Wednesday, February 18, 2015

በ “ዘወረደ” ተጀምሮ በ “ትንሣኤ” የሚደመደመው የዐቢይ ጾም ዋና መልእክት

Read in PDF


ዐቢይ ጾም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ የሚጾም ታላቅ ጾም ነው፡፡ ጾሙ በዋናነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ነው፡፡ ጾሙን የሃይማኖቱ ተከታዮች እንዲጾሙት ሥርዓቱን የደነገጉት አባቶች በጾሙ ወራት ጌታችን አየሱስ ክርስቶስ የጾመውን ጾም እያሰቡ፣ እርሱና ካከናወናቸው ተግባራትና ካስተማራቸው ትምህርቶች ዋና ዋናዎቹ እንዲዘከሩ በማድረግ፣ በተለይም ጌታ ስለ እኛ ያከናወነውን የማዳን ሥራ በማሰብ እንዲጾም ማድረጋቸው እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ 

“ዘወረደ” በሚል ስያሜ የሚጀመረው የዐቢይ ጾም በ“ትንሣኤ” ይደመደማል፡፡ ዐቢይ ጾም ጌታ ሰው ሆኖ መምጣቱን በመተረክ ጀምሮ በዚህ ምድር እየተመላለሰ ከሠራቸው ድንቅና ተአምራት፣ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል የተመረጡትን በማቅረብ፣ በመጨረሻም ጌታችን ስለእኛ የተቀበላቸውን ሕማማተ መስቀልና ሞቱን ከዚያም ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱን በማወጅ ይጠናቀቃል ማለት ነው፡፡ እንዴት ድንቅ ነው!! እውነትም ዐቢይ ጾም!! 

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የሆነውንና ያደረገውን እንዲህ ያለ ወቅትን ለይቶ ማሰብ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ስለእኛ ከሰማይ የወረደውን ኃጢአታችንን ተሸክሞ የሞተውንና ሞትን ድል አድርጎ የተነሣውን ጌታ ከማሰብ የበለጠ ምን ነገር ይኖር ይሆን? ነገር ግን ይህ ሥርዓቱን ብቻ በመፈጸምና ያለፈውን ታሪክ በመዘከር ብቻ የሚከናወን ከሆነ ዓላማውን ስተናል የሚያሰኝ ነው፡፡

እዚህ ላይ ትልቁ ጥያቄ አባቶች ሥርዓት አበጅተው በዚህ ወቅት እንዲዘከር ያደረጉትን ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ማእከላዊ ሐሣብ ማለትም፣ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር ተመላልሶ በመጨረሻ መሞቱንና ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱን፣ ይህን ያደረገውም ስለእያንዳንዱ ሰው መዳን መሆኑን ስንቱ ሰው ተረድቶት ይሆን? የሚለው ነው፡፡ ብዙው ሰው ለዚህ ጾም ትልቅ ግምት ስላለው በጾሙ ወራት ከጥሉላት ምግቦች ተከልክሎ በመጾምና ቤተክርስቲያን እየተገኘ በማስቀደስ፣ ያልቻለም ባለበት ስፍራ በመጾም እንደሚያሳልፍ ይታወቃል፡፡ በአንዳንድ ከዚህ ቀደም በሚያደርጋቸውና ዘወትር ሊጾማቸው በሚገቡ ዓለማዊ ነገሮች ላይም ለምሳሌ በዘፈን ላይ ጊዜያዊ ማዕቀብ ይጥላል፡፡ ስለጾሙ እናውቃለን እናስተምራለን የሚሉ አንዳንዶችም የጾሙን መልእክትና የየሳምንታቱን ስያሜ በተመለከተ ማብራሪያ በመስጠት ሥርዓቱን በማዳነቅና በመተረክ ሥራ የሚጠመዱበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ሁሉ ግን ምእመናንን ወደዋናው መልእክት ካላደረሰና በተግባርም የነፍሳቸውን ድኅነት በእምነት እንዲቀበሉና የልብ ሰላምና ዕረፍት እንዲያገኙ ካላደረገ ምን ጥቅም ይኖረዋል? እንደ እውነቱ ከሆነ አፍኣዊ ሥርዓት ከመሆን ያለፈ አንዳች ለነፍስ የሚተርፍ ነገር ይኖረዋል ማለት ከቶ አይቻልም፡፡ 

ከዚህ አኳያ አብዛኛው በዚህ የጾም ወቅት ሰው ይህን እውነት በመረዳትና ጌታችን ከሰማይ ወደ ምድር ወርዶ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር ተመላልሶ ኃጢአቱን ተሸክሞ እንደሞተለትና ዕዳውን ከፍሎለት በትንሣኤው መጽደቁን አረጋግጦለት እንደተነሣ በማመንና ልቡ በዚህ እውነት አርፎ ነው ማለት ይከብዳል፡፡ ከዚህ ይልቅ የብዙው ሰው ትኩረት በጾሙ ወቅት እንዲጠበቁ የታዘዙ ልዩ ልዩ ሥርዓቶችን በመጠበቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ጥረት ማድረግ ነው፡፡ በዘወረደ ተጀምሮ በትንሣኤ የሚደመደመው የዐቢይ ጾም ዋና መልእክት ግን ይህ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የጾሙ ወቅት ከመጾም ባሻገር ይህን ጌታ ለእኛ የሆነልንንና ያደረገልንን የምናስተውልበት፣ የምናስብበትና ጌታን ስላደረገልን ሁሉ አብዝተን የምናመሰግንበት ጊዜ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ግን በቅድሚያ የኢየሱስ ክርስቶስን መድኃኒትነት በመረጃ መልክና በዕውቀት ደረጃ ስላወቅን ሳይሆን አምነንበት የኃጢአታችንን ስርየት የተቀበልን እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ 

በዚህ የጾም ወቅት የኢየሱስ ክርስቶስን መድኃኒትነት ያላመንንና የእኛ ያላደረግነው ካለን ስለምን እንዘገያለን? በጾሙ የተሠራው ሥርዓት የሚያመለክተን የምንድንበት መንገድ ነው እኮ! ስለዚህ ከዛሬ ሁለት ሺሕ ዓመታት በፊት በቀራንዮ መስቀል ላይ የተሰራው የማዳን ሥራ ለእያንዳንዳችን መሆኑንና እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለዘወትር የሚያገለግል መሆኑን ተረድተን አሁኑኑ በእምነት እንቀበለውና መዳናችንን በእምነት እናውጅ፡፡ በጾሙም ጌታ ያደረገልንን የማዳን ሥራ እያሰብን እናምልከው፤ ሰውነታችንን በጾም አዋርደን ፊቱን እንፈልግና ራሳችንን እንመርምር፣ ሕይወታችንን እናስተካክል፣ በመንፈሳዊ ኃይልም እንሞላ፤ በጾማችን ወቅት ካለን ላይ ለድኾችና ለተቸገሩ በማካፈልም በጾም ሰበብ መቆጠባችንን ትተን በእምነት መጽደቃችንን በምግባር እየገለጥን የታዘዝነውን እንፈጽም፡፡ እንዲህ ከሆነ ጾመናል፤ የዐቢይ ጾም መልእክትም ገብቶናል በሕይወታችንም ተግባራዊ ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡

               

11 comments:

 1. are u serious??? have your bosses (protestants) taken the footsteps of catholic church to fast it? nice!!! u will have no option

  ReplyDelete
 2. Satan has been won. The blog started to be confused,going out of its mission.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለ ሰይጣን አሸነፈ
   በመጀመሪያ አንተም ለክርስትናና ለእግዚአብሔር ቃል እሩቅ መሆንህን ነው አስተያየትህ የሚያረጋግጠው ። ምክንያቱም ጾም በክርስትና ያለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን አለማወቅህና መካድህ ነው። በሁለተኛ ደረጃ የጽሑፉ ድብቅ መልእክት በራሱ የአንድን እምነት ተቋም የአማኞቿን ለመንቀፍና አላዋቂ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። አንተ ሰይጣን አሸነፈ ብለህ ትደልቃለህ። እኛ ግን ሰይጣን አፈረ ተሸነፈ እንላለን። ለምን ካልከኝ ሰይጣን ጾምን አያስፈልግም ብሎ መናገርም መሞገትም ስለማይችል ነው። በተረፈ ምንም እንሿን ሚሽነሪዎችህ ተልኮህን እየፈፀሙል ያሉ ቢሆንም የጽሑፋቸው መልእክት ስላልገባህ ተናደህባቸዋል። ስለሆነም ሚሽነሪውን እኔ በምፈልገው መንገድ አላስኬዳችሁትምና ደሞዝ ተቀንሶባችኋል በላቸው።

   Delete
 3. "aba selamawoch" enanten aymeleketachihum

  ReplyDelete
  Replies
  1. tikikil somu enesun aymeleketim

   Delete
 4. ምን ማለት ነው?

  ReplyDelete
 5. Good job Aba Selama

  ReplyDelete
 6. Aba selamawech bertu beta tire newu yemtsfut ewunetun ewunet : wushetun wushet eyalachu ende
  Mersha qibusu qal teramedu
  Egziebher ybarkachhu

  ReplyDelete
 7. @Damot
  You have agreed with yourself not to agree with any one. If this article had been posted on one of the pro MK blogs , you would have been the first to clap your hand. But here you are saying the article has hidden mission. Are you fool bro? When truth is told Satan comprises and tries to shift the agenda. You had better think positive.

  ReplyDelete
 8. Mf. Mk, stop to curse some not agree with your idea.

  ReplyDelete