Sunday, February 22, 2015

ቤተ ክርስቲያን በአደጋ ክበብ ውስጥ….(ክፍል አንድ)

                                                  ከዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ  
                               
             “ … በቤተ ክርስቲያን መጻህፍት ላይ ሂስ ማድረግ እንደ ክህደት ስለሚቆጠር
               ብዙ አስተያየት አልዳበረም፡፡ ይህ ባህል ቅዱስ መጽሐፍን ተመራመሩ የሚለው
               መሠረተ ሐሳብ ተመራመርና እመን ከሚለው ንድፈ ሐሳብ በተቃራኒ እመን ግን
               አትመራመር ከሚል ንድፈ ሐሳብ ላይ ይመሠረታል፡፡”

      (ዲበኩሉ ዘውዴ(ዶ/ር)፤ ፍትሐ ነገሥት ፡ ብሔረ ህግ ወቀኖና ፤ 1986፤ አዲስ አበባ ገጽ.82)

    በእርግጥ ይህን ሐሳብ ዶ/ር ዲበኩሉ ዘውዴ ያቀረቡት “እንደኢትዮጲያ ልምድ ስለፍትሐ ነገሥት ዝግጅትና የትርጉም ሥራ ላይ አብርሃም ወልደ ሐናናጥያን ምንም ሚና እንዳልተጫወተ እየታወቀ አለመተቸቱንና እንደወረደ መቀበላችንን በግልጥ ለመናገር በማሰብ ነው፡፡ እውነታው ግን ለፍትሐ ነገስት ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው አሁን ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ማለትም አስተምህሯዊ ችግሯን ፣ አምልኳዊ ጉድለቷን ፣ ሥነ ምግባራዊ ውድቀቷን … በሚበዛ ጎኑ የሚያጸባርቅ ነው፡፡
      ቤተ ክርስቲያን በትውልድና በዘመን መካከል የምታልፍ፥ ሕያው የክርስቶስ አካል ናት፡፡ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን የመሠረተው በተኩላው ጨካኝ ዓለም መካከል እንጂ ከዓለም በማውጣት አይደለም ፤ እንዲሁም ጌታ “ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።” በማለት ጸልይዋል፡፡ (ማቴ.10፥16 ፤ ዮሐ.17፥15) ቤተ ክርስቲያን በክፉው ዓለምና በጠማማው ትውልድ መካከል ከክፋትና ከጥመቱ ሳትተባበር (ሐዋ.2፥40) ራስዋን “ለአንድ ወንድ በድንግልና እንደታጨች ንጽሕት ሴት በቅድስናና በንጽሕና በሐሰተኞች ትምህርት ያልተበከለች ሆና ራስዋን ለክርስቶስ ልታቀርብ ይገባታል፡፡” (2ቆሮ.11፥2) ቤተ ክርስቲያን ለአማኞቿ እናትም አባትም ናት፡፡ ለእርሷ ልጆች እንደመሆናችን መጠን (2ቆሮ.6፥13) ስለልጆቿ የህሊና አምልኰ ቅድስና አብዝታ ልትተጋ ፤ እንዲበዛላቸውም በመስቀሉ ርኅራኄ ልትለምናቸው፤ ልትለምንላቸውም ይገባታል፡፡

    ቤተ ክርስቲያን ለዓለም ታበራ ዘንድ “በተራራ ላይ ያለች ከተማ ናትና ልትሰወር አትችልም፡፡” ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ለዓለሙ ሁሉ ልታበራ ሥፍራዋ ከፍታ እንጂ ዝቅታ አይደለም፡፡(ማቴ.5፥14) በብርሃን በከፍታ የምትመላለስ ቤተ ክርስቲያን በጨለማ ልትመላለስ አልተባለላትም፤ አልተፈቀደላትምም፡፡ (ዮሐ.8፥12)  በፍጥረት መጀመርያ እግዚአብሔር  “በጥልቁ  ጨለማ ላይ ብርሃን ይብራ” (ዘፍ.1፥3) እንዳለ እንዲሁ በአዲሱና ከማይጠፋው ከእርሱ በተወለደችው ልደት (1ጴጥ.1፥3) “የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራውን የክርስቶስን ወንጌል” (2ቆሮ.4፥6) እንዳይበራ ጨለማ የሆነውን ያለመታዘዝና የኃጢአትን ሕይወት ድል ለመንሳት ፤ ለማፍረስም (1ዮሐ.3፥8) የተገለጠው ጌታ አገልጋይና ሙሽሪት ናት፡፡
    እንዲህ ያለች ሆና ሳለ ቤተ ክርስቲያን ራስዋን ከተራራው ከመከበርና ከልዕልና ብታወርድ የሚገጥማት መጣልና መናቅ ነው፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን የመፍራት ምሳሌ ሆና ከመታየቷም ባሻገር የማህበረሰቡ አምልኰ እንዳይበላሽና እንዳይነቅዝ የመጠበቅ ኃላፊነት አለባት፡፡             
                                የችግሩ ዋና ምንጭ
      ዛሬ ላይ አግጦና አፍጦ ፍንትው ብሎ ለሚታየው የቤተ ክርስቲያን ችግር በአብዛኛው የሚጠቀሰው “ሥነ ምግባራዊና አስተዳደራዊ ችግር” እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ችግር አብርሖታዊና መዋቅራዊ ሽግግርን ( Structural Transformation) መሠረት በማድረግ የትንሣኤ (Renaissance or Revival) ሥራ ከተሠራ፥  ቤተ ክርስቲያን ወደቀደመ ክብሯ እንደምትመለስና የሐዋርያትን ዘመን ቤተ ክርስቲያን ልትመስል እንደምትችል የሚናገሩ አሉ፡፡ ( ዲ.ን ዳንኤል ክብረት ፤ ስማችሁ የለም ፤ ነሐሴ 2006 ፤ አግዮስ ኅትመትና ጠቅላላ ንግድ ሥራ ሐላ.የተ.የግል ማኅበር ፤ ገጽ.16-17)”
    በተለይም ደግሞ ከዘውዳዊው ንጉሥ መውረድ በኋላ ስለተስፋፋው ዓለማዊነትና “እግዚአብሔር የለሽነት” አስተምህሮዎችንም “ … በዚህ ወቅት እግዚአብሔር የለም የሚለው የክህደት ፍልስፍና በብዙዎች የሠለጠንን ነን በሚሉ ወገኖች በመሰበኩና ካህናትን ጨምሮ ብዙ ክርስቲያኖችንም የዚሁ ፍልስፍና ሰለባ በመሆናቸው ብዙ ክርስቲያናዊ ዕሴቶች ከማኅበረሰቡ ውስጥ ተደምስሰዋል ማለት ይቻላል፡፡” በማለት በግማሽም ቢሆን የእውነተኛ አስተምህሮ ችግር እንዳለም የተጠቆመበት ጊዜ አልጠፋም፡፡ (ሐመረ ተዋህዶ ዘዕሥራ ምእት፤ ማህበረ ቅዱሳን ፤ ሐምሌ 2000፤ አዲስ አበባ፡፡ ገጽ.76)  

    በእርግጥም ይህም ችግር የቤተ ክርስቲያን አንዱ የችግር አካል ነው፡፡ ነገር ግን ለምን ዋናውን ምክንያት እንደምንሸሸው ግልጽ አይደለም፡፡ ምክንያቱም መዋቅራዊ ችግሮችን በማጥናት፥ እጅግ ውብ በሆነ መልኩ ነገሮችን ማደራጀት ይቻላል፡፡ በተለይ አሁን ያለንበት ዘመን የቴክኖሎጂው ጫፍ የተደረሰበት ዘመን ነውና ፥ በብዙ ሰው የሚሠሩ ሥራዎችን በጣም በጥቂት ሰዎችና በቀላል ጉልበት መሥራት የሚቻልበት ዘመን ላይ ነን፡፡ የሰው ኃይል አደረጃጀትን ፣ የበጀት አመዳደብ ፣ የሰው ኃይል ሥምሪት ፣ የቢሮና የመጓጓዣ አደረጃጀት ፣ ምንኩስናንና አሰጣጡን ፣ ብህትውናውንና አነዋወሩን ፣ የበዓላት ብዛትንና አከባበራቸውን ፣ ድንጋጌያቸውን ፣ የጳጳሳት አመራረጥና አሿሿም ፣ በመቀራረብና በመተዋወቅ አሠረ ክህነት መሠጣጠት ፣ የዳታ ቤዝ አለመኖር ፣ በየቤተ ክርስቲያኑ ሥር የሰደደው የመልካም አስተዳደር እጦት ፣ በሥነ ምግባር የመዝቀጡና የመውረዱ ነገር ፣ በየሐገረ ስብከቱ የካህናትና የዲያቆናት ምዝገባ አለመኖር … እነዚህና ሌሎች ነገሮች በራሳቸው የአሁን የቤተ ክርስቲያን አባባሽ ችግሮች ወይም የዋናው ችግር ፍልቃቂ መገለጫዎች እንጂ ዋናና የችግሮቹ መነሻ ምንጭ አይደሉም፡፡
     ሁሌም የቤተ ክርስቲያንን ችግር አንስተን ከብዙ ወገኖች ጋር በግልም በጋራም ስንወያይ፥ ውስጤን የሚነካኝና የሚያስጨንቀኝ ነገር ይህ ነው፡፡ ወደዋናው የችግሩ መንስኤ መሄድን አንፈልግም፡፡   በደፈረሰው ወራጅ ላይ እንከራከራለን እንጂ ምንጩን የማጥራት ሥራ ላይ ለመረባረብ እንገፋፋለን እንጂ አንተባበርም፡፡ ምንጩ ሲጠራ ወራጁም እንደሚጠራ እናውቃለን እንጂ አምነን ለመነሣት ለክፋት ጨካኞችና ለእግዚአብሔር ፍጹም ያደላን አይደለንም፡፡ ከዚህ የሚከፉት ይልቅ ያሉትን ችግሮች ብናይ በአሁን ሰዓት በግልጽ ከሚታዩት ችግሮች አንዱና ዋናው፦ 
1.    እግዚአብሔርን ብቻ አለማምለካችን ነው፡፡   
 የእግዚአብሔር ህዝብ ከእግዚአብሔር ጋር እያለ፥ እግዚአብሔርን አዝኖ የተከተለበት ጊዜ እንዳለ ታላቁ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡ እግዚአብሔር የመጽናናት አምላክ ነው ፤ ከእርሱ ጋር ሆኖ ማንም ያዘነ የለም፡፡ እርሱ “የርኅራኄ አባት የመጽናናት አምላክ” (2ቆሮ.1፥3) ፤ “ኃዘንተኞችን የሚያጽናና አምላክም ነውና” (2ቆሮ.7፥6) ከእርሱ ጋር ሆኖ ምንም አላዘነም፡፡ ሁሉም የእግዚአሔር ቅዱሳንና አማኞች በዚህ ዓለም ሳሉ በመረረ ጥላቻና በከባድ መከራ በተከበቡ ጊዜ አጽናኛቸውና ሁሉን ነገር ተክቶ ከጐናቸው የቆመላቸው አጽናኙ እግዚአብሔር ነው፡፡
       በነቢዩ ሳሙኤል ዘመን የነበረውን የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሁኔታ ጸሐፊው ሲገልጠው  “ … የእስራኤልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግዚአብሔርን ተከተለ።” ይለናል፡፡(1ሳሙ.7፥2) በዚህ ቃል ውስጥ ሁለት ከባድ አገላለጦች አሉ፤ አንዱ የእስራኤል ሁሉ እግዚአብሔርን መከተል ሲሆን ፤ ሁለተኛው ግን እግዚአብሔርን እየተከተሉ ማዘን የሚሉት ናቸው፡፡ መንፈሳዊ ኀዘን እንኳ ከልክ ባለፈ ወይም በሚበዛ ኀዘን መዋጥ አይደለም፡፡ (2ቆሮ.2፥7) የእስራኤል ልጆች ደግሞ ያዘኑት መንፈሳዊ ኀዘን ሳይሆን ከኃጢአታቸውና ከበደላቸው የተነሳ ያዘኑትን ኀዘን ነው ታላቁ መጽሐፍ የሚነግረን፡፡ 
   የእግዚአብሔር ታቦት ለሐያ አመታት በስደት በነበረበት ወራት ሳዖል ይህንን የእግዚአብሔር ኪዳን የመፈለግ ሃሳብ በልቡ አልነበረም፥ ይልቁን ወደጣዖታት ልቡን አዘነበለ እንጂ ፤ በኋላ ላይ ዳዊት ደግሞ እንደሥርዓቱ አልፈለገውም፡፡ ለዖዛ መቀሠፍና ለቤትሳሚስ ሰዎች በመቅሰፍት መመታት (1ሳሙ.6፥19 ፤ 2ሳሙ.6፥7) ዋናው ምክንያት የታቦቱ ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ውጪ ዳዊት ያዘዛቸው ከእስራኤል የተመረጡት ሠላሳው ሺህ ሰዎች እንደሥርዓቱ ከፍልስጥኤማውያን እጅ ወደእስራኤል አለማምጣታቸው ነው፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ታቦት ከአንድ ሥፍራ ወደሌላ ሥፍራ እንዲንቀሳቀስ የታዘዘው በላሞች(በበሬዎች) ትከሻ እንዲጫኑ ሳይሆን (1ሳሙ.6፥12) በሌዋውያን ካህናት ራስ ላይ በማድረግ እንዲጓጓዝ ነበር፡፡ ስለዚህም ታቦቱ በበሬዎቹ ጫንቃ ተጭኖ ሳለ በሬዎቹ ፋነኑ ፤ በፋነኑ ጊዜ ዖዛ ታቦቱ ሊወድቅ ያለ መስሎት ሊደግፍ ሲል ተቀሰፈ፡፡ የቤት ሳሚስም ሰዎች የሆኑት እንዲሁ ነው፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ሥርዓቱ በሬ ሳይሆን አሠራሩ ራሱ ካህናቱ እንዲሸከሙት በሚያመች መልኩና  እነርሱም እንዲሸከሙት ነበር ትዕዛዙና የተደነገገው ሥርዓት፡፡ (ዘጸ.25፥1-22 ፤ ኢያሱ.3፥6)   
       አገልጋይ ሊያገለግል ተጠርቶ ሳለ የአገልግሎቱን ሸክም ለሌሎች እንደማሸከም ያለ ፈሪሳዊ ደንታ ቢስነት የለም፡፡ የአገልግሎቱን አደራ በሌሎች ጫንቃ እያሸከሙ “የአገልግሎቱን ፍሬ የክብር ሽልማት” ላይ ግን በጋራ ለመሸለም  መቅረብ ግብዝነት ነው፡፡ ዳዊት የቃል ኪዳኑ ታቦት በአህዛብ ምድር ያደረገውን ተአምራት ሲሰማ ታቦቱን ለመቀበል ፈርቶ በመጀመርያ በአሚናዳብ ቤት ተወው ፤ ከዚያ ደግሞ ሊወስደው ባለ ጊዜ እንደሕጉ ሳይሆን እንደአህዛብ ልማድ በግዕዛን ላሞች አሸክሞ ለመውሰድ ሰዎችን ላከ፡፡ ሕያው አምላክ ሊገለገል የወደደው ሕያዋን በሆኑት ፍጡራን በሰውና በመላዕክት ነበር፡፡ የሰው ልጅ ግን ሕያው አምላክ በእርሱ ሳይሆን በግዑዝ ፍጡር እንዲመለክ ወደደ፡፡
  ከዚህ የተነሳ የእስራኤል ልጆች የጣዖታቱን ሥርዓት ለታቦቱ እንዳደረጉት እንዲሁ የአህዛብ ልማድ የሆነውን የጣዖት አምልኰንም ተለማምደው ፤ ወርሰው ያመልኩም ነበር፡፡ ስለዚህም ታላቁ መጽሐፍ “ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ ፦ በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እግዚአብሔር አቅኑ፥ እርሱንም ብቻ አምልኩ … ” (1ሳሙ.7፥3) አላቸው ይላል፡፡

    የእስራኤል ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር ሆነው የማዘናቸው ምስጢር ጣዖትን በጉያቸው ይዘው እግዚአብሔርን ለማምለክ ማሰባቸው ነው፡፡ እግዚአብሔርን እያወቁ እንደእግዚአብሔርነቱ ብቻ አለማክበርና አለማመስገን የሚያስተውለውን ልብ ያጨልማል፡፡ (ሮሜ.1፥21) በእርግጥም የቃየል ልብ ጨልሞ የነበረው፥ አቤልን ቀድሞ ለመግደል በማሰቡና በመግደሉ ምክንያት ነው፡፡ ቃየል ግን ልቡን አጨልሞ መሥዋዕትን በእግዚአብሔር ፊት ይዞ ቀረበ፡፡ (ዘፍ.4፥7) የልብ አለመብራት በጨለማ ሥራ በኃጢአት መመላለስን ያሳያል፤ የእስራኤል ልጆች በብርሃኑ በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጠው ጨለማቸውን ማየት አልተቻላቸውም፡፡ ይህ ከባድ ድንዛዜ ነው፡፡  
     ቅዱስ ነቢይ ሳሙኤል ይህን የጨለማ ሥራ ስለመስበር አወሳ፡፡ ከእግዚአብሔርን እየተከተሉ እንዲያዝኑ ካደረጋቸው ከንቱ የጣዖት አምልኰ እንዲርቁ አስጠነቀቃቸው፡፡ ሳሙኤል ልከኛ አገልጋይ ነው ፤ የህዝቡን ነውር አይቶ አልተደራደረም ፤ አልሸቃቀጠምም፡፡ ከእግዚአብሔር የለያቸውን ነገር በግልጥና ምንም ሳይፈራ ነው የተናገረው፡፡  ለእግዚአብሔር ያደላ እውነተኛ መሪ ሕዝቡን ይመራል እንጂ በሕዝብ አይመራም፤ መከራን ሊያመጣ በአይኑ ለተንኰልና ለአድማ አይጠቅስም ፤ ሰላምን ሊያደርግ ደፍሮ ይገስጻል እንጂ፡፡ (ምሳ.10፥10) ስለዚህም “የእስራኤልም ልጆች በኣሊምንና አስታሮትን አራቁ፥ እግዚአብሔርንም ብቻ አመለኩ።” (1ሳሙ.7፥4) እግዚአብሔርን ብቻ ማምለክ ማለት ከእርሱ ውጪ ማንንም አለማየት ፤ ለእርሱ ብቻ መገዛት ማለት ነው፡፡ የእስራኤል ልጆች እግዚአብሔርን ብቻ ማምለካቸውና በፊቱም መሥዋእትን ለማቅረብ ውኃን ማፍሰሳቸው (ፍጹም በመዋረድ ንስሐ መግባታቸው) እግዚአብሔር “አቤንኤዘር” ሆኖላቸዋል፥ ጠላቶቻቸውን እንደአንድ ሰው ተፈጥሮ ሠራዊት ሆኖ መትቶላቸዋል፡፡
   ልክ እንዲሁ፥ ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችን እግዚአብሔር ብቻ አለመመለኩ የወለዳቸው የራሱ ከባባድ ችግሮች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነውና (ዘጸ.20፥6) በእርሱ ትይዩም ሆነ ከእርሱ በታች ማናቸውም ፍጡር ሆነ እርሱን የሚተካከለው ያይደለ እንግዳ ነገር እንዲመለክ ፈጽሞ አይፈልግም፡፡ ከእግዚአብሔር ውጪ ብዙ ነገሮች በሕይወታችን ጌቶች ሊሆኑ ይችላሉ ፤ ነገር ግን ለሁለት ጌታ መገዛትና በሁለት አምላክ ማነከስ አንችልም፡፡ (1ነገ.18፥21 ፤ ማቴ.6፥24) እግዚአብሔር ግን ከእኛ ጋር ፍጹም በአገልግሎት የሚሠራው በቅድስና በፊቱ መቆም ሲቻለን ነው፡፡
     ጌታ ሕይወትን በተመለከተ ከእኛ ምንም አልፈለገም፤ ጠላቶች ፣ ደካሞች ፣ ኃጢአተኞችና የማይገባን ሆነን ሳለን ተቀብሎናል ፤ አገልግሎትን በተመለከተ ግን በፍጹም ንጽዕና እንድንቆም ማዘዙን በብሉይ በዘሌዋውያን የቅድስና መጽሐፍ ላይ ስናይ፥ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ከቃል(ከትምህርት) ይልቅ በሕይወቱ ጌታ ኢየሱስ አስተምሮናል፡፡
    ሙሽሪት ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ሙሽራዋን ማስደሰት የምትችለው ያለዕድፈት ፣ ያለነቀፋ ፣ ያለፊት ማጨማደድም ቅድስትና ነውር የሌለባት ሆና በፊቱ መቆም ሲቻላት ነው፡፡(ኤፌ.5፥27)  ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ዋጋ ስለከፈለላት አብሯት ሊኖር ሙሉ መብት አለው፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ሙሉ ዋጋ በስሟ ክርስቶስ ከፍሎላታልና ከእርሱ ጋር የመኖር ግዴታ አለባት፡፡ ደግሜ እላለሁ፥ ከእርሱ ጋር ብቻ የመኖር ግዴታ ነው ያለባት፡፡ 
    ቤተ ክርስቲያን ለሞተላት ጌታ ራስዋን በፈቃድዋ አሳልፋ ባትሰጥ አስጨንቆ ለሚገዛት ክፉ ራሰዋን አሳልፋ ትሰጣለች፡፡ የክፋት አሠራርና ፍጹም ኃጢአተኝነት በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚነግሰው ወይም የመስቀሉን የማዳን ሥራ እንዳታይ በአይኗ ላይ አዚም ረቦ የሚጋርዳት ከሙሽራዋ ክርስቶስ ጋር ፤ ከአጽናኝዋ መንፈስ ቅዱስ ፍጹም ስትለያይ ወይም ከእርሱ ፊቷን ዘወር ስታድርግ  ነው፡፡
     ቤተ ክርስቲያናችን እግዚአብሔርን ብቻ አለማምለኳ ብዙ ኃጢአቶቿ በአገልጋዮቿና በተከታዮቿ መካከል ለብዙዎች መሳለቂያ ሆናለች፡፡ እኛ እኒህን ግልጥ ነውሮች የምናነሳው ብዙዎች ይህንን የአደባባይ ገመና ሰፋፍነው የአሁኑን የቤተ ክርስቲያን ችግር ከዚህ ስለማይጀምሩት ነው፡፡ እውነት ለመናገር እኒህ ኃጢአቶችና ነውሮች ቤተ ክርስቲያናችን እግዚአብሔርን ብቻ ባለማምለኳ ያገኟት ናቸውና ይመለከቷታል፦ 
….ይቀጥላል

                                             

20 comments:

 1. እንደተለመደው አርቲ ቡርቲ ፅሁፍ ነው። የተጠናወትህ ተሀድሷዊ ልክፍት ነው እንጅ የሚየስቀባጥርህ ይህች ቅድስት ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን ብቻ እንደምታመልክ ቅዱሳንን ደግሞ እንደምታከብር አጥተኸው አይደለም። ደግሞ ይቀጥላል ትላለህ? ሥራ የለህም ወንድም?

  ReplyDelete
  Replies
  1. min aynetu nehe bakehe? yehe sehuf ahun min setet alebet?

   Delete
 2. ሥራ የለህም ወንድም? ይህች ቅድስት ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን ብቻ እንደምታመልክ

  ReplyDelete
 3. ABAZELEBANOSE FROM Atlanta, Regularly, accused for sexual insulting that including to sex with married women. Shameful, he met the women when husband left his home to work. DC, source reporter claimed in very similar case former priest A to Tadess met women in same way. Drastically, this gang members of priest activity heart broken to their follower of Eotc across the USA.

  ReplyDelete
  Replies
  1. So what? who tie to stay in eotc? Do you think this your nonsense nonse false accusations take you to the heaven? if it is, you can continue 70 times 70. If you don't don believe beli what the eotc belives, just leave everything for it's belivers. The reason why I said this idea, when I see you according to your comment message, you are not the eotc believer.

   Delete
 4. waiting impatiently to read the next...
  tnx

  ReplyDelete
 5. አርቲ ቡርቲ ማለት ምንማለት ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. አርቲ ቡርቲ ማለት የማይረባና የማያስፈልግ ኮተት ማለት ነው

   Delete
 6. I am wondering why the writers tries to focus on what Woyane says the problem i? Although people's, particularly priests lost the very trust & respect they used have because of the failing of their own, it is ironic to think who is working to destroy our church. Please read Dr. Aregawi Berhe"s thesis as well as Kesis Asteraye Tsige ' s articles
  By writing, seeming half true study, your plan seem to confuse more. Why don't you talk " Kez" Taddesse?

  ReplyDelete
 7. amerika yalu setochn tesadebe endatilugn enji yaligebugn negeroch alu.I am here in addis.But bizu abatoch...menekosat..deakonat..kesawust...keset gar betedegagami bzimut wedequ sibal enisemalen abaselamawochm yemititsifuachewun anebalehu.setochu feqadegna bayihonu..lekirisitos yetesete maninet binorachew tedegagami tifat balitesifafa nbere.abaselamawoch setoch tedeferu kehone behig yemiteyiq polis yelem ende?...setoch tesimamu kehone degimo amerikan hager yalu bizu setoch gelachewun lemanim new ende yemigelitut?enema kemanebew bemenesat church yemibal hintsa bicha new ende yekerew?bezih agatami ageligayochn siyabalana neger siyaaketatil yenerew daniel girma usa geb alu..ewunet new?kehone eza lalu wendimochachin yelemedewun negere serinet endayaketatil begize zim asegnulachew...abaselamawoch beterefe silemititsfifuachew hulu tebareku!!!

  ReplyDelete
 8. bemar yeletelese merz malet enante nachehu !! Egziabher Yimarachehu !! kewedet endehonachehu ke fireachehu tastawikalachehu. Gin Lemin berasachehu maninet atgeletum..?? Mikniyatum Seitan Yichin betekrstian lemafres enji be ewnet sewochiun silemadan liasib aychilimna !! You have night session at FBI Church...

  ReplyDelete
 9. መልስ መስጠት ፈልጌ ጊዜ በማጣቴ ዛሬ ብሎጋችሁን ስከፍት ፖስት ያደረጋችሁትን ሰርዛችሁታል፡፡ የማታምኑበትን መለጠፋችሁ ትክክል አለመሆኑን ተገንዝባችሁ ከሆነ ያጠፋችሁት ትክክል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ስለ ግብጻውያን ሰማዕታት ጽፋችሁት ስለነበረዉ ጉዳይ የሚከተለውን ልበላችሁ፡-
  “መታሠቢያቸውም በየወሩ በስምተኛው ቀን ዓመታዊ መታሠቢያቸው ደግሞ በየካቲት ፰ ቀን (February 15) ታስቦ እንዲውል ውሳኔ አስተላልፈው ስሞቻቸውንም በመጽሐፈ ስንክሳራቸው ጨምረውታል”
  በመጀመሪያ ይህንን ዜና ለምን ማቅረብ እንደፈለጋችሁ እያሰብኩ በብዙ መንገድ መመልከት እንዳለብኝ ተገነዘብኩ፡፡ ይህ ሰማዕትነት ዓለም ያደነቀውና ከሰው ልጆች ኅሊና በላይ የሆነ በመሆኑ ይህንን በመዘገብ ርካሽ ተወዳጅነትን ለማግኘት ብላችሁ፣ ቀጥሎም ኦርቶዶክሳዊ ነን የሚለውን የሃሰት ሽፋናችሁን ለማጠናከር እንዲሆችሁ ምዕመናንን ለማሳሳት እንዲሁም ዘገባውን ስታስተጋቡ የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከእናንተ ጋር ተመሳሳይ አስተምህሮ ያላት በማስመሰል ተቀባይነትን ለማግኘት … ወዘተ እሳቤ እደሚኖራችሁ አልጠራጠርም፡፡
  በሁለተኛ ደገጃ የቅዱሳን መታሰቢያ አያስፈልግም የምትሉ እናንተ ጠንካራዋቤተ ክርስቲያን ያስተላለፈችውን ውሳኔ ምን ሊያደርግላችሁ አስተጋባችሁት? ለመሆኑ ለቅዱሳን አባቶቻችን የሚደረገውን መታሰቢያ ትቀበላላችሁ? ነው ወይንስ የአስተምህሮ ለውጥ አድርጋችሁ ነው?
  ለጥያቄዎቼ መልስ እፈልጋለሁ፡፡ እናንተ ሁልጊዜም የመናፍቃን ተላላኪና አስፈጻሚ ከመሆናችሁ በላይ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ተሳስታለች ብላችሁ የኮበለላችሁ ፍየሎች ናችሁ፡፡ እናንተ እንደነዚህ ዓይነት ነገሮች ስለማይመለከቷችሁ እንዲሁም ስለማታምኑባቸው ለወደፊቱ ፖስት ባታደርጉ ይሻላችኋል፡፡ እርግጥ ነው የማይገባ ጥቅም እናገኝበታለን ብላችሁ ፖስት አደረጋችሁት፣ በኋላ ደግሞ ከእምነታችሁ ጋር ስለሚጋጭ ሰረዛችሁት፡፡ የእመነት ለውጥ ካላካሄዳችሁ የዚህ ዓይነት ጉዳ ለእናንተ ዓይነቱ አይመችምና ስለሰረዛችሁት ደስ ብሎኛል፡፡

  ReplyDelete
 10. እንዲህ ነው እንጂ መጻፍ ድንቅ ምልከታ ነው

  ReplyDelete
 11. I agree with the central idea of this message. Those of you who label it as 'arti burti' had better to open your eye. Hasty generalization will not take you any where. Do not try to hide the truth.


  ReplyDelete
 12. Why do you delete the post related to Egypt martyrs? I wan wondering why you post it.

  ReplyDelete
 13. yaltadele angol
  hul gize tenkol

  ReplyDelete
 14. የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች የቅዱስ
  ሲኖዶሱ ውሳኔ በፓትርያርኩ መታገዱን
  ተቃወሙ ትላለች ሓራ። የሰንበት ተማሪ በመንፈስ ቅዱስ የተሾመን ፓትርያርክ ያህል የሃይማኖት አባት መቃወም ይችላል እንዴ? አረ ጉድ ነው

  ReplyDelete