Saturday, February 28, 2015

ቤተ ክርስቲያን በአደጋ ክበብ ውስጥ (ክፍል ሁለት)                      Read in PDF            

                                                     ከዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ
በክፍል አንድ ላይ ቤተክርሰቲያን እንዴት ወደ አደጋ ክበቡ እንደገባች የሚጠቁም ጽሁፍ አቅርቤ ነበር፡፡ እናት ቤተክርሰቲያን ትታደስ ብለን የተነሳን ሰዎች የቤተክርስቲያኒቱ ችግሮችን መጠቆማችን እንግዳ ነገር ሊሆን አይችልም፡፡ አይገባምም፡፡ በጽሁፉ ላይ የተሰጡትን የተለያዩ አስተያየቶች ለመመልከት ችያለሁ፡፡ አንዳንዶቹ ምክንያታቻውና መነሻ ሀሳባቸው የማይታወቅ ስድቦች ብቻ ናቸው፡፡ የተጻፈውን ጽሁፍ በሰለጠነ መንገድ በምክንያት ከመሞገት ይልቅ በመንደር ቋንቋ እንዲህና እንዲያ ተብያለሁ፡፡ የሆነው ሆኖ ግን ቤተክርስቲያን በአደጋ ክበብ ውስጥ የሆነችበትን ሀሳብ ሳስቀምጥ ዋነኛ ምክንያት አድርጌ ያነሳሁት እግዚአብሔርን ብቻ አለማምለካችን የሚለውን ሀሳብ ነው፡፡ አሁንም እሱን ማብራራት እቀጥላሁ፡፡ አሁንም አስተያየታችሁን በሰለጠነ መንገድ በምክንያት እንድትገልጡልኝ በፍቅር አሳስባለሁ፡፡ መልካም ንባብ  
1.1.       ጥንቈላ
   የእግዚአብሔርን እውነተኛ አስተማሪነት (ኢሳ.30፥20) አለመቀበል  ፤ በትምህርቱም አለመጽናት የሐሰት መመህራን ትምህርት ሾልኮ ለመግባት ሠፊ በር ይከፍታል፡፡ (2ጴጥ.2፥1) በቤተ ክርስቲያናችን እንደቤተ ክርስቲያናችን የመጻህፍት ጽህፈት ቀኖና መሠረት በቀለማት አጊጦ ከሚባዙትና ከቤተ ክርስቲያኒቱ መጻህፍት ጋር ታትሞ እኩል በየመጻህፍት መደብሩ ከሚሸጡት መጻህፍት መካከል አንዱ አውደ ነገሥት የሚባለው የጥንቈላ መጽሐፍ ነው፡፡ መሥተፋቅር ፣ አስማት የሚደግሙ ፣ ሞራ ገላጮች ፣ መናፍስት ጠሪ ፣ ሙታን ሳቢዎች … እና ሌሎችም የጥንቈላ ሥራዎች ሁሉም ለማለት ሊያስደፍር በሚችል መልኩ የሚከናወነው ከደብተራ እስከካህናት ባሉት የቤተ ክርስቲያኑቱ አገልጋዮች ነው፡፡
   ጥንቈላ የሥጋ ሥራና (ገላ.5፥20) ከእግዚአብሔር ሃሳብና ፈቃድ ውጪ መንፈሳዊ ኃይልና መገለጥን የሚፈለግበት መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሔር ጠንቋይንም አስጠንቋይንም አብዝቶ ይቃወማል፡፡ እስራኤል በጠንቋዮች መንገድ እንዳይሄዱ አስጠንቅቋቸዋል ፤ እንዲያጠፏቸውም ነግሯቸዋል፡፡ (ዘጸ.22፥18 ፤ ዘሌ.20፥27) ሐዋርያት የክርስቶስን ወንጌል ለብዙዎች ከመሠከሩ በኋላ ከጥንቈላና አስማተኝነት የተመለሱትን አማኞች ይገለገሉበት የነበረውንም ዕቃ እንዲያቃጥሉ አድርገዋል፡፡ ለጥንቆላ ሥራ አገልግሎት ይሰጠው የነበረው ማናቸውም ነገር ሲቃጠልና ሲወድም ተቀይሮ ለመንፈሳዊ ሥራ ሲውል አልታየም፡፡ (ሐዋ.19፥19)

Friday, February 27, 2015

ይቅርታ መጠየቅ ታላቅነት፣ ይቅር ባይነት ደግሞ ጀግንነት ነው!


Read PDF 
(ከሰደንቅ ጋዜጣ ላይ የተወሰደ)
በዲ/ን ተረፈ ወርቁ
በመንግሥት ታግዳ ከኅትመት ውጪ የሆነችው ‹‹የአዲስ ጉዳይ መጽሔት›› ዓምደኛ የሆኑት አቶ ሰለሞን ተሰማ ባለፈው ሳምንት በዚሁ በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ባስነበቡን ጽሑፍ የዚሁ ጋዜጣ ም/ዋና  አዘጋጅ አቶ ፋኑኤል ክንፉን፣ አቶ ዳንኤል ብርሃነንና የአዲስ ጉዳይ መጽሔት አንባቢዎችንና ወዳጆችን በይፋ/በአደባባይ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ አቶ ሰለሞን ባልተረጋገጠ ወሬ በሐሜት የጎዷቸውን በተለይም አቶ ፋኑኤልንና አቶ ዳንኤልን ከታላቅ አክብሮት ጋር በይፋ ይቅርታ መጠየቃቸውን አስነብበውናል፡፡
አቶ ሰለሞን ይህን ማድረጋቸውም አንድም ከእምነታቸው አስተምህሮ፣ ከሕሊና ፍርድ፣ ከሞራል ጥያቄና ለወደፊትም ታሪካችንን ከነትሩፋቱና ከነጠባሳው ለሚወርሱት ልጆቻችን ኩራትና ተምሳሌት ለመሆን በማሰብም ጭምር እንደሆነ በትሕትና ገልጸውልናል፡፡ ይህ በእውነትም ይበል የሚያሰኝ ታላቅ፣ የተቀደሰ በጎና ሰው ከሆነ ሰው የሚጠበቅ ሰናይ ምግባር ነው፡፡
አቶ ሰለሞን ተሰማ ባልተጨበጠ መረጃ፣ በሐሰት ወሬና በሐሜት ላይ ተመርኩዘው በመንግሥት በታገደችው በተወዳጇ አዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ፡- ‹‹የአዲስ ዘመን አሮጌ ወሬዎች፣ (ንኩ ጋዜጣ እና ንኩዎቹ ጋዜጠኞች!)›› በሚል ርዕስ ባስነበቡበት ጽሑፋቸው ያስቀየሟቸውን፣ ክብራቸውንና ሰብእናቸውን የጎዷቸውን ሰዎች በይፋ ይቅርታ በመጠየቃቸውም በግሌ ላመሰግናቸው፣ ላከብራቸው እወዳለኹ፡

Tuesday, February 24, 2015

የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ዓዲግራት ሀገረ ስብከት ምእመናን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ላይ ላቀረብነው አቤቱታ ፍትሕ አጣን ይላሉ

Read in PDF 

የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ዓዲግራት ሀገረ ስብከት ምእመናን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ላይ ላቀረብነው አቤቱታ ፍትሕ አጣን ይላሉ
ከጥቂት ሳምንታት በፊት በዚህ ብሎግ ላይ ምንጮችን ጠቅሰንና ሰነዶችን አባሪ አድርገን በትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ዓዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአባ መቃርዮስ እየተፈጸመ ያለውን ሙስናና ብልሹ አሠራር ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በጊዜው ለብሎጋችን ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ሰዎች እንደተመለደው ሐሰት ነው እያሉ ለማስተባበል በመሞከር አስተያየት ሲሰጡ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ የዜናውን እውነተኛነት ግን ዜና ቤተክርስቲያንም ስላረጋገጠልን ያን የተሳሳተ አስተያየት ሲሰጡ የነበሩ ሰዎች አሁን አቋማቸውን ሊለወጡ እንደሚችሉ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ዜናው በዜና ቤተ ክርስቲያን ላይ የወጣው ችግሩ እስካሁን ሰሚ ባለማግኘቱና ባለመቀረፉ፣ እየተባባሰም በመሄዱ በአዲግራት ከተማ የሚገኙ የስድስቱ አድባራት አስተዳዳሪዎች ፊርማና የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ማህተም ያረፈበትን ደብዳቤ ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ በታኅሣሥና ጥር ወር እትሙ አውጥቶታል፡፡ ጋዜጣው “አቤት ባዮቹ በቃልና በጽሑፍ ያቀረቡልን ነገር ግን እኛ ለቤተ ክርስቲያን ክብር ስንል የዘለልናቸው ሌሎች የክስ ነጥቦችም አሉ፡፡” በማለት ከደብዳቤው ውስጥ ሳያትም ያስቀራቸው የክስ ነጥቦች መኖራቸውን ጠቅሷል፡፡
ይሁን እንጂ የቤተ ክርስቲያን ክብር የሚጠበቀው ነውርን በመሸፈን ሳይሆን ወደብርሃን በማምጣትና ንስሐ እንዲገባበት፣ አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃም እንዲወሰድበት በማድረግ ይመስለናል፡፡ እንዲህ ካልሆነ ብዙዎች እንዲህ ካለው ስሕተት አይማሩም፤ እንዲያውም ሕገወጥ ሆኖ መኖር ሕጋዊነት እየመሰላቸው በጥፋታቸው ይገፉበታል፡፡ የሚታየውም እውነታ ይህ ነው፡፡ በእርግጥ ቤተ ክርስቲያኗ ጳጳሳት የቱንም ዓይነት ጥፋት ቢያጠፉ የማይከሰሱባትና ከሕግ በላይ የሆኑባት ስለሆነች ጋዜጣው የክስ ነጥቦቹን ቢያወጣም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በቤተክህነቱ በኩል የሚለወጥ ነገር ይኖራል ማለት አይቻልም፤ ምናልባት በአዘጋጆቹ ላይ ጥቃት ሊሰነዘርባቸው፣ ከእንጀራቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ፡፡ ይህ ሁኔታ ግን እግዚአብሔር በፍርዱ ሲገለጥ አንድ ቀን መለወጡ አይቀርም፡፡ ለሁሉም የጋዜጣውን ጽሑፍ ከዚህ ቀጥሎ አቅርበነዋል፡፡    
የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ዓዲግራት ሀገረ ስብከት ምእመናን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ላቀረብነው አቤቱታ ፍትሕ አጣን ይላሉ
ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለሁለተኛ ጊዜ አጣሪ ኮሚቴ ልኮ ውጤቱ እየተጠበቀ ነው
የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ዓዲግራት ሀገረ ስብከት ምእመናን ተወካዮች ነን ያሉና አለአግባብ ከሥራ ታግደናል ደመወዛችን ተይዞ ብናል ከክህነት ማዕረጋችን ታግደናል ወዘተ የሚሉ ምእመናን ካህናትና ዲያቆናት በተለይ ለዜና ቤተ ክርስቲያን በሰጡት መግለጫ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በምእመናንና በካህናት ላይ እያደረሱት ያለ አስተዳደራዊ በደልና እየተከተሉት ያለ የሙስና አሠራር ተጣርቶ መፍትሔ እንዲሰጠን ከጠየቅን የቆየን ቢሆንም እስከ አሁን መፍትሔና ምላሽ ባለማግኘታችን ጉዳዩ ከአቅማችን በላይ ሆኖብናል በማለት አስረድተውናል፡

Sunday, February 22, 2015

ቤተ ክርስቲያን በአደጋ ክበብ ውስጥ….(ክፍል አንድ)

                                                  ከዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ  
                               
             “ … በቤተ ክርስቲያን መጻህፍት ላይ ሂስ ማድረግ እንደ ክህደት ስለሚቆጠር
               ብዙ አስተያየት አልዳበረም፡፡ ይህ ባህል ቅዱስ መጽሐፍን ተመራመሩ የሚለው
               መሠረተ ሐሳብ ተመራመርና እመን ከሚለው ንድፈ ሐሳብ በተቃራኒ እመን ግን
               አትመራመር ከሚል ንድፈ ሐሳብ ላይ ይመሠረታል፡፡”

      (ዲበኩሉ ዘውዴ(ዶ/ር)፤ ፍትሐ ነገሥት ፡ ብሔረ ህግ ወቀኖና ፤ 1986፤ አዲስ አበባ ገጽ.82)

    በእርግጥ ይህን ሐሳብ ዶ/ር ዲበኩሉ ዘውዴ ያቀረቡት “እንደኢትዮጲያ ልምድ ስለፍትሐ ነገሥት ዝግጅትና የትርጉም ሥራ ላይ አብርሃም ወልደ ሐናናጥያን ምንም ሚና እንዳልተጫወተ እየታወቀ አለመተቸቱንና እንደወረደ መቀበላችንን በግልጥ ለመናገር በማሰብ ነው፡፡ እውነታው ግን ለፍትሐ ነገስት ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው አሁን ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ማለትም አስተምህሯዊ ችግሯን ፣ አምልኳዊ ጉድለቷን ፣ ሥነ ምግባራዊ ውድቀቷን … በሚበዛ ጎኑ የሚያጸባርቅ ነው፡፡
      ቤተ ክርስቲያን በትውልድና በዘመን መካከል የምታልፍ፥ ሕያው የክርስቶስ አካል ናት፡፡ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን የመሠረተው በተኩላው ጨካኝ ዓለም መካከል እንጂ ከዓለም በማውጣት አይደለም ፤ እንዲሁም ጌታ “ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።” በማለት ጸልይዋል፡፡ (ማቴ.10፥16 ፤ ዮሐ.17፥15) ቤተ ክርስቲያን በክፉው ዓለምና በጠማማው ትውልድ መካከል ከክፋትና ከጥመቱ ሳትተባበር (ሐዋ.2፥40) ራስዋን “ለአንድ ወንድ በድንግልና እንደታጨች ንጽሕት ሴት በቅድስናና በንጽሕና በሐሰተኞች ትምህርት ያልተበከለች ሆና ራስዋን ለክርስቶስ ልታቀርብ ይገባታል፡፡” (2ቆሮ.11፥2) ቤተ ክርስቲያን ለአማኞቿ እናትም አባትም ናት፡፡ ለእርሷ ልጆች እንደመሆናችን መጠን (2ቆሮ.6፥13) ስለልጆቿ የህሊና አምልኰ ቅድስና አብዝታ ልትተጋ ፤ እንዲበዛላቸውም በመስቀሉ ርኅራኄ ልትለምናቸው፤ ልትለምንላቸውም ይገባታል፡፡

Wednesday, February 18, 2015

በ “ዘወረደ” ተጀምሮ በ “ትንሣኤ” የሚደመደመው የዐቢይ ጾም ዋና መልእክት

Read in PDF


ዐቢይ ጾም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ የሚጾም ታላቅ ጾም ነው፡፡ ጾሙ በዋናነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ነው፡፡ ጾሙን የሃይማኖቱ ተከታዮች እንዲጾሙት ሥርዓቱን የደነገጉት አባቶች በጾሙ ወራት ጌታችን አየሱስ ክርስቶስ የጾመውን ጾም እያሰቡ፣ እርሱና ካከናወናቸው ተግባራትና ካስተማራቸው ትምህርቶች ዋና ዋናዎቹ እንዲዘከሩ በማድረግ፣ በተለይም ጌታ ስለ እኛ ያከናወነውን የማዳን ሥራ በማሰብ እንዲጾም ማድረጋቸው እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ 

“ዘወረደ” በሚል ስያሜ የሚጀመረው የዐቢይ ጾም በ“ትንሣኤ” ይደመደማል፡፡ ዐቢይ ጾም ጌታ ሰው ሆኖ መምጣቱን በመተረክ ጀምሮ በዚህ ምድር እየተመላለሰ ከሠራቸው ድንቅና ተአምራት፣ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል የተመረጡትን በማቅረብ፣ በመጨረሻም ጌታችን ስለእኛ የተቀበላቸውን ሕማማተ መስቀልና ሞቱን ከዚያም ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱን በማወጅ ይጠናቀቃል ማለት ነው፡፡ እንዴት ድንቅ ነው!! እውነትም ዐቢይ ጾም!! 

Saturday, February 14, 2015

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍና ቆሞስ አባ ወልደ ኢየሱስ ለረጅም ጊዜ ካገለገሉበት ከላስቤጋስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተባረሩ መምህር ውብ አምላክም ታግዷል።

Read in PDF

በአንድ ጊዜ ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ሦስት አገልጋይ ታግዷል። ከሚኖሩበት ቤትም ባስቸኳይ እንዲወጡ ታዝዘዋል። "አድኅነኒ እግዚኦ እምብሲ እኩይ ወባልሃኒ እምገበርተ አመጻ‚ አቤቱ ከክፉ ሰው አድነኝ፣ ነውር ከሚፈጽሙ ሰዎችም ታደገኝ የምንልበት ክስተት ነው።
  ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ይከበር በሚለው አቋማቸው ጎልተው ይታወቃሉ። በቅዱስ ሲኖዶስ ምክትል ጸሐፊነታቸው በየቤተ ክርስቲያኑ በሚነሣ ብጥብጥ ችግር ለመፍታት ሲንቀሳቀሱ የቆዩት ብፁዕነታቸው የሲኖዶስ ደጋፊ እየተባለ ከሚጠራው ስውር ቡድን ጋር ሲፋለሙ ቆይተው ይህ ቡድን ከብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ጋር አጣልቷቸው እንደነበር ይታወሳል። ከጊዜ በኋላ ግን የሥዉሩ እንቅሥቃሴ አካሄድ የተገለጠላቸው አቡነ መልከ ጼዴቅ ከብፁዕነታቸው ጋር እርቅ ፈጽመው ወደ ፍቅራቸው ተመልስው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ለማስከበር በጋራ መቆማቸው ይነገራል። ይህን ሥርዓትና ሕግ የማስከበር እንቅሥቃሴ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በጥምቀት በዓል ላይ በመገኘት ለሕዝብ አስታውቀዋል። ሕጉ በየአብያተ ክርስቲያናቱ እንዲላክና ሕዝብ እንዲወያይበት ተደርጎ መልሱን በመያዝ እርምጃ ለመውሰድ ታቅዷል። ይህ ሁኔታ የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ እና የጳጳሳቱ እንዲሁም የካህናቱ አንድነት ያመጣው ለውጥ ነው ተብሏል። ሥርዓትና ሕግን የማያከብር ቤተ ክርስቲያንና ሕጉን የማያስከብር ካህን ከሲኖዶሱ እንዲለይና ወደ ፈለገው እንዲሄድ የሚያደርግ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችልም ተጠቁሟል። 

Thursday, February 12, 2015

ጌታ የማያውቃቸው “የጌታ አገልጋዮች”ምስክርነት አንዱ የአምልኮ መገለጫ ነው፡፡ አንድ አማኝ “ክርስቶስ እርሱ ኢየሱስ ነው ወይም ክርስቶስ እርሱ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነው” (ማቴ.16፥16 ፤ ሐዋ.9፥20 ፤22)ብሎ ወደቤተ ክርስቲያን አካል ሲጨመር አንዱ የየዕለት ዋና ተግባሩ ምስክርነት ነው፡፡ ያመንነውን በመናገር ብቻ የምንመሰክር አይደለንም ፤ በሕይወትና በምግባር(በሥራ) እንጂ፡፡ “በጸጋ ድነናል”(ኤፌ.2፥5) ካልን ልክ እንደመዳናችን ማመናችንም ከእኛ የሆነ አይደለም፡፡ ጸጋው በእምነት ካዳነን “ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ” ከእኛ ሥራ የተነሳ አይደለም፡፡(ኤፌ.2፥8)
  እኛን ለማዳን አብ ልጁን ወደምድር ሲልክ ፤ እኛ ምንም የተገባን አልነበርንም፡፡ ስለዚህ “በእንዲሁ ፍቅር”(ዮሐ.3፥16) ወዶን በልጁ ሞት አዳነን፡፡ የልጁን ማዳንም እንድንቀበልም በልባችን የእምነትን አቅም ያኖረው እርሱ ነው፡፡ ነጻ ምርጫችንን ጠብቆ ፥ አምነን ወደእርሱ በመጣን ጊዜ ግን እንድናምነው ጉልበት የሆነን ያዳነን ያው ጌታ ነው፡፡ እንዲሁ “መልካሙን ሥራ ለማድረግም በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነልን አዲስ ፍጥረት መወለድ(መፈጠር) ያስፈልገናል፡፡ (ኤፌ.2፥10)
   ከክርስቶስ ኢየሱስ በአዲስ ልደት ያልተወለደ መልካም ለማድረግ አቅም የለውም፡፡ “ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው”ና (ዮሐ.3፥6) ከመንፈስ ቅዱስ የሆነውን የመንፈስን ሥራ(ፍሬ) ለማፍራት አይቻለውም፡፡ ምክንያቱም “እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና …  ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና” (ሮሜ.8፥5-6) ስለዚህም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ “ … ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የተወለዱ” (1ጴጥ.1፥5) በምንም አይነት መንገድ “ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት አይለውጡም፡፡” (ይሁ.4)

Tuesday, February 3, 2015

እውነትን ለማውገዝ ማንም የማይቀድማት ኑፋቄንና ክሕደትን ግን ለመቃወም ድፍረት የሌላት ቤተ ክርስቲያን

 Read in PDF
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በእውነተኛው ትምህርተ ወንጌል ላይ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ ቆመን ስናስተውለው ይህ ታሪክ ብቻ ከመሆን አላለፈም፡፡ ኑፋቄን በኑፋቄነቱ የሚጸየፉና የሚያወግዙ ሊቃውንት የነበሩባት ቤተ ክርስቲያንም ነበረች፡፡ ቦሩ ሜዳ ላይ ተደርጎ በነበረው የሃይማኖት ክርክር ላይ ከተወገዙትና ማስተካከያ እንዲሰጥባቸው ከተደረጉት ኑፋቄዎች አንዱ “ለማርያም ከልጇ ጋር አምልኮትና ስግደት ይገባታል” የሚለው ይገኝበታል፡፡ ይህም “ለልጇ አምልኮትና ስግደት ይገባል” በሚለው ማስተካከያ ተሰጥቶበታል፡፡
 ይህም ብቻ አይደለም የቦሩ ሜዳው ጉባኤ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ማርያም ተገለጠችልኝ ብሎ ያስተረጎመውና ያጻፈው፣ ዛሬ ድረስም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ለአምልኮተ ማርያም መስፋፋት መሠረት የሆነውን የክሕደትና የኑፋቄ መጽሐፍ የሆነው ተአምረ ማርያምም ለሃይማኖት ትምህርት ለመጠቀስ የማይበቃ ተራ መጽሐፍ መሆኑ የተነገረበት ጉባኤ ነበር፡፡ በጉባኤው ላይ ዳኛ ሆነው የተቀመጡት ዐፄ ዮሐንስ ተአምረ ማርያምን ማስረጃ አድርጎ ላቀረበው አንድ ተከራካሪ ምነው አንተ “ከአራቱ ጉባኤ አጣህና ስለ ሃይማኖት ተአምረ ማርያምን ትጠቅሳለህን?” ማለታቸው በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመዝግቦ የሚገኝ እውነት ነው (እንደ ዳንኤል ክብረት ያሉ ለራሳቸው “የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመራማሪ” የሚል ማዕርግ የሰጡ የተአምረ ማርያም ወዳጆች የተባለውን ለመሸራረፍ በመሞከር  “ስለ ሃይማኖት” የምትለዋን ሐረግ ገድፈው የአፄ ዮሐንስን አነጋገር ቢያዛቡትም)፡፡ ይሁን እንጂ ይህም ያለፈ ታሪክ ብቻ ከመሆን አላለፈም፡፡