Monday, January 5, 2015

አቡነ ቀለሜንጦስ በውጥረት ላይ ናቸውበቅርቡ የቅዱስ ፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በመሆን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አባ ቀለሜንጦስ ብልሹ አሠራርንና ዘረኝነትን ያስወግዳሉ ተብለው በቅዱስ ፓትርያርኩ አቅራቢነት ከቅዱስ ሲኖዶስ ኃላፊነት ቢሰጣቸውም አስተዳደራቸው ግን ገና ከጅምሩ ከዚህ በፊቱ ባልተናነሰ ዘረኝነት ውስጥ የተዘፈቀ እየሆነ ነው የሚል ትችት እየተሰነዘረባቸው ይገኛል።
ይህንን የሚሉ ሰዎች ለማስረጃነት ከሚያቀርቡት አንዱ የሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ዋና ጸሀፊ ለነበረው ዲያቆን ሩፋኤል የማነብርሃን ያደረጉት ነገር ነው። ይህ ግለሰብ በዘረፋ እና ንዋየ ቅድሳትን በማተራመስ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሲሆን ተነቃብኝ ብሎ የቤት እቃውን ሸጦ ወደ አሜሪካ ሊሄድ ሲል የካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ አድርገው በመሾማቸው ጉዞውን ሰርዞ ተደላድሎ ተቀምጧል።
አመጸኛውና መዝባሪው ዳቆን ሩፋኤል በሄደበት ቦታ ሁሉ ከህዝበ ክርስቲያኑ እና ከማህበረ ካህናቱ ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት የሚኖር ሰው ነው። የሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ካህናትና ምዕመናንም የቅዱስ ፓትርያርኩንና የሀግገረ ስብከቱን ቢሮ በተቃውሞ እያጨናነቁት ሳለ ዲያቆኑ ግን መልካም እንደሰራ ተደርጎ ለአስተዳዳሪነት መሾሙ አባ ቀለምንጦስን ዘረኛ የሚለውን ስም ሊያሰጣቸው ችሏል።
ከዚህም ጋራ ተያይዞ የሥጋ ዘመዳቸውን ሳሕለ ማርያምን የሀገረ ስብከቱ ዋና አስተዳዳሪ አድርገው በመሾማቸው የጳጳስ ወገንተኛ ናቸው እየተባለ ስማቸው እየተነሳ ይገኛል። ትችቱንም የሚያቀርቡት በአብ ዛኛው የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ልዩ ልዩ ሠራተኞች ናቸው።

በሌላ በኩል የሀገረ ስብከቱ የመምሪያ ኃላፊዎችና የክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጆች እስከ ዛሬ የነበረንን የሥራ ኃላፊነትና ሥልጣን በአባ ቀለሚንጦስ ተቀማን በማለት ለቅዱስ ፓትርያርኩ አቤቱታ እያቀረቡ ነው።
አቡነ ቀለምንጦስ የምስራቅ ሓረርጌ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት ከካህናቱ ከህዝበ ክርስቲያኑ ጋር በከፍተኛ ሁኔታ በመጣላታቸው በሌሊት ጠፍተው አዲስ አበባ በመምጣት እዚሁ ቀርተዋል። በወቅቱ የነበሩ ሰዎች የጸቡን መንስኤ የጎጃምን ሰው አምርረው መጥላታቸው ነበር ሲሉ ይገልጻሉ።
አሁን በሚኖሩበት የሆሳእና ከተማም አንድ ቄስ ከቀጠሩ በኃላ የጎጃም ሰው መሆኑን ሲያውቁ አምርረው እንደጠሉት በቦታው ያሉ ሰዎች እና ቄሱም እየተናገሩ ይገኛሉ።  
በአንድ ወቅት የማኅበረ ቅዱሳኑ ብሎግ ሀራ ብአዴኑ ጳጳስ ሲል የጻፈባቸው ዕና እሳቸውም በግልጥ ለማቅ ያላቸውን እበገሬነት የሚናገሩት አቡነ ቀለምንጦስ የማቅ አባላትን ሰብስበው በመጥራት እብረን እንስራ የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው እየተነገረ ይገኛል። በስውርም ከማህበሩ ጋር እየሰሩ ነው እየተባለ ይገኛል። የማኅበሩን አባላት በኮሚቴ በኮሚቴ አደራጅተው በየአብያተ ክርስቲያኑ ለማስገባት ጥረት እያደረጉ ነው እየተባለ ነው።
እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን እየተበራከተ የሚገኘውን ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ያስተካክላሉ ተብለው የነበሩት አቡነ ቀሌምንጦስ ለዚህ የሚረዳቸውን ፍትሐዊ የሆነ አስተዳደር መዘርጋት ሲገባ አሁነ ቀለምንጦስ ግን አቡነ እስጢፋ እንዳደረጉት ማቅንና የማቅን ዓላማ ደግፈው ከብዙ የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ጋር እየተጋጩ ይገኛሉ። አንዲያውም በቀን 25 04 07 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሰባኪዎችን ሰብስበው የደብር አስተዳዳሪዎችና ጸሀፊዎችን ሲተቹና ሲያስተቹ ውለዋል። በዚህ ምክንያትም በቤተክርስቲያን አለቆች ዘንድ ከፍ ያለ ቅሬታን አሳድረዋል፡፡
የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልና የጎላ ሚካኤልን አስተዳዳሪዎችን ጡረታ ለማውጣት እየተንቀሳቀሱ ይገኛል። ይሀንን የሚያደርጉት በእነርሱ ቦታ የአካባቢያቸውን ሰዎች ለመሾም እንደሆነ እየተነገረ ነው። ሰው አይውጣብህ ተብሎ የተረገመ የሚመስለው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አሁንም መልካም አስተዳደርና ከዘረኝነት የጸዳ አሰራር እንደ ሰማይ ርቆታል። ብጹዕነታቸው ሥራ ከጀመሩ በኋላ ብዙ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ከሥራ ተፈናቅለው የነበሩ አገልጋዮች ጉዳይ ምንም መፍትሔ ሳያገኝ ቀርቷል። ከሥራ ተፈናቅለው እየተንከራተቱ የነበሩ አገልጋዮች አሁንም እየተንከራተቱ ናቸው። አቡኑም መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ግራ ተጋብተው ይገኛሉ።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስም ይሆነኝ መስሏቸው የሚያስቀምጧቸው ሰዎች ሁሉ እስካሁን ለችግሮች ተገቢውን መፍትሔ ሲሰጡ አልታዩም። ቅዱስነታቸውም በዚህስ ነገሮች እንዳሰቡት አልሆነላቸውም። በዚህሳ እድለኛ አይደሉም።
ከሁሉ የከፋው የዚህ የዘረኝነቱ ጉዳይ አንጀት አቁስል ልብ አብስል ሆኖብን ይገኛል። ሰው ጌታዬ አምላኬ የሚለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነጻ ካወጣው ዘረኝነት ውስጥ ተመልሶ እንዴት ይዘፈቃል? ሀፍረት አይደለም ወይ? ውድቀት አይደለም ወይ? ታጥቦ ጭቃ አለቅልቆም እንደ ልጅ ጨምላቃ መሆን ነው። ቅዱሳን አባቶች እባካችሁ በጀ ብትሉ እንምከራችሁ። ሁነኛ ልብ ካላችሁ ስሙን። ከዘረኝነት ነጻ ውጡ። ጌታችን ወንዝ የሚያሻግር እምነት ነው የሰጠን። የክርስቶስ ለሆኑት እንድናደላ ነው እንጂ ለቀዬ ሰው እንድናደላ አልተጠራነምን። እባካችሁ ልብ ግዙ። ከድንግዝግዝ ነጻ ውጡ። ጌታ ይታረቃችሁ። ሰላሙንና ምህረቱን ያብዛላችሁ። 
ሌሎች መረጃዎችን በቀጣይ እልካለሁ
                                         መሪጌታ ቀጸላ ዘጎንደር

9 comments:

 1. መ/ቀፀላ ዘጎጃም ቢል በቀና ነበር። ምክንያቱም የዚህኛው ፅሁፍ አላማ ሊቀ ጳጳሱን በጎጃም ተወላጆች ዘንድ የማስጠላት ዘመቻ ይመስላል። የሚሰማችሁ ባይኖርም።
  ጀመራችሁ እንግዲህ! አገልጋዮችን እርስ በርስ የማባላት የነፍሰ ገዳይ ስራችሁን

  ReplyDelete
 2. ይቺ ወሬ ጎንደርና ሸዋን ለማዋጋት የተጠነሰሰች ናት፣ እሺ እኛ ኦሮሞዎች ከማን ወገን እንሁንላችሁ?????

  ReplyDelete
 3. " አቡነ ቀለምንጦስ የማቅ አባላትን ሰብስበው በመጥራት እብረን እንስራ የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው እየተነገረ ይገኛል። በስውርም ከማህበሩ ጋር እየሰሩ ነው እየተባለ ይገኛል። የማኅበሩን አባላት በኮሚቴ በኮሚቴ አደራጅተው በየአብያተ ክርስቲያኑ ለማስገባት ጥረት እያደረጉ "
  This is the main problem you have .LET US WORK TOGETHER ..??????It is hard for you .Egziabher amlak ayene lebonachehun yekfetlachehu.

  ReplyDelete
 4. What is the problem working together? You guys have a big problem. You think everybody is dummy. Oh Lord have mercy.

  ReplyDelete
 5. You are protestant in belief! You should rather talk about " Pastors " and "Prophets ( Magicians)" that are stealing money and make possessed by evil spirit their naive followers!
  Your motive is one and one to stir riot and steal the sheep during confusion.
  Although our holy Father is not free from making errors, this shall be rectified through peaceful discussion!

  Haile Gabrielb Ze Gojjame

  ReplyDelete
 6. ይድረስ ለሉተር ቡችሎች
  በአባ ሰለማ website January 5, 2015 አቡነ ቀለሜንጦስ በውጥረት ላይ ናቸው ብላችሁ ስለጻፋችሁት የውሸት ዝርዘር እውነት ስለሆነው ነገር ትንሽ ልበል ብዬ ነው፡፡ አናንተ የቆማችሁት ለሐሰት አባት ለዳቢሎስ እንደሆነ ቢታወቅም የቆምነው ለእውነት ነው ትላላችሁ፡፡እውነት ከሆነ አዲስ አበባ ላይ ሆነህ ሐረር ላይ በሬው ወለደ ወሬህ በጣም ስለገረመኝ ነው፡፡ መቸም የሐረር ሰንጋ እየተባለ በአግራሞት ቢወራለትም ጮማ እና ብርንዶ ቢዘለዘልም ጥጃ ወለደ ተብሎ ግን አይታወቅም፡፡ ማለትም ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ አንተ እንዳልከው የማታውቀውን እንድቀባጠርከው ሳይሆን በደብረ ሊባኖስ ገዳም በደብረ ጽጌ እና በደብረ ሊባኖስ ገዳም በደብረ ብርሃን ቅ/ሥላሴ እና በሐረርም ቢሆን ጎጃሜውን; ጎንዴሬውን፤ ወሎየውን፤ ትግሬውን በአጠቃካይ ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው እንደ አባትነታቸው የሚጠበቅባቸውን ሲያድረጉ፤ ሲድሩ ሲኩሉ ለወግ ለማእረግ ሲያበቁ ዕድገት ሲሰጡ ኖሩ እንጅ አሉባልታህን እንደ ደሰኮርከው አይደለም ምክንያቱም የእሳቸው አገራቸው በሰማይ እንጅ አንተ በስጋዊ አይንህ እንደከፋፈልከው አይደልምና ነው፡፡ እኔ የምለው ለምትናገሩት ነገር ቢያንስ ትንሽ እንኳን የእውነት እንጥፍጣፊ ቢኖረው ጥሩ ነበር፡፡ ጌታ በወንጌሉ በስሜ ይመጣሉ ብሎ የለ እናንተ የምትናገሩት ፍፁም ውሸት ሁኖ ሳለ የጻድቁን ስም የብሎጋችሁ ስም አደረጋችሁት ከላይ ያለውን የኋላውን ፍርድ ያየ ሰው፡፡
  ሌላው ከሐረር ተደብቀው ወጡ ያልከው ነው ከሕዳር 5-7/2003 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፤ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣጢዎስ፤ ብፁዕ አቡነ ያሬድ እና ብፁዕ አቡነ ቀዎስጦስ በአደባባይ (በመካነ ቅ/ሥላሴ ካቴደራል) የሺኝት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶላቸው የከተማው ልዩ ልዩ ማኅበራትና ሀገረ ሰብከቱ ሸልመው በእንባና በለቅሶ በቅኔና በዝማሬ በክብር የተሸኙትን አባት አይናችሁን በጨው አጥባችሁ አይናችሁ ባላየው ጀሮአችሁ ባልሰማው የበሬው ወለደ ውሸት ይገርማል ሂዱና የሐረርን ህዝብ ጠይቁ እውነታውን ይነግራችኋል በእርግጥ እናንተ እውነቱ ጠፍቷችሁ አይደልም ቤተክርስቲያያቱን አተራምሳችሁ የምንፍቅና መርዛችሁን በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ልትረጩ እንጅ፡፡ ለነገሩ እንድህ ተበሎ ተጽፏል እናንተ ከአባታችሁ ከሰይጣን ናችሁ፡፡ምን ዋጋ አለው ለእራሱ ለባለቤቱ፤ ለወለደችው ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም፤ለቅዱሳን መላይክት፤ በአጠቃላይ ለቅዱሳን ክብር ያልሰጣችሁ ለማን ክብር ትሰጣላችሁ ተብሎ ይታሰባል፡፡
  በነገራችን ላይ ያልተነቃባችሁ መስሏችኋል ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን አስከ ሀገረ ስብከቱ አልፎም እሰከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ድረስ የዘረጋችሁት የሙሰኝነት ሰንሰልት እንዳይበጠስባችሁ እንደሆነ ሕዝቡም አውቆባችኋል፡፡ ምእመኑም ቤተክርስቲያኑን ከእናነተ (ቀሳጭ) ለመጠበቅ ስለነቃባችሁ ነው የቆጥ የባጡን የምተቀባጥሩት፡፡

  (We do not expect honey from the fly)

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይድረስ ለሉተር ቡችሎች

   Delete
 7. Be Ethiopia betekrstian ende kelemntos Yale zeregna tayto aytawekim. Aynachihun chefinuna lamognachu eyalken new? Yebefitun bintewew ahun min eyeseru endehone tsehayun bedenb eyemoknew new. Chifin zeregnoch lib endiyagegnu entsely Kenji kelemintis yetaweru zeregninetachewin ende lot mist yechew amid eskihonu endamaytewut yetaweke new.

  ReplyDelete