Sunday, January 25, 2015

የተሐድሶ እንቅስቃሴ በሚያስገርም ፍጥነት እየሄደ ነው።

Read in PDF


እኔው ነኝ
  ከዛሬ አራት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ያለውን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ያለበትን ደረጃ በጽሑፍ አቅርቤ እንደነበረ ይታወሳል። በዚያ ጽሑፌ ማህበረ ቅዱሳንና የተሐድሶ አንቀሳቃሾችን "ሁለቱ ኃያላን‚ በማለት ገልጫቸው ነበር አሁን ግን ኃያልነቱን ለተሐድሶዎች ብሰጥ የተሳሳትሁ አልሆንም። ከአራት ዓመት በኋላ ያለው እይታዬን ደግሞ እነሆ!  ሁለቱ እንደ እስማኤልና ይስሐቅ ወይም እንደ ኤሳውና ያዕቆብ እርስ በርስ የሚገፋፉ ናቸው። ተሐድሶዎች ማህበረ ቅዱሳንን የባሪያቱ ልጅ ይሏቸዋል። እስማኤልና ይስሐቅ ከአንድ አባት እንደተወለዱ ሁሉ ማህበረ ቅዱሳንና ተሐድሶዎችም ከአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የተወለዱ ናችው። ሁለቱ በአንድ ባል ከሚተዳደሩ፣ በአንድ ቤት ከሚኖሩ ሁለት እናት እንደተወለዱ ሁሉ ማህበረ ቅዱሳንና ተሐድሶዎችም ባንድ ጌታ ከተሰጡ በአንድ ሐሳብ ላይ ከሚያጠነጥኑ ከብሉይ ኪዳን እና ከሐዲስ ኪዳን የተወለዱ
ማህበረ ቅዱሳን ከብሉይ ኪዳን ተሐድሶዎች ከሐዲስ ኪዳን ተወልደዋል። ይህን ያልኩበት ምክንያት ማህበረ ቅዱሳን እንደ ፈሪሳውያን ወግ አጥባቂ ሲሆኑ ታቦትና የብሉይ ኪዳን ሕጎችን እንደ ወር አበባና የአመጋገብ ሥራት የመሳሰሉትን ልክ እንደ አይሁድ ስለሚከተሉ ነው። ተሐድሶዎች ግን ብሉይ በሐዲስ ስለተተካ የአይሁድን ሕግ የመከተል ግዴታ የለብንም ኃጢአትን ማድረግ የለብንም እንጂ የአይሁድን ልማድ ለመከተል አንገደድም ይላሉ። በዚህም ምክንያት ማህበረ ቅዱሳን ተሐድሶዎችን ያሳድዳሉ። በገላትያ ም 4፥22 ላይ ባርያይቱ አጋር በብሉይ ኪዳን የተመሰለች ሲሆን ልጇ እስማኤል የአሳዳጆች ምሳሌ ሆኖ ቀርቧል። ሳራ ደግሞ የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ ስትሆን በስተርጅና የወለደችው ልጇ ይስሐቅም የስደተኞች ምሳሌ ሆኗል። ስለዚህ ማህበረ ቅዱሳን የባሪያይቱ ልጅ፣ ተሐድሶዎች የጭዋይቱ ልጅ ይባላሉ። ተሐድሶዎች ኦርቶዶክስ በስተርጅና የወለደቻቸው የተስፋው ቃል ልጆች ናቸው። 

   እስኪ ቃሉን አንብቡትና ሐሳቡን አስተውሉት "እናንተ ከሕግ በታች ልትኖሩ የምትፈልጉ ሕጉን አትሰሙምን? እስኪ ንገሩኝ አንዱ ከባሪያይቱ አንዱም ከጭዋይቱ የሆኑ ሁለት ልጆች ለአብርሃም እንደነበሩት ተጽፏልና። ነገር ግን የባሪያይቱ ልጅ እንደ ሥጋ ተወልዷል የጭዋይቱ ልጅ ግን በተስፋው ቃል ተወልዷል። ይህም ነገር ምሳሌ ነው። እነዚህ ሴቶች እንደሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና ከደብረ ሲና የሆነችው አንዲቱ ልጆችን ለባርነት ትወልዳለች እርስዋም አጋር ናት.. . እኛም ወንድሞች ሆይ እንደ ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጆች ነን። ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው። ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? የባሪያይቱ ልጅ ከጭዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት‚ ይላል ገላ 4፥30። ሙሉ ቃሉን ከዚያው ከመጽሐፍ ቅዱሱ በማንበብ ሐሳቡን ልትገነዘቡ ትችላላችሁ።
  እስማኤል እንደ ሥጋ የተወለደ ነው ማለት በአብርሃምና በሣራ ምክር የተወለደ ነው እስማኤል ሲወለድ አብርሃም ሥጋው ገና አልሞተም ነበር። ስለዚህ እንደ ሥጋ የተወለደ ተባለ። ይስሐቅ ግን አብርሃም ሥጋው ከሞተ በኋላ ማለት የግብረ ሥጋ ፍትወቱ ከደከመ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ አነቃቂነት የተወለደ ስለሆነ የእምነት ልጅ ወይም እንደ መንፈስ የተወለደ ነው።
  እስማኤል ይስሐቅን ያሳድደው ነበር ሣራ በዚህ ተቆጣች፣ አብርሃምም በሁለቱ ልጆች ተቸገረ እግዚአብሔርም የባሪያቱ ልጅ አይወርስምና አስወጣ አለው። የባሪያይቱ ልጅ የተስፋውን ቃል ስለማይወርስ ማሳደድን እስከ ዛሬ ድረስ ሥራ አድርጎ ይዞታል።
 ወደ ዋናው መልክቴ ልመለስ፣ በርካታ ተሐድሶዎች እንደሚመሰክሩት በማህበረ ቅዱሳን የተገፉ የተደበደቡ ከደሞዛቸው የታገዱ የተገለሉ ናቸው። በዚህ ምክንያት አገልግሎታቸውን በሥውር አድርገውታል። ማኅበረ ቅዱሳን እንዳንድ የመድረክ አገልጋዮችን ተሐድሶ ናቸው ይላል። እነዚህ ሰዎች  እንኳን ተሐድሶ ሊሆኑ በተሐድሶ መንደርም አላለፉም ተሐድሶዎች እነዚህን የመድረክ አገልጋዮች ቢሆኑ ኖሮ በተሃድሶ ተስፋ እቆርጥ ነበር። ተሐድሶዎች የመድረክ ሰዎች አይደሉም ማንም አያውቃቸውም የመታየት ፍላጎትም የላቸውም ሥራቸው እንጂ እነርሱ አይታወቁም። የተሠወሩት እውነትን ስለአልያዙ ሳይሆን የማህበረ ቅዱሳንን ድብደባ ስለፈሩ ብቻ ነው። ዛሬ በየትኛውም ገዳምና ደብር ተሐድሶዎች አሉ። የዛሬ አራት ዓመት ጥቂት ቢሮዎች ነበሯቸው አሁን ግን በመላ ኢትዮጵያ ተዘርግተዋል። በተለይም የተወሰኑ ተሐድሶዎች በሲኖዶሱ ቀርበው ሳይጠየቁ በማህበረ ቅዱሳን ከሳሽነት ከተወገዙና በሚዲያ ከተነገረ በኋላ ወደ ተሐድሶዎች የሚሔደውን ሕዝብ ብዛት ለማስተናገድ ካቅም በላይ መሆኑን ብዙ የተሐድሶ መሪዎች ይናገራሉ። ዘንድሮ በ2007 ጥቅምት ላይ በተካሄደው ሲኖዶስ ላይም የተሐድሶዎች መስፋፋት መላ አገሪቱን እያዳረሰ መሆኑን ብዙ ጳጳሳት ሪፖርት አቅርበው አጥኚ ኮሚቴ እስከማቋቋም ተደርሷል። በብዙ አካባቢዎች ማህበረ ቅዱሳን እየወጣ ተሐድሶዎች እየገቡ ነው። ታዲያ የባርያቱ ልጅ አይወርስም ማለት ይህ አይደል?
   የተሐድሶዎች እንቅስቃሴ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ ኢትዮጵያን እንደሚወርሱ ምንም ጥርጥር የለውም። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ይህን የተሐድሶ ማዕበል ለማስተናገድ እራሷን ከወዲሁ ማዘጋጀት አለባት፤ ከዚህ ውጭ ማሳደዱ አያዋጣም የበለጠ ማቀጣጠል ነው የሚሆነው። በጣም የሚያስደንቀው ነገር የተሐድሶ እንቅስቃሴው በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ እንደ ሰደድ እሳት በጣም እየተቀጣጠለ መምጣቱ ነው።ይህም በሥውር በጥንቃቄ የሚካሄድ በመሆኑ ማን ምን እንደሆነ ማወቅ አይቻልም። ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶው ከስዉርነት እንዲወጣና በግልጥ እንዲንቀሳቀስ ብታደርግ ለመቆጣጠርና በራሷ መንገድ እንዲሄድ ማድረግ ትችል ነበር። ይህም ቤተ ክርስቲያኒቱ ያሏትን ጠቃሚ እሴቶች ለመታደግ የሚያመች መንገድ ነው። በግትርነቷ ከጸናች ግን የተሐድሶ ማዕበል ይዟት ጥርግ ሊል ይችላል። ማህበረ ቅዱሳን ላይወርስ በከንቱ የተስፋውን ልጅ መግፋቱ ከባሪያይቱ እናቱ ጋር ከቤት ለመውጣት የቀረለት ዘመን ጥቂት ሆኖ ነው የሚታየኝ። የባሪያይቱ ልጅ አይወርስም ማለት የሥጋ ሥራት በሆነው በብሉይ ኪዳን አስተሳሰብ የተወለደ ሁሉ አይወርስም ማለት ነው። ማህበረ ቅዱሳንም የሥጋ ሥርዓትን ማለት የፊደል አገልግሎትን እየተከተለ ይስሐቅን ማለት ተሐድሶን አስወጥቶ እወርሳለሁ ማለቱ የማይሆን ነገር ነው።  
 ተሐድሶዎች በቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ ትምህርት የበለጸጉ ናቸው። እንዲሁ ሲመለከቷቸው ምንም አቅም የሌላቸው የሚመስሉ ያው የቆሎ ተማሪዎች ናቸው። በአንጻሩ ማህበረ ቅዱሳን በዘመናዊ ትምህርት የበለጸጉ ዶክቶሮች ኢንጅነሮች ሲሆኑ በርካታ ካህናትን ሊቃውንትንም ከነርሱ ጋር ማሰለፍ ችለዋል ልክ እንደ እስማኤል ትልቅ ናቸው። ተሐድሶዎች ደግሞ እንደ ይስሐቅ ትንሽ ናቸው ግን እንደ ተስፋው ቃል እየወረሱ ናቸው። ብዙዎቹ የኦርቶዶክስ ካህናት አባሎቻቸው ከተሐድሶዎች ሓሳብ የራቁ አይደሉም።
   ሌሎች የማህበረ ቅዱሳን አባላት በየዋሕነት ጊዚያቸውንና ገንዘባቸውን ሙያቸውን ለቤተ ክርስቲያን በመስጠት ጠንካራ ጎን አላቸው። ነገር ግን ወግና ሥርዓትን ጠንቅቀው በመፈጸም መንፈሳዊ የሆኑ ስለሚመስላቸው መንፈሳዊ አይደለም ብለው የገመቱትን ሰው አድመው ያዋክቡታል። ተሐድሶዎችን ያበዛቸው ይህ ዓይነቱ የማህበረ ቅዱሳን አካሄድ ነው እግዚአብሔር ይስሐቅን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋ አበዛሃለሁ ነበር ያለው ለተሐድሶዎችም እየሆነ ያለው ይኸው የተስፋ ቃል ነው። እኔ ግን እግዚአብሔር ሁሉንም ለበጎ ያደረገው ይመስለኛል ተሐድሶዎች ባይገፉ ኖሮ እንደዚህ ጨካኞች ሊሆኑ አይችሉም ነበር፣ ማህበረ ቅዱሳንም ባይገፋቸው ኖሮ እውነት አይገለጥም ነበር። ስለዚህ ሁሉም ለበጎ ነው ማለት ይቻላል። ብልህ ለሆነ የቤተ ክርስቲያን መሪ የምመክረው ግን ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶዎችን ወደ ውጭ መግፋት የለባትም ነው። ይልቁንም ተቀብላ ብታስተናግዳቸው ተሐድሶውን እንደምትፈልገው ለማካሄድና ተቋማዊ ያስተዳደር ሥርዓቷን ለትውልዱ በማስረከብ ለምድራችን ታላቅ በረከት ትሆናለች የሚለውን ነው። ይታሰብበት!!!!

27 comments:

 1. እኔ አልሰማህምJanuary 25, 2015 at 8:49 PM

  አንተው ነህ ሰይጣን? ምነው ተርበደበዳችሁ? በተሐድሶ መናፍቃን ዙሪያ ጥናት ለማካሔድ መታቀዱ ከርምጃው በፊት እያስደነበራችሁ ነው አይደል? ሰይጣን መቸም የምናገረውና የምሰራው ትክክል ነው እንደማይል የታወቀ ነው ። ታዲያ የቁጥር ቀመሩን ቀመርከውና ተሐድሶ ምደድርን አጥለቀለቃት አልክ። አይ አንተውነህ ሰይጣን! ታዲያ ምድር እኮ በርኩሰት ነው የተሞላው። ያ ማለት ደግሞ አንተና መናፍቃን ተሐድሶዎች ናችሁ። ለሁሉም ክርስቶስ ቀራጮችንና ነጋዴዎችን ቤቴ የፀሎት ቤት ናት ብሎ እንዳስወጣቸው ቤተክርስቲያንም ኦርቶዶክስ ተዋህዶም ቤቴ የክርስቶስ እውነት የሚነገርባት እንጂ የሐሰት ወሬና ምንፍቅና የሚቦለትባት አይደለችምና ከቅጥሯ ታስወጣችኋለች። ቤተክርስቲያን እውነትን መንገር እንጂ እውነትን መቀበል የሰሚው ምርጫ ነው። እናንተ ከቁጥር ጋር ትጫወታላችሁ የቁጥር ብዛት የሚያፀድቅ ይመስል። የተጠሩት ብዙዎች የታደሙት ግን ጥቂቶች ተብሎ እንተፃፈ አትርሳ። ሌላው አስገራሚው ምን ያህል ከውነት የራቅና የወጣችሁ እንደሆነና ምን ያክል ለክርስቶስ እውነተኛ ወንጌል ተፃራሪዎች መሀንህና መሆናችሁን ያገለጥህበት እራሳቸውን ደብቀው ማለትህ ነው። በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ነው እንጂ ተደብቆ የሚል የለም። ተደብቆና ተመሳስሎ የሚያሰናክል ጠላት ሰይጣንና ግብር አበሮቹ እንተና መሰሎችህ ናቸው። በመጨረሻ እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች የሆናችሁ ይሔ የሞት ማወጃ ና አሉባልታ መንዣ የሆነ ብሎግ አትጎብኙ። እነሱ በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡ ስማቸውን እየለዋወጡ ብዙ ነን ለማለት ይሞክራሉ። አላማቸው ደግሞ አሉባልታ እየነዙ ብሎጋቸው እንዲታይና ገንዘብ መሰብሰቢያ ለማድረግ ነውና። በተረፈ የአቶ እኔው ነኝ ሰይጣን እርህሰ አንቀፅ አንድም እውነት የለውም። የጠቀሳችው በአባታቸው አንድ የሆኑት ወንድማማቾችም አንዱ አንዱን አሳደደ አልተባለም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ ሰይጣንማ ያለዉ የት እንደሆነ ጠንቅቀን ስላወቅን ነዉ ጥለነዉ የወጣነዉ፡፡ ፍትሐ ነግስት የምን መጽሐፍ ይመስልሃል? የድግምትና የጥንቆላ አይደለም? ደጋሚዎች፣አስማተኞች፣ ሟርተኞች፣ ደብተራዎች ማንን ተጠግተዉ የሚኖሩ ይመስልሃል? ዝምብሎ ማፏጨት የትም አያደርስህም ወንድም፡፡

   Delete
  2. please take and read it. you do not now b/c some body told you thet it is but your knowledge is up to this

   Delete
 2. Keep dreaming fools!

  ReplyDelete
 3. 100%
  false story orthodox tewido and mahibere kidusan will never fail

  ReplyDelete
 4. ስለላካችሁልኝ ወቅታዊ መረጃ በጣም አመሰግናልሁ ተባረኩ ፣በርቱ የሰማይ አምላክ ያከናዉንልናል እኛም ባሪያዎኡ ተነስተን እንሰራለን ፡፡ነህ2፡21 አስተያየት አለኝ 1) ዉዳሴ ማርያም ን ወይም መዝገበ ጸሎትን ከክርስትያናዉ አምልኮ አንጻር ሌሎችንም ጭምቅ እያደረጋችሁ በቃሉ ብትተቹት 2) ከተቻለ ዚቅንም› 3) መልካመልኮችን ሁሉ ገድላገድሎችንም 4) የተአምራትና ድርሳንትን ሁሉ 5) እንዲሁም የቅዳሴ መጸህፍትን ሁሉ ከእዉነተኛ አምልኮ አንጸር መገምገም ቢቻል 6) መጸሀፈ መነኮሳትን ሁሉ በቃሉ ሚዛን ጭምቅ እያደረጋችሁ ብታቀርቡት ደስ ባለኝ ፡፡፡ ተባረኩ!!!!!!!! በተረፈ አባሰላማ ብሎግን ብዙ ሰዎች ይጎበኟታል በርቱ በጌታ ወንድማችሁ

  ReplyDelete
 5. I appreciate your work against those tares like Mahibere Kidusan. But I don't like your way of addressing issues on some church teaching as most of your ideas are against the teachings of the the orthodox world... Take the teachings of Eastern and Oriental orthodox, if you oppose these teachings it means you are closer to the protestant teachings. Please correct your approaches and keep on teaching the ferisawian mahibere and creating awareness for Ethiopians. We can see they are making a network of church servants and followers who are pro mahibere kidusan... and use all means to let down all others who are not standing and working with them... keep on lettings us know what they are doing on potential servants and followers of the church...

  ReplyDelete
  Replies
  1. God bless your Sir! I concur with your remark, especially about following in the footsteps of the Eastern & Oriental churches. I've realized we're such a conceited church and it's so refreshing to see such kind of comment. We have so many unbiblical & "unapostolic" teachings, if it were to be translated into English, I think without a doubt we'd be categorized as heretical.

   Delete
 6. አባ ሰላማዎች ፣ የኢትዮጵያን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፕሮቴስታንት ለማድረግ ያለ እረፍት እየሰራችሁ እንደሆነ እየነገራችሁን ነው፣ እኔ የምለው ከ400 አመት ጀምረው ፕሮቴስታንት የሆኑት ምዕራባውያን ለምንድነው ሞራላቸው የዘቀጠ? የፕሮቴስታንቲዝም መስራች የሆኑት አውሮፓውያን ችርቾቻቸውን ለምንድነው ለጭፈራ ቤት ፣ ለመስጊድ፣ ለገበያ ማእከል business center እየሸጡ ያሉት? የፕሮቴስታቲዝም ግቡ ይህ አለማዊነት ነው ማለት ነው? አሁን እናንተ እንደምትሉት አውሮፓውያን ከጥንት የመጣውን ትውፊት ሁሉ አሽቀንጥረው ጥለው፣ ለምንድነው ራቁታቸውን የቀሩት? በምእራቡ አለም ፕሮቴስታንቲዝም ለምንድነው ምግባረ ብልሹ፣ ፍጹም አለማዊ፣ ግብረ ሰዶማዊ፣ አምላክ የለሽ ትውልድ ያፈራው? መቼም ይህ እውነታ እናንተ ይጠፋችኋል አይባልም፣ የናንተ አላማ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጅ በሙሉ እግዚአብሔርን እንዲክድ ነው አይደል ይህ ሁሉ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ? የገሀነም ደጆች አይችሏትም። እምነታችሁ እጅግ ከመዝቀጡ የተነሳ እኮ ነው ፓስተሮቻችሁ ችርች ውስጥ ዝሙት የሚፈፅሙት!!! ፕሮቴስታንት የሰይጣን ቀኝ እጅ ነው፣ የቅዱሳን አምላክ ተዋህዶን ይጠብቅልን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የዘረዘርካቸው የምዕራባውያን ፕሮቴስታንት አብያተ ክርስትያናት ችግሮች የተከሰቱት ምዕራባውያን ከእግዚአብሔር ቃልና ከወንጌል ፈቀቅ በማለታቸው ነው:: ለነርሱም የ ሚያስፈልጋቸው ወደቀደመው በክርስቶስ ላይ የተመሠረተው እምነት መመለስ: ባጭሩ ተሃድሶ ነው::

   Delete
 7. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!!
  መቼም ጥሩ ስምንና ዝናን የማይመኝ ሰው የለም። ምኞት አይከለከልም። ብላችሁ ብላችሁ ሳራን(ጨዋይቱን) እና የጨዋይቱን ልጅ ይስሀቅን ለመምሰል ፈለጋችሁ? እንዴት ሊሆን ይችላል? ሊሆንላችሁ ስላልቻለና ልክ እንደ እስማኤል ተዋጊና ተቀናቃኝ ስለሆናችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ እምነታችንንና አገልጋዮቿን ከተለያዩ የፖለቲካ፣ የሀይማኖትና ስውር የመክበርና የመበልጸግ ፍላጎት ካላቸው ግለሰቦች ተውጣጥታችሁ ስማችሁን ተሃድሶ ብላቸሁ ሰይማችሁ በግብር አባታችሁ በሉሲፈር የተሾማችሁና እግዚአብሄርን በመደፋፈርና አይምሮን በማጣትና ባለማመዛዘን የምትንቀሳቀሱ ደፋሮች ልክ እንደ የባቢሎንን ግንብ እንደገነቡትና (እገዚአብሄር ይቅር ይበለኝ) ድንጋይ ወደ ሰማይ እየወረወሩ አብን መታነው.......... እያሉ ዲያቢሎስ አባታቸው ባሳያቸው ምትሃታዊ ደም ፈነከትነው እያሉ እንደተዘባበቱት ባቢሎናውያን እናንተም ክርስቶስ ኢየሱስ በቃተተባትና በደሙ በመሰረታት ቅድስት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን ላይ ወረርናት ብላችሁ ልትዘባበቱ ትወዳላችሁ??? እንዴት ሊሆንላችሁ ይችላል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አኮ ናት ማን መሰለቻችሁ በጭራሽ አተደርሱባትም እኮ ስራዋና ሃሳቧ ሁሉ ስርዓቷን ከሚሠራላት ከመንፈስቅዱስ ጋር ናት የመንፈስ ቅዱስን ስራ እናንተ ልታድሱ እንዴት ተደፋፈራችሁ??? ገንዘብ ማካበትና ዝናን ማትረፍ እንዲሁም ውስኪ መጨለጥና ከሴት ጋር መዳራት ወይም አለሙንና ብልጭልጭ ቁሳቁሱን በመረጡ ጥቂት እፍረተቢስ አገልጋዮች ነን ባዮች እድሉ ተሠጥቷችሁ ወደ ውስጥ ብትገቡም አምላክ አኮ እስኪ ድፍረታችሁ የት እንደሚደርስ ልየው ብሎ ነው ዝም ያላችሁ። ድፍረታችሁማ እገዳማት ድረስ ገብታችሁ ንብረቶቹን በመንካት እሄው ነካነው ምን ታመጣለህ ማለት ይመስላል። እግዚአብሄር አኮ ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሄር ነው። ተደፋፋሪዎች ውሃ ወስዷቸዋል የሉም የሉም የሉም በቃ!!! እግዚአብሔር ሃያል ነው!!!!!!!!!!! አይገባችሁም?????
  ማህበረ ቅዱሳን ብለችሁ የምትነዘንዙት ማህበር እኮ የቅዱሳን ነው። ቅዱሳን ማለት ደግሞ ከቅዱሱ ከመድሀኒተአለም ከሠላሙ መሪ ከሠላሙ ዳኛ የሆኑ ቀዱስ ነገርን የሚሰሩ ለተቀደሰ ተግባር ዘርና ቀለም ሳይለይ የመረጣቸው ናቸው። ጭራሽ ሸዋና ጎጃም ጎንደር እያላችሁ በዘር በመከፋፈል ትናረታላችሁ??? ምን ጉደኞች ናችሁ??? አባ ሰላማን ከተለያዩ አህጉራት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ቅዱሳንን ተመልከቷቸው። ታሪክና ቅዱሳንና ቅዱሳትን አትቀበሉም እንጂ፣ ምነው ተቁነጠነጣችሁ ምን ጎደለባችሁ ከዓለም የሆነው መኪና ቪላ፣ ፎቅ አፓታማ ሌላውም ሁሉ ውሰዱ አባቶቻችንን ግን አላሰራ ብላችሁ በማስፈራራት ከሥራ በማባርር አታውኳቸው። ይቀጥላል............

  ReplyDelete
 8. ተሐድሶ=የተውሶ
  1. ተሐድሶ ማለት እልል የተባለለት ፕሮቴስታንት ማለት ነው፡፡ማኅበረቅደሳን ግን በቤተክርስቲያን ሕግና ጥላ ስር ያለ ማኅበር ነው፡፡ልጅና እንግዴ ልጅ፣ጭቃና ጨረቃ የት ይገናኝና፡፡ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል፡፡ሲነገራችሁ ስሙ እንጅ፡፡የሌባ ዐይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ፡፡ተሐድሶ ሲወገዝ ነው የምናውቀው፡፡ገና ይወገዛል፡፡ምክንያቱም ፕሮቴስታንትና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በሥም ብቻ ሳይሖን በአስተምህሮም ይለያያሉ፡፡ፕሮቴስታንት ጥንተ - ልደቱ ከካቶሊክ ነው፡፡ከዛ ወዲህ ያለው ልደቱ ደግሞ ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ይዋለዳል፡፡ሁሉም እንዳሻው በኢየሱስ ስም እየማለ ያድሰዋል፡፡ስንት ኢየሱስ እንዳለ እሱ ይወቅ፡፡ያለ ውል አትጩሑብን፡፡
  2. አዳሜ ረስሽ ጮኸሽ ራስሽ እልል ትያለሽ፡፡የበላይ ሆንን የምትሉት የትኛውን ግብና ዐላማ አሳክታችሁ ነው??መወገዝ ከሆነ አላማችሁ እሱ ተሳክቶላችኋል፡፡በአሁን ሰዓት ወሬዎችን በተናጠል ከመቃረምና አሉባልታ ከመናገር ውጭ በሴል ደረጃ ስጋት የመሆን እድላችሁ መንምኗል፡፡ተሐድሶን ስለማጥፋት እንጅ ስለማምጣት ማሰብ ከፕሮቴስታንት እንደመዋሀድ ይቆጠራል፡፡አይደረግም፡፡አልተረደገም፡፡
  3. ብሎግ ላይ ተደብቆ ጥሩንባ መንፋት ግን ይቻላል፡፡ምክንያቱም በኢየሱስ ሥም እስከተነገረ ድረስ ውሸትም ጽድቅ ነው ይላል የእናንተ መዝገበቃላት፡፡ደቅደቅደቅደቅደቅ….ባትሪያችሁ እስኪያልቅ ተንደቅደቁ፡፡ቤተክርስቲያን ግን ተጸጽቶ የሚመለስ ልብ ካላችሁ በሩን ክፍት አድርጋ ለጊዜው በውግዘት መጋዝ ቆርጣ ለይታችኋለች፡፡ጩኹ፡፡ኮምፕሌክሳችሁ እስኪለቃችሁ ጩሁ፡፡በሕልም እንጀራ ጠግባችሁ ዝለሉ፡፡ዘልዘልዘል…ተንዘልዘሉ፡፡ትጮኻላችሁ፡፡ግን አትገቡም፡፡
  4. እውነት ለመናገር ሶፍትዌራችሁ አንድ ቢሆንም ቢያንስ ከላይ-ከላይ ሲታይ በይፋ ፕሮቴስታንት ሆነው በግሩፕ የሚንቀሳቀሱት የተሻለ ሥነምግባር ስላላቸው ከእናንተ እነሱ ይሻላሉ፡፡እናንተ ግን ወይ ከእምነቱ ወይ ከምግባሩ የላችሁ ስድብ ብቻ፡፡በእናንተ የተነሳ ልዩነታችንን ተቀብለው ቤት የለዩ ፕሮቴስታንቶች ይሰደባሉ፡፡አሰዳቢዎች፡፡ደግሞ ማኅበረቅዱሳንና ማኅበረከንቱ አንድ ሊሆን አይችልም፡፡እናንተ ማኅበረከንቱ ናችሁ፡፡ማኅበሩ ከነምግባር ድክመቱ ያለአንዳች የእምነት ህጸጽ እንደሚንቀሳቀስ ለመመስከር እኛ በቤተክርስቲያን ጉያ ያለነው ምስክር ነን፡፡እናንተማ ለምስክርነት አትበቁም፡፡የተወገዘው ስለተወገዘበት ጉዳይና ስላስወገዘው ማኅበር ዳኝነት ሊቀመጥ አይችልም፡፡በፍጹም፡፡ሕጉ አይፈቅድም፡፡
  NO ONE CAN BE A JUDGE IN HIS OWN CASE!!HENCE,YOU CONDEMNED HERETICS ARE NOT QUALIFIED TO ENTERTAIN MATTERS RELATED TO OUR BELOVED EOTC OR MK!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማኅበረቅደሳን ግን በቤተክርስቲያን ሕግና ጥላ ስር ያለ ማኅበር ነው፡፡ ነዉ ያልከዉ? በአገር የለህም ማለት ነዉ፡፡ ቢያንስ የጥቅምቱን የሲኖዶስ ጉባዬ አጀንዳዎች አላወቅህም፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያኒቱን በቅኝ ገዥነት ለመያዝ በመጣር ላይ ያለ፤ የቤተ ክርስቲያኒቷን አባቶች በመዝለፍ አቻ የሌለዉ የጋጠወጦች ስብስብ ነዉ፡፡ አስራት እና በኩራት በራሱ አካዉንት እየሰበሰበ ካፒታሉን የሚያሳድግ፣ ገቢዉና ወጭዉ የማይታወቅ፣ በህግ የማይመራ፣ እምነትን ከፖለቲካ እያጣረሰ እዚህና እዚያ የሚረግጥ፣ በልዩነትና በመቻቻል የማያምን ነዉረኛ ማህበር ነዉ፡፡ ልታታልለን አትሞክር፡፡ አስመሳይ፡፡

   Delete
  2. ውድ AnonymousJanuary 27, 2015 at 9:55 PMማኅበረቅዱሳንን በሚመለከት ያነሳሀቸው ነጥቦች የምግባር ችግሮች ናቸው፡፡የአካሄድ ነው፡፡ስለዚህ በሂደት ይስተካከላል፡፡እንታገሰዋለን፡፡የተሐድሶዎች ግን የእምነት ችግር ነው፡፡የዕምነት መጻጉዕ ናቸው ተሐድሶዎች፡፡የእምነት መጻጉዕ ማስታመም አንችልም፡ተመክሮ ተዘክሮ ያልተመለሰውን መለየት ግድ ነው፡፡እየተደረገ ያለውም እሱ ነው፡፡ተሐድሶን እንደማኅበረቅዱሳን ለዚህኛው ወር ሲኖዶስ ለዚያኛው ወር ሲኖዶስ እያልን የማንቀጥረውም ለዚህ ነው፡፡ሲኖዶሱ ስለማኅበሩ አጀንዳ ይዞ የሚመክረውም በእኔ ጥላ ስር ነው ብሎ መሰለኝ፡፡ፓትርያርኩም ቢሆኑ ሕግ ይውጣለት አሉ እንጅ እንደ ተሐድሶ ተወግዞ ይለይ አላሉም፡፡ምክንያቱም ልድገመውና ማኅበረቅዱሳን ከነምግባር ድክመቱ የቤተክርስቲያኗ አካል ነው፡፡፡

   Delete
 9. Orthodox will stay as it is before. Your dream can not be come true.

  ReplyDelete
 10. I am not from Mahibere Kidusan...I was simply following my Orthodox religion from a distance... But now i decided to become member of MK and to be beside them...COS I CARE ABOUT MY RELIGION.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Don't worry, you have joined your fellow brethren. A group for the ignorant & rebellious. They welcome illiterate like yourself because you are easy to manipulate. You follow like a sheep so you're an easy prey. Stay true to your "distance running"!

   Delete
  2. As far as I know ignorant is one who changes his Religion as Clothes now and then....easy going.....directed elsewhere....
   LONG LIVE TEWAHIDO and DOWNFALL TO TEHADISO.

   Delete
 11. Great and blessed statement guys. Be patient everything will happen on the time, according God will. We all have to trust in Lord Good. Excellent job our writer,

  ReplyDelete
 12. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
  እኔ የኦረቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ እስከሆንኩኝ ድረስ ክርስቶስ የተቀባ ንጉስ የሚል አስተምህሮ በፍጹም አልቀበልም። ይህንን ያገኘሁት በቅዱስ እስጢኖስና በየረር ስላሴ ቤተክርስቲያናት እየተዘዋወሩ ከሚያጥምቁ መምህር ተምረናል ድነናል ከሚሉ መስካሪዎች ከድህረገጽ ላይ አንብቤ ነው። ይህ ትምህርት እንዴት ያለ ትምህርት ነው? ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እንዴት ተዋጠላቸው? ለመሆኑ ወጣቱ ትውልድ መምህራቸው ማን እንደሆነ አውቀው ነው ወይ የሚማሩት? ከባድ ምንፍቅና አይደልም ወይ? እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን። ኦረቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖታችንን ይጠብቅልን ሀገራችንን ይባርክልን አሜን!!!!!!!

  ReplyDelete
 13. Wanna share and post Ethiopian Orthodox Tewahido Church Holy Icons?
  follow us and like our Facebook group,be a member to upload Ethiopic Icons only!
  https://www.facebook.com/groups/ethiopiantewahidoicons/

  ReplyDelete
 14. ምን አለበት አባ ሰላማዎች ውድ ጊዜ አችሁን ባትቀልዱበት ይልቅሰ እንደ ወንድማችን ዳንኤል ክብረት ለሀገር እና ለእምነት የሚጠቅም ሰራ ብትሰሩ መልካም ነበር ለማንኛውም ፈጣሪ ልቦና ይሰጣቹ

  ReplyDelete
 15. ተሳስተህ የምታሳስተው እንዳንተ አይነቱን ወዴት መሆን ያቃተውንና ወላዋዩን ነው፡፡የተከበረ የተዋህዶ እውነተኛ የቁርጥ ቀን ልጅ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እንካን አንተን የማያቅህን ፊት ለፊቱ የተናገሩትን እንካን መልስ የማይሰጥ ወንድም ነው ፡፡ይሄን የጻፍኩልህ አንተ የምታሳስታቸው መነጆዎች እንዲሰሙ እንጂ አሱ ከዚህም በላይ ተበሎአል፡፡ ከላሰ ቬጋስ

  ReplyDelete
 16. The writer of this blasphemy is anti-orthodox tewahido, jackal with in sheeps and his life is completely in hallucination. This EOTC will never be the play ground of your dirty dream, if you leave eotc this means you have no knowledge of the history of your country; about art; about music, about philosophy; about medicine...and so on. Your dream brings nothing but morally collapsed protestantism. And go to your amphitheatre-hall and say, tararara...tamtaram tamtaram...turreeee...pipipipi.......levendo toronto toto...waywayway..... Nothing more than this. Mengedun cherq yargileh.

  ReplyDelete
 17. ዜና
  የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በእንግሊዝኛ ፕሮግራም ላይ እንደገለጸዉ የኢትዮጲያ ኦረቶዶክስ ቤተክርሰትያን ባለፈዉ በሙስሊም አክራሪዎች በተሰዉት ሰዎች ምክንያት የሟቾችን ቤተሰብ ለማጽናናት ከ100 በላይ ልኡካን ጳጳሳትን ወደግብጽ በመላክ የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን ገለጸች ፡፡

  ReplyDelete
 18. አይ ተሀድሶ ተኩላ ከመቼ ጀምሮ ነው ደግሞ ቤተክርስቲያንን ሊያድስ የቻለው??????????????????????? እኛ የሰማነው በኋለኛው ዘመን ተኩላው የሰውን ነፍስ እንደሚባላ እንጂ ቤተክርስቲያንን እንደሚያድስ እስከአሁን የሰማነውና ያነበብነው ወንጌል ውስጥ አላገኘንም፡፡ ወዳጄ፣ እባክህ ለሆድህ በከንቱ አትድከም፤ ሆድህን እርሱ የፈጠረህ የሞላዋል፡፡ ሆድህን ለመሙላት የስድብና የነቀፋ፣ የፈጠራ ወሬ እያወራህ ነፍስህን አታሰቃያት፡፡ ወንጌል መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሀ ግባ እያለች ትሞግትሀለች፤ እርሷን ንባብ አትዘለላት ወንድሜ ትልቅ መልእክት ነው፡፡ በኋላ የምትፈርድብህ እርሷ ንባብ ናትና ጊዜህንና እድሜህን፣ በውሸትና በፈጠራ፣ በሀሜት አትጨርስ፤ ይህች ዘመንና እድሜ አትመለስም፡፡ እኔ የሚገርመኝ ሁልጊዜ ሰይጣን የቀደመ ለምን ይመስለዋል? የእርሱ ሀሳብ ሁልጊዜ የመቅደም ሀሳብ ነው፡፡ እርሱ የሚቀድመው እንደሌለ እንኳን መገንዘብ ያሚያቅተው ለምን ይሁን፡፡ ሰይጣን ሆይ ለምን ካሳለፍከው ዘመን አትማርም፡፡ መቼም በእኛ አቆጣጠር እንኳን ከ8ዐዐዐ ዓመት በላይ ልምድ ነበረህ፡፡ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን አሸንፈኸው እንደማታውቅ ከነበርክበት ስልጣን ወደ ሲኦል ሲወረውርህ ታውቀዋለህ? ለምን እግዚአብሔርን ትሞግተዋለህ?

  ReplyDelete