Saturday, January 17, 2015

የክርስቶስ ሰምራ ክንፎች

Read in PDF

እኔ ካነበብኋቸው መጻሕፍት እንደተረዳሁት ባገራችን በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክንፍ አውጥተው የሚበሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ። እነርሱም አንደኛ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሁለተኛይቱ ክርስቶስ ሰምራ ናቸው። ሁለቱም የቡልጋ ተወላጆች የነበሩ ሲሆን በሥጋም ዘመድ መሆናቸውን ገድላቸው ይናገራል። ክንፉ የዘር ይሆን የታምር ለተመራማሪዎች ትቼዋለሁ።

 የተክለ ሃይማኖት  ስድስት ክንፎች አበቃቀል ሁለት ዓይነት ታሪክ ያላቸው ሲሆን አንደኛው ሰባት ዓመት ቁመው በመጸለያቸው እግራቸው ስለተቆረጠ ክንፍ ተሸለሙ ይላል። ሁለተኛው ግን ደብረ ዳሞ ላይ ሰይጣን ገፍቶ ሊጥላቸው ሲሞክር ክንፍ ተሰጧቸው ስለበረሩ ሳይወድቁ ቀርተዋል የሚል ነው። እዚህ ላይ ጥያቄ አለኝ የተክለሃይማኖት ክንፎች መቼ በቀሉ? ትክክለኛውን ታሪክ አጥርታችሁ ንገሩኝ? ሁለተኛው ጥያቄዬ የተክለ ሃይማኖት አጥንት ከተቀበረበት ወጥቶ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ተቀምጧል ክንፎቻቸው የት ሄዱ? እነዚህን ጥያቄዎች ዳንኤል ክብረት ቢመልስልኝ ካልተቻለ ግን ማንኛውም ሊቀ ሊቃውንት ይመልስልኝ። እኔ ግን ወደ ክርስቶስ ሰምራ ክንፎች ትንታኔ ላቅና። በመጀመሪያ ስለክንፎቿ የሚተርከውን ክፍል በግእዝ ልጻፍላችሁና ከዚያ በአማርኛ ልተርጉምላችሁ እናንተ ግን ምዕራፍና ቁጥሩን ከመጽሐፈ ገድሉ በማንበብ የበለጠ እንድትረዱልኝ እጠይቃለሁ።
 "ወሶቤሃ ሠረፁ ላዕለ ሥጋሃ ስድስቱ አክናፍ ሠለስቱ በየማና ወሠለስቱ በጸጋማ። ወሶበ ሰፍሐት ዘይንእስ ክነፊሃ በጽሐ እስከ ደብረ ዳጋ። ወለእለ ይልሕቁሰ አክናፊሃ ኢያእመረት ብጽሐቶሙ። ወበኅሊናሃሰ ሐለየት እንዘ ትብል አይቴ ያበጽሑኒ እሙንቱ አክናፍ። ወእንዘ ትሄሊ ከመዝ አውስአ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይቤላ ምንተ ትሄልዪ ክርስቶስ ሰምራ ፍቅርትየ። ወትቤሎ ትሄሊ አመትከ እንዘ ትብል አይቴ ያበጽሑኒ እሙንቱ አክናፍየ። ወይቤላ ሶበሰ ፈቀድኩ በሥልጣነ መለኮትየ እምጽንፍ እስከ ጽንፍ እምአብጽሑኪ ክልኤቱ እምኔሆሙ። ወባሕቱ ለክብረ ዚአኪ ረሰይኩ ለኪ እሎንተ ስድስተ አክናፈ ከመ አርባዕቱ እንስሳ መናብርትየ። ወእሙንቱሰ አክናፍ ምሉዓን አዕይንት ወኍላቈሆሙ ዐሠርቱ ምዕት ወሥዑል ውስቴቶሙ ሥዕለ ኪሩቤል። ወሶበ ከሠተ ዓይኖ አሐዱ እምኔሆሙ አብርሃ ኩሎ ዓለመ ከመ ፀሐይ። ርእዩኬ አበውየ ወአኃውየ ዘመጠነዝ ጸጋ ዘአሰርገዋ በአክናፈ ስብሐት ከመ አርባዕቱ እስንስሳ መናብርት።” ገድለ ክርስቶስ ሰምራ ዘጥር ም 1፥64-74።

ግእዝ ለማትችሉ ይኸውላችሁ አማርኛ ትርጉሙ
"ከዚህም በኋላ ስድስት ክንፎች በሰውነቷ ላይ ማለት ሦስቱ በቀኝ ጐኗ ሦስቱ በግራ ጐኗ በቀሉ። አነሥተኛ ክንፎቿን ብትዘረጋቸው እስከ ደብረ ዳጋ ደረሱ። ትላላልቅ ክንፎቿ ግን የት እንደሚደርሱ ለማወቅ አልቻለችም። በሐሳቧም እነዚህ ክንፎች የት ያደርሱኝ ይሆን? ኃይላቸውስ እስከምን ድረስ ነው አያለች አሰበች። እንደዚህ እያለች በምታስብበት ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ ወዳጄ ክርስቶስ ሰምራ ሆይ ምን እያልሽ ታስቢያለሽ አላት። እስዋም እነዚህ ክንፎች ከየት ወደ የት ያደርሱኛል እያለች ባሪያህ ታስባለች አለችው። እሱም ከነዚህ ስድስት ክንፎች ሁለቱ ክንፎችሽ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ እንዲያደርሱሽ በመለኮታዊ ሥልጣኔ ባዘዝኳቸው ነበር። ነገር ግን ክብርሽ የጌትነቴን ዙፋን እንደተሸከሙ እንደ ኪሩቤል ክብር ይሆንልሽ ዘንድ እሊህን እነዚህን ስድስት ክንፎች ሰጠሁሽ እንጂ አላት። እነዚህም ክንፎች በዓይን የተሞሉ ነበሩ የዓይኖችም ቍጥር አንድ ሺህ ነው በላያቸውም የኪሩቤል ስእል ተስሎባቸዋል። ከነዚህ ዓይኖች አንዱ በተገለጠ ጊዜ እንደ ፀሐይ ብርሃን ዓለሙን ሁሉ ያበራል። አባቶቼና ወገኖቼ ሆይ የጌትነቱን ዙፋን እነደተሸከሙ እንደኪሩቤል በአክናፈ ክብር እንዳስጌጣትና በልዩ ችሮታው እንደሸለማት ተመልከቱ።
 ይህን በእግዚአብሔር ስም የተቦለተ ቧልት ያነበበ፣ ባገራችን እግዚአብሔርን የማይፈሩ ሰዎች የበቀሉት ገና ድሮ መሆኑንና የእነርሱ እርግማን እስከዛሬ ድረስ ወድቆብን እንደሚገኝ የማይገነዘብ ያለ አይመስለኝም። ነቢዩ ሕዝቅኤል ሐስትን ስለሚናገሩ አሳቾች እግዚአብሔር የተናገረውን እንዲህ ጽፎታል "እግዚአብሔር ሳይናገር ነቢያቶችዋ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እያሉ ከንቱን ራእይ በማየት የሐሰትንም ምዋርት ለእነርሱ በማምዋረት ያለ ገለባ በጭቃ ይመርጓቸዋል።” ሕዝ. 22፥28፤ ያለ ገለባ የተቦካ ጭቃ ግድግዳ ላይ ቢለጥፉት እየተንሸራተተ ያስቸግራል። በሐሰት ላይ የተመሰረተ መገለጥ፣ ትምህርት ወይም ታሪክም፣ ተንሸራታች ትውልድ ያፈራል እንጂ የተባረከ እውነተኛ ዜጋ አያስገኝም። እንዲህ ዓይነቱን ጭቃ በቤተ ክርስቲያን ሲለጥፉ የኖሩ ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ የዋሹ ከንቱዎች ናቸው።
   በዛሬው ጊዜ እንኮራባቸው፣ እንሳለማቸው፣ እንስማቸው የነበሩ ገድላት በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ አንገት የሚያስደፉ ማፈሪያዎች ሆነው አግኝተናቸዋል። ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ቤት ለማቆም ብንሳደብ፣ ብንደባደብ፣ አዳዲስ ትርጉሞች ብናመጣ፣ የጉዞ ማህበር ብናቋቋም፣ ሻማ ብናበራ፣ ታሪክ ብንተርክ፣ ታላላቅ ጉባኤዎችን ብናካሂድ ያለ ገለባ የተመረገ ጭቃ ስለሚበዛ ከመንሸራተት አልዳነችም። ኦርቶዶክስን እንደ ቤት ለማቆም ተሐድሶ ከማድረግ በቀር አማራጭ የለም። እንደዚህ ዐይኑን ያፈጠጠ፣ ጥርሱን ያገጠጠ ውሸት ይዘን እንኳንስ አዳዲስ አማኝ ልናመጣ ያለውንም ይዘን መቆየት አልቻልንም። አዳዲስ ሃይማኖት ከውጭም ከውስጥም ሲፈለሰፍ የመጀመሪያው ተቀባይ ኦርቶዶክሱ ነው። ፕሮቴስታንት የሆነው፣ እስላም የሚሆነው፣ ጀሆባ፣ ኦንሊ ጅሰስ፣ በሃኢ፣ ወዘተ እየሆነ ያለው የኛው ያለገለባ የተመረገው ጭቃ ነው።
"ከዚህም በኋላ ስድስት ክንፎች በሰውነቷ ላይ ማለት ሦስቱ በቀኝ ጐኗ ሦስቱ በግራ ጐኗ በቀሉ። አነሥተኛ ክንፎቿን ብትዘረጋቸው እስከ ደብረ ዳጋ ደረሱ”
ይህ አባባል ያለ ገለባ የተመረገ ጭቃ አይደለምን? ክርስቶስ ሰምራ ያበቀለቻቸው እነዚህ ስድስት ክንፎች እርሷ ጸለየችበት ከተባለው ደብሯ እስከ ዳጋ እስጢፋኖስ ይደርስ ነበር ተብሏል። ይህም ቢሆን በጣም ትንሹ ክንፏ ነው። ሌሎች ክንፎች ግን እስከ ምድር ዳር የሚደርሱና አንድ ሺህ ዐይኖች ያሉባቸው ናቸው። ሰው ሥጋ ለባሽ የአዳም ልጅ ነው አሞራ ሊሆን አይችልም። ይህን ታሪክ የጻፈ ሰው እንዴት በዲያብሎስ ወጥመድ ተይዞ ወገኔንም አጠመደ? ይህ ሁሉ የተጋነነ ክብር በክርስቶስ ሰምራ ቃል ኪዳን መዳን ይቻላል ወደሚለው ክህደት ለመውሰድ እንደሆነ ከምዕራፉ መጨረሻ ላይ ማስተዋል ይቻላል።
“አባቶቼና ወገኖቼ ሆይ የጌትነቱን ዙፋን እነደተሸከሙ እንደኪሩቤል በአክናፈ ክብር እንዳስጌጣትና በልዩ ችሮታው እንደሸለማት ተመልከቱ።”
በማለት ወደ ዋናው ሐሳቡ ለመንደርደር ሲሞክር ተመልከቱ። አስገራሚው ነገር ጸሐፊው ሲዋሽ ክንፏ እስከ ዳጋ የሚደርስ መሆኑ እና እንዴት ትበራለች? ብለው የሚጠይቁ ትውልዶች ቢመጡስ ብሎ ሳያስብ መቅረቱ ነው። ነገር ግን እስከ ዛሬም ድረስ ይህ የሰይጣን ሥራ ያልተገለጠላቸው የዚህ ውሸታም ጸሐፊ ሰለባዎች የሆኑ ብዙዎች ናቸው። ይህች ክርስቶስ ሠምራ በአንድ ወቅት በእግዚአብሔር መንግሥትና በዲያብሎስ መንግሥት መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት ለማጥበብ የሞከረች ታዋቂ “ዲፕሎማት” ነበረች ይለናል ገድሏ። ዲያብሎስን ለማስታረቅ እግዚአብሔርን ጠይቃ ተፈቅዶላት ወደ ሲኦል ወርዳ ነበር፤ ዲያብሎስ ግን ጎትቶ ወደ ሲኦል ካወረዳት በኋላ በሚካኤል ጥረት ከሲኦል አምልጣለች በማለትም ሊያስቀን ይሞክራል ገድሉ። ዘመዷ ተክልዬም ሰይጣንን አመንኩሰው የደብረ ሊባኖስ አገልጋይ አድርገውት ነበር ሲል ገድለ ተክለ ሃይማኖት ም 48 ያጫውተናል። እኔ የምለው ግን ሰይጣንን ከጌታ ለማስታረቅ ይህን ያህል ጥረት ካደረጉ ወገናቸውን የጎጃምን ሰው ለምን ጠሉት? ገድለ ተክለ ሃይማኖት “ተክልዬን ለማጥፋት ጎጃም ጅብ ሆነው መጡ፣ ተክልየም ሲያማትቡባቸው ወደ ገደል ሰጠሙ” ይላል ጎጃሞች የሰጠሙበት ገደል እስከ ዛሬ ድረስ በደብረ ሊባኖስ ይጎበኛል። ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ “እምህር ለከ ሰብአ ኢትዮጵያ ዘእንበለ ብሔረ ጎጃም” ትርጉም “ከጎጃም በስተቀር ኢትዮጵያን በሙሉ ምሬልሃለሁ” ይላል። በክርስቶስ አምኖ የተጠመቀን ክርስቲያን ሕዝብ እንደገና በሌላ ቃል ኪዳን ጎጃምን አልምርም ብሏል ተብሎ መጻፉ ይህች ቤተ ክርስቲያን አላማዋ ምንድን ነው እንድንል ያደርገናል። ምን ነው ቅዱሳን ዲያብሎስን ሲያስታርቁ ወገናቸውን ጎጅሜውን ናቁ? ይህ ጥላቻ ዛሬስ ተቀይሮ ይሆን? በቅርቡ የሞቱት አቡነ ማቴዎስ የጻፉት መጽሐፍስ? ስለ ጎጃም ምን ይላል? ይህ ገድል የሚባል የፖለቲካ ሽኩቻ መቼ ይቆም ይሆን? እንግዲህ ጥላቻ ያገለላቸው ብሶት የወለዳቸው ጎጃሜዎች እንገንጠል ብለው ቢነሱ ማን ያቆማቸው ይሆን? ኧረ ተሃድሶ ያስፈልጋል ወገኖቼ! ሳይቃጠል በቅጠል!
 ስሙ ይህን ነውር የሚያውቁ መነኮሳትና ሊቃውንት ተብየዎችም እየሳቁ ይኖራሉ። የኑሯቸው መሠረት እንዳይናጋ በመፍራት ወንጌል እንዳይሰብክ ይታገላሉ። ወንጌልን የሚቃወሙት እንዳይጋለጡ ብቻ ነው። እኛ ግን ይህን ትውልድን ያጎበጠ ያገር ሸክም ከተሰቀለበት እያወረድን ሕዝባችን ቀና ብሎ እንዲሄድ እርዳታ ማድረጋችንን አናቋርጥም።
 እውነት ታሸንፋለች፣ ኢትዮጵያ ትነሣለች ክብር ሰማይና ምድርን ለሠራ ለክርስቶስ ይሆናል አሜን!
                          ተስፋ ነኝ

63 comments:

 1. It is a good idea.Evil men always write evil things for their evil plan but God knows man's heart and destroy all evil.
  Anyhow Gojjam is the bread bus key for all
  whoever eats her bread can be ingrateful

  ReplyDelete
 2. ባገራችን በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክንፍ አውጥተው የሚበሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ። እነርሱም አንደኛ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሁለተኛይቱ ክርስቶስ ሰምራ ናቸው። ሁለቱም የቡልጋ ተወላጆች የነበሩ ሲሆን በሥጋም ዘመድ መሆናቸውን ገድላቸው ይናገራል። ክንፉ የዘር ይሆን የታምር ለተመራማሪዎች ትቼዋለሁ።
  ሀ. በቃ እኔ ተመራምሬ አረጋግጨልሀለሁ። አረ ተው ተው የተአምር ነው
  ለ. ተው ባክህ የዘር ነው
  ሀ. የለ የለ የበረከት ነው
  ለ. እይይ ፓለቲካ ነው ስልህ
  ሀ. አንተ ደግሞ እምነት የለህም ማለት ነው
  ለ. እምነትማ አለኝ ተረት እንዳምን አልተጠራሁም እንጂ
  ኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪከ በሳቅ ነው የሞትኩት። አረ ባካችሁ አሳስቁኝ

  ReplyDelete
 3. o !! geraminew gena orthodox gudua yifelal

  ReplyDelete
 4. ባገራችን እግዚአብሔርን የማይፈሩ ሰዎች የበቀሉት ገና ድሮ መሆኑንና የእነርሱ እርግማን እስከዛሬ ድረስ ወድቆብን እንደሚገኝ የማይገነዘብ ያለ አይመስለኝም
  ይህን አንተ አልክ እኛ የእርግማን ቀንበር የወረደልን የኦርቶዶክስ ልጆች ነን አንተ ገና ከእርግማን ካልወጣህ በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ እመን ቅዱሳንን ማሳደድ አቁም ያን ግዜ የጌታ ትሆናለህ
  ጌታ በቀድሞ ስሙ ሳኦል(ቅ/ጳውሎስ) ለምን ታሳድደኛለህ ያለው እርሱን ስላሳደደው ሳይሆን የእርሱ የሆኑትን ቅዱሳኑን ለመግደል ሲያሳድድ ባገኘው ጊዜ ነው (ግብረሐወርያት)ን ግለጥና አንብብ ።
  ስለራስህ ሐጢያት ዞር ብለህ አልቅስ በአፍህ ብቻ ስለመዳን ስላወራህ የምትድን እንዳይመስልህ ለራስህ ተጠንቀቅ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ! ምንም ምርጫ የለንም እውነትን ከመቀበል ውጪ፡፡ እንደዚህ አይነት አሳፋሪና አንገትን የሚያስደፉ ብዙ ተረቶች ታቅፈን ዘመናችንን ሁሉ እግዚአብሔርን ስንበድል ኖረናል፡፡ አሁን ግን ወደ እውነቱ ልንመለስ ግድ ይለናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳችንን ማነበብ ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡ ባለማንበባችን እንደመሃይም መስማት ብቻ ሰምተን ስንከተል አብረን ገደል ለገደል ስናዘግም ዛሬ እግዚአብሔር ደርሶልናል፡፡ እጅ እንስጥ!!

   Delete
  2. You said it nicely. Daniel Kibret menafik sil yeneberew..endeh afun sikefit semtot yihonal. Newur new bilgena new...yihe beblogm bihone yesew haymanot mesadeb new. It has no relation with preaching a bible. We didn't see a single miracle from protestant church but we have a lot from Ortodox. Lalibela ye miracle wutet new...for me it is more impressive and miracle than having a wing like t/haimanot or christossemra. There are a number of more miracles than this...so amenum alamenum yihe yegezer sira new. Ye lalibela hinsa ye miracle wute enji yesew sira ayidelem

   Delete
  3. Who gave you this 'Haymanot'? Do you think is that God? Do you think does God care about your 'Haymanot'? Never! God knows and wants to know everyone through the lord Jesus. Without him you're nothing for God with your damn 'Haymanot' and those TERETS. Yemanim kizhetamna denbara bekifu menafist eyeteneda yetsafewun ena yetenagerewun hulu sebsebeh yizeh letmote new ende? Kemetshaf kidus gar atamesakerm ende?Bible titeh esun zemenihin hulu setaneb selenork ahun minim bitibal mesmiya yelehim. Silezih, Please kechalk ezih blog lay kemetsafih befit BIBLE kuch bleh anbib. teregaga. Atchekul. Tewededem tetela sewu wedelibonaw simeles (geta yewust aynochachihun siyabera malet new) yihe hulu kotetakotet meragefu ayqerim. It's a matter of time bro! Yes, this will be a HISTORY. and Shameful history.

   Delete
  4. ለምን በእግዚአብሔር ሀይል የተደረገን ትቃወማለህ?January 20, 2015 at 9:14 PM

   አሁን ጥርጣሪዬ ከ እውነታው ደረሰ። የዚህ ብሎግ አዘጋጆች ማንነትና የእስከዛሬው ጥየቄይ ይህን ብሎግ በህግ እንሿን የሚጠይቀው እንዴት ጠፋ ለሚለው ዛሬ ተመለሰልኝ። አቶ ናሆም አርያስላሴ፦ ሁለት ጥያቄ አለኝና መልስልኝ። 1ኛ- መጽሐፍ ቅዱስን ማን ነው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ብሎ የሰጠህ? 2ኛ- መጽሐፍ ቅዱስን መጽሐፍ ቅዱስ ብሎ የሰየመው ማን ነው? እነዚህን ጥያቄዎች የጠየቅሁህ አንተ ይህን ሀይማኖት ማን ሰጠህ ብለህ ከአንተ ጽሑፍ በላይ ላለው አስተያየት ሰጭ ጥያቄ ስላሸረብሀ ነው። እሱ መልስ አልሰጠህም ምናልባት ማንነትህን ስላወቀ ከከንቱ መላፋለፍ ብሎ ይመስለኛል። ለሁሉም ግን በክርስቶስ የሆነችውን አንዲቷን ሀይማኖታችንን ያገኘናት ከአባቶቻችን ከቅዱሳን ሐዋርያት ነው። ማረጋገጫውንም በያዕቆብ 1፤ከ3-4 አንብበው። መጽሐፍ ቅዱስ አንብብ ላልከው የእሱን ለሱ እንተወውና አንተ ግን አንብበህ ጠፍህበት ሀሰተኛ መምህርም ሆንክበት እንጂ ህይወት አልሆነህም እኮ! ሌላወ አስገራሚው የጊዜ ጉዳይ ነው ስትል ለጊዜ እውነትን ማሳደድና ማጥፍት ሙሉ በሙሉ እንደልተሳካላችሁ ታረጋግጥና ነገር ግን በሀሰት ትምህርትህ እያወጂህለት ያለው ሐሰተኛው መሲህ እራሱን በሚገልጥበት ጊዘ በአለም ላየ እንደምትሰለጥኑ ተናገህ። አለም ለክርስቶስ አትመችምና እውነት ብለሀል እውነትን ከአሁኑ በባሰ የምታሳድዱበት ሰዓቱ መቃረቡ በምትፈጽሟቸው የጥፋት ምልክቶች እየተገነዘብን ነው። በቅዱሳን ስለተፈፀሙትና ስለሚፈፀሙት ታምራቶች መናገር ለአንተ አያስፈልግም። ምክንያቱም ለማመን ልብህ የተከፈተ አይደለምና ነው። አንተ እኮ መጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ተብሎ እንዴት እንደመጣ መመለስ በማትችልበት የእወነት መጽሐፍ ውስጥ ባይጻፍ ኖሮ ጴጥሮስ ሐናና ሰፒራን የቀጣበትን ታምር ነፍስ ገዳይነትና አሱንም ደም አፍሳሽ ማለታችሁ አይርም ነበር ነውና። ሆኖ ቅዱሳን በተሰጣቸው ፀጋና ሀይል በእምነት ገራ ተው ገተ ኢየሱስ ካደረጋቸው በላይ ብዙ ታምራቶችን ማድረግ እንደሚችሉ ይህን ተራራ ተነስ ብትሉት ይነሳል ሲል ገልጿል።

   Delete
 5. Igziabiher kinf mestet aychilim hoy lekidusanochu?

  ReplyDelete
 6. በተዋህዶ እምነቴ አላፍርምJanuary 18, 2015 at 2:31 PM

  ለማያምን ምንም ቢነገረው አያምንም። የዘመኑ መናፍቃን በአዲሱ መጠሪያቸው ተሐድሶ ተብየዎች የተነገራቸውን ባያምኑ አይገርምም። ምክንያቱም ላለማመን አስቀድመው ተወስነው እንዳይሁድ እውነትን ያሳድዳሉ። አይሁድ የእጁን ታምራት አይተውና ትምህርቱን ሰምተው ከማመን ይልቅ በለማመን ፀንተው ሊያድናቸው የመጣውን ጌታ ኢየሱስን ሰቅለው ነው የገደሉት። አሁንም አቶ ተስፋ ነኝ ባዩ ላለማመን ቆርጦ ተነስቶ አሳዳሪዎችንና መሰሎቹን ለማስደሰት ሲል በመንፈስ ቅዱስ የተሰጠን የፀጋ ስጦታ በስጋ አካል ካላየሁ አላምንም ብሎ የመንፈስ ቅዱስን ሥራና ስጦታ በባለጌ ብዕሩ ይሳለቅበታል። እኛ ኦርቶዶክሳውያን በክርስቶስ ቀንበራችን የተወገደልንና ሸክማችንም የተራገፈልን ስለሆነ ቀና ብለን የምንሔድ ኦርቶዶክሳውያን ን። አንተና መሰሎቻችሁ በስም አጥፊነት፣ በሐሰተኛ ከሳሽነት፣ በፀያፍ ስድቦች፣ እውነት የሆነውን ክርስቶስን በመካድ፣ እውነትን በመቃወም፣ በሴሰኝነት ፣ አለምንና ገንዘብን በመውደድ፣ በአጠቃላይ ባለማመን ሀጢያቶች የጎበጣችና ሸከምም የከበደባችሁ። ለናንተ ማንም የቤተክርስቲያን አገልጋይ መልስ አይሰጥ። ምክንያቱ ለመዳን አትፈልጉምና ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እጅግ እጅገ ያሳፍራል ተበራክ ይህን ጉዳችንን ስላወጣህ
   የሚገርምው በኦረቶደክስ አላፍርም እያለህ መመጻደቅህ ነው
   እነዲት አይነት አነገተ ደንዳና ነህ ባክህ?ከመሳደብ ይልቅ አግብብ ያለው መልስ በመጻህፍ ቅዱስ አስረጅነት አቅርብ
   ሃይማኖቴ እያልህ ስትመጻደቅ ሲኦል እንዳትገባ ንስሃ ግባ
   ክርሰቶስ በሞቱ የሰጠንን ዘላለማዊ ህይወት ክርስቶስ ወጋ የከፈለበትን ድህነት በእንደዚህ ያለ ያረጅና ያፈጀ ሰይጣናዊ ተረት አትጠመድ፡፡
   አነዚህ ርግማንን ያመጡ የሰይጣን ወጠመዶች የእግዚያብሄር የበቀል እሳት ሊወርድባቸው ጊዜው ደርሠዋል አሚን፡፡ስፍራውን አልፋና ኦሜጋ ለሆነው ክርሰቶስ ወደው ሳይሆን ተገደው ይለቃሉ፡፡


   Delete
  2. አቤት እዉቀት፣ትምህርት …. አፈሰስከዉ እኮ! ጨዋ ሂድና መጽሐፍ ቅዱስ አንብብ፡፡

   Delete
  3. Why too much talk & sideb?? just answer the damn question! When did aba tekleye get the wings? Was christos semra an eagle or a human? how can christos semra reconcile God and the fallen angel satnael?

   Delete
  4. ለanonymous January 20, 2015 10:48am
   እንግሊዘኛውን እኮ አንቆረቆርከው።ባለቋንቋዎችም እንዳንተ መናገርም መጻፍም አይችሉም። የሚያሳዝነው ግን ይሄን ችሎታ ይዘህ አሉባልታ አራጋቢና ያልተጻፈ አንባቢ መሆንህ ነው። ለምን ብዙ ወሬና ስድብ ብለህ ጠየቅህና እዛው ቀጥለህ ዝም ብለህ ለdamn ጥያቄው መልስ ትላለህ። ለመሆኑ የኛ የእንግሊዘኛ ፕሮፌሰር damn ማለት ምስጋና ነው ምርቃት? ተሳዳቢና ብዙ የምታወራው እኮ አንተው መሆንህን እራስህ መሰከርክ እኮ። ሌላው ክርስቶስ ሰምራ ሰው ናት መላክ ብለህ ትጠይቅና ተመልሰህ ደግሞ ክርስቶስ ሰምራ እንዴት ሰይጣንን ለማስታረቅ ሞከረች በማለት ለመጠየቅ ትሞክራለህ ? በመጀመሪያ ለጠየቅሐቸው ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ቅዱሳን እግዚአብሔር በሰጣቸው ፀጋና ሐይል ድንቅ ታምራቶችን ማድረግ እንደሚችሉና እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ ልዩ ልዩ ፀጋዎችን እደሰጣቸውና እንደሚሰጣቸው ማመን አለብ። ሰው ናት መላክ ላልከ፣ የምታጨበጭብለትን የእግዚአብሔርን ሰዎች ከተሰጣቸው ፀጋ ጋር የሚያንቋሽሸውን ጽሑፍ እንሿን ተመልሰህ ብታነበው መልሱን ታገኘዋለህ። ለማንኛውም ሰው ናት። ነገር ግን አንተና እሷ ከጾታ ባለፈ ትመያያላችሁ። እሷ የክርስቶስ ስትሆን አንተ ደግሞ የሐሳዊው መሲህ ባለሟል ነህ።

   Delete
  5. ለanonymous January 20, 2015 3:34am
   እኔ እውቀትም የለኝም አስተማሪም አይደለሁም ደስ ይበልህ። አንበ መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢው ግን አንብበክ እውቀት ብለህ የያዝከው የእግዚአብሔርን ሰዎች ከተሰጣቸው ፀጋ ጋር ስትንቅና ስታንቋሽሽ ነው የአየሁህ። የአንተ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ሐሰተኛ መምህር ሆነህ እየተሹለከለክህ ሐሰትን ተናገርህ እንጂ ህይወትን አላገኘህበትም። ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ፀጋ ስትንቅ ተገኝተሐልና ነው።

   Delete
  6. @ዳሞት
   Why bother to comment about the language in which I used to express my thought? Are you insecure? English is just a median of communication but you are one envious human being. A person is not judged by his or her tongue but by the level of intellect.

   Second, 'damn' is not a slander or sideb but rather an emphasis used to convey exasperation. You sound like you watch too many movies.

   Third, learn to read before you make a fool out of yourself, as you just did. 'angel' & 'eagle' are completely different terminologies. I used the latter defined as large bird with broad wings.

   Fourth, you didn't answer the original questions presented by the author so you're response is irrelevant.

   Delete
  7. ዋው!በጣም አንቆረቆርከው። አምስተኛ፣ ስድስተኛ ወዘተ ነጥቦችስ የሉህምን?ለምን አትቀጥልበትም ወዳጀ? ሐሳብህን መግለጽ ትችላለህ በፈለግከውቋንቋ። ግን ደግሞ ክርስትና ሆነና ቤተክርስቲያንም በውሸት ስማቸውን ከፍ ዝቅ እያደረጋችሁ የምታብጠለጥሏቸው የሚያደርጉትንና የሚናገሩትን አያውቁምና ይቅር በማለትና ብድራትን የሚከፍል እግዚአብሔር ነው ብለው ትተውት እንጂ በእያንዳንዷ ቃላቶታች በህግ ሊጠይቋችሁና
   ሊያስቀጧችሁ በቻሉ ነበር ፍርድ የማያጏድልም ዳኛ ካለ። አሁንም ገደቡን ያለፋችሁት ይመስላል። አንዲት ተቋምም ሆነች ግለሰብ የአመኑበትን እምነት በፈለጉት መንገድ ማመንና ማከናው የሚችሉበትን ነፃነት በህግ የተሰጠና የአንድን ተቋም የአምልኮ ስርዓት ደግሞ ማንቋሸሽና በፅሁፍ ማጥላላት በወንጀል የሚያስጠይ ነው። ሌላው እንግሊዘኛ ሚዲያ ነው ብለሀል። ምን የሚባል የሚዲያ እንበለው? የቲያትር ፤ የፊልም ወይስ ምን? ለእኔ እንግሊዘኛ ቋንቋ ነው። ቋንቋም መግባቢያ ነው። ዌብሳይቶችም ሚዲያ ናቸው። ሌላው በሚናገረው ወይም በምላሱ አይደለም ሰው የሚለካው በጭንቅላቱ ብቃት ነው ብለሀል።ታዲያ እኔም እኮ የእንግሊዘኛ ብቃትህ መጥቋል የቋንቋው ባለቤቶችም እንዳት አይጽፉም ነው የአልኩት። እኔ ደግሞ አንተ እንዳልከው ኢግልንና ኤንጅልን ምንነታቸውን የማላቅ ደደብ ነኝ። አሁንስ ደስ አለህ? አደራ የተለመደውን የአዳራሽ ድለቃህን መንገድ ላይ ሆነህ በደስታ እንዳታቀልጠው። እኔ ማንበብና ምንነታቸውን ባለማወቄ ተሳሳትሁኝ ታዲያ የአንተ ኢንቴሌክት ወንድምህ የጻፈውን አንብበህ ቁራ ናት የሚል አንብበሀልን ወይስ አንተ የአይምሮ ብቃት ውጤት የወንድምህን ጽሑፍ ቁራ ብሎ ያነባልን? ክርስቶስ ሰምራ ክርስቶስ በአምሳሉ የፈጠራት የእግዚአብሔር ሰው ናት። እሷን ቁራ የምትለ ከሆነ አንተም ትንሳኤ የሌለህ አዋፍ ቁራ ነህ ማለት ነው። በምግባር ግን አንተ ቁራ ክርስቶስ ሰምራ እርግብ ናት። Damn( ዳመን) ደሚለውን ቃል በጣም ተነተንከው እኮ ወዳጀ። ቱ ኮንቬይ ኤግዛስፕሬሽን ማለት ነው ያልከውን? ቁጣ ማስተላለፍ ፤ ብስጭት መግለጽ ወይስ ንዴትን ማንፀባረቅ፦ምን እንበለው ባክህ። ለእኔ ግን ቃሉ ከተገለጠበት ሐሳብ አንፃር የሚተረጎም ይመስለኛል። መልስ የጠየቅኸው ደግሞ የማጥላላትና የማንቋሸሽ ጥያቄዎችህ ነው። ማጥላላትም ማንቋሸሽም ሁለቱም ስድብ ናቸው። ደሞ መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ አይደለህ፤ ዳመን የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ የት እንደሚገኝ ብትነግረኝ ወዳጀ ኢንቴሌክት? ሌላው ከጂልነትህን ወይም ከቂልነትህ በፊት ለማንበብ ተማር ብለኸኛል ። እናም ኬጂ ገብቸ ፊደል ከሀ፤ ቁጥር ከዜሮ። እንግሊዘኛ ከኤ ጀምሬ አኛ አየዳከርሁልህ ነኝ። እንዲያው እንዳንተ ኢንቴሌክት እሆን ይሆን ወዳጄ? ተወው ይቅርብኝ ወዳጄ፤ ደግሞ ኢንቴሌክት ሆኘ ትንሽ ትልቅ ሳልል የስድብ አፍ ተቀብዬ ልዘልፍ፤ ካለ እምነቴ ምንም ሳላውቅ በስማበለው የሰው እምነት ለመበጥበጥ? ይቅርብኝ ኢንቴሌክት። መልስ ላልከው፦ ለማያምን መልስ ቢሰጠውም ለማመን አልተዘጋጀምና መልስ አይሰጠውም። አንተም ላለማመን ልብህን አደንድነሀልና መልስ የለም ኢንቴሌክት።

   Delete
  8. ዳሞት
   Mental capacity of a kid. Flee..

   Delete
 7. እግዚአብሔር ይስጥልን!! እንደዚህ ያሉ ብዙ ጉዶች ተሸክመናል፡፡ ከዚህ በላይ ምን የእርግማን ቀንበር አለ? የተክለሐይማኖት ገድልማ እግዚአብሔርን ከመሳደብ አይተናነስም፡፡ እሱ ይማረን!

  ReplyDelete
 8. yeaba tekilehayimanot..yeaba gebiremenfeskidus..yekirisitos semira...wezete teret teret..midiritu bechigir..besidet...bezeregnninet...bebiher tekefafilen behayimanit sim gora leyiten endinibala adirigonal...geta hoy bemihiret asiben.....yewegelih birhan bemidiritu yileqeq..hizbihin yasere kifu menfes beeyesus sim yetewarede yihun..amen..orthodox tewahido teketilalech..beorthodox sim yemigegnu teretateretoch yiwegedalu..!!

  ReplyDelete
 9. What is the weight and size of Tabot? In Atlanta, fake priest Yacob carried rectangular Samsonite seems like over weights. He got experience to carry objects from his daily Carrier of trucking Industry. The one he was carry the Tabot looks like over weight samsonite, when they were celebrating Timket. Reliable sources confirmed that Ergetkulla filled concrete inside the samsonite to hurt his opponent Yacob. Why they carried samsonite to cheat there own people?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ልንገርህ ማንነትህንJanuary 19, 2015 at 5:45 PM

   ለanonymous January 19, 2015 at 5:11AM
   ወንድም! ምን ይደረግ በሰው አምሳል ተፈጥረሀልና ወንድም ልበልህ እንጂ። ለመሆኑ እምነት አለህን?አለኝ ካልክ ለምን ያመንክበትን በአመንክበት ቦታ ሆነህ አትተገብርም? አሁን ተምሪያለሁ ተመራምሪያለሁ ፤ አውቂያለሁ መጥቂያለሁ ለማለት ነው ባልበሰልኸበት የእንግሊዘኛ ባህር ገብተህ የምታቃስተው። በእውነት የእንግሊዘኛው ባህር ውስጥ መግባትህ ምንም የማታውቅ ባዶ ደደብ መሆንህን ነው አፍጥጦ ያጋለጠብህ። ኬሪድ፤ ኬሪ እያልክ የምትዘባርቀው የሰው ስም ነው የእንስሳ? ስለ ሬክታንግልና ሳምሶናይት ያወቅኸው ዛሬ ነውን? ወይስ ከቤትህ ያለችው አንድ ሳጥንና የተቀዳደደች ሳምሶናዊት እንዳለህ አዋጂ አዋጂ እወቁልኝ ነው? የአዕምሮ ድሀ። ታቦትንና ስለታቦት መናከርን ክርስቶስ በደሙ ለዋጃቸውና ለአዳናቸው ለኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ተወት አድርግና እዛው ከአደራሽህ ገብተህ የቃልቻ ጉሪያህንና ጩኸትህን ከመሪዎችህ ፓስተሮች ጋር ሆነህ አቅልጠው። ሒድና እዛው በአዳራሽህ ከትመህ የወፍ ይሁን የአሞራ የማይተረጎምና የማይታወቅ ብቻ ከዲያብሎስ መንፈስ እየተናጣችሁ ሻላላላላላ ሯሟሟሟሟ የጉሪያ ቋንቋችሁ የሚውጥውን ፍለጋ እንደሚያገሳ አንበሳ አጉሩ። አዳራሹ አልሞቅ፤ የዲያቢሎሱ መንፈስም አልደሰት ካለህም የምቱ ምንነት በማይታወቀው የኦርጋናችሁ ወይም ፒያኗችሁ ምት ቲሪሪሪ አድርጉት። ሒድና ተረታተረትህን ድሪቶኸን እየደረትህ ረጌ ራጋ ፤ ካንትሪ ራምፕ ጭፈራ ድለቃህን ደልቅ። ሒድና ሸላላላለ ራሟሟሟሟ እያልክ በዳቢሎስ መንፈስ እያቧረቅህ በስቴጁና በየወንበሩ ስር ተንደፋደፍ። የየአዳራሾቻችሁ ጉድ የማይታወቅ እንዳይመስልህ። ባዶ ሆነኸ እንጂ ታቦት እንዴት እንደመጣ፣ ታቦት ማለት ምንማለት እንደሆነና በታቦቱላይ ስለተጻፉት ቃላቶችና ስለተሳሉት ስዕላት ብታውቅ ኖሮ የእግዚአብሔርን ነገር ባልተቃወምህ ነበር። ነገር ግን በጨለማው አበጋዝ በዚህ አለም ገዠ ዲያብሎስ እንዳታውቅ ታውረሀልና ሳታውቅ ትዘላብዳለህ። አዕምሮህና አንደበትህ እጂግ ገምቷልና ሰውም አያስቀርብምና ምናልባት ምድራዊ ዶክበር ችግርኸን ሊፈታልህ ከቻለ ወደ ሆስፒታል ጎራ በል ወንድም። የት እንዳትለኝ ምክንያቱም አንተ ያወቅህ የመጠቅህ እንግሊዘኛ ተናጋሪና ፀሐፊ ነህና።

   Delete
  2. ለልንገርህ ማንነትህን
   የስድብ ውድድር ቢዘጋጅ ኢትዮጵያን ወክለህ አንደኛ ትወጣ ነበር። ከዛ በተረፈ ግን ሀሳብህ ሁሉ ፍሬ ከርስኪ ነው። ጌታ ይፈውስህ። ቅዱስ ቃሉን የምታነብበትና እሱን ጠቅሰህ የምትናገርበትን ማስተዋል ይስጥህ

   Delete
  3. ልንገርህ ማንነትህን ነኝJanuary 20, 2015 at 8:05 PM

   እስቲ በናትህ አዘጋጅና እንወዳደር። ሀሳህ ሁሉ ፍሬ ከርስኪ ነው ያልከው አንተ ነጥረህ ባልወጣህበት የእንግሊዘኛ ቋንቋ የእግዚአብሔርንና የጣኦትን ነገር ሳታውቅና መጽሐፍትን ሳታስተውል የዘባረቅኸውን ቧልትና በእግዚአብሔር ነገር ላይ ያደረግከውን አመፀኝነት ስለመለስኩልህ ነውን? ደግሞ ጌታ ይፈውስህ ተባለልኝ። የትኛው ጌታ? እውነተኛው ከድንግል ማርያም የተወለደው ሰማያዊው ፈራጅ የሆነው ጌታ ኢየሱስ ወይስ የዚህ አለም ገዠ የቅዱሳን ጠላትና አሳዳጂ የሰው ልጆች ከሳሽ የሆነው ሐሳዊው መሲህ አንተ የምትገዛለት ምድራዊው ጌታ? አዎ ሰማያዊው አልፋና ኦሜጋ የሆነው ኤልሻዳዮ ጌታ የድንግል ማርያም ልጅ ከሆነ አሜን የሺ የፈውሰኝ ብያለሁኝ። ነገር ግን አንተ የምትበረከክለትና በየ አዳራሹ የሚያጏራህና በወንበሩ ስር ጥሉ የሚያንፈራግጥህ ገራ ገታ ኢየሱስ በመስቀሉ ድል አድርጎ የጣለው የምድር ገዠ የተባለው ምድራዊው ጌታ ከሆነ በእግዚአብሔር ስም ከእኔ ይራቅ፤ ጌታ ኢየሱስ ይገስፀው። አነ የእግዚአብሔርን ቃለ የማነበዉ በአመንሁበትና በተማርሁበት ለመጽናትና ለሚቃወሙኝ መልስ ለመስጠት ነው። አንተ መጽሐፍ ቅዱስን የተሸከምኸው ሐሰተኛ መምህር ሆነህ እንክርዳድን ለመዝራት አባትህ የሆነውን ሐሰተኛውን ክርስቶስን ለማወጂ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ማንብብ ብቻውን ማወቅ አይደለም። ምክንያቱም የህንደኬው ጃንደረባ የነብዩ ኢሳያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር ። ነገር ግን ፊሊጶስ ጃንደረባውን ተገናኝቶ የሚያነበው ታውቀዋለህ ሲለው ማን መርቶኝ አለው። እናም ስለምታነበው የሚነግር የሚመራህ ያስፈልጋል ማለት ነው። መስማትም ብቻውን አይጠቅምም ምክንያቱም ቃሉን የሚለንን የምናደርግ እንጂ የምንሰማ ብቻ እንዳንሆን መጽሐፍ ቅዱስ ቃሉን የምታደርጉ እንጂ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ ሲል ይናገረናልና ነው። በመጨረሻ የሀሰት ቄስ ብለህ መዝለፍሕስ እየመረቅሀቸው ይሆንን? ደግሞስ የቄስነት ማእረግን ሰጭ አንተነህን የሀሰት ቄስ እያልክ የምትዘላብደው? አንበንስ ማኔ ፈራጅ ዳኛ አድርጎ ሾመኸና ነው ሀሰተኛ ቄስ ብለህ የፈረጂኸው? አይ የኛ ቃሉን አንባቢና አስተዋይ!

   Delete
 10. አባ ሰላማዎች አሁንስግራ ገባቹ አላማቹ ኦርቶዶክሰን ማጣጣል ብቻ ነዉ እንዴ ማህበረ ቅዶሳን ከአቅማቹ በላይ ሁነባቹ መሰለኝ ሰሙኖን ተወት አርጋችሁታል እሰኪ አልፎ አልፎ መልካምነገሯንም መቼም እምነት የላችሁም ሕሊና ካላቹ ለ ሕሊናቹ ሰትሉ ፃፉ እሰኪ ለመላዉ ኦርቶዶክሳውያን እነኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ

  ReplyDelete
 11. በተዋህዶ ሀይማኖቴ አላፍርምJanuary 19, 2015 at 9:08 PM

  ለአንባቢውና የአሉባልታ እንዲሁም የክህደት ድሪቶ ተረት ደራቹ
  አቶ ቀቢፀ ተስፋ፦ ተስፋ የጎረጥህ መሸነፍኸንም ያመንክ ትመስላለህ። ምክንያቱ ውጊያህ ሁሉ ከሀያሉ ጌታ ከእግዚአብሔርና ከሰራዊቶቹ ቅዱሳን ጋር በመሆኑ። አሁን አንተ አነበብክና መጠቅህ ማርስ ላይ ወጣህ ማለት ነው። አይ ግብዝነ
  ት! ለሐዋርያውም ሕግን ከገማልያ እግር ስር ሆኖ መማሩና ሕግን
  ማወቁ አልጠቀመውም። የክርስቶስ ባሪያዎችን ሲያሳድድ፣ ካለ
  ህግ ሲያስርና ሲገርፍ በደማስቆ ጌት ኢየሱ ተናገረው
  የመውጊያውን ቀስት ቢቃወም ለእሱ እንደሚብስበት። አንተም
  ፊደል ቆጠርኩና አነበብኩ በማለት የእግዚአብሔርን ሀይል
  የመንፈስ ቅዱስን ጥበብና ፀጋ በምድራዊ የእውቀት ሚዛን
  እየመዘንህ ማናናቅህና መቃወምህ ለአንተው ነው እዳው
  የሚብስብህ። አንዲት ጥያቄ ልጠይቅህ፦ስንት መጽሐፍት
  አንብበሀል አቶ ቀቢፀ ተስፋ? ሌላ የተናገርከው በዘር ነው ክንፍ
  የሚሰጠው ስትል አለማዊነህና የአለማዊ ቋንቋህን የዘር ድሪቶ
  አንስተሀል? እስቲ እኔ አንተን ልጠይቅህ አንባቢው ቀቢፀ ተስፋ፦
  ቅዱስ ጴጥሮስ ከነወንድሙ እንድርያስ፤ ቅዱስ ያዕቆብም
  ከነወንድሙ ከዩሐንስ ሐዋርያ የሆኑት በዘር ነውን? አይ የማንበብ
  እውቀት!አንድ ስንዝር ወደ ሕይወት የማያቀርብ የፊደል ውጊያ
  የቃል ስሕተት ጥርቅም። ሌላውየጻድቁ የአቡነ ተክለሀይማኖት
  አጥም ከተቀበረበት ወጥቶ በቤተ መቅደስ ተቀምጧል ክንፎቹ
  የትሄዱ የሚል የእግዚአብሔርን አገልጋዮች ለመፈተን የሚመስል
  የእግዚአብሔርን ፀጋ ከስጋ ሞት በኋላ ከስጋ አካል ካለየሁ የሚል
  ያለማመን ጥያቄ ጠይቀሀል። እስቲ አንባቢው አቶ ቀቢፀ ተስፋ
  የሐዋሪያው የቅዱስ ጳውሎስ ቀሚስ አጋንትን ታወጣ ነበና ያች
  ቀሚስ ሐዋርያው ጳውሎስ በስ አርፏል ቀሚሱ ግን ወዴት አለች?
  አልቃለች ካልከኝ መቸና እንዴት? ሌላው ለታምር ተመራማሪዎች ትቸዋለሁ የሚል የንባብና የእውቀት ብልጭታ ምጥቀትህን ተውነሀል። ብራሾ አንባቢ! ከየትኛው የአነበብከው መጽሐፍ ይሆን የታምር ተመራማሪዎች እንዳሉ ያነበብከው? ታምርስ በምርምር ይደረስበታል እንዴ? ካልክም እባክህ ልለምንህ አቶ ቀቢፀ ተስፋ ፍሊጶስን መንፈስ እንዴት እንደነጠቀው የታምር ተመራማሪዎችህን ጠይቅና ንገረኝ። ይሔን ከመለስክልኝ በኋላ ደግሞ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዴት በባህር ላይ እንደተጓዘን ታምር ተመራማሪዎችን ትጠይቃለህ እሺ አንባቢው። ሌላው ክንፎቹ መቸ በቀሉ የሚል የእውቀትህንና የአንባቢነትህ ጥልቀት የሚያሳየውን ጥያቄን
  ጠይሀል። በመጀመሪያ መሰጠትና መብቀል በምንም ሁኔታ አለመገናኘታቸውን ጠይቀህ ተረዳ። አንተን ልጠይቅህና ፍሊጶስ በመንፈስ የመነጠቅ ፀጋ መቸና በስንት ሰዓት እንደተሰጠው እንድትመልስልኝ እፈልጋለሁኝ? እንዲመልስል የጠየቅኸውም ሆነ የትኛውም የቤተክርስቲያን ሊቅ ለአንተ በእኔ እይታ ስለሁለት ምክንያቶች አይመልስሉህም። 1ኛ፦ አንተ አውቀህ የካድህና ለማመንም የማትፈልግ የፈሪሳውያን ልጅ ነህና። ፈሪሳውያን ክርስቶስን ብዙ ጊዜ ጥያቄዎችን የሺ የጠይቁት ነበር። እሱ ግን ለማመን ልባቸው እንዳልተከፈተ ስለሚያውቅ አይመልስላቸውም ነበር። 2ኛ፦ አንተ አኛ አራስህን አንባቢና ሁሉን ያወቅህ በእውቀት ማማ አናት የወጣህ መሆንህን ስለገለጽክና ከሁሉ እበልጣለሁ በሚል ግብዝ ስሜት ስለተኮፈስህ ለሚሰጡህ መልስም አውቀህ እንደምትተኛ ስለሚገነዘቡ ነው። በመጨረሻ አንዲት ነገር ልበልና ቀሪውን በቀጣይ አስተያየት እሰጣለሁኝ። አቡነ ተክለሀይማኖት ሰይጣንን አሳምነው አመለኮሱት የሚለውን ነቅፈሐል። ለመሆኑ የኛ አንባቢ አቶ ቀቢፀ ተስፍ ፀይጣን ግዙፍ አካል አለውን? ይሔ ነው እንዴ የአንተ አንባቢነትና የእውቀት ምጥቀት? ይገርማል። ማንኛውም የበአድ አምልኮት አምላኪ፣ የእርኩስ መንፈስ የተፀናወተው ወይም አህዛብ የሆነ የሰይጣን ነውና በእነዚህ የሰይጣን ሰንሰለት የታሰረን በእግዚአብሔር ሐይል አስፈትቶ በክርስትና አሳምኖ ማመልኮስን የሚያመለክት እንጂ በቁሙ ስጋና ደም የሌለውን እርኩስ መንፈስ ሰየጣንን መራ መለት አይደለም።

  ReplyDelete
 12. What a devil spirit is with you? You believe what the white people are saying as miracle but do not believe your fathers' doings.

  I think this is because of the fact that you do not have sense of nationality. Your words are not totally ethical. Of course nothing is expected from you!

  ReplyDelete
 13. እንግዲህ እንዲህ ያለዉን ትምህርት እያስተማረች እዉነተኛዉን የክርስቶስ ወንጌል የሚሰብኩትን ግን የምታሳድድ ቤተክርስቲያን ነዉ መታደስ አለባት የምንለዉ፡፡ ወንጌል ሰባኪዉ መናፍቅ እየተባለ ገድለ ክርስቶስ ሰምራ በየአዉደ ምህረቱ ይተረካል፡፡ አይ አንች ቤተክርስቲያን!

  ReplyDelete
 14. ቁንጽሉን እንቆንጽለው!!
  1. አንድ ፓራግራፍ ስላልተመቸኝ ተሐድሶ ያስፈልጋል ትላለህ፡፡አውሮፓና አሜሪካ ፕሮቴስታንት ወደ ዐለማዊነት የወረደው የቅዱሳን ገድል ባመጣው ፈተና ይሆን!!ናቡከደነጾር ወደ እንስሳነት፣ከዛም ተመልሶ ወደ ሰውነት ሲቀየር ጅራቱንና ቀንዶቹን የት እንዳደረጋቸው ስትነግረን የአክናፋቱን ነገር እንነገርሃለን፡፡ሳይቃጠል በቅጠል ስላልከው በተወሰኑ አመታት እየተቃጠለ ገለባ የሚሆነው የሉተር ውልድ የሆነውና በሎጂክ ሲራቀቅ የሚውለው ፕሮቴስታንት እንጅ በዘመናት የተፈተነችው የኛይቱ ተዋሕዶ አይደለችም፡፡
  2. ጎጃም ምናምን እያልክ በኛ በጎጄዎች ሥነ-ልቦና ለመጫወት መሞከሩን ተወው፡፡እንደሱ ከሆነማ ግብጾች በመጽሐፍቅዱስ ስለግብጽ ክፋት ስለተጻፈ መጽሐፉን አናምንበትም ሊሉ ነው፡፡በነቢያቱ ሸክም የተነገረባቸው አህጉራት ሁሉ መጽሐፍቅዱስ ላይ ማመጻቸው ነው፡፡ተይ እንጅ ተስፊቲ!!እፎ-እፎ ትብሊ!!የጻድቃን ተዛምዶ ካስቀየመህ የአብርሃም፣ይስሀቅና ያዕቆብ፣የሙሴና አሮን፣12ቱ የያዕቆብ ልጆች፣የዳዊትና የሰሎሞን፣የሐዲስ ኪዳኖቹ ያዕቆብና ዮሐንስ፣የጌታና የእመቤታችን፣የሉቃስና የእናቱ ማርያም፣የዮሴፍና የሰሎሜ…ዝምድና ጅራት ሊያስበቅልህ ነው!!ያንተ ከሺህ አመታት በፊት አለመፈጠር ሳይጎዳን ቀረ ብለህ!!መጽሐፍ ቅዱሱን ለተረጎመውና የጌታን ዐበይት በዐላት በካሌንደር ደንግጎ መጫወቻ ካደረገን ሥርዓት አላቀህ በነጆሽዋ፣በነፓስተር አብዲ፣በነቡሽራ ታዘልለን ነበር፡፡ፊልጶስ ያጠመቀው ጃንደረባ አንተ አለመሆንህ ያስቆጫል!!ይሄኔ ወንድና ወንድ የማጋባት ደረጃ ላይ የምንደርሰውን ቅዱሳንን እየዘከርን ምድረ-ድሃን ስናበላ እድሜያችንን በኋላቀርነት መፍጀታችን ያሳዝናል!!
  3. ኦርቶዶክሱ ብቻ ነው የሚፈልሰው ትለናለህ፡፡ሌላውማ መቼ ገና በቀለና ይፈልሳል፡፡ የፕሮቴስታንት ዓለም የሚባሉት ምዕራባውያን ከመጽሐፍቅዱስ አኗኗር እያፈነገጡ ወደ ዓለማዊነት የሚፈልሱትና የተቀሩትም ሎጂስቲካቸውን ወደ እኛ አዙረው የሚወጉን ስላልተመረጉ ይሆን!!እስላሙ ወንጌል ተሰብኮ ነው ያልጰነጠጠው--እስኪ ኦጋዴን ሄደሽ ሞክሪያት--በገጀራ ትገረዣለሽ--እዚህ ግን ሆደ ሰፊ ምዕመን ስላገኘሽ በብዕር ሥም ወንጀልሽን ወንጌል እየቀባሽ ትደሰኩሪያለሽ!!
  4. መጽሐፍን በሊቃውንት ደረጃ መርምሮ ወጥ የሆነ ትርጓሜ ከመስጠት ይልቅ ሁሉም እንዳሻው--እንደሥጋ ፈቃዱ እየተረጎመ በራሱ ቦይ የሚፈስበት ሥርዓት የሉተር ልጆችን በያይነቱ ሲያራባቸው እኛ አሐቲ ሆነን ቀረን አይደል!!ልጅ ተስፋ ስማኝማ!!መጻሕፍቶቻችንን ማየት ማረም ቢያስፈልግ እንኳ አንዷን አንቀጽ ለይተን በሊቃውንት ጉባኤ ደረጃ የማቃናት ሥራ ይሰራል እንጅ ቆንጽሎ በመሮጥ በየቤተ-ፕሮቴስታንቱ ሁሉን በጀምላ ፈርጆ ማስጨብጨብ የልጅነት ተግባር ሳይሆን ጡት ነካሽነት ነው--ዝርውነት!!በነገራችን ላይ የተቀረውን የገድሉን ታሪክ ተቀብለህ ይቺ ብቻ ከበደችኝ ብትል አንጀታችንን ታራራው ነበር!!አንተ ግን ቆንጻይ ነህና ቆንጽለህ በሎጂክ ትንደፋደፋለህ!!ስድቡን ሁሉ በአንድ ጽሑፍ ስር ለመጎድጎድ ስትል ጭብጥ ትለቃለህ!!
  5. በአንድ አንቀጽ የተነሳ ሁሉን ገድል እናቃጥል ማለት የባእድ እንጅ የወዳጅ ሥራ አይደለም!!ጌታን ከዘመነ-ሐዋርያት ወዲህ የዓመት ፈቃድ ላያ ያለ እያስመሰሉ በብዙ መከራና ተጋድሎ የተስፋፋቸውን ቤ/ክ እና የልጇቿን የ2ሺህ አመታት መሥዋዕትነት እያቃለሉ በየአዳራሻቸው ወርቅ ዘነበልን፣ጌታ ተናገረን፣እሳት ወረደ…. ያ ሶራ ማራ ሲሮ ከኔ ካሎ ዱባ ቡራ ማኞ… እያሉ 82ኛ ብሔረሰብ የሆኑ ልሳናም ፓስትሮችን ታሪክ መደስኮር ከተሻለ ምርጫው የእናንተ ነው!!እኛ ግን ነጩ ሳይቀር የሚደመምበትንና የሚተምበትን፣ኦሪት ከሐዲስ፣ትውፊት ከመጽሐፍ፣ገድለ ቅዱሳን ከሕዝቡ አኗኗር የተገመደበትን ሥርዓት ስንከተል ለሺህ አመታት ቀና ብለን ነው!!በፕሮቴስታንት አስተምህሮ ላይ ነቁጥና ኮማ ሳይጨምር በሥመ - ተሐድሶ የትናቱን ዛሬ እየሻረ የሚሄድ ሃይማኖትስ አያሻንም!!ፍሬውን አየነዋ!!የዓለምን ሞራሊቲ ወደ ቁልቁለት ጉዞ የመራው ማን ሆነና!!

  ReplyDelete
 15. It is so funny. thanks Lord our God he is good , he opened our spiritual eye glory for God he taken away such blablablabla.......

  ReplyDelete
 16. ተረቱ እንዲህ ቀርቦ ነበርተረቱ እንዲህ ቀርቦ ነበር
  ተረቱ እንዲህ ቀርቦ ነበርተረቱ እንዲህ ቀርቦ ነበር


  http://zemahbereabuneselama.org/index.php/aa-promotion/27-saints/59-st-kerstossemra-history

  የእናታችን የክርስቶስ ሠምራ የትውልድ ሀገሯ ሸዋ ቡልጋ ልዩ ስሙ ቅዱስ ጌየ የተባለ ቦታ ነው፡፡ የአባቷ ስም ደረሳኒ የእናቷ ስም ዕሌኒ ይባላል እኒህም ቅዱሳን ሰዎች ደጋጎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ በሃይማኖት የፀኑ በበጎም ምግባር የከበሩ ነበሩ፡፡ ይህችንም ከእግዚአብሔር የተመረጠች የከበረችና የተመሰገነች ልጅ ከወለዱ በኋላ በክብርና በሥርዓት አሳድገው የእግዚአብሔርን ህግጋትና ትእዛዝ እያስጠኑ ብሉይ ከሐዲስ አስተማሯት፡፡

  ከዚያም የመኳንንት የመሳፍንት ልጅ ናትና ለኢየሱስ ሞዓ ልጅ ሠምረ ጊዮርጊስ ለሚባል ሰው አጋቧት እሷም ዓሥር ወንዶች እና 2 ሴቶች ልጆቿን በክብር በሥርዓት አሳድጋ አስተማረቻቸው፡፡

  በዘመኑ ዐፄ ገብረ መስቀል የሚባል ደግ ንጉሥ ነበረና ደግነቷን ዐይቶ ዝናዋን ሰምቶ አትርሽኝ ብሎ ፪፻፸፪ አገልጋይ ላከላት እርሷም ይህማ ከንቱ ውዳሴ ሊሆንብኝ አይደለምን መጽሐፍ ቢሆን ይነበብበት ይጸለይበት ገንዘብ ቢሆን ይመፀወት ነበር ብላ ወደ እግዚአብሔር አመለከተች፡፡

  በዚችም ዕለት ፊቱ እንደ ፀሐይ እያበራ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ የተወደድሽ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እንዴት ነሽ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠሽን ምግብ አንቺ ተመገቢ ብሎ ቅዱሳን በሚሆኑ እጆቹ ሰጣት እሷም ተቀብላ ፈጣሪዋን አመስግና ተመግባለች፡፡ ከተመገበችም በኋላ መንፈስ ቅዱስ በሰውነቷ መላባት አደረባት ከዚህም የተነሣ ብዙ ዘመን እህል ሳትበላ ውሃ ሳትጠጣ ቆየች፡፡

  ከዚህም በኋላ ያ መልአከ እግዚአብሔር ከእንግዲህ የእግዚአብሔር በረከት ረድኤት ካንቺ ጋር ይሁን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ሥሪ ዐፀደ ቤተ ክርስቲያን ትከይ ብሎ ሠላምታ ሰጥቷት ዐረገ፡፡

  ያ ደገኛ ንጉሥ የሰጣትን አገልጋዮች አስጠርታ ቤተ ክርስቲያን ሥሩ ዐጸድ ትከሉ አለቻቸው እነሱም ሳይንገራግሩ ዐጸድ ትከሉ ቤተ ክርስቲያን ሠሩ፡፡ ሥራውም ከተፈፀመ በኋላ ታቦተ ሚካኤልን አስገባች ለሷም በሰው እጅ ያልታነፀ በመቁረፅ ያልተቀረፀ ኀብሩ የማይታወቅ መንበር አምጥቶ አንቺ አስቀድሽበት ብሎ ሰጣት እሷም ተቀብላ ፈጣሪዋን እያመሰገነች ስትኖር ከዕለታት አንድ ቀን ያ ደግ ንጉሥ ከሠጣት አገልጋዮች አንዲቷ መንፈስ ቅዱስ የራቃት አገልጋይ ነበረችና ከክፋቷ እንድትመለስ ብትመክራት ክፉ አትናገሪ ብትላት አልሰማም ብላ አስቀየመቻት ብታዝንባት ሞተች፡፡

  እሷም ይህማ በኔ ምክንያት ስትሞት ነፍሰ ገዳይ መሆኔ አይደለምን ፈጣሪዬ የቸርነትህን ሥራ ሥራልኝ ብላ ብታዝንና ብታለቅስ ያች ሙት የነበረችው አገልጋይ ተነሣችላት፡፡ ቤተሰቦቿም መጥተው አገልጋይሽ በእግዚአብሔር ኃይልና በአንቺ ጸሎት ተነሣች አሏት፡፡

  እናታችን ክርስቶስ ሳምራ ሄዳ ያችን አገልጋይ ከሞትሽ በኋላ ማን አስነሣሽ ብትላት አምላክ ክርስቶስ ሠምራ (የአንዲ አምላክ) አስነሣኝ አለቻት፡፡

  ከዚህም በኋላ እናታችን ክርስቶስ ሠምራ በዓለመ ሥጋ ሳለሁ ሙት ያስነሣልኝ ከሰው ተለይቼ ከሀገር ወጥቼ ብለምነው እንዴት በሰማኝ ብላ ልብስ ምንኵስናዋን ፤ ቆቧን (አስኬማዋን) አዘጋጀች፡፡ ቤተሰቦቿም ይህ ሁሉ የምናኔ ልብስ የማነው አሏት እሷም ሃይማኖት ያስተማሩኝ አባቴ ልብስ አልቆባቸዋል ሲሉ ሰምቼ ነው አለቻቸው እነሱም መልካም ነው ብለው ተቀምጠው ሳለ ከእለታት አንድ ቀን ልብሰ ምንኩስናዋን አስይዛ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሔደች ልብስ ምንኵስናዋን ለብሳ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብታ ሰውነቷ እስኪደክም ትሰግድና ትጸልይ ጀመረች፡፡

  ከእግዚአብሔር የተሠጣት ቃል ኪዳን - ከዚህ ዓለም ንብረትሽን ንቀሽ ፣ ልጆችሽን፣ እናት አባትሽን ጥለሽ ስለወጣሽ እንዲሁም 22 /፳፪/ ከጉድጓድ ከባሕር እያለቀሽ ኖረሻልና

  1/ የቃል ኪዳኑም መጀመሪያ በቤተ ክርስቲያን ሙሉ ስንዴ ምርት አሳያትና አንዲት የስንዴ ፍሬ ከምድር ወድቃ ብዙ ፍሬ ሁና እንደምትነሳ አንቺም በመንግስተ ሰማያት ብዙ ነፍሳትን ይዘሽ ለመግባትሽ ምሳሌ ነው አላት

  2/ ጌታ እየሱስ ክርስቶስም ለክርስቶስ ሠምራ እንዲህ አላት - ያንቺ ቦታ እናቴ ከወለደችኝ ከማርያም በስተቀኝ ነው ከእንግዲህም ስምሽ በትረ ማርያም ይሁን አላት፡፡

  3/ በየቀኑ ሦስት ሦስት እልፍ ነፍሳት ኃጥአንን ከሲኦል እንድታወጪ ሥልጣን (ዓሥራት) ሰጥቼሻለሁ አላት

  4/ አንቺን ያመሰገኑ፣ የአንቺን ገድል የፃፉ ያፃፉ ፣ የሚሰሙ የሚያሰሙ ፣ ስምሽን የሚወዱ የሚጠሩ፣ ዝክርሽን ያዘከሩ፣ በአልሽን ያከበሩ እስከ 12 /፲፪/ ትውልድ እምርልሻለሁ፤

  ከዚህ በኋላ ጌታን አብዝታ አመሰገነችው ነፍሷ ከስጋዋ ተለየች የመላእክትም እልልታ ደስታ አደረጉ ነብያት ሐዋርያት ሰማዕታት ጻድቃንም ሁሉ በእጃቸው እያጨበጨቡ በእግራቸው እያሸበሸቡ በአፋቸው እልል እያሉ ተቀበሏት፡፡

  É የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ታሪክ ከረጅም ባጭሩ እዚህ ላይ ተፈፀመ፡፡

  Êእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እኛን ወገኖችሽን ከፈጣሪያችን ታማልጅን ዘንድ በቅድስት ፀሎትሽ እንማፀናለን፡፡

  ReplyDelete
 17. ደረቅ ንባብን በደረቅ ንባብ!!
  ከንስርና አእዋፍ እንዲሁም መላእክት ውጭ ላሉ ፍጥረታት ክንፍ ሰጥቶ መተረክ ያለው በገድላት ብቻ እንደሆነ ለማስመሰል ትሞክራለህሳ!!እስኪ ወደ ሜዳህ እንውረድ!!ታዲያ ትርጉም/አንድምታ ምናምን አንፈልግም--በሕግህ ተዳኝ!!ቀጥታ ከ66ቱ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እንጠቅስልሀለን፤ቀጥታ ትቀበላለህ!!
  1. ኢሳይያስ ምዕራፍ 40 ቁጥር 31 ያመነ ሁሉ እንደንስር በክንፍ እንደሚበር ይነግረናል፡፡እንዲህ እያለ “….እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
  2. ኤርምያስም በምዕራፍ 48 ቁጥር 9 ለሞዐብ ክንፍ ስጡዋት ይለናል፡፡ይሄው “…በርራ እንድትወጣ ለሞዓብ ክንፍ ስጡአት፤ ከተሞችዋም ባድማና ወና ይሆናሉ።” እዚሁ ምዕራፍ ላይ በቁጥር 40ም “…እነሆ፥ እንደ ንስር ይበርራል ክንፉንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል።”
  3. ከላይ ያሉት ጥቅሶች በማንጸሪያ መልክ የተቀመጡ ናቸው ብለህ ልትራቀቅ ብትወድ ደግሞ ቀጥታ ለአንስቱ የተነገረውን ቃል ከትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 9 እጠቅስብሃለሁ፡፡አንብበው “…ዓይኖቼንም አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ሴቶች ወጡ፥ ነፋስም በክንፎቻቸው ነበረ፤ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፤ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።”
  4. ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 7 ቁጥር 4 ጀምሮ እስከ 6 እንዲህ የሚል በአክናፋት የተሞላ ቃል አለ “… መጀመሪያይቱ አንበሳ ትመስል ነበር፥ የንስርም ክንፍ ነበራት፤ ክንፎችዋም ከእርስዋ እስኪነቀሉ ድረስ አይ ነበር፥ ከምድርም ከፍ ከፍ ተደረገች፥ እንደ ሰውም በሁለት እግር እንድትቆም ተደረገች፥ የሰውም ልብ ተሰጣት። እነሆም፥ ሁለተኛይቱ ድብ የምትመስል ሌላ አውሬ ነበረች፥ በአንድ ወገንም ቆመች፥ ሦስትም የጐድን አጥንቶች በአፍዋ ውስጥ በጥርስዋ መካከል ነበሩ፤ እንደዚህም። ተነሥተሽ እጅግ ሥጋ ብዪ ተባለላት። ከዚህም በኋላ፥ እነሆ፥ ነብር የምትመስል በጀርባዋም ላይ አራት የወፍ ክንፎች የነበሩአት ሌላ አውሬ አየሁ፤ ለአውሬይቱም አራት ራሶች ነበሩአት፥ ግዛትም ተሰጣት።”
  5. ሚልክያስም ፀሐይን በምእራፍ 4 ቁጥር 2 ባለክንፍ አድርጓታል፡፡እንካ “…ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።”
  6. በሐዲስ ኪዳንም ባለራዕዩ ዮሐንስ በምዕራፍ 12 ቁ 14 ስለባለክንፏ ሴት ይተርካል፡፡አንበበውማ፡፡ተቀበል “…ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።”
  ጌታው ተስፋ ከላይ ያሉት ጥቅሶች ያሉበትን መጽሐፍቅዱስ ስትቀበል ሎጂክ ሳትደረደር ደርሰህ ለገድል ሲሆን ምክንያታዊ መስሎ ማደናገሩ ደግም አይደል!!ተመየጥ!!ይቺ ለመማር ሳይሆን ለማደናገር የምትደረግ ንባብ መጨረሻዋ ኢ-አማኒነት ነው!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yekidusan Amlak Aemirohin Yabiralih Wendime Hiruy. Enesus Libonachew Lemenfesawi neger chelimowalina Yemisemuh Bayimesilegnim ante gin Yemitebekibihin tenagirehalina ahunim ewuketun abezito yistih!!!

   Delete
  2. ኅሩይ፤ አስቸጋሪ ማይም ትመስላለህ። ምሳሌ ሁሉ በገሀዱ ዓለም የሚደረግ እውነት አይደለም። «የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖራችሁ» ማለት እምነት የሰናፍጭ ፍሬ ታክላለች ማለት ነው? «እናንተ የተለሰነ መቃብር የምትመስሉ» ማለት ሰዎቹ የተለሰኑ መቃብር ናቸው ማለት ነው?
   ስንት ድንጋይ አንከባልለን እንዘልቃለን።

   Delete
  3. ሂሩይ አን ራስህ ግራ የገባህ ነህ፡፡
   እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ሲል ክንፍ ያበቅላሉ ማለቱ መስሎህ ነዉ? እስኪናገር ድረስ ሁሉም አዋቂ ይመስላል ማለት ይኼ ነዉ፡፡ ገድል ወይስ ገደል የሚለዉን አንድ የእናንተ ሰዉ የጻፈዉን መጽሀፍ አንብብና በመጽሐፍ ቅዱስ መዝነህ የራስህን ድምዳሜ ዉሰድ፡፡ ለመከራከር በቂ የሚሆን እዉቀት ያለህ አልመሰለኝም፡፡

   Delete
  4. ለanonymous January 21, 2015 at 3:01am
   በእግዚአብሔር ቃል መከራከር ተገቢ አለመሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። መቸም መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ ትመስለኛለህና መከራከር ተገቢ አለመሆኑን ስታነብ ትደርስበታለህ። በቂ እውቀት የለህ ስትል hiruyን የተቸህበት መንገድ ትክለኛ አይደለም። ያወቀውንክንፍ ተሰጣቸው ብሎ መናገሩን አይ ክንፍ ተሰጣቸው የሚል የለም ብለህ አልተቃወምህም። ክንፍ ተሰጣቸው ያለውን ካልተቃወምህ ደግሞ ያወቀውን መናገሩ ትክክል ነውና በተናገረው ጉዳይ ላይ እውቀት አለው ማለት ነው። እውቀት ግን ብቻውን ዋጋ የለውም ምክንያቱም በአውቁ ነገር ማመንና ያመኑትም እንደሚሆን አምኖ መቀበል ያስፈልጋልና ነው። ሌላው አስገራሚው እንደንስር በክንፍ ይወጣሉ ሲል ክንፍ ያበቅላሉ ማለቱ መስሎህ ነው ብለህ ጥያቄ ታቃርብና እንዲህ ስትል እስኪናገር ድረስ ሁሉም አዋቂ ይመስላሉ ማለት ይሔ ነው ተረት ይሁን አባባል ትቀጥላለህ። የኛ መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢዎች በቀለም አላችሁ ተተከለ ወይም ተደረገላቸው ተሰጣቸው ክንፍ የተባለን ምን ይሆን የምትሉት? እንግዲህ መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢዎችነን በእውቀታችን መጥቀናል ረቀናል ባዮች እንደንስር የሚወጡበት ክንፍ ተሰጣቸው የተባለውን ክንፍ አይደለም የምትሉ ከሆነ እንግዲህ ምትሀት ልትሉት ይሆንን ወይስ የቁራ ክንፍ ጥላ? መቸም እናንተ አታፍሩምና ሁለቱንም እንዳትሉና እንዳትገላግሉን? አሁን ለቅዱስ ተክለሀየማኖትና ለቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ተሰጣቸው የተባለው ለእነ ፓስተር ቾው ወይም ለፓስተር ቢልግራሀማን ወይም ለቦንኬ እንዲያው በአጠቃላይ ለአንድ ነጭ ፓስተር ተሰጠ ቢባል ኖሮ የየአዳራሾቻችሁ ጊታር ፒያኖዎቻችሁ፣ ኦርጋን ሳክስፎኖቻችሁ ባንቧረቁ ነበር። አይተናችኋል እኮ ከመንገድ ላይ ጎትታችሁ የኔቢጤ አዳራሻችሁ ጳጳስ ጴንጤ ሆነ ብላችሁ በሐሰት ስትደልቁ።

   Delete
  5. ገድል ወይስ ገደል ፀሐፊው መጽሐፉም የቤተክርስቲያን አይደለም ። እዛው የናንተው ጏድ ነው።

   Delete
 18. menew abaselamawoche commenten yet aderesachut lemanegawem mizanawi mehone melkam ged enate yemetakerboten yemidegef mehone alebet

  ReplyDelete
  Replies
  1. በዚህ ርዕስ ላይ ከተላኩልን አስተያየቶች ሳናወጣ ያስቀረነው ምንም የለም። ምናልባት አስተያየትዎ ሳይላክ ቀርቶ እንዳይሆን? እንደገና ይላኩት እናወጣልዎታለን።
   የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ከእርስዎ ጋር ይሁን።

   Delete
 19. የሚመልስልኝ ማነው????
  1- በተክልዬ ገድል ላይ እነኚህን አንብቤያለሁ፡፡
  ሀ- ተክልዬ ሰይጣንን አጥምቀው ኦርቶዶክስ ካደረጉት በኋላ ስሙን “ክርስቶስ ሃረዮ” ብለው ማተብ አሰሩለትና መነኮሰ ይላል፡፡
  ለ- በዚሁ በተክልዬ ገድል ላይ “የተክልዬ ተቅማጥ ከክርስቶስ ደም ጋር እኩል ነው” ይላል፡፡ የክርስቶስ ደም የዚህን ያህል ረክሶአል ማለት ነው????
  2- በክርስቶስ ሰምራ ገድል ላይ ደግሞ
  - ክርስቶስ ሰምራ ሰይጣንንና እግዚአብሔርን ለማስታረቅ እግዚአብሔርን ስትጠይቀው እግዚአብሔር “እኔ መታረቅ እፈልጋለሁ እሺ ካለሽ ሞክሪ” ይላታል፡፡ የእርቁን ጉዳይ ለመፈጸም ሰይጣን ወደሚገኝበት ወደ መቃብር ስፍራ ስትሄድ ሰይጣን እርቁን እምቢ ብሎ ጭራሽ እሷንም እንዳንገላታት ይተርካል፡፡
  ጥያቄ፡-
  - ሰይጣን መንኩሶ ክርስትና ተነስቶ ክርስቲያን ሊሆንና ማተብ ሊያስር ይችላልን????
  - የክርስቶስ ደም በዚህ መጠን የረከሰ ነው ከተቅማጥ እኩል ነው የተባለው????
  - ሰይጣንና እግዚአብሔር ይታረቃሉን????
  - ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ከርቸሌዎች ሂዱ 99% የታሰረው ሌባ፣ ነፍሰ ገዳይ . . . ኦርቶዶክስ ነው፡፡
  - የኢትዮጵያ ዘፋኞችና ሴተኛ አዳሪዎች ሃይማኖታቸው ኦርቶዶክስ ናት፡፡
  - ሱሰኞች ሰካራሞች ማጅራት መቺዎች . . . ሃይማኖታቸው ስትወርድ ስትዋረድና ስታዋርድ እዚህ የደረሰችው ኦርቶዶክስ ናት፡፡
  - በኢትዮጵያ ምድር ያሉ ጠንቋዮች፣ መናፍስት ጠሪዎች፣ ሰላቢዎች፣ አስማተኞች፣ ደጋሚዎች፣ ደብተራዎች፣ መተተኞች . . . ሃይማኖታቸው ኦርቶዶክስ ትባላለች፡፡
  አሁን ግን በዋናው ጥያቄዬ ላይ እባካሁ ምላሽ????

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለእንዲህ ላለው ደረቅ ምንፍቅና ራሱ ደብረ ሊባኖስ የተጠመቀው ሰይጣን ካልሆነ በቀር ክርስቲያን ሁሉ ትክክል ነው ብሎ ምላሽ መስጠት ሊከራከር አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃወመረ ትምህርት ሁሉ ከሰይጣን ነው። ጌታ ይገስጸው

   Delete
  2. ሌላም አለ የረኸዉ
   1. ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ አብዛኞቹ ዘፋኞች ኦርቶዶክስ ናቸዉ፡፡
   2. በየጠንቋይ ቤቱ የሚሰለፈዉ ህዝብ ሃይማቱ ኦርቶዶክስ ነዉ፡፡
   3. ራሳቸዉ የኦርቶዶክስ እምነት አባቶች ደጋሚዎችና አጋንንት ሳቢዎች ናቸዉ፡፡
   4. ሲወርድ ሲዋረድ በሚል ብሂል ማንም ስለ እምነቱ ሳይማርና ሳያዉቅ አድጎ የሚሞትበት ሃይማት ቢኖር ኦርቶዶክስ ነዉ፡፡

   Delete
 20. ወዳጆቼ
  እዚህ ብሎግ ላይ የኦርቶዶክስ ሃይማትን የሚቃረን አስተያየት ከተሰጠ ዘላችሁ የፕሮቴስታንት እምነትን ማጣጣል የምትፈልጉበት ምክንያት ግልጽ አይደለም፡፡
  በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉት ሃይማኖቶች ቁጥር ከሁለት በላይ እስከሆነ ድረስ ፕሮቴስታንትን የመረጣችሁበት ምክንያት ግልጽ አይደለም፡፡ ለምሳሌ አስተያየቱን የሰጠዉ ሰዉኮ ሙስሊም፣ ካቶሊክ፣ ጅሆቫ፣ አድቬንቲስት………ወዘተ ሊሆን ይችላል፣ አጻፋዉ ግን ሲመለስ ሁሉም ፕሮቴስታንት እንደሆነ ተደርጎ ነዉ፡፡ አትጃጃሉ እኛ ፕሮቴስታንቶች መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብና ለመጸለይ እንጅ አተካራ ለመግባት የሚበቃ ጊዜ የለንም፡፡ ስራ ፈት ሁሉ እዚህ ከምትሰዳደብ ቢያንስ የራሴ የምትለዉ እምነት ምን እንደሚል ጠንቅቀህ ብታጠና ብዙ ታተርፋለህ፡፡ ስድብ፣ ጠብና ዘለፋ ከሰይጣን እንጅ የእግዚአብሔር ከሆነ ህዝብ አይጠበቅም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. You know why? it is Protestant who is working day and night to degrade orthodox church. All religions that you mention above do not involve in ortodox church matters except protestant. So don't be surprised since you are exposed. Pente. will never succeed except talking and insulting here and there. Thehadiso is under cover protestant....ke ortodox chruch telekemew mebarer alebachewu...

   Delete
  2. You Idiot, don't you know any thing than " mabarer"?

   Delete
 21. አስገራሚም አስቂኝም ነው!!

  ReplyDelete
 22. ሒሩይ! እባክህ ከቻልክ ትንሽዬ ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ገብተህ ብትማር ጥሩ ነበር፡፡ ምኑን ከምኑ እንዳገናኘኸው ያኔ ሲገባህ በራስህ ታፍራለህ! በእውነት ትሸማቀቃለህ! (ሳታቋርጡ ፀልዩ የተባለውን ማነው ሰዉዬው ላለማቋረጥ ነው አይናቸውን ለአሞራው ያጠጡት እንዳለው ያ ዘባራቂ ለ ፓስተር ምላሽ ሰጠሁ ብሎ)..

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለናሆም አርያስላሴ
   ማን ከሚባለው ፓስተር ጋር ነው ይችን ቧልት የጠነሰሳችኋት። የሰይጣን የፈጠራ ክስ እንደሆን አያልቅም የቅዱሳኑን የእምነት ጽናትና ገድል የመድረክ ላይ ቀልድ ለማስመሰል ቀን ከሌሊት ይዳክራል። መጽሐፍም ጽፍችሁ ነበር "ገድል ወይስ ገደል" ብላችሁ። መጽሐፍም የማጥላያው ተረታችሁም ገደል ገብቶ ቀረ እንጅ። አቶ ናሆም መጽሐፍ ቅዱስን ጠቅሱ መልስ ሲሰጥህ መጽሐፍ ቅዱስ አዋቂና በመጽሐፍ ቅዱስ የፕሮፌሰር ምሩቅ ለመምሰል ሞከርህ። ትንሽዬ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትቤት ገብተህ ብትማር ጥሩ ነው ነው ያልከው። ይሔን ከበዋቂ ቲያትር ቤቶች አንዱ ጋ መድረክ ላይ ይዘኸው ብትቀርብ በጣም ያስቅልህ ነበር። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን እንደማታውቀው ነግግርህን ሰምተው ስለሚረዱ ነው። ለማንኛውም እናንተ አሉባልታ እየነዛችሁ በድረገፅ ጎብኝ ገንዘብ ሰብስቡ። ከዛም እንደ ሀናንያና ሰፒራ እናንተም ገንዘባችሁም በክርስቶስ ሰይፍ ትጠፍላችሁ።

   Delete
  2. ዳሞት
   ድንቅ ተጋድሎ እያደረክ ነዉ፡፡ በዚሁ ከቀጠልክ 45ኛዉ ታቦት በአንተ ስም ተሰይሞ የምንሰማበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡

   Delete
  3. ለaninymous january 25,2015 at 10:05pm
   ወዳጄ የምን ድንቅ ነው የምታወራው? ድንቅ መጽሔት ነው ወይስ ምን? የታቦት ቁጥር 44 ነው ያለህ የምትንበረከክለት ሰይጣን ነውን? ለምን ስለታቦት የማታውቀውን ከምትዘላብድ ከትቢት ማማ ላይ እራስህን አውርደህ ወደ አባቶች ቀርበህ አትጠይቅምና አትረዳም? ለሁሉም የፍጡር ታቦት የለም። ታቦት አንድ ነው። አንዱ ታቦትም የእግዚአብሔር ታቦት ክብሩን የሚገልጥበት፣ የእምነት ስርዓት የሚፈፀምበት ነው። ታቦትን አንቋሸሽኩ ብለህ ብዙ ባትወራጫ ይሻልሀል። ከእግዚአብሔር ጋር ባትጣላ መልካም ነው ያ ካልሆ ግን ትደቃለህ። የሰው ታቦት የለም!!!

   Delete
 23. Tewahdo lezelalem senta tenoralc
  ''protestant ansemachume '' dengal maryame tamaldalech kidusan yamldalu esti men thunw .....orthodox lezelalem
  orthodox lezelalem
  orthodox lezelalem
  tenoralc

  ReplyDelete
 24. Free Orthodox Teams have identified fake and none educated idiot Eotc priest in USA. Ato. Merkebu, Ato. FIKRU, from Atlanta. Free Eotc teams flying to Dc to investigate more naive priests in all over U SA.

  ReplyDelete
 25. አባቶቻችን በዶግማ ሲከራከሩ አቃለሁ የአሁኑ የቀለለ ትውልድ (አሪፉ ልበለው) በቀኖና እና በመጽሐፍት በገድል በድርሳናት ይላከፋል::
  ጽሃፊው ያላዋቂ ሳሚ አይነት ነው በመሠረቱ::ግዕዝ ማወቅ አዋቂ አያስብልም እኮ::ልክ ቻይንኛ ቁአንቁአ ወይም እንግሊዝኛ እንዳወቅህ ቁጠረው::ግዕዝ ማወቅህ የቤተክርስቲያንን ዶግማ ለማወቅ ካልጠቀመህ ያው እንደ ሌላ ቁአንቁአ ነው::
  ሕሩይ ከላይ በቂ መልስ ሰጥቷል እንዲያውም ወደ ጽሐፊው ወርዶ በ ፷፮ መጽሐፍ ቅዱስ መልስ ሰጥቷል ካለ ሕይወት ያሰማልን!
  "መታደስ አለባት" የሚል አባባል ያረጀ ያፈጀ ያለፈበት እንቅስቃሴ ነው በቃ በ 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጀመረ ነው::አቶ ተስፋ ዛሬ ስለነቃ እሱ የነቃበት ስዓት ቀኑ የነጋበት ሰዓት መስሎት ነው እንጅ ::
  ቤተክርስቲያን ሣትሆን የምትታደሰው እኛ ነን::
  ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:23
  << ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።>>
  ቤተክርስቲያንን ማደስ ማለት ራሷ የሆነን ክርስቶስን ማደስ ማለት ነው::
  ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች(ተከታዮች አላልሁም!):
  ይህ ሁሉ ነቀፋ ወይም ችግር ቢደርስ አስቀድመው አባቶቻችን ነግረውናል::ምንም አዲስ ነገር የለም::ቤተክርስቲያን ሁሉ በጇ ሁሉ በደጇ ነው ከክርስቶስ ጋር::ነገር ግን በገድልና በድርሳናት ጉዳይ ላይ የተለያዩ የመጽሐፍት ቅጅወች በመኖራቸው(ይህም ተሃድሶ ተባዮች በተለያየ ጊዜ እየገቡ የረጩት መርዝ ነው) ትክክለኛውን ቅጅ ማንበብ አለብን::
  ከዚህ ውጭ በመሠረታዊ የሃይማኖት ዶግማ ላይ ስሕተት ወይም ጉድለት ከሌለ መከራከር አያስፈልግም::ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት በጾም(ይሄ ለነተስፋ አይሆንም) ተገቢ ጥያቄ ካሉንም ምሥጢር ያደላደሉ ጉባዔ የዋሉ የክርስቶስ ባሮች የሆኑ አባቶች አሉን መጠየቅ ተገቢ ነው::
  በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፬ አይነት እምነት ብቻ ነው::
  ፩.ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ(ክርስቶስ አምላክ ማርያም የአምላክ እናት)
  ፪.ሙስሊም(የማይታወቅ የማይታይ የማይገለጥ አንድ አምላክ)
  ፫.ካቶሊክ (ከ ቁ.፩ ጋር ተመሳሳይ ነው ለዚህ ውይይት ሲባል)
  ፬.ፕሮቴስታንት(ክርስቶስ አማላጅ በዚህ ግሩፕ ውስጥ ያሉ ቁጥራቸው ከመብዛቱ የተነሳ እልፍ አእላፍት ድርጅቶች ተመስርተዋል::ዋናው ግን ዶግማ ስለሌላቸውና ክርስቶስን አማላጅ በማለታቸው አንድ ናቸው::ጅሆቫ፣ አድቬንቲስት ሙሉ ወንጌል ግማሽ ወንጌል አንድነት ቅንጅት ወዘተ የሚባሉ ቢኖሩም ያው ነው ሁሉም ክርስቶስ አማልጅ በማለት የእምነት ድንጋጌ አላቸው እምነት ደግሞ የሚከፈለው በክርስቶስ ላይ ባለን አቁአም ነው::
  ስለዚህ አቶ ተሥፋ የመጨረሻው አላማው የ16ኛውን መ.ክ.ዘ ፕሮቴስታንት በኢትዮጵያ ማስፈን ብቻ ነው::

  ReplyDelete
 26. I have seen the fake none educated Eotc priest in Atlanta, as mentioned by Free Eotc team. After the game was over, Fikru and Merkebu , every body knews them they came from rural side of Armachow as x soldier of Military regime in Ethiopia. They were laborers in bus station in Addis.

  ReplyDelete
 27. Merkebu an excellent laborer in farmer market. Part time priest in Mr. Efrem church.

  ReplyDelete
 28. Mr. Efrem, who has driven taxi in night club after mid night, please he is not ethically or morally own the church.

  ReplyDelete
 29. Gemalya yalew "yih ke Egziabher kehone matfat atechilum,ke sew kehone rewacgew yitefal,je Egziabher gar eyetetakachihu endayihon alachew"Ye EOTC lematfat yodit (ayihud 10th c),Ahmed Gragn (Islam-16thc),catholics (17thc) and protestants (since19thc) mokeru alchalum,lemen????Te heg Memher Gemalya endalew,EOTC ke Egziabher selehonech.ahunem Tehadso,menafekan;muslims wezete...qen ke let bichohu,bitstfu selemayatefuat ayasasebegnem,EOTC ke Egziabher selehonech.le qebitse tesfa melsu yih new

  ReplyDelete
 30. @Anonymous, commenting against priests in atlanta. We can imagine that the prists are not in good terms with mahberr kidusan. We are not accepting you as we know them very well.

  ReplyDelete
 31. @Anonymous, commenting against priests in atlanta. We can imagine that the prists are not in good terms with mahberr kidusan. We are not accepting you as we know them very well.

  ReplyDelete
 32. manafiq "menafiq" yasegnew metrateru new. besrachew tawquchewalachihu.

  ReplyDelete
 33. አሁን ጥርጣሪዬ ከ እውነታው ደረሰ። የዚህ ብሎግ አዘጋጆች ማንነትና የእስከዛሬው ጥየቄይ ይህን ብሎግ በህግ እንሿን የሚጠይቀው እንዴት ጠፋ ለሚለው ዛሬ ተመለሰልኝ። አቶ ናሆም አርያስላሴ፦ ሁለት ጥያቄ አለኝና መልስልኝ። 1ኛ- መጽሐፍ ቅዱስን ማን ነው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ብሎ የሰጠህ? 2ኛ- መጽሐፍ ቅዱስን መጽሐፍ ቅዱስ ብሎ የሰየመው ማን ነው? እነዚህን ጥያቄዎች የጠየቅሁህ አንተ ይህን ሀይማኖት ማን ሰጠህ ብለህ ከአንተ ጽሑፍ በላይ ላለው አስተያየት ሰጭ ጥያቄ ስላሸረብሀ ነው። እሱ መልስ አልሰጠህም ምናልባት ማንነትህን ስላወቀ ከከንቱ መላፋለፍ ብሎ ይመስለኛል። ለሁሉም ግን በክርስቶስ የሆነችውን አንዲቷን ሀይማኖታችንን ያገኘናት ከአባቶቻችን ከቅዱሳን ሐዋርያት ነው። ማረጋገጫውንም በያዕቆብ 1፤ከ3-4 አንብበው። መጽሐፍ ቅዱስ አንብብ ላልከው የእሱን ለሱ እንተወውና አንተ ግን አንብበህ ጠፍህበት ሀሰተኛ መምህርም ሆንክበት እንጂ ህይወት አልሆነህም እኮ! ሌላወ አስገራሚው የጊዜ ጉዳይ ነው ስትል ለጊዜ እውነትን ማሳደድና ማጥፍት ሙሉ በሙሉ እንደልተሳካላችሁ ታረጋግጥና ነገር ግን በሀሰት ትምህርትህ እያወጂህለት ያለው ሐሰተኛው መሲህ እራሱን በሚገልጥበት ጊዘ በአለም ላየ እንደምትሰለጥኑ ተናገህ። አለም ለክርስቶስ አትመችምና እውነት ብለሀል እውነትን ከአሁኑ በባሰ የምታሳድዱበት ሰዓቱ መቃረቡ በምትፈጽሟቸው የጥፋት ምልክቶች እየተገነዘብን ነው። በቅዱሳን ስለተፈፀሙትና ስለሚፈፀሙት ታምራቶች መናገር ለአንተ አያስፈልግም። ምክንያቱም ለማመን ልብህ የተከፈተ አይደለምና ነው። አንተ እኮ መጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ተብሎ እንዴት እንደመጣ መመለስ በማትችልበት የእወነት መጽሐፍ ውስጥ ባይጻፍ ኖሮ ጴጥሮስ ሐናና ሰፒራን የቀጣበትን ታምር ነፍስ ገዳይነትና አሱንም ደም አፍሳሽ ማለታችሁ አይርም ነበር ነውና። ሆኖ ቅዱሳን በተሰጣቸው ፀጋና ሀይል በእምነት ገራ ተው ገተ ኢየሱስ ካደረጋቸው በላይ ብዙ ታምራቶችን ማድረግ እንደሚችሉ ይህን ተራራ ተነስ ብትሉት ይነሳል ሲል ገልጿል።

  ReplyDelete