Tuesday, February 3, 2015

እውነትን ለማውገዝ ማንም የማይቀድማት ኑፋቄንና ክሕደትን ግን ለመቃወም ድፍረት የሌላት ቤተ ክርስቲያን

 Read in PDF
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በእውነተኛው ትምህርተ ወንጌል ላይ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ ቆመን ስናስተውለው ይህ ታሪክ ብቻ ከመሆን አላለፈም፡፡ ኑፋቄን በኑፋቄነቱ የሚጸየፉና የሚያወግዙ ሊቃውንት የነበሩባት ቤተ ክርስቲያንም ነበረች፡፡ ቦሩ ሜዳ ላይ ተደርጎ በነበረው የሃይማኖት ክርክር ላይ ከተወገዙትና ማስተካከያ እንዲሰጥባቸው ከተደረጉት ኑፋቄዎች አንዱ “ለማርያም ከልጇ ጋር አምልኮትና ስግደት ይገባታል” የሚለው ይገኝበታል፡፡ ይህም “ለልጇ አምልኮትና ስግደት ይገባል” በሚለው ማስተካከያ ተሰጥቶበታል፡፡
 ይህም ብቻ አይደለም የቦሩ ሜዳው ጉባኤ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ማርያም ተገለጠችልኝ ብሎ ያስተረጎመውና ያጻፈው፣ ዛሬ ድረስም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ለአምልኮተ ማርያም መስፋፋት መሠረት የሆነውን የክሕደትና የኑፋቄ መጽሐፍ የሆነው ተአምረ ማርያምም ለሃይማኖት ትምህርት ለመጠቀስ የማይበቃ ተራ መጽሐፍ መሆኑ የተነገረበት ጉባኤ ነበር፡፡ በጉባኤው ላይ ዳኛ ሆነው የተቀመጡት ዐፄ ዮሐንስ ተአምረ ማርያምን ማስረጃ አድርጎ ላቀረበው አንድ ተከራካሪ ምነው አንተ “ከአራቱ ጉባኤ አጣህና ስለ ሃይማኖት ተአምረ ማርያምን ትጠቅሳለህን?” ማለታቸው በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመዝግቦ የሚገኝ እውነት ነው (እንደ ዳንኤል ክብረት ያሉ ለራሳቸው “የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመራማሪ” የሚል ማዕርግ የሰጡ የተአምረ ማርያም ወዳጆች የተባለውን ለመሸራረፍ በመሞከር  “ስለ ሃይማኖት” የምትለዋን ሐረግ ገድፈው የአፄ ዮሐንስን አነጋገር ቢያዛቡትም)፡፡ ይሁን እንጂ ይህም ያለፈ ታሪክ ብቻ ከመሆን አላለፈም፡፡  

ዛሬ በአንድ በኩል ቤተክርስቲያናችን ውስጥ የወንጌል እሳት በስብከትም በዝማሬም እየተቀጣጠለ ቢሆንም ይህን ማንም ሊያጠፋው የማይችለውን የወንጌል እሳት ለማጥፋት እየተረባረቡ ያሉ የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የግብር ልጆች ያን የተወገዘ ኑፋቄ ወደቤተክርስቲያን ለመመለስ እየታገሉ ይገኛሉ፡፡ እውነተኛው አምላክ ብቻ እንዳይመለክና ለእርሱም ብቻ እንዳይዘመርለት የቅዱሳን ወዳጅ መስለው በተግባር ግን የቅዱሳን ጠላት የሆኑ ከሓድያንና መናፍቃን ቤተክርስቲያን ውስጥ መሽገው የወንጌልን ቃል በሚጻረር ሁኔታና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነ መንገድ ማርያም እንድትመለክ ለማድረግ ከዚያው ከተአምረ ማርያምና ከመሰሎቹ አዋልድ መጻሕፍት ውስጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የሚጋጩና የጌታችንን ማንነትና ግብር ለማርያም በመስጠት ማርያም የጌታ እናት በመሆኗ ከሚገባት ክብር አልፋ ወደ መመልክ ደረጃ እንድትደርስ ለማድረግ ባገኙት አጋጣሚ ሲናገሩና ሲጽፉ እየታዘብን ነው፡፡ እነዚህ መናፍቃን ይህን ክሕደትና ኑፋቄ በማርያም ስም እንዲነዙ የረዳቸው አንድ ምቹ ሁኔታ ደግሞ ኑፋቄን ለማውገዝና ይህማ ልክ አይደለም ለማለት ድፍረት ያላቸው ሊቃውንት የመታጣቸው ጉዳይ ነው፡፡ ጥቂቶች ቢኖሩም እንኳን ለመናገር ሲሞክሩ ሰሚ ማጣታቸው፣ ስፍራ አለማግኘታቸውና እውነተኛነታቸው መናፍቅ የሚል ስም ስለሚያሰጣቸው በትምህርት መናፍቃን የሆኑትን የልብ ልብ ሰጥቷቸዋል፡፡ በሌላም በኩል ይህን ትምህርት የወለደውና በማርያም ስም አምልኮትን ለራሱ ሊቀበል የሚፈልገው ሰይጣንም በእነዚህ ከሃድያንና መናፍቃን ስለሚጠቀምባቸውና ስፍራውን ስለተቆጣጠረው ነገሮች እንዲህ ቢሆኑ አይደንቅም፣ የጨለማው ገዥ አሠራር እንዲሁ ነውና፡፡

ከሰሞኑ ለጥምቀት በዓል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ለ2007 ዓ.ም. በዓለ ጥምቀት ተዘጋጅቶ በነጻ በታደለውና “በእርሱ አምሳል እንወለድ ዘንድ ስለእኛ ተጠመቀ” በሚል ርእስ በወጣው መጽሔት ውስጥ ትልቅ ኑፋቄ ተላልፏል፡፡ ኑፋቄው አዲስ ባይሆንም እንደ አዲስ የጻፈው ከሰሞኑ በአባ ሰላማ ድረገጽ ላይ ስለእርሱ አሳፋሪ ማንነትና ስራ ተጽፎ ያነበብንለት ሊቀትጉሃን ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ ነው፡፡ ይህ አደገኛ መናፍቅና ለክፋት የሚተጋ ከሓዲ የጌታን እናት ያከበረ መስሎት እርሷ ያልሆነችውንና ያልሠራችውን ሆናለች ሰርታለች በማለት ሕዝብን የሚያሳስት የክርስቶስን አዳኝነት ጎዶሎ የሚያደርግና በማርያም ይሟላል የሚል፣ እርሷን የጌታ እናት ሳይሆን ፈጣሪ አድራጊ አስመስሎ በማቅረብ ኑፋቄን ዘርቷል፣ ክሕደትን አስተምሯል፡፡ እርሱ ይህን ሲጽፍ የመጽሔት ዝግጅት ክፍሉ ጽሑፉን አልመረመረም ወይ? ከመረመረስ እንዴት ሊያሳልፈው ቻለ? ቤተ ክርስቲያኒቱ እርሱ እንደጻፈው ነው የምታምነው ማለት ነው? ወይስ ግለሰቡ የማቅ ቀንደኛ ወዳጅ ስለሆነ ይህ ጽሑፍ እንዲወጣ የማኅበሩ ስውር እጅ ይኖርበት ይሆን? እኒዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ምላሽ ይሻሉ፡፡ ለማንኛውም ኑፋቄውን በእግዚአብሔር ቃል እንመርምረው፡፡

በቅድሚያ ጽሑፉ አንድ ቡድን ስለማርያም ያወጣው የእምነት መግለጫ ዓይነት ይዘት ያለው መሆኑን መግለጽ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ነው ከዚህ ጽሑፍ ታትሞ መውጣት በስተጀርባ የማቅ ስውር እጅ ይኖር ይሆን ወይ? ለማለት የተቻለው፡፡ በነጥብ የተቀመጡት ሐሣቦች በአብዛኛው ክሕደትና ኑፋቄን የተሞሉ ናቸው እስኪ ጎላ ያሉትን ጥቂቶቹን ብቻ ቀጥሎ እንመልከት፡፡

·        “እመቤታችንን መሠረት አድርጎ መማርና ማስተማር የኦርቶዶክሳውያን መምህራነ ወንጌልና ሕዝበ ክርስቲያን ልዩ ሥርዓትነው” (ገጽ 36)
ጸሐፊውን ይህን ያለው ማነው? ብንለው መልስ ይኖረው ይሆን? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የክርስትና ተቋም እስከ ሆነች ድረስ የሃይማኖቷና የትምህርቷ መሠረትና ማእከል ሊሆን የሚችለው የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ ማርያም አይደለችም፡፡ በክርስትና ትምህርት ከዚህ በቀር ሌላ መሠረት ፈጽሞ የለም፡፡ ማርያም የጌታችን እናት በመሆኗ በቤተክርስቲያን ትልቅ አክብሮትና ስፍራ የሚሰጣት ቢሆንም ይህ ስፍራ የክርስትና መሠረት እስከመሆን ከደረሰ ግን ትልቅ ስሕተት ነው፡፡ ወንጌል ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ቅዱሳን በወንጌል የሚነሡ ቢሆንም እንኳ የተሰቀለውን ክርስቶስን ለማጉላት እንጂ እነርሱው እንዲሰበኩ አይደለም፡፡ ስለዚህ ይህ የኃይለ ጊዮርጊስ አመለካከት እንጂ መሠረቷ ክርስቶስ የሆነችው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት አይደለም፤ እርሱ በግድ ልጫንባት ካላለ በቀር ቤተ ክርስቲያኗ ይህን አታውቀውም፡፡ አሊያ ኦርቶዶክስ የክርስትና ተቋም ሳትሆን ሌላ ሆናለች ወደሚለው አስተሳሰብ ይመራናል፡፡

·        “እመቤታችን ጥንቱን ሰው ሲፈጠር ንጽሕት ዘር ሆና ተወልዳለች፡፡ ጥንተ አብሶ የለባትም የልጇም ንጹሐ ባሕርይነት ከምንጩ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ፍጹም ንጽሕና የተነሣ ነው፡፡”   (ገጽ 36)
በዚህ ነጥብ ሥር       ደፋሩ ኃይለ ጊዮርጊስ የዘራቸውን ቢያንስ 3 ኑፋቄዎችን እንመለከታለን፡፡ የመጀመሪያው እመቤታችን ጥንቱን ሰው ሲፈጠር ንጽሕት ዘር ሆና ተወልዳለች፡፡የሚለው ነው፡፡ ኃይለ ጊዮርጊስ ማርያም ንጽሕት ዘር ሆና የተወለደችው ጥንቱኑ ሰው ሲፈጠር ነው እያለን ነው፡፡ ይህ ማርያምን ወደ እምቅድመ ዓለም የሚወስድና አባቶቹ በመጽሐፈ ሰዓታት “እምቅድመ ሰማይ ወምድር ሀልዎትኪ ፀሐይ ወወርኅ ኢቀደሙኪ ..” መኖርሽ ከሰማይና ምድር መፈጠር አስቀድሞ ነው፡፡ ፀሐይና ጨረቃም አልቀደሙሽም” በማለት የስነ ፍጥረትን ቅደም ተከተል ያዛቡበትን፣ ማርያምን እግዚአብሔር ያደረጉበትን የግእዝ ድርሰት በአማርኛ ለማጽናት ፈልጎ ነው እንዲህ ያለው፡፡  ይሁን እንጂ ይህ ምንም ማስረጃ የማይገኝለት እነርሱ በፈቃዳቸው መንፈሳዊ ምንዝርና ለመፈጸም ብለው በእግዚአብሔር ላይ በማርያም ስም መመለክ ፈልጎ ይህን ሐሳብ ወደ ልባቸው የጨመረውንና የብርሃን መልአክን ለመምሰል ራሱን የሚለውጠውን ሰይጣንን ለመደረብ ፈልገው ያደረጉት ነው፡፡ በምንዝርናቸው የሚተባበራቸው ካለ ይህን የኑፋቄ ትምህርት ይቀበላል፡፡ አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚል ግን ከዚህ መንገድ ራሱን ይጠብቅ፡፡

 ሌላው ነጥብ ማርያምጥንተ አብሶ የለባትም የሚለው ነው፡፡ አሁን አሁን ይህ የስሕተት ትምህርት፣ የስሕተት ትምህርት መሆኑ ቀርቶ እውነተኛ ተደርጎ እየቀረበ ነው፡፡ ትምህርቱ የካቶሊኮች እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊም ሆነ በብዙዎቹ የጥንት አባቶች የሚታመን እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ የግብጽ ኦርቶዶክስም ሆነች ሌሎቹ ኦሬንታልና ምሥራቃውያን ኦርቶዶክሶች ትምህርትም አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ዘንድም ሙግቱ እስካሁን የበረደ አይደለም፡፡ ማርያም ጥንተ አብሶ የሌለባት ከሆነች ለምን ሞተች? ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ የዚህ አመለካከት ደጋፊዎች መልስ የላቸውም፡፡  ማርያም የሞተችው ግን ጥንተ አብሶ ስላለባት ነው የሚለው ያስኬዳል፡፡ ጥንተ አብሶ ባይኖርባት የኃጢአት ደመወዝ የሆነው ሞት ወደእርሷም ባልመጣ ነበር፡፡ ለሰው ልጆችም ቤዛ ሆና የምትሞት ተገኝታለችና ቃል ሥጋ ሆኖ መምጣትና መሞት ባላስፈለገውም ነበር ወደሚል አስተሳሰብ በተመራን ነበር፡፡ ግን ይህ ሁሉ ያልሆነው ማርያም ከጥንተ አብሶ ነጻ ስላልሆነች ነው፡፡ ስለዚህ የሁሉም ሰው ዕጣ የሆነው ሞት በእርሷም ላይ ደረሰባት፡፡  

የልጇም ንጹሐ ባሕርይነት ከምንጩ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ፍጹም ንጽሕና የተነሣ ነው፡፡”  
ለኑፋቄው ለከት ያጣው ኃይለ ጊዮርጊስ ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም ሲል ኦርቶዶክሳዊውን ትምህርት መለወጡ ሳያንስ የክርስቶስ ንጹሐ ባሕርይነት ከምንጩ ከማርያም ፍጹም ንጽሕና የተነሣ ነው በማለት ኢየሱስ ጥንተ አብሶን ሳይወርስ ቅዱስ ሆኖ የተወለደው በማርያም ንጽሕና ምክንያት ነው በማለት ማርያምን አከብር ብሎ ጌታን ያዋርዳል፡፡ ማርያምን የንጽሕና ምንጭ ጌታን ደግሞ ንጽሕና ተቀባይ ያደርገዋል፡፡ ይህም ሌላው ቢቀር እንኳ ቅዱስ ያሬድ “አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ” ሲል ሥጋዋን አንጸቶ በእርሷ ማደሩን የመሰከረውን ምስክርነት እንኳ ያላከበረና እርሱን ገልብጦ ማርያም ንጽሕት ስለሆነች ክርስቶስም ንጹሕ ሆኖ መወለድ ቻለ በማለት ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ንጹሕ አልነበረም ወደ ማለት ደርሷል፡፡ ለመሆኑ መናፍቁ ኃይለ ጊዮርጊስ ይህን ከየትኛው መጽሐፍ ላይ ነው ያነበበው? ያው አባቶቹ “ወመሠረተ ንጽሕነ ኮነ በማርያም ድንግል” “የንጽሕናችን መሠረት በድንግል ማርያም ሆነ” ያሉትን ይዞና እርሱኑ አለቅጥ አስፍቶ የክርስቶስም የንጽሕና መሠረት ማርያም ናት ወደማለት ገባ፡፡  ከእርሱ ይልቅ በዚህ ጉድ ላይ ተጠያቂው የመጽሔት ዝግጅት ክፍሉ ነው፡፡ ዝግጅት ክፍሉ ይህን ትልቅ ክሕደት እንዴት በዝምታ አሳልፎ እንዲታተም ፈቀደ? እንዴትስ የጌታ ክብር ሲዋረድ ከምንም አልቆጠረውም? ቤተክህነቱስ ምን ያስባል? ለነገሩ እውነትን አውጋዥ ሐሰትን አንጋሽ ስለሆነ ክሕደቱ ከዚህም በላይ ተለጥጦ ቢነገር ምንም አይመስለውምና በዚህ ጉዳይ ላይ የሚወስደው እርምጃ ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ጥቂት እውነት ቢነገር ያለው መንጫጫትና ትርምስ አይጣል ነው፡፡ ስሕተት ግን እስከ ጥግ ቢነገር ማንም ከልካይ የለበትም፡፡

ኃይለጊዮርጊስ ኑፋቄውንና ክሕደቱን በዚህ ሳያበቃ እንደገና ሌላ ኑፋቄና ክሕደት እንዲህ በማለት ይጨምራል፣ “ማርያም ማለት ራሱ ልዩ ከፍጥረት ንጹሕ ከኀጢአት መልክ ከደም ግባት አንድ ሆኖ የተሰጣት ማለት ነው፡፡” (ገጽ 36) ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ያስደረሰው ወይም አስተረጎምኩት ያለው ተአምረ ማርያም የማርያምን የስሟን ትርጓሜ በዕብራይስጥ ማሪሃም ብሂል መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት” “በዕብራይስጥ ማሪሃም ማለት ወደ መንግሥተ ሰማያት መርታ የምታስገባ ማለት ነው” ይላል፡፡ የማርያም የስሟ ትርጓሜ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ሲጀመርም በዕብራይስጥ ሚርያም እንጂ ማሪሃም አይልም፡፡ ማርያም የሚለው ስም ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ ማር ወይም ሚር ማለት መራራ መራር ማለት ሲሆን ያም ደግሞ ዕለት ዘመን እንደ ማለት ነው፡፡ በተገናኝ ማርያም ማለት ምርርተ ዘመን፣ ዘመኗ የመረረ ወይም የከፋ እንደ ማለት ነው፡፡ በዚህ ስም የተጠራችው የሙሴ እህት ማርያም እስራኤልን በሚያሠቃየው በፈርኦን ዘመን ስለተወለደች ይህ ስያሜ እንደተሰጣትና የጌታን እናት ጨምሮ ሌሎች እስራኤላውያት ሴቶችም በዚህ ስም እንደተጠሩበት ይታወቃል (የኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ  ቃላት ገጽ 610)፡፡ እውነታው ይህ ቢሆንም ስያሜው ከሚሰጠው ፍቺ ውጪና ለጌታ እናት ለማርያም የአዳኝነት ስፍራ ለመስጠት እንዲመቻቸው እነአፄ ዘርዓ ያዕቆብ “ወደመንግሥተ ሰማያት መርታ የምታስገባ” የሚል የራሳቸውን ፍቺ ሰጡ፡፡ ስያሜው ግን እንዲህ ያለ ፍቺ የለውም፡፡

ኀይለ ጊዮርጊስም ስሟ ሊሰጥ የማይችለውን ትርጓሜ ለመስጠት ከተጻፈው በማለፍ ስለ ማርያም ከእውነታው ውጪ የሆነ ነገር ጽፎ እናነባለን፡፡ ማርያም ከሴቶች መካከል ተለይታ የተባረከች እንጂ ከፍጥረት ልዩ የሆነች ፍጥረት አይደለችም፡፡ ከፍጥረት ልዩ ማለትም በራሱ ግልጽ ነት የሚጎድለው አገላለጽ ነው፡፡ ከሰው ወገን አይደለችም ለማለት ነው? ወይስ ምን ለማለት ተፈልጎ ነው? እንደገናም “ንጹሕ ከኀጢአት” የሚለውም አገላለጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡ ማርያም ከሴቶች ተለይታ የተባረከች ብትሆንም ሰው መሆኗን መዘንጋት ከቶ አይቻልም፡፡ ከኀጢአት ንጹሕ ተብሎ ሊገለጽ የሚችል ንጹሐ ባሕርይ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ፍጡር ግን ይህን ሊያሟላ ስለማይችል “ንጹሕ ከኀጢአት” ሊባል አይገባውም፡፡      

“በባሕርየ መለኮቱ ሞት የሌለበት አንድ ልጇ መድኀኒታችን ሰው በመሆኑ ለቤዛ ዓለም ሞቷል፡፡ እመቤታችንም ለቤዛ ብዙኃን ጥር 21 ቀን በዕለተ እሑድ ሞታ በዕለተ ሠሉስ እንደ ልጇ በሦስተኛው ቀኝ ተነሥታ ዐርጋለች፡፡” (ገጽ 36) ይህ የኃይለ ጊዮርጊስ ሌላው ኑፋቄ ነው፡፡ በዚህ ኑፋቄ መሠረት የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት የጠቀመው ሁሉን አይደለም፤ ወይም ለሁሉም አልበቃም፡፡ ስለዚህ እናቱ የብዙሃን ቤዛ ሆና መሞት ስላስፈለገ ጥር 21 ቀን ሞተችና በ3ኛው ቀንም እንደልጇ ተነሥታ ዐረገች በማለት ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጋር የሚጋጭና የክርስትናን መሠረት የሚንድ አደገኛ ኑፋቄ ይዘራል፡፡ ለመሆኑ የክርስቶስ ሞት አልበቃ ብሎ ነው ማርያም ስለብዙሃን ቤዛ ሞተች ተብሎ የሚነገረው? መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ኢየሱስ ክርስቶስ ለኀጢአት ሁሉ የሚበቃ አንድን መሥዋዕት ራሱን በማቅረብ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል ይላል፡፡ “እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥” (ዕብ. 10፥12)፡፡ የኃይለ ጊዮርጊስ ዋነኛ መጽሐፍ ግን ነገረ ማርያም ነውና መጽሐፍ ቅዱስን ወደጎን ገፍቶ በተረት የተሞላውንና ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የሚቃረነውን ነገረ ማርያምን በመጥቀስ ሊያጃጅለን ይሞክራል፡፡

ቀደምት አባቶችም መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት በማድረግ እንዳስተማሩን ሰውን የሚያድነው የክርስቶስ ሞት ብቻ እንጂ የሌላ ሰው ሞት ሊያድነው ከቶ አይችልም፡፡ በሃማኖተ አበው ላይ ከሚታወቁት ሊቃውንት መካከል አንዱ አቡሊዲስ እንዲህ ይላል “ብእሲ ኢይክል ያድኅን ዓለመ ወሞቱ ለብእሲ ኢያነጽሖ። ... ወኢይክል ሙኑሂ እም ሰብእ ያብጥል መዊተ፤ ወያብርሃ ለሕይወት በከመ ይቤ ዳዊት መኑ ውእቱ ሰብእ ዘየሐዩ ወኢይሬእያ ለሞት፤ ወመኑ ዘያድኅና ለነፍሱ እም እደ ሲኦል። ወዘኢክህል ያደኅን ነፍሶ እፎኑመ ይክል ያድኅን ኵሎ ዓለመ፤”
ትርጉም፦ “ሰው ዓለምን ለማዳን አይችልም። የሰው መሞትም ከኃጢአት አያነጻም… ዳዊት ሕያው ሆኖ የሚኖር ሞትንም የማያይ ሰው ማነው? ከሲኦል እጅስ ነፍሱን የሚያድን ማነው? ሲል እንደ ተናገረ ሞትን ያጠፋ ዘንድ ሕይወትንም ያበራ ዘንድ የሚቻለው ከሰዎች ይገኛልን? ነፍሱን ለማዳን ያልቻለ ከሆነማ ሌላውን ለማዳን እንዴት ይችላል? አንዱን ለማዳን ካልቻለስ መላውን ዓለም እንዴት ሊያድን ይችላል?” (ሃይማኖተ አበው ገጽ 145)። ታዲያ ይህ ማርያምንስ አይጨምርምን? ይጨምራል እንጂ፡፡ ለመሆኑ የነገረ ማርያም ደራሲና የእርሱ አፍቃሪ ኃይለ ጊዮርጊስ ትልቁ ችግራቸው መጽሐፍ ቅዱስን አለማንበባቸው ነው፡፡ ቢያነቡማ ይህን ግልጽ እውነት ባላስተባበሉ ነበር፡፡

ማርያም በሞተች በ3ኛው ቀን ተነሥታ ዐርጋለች የሚለው ሐሰተኛ ትምህርትም እንዲሁ ልቦለድ እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው ጾመ ፍልሰታ የተሰኘ ጾም ተዘጋጅቶለታል በብዙዎች ልብ ውስጥ እውነት ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስላልሆነና ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር ስለሚጣረስ ተቀባይነት የለውም፡፡ ይህ ጉዳይ ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ሐዋርያት ጽፈዉት ባለፉ ነበር፡፡ በተለይም እነኋት እናትህ ተብሎ ዐደራ የተሰጠው ዮሐንስ ይህ በጻፈልን ነበር፡፡ እርሱ ግን በቃና ዘገሊላ ሠርግ ላይ መገኘቷን የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም ማለቷንና በኋላም የሚላችሁን አድርጉ ማለቷን፣ በተሰቀለ ጊዜ በመስቀሉ ሥር የነበረች መሆኗን ከመዘገብ በቀር ስለእርሷ የጻፈው ሌላ ነገር የለም፡፡ ለተመረጠች እመቤትና ለልጆቿ 2ኛ መልእክቱን እንዲሁም ለጋይዮስ 3ኛ መልእክቱን ሲጽፍ ስለ ማርያም ግን ከላይ ከተጠቀሰው ውጪ የጻፈው ነገር እንደሌለ መመልከት እንችላለን፡፡ ታዲያ እርሱ በአደራ የተቀበላት ያልጻፈውን ከየት አምጥተን ነው ማርያም ተነሣች አረገች የምንለው? ይህ እኮ ጌታን አድሏዊ የሚያስመስል ታሪክ ነው፡፡ ጌታ ለእናቱ አድልቶ እርሷን በሞተች በ3ኛው ቀን እርሱ በተነሣበት አካል አስነሣት እንደእርሱም ወደሰማይ አሳረጋት ማለት ምንም መሠረት የሌለው የቃሉ ድጋፍም የማይገኝለት ኑፋቄ ነው፡፡ ጌታ ከሙታን በኩር ሆኖ እንደተነሣ ሙታን ሁሉ (ማርያምን ጨምሮ) በመጨረሻው ቀን እንደሚነሡ ይጠበቃል፡፡ ከዚያ አስቀድሞ ከሙታን የተነሣና ወደሰማይ ያረገ ግን የለም፡፡

ይቀጥልና ኀይለ ጊዮርጊስ ማርያም “የቅድስት ቤተክርስቲያን እናት ስለሆነች በምድር ትግህት ጠባቂ በሰማይ የታመነች አስታራቂ ነች፡፡” (ገጽ 37) ይላል፡፡ ለኀይለ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማን መሆኗ አይታወቅም፡፡ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤተክርስቲያን ማርያምን ጨምሮ በክርስቶስ የአድኅኖት ሥራ ያመኑ ምእመናን ሁሉ አንድነት ናት፡፡ ስለዚህ ማርያም የቤተክርስቲያን አባል እንጂ እናት የምትባልበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ይህን ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማነው ከኃይለ ጊዮርጊስ መሆኑን መናገር ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡ ቤተክርስቲያን ሙሽራ እንጂ እናት አላት ተብሎ አልተጻፈም፡፡ ሙሽራዋም ክርስቶስ ነው፡፡ ደግሞም ቤተክርስቲያንን የሚጠብቅ እንደተጻፈው ኖላዊ ትጉሕ እግዚአብሔር ብቻ ነው እንጂ ማርያም አይደለችም፡፡ ደግሞስ ማርያምን “በምድር ትግሕት ጠባቂ” ማድረግ እርሷን ምሉዕ በኩለሄ ማድረግ አይሆንምን? እንዲህ የሚለው ትምህርትስ ከየት የተገኘ ነው? ምናልባት ከዚያችው ከፈረደባት ከተአምረ ማርያም ይሆናል እንጂ ይህ የክርስትና ትምህርት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ለሰዎች ጠባቂ ያደረጋቸው መላእክት ናቸው እንጂ ቅዱሳን ሰዎችን ለሰዎች ጠባቂ ያደረገበት ሁኔታ የለም፡፡ በመጽሐፈ ቅዳሴ እንደ ተጻፈውም መላእክትንም እርሱ ይጠብቃቸዋል፡፡ ስለዚህ ማርያም በአጸደ ነፍስ ሆና በምድር ትጠብቃለች ማለት በብዙ መልኩ የማስኬድ ከመሆኑም በላይ በፍጡር መታመን ስለሚሆን በፍጡር የመታመን ውጤትን በሰው ላይ ያመጣል፡፡ በነቢዩ በኤርምያስ አድሮ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም ሰውም በሌለበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል።” ከዚህ በተቃራኒ፣ “በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል። (ኤር. 17፥5-8)፡፡

በምድር ትግህት ጠባቂ ማድረጉ ሳያንስ “በሰማይ የታመነች አስታራቂ ነች” ሲል የክርስቶስን የሊቀካህናትነት ሥፍራ ለእርሷ ይሰጣል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን “እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ።” ይላል (ዕብ. 4፥14)፡፡ ሃይማኖተ አበውም “ከእርሱ በቀር ራሱ ብቻውን ኃጢአትን ማስተስረይ የሚቻለው የታመነ አስታራቂ ማነው? ለማስታረቅ ኃጢአትንም ለማስተስረይ ያቀረበው መሥዋዕትስ ምንድነው? መሥዋዕት ለመኾን የነሣው ሥጋው ብቻ ነው እንጂ።” (ሃይማኖተ አበው ገጽ 222)። ስለዚህ አንድ ጊዜ ባቀረበው መሥዋዕት ለሁል ጊዜም የሚያስታርቅ በሰማያት ያለው አስታራቂ አንድ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡    
 
ማርያም አምላኩ ኃይለ ጊዮርጊስ በመቀጠል የዘራው ኑፋቄ የሚከተለው ነው፡፡ “በሰማይ የማያልፍ ጽድቁን እንደምናገኝ በተስፋ የምንጸናው ከእመ ብርሃን እመቤታችን እናትነት የተነሣ ነው፡፡ ያለእመቤታችን ድንግል ማርያም ሁለንተና በምድርም በሰማይም የተገኘና የሚገኝ ረድኤት በረከት በጭራሽ የለም፡፡” (ገጽ 37)፡፡ በዚህ አነጋገሩ ማርያም አምላክ እንጂ የጌታ እናት ብቻ አይደለችም፡፡ እርሱ የጠቀሳቸውን ነገሮች ጽድቅን ረድኤትንና በረከትን ለመስጠት እግዚአብሔር ብቻውን በቂ ነው የማንንም እርዳታ አይሻም፡፡ እነዚህን ሁሉ በአንድ ልጁ በክርስቶስ በኩል ስላደረገና ስለሚያደርግም ይህንኑ የተገለጠ እውነት መቀበልና መስበክ እንጂ ሌላ አምልኮ ባዕድን በማርያም ስም ማስፋፋት ትልቅ ኃጢአት ነው፡፡ የክርስቶስን ሥራም ገደል መጨመር ይሆናል፡፡ ስለዚህ ይህ ነጥብ በሙሉ አምልኮ ባዕድ ነውና ሊወገዝ ይገባል እንጂ በዝምታ መታለፍ የለበትም፡፡

“ያለነገረ መስቀል ነገረ አድኅኖት እንደሌለ ሁሉ ነገረ ክርስቶስ የተገለጸው በነገረ ማርያም ነው፡፡ የእመቤታችንን ክብርና ልዕልና ከዘለዓለም ድንግልናና ንጽህናዋ ጋር ሳያውቁና ሳያምኑ ጽሩየ ባህርይ ልጇ ክርስቶስን እንወዳለን የባሕርይ አምላክነቱን እናምናለን ማለት ያለደረጃ ፎቅ እወጣለሁ ብሎ በከንቱ ተንቆጫቁጮ ተንከባሎ መውደቅ ነው፡፡ ለቃል ርደት ለሥጋም ዕርገት ዐይነተኛዪቱ ምክንያት እመቤታችን ብቻ መሆኗ በውል መታወቅና መታመን አለበት፡፡” (ገጽ 30) መናፍቁ ኃይለ ጊዮርጊስ ወደሌላው ኑፋቄ ሲሸጋገር አሁንም ክርስቶስንና የመስቀል ሥራውን የዕፀ መስቀልና የማርያም ጥገኛ ሊያደርገው ይሞክራል፡፡ ኃይለ ጊዮርጎርጊስ ነገረ መስቀል ሲል ዕንጨቱን ነው፤ ምስኪን! መጽሐፍ ቅዱስና በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ላይ የtመሠረቱ ሊቃውንት ግን ነገረ መስቀል የሚሉት የክርስቶስን መከራና የማዳን ሥራውን ነው፡፡ የምንድንበት መስቀልም ዕንጨቱ ሳይሆን ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን የተቀበለው መከራና የማዳን ሥራው ነው፡፡ በኃይለ ጊዮርጊስ ዘንድ ግን ዕንጨቱ እንጂ የክርስቶስ መከራ ስፍራ የለውም፡፡ በተመሳሳይም ነገረ ሃይማኖት የሆነውን ነገረ ክርስቶስን፣ ማስተዋል የጎደላቸው ሰዎች ማርያም የጌታ እናት መሆኗን ይዘውና በዚያ ላይ የራሳቸውን ሐሣብ ጨምረው ነገረ ማርያም ሲሉ የደረሱትን ተረት ኃይለ ጊዮርጊስ ለነገረ ክርስቶስ መገለጫ ሲያደርገው ክርስቶስን አሳንሶ ማርያምን ከፍ ማድረጉ ነው፡፡ ማርያምን ሳያምኑ ክርስቶስን መውደድም ሆነ ማመን እንደማይቻልና ይህን ይቻላል ማለት ያለደረጃ ፎቅ እወጣለሁ ብሎ መሞከርና ተንቆጫቁጮ መውደቅ ነው በማለትም ይዘባበታል፡፡ በዚህም አነጋገሩ ወደአብ መድረሻ መንገዱ ማርያም ናት እያለን ነው፡፡ ወደአብ የምንቀርበው በማርያም በኩል ነው የሚል ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ሐሣባቸውን ባሰፈሩ አባቶች ዘንድ ካልሆነ በቀር በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በአበው ሃይማኖት አይገኝም፡፡ መንገዱ ኢየሱስ ብቻ ነው፤ እርሱም በእኔ በኩል ካልሆነ በስተቀር ወደ አብ የሚመጣ ማንም የለም ነው ያለው፡፡ ደግሞም በእኔ እመኑ በአባቴም እመኑ አለ እንጂ በእናቴም እመኑ አላለም፡፡ (ዮሐ. 14፥1፡6)፡፡ ስለዚህ በማርያም ነው ወደ አብ የምንደርሰው የሚለው ትምህርት ዓይን ያወጣ ክህደት ነው፡፡

ከሁሉም የሚያሰዝነው ደግሞ “ለቃል ርደት ለሥጋም ዕርገት ዐይነተኛዪቱ ምክንያት እመቤታችን ብቻ መሆኗ በውል መታወቅና መታመን አለበት፡፡” የሚለው አነጋገሩ ነው፡፡ ለቃል ርደት ምክንያቱ እግዚአብሔር እኛን የወደደበት ታላቅ ፍቅሩ እንጂ ማርያም አይደለችም፡፡ ማርያምማ ለዚህ ታላቅ ሥራ እናት ሆና እንድታገለግል ተመረጠች እንጂ ለቃል ርደት መንሥኤም ምክንያትም እርሷ አይደለችም፡፡ ምክንያቱ የእኛ ፍቅር መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት አድርገው የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትም ይመሰክራሉ “ፍቅር ሰሐቦ ለወልደ አምላክ እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት” የአምላክን ልጅ ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው” በማለት፡፡ እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ቃልን እንዲወርድ ያደረገችው በኋላም ሥራውን ከፈጸመ በኋላ እንዲያርግ ያደረገችው ማርያም ናት እንዴት ይባላል? እውን እንዲህ ያለው ሰው ጤነኛ ነው ትላላችሁ? እንጃ!      

ማነው ታዲያ ይህን ከሓዲና መናፍቅ ከሶ ወደሊቃውንት ጉባኤ የሚያቀርብልንና የወንጌልን እውነት በመናፈቁ እንዲጠየቅልን የሚያደርግ? የሚገርመው በዚህ ዘመን መናፍቅ የሚያሰኘው ይህን ውሸት መቃወም እና እውነቱን መጽሐፍ ቅዱስ በሚያስተምረው መሠረት መግለጥ ስለሆነ ኃይለጊዮርጊስን በመናፍቅነት የሚጠይቀው አካል የለም፡፡ ኃይሌም ይህን ሁሉ ኑፋቄ ክህደት ተናግሮና ሕዝብን አሳስቶ ከሳሽና ወቃሽ ሳይኖርበት ዘና ፈታ ብሎ ይኖራል፡፡  

ለሁሉም ኀይለ ጊዮርጊስ ከደብረ ብርሃን ጀምሮ እስካሁን የምታሳድደው፣ የምትጠላውና በሁሉ ነገር ከማርያም አሳንሰህ የምታየው ጌታ ይወድሃልና በሰጠህ የንስሓ ዕድሜ ከአምልኮተ ማርያም ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር ተመለስ፡፡ ጌታም ምሕረትን የተሞላ ነውና እንድትመለስ ማስተዋልን ይስጥህ፡፡

ከመምህር አዲስ      

39 comments:

 1. ማንም የኦርቶዶክስ አማኝ ድንግል ማርያም ከልጇጋር አምልኮ እና ስግደት ይገባል የሚል የለም ለሷ የፀጋ ስግደት እንደሚገባት እናውቀለን ለጌታ ግነ የሚገባውን የአምልኮ ስግደት እንሰግድለታለን እንዲህ እያላችሁ አታምታቱ

  ReplyDelete
 2. I had no Idea this web page was pentecost propaganda section.
  Thanks for coming clean.

  ReplyDelete
 3. እግዚኦ…………ከማለት ውጪ ምን ይባላል! Shame on you Haile! በጣም አሳፋሪ ነው፡፡ አንገትን የሚያስደፋ! ይኼ ሰውዬ መጽሐፍ ቅዱስ የለውም! እርግጠኛ ነኝ አንብቦም አያውቅም! ኧረ ጉድ! ኧረ ጉድ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቶ ናሆም አርያስላሴ፦ ለምን እጅህን ከጭንቅላትህ ላይ አላደረግህም ነበር እግዘኦ ስትል? ከሳሽና ዋልጌ የሆንህ አንተና ይሔ ልቦለድ ለመሆን ተማኒነት የሌለው ጽሑፍ ፀሐፊ ነኝ ባዮ የጨለማው አዲስ እብድ ውሾች ናችሁና በውሾት እዚህም እዛም ትናከሳላችሁ። የኛ የሾም ኦን ዩ ግኝት ባለቤት ለምን በራስህ አታፍርም? ምክንያቱም አማኝ ባልሆናችሁበት እምነት ሳታውቁትና እውነት ሳይኖራችሁ የመንደር ወሬ የምትነዙ በመሆናችሁ። አጭበርባሪነት የጽድቅ መንገድ አይደለምና አንተው በተግባርህ አንገትህን ድፋ።

   Delete
  2. አቶ ዳ-ሞት
   የመንደር ወሬ ነዉ ያልከዉ? ይሉሽን ባለሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ አሉ፡፡ አንተ ለመሆኑ ምን ሞራል ኖሮህ ነዉ ለሃይለጊዮርጊስ ጥብቅና የቆምከዉ? ጭፍን ጥላቻስ የት ያደርስሃል? ጭንቅላትህ የሚያስብ ከሆነ የተባለዉን ነገር ለመቃወም ጠቢብ መሆን አይጠይቅም፡፡ አንተ ኦርቶዶክስ ራሱ ምን እንደሆነ አልገባህም፡፡ ግንብ ስሞ በመመለስ ብቻ ገነት የምትገባ ከሆነ ተሳስተሃል፡፡ ንስሃ ግባና ወደ አዳኙ ጌታ በእምነት ቅረብ፡፡ ተረት ተረት የትም አያደርስም፡፡

   Delete
  3. ለanonymousFebruary 6,2015 at 10:08 am
   ወንድሜ፦ ይሔ በጨለማ ያለ የራሱ የሆነ የእምነት መገለጫ የሌለው፤ እንደ ዝንብ እዚህም እዛም የሚቅበዘበዝ የአቶ አዲስ እንቶ ፈንቶ የአለም ርዕሰ አንቀጽ አይሉት ስድ ንባብ የመንደር ወሬ መባሉ ያሳበደህ ትመስላለህ። ግን ምንም ማድረግ አይቻልም። እውነትን ለሚያጣምም፣ የተባለውን ቆርጦ ያልተባለውን ለሚቀጥል፣ ካለ እምነቱ ገብቶ የአማኞችን እምነት ለሚበጠብጥ፣ ሳያውቅና ሳይረዳ አዋቂ መስሎ ወተቱን ለሚያጠቁር፣ ለእንክርዳዴ መዝሪያ ቦታ ከለከለኝ ብሎ ስለእምነቱ በጽናት የቆመውን ለሚያብጠለጥልና በሐሰት ለሚወነጂል፣ በአጠቃላይ የክርስቶስ እውነትና የክርስቶስ የሆኑት እንዳይገለጡ ለሚያንቋሽሽና ለሚያጥላላ የጠላት ሰይጣን መልዕክተኛ የሆነው የአቶ አዲስ ጽሑፍ ተብየ ከመንደር ወሬነት ውጭ ሌላ መጠሪያ የለውም። አቶ አዲስ ለምን እውነተኛ ከሆኑ የጸሐፊውን ጽሑፍ ሳይቀናንሱና ሳቆራርጡ ሙሉውን ከራሳቸው ጽሑፍ ጋር አታች አድርገው አላቀረቡትም? "ይሉሽን ባልሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ አሉ" የሚል ተረት ይሁን አባባል አስቀምጠሀል። ስለኔ ከሆነ ምን እንደሚባል መናገር ነው። ግን ደግሞ ከዳሞትነቴ ውጭ አታውቀኝም። በበውሸትና በሐሰት ስም አጥፊና ከሳሽ መሆናችሁ እንደሆን ሰው ሳይሆን ይህ ብሎጋችሁ የተሸከማቸው ጽሑፎቻችሁ ምስክሮች ናቸውና የፈለግኸውን ማለት ትችላለህ። ምን ሞራል አለህ ላልከው ከእውነትና ከንፁሐን ጋር ለመሆን ሞራል የሚባል አያስፈልግም። ሞራል በስሜታዊነት የሚገለጥ የእናንተ የአለማዊያኑ መገለጫ ነው። ለጠቀስከው ግለሰብ ጥብቅና የሚቆመው ከማን በፊት የሚያምነው እግዚአብሔር ነው። ከእግዚአብሔር በታች ቤተክርስቲያን ልጇ ነውና እናንት መናፍቃን የእውነት አሳዳጂና ተቃዋሚዎች ስለልጄ አይመለከታችሁም መልካም ሰራ መጥፎ የምናገረው እኔ እንጂ እናንተ አይደላችሁም ብላ ጥብቅና ትቆማለች። ሌላው ጭፍን ጥላቻ የት ያደርስሃል የሚል ቋንቋ ተናግረሃል። ምንድነው ጭፍን ጥላቻ ማለት? ይሔ ፓለቲካና የአለም ኑሮ አይደለም የምንናገረው። ይሄ ጽድቅ የሚገኝበትና የዘላለም ሕይወት የእግዚአብሔር መንግስት የሚወረስበት የእምነትና የእውነት ንግግር ነው። ስለእምነት ደግሞ ከዛም ከዚህም፣ ማጠጋጋት ማቀራረብ፣ ማቻቻል ማጣጣም የሚባል ምድራዊ አስተሳሰብ አይሰራም። እውነትን እውነት ሐሰትን ሐሰት እንላለን ሳናወላውል ሳንጠራጠር። ሌላው ለመቃወም ጠቢብ መሆን አያስፈልግም የሚል አስተሳሰብ ተናግረሀል። በዚህ ንግግርህ ከላይ ጭፍን ጥላቻ የሚለውን የራስህን እሳቤ የምትቃረን ይመስላል። ለሁሉም ጠቢብነት ወደእውነት አያቀርብም። ለመቃወም ጠቢብ መሆን አያስፈልግም ላልከው እውነት አይመስለኝም ። አለም ክርስቶስ ከተቃወመችባቸውና ከምትቃወምባቸው አንዱ በጥበቧ ነው። ከፈለግህ መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ ነኝ ስላልክ ፈልግና አግኘው። አንተና መሰሎችህ መናፍቃን ጥበበኛ ነን እያላችሁ ነው ቤተክርስቲያንና የክርስቶስን አምላክነት እንዲሁም የክርስቶስ የሆኑትን ሁሉ ከመጽሐፍቅዱስ እውነት ወጥታችሁ የምትቃወሙት። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖታችን በእምነት ሰይጣንና የእርሱ የሆኑትን አጋንትንና ስራዎቻቸውን ትቃወማለች እንጂ ጠቢብ በመሆን አይደለም። ኦርቶዶክስ ምን እንደሆነ አልገባህም የሚል ገለፃ በጥበብህ ይሁን በምን እንደተገለጠልህ ሳታብራራ ደምድመሀል። በአጭሩ የምነግርህ ኦርቶዶክስ ምን እንደሆነ ይግባኝም አይግባኝም አንተ መናፍቁ እንድትመሰክርልኝ አልጠብቅም። ምክንያቱም አንተ የኦርቶዶክስተዋህዶ እምነት አማኝ አይደለህምና ነው። ኦርቶዶክስ ማለት ምን ማለት እንደሆነም ለአንተም ሆነ ለመሰሎችህ መናፍቃን መናገር አያስፈልግም። ምክንያቱም እውነትን ላመስማት አውቃችሁ ተኝታችኋልና ነው። ሌላው የአጣጣልህ፣ የተቸህ፣ የነቀፍህ፣ ያሳፈርህና ወዳጆችህን በአዳራሻችሁ መድረክ በኮመዲያንነትህ ያዝናናህና በሳቅ የአስፈነደቅህ መስሎህ " ግንብ ስሞ በመመለስ ብቻ ገነት የምትገባ ከሆነ ተሳስተሀል" የሚል የዝበታ አስተሳሰብ ገልፀሃል። አይ ወንድሜ ብታስተውል ኖሮ በመጽሐፍ " ዘባቾች " የሚለው ሃይለቃል የተነገረው እንዲህ አይነቱን ንግግርና አስተሳሰብን ስለምታደርጉ ነው። ለሁሉም እኔ የምስመው በአለት ላይ የተገነባውን ግንብ እንጂ የአንተን በአሸዋ ላይ የተሰራ ግድግዳ አይደለም። 36 ዘመን ደም ይፈሳት የነበረችው ሴት የልብሱን ጫፍ እንሿን ብነካ እድናለሁ ብላ ብትነካው እንደተፈወሰች ያው አንባቢ ስለሆንህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈልግና ተረዳ። እንዲሁም በሕንፃ ቤተክርስቲያን ክርስቶስ አለና የመሠረታትም እሱ ነውና የተቀደሰችውም በክርስቶስ ስም ነውና የሚነገርባትም ክርስቶስና የሱ የሆኑት ናቸውና ግንቡን አፈሩን አውደምህረቱን በፍቅርና በእምነት ይህ የእግዚአብሔር ቤት ቅጥር ነው በማለት እስም እሰግዳለሁ። በመጽሐፍ እንዲህ ተብሏል "ለእግዚአብሔር በተቀደሰው ተራራ እሰግዳለሁ " ተብሎ። ቤተክርስቲያንን የምስመውም ወይም የምሳለመውና የምሰግደው ገነት እገባለሁ ተብሎ ሳይሆን ስለሚገባ ነው። ይሄን በማድረግም በረከተ ነፍስ በረከተ ስጋን በእምነት እናገኛለን። እንግዲህ ሰይጣን ሆይ አንተ በእውነት ላይ ዘባች ሁነህ ቀጥል ቤተክርስቲያን ደግሞ በእምነት እውነትን ትተገብራለች። ሌላ የተናገርኸው ንስሃ ግባና ወደ አዳኙ ጌታ ቅረብ የሚል ነው። ለመሆኑ ንስሃ ማለት ምን ማለት ነው? ንስሃ መግባት ማለትስ ምን ማለት ነው? ንስሃስ የሚገባው እንዴት ነው? ወደ አዳኙ ጌታ በእምነት መቅረብ ማለት ምን ማለት ነው? በእምነት የምንቀርበውስ ወደየትኛው ጌታ ነው? አንተና ወገኖችህ መናፍቃን ለምትገዙለት የዚህ አለም ገዠ ወደተባለው ሰይጣን ነው ወይስ ፈራጂ በሆነው የጌቶች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ? አዎ አልፋና ኦሜጋ፤ ኤልሻዳይ ወደሆነው የቅዱሳን ወዳጂ አምላክና ፈራጂ ወደሆነው ወደ ጌታ ኢየሱስ ዕለት ዕለት ስለ ሀጢያታችን ንስሀ መግባት ያስፈልጋል። በመጨረሻ ተረት ተረት ለምትለው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተረት ተረት ከሆነ ለአንተ ይሁንልህ ከማለት ያለፈ መልስ አያስፈልግም። ምክንያቱም እውነትን ለመቃወም አንዴ ወስነህ በትእቢት ማማ ላይ እራስህ አውጥተሀልና ነው።

   Delete

  4. @ዳሞት
   ካንተ ጋር መግባባት አይቻልም፡፡ ቅዱስ ጳዉሎስ ጌታ ሳይገለጥለት የነበረዉን አይነት ሰብዕና ያለህ ትመስላለህ፡፡ እዉነተኛ ክርስቲያኖችን ሳታዉቀዉ እየተቃወምክ እግዚአብሔርን የምታስደስት የሚመስልህ ከሆነ የመዉጊያዉን ብረት ብትቃወም ባንተ ይብስብሃል የሚለዉ ላንተም ይሰራል፡፡ ከ1600 ዓ.ም በፊት በነበረዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተምሮ ሁላችንም እንስማማለን፡፡ ከዚያ በኋላ ሰርገዉ በገቡት የምንፍቅና ትምህርቶች ግን ፈጽሞ ልንግባባ አንችልም፡፡
   ወንድሜ እስኪ የቤተክርሲቲያንን ታሪክ አጥና፡፡ ትናንት የተፈጠረችዉ አርሴማ የጌታን ቦታ ወስዳ በምትመለክበት አገር፣ አይ ይኼ ነገር ትክክል አይደለም፤ ቤተክርስቲያናችን በጊዜ ሂደት ሰርገዉ በገቡ እንግዳ ትምህርቶች ተልዕኮዋን(ወንጌል መስበክን) ዘንግታ ወደ ሌላ መስመር ገብታለችና መታደስ አለባት ማለት ለምን አቧራ ያስነሳል?
   ለምን ሚዛናችን ተዛባ? ጩኸቴን ቀሙኝ እንዲሉ እናንተ ለአርባ አራት ጌቶች የምትንበረከኩት መናፍቅ ሳትባሉ እኛ የተሰቀለዉ ክርስቶስ ብቻ ነዉ እዉነተኛዉ አምላክና አዳኝ የምንለዉ መናፍቅ እየተባልን መብጠልጠላችን ለምን ይሆን?
   ወንድሜ የማይጥምህን አስተያየት የሚሰጠዉን ሁሉ የሌላ እምነት አራማጅ አድርገህ ከመፈረጅ ለምን ወደራስህ አትመለከትም? አጼ ዘረያዕቆብ በጉልበት ባስገባቸዉ እንግዳ ትምህርቶች ተኮፍሰህ ከምትኩራራ ለምን እዉነተኛዋ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን አስተምሮዎች ምን እንደነበሩ መጻህፍትን በመመርመር አትረዳም?

   Delete
  5. ለanonymous February 7,2015 at 7:47am
   ወንድሜ፦ እንዳልከው አንተ ከቤተክርስቲያን ጠላት ጋር ሆነህ የቤተክርስቲያኗ እምነትና ስነምግባር ሳይኖርህ በውሸት ቤተክርስቲያንን ጠቅሰህ ነቀፍና ሐሰተኛ ትምህርትን ትናገራለህ። እኔ ደግሞ አንተ ከክርስቶስ ቤተክርስቲያን ወገን አይደለህምና እውነተኛውን የክርስቶስ ቃልም ታጣምማለህና በእምነት ስለ እምነቴ እቃወምሀለሁ። እኔ የክርስቶስ የሆኑትን እውነተኞችን እቀበል አከብራለሁ። አንተ ደግሞ እንደጠቀስከው ሐዋርያ በሳኦልነቱ ዘመን ይፈጽም እንደነበረው የክርስቶስ የሆኑትን በሰይጣናዊው አንደበትህ ታሳድድ ፣ ታዋርድና ታቃልላለህ። ስለሆነም ልንግባባ እንደማንችል የታወቀ ነው። አንተ ክርስቶስን በፍጡር ተርታ አስቀምጠህ ስለኔ ይለምንልኛል ትላለህ። እኔ ቤተክርስቲያንም መጽሐፍ ቅዱስም አምላክ ፈራጂ ለሁሉም እንደ እምነቱና ስራው ዋጋ ከፋይ ነው ብለው ያስተምሩኝ ይነግሩኛል። ስለሆነም እንዳልከው መግባባት አንችልም። አንተ በትቢት ተወጥረሀልና ለመስማትና ለመዳንም አትሻምና፤ ክርስቶስ የሰጠንን እምነታችንን በነፃነት እንዳንፈጽም ካለቦታህ ገብተህ በሐሰት እየከሰስህ ጥላቻን ትዘራለህና መቸም አንግባባም። አጠቃላይ መንገድህና መንገዴ አይገናኙምና መግባባት አይቻልም። እምነት ከዚህም ከዛም የሚባል ነገር የለውም። በአመኑበት ቤት ፀንቶ መቆም፤ ከማያምኑበት ቤት ደግሞ ውልቅ ብሎ መራቅ ነው ትክክለኛው ውሳኔ። የመውጊያውን ቀስት ብትቃወም ለማን እንደሚብስበት ተግባርህና አንደበትህ እራሱ ይመሰክርብሀልና አንተው ወደ ልብህ ተመለሥ። ከ1600 ዓ.ም በነበረው አስተምሮ እንስማማለን ነው ያልከው? ለመሆኑ አንተ እድሜህ 2015 ነውን ከ1600 ዓ•ም በፊት ስለነበረው ለማውራት የተንጠራራኸው? አትዋሽ አትዘላብድ ወንድም! ክርስቶስ ዛሬም ነገም ያውነውና የኦርቶደክስ ተዋህዶ ትምህርቷም እምነቷም አንድ ነው። መሰሎችህን የቤተክርስቲያ ጠላቶች የነበሩትን እንክርዳድ በታኞችን ለማዘከር ይመስላል 1600 የገባኸው።
   ወንድሜ ያልተፃፈ ከምታነብና ከምትጽፍ ብትጠይቅና ብትማር መልካም ነበር ግን አንድ ጊዜ አዚም ተደረገብህና ለመባረክ ሳይሆን ለመረገም ፈጠንህ። ቤተክርስቲያን ቅድስት አርሴማን ታከብራታለች እንጂ በአምላክ ናተ ብላ በክርስቶስ ቦታ አልተካቻትም። አንተው አምላክ አድገሀት ከሆነ እራስህ ታውቃለህ። ቤተክርስቲያንንና ልጆቿን በሐሰት አትክሰስ። ይሔ ሰረገ አሰረገ የምትለው ያንተው እንክርዳድ ካልሆነ ነገር ሁሉ ተራ የተለመደ የቁራ ጩኸት ነው። መዘንጋትና ማዘናጋት የአንተና የወገኖችህ የመናፍቃኑ የክርስቶስ ወንጌል
   መቃወሚያ መሳሪያዎቻችሁ ናቸው እንጂ የቤተክርስቲያን አይደለም። ደግሞ ነገር እንዲያምርልኝና አራዳ ነኝ ለማለት ይመስላል ለምን አቧራ ያስነሳል ተባለልኝ። ለምን የአቧራውን መነሳት የዘመኑን አኒሜሽን ጨምረህ አትገልፀውም ነበር የአሮጊቶቹ ተረትህ እንዲዋብልህ።
   ስለሚዛን ካነሳይማ የተዛባባው የአንተው ነው ከዚህም ከዛም አየረገጥህ የምትወዛወዝና የምትጋደደው። የጩኸቴን ቀሙኝ ተራች፦ ለመሆኑ አርባ አራቱ ጌቱች እነማን ናቸው? ለምን አትዘረዝራቸውም?መንበርከክ ላልከው ግን ለክርስቶስ ለሆኑት ሁሉ ክብር ይገባችኋልና በማለት እንበረከካለን። ተቃጠል ሰይጣን። የክርስቶስን ስም ስለጠራህ እውነተኛ መሆንህን አያመለክትምና መናፍቅ ትባላለህ። ሰይጣን ኢየሱስን አውቀዋለሁ ስላለ የእግዚአብሔር መላክ ሊባል አይችልም።
   የማይጥም ባለሙያ የሚባለ ቋንቋ ያንተው ነው። ለእኔ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ያልሆነ አስተምሮና ቅዱሳንን የሚጠላ ሁሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትተከታይ አይደለምና ቤተክርስቲያንን ትቶ መውጣትና ከሚመስሉት ጋር መጨር ነው ያለበት። ይሄ እራስን የመመልከት ጉዳይ ሳይሆን የእምነትና የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው። አጼ ዘርያቆብ አጼዘርያቆብ ትላለህ ደጋግመህ፤ ማን አስገደደህ እውነትን አልቀበልም ከሆነ ነገርህ መብትህ ነው። ቤተክርስቲያንን ለኦርቶዶክሳውያኑ ተወት ነው። አጼ ዘርያዕቆብም ጥንት እንጂ ትናንት ወይም ዛሬ አይደለም ያለው። ዛሬ ደግሞ ስለ ብዙ መጽሐፍቶች አወራህ። ይሄ ነው ሚዛንህ መዛባት ማለት። ለሁሉም መጽሐፍት የምትሏቸው እንክርዳዳችሁን የቤተክርስቲያን ለማስመሰል በሽፍን ስዕል ጋርዳችሁ የጻፍችኋቸውን የምንፍቅና መጽሐፍቶቻችሁን እንደሆነ ግልጽ ነው። ግን እግዚአብሔር አጋልጦባችኋልና ማንም አይቀበላቸውም። ደህና ሁን ወንድሜ።

   Delete
 4. ይእ መናፍቅ በመጨረሻዉ ዘመን ይነሳል የተባለዉ ባለ666ቱ ማእረግ የቀድሞዉ ዘንዶ ነዉ። ኤረ አንቴ መናፍቅ እዝቡን በሀሰት ትምእርት አታወናብድ!!

  ReplyDelete
 5. May God Bless you and open the Heart of the Orthodox Church leaders to accept this truth and preach the gospel for the followers.

  ReplyDelete
 6. Anseo segeha hadere laleha .segawan anseto aderebat blend lemen enzemaralen radiya????

  ReplyDelete
 7. Nice Addis you are coming to our Protestant Religion. We will help you out.

  ReplyDelete
 8. OMG this is what devil really wants to be. To hide the salivation through christ and to build the image of saints who are in heaven now. Once they receive their prize, it is non-biblical to give them such fake names.

  ReplyDelete
 9. Mr Damot! እርሰዎ እና የእርሰዎ ተከታዮች እንደምትሉት ከሆነ ወንገል በማእምነት ስልጡን በሆኑ ደብተራዎች በየመቃብር ሰፌራዎች የሚፃፍ ይመስላቸዋል። እዉነቱ ግን ከዚ የራቀ ነዉ።በነብያትና በሀዋሪያት የተፃፌዉ የእግዚሃብሄር ቅዱሰ ቃል ወደ ኢትዮጵያ ሰገባ በሀገሬ ደብተራዎች እርሰዎን ጨምሮ በኑፋቄና በክእደት ቃላት እንደተበረዘ አለም የምትመሰክር አቅ ነዉ። ከነዚእ ኑፋቄ ቃላት የጌታ እናት ማሪያምን ሰትፌልጉ ፅዮን፣ ማር ፣ያም፣በትር፣መርከብ፣ ተራራ፣ ብርሌ፣ መሰንቆ፣ክራር፣ በገና ፣አበባ፣..... ምን የማትሉት ነገር አለ?ወንገል ግን የምለዉ እሷ የጌታ እናት ጌታን ለተቀበሉትም ለእና ዮሀንሰም ለእኛም እናት ናት፣ ከፍጥረት ሁሉ ሳይሆን ከሰቶች መካከል ብፅእት፣ ከልዷ ጋር ክርክር የምገጥማት ሳይሆን እርሱ የምለዉን የምትቀበል እናትን ባሻችዉ መንገድ አንድምታ በምትሉት በክእደት መፈልሰፍያ መሳሪያ የዚች ቅድሰት እናት ስም በጠፍና በወዳቅ ቁሳቁሶች እያሰመሰላችዉ ሰሟን ለሰድብ፣ለነቃፋ፣ ለመወናበጃ ሰታደርጉ ቆይታቸዋል። ይእ ፀረ ወንጌል አንድምታ ትርገሜ ለብዙ ምእመናን ወድቀት ምክንያት ሆኖ ቆይቷል፤ አሁን ግን የክርሰቶሰ ትክክለኛ ወንገል ምን እንደሆነ እዝቡ ሁሉ አዉቀዋል። ደብተራዉም ሆኔ አንቴ ዉሸተኛዉ አሰተማሪም ዉሸታችዉ ተነቅቶባቸዋልና እረፉ። እዉነተኛዉን ወንገል ለሰተማረን ለእግዚሃብሄር ክብር ይሁን። አሜን!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous February 5,2015 at 3:12am.
   አቶ anonymous በመጀመሪያ ክህደትና ሐሰተኛ ውንጀላ ቢሆንም የጻፍከው አስተያየት ተብየ ከመጻፍህ በፊት ቃላት አስተካክለህ ለመጻፍ ተለማመድ። ጭቃ እንደሚረግጥ እዛም እዚህም አትዛክር። የጻፍከውን ተመልሰህ ብትመለከተው ምን እያልክ እንደሆነ የምታውቅና የሚገባህም አይመስለኝም። ስለኦርቶዶክስ የወንጌል አስተምሮ እውነተኛነት ከአንተ ከሰይጣኑ ፈረስና ከግብር አበሮችህ መናፍቃን ምስክርነት እንደማይገኝ የታወቀ ነው። ምክንያቱም አባታህ ዲያቢሎስ ሐሰተኛና ሐሰት ተናጋሪ የእውነት ተቃዋሚ
   በመሆኑ ነው። እስቲ በናትህ ንገረኝ ማነው በነቢያትና በሐዋርያት የተፃፈውን የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ኢትዮጵያ ያስገባው? መቸ ነው የገባው? ደርሶ አዋቂ መምሰል ባዶነትህን ነው የሚያሳብቅብህ። ደሞ እየበረዛችሁ አልክ! እየበረዛችሁና እውነትን እያቃለልህ ያለኸው አንተው እኮ ነህ? ምንም እንሿን ከመጽሐፍ ቅዱሱ እውነተኛ መልእክ የወጣችሁና የካዳችሁ ቢሆንም እስቲ ዘወር ብለህ 66ቱ እያላችሁ የተሸከምኸውን የተለያዮ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍቶቻችሁን በቅንፍ ውስጥ የተቀመጡትን ቃላቶች ተመልከት። ያን የምታደርጉት እውነትን ለመቃውምና ለመበረዝ እንደሆነ ግልጽ ነው። ቀላል አማረኛ እየተባለ ካለጠያቄ እያሳተማችሁ በእርዳታ ስም የምትበትኗቸው የአዲስ ኪዳን ተብየ መጽሐፍቶቻችሁስ ምስክሮች አይደሉም እንዴ እውነትን የምትበርዙ እናንተው ስለመሆናችሁ። ደግሞስ የሚያስተምረው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንጂ ቀላል የሚባል ፊደል ነውን? ሰሞኑን ቮድካና ሻምፓኝ እንደምትጨልጡ ገሀድ ወጥቷል። ከዛም ዘማዊነታችሁ። አሁንም አንተተበረዘ እያልክ የብርዝ ሱሰኝነትህን አደባባይ ለማውጣት የፈለግህ ነው የምትመስለው። ለሁሉም ቤተክርስቲያን የተበረዘ የሚባል ነገር የላትም። ያላት ንፁህ የክርስቶስ የእውነት ወንጌል ነው። ቤተክርስቲያን ያመነችበትን እምነቷን ሳትጠራጠር፣ ሳታፍርና ሳትደብቅ በግልጽ ታከናውናለች። እንዳንተ ባለመነችበት ቦታ አትገኝም የሌሎችንም የእምነት ተቋም አትበጠብጥም። በዚህ ብቻ እንሿንኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን እውነተኛና
   የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለመሆኗ ማረጋገጥ ይቻላል። ሌላው የተናገርከው "በጠፋና በወደቀ ቁሳቁስ" የሚል አስተሳሰብ አንፀባርቀሀል። አይ እውነትና የመጽሐፋን መልክት አዋቂው! ምነው አማኝነትህና አዋቂነትህ በእውር ድንብር አሉባልታና ውሸትን ማራገብ ሆነ? ለምን በልገባህና ባልተረዳኸው ነገር ላይ ያልተገባ ነውረኛ ንግግርን ተናግረህ ሐጢያትን በራስህ ከምታከማች ጠጋ ብለህ የቤተክርስቲያኗን እውነተኞቹን መምህራኖቿን ይህ ለምን እንደዚህ ተባለ ብለህ አትጠይቅም። አለማወቅህን መናገርህ እኮ ሐጢያት አይደለም። ሐጢያት የሚሆነው ሳታውቅ ሐሰትንና ነቀፋን መናገርህ ነው። ለሁሉም በምሳሌ የመናገርና ማስተማር አንተ እንደምትለው መበረዝ ወይም ያልተገባ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። በመጽሐፍ እንዲህ ተብሏል "አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ"ተብሎ። ለምሳሌ ክርስቶስ በበግ ተመስሏል እንዲህ ተብሎ " እነሆ የአለሙን ሐጢያት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ" ተብሎ ዮሐንስ 1፤ 29። ሌላም "እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ገበሬው አባቴ ነው" ተብሏል ዮሐንስ 15፥1። በነዚ በሁለቱ ምሳሌያዊ መልክቶች ክርስቶስ በበግና በወይን ግንድ ተመስሏል። ነገር ግን ክርስቶስ በግም ግንድም ነው ማለት አይደለም። እንዳንተ እንደመናፍቁ አባባል ከሆ ክርስቶስ በሚጠፋ በግና በቁሳቁስ ተሰድቧል፣ ተቃሏል እንዲሁም ማወናበጃ ሆኗል ማለት ነው። እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ወንድሜ። ሌላው እመቤታችን የተጠራችባቸውን ምሳሌያዊ ንግግሮች መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም ለማለትና ወንጌል አይደለም ለማለት ሞክረዋል። ያሳዝናል ሳያውቁ ያወቁ መስለው መዘላበድዎትና በክህደት ጦር እራስዎን መውጋትዎ። ምሳሌያዊ ንግግሩ ስለእመቤታችን መሆኑ ካልገባዎት ለምን ብለው መጠየቅ ነው እንጂ በመጽሐፍ የሌለ ለማስመሰል መሞከር ግን አላዋቂነት ነው። ሌላው ማርያም የሚለውን የስሟን ትርጓሜን ለማብራራት የተገለጡትን ሁለት ቃላቶች ለያይተው ለማወናበድ ማርና ያም ብለው አስቀምጠዋል። ሌላው ደብተራ ደብተራ እያሉ ማንን ደብተራ እንደሚሉት ባላውቅም ደብተራን ወንጌል ፀሐፊ ለማስመሰል ሞክረዋል። ወዳጄ ወንጌል አንዴ በሐዋርያትና በነቢያት አንዴ ተጽፏል። ደብተራ በምትለው በየመቃብሩ የተጻፈ ወንጌል የሚባል በእናንተ አዳራሽ ካለ ተናገር እንጂ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የለም። ወንጌልም የሚሰበክ፣ የሚነገር፣ የሚመሰከርና የሚገለጥ ሆኖ አንዴ የተሰጠ እንጂ ይሔ እንዲህ ይሁንና በቀላል ቋንቋ እየተባለ የሚፃፍ አይደለም። ሌላ የትናገርከውና የነቀፍከው አንድምታና ትጓሜን ነው። ከሰይጣን የሚጠበቅ ነውና አንተም የሰይጣን አገልጋዩ ወደ ክርስቶስ ወንጌል የሚያደርሱትን መጽሐፍት ብትቃወምና ብትነቅፍ አይገርምም። ምክንያቱም አንድምታንም ትርጓሜንም ስለማታውቃቸውና ለእውነት ጠላት በመሆንህ ነው። ህዝቡ ሁሉ የክርስቶስን ወንጌል አውቋል ላልከው ከሆነ መልካም ነው። ግን ወንጌል ማለት ምን ማለት ነው? ማወቅስ ማለት እንዴት ነው? ማወቅስ በራሱ ሊያፀድቅና ሊያድን ይችል ይሆንን? ነገር ግን እንዳንተ አሉባልታና ስለማያውቁት እምነት በውሸት መዘላበድ ከሆነ የክርስቶስን ወንጌል አውቀዋል የሚያስብል ይሔ አያድንም ያጠፋል እንጂ። ከዛም ትቀጥልና ደብተራው የምትለውንና እኔን ተነቅቶባችኋልና እረፉ ትለናለህ። ደብተራው የምትለውንግለሰብ ስለማላውቀው ስለሱ አንተ ታውቃለህ። እኔ ግን በመጀመሪያ ማወቅ ያለብህ አስተማሪ አለመሆኔንና በእምነት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታይ መሆኔን ነው። ስለሆነም ዋሽተሀልና ፈቃደኛ ከሆንክ ከስህተትህ ታረም። ተነቅቶባችኋል እረፍ ለምትለው መልዕክቱ አንተን አስመሳዩንና መሰሎችህን ነው የሚመለከተው። ምክንያቱም አሉባልተኛ የክርስቶስ ጠላቶችና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት አማኞች አለመሆናችሁን በተለያዩ ጽሑፎቻችሁና ተግባሮቻችሁ ታውቃችኋልና ነው። በመጨረሻ "እውነተኛውን ወንጌል ላስተማረን ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን። አሜን" ብለህ ጨረስክ። አይ ወጉ አይቅረኝ! ማን ሆንክና! ሰይጣን ጥንቱንስ አዳምንና ሔዋንን የገደላቸው መልካም መስሎ አይደል። ወዳጄ እግዚአብሔር የአንተን፣ የአቶ አዲስንና የመሰሎቻችሁን ውሸት፣ ክስ፣ አሉባልታ፣ ክህደት፣ እውነትን መቃወም፣ ክርስቶስን ማሳደድና የሐጢያት
   ተግባሮችን አያስተምርም። እንዲህ ያለውን ክህደትና መናፍቅነት ያስተማረህ አባትህ ሰይጣን ብቻ ነው። በመጨረሻ አቶ አዲስን በአዳራሽህ እንሿን ደህና መጣህ ወደ ሉተር መርህ ብለህ ተቀበለው። ከዛም የዳንስ አይነቶችን ታሰለጥነዋለህ።

   Delete
  2. ለዳሞት ---
   የምስራች ጆሮ ያለው ይስማ!የቀመስነውን ሰላምና ፍቅር፤ ስላገኘነው ዘላለማዊ ሕይወትና የእግዚአብሔር ልጅነት እንመሰክራለን!ኢየሱስ ጌታ ነው!የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል መዳን ትፈልጋለህ/ሽ ’’ ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤’’እንግዲህ ተወዳጆች ያየነውን የቀመስነው እውነት እንመሰክራለን ኢየሱስ ያድናል!ሰላም ላጣ ሰላም የሚሰጥ!በፍርሃትና በጨለማ ላሉ ብርሃን የሆነ ኢየሱስ ሀሌሉያ!የመዳን ቀን ዛሬ ነው!ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን እንድትመጡ የዘላለም ህይወትን እንድታገኙ መልዕክታችን ይኸው! ’’ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት1፡1ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤’’

   Delete
 10. @DA M O T
  You blindly bark without having a clue of spritual issues. If you are in good health please do not vomit your trash and bullshit idea here. Go to hara tewahodo blog where trash ppl like you are gathered.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous February5,2015 at 7:59 am
   ውድ ወንድሜ በመጀመሪያ የእንግሊዘኛ ችሎታህን አደንቃለሁ። ነገር ግን የእንግሊዘኛ ችሎታህ በአምስት መስመሮች ማቆምህ ትክክል አይደለህምና በሚቀጥለው ብዙ ገጽ እንደምትጽፍ እገምታለሁ። ይሄን ካልኩ በኋላ፤ ብላይድሊ ባርክ ምን ማለት ነው? ጭፍን ጩኸት ወይስ እውር ጩኸት? ነው እውርና ጭፍን የዛፍ ቅርፊት? ከየት ይሆን ይሄን የመሰለ ከትራሽ ሰው ያልተገኘን የቁምነገረኛን ሰው አባባል ያገኘኸው? "ክሉ ኦፍ ስፕሪችዋል ኢሹስ" ምን አይነት ነው እባክህ? የአንተ ስፕሪችዋል ክሉ ለመሆኑ "ትራሽና ቡልሽት" የሚባሉት ቃላት ይሆኑ ይሆንን? ለምን ወንድሜ አሉባልታና ወሸታችሁን፣ ክህደት ጥርጥራችሁን፣ ስድብ ፀያፍ ቃላቶቻችሁን፣ ወተቱን ማጥቆራችሁን ደግ አደረ ጋችሁእንድልህ ትጠብቃለህ? እነዚህ የዘረዘርኋቸው የሰይጣን መገለጫዎች ከሆኑ ለአንተ ክሉ ኦፍ
   ስፕሪችዋል ኢሹስ እኔ እነዚህን አላራምድም ትራሽም አልከኝ ቡልሽት። ሌለው ያልከኝ ያው እንግሊዘኛ መተርጎም ባልችልም እንዲህ ያልከኝ ይመስለኛል፦ ጤናማ ከሆንክ እባክህ ትራሽህንና ቡልሽት ሀሳብህን በዚህ ብሎግ አታስታውክ ወይም አትትፍ ። መልካም አገላለጽ ነው ወንድሜ። እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድም። የትኛውን ሀሳቤን ወይም ንግግሬ በእንደዚህ ያማረ ከመልካሙ የስድ አፍ ከተሰጠው ልጂ በተገኘ አገላለጽ የተወደሰው? ለነገሩ ይሄ የምታሞጋግሰው ብሎግ የተሞላው እንዲህ አንተ በተጠቀምክባቸው ያማሩ ቃላቶች የተጻፉ ጽሑፎች ናቸውና የኔ ሐሳብ አንተ ከተጠቀምክባቸው ቃላቶች ጋር አብረው አይሄዱምና እንዳልከው እዚህ ካንተው የአለም ከተማ መታየት የለባቸውም። በመጨረሻ ዘለህ የት ገባህ ሃራ ተዋህዶናስለብዙ ሰዎች። ወንድሜ ይህ አንተ የቆምህለት ብሎግ የያዛቸውን የጽሑፍ መልክቶችና በሃራ ተዋህዶ የተጻፉ ጽሑፎችህን መልእክቶች አነፃጽርና ማን በአሉባልታ፣ በስድብ፣ በሐሰት ክስ፣ በትችት፣ በፈጠራ ታሪክና ወሬ፣ በሐሜትና በሰይጣናዊ ንግግሮች
   እንደተሞላ ተናገር። መቸም አንተ "ብላይንድሊ ባርክ" ያልሆንህ ነገር ግን "ብራይትሊ ባርክ" ስለሆንህ ትራሽና ቡልሽት ያልሆነ አስተያየት እንደምትሰጥ ነው። አመንክም አላመንክም አንተ ያከበርከው ብሎግ ከሰይጣን ድምጽ ሌላ አንድም የመንፈሳዊነት ሽውታም የለውም። ሌላ ያልከው "ጎ ቱ ሃራ ተዋህዶ ብሎግ ሁየር ትራሽ ፒዩፕል ላይክ ዮ አር ጋዘርድ" ብለሃል። ስለ ንግግርህ እግዚአብሔር ይባርክህ። አዎ እኔ ትራሽ ነኝ። ሌሎችን ግን አንተ ትራሽ ብትላቸውም በእግዚአብሔር ዘንድ ይከብራሉ። በመጽሐፍ እንዲህ ተብሏል በሰው ዘንድ የተናቀ በእግዚአብሔር ዘንድ ይከብራል ተብሏል። ያው መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢና ኢንቴሌክት ስለሆንክ በሰው ዘንድ የተናቀ የሚለውን እንደምታገኘው እተማመንብሀለሁኝ። ሰላም ሁን።

   Delete
  2. @ዳሞት
   መሰሎችህ የተሰበሰቡበት ሃራ ተዋህዶ ብሎግ እያለልህ ለምን እዚህ የእኛን አስተያየቶች እያነበብክ ትበግናለህ መባልህ ሊያናድድህ አይገባም፡፡ ለአህያ ማር አይጥማትም እንደተባለዉ ለአንተ አይነቱ ግብዝ የሚመቸዉ፡ በዘንዶ ስለሚጠበቅ ገዳም፣ ስለ ሰማዕት እከሌ…… ገድል ወዘተ ሲተረክ ስለሆነና ያ ደግሞ በዚህ ብሎግ ስለሌለ ነዉ፡፡ አዕምሮህ ጤነኛ ከሆነ፣ ሁሉንም ነገር የምትጠላበት ምክንያት አይኖርም፡፡
   2ኛ ቆሮንቶስ 4፥4 ላይ “ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።” እንደተባለዉ ግራ ተጋብተህ ከምትዳክር ልብህን ለእዉነተኛዉ ወንጌል ክፈት፡፡ በመስቀል ላይ የሰዉን ልጅ በደል ለማንጻት ከተሰቀለዉ አንዱ ጌታ በቀር አዳኝ እንደሌለ ቃሉ ይናገራል፣ ታዲያ ማንን እንመን ወዳጄ?


   Delete
  3. @ዳሞት
   "በመጀመሪያ የእንግሊዘኛ ችሎታህን አደንቃለሁ። ነገር ግን የእንግሊዘኛ ችሎታህ በአምስት መስመሮች ማቆምህ ትክክል አይደለህምና በሚቀጥለው ብዙ ገጽ እንደምትጽፍ እገምታለሁ። "
   Is the English language unique to your limited mind? You always get timid when people comment in English. how old are you, 5?

   Delete
  4. ለanonymous February 7,2015 at 10:00 am and 1:32pm
   ወዳጄ የበግንሀና አይን የቀላውስ አንተነህ። ለምን ካልከኝ እዚህ ጋ የመለስኩልህ እኔ እያለሁ አልፈህ ከንዴትህ የተነሳ ሃራዘተዋህዶ ገባህ። እነሱ ላንተ መልስ አይሰጡህምና ባትቀባጥር መልካም ይመስለኛል። ለአህያ ማር አይጥማትም ያልከው አቅምሰህ ሞክረሀታልን? ለፈረስ ለበቅሎና ለሌሎች እንስሳትስ ማር ይጥማቸው ይሆንን? ለነገሩ የአህያን ያክል ማስተዋል ቢኖርህ ኖሮስ ቤተክርስቲያንን ባልተቃወምህ ነበር። እራሳቸወን ለክርስቶስና ለእውነት ጃንደረባ ስላደረጉት መነገሩ ሰይጣንን እንደማያስደስተው የታወቀ ነው። ስለሆነም አንተን ከመሰለ ኢአማኒ ስለክርስቶስ እውነትና ቅደዱሳን በእምነታቸው ጽናት ክርስቶስ ስለሰጣቸው ክብርና የእምነት ተጋድሏቸው፤ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ሐይል ስለሰሯቸው ታምራቶች መቸም ቢሆን ይናገራል ተብሎ አይጠበቅም። ወዳጄ፦ የከርስቶስ አምላክነትና እውነት፤ የቀላል የቀዱሳኑ በክርስቶስ ዘንድ ያላቸው ክብርና ቃልኪዳን፤ እንዲሁም የእምነት ጽናታቸውና ስራዎቻቸው ሲነገሩ የማያስደስተው በክሸርስትና የማያምንና ጠላት ሰይጣን ብቻ ነው። የጠቀስከው ጥቅስም ሀሜትና የመንደር ወሬ፣ ሐሰትና ፀያፍ ንግግርን፣ በአጠቃላይ የክፉውን መገለጫ ተግባራትን መተግበርን ወንጌል ነው ብለህ የምታቆለጳጵሰውን አንተን የሚያነብህ ይመስለኛልና ወደ እውነት ተመለስ። ማንን እንመን ላልከው የፈቀድከውን ለኔ አውነት ነው ያልከውን ማመን ነጻ ፈቃድህ ነው። ነገር ግን እምነት ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን በትክክል ተገንዝቦ መከተል እንጂ ይሄ የሰይጣን ማዘናጊ በሆነ አካሄድ ጥቅስ ጠቅሶ በቃላት መዋጋት አያድንም። አዳኝ የምትለውን ቃል ብቻ ተጠቅመህ ምንፍቅናን ለመተግበርና ለመዋጋት ሞከርህ። መላእክትም እንደሚያድኑ በመጽሐፍ ተጽፏል እንዲህ ተብሎ " የእግዚአብሔር መላእክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል " ተብሎ መዝ 33(34)፥ 7። ስለዚህ የመላአክትን አዳኝነት ማመን አለብህ። ስለዚህ አዳኝ እያልክ መናገር ሳይሆን ቃሉ ከተነገረለትና ከተነገረበት አንፃር ተረድቶ ማመን እንጂ በእውር ድንብር መናገር አይደለም። አቶ Broad mind፦ ቋንቋ ለተናጋሪውም ሆነ ለሌላው unique ነው። እድሜ ጠይቀኸኛልና ከአንተ ከፍ ወይም ዝቅ ነው እድሜየ። ለሌላው ድሪቶህ ግን መልስ አያስፈልግም። ደህና ሁን።

   Delete
  5. ዳሞት
   Nobody has time for your long soliloquy. Make it brief & do something else with your life besides posting comments!

   Delete
  6. So, who cares about your speach? Don't worry about my life; just find yiur self instead of talking about others religion. I want certain for you, I am not give you a comment, but I am giving you a respond what you are saying.

   Delete
 11. Adis adis haymanot new temetastemerew temhereten yizeh hed, Orthodox bete krestian yemetamenew lek like teguhan Haile Giorgis endetsafut new,yihenen meqawem mebteh new,ante betekrestian yemetastemerewun anbeben,temhetehen yizeh tereg bel.yante terguame je egna je Orthodox tergum gar selemayihed,egnan orthodox tewahedo amagnochen tewen.le ante nufaqe new,le egna degmo emnet new,ante tehadso enjo orthodox selalhonk ayagebahem

  ReplyDelete
 12. I think as I understood from the above article , there is no presence of God in the orthodox 'Church' thank you for sharing us the truth it is one step to reach to the people who are following anti Christ doctrine and make a decision about their faith. I hope many of us reading the above article make a decision to follow Lord Jesus as savior! Thanks!

  ReplyDelete
 13. ክርስትና በአንደበት ከሚገለጸው በላይ በሕይወት የምንኖረው እውነተኛ እምነት ነው፡፡ አንድ ነገር ማወቅ ይገባናል ከዘላለም ሞት ፍርድ የሚያድነን ወይም ለዘላለለም ሞት የሚያስፈርድብን ክርስቶስን ብቸኛው አዳኝ እንደሆነ ማመን ወይም አለማመን ነው፡፡ አለማመን ማለት ደግሞ በክርስቶስ አዳኝነት በአፍ አምናለሁ ብሎ እንደዚህ ያለ ክርስቶስን የሚያሳንስ ትምህርትን መቀበል ነው፡፡ አንዳንዴ ስለ ኦርቶዶክስ ይሁን ስለሌላው የክርስትና ተቋም ተቆርቁረን ስንቆም ከሰማይ እነዚህ ተቋማት ያሉና የወከሉን ያህል ይሰማናል፡፡ ወንድሜ/እህቴ በሰማይ ያለን አንድ ብቻ ነው፤ ሁሉን ማድረግ የሚቻላው በአብ ቀኝ የተቀመጠው የታረደው በግ የናዝሬቱ ኢየሱስ፤ በእርሱ እመን ትድናለህ፤ ለመሆኑ መዳንህን አሁን አረጋግጠሃል; ካልሆነ እርግጠኛ ለመሆን ቅዱስ ቃሉን (መጽሐፍ ቅዱስን) አንብብ የሚልህን አድርግና እርግጠኛ ሁን፡፡ የዚያን ጊዜ የመንፈስ ፍሬዎችን ታፈራለህ፤ ክርስትና በፍሬ የሚታይ ህይወት ነው፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡

  ReplyDelete
 14. Shame on all Ethiopian Christian all over the world, pastor Tekest, Deacon Habitamu, Tebate, Abazelebanose and others sleeping with married women. Those priests are a carrier of sexual transmitted disease according to CDC. ALL THOSE PRIEST serving churches in U SA.

  ReplyDelete
 15. Why this Tehadiso people don't go to protestant or create their own church if they are not accepting the base for orthodox religion?

  ReplyDelete
 16. Krestosen Metsehaf kedus "ye ma'ezen dengay "new yilal.Dengay sil mesadebu new bante tergum.gen ayidekem yih messale lik bemesenko, be mesobe werk emebetachen yetemedelechew.

  ReplyDelete

 17. እዚህ ብሎግ ላይ የሚወጡ ጽሑፎችን ከሞላ ጎደል እከታተላለሁ፡፡ የሚጠቅመኝንም እይዛለሁ እንዲሁም የማይጠቅም የመሰለኝን እጥላለሁ፡፡ ከጽሁፎቹ በኋላ የሚቀርቡ አስተያየቶች ግን በመርህ እና በመከባበር ላይ የተመሰረቱ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ በቤተ ክህነትም ሆነ በቤተ መንግስት አንድ ሰዉ የሚያምንበትን ነገር ለሌሎች የማስተማርና የመግለጥ ሙሉ መብት አለዉ፡፡ ሰዉ ከምንም በላይ ራሱን ይወዳልና በግድ ተጠምዝዞ ሳይሆን በግል ፍላጎቱ ያዋጣኛል የሚለዉን መንገድ ይከተላል፡፡ በአለም ላይ ያሉ የሁሉም እምነቶች ተከታዮች ቢጠየቁ ለእነሱ የእነሱ ሃይማኖት አንደኛና ብቸኛ ነዉ፡፡ ቁምነገሩ ልክ እነሱ የሚከተሉት እምነት አንደኛ ነዉ ብለዉ እንደሚያስቡት ሁሉ የሌሎችን እምነት ሲያንቋሽሹ ሌላሎች የዚያ እምነት ተከታዮች ምን ሊሰማቸዉ እንደሚችሉ አለማሰባቸዉ ነዉ፡፡ በሌላ አነጋገር እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አይነት የራስ ወዳድነት አባዜ የተጠናወታቸዉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡
  አባ ሰላማ ብሎግ የተሃድሶ እንቅስቃሴን የሚደግፉ ጽሁፎችን ብዙ ጊዜ ያወጣል፡፡ የመቀበል እና ያለመቀበል ነገር የአንባቢዉ ዉሳኔ ነዉ፡፡ እኔ በመረጃ የተደገፉና መጽሃፍ ቅዱሳዊ ትንታኔዎች የታከሉባቸዉ በርካታ ነገሮችን በግሌ ለማንበብ የቻልኩት በዚህ ብሎግ ነዉ፡፡ ያ ማለት ግን ከላይ እንዳልኩት ሁሉም እዚህ የሚጻፉ ነገሮች ሁሉ ጠቀሜታ አላቸዉ ማለት አይደለም፡፡
  ወደዋናዉ ሀሳቤ ስመጣ በዚህ ብሎግ ለሚወጡ ጽሁፎች ድጋፍም ሆነ ተቃዉሞ በጨዋነት እና በሰለጠነ መንገድ መልስ በመሰጣጠት መማማር እየተቻለ አንዳንድ ግለሰቦች ቱግ ብለዉ ወደ ተራ መዘላለፍ ሲገቡ ይስተዋላል፡፡ በመሰረቱ እነዚህ ወፈፌዎች ቅናትና ክርክር ስለተጠናዎታቸዉ ብቻ የግል አመለካከታቸዉን ከመዝራት ዉጭ ስለሚከተሉት እምነት በቂ እዉቀት የሌላቸዉ፣ በተባራሪ በሰሟቸዉ ታሪኮች ላይ ተመስርተዉ የሚኖሩ፣ በመቻቻልና በብዝሃነት የማያምኑ፣ በሁሉም መስፈረት የበታችነት ስሜት ስለሚሟገታቸዉ ብቻ ያልተገባ ነገር ሳይቀር በመናገር ጊዚያዊ ሰይጣናዊ እፎይታ የሚያገኙ ናቸዉ፡፡
  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን የተመለከተ ማንኛዉም ጽሁፍ ይዉጣ፣ ጸሃፊዉም ሆነ ያንን ጽሁፍ ደግፎ አስተያየት የሰጠ ሁሉ አንተ መናፍቅ እየተባለ ይወረድበታል፡፡ ደስ ሲላቸዉም ራሳቸዉን ብቸኛ የቤተክርስቲያኗ ተቆርቋሪዎች በማድረግ ሌላዉ የእንጀራ ልጅ ይመስል ያሻቸዉን ዉርጅብኝ ያወርዱበታል፡፡ በቂ እዉቀት ስለሌላቸዉ ተሳስቷል ብለዉ ያመኑትን ሰዉ ከመምከርና በጥበብ ከመሞግት ይልቅ ተራ የመንደር ስድብ በመስደብ ለማሸማቀቅ ይጥራሉ፡፡ ለነገሩ በኢንተርኔት ተደብቆ ለሚሰነዘር ዘለፋ ቁብ የሚሰጥ አይኖርም፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ሰዎችን መዝለፍ በየትኛዉም ቤተ እምነት እንደበጎ ነገር የሚታይ አይደለም፡፡
  ስለዚህ አንዳንድ ግለሰቦች፣ ከቻላችሁ ቤተክርስቲያንን ወግናችሁ ከምትሳደቡ ይልቅ በመርህ ላይ የተመሰረተ ምላሽ በመስጠት የጨዋይቱ ሳራ ልጆች መሆናችሁን አስመስክሩ፣ ካልቻላችሁ ደግሞ ቢያንስ በአንደበታችሁ ከምትስቱ ዝም በማለት የሚባለዉን ታዘቡ፡፡ ብትሰደቡ እንኳ ስድብን በምርቃት እንጅ በስድብ የምትመልሱ ከሆነ የእናንተ ክርስትና ምኑ ጋ ነዉ?
  ሌላዉ ነገር፣ ሁሉንም የማይጥሙንን አስተያየቶች ለአስተያየቱ መልስ በመስጠት እንጅ አስተያየት የሚሰጠዉን ሰዉ የዚህና የዚያ እምነት አባል ነህ ብሎ መፈረጅ ተገቢ አይመስለኝም፡፡ ጉዳትም አለዉ፡፡ ተሳዳቢዉ እንደ ኦርቶዶክስ አማኝ እየተቆጠረ፣ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ አስታኮ ሃሳቡን የሚሰነዝረዉ የሌላ እምነት ተከታይ ተደርጎ የሚታይ ከሆነ፣ በተዘዋዋሪ የሌላዉን ወገን የተሻለ ገጽታ ለማስተዋወቅ የሚደረግ ጥረት ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሃሳብን በሃሳብ የመሞገት ልምድን ብናዳብር መልካም ነዉ፡፡
  ቸር እንሰንብት

  ReplyDelete
  Replies
  1. የአይጥ ምስክር ድንቢጥ አሉ። ገራገር አደናጋሪ ነህ። " የሚጠቅመኝን አይዛለሁ የማይጠቅመኝን እጥላለሁ።" ጥሩ አለማዊ ፈላስፋ ነህ። ማረፊያ ያጣህ ፍልስፍና ንፍስ እንደሚያወዛውዘው ዛፍ የምታንከራትትህ ሆነሀል። ወረድ ትልና ደግሞ ምሽግህን ትነግረናለህ እንዲህ ስትል በመረጃና በመጽሐፍ ቅዱስ የተደገፈ ትንታኔዎች ያነበብኩት ስትል። ሐሰተኛና ተሳዳቢ ትንታኔ ያልካቸው ጽሑፎች እውነትማለት መብትህ ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ያለውን ትንታኔ አይሰጥም። ወዳጄ ሌባ ከሌባነቱ ውጭ ሌላ መጠሪያ የለውም ሌብነቱን እስካላቆመ። ካሀዲው፣ ተጠራጣሪው፣ እውነት አጣማሚው፣ሐሰተኛው፣ ቅዱሳንን የሚነቅፍና የሚያጥላላው፣ እንክርዳድ የሚዘራው፣ ካለ እምነቱ ገብቶ ያመነ መስሎ የሰላምን ቤት ለሚያውከውና ለሚቃወመው፣ የክርስቶስን አምላክነትና ፈራጅነት ክደው ፍጡር አድርገው አማላጅ ብለው ለሚሰድቡ፣ ለእውነት ጠላት ሆነው እውነትን ለሚቃወሙና ለመየሳድዱ መናፍቅ ጠላት ከመባል ሌላ ምን እንዲባሉ ፈለግህ። በክርስትና ወላዋየ አስተሳሰብና ማጠጋጋት የሚባል ነገር አይሰራም። አንዲት እምነት አንድ ጥምቀት ተብሏልና በአመኑት ፀንቶ መቆም እንጂ ያም ይሄም ትክክል ነው አይነት ጨዋታ አያድንም። እንዳንተ አባባልማ ከሆነ የሰው ልጆች ጠላት የተባለው ሰይጣንም ኢየሱስንም አውቀዋለሁ ብሏልና ከእሱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንታኔ አግኝቻለሁ ልትል ነው ማለት ነው። ለሁሉም አንተ ማን ነህ? አቶ ስሜ እገሌ ወይስ አቶ አዲስ? በል በል ይሔን በመርዝ የተለወሰን ምክርህን ለራስህ አድርገው። ምክንያቱም መርዝ ያለበት ነገር ሁሉ ገዳይ አጥፊ ነውና!

   Delete
 18. Damot .............  ReplyDelete
 19. @Damot
  You are victim of inferiority complex.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Then, are you felt happy? Go get your Piano, Guitar and other you dancing instrumentand start explaning your happiness about my victim of inferiority complex.

   Delete
  2. Damot

   Seek help..

   Delete
  3. For anonymous February 11, 2015 at 12:35pm
   Why you got mad? you were saying, I am Bible reader, but now you are coming different to speech. Do use all words you read in the bible. Now I do understand you Bible knowledge is very limited. And also I do understood my ideally defense defeated your false thought and comments. I advise you to seat and learn from others.

   Delete
  4. @Damot
   I will not be scared to walk on the path I choose to be correct, and I will never be scared about it. Your negativity never stop me from being the child of Jesus Christ, the source of my salivation.

   Stay with your hate

   Delete
 20. Damot is not only ignorant but arrogant also. So let him bark. No one give attention for his nagging.

  ReplyDelete