Thursday, January 22, 2015

ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶን ከመቀበል ይልቅ ለማጥናት ኮሚቴ የማቋቋሟ አንድምታ

በእግዚአብሔር መንግሥትና በሰይጣን መንግሥት መካከል ያለው ትግል ከጥንት እስከ ዛሬ እንደቀጠለ ነው። ሰይጣን የእግዚአብሔርን ዕቅድና ዓላማ ሊያበላሽ በተንኮልና በማስፈራራት ሲሠራ ኖሯል። የቱንም ያህል ቢፍጨረጨር ግን እግዚአብሔር ያቀደውን ከመፈጸም አላገደውም። ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ ሰይጣን የሚጠቀምበት ስልት አንድ ዓይነት መሆኑ ነው። በብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ነቢያት የእግዚአብሔርን ቃል ወደሕዝቡ ሲያመጡና ፍርዱን ሲገልጡ ሕዝቡም ንስሐ እንዲገቡ ሲናገሩ ይህ እንዲሆን የማይፈልገው ሰይጣን ነቢያትን የሚያሳድዱ ሰዎችን በተለይም ነቢያት ነን የሚሉ ሐሰተኛ ነቢያትንና መምለክያነ ጣኦት የሆኑ ነገሥትን ጭምር በእውነተኞቹ ነቢያት ላይ ያስነሣና ያሳድዳቸው ያስደበድባቸው ያስገድላቸውም ነበር። በዚህ ውስጥ የእግዚአብሔር ዕቅድ መፈጸሙ ግን አልቀረም። ይሁን እንጂ የነቢያቱን ድምፅ ያልሰሙት የተነገረው ፍርድ ደርሶባቸው ለምርኮና ለብዝበዛ ተዳርገዋል። ብሉይ ኪዳን ይህን በመሰለ ታሪክ ተሞልቷል።


በሐዲስ ኪዳን ዘመንም ሰይጣን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በተከታዮቹ ሐዋርያት ላይ ተመሳሳይ ስልት ነው የተጠቀመው፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆንና በምድረ እስራኤል እየተመላለሰ ማስተማሩና ብዙ ተከታይ ማፍራቱ ያበሳጨው የእግዚአብሔር መንግሥት ጠላት ሰይጣን የሃይማኖት ሰዎችን በመቀስቀስ መድኃኒታችን እንዲያዝና እንዲሰቀል አደረገ፡፡ እርሱ ቢሞት እንቅስቃሴው ይቆማል ብሎ ነበር፡፡ ለጊዜው እርሱ ተይዞ ሲሰቀልና ደቀመዛሙርቱም ሲበተኑ ሰይጣን ድል የደረገ መሰለው፡፡ ነገር ግን ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ሰይጣን ያሰበው አልሆነም፡፡ እንዲያውም ባሰበት፡፡ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት የሃይማኖት ሰዎች ነን በሚሉ ጻፎች ፈሪሳውያንና ሊቃነ ካህናት ብዙ ዛቻና ማስፈራሪያ፣ እስርና ስደት እስከ ሞት የደረሰ መከራም ደርሶባቸዋል። ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ዕቅድ ከመፈጸም ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ድኅነተ ነፍሳቸውን ማግኘታቸው ወንጌል መሰበኩ ቤተ ክርስቲያን (ምእመናን) እየበዙ መሄዳቸው፣ ቤተክርስቲያን በዓለም ሁሉ መስፋፋቷ አልቀረም፡፡ ዛሬ ግን ክርስቶስን የምታሳድድ እውነተኛውና መጽሐፍ ቅዱሳዊው የክርስትና ሕይወት የተለያትና በልማዳዊ ሥርዐት የምትመራ ሃይማኖታዊ ተቋም የሆነች “ቤተክርስቲያን” መሆኗ በእጅጉ ያሳዝናል፡፡ ስለዚህ ሰይጣን ቤተክርስቲያንን ለማሳደድ እየተጠቀመ ያለው ቤተክርስቲያን ነኝ የምትል ሃይማኖታዊ ተቋምን መሆኑ ያስገርማል፡፡

በየዘመናቱ የተነሣውን የተሐድሶ ሐሳብ ለማጨናገፍ ሰይጣን የተጠቀመው ያንኑ የተለመደ የማሳደድና እውነትን የማውገዝ ስልቱን ነው፡፡ በዚህ ግን ከስሮ እንጂ አትርፎ አያውቅም፡፡ ወደአገራችን ሁኔታ መለስ ብለን ታሪካችንን ስንቃኝ በሕዝቡ ሕይወት ውስጥ የሚታየውን ኢመንፈሳዊ የኑሮና በንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብ ዘንድ የሚስተዋለውን የአምልኩኝ አባዜ ሌሎችንም በእነርሱ እይታ ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ውጪ የሆኑ ትምህርቶችንና ሥርዓቶችን ባለመቀበላቸውና እንዲስተካከሉ በመጠየቃቸው ብዙ የጥፋት አዋጅ ታውጆባቸው እነርሱንና ትምህርታቸውን ለጊዜውም ቢሆን መግታት የተቻለ መስሎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከብዙ ምእተ ዓመታት በኋላ ያ ታሪክ ከተቀበረበት ወጣ፡፡ የእነርሱን ዓርማ ያነሣ የተሐድሶ ሰራዊትም የተሳሳተውን የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን አስተምህሮና ወደ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ያስገባቸውንና የወንጌልን ስፍራ የነጠቁትን፣ በሕዝቡ አስተሳሰብና አካሄድ ላይ አዚምና ድንዛዜ የጫኑትን፣ የሕዝቡን የመሥራት ባህል ገድለው በበዓላት ብዛት ሥራ ፈት ያደረጉትን ልቦለድና አጋንንታዊ ድርሰቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጠራርጎ ለማስወጣትና በሕዝቡ ሕይወት ተሐድሶ እንዲመጣ፣ ማንነቷ፣ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነው ትምህርቷና ሥርዓቷ ተጠብቀው ከዚህ ውጪ ያሉት የተሳሳቱ ትምህርቶችና ሥርዐቶች በእግዚአብሔር ቃል እንዲታረሙና የታደሰች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማየት መንፈሳዊውን ተጋድሎ እያደረጉና ብዙ ለውጦች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ ይህ እውነት ታዲያ በጠላት መንደር ሽብር ፈጥሯል፡፡ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ፣ ለእግዚአብሔር በመቅናትም ይሁን የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ፣ በኖረው ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርትና ሥርዓት የዐመጽን ትርፍ ለማጋበስ፣ የእግዚአብሔር ሳይሆን የሰይጣን ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው በተሰለፉ ሰዎች የእግዚአብሔር አጀንዳ የሆነውን ተሐድሶን ለመቀልበስ ዛሬም ብዙ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ካለፉት የታሪክ አጋጣሚዎች መማር እንደሚቻለው ተሐድሶን መቀልበስ የሚታሰብ ነገር አይደለም፡፡ ተሐድሶን መቀልበስ ማለት እግዚአብሔር እንዳይሠራ ማገድ ማለት ነውና፡፡ ግን ይቻላል? በፍጹም!!!!!!!!!!!!!!!

ከታሪክ መማር የተሳነው ቅዱስ የተባለው ሲኖዶስ ለአስፈላጊውና ለጠቃሚው የተሐድሶ እንቅስቃሴ ሌላ ስም በመስጠትና በቤተክርስቲያን ሌላ ትልቅ አደጋ ጋርጧል በሚል በማኅበረ ቅዱሳን ከሳሽነት ሕጋዊም መንፈሳዊም ሞራላዊም ኅሊናዊም አካሄድን ባልተከተለና ግብታዊነት በተሞላው መንገድ ግንቦት 15/2004 ዓ.ም ውግዘት አስተላለፈ፡፡ በዚህም ተሐድሶ ተመታ ተብሎ ብዙ ብዙ ተባለ፡፡ ይህን ያደረገው የተሐድሶ ባለቤቶች ያወገዛቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች መስለውት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ሥራ ላይ እንዲህ ዓይነቱ ዱላ ሲያርፍ የእግዚአብሔር ሥራ ይበልጥ እንደሚሰፋና ቃሉን የሚከተሉት ቁጥር እንደሚጨምር የሐዋርያት ሥራ ይመሰክራል፡፡ ከግንቦት 2004 ወዲህ እየሆነ ያለውም ልክ እንደዚያው ነው፡፡ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የተወገዘው የተሐድሶ እንቅስቃሴ የእግዚአብሔር ሐሣብ በመሆኑ ተጽዕኖውን በቤተክርስቲያን ላይ ማሰደሩን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከመቼውም ጊዜ ይልቅ እገሌ የተባለ ዲያቆን፣ እገሌ የተባለ ቄስ እገሌ የተባለ መነኩሴ፣ እገሌ የተባለ ሰባኪ፣ እገሌ የተባለ የመጽሐፍ መምህር ወዘተ ተሐድሶ ሆኗልና አግደነዋል በሚሉ ክሶች መጨናነቁ በሰፊው እየተወራ ነው፡፡ ሲኖዶሱም በየሀገረ ስብከቱ እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፋ የሚታየውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ ለሌላ ሕገወጥና አግባብነት የሌለው ውሳኔ እያነሣሣው ይገኛል፡፡ እንዲያውም እያንዳንዱ ጳጳስ በየሀገረ ስብከቱ በተሐድሶነት የጠረጠረውን አገልጋይ ወደሲኖዶስ ሳያደርስ እዚያው እንዲያወግዘው ሥልጣን ሰጥቶታል፡፡ ይህ ለቤተክርስቲያን ትልቅ ውድቀት ነው፡፡ ሰኖዶስን ዋጋ ቢስ የሚያደርግ፣ ለጊዜያዊና ለራስ ጥቅም ሲባል የተዘየደ መላ ነው፡፡ ለነገሩ ጳጳሳቱ ይህ ሥልጣን ባይሰጣቸውም ከዚህ ቀደም ያሻቸውን ሲያወግዙና ሲያግዱ ነው የኖሩት፡፡  የሚጠበቀው ግን ሲኖዶሱም በማውገዙ ተሐድሶም በመስፋፋቱ መቀጠላቸው ነው፡፡ ከታሪክ አለመማር፣ የእግዚአብሔርን ቃል አለማስተዋል፣ ሌላ ስሕተት ከመድገም ውጪ የሚያመጣው ነገር የለም፡፡ ተሐድሶን ለመቀልበስ አዝማች የሆነው ሰይጣንም በዋናነት የሚጠቀመው ያንኑ ያረጀና ያፈጀ የማሳደድና የማውገዝ ስልት ነው፡፡ ይገርማል!!!

መቼ ይሆን ለእውነት የምንሸነፈው? መቼ ይሆን ለእውነት የምንታዘዘው? መቼ ይሆን ለጊዜያዊና ለኃላፊ  ኑሮ ሳይሆን ለዘላለም ሕይወት የምንሠራው? መቼ ይሆን ለድርጅታዊ ተቋም ሳይሆን የክርስቶስ ለሆነችው ለአንዲቱ ቤተክርስቲያን መታነጽ የምናገለግለው? በእውነት ለሌላ ታሪካዊ ስሕተት እየተንደረደሩ ያሉትን ጳጳሳት የሚመክርና አቅጣጫ የሚያሳይ እንደ ገማልያል ያለ አስተዋይ የሆነ አንድ ሰው እንኳ የለም እንዴ? ገማልያል ታሪካዊ ስሕተት እየፈጸሙ ለነበሩት የካህናት አለቆች እንዲህ ነበር ያላቸው “… አሁንም እላችኋለሁ። ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ። ሰሙትም፥” (የሐዋ. 5፥38-39) ይላል፡፡

የተሐድሶ እንቅስቃሴ በውግዘት አይገታም፡፡ እንዲያውም ይብሳል፡፡ ከዚያ ይልቅ ተሐድሶን በአዎንታዊነቱ ተቀብሎ አቅጣጫ ማስያዙ ነው ለቤተ ክርስቲያን የሚበጀው፡፡ በጥቅምቱ ሲኖዶስ በተሐድሶ ዙሪያ ጥናት እንዲደረግ የተላለፈው ውሳኔ አሉታዊነት ያጠላበት በመሆኑ ችግሩን ያባብሳል እንጂ መፍትሔ እንደማያመጣ እሙን ነው፡፡ ስለዚህ በእብሪትና በማንአለብኝነት ተሞልቶ ምንም አይመጣም፤ የሰዎችን በየጊዜው ከቤተክርስቲያን መሰደድና መፍለስም “ከጎጆ ቤት ላይ ሳር ቢመዘዝ ጎጆው አያፈስም” የሚለው ፈሊጥ አሁን የሚሰራ አይደለም፡፡ እየተመዘዘ ካለው የሳር መጠን አንጻር ጎጆው ማፍሰሱ አይቀርምና ቆም ብሎ ማሰብና ለኖረ ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ልማድ ጠበቃ ከመሆንና የእግዚአብሔርን እውነት ከማሳደድ የእግዚአብሔር ቃል ቤተክርስቲያኗን እንዲገዛ ማድረጉ አማራጭ የለውም፡፡ ይህ እስካልሆነ ድረስ ተሐድሶ ኢየሱስ ክርስቶስ በሕዝቡ ዐይን ፊት በመንፈስ ቅዱስ እስኪሳል ድረስ ተጋድሎውን ይቀጥላል፡፡ የተሐድሶ ዓላማ ይህ እንጂ ሌላ አለመሆኑን ተገንዝቦ በእግዚአብሔር ሐሣብ አንጻር አሰላለፍን ማሳመሩ ይበጃል፡፡   
በዚህ ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተክርስቲያንንና ሃይማኖትን ከተሐድሶ አራማጆች ትምህርት ለመጠበቅ በሚል ተሐድሶ ሲል የፈረጃቸውን ወገኖች በማሳደድና በማውገዝ ተግባሩ ገፍቶበታል፡፡ ስለተሐድሶ እንዲያጠኑ በሚል ሰዎችንም ጠቅላይ ቤተክህነት መድቧል፡፡ ጥናቱ አስፈላጊ ሊሆን ቢችልም ትኩረቱ ግን ተሐድሶን ለማጥፋት የሚል መሆኑ ቤተክህነቱ አሁንም በእንቅልፍ ላይ እንደሚገኝ የሚያሳይ ነው፡፡ ጥናቱና ለጥናቱ የመደባቸው ሰዎች ማንነትና የተመደቡበት መንገድም ከወዲሁ ተሐድሶን ከምንጩ ለማድረቅ ታስቦ የተደረገ ነው፡፡ አለመታደስ መብት ቢሆንም ተሐድሶን ማስቀርት ግን ከቶም አይቻልምና ድካሙ ሁሉ ከንቱ ድካም ሆኖ ይታያል፡፡

እውን ኮሚቴ ከተባሉት አንዳንዶቹ ጉዳዩን ለማጥናት በቁ ናቸውን? በእኛ በኩል አይመስለንም ምክንያቱም አንዳንዶቹ የማቅን ፍላጎት ለማሟላት እንጂ ከፍተኛ የዕውቀት ክፍተት የሚታይባቸው የሥነ ምግባር ችግር የሚስተዋልባቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ ተሐድሶን በቀና መንፈስ ይመለከቱታል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ጥያቄ ከምናነሳባቸው የኮሚቴው አባላት መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ፡፡

ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ
በፊት ቡረ እድ ኤልያስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ በነበሩ ጊዜ ምክትላቸው ሆነው ሳሉ አይን ያወጣ የጉቦ ቅሌት ውስጥ ተዘፍቀውና ከፍተኛውን ዝውውር ገንዘብ በማስከፈል ሪከርድ ሰብረው የነበሩ፣ በተለይም የዲቁናውን ዝውውር በከፍተኛ ጉቦ ያጧጡፍ ስለነበር በብዙ ዲያቆናት ላይ አማራሪ የሆነ ሙስና ሲፈጽሙ ኖረው አሁን ሙሰኞች ዕረፍት ወደሚወስዱበት ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የተዛወሩ ሰው ናቸው፡፡ እኚህ ከትምህርቱም ከምግባሩም የሌሉበት ሰው የተሐድሶን ጉዳይ ለማየት ታዲያ በምን መስፈርት ነው የታጩት?

ሊቀ ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ ዳኜ
ይህ ሰው (በማቅ አጠራር ኃይሌ) ዘመኑን ሙሉ ለክፉ ነገር የሚተጋ ሰው በመሆኑ ይታወቃል፡፡ ያ ክፉ ነገሩ በተለይ ለማቅ እንደ መልካም የሚታይለት ሰው ነው፡፡ ስለዚህ ሰው ከዚህ ቀደም አንዳንድ መረጃዎችን ማቅረባችን የሚታወስ ነው፡፡ ቀደም ሲል የማቅ መናኸሪያ የነበረው የፍቼ ሥራ አስኪያጅ የነበረ ሲሆን ከዚህ ቀደም በሰበካ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተሐድሶ መፈልፈያ ነውና ይዘጋ ብሎ የተናገረ፣ ማቅ በሰበካ አጠቃላይ ጉባኤ መዝጊያ ላይ በየዓመቱ ራት ሲያበላ (ግብር ሲያገባ) የሚመርቅ እርሱ ሲሆን ከምርቃቱ አንዱ ተሐድሶን በእግራችን ረግጠናታል የሚል እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ግብዣ ሁልጊዜ ሊቀጥል ይገባል እያለ የሚሰብክም ሰባኬ ከርስ ነው፡፡ ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ በቅርቡ በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ሙስና ፈጽሞ ውሳኔ የተላለፈበት ሰው ነው፡፡ ውሳኔው የተላለፈበት በአንድ ማሽን ግዢ ላይ ሙስናን በመፈጸሙ ነው፡፡ ይኸውም አሮጌ የሆነውን ማሽን ቀለም በመቀባት አዲስ አስመስሎ አቅርቧል ተብሎ ነው፡፡ ድርጊቱ በተጨባጭ በተደረስበት ጊዜ የአቡነ ማቴዎስን አንገት ያስደፋ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ በማንኛውም የአስተዳደር (መምሪያ) ውስጥ እንዳይገባና የሰረቀውን ገንዘብ ደግሞ በየወሩ ከደሞዙ እየተቆረጠ ተመላሽ እንዲሆን በራሳቸው በአቡነ ማቴዎስና በጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ ተወስኖበታል፡፡ ለሌብነት ሲሆን እድሳትን የፈለገው ኃይለ ጊዮርጊስ የቤተክርስቲያንን ተሐድሶ ግን በጽኑ የሚቃወም ነው፡፡ ይህን ሰው ስለተሐድሶ እንዲያጠና በተቋቋመው ኮሚቴ ውስጥ መግባቱ እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ እንዲገባ የተፈለገው የማቅን ፍላጎት ያሟላል፣ የማቅን ዓላማ ያሳካል ተብሎ ነው፡፡ ማቅም ቢሆን እንዲህ ያለውን ምግባረ ብልሹ ሰው አቅፎ ሲይዝ በተጨባጭ ወንጀሎችና ሙስናዎች ውስጥ መዘፈቁን እያየና እየሠማ አንድም ቀን ትንፍሽ ብሎ አያውቅም፡፡

ሰለሞን ቶልቻ
ስለዚህ ግለሰብ ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ጠቅላይ ቤተ ህነት ቤተ መጻሕፍት ወመዘክ መምሪያ ኃላፊ ሲሆን፣ በግል ህይወትም ሆነ በተሠማራባቸው የሥራ መስኮች ሁሉ በከፍተኛ ሙስና ላይ የተሠማራ ሰው ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
1.     በጸሐፊነት ሩፋኤል ከተራ ሠራኞች ሙዳየ ምጽዋት ሪዎች ሳይቀር ሳንቲም የሚቀማ አሳድጋቸዋለሁ እያለ የሚዘርፍ ነበር፡፡ በዚህ ደብር 3 ወር እንደ ሠራ ቢሮው ታሽጐ ተባሯል፡፡
2.    አስኮ ገብርኤል በተመሳሳይ ሁኔታ ቢሮ ታሽጐ ሰዎች አባረውታል፡፡
3.    እንጦጦ ማርያም የሠራው አንድ ወር ብቻ ነው፡፡ በደብሩ ውስጥ ያለውን ሙዚየም ጐብኝቶ እር መስቀ ማንኪያ ሰርቆ በኪሱ ይዞ ሲወጣ ተይዞ ቢሮ ታሽጐ ተባሮ ነበር፡፡
አባ ጳውሎስ እሮሮው እየበዛባቸው ሲመጣ ከሮ ሠራተኛነት እዚያው ቅድስት ማርም በሰባኪነት መደቡት፡፡ የሳቸውን ሞት ተከትሎ ግን ወደ ማህበሩ በመለጠፍ በአቃቤ መንበር ናትናኤል ጊዜ ሳይመነኩስ የገዳማት መምሪያ ሀላፊ ሆነ፡፡ ገንዘብ ካገኘ ወደ ኋላ የማይለው ሰሎሞን ቶልቻ በቤተ ክህነት ተቋቁሞ የነበረው ጉባኤ አርድእት የወደፊቱን ላማ በአስመሳይነት ሰርጐ በመግባት ጉባኤተኛው ባያምንበትም አጀንዳዎችን የጉባኤውን ራእይ በ9 ሺህ ብር ለማኅረ ቅዱሳን ሽጦ ጉባኤው በቤተክርስቲያን እንዳይሰበስብ በአቡነ ፊሊጶስ እገዳ እንዲልበት በብርቱ የታገለ ሰው ፡፡
4.    ተመደበበት የሰባኪ ወንጌልነት ሥራ እጅግ አሳፋሪ የሆነው አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዱ ደግሞ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ላሴ ካቴድራል ተመድቦ ሲሰራ የካቴድራሉ እስፒከር አዟሪ የሆነ አገልጋይን ሚስት (እዚያው አካባቢ ፎቶ አንሺ ናት) ይዞአት በመጥፋት ስትመለስ ጉዳዩ የደረሰት ባልዋ ቄሱሰለሞን ቶልቻ ለ3 ወር አሳስሮአት ነበር፡፡ እንግዲህ ከሰባነት ጸሐፊነት ወደ መምሪያ ኃላፊነት የተሻገረውና ሥነምግባሩ ይህን የመሰለው ሰለሞን የተሐድሶን ጉዳይ ለማጥናት ከሞራልም ከሥነ ምግባርም ከትምህርት ዝግጅትም ከልምድም አንጻር ብቁ ነው ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የወደደው ሰው ስለሆነ በማኅበሩ አባት በአባ ማቴዎስ ግን ተመራጭ ሰው ሆኖ የዚህ ኮሚቴ አባል ሆኗል፡፡
ይቅር ባይ
ይህ ወጣት በወላዋይነቱ ነው የሚታወቀው፡፡ ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዲፕሎማ ተመርቆ ሲወጣ፣ በአባ ሠረቀ የመምሪያ ኃላፊነት ጊዜ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ውስጥ በኦሮምኛ የጋዜጣ ዝግጅት ሲቀጠር ላይ ላዩን እሳቸውን ያስደሰተ ለመምሰልና የመምሪያውን ደንብ ለማክበር ፊት ቢያሳይምውስጡን ግን በተደጋጋሚ ደብዳቤዎችንና ቃለ ጉባኤዎችን ሌሎችንም የመምሪያው እቅዶች ሁሉ በድብቅ ለማቅ አመራሮች በተለይ ለአቶ ታደሰ ወርቁ፣ ለአቶ ሙሉጌታ ኃይለማርያም ሲሰጥ በተደጋጋሚ የተመለከቱ የመምሪያው ሠራተኞች ነበሩ፡፡ እሳቸው ከዚህ መምሪያ እንዲለቁ ውስጥ ውስጡን ነገር የሚሠሩ እነ ይቅር ባይ ነበሩ፡፡ እንዲህ ያለው ላይ ላዩን ለቤተክርስቲያን የቆመ የሚመስል፣ ውስጥ ውስጡንና በተግባር ግን ለማቅ የቆመ፣ በቂ ዕውቀትና ልምድ የሌለው ሰው የተሐድሶን ለማጣራት ብቁ አይደለም፡፡

እንግዲህ ይህን ታላቅ ሐሳብ የሆነውን የምድሪቱን አጀንዳ ተሐድሶን የሥነ ምግባርም፣ የሃይማኖት አስተምህሮ ተሐድሶ የሚያስፈልጋቸው ግለሰቦች ናቸው እንዲያጠኑት የተደረገው፡፡ አባ ማቴዎስ እነዚህን ሰዎች ሲመርጡ ግለሰቦቹን አያውቋቸውም ማለት አይቻልም፡፡ ምናልባት ሞራል እንደሌላቸው ስለሚያውቁ ይሆናል ብለን እናስባለን?

በብዙዎች ዘንድ ይህ ጉዳይ በታላቅ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲወድቅ የሆነው ለእነዚህ ሰዎች ለሥራ የሚሆን በጀት በማቅ መመደቡ አይቀሬ መሆኑና ማኅበሩም እነማንን መምታት እንዳለበት ስለሚያወቅ ለእነዚህ ሰዎች የቤት ሥራ መስጠቱ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ መንገድ በመጠቀም አንዳንዶችን መምታት ቢቻልም እንኳን እስካሁን እንደታየው የተሐድሶ እንቅስቃሴን ማስቆም ፈጽሞ አይቻልም፡፡ የወንጌልን ሥራ የሮም ቄሣሮች አላቆሙትም፣ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በእነ አባ እስጢፋኖስ የተነሣውን የተሃድሶ አላማ ዘርዓ ያዕቆብ አልገደበውም፡፡ አሁን ያሉት የሲኖዶስ አባላት ውሳኔዎችም የዘመኑን የተሐድሶ እንቅስቃሴ ሊያሰቆመው አይችልም፡፡ 

በዚህ ዘመን የምእመናን ፍልሰት በዝቷል፣ ምእመናን ወደሌሎች እየሄዱ ነው፣ ቤተክርስቲያናችን ሰዎችን እያጣች ነው እየተባለ ለሚቀርበው ሮሮና ሥጋት መፍትሔው ሌላ ሳይሆን ተሐድሶን ማድረግ ነው፡፡ ጥያቄን አለመፍራት ነው፤ የተሐድሶን ጥያቄ መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ወደ ቁልቁለት እየሄደች ያለችውን ቤተክርቲያን ከውድቀቷ ለመታደግ ከላይ ስማቸው የተዘረዘረውን ተራ ሰራተኞች ሳይሆን በቂ የነገረ መለኮት ዕውቀትና ልምድ ያላቸውን፣ አርቀው የሚያስቡትን፣ በሥነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸውን፣ መንፈሳዊነት ያላቸውን ሊቃውንት መመደቡ የተሻለ ውጤት አለው፡፡ በእነዚህ ሰዎች እንዲሰራ መደረጉ ግን የማቅን ፍላጎት ከማሟላት የዘለለ አይሆንም፡፡

16 comments:

 1. ቤተክርስቲያንን ለማደስ ከምትጥር ለምን እራስህን አታድስም፡፡ ቤተክርሰቲያንማ አንዴ በደሙ ተዋጅታልች፡፡ ክርስቶስን ለብሳለች፡፡ አርማዋ ክርስቶስ ነው…በውስጧም በወንጌል የተጠቀሱት ምሥጢራት በሙሉ ይፈፀሙባታል፡፡ እኛም እንላለን" ሰላም ላንቺ ይሁን እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ ግድግዳዎቿ ያጌጡ ፥ በብጫቴ ዕንቁ የተሸለሙ ናቸው፡፡ ሰላም ላንቺ ይኹን እናታችን ቅድስተ ቤተ ክርስቲያን" ከስሞች ሁሉ በላይ ለሆነው ስሙም እንዲህ እያልን እንሰግዳልን" ብሩክ ከቤተ መቅደስ የተቀበላት የእሳትን ፍሕም የተሸከምሽ የወርቅ ጥና አንቺ ነሽ፡፡ ኀጢአትን የሚያስተሰርይ በደልንም የሚያጠፋ የኸውም ካንቺ ሰው የኾነ የእግዚአብሔር ቃል ነው፤ ራሱን ያማረ መሥዋዕትና ዕጣን አድርጎ ላባቱ ያሳረገ፡፡ ይኸውም ካንቺ ሰው የኾነ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ክርስቶስ ሆይ፤ ቸር ሰማያዊ ከሚኾን አባትኽ ጋራ ከማሕየዊ ቅዱስ መንፈስኽም ጋራ አንሰግድልኻለን መጥተኽ አድነኸናልና፡፡" ቤተክርስቲያን በትምህርቷ በፀሎቷ ሰውን ታድሳለች ታንፃለች እንጂ ሊበሏት ባሰፈሰፉ ምእራባውያን ባሰለጠኗቸው የዲያብሎስ የግብር ልጆች አትታደስም፡፡ ትውልዱም " የአባቶቼን/የሃዋርያቱን ፣ የነቢያቱን፣ የሊቃውንቱን፣ የእግዚአብሔር ሕዝብን/ ርስት አልሰጥህም " ብሎ አውጆብሃል፡፡ አዲዮ ተሐድሶ አዲዮ ምንፍቅና አዲዮ ከሃዲነት…አዲዮ ….ሳንታ ማሪያ፡፡

  ReplyDelete
 2. ere anifer tehadisowoch egziabher hulun yemiawq amlak new. bemeshuleklek maruin bemamrer wotetuin bematkor aliam yebetechirstian agelgayochin bemashemakek tehadison masfafat aychalim wede libonachuh temelesu. lezihim amlake kidusan yigobignachuh

  ReplyDelete
 3. ኡኡቴ!!ለምን በኃይል እንድንናገራችሁ ትሻላችሁ??!!
  1. አስደሳች ዜና ብላችሁ ዘገባችሁ፡፡አናፈሳችሁ፡፡ስታዩት ጦሩ የተሳለው በእናንተ ነው፡፡ስለዚህ ሀተታ ጀመራችሁ፡፡ስለ አጥኚ ኮሚቴው ስብጥር ትራቀቃላችሁ፡፡የተመረጡት ሰዎች ለሥነ - ምግባር ኮሚቴ አይደለም፡፡ተሐድሶን ለመዋጋት ነው፡፡ለእሱ ደግሞ በእምነታቸው ህጸጽ የሌለባቸው መሆናቸው በቂ ነው፡፡ “የምግባር ነገር እያደር ይሆናል” እንዲል ትርጓሜ-ጳውሎስ በዕብራውያን 13 ቁ 7 “ተዘከሩ መኳንንቲክሙ”ን (ዋኖቻችሁን አስቡ!) አበው ሲያመሰጥሩት፡፡
  2. ደቡብ ላይ ብዙ ወረዳዎችን በበላይነት ይዛችኋል፡፡በነዚህ ወረዳዎች ከሌሎች ኦርቶዶክሳውያን የበዙባቸው ወረዳዎች በንጽጽር የታየውን ብልጽግና፣ማኅበራዊ መረዳዳት፣የወንጀል መቀነስ፣ወዘተ…ለውጦች በሪፖርት መልክ አቅርቡና አሳፍሩን እስኪ!!ኡኡቴ!!ሰርቶ ማሳየት የለም እንዴ!!ጀርመን ላይ የዘራችሁት ናዚ በቅሎ አይተነዋል፣አሜሪካም ከነፕሬዝዳንቱ በጌታ ታድሰው ወንድና ወንድ ማጋባትን ሕጋዊ አድርገዋል፣የተከበሩ ኦባማ ሲሾሙ በወንጌል ምለው ነበር!! ምን ያደርጋል!ከየዘመኑ ጋር የሚሄደው ተሐድሶ መጽሐፍን ሳይሆን ጊዜን የሚከተል ሆነ!!
  3. ለማንኛውም እንደነገራችሁን በግንቦት 2004 ዓ.ም ሲኖዶስ በግልጽ ውግዘት ተለይታችኋል፡፡ውሳኔው የቅ/ሲኖዶስ ነውና ይግባኝ የለውም!!ከተወገዛችሁበት ኑፋቄ ከተመለሳችሁ ግን አሁንም በሩ ክፍት ነው!!በተረፈ ከቅጽር ውጭ ተደርጋችኋል፡፡ቤቱ የእናንተ አይደለም ተብላችኋል፡፡ለቃችኋል፡፡ቤት ለይታችኋል!!ስለዚህ በማትኖሩበት ቤት ውስጥ ስለሚካሄድ ነገር ሁሉ አስተያየት የመስጠት መብት የላችሁም፡፡ብቁ አይደላችሁም፡፡to put it in legal term፡- you do not have vested interest, you do not have legal capacity to institute any case against our beloved EOTC!!አ…ያ…ገ…ባ…ች…ሁ…ም!!ቢገባችሁ እየፈጸማችሁት ያላችሁት ድርጊት ደረቅ ወንጀል ነው!!እረፉ!!ሕገ - መንግሥቱ የሃይማት ነጻነትን ስለሚፈቅድ ከማለቃቀስ ሰልፍ ይዛችሁ ከማኅበራት ኤጄንሲ ፈቃድ አውጡ!!ከዛ ከወፋፍራም የሀገራችንና የናይጄሪያ ፓስተሮች ጋር ተኮልኩላችሁ የምዕራባውያንን ደጅ ጥኑ!!ቤታችሁ ይሞላል!!እውነቴን ነው!!ጌታ ምስክሬ!!
  4. እንግዲህ እኛ ተሐድሶን ለማስጠናት ቅኔ ሞላሁ ብላ ራሷን እንደ መጽሐፍ ሊቅ እንደምታየው ውትርትሯ ሙሴ ወይም ኦርቶዶክሳዊነቱን በትሪኒቲ የፕሮቴስታንት መጽሔት በኩል ከነገረን በኋላ መልሶ “ኦርቶዶክስ መልስ ካላት ጥያቄ አለኝ” እንደሚለው ጥራዝ - ነጠቁ ፅጌ ባሉ ሰዎች እንድናስጠና አይጠበቅም!!ካልሆነ ፕሮፖዛል ለኦባማ እንላክ እንዴ!!እሱ ደግሞ ወንድን ከወንድ በተክሊል ካላጋባችሁ ኋላቀር ናችሁ ሊለን ነው!!የስዊድን ሚሽነሪም እንኳን ለኛ ለመካነ ኢየሱስም የጌይ መብት ካልጠበቅሽ አልረዳሽም ብላ ፈንድ አቋርጣለች!!ፓስተር ዳዊት እንዳያጠናልን ደግሞ ለአንድ ሰይጣን ማባረሪያ ከሩኒ እኩል ክፈሉኝ ማለትን አምጥቷል!!በሰይጣን 80ሺህ ብር!!እናንተን እንዳንቀጥር አድራሻና ሥም የላችሁም!!በዚህ ላይ በየትኛው ሰበካ ጉባኤ ሥር፣በየትኛው ቅ/ሲኖዶስ ሥር፣በየትኛው ጉባኤ እንደተማራችሁ፣አናውቅም!!የምናውቀው የፕሮቴስታንትና ሥጋዊ ባለሥልጣናት ተቋማት ሳይቀር በአክብሮት የሚመለከቷቸውን የኢኦተቤክ አስተዋጽኦች ስታጣጥሉ ነው!!ከሚያጣጥለንን ለመጠበቅ አጣጣዩን እንቀጥር!!ኡኡቴ!!ክላ!!ወግድ!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Very Nice Brother. Anjeten Arasekew.

   Delete
  2. ሂሩይ አለማወቅህን አለማወቅህ ያሳዝናል፡፡ ፍሬ ሃሳቡን ለቀህ አንዴ አሜሪካ አንዴ ጀርመን እንዲሁም ስዊድን ከምትረግጥ ምናለ ጭብጥ ይዘህ ብታወራ፡፡ በነገራችን ላይ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከጀርመን እርዳታ ታገኛለች፡፡ ካላመንክ ሂድና የነስሃ አባትህን ጠይቃቸዉ፡፡ ጀርመኖች እርዳታዉን የሚሰጡት አገሪቱ የክርስቲያን አገር ነች ብለዉ በማሰብ ለወንጌል አገልግሎት እንዲዉል ነዉ፡፡ እዚህ ግን የሚሰራዉ ለሌላ ነዉ፡፡ ስለ ተክልዬ ፣ አቦዬ፣ አርሴማ….ወዘተ ስታወራ ዉለህ ብታድር የሚተናኪልህ የለም፣ ስለክርስቶስ አዳኝነት አንዲት ቃል ከተናገርህ ግን ጀርባዉ ይጠና ትባላለህ፡፡ ሰይጣን የፈጣሪን ክብር ለፍጡራን እንዲሰጥ በማድረግ ሰዉን ከእግዚአብሔር መለየት ዋና አላማዉ ነዉና በዚህ መንገድ ተሳክቶለታል፡፡ የክስርስቶስን ስም ስትሰማ እየደነገጥክ፣ ስብከቱና ዝማሬዉ ሁሉ ስለእነ ተክልዬና አቦዬ ብቻ እንዲሆን እየተመኘህ በምን ሞራል ስለ ቤተ ክርስቲያን ትሟገታለህ? ቤተ ክርስቲያን ማለት እኮ የክርስቲያች ቤት ማለት ነዉ፡፡ ክርስቲያን ማለት ደግሞ ክርስቶስን የሚከተል ማለት ነዉ፡፡ ክርስቶስን የሚከተሉትን እያሳደዳችሁ ስለ ቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ ልትሆኑ አትችሉም፡፡ በየገዳሙ የተደረቱ የፈጠራ ድርሰቶችን በማነብነብ ተዉልዱን ይዘን እንዘልቃለን ለማለት ደግሞ ረፍዶባችኋል፡፡ ትዉልዱ ነቅቷል፡፡ ስለዚህ መታደስን ይፈልጋል፡፡ ሲወርድ ሲዋረድ በሚል ብሂል በስማ በለዉ ከመኖር ወጥቶ እዉነተኛዉን የእግዚአብሔር ቃል፣ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ጀምሯል፡፡ ስለዚህም ወደድክም ጠላህም ተሀድሶ ያስፈልጋል፡፡

   Delete
  3. ለanonymous january 23, 2015 at 10:36am
   አቶ አናኒሞስ እንዲህ አይነት የፍልስፍና ባለሟያ ሆነህ ግን እስካሁን በክህደት ውነስጥ ሆነህ አሉባልታ የምትነዛ መሆንህ በጣም ያደነግጣል። ፈላስፍው፦ ለመሆኑ አለማወቅህ አለማወቅህ መቸ ተነገረ? ምንስ ማለት ነው? አንተ ማወቅህን አወቅህ ማለት ነው የእውነት ወንጌልን በሐሰት መለወጥህ፤ ያልተፃፈ ማንበብህ፤ ክርስቶስ በዋለበት አላስዉል ብለህ ከነግብር አበሮችህ ሳትሆንና ሆነህ ሳትገኝ በክርስቶስ ደምና አለትነት የተመሰረተችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የምታንቋሽሽና የምትሰድብ፤ በክርስቶስ ቤተመቅደስ እንክርዳድ ጥርጥርካልተዘራ ብለህ የምትወራጭ፤ ሐሰተኛው ክርስቶስ ካልተሰበከ እያልክ በእውነተኛው ክርስቶስ ወንጌል የተሞላችውንና በፀሎት መጽሐፋቶቿ ሁሉ ክርስቶስን የየምትሰብከውንና የምታከብረውን ቤተክርስቲያን ወንጌል አትሰብክም እያልክ የአባትህ የሰይጣን መልክተኛ ሆነህ በሐሰት መክሰስህ በአጠቃላ ብዙ የእርኩሰትና የክፋት ንግግሮችን መናገርህ? ሌላው የሚያስገርመው የጀርመን መንግስት የክርስቲያን አገር ነች ብሎ በማሰብ ለወንጌል ማስፋፊያ ብሎ ገንዘብ ይሰጠል አልክና ካላመንህ ደግሞ የንስሐ አባትህን ጠይቅ አልከው። ይገርማል ድንቅ ተዋይ ነህ። ለምን ይሄን የተውኔት ችሎታህን ይዘህ የእሁድ መዝናኛ መድረክ ላይ አትወጣም። ተመልካቹ በተውኔት ችሎታህ ሳይሆን በበሬ ወለደ የፈጠራ ችሎታህና የሰው ልጆች ጠላት ከሆነው ከአባትህ ከሰይጣን በላይ ቀዳዳ መሆንህን በመረዳት በለበጣ ሳቅ በተፍነከነኩ ነበር። አንተ ደግሞ የመቸው ሉተር ነህ ባክህ?የእርዳታው አስማሚና አፈራራሚ ነበርህን? ያስደምማል! በክርስቶስ አምላክነትና አዳኝነት ያላመነ መንግስት ክርስቶስን ለለበሰች ቤተክርስቲያን የወንጌል ማስፋፊያ ብሎ ገንዘብ ይሰጠል አልክ! ልጄ ሆይ ና እግዚአብሔርን መፍራት አስተምርሀለሁ ተብሎ በተነገረው መልእክት ስር እግዚአብሔርን ስለመፍራት ከተዘረዘሩት አንዱ በሐሰት አትመስክርና አትዋሽ አንደኛው ሆኖ ሳለ አንተ ግን እግዚአብሔርን ሳትፈራ በሐሰተት እየመሰከርህ ትዋሻለህ። ለሁሉም ትንሽ ጫፍ ላይ ተንጠልጥለህ ዝሆን የሚያክል ውሸት አትልቀቅ። ለበጎ አድራጎት ስራ የሚውል እርዳታዎችን ከለጋሽ ተቋማት ምናልባት ልትቀበል ትችላለች፤ አንተ እንደተወንከው ውሸት ግን አይደለም። ለሁሉም በውሸት ተወልደህ በውሸት አድገሀልና መዋሸትህ ከአንተ በመቶ ሲደመር ጊዜ የሚጠበቅ ነው። የወለህ የውሸት አባት ሰይጣን ነውና። ከዛም ትቀጥልና የሚሰራው ግን ሌላ ነው ትላለህ። ምን ይሰራል እንደምትል ግልጽ ነው። ያም በንፋስ ተበትኑ የሚቀረው የተለመደው ሐሰተኛ አሉባልታህ ነው። ከአባትህ ከሰይጣን ስለእውነት እንደማይመሰክር አንተም ስለቤተክርስቲያን እውነተኛነት እንድትመሰክር አንጠብቅም። ከዛም ትቀጥልና ስለ አቡዬ፣ ስለተክልዬ፣ ስለ አርሴማ ወዘተ ስታወራ ብትውል ማንም አይተናኮልህም አልክ። ከማን ቤት ቁጭ ብለሽ ማንን ታሚያለሽ ነው የተባለው። በቤቷም ያመነችበትን ለመተናኮል ታስባለህ። የመጨረሻውን ግባችሁን በአጭሩ ተነፈስከው። አዎ እኛም ከመጽሐፍ ቅዱስ ተረድተናል እያወጃችሁለት ያለው ሐሳዊው መሲሐችሁ በመጣ ጊዜ ሰይፍና ቆንጨራችሁን ይዛችሁ የክርስቲያኖችን አንገት እንደምትከትፉ፤ ከምኩራብ(ከቤተክርስቲየን)እንደምታሳድዱ፤ የኤልያስንና የሄኖክን ምስክርነትም አልሰማ ብላችሁ ደማቸውን በአዳባባይ እንደምታፈሱ ፤በተቀደሰው አውደምህረት ላይም ከነአርኩሰታችሁ እንደምትቆሙ ተገልጧል። አንተም ወዳጄ ልብህ ለአመፃ እየተነሳሳ መሆኑን፤ የሰላምን ቤት ለማወክ ማቀድህን በተዘዋዋሪ ገለጥኸው። አይ ግብዝነት!ስለክርስቶስ አዳኝነት አንዲት ቃል ከተናገርህ ግን ጀርባው ይጠና ትባላለህ ተባለልኝ። መምሰል ትችሉበታላችሁ እናንት የሰይጣን መልክተኛ አባቦች። በመጀመሪያ ሳትማር ማን አስተማሪ አደረገህ? ሁለተኛ ቅጠለን ከበላችሁ ሁሉን አዋቂ ትሆናላችሁ አይነት የእባብ ምክራችሁንና ሐሰተኛ ትምህርታችሁን በቤተክርስቲያን ማራመድ አይፈቀድላችሁም። በቤተክርስቲየን አኛ አውነተኛው ሐዋሪያት የሰበኩልን ወንጌል ይሰበካል እንጂ ሌላ አዲስ እንግዳ ትምህርት አይነገርባትም። በቤተክርስቲያን ንፁሕ ጥርጥር የሌለበት ፍሬ ሀይማኖት ስንዴ ይዘራባታል እንጂ ጥርጥር ሀይማኖት የሚያስጥል እንክርዳድ አይበተንባትም። በቤተክርስቲያን እውነተኛው መሲህ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለካል እንጂ ሐሳዊ መሲህ የተባለው ሀሰተኛው ኢየሱስ አይመለክም። ስለሆነህም ከነመናፍቅነትህ የቤተክርስቲያኗ ልጅ ነኝ ማለት አይቻልም። የሐሰት ትምህርት ይዘህ በቤተክርስቲያን መቆም አይቻልም። ሌላው ምንም አይነት የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀቱ እንደሌለህ የሚታወቀው ሰይጣን የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡር አንዲጥ በማድረግ ነው ማለትህ ነው። አይጉድ ወዴት ጠጋ ጠጋ ወንድም። አደራ ሰይጣን ቅዱስ ሆኖ ለሰው ልጆች ክብሩን መንግስተ ሰማይን ይወርሱ ዘንድ የእግዚአብሔርን ወንጌል መስበክ ጀመረ እንዳትለንና እቅጩን አኛ አንዳትነግረን። ክርስቶስ እኮ ቤዛ የሆነን ትንሳኤውን በሚመስል እንድንነሳ የክብሩ ወራሾች የመንግስተሰማይ ባለቤት እንሆን ዘንድ ነው ወንድም። አንተ ያመኑት የክብሩ ወራሾቹ መሆናቸው ከሆነ የደነቀህ፦ጌታ ኢየሱስ ሐዋርያቱን " እናንተስ አስራሁለት ወንበር ላይ ቁጭ ብላችሁ ትፈርዳላችሁ" ብሎ የመፍረድ ስልጣንን ሰጧቸዋልና ገና በምፅዓተ ጊዜ የናቃችኋቸው ሁሉ ይፈርዱባችኋል።አትቅጠፍ! የአቡየ የተክልየ የሚባል ስብከት የለም። ነገር ግን የእግዚአብሔር ባሪያዎች ናቸውን በእምነታችው ፍፁምነት ስለተሰጣቸውና የእግዚአብሔርን ስም ጠርተው ስላደረጉት ተጋድሎ የሺ የነገራል። ይሔ ደግሞ በወንጌል "ይች ሴት ያደረገችው ወንጌል በሚነገርበት ሁሉ የሺ የነገራል" ተብሎ እንደተነገረው ማለት ነው። ስሙን ስትሰማ አኛ አየደነገጥ ላልከው ለማያውቅህ ቧልትህን ቧልትለት። አላየናችሁም እንዴ ሐያል ስሙን ለተጣለው ሰጥታችሁ ፈንግል እንደያዛት ደሮ በአዳራሾቻችሁ አግዳሚ ወንበር ስር ስትንፈራገጡና ስታጓሩ። ተቃጠልን እያላችሁ ወባ እንደያዘው ስትንቀጠቀጡና ስትርበደበዱ። ምን ይሆን በየአዳራሾቻችሁ ያለው የሁከትና የጩኸት እሪታ መንስኤው? ሳታምን በሰይጣን ታስረህ ስሙን መጥራትህ አቃጥሎህ አይደለምን? ሌላው ቤተክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች ቤት ማለት ነው፤ ክርስቲያን ማለት ደግሞ ክርስቶስን የሚከተል ማለት ነው ብለሀል። እውነት ነው ግን ይችን የወሰድካትና የሰማሀት ከተሐድሶ ፕሮቴስታንቶች አይደለም እርግጠኛ ነኝ። ለሁሉም አንተ ካለህበት የመጣ የለም፤ አንተና መሰሎቻችሁ ሐሰተኛ እንግዳ ትምህር ይዛችሁብን መጥታችሁ የምትበጠብጡን እናንተው ናችሁ። ቤተክርስቲያን ይህ የኔ እርስት ነውና አልሰጥም ወግዱ ፤ እኔ ወደ እናንተ አልመጣም፤ መንገዴም ከመንገዳችሁ የተለየ ነው፤ እናንተ ከሰይጣን ናችሀ እኔ ከክርስቶስ ነኝ ነው ያለቻችሁ። ሌላው ያላዋቂ ሳሚ የሆነውን ከሰይጣን በስተቀር ሰሚ ያጣውን ቅዱሳንን፣ ገዳማትንና ቅዱሳት መጽሐፍትን የምትነቅፉበትን ሐሰተኛ ክስና ቧልት እንዳልከው ትውልዱ ነቅቶባችኋልና እነዚህ ማንነታቸው የጠፍባቸው እንዳያስተውሉ አዚም የተደረገባቸው እያለ ያልፍችኋል እንጂ አይሰሟችሁም። አንተ እንዳልከው ዛሬ ትውሉዱ መጽሐፍ ቅዱስ አንብቡ የሚለውን የማስመሰያ የሰይጣን ሽንገላን ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለምን ያስተምራል የሚለውን ያወቀበት ሰዓት ነውና ያንተን ተውኔት ተወው ይልሀል።

   Delete
  4. So join the group which agree with what you say. Why bother ?

   Delete
  5. አቶ ዳ-ሞት
   በጥራዝ ነጠቅ ከምትኖር ምናለበት መጽሐፍ ቅዱስ ብታነብ? ሰፋ አድርገህ ማሰብ በቻልክ ነበር፡፡ በራስህ ጎሬ ሆነህ ከምታላዝን የአስተሳሰብ አድማስክን ሰፋ አድርገህ ነገሮችን ከተለያዬ አቅጣጫ መመዘን ብትችል መልካም ነዉ፡፡

   Delete
  6. ዳ-ሞት በሌላ ብሎግ እንዲህ ብለህ ተናዘህ ነበር

   አዩJanuary 25, 2015 at 5:35 PM

   ዉድ ወልድ ዋህዶች እንደምን አላችሁ? እኔ መናፍቃኑ ለሚያወጧቸው ቤተክርስቲያንንና የቤተክርስቲን ልጆችን በሐሰት ለሚወነጂሉበትና በፀያፍ ቃላቶቻቸው ለሚዘልፉበት፤ እንዲሁም ሐሰተኛ ትምህርታቸው በሚያስተላልፍባቸው ጽሑፎቻቸው እሾህን በሾህ እንደሚባለው ባይሆንም በአዳራሾቻቸው የማውቀውን የክህደት ሰይጣናዊ የሆነውን ተውኔት እየጠቀስኩ አስተያየት እሰጣለሁ። ብዙ ጊዜ የኮሜን ስሜን እየቀያየርሁ ነው አስተያየት የምሰጠው። ያንም የማደርገው ካወጡት ክህደት አንፃር ይሄን ልጠቀም በማለት ነው። በቅርብ ግን ዳሞት በሚል ብዙ አስተያት ሰጥቻለሁ። በእናንተ እይታ አስተያየት መስጠቴ ስህተት አድርጌ ይሆን? በአስተያየቴስ ቤተክርስቲያንን አስነቅፊያት ይሆን? ሌላው መናፍቃኑ የተጠቀሙበት የመጠሪያ ስም ተሐድሶ ከሚለው ውጪ የቤተክርስቲያኗ ስም ነውና ስሟን በህግ ለምን አታስከብርም? ሰይጣን ይሄን ስም የመረጠው ለማወናበድና ለማሳሳት መሆኑ ግልጽ ነው። በተረፈ በእኔ አይታ የያዛችሁት ተሐድሶ ተብየዎቹ ምን እየሰሩና ምን እያሉ በሐሰት መንገድ እንደሚጏዙ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እየጠቀሳች የምታደርጉት ማጋለጥና የምትሰጡት ትምህርት መልካም ሆኖ አግኝቸዋለሁና በዚሁ በርትታችሁ ቀጥሉ። ለእናንተም እግዚአብሔር ከፈታኙ ፈተና ድል የምታደርጉበትን ሐይል ይስጣችሁ።አዩJanuary 25, 2015 at 5:35 PM

   ዉድ ወልድ ዋህዶች እንደምን አላችሁ? እኔ መናፍቃኑ ለሚያወጧቸው ቤተክርስቲያንንና የቤተክርስቲን ልጆችን በሐሰት ለሚወነጂሉበትና በፀያፍ ቃላቶቻቸው ለሚዘልፉበት፤ እንዲሁም ሐሰተኛ ትምህርታቸው በሚያስተላልፍባቸው ጽሑፎቻቸው እሾህን በሾህ እንደሚባለው ባይሆንም በአዳራሾቻቸው የማውቀውን የክህደት ሰይጣናዊ የሆነውን ተውኔት እየጠቀስኩ አስተያየት እሰጣለሁ። ብዙ ጊዜ የኮሜን ስሜን እየቀያየርሁ ነው አስተያየት የምሰጠው። ያንም የማደርገው ካወጡት ክህደት አንፃር ይሄን ልጠቀም በማለት ነው። በቅርብ ግን ዳሞት በሚል ብዙ አስተያት ሰጥቻለሁ። በእናንተ እይታ አስተያየት መስጠቴ ስህተት አድርጌ ይሆን? በአስተያየቴስ ቤተክርስቲያንን አስነቅፊያት ይሆን? ሌላው መናፍቃኑ የተጠቀሙበት የመጠሪያ ስም ተሐድሶ ከሚለው ውጪ የቤተክርስቲያኗ ስም ነውና ስሟን በህግ ለምን አታስከብርም? ሰይጣን ይሄን ስም የመረጠው ለማወናበድና ለማሳሳት መሆኑ ግልጽ ነው። በተረፈ በእኔ አይታ የያዛችሁት ተሐድሶ ተብየዎቹ ምን እየሰሩና ምን እያሉ በሐሰት መንገድ እንደሚጏዙ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እየጠቀሳች የምታደርጉት ማጋለጥና የምትሰጡት ትምህርት መልካም ሆኖ አግኝቸዋለሁና በዚሁ በርትታችሁ ቀጥሉ። ለእናንተም እግዚአብሔር ከፈታኙ ፈተና ድል የምታደርጉበትን ሐይል ይስጣችሁ።

   Delete
 4. ለዘመናት ትክሻችንን ያጎበጡት ሰርጎ ገብ የኑፋቄ ትምህርቶች እስካልተወገዱና ቤተ ክርስቲያን እዉነተኛዉን የክርስቶስ ወንጌል ብቻ አጠናክራ እስካልሰበከች ድረስ የተሀድሶ ጥያቄ አይቆምም፡፡ ሰይጣን በተለያዩ ስልቶችና መንገዶች የተሃድሶ እንቅስቃሴአችንን ለመገደብ ቀን ከሌት ቢደክምም ከእኛ ጋር ያለዉ ከሁሉ ይበልጣልና ጭንቅላቱን እንረግጠዋለን እንጅ ሊቋቋመን አይችልም፡፡

  ReplyDelete
 5. ትክክለኛ የምድራውያን አስተሳሰብ ርዕሰ አንቀጽ ነው። ገማልያን ካነሳችሁማ እናንተን ነበር እንደገማልያ ኦርቶዶክስ ሐይማኖትን ለከነትምህርቷ ለአማኞቿና ለአገልጋዮቿ ተዋት ተመሳስላችሁ ሐዋርያት ያልሰበኩላትን የሐሰት ወንጌልን ለማስጋባት በውስጧ ሆናችሁ አትበጥብጧት የሚላችሁ የሚያስፈልገው። እናንተን ነበር እንጂ የተለየ አጀንዳ ካላችሁ አጀንዳችሁን አዳራሽ ሰርታችሁ አራምዱ የሚላችሁ እንደገማለያ ያለ በተነሳላችሁ። በርዕሰ አንቀጻችሁ ማንነታችሁን ገለጣችሁ። ይኸውም ቅዱሳንና መጥላትና ማሳደድ የእውነተኞች ክርስቶሳውያን መገለጫ አለመሆኑን። እናንተ ግን አምላክን ተራ ደካማ ሰው አድርጋችሁ አማላጂ ስትሉ ያከበራቸውን ለምን ከበሩ እያላቸሁ ስታላግጡ ፤ የእግዚአብሔር የአምልኮ ስርዓት ልማዳዊ እያላችሁ እስትክዱና ስትተቹ ነው በየጽሑፎቻችሁ የምትታዩት። ደግሞ በበአላት ምክንያት ድህነት በዛ። አይጉድ እናንተ ሰርታችሁ መቸ ከብልጌት በአላሙዲንም በልጣችሁ ተገኛችሁ?ከስም አጥፊነትና በጥባጭነት ውጭ ምን መታወቂያና መጠሪያስ አላችሁ?ለመን ከአሜሪካ ጎን ያለችው ሀይቲ ድሀ ሆነች?የሀይቲ ህዝብ በአል ብቻ እያከበረ ሥራ ስለማይሰራ ነውን?ሌላም ብዙ ድሀ አገሮችን መጥቀስ ይቻላል። ለማንኛው የጻፋችሁት አንድ ነገር ጎሎታል። ይኸውም የአዳራሾቻችሁ ኦርጋን ሳክስፎን፣ ጊታር ፒያኖ፣ ረጌ ራጋ ኦፔራ ዳንሳችሁ። ለሁሉ የአርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንድ ጊዜ አለቱ አዲስ አድርጎ መስርቷታል። አለቷም ክርስቶስ ነው። እዛው እናንተው የአሸዋ ላይ ቤታችሁን አድሱ። ምናልባት የአዳራሾቻችሁ ጣራዎች ብልና ዝግ በልቷቸው ከሆነ እነሱን አድሱ። መታደስ ካለባችሁ እዛው ታደሱ። የጉሪያ መንፈስ፣ ሎሮሮሮ ሟሟሟ ተረረም የሁከት መንፈስ፣ ስርዓት አልባ የእሪታ የሁከት ድብልቅልቅ እንዲሁም የውሸት ወንጌል መገለጫዎቻችሁ እረ በጭራሽ እዛው በቦታችሁ።

  ReplyDelete
 6. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ ያነጣጠረው የ”ተሓድሶ” እንቅስቃሴ ከምን ተነስቶ እዚህ እንደደረሰ በማወቅና ብሎም የበኩላችንን አስተዋጽኦ በማድረግ ያላወቁትን ደግሞ በማሳወቅ ከዚህ የኑፋቄ መንገድ እንዲጠበቁ እናድርግ፡፡
  http://weldwahed.blogspot.nl/2015/01/715.html

  ReplyDelete
 7. በጣም ደስ ብሎኛል ተባረኩ አዳዲስ መረጃዎችን አሁንም ብታቀርቡ በጣም ነዉ ደስ የሚለኝ ፣

  ReplyDelete
 8. አጥኞቹ መጀመሪያ ራሳችውን ቢያጠኑ ምናልባት ለራሳቸው ይሆኑ ይሆናል ሕቱ ርእሰክሙ ራሳችሁን እዩ!
  ቢሆንም ባይሆንም ይኸው ነው ከዚህ በስተቀር ለመላዋ ቤተ ክርስቲያንስ ይቅርና ለቤተ ሰብእም አይሆኑ
  ዳሩ ግን መራጮችንም ተመራጮችንም እንዲሁም ባዮችንም ተባዮችንም ባይነ ምሕረት ይመልከት።

  ReplyDelete
 9. አጥኞቹ መጀመሪያ ራሳችውን ቢያጠኑ ምናልባት ለራሳቸው ይሆኑ ይሆናል ሕቱ ርእሰክሙ ራሳችሁን እዩ!
  ቢሆንም ባይሆንም ይኸው ነው ከዚህ በስተቀር ለመላዋ ቤተ ክርስቲያንስ ይቅርና ለቤተ ሰብእም አይሆኑ
  ዳሩ ግን መራጮችንም ተመራጮችንም እንዲሁም ባዮችንም ተባዮችንም ባይነ ምሕረት ይመልከት።

  ReplyDelete
 10. If you think tehdiso is doing well you will never publish it. We know the truth. We don't need tehadiso. What we need it preach the gospel and create awareness about your false movement. Thanks

  ReplyDelete