንድ ዳቦ የሚሰጠኝ ያጣሁበት ጊዜ እንዴት የሚያስፈራ ነበር? በዚህ ጊዜ አንድ ነገር ገባኝ እግዚአብሔር ስለስሙ መከራ እንደቀበል እንጂ ኑሮ ተመችቶኝ ዓለማዊ እንድሆን እንደማይፈልግ ተረዳሁ። ሆኖም በእምነት የበሰለ ሰው አግኝቶ እስኪረዳኝ ድረስ እምነቴ ጠንካራ አልነበረም። ከዚህ በኋላ እስኪ ዳንኤል የሚተወኝ ከሆነ፣ ሰውም የማያገለኝ ከሆነ ልመንኩስ ብየ መነኮስሁ። እኔ ማግባት እንጂ መመንኮስ አልፈልግም ነበር። ማህበረ ቅዱሳን መነኩሴ ይወድ እንደሆነ ብዬ አደረግሁት? እውነትም መከራው ቀነሰልኝ ጌታ ግን ይህን አካሄዴን አልወደደውምና ደስታ የለኝም። በመሠረቱ እኔ ግፍን ስቀበል ተሐድሶ አልነበርሁም ተሃድሶ የተባልሁበት ነገር ምንድን ነው? ብዬ ሳጠና ግን ተሐድሶ ሆንሁ። ጌታ ያንን ሁሉ ግፍ እንድመለከት ያደረገኝ ለካ ተሃድሶ እንድሆን ነው። እንዲህ ዓይነቱ የግፍ ሥራ እንዲቆም የማይመኝ ማን አለና?
 ወንድሜ ዳንኤል ሆይ!አንተ በክብር በዝና በብልጽግና እየተጨበጨበልህ እየኖርህ ነው። ግን በዚህ ነገር ንስሐ ግብተህ ይሆን? ወይስ ረስተኸው ይሆን? ስንት ያልታበሱ እንባዎች እንዳሉ ታውቅ ይሆን? ሕይወታቸው የተጎሳቆለ፣ የተሰደዱ የተገደሉ፣ አንገት የደፉ፣ የተደበደቡ፣ ከቤተ ሰባቸው የተፈናቀሉ ስንት እንዳሉ ታውቃለህ? አንተ እኔን ከጨዋታው ሜዳ ገፍተህ አስወጥተህ አንተ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ስትባል በየትኛው ህሊናህ ተቀበልኸው? ጌታ በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ይህን ነገር እንዴት ያየው ይሆን?
 አይ አንቺ በርባንን እየፈታሽ ክርስቶስን የምትሰቅዪ የይሁዳ ዓለም?! ጌታ በመጣ ጊዜ የሚያድንሽ የለም።
ስሜን ከመጽሐፌ ላይ ታገኛላችሁ ታሪኬን እየጻፍሁ ነው። አሁን ስሜን ብነግራችሁ ለስማ ጽድቅ እጋለጣለሁ ጥቂት ጊዜ ተውኝ እባካችሁ። ታሪኬን ሳልጽፈው መሞት አልፈልግም።

78 comments:

 1. betam yemigerem newu Yatenahwune ena Ytemarekewu yetemherte bezate Yemkgerem newu wendeme enem endantewu tehadeso tebye kebete kerestian tegefeche yewetahu wenbemih negn ,degemome endante temeryalehu gene Yeadisu kidan liqe kahen gebetohal weye ? ayzoh geta yeredahal gin keresetosene nurewu enji lenjera atenure,

  ReplyDelete
 2. yasznal amlak brtat ysth wendme

  ReplyDelete
 3. So Daniel Kibret was right to expose you. You talked a lot and finally you accepted that you are Tehadiso. Yihe endante ayinetu bekurat yemitemesekirulet ...tehadiso yemibal ye protestant wing....eskaltefa direse Danile Kibretim hone lelawu MK memeber enkilf yelewum. You talked a lot and gave a lot of detail, and finally gave evidence about why Danile talked about on the news paper. Sima Gojam gin tehadiso ale elnde? eskahun sint sew asitehal? Cheers!

  ReplyDelete
  Replies
  1. sema ye Daniel Kebret adnaki,be alem fetsame chaf lay honeh sele Orthodoxena seletehadeso taweraleh...please start your mind gears!This is the last moment...Leju yalew yiwot alew..beka be Kirstos betederegeleh free gift lemedan kefelek ok...alebeleziya ...yante Orthodox/pente or any.. mehon alemohone lay aydelem...please when you stand before the judge of the Lord,you won't stand by your "Religious" group or noone will defend to you...you yourself will answer what your faith just was on the Lamb of God Jesus.Other than this....everything is fables!

   Delete
  2. hiywetun ema lesatnael esetalehu bilual yihe menafik ere yigermal gojjam new yeteweldhut wey defar gojjam endante yale manda/kehadi sew atabeklm

   Delete
 4. TULTULA HULU, TAWORALACHIHU AYIDEL. YIH YEFETERA SIRA KEMESELACHIHU COPY RIGHT TEYEQUBET.

  ReplyDelete
 5. አምላክ ይርዳህ ዳንኤል ሆይ አምላክን የምትፈራበትን ንስሀ የምትገባበትን ህሊና ያድልህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ayzoh deacon daniel gena gena yasabidhal

   Delete
 6. ለተረት ተረቱ የላም በረት ብለናል!

  ReplyDelete
 7. ወዳጅ እገሌ የምትለውን ለማመን በ2 ምክንያቶች እቸገራለሁ፡፡
  1-- መገፋት ሃይማኖትን ለመቀየር ምክንያት ሊሆን ይገባዋል ብየ አላምንም፡፡የነቢያት፣የሐዋርያት፣የሊቃውንት፣የሰማዕታትና የጻድቃን የተጋድሎ ታሪክም ያንን አይነግረንም፡፡እንደሱ ከሆነ ነገ ተሐድሶዎች ሲገፉህ ደግሞ ሙስሊም ልትሆን ነው ማለት ነው??!!ለሥጋህ ካልደላህ እምነት ላይኖርህ ነዋ!!በል እንካ ይችን የአባቶች ጉባኤ ቃና…
  ይትወላወል ሰብእ፡ልበ - ፈሪሳዊ ቀሊል፣
  እምጊዜ-ልደቱ ኦሪት፡እስከ-ጊዜ-ሞቱ ወንጌል፡፡
  2-- ጽሑፉ የምትለውን ያክል ስለመማርህ የሚገልጽ ሆኖ አላገኘሁትም--በጉባኤ ቤት የሚሰጡትን የትምህርት አይነቶች ሸምድዶ ከመደርደር በቀር!!ጥልቀት ከማጣቱም በላይ “ስምዓ-ጽድቅ” የምትለዋን ከግእዝ ዘይቤ የተቀዳች ጋዜጣና አንተ ራስህም አዞርኳት የምትላትን “ስማ ጽድቅ” እያልክ እንደመሃይምን መጻፍህ በጉባኤ ቤታችን ስለማለፍህ እንድጠራጠር አድርጎኛል፡፡ተልሚድ (እግረ-ተማሪ፡-አንዳች እውቀት ሳይዝ ዝምብሎ ጉባኤ ቤቶችን የሚያዳርስ) የሚል ማእረግ እንኳ ለመስጠት አጻጻፍህ አልስቻለንም፡፡
  እንደማስገንዘቢያ--2 ነገሮች!!
  1-- ማኅበረቅዱሳን ማስረጃ እያሰባሰብ በተሐድሶ ሥም የኢኦተቤክ ላይ ፕሮቴስታንታዊ አመጻ ለማምጣት የሚጥሩ ግለሰቦችንና ቡድኖችን በቅ/ሲኖዶስ ለማስወገዝ ቀደም ሲልም ሆነ አሁንም የሚያደርገውን ጥረት ያለምንታዊ ከሚደግፉት ወገን ነኝ--በሙሉ ልቤ!!ነገር ግን በግልጽም ሆነ በኅቡዕ ልሳናቱ ሥሙን በቅሬታ ባነሱ ወገኖች ላይ ሁሉ ሥያሜውን በራሱ ሥልጣን እየለጠፈ ማሳደጃ ማድረጉን አልደግፍም፡፡ጥፋት ነው፡፡ፕሮቴስታንታዊነትን በመመከት ረገድ ያለውን ትግል “የተለመደ የማኅበረቅዱሳን ክስ” በሚል ማደናገሪያ ተጠርጣሪ መናፍቃን ጊዜ እንዲገዙ በር እንዳይከፍት ስለምንሰጋ መረን የለቀቀ ግዝት-ዘበከንቱ ከቶም አንደግፍም፡፡ለጊዜው በብዙኃን ድምጽ ብንታፈንም ይህን አቋማችንን ያቅማችንን ያህል በየኅቡዕ ልሳናቱ እየገለጽን ነው--ከነግዝት ትርጓሜና ብያኔው!!በተለይ ያልተወገዙ ሰባክያንና ዘማርያንን እንደተወገዙ እያስመሰሉ አባላቱ በማኅበራዊና በኅትመት ሚዲያው የሚያራምዱት አቋም የቅ/ሲኖዶስን ሥልጣን የሚጋፋና ማዕከላዊነትን የሚጻረር፣የምዕመናን ልብ የሚከፍል፣ተቋሙን የሚፈታተን፣መንፈሰ - ቀሊላን ሰባክያንና ዘማርያንን ወደ ፕሮቴስታንት ካምፕ የሚገፋፋና እንኳንስ የእናንተ ነው ተብለው ያልተባለውንም የኛ ለሚሉት ቀሳጥያን ሲሳይ የሚዳርግ ዝርው ድርጊት በመሆኑ ደጋግመን ኮንነነዋል፡፡ድርጊቱ እስካልታረመ ቅሬታችንን ከመግለጽ አንቦዝንም፡፡ግዝት/ውግዘት የራሱ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓት አለው!!ሥርዓቱን እንጠቀምበት!!
  2-- በሌላ በኩል ይህን የማኅበረቅዱሳን አካሄድ ማኅበሩ የኢኦተቤክ አካል መሆኑን ተቀብሎ እስከ ቅ/ሲኖዶስ ድረስ በይግባኝ በመሄድ እንዲታረም ለማድረግ ከመጣር ይልቅ ማኅበረቅዱሳንን ለመበቀል ብሎ ማዕተብን በጥሶ የተሐድሶ ብሎጎች ማድመቂያ መሆንና ማኅበር አሳቦ ቅድስት ተዋሕዶ ላይ የውጹአንን አጀንዳ ተሸክሞ መዝመት ስርየት የሌለው በደል በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ መፈጸም ነው፡፡ጥምቀቱ፣እምነቱ፣ትውፊቱ፣ትርጓሜው፣ጉባኤው፣የቅ/ያሬድ ጸዋትወ-ዜማዎች፣ገድለ -ቅዱሳን፣ሥርዓቱ፣ዶግማው፣ቀኖናው፣….ማኅበረቅዱሳን ያመጣቸው አይደሉም፡፡ሳይመሰረት ነበሩ፡፡አሁንም አሉ፡፡ባይኖርም ይኖራሉ፡፡ለሺህ አመታት አብረውን የኖሩ ናቸው፡፡ስለሆነም ማኅበረቅዱሳንና ዳንኤል ክብረትን ሰበብ አድርጎ ከተዋሕዶ መንጋ ራስን መነጠል በብስለት ማጣትና የኢኦተቤክንን ታሪክና ትውፊት ባለማገናዘብ እንጅ በሌላ ሊተረጎም አይችልም፡፡ከሀዲ የሚባለው እኮ ምቾቱን ከሚያምንበት ያስቀደመ ነው፡፡ስለዚህ በማኅበረቅዱሳንና በዳንኤል የተነሳ ምቾት አጣሁ ብሎ እምነቱን የጣለ ሰው በዚህ ትርጓሜያችን ሊጠቃለል ግድ ነው፡፡
  በነገራችን ላይ ይሕን ጽሑፍ የጻፍከው ግለሰብ ከጠቀስካቸው የሕይወት መንገዶችህ በመነሳት ማን ልትሆን እንደምትችል በህሊናየ ገምቼሀለሁ፡፡ግምቴ እውነት ባይሆን ደስ ይለኛል፡፡ስላለፈ ትውውቃችንና ስለ ሀገር ልጅነታችን ስል አንተ ባትሆን ደስ ይለኛል!!በበኩሌ ከእልህ ጎዳናህ ተመልሰሃል ብየ ነው የማምነው--ለማመኔ ምክንያት አለኝ!!ባንተ ላይ ያለኝን እምነት አፍርሰህ ይሕን የጻፍከው አንተ ከሆንክ ግን ማዘኔ አይቀርም!!ብቻ አንተ እንዳትሆን እጸልያለሁ!!

  ReplyDelete
 8. አይ ዳንኤል ግፍህ ብዙ ነው ተንሥኡ ና ጸልዩ ብለህ መቀደስ የማትችል መተኪያ የሌላቸውን የቤተ ክርስቲያነ ልጆች በላሀቸው ስንቱ አዘንብህ ? እባክህን ንስሀ ግባ ?
  ከባህር ዳር ጅምሮ የወለድህላት ሴት ፡ የሊቃውንቱ ፡ የካህናቱ ፡ የመነኰሳቱ ና የደቀ መዛሙርት
  እንባ ና ደም ይከስሀል ፡ ፡ ከምንጩ የተማሩትን ሊቀውንትን እየሳደድህ አንተ ኬክህን እየበላህ በየትኛም የቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ሳትማር ትንሽ በማንበብህ ሊጡ ሊቅ ተባልህ ቤተ ክርስቲያኒቱንም የወላድ መካን አደረግሀት

  ይህ መልዕክቴ ለኣንተ ና ለግበረ አበሮችህ ለ ማ/ቅ ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. indet tenagrehal! bakh? inadantem ayinet lik iyalen newu ye danielin metsahift yeminanebewu? be iwunet bagegnih daniel kemibelawu kek agorsih neber! miskin!

   Delete
  2. atalqisu eshi maMUSHU. ENE ERIR LIBELILIH.

   Delete
 9. "አባ" ሰላማ ትቀባጥራላችህ አይደል? አይ አንች ቤተክርስትያን!!!

  ReplyDelete
 10. hahha, which edition of 'sima tsedik'. ???

  ReplyDelete
 11. Ahzenuni Lite Ardite Ziaye Kifti,
  Isme Adnenu Riisomu Begubae Kana Alekti..

  ReplyDelete
 12. wendeme melsun eko antewe meleskewe tehadesu kehoneke esu idelehem endelehe new yefelekewe lemen tenekabege yemeslale

  ReplyDelete
 13. daniel tegrmahlehe sentune aswgezeke sentune asdbdbke

  ReplyDelete
 14. What a horrible story. metshafihin le manbeb chekolku. Ebakachihu ke church atiwutu tiyakachinin yemimelisilin latan orthodoxawyan yalachihus meftihie mindin new?

  ReplyDelete

 15. ማን ይረዳኛል? ዳንኤል? በዚያን ጊዜ አንተና ጓደኞችህ አምስት ኪሎ በሚገኘው የማህበረ ቅዱሳን ሆቴል አልጫና ቀይ ወጥ እየቀላቀላችሁ ትበሉ ነበር። እኔ ሳለቅስ እናንተ ትስቁ ነበር። ጌታ በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ይህን ነገር እንዴት ያየው ይሆን?

  ReplyDelete
 16. አንተ እኔን ከጨዋታው ሜዳ ገፍተህ አስወጥተህ አንተ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ስትባል በየትኛው ህሊናህ ተቀበልኸው? ጌታ በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ይህን ነገር እንዴት ያየው ይሆን?

  ReplyDelete
 17. በህይውቴ ከአዘንሁባቸው በላይ ይህን ታሪክ ሳንብ በጣም ውስጤ አዝኗል አይ ዳንኤል የምትደርገውን የማታስተውል ሰው ነህ

  ReplyDelete
 18. Egna ye-cherkos- sefer legoche lemen semehen anenegrehem.Tsige Setotaw nehe -or Tsige equivalent.U are a strategic leader of Tehadeso network in kirkos atbia & other Eotc churches.Betam dekama behonut bene Hailu bekul awkenacehual. We blocked u in the Name of Christ.But ur writing skill is so good .i appreciate.so ,why u are trying to write Like Dn.Daniel(a very respected person by his general contribution to our nation) .This is the right way to be Dn.Daniel,Not Tilacha.ጌታ በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ይህን ነገር እንዴት ያየው ት ያየው ይሆን? yanten yewndemen telacha ,seme-matefat,mesadeb,mamtatat,mesrenet,ጌታ በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ እንዴት ያየው ይሆን?sewen-balseraw-sera-mekses,asmesaynetehen,ጌታ በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ እንዴት ያየው ይሆን?seytanawe kenatehen,mekegnetehen,አልጫና ቀይ ወጥ እየቀላቀላችሁ ትበሉ ነበር Abet telacha,aynehe dem lebese ጌታ በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ እንዴት ያየው ይሆን?..Yecherkos legoche BETAM AWEKNACHU.U DID NOT STAND FOR TRUTH.

  ReplyDelete
 19. የብራዘር ሁድ ደጋፈዎች እና ማህበረ……፡፡እዉነት ነዉ ማህበረ ቅዱሳን ሳይሆን ማሀበረ ……… ነዉ ዳሹን እናነተ ሙሉት ፣ወገን ማህበረ ቅዱሳን ፣ማህበረ ቅዱሳን ተብሎ መጠራትም መባልም የለብህም እንላለን ምክንያቱም ‹መልከጥፉን በስም ይደግፉ››እንዲሉ ነዉ ይህ ማለት ፍጡርን በፈጣሪ ፣አምላኪዉን ተመላኪ፣ እንዲሆን በሰይጣን ድግምንት እና በአስማት ‹‹በአዉደ ነገስት›› የሚመራ ለቤተክርስትያናችን የመርገምና የመለኮታዉ ጉብኝት እንቅፋት የሆ አሸባሪ ድርጂት ነዉ መተት በንጹሀን ምእመናን እየመተተ የአዚም መጋረጃ የደረገ ፣ የመዳንን መንገድ የዘጋ ነፍሰ ገዳይ ድርጂት ነዉ ልብ በሉ ‹‹ስጋ ገዳይ አላልኩም ›› ማህበረ …….አረስንቱ እስኪ ልጠይቃችሁ መልሱልኝ ስለማሪያም በግእዝ የተባለዉን ‹‹ንኡ ንስግድ ወንግነይ ላቲ ለመድሐኒትነ ማርያም ድንግል፣እስመገብረት አበይተ ብርሃናተ ባህቲታ›› ይላል ትርጉም ብቻዋን ታላላቅ ብርሀናትን ፈጥራለችና ለመድሃኒታቸችን ለድንግል ማሪያም እንሰገድላት እንገዛላትም› ማለት ነዉ ይህን ማለት ምን ማለት ነዉ ማነዉ የሰማይ ብርሀናትን የፈጠረዉ ? መድሀኒታችንስ ማነዉ? ነገሩ ማህበረ ቅዱሳን ማለት የሰንበት ተማሪ እንጂ በየትኛዉኛ የአብነት ትምህርት ቤት ገብቶ ይማርእና ፡፡ አንባቢወች ደግሞ ሁሉን ከነቀፌታ አንጻር ብቻ አንመልከተዉ !!!! አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. I agree 100% with you. MK is the other image of brotherhood.

   Delete
  2. True, mk is mahebere Seytan.

   Delete
 20. You simply accused Daniel and it is not fair
  How do Daniel and Mahibere Kidusan do all this with out looking something wrong from your side. After all you yourself confessed that you spent all your life in church education to enjoy your latter life. I think this is not right. As far as you entered to it, your prim objective should be to serve the church. Every thing you are claiming seems wrong to me.You better comeback to your sens
  God Bless you

  ReplyDelete
 21. My name Banchi, I came from Ethiopia at age 10. Now, I am 16 years old. My mother sleeping with one priest his name is Komoss Melakhiwot Ergetkal. I feel shame and guilty. I will call police next time when he came to our house. I stop to participate on his church any more. What is your advice abaselama?

  ReplyDelete
  Replies
  1. In which city are you living? In Ottawa Mar....

   Delete
 22. My question to you is "have you forgiven Dadiel Kibret or are you still bitter against him" You better forgive him for you own sake.
  Christ Jesus teaches us to forgive those that offend us.

  ReplyDelete
 23. በእውነቱ በጣም አሳዛኝ ታሪክ ነው፣ ግን እንደው ሚዛናዊ እንድንሆን ሰውንም ያለሃጢያቱ እንዳንከስ በየትኛው ጊዜ በየትኛው ዓመተ ምሕረት በስምዓ ጽድቅ ላይ እንደወጣ የተባለው ጽሁፍ ምናልባት አንባቢያንን ይበልጥ ሊያሳምን ይችላል። ይሄ ሊፈጸም አይችልም እያልኩ እንዳልሆነ ልብ ይበሉልኝ ውድ ጸሐፊ፣ነገር ግን ጊዜውን ቢጠቅሱ ጊዜው የቴክኖሎጂም አይደል እነዛ ስምዎን የጠፉበትን ጋዜጦች ማግኘት የሚቻል ይመስለኛል ስለዚህ ጊዜውን በግልጽ ቢጽፉት፣ ያገለግሉበት የነበረበትን ቤተክርስቲያን ቢገልጹ በዚህ መሰረት ጉዳዩን በጥልቀት ልንመለከተው እና ለተፈጸመብዎት ጥፋትም ተከሳሹ አስፈላጊውን ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣትን ሊያገኝ ይገባዋል የሚል እምነት አለኝ፥ ምክንያቱም ባልተጨበጠ ነገር አንድ ሰው ተነስቶ የሰውን ስም እንዲህ አጥፍቶ አንገት አስደፍቶ በተጨማሪ በእርሶ ላይ የደረሰውን ማኅበራዊና አካላዊ ቀውሶችን አድርሶ ዝም ብሎ ሊታለፍ መቻል የለበትም ከሚሉት ወገን ነኝ።
  ስለሆነም እርሶ የተጠየቁትን ነገሮች ለአንባቢያን ይፋ ቢያደርጉ፣ አንባቢያንም እነዚህ የተባሉትን በደሎች በተፈጸሙበት ጊዜ የተጻፉትን ስምዓ ጽድቅ ኮቢ አድርገው ለአንባቢያን ቢያደርሱ ትክክለኛ እና ሚዛናዊ የሆነ ፍርድ አንባቢያን ይሰጣሉ ብዪ አምናለሁ አለበለዚያ ግን ጸሐፊው ጥሩ ደራሲ ነውት እንዳይስብሎት እያልኩኝ ጽሑፌን አጠቃልላለሁ
  ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
 24. ጽሑፉ የምትለውን ያክል ስለመማርህ የሚገልጽ ሆኖ አላገኘሁትም--በጉባኤ ቤት የሚሰጡትን የትምህርት አይነቶች ሸምድዶ ከመደርደር በቀር!!ጥልቀት ከማጣቱም በላይ “ስምዓ-ጽድቅ” የምትለዋን ከግእዝ ዘይቤ የተቀዳች ጋዜጣና አንተ ራስህም አዞርኳት የምትላትን “ስማ ጽድቅ” እያልክ እንደመሃይምን መጻፍህ በጉባኤ ቤታችን ስለማለፍህ እንድጠራጠር አድርጎኛል፡፡ተልሚድ (እግረ-ተማሪ፡-አንዳች እውቀት ሳይዝ ዝምብሎ ጉባኤ ቤቶችን የሚያዳርስ) የሚል ማእረግ እንኳ ለመስጠት አጻጻፍህ አልስቻለንም፡፡

  ReplyDelete
 25. ጽሑፉ የምትለውን ያክል ስለመማርህ የሚገልጽ ሆኖ አላገኘሁትም--በጉባኤ ቤት የሚሰጡትን የትምህርት አይነቶች ሸምድዶ ከመደርደር በቀር!!ጥልቀት ከማጣቱም በላይ “ስምዓ-ጽድቅ” የምትለዋን ከግእዝ ዘይቤ የተቀዳች ጋዜጣና አንተ ራስህም አዞርኳት የምትላትን “ስማ ጽድቅ” እያልክ እንደመሃይምን መጻፍህ በጉባኤ ቤታችን ስለማለፍህ እንድጠራጠር አድርጎኛል፡፡ተልሚድ (እግረ-ተማሪ፡-አንዳች እውቀት ሳይዝ ዝምብሎ ጉባኤ ቤቶችን የሚያዳርስ) የሚል ማእረግ እንኳ ለመስጠት አጻጻፍህ አልስቻለንም፡፡

  ReplyDelete
 26. egzihabier libona yisth endzih kala astesaseb yisewren amlakachn medanitachn eyesus kirstos kfu menafst yalebachwn sewech endaante yalewn keziya yikellen enji enima min elallew temeles temeles temeles wodebieth giba???????????(********* tewahdo haymanotie alfrebetm new kuratie tewahdo haymanotie alfrebetm new kuratie tewahdo haymanotie alfrebetm new kuratietewahdo haymanotie alfrebetm new kuratietewahdo haymanotie alfrebetm new kuratie tewahdo haymanotie alfrebetm new kuratie***********************")

  ReplyDelete
 27. ዳኒ እንዳዉ ጌታ እድሜና ጤና አብዝቶ ይሰጥኽ እንዲኽ ያለዉን ተሀድሶ መድረሻ አሳጣልን አንተም ወንድሜ ልቡና ይሰጥኽ በሰበቡ መፀሐፍ አወጣለዉ ብለኽቢዝነሰ ለማሰተዋወቅ ነዉ ሚመስልብኽ

  ReplyDelete
  Replies
  1. dan endow gta edmana tma abzeto ystlen thads medresh asatalem

   Delete
 28. why you hide your name?
  Tell us who you are then we know who you are.
  Abaselama we are not kids.

  ReplyDelete
 29. አንዳንዶች በአስተያየታቸው በሰው ላይ ሲፈርዱ አያለሁ። በጭንቅና በመከራ መያዝን ያልደረሰበት ሰው እንዴት ሊረዳው ይችላል? እንኳን የቆሎ ተማሪ የነበረ ሰው ይቅርና ሐዋርያትም ረሀብ ሲጠናባቸው «እምነ ረሀብ ይኄይስ ኩናት» ማለታቸውን አባቶች ደጋግመው ይናገራሉ። «ከረሀብ ጦር ይሻላል»ማለት ነው። በግል የምናውቃቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ያለአንዳች ምክንያት ስማቸው ጠፍቶ ተሰደው የቀሩ አሉ። አንዳንዶቹም በዳኅፀ ልሳንና በእምነት ድክመት እየተወነጀሉ የስደት ሰይፍ አርፎባቸዋል። «በማንኛቸውም በደል ቢገኝ እንኳን በእምነት የደከመውን በየዋህነት መንፈስ አቅኑት» ገላ 6፤1 የሚለውን የወንጌል ቃል ሽረው በጋዜጣና በጉባዔ እየለቀለቁ አስደንብረው ገደል የከቱት ስፍር ቁጥር የለውም። ሊቃውንቱ ሲገፉ፤ ሲናጡ፤ የትንቢተ አባት ዛሬም ዲያቆን ይባላል።
  እስክንድሮስ የተባለ ሰው ሐዋርያው ጳውሎስን መከራ ሲያበዛበት እንዲህ ብሎት ነበር። «የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ እጅግ ከፋብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይመልስለታል» 2ኛ ጢሞ 4፤14
  ዳንኤልም የእጁን ማግኘትህ አይቀርም። ሳታውቀው የበደልከውን ሰው ፈልገህ ይቅርታ ጠይቀው! ንስሐም ግባ!

  ReplyDelete
 30. An interesting TIWONA and Gobez TEWANAY. By the Way Deaniel alone has nothing to do with SIMEA TSIDK. It is MK as a whole and we all support these TEHADISO to be eradicated from our church. If u learn all the listed church lessons,...u know what to do. But now Tehadiso, next Paster etc...

  ReplyDelete
 31. ጌታ ይየው እንጂ፣ ዳንኤልማ ምን ኅሊና አለው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተም ህሊና አለኸ ተረት ተረት እውነት ነው ብለህ የተቀበልህ። መጽሐፍ ቅዱስ አንብቡ በማለት ለሰይጣናዊ ማንነታችሁ መሸፈኛ ማናፋት አይደለም የመጽሐፉን መልዕክት በማስተዋል እንጂ።

   Delete
 32. መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንዲሉ ይኼ ነፍሰ ገዳይ ማህበር የተመሰረተዉ እንግዲህ እንደነ ዳንኤል ክስረት ባሉ ህሊና ቢሶች ነዉ፡፡ አይ ዳንኤል ሰዎች ያለበቂ ምክንያት በሚጠሉበትና በሚሞገሱበት አገር ላይ ሆንክና አንተም ሊቅ ተብለህ በኢቲቪ ሳይቀር የታሪክ ተመራማሪ የሚል ካባ ተደርቦልህ እያየን ነዉ፡፡ ሰዉ በዚች ምድር የሚኖረዉ አንዴ ነዉና ስለምን ከህሊናህ ተጣልተህ እንደምትኖር አይገባኝም፡፡ ዛሬ አንተ ምሁር ተብለህ የራስህን ብሎግ ከፍተህ የምትደርታቸዉን የተረት መጻህፍት ታሻሽጣለህ ባንተ ምክንያት ግን ስንት የቤተክርሲቲያን ልጆች ተሰደዋል፡፡ ዳንኤልን የስራህን ይስጥህ ከማለት በቀር ምን ማለት ይቻል ይሆን?

  ReplyDelete
 33. you are the real example of devil stupid. some one who wanted to see Devil can see you and know what it look like. it is clear that you ae the reporter of it.

  ReplyDelete
 34. ያለ መረጃ እንኩዋን በጋዜጣ በየትኛዉም መልኩ መናፍቅ አትባልም፡፡ ስምህን ንገረን እና የተሀድሶነትህን ምክንያት ከማህበሩ እንጠይቅ፡፡ አለበለዚያ ልቦለድ ድርስት የሚመስል እና በመዋጮ የተፃፈ ትረካችሁን ይዘን የምትፈልጉትን የቁርጥ ቀን ልጆችን እና ዉድ ወንድማችን እና መምህራችንን ዳንኤልን አንጠላም፡፡ ሴራችሁ ገብቶናል ራሳችሁን ምሁር እና የቤተክርስቲያን ተቆርሪ ለማድረግ አትሞክሩ፤ ቤተክርስቲያን አትታደስም!

  ReplyDelete
 35. ተረት የፈጠራ ወሬ ሕይወት አይደለምJanuary 16, 2015 at 8:40 PM

  ተረትና ሐሰት የፈጠራም ልቦለዶች እንደወንጌል እንደ ሕይወት ተቆጥረው ሲሰበኩ ሲተረኩ በአባ ሰላማ ብሎ አየሁ። ይገርማል ድሮ በፕሮቴስታንት አዳራሾች ነበር የፈውስ አገልጋይ ተብዮዎች ጌታ ነገረኝ ይሔን ጉባኤ ሊያውክ የመጣ መንፈስ አለ አሁን ይወጣል እጅ ለጅ ተያያዙ እየተባለ በአዳራሹ የተኮለኮለውን ለመሸንገል የሐሰቱ መንፈሰ የሚያውጀው። የሚገርመው እውነተኛው ጌታ ተናግሮ የማያደርግ ይመስል እጅ ለጅ ተያያዙ ይባልልኛል። ሌላም ብዙ የሚባሉ የፈጠራ ተውኔቶች በፕሮቴስታንቶች አዳራሽ ሲተወኑ ተመልክቻለሁ። በአንድ ወቅት በሙሉ ወንጌል አዳራሽ የፈውስ አገልጋይ ተብዮው እንዲህ ሲል አዳራሹን በጩኸት አደበላለቁው። አሁን በሰማይ የእግዚአብሔርና የዲያቢሎስ መላክ እየተዋጉ እየተመለከትኩ ነው እየተዋጉነው ወወወወ የቀደመው
  እባብ ተጣለ ተጣለ የእግዚአብሔር መላክ አሸነፈ ሲል መሪና ተመሪ የሌለበት እሪታ ቀለጠ። እዚህ ጋ ማስተዋል ያለብን ዲያቢሎስ የተጣለው እሱ አየሁ ባለበት ጊዜ አይደለም በውሸትና ክፉ መንፈስ ያሳየውን አስመሳይ ታሪክ ነው የተረከው። ሌላም አለ በአንድ ወቅት በአዲስ አበባ ስታዲየም በአዘጋጁት ኮንፈረስ ተብየ ጌታ እሩጥ ብሎኛል ደስም ብሎኛል ብለው ሜዳውን በሩጫ ሲዞሩ የነበሩ ሽማግሌ ተብየ በአይኔ አይቻለሁኝ። አሁን በእውነት ጌታ እግዚአብሔር የትራክ እሩጫ ሩጡ ይላልን? ደግሞስ በትራክ እሩጫ እግዚአብሔር ይከብራልን? ምነው ነገራቸው ሁሉ የልጆች ጨዋታ ተረ እቃቃ ሆነ?የታየህ ለምትሉ በስራ ምክንያት የተለያዩ የፕሮቴስታን አዳራሾችንና የስታዲየም ኮንፍረስ ተብየዎችን ተመልክቻለሁኝ። ወደ ዋናው ምልከተያ ልመለስና አቶ ስሜ ገሌ ባዩ በመጀመሪያ ጤነኝነቱ በራሱ አጠያያቂ ነው። ምክንያቱም ብዙ የሚጋጩ ነገሮችን የፃፈና የመውደቅና የመዝለፍ ለፍ ክስተቶች ያጋጠሙት መሆኑን በራሱ ቋንቋ ፅፏልና ነው። ከዚህ አንፃር የአቶ እገሌ የአይምሮ ችግር ያለበት ይመስላል። ለማንኛው አንጀት ስትበላ! ወይኔ ልብ ስትሰብር! አንጀት ስታላውስ! ታዲያ የክርስቶስን ወንጌልና ቤተክርስቲያን የምትቃወምና የምትነቅፍ ከሆነ አይደለም መናፍቅ ሌላም ስም ካለ መባልህ ተገቢ ነው። ከዚህ ተነስቸ እዚህ ድረስ ተማርኩኝ። ቁንጫ ትኋን በላኝ። ባለጌ ውሻ አባረረኝ። እናቴና አባቴ ጥሩ አሳዳጊዎችና በእግ እንድጠብቅላቸው ነበር የሚል ትረካዎችን ደርድረሀል። እውነትም ውሸትም ሊሆኑ ይችላሉ። ግን ምን ይጠቅማል። አንድ ሰው በሒሳ ሙያ ተምሮ በተማረበት ሙያ በብቃት ተሰማርቶ ካሠራበትና ካላገለገለ ተምሬ ነበር ቢል ምን ይጠቅመዋል። በመንፈሳዊው ደግሞ በእምነት ፀንቶ ሆኖ መገኘት እንጂ ነበርኩ ዋጋ የለውም። ሌላው የአቶ እገሌ ውሸት እናትና አባቲ ሊድሩኝ እንደሆነ ሰማሁ በትዳር አልታሰርም ብየ አዲስ አበባ ባታ ማርያ ገዳም ቤተክርስቲያን ገባሁኝ ይላል። ለመሆኑ ትዳር እስር ቤት ነው የሚል ትምህርት አለ እንዴ። ይቀጥላሉ አቶ እገሌ ቅዶስ ጳውሎስ ኮሌጂ ገባሁ። አንድ ልጅ ተዋወቅሁኝ የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆነ ። ታቦት እየቀረፀ እንደሚሸጥና የአቡነ ጎርጎሪወስን ታቦት ቀርጾ ሳየው ተቃወምኩት ይሉና ከኮልፌ አምስት ኪሎ ይመላለስ ነበር። ከዛን ጊዜ ጀምሮ አየንውስጥ ገባሁ ሲሉ የመናፍቅነታቸውን የመጀመሪያ ማስረጃ በጃቸው ጽፈው ያረጋግጣሉ አቶ እገሌ። ለምን ልጁን ከኮልፌ አምስ ኪሎ መመላለሱ ይከታተለታል ? የአቶ እገሌን ማንነታቸውን ስለደረሰባቸው ያጋልጠኛል ብለው ስለሰጉ መሆኑ ግልጥ ነው። ደሞ ዳንኤል ስሜን በጋዜጣ አውጥቶ ይላሉ። ታዲያ የተባረሩት ስምዎ በጋዜጣ በመውጣቱ ሳይሆን ማንነትዎ በመረጃ ሲረጋገጥ የክርስቶስ አይደሉምና ከክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተባረዋል። ውሳኔው ደግሞ ትክክል ነው። ምክንያቱ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የክርስቶሳውያን እንጂ የቀራጮች የነጋዲዎች የመናፍቃን አይደለችምና ነው። ደሞ ትውልዴ ከጎጃም ክፍለ ሀገር። ሊሆኑም ላይሆኑም ይችላሉ ግን ምን ይሁንልወት ጎጃም? እኔም የጎጃም ዳሞት ፍኖተ ሰላም ከተማ ልጅ ነኝ ግን በተዋህዶ ሐይማኖቴ ነው ያለሁት። ደግሞ ጎጃም ምንም እንሿን እርስዎን አቶ እገሌን መሰሎችዎት የመሳሰሉ እንክርዳዶች ባይጠፍም በኦርቶዶክስ እምነታቸው ፀንተው ክፉ መንፈስንና መናፍቅነትን የሚቃወሙ የክርስቲያኖች ምድር ናት። እንደምሳሌ በአንድ ወቅት በፍኖተ ሰላም ከተማ አንድ አዋቂነኝ ባይ ዲብ አስደላቂ ግለሰብ የከተማዋን አፈር አይረግጥም ብለው የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ዘማሪያንና ወጣቶች ሀይል እግዚአብሔር ማዳን የእግዚአብሔር እያሉ በመቃወም ጠንቋዩ በመኪናው ከማለፍ ውጭ መሬቷን እንዳይረግጣት ያደረጉ ጠንካራ ክርስቲያኖች አጀር ናት። እኔ ከአቶ እገሌ የተገነዘብኩ ት ስማ ጽድቅ ጋዜጣ የእግዚአብሔር ሀይል እንደሚገለጥባትም ነው። ምክንያቱ ስማ ጽድቅ ስትጠራና ሲያዮት እራሳቸውን እንደሚያዞራቸውና እንደሚወድቁ አቶ እገሌ በእጃቸው በጻፉት አረጋግጠዋል። እኔ ስማ ጽድቅ ጋዜጣ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ የመሳሰሉትን ለምእመናን የምታስተምር ጋዜጣ ነበር የማውቃት ለካም አጋንትንም ታስጨንቃለች በአቶ እገሌ ምስክርነት መሰረት። ሌላው ደግሞ ስመረምር ተሐድሶ መሆኔ ተገቢ መሆኑን ደረስኩበት ይላሉ አቶ እገሌ። አቶ እገሌ የቤትህ ጣራና ግርግዳ መሰለህ እንዴ የክርስቶስን ወንጌልንና አካሉን ቤተክርስቲያንን የምታድስ?ደሞስ አንተ ማን ነህና ነው " ሁሉን አዲስ አድርጊያለሁ" ደሞም አሁን " አዲስ ፍጥረት ናችሁ " የተባለውን አድሳለሁ የምትል? በል በል አቶ እገሌ የኔን ቅኔ ለመስማት የማይሰለፍ ሊቅ አልነበረም እኔ በማስተምረው የማያደንቀኝ አልነበረም እያል የዘባረቅኸው ተረታተረትና በግብዝነት እራስኸን የሰቀልክበት የውሸት ተውኔት ይብቃ። ትንሽ ቆይተህ እኔ ከክርስቶስ እበልጣለሁ እንዳትል አቶ እገሌ። ደሞ ታርኬን ሳልተርክ እንዳልሞት! በጣም ያስቃል። ታሪክህንማ ጨረስከው እኮ በተረት በዚህ ብሎግ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የዳሞቱ አፍቃሬ ማህበረ ቅዱሳን፣ የጸሐፊዉ ሃሳብ ሳይገባህ ለምን ትቀባጥራለህ? እሱ ያለዉ ያለምንም በቂ ማስረጃ ዳንኤል ክብረት ስሜን በጋዜጣ ስላጠፋዉ ብቻ ከቤተክርስቲያን እና ከአገልግሎቴ ታገድሁኝ ነዉ፡፡ አንተ በፕሮቴስታንት ጸሎት ቤቶች ስለሚሆነዉ ነገር ትዘባርቃለህ፡፡ ምን እዚያ ድረስ ወሰደህ? ወይስ በማቴ 7 ቁ 3-4 ላይ እንደተጻፈዉ በወንድምህ አይን ያለዉን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፣በአይንህ ግን ያለዉን ምሰሶ ስለምን አትመለከትም? ሰኔ ጎለጎታ ከመድገምና ነጠላ ለብሶ ላይ ታች ከማለት በማያልፈዉ የክርስትና ህይዎትህ ልታስተምረን ከምትሞክር ለምን የእግዚአብሔርን ቃል መጽሐፍ ቅዱስን አታጠናም? ምክንያቱም መጽሐፉ በእምነት የደከመዉን ተቀበሉት እንጅ አሳዱት አይልምና፡፡ የዳንኤል ክስረት አድናቂ መሆን መብትህ ነዉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ዲያቆን ተብየዉ ለሰራዉ በደል ግን ጠበቃ ለመሆን የሞራል ብቃት የለህም፡፡
   “ጎጃም በኦርቶዶክስ እምነታቸው ፀንተው ክፉ መንፈስንና መናፍቅነትን የሚቃወሙ የክርስቲያኖች ምድር ናት” ስትል መፎከርህ ምን ያህል ጨዋ እንደሆንክ ያሳያል፡፡ ክርስትና ማለት በቃ በለዉ፣ ደብልቀዉ………አመጽ ትርምስ………ነዉ አይደል የሚመስላችሁ? ለዚያ እኮ ነዉ መንግስት ሳይቀር ከነ ብራዘር ሁድና አልሸባብ ጋር የሚያመሳስላችሁ፡፡
   “በአንድ ወቅት በፍኖተ ሰላም ከተማ አንድ አዋቂ ነኝ ባይ ዲብ አስደላቂ ግለሰብ የከተማዋን አፈር አይረግጥም ብለው የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ዘማሪያንና ወጣቶች ሀይል እግዚአብሔር ማዳን የእግዚአብሔር እያሉ በመቃወም ጠንቋዩ በመኪናው ከማለፍ ውጭ መሬቷን እንዳይረግጣት ያደረጉ ጠንካራ ክርስቲያኖች አገር ናት” ስትል ቱልቱላህን የነፋህበት መንገድም ሌላዉ የአላዋቂነትህ መገለጫ ነዉ፡፡ እንዲያዉ ነገራችሁ ሁሉ ከተቃዉሞ የማይዘል ነዉ ማለት ነዉ? ጸልየን የጠንቋዩ ሀሳብ እንዳይሰምር አደረግን ብትለን ኖሩ ቢያንስ እናመሰግናችሁ ነበር፤ ግን የጎዳና ላይ ነዉጥን የክርስቲያን መገለጫ፣ ሰዎችን ከመምከርና ከማስተማር ይልቅ መወንጀልንና ማሳደድን እንደመልካም ነገር ቆጥረህ ስትመጻደቅ፤ ድሮስ ከማቅ ምን ይጠበቃል ያስብላል፡፡

   Delete
  2. ለanonymous January 20, 2015 at 3:29 AM ከዳሞት፦
   ምነው አይንህ ቀላ? እውነቱን ስለተነገረህ? የወንድሞችህ የመናፍቃኑ ስራ ከክርስትና ከመጽሐፍ
   ቅዱስ እውነታ የወጣ የአጋንት መንፈስ መሆኑ
   ስለተነገረህ? ፀሐፊወ እራሱ ስማጽድቅ ጋዜጣን
   ሲያያትና ስትነሳ ሲሰማ እራሱን አዙራ
   እንደምትጥለው ተናገግሮ የጋዜጣዋን ሀይል
   መመስከሩን መናገሬ? ወይስ ፀሐፊው አንተው ሆነህ
   አስተየየቶቹ አብነውህ የምትለው ጠፍቶብህ አይኖችህ ተጉረጠረጡብህ። ምነው የቃልቻው መንፈስ ሐይል የእግዚአብሔር ማዳን የእግዚአብሔር እየተዘመረ ከከተማዋ መውጣቱ
   አቃጠለህና አንዴ ብራዘርሁድ አንዴ አልሸባብ እያልክ በመንግስት ትታከካለህ። መንግስት እንደሆን እናንተ
   ማን እነደሆናችሁና አላማችሁም ምን እንደሆነ አንተና መሰሎቻችሁ ከመናገራችሁ በፊት ያውቃችኋልና አይደለም አንድ ሁለት መቶ ስም ብታወጡ አይሰማችሁም። ነገ ደግሞ IS በማለት መንግስት
   አይሰማችሁም እንጂ ፈርኦን እንደጨፈጨፋቸው
   ህፃናት ንፁሐንን ለማስመታት መሞከራችሁ
   አይቀርም። አይሁድ ፈሪሳውያን አስቀድመው
   ክርስቶስንና ተከታዮቹን ይከሱ፣ ያሳድዱ፣ ካለ ስማቸው ስም ይሰጡ ነበር። የሚገርመው ክርስቶስና
   ተከታዮቹ እርቀው ሲሔዱ አይሁድና ፈሪሳውያን
   ተከትለው ሔደው ያሳድዷቸው ነበር። ዛሬም የአይሁድ የፈሪሳውያን ልጆች የሆናችሁት እናንተ የክርስቶስን ቤተክርስቲያን የሆነችውን ኦርቶዶክስ
   ተዋህዶንና ተከታዮቿን ያሳድዳሉ፣ ይከሳሉ፣ ካለስማቸው ስም ይሰጣሉ፣ ሌላም ብዙ የሰይጣንን
   ሰይፎች ትመዛላችሁ። እናም ወዳጀ የቃልቻው መባረር ያቃጠለህ ትመስላለህ። ምክንያቱም በአላማና በምግባር ስለምትመሳሰሉ። ለመሆኑ መዝሙር ፀሎት እንደሆነና ሐይል እንዳለው ታውቃለህን? ለነገሩ ብታውቅም አታውቅም ምክንያቱም ላለማወቅ ከእውነት ጋር ተጣልተሀልና ነው። እውነትም ክርስቶስ ነው ስለሆነም ከክርስቶስ ጋር ተጣልተሀልና ነው። ደሞ ፀሎተኛ ለመምሰል ፀልየን አስወጣን ብትል ባማረብህ ነገር ግን ነገራችሁ ከተቃውሞ አይዘልምና በመቃወም ስትል ቱልቱላህን ነፋህ ብለኸኛል። እውነት መናገር ቱልቱላ መንፋት ከሆነ ይሁንልህ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ እራሱ ዲያቢሎስን ተቃወሙት ሲል መቃወም የሚለውን ቃል ጠቅሷልና መጽሐፋም ትሉቱላ መንፋቱ ይሆን በአንተ የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢነት?መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢው መምሰል ትችለበታለህና ሐጢያትንና ወንጀልን ጽፈህና በአንደበትህ ተናግረህ እራስህን መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ በማስመሰል ለሐሰተኛነትህ መልስ የሰጡትን ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስአንብቡ ይባልልኛል። እስቲ መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢውና አዋቂው አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ንገረኝ። መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ ጥራዝ ማን አዘጋጀው?እንዴትና መቸ ተዘጋጁ? ማን ነው ያዘጋጃቸው?እባክህ የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂው እነዚህን መልስልኝና መልስህን አይቸም ጥያቄ ሊኖረኝ ይችላል። ደግሞ ወንድሜ ምነው ተልመጠመጥ እን ሸለመጥማጥ። የፀሐፊዉ ሀሳብ ሳይገባህ ምን ትቀባጥራለህ ጥያቄው ዳኔል በፃፈው ካለበቂ ማስረጃ ከቤተክርስቲያን ነው ስትል የመልመጥመጥ ትችትና አስተያየት አስቀምጠሀል። ምነው ወንድም ጽሑፉን ለምን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ግርጌ አታነበውም? ነው ፀሐፊው አንተው ሆነህ ማንነትህን በጽሑፍሕ መስታውትነት አይተኸው አሳፍሮኸ መውጫ እየፈለግህ ነው? ነውየወንድምህ ስራ አሳፍሮኸ ከአፈርሁ አይመልሰኝ ብለህ ነውራችሁን ለመሸፈን? ለእናንተ መናገር ባያስፈልግም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካለመረጃ ማንንም አታስወጣም። ፀሐፊው ግን አንዴ በስማ ጽድቅ ጋዜጣ መናፍቅ በመባሌ ተባረርኩ ካለ በኋላ በአንድ ካህን መናፍቅ ተብሎ ተነግሮብኝ እያለ የተምታታ ወሬ ያወራል። ተሐድሶ መሆኑን ደግሞ እራሱን መርምሮ አረጋግጧል። ተሐድሶ ደግሞ የበቃ የበተክርስቲያን አይደለምና ከቤተክርስቲያን ወጥቷል። በፕሮቴስታንቶች ጎራ የሚሆነውን መናገሬንም ጉዴ ወጣ ብለህ ደነገጥህ መሰለኝ ትዘባርቃለህ ብለኸኛል። እኔ እንሿን አልዘባረቅሁኝም አመንክም አላመነክም በአይኔ ያየሁትን እውነት ገለጥኩኝ እንጂ። በዛ የሚደረገው ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ በሐሳዊው መሲህ የሚደረግ የእርኩስ መንፈስ ነው። ሌላው አስገራሚው እውነተኛና መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ ነኝ ለማለት ይመስላል በማቴዎስ 7፤ ከ3-4 የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል ጠቅሰህ በአይኔ የአየሁትን የሐሰተኛውን ክፉ ተግባር መናገሬን ተገቢ አለመሆኑን ተናግረህ በእኔ አይን ያለውን ምሰሶ እንዳወጣ ነግረኸኛል። አይ እፉኝትነት! ምነው ትንሽ ትልቅ ሳትሉ የፈጠራ ታሪኮችን እተረካችሁ በፀያፍ ቋንቋ ነውረኛ የሆኑ ቃላቶችን እየመዘዛችሁ ስም ስታጠፉና ስትዘልፉ ማቴዎስ 7፤ ከ3-4 ያለው የተግሳፅና የምክር ቃል አልታያችሁም? ነው በፈጠራ ታሪክ ስም ማጥፋትና መሳደብ በመጽሐፍ ቅዱስ ተፈቅዳል በእናንተ መጽሐፍ ቅዱስ እውቀት። ካላመንክም በዚህ ብሎግ የወጡትን ጽሑፎችን በሙሉ ተመልከት። በመጨረሻ ማህበረ ቅዱሳንን ጠቅሰህ እኔን የማህበሩ አባል አስተያየቴንም የማህበሩ አድርገህ ገልፀሐል። እኔ የማህበሩ አባል አይደለሁም፤ አስተያየቱም የኔው ነው። የማህበሩ አባል ብሆን ደስ ባለኝ ነበር ግን አይደለሁም። እኔ በአንደኝነት የማስቀድመው እምነቴን ነውና እምነቴን እከተላለሁኝ። ከዛም ስለ እምነቴ እንክርዳድን ሳይቀላቅሉ የሚነግሩኝን እሰማለሁኝ። እንክርዳድም ስል በጥቅሉ ሐሰተኛ ወንጌልን ማለቴ ነው። ዳንኤልም የኦርቶ ዶክስ እውነተኛ አገልጋይ ነውና እሰማዋለሁ። እንግዲህ ምንትሆን ወዳጄ?

   Delete
  3. አይ ዳሞቴዉ፣ መናፍቃን ብለህ ጣትህን ወደሌሎች ከመቀሰር ምናለ የመናፍቅ ትረጉሙ ቢገባህና አንድን ሰዉ መናፍቅ ብሎ ለመፈረጅ መስፈርቱ ምን እንደሆነ ብትረዳ፡፡ ክርስትና ህይወት ነዉ እንጅ አካኪ ዘራፍ እያሉ በመወራጨት አይደለም፡፡ ለዚህ እጅ እግር ለሌለዉ ዘባተሎ አስተያየትህ መልስ መስጠት ባልፈልግም ሁለት ነገሮችን ግን አስረግጬ ልነግርህ ወደድሁ፡፡
   1. የምትድነዉ የየትኛዉም ቤተ እምነት አባል ስለሆንክ ሳይሆን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ከድንግል ማርያም ተወልዶ፣ ሰዉን ለማዳን ሲል ራሱን ለመስቀል ሞት አሳልፎ በሰጠዉ፣ ለሰዉ ልጆች መዳን ሲል በሞተዉ፣በሶስተኛዉም ቀን ሞትን ድል አድርጎ በተነሳዉ፣ በክብር ወደ ሰማይ በአረገዉና ዳግመኛ በክብር በሚመጣዉ የናዝሬቱ ኢየሱስ በማመን ብቻ ነዉ፡፡ ለዚህ አስረጅ ከፈለግህ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፣
    የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም። የዮሐንስ ወንጌል 6፥35
    እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም። የዮሐንስ ወንጌል 8፥12
    በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል። የዮሐንስ ወንጌል 10፥9
    መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። የሐዋርያት ሥራ 4፥12
   2. መናፍቅ ማለት የተገለጠዉን የክርስቶስ አዳኝነት መካድ ሲሆን ለዚህም ምሳሌ መጥቀስ ቢያስፈልግ፤
    ገድለ ተክለሃይማኖት ምዕራፍ 54፡23 ላይ እንዲህ ይላል “እነሆ በክፉ ሞት በተቅማጥ ትሞታለህ፣እሷንም እንደ ስቅለቴና ከአንተ በፊት እንደነበሩት ሰማዕታት ደም እቆጥርልሃለሁ ነገር ግን ለብቻህ አይደለም በዚህ ገዳም በተቅማጥ በሽታ የሚሞቱትን ልጆችህንም ቁጥራቸዉን ከሰማዕታት ጋራ አደርጋለሁ፣ በመንግስተ ሰማያትም ለአንተ እሰጣቸዋለሁ……”::
   ዳሞቴዉ ቢገባህ ኑሮ ይኼ ነዉ ትልቅ መናፍቅነት፡፡ ክቡር የሆነዉን የክርስቶስ ደም በማክፋፋትና በፈጠራ ድርሰት የህዝብን ህሊና በመያዝ ክርስቶስ በደሙ ፈሳሽነት ያደረገዉን ስርዬት ዋጋ ማሳጣት መናፍቅ ካላስባለ ከዚህ የከፋ ክህደት የት ይኖራል?
    ገድለ ክርስቶስ ሰምራ ደግሞ እንዲህ ይለናል, “ክርስቶስ ሰምራ ወደ ሲኦል ሄዳ ሳጥናኤል ብላ ጠራችዉ፡፡ሰይጣንም ‘ማነዉ በድሮ ስሜ የሚጠራኝ ?’ ብሎ ተገረመ፡፡ ከሲኦል ወጥቶም አጇን ይዞ የሃጥአን ነፍስ ባለበት መጨረሻ ላይ ጣላት፡፡ እግዚአብሔርም ሚካኤልን ጠርቶ ፍጠንና ሂድ ክርስቶስ ሰምራ ወዳጄን አስጥላት ብሎ ላከዉ፡፡ ሚካኤልም ሄዶ ባጣት ጊዜ የት እንደደበቃት ለመፈለግ እንዲያመቸዉ በሲኦል የነበሩትን ነፍሳት አንድ በአንድ እያወጣ ከጨረሰ በኋላ የክረስቶስ ሰምራን ነፍስ አገኘና ይዟት ሄደ፡፡ እነዚያ በክርስቶስ ሰምራ ምክንያት ወጥተዉ የነበሩት ነፍሳት ገነት መንግስተ ሰማያት ገቡ”፡፡
   ዳሞቴዉ ስታስበዉ እግዚአብሔርን ሰዉ ሊያማክረዉ ይችላል? ከሰይጣን ጋራስ ሊታረቅ ይችላል? ለዚህስ እግዚአብሔር የሰዉን ሽምግልና ይፈልጋል?

   ሌሎችም ቀንና ሌሊት የሚሰበኩ ገድል ተብዬ ድርሰቶች አሉ፡፡ ሰይጣን ክቡር የሆነዉን የክርስቶስ አዳኝነት ለመሸፈን የተጠቀመባቸዉን የፈጠራ ድርሰቶች ጠዋትና ማታ ሳያቋርጡ እየደገሙ በስመ ክርስትና የሚኖሩት መናፍቅ ሳይባሉ የክርስቶስን አዳኝነት የሚሰብኩት ግን የተለያየ ስም እየተሰጣቸዉ ከቤተ ክርስቲያን ይባረራሉ፡፡ ይኼ ትክክል ነዉ ብለህ የምታምን ከሆነ አንተ ታዉቃለህ፡፡

   ከዚያ ዉጭ ከፕሮቴስታንት እምነት ጋር ያለብህን ችግር ራስህ ታዉቃለህ፡፡ መቼም፡
    ጠዋት ቤተ ክርስቲያን ሲመሽ ደግሞ በየ መሸታ ቤቱ የሚታጎረዉ፤
    በየቃልቻ ቤቱ የሚሰለፈዉ፣
    በዝርፊያና ግድያ ማረሚያ ቤቱን ያጨናነቀዉ፣
    በኤድስ በሽታ የአልጋ ቁራኛ የሆነዉ፣
    በየመንገዱ የሚቆመዉ ሴተኛ አዳሪ…….ወዘተ ሁሉ ፕሮቴስታንት ነዉ አትለኝም፡፡ ግን ደግሞ እነዚህ ሁሉ የአንዲት የክርስቲያን ደሴት እየተባለች በምትሞካሽ ሃገር ቁልፍ ማህበራዊ ችግሮች ናቸዉ፡፡ ተግባባን?

   Delete
  4. ለanonymous January 23, 2015 at 12:28am
   ወንድሜ መጽሐፍ ቅድሱን እኮ እንዴለ ሸምድደኸዋል። ወይ ችሎታ! ወይ ብቃት! ማን አስተማረህ ባክህ? ዋው የመጽሐፍን ንባብ ተንትኖ ነው ያስተማረህ። እንዲህ ያላ የእምነት ፍፁምነት ይዘህ ግን የእንደ ቅዱስ ጳውሎስ ጨርቅህ ታምር አለመስራቷ ያሳዝናል። " እንደ በሽተኛ በቃላት መዋጋት ይፈልጋሉ" ማለት ምን ማለት ይሆን? አባተትህም ጌታ ክርስቶስን የተፈታተነውና ለመጣለ የሞከረው እኮ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የእጠቀሰ ነው እኮ? ታዲያ ቃላት ብትደረድር ፤ ምዕራፍና ቁጥር ብትደረድር በእምነት የቃሉን ትርጉምና መልክት ተረድተው ካልኖሩበትና በምግባር ካልተገበሩበት ምን ፍየዳ አለው። እንደህፃን ካልሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር መንግስት አትገቡም ተብሏልና ቃሉን እን ህፃን በማለት መንገስተ ሰማይ ልትገባ ነው ወይስ እናትና አባትህን እንደገና ውለዱኝ ልትላቸው ነው። የአንተ የግንዛቤህ ጥልቀት እኮ የረቀቀ ነውና ውለዱኝ እንዳትላቸውና በጊነስ ቡክ እንዳትመዘገብ።ቃሉ በሙላት ይኑርባችሁም ተብሏልና ቃሉን ሸምድዱ ማለት ነው ወይስ በቀረጢት በስልቻ ሞልታችሁ ያዙ ማለት ነው? ደግሞ መጽሐፉ እንዲህ ይላል ቃሉን የምታደርጉ እንጂ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ ይላል። ምን ማለተ የሺ የሆን ዝም ብሎ ማውራት ይሆንለአንተ? ምነው ስለሀየማኖትህ ማውራትና መግለፅ ፈራህ? ማንነቴ ይጋለጣል ብለህ ነውን? ነው እውነት የሌለው ድርጅት ስለሆነ አፈርክበትን? የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኦርቶዶክ እምነት ተከታይ አለመሆንህ በከሳሽነትና በቃላት ውጊያህ እራስህ አረጋግጠሀል። እኔ በአለቱ ላይ የተመሰረተች የኦርቶዶክስ ይማኖት ተከታይ ነኝ። ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችንም የክርስቶስ ናትና ንፁሑን ስንዴ የወንጌል ትምህርት ታስተምራለች። ሀይማኖት አያስፈልግም በማለት የተናገርከው አንተን ከሚህለ የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂና ሸምዳጂ መስማቴ መጽሐፍቅዱሱም ምን አይነት እንደሆነ ማወቅህን ተጠራጠርኩኝ። ለሁሉም የሺ የሁዳ መልእክት ምዕራፍ 1 ከቁጥር 3 እስከ 4 አንብብና ምን እንደምትል ለመስማት ዝግጁ ነኝ። መቸም ተርጏሚነኝ ብለህ ትርጉሙን እንዳትፈለፍለው። በሁለተኛ ደረጃ ጻድቁ ተክለሐይማኖትንና ቅድስት ክርስቶስ ሰምራን በተመለከተ ያነሳህው ዛሬ የጀመራችሁት ሳይሆን ከቀድሞም ጀምሮ የመናፍቅነታሁ አንዱ መገለጫችሁ ነው። በተረፈ አንተ የገለጽሕበት የመንደርና የአለም ቋንቋና ገድሉ የተጻፈበትና ቤተክርስቲያን የምትገልጥበት ቃላቶች በምንም አይገናኝም። ለምሳሌ አማካሪ ፤ ሽምግልና የሚባሉት የሚባሉት አለም የሚጠቀምባቸው ቃላቶች ናቸው። ለሁሉም በእምነት ፀሎት መለመንና ማማለድ አንተ ሽምግልናና ማማከር ከምትለው ጋር በምንም አይገናኝም። ያልተፃፈ ማንበብና መጻፍ የመናፍቆች አንዱ ልማዳችሁ ነው። ለሁሉም ስለገድላት ለማውራት ገድል ማለት ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ አለብህ። እሩጫየን ጨርሻለሁ መልካሙንም ገድል ተጋድያለሁ ዘብሎ በመጽሐፍ ተጽፏል እንዴት እንደምትተረጉመው ባላውቅም። እናም የቅዱስ ተክለሀይማኖትና ቅዱስት ክርስቶስ ሰምራ ስለክርስቶስና ሰዎች ክርስቶስን አምነው እንዲድኑ ያደረጉትን የእምነት ተጋድሎ መተቸትህ ምን ያክል ከመጽሐፍ ቅዱስ የራቅህና ለመንፈሳዊ ነገር እንግዳ እንደሆንህ ያሳብቅብሀል። በመጽሐፍ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፦ ለስጋየም መጎሰሚያ ይሆነኝ ዘንድ ህማም ተሰጠኝ ተብሏል። እናም አንተ ቀንጭበህ በአወጣሀት ሀረግና የገድሉ ትርጉም ሳይገባህ "የክርስቶስን ደም ማክፋፋት" ነው ስትል ያልተፃፈ ጽፈሐል። ብታውቅ ኖሮ በክርስቲያኖች የእምነት ተጋድሎ የበመጀመሪያ የሚከብረውና የሚሰበከው ክርስቶስ ነው። አስተያየትስ እጅ እግር አለው እንዴ? አለው ካልክም አፍንጫ አፍ ከንፈር ጥርስ ብቻ ብዙ የሰውነት ክፍሎች አሉት ማለት ነው። ዘባቶሎ ላልከው ካንት አሉባልታ የሚሻል ይመስለኛል። በበሽታና በተለያዩ ሱሶች የተያዙትን ገልፀክ ለአንድ የእምነት ተቋም እውነተኛነት መለኪያማድረግህ በጣም ይገርማል። ይሔ ደግሞ በአዕምሮህ ከእንስሳነት በታች መሆንህን ያመለክታል። አላወቅህውም እንጅ ነፍስህ በክህደትና በሀጢያት መቅሰፍት ጎስቁላለች። ብቻ ፍፁሙ ፕሮቴስታን መንገድ ዳር ማትቆመው መሸታቤት ማትገባው የማትዘርፈው በኤድስ በሽታ አልጋ ቁራኛ ያልሆንኸው ሴተኛ አዳሪ ያልሆንኸው፡፦ ዋው ድንቅ ሰው ነህ ባክህ። ለማያውቅህ ሒድና ንገረው። በአዳር ብሮግራሙ እየተዳራችሁ ጽንስ አስወጥታችሁ ሽንትቤት የምትጨምሩት እናንተው አይደላችሁምን። አይ ማስመሰል!ማስመሰሉንስ ችለህበታል ግን ሒድና በጨው ታጠበው አስመሳይነትህን።

   Delete
  5. ዳሞት
   መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ አለመሆንህ ምን ያህል እንደጎዳህ አየህ?በጥራዝ ነጠቅ የሰማሃቸዉን ነገሮች እዚህና እዚያ ከመሰንቀር ዉጭ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ምዕራፍና ቁጥር እንደዚህ ይላል…….ብሎ ለመናገር አንዴም አልደፈርክም፡፡ እኔ ደግሞ ትክክለኛዉ ሚዛን የእግዚአብሔር ቃል(መጽሐፍ ቅዱስ) ስለሆነ ከዚያ አንጻር ነገሮችን እመዝናለሁ፡፡ እናም ልዩነታችን እዚያ ላይ ነዉ፡፡
   እኔ ሲጀመር ሃይማኖት አያስፈልግም ሳይሆን ያልኩት፣ ሃይማኖት ድርጅት ነዉ፣ ማንም ሰዉ በልቡ ሳይለወጥ ነኝ ለማለት ብቻ የዚህ ወይም የዚያ ሃይማኖት ተቋም አባል ነኝ ሊል ይችላል ግን የሚያድነዉ የግለሰቡ እምነቱ ነዉ፡፡ እምነት ደግሞ የግል ጉዳይ ነዉ፡፡
   ሮሜ 10፤ 10 ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።
   ይላል፡፡ ስለዚህ በልብህ ታምናለህ በአፍህ ደግሞ ስላመንክበት ነገር ትመሰክራለህ፡፡ ከዚያ ዉጭ ክርስትና በሰላማዊ ሰልፍ የምትገልጠዉ ጉዳይ አይደለም፡፡ በኑሮና ሕይወት እንጅ፡፡
   ብዙ ቦታዎች ላይ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ መሆንክን ለማሳየት ብዙ ደክመሃል፡፡ ወዳጄ የፈለግኸዉን ብትል ሃቁን ልትሸፍነዉ አትችልም፡፡ በአብሾ ስካር በየገዳማቱ የተደረቱ ድርሳንና ገድል ተብዬዎች ተነቅለዉ ወጥተዉ እዉነተኛዉ የእግዚአብሔር ቃል የሚሰበክበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ በነገራችን ላይ ገድልና ድርሳናትን የምንቃወመዉ የሚያስተላልፉት መልክት ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስለሆነ ብቻ ነዉ፡፡ ለዚህ አስረጅ የምትፈልግ ከሆነ ራስህ ገድላቱንና ድርሳናቱን አግኝተህ በማንበብና መጽሐፍ ቅዱስ ከሚለዉ ጋር በማነጻጸር የራስክን ድምዳሜ መዉሰድ ትችላለህ፡፡
   በምጸት ዘይቤና እንካ ስለካንትያ ከምትዳክር ቁጭ ብለህ ቃሉን አጥና፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አለማቀፋዊ ነዉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ የአለም 7.3 ቢሊየን ህዝብ ጉዳይ ይገደዋል፡፡ ሁሉንም ነገር ኢትዮጵያዊ በማድረግ በግብዝነት አትመጻደቅ፡፡ ሰዉ በየትኛዉም የአለም ጫፍ ቢሆን አምኖ እንዲድንበት እግዚአብሔር የአዘጋጀዉ መንገድ አለ፡፡ እሱም አንድ ልጁን በመስጠት ነዉ፡፡ መጽሐፍም
   በየዮሐንስ ወንጌል 3፥16

   በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ይለናል፡፡
   ዳሞት
   መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ አለመሆንህ ምን ያህል እንደጎዳህ አየህ?በጥራዝ ነጠቅ የሰማሃቸዉን ነገሮች እዚህና እዚያ ከመሰንቀር ዉጭ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ምዕራፍና ቁጥር እንደዚህ ይላል…….ብሎ ለመናገር አንዴም አልደፈርክም፡፡ እኔ ደግሞ ትክክለኛዉ ሚዛን የእግዚአብሔር ቃል(መጽሐፍ ቅዱስ) ስለሆነ ከዚያ አንጻር ነገሮችን እመዝናለሁ፡፡ እናም ልዩነታችን እዚያ ላይ ነዉ፡፡
   እኔ ሲጀመር ሃይማት አያስፈልግም ሳይሆን ያልኩት፣ ሃይማኖት ድርጅት ነዉ፣ ማንም ሰዉ በልቡ ሳይለወጥ ነኝ ለማለት ብቻ የዚህ ወይም የዚያ ሃይማኖት ተቋም አባል ነኝ ሊል ይችላል ግን የሚያድነዉ የግለሰቡ እምነቱ ነዉ፡፡ እምነት ደግሞ የግል ጉዳይ ነዉ፡፡
   ሮሜ 10፤ 10 ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።
   ይላል፡፡ ስለዚህ በልብህ ታምናለህ በአፍህ ደግሞ ስላመንክበት ነገር ትመሰክራለህ፡፡ ከዚያ ዉጭ ክርስትና በሰላማዊ ሰልፍ የምትገልጠዉ ጉዳይ አይደለም፡፡ በኑሮና ሕይወት እንጅ፡፡
   ብዙ ቦታዎች ላይ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ መሆንክን ለማሳየት ብዙ ደክመሃል፡፡ ወዳጄ የፈለግኸዉን ብትል ሃቁን ልትሸፍነዉ አትችልም፡፡ በአብሾ ስካር በየገዳማቱ የተደረቱ ድርሳንና ገድል ተብዬዎች ተነቅለዉ ወጥተዉ እዉነተኛዉ የእግዚአብሔር ቃል የሚሰበክበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ በነገራችን ላይ ገድልና ድርሳናትን የምንቃወመዉ የሚያስላልፉት መልክት ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስለሆነ ብቻ ነዉ፡፡ ለዚህ አስረጅ የምትፈልግ ከሆነ ራስህ ገድላቱንና ድርሳናቱን አግኝተህ በማንበብና መጽሐፍ ቅዱስ ከሚለዉ ጋር በማነጻጸር የራስክን ድምዳሜ መዉሰድ ትችላለህ፡፡
   በምጸት ዘይቤና እንካ ስለካንትያ ከምትዳክር ቁጭ ብለህ ቃሉን አጥና፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አለማቀፋዊ ነዉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ የአለም 7.3 ቢሊየን ህዝብ ጉዳይ ይገደዋል፡፡ ሁሉንም ነገር ኢትዮጵያዊ በማድረግ በግብዝነት አትመጻደቅ፡፡ ሰዉ በየትኛዉም የአለም ጫፍ ቢሆን አምኖ እንዲድንበት እግዚአብሔር የአዘጋጀዉ መንገድ አለ፡፡ እሱም አንድ ልጁን በመስጠት ነዉ፡፡ መጽሐፍም
   በየዮሐንስ ወንጌል 3፥16

   በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ይለናል፡፡
   Delete

  6. ዳሞት
   የምትሰጠዉ አስተያየት ያልበሰለ ስለሆነ ለዚህ መድረክ አይመጥንም፡፡ የማቅ አባል አይደለሁም ያልከዉ ለካ እዉነትህን ነዉ፡፡ እንዳንት አይነቱን ወደል መሀይም ማቅ ራሱ አባል አያደርግም፡፡ ዲግሪና ከዚያ በላይ የተማሩ ስለሚል የምርጫ መስፈርቱ፡፡ ስለዚህ የሆነ ያልሆነዉን በመዘላበድ ቤተክርስቲያኒቷን ሰዉ የሌላት አታስመስላት፡፡ ካላወቅህ ዝም ብትል ምን ችግር አለዉ? አስሮ የገረፈህ የለ፡፡

   Delete
  7. ለanonymous january 25,26,2015 at11:09pm and 2:56am
   ወድ anonymous በጥራዝ ነጠቅ ነው ያልከው? የምን ጥራዝ? የመጽሐፍ ነው ወይስ የወረቀት? ደግሞስ የሰማሀቸውን ሰንቅረህ ነው ያልከው እንዴትና የት ነው የተሰነቀሩት?የአሰነቃቀራቸውን ሁኔታ ብታብራራው? ምነው የተሰነቀሩ እያልክ ስለተናገርካቸው የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት በመጽሐፉ የሉም ውሸት ናቸው አትልም ነበር። አቶ መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢው፦ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ የጀመራችሁትና ንባብ ያወቅኸው ዛሬ ነወ እንዴ? ልስን መቃብር! አቶ አንባቢው፦ ምራፍና ቁጥር ነው እንዴ የሚያድንህና የሚያስተምርህ? የእውቀት ተፈላሳፊው፦ ቁጥርና ምዕራፍ ጠርዝ ደርሰሀል። እንዳትም ቁጥርና ምዕራፍ አዋቂ የለም። ለገሩ ገብቶኛል የመጽሐፉ መልክት የት እንደሚገኝ ስለጠፋብህ ነው የንዴት ንግግር የተናገርኸው። ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ አንብቡ ማለት መስክሩ ፤ የምትድኑትም ካነበባችሁ ብቻ ነው የሚል ቃል አለ እንዴ? በማንበብ የሚዳን ከሆነማ ለምን ስለኔ መከራ ትቀበላላችሁ ተባለ? ምክንያቱ እንደቤት እቃ በየጏዳው ማንበብ ስለሚቻል። ሌላው የሰማሀቸውን ነው የሰነቀርኸው ነው ያልከኝ። ለመሆኑ መቀርቀር መሰንቀር እዚህ ጋ ምን አመጣቸው? ከመጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ ነው ያገኘኸውን? ምነው የመሰንቀርን ምዕራፍና ቁጥር አልጠቀስኸውም? የሰማኸውን ነው ላልከው መልሱ አዎን ነው። የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩን እኮ ያዮትን፣ የሰሙትንና ከጌታ እግር ስር ቁጭ ብለው የተማሩትን አይደለም። እናም የተማርኩትን፣ የሰማሁትንና ያየሁት እውነት ነው። ሌላ የተናገርኸው እኔ ሀይማኖት አያስፈልግም አላልኩ ስትል መጀመሪያ የተናገርከውን ስትክድና ተንሸራተህ ወርደህ በማታውቀው የፍልስፍና አለም ገብተህ ትዳክራለህ። ካላወቅህ አላውቅም እኔ እምነትም ሀይማኖትም የለኝም ማለት ትችላለህ። መዋኘት ሳትችል ለምን ባህር ውስጥ ገብተህ ታቃስታለህ። አስገራሚ ተዋናኝ ዘባች ነህ፤ "አንድ ሰው በልቡ ሳይለወጥ የዚህ ወይም የዘይት የዘያ ሀይማኖት ተቋም ነኝ ሊል ይችላል። ግን የሚያድነው የግለሰቡ እምነቱ ነው። እምነቱ ደግሞ የግል ጉዳይ ነው" ትላለህ። ምንም እንሿን እንዳልከው አንተም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኝ ሳትሆን ነኝ እያልክ ትንሽ ትልቅ ሳትል እየዘለፍክና ራስህን በዜሮ ኮፍሰህ የእግዚአብሔር የሆነውንና የመንፈስ ቅዱስን ስራ በአለማዊ አስተሳሰብ እየተመለከት የምታራክስና ስታጥላላ እየተመለከት ስለሆነ ሳይሆኑ ነን የሚለው እውነት ነው። ግና የሚያድነው እምነቱ ነው ሲባል ምን ማለት ነው? በአለም ላይስ ስንት የእምነት ተቋማት ይገኛሉ? ሚሊየን አይነት የእምነት ተቋም ቢኖር በዛውስጥ ያሉ አኛ አንደየ እምነታቸው እምነታቸውን ተግባራዊ ያደርጋሉ እያልክ ነውን? እረ አትዘባር ወንድሜ። ልንድን የምንችለው የያዕቆብ ወንድም ይሁዳ በምዕራፍ 1ከቁጥር 1 እስከ 4 እንደፃፈው ለቅዱሳን አንድ ጊዜ በተሰጠችው ሐይማኖት ሆነን ለመዳናችን የሚሆነውን እምነታችን በማመንና በምግባር ስራ በመፈፀም ነው። ለአንድ ግለሰብ እምነቱ የግሉ ነው ላልከው ትክል ነህ። ቤተክርስቲያን ማንንም የእኔ እምነት ይሄ ነው ፤ በዚህ የእምነት መንገድ ነው የምሄደው ብላ ትነግራለች እንጂ አስገድዳ ማንንም አማኝ አታደርግም። ይሔም ሰሪዋ ኢየሱስ ክርስቶስ "የሚወድኝ ቢኖር ይከተለኝ" ፤ "እነሆ በፊትህ ውሀና እሳት ቀርቦሀል ወደ መረጥከው እጅህን ላክ" ብሎ ነፃ ፈቃድና ምርጫን እንደሰጠ ማለት ነው። እናም ወዳጄ መጽሐፍ ቅዱስ አነባለሁ እያልክ ከምትዘላብድና ከምትመጻደቅ የእግዚአብሔር ቃል ምን ይላል ? በእግዚአብሔር ቃል አምኖስ መዳን የሚቻለውስ እንዴት ነው? የሚለውን ለመማር በየዋህነትና በሞኝነት ብትጥር መልካም ነው። ከዛም ትቀጥለና፦ "ሰው በልቡ አምኖ ይፀድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናል" የሚለውን የእግዚአብሔርን ቃል ያው የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ መሆንህንም ለማስመስከር ይመስላል ከነ ምዕራፍና ቁጥሩ ጠቅሰሀል። ልጠይቅህና በልብ ማመን ማለት ምን ማለት ነው? በአፍ መመስከርስ እንዴት ነው? መልክቱን ለምን እንደተጠቀምህበት በራሱ አጠያያቂ ቢሆንም እምነት እምነቱ እያልክ የተፈላሰፍክበትን ያስረዳልኛል ብለህ መሆኑ ይመስላል ግን ደግሞ አይመሳሰሉም። ምክንያቱም አንተ እምነቱ ያድነዋል ስትል፤ የጠቀስከው መልክት ደግሞ አምኖ ይፀድቃል መስክሮ ይድናል ስለሚል ። አኛ አስቲ እኔ ደግሞ ያው እንዳልከው መጽሐፍ ቅዱስ ስለማላነብ የሰማሁትን በጥራዝ ነጠቅ ልጠይቅህ፦ "ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል" ማለትስ ምን ይሆን? ሌላው የማታገናዝብ ክፉ ከሳሽ በመሆን "ክርስትናን በሰላማዊ ሰልፍ የምትገልጠው አይደለም በኑሮና በሒወት እንጂ" አልክ። አይ የተነቃብሽ፣ ጭንቅላትሽን የተቀጠቀጥሽ እባብ! ድንቅ የናዚ ፓለቲከኛ ነህ። የት ለመሄድና ምን ለማለት እንደፈለግህ ግልጽ ነው። ለሁሉም በክርስትና ታከህ ለመናገር የፈለግኸውን አንተው በግልጽ ተናገርና ይመለስልሀል። ስለ "ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ መሆንህን ለማሳየት ብዙ ደክመሀል" ብለኸኛል። እኔ እንሿን የሚጠበቅብኝ አድርጊያለሁኝ ብየ አላምንም ያንተንም የክፍውን ምስክርነት አልፈልግም። ስለ አብሾ ጠቅሰህ ያው የማንነትህ መገለጫ የሆነውን ቅዱሳንንና ቅዱሳት መጽሐፍትን የመስደብ፣ የማጥላላት፣ የመናቅ እንዲሁም የማንቋሸሽ ተግባርህን አከናውነሀል። ይሄ ደግሞ ጠላት ከሆነው ከሰይጣንና ከተከታዮቹ የሚጠበቅ ነው። ሰይጣን የእግዚአብሔርን ቃል ሲገልጽ እንጂ እውነት ነው ብሎ አምኖ አይፈጽምም ። እና አንተም የእግዚአብሔር የሆኑትን ብትቃወም አያስደንቅም። ነገር ግን በአብሾ ስካር ብለሀል፦ አብሾ እንደሚያሰክር ቀምሰኸዋል እንዴ? ለክሱ ችግር የለውም ሁሉንም በአመንበት ሀይማኖታችን ሆነን የምንጠቀምባቸው እኛው ስለሆንን አንተ እንደከሰስህ ትቀራለህ እንጂ የሚሰማህ ማንም የለም። ምክንያቱም ከእናንተ አዳራሽ አላመጣናቸውምና ነው። በአብሾ ስካር ስትል ግን በሐዋርያት ስራ ላይ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስ ወርዶባቸው በልዮ ልዮ ቋንቋ ሲናገሩ ቡሽ ጠላ ጠጥተው ሰክረው ነው ነዐር ያሏቸው በኢየሩሳሌም አብረዋቸው የነበሩት ሰዎች። እና አንተም ይሄን በማለት የሚደንቅ አይደለም። ሌላው አንብብ፣ አጥና ፣ 7.3 ሚሊየን ወዘተ እያል ለምትቀባጥረው አንተ አዋቂ ከሆንክ ይሁንልህ። ሌላ የተናገርኸው የምሰጠው አስተያየት እንደማይመጥን ነው የተናገርከው። እውነት ነው አይመጥንም ምክንያቱ ዳቢሎስን ይቃወማልና ነው። የማህበረ ቅዱሳን አባል ያልሆንኸው መሀይም ስለሆንህ ነው ላልከው ፤ ያልሆንሁት በማሀይምነቴ ባይሆንም መሀይም ነህ ላልከው ግን አዎ መሀይም ነኝ። በል እንግዲ አጃቢ ይዘህ አዳራሽህ ግባና ኦርጋን ሳክስፎንህን፣ ጊታር ፒያኖህን እየመታህ በረጌ ራጋጭፈራ በደስታ ደልቅ። ቤተክርስቲያኗ ሰው የሌላት አታስመስል ላልከው ያ የአንተው ሀሳብ ነው፡ ኦርቶ ኮክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እውነተኛ የክርስቶስ የሆኑ ሰዎች አሏት። እነሱ ባይኖሩ ኖሮማ እናንት ጠላቶቿ ባጠፋችኋት ነበር። ዝም አትልም ላልከው ዝም አልልም አንተን የመሰለ አወናባጂ እቃወማለሁ። አስሮ የገረፈህ ላልከው እኔ የገረፈኝ የለም አንተ ታስረህ ተገርፈህ ከሆነ በሬ ወለደና ሀሰት የምትቀባጥረው ተናገር።

   Delete
  8. The worst form of ignorance is spiritual ignorance. A person who did not read a single page / chapter from the Bible is full of confusion like you. Read the Bible , pray and ask the Lord for the truth. He will guide you. Do not remain ignorant.

   Delete
 36. Ayzoh wondime Ye tehadiso Diha Yelem....Ye ewunetegna kahinat diha enji.....You will drive .Rav 4 , Vx etc if u are in tehadiso......hahahaha
  By the way, if this is not a story, tell me your name and will check out that.....Endihu Befetera Teret Yemineda yale Endayimesilh. Hidina le aba sereke nigerachew.....TEHAAAAADIIIIISOOOOO

  ReplyDelete
 37. The man who posted this history was given the name 'menafik' before he join 'tehadiso'. But some people who put their comments above are saying that he said he was 'tehadiso' from the begining. Because of this, i doubt your reading skill. There fore, i recommend you to read the text once again. " . . . በመሠረቱ እኔ ግፍን ስቀበል ተሐድሶ አልነበርሁም ተሃድሶ የተባልሁበት ነገር ምንድን ነው? ብዬ ሳጠና ግን ተሐድሶ ሆንሁ። . . . "

  ReplyDelete
 38. ከቤ/ክር ጉያ የተነሱ የበግ ለምድ የለበሱ ሳይቀደሱ የተቀደሱ የሳጥናኤልን ተንኮል የወረሱ ከዘርዐ ያዕቆብ
  እንዲሁም ከግራኝ የማይተናነሱ መንፈሳዊ ህግን የሚያፋልሱ የሚቀውስላቸው ቢገኝ ቀውሰው የሚያቀውሱ
  በዘመናችን የረዥም ርቀት መሣሪያ አሻግረው የሚተኩሱ ነገረኞች አሕዛብ ተቋቁመው ሁሉን በማወክ ላይ ይገኛሉ። እንዚህን አረመኔዎች ለመቋቋም ተገፋሁ የሚል ሰው አማራጩ ዝርዎሙ ለአሕዛብ እለ ይፈቅዱ ቀትለ የነገር ጦረኞችን በረቀቀ አውሎ ነፋስ በትናቸው በማለት ለፈጣሪ መንገር ተገቢ ነው።

  ReplyDelete
 39. ከቤ/ክር ጉያ የተነሱ የበግ ለምድ የለበሱ ሳይቀደሱ የተቀደሱ የሳጥናኤልን ተንኮል የወረሱ ከዘርዐ ያዕቆብ
  እንዲሁም ከግራኝ የማይተናነሱ መንፈሳዊ ህግን የሚያፋልሱ የሚቀውስላቸው ቢገኝ ቀውሰው የሚያቀውሱ
  በዘመናችን የረዥም ርቀት መሣሪያ አሻግረው የሚተኩሱ ነገረኞች አሕዛብ ተቋቁመው ሁሉን በማወክ ላይ ይገኛሉ። እንዚህን አረመኔዎች ለመቋቋም ተገፋሁ የሚል ሰው አማራጩ ዝርዎሙ ለአሕዛብ እለ ይፈቅዱ ቀትለ የነገር ጦረኞችን በረቀቀ አውሎ ነፋስ በትናቸው በማለት ለፈጣሪ መንገር ተገቢ ነው።

  ReplyDelete
 40. The so called MKS is the ISIS terrorist version of the ETOTC. Their leaders love stage and lime lights.They demonize any one who has a different opinion from them. who is Daniel? who give him the mandate to judge other ? Look up Professor Mesfin reply on his account. My dear Yeneta, Please stick to your principles. Do not give any attention to these cone heads. They have started to disseminate and are heading down to the hell hole.

  ReplyDelete
 41. ዳኒ ፒክቸርሽን አየሽው ጥርግ በል የምትይ ነው የምትመስይው፡፡ ስንቱን ጠርገህ ጠርገህ መጨረሻ ማቅ አንተንም ጠረገህ፡፡ በጣም የምታሳዝን ሰው ነህ

  ReplyDelete
 42. Complete crap.....meregea....wore sayihone merega.......fiction bitistife yawatahal........lelae bikere simihin enkwane menager ferah be'gazetta yewotta simihin......gobez ke'honki gazetawe yewotabetin ken astawusen.........alubalta manafes hilinahin sikochew yinoral.....

  ReplyDelete
 43. betekirstiyan bezih gize kaluat enkuwoch mekakel andu Dn Daniel mehonu yemaykad haq new.

  ReplyDelete
 44. I think it is pretending .yemasmesel ..neger yalew yemeselal .it is not true.

  ReplyDelete
 45. teret tert were alebeh ande sew enkwan ende dani yelem were betabezu alsemam weregoch menafekan sebeseb rasachun adesu leba hula

  ReplyDelete
 46. God will lift you up brother. Trust me, the end of so called mahibere kidusan is coming soon after may 2015. Just wait and see. Hailemariam is cooking a delicious meal for this evil mahiber. By the way, daniel is no longer member of mahibere kidusan. He disbanded that mahiber to save his life in the near future.

  ReplyDelete
 47. wow this is disturbance word that is bullish et

  ReplyDelete
 48. ወገኖቼ፤ ዳንኤል ስንት ከሥራ ያፈናቀለው፣ ስሙን ጥላሸት እየቀባ ያስጠቆረው፣ ከዕለት ጉርሱ ያሳገደው፣ ቆሎ ቆርጥመው ደበሎ ለብሰው፣ ለ’በእንተ ስማ ለማርያም’ ከውሻ ተፋልመው (ዛሬ ዳንኤልና ግብረ አበሮቹ “የአብነት ትምህርት” እያሉ የሚነግዱበት) ከአሥርት ዓመታት በላይ መተኪያ የሌለውን ዕንቁ የቤተክርስቲያን ትምህርት ተምረው እናት ቤተ ክርስቲያንን በሙሉ አቅም እንዳያገለግሉና የእግዚአብሔር ቃል ሊሮጥ የሚገባውን ያክል ቃሉን ለተጠሙ ፈጥኖ እንዳይዳረስ እንቅፋት፣ መሰናክል መሆኑን ያልተረዳ አለ ማለት ያስቸግራል። ምናልባት ገላ በልብስ እንደሚሸፈን እኩይ ምግባርም በምላስና ላይ ላዩን በተሰጠ ስም ሊሸፈን እስከ ቻለ ድረስ ክብደት ላይኖረው ይችላል። ከሁሉም የሚያሳዝነው ዳንኤልና ወንድሞቹ እድሜ ለአቡነ ጎርጎርዮስ ለተልእኮ በሚል በዝዋይ የካህናት ማሰልጠኛ ክረምት ክረምት ት/ቤት ሲዘጋ ለሥስት ወራት በሚሰጥ ስልጠና ሊሸከሙት ከሚችሉት በላይ ባከናነቧቸው ስመ ዲቁና መጫወታቸው ነው። ለመሆኑ ተንሥኡ ብሎ አፉን ማላቀቅ ይሞክርና ነው በተሰደደበት አሜሪካ ልብሱን ለብሶ መቅደስ የገባው!? አቤት የዳንኤል ድፍረት ለሰሚም ግራ ነው? ? ? ዳንኤል ከባህር ዳሯ የልጅ እናቱ “ዓለሚቱ” ከአብራኩ ከተከፈለችው ልጁ እና ማንነቱን ከሚያውቁት አብሮ አደጎቹ ተሰውሮ በእንጦጦ ኪዳነ ምህረት በተክሊል ሲያገባ ዓለምን ሁሉ ከሚያየው ምሉእ በኩለሄ ሁሉን ቻይ አምላክ ዕይታ ሊሰወር እንደ ሚችል ምን ያክል ርግጠኛ ቢሆን ነው? የማያውቀው ሰው ‘ዲያቆን’ ተብሎ ሲጠራ ያው ዲያቆን ነው። ምናልባትም ዲያቆን በሚለው ስሙ ብቻም ይሆናል አሜሪካ ከመጣ በኋላ ና ግባ እንጂ ቀድስ ሲሉት ገመናውን ደብቆ በድፍረት መቅደስ ገባው፣ ከአገልግሎትም በኋላ በዚያው ልብስ መድረክ ይዞ ለስብከት አውደ ምሕረት ላይ የቆመው። የአብሮ አደጎቹ ዓይን እኮ የትም ይከተለዋል፤ አሁንማ እድሜ ለቴክኖሎጂ። ከአብሮ አደግህ አትሰደድ በሚለው መርህ ድሮ የሚያውቃቸውን ከአጠገቡ ስላራቀ የማያዩት መስሎት ካልሆነ በስተቀር። እና ይህን ሁሉ ጉድ ተሸክሞ አባቶችን ሲገዳደርና እርሱን ያልደገፉትን ሁሉ ተሐድሶና መናፍቅ እያለ በሰላ ምላሱ ሲያዋርዳቸው ይሉኝታና ሀፍረተ ቢስነቱ ለእርሱ ቀላል ነው። ፈሪሳዊነትንና ልብን ሳያጠሩ በሕያው አምላክ ቃል መጫወቱ - የመውጊያውን ብረት ብትቃውም ለአንተ ይብስብሃል ነውና!!!

  ReplyDelete
 49. አንተ በቆሎ ትምህርት ቤት ከተማርከዉ ሁሉ በደንብ የገባህ ልመናዉ ስለሆነ ዲስኩርህ ደካማዉን ለመሳብ ዓመታት የፈጀብህ ይመስላል ግን በአንተዉ ጽሁፍ የመጨረሻ ማንነትህን ገለጽከዉ አሁን እከሌ እንዲህ አለኝ ለማለት ምን አስፈለገህ አንተማ ሳትፈልግ የመነኮስህ ሳትማርም የተማርክ የድንግል ማርያም ልጅ ምህረቱን ይስጥህ አሁን ሌላዉን ለማየት የሚቃትቱ አይኖችህ ምህረት ስታገኝ እራስህን ማየት ትጀምራለህ !!

  ReplyDelete
 50. yemigerm yehiwote tarik aleh gojjam teweldeh kekolo temarinet ethih deresh. betam tigermaleh. wusha chohobachew balege tesadboachew yemimarut lemnfkna sayhon ewketn, emnetn ke mgbar tenkiko bemawek yewengel arbegna ,yebetekirstian tekorkoary bemehon erasachewnna wegenochachewn kenetaky tekulawoch tebkew lemenorna mengste semayatn lemewres engy bemenafkan tedelilo kissun lebirr hodun lemsr angetun lekerabat asgezto midrawi hiotn bicha lemenor aydelem .tigermaleh masmesel tichlaleh.

  ReplyDelete
 51. ቀኑ ዛሬ ኦክቶበር 2ዐ/2ዐ15 ነው ይህንን የተናገረው ሰው እንግዲህ 9 ወር ሆነው፡፡ የሕይወት ታሪኩን ለመጻፍ 9 ወር አልበቃ ብሎ ነው ወይስ ሞቶ ነው? ይገርማል፡፡ ይህ ብሎግ የሰው ስም እየተጠቀመ ልብ ወለድ ሁሉ መፃፍ ጀመረ እንዴ? ለየት ያለ አቀራረብ ነው፡፡ ምክንያቱም እንደዚህ አይነት ልብወለድ እስከአሁን በዚህ ዓለም ሰምቼ አላውቅም፡፡እኔ ምለው በዚህ ብሎግ ውስጥ የሰው መብት የሚባል ነገር የለም እንዴ? አሁን እንግዲህ እነዚህ ናቸው ቤተክርስቲያንን እናድሳለን በለው የተነሱት? ዛሬ አህዛብ እንኳን ለሰው መብት አይደለም ለእንስሳት መብት እየተቆረቆሩ እያየን ዛሬ የዚሁ ትውልድ የእፍኝት ልጆች ስማቸው መቼም አይከለከል ክርስቲያ ነን ነው የሚሉት፡፡ በእውነቱ የቱ ጋር ይሁን ክርስቶስ የሰው ልጅ ስም እየጠራ ሲጎድፍ የሰማነው፤ ኧረ የቱ ጋር ነው ሐዋርያት እንደዚህ አይነት ወንጌል ያስተማሩት፡፡ አይ አባ ሰላማ፤ አሁን እርሶ ወንጌል በሰበኩባት ምድር ስሞት እነዚህ አልባሌ ሰዎች ወድቆ እናግኘው፡፡ አይ አባቴ በረከቶት ይደርብኝና፤ እነዚህን ሰዎች የሰማይ አምላክ እንዲፈውሳቸውና ማዳኑን ልኮ ንስሀ እንዲገቡ ማስተዋል እንዲሰጣቸው በምልጃዎት አይርሷቸው፡፡ አልፋና ኦሜጋ፣ ኤልሻዳይ፣ አዱናይ፣ ያህዌ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን የስድብ መንፈስ ያንሳላችሁ፡፡ አሜን፣

  ReplyDelete
 52. It is commonly happening but God shall comfort those who suffered such a sabotage. I advise Daniel to stop and confess his wrong doing.

  ReplyDelete
 53. were alebih allah yanisalih abo!

  ReplyDelete
 54. እነ አርዮስም እስከሚወገዙ ድረስ ጳጳስ ነበሩ፡፡በቃ ብዙ ነገር አያስፈልግም መታደስ ያለበት ያንተው አእምሮ ነው እንጅ ኦርቶዶክስ አይደለቺም።ተሃድሶነትህን ማመንህ መልካም ሆኖ ሳለ ዳንኤል ክብረትን ለምን ትወቅሳለህ ቤተ ክርስቲያንም አላባረረች ህም እራስ ህ አሻፈረኝ ብለህ ከህይወት መንገድ ወጣህ እንጅ። መናፍቅ ለምን ልብ ወለድ የሚል ርዕስ አት ሰጡትም ማለቴ ያሁኑ ወጣት ልብ ወለድ ይወዳል እና ብዙ ሰው እንዲያነብላችሁ iiiiiiiiiiiiiየወሬ ቋቶች! ደግሞ ጎጃም ዉስጥ እንደዚህ አይነት መናፍቅ ተገኝቶ አያውቅም እሽ። የሃገሬን ስም አታጥፉ በህግ አምላክ ብያለሁ እኛ ጎጃሞች በሃይማኖት እንጅ በመናፍቅነት አይደለም የምንታወቀው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. endia belilign yehagere lig oh!!!!!! manim kehadi lemasmesel gojjam new yeteweledhut aybel

   Delete
 55. ሁሉን አዋቂ ቅዱስ እግዚአብሄር ነው! ቅዱስ እግዚአብሄር በዓለማዊ የኑሮ ሚዛን ተመዝኖ የሚመለክ አይደለም! ቅዱስ እግዚአብሄርን ለማምለክ የግድ አገልጋይ መሆን አይጠበቅብህም ወይም የእምነት ተቋማትን ማቀያየር አይደለም በጽናት የእውነትን ባለቤት የቅዱሳኑን አባት መጠበቅ እንጂ ማንም እራሱን እንደ እውቀት ባለቤት የሚቆጥር እራሱን እንዲህ ነኝ ብሎ በአደባባይ የሚገልፅ ፈጣሪውን አያውቀውም ሊያውቀውም አይችልም ደግሞም ታሪኬን ሳልጽፍ አትበል ታሪክህ ተጀምሮ የተቋጨው በድንግል ማሪያም ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ቅዱስ እግዚአብሄር ሁላችንንም ይርዳን! አሜን!

  ReplyDelete
 56. betam yemigerem hiwot new yasalefkew. hulum neger yemihonew lebego new. geta kante gar yehun

  ReplyDelete
 57. wanaw neger ante be geta tamneh menor new yalebeh.

  ReplyDelete
 58. please being and save yourself rather than being a philosopher it is not expected from true believers as well as insulting is the way of Devil.

  ReplyDelete