Thursday, February 12, 2015

ጌታ የማያውቃቸው “የጌታ አገልጋዮች”ምስክርነት አንዱ የአምልኮ መገለጫ ነው፡፡ አንድ አማኝ “ክርስቶስ እርሱ ኢየሱስ ነው ወይም ክርስቶስ እርሱ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነው” (ማቴ.16፥16 ፤ ሐዋ.9፥20 ፤22)ብሎ ወደቤተ ክርስቲያን አካል ሲጨመር አንዱ የየዕለት ዋና ተግባሩ ምስክርነት ነው፡፡ ያመንነውን በመናገር ብቻ የምንመሰክር አይደለንም ፤ በሕይወትና በምግባር(በሥራ) እንጂ፡፡ “በጸጋ ድነናል”(ኤፌ.2፥5) ካልን ልክ እንደመዳናችን ማመናችንም ከእኛ የሆነ አይደለም፡፡ ጸጋው በእምነት ካዳነን “ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ” ከእኛ ሥራ የተነሳ አይደለም፡፡(ኤፌ.2፥8)
  እኛን ለማዳን አብ ልጁን ወደምድር ሲልክ ፤ እኛ ምንም የተገባን አልነበርንም፡፡ ስለዚህ “በእንዲሁ ፍቅር”(ዮሐ.3፥16) ወዶን በልጁ ሞት አዳነን፡፡ የልጁን ማዳንም እንድንቀበልም በልባችን የእምነትን አቅም ያኖረው እርሱ ነው፡፡ ነጻ ምርጫችንን ጠብቆ ፥ አምነን ወደእርሱ በመጣን ጊዜ ግን እንድናምነው ጉልበት የሆነን ያዳነን ያው ጌታ ነው፡፡ እንዲሁ “መልካሙን ሥራ ለማድረግም በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነልን አዲስ ፍጥረት መወለድ(መፈጠር) ያስፈልገናል፡፡ (ኤፌ.2፥10)
   ከክርስቶስ ኢየሱስ በአዲስ ልደት ያልተወለደ መልካም ለማድረግ አቅም የለውም፡፡ “ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው”ና (ዮሐ.3፥6) ከመንፈስ ቅዱስ የሆነውን የመንፈስን ሥራ(ፍሬ) ለማፍራት አይቻለውም፡፡ ምክንያቱም “እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና …  ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና” (ሮሜ.8፥5-6) ስለዚህም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ “ … ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የተወለዱ” (1ጴጥ.1፥5) በምንም አይነት መንገድ “ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት አይለውጡም፡፡” (ይሁ.4)

   ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዌው (ሥጋ ለብሶ በተመላሰበት ዘመኑ) ድውያንና ኃጢአተኞችን ካለባቸው ነገር ከፈወሰ በኋላ ከሚሰጣቸው ማስጠንቀቂያዎች “ወደ መንደሩ አትግባ” (ማር.8፥26) ፤ “እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ” (ዮሐ.5፥14) ፤“ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ”(ዮሐ.8፥11) የሚሉት በዋናነት ይገኙባቸዋል፡፡ ካመነ በኋላ ወደኋላ የሚመለስን አማኝ ጠላት ከፊት ይልቅ ሰባት እጥፍ እንደሚሰብረውና እንደሚያጠቃው (ማቴ.12፥45) ፤ ደግሞም “በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ እንደሚሆንባቸው” የተረገጠ የታላቁ መጽሐፍ እውነት ነው፡፡ (2ጴጥ.2፥20) ሶምሶን የገዛ መንገዱን ተከትሎ የወላጆቹንና የአምላኩን ቃል ችላ ባለ ጊዜ ያገኘው ክፉ ውርደት ነው፡፡ (መሳ.14፥3 ፤ 16፥21 ፤ 25) ይሁዳም ቢሆን በብዙ ምክር ቢነገረውም ከማስተዋል ቸል ብሎ(ሉቃ.22፥22 ፤ ሐዋ.1፥18) በክፋቱ በጸና ጊዜ ያገኘው እጅግ ክፉ ነው፡፡
   በአገልጋዮች መካከል ዛሬ እየሰማን ያለነው ነገር እጅግ አስነዋሪ ፥ አህዛብና አለማውያን በእግዚአብሔር እንዲዘብቱ የሚያደርግ ድርጊትን ነው፡፡ ከአንዱ ቤተ ሃይማኖት ግብረ ሰዶማዊነት አብቦ በብዙ ደጋፊዎች አጃቢነት ይፈካል ፤ ከሌላኛው ቤተ ሃይማኖት ደግሞ ሴሰኝነትና ልቅ አመንዝራነት ገደቡን ጥሶ ይፈሳል፡፡ የሚገርመውና የሚደንቀው ነገር አይን ባወጣ ነውር የሚመላለሱና ንስሐ ለመግባት በእልኸኝነት የሚመላለሱ “አገልጋዮችና አጃቢዎቻቸው” ጽሁፎቻቸው ፣ መጻህፍቶቻቸው ፣ ግጥሞቻቸው ፣ ዜማ መዝሙራቸው ፣ ስብከቶቻቸው … ፍጹም መንፈሳዊና የብርሃን መልአክ የሚመስል መሆኑ “አውቀን” እንኳ ዛሬም ብዙዎች አለማስተዋላችን ነው፡፡ (2ቆሮ.11፥14)
   በእርግጥ ቅዱስ ፣ ነውር የሌለባቸው ፣ ጻድቃን … ያልናቸውና ብለን የተሟገትንላቸው አገልጋዮች ድንገት አድራሻቸው አመንዝራነት ፣ ግብረ ሰዶማዊነት ፣ ሴሰኝነትና የከፋ ነውር ሲሆን ጌታ ሳያውቃቸው እንደሰው ልማድ በማወቃችን ተሸማቅቀናል ፤ አፍረናልም፡፡ የእነርሱ ወገን ተብሎ መጠራትንም ተጠይፈናል፡፡ የተጠየፍናቸው እኛ ንጹሐን ፣ ንዑዳን ፣ ክቡራን ፣ ምንም ነውር የሌለብን ሆነን ሳይሆን ለራሳቸው ስድ ሆነው ሕዝቡን እንዲነወሩ ወደስድነት ስለለቀቁት በመቃረንና በመቃወም እንደሌዋውያን ለእግዚአብሔር ሥራ በማድላት ወግነን ነው፡፡ (ዘጸ.32፥25-26) ኃጢአተኞች ብንሆንም በእግዚአብሔር ምህረት ላይ እየዘበትን ሌሎችን ከሚያሰናክሉ የአፍ አማኞች ወገን አይደለንም፡፡ አንድ ነገር ታወሰኝ ፦እንዲህ የሚል የአንድ ወንድም ጸሎት፥ “ጌታ ሆይ “ከኢየሱስ እንደነበሩ አወቁአቸው” ተብሎ እንደተጻፈ ፤ እኚህ ነበሩ አይሁንብን” አሜን፡፡ አዎን አሜን፡፡
  ጌታ ኢየሱስ “ማንም እርፍ በእጁ ይዞ ወደኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም” (ሉቃ.9፥62) ብሎ ሙታናቸውን ለሚቀብሩ ሙታን ተናግሯል፡፡ አማኝም ሆነ ያመነ አገልጋይ ጌታ ኢየሱስን ሁል ጊዜ በማየት ካላገለገለ “ለእውነት እንዳይታዘዝ በሚያደርግ አዚም ” መያዙ አይቀርም፡፡ (ገላ.3፥1) እውነተኛ አገልጋይ ከተማው ወንጌል ፤ አላማው መስቀል ነው ፤ ከዚህ በቀር ምንም ምን አድራሻ የለውም፡፡ ዳሩ በተቃራኒው የሚሰለፉ ደፋር አገልጋዮች እንዳሉ ታላቁ ጌታ ፤ ጌታ ኢየሱስ ነግሮናል፡፡ እኒህ አገልጋዮች “በጌታ ስም ትንቢት ሊናገሩ ፣ በስሙ አጋንንትን ሊያወጡ ፣ በስሙ ብዙ ተአምራትንም ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡” (ማቴ.7፥22-23) ይህ ብቻ ሳይሆን ከላይ እንዳልኩት አገልግሎታቸው ፣ መዝሙራቸው ፣ መጻህፍቶቻቸው ፣ ስብከታቸው … ውብ ሆኖ ብዙዎችን ሊማርክ ይችላል ፤ ነገር ግን የጌታ መልስ አንዲት ብቻ ናት “ከቶ አላወቅኋችሁም ፤ እናንተ ዓመጸኞች ከእኔ ራቁ” ወይም “እናንተ ርጉማን … ከእኔ ሂዱ” (ማቴ.7፥23 ፤ 25፥41) የምትል፡፡
    እኒህን የአምልኮ መልክ ብቻ ይዘው ኃይሉን የካዱትን (2ጢሞ.3፥2) ፣ ጥበበኞች ነን ሲሉ የደነቆሩትን (ሮሜ.1፥22) የማያውቃቸው ከመጀመርያው ነው፡፡ እርሱ ለሚመለስ ኃጢአተኛ እንጂ ሊሰበር አንገቱን ለሚያደነድን ሰነፍ የማያዳላ እውነተኛ ዳኛ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለኃጢአት ፍርድ የማይቸኩለው “የአንዳንዶች ሰዎች ኃጢአት የተገለጠ፥ ፍርድንም የሚያመለክት ሆኖ ፥ ሌሎችን ግን የሚከተላቸውና ፤ እንዲሁ መልካም ሥራ ደግሞ የተገለጠ ሆኖ፥ ያልተገለጠም ከሆነ ሊሰወር ስለማይችል ነው።” አዎ! ግብረ ሰዶማውያኑም ፣ አመንዝራውና ሴሰኛው ምዕመንም ይሁን አገልጋይ  ከልቡ ዳግም ወደኃጢአት ላይመለስ፥ እንደጌታ ትምህርት ቢመለስ የእግዚአብሔር እጅ ዛሬም ለማዳና ያላጠረች ፤ የምትቀበል ናት፡፡ ከኃጢአታቸው ጋር መቼም መች አንተባበርም ፤ አምላካችን ቅዱስ ነው ፤ እንዲገለገልም ፤ እንዲመለክም የሚሻው በቅድስናና በንጽዕና ብቻ ነው!
   አመንዝሮችንና ግብረ ሰዶማውያንን ፣ ዘፋኞችንና ጠንቋዮችን … በመካከሏ ይዛ ቤተ ክርስቲያን ነኝ ብላ የምትሟገት ፤ ዳሩ ስለኃጢአቷ ንስሐ የማትገባዋን ቤተ ክርስቲያን ጌታ በጅራፍ እንደሚነሳባት  እናምናለን! እጅግ የሚያሳዝነው በአደባባይ የበደለ አገልጋይ ንስሐ እንዲገባ ፣ የበደላቸውን ይቅርታ እንዲጠይቅ ፣ ኃጢአቱን በመናዘዝ ይቅርታ እንዲያገኝ ከመምከር ፣ ከመገሰጽ ፣ መንገድ ከማሳየት ይልቅ በጭፍን የተሳሳተውን አገልጋይ “ያንተ ኃጢአት ከሌላው በምን ይለያል? ፤ ምነው አንተ ብቻ ነህ እንዴ ኃጢአት የሠራኸው? ፣ ኃጢአት ባንተ አልተጀመረ?! ፣ ስለሚበልጣቸው በዚህ አጥምደው ጣሉት … የሚሉና  … እርሱን የምትናገሩ እርሱን ለመናገር ሞራል የላችሁም ፣ ኃጢአት የሌለበት ብቻ እርሱን ይናገረው ፣ ሠራ … ታዲያ ምን ይጠበስ?...” የሚሉ አንዳንዴ በክርስቶስ ቦታ ፣ አንዳንዴ በበዳዩ ሥፍራ ፣ አንዳንዴ በሰይጣን ሥፍራ ተቀምጠው መፍረድ አይሉት ፣ መርዳት አይሉት ፣ መከላከል አይሉት … የሚሠሩትን የማያውቁ ደጋፊዎችና አጃቢዎች በዳዩን ንስሐ ከመግባት እያዘገዩና እልኸኛ እያደረጉት እንደሆን ቢያስተውሉ እጅግ መልካም ነው፡፡ እውነተኛ የአማኝ ልብ፥ ለበደለው ጥፋቱ ግልጽ ይቅርታን የሚጠይቅና ለአምልኮ ንጽሕናው የሚተጋ እንጂ ከጌታ ፍርድ የማያስጥሉ የእንቧ ካብ ደጋፊዎችን ተከልሎ የሚያስሟግትና ዳር ሆኖም የሚያይ አይደለም፡፡
     እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ እውነተኛ ፍቅር ደግሞ ከእውነት ጋር ብቻ ይተባበራል እንጂ ሐሰትንና ኃጢአትን አያሽሞነምንም፡፡ ስለዚህም ፈራጁ ጌታ በፍቅርና በርኅራኄ እንዲመጣ ንስሐ እንግባ! እልኸኛ ልባችንን በትህትና እናዋርደው እንጂ የቤት ልጅ በመሆናችን በከንቱ ልንታበይ አይገባንም ፤ እርሱ ለአብርሃም ልጆችን ድንጋይ ከተባሉት ከአህዛብ መካከል ሊያስነሳ እንደሚችል ሲናገር እንዴት ብሎ የጠየቀው አንድም የለምና፡፡ ጌታ የማያውቃችሁ የጌታ አገልጋዮች ሆይ መንገዳችሁን በመንገዱ ፊት አሁኑኑ አጥሩ፡፡  

       እኛን ከኃጢአተኞች ኃጢአት ጋር ከመተባበር ጌታ ይርዳን፡፡ ከኃጢአተኞች ጋር የሚተባበሩትንም ልብ ይስጣቸው፡፡ አሜን፡፡

6 comments:

 1. I do not accept any kind of adultery or sodomy as it is not godly. According to the information I have about the Tehadso person was that two of his followers accused him that he had abused them or tried to abuse them some five years back. Even if we believe that he had done that before 5 years, can't we think that he has repented for that and should not continuously be harassed? Why do we keep on pushing for repentance of a failure for which God has already forgiven. Is this a right treatment of a Christian to a Christian brother? Or, is there a proof that he is still practising sodomy? If yes, then how can he get people in his gubae? I am sure those who go there know that he is doing it and not many people can afford such religious crimes. What I want to say is, instead of judging people by past history why do we not take people as they appear today. May God bless you all.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰላም
   ከልብህ ከሆነ ዝሙትንና ግብረ ሰዶማዊነትን መቃወምህ ጥሩ ነው፡፡
   ከዛ ባላፈ ግን ስለ አሸናፊ መኮንን የጻፍከው ምላሽ ይሁን ሀሳብ የተንሸዋረረና የነገሩን ቁልፍ የሳተ ነው፡፡ በመጀመሪያ አሸናፊ ላይ አንተ እንዳልከው የስም ማጥፋት ዘመቻ ሳይሆን የተደረገው የንስሀ ግባና ተመለስ ዘመቻ ነው፡፡ የሰዶማዊነቱ ሰለባ የሆኑ ወንድሞችም ቢሆኑ የሚፈልጉት ንስሀ እንዲገባ ሌሎች ወንድሞችን ማማገጥ እንዲያቆም እና ሌሎች የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ወንድሞችን ስም ተናግሮ እነርሱም እርዳታ እንዲደረግላቸው ነበር፡፡ አንተ እንዳልከው ሁለት ሰዎች ሳይሆኑ በትንሹ አምስት ሰዎች ናቸው፡፡ አሸናፊ ከአምስት አመት በፊት እንዲህ አደረገብኝ ብቻ አይደለም ከአስር አመት በፊትምሰዶማዊ እንደነበር በቂ መረጃ አለ፡፡
   ከዛም አልፎ ሰዶማዊነቱ ከመገለጡ ከሁለት ወራት በፊት የቢሮውን በር ዘግቶ ሊደፍረው የነበረ ወንድምም አለ፡፡ የተሞላከውን ብቻ አትተንፍስ፡፡ የነገሩን ግራና ቀኝ ለመመልክት ሞክር፡፡ ነገሩ እንዳልከው አምስት አመት ያለፈው ቢሆን እንኳ መንፈሳዊው ሥርዓት እንደ አለማዊውም ሥርዓት የይርጋ ህግ እንደሌለው ማወቅ ይኖርብሀል፡፡ ኃጢአት ከሀምሳ አመት በፊትም ተሰራ ከአምስት ቀን በፊት እግዚአብሔር የሚቀበለን ንስሀ ስንገባበት ብቻ ነው፡፡ አሸናፊ አምስት አመት ስለሞላው ንስሀ ገብቷል የሚል የቂል ሀሳብ ታነሳለህ፡፡ ይህ የንስሀ ትርጉም እንዳልገባህ ብቻ ነው የሚያስረዳኝ፡፡ በተረፈ አሸናፊ ሰዶማዊ መሆኑን ማመኑንና ንስሀ ለመግባት እንቅስቃሴ ጀምሮ እንደነበር አትርሳ፡፡ አንተ የጠቀስካቸው በጉባኤው አሉ የምትላቸው የሱ ተከታዮችም አምላኪዎችም አይዞህ ሲሉት ግን አምበሳው ዞር አለና ስም ማጥፋት ተደረገብኝ እያለ ማስወራት ጀመረ፡፡
   ሀሳብህ ራሱ የተምታታ ነው፡፡ አንዴ ስም ማጥፋት ነው ትላለህ ቀጥሎ ደግሞ ንስሀ ገብቷል ትላለህ፡፡ የቱ ጋር ነው አድራሻህ? መመለስ ንስሀ መግባት የሚባሉ ነገሮች ግልጽ የሆነ አካሄድ ናቸው ያላቸው፡፡ ንስሀ ቢገባና ቢመለስ ስም ማጥፍት ተደረገብኝ ብሎ አያወራም አያስወራም፡፡ ንስሀ ከገባ አብሮ ይህን ልምምድ ሲፈጽም የነበሩ ሰዎችን ሚስጢራቸው ተጠብቆ ነጻ እንዲወጡ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ይልቅስ ከየከተማው ግብረ ሰዶማውያንን ሰብስቦ አይደል እንዴ ያለው፡፡ የትኛዋ እንስሳ ነች ባክህ ስንተዋወቅ አንተናነቅ ያለችው?
   ሰላም

   Delete
  2. ከጉባኤው ሰዎች አሁንም አሉ ብለኃል፡፡ ምን ይደንቃል? ጠንቋይ ቤትም እኮ ሰዎች ይሰበሰባሉ፡፡ የሰው መሰብሰብ ለንጹህነትና ለእውነተናነት ማረጋገጫ መሰለህ እንዴ? የዋህ ነህ፡፡
   ለማንኛም እሱ ጋር የሚሰባሰቡ አምስት አይነት ሰዎች ናቸው
   1. ሰዶማዊ መሆኑን የማያውቁ ወሬውንም ያልሰሙ
   2. ወሬውን የሰሙ አይደልም ብለው የሚያምኑ
   3. ሰዶማዊ መሆኑን የሚያውቁና ንስሀ ገብቷል የሚሉ
   4. ሰዶማዊ ቢሆንም የግል ችግሩ ነው የሚሉና
   5. ሰዶማዊ መሆኑን አና ከዛም አለመውጣቱን እያወቁ ሆን ብለው የሚያስተባብሉ
   አንተ ከየትኛው ወገን ነህ?
   እግዚአብሔርን የምትወድና ተስፋህ ከሱ ጋር እንደሆነ የምታምን ከሆነ ከሰዶማውያንን ጋር ህብረት ከማድረግ ጌታ ይጠብቅህ እልሃለሁ፡፡
   ይህንን ስልህ አሸናፊ ሰዶማዊ መሆኑን ከ100 ፐርሰንት በላይ እርግጠኛ ሆኜ ነው፡፡ ከምትገምተው በላይ ማስረጃዎች አሉኝ፡፡ ለጊዜው ዝምታን መርጫለሁ፡፡ እንደ አንተ አይነት ሰዎች ግን ችኮ ሙግት ይዛችሁ ስትቀርቡ ደስ ስለማይለኝ ነው ምላሽ የሰጠሁህ፡፡ እውነቴን ልንገርህ አሁንም ቢሆን ለአሸናፊ የሚጠቅመው በተገለጠ መንገድ ንስሀ መግባት ነው፡፡ ያን ካላደረገ እና እንደ ውሻ ከግብረ አበሮቹ ጋር እየተልከሰከሰ የሰውን ስም ማጥፋቱን ካልተወ ያለመመለስን እና የጌታን ክብር የመጋፋቱን ፍሬ ያጭዳል፡፡
   እውነት ለመናገር አንተ እንዳልከው ማንንም ሰው በአለፈ ታሪኩ መውቀስ አያስፈልግም፡፡ ችግሩ አሸናፊ ይህ ያለፈ ታሪኩ አይደለም፡፡ ንስሀ ያልገባበት ያልተመለሰበት የጌታን ክብር የተጋፋበት፡፡ ኃጢአቱን አሽሞንሙኖ የያዘበት የአሁን ታሪኩ ነው፡፡
   የአሸናፊ ግብረ ሰዶማዊነት የማያፈናፍን እውነት ነው፡፡ ዝም ብሎ ከመንጫጫት እስቲ ለእግዚአብሔር ወግኑና ንስሀ እንዲገባ እርዱት፡፡ ንስሀ ከገባና ከተመለሰ ማንም ምንም ሊለው አይችልም፡፡ ያን ካላደረገ ግን እንደ ሰጎን ራሱን ጉድጓድ ውስጥ ቀብሮ መኖሩን ይቀጥላል፡፡ እናንተም ጽድቅ መስሎዋችሁ ራሳችሁን ጉድጓድ ውስጥ ቀብራችሁ መኖር ከተባለ መኖር ትቀጥላላችሁ፡፡ በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ የተረዳሁት ነገር ቢኖር አሸናፊ ለእርሱ በእውነትና በጽድቅ የሚያስብለት አንድም ወዳጅ አብሮት አለመሆኑን ነወ፡፡ እውነተኛ ወዳጅ ግራና ቀኙን አይቶ ጉድለትን የሚያሳይ እና መፍትሔውን በግልጽ አስቀምጦ የሚረዳ ነው፡፡ ኃጢአት አይዞህ በማለት አትሰረይም ንስሀ እንዲገባና ጌታን እንዲታረቅ በመርዳት እንጂ፡፡ ሆይ ሆይ ለጠጅ ቤት ነው ለክርስተና አያስፈልግም፡፡ ሀሳቡን የሰጠኸው በቅንንነት ከሆነ ጌታ እውነቱን ተረድተህ እሱን ለመርዳት የሚያስችለውን ጸጋ ጌታ ይስጥህ፡፡
   በተረፈ ግን እሱን መርዳት ካልቻላችሁ ዝም ብሎ መንዘባዘቡ አይጠቀማችሁም፡፡ በተቻለ መጠን ዝም ለማለት ሞክሩ ለእንዲህ አይነቱ ኃጢአት ጥብቅና መቆም የሚያስከፍለው ዋጋ ብዙ ነው፡፡ ግን ለምን ዝም አትሉም!! እየለፈለፋችሁ አታስለፍልፉን፡፡ ምናለ ስንረሳችሁ ብትረሱን?

   ከጉባኤው ሰዎች አሁንም አሉ ብለኃል፡፡ ምን ይደንቃል? ጠንቋይ ቤትም እኮ ሰዎች ይሰበሰባሉ፡፡ የሰው መሰብሰብ ለንጹህነትና ለእውነተናነት ማረጋገጫ መሰለህ እንዴ? የዋህ ነህ፡፡

 2. Amen!!! Geta Yibarkeh

  ReplyDelete
 3. YOU ALL ARE RESPONIBLE TO BRING EVERYTHING TO LIGHT IF YOU CALL YOURSELF SERVANT OF CHRIST. HIS TEACHING HAS TO BE STOPPED FROM SPREADING EVERYWHERE.

  ReplyDelete
 4. bgeta lelaw metsfut nger melkme hono sali gen ahun men eydrghu naw.andi semon abrchu nbrchu ahun gen tkem alyaychu na andu andun sem matfat jmere yaszenli lmnjawem ayfri sera lsew atngeru gudchu ezaw eni btme afrbchuhlw.nger geni ahun semlket hulchume bzi sera lay yalchu tmseljalchu bzhi grop yalch bzyami yalchu andi nchu nger gen hzbni gera atgbu ydbrbchhli .geta lhlchme lbi ysetchu.enaneten blo thdeso amchi.......afrbchulu..

  ReplyDelete