Sunday, March 29, 2015

ቤተ ክርስቲያን በአደጋ ክበብ ውስጥ (ክፍል አራት)                                         ከዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ
…….ካለፈው የቀጠለ
1.7.      እንደወንጌሉ ታላቅ መርሖ አለመኖር

1.7.1    መርሖ አንድ፦ “ሂዱ”

     ከወንጌል ትውፊትና ዋና መርሖ አንዱ ሂዱ የሚለው ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን የዕድሜ ልክ ታላቁ ተልዕኮዋም “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ …” (ማቴ.28፥19) የሚለው ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ተዘልላ ተቀምጣ የሚመጡትን ብቻ መጠበቅ የለባትም፡፡ ውኃ በአንድ ቦታ ሲቀመጥ ይሸታል ፤ አማኞችም አንድ ቦታ ሰፍረው እንዲቀመጡ አልተባለላቸውም፡፡ እንደዘር እንዲበተኑና እየዞሩ ወንጌሉን እንዲሰብኩ እንጂ፡፡  (ሉቃ.10፥1 ፤ ሐዋ.8፥4 ፤ 13፥1-4)
   ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያት በትምህርታቸው የገለጡትን የክርስቶስን የማዳን እውነትና የገለጡትን አዲስ ኪዳን መሠረት አድርጋ በዓለም ሁሉ በመሔድ ወንጌልን መናገር ይገባታል፡፡ በእርግጥም የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአፍሪካ ወንድሞችና እህቶቿ ከተወቀሰችው አንዱ ነገር፥ ይህን የታላቁን ጌታ ታላቅ ተልዕኮ ይዛ ጎረቤቷ ያሉትን አፍሪካዊ ወንድሞችና እህቶቿን እንኳ እንደታዘዘችው ሄዳ ማገልግል ሳትችል ቀርታ ምዕራባውያን ከሩቅ አህጉር መጥተው ሰብከው እንደወሰዷቸው በቁጭት ሲናገሩ ተሰምቷል፡፡ ( እንዴት ልብ የሚነካ ቁጭት ነው!!!) እንኳን በሩቅ ላሉት በቅርባችን ላሉት መድረስ አለመቻላችን እንዴት ያለ ከባድ ድንዛዜ ያዘን የሚያስብል የቁጭት ጥያቄ ያጭራል፡፡ (በእርግጥ ዛሬም አልመሸም፡፡ ለአፍሪካ ስደት ፣ ዘረኝነት ፣ ጦርነት ፣ እርስ በእርስ አለመተያየት ፣ ሙስና  … መፍትሔ ለማምጣትና ለማሳየትና እንዲጠቀሙበት እንደጌታ በጸሎት ማሰብና ፍሬውን ማየት … አዎን! አልመሸም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሆይ! ተነሺና ሂጂ!!!)
   ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ያዘዘው ለእርሱ ደቀ መዛሙርትን እንድታፈራ ነው፡፡ ይህም ማለት ቤተ ክርስቲያን የአባላትን ቁጥር በማብዛት ላይ ብዙ መሥራት አለባት ሳይሆን የዚህን ዓለም ክፉ ኃጢአትና ርኩሰት ተጠይፈው የተለዩ ፥ ከበጎ ነገር ጋር የሚተባበሩትን (ሮሜ.12፥9) ፤ “የጨለማውን ሥራ አውጥተው የብርሃንን ጋሻ ጦር የለበሱትን” (ሮሜ.13፥12) ፤ “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ የማይጠመዱትን” (2ቆሮ.6፥14) ፤ “በክርስቶስ ፍርሃት የሚገዙትን” (ኤፌ.5፥21) ፤ “ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር የሚርቁትን” (1ተሰ.5፥22) ፤ “በእውነት ቃሉ የሚኖሩትን” (ዮሐ.8፥31) ደቀ መዛሙርትን ማፍራት ይገባታል ማለት ነው፡፡ ለዚህ ማስፈጸሚያው ዋናው መርሖ ደግሞ ሂጂ ተብላለችና ፈጽሞ መቀመጥ አይገባትም፡፡

Wednesday, March 25, 2015

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ እና ለመጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር ደማቅ አቀባበል ተደረገ

Read in PDF

ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለግል ጥቅማቸውና መንደረተኛ ፖለቲካ በቤተክህነት በኩል አድርጎ ወደ ቤተመንግሥት የሚያደርገውን ግስጋሴ ለማሳለጥ ውስጥ ውስጡን በመናበብ ሲሠሩ የቆዩት አባ ማቴዎስና ማቅ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚችሉትን ያህል የወንዞቻቸውን ሰዎች በቅጥርም በሰበካ ጉባኤ አባልነትም ቦታ ቦታ ሲያሲዙ ከቆዩ በኋላ በሙስና የተጨማለቁትና ብዙዎችን በጉቦ ሲያስለቅሱ የነበሩት የወንዛቸው ልጅ ቀሲስ በላይ መኮንን በፓትርያርኩ ትእዛዝ ከቦታቸው መነሣታቸውንና በቦታቸው ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ መሾማቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ዘመቻ ከፍተው መሰንበታቸው ይታወሳል፡፡ 

ዘመቻቸው የማኅበረ ቅዱሳን ንብረት በሆነው በሐራ ተዋህዶ ላይ ከፍተው የሰነበቱ ሲሆን፣ አባ ማቴዎስ አለኝ በሚሉት የሥራ አስኪያጅነት ሥልጣን ሹመቱን አልቀበልም በሚልና ወደ ቋሚ ሲኖዶስ እወስደዋለሁ በማለት ለማደናቀፍ ሲጥሩና ሲያንገራግሩ፣ ማቅም ሕግ ተጥሷል በሚልና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሆነው አዲስ በተሾሙት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻውን ከፍቶባቸው መሰንበቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከቆራጥ ውሳኔያቸው ማንም ዝንፍ ያላደረጋቸው ቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ በውሳኔያቸው ጸንተው ለሥራው ይመጥናሉ ለውጥም ያመጣሉ ብለው ያሰቧቸውን ሊቀማእምራን የማነንና መጋቤ ብሉይ አእመረን ሾመዋል፡፡ የቅዱስ ፓትርያርኩን ሥልጣንና ትእዛዝ ለመጋፋት መሞከር ዛሬ ያበቃለት ይመስላል፡፡
ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ተጀምሮ አባ ማቴዎስ እንደ ኮሶ ከተጣባቸው ዘረኛነትና የአንኮበር ፖለቲካ የተነሣ በእንቢተኛነታቸው ሲታሽ የሰነበተው የሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራአስኪያጅ ሹመት በቅዱስ ፓትርያርኩ ቆራጥ አመራርና ቀጥተኛ ትእዛዝ ተፈጻሚ ሆኖ በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለተሾሙት ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ ለአቀባበሉ አዳራሹ ከአፍ እስከ ገደፉ የሞላ ሲሆን ወንበር መቀመጫ ጠፍቶ የቆሙ ሰዎች ይታዩ እንደነበር በስፍራው የነበሩ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በፓትርያርኩ ቀጥተኛ ትእዛዝ ለተሾሙት ሰዎች የተጻፈላቸው ደብዳቤ በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ መነበቡን የገለጹት ምንጮች፣ በሹመቱ የተከፉትና ሁል ጊዜ ድብቅ ዓላማቸውን ለማሳከትና የመንደር ፖለቲካ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ተንጠላጥለው ለማራመድ የሚፈለጉት አባ ማቴዎስና ብጤያቸው አባ ቀሌምንጦስ በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ብዙዎችን አነጋግሯል፡፡ በዚህም ትልቅ ትዝብት ላይ የወደቁ ሲሆን ማንነታቸውን አጋልጠዋል፡፡ በመሆኑም አዲስ የተሾሙት ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች በፓትርያርኩ ቀጥተኛ ትእዛዝ የተሾሙ ሥራ አስኪያጆች ሆነዋል፡:

Tuesday, March 24, 2015

የአባ ቀለምንጦስ የአካሄድ ስህተትና የማቅ መሸበር ምክንያቱ

Read in PDF


ያበራል እውነቱ ከቤተክህነት
የቀሲስ በላይ መኮንን ከሥልጣን መነሳትና የእነ ሊቀ አእምራን የማነ ዘመንፈስ እንዲተኩ መመረጥ አስመልክቶ የሁኔታዎች ሂደትና አፈጻጸም እንደሚከተለው ተዳሷል። ውኃ ከጥሩ ነገር ከሥሩ. እንዲሉ። የቀሲስ በላይ ዓይን ያወጣ ሙስና የፈጠረው ጩኸት ያስተጋባው አባ ቀሌምንጦስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከመሾማቸው በፊት ነበረ። ከሹመታቸው በኋላ የቀሲስን ዓይን ያወጣ ሙስና በተመለከተ ከቅዱስ ፓትርያሪኩ ጋር ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ አባ ቀሌምንጦስ ትንሽ ጊዜ ይሰጠኝ በማለታቸው ለጊዜው ባለበት ቆመ።
ይሁን እንጂ ከተወሰኑ ወራት በኋላ ራሳቸው አባ ቀሌምንጦስ ወደ ቅዱስነታቸው መጥተው ይህ ሰው  (ቀሲስ በላይ)መውረድ አለበት፤ ጩኸት በዛ። በቅዱስነትዎ በኩል  የሚጠቁሙት ሰው አለ ወይ? ብለው ይጠይቃሉ። ቅዱስነታቸው ለጊዜው ላስብበት ብለው ይለያያሉ። በቀጣዩ ጊዜ አባ ቀሌምንጦስ የራሳቸው ሦስት ሰዎችን መርጠው ያቀርባሉ። ሦስቱም ሰዎች የማቅ አባላት ነበሩ። እነዚህ ሦስት ሰዎች ታሪካቸው ሲጠና ሁለቱ ክህነት የሌላቸው፤ ከሦስቱ አንዱ ደግሞ ክህነት ያለውና በዘመናዊ በኩል ግን አራተኛ ክፍል እንኳን ያልደረሰ መሆኑ ይረጋገጣል። በመሆኑም ሦስቱም ለዋና እና ለምክትል ሥራ አስኪያጅነት የሚያበቃ መሥፈርት ሳያሟሉ ይቀራሉ። ስለሆነም በቅዱስነታቸው በኩል በቤተ ክርስቲያንዋ መንፈሳዊ ትምህርትም
ሆነ በዘመናዊ (አካዳሚ) ትምህርት መሥፈርት ያማሉት ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስና መጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር ይቀርባሉ። ይኽንኑ ተከትሎ ባለው ህጋዊ አሠራር መሠረት የሹመት ደብዳቤያቸው በዋና ሥራ አስኪያጅ በኩል ተፈጻሚነት እንዲኖረው ቅዱስነታቸው ለዋና ሥራ አስኪያጁ መመሪያ ይሰጣሉ።

Friday, March 20, 2015

በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት፤ የቀሲስ በላይ መሻርና የሊቀ ማእምራን የማነ መሾም በማቅ መንደር ሽብር ፈጠረበሙስና የተዘፈቀውና እጅግ የተጨማለቀው የቀሲስ በላይ አስተዳደር ለሙሰኞች ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጥሮ በርካታ ድኾች አገልጋዮችን፣ ጉቦ እየበላ በአየር ላይ በማንሳፈፍ፣ ሕገ ወጥ ዝውውር በማድረግ ከደረጃ በማውረድ ከሥራ በማገድና በመሳሰለው የዝርፊያ ስልቶቹ ሲያስጨንቅና ሲያውክ ለበርካታ ወራት ከቆየ በኋላ ከሥልጣን እንዲነሣ መደረጉን የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ ሐራ ዘገበ፡፡ ሐራ ሙሰኛው ሥራ አስኪያጅ ሲሾሙ ተበሳጭቶ “የፓርላማ ተመራጩ ሊቀ አእላፍ በላይ መኰንን የአዲስ አበባ /ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ” በማለት ዘግቦ የነበረ ሲሆን፣ የመሻራቸው ዜና በአባ ማቴዎስ በኩል ሲደርሰው ግን በሐዘን ስሜት “የፓርላማ ተመራጭ” የሚለውንና ሲሾሙ የቀጸለላቸውን “ማዕርግ” አንሥቶላቸው “የአ/አበባ /ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን ከሓላፊነታቸው ተነሡ፤” ሲል ነው የዘገበው፡፡ ይህም በግልጽ የሚያሳየው ቀሲስ በላይ ማቅ በመጀመሪያ ያሳያቸውን ጥላቻ ለማስወገድ ማቅ እንደሚፈልገው ሆነው የሥልጣን ዘመናቸውን መጨረሻቸውን ነው፡፡ ለዚያ ነው ሊቃውንቱና ካህናቱ የፍትሕ ያለህ እያሉ ጩኸት ሲያሰሙ የማቅ ብሎግ ሐራ አንድም ቀን ምንም ትንፍሽ ያላለው፡፡
በቀሰስ በላይ የአስተዳደር ዘመን ለግል ጥቅሙና ለሥልጣኑ እንጂ ለቤተክርስቲያንና ለአገልጋዮቿ ደኅንነት ግድ እንደሌለው ያሳየው ማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት በሙስና በጉቦ በዘረኛነት ሕገ ወጥ አሰራሮችና የአስተዳደር ብልሹነቶች ማለቃችን ነው እያሉ ድምፃቸውን ሲያሰሙ “አይሰማም” በሚል ዝምታን መርጦ መቆየቱ የማኅበሩን ትክክለኛ ማንነት ገሃድ ያወጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ስለአንዳንድ ደብሮች ሙስና ሲዘግብም የዘገባው ዋና ነጥብ ሙስናው ሳይሆን ለማቅ ያልተመቸው የዚያ ደብር አለቃ ወይም ጸሐፊ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል፡፡ 

Wednesday, March 18, 2015

ዝማሬዎቻችን በወንጌል ጐዳና እየተጓዙ ነው የዘማሪ ገ/ዮሐንስ፣ የዘማርያት ጽጌረዳና ዘርፌ እውነተኛ ዝማሬዎች በጥቂቱ ሲቃኙዝማሬዎቻችን ከጊዜ ወደጊዜ ከፍተኛ ለውጥ እየታየባቸውና ለሕዝበ ክርስቲያኑ መንፈሳዊ መነቃቃትን እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ የክርስቶስን አዳኝነት የሚሰብኩ፣ መንፈሳዊ ቆራጥነትንና ጀግንነትን በማወጅ ክርስቲያኖች ሁሉ ስለክርስቶስና ስለወንጌል እንዲጀግኑ እንጂ እንዳይፈሩ የሚያደፋፍሩ ዝማሬዎች በስፋት እየፈሰሱ ነው፡፡ የሕዝበ ክርስቲያኑን መንፈሳዊ ረሃብና ጥማት እያስወገዱና እያረኩ እንዳሉም ዝማሬዎቹ ካላቸው ተደማጭነትና ተቀባይነት መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለዛሬው በቅርቡ ተደማጭነት እያተረፉ ካሉ ዝማሬዎች የዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገብረ ጻድቅ፣ የዘማሪት ጽጌረዳንና የዘማሪት ዘርፌ ከበደን ጥቂት ዝማሬዎች ለአብነት እንዳስስ፡፡

“ዘፀአት ነው ለሕዝቡ” የሚል ስያሜ የተሰጠው የዘማሪ ገብረ ዮሐንስ ቍጥር 2 የዝማሬ ሲዲ ውስጥ ከተካተቱት ድንቅ ዝማሬዎች መካከል አንዱ “አብ የተከለው” የሚል ነው፡፡ ርእሱ እንደሚመሰክረው ዝማሬው ጌታችን በተናገረው ሕያው ቃል ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል” (ማቴ. 15፥13) በሚለው ቃል ላይ፡፡ በዚህ ቃል አዝማችነት የተዋቀሩት የመዝሙሩ ስንኞች በሰማዩ አባት የተተከለ ክርስቲያን ሕይወቱ የድል፣ የጽናት፣ የውጤት መሆኑን ያመለክታሉ፡፡ ይህም የሚሆነው የወይን ግንዱን ኢየሱስ ክርስቶስን የተደገፈ ሕይወት ስለሚኖረው ነው፡፡ የዝማሬው አዝማች እነሆ
አብ የተከለው አይነቀልም
ያድጋል በጸጋ ለዘለዓለም
የወይን ግንዱን የተደገፈ
ያልፋል ሁሉንም እያሸነፈ
ሌላው የዘማሪው ድንቅ መዝሙር “ኢየሱስ ልበል ኢየሱስ እርሱ ነው ሕይወቴ
                                   የምኖርበት ተስፋ እርሱ ነው ዕረፍቴ
   ያለጌታ ብኖርማ እንዴት እሆናለሁ
   ስለስሙ ብነቀፍም ነፍሴን እሰጣለሁ
ይህ ዝማሬ ከጥቂት ዓመታት በፊት “ኢየሱስ” ብሎ ስሙን መጥራት እንደሌላ በሚያስቆጥርበት ማኅበረሰብ ውስጥ የተዘመረ መሆኑን ስናስብ፣ ምንም እንኳ ስሙ መጠራቱ የሚያስቈጣቸው ቢኖሩም ነገሮች እየተለወጡ መሄዳቸውን ግን ያሳያል፡፡ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በሊቀ ጳጳስ ደረጃ እንኳ “ኢየሱስ አትበሉ” ሲባል በሰማንባት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ፦

Saturday, March 14, 2015

ሰበር ዜና፦ ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ በሊቃውንተ ጉባኤ ፊት ተጠይቆ ኑፋቄውንና ክሕደቱን አመነከዚህ ቀደም እንደ ዘገብነው ለዘንድሮው የጥምቀት በዓል በተዘጋጀ መጽሔት ላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ የሆነና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም ታይተውም ተሰምተውም የማይታወቁ ኑፋቄዎችን በመዝራት ቤተክህነት ውስጥ ትልቅ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ የሰነበተው፣ በቅዱስ ፓትርያርኩ ስለኑፋቄው የተገሠጸውና ቋሚ ሲኖዶስም ስብሰባ አድርጎ ኑፋቄው በአስቸኳይ ተጣርቶ እንዲቀርብና ምላሽ እንዲሰጥበት ውሳኔ ያሳለፈበት፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስም በፓትርያርኩ በዓለ ሢመት ላይ ከኑፋቄዎቹ አንዱን ነቅሰው “ይበል” በሚያሰኝ ግሩም ቅኔያቸው ለኑፋቄው የቤተ ክርስቲያን ዝምታ እንዲሰበር የቀሰቀሱበት ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ ከብዙ ማንገራገር በኋላ አርብ መጋቢት 4/2007 ዓ.ም. በሊቃወንት ጉባኤ ፊት ቀርቦ የእምነት ክሕደት ቃሉን በመስጠት በጽሑፍ ያስተላለፈወ ትምህርት ኑፋቄ መሆኑንና መሳሳቱን እንዳመነ ምንጮቻችን ገለጹ፡፡

እንደ ምንጮቻችን ከሆነ በዕለቱ የመጽሔት ዝግጅት ክፍሉ አባላት በተገኙበት በሊቃውንት ጉባኤ ተጠይቆ የፈጸመውን ትልቅ ስሕተት በመጽሔት ዝግጅት ክፍሉ ላይ በማላከክና ታይቶ የታተመ ጽሑፍ አስመስሎ በማቅረብ ለማምለጥ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም፣ የመጽሔቱ ዝግጅት ክፍል አባላት በበኩላቸው ቅድመ ኅትመት ሁሉም ጽሑፎች በኮሚቴው አባላት የተገመገሙ መሆኑን በአንድ ድምፅ ገልጸው፣ በግምገማቸው ላይ ኃይለ ጊዮርጊስ ጽሑፉን እንዲያርም የነገሩት መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በምን መንገድ እንደሆነ ለጊዜው ባይታወቅም በበሩ ሳይሆን በሌላ በር ገብቶ ጽሑፉ መታተሙን ኮሚቴው አስረድቷል፡፡ ኮሚቴው በመጽሔቱ ላይ ለወጡት ጽሑፎች እያንዳንዱ ጸሐፊ ለጻፈው ጽሑፍ ኃላፊነቱን የመውሰድ አሠራር እንዳላቸው ታውቋል፡፡ የሊቃውንት ጉባኤው በኃይለ ጊዮርጊስ ጽሑፍ ላይ ከሰባት በላይ ኑፋቄዎችን ነቅሶ ቢያወጣም ወደ ክርክሩ ከመግባቱ በፊት ኃይለ ጊዮርጊስ መሳሳቱን በሊቃውንት ጉባኤው እርምት እንደሚያምን አረጋግጧል፡፡

Tuesday, March 10, 2015

ቤተ ክርስቲያን በአደጋ ክበብ ውስጥ (ክፍል ሦስት)      Read in PDF                                    
ከዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ
(ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጽሁፎቼ ቤተክርስቲያን በአደጋ ክበብ ውስጥ ነች የሚያሰኙዋትን ምክንያቶች እየዘረዘርኩ ነበር። ዛሬም ካቆምኩበት የሚቀጥለውን ክፍል ለአንባቢያን በትህትና አቀርባለሁ። መልካም ንባብ)
1.4  አይን ያወጣ ጉበኝነት

·        ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል፡፡
·        ሹም ሲቆጣ ማር ይዞ እደጁ፥ ደስ ሲለው ማር ይዞ እደጁ፡፡
    በምሳሌነት ይህን ተረት አነሳን እንጂ ከዚህ ተመሳሳይነት ያላቸው ተረቶችና ምሳሌያዊ ንግግሮች በተወሰነ መልኩ በባህላችን ውስጥ ተሰንቅረው ለጉበኝነትና ለመታያ የሚሰጡት ድጋፍ አለ፡፡  
     የእግዚአብሔር ቃል በግልጥ “ፍርድን አታጣምም ፊት አይተህም አታድላ ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና ጉቦ አትቀበል።” (ዘዳግ.16፥19) ይናገራል፡፡ አንድ ሹም ጉቦ ወይም መማለጃን የሚቀበለው እውነቱን ሐሰት ፤ ሐሰቱን እውነት ለማለት ወይም ለማድረግ ነው፡፡ እውነቱን ሐሰት ስንል ጻድቁን ወይም እውነተኛውን እንበድላለን ፤ ሐሰቱን ደግሞ እውነት ነው ስልን ኅጢአተኛውን በጻድቁ ላይ እናሰለጥናለን፡፡
    በእስራኤል ፊት ያለነውር በሞገስና በመወደድ ፤ ያለምንም መማለጃ ይመላለስ የነበረው (1ሳሙ.12፥3) ታላቁ ነቢይ ሳሙኤል ልጆቹ እንደእርሱ የተባረኩ አልነበሩም፡፡ ስለልጆቹ ታላቁ መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ “ልጆቹም በመንገዱ አልሄዱም፥ ነገር ግን ረብ ለማግኘት ፈቀቅ አሉ፥ ጉቦም እየተቀበሉ ፍርድን ያጣምሙ ነበር።” (1ሳሙ.8፥3) ይላል፡፡ ይህ ማለት በሳሙኤል እጅ ትፈረድ የነበረችው የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ መማለጃን በቀኝ እጃቸው በተመሉ (መዝ.26፥10) በልጆቹ ጠማማ ፍርድ በሌላ መንገድ ትፈርስ ነበር ማለት ነው፡፡
   ያለምንም ማባበያ ቃል ዛሬ ቤተ ክርስቲያን በጉበኞችና መማለጃን በሚወድዱ፥ ንብ የማር ቀፎን እንዲከብብ ተከብባለች፡፡ አምስትና ሐምሳ ሺህ ለመጠየቅ አምስቱን አዕማድ ፣ ሰባት ሺህ ለመጠየቅ ሰባቱን ምስጢራት ፣ አስር ሺህ ለመጠየቅ አስሩን ሕግጋት በኰድ የሚጠቀሙ ፌዘኛና አታላዮች ቤተ ክርስቲያናችን ከተከበበች ውላ አድራለች፡፡ ዛሬ የተመረጡ አድባራት ላይ ከድቁና እስከ ቁምስና  ለመመደብ ጉቦው ራሱ በልዩ ጨረታና በእሽቅድምድም ነው የሚሰጠው፡፡ ከተመደቡ በኋላ ደግሞ ለመቆየትና ላለመነሳት ምጽዋተ ሙዳይ እየሰበሩና ካላቸውና ከወዛቸው እየቆረሱ መማለጃ የሚሠጡትን ስንሰማ ጆሮ ጭው ሊያደርግ ይችላል፡፡
    ከብሔርተኝነት በማይተናነስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምናየው አስጨናቂ ነውር ጉበኝነትና መማለጃን መውደድ ነው፡፡ ነገር ግን ጉቦን በመቀበል የችጋረኛውን ፍርድ የሚያጣምሙትን እግዚአብሔር ኃጢአታቸው የጸና እንደሆነ ይናገራል፡፡ (አሞ.5፥12)
   “መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚያራግፍ …  እርሱ ከፍ ባለ ስፍራ ይቀመጣል ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል እንጀራም ይሰጠዋል፥ ውኃውም የታመነች ትሆናለች።” (ኢሳ.33፥15-16)
    ፍትሐ ነገሥቱም “ሳይገባው ገንዘብ ተቀብሎ የሚሾም ኤጲስቆጶስ ቢኖር ይለይ፡፡ …” (አን.5 ቁ.177)
ምን እናድርግ?
1.4.1    በልክ መኖር

     ኑሮዬ ይበቃኛል አለማለትና ባለጠግነትን አብዝቶ መሻት “በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም እንደሚጥል” (1ጢሞ.6፥9) የእግዚአብር ቃል በግልጥ ያስቀምጣል፡፡ ይልቁን የእግዚአብሔር አገልጋዮች “ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል።” (ምሳ.30፥8 ፤ 1ጢሞ.6፥8) ሊሉ ይገባቸዋል እንጂ ወይም ፍትሐ ነገሥቱ እንደሚለው “ኤጲስቆጶስ ከምግብና ከልብስ የሚበቃውን ያህል የሚወስድ ይሁን ለሚያገለግል ዋጋው ይገባዋልና ፡፡ ልብሱን አያሳምር ሥጋውን ለመሸፈን የሚበቃውን ያህል ይውሰድ እንጂ፡፡ ሌላ ጌጥ የሚያስፈልግ አይደለም፡፡” (ፍትሐ ነገሥት አን.5 ቁ.127) እንደሚለው ራሳቸውን ልከኞች አድርገው ሊኖሩ ይገባቸዋል፡፡
   መጥምቁ መለኮት የጌታን መንገድ ለመጥረግ ይመላለስ  በነበረበት ዘመኑ ልብሱ የግመል ጠጉር ፤ ወገቡ ጠፍር የታጠቀ ፣ ምግቡ አንበጣና የበረሃ ማር ፣ ቤቱ ምድር በዳ መሆኑ ምን ይሆን የሚያስተምረን? እንደዛሬው አገልጋዮች ሽቶ የተገቡና ውድ የሆኑ ቀሚሶችንና የእጅ ፣ የአንገት መስቀልን መልበስና መያዝ ይሆንን? ወይስ በሁለትና በሦስት ከተማ ያማሩ ቤቶችን መገንባት? ወይስ ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻቸውን ቤት ትተው የራሳቸውን በከተማው መካከል ቪላ መገንባት ነውን? ወይስ ጰጵሶ ብዙ ሚሊየን ብር በባንክ አስቀምጦ ወለዱን ቁጭ ብሎ መብላት ነውን? ወይስ መንኩሶ ሳይሰሩ ቁጭ ብሎ ፍትፍት እያማረጡ መብላት ነውን?
     በእውኑ “ለቀበሮዎች ጕድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም” (ሉቃ.9፥58) ያለው ጌታ ምንን ይሆን የሚያተምረን? ሁሉን እያለው ድሃ የሆነው ጌታ ሕይወቱ አይዘልፈንንምን?
   አዎ! “ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነውና” በኑሯችን ልከኞች እንሁንና በኑሯችን ጌታችንን እናክብረው ፤ ከጉበኝነትም እንራቅ፡፡

1.4.2   ከክፉ መጎምጀት መራቅ

             “የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም
                           ሁሉ ተጠበቁ” (ሉቃ.12፥15)
             “ … አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን
              ወጉ። አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ … ” (1ጢሞ.6፥10-11)

 በልክ ለመኖር መሠረቱ ልብን ከሚከፍለው ክፉ መጎምጀትና ራስን በክፉ ከሚወጋ ምኞት መጠበቅ ፤ መጠበቅና መሸሽ ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ ላይ በምንኩስናና በተለያየ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ዘርፍ መሳተፍ ለቅዱስ አገልግሎት ከመሠማራት ይልቅ ምድራዊ ሀብትን ማግኛ አጭር መንገድ ሆኗል ብንል ምንም ግነት የለበትም፡፡ ክፉ መጎምጀት ወይም ስግብግብነት  ወደዘላለም ጥፋት የሚመራ ኃጢአት ነው፡፡
   በአንድ ወቅት በእስራኤል ልጆች የበረሃ ጉዞ ታሪክ “በመካከላቸውም የነበሩ ልዩ ልዩ ሕዝብ እጅግ ጐመጁ … ” (ዘኁል.11፥4) ይለናል ታላቁ መጽሐፍ፡፡ የእነዚህ ሕዝቦች ፍጻሜ ግን “የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ መቅሠፍት እጅግ መታ። የጐመጁ ሕዝብ በዚያ ተቀብረዋልና የዚያ ስፍራ ስም የምኞት መቃብር ተብሎ ተጠራ።” (ቁ.33-34) በማለት በአጭሩ ያስቀምጥልናል፡፡ እንኪያስ የዛሬዎቹም አገልጋዮች ለጉበኝነትና የሌላውን ቤት የሚያሳያቸው አንዱ ነገር ክፉ መጎምጀት ወይም ስግብግብነት ወይም ራስ ወዳድነት ነውና ከዚህ መራቅ ይገባል፡፡

Thursday, March 5, 2015

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የመሪነት ኀላፊነታቸውን በተገቢ እየተወጡ አለመሆኑን አስታወቁ፡፡

  •  Read in PDF 
  •   ምንጭ ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ
  •  
  • ቤተ ክርስቲያን ሰውም እግዚአብሔርም በሚወድደው መንገድ ልትመራ ይገባል፡፡  
  • ·        የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሁለተኛ ዓመት በዓለ ሢመት ተከበረ፡፡
  • ·        የቤተ ክርስቲያን የመሪነት አቅም አጠያያቀቂ መሆኑ በፓትርያርኩ ተገልጧል፡፡
  • ·        ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስሕተት ትምህርቶችን፣ ሙስናንና በዓለም አቀፍ ደረጃ በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ የተመለከቱ ቅኔዎችን በበዓሉ ላይ አቅርበዋል፡፡፡
የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ/ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓጥርያርክ ሆነው የተሾሙ መሆኑን አንባብያን ያስታውሳሉ ብለን እናስባለን፤ የካቲት 24 ቀን 2007 ዓ/ም ደግሞ የፓትርያርኩ በዓለ ሢመት ሁለተኛ ዓመት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከብሯል፡፡ በዓሉ የአንድ ፓትርያርክ በዓለ ሢመት ሳይሆን የቤተ ክርስቲያን በዓል እንደመሆኑ መጠን ቤተ ክርስቲያን በአግባቡ በማስተባበርና በማደራጀት ብትጠቀምበት ትልቅ የትምህርት መድረክ ሆኖ ሊያገለግል ስሚችል እንደቀላል እድል ታይቶ ምእመናን የማይሳተፉበትና ካህናትም በግዴታ ትቀጣላችሁ ተብለው ለእንጀራ ብቻ የሚያከብሩት የፖለቲካ በዓል አይነት ሆኗል፡፡ በበዓሉ ላይ ልብሰ ተክህኖ ለብሰው፣ መስቀልና ጽና ይዘው የመጡ አንዳንድ ካህናት ካልመጣችሁ ትቀጣላችሁ፣ ከሥራ ትባረራላችሁ እየተባሉ ስለመጡ ሲያማርሩ ሰምተናቸዋል፡፡ አንዳንዶችም በዓሉ በጸሎት ከተከፈተ በኋላ ልብሰ ተክህኖአቸውን በፌስታልና በቦርሳ እየከተቱ ወጥተው ሲሄዱ አይተናል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የበዓሉን ጠቃሚነት ለካህናትና ለምእመናን ከማስረዳት ይልቅ በፓርቲ አካሄድ አይነት ሰውን ባላመነበት በዓል ላይ በግድ እንዲሳተፍ ማድረግ ተገቢ ስላይደለ ካህናት ደስተኛ ስላልሆነ ነው፡፡
የበዓሉ ሥርዐተ-ጸሎት መዝ.109 ቁጥር 4 ላይ “መሐለ እግዚአብሔር ወኢይኔስሕ አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሢመቱ ለመልከጼዴቅ እግዚአብሔር በየማንከ” በአማርኛ “እግዚአብሔር ማለ፤ አይጸጸትም፤ እንደመልከጼዴቅ ባለሹመት አንተ የዓለም ካህን ነህ፤ እግዚአብሔር በቀኝህ ነው” የሚለው መዝሙር በዲያቆን ከተዘመረ በኋላ ከዮሐንስ ወንጌል ምዕ. ቁጥር 15-24 ያለው ተነብቧል፤ ነገር ግን የወንጌሉም ሆነ የመዝሙረ ዳዊት መልእክት አልተሰበከም ወይም መልእክቱ ተብራርቶ አልቀረበም፡፡
እኛ እንደተረዳነው ከመዝሙረ ዳዊት የተሰበከው ቃል ለክርቶስ የተነገረ ትንቢትና በክረስቶስ የተፈጸመ የክርስቶስን የዘለዓለም ካህንነት የሚገልጥ ቃል ነው፤ የዕለቱ ተረኛ የሆነው የሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካህናት ይህን መዝሙር የመረጡት ክርስቶስን ለመስበክ ፈልገው ከሆነ ተገቢ ነው እንላለን፤ የአባ ማትያስ ክህነት እንደመልከጼዴቅ ባለ ሹመት የዘለዓለም ነው ብለው ከሆነ ግን አባ ማትያስ እንደማንኛውም ሰው ሟች ስለሆኑ ሞት በሚከለክለው ሕይወት የተሾሙ እንጂ እንደ ክርስቶስ የዘለዓለም ክህነት የላቸውምና አስተካክሉ ብለን በክርስትና ፍቅር እንመክራቸዋለን፡፡

Tuesday, March 3, 2015

በቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ሲመት ላይ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የኃይለ ጊዮርጊስን ኑፋቄ በቅኔ ተቹ
የቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ሲመት በዛሬው ዕለት የካቲት 24/2007 ዓ.ም. ተከብሮ ውሏል፡፡ በዚሁ በዓለ ሲመት አከባበር ላይ መልእክት ካስተላለፉት አባቶች መካከል አንዱ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሲሆኑ ብፁዕነታቸው ሰሞኑን በቤተክህነት ግቢ ውስጥ መነጋገሪያ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የሆነውን ደፋሩ፣ ጥራዝ ነጠቁና ጨዋው ኃይለ ጊዮርጊስ ማኅበረ ቅዱሳን የጫነውንና በቤተ ክርስቲያን ስም ምእመናን ላይ ያራገፈውን የኑፋቄ ጽሁፍ በግሩም ቅኔ ተችተዋል፡፡ እኚህ አባት የስብከተ ወንጌል መምሪያ ሊቀ ጳጳስ እንደመሆናቸው እንደ ኃይለጊዮርጊስ ያለ ከሓዲና መናፍቅ በቤተ ክርስቲያን ስም በወጣ መጽሔት ላይ አሹልኮ ያስገባውን ኑፋቄ ማየታቸው ስላልቀረ በጽሁፉ የተሰማቸውን ሀዘንና ቁጭት በቅኔ ገልጸዋል፡፡ ቅኔው እንዲህ የሚል ነው፡፡
“ለምንት አርመምኪ ኒቅያ ወኢተናገርኪ ምንተ
ዘእም ድንግል ይትሌቃሕ ፈጣሪ ንጽሐ ባሕርይ መክሊተ”
ሲተረጎምም፦
“ኒቅያ ሆይ ለምን ዝም አልሽ? ለምንስ አልተናገርሽም?
ፈጣሪ ከድንግል የባህርይ ንጽሕና ገንዘብን የሚበደር ሆኗልና” እንደ ማለት ነው፡፡
ይህ ቅኔ ቁጭት የተሞላና እንዲህ አይነቱን ኑፋቄ በኒቅያ የነበሩ አባቶች ቢሰሙ ኖሮ እኛ እንደተኛነው ተኝተው አያድሩም ነበረ፡፡ እኛ ለሃይማኖት ጽናት መከራከርና መምዋገት ስላልቻልን እንግዲህ እነኛ ደገኛ አባቶች ተቀስቅሰው መጥተው ችግሩን ይዩልን የሚል ይዘት ያለው ይመስላል፡፡ ቅኔው በዚያ ሐሰተኛ ጽሑፍ ኃይለ ጊዮርጊስ ከዘራቸው ኑፋቄዎች አንዱን ነጥብ በግልጽ ያስቀመጠ ነው፡፡ በዚህም ብፁዕነታቸው ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፡፡ አባት ማለት እንዲህ የሚገሥጽ እንጂ እውነት በአደባባይ በሐሰት ስትተካ ዝም ብሎ የሚመለከት አይደለምና፡፡
ይህ የቅኔ ምላሽ የተሰጠበትና በኒቅያ ለሀይማኖት የተከራከሩት አባቶች ቢኖሩ ኖሩ ከአርዮስ ደምረው ውግዘት ያስተላልፉበት እንደ ነበር የማይጠረጠረው ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ በስሙ የወጣው ጽሑፍ በዝርዝር የተጻፈ ሳይሆን እንደ እምነት መግለጫ በነጥብ የተቀመጠ በመሆኑ የዕርሱ ብቻ ሳይሆን ከጀርባው ያለ አይዞህ ባይ ኃይል ሃይማኖት ሳይሆን እንደማይቀር ይታመናል፡፡ አንዱና ብፁዕነታቸው በቅኔ የተቹት የእምነት መግለጫው እንዲህ የሚል ነው “እመቤታችን ጥንቱን ሰው ሲፈጠር ንጽሕት ዘር ሆና ተወልዳለች፡፡ ጥንተ አብሶ የለባትም የልጇም ንጹሐ ባሕርይነት ከምንጩ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ፍጹም ንጽሕና የተነሣ ነው፡፡” (ገጽ 36)

Sunday, March 1, 2015

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሙስና ለበከቱ ባለሥልጣናቷ ምቹ መኖሪያ ለእውነተኛ አገልጋዮቿ ግን እስር ቤት እየሆነች ነው፡፡


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለይም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሕግ እይታ ውጪ የሆነና ሕግ የማይገዛው ሀገረ ስብከት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ ህገ ወጥነት ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ የሚሠራበት ቤተ ሙስና ከሆነም ሰነባብቷል፡፡ ፓትርያርኩ ባሉበት ከተማ የሚገኘውና የፓትርያርኩ ሀገረ ስብከት የሆነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በድብቅ ሳይሆን በግልጽ ጉቦን እንደ መተዳደሪያ ቢዝነሳቸው የያዙና ወርኃዊ ደመወዛቸውን የዘነጉ ሹመኞች ያሉበት ሀገረ ስብከት ነው፡፡ አሁን አሁንማ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል እንደነበረውና ሙስናን በሚዲያ ሲኮንንና ሲያወግዝ ንጹሕ ይመስል እንደነበረው በኋላ ግን ዋነኛው ሙሰኛ ሆኖ እንደ ተገኘው እንደ ገብረ ዋህድ ዋነኞቹ ሙሰኞች ስለሙስና አስከፊነትና ሙስናን ስለመዋጋት አቋም መያዛቸውን በቤተክርስቲያን ሚዲያዎች እየለፈፉ መሆናቸውን ስንሰማ፣ ብዙዎቻችን ገብረ ዋህድ በየት ዞሮ መጣ? ለማለት ተገደናል፡፡ ምክንያቱም ሙስናን በአፋቸው እየኮነኑ በገቢር ግን በዚያው ቅጽበት እንኳ ስንቶችን በዝውውርና አየር ላይ በማንሳፈፍ፣ በማገድና በጉቦ እስኪያስለቅቁ ድረስ ደብዳቤያቸውን አፍኖ በመያዝ እጅግ በርካታ የሆኑ፣ በመረጃ የተደገፉና ክስ የቀረበባቸው የሙስና ፍይሎች ላይ ለጥ ብለው ተኝተው ለሙሰኞቹ ሽፋን በመስጠት ሙስናን ለመዋጋት ቆርጠው የተነሡትንና መሥዋዕትነትን እየከፈሉ ያሉትን እውነተኞችን ደግሞ እያንገላቱ እንደሚገኙ ስናስብ እጅግ አዝነናል፡፡ እንዲህ ለማለት የበቃነው በታኅሣሥና ጥር ወር ዕትም ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ላይ በፊት ገጽ ከተጻፉት ዜናዎች አንዱ “የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሙስናን ለመቋቋም ቆርጦ መነሣቱን አሳወቀ” የሚለውን ካነበብን በኋላ ነው፡፡

ዜናው ታኅሣሥ 27 ቀን/2007 ዓ.ም. ፓትርያርኩ በተገኙበት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሀገረ ስብከቱ ሥር ላሉ አድባራትና ገዳማት ለሚገኙ አስተዳዳሪዎች ጸሐፊዎችና ምክትል ሊቃነ መናብርት የተለያዩ መመሪያዎችን ማስተላለፋቸው የተዘገበበት ነው፡፡ እኛን የገረመን ከዚህ ቀደም በእውነተኛ መረጃ ላይ አስደግፈን ካወጣነው ዘገባ የተነሣ በሁሉም ስፍራ ባይሆንም ጥቂት ቦታዎች ላይ የማስተካከያ እርምጃዎች እንደመውሰድ ያሉትና እኛም ወቀሳውን ትተን ያበረታታናቸው ሊቀአእላፍ በላይ መኮንን በአሁኑ ጊዜ “ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር” ብለው ወደቀደመው ሙስናዊ ግብራቸው ጭልጥ ብለው መግባታቸው በገሃድ እየታወቀ ለጋዜጣው የሰጡት መግለጫ አስገርሞናል፡፡ “የእንትን ኣይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” እንዲሉ አበው፡፡