Sunday, March 1, 2015

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሙስና ለበከቱ ባለሥልጣናቷ ምቹ መኖሪያ ለእውነተኛ አገልጋዮቿ ግን እስር ቤት እየሆነች ነው፡፡


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለይም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሕግ እይታ ውጪ የሆነና ሕግ የማይገዛው ሀገረ ስብከት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ ህገ ወጥነት ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ የሚሠራበት ቤተ ሙስና ከሆነም ሰነባብቷል፡፡ ፓትርያርኩ ባሉበት ከተማ የሚገኘውና የፓትርያርኩ ሀገረ ስብከት የሆነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በድብቅ ሳይሆን በግልጽ ጉቦን እንደ መተዳደሪያ ቢዝነሳቸው የያዙና ወርኃዊ ደመወዛቸውን የዘነጉ ሹመኞች ያሉበት ሀገረ ስብከት ነው፡፡ አሁን አሁንማ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል እንደነበረውና ሙስናን በሚዲያ ሲኮንንና ሲያወግዝ ንጹሕ ይመስል እንደነበረው በኋላ ግን ዋነኛው ሙሰኛ ሆኖ እንደ ተገኘው እንደ ገብረ ዋህድ ዋነኞቹ ሙሰኞች ስለሙስና አስከፊነትና ሙስናን ስለመዋጋት አቋም መያዛቸውን በቤተክርስቲያን ሚዲያዎች እየለፈፉ መሆናቸውን ስንሰማ፣ ብዙዎቻችን ገብረ ዋህድ በየት ዞሮ መጣ? ለማለት ተገደናል፡፡ ምክንያቱም ሙስናን በአፋቸው እየኮነኑ በገቢር ግን በዚያው ቅጽበት እንኳ ስንቶችን በዝውውርና አየር ላይ በማንሳፈፍ፣ በማገድና በጉቦ እስኪያስለቅቁ ድረስ ደብዳቤያቸውን አፍኖ በመያዝ እጅግ በርካታ የሆኑ፣ በመረጃ የተደገፉና ክስ የቀረበባቸው የሙስና ፍይሎች ላይ ለጥ ብለው ተኝተው ለሙሰኞቹ ሽፋን በመስጠት ሙስናን ለመዋጋት ቆርጠው የተነሡትንና መሥዋዕትነትን እየከፈሉ ያሉትን እውነተኞችን ደግሞ እያንገላቱ እንደሚገኙ ስናስብ እጅግ አዝነናል፡፡ እንዲህ ለማለት የበቃነው በታኅሣሥና ጥር ወር ዕትም ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ላይ በፊት ገጽ ከተጻፉት ዜናዎች አንዱ “የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሙስናን ለመቋቋም ቆርጦ መነሣቱን አሳወቀ” የሚለውን ካነበብን በኋላ ነው፡፡

ዜናው ታኅሣሥ 27 ቀን/2007 ዓ.ም. ፓትርያርኩ በተገኙበት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሀገረ ስብከቱ ሥር ላሉ አድባራትና ገዳማት ለሚገኙ አስተዳዳሪዎች ጸሐፊዎችና ምክትል ሊቃነ መናብርት የተለያዩ መመሪያዎችን ማስተላለፋቸው የተዘገበበት ነው፡፡ እኛን የገረመን ከዚህ ቀደም በእውነተኛ መረጃ ላይ አስደግፈን ካወጣነው ዘገባ የተነሣ በሁሉም ስፍራ ባይሆንም ጥቂት ቦታዎች ላይ የማስተካከያ እርምጃዎች እንደመውሰድ ያሉትና እኛም ወቀሳውን ትተን ያበረታታናቸው ሊቀአእላፍ በላይ መኮንን በአሁኑ ጊዜ “ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር” ብለው ወደቀደመው ሙስናዊ ግብራቸው ጭልጥ ብለው መግባታቸው በገሃድ እየታወቀ ለጋዜጣው የሰጡት መግለጫ አስገርሞናል፡፡ “የእንትን ኣይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” እንዲሉ አበው፡፡ 
      በጋዜጣው መግለጫቸው ሊቀ አእላፍ በላይ በስብሰባው የተላለፉ መልእክቶች ሙስናን ለመዋጋት ለሚደረገው ጥረት ስለሚኖራቸው አስተዋፅኦ ተጠይቀው ሲመልሱ በፓትርያርኩ የተላለፉ መመሪያዎች በሀገረ ስብከቱ ያሉትን ችግሮች ዘጠና ከመቶ ሊቀርፉ እንደሚችሉ እምነታቸው መሆኑን ገልጸው “በእርግጥ ይህ ሊሆን የሚችለው ካህናት፣ ምእመናንና ወጣቶች ለለውጥ ዝግጁ ሆነው ሲገኙ ነው፡፡ ሙስና የሚፈጸመው በስውር በመሆኑ ይህን ችግር ለመቅረፍ የረቀቀ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ እኛም ይህንን ሥርዓት ፈጥረን ከሕዝቡ ጋር በመኾን  ለውጤት እንበቃለን ብለን እናምናለን፤ ለዚህም ቆርጠን ተነሥተናል፡፡” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ አክለውም “በሀገረ ስብከታችን ሙስና በጣም እንደተስፋፋ ተደርጎ የሚነገረው ሁሉ ትክክል አይደለም ችግር ያለባቸው አካላት እንዳሉ ሁሉ ሥራቸውን ሥራቸውን በሐቅና በንጽሕና የሚያካሂዱ እንዳሉም ሊታወቅ ይገባል” ማለታቸውን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡

ይገርማል!! ንግግራቸውና ሥራቸው ቁርጥ ገብረ ዋሕድን የመሰለው ሊቀ አእላፍ በላይ ሙስናን ለመወጋት “ካህናት፣ ምእመናንና ወጣቶች ለለውጥ ዝግጁ ሆነው ሲገኙ ነው” ብለዋል፡፡ በቅድሚያ እውነት እንነጋገር ካልን ለውጡን እየናፈቁ ያሉት እነዚህ ወገኖች አይደሉም ወይ? ጠዋት ማታ ለአቤቱታ የሀገረስብከቱን ደጅ አጣብበው ያሉትስ እነርሱ አይደሉም ወይ? ይህ እኮ በራሱ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ችግር መኖሩንና ለውጥ እንደሚያስፈልግ አፍ አውጥቶ የሚናገር በቂ ምስክር ነው፡፡ ለለውጥ ዝግጁነት እኮ የጠፋው ከእርስዎ ጀምሮ በሙስናዊ መዋቅሩ ውስጥ ከተሰገሰጋችሁት አልጠግብ ባዮች በኩል ነው፡፡ ከቅዱስ ፓትርያርኩ የተላለፈው ትእዛዝ እስከዛሬ  ተግባራዊ አለመሆኑ በማን ምክንያት ነው? ወይም የማን ችግር ነው? እንደሚያውቁት ብዙ ጊዜ እርስዎ ከሰዓት በኋላ ነው የሚገቡት ጠዋት ላይማ ወደፊት የምንገልጻቸው ደላሎችዎ በጉቦ የተሻለ ገቢ ወዳለበት የዝውውር ጥያቄ ያቀረበውንናየ ሚከፍለውን የገንዘብ መጠን፣ ለእርሱ ሲባልም በሰላም ከተቀመጠበት ደብሩ የሚፈናቀለውን ሰው ማንነትና የሚዘዋወርበትን መንገድ፣ ካስፈለገም በአየር ላይ የሚንሳፈፍበትን ወይም የሚታገድበትን መንገድ አጣርተውና አደራጅተው ይጠብቁዎታል፡፡ ከዚያ ዛሬ የእነ እገሌ ተራ ነው አሰኝተው ጉዳይ ከመስማትና ፍትሕ ከመስጠት ይልቅ ከደላሎችዎ ጋር ይሞዳሞዳሉ፡፡ ምናለ የእስከ ዛሬው እንኳ ቢበቃችሁና አገልጋዮችን ማንገላታታችሁና የጠራራ ፀሐይ ዘረፋችሁ ቢያበቃ? ምነው እናንተን የሚጠይቅ ሕግ ጠፋ? ለመሆኑ ሥራ አስኪያጅነቱን የትርፍ ሰዓት ሥራ ማድረግ ተገቢ ነው ይላሉ? ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነውን አገልጋይ በትርፍ ጊዜ ማስተናገድ ተገቢ ነውን? እርስዎ እኮ ሙስና እየፈጸሙ ያለው በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በሥራ ጊዜዎ ላይ ጭምር ነው፡፡ 

ሌላው አስገራሚ አስተያየትዎ “ሙስና የሚፈጸመው በስውር በመሆኑ ይህን ችግር ለመቅረፍ የረቀቀ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ እኛም ይህንን ሥርዓት ፈጥረን ከሕዝቡ ጋር በመኾን ለውጤት እንበቃለን ብለን እናምናለን፤ ለዚህም ቆርጠን ተነሥተናል፡፡” የሚለው ነው፡፡ በርግጥ ሙስና ተጠያቂነት ስላለበት በስውር የሚሰራ ወንጀል መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ግን ሕግ ስለሌለ ሙስና በስውር ሳይሆን በግልጽ ነው እየተፈጸመ ያለው፡፡ የሙስና አቀባባዮችና ደላሎች እነማን እንደሆኑ በግልጽ ይታወቃል፡፡ ማን ስንት ብር ተጠይቆና ጉቦ ሰጥቶ ከደብር ወደ ደብር፣ ምንም ከማይበላበት የሥራ መደብ ወደሚበላበት የሥራ መደብ እንደተዘዋወረ፣ ማን ደግሞ እንደተባረረ ወይም እንደ ታገደ፣ ማን በማን በኩል ጉቦውን እንደሰጠ ስንት ብር እንደሰጠ ሁሉ በግልጽ ይታወቃል፡፡ ይህ ሁሉ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ የእናንተ ጆሮ ባዳ ሆኖባችሁ ካልሆነ በቀር እያንዳንዱ ሙስናዊ ሥራችሁ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ካሉ አገልጋዮች እይታ የተሰወረ አይደለም፡፡ ስለዚህ ሙስናን ለመዋጋት በቅድሚያ የሚያስፈልገው የእናንተ ቁርጠኝነት እንጂ የረቀቀ ሥርዓት መዘርጋት አይመስለንም፡፡ ደግሞስ  እናንተው ሙሰኞቹ የምትዘረጉት “የረቀቀ ሥርዓት” ሙስናውን የረቀቀ ለማድረግ ካልሆነ በቀር ሙስናን ለመዋጋት ምን ያህል ይረዳል ብለው ነው?

ደግሞስ ከየትኛው ሕዝብ ጋር ነው የምትሠሩት? ሕዝቡ እኮ እናንተን ትቷችኋል፡፡ እንደ እናንተ ቢሆን ሃይማኖቱን እየለወጠ ወደሌላ በኮበለለ ነበር፡፡ እርግጥ ጥቂት የማይባሉ ሕዝበ ክርስቲያን ወደሌሎች የእምነት ድርጅቶች ፈልሰዋል፡፡ ለዚህም በዋናነት የምትጠየቁት እናንተ ናችሁ፡፡ ያልሄደውም በሃይማኖቱ ጸንቶ ከእናንተ በተሻለ ሁኔታ ሃይማኖቱን ለመጠበቅ ዘብ የቆመው እናንተ ስላላችሁለት ሳይሆን ፈጣውን እያሰበና ቤተክርስቲያኑን ስለሚወድ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ከሕዝቡ ጋር እንሠራለን የሚል ማምለጫ በር ከሚከፍቱ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ከሆኑና በሙስናዊ አሰራራችሁ እጅግ ከተማረሩ የቤተክርስቲያኒቱ መምህራን፣ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ መሪጌቶች ጋር ብትሰሩ ነው የተሻለ ውጤት ሊመጣ የሚችለው፡፡ የዚያን ጊዜ ሕዝቡም የሚገባውን አስተዋፅኦ በማበርከት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት እምነታችን ጽኑ ነው፡፡ ለሁሉም ግን ሙስናን ለመዋጋት ቆርጣችሁ መነሣታችሁን መቼም ቢሆን አናምንም፡፡ ምክንያቱም ይህን መግለጫ ከሰጡ በኋላ እንኳን ብዙ የሙስና ወንጀሎች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች በእጃችን አሉና፡፡

ከሁሉም የገረመን “በሀገረ ስብከታችን ሙስና በጣም እንደተስፋፋ ተደርጎ የሚነገረው ሁሉ ትክክል አይደለም ችግር ያለባቸው አካላት እንዳሉ ሁሉ ሥራቸውን ሥራቸውን በሐቅና በንጽሕና የሚያካሂዱ እንዳሉም ሊታወቅ ይገባል” ያሉት ንግግርዎ ነው፡፡ መቼም ሌላው ቢቀር ሕግ ተምረዋል፤ በፖለቲካውም ውስጥ ፖለቲከኛና የሕዝብ ውክልና አለዎት፤ በዚህ ላይ ቄስም ነዎት ታዲያ እንዲህ ብለው ሲናገሩ ኅሊናዎ ፈጽሞ አልከሰስዎትም ይሆን? በእኛ እምነት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስለተፈጸመውና እየተፈጸመ ስላለው ሙስና እንኳን ተጋኖ ሊቀርብ ሊነገር የሚገባውም በወጉ ገና አልተነገረም ባዮች ነን፡፡ ስንቱስ ይነገራል? የቱ ተነገሮስ የቱ ይቀራል? እስካሁን እየተነገረ ያለው ያልተጋነነና ትክክለኛ መሆኑን ከዚህ ቀደም ጥቂቱን በመረጃዎች አስደግፈን እንዳቀረብን ሁሉ አሁንም በመረጃዎች እያስደገፍን ማቅረባችንን እንቀጥል፡፡

በቅድሚያ ምንም ዓይነት ዝውውር እንዳይደረግ ቅዱስ ፓትርያርኩ አዘው ነበር፡፡ ነገር ግን ጥለውት የነበረውን እገዳ ማን እናዳነሣው ሳይታወቅ እርስዎ ሊቀ አእላፍ በላይ፣ ደላሎችዎና የጥቅም ባልደረቦችዎ የዝውውሩን መስኮት፣ ምን መስኮት አሁንማ የዝውውር በር ብንለው ይቀላል የዝውውሩን በር ከፍታችሁ ሃይለኛ ቢዝነሳቸውን እያጧጧፋችሁት አይደለምን? የዝውውሩን ገበያ የተቀላቀሉት ደግሞ እንደተለመደው አነስተኛ ገቢ ካላቸው ደብሮች ገቢያቸው ከፍ ወዳለ ደብሮች ለመግባት የሚፈልጉ በዋናነት አለቆችና ጸሐፊዎች ናቸው፡፡ ከእገዳው በኋላ በከፈታችሁት የዝውውር በር ለአለቃ 150 ሺህ ብር፣ ሲጠይቁ፣ ለጸሀፊ ደግሞ 40 እና 50 ሺህ ብር እየተጠየቀ ነው፡፡ 

ይህ “ቢዝነስ” እየተሠራ ያለበት አንዱ መንገድ ደግሞ ጥሩ ገቢ ባላቸው ደብሮች ውስጥ ቦታቸው በጥብቅ የሚፈለጉ ቁልፍ ቦታዎች ላይ በሚገኙ የሥራ መደቦች የሚገኙ ሠራተኞች ላይ እግድ በመጣል ነው፡፡ ከደብሩ ሙሰኛ አለቃ ወይም ጸሀፊ ለሊቀ አእላፍ በላይ ሹክ ይሉና እገሌ አስቸግሯል ይላሉ፡፡ ሊቀ አእላፍ በላይም አግዱት ይላሉ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሙሰኛ ሠራተኞች እግድ ሲጣል እጅግ ደስ ነው የሚላቸው፤ ምክንያቱም እግዱን ለማጣራት ወደ ደብሩ ስለሚላኩና ሰራተኞቹ በማጣራት ስም ውሎ አበልና ከአጋጅም ከታጋጅም በየፊናቸው ለእናንተ እንመሰክራለን በሚል የሚቀበሉት ጉቦ አለና፡፡ ሊቀአእላፍ በላይም በእግዱ በጣም ደስተኛ ነው የሚሆኑት ምክንያቱም የታገደውን ሠራተኛ ቦታ በሙስና በመሸጥ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ያገኛሉና፡፡ ምናልባትም በማጣራቱ የታገደው ሰው መታገድ የሌለበት መሆኑ ቢረጋገጥም ሊቀአእላፍ በላይ እግዱን በነጻ አያነሱም፡፡ ታጋጁ ደብዳቤ ይጻፍለት ዘንድ ጉቦ መስጠት አለበት፡፡ ስለዚህ በሁሉም አቅጣጫ ተጠቃሚ ናቸው፡፡

የሚያሳዝነው ንጹሕ ሰው ይታገድና ወይም ዝውውር ይጻፍለትና ቦታው በሙስና ለጨቀየና ከአንዱ ደብር ወደሌላው ደብር በምእመናንና በካህናቱ ጩኸት ብዛት ለተነሣ ሰው ይሰጣል፡፡ በቅርቡ እንኳ ከአውግስታ ማርያም በጩኸት የተነሣው ሙሰኛ ጸሐፊ በጩኸት ብዛት ወደ ቁስቋም ማርያም እንዲዛወር ተጻፈለት፡፡ በሰላም የተቀመጠው የቁስቋም ማርያም ቤተክርስቲያን ጸሐፊ ደግሞ ያለበደሉ ወደ ሸጎሌ ኪዳነ ምህረት እንዲዛወር ተጽፎለታል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ዝውውር የሚደረገውና ለሙሰኞች የተሻለ ሌላ የመብያ ቦታ የሚፈለገው ሙሰኞቹ ለሀገረ ስብከቱ ባለሥልጣናት ከሚበሉት ስለሚያጋሩ መሆኑ አንድና ሁለት የለውም፡፡

በገንዘብ ዝውውሩ በኩል ድለላውን እያጧጧት ያሉት ዳዊት፣ ማሙዬ እና ታዴዎስ የተባሉት የሀገረ ስብከቱ ሰራተኞች ሲሆኑ፣ የጥቅም ተካፋዮቹ ደግሞ በዋናነት አስተዳሩ እና ሥራ አስኪያጁ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በእነዚህ በቤተክርስቲያን ትምህርት ውስጥ ባላለፉ ጨዋዎችና ሙሰኞች ሊቃውንቱ እየተመዘኑና በመማራቸው እየተዋረዱ ከፍተኛ እንግልት እየተፈጸመባው ይገኛል፡፡ ለመጥቀስ ያህል አንደኛው ደላላ ታዴዎስ በስብሰባ ላይ “የአቋቋምና የድጓ መምህራን ለቤተ ክርስቲያን ምን ይሠሩላታል?” ሲል በቀበና መድኃኔ ዓለም አለቃ ላይ የተናገረ ሲሆን፣ እርሳቸውን ከቦታቸው ለማስነሣት ጥረት እያደረገ መሆኑም ይታወቃል፡፡ እንደእርሱ ያሉ ጨዋዎች በሊቃውንቱ ላይ አፋቸውን እንዲያላቅቁ በእነርሱ ላይ አለቃ አድርጎ የሾማቸው አስተዳደር ምን ያህል ፀረ ቤተክርስቲያን መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጎንደሮች ላይ ዘመቻ የተከፈተ እስኪመስል ድረስ እነርሱን የማፈናቀል ሥራ በስፋት እየተሠራ ነው፡፡ ለምሳሌ በፋኑኤል ቤተክርስቲያን ሊቀ ጠበብት የሆኑት ሰው ወደ ሊቄ ሚካኤል በማዘወር ጉዳይ አስፈጻሚ አድርገዋቸዋል፡፡  ጉቦ ለከፈለ አንድ ዲያቆንም ያለሙያው የሊቀ ጠበብቱን በጀት ሰጥተዋል፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው በመሃይምናንና ጊዜ በሰጣቸው ጨዋዎች በመሆኑ ብዙ ሊቃውንት ነገሩን በሐዘን እየተመለከቱና ይህን ዘመን እየኮነኑት ይገኛሉ፡፡ እንዲህ እያደረጓቸው ባሉት ላይም አንዱ ብሶተኛ ባለቅኔ የሚከተለውን ቅኔ ተቀኝቷል፤
ጎንደር ዳዊት ወበላይ ያስተሐቅሩኪ ለኪ
እስመ ወይነኪ ኢሰትዩ ወኢጠዐሙ እክለኪ

ትርጉሙ ሊቀ አእላፍ የተባሉት በላይና ዳዊት እንዲያስተረጉሙትና ምስጢሩን እንዲረዱት ለእነርሱው እንተውላቸው፡፡ እነርሱ ያጣጣሏቸው ሊቃውንት ምን ያህል እንደሚያስፈልጉና እነርሱ ባይኖሩ ምን ያህል እንደሚያጎድሉ ሊረዱ ይችላሉ፡፡ በእርግጥ ጥፋት ያለባቸው ከሆኑ ጎንደሮች እንደማንኛውም ዜጋ እነርሱ አይጠየቁ የሚል እምነት ከቶ የለንም፤ ነገር ግን ከዚህ ውጪ እየተደረጉ ያሉ ነገሮች ቤተክርስቲያን ውስጥ ዘረኛነትን ከዚህ በበለጠ የሚያነግሥ ነውና እንዲህ ያለው ድርጊት መቅረት አለበት፡፡

ለሥራ አስኪያጁም ሆነ ለደላሎቻቸው ምቹ ሁኔታን የፈጠረው የሊቀጳጰሱ የብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የክትትል ማነስ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ብፁዕነታቸው ወደእርሳቸው የደረሰውን ደብዳቤ ወደሚመለከተው አካል እንዲፈጸም ይመሩበታል፡፡ ነገር ግን ጉቦኞቹ ጉቦ ካልበሉበት በቀር ለመልቀቅ እንቢ ስለሚሉ ደብዳቤው እዚያው እየታሸ ይቆያል፡፡ ባለጉዳዮችም ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን በከንቱ 4 ኪሎ በመመላለስ ያባክናሉ፤ ለብዙ ችግርና ውጣ ውረድም ይዳረጋሉ፡፡ ስለዚህ ይህን ጉዳይ ብፁዕነታቸው የሚከታተሉበትና የተመራው ደብዳቤ በቶሎ ተፈጻሚ እንዲሆን የሚያደርጉበት ሁኔታ ቢመቻች ትልቅ ለውጥ ይመጣል ብለን እናስባለን፡፡ አሊያ ማማረሩ ወደ እርሳቸውም መዞሩ አይቀርም፡፡  

ሌላው በሙሰኞች ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎችና የሚጻፉ ደብዳቤዎች ተግባራዊ ሲሆኑ አይታይም፡፡ ይህም የሚሆነው በሚጻፉ ደብዳቤዎች ላይ በሙስናዊ ሰንሰለቱ የተሳሰሩ ባለሥልጣናት ጉዳዩ ተፈጻሚ እንዳይሆን በአቤቱታ አቅራቢዎች ላይ ልዩ ልዩ የማዳከም ሥራን ስለሚሠሩ ነው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የብሔረ ጽጌ ማርያም አስተዳዳሪ የአባ ነአኩቶ ለአብ የሙስና ወንጀል ነው፡፡

ይህ በሙስና የተጨማለቀ ግፈኛ መነኩሴ በቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት ላይ ለዓመታት የፈጸመውን መዝበራ በተመለከተ ከአጥቢያው ምእመናን 13 ገጽ ከደብሩ ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር 12 ገጽ ደብዳቤ ለሀገረ ስብከቱና በግልባጭም ለሌሎች የቤተክህነት ክፍሎች ተጽፎ የነበረ ሲሆን፣ በንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ የብፁዕ ወቅዱስ ልዩ ጸሐፊ ፊርማ የወጣው ደብዳቤ በደብሩ ውስጥ ስለደረሰው የአስተዳደር በደልና የንብረት ብክነት ተመርምሮና ተጣርቶ ሕጋዊ ውሳኔ እንዲያገኝ ከፓትርያርኩ መታዘዙን ይገልጻል፡፡ መስከረም 23/2007 ዓ.ም. የወጣው ደብዳቤ ግን እስካሁን ምንም ያመጣው ለውጥ የለም፤ የተደረገ ምርመራና ማጣራትም የለም፤ ይህም ማንአለብኝ ባዩ ነአኩቶ ለአብ በጥፋቱ እየበረታ እንዲሄድ አድርጎታል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ ያዘዙት ትእዛዝ የት እንደደረሰ፣ በምርመራው ምን ውጤት እንደ ተገኘ መጠየቅ ካልተቻለ፣ ደብዳቤ መጻፉ ብቻውን የሚያመጣው ለውጥ የለም፡፡ ከዚህ ቀደም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ የተከሠተውን ችግር በአካል ተገኝተው ያለውን ችግር በመመርመራቸውና በመፍታታቸው አንዳንድ ውሳኔዎችም በመተላለፋቸውና ተግባራዊ በመሆናቸው ጥሩ ለውጥ ታይቷል፡፡ ለምሳሌ አለቃው ጡረታ እንዲወጡ መደረጉ አንድ ጥሩ ውሳኔ ነው፡፡ የነአኩቶ ለአብ ጉዳይም እንዲህ ዓይነት ውሳኔን የሚጠይቅ ነውና ቅዱስ ፓትርያርኩ አንድ ነገር እንዲያደርጉ አቤት ያሉ ሁሉ የሚጠብቁት ጉዳይ ነው፡፡ ውሳኔ ማሳለፍና ደብዳቤ መጸፍ ብቻም ሳይሆን ውሳኔው ተግበራዊ መሆኑን መከታተል ይገባል፡፡ አሊያ እነ ቀሲስ በላይ ሆነ ብለው ደብዳቤው ላይ በመተኛት በቅዱስነትዎ ላይ ቅሬታ እየተፈጠረ ይሄዳል የሚል ሥጋት አለን፡፡   

የዚህ ሐሳዊ መነኩሴ ጉድ መቼ በዚህ ያበቃና? ህግ ባለበት አገር ከመቶ በላይ ካህናትን በማን አለብኝነትና “በፈጣጣ” መኪና ሸልሙኝ በማለት በአደባባይ ደመወዛቸውን ቀምቷል፡፡ በጊዜው ለመብቱ የቆመ አንድ ሰባኪ በዚህ ጉዳይ አልተባበርም በማለቱ በሊቀ አእላፍ በላይ እና በነአኩቶ ለአብ ሴራ በሰላም ከሚያገለግልበት ከብሔረ ጽጌ ወደ ጠሮ ሥላሴ እንዲዛወር ተደርጓል፡፡ ነአኩቶ ለአብ ከቤተ ክርስቲያን የሚዘርፈው ብር አልበቃ ብሎት ታሪክ በማይረሳው  ሁኔታ ከአገልጋዮች ላይ ነጥቆ ሲወስድ ሊቃውንቱ የሕግ ያለህ ቢሉም፣ እነ ሊቀአእላፍ በላይ ከሊቃውንቱ ጩኸት ይልቅ ከነአኩቶ የሚያገኙት ጥቅም ስላየለባቸው ጩኸቱን አፍነዉት ቀርተዋል፡፡ ለጊዜው ነው እንጂ አንድ ቀን ለድሃና ለፍትሕ የቆመ ሰው ሲሾም ሰሚ ያገኛል፡፡ እነቀሲስ በላይ ደግሞ በሕግ ይጠየቃሉ፡፡ የ200 ወይም የ300 ብር ሞባይል የሰረቀ ሰው ከ3 - 4 ዓመት በሚደርስ እስራት እየተቀጣ ባለበት አገር የብዙዎችን ኑሮ አዛብቶ የሚኖር የመነኩሴ ቀማኛ ግን በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ብር በአደባባይ ዘርፎ ቤተክህነቱም ቤተ መንግስቱም ዝምታን መርጠዋል፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረስብከት አድባራትና ገዳማት የምንገኝ ግፉዓን

8 comments:

 1. IT IS GOOD INFORMATION

  ReplyDelete
 2. ዘገባው እውነት ነው ግን ማን የስተካከለው? ስራ አስኪያጅ ተብሎ የተመደበው ሰውየ በቤተ ክርስቲያን ትምህርቱ ሳይሆን በኮታ ነው ጉቦ አቀባባዮቹም የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የሌላቸው ጊዜ የሰጣቸው ደናቁርት ናቸው።

  ReplyDelete
 3. I don think they are called 'balesiltanat' but abatoch! ... in the title.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yetsafew Kiristian Meseleh Ende?

   Delete
 4. Also criticize the BIG BOSS OF THE THIEVES "Haile Abraha"

  ReplyDelete
 5. ለአብ ቀሌሚንጦስ ትፍስህተ ልቡና አልቦቱ፤
  ውልዱ ዳዊት፤በላይ ፤ማሙሽ ወታዴዎስ አምጣነ ሀሙ ይሙቱ
  በህማም ሙስና /ጉቦ / ዘሆሳእና አልቦቱ
  አንድ ደጀ ጠኝ የቅኔ ባለሙያ ሊቀጳጳሱ በመኪና ከቢሮ ሲወጡ ያንጎረጎረው ቅኔ መነሻ በማድረግ አስተያየተን ልለግሳችሁ ፈለግኩ ዘመን በሰለጠነበት ጊዜ ሰው እንደ እንስሳት በዋጋ በውድ በርካስ የሚሸጥበት ሀገር የት ነው ከተባለ አዲስ አበባ የት አከባቢ ከተባለ 4ኪሎ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ሰው የሚነገድዱት እነማናቸው ከተባለ ሃይማኖተ አልባው ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ በላይ መኮነንና ደላላዎቹ ማሙዬ፤ታዴዎስና ዳዊት ሲሆኑ በዚህ መስርያቤት ሰዎች ሥራ የሚቀጠሩት ባላቸው እውቀት ሳይሆን ተበድረውም ቢሆን በሚያቀርቡት ጉቦ መሆኑ የዋ፤ላ ያደረ ጭጋር በመሆኑ በየዓመቱ ቅዱስ ሲኖዶስ አንዴ ሊቀጳጳስ አንዴ ሥራ አስኪያጅ ቢያቀያይርም ሁሉ ኩሉ አረዬ ወህቡረ አለወ ሆኖ በአለባበሳቸውና አለሁ አለሁ ማለታቸው የተሸሙት የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጆች ሁሉም የተለያዬ አይነት የሌብነት ዘዴ የሚፈጥሩና እከካቸውን ከማራገፍ ውጭ ለድርጅቱ የማያሳብ በመሆናቸው በተለይ ቀሲስ በላይ መኮነን ለስርቆት ሲል የፈጠረው ዘዴ ከአሁን በፊት ያለፉት ወፍራም ጉበኛ ሥራአስኪያጆች ያላገኙት ዘዴ ያለመመዘኛ እና ፈጠና ቅጥር እንዳይፈጸም በማለት ቅዱስ ፓትርያርኩ የሰጡትን መመሪያ ባለማክበርና በስራ አለም ላይ ያልነበሩት ግለሰዎች በስራ እንደነበሩ በማስመሰል ቦታው ሳይገለጽ አሁን ከሚሰሩበት ቦታ ውደ እገሌ ደብር ተዛውረው በእገሌ ስረና በጀት በማለት አዲስ ጠቀጣሪ /ገንዘብ ከፋይ ሠዎች ብር 4000 እና 3000 በመቅጠር ከፍተኛ ገንዘብ መሰብሰቡን ባንዳንድ አድባራት ደግሞ የሙዳዬ ሙጽዋት ዘረፋ አበል በመሆን፤ ሰዎችን አግዶ ገንዘብ ማስከፈል ፤ገንዘብ ተቀብሎ ተራ ሰራተኞችን ከነበሩበት ደብሮ ደመወዝ እየተከፈላቸው በአዳዲስ አድባረት ሒሳብክፍል ጸሐፊ አድርጎ መመደብ አዳዳሲ የዘረፋ ረቂቅ ስልቶቹ ዚሆኑ እነዚህ የሌብነት መንገድ ች የሚጠርጉልት በአንደኛ ደረጃ ታዴዎስና ማሙዬ ናቸው በቅርቡም በ2 ተከታታይ ቀናት ከ84 ሰራተኞች በላይ በራሱና ደላላዎቹ ድብቅ ስምምነት መሰረት ያዛወራቸው ሲሆን ከነዚህ ውስስጥ ከብር 1700እስከ 200 አድገው ከተዛወሩ ሰራተኞች ከፍተኛ ገንዘብ ከተቀበለ በሃላ ደመወዛችን ተቀንሶብን መዛወር የለብነም ከሚሉትም ጉዳያችሁ ፍርድቤት ስለማይታይላችሁ እንደራደር በማለት ገንዘብ እየከፈሉ የተቀነሰ ደማወዛቸውን እንዲስተካከልላቸው በማድረግላይ ናቸው በተለይ በዚህ ወቅት የከፋ የዘረፋ አይነት እየታየዬ ስለሆነ ሊቀውንቱ እያለቀሱ ጉቦኞች የሌብነት አይነት እያስተማሩ ስለሆነ ሰልፍ መውጣት አለበን በማለት የጻፋችሁት ሁሉ አውነት በመሆኑ በእጅጉ መደሰቴን አገልጻለሁ

  ReplyDelete
 6. Haile abrha beakal hedo yemusena lemed yakafelachew yegerji Giorgis Aleqa sayferetetu yeyazulen!

  ReplyDelete