Saturday, February 14, 2015

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍና ቆሞስ አባ ወልደ ኢየሱስ ለረጅም ጊዜ ካገለገሉበት ከላስቤጋስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተባረሩ መምህር ውብ አምላክም ታግዷል።

Read in PDF

በአንድ ጊዜ ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ሦስት አገልጋይ ታግዷል። ከሚኖሩበት ቤትም ባስቸኳይ እንዲወጡ ታዝዘዋል። "አድኅነኒ እግዚኦ እምብሲ እኩይ ወባልሃኒ እምገበርተ አመጻ‚ አቤቱ ከክፉ ሰው አድነኝ፣ ነውር ከሚፈጽሙ ሰዎችም ታደገኝ የምንልበት ክስተት ነው።
  ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ይከበር በሚለው አቋማቸው ጎልተው ይታወቃሉ። በቅዱስ ሲኖዶስ ምክትል ጸሐፊነታቸው በየቤተ ክርስቲያኑ በሚነሣ ብጥብጥ ችግር ለመፍታት ሲንቀሳቀሱ የቆዩት ብፁዕነታቸው የሲኖዶስ ደጋፊ እየተባለ ከሚጠራው ስውር ቡድን ጋር ሲፋለሙ ቆይተው ይህ ቡድን ከብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ጋር አጣልቷቸው እንደነበር ይታወሳል። ከጊዜ በኋላ ግን የሥዉሩ እንቅሥቃሴ አካሄድ የተገለጠላቸው አቡነ መልከ ጼዴቅ ከብፁዕነታቸው ጋር እርቅ ፈጽመው ወደ ፍቅራቸው ተመልስው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ለማስከበር በጋራ መቆማቸው ይነገራል። ይህን ሥርዓትና ሕግ የማስከበር እንቅሥቃሴ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በጥምቀት በዓል ላይ በመገኘት ለሕዝብ አስታውቀዋል። ሕጉ በየአብያተ ክርስቲያናቱ እንዲላክና ሕዝብ እንዲወያይበት ተደርጎ መልሱን በመያዝ እርምጃ ለመውሰድ ታቅዷል። ይህ ሁኔታ የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ እና የጳጳሳቱ እንዲሁም የካህናቱ አንድነት ያመጣው ለውጥ ነው ተብሏል። ሥርዓትና ሕግን የማያከብር ቤተ ክርስቲያንና ሕጉን የማያስከብር ካህን ከሲኖዶሱ እንዲለይና ወደ ፈለገው እንዲሄድ የሚያደርግ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችልም ተጠቁሟል። 

  በውጭ የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ካህናት ከመቀደስና ከማስተማር ውጭ ሌላ መብት የላቸውም። ደጋግመው ንስሐ ግቡ የሚሉ አገልጋዮች ካሉም ቦርድ የሚባለው ክፍል ለንስሐ ግድ በሌላቸው ጥቅመኛ ካህናት ይመታቸዋል። ካህናቱን ለሁለት ከፍሎ ካጋጬ በኋላ ገላጋይ መስሎ በመኃል በመግባት የማይፈለገውን ካህን ያባርራል። በዚህ ሁኔታ ቅዳሴ አታስረዝሙ፣ ትምህርቱ ይከብዳል፣ ዛሬ እንዲህ ያለው እኛን ለመሳደብ ነው፤ እያሉ የማይፈለጉትን ሰው ያሳድዳሉ። ሥጋውና ደሙን ተቀበሉ፣ አታመንዝሩ፣ ንስሐ ግቡ የሚለው ስብከት በአሜሪካ አስፈሪ ስብከት እየሆነ ነው። ተወዳጁ ስብከት ይሳካልሃል፣ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው፣ ተስፋ አትቁረጥ፣ ጌታ ይወድሻል፣ ድካምሽን ያውቀዋልና አይዞሽ ወዘተ የሚለው የሚያስጨበጭብ ስብከት ነው። ስለዚህ ቦርድ ተብለው የሚመረጡት የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች። አግብተው የፈቱ፣ ንስሐ ገብተው የማያውቁ፣ ሥጋውና ደሙን የማይቀበሉ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የማያውቁ ናቸው። እነዚህ ሰዎች እንደምንም በጓደኛና በዘመድ የምረጡኝ ቅስቀሳ በቤተ ክርስቲያን ዙፋን ላይ ከወጡ በኋላ ተመልሰው ለመውረድ ከሰማይ እንደመውደቅ ያህል ይሆንባቸዋል። ምክንያቱም በሥልጣናቸው የሚያገኙት ጥቅም ስላለ ነው። ገንዘብ የሚዘርፉ አሉ፣ በቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ዘመዳቸውን ወደ አሜሪካ የሚወስዱ አሉ፣ የፖለቲካ ግሩፕ ለመፍጠርም ዋናኛው ጥቅም ነው።
   ከላይ ከተዘረዘሩት ጥቅሞች ውስጥ በየትኛው እንደተያዙ ያልተገለጠልን ሦስት የላስቬጋስ ሚካኤል ቦርዶች ወይዘሮ ፍሬዘውድ፣ ወይዘሮ በልዩና ሌላ ለጊዜው ስሙ ያልደረሰን ሰው ከሥልጣን አንወርድም ብለው ለሦስተኛ ጊዜ ወደ በቤተ ክርስቲያን መንበር ላይ ተጣብቀው ከቀሩት ውስጥ ናቸው ተብሏል።  ወይዘሮ ፍሬዘውድ ሊቀ መንበሯ ነች። ለሌላ ሰው ተራ ስጪ ተብላ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የተመከረችው ወይዘሮ ፍሬዘውድ እኔን አይወዱኝም ይጠሉኛል በማለት ድሮ ከቤተ ክርስቲያን ጥለው የወጡትን እነአቶ ታምሩን ይዛ ጦርነቱን በአቡነ ዮሴፍና በአባ ወልደ ኢየሱስ ላይ ስታካሂድ ቆይታ ዛሬ እነርሱን ከቤተ ክርስቲያን አስወጥታለች። አባቶች ለቅዳሴ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ለመቀደስ ሲሞክሩ በፖሊስ ታግደዋል። ወደ ሁለት መቶ የሚጠጋ ሕዝብ በውጭ ካባቶች ጋር ጸሎት አድርጎ ተቆጥቶ ወደ ቤቱ የተመለሰ ሲሆን ወደ ሰላሳ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ቄስ ተስፋዬ የተባለውን የተገነጠለ ካህን ይዘው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብተው ጸሎት አድርገው በፖሊስ ጣልቃ ገብነት ተለያይተዋል። የላስ ቤጋስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሕንጻ ገዝቶ በቅርቡ ማስመረቁ ይታወቃል። ይህን እድገት በብዙ ትግልና ጥረት ከምዕመናን ጋር በመሆን ያመጡት አባ ወልደ ኢየሱስና አቡነ ዮሴፍ እንደነበሩ የሚናገሩት ምእመናን ውለታቸውና ያገልግሎት ክፍያቸው ይህ መሆኑ አሳዝኗቸዋል።  
 ይህ በእንዲህ እንዳለ የውጩ ሲኖዶስ ከእጄ ሊወጣ ነው ብሎ የሠጋው ሥዉሩ ቡድን ጥቂት ካህናትን ይዞ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ላይ ጥቃት ፈጽሟል የሚሉም አሉ። የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ቸል ያለችው ወይዘሮ ዘውዴ ቤተ ክርስቲያንን ለመምራት በቅብዓ ክህነት የተሾሙትን ሊቀ ጳጳስ ከቤተ ክርስቲያን አባራለች። ሊቀ ጳጳስን ከቤተ ክርስቲያን የማባረር ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ አንጂ የሴት ወይዘሮዎች አልነበረም። የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት አለማወቅና አለማስተማር የሚያመጣው ጣጣ እንዲህ የከፋ መሆኑን ማን ባወቀልን? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሐዋርያነት ሥልጣኑ "ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር፣ ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም‚ ያለው፤ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ለማስተማር ሲሆን ያለ ሥርዓት የምትመራ ቤተ ክርስቲያን ምን ዓይነት ከባድ ችግር እንደሚመጣባት በመንፈስ ቅዱስ ስለተረዳ ነው። 1ጢሞ 2፥11። ጳውሎስ የፈራው አልቀረም። ዛሬ ዛሬ የዚህ ዓለም የፖለቲካ ትምህርት ያሰለጠናቸው እህቶች የእግዚአብሔርን መንግሥት ትምህርት እምቢ ብለዋል። በእግዚአብሔር መንግሥት የተወሰነላቸውን የአገልግሎት ሥርዓት፣ መብታቸው እንደተነካ ከወንድ እንዳነሱ አድርገው ይቆጥሩታል። ስለዚህ በምዕራቡ ዓለም ቄስና ጳጳስ መሆን አለብን ካሉ ሰንብተዋል። በእግዚአብሔር መንግሥት ሥርዓት እንጂ ትንሽ እና ትልቅ ተብሎ የተከፈለ ነገር የለም። ባለ ሥልጣንም ሆነን፣ ባለ ሥልጣንም ሳንሆን የምናገለግለው አገልግሎት ዋጋው በጌታ ፊት እኩል ነው። ታላቅ ካልሆንሁ ብሎ መታገል የጤንነት አይደለም። ሰው ከዚህ ዓለም ገዢ እየተማረ እየመጣ በክርስቶስ አካል ውስጥ የመብት ጉዳይና የይገባኛል ጥያቄ ማንሳቱ ለፍርድ የሚያጋልጥ ነው። ሴት በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም ያለው ሐዋርያው ጳውሎስ  እንጂ የዛሬ ጳጳሳት ያመጡት ዕንግዳ ትምህርት አይደለም። ዛሬ ነገር ተገልብጧል። ወይዘሮዋ ሊቀ ጳጳሱን ከቤተ ክርስቲያን አስወጥታለች። አልወርድም ብላ ጳጳሱን አውርዳለች። የዘመኑ ክፋት በዚህ ሁኔታ እየተገለጠ የጌታን ዳግም መምጣት ለምንጠባበቅ ሁሉ ትምህርት የምናገኝበት ነው። ወይዘሮ ፍሬዘውድ ሽሃይ በማፍላት ሰውን በማስተባበር ሥራ ጥሩ የምትባል ሴት ናት፣ ከቦርድ ሥልጣን ውረጂ የተባለውን ነገር ግን አምርራ የምትጠላው ነገር ነው ይላሉ ታዛቢዎች። ውረዱ የተባሉት ሁሉም የቦርድ አባላት ሆነው ሳሉ ሌሎች በትሕትና ራሳቸውን ዝቅ ሲያደርጉ፣ ሦስቱ ግን አንወርድም በማለት ራሳቸውን ከፍ አድርገዋል ተብሏል። እነአቡነ ዮሴፍም ከማን እንደሆነ ያልተረጋገጠው የበቀል ክንድ አርፎባቸው የሚቀጥለውን እርምጃ እስኪውስዱ ድረስ በጸሎት ላይ ይገኛሉ። እስኪ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ እያልን እንቆይ!!!   


በአንድ ጊዜ ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ሦስት አገልጋይ ታግዷል። ከሚኖሩበት ቤትም ባስቸኳይ እንዲወጡ ታዝዘዋል። "አድኅነኒ እግዚኦ እምብሲ እኩይ ወባልሃኒ እምገበርተ አመጻ‚ አቤቱ ከክፉ ሰው አድነኝ፣ ነውር ከሚፈጽሙ ሰዎችም ታደገኝ የምንልበት ክስተት ነው።
  ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ይከበር በሚለው አቋማቸው ጎልተው ይታወቃሉ። በቅዱስ ሲኖዶስ ምክትል ጸሐፊነታቸው በየቤተ ክርስቲያኑ በሚነሣ ብጥብጥ ችግር ለመፍታት ሲንቀሳቀሱ የቆዩት ብፁዕነታቸው የሲኖዶስ ደጋፊ እየተባለ ከሚጠራው ስውር ቡድን ጋር ሲፋለሙ ቆይተው ይህ ቡድን ከብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ጋር አጣልቷቸው እንደነበር ይታወሳል። ከጊዜ በኋላ ግን የሥዉሩ እንቅሥቃሴ አካሄድ የተገለጠላቸው አቡነ መልከ ጼዴቅ ከብፁዕነታቸው ጋር እርቅ ፈጽመው ወደ ፍቅራቸው ተመልስው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ለማስከበር በጋራ መቆማቸው ይነገራል። ይህን ሥርዓትና ሕግ የማስከበር እንቅሥቃሴ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በጥምቀት በዓል ላይ በመገኘት ለሕዝብ አስታውቀዋል። ሕጉ በየአብያተ ክርስቲያናቱ እንዲላክና ሕዝብ እንዲወያይበት ተደርጎ መልሱን በመያዝ እርምጃ ለመውሰድ ታቅዷል። ይህ ሁኔታ የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ እና የጳጳሳቱ እንዲሁም የካህናቱ አንድነት ያመጣው ለውጥ ነው ተብሏል። ሥርዓትና ሕግን የማያከብር ቤተ ክርስቲያንና ሕጉን የማያስከብር ካህን ከሲኖዶሱ እንዲለይና ወደ ፈለገው እንዲሄድ የሚያደርግ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችልም ተጠቁሟል።
  በውጭ የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ካህናት ከመቀደስና ከማስተማር ውጭ ሌላ መብት የላቸውም። ደጋግመው ንስሐ ግቡ የሚሉ አገልጋዮች ካሉም ቦርድ የሚባለው ክፍል ለንስሐ ግድ በሌላቸው ጥቅመኛ ካህናት ይመታቸዋል። ካህናቱን ለሁለት ከፍሎ ካጋጬ በኋላ ገላጋይ መስሎ በመኃል በመግባት የማይፈለገውን ካህን ያባርራል። በዚህ ሁኔታ ቅዳሴ አታስረዝሙ፣ ትምህርቱ ይከብዳል፣ ዛሬ እንዲህ ያለው እኛን ለመሳደብ ነው፤ እያሉ የማይፈለጉትን ሰው ያሳድዳሉ። ሥጋውና ደሙን ተቀበሉ፣ አታመንዝሩ፣ ንስሐ ግቡ የሚለው ስብከት በአሜሪካ አስፈሪ ስብከት እየሆነ ነው። ተወዳጁ ስብከት ይሳካልሃል፣ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው፣ ተስፋ አትቁረጥ፣ ጌታ ይወድሻል፣ ድካምሽን ያውቀዋልና አይዞሽ ወዘተ የሚለው የሚያስጨበጭብ ስብከት ነው። ስለዚህ ቦርድ ተብለው የሚመረጡት የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች። አግብተው የፈቱ፣ ንስሐ ገብተው የማያውቁ፣ ሥጋውና ደሙን የማይቀበሉ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የማያውቁ ናቸው። እነዚህ ሰዎች እንደምንም በጓደኛና በዘመድ የምረጡኝ ቅስቀሳ በቤተ ክርስቲያን ዙፋን ላይ ከወጡ በኋላ ተመልሰው ለመውረድ ከሰማይ እንደመውደቅ ያህል ይሆንባቸዋል። ምክንያቱም በሥልጣናቸው የሚያገኙት ጥቅም ስላለ ነው። ገንዘብ የሚዘርፉ አሉ፣ በቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ዘመዳቸውን ወደ አሜሪካ የሚወስዱ አሉ፣ የፖለቲካ ግሩፕ ለመፍጠርም ዋናኛው ጥቅም ነው።
   ከላይ ከተዘረዘሩት ጥቅሞች ውስጥ በየትኛው እንደተያዙ ያልተገለጠልን ሦስት የላስቬጋስ ሚካኤል ቦርዶች ወይዘሮ ፍሬዘውድ፣ ወይዘሮ በልዩና ሌላ ለጊዜው ስሙ ያልደረሰን ሰው ከሥልጣን አንወርድም ብለው ለሦስተኛ ጊዜ ወደ በቤተ ክርስቲያን መንበር ላይ ተጣብቀው ከቀሩት ውስጥ ናቸው ተብሏል።  ወይዘሮ ፍሬዘውድ ሊቀ መንበሯ ነች። ለሌላ ሰው ተራ ስጪ ተብላ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የተመከረችው ወይዘሮ ፍሬዘውድ እኔን አይወዱኝም ይጠሉኛል በማለት ድሮ ከቤተ ክርስቲያን ጥለው የወጡትን እነአቶ ታምሩን ይዛ ጦርነቱን በአቡነ ዮሴፍና በአባ ወልደ ኢየሱስ ላይ ስታካሂድ ቆይታ ዛሬ እነርሱን ከቤተ ክርስቲያን አስወጥታለች። አባቶች ለቅዳሴ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ለመቀደስ ሲሞክሩ በፖሊስ ታግደዋል። ወደ ሁለት መቶ የሚጠጋ ሕዝብ በውጭ ካባቶች ጋር ጸሎት አድርጎ ተቆጥቶ ወደ ቤቱ የተመለሰ ሲሆን ወደ ሰላሳ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ቄስ ተስፋዬ የተባለውን የተገነጠለ ካህን ይዘው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብተው ጸሎት አድርገው በፖሊስ ጣልቃ ገብነት ተለያይተዋል። የላስ ቤጋስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሕንጻ ገዝቶ በቅርቡ ማስመረቁ ይታወቃል። ይህን እድገት በብዙ ትግልና ጥረት ከምዕመናን ጋር በመሆን ያመጡት አባ ወልደ ኢየሱስና አቡነ ዮሴፍ እንደነበሩ የሚናገሩት ምእመናን ውለታቸውና ያገልግሎት ክፍያቸው ይህ መሆኑ አሳዝኗቸዋል።  
 ይህ በእንዲህ እንዳለ የውጩ ሲኖዶስ ከእጄ ሊወጣ ነው ብሎ የሠጋው ሥዉሩ ቡድን ጥቂት ካህናትን ይዞ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ላይ ጥቃት ፈጽሟል የሚሉም አሉ። የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ቸል ያለችው ወይዘሮ ዘውዴ ቤተ ክርስቲያንን ለመምራት በቅብዓ ክህነት የተሾሙትን ሊቀ ጳጳስ ከቤተ ክርስቲያን አባራለች። ሊቀ ጳጳስን ከቤተ ክርስቲያን የማባረር ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ አንጂ የሴት ወይዘሮዎች አልነበረም። የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት አለማወቅና አለማስተማር የሚያመጣው ጣጣ እንዲህ የከፋ መሆኑን ማን ባወቀልን? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሐዋርያነት ሥልጣኑ "ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር፣ ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም‚ ያለው፤ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ለማስተማር ሲሆን ያለ ሥርዓት የምትመራ ቤተ ክርስቲያን ምን ዓይነት ከባድ ችግር እንደሚመጣባት በመንፈስ ቅዱስ ስለተረዳ ነው። 1ጢሞ 2፥11። ጳውሎስ የፈራው አልቀረም። ዛሬ ዛሬ የዚህ ዓለም የፖለቲካ ትምህርት ያሰለጠናቸው እህቶች የእግዚአብሔርን መንግሥት ትምህርት እምቢ ብለዋል። በእግዚአብሔር መንግሥት የተወሰነላቸውን የአገልግሎት ሥርዓት፣ መብታቸው እንደተነካ ከወንድ እንዳነሱ አድርገው ይቆጥሩታል። ስለዚህ በምዕራቡ ዓለም ቄስና ጳጳስ መሆን አለብን ካሉ ሰንብተዋል። በእግዚአብሔር መንግሥት ሥርዓት እንጂ ትንሽ እና ትልቅ ተብሎ የተከፈለ ነገር የለም። ባለ ሥልጣንም ሆነን፣ ባለ ሥልጣንም ሳንሆን የምናገለግለው አገልግሎት ዋጋው በጌታ ፊት እኩል ነው። ታላቅ ካልሆንሁ ብሎ መታገል የጤንነት አይደለም። ሰው ከዚህ ዓለም ገዢ እየተማረ እየመጣ በክርስቶስ አካል ውስጥ የመብት ጉዳይና የይገባኛል ጥያቄ ማንሳቱ ለፍርድ የሚያጋልጥ ነው። ሴት በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም ያለው ሐዋርያው ጳውሎስ  እንጂ የዛሬ ጳጳሳት ያመጡት ዕንግዳ ትምህርት አይደለም። ዛሬ ነገር ተገልብጧል። ወይዘሮዋ ሊቀ ጳጳሱን ከቤተ ክርስቲያን አስወጥታለች። አልወርድም ብላ ጳጳሱን አውርዳለች። የዘመኑ ክፋት በዚህ ሁኔታ እየተገለጠ የጌታን ዳግም መምጣት ለምንጠባበቅ ሁሉ ትምህርት የምናገኝበት ነው። ወይዘሮ ፍሬዘውድ ሽሃይ በማፍላት ሰውን በማስተባበር ሥራ ጥሩ የምትባል ሴት ናት፣ ከቦርድ ሥልጣን ውረጂ የተባለውን ነገር ግን አምርራ የምትጠላው ነገር ነው ይላሉ ታዛቢዎች። ውረዱ የተባሉት ሁሉም የቦርድ አባላት ሆነው ሳሉ ሌሎች በትሕትና ራሳቸውን ዝቅ ሲያደርጉ፣ ሦስቱ ግን አንወርድም በማለት ራሳቸውን ከፍ አድርገዋል ተብሏል። እነአቡነ ዮሴፍም ከማን እንደሆነ ያልተረጋገጠው የበቀል ክንድ አርፎባቸው የሚቀጥለውን እርምጃ እስኪውስዱ ድረስ በጸሎት ላይ ይገኛሉ። እስኪ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ እያልን እንቆይ!!!   

36 comments:

 1. አቡነ ዮሴፍን አውቃቸዋለሁ። ናሽቪል ቴነሲ ከራንዮ መድኃኒያለም ነበሩ። ከኔምጋ እንግባባ ነበር። ሊቀ ጵጵስና ለማግኘት በሰላም ከናሽቪል ለቀዋል። ይህ አሁን ተፈጠረ የሚባለውን ችግር በድረ-ገጾች ከማንበብ ሌላ በመጠኑ ችግሩን ሰምቻለሁ። አሁን እዚህ ላይ የተፃፈው የቦርድ አምባገነነት የሚባለው በአንዳንድ ቦታዎች ይከሰታል። ይህን ችግር አለሁ፣ አለሁ፣ ከኔ በላይ ማን አለ ስልጣን የምትማቸው ለመመረጥ ያለው ዕድል በጣም የሰፋ ነው። እውነተኛ የሆነ ሰው ና ተመረጥ ሲባል ይሸሻል። ይንን ችግር ለመቅረፍ የምእመናን ንቃት አስፈላጊ ነው። ሌሎች አላስፈላጊ ለምግባረ ብልሹነት የሚጋብዙትን የሕግና የአሰራር ቀዳዳዎች መድፈን ያስፈልጋል።

  በሌላ በኩል ዝሙት አታድርጉ፣ ገንዘብ አትስረቁ፣ ሚስቱን የፈታ ካህን አይቀድስ ሲባል ብለው የቆሙ ምእመናን በየቦታው ብዙ ችግር የሚደርስባቸው አሉ። ለምሳሌ በቨርጅኒያ ሐማረ -ኖሕ ኪዳነምህረት በዝሙት ምክንያት አቶ ታደሰ ሲሳይ የሚባል ሚስቱን ፈትቶ አሁን ቆሞስነት ተቀብሎ ይገኛል። አባሰላማ ይህንን ጉዳይ ትንፍሽ ስል አላየንም። ስለቤተክርስቲያን ሥርዓት መፍረስና ንግድቤት ለማድረግ የሚመጡ ብዙ አስመሳይ ካህናት እንዳሉ የታወቀ ነው። ቤተክርስቲያንን እንደ የግል ንግድ ቤት የሚመለከቱ በርከታ ካህናት፣ በተለይም በዘመኑ መነኮስን ብለው ገዳምን የማያውቁ ካድሬ መነኮሳት ነን ባዮች ቤተክርስቲያንቱን ወረዋት የሚገኙበት ዘመን ነው። ስለዚህ ጥፋቱ ወደ ሰበካ ጉባኤ የሚመጡ ጥቂት ስግብግብ ግለሰቦችም ሆኑ፤ የዘመኑ ነጋዴ ካህናት፣ ሰባኪያንና መለኮሳት ልዩነቱ አይታየኝም።

  ReplyDelete
 2. የዚህ ድረገጽ አዘጋጆች እውነተኝነት ካላችሁ በስፋት የተዘገበውንና ትዳርን አፍርሶ ለከፍተኛ ችግር ልጆችን ያጋለጠውን እንዲሁም በዲሲ አባ መላኩ (አቡነ ፋኑኤል) የሚያውቁትንና የኢትዮጵያው ሲኖዶስም ጆሮ ዳባ ልበስ ያለውን የቨርጂኒያ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ውስጥ የዝሙት ቅሌት ፈጽሞ አሁን ድረስ ቆሞስ ነኝ እያለ በማወናበድ ላይ ስሊሚገኘው ታደሰ ሲሳይ ምነው ትንፍሽም አላላቸሁ። ሶስት ካህናት በምዕመናን ፊት ታደሰ ሲሳይ ማወገዛቸው ትልቅ የቤተክርስቲያን ዜና አይደለምን? ከዚህ የበለጠ አንገብጋቢ ችግር አለ እንዴ? አሁንም አልመሸባችሁም ታደሰ ሲሳይ በምዕመናን ላይ ስላደረሰው ጉዳትና ስለፈጸመው ወንጀል መዘገብ አለባችሁ።

  ReplyDelete

 3. አባሰላማዎች

  ቤተክርስትያናችን የገጠማት ፈተና በጣም ብዙ ነው። ብዙ ጊዜ አባሰላማና ሐራ ተዋህዶ ዉድድር የያዝችሁ ይመስላል። በዚህ ዓይነት የሚወዱትን ለመሸፈን፣ የሚጠሉትን ለማርከስ የሚደረግ የሚመስል አካሄድ እውነት ክርስትና ነውን?

  በርግጥ ከአሁን በፊት አንድ ጳጳስ ከኮሌጅ የተሰናበቱበት በሴቶች ምክንያት እንደነበረ አቅርባችሁ ነበር። ሆኖም ግን ጳጳሱ ከአቡነ ማትያስ ስር የሚገኙ ናቸው፣ ምንም ዓይነት ተግሳፅ እንዳልደረሰባቸው ነው የምናውቀው። በወቅቱ ያቀረባችሁትም የማህበረ ቅዱስን ሊቀ ጳጳስ የሚል ለጥፋችሁ ነበር። በሌላ በኩል ብዙ ችግር የሚፈጥሩ ለምሳሌ እንደ አባ ግርማ ያሉ የለንደኑ ደብረ ፅዮን ማርያምን የመሳሰሉ ቤተክርስትያን በርግጥ በመነኩሴው ችግር የተነሳ ነው ወይስ ስግብግብ ግለሰቦች ወይም ፖለቲከኞች የፈጠሩት ነው ትላላችሁ?

  ReplyDelete
 4. Good job Abba Selama!!

  ReplyDelete
 5. The third person was Doctor Alebachew Yimer (who is called Lidetu.) He is one of the selfish person who doesn't have respect for the fathers. He is a mean person and doesn't have any clue about church tradition. They divided the people for their personal benefits.

  ReplyDelete
 6. Thank you for the information. We need to be united and save our church and religion. It is true the is a lot going on At Hamerenoh Kidanemeheret in Virginia even the preacher Eliyas doing the worst with the Mezemiran and the the so called fundraising chairwoman Addi who is the weyane supporter please le us do something before it is to late.

  ReplyDelete
 7. እግዚአብሄር ይባርካችሁ ፡፤ ዛሬም ቅድስት ቤተ ከርስቲያናችን የገጠማት ችግር የፖለትካ በሽታ ነው፡፤ እነዚህ ፖለትክኞች ለኢትዮጵያ ህዝብና ለሃይማኖቱዋ የቆሙ አለመሆናችውን የሚገልጡ ሁታዎች እየታዩ ናቸው፡፤ ለምሳሌ የኢትዮጵያን ህዝብ ደም ከ30 ዓመታት በላይ ያፈሰሰውን የኤርትራውን መሪ ወዳጅ ያደረጉት የጎንደር ተወላጅ የሆኑ በዘራቸው ኤርትራዊያን የሆኑ ኢትዮጵያን ዳግም ለሞት እያዘጋጁዋት ነው። ለመሆኑ የሻብያው መሪ ከወያኔ መንግስት ለኢትዮጵያ ህዝብ ይሻል ይሆን ? መልሱን ለእያንዳንዱ ሰው እተዋለሁ። የቤተ ከርስትያን አንድነትም እንዳይፈጠርና ሰላም እንዳይሆነም እያደረጉ ያሉት እነዚህ በትውልዳቸው ጎንደር የሆኑት የሻብያ ዝርያ ያላቸው ናቸው። ጠንቀቅ ጠንቀቅ ነው ኢየትዮጵያዊያን እንዳትሞኝ ። የወያኔ ጥላቻ አስመስለው ሀይማኖታችንና ሀገራችን አየጎዱ ናቸው። ንቃ ንቃ ለሀገር ለወገን አበጅም አካሄዱ...........በእውነት የኤርትራው መሪ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስብ ከሆነ አሰብን ለሀገራችን ይመልስ......የግፍ ሥራ ከሻብያ በድጋም አንፈልግም ይበቃናል። እዚያ በጠበሉ.............አንድነት ለኢትዮጵያ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Aseb will be given back in your dreams!!! why don't you cry about Djibouti the same way you think you are entitled about Asab??? Stop winning and move on. accept the reality.
   Aba Selama, is this a political Forum or Religious forum? It is a shame to see what happen in Vegas, or anywhere else in the church. May God give his people wisdom and time to repent before he send his punishment. Amen

   Delete
 8. … የቤተክርስቲያን ራስ ክርስቶስ ነው ። እንደማየው ግን የቤ/ክ ራስ እኔነት ማንነት ግለሰብና ቡድን ከሆነ ቤተ/ክ አይደለም። … ሰበካ ጉባኤ ፥ አስመራጭ ኮሚቴ ክርስቶስን አውርዶ የቤተ/ክርስቲያን ራስ እኔ ነኝ ካለና ጉልላቷም እኔው ነኝ ካለ ምን ለማየት ሰው ወደዚያ ስፍራ ይምጣ። የማንን ክብር ለማየት?የክርስቶስን ወይስ የሰዎችን ??

  ReplyDelete
 9. ምንም እንኳን ጉዳዩን በጥልቀት የማላውቀው ስለሆነ ብዙ አስተያየት ለመስጠት ቢቸግረኝም የአንድን ወገን ሃሳብ ብቻ ይዞ የወጣውና አንቀጾችን የደጋገመው የዛሬው ጽሁፋችሁ የሚያሳዝን ነው:: በተለይ ስርዓት አፍቃሬ እንደሆነው ማህበረ ቅዱሳን ሆናችሁ ቤተክርስቲያናንን በቅንነት የሚያገለግሉ ምዕመናንን ሁሉ የኮነናችሁበትና ያጥላላችሁበት በመሆኑ ያስገርማል:: ያጠፋ ምዕመን፣ የቦርድ ወይም የሰበካ ጉባኤ አባል ካለ በግል ያጠፋው ጥፋት ሊገለጽ ይችላል እንጅ ሁሉንም መጨፍጨፍ አሳፋሪ ነው::

  ከላይ እንደተገለጸው በውጭ አገር ያሉት የተወሰኑ ካህናት መንፈሳዊ ነገር ማስተማር ትተው ገንዘብ ሰብሳቢ ሲሆኑ፣ ምዕመንን በቡድን እየከፈሉ ሲያጣሉ፣ ቤተክርስቲያንን የግል ሃብት ማበልጸጊያ (business) ሲያደርጉ፣ የክህነት ስልጣናቸውን በስነ ምግባር ጉድለት ሲያቃልሉ በአስተዳደር ላይ ያሉ ምዕመናን እና ቤተክርስቲያን እርምጃ መውሰድ የለባትም ማለቱም አያዋጣም::

  ለመሆኑ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 6 ላይ እንደተገለጸው ሐዋርያት የእግዚአብሔርን ቃል ለማገልገልና ለጸሎት እንደተጉት እንዲሁም ከህዝብ መሃል የተመረጡት ሽማግሌዎች ደግም ገንዘብ ቢሰበስቡ እና አስተዳደራዊ አገልግሎት መስጠታቸው ችግሩ ምንድን ነው?

  ReplyDelete
 10. በቅድሚያ እራሳችሁን ፈትሹ እውነት የት እንዳለ መርምሩ ይህን ያልኩት ሰለአባ ሰላማ ብሎግ መግቢያችሁ ላይ የግለሰብ ን ሰም ያለ እውነተኛ መረጃ በመጥፎ የሚያነሱ ሥነጽሑፍም ሆነ አስተያየት ፈጽሞ አትቀበልም ትላላችሁ ግን እውነቱ እናንተ ጋ አልተጻፈም የተዛባና የአንደኛውን ወገንተኞነት የያዘ ነው፡፡ እርምት ውሰዱ እውነትን ፈልጉ ንጹሐንን አታሳስቱ የቦርድ አባላቱ ህጋዊ በሆነ በቤተክርስቲያኗ ህግና ደንብን በተከተለ በመላ አባላቱ አብዛኛውን ድምጽ በማግኘታቸው ነዉ የተመረጡት አባ ግን እነዚህን 3ሰወች ካለወረዳችሁ አኛ አናገለግለም ማለታቸው የአደባባይ ሚስጢር ነዉ እዉነቱን ፈልጉና እነዚኸን 3ሰወች ይቅርታ አንደምትጠይቁ ተስፋ አደርጋለሁ እውነትና ንጋት እያደር ይገልጣል በቂመረጃ ወይም ማስረጃ ሳትይዙ የሰው ሰም ማጥፋት ትክክል አይደለምና የተዛባ ጽሁፍ ትዝብት ላይ ትወድቃላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 11. በአንተ ላይ ሊደረግብህ የማትሻውን በሰው ላይ አታድርግ

  ReplyDelete
 12. It looks like Abune Yoseph, Aba W/Eyesus and Memhir Wubleak have resigned from the church by themselves because of some minor disagreements with the Election committee. They also refused to accept the reconciliation proposal from the holy Synod in exile. Begochahchewn medda lay betinew mekobilelachew agibab new biye alasibim.

  ReplyDelete
 13. የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! ይህ ሁሉ እንግዳ አይደለም ። የዚህም ሁሉ ችግር ምንጩ የሁላችን ልብ ነው። በልቦናችን ያለውና የተቀርጸው የተለምዶ አምልኮት ትምህርት ወጤት ነው። በዚህም ይህ የመንፈስ ስይፍ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል በልቦናችን ስለሌል ጠላታችን ስይጣን እንደፈለገ ያበራየናል። መጨነቅ ያለብን ሁላችንም ስለ ራሳችን ቤተ- መቅደስ ነው። እግዚአብሔር ስለ ራሱ መቅደስ ራሱ ይውቃል። ቅዱስ ሰለሞንም በጥበብ ሆኖ ታላቅ ግንብ ሠርቶለት ነበር። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ወይም ቃል ኪዳኑን ባለመጠበቁ ምክንያት ወደ ሞኝነት ተለውጦ ክፉ ነገርን በእግዚአብሔር ፊት አድርጓል። በዚህም ምክንያት ያ ሁሉ ባድማ ሆኖ ተርት ተርት ሆኗል። ስለዚህ እኛ አሁን መጨነቅ የሚገባን እኛን የሚቀድሰንን ቃሉን እናውቃለን ወይ ብለን ራሳችንን መጠየቅ ይገባናል። እግዚአብሔር የሚፈልገውን ነገር ከቃሉ ሳናስንስ ሳንጨምር የተጻፈውን መረዳት ይገባናል። ሁላችንም በራሳችን ጥበብ ትምህርት ስለምንጓዝ እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ተሰውሮብናል ወይም መጽሀፉ ተቆልፎብናል። እና ሁላችን የምንጨነቀው ስል እግዚአብሔር ሥራአት ሳይሆን እኛ ስላወታነው ሥራአት ነው። በዚህም ምክንያት ተስፋችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን በስሙ ብቻ እንውቀዋለን ነገር ግን እርሱ ያለውን ቃል ያስተዋለው የለም። በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር እኛን ሁሉ በቤቱ ያለውነውን ወግኖቹን ለጠላታችን አሳልፎ ሰጥቶናል። አህንም እንዲህ ዓይነቱ ብጥብጥና ጥል መለያየት የሚመጣው በዚህም ምክንያት ነው። እሥራኤል አስቀድማ ፊቷን ከእግዚአብሔር ስትሰውር ጠላት ያሸንፋት ነበር። እንደገና ንስሐ ገብታ ዕግዚአብሔርን ስትፈልግ ከጠላቷ እጅ ያድናት ነበር። ዛሬም እና በመዋደድ ሰዎችን ከማውገዝ ርቀን ወደርሱ መቅረብ ይገባናል። አለበለዚያ እርስ በራሳችን የምናካሰስ ከሆነ ጥሩ ነገርን ከእግዚአብሔር መተበቅ ሞኝነት ነው። ለምሳሌ ያህል።
  ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች ስለ ወገኖቹ እንዲህ ሲል ነግሯቸዋል።
  " ወንድሞች ሆይ፥ የልቤ በጎ ፈቃድና ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ልመናዬ እንዲድኑ ነው። በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና።3 የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም። የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።" ( ሮሜ ም10: 1-4) ይላል።
  የራሳቸው ጽድቅ ምንድን ነው? የእግዚአብሔርን ጸጋ በመጽሀፉ የተመዘገበውን ቃል ባለመረዳታቸው ምክንያት እግዚአብሔር ለኃጢያታቸው ስርየት የሚሰጠውን የከብት ደም ያፈሱና የክርስቶስን ደም እንደ ተራ ወንበዴ ደም አድርገው በመቁጠራቸው ምክንያት ሊድኑና ሰላምን እንዳለገኙ ያስተምረናል። የእግዚአብሔርም ጽድቅ ደግሞ በመጽሀፉ እንድተጻፈው ለሚያምኑ ሁሉ ክርስቶስ ራሱን በመስቀል በማዋል ያፈሰሰው ደም አስቀድሞ ይፈስ የነበረውን ሕግ የቁርባኑና የመስዋዕቱን ሕግ አቁሞታል። በዚህም ብዙዎች የእርሱ ወገኖች ተስናክለው ወድቀውበታል። ይህም ሕግ ክርስቶስ የፈጸመው ምን እንደሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች እንዳስተማራቸው፡ "እንግዲህ ሕግ ምንድር ነው? ተስፋው የተሰጠው ዘር እስኪመጣ ድረስ በመካከለኛ እጅ በመላእክት በኩል ስለ ሕግ መተላለፍ ተጨመረ። (ገላ. ም3፡ 19)። የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የፈጸመው ሕግ ነው።
  በተመሳሳይ መልኩ አህንም ሁላችንም እንድ እሥራኤል ወገኖች የእግዚአብሔር ቃል ሳንረዳ የምናመልከውን አምላክ በቃሉ ሳናውቀው በጣም የምንጨነቀው ስለ ራሳችን በጥበባችን ስለምናደርገው ሥራአት ነው። እንዲሁም ወገኖቻችንም ሕዝቡንም ይህንኑ ቃል ባልማስተማራችን መሠረት የእግዚአብሔር ጥብብ ማስተዋልና እውቀት ባለመኖራችን ምክንያት ሁላችንም እንተራመሳለን። ይህ ሁሉ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ማን እንደሆነ ስለማንወቀ ነው። በእኛም ዘንድ አንድ የማያደርገንን የክርስቶስ ወገን አድርጎ እርስ በርሳችን ፍቅር የሚሰጠንን የክርስቶስ ልቦና ከእያንዳንዳችን ዘንድ የለም። እንዲሁም ይህ የክርስቶስ ልቦና የሚገኝበትን የእግዚአብሔርን መንፈስ ከቃሉ ባለመመጋባችን ብች ይህ ሁሉ እሳት ሆኖ እንቅበዘበዛለን። ጊዜውም ለጠላታችን ጥሩ ስለሆነ እርሱም ያበራየናል።
  የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ! መጀመሪያ እራስችንን ማዳን ተገቢ ነው። በራሳችን ጥበብ አንመራ ። የእግዚአብሔርን ቃል የተመዘገበውን እንወቀው። የምናመልከውን አምላክ በቃል እንረዳው። ይህ ሁሉ ከሆነ ደግሞ እንድዚህ ያለ ክፉ መንፈስ ይወገዳል። ስለዚህ የሰውን ኃጢያት ከማውራት ተቆጥበን እረኞች የእግዚአብሔርን በጎች መመገብና በትክክለኛ ማሰማሪያ በሆነ በቃሉ እንዲጸኑ ማስተማር ግዴታ ይሆናል። በዚህም ሰው የዘራውን ያጭዳል ይላል። ጤፍ የዘራ ጤፍ ያጭዳል። በቆሎም የዘራ በቆሎም ያጭዳል። ቤተ ክርስትያናችንም የዘራችውን መለያይትን እያጨደች መሆኑን መረዳት ይገባናል። ስለዚህ ጽድቅን መማር ይገባናል። ጽድቅም የሚሰጠንን የእግዚአብሔርን ቃል በሰው ልቦና መዝራት ይገባናል። አሁንም ሁላችንም ምሕረትን ጽድቅንና ቅንነትን ፍርድን ካላደርግን የምናጭደው ምርታችን ሁሉ ለሚመታው ወራት መለያይት ይሆናል። በቤተክርስትያናችንም ያለው ይህ ስለሆነ ጥበበኛ ሊቀ ጠበብቱ ሊቀ ዘማሪው የት አለ ጥበብህ? የት አለ ያ እንደ አንበሳ እያገሳህ የዘራህው ዘር ፍሬው? መልያትን ነው የዘራሀው ወይስ ጽድቅን? ብዙ ሊቃውንት ጥበባውያን የበዙባት ከተማ እንዴት በጠላት ተወረሰች? የሚያስተውል የለምን? ዝም ብለን ለሥጋችን የምንሮጠው ን? እባካችሁ ማስተዋልን ጥበበን እግዚአብሔር ሰጥቶን ሁላችንም በሰላም እንድኖር እግዚአብሔር ይርዳን!
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር!

  ReplyDelete
 14. I feel that Abune Yoseph has something to do with this. He has his hands on all of this and instead of trying to fix the problem as I have heard he has already gotten started to open a new church called Bisrat Gabriel. What is the point. The Holy Synod gave him a letter and told him to wait and let the people continue serving that were previously serving. He disagreed with this decision and took measures in his own hands. What didn't he listen and follow the instructions given to him from above?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Getting a license for the church took one day. If more than 80% of the church left with Our fathers in revolt be cause doors were locked on our fathers, we will need a place to worship, dont you think. As far as the sinodos, for the first day when we received the tabot, guess who came to encourage us: the like' Papas frim virginia, dc, maryland. The one who lives with the payriarch, with messages of encouragement from Abune Merkorios, the headbof the Sinodos. And dont forget also aba Yoseph is a sinodos representative here, utah, arizona. What you have written is very misleading and distortes the truth.

   Delete

 15. Its very obvious that the EOTC in N America is disturbed by the so called unethical board members every time. Look the history of former boards of: Las Vegas st Michael EOTC, Debre hail st Gebriel at DC, Debre Keranyo Medhanialem at Nashvile, Mekane Selam Medhaniyalem at Oakland, St Mary of Zion at New York, and the current issue in LV St Michael ,,,,,etc all have the same issue at all.
  All Christians please be alert, be alert, be alert.
  If we can, lets try to straighten up the boards culture if not the EOTC in N America is in DANGER

  ReplyDelete
 16. ብርሐነተንሳይ ዘጋስጫFebruary 18, 2015 at 1:32 AM

  አባሠላ እደምን ሠነበታችሁ፡፡ ሰለደብረምህረት ቅዱስ ሚካኢል ቤ/ክ እውነቱን ማውራትና መፃፍ መልካም ነው፡፡ ወገናዊነት፡አብሮ መብላት እና ጏደኜነት የክርስትና መስፈርት አይደለም፡ክርስትና የመከራ ጉዞ ነው፡፡አቡነዮሴፍ እና ቆሞ አባወልደየሱስነ ፡ማንም አላባረረም ነገርግን ፡በቤተክርሰትያን ህግ በአጠቃላይ ማለት እችላለሁ ፡ለመጀመሪያ ጌዜ በራሳቸው ፈቃድ ከ2ዲያቆየናት ጋር በመተባበር ለተሻለ ደሞዝ የተሻለ ገቤ ለመሠብሠብ ሢሉ ለ3 ተከታታይ ቀናት አገልግሎት የማንሠጥ እና ሥራ እናቆማለን ማለታቸውን፡በቪዲዮ የተቀረፀው ለምን ተሸሸገ እውነቱ ይሆኖሳለ ለምን የማይመስል ነገር ለምን ይዋሻል፡፡ሌላውደግሞ ስለ ውብአምላክበተመለከተ አንድሠው የአገልግሎቱ ዘመን ካለቀ ከሥራ ገበታው ይሠናበታል፡ እንጂ አይተገድም ሥለዚህ ይሠው ፡የሥራው ሂደት አለቀሥለዚህ ከሥራው አልታገደም፡ ተሠናብቷል፡፡ እሥቴ እውነትየአለም መድኋኒትኢየሱስን ክርስቶስን የምትሠብኩ ከሆነ እውነት የት እደሚገኝ እወቁ፡፡ እግዚአብሒር አምላክ ቤተክርቴያናችንን ይጠብቅ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቪዲዮ ሳይኖር አለ ማለት ትርጉም የለውም!

   Delete
 17. እንደምን ሠነበታችሁ፡፡ጉድ ሳይሠማ አያድር፡ ይሉ የለ የቀደሙ አባቶቼችን፡፡ እንዲህ ነው ነገሩ፡ የአሪዞና፡ የዮታ፡ የነቫዳ ፡ተጠሪ የሆኑት ሊቀጻጻስ፡አቡነዮሴፍ፡ ቤተክርስቴያን ፈቃድ፡ለመስጠት፡ሲኖዶስ፡ሳይፈቅድ፡እችላለሁ ፡በማለት እነሆ ዛሬ በነቫዳ ፡ደብረብስራት ቅዱስ ገብርኤል፡ከፊታችን እሁድ ጀምሮ አገልግሎት እንደሚጀምሩ ለመንጋው ህብረተሰብ ፡አሳወቁ ፡፡አባሰላማዎች ፡እባካችሁ፡እኔን እና ማህበረሰቡን፡እያጨቃጨቀን ነው፡፡የማመለከተውን ፡ህጋዊ ሲኖዶስ ጠይቃችሁ መልስ፡እንድሰጡን ፡አደራ እላለሁ፡፡ እውነት ዛሬ እንዴህ ከሆነ በየትኛው ሲኖዶስ ነው የሚመራው፡ እውቅናውስ፡እንዴት ነው፡፡አባሰላማዎች፡ ለነዚህ ለመሳሰሉት መልሳችሁን፡አጠባበቃለሁ፡፡ የእናንተው

  ReplyDelete
  Replies
  1. አትሳሳቱ ስለሲኖዶስ 100% በሲኖዶስ ስር ነን። ሲቀጥል ሊቀጳጳስ ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ሞክሩ።

   Delete
 18. The information you gave us very true. However you only focused on the biblical perspectives of the servants. We need more information about those corrupted boards. The don't know about God. Because of that they don't care about the people. I am ashamed of their action not to leave the position.

  ReplyDelete
 19. When Abune Yoseph & Aba Melake Mehiret tried to open the doors as usual to do Kidase.. The door locks were changed, so that is how they found out that they were thrown out by the board. There were no other options left for them and they could not watch a greed driven sophisticated educated few destroy the church. Do you know that the house that our fathers lived in was put on the market in secret, meaning the parishioners were not informed. That caused a lot of problems. Do you know that their has not been an audit of the church accounts for 11 years. Finally Frezewd, Markos, Teshagere went to the Church where we were supposed to start kidase and defamed us, and told lies about us & put a stop to our services. (which by the way they lied to the police that it wasn't them and the police will be investigating them on this matter) & We will all come back with Kidus Gabriel Tabot to our church Debre Meheret. Only with the re-involvement of the three board re-elected, that is the only way those taking advantage of the church accounts, can cover their tracks.

  ReplyDelete
 20. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡ በመሠረቱ ሴቶች በመጽሐፉ ቅዱስም በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ታላቅ ቦታ እንዳላቸው ዓለምን የፈጠረው ንጉስ ክርስቶስን በማህፀኗ ከተሸከመችው ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ድንግል ማርያም ብንጀምር ሴት መሆኗን የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ (ገላትያ ም4 ቁ4) የመጀመሪያዋ ወንጌል ሰባኪ ሐዋርያት እንኳን ፈርተው በተቀመጡበት ሰዓት ጌታ መነሳቱን ለዓለም ያበሰረች መግደላዊት ማርያም ሴት መሆኗን 36ቱን ቅዱሳን አንስት ሴቶች መሆናቸውን፤ እነ ሊዲያ፣ ማርታ፣ አስቴር ስንቱን እንጥቀስ፡፡
  እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ባረካቸውም (ኦሪት ዘፍጥረት ም5 ቁ1-2);; ስለዚህ ሴቶች በቤ/ክ ውስጥ ታላቅ አስተዋፅኦ እንዳላቸው የፅሁፉ ባለቤት መጽሐፍ ቅዱስ አንብበው የሚያውቁ አይመስለኝም፡፡ ሴቶች ከዚህም አልፈው ልጆች ወልደው አሳዳጊዎች ሥነ ሥርዓትና ሥነ ምግባር አስተማሪዎች፣ በሰለጠነው ዓለም ብቻ ሳይሆን በቀደመው ዓለም የኢትዮጵያ ታሪክ የአገር መሪዎች እንደነበሩ ታሪክ ያስረዳናል፤ ንግስተ ሳባ፣ ንግስት ዮዲት፣ እተጌ ጣይቱ ወዘተ ፡ በዘመናችንም ቢሆን ከወንዶች እኩል ተምረው በታላላቅ የሥራ ኃላፊነት ተቀምጠው የሚያስተዳድሩ ሴቶች በርካታ መሆናቸውን መግለጽ እወዳለሁ፡፡
  የጽሁፉ ባለቤት እንዳሉት ከሻይ ማፍላት በላይ ለቤ/ክርስቲያናችንም ሆነ በሕብረተሰቡ ውስጥ ታላቅ ሥራ በመስራት የሚያገለግሉ ጠንካራ ምዕምንት ናቸው ።
  በድብረ ምሕረት ቅ/ሚ ቤ/ክ የተፈጠረው ችግር በካህናትና በአስተዳደር ቦርድ መሀከል ሲሆን ካሕናቱ በሕገ ደንቡ ላይ በተደነገገው መሠረት መጓዝ አለመቻላቸው የቤ/ክርስቲያኗ አባላት የመረጧቸውን 3 ግለሰቦች በመቃወም በፈቃዳቸው ሥራቸውን በመልቀቃቸውና ለአንድ ወር ያህል ሲለመኑ እንደቆዩ ብሎም ቅዱስ ሲኖዶሱ ድረስ ጉድዩ ደርሶ በሸምጋዮች የቀረበውን የዕርቅ ስምምነት መቀበል ስላልፈለጉ ቀደም ብሎ ለምዕመናን ያቀረቡት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄን እንደተቀበልናቸው መደረጉ እየታወቀ ፣ ሴት ወይዘሮዋ ጳጳሱን አዋረዱ የሚለው ንግግር ስህተት መሆኑን ፀሐፊውም ሆኑ አንባቢያን ሐቁን ሊረዱ ይገባል፡፡
  የወ ንጌ ል አስተምሆሮን በተመለከተ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠይቆ ሲመልስ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር እንዳላ የቤ/ክ አውደ ምሕረት ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ መነገር የለበ ትም፤ ይህም የተባለበት ምክንያት መድረኩን የያዙት አባቶች ቃለ እግዚአብሔርን ትተው ሙገሳ፣ ነቀፋ፣ ፖለቲካ፣ ዘር መለያያ ቅስቀሳ ሲያካሂዱበት ስለታየ ምዕመናኑ ሰልችቶት ከወንጌሉ አትውጡ ቢባሉም ሊሰሙ አልቻሉም፡፡ አለፈው ተርፈው እከሌን አትምረጡ ገዝቻለሁ እስከ ማለት ላይ በመደረሱ ነው፡፡
  በተጨማሪም የደ/ምቅ/ሚ በየትኛውም ቤ/ክ እንደሚታወቀው ሴቶች ብንሆንም ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለን ትጉሆችና ቤተ ክርስቲያናችንን የምንወድ፣ ቃል ኪዳናችንን የምናከብር፣ ልጆቻችን ሃይማኖታቸውንና ባህላቸውን እንዲጠብቁ የምንችለውን ሁሉ የምንጥር እውነተኛ ክርስቲያኖች መሆናችንን ስገልፅ፤ በቤት ያለብንን የሥራ ሃላፊነት ፤ ልጅ ማሳደግ፣ ምግብ ማብሰል፣ ማፅዳት በውጭ ሥራ ሰርተን ቢል በመክፈል አልፎ ተርፎም ለቤተ ክርስቲያናችን በጉልበታችን ፣ በገንዘባችን፣በዕውቀታችን የምንረዳ መሆናችን እንዲታወቅልን በዚሁ አጋጣሚ መግለጽ እወዳለሁ፡፡ በሴቶች እህቶች ጥንካሬ ባይሆን ኖሮ በወር ሁለት አሥርት ሺ ወጪ ያለውን ቤ/ክ እንዴት ማካሄድ ይቻላል ?
  እንዲሁም ጸሐፊው እናዳሉት ሳይሆን እውጭ ቆመው የቦርዱን ውሳኔ የሚቃወሙት ወርሃዊ መዋጮ ከፍለው የማያውቁ የቤ/ክ አባላት ያልሆኑ 30 ሰዎች ሲሆኑ አሁንም በቤተ ክርስቲያናችን ተገኝቶ አገልግሎቱን እየወሰደ ያለ ቋሚ አባላት እንዳሉን አንባቢያን እንዲረዱልን በቸሩ እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

  ReplyDelete
 21. እንደ ድህረ ገፃቹህ ዓርማ ሚዛናዊ ከሆናችሁ ለአንባብያን ግንዛቤ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት Reply ፅፌ ነበር ብታወጡልኝ ደስ ይለኛል ካልሆነም በሌሎች ሚዛናዊ በሆኑ ድህረ ገፆች ፅሁፌን ፖስት አደርጋለሁ፡፡

  ReplyDelete
 22. can we be one all of us please please we are orthodox why we separated? if it is continuing we going despair ena seyetan yenegsal please please late us together aba memenan bored we believe the same orthodox enemamar positive enehun gezeb yatefanal atasebu genezeben

  ReplyDelete
  Replies
  1. Being one is the best idea, as long one side is not intentionally destroying the other side. What do u do once the board chases all fathers out? Everybody who followed the fathers made a personal decision to support our fathers. My friend, if you think all people are good and all problems can be solved, you are mistaken. Some people are mistaken but good. Others are good and courageous enough to stand up for what is right. Then there are pople who are very comfortable doing bad thing and happy to do so for personal gain. Same reason why god is innately good and the devil innately bad. They cannot get along. Those who are not aware of people's capacity of evil are always manipulated. So becoming one is the best solution for those who are good but made a mistake.

   Delete
 23. ሰላም ለአባዮሴፍ እና ለቆሞስ አባወልደየስ፡ ከሁሉ አስቀድሚ ፡የከበረሰላምታዮ ፡ቀጠልበማድረግ ፡የምነግሩዎት የንሰሀ ሚስጥር፡እንዴህነው፡፡ቤተክርስቴያን በመክፈታችሁ፡ በጣም አዝኛለሁ፡፡ይህ የሚያመለክተው፡ ደግሞ ፡የገንዘብ ማፍቀር፡ ሞልክት ነው ፡፡እግዚአብሒር፡የገንዘብ አምልኮታችሁን ፡የቀበልላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 24. In pente church, the board is above the pastors and pastor is emloyee. In orthodox church the fathers have the highest esteem. When fathers are not happy with how affairs are managed, yigesiYsalu. The affairs of the church are taken care of by z board. So board cannot oppress abatochin. If board takes advantage, like in our case, Abune Yoseph told board you have to let the parishioners know and ask them if they want to sell property. If board dominates the church, it will silence fathers. And christ said to Peter: you are my rock, i will build my church through you. He didn't say that to the board members

  ReplyDelete
 25. አባ ሰላማዎች የካህን ስብስቦች መሆናችሁን ባውቅም ከኦርቶዶክስ ትምህርት ውጪ በተለይ በሴቶች ላይ ያላችሁን የተሳሳተ አመለካከት ሳየው ከእግዚአብሔር ህግጋት ውጪ መሆናችሁ አያሳዝነኝም እናንተነታችሁ የጠፋው ገንዘብ ካልኩሌሽን ውስጥ የገባችሁ ዕለት ነው፡፡ ፍሬና በልዩ ምንድነው የሚሰሩት የአቡኑ አባባል እኔ ነኝ ወይስ አባ ገንዘብ ሰብስበን ባንክ ማስገባት የሚያቅተን ይህን ቃል አላልኩም ቢሉ መቼም ፈሪሀ እግዚአብሔር ቀርቷል ህሊናዎት ግን ይሞግትዎታል መም. ውብ…… ምንድ ነው ያሉት ሻይ ማፍላት ነው ያሉት አልፈርድብዎትም፣ አባታችን ብረት ድስት አጣቢ ሲሉ፣ አባ ኩሽናዎች/ወጥቤቶች/ሲሉ እርስዎም ድርሻዎን አዋጥተዋል ። ይህ ሁሉ በረዶ የወረደብን የዛሬ ፪ ዓመት ገደማ አቡነ ዮሴፍ ባጠፋት ጥፋት ከስደተኛው ሲኖዶስ ምክትል ፀሐፊነታቸው ሲታገዱ አኩርፈው አዉስትራሊያ ሄዱ፣ ልክ አሁን የፀቡን ክብሪት ጭረው ሳንዲያጎ እንደተሸሸጉ እና አሁን ለምን ቦርዱ፣ ምእመኑ፣ ግለስብ፣ ሴቱ ታርጌት ሆንን አላማው ቁልጭ ብሎ ወጣ፡፡ የ፪አመት ህልም ምኞትና እልህ የ0ዛሬው ገብርኤልን ይዞ ከተፍ አለ፡፡ ደግሞ ገብርኤል ለስንት ዓመት እቅድ የተያዘለት ይሆን? እናንተ እንደሆን የታቦት ችግር የለባችሁም እያንዳንዳችሁ በየድሮወራችሁ ስላለና አማካሪዎቻችሁ የነዮሐንስ ዳኘው ቤተሰቦች ከአባታቸው የወረሱት የታቦት አሰባሰብና ምንጭ ስለሆኑ ሊቸግራችሁ አይችልም እንኳን ብቻ የእኛን ብቻ መለሳችሁልን፡፡ ደሀው ሚካኤላችንን እንደደህነታችን እንይዘዋለን፡፡ ከእኛ እንደማይወጣ እራሱ ምስክር ሆኖናል። አቡነ ዮሴፍስ አንድ ፫ ቦታ ከዚህ ጋር ፬ ቦታ ልምድ አላቸው ምንም ማንንም አይፈሩም ኣባ ወልደእየሱስ ከልብዎ ነው ሚካኤልን? ሚካኤልን? የጨከኑበት ይመቻችሁ፡፡
  አሁንም በዚህ አጋጣሚ እህቶቼንና ወንድምቼ ምንም ቂም የሚያይዝ ነገር ስለሌለን እናንተ የገብርኤል እኛ የሚካኤል መጨረሻው ይሄ ሆኖ በቀረ። አቡነ ዮሴፍም ሆኑ አባ ወልደየሱስ ይህን ፅሁፌን በአፋቸው አትደጊ ብለው በልባቸው እውነት መሆኑን ያውቁታል አቤት ህሊናቸው እንዴት እንደሚሞግታቸው እኔ በጣም የማዝነው እኛ ሰዎች ሁሉን አዋቂውን እንዋሸዋለን እናታልለዋለን እንቀጥፈዋለን ግን ይቅር ባይ ነውና ይቅር ይለናል። ይመቻችሁ

  ReplyDelete
 26. Abaselama, please don't be judgmental! Before accusing ,do your home work! The comment about women is very offensive and irrelevant to support your claim.

  ReplyDelete
 27. ከዐሥርቱ ቃላት አንዱ አትስረቅ ይላል ታድያ ሠርቃችሁ የወሰዳችሁት መጎናፀፍያችን, ሥዕሎቻችን, መፅሐፍቶቻችን..... ተገቢ ነውን? ወይስ የገለልተኛው ሲኖዶስ ዐሥርቱ ትእዛዛት ላይ ስረቅ ይላልን? በጣም አዝናለሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከላስቬጋስ ቅ/ሚካኤል ቤተክርስትያናችን የተወስደውን ንብረታችንን ማለቴ ነው

   Delete
  2. ስለ ቤተክርስቲያን ህግ ስታውቅ ለዚ ንግግር ንስሀ እንደምትገባ እርግጠኛ ነኝ።

   Delete
 28. የዚህ ድረገጽ አዘጋጆች እውነተኝነት ካላችሁ በስፋት የተዘገበውንና ትዳርን አፍርሶ ለከፍተኛ ችግር ልጆችን ያጋለጠውን እንዲሁም ሳንዲያጎ አቶ ወይም (አቡነ ፋኑኤል) የሚያውቁትንና የኢትዮጵያው ሲኖዶስም ጆሮ ዳባ ልበስ ያለውን ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስትያን ውስጥ የዝሙት ቅሌት ፈጽሞ አሁን ድረስ መምህር ነኝ እያለ በማወናበድ ላይ ስሊሚገኘው ምናሴ ሀይሉ ትንፍሽም አላላቸሁ። ትልቅ የቤተክርስቲያን ዜና አይደለምን? ከዚህ የበለጠ አንገብጋቢ ችግር አለ እንዴ? አሁንም አልመሸባችሁም ምናሴ ሀይሉ በምዕመናን ላይ ስላደረሰው ጉዳትና ስለፈጸመው ወንጀል መዘገብ አለባችሁ።

  ReplyDelete