Tuesday, March 3, 2015

በቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ሲመት ላይ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የኃይለ ጊዮርጊስን ኑፋቄ በቅኔ ተቹ
የቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ሲመት በዛሬው ዕለት የካቲት 24/2007 ዓ.ም. ተከብሮ ውሏል፡፡ በዚሁ በዓለ ሲመት አከባበር ላይ መልእክት ካስተላለፉት አባቶች መካከል አንዱ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሲሆኑ ብፁዕነታቸው ሰሞኑን በቤተክህነት ግቢ ውስጥ መነጋገሪያ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የሆነውን ደፋሩ፣ ጥራዝ ነጠቁና ጨዋው ኃይለ ጊዮርጊስ ማኅበረ ቅዱሳን የጫነውንና በቤተ ክርስቲያን ስም ምእመናን ላይ ያራገፈውን የኑፋቄ ጽሁፍ በግሩም ቅኔ ተችተዋል፡፡ እኚህ አባት የስብከተ ወንጌል መምሪያ ሊቀ ጳጳስ እንደመሆናቸው እንደ ኃይለጊዮርጊስ ያለ ከሓዲና መናፍቅ በቤተ ክርስቲያን ስም በወጣ መጽሔት ላይ አሹልኮ ያስገባውን ኑፋቄ ማየታቸው ስላልቀረ በጽሁፉ የተሰማቸውን ሀዘንና ቁጭት በቅኔ ገልጸዋል፡፡ ቅኔው እንዲህ የሚል ነው፡፡
“ለምንት አርመምኪ ኒቅያ ወኢተናገርኪ ምንተ
ዘእም ድንግል ይትሌቃሕ ፈጣሪ ንጽሐ ባሕርይ መክሊተ”
ሲተረጎምም፦
“ኒቅያ ሆይ ለምን ዝም አልሽ? ለምንስ አልተናገርሽም?
ፈጣሪ ከድንግል የባህርይ ንጽሕና ገንዘብን የሚበደር ሆኗልና” እንደ ማለት ነው፡፡
ይህ ቅኔ ቁጭት የተሞላና እንዲህ አይነቱን ኑፋቄ በኒቅያ የነበሩ አባቶች ቢሰሙ ኖሮ እኛ እንደተኛነው ተኝተው አያድሩም ነበረ፡፡ እኛ ለሃይማኖት ጽናት መከራከርና መምዋገት ስላልቻልን እንግዲህ እነኛ ደገኛ አባቶች ተቀስቅሰው መጥተው ችግሩን ይዩልን የሚል ይዘት ያለው ይመስላል፡፡ ቅኔው በዚያ ሐሰተኛ ጽሑፍ ኃይለ ጊዮርጊስ ከዘራቸው ኑፋቄዎች አንዱን ነጥብ በግልጽ ያስቀመጠ ነው፡፡ በዚህም ብፁዕነታቸው ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፡፡ አባት ማለት እንዲህ የሚገሥጽ እንጂ እውነት በአደባባይ በሐሰት ስትተካ ዝም ብሎ የሚመለከት አይደለምና፡፡
ይህ የቅኔ ምላሽ የተሰጠበትና በኒቅያ ለሀይማኖት የተከራከሩት አባቶች ቢኖሩ ኖሩ ከአርዮስ ደምረው ውግዘት ያስተላልፉበት እንደ ነበር የማይጠረጠረው ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ በስሙ የወጣው ጽሑፍ በዝርዝር የተጻፈ ሳይሆን እንደ እምነት መግለጫ በነጥብ የተቀመጠ በመሆኑ የዕርሱ ብቻ ሳይሆን ከጀርባው ያለ አይዞህ ባይ ኃይል ሃይማኖት ሳይሆን እንደማይቀር ይታመናል፡፡ አንዱና ብፁዕነታቸው በቅኔ የተቹት የእምነት መግለጫው እንዲህ የሚል ነው “እመቤታችን ጥንቱን ሰው ሲፈጠር ንጽሕት ዘር ሆና ተወልዳለች፡፡ ጥንተ አብሶ የለባትም የልጇም ንጹሐ ባሕርይነት ከምንጩ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ፍጹም ንጽሕና የተነሣ ነው፡፡” (ገጽ 36)

የእውነት ጩህ ጩህ ያሰኛል፡፡ ነገሮች በዚህ ከቀጠሉ እና ይህን የመለሰ ትልቅ ኑፋቄ በዝምታ የሚታለፍ ከሆነ ቤተክርስቲያኒቱን ወደ ባሰ ውድቀት ይከታታል፡፡ ይህንን አባባል እንደ ትምህርቷ የምትቀበል ቤተክርስቲያን ካለች በግልጥ የማርያምን አምልኮ መጀመርዋን ስለሚያመለክት ከቤተክርስቲያን ቁጥር መደመሩም ያበቃላታል፡፡ ጌታችን ንጹህ ባህሪ የኖረው ከማርያም የተነሳ ነው ካልን አለም ከተፈጠረ ጀምሮ የሌለበትን ንጽህና ማርያም ሰጠችው ያሰኛል፡፡ ይህ እስከዛሬ ድረስ ከተሰሙ ምንፍቅናዎች ሁሉ የከፋ ያደርገዋል፡፡ እንደ ኃይለጊዮርጊስ ጽሁፍ ለመዳናችን ዋናው ነገር የጌታችን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መሞት መሆኑ ይቀርና የማርያም መወለድና “ክርስቶስን መቀደስ” ይሆናል ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ ንጹኅ ባህሪን ከድንገል ማርያም ከነሳ ሁሉን ማድረግ የማይችል ደካማ ፍጡርና ለንጽህናው እንኳን የማርያምን መወለድ ሲጠባበቅ የነበረ ምስኪን ያሰኘዋል፡፡ ድንግል ማርያምም ቢሆን ነፍሴ በአምላኬ ሀሴት ታደርጋለች ያለችውን ትታ “አምላኬ በኔ ሀሴት ያደርጋል የጎደለውን ነገር ሞልቼለታለሁና” የሚል ቅኔ ልታመጣ ነው ማለት ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡ ያሳፍራል፡፡ ያስደነግጣልም፡፡ ቤተክርሰቲያኒቱ ወዴት እየሄደች ነውም? ያሰኛል፡፡
አንባቢ እስኪ ይህን ደግሞ ይመልከተው “…የልጇም ንጹሐ ባሕርይነት ከምንጩ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ፍጹም ንጽሕና የተነሣ ነው፡፡” ጉድ በል ጎንደር ይሉሀል ይሄ ነው፡፡ አረ ምን ጉድ ብቻ አልቅሽ ቤተክርሰቲያንም እንጂ፡፡ በዘመናችን እንደዚህ አይነት ምንፍቅናን በመስማታችን ልብ ይሰብራል፡፡ ክርስትና ወዴት አለ? ኢየሱስ ክርስቶስ ንጹህ የሆነው ማርያም ንጹህ ስለሆነች ነው የሚል ትምህርትንስ አንብቦ እንዲታተም የወሰነው ኮሚቴ ሃይማኖቱ ምንድር ነው? የሚያምነውና የሚያስተምረውስ ትምህርት ምንድር ነው? ማርያምን የፈጠረው ጌታ ከፍጡር ንጽህና የተነሳ ንጹህ ሆኗል ማለትን እንዴት ይሁን ብሎ ይበል ብሎ? አሳተመው፡፡ እንደእኛ እምነት መናፍቁ ኃይለጊዮርጊስ ብቻ ሳይሆን ይህ ጽሑፍ እንዲታተም የፈቀደው የመጽሔቱ ዝግጅት ክፍልም መጠየቅ አለበት ባይ ነን፡፡ ኮሚቴው ጽሑፉ እንዲታተም ከተስማማ የኮሚቴው አባላት እምነት እንዲህ ነው ማለት ነውና እነርሱም መጠየቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ለወደፊቱም እውነት ለማፈን የሚያደርጉትን ሳንሱር እንዲያነሱና ከዚህ ይልቅ ኑፋቄን መከላከል እንዲችሉ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ተሞክሮ ስለሚሆን እነርሱም መጠየቅ አለባቸው የሚል ጽኑ እምነት አለን፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህን በኑፋቄ የተሞላ ጽሑፍ ካነበቡ በኋላ ኃይለጊዮርጊስን አስጠርተው “አንተ ተዋርደህ ቤተክርስቲያንን አዋረድካት” በማለት እንደ ገሠጹት ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸውልናል፡፡ ቋሚ ሲኖዱሱም ጽሑፉን አስቀርቦ ከመረመረ በኋላ ስህተት መሆኑን አምኖ የሊቃውንት ጉባኤው እንዲመለከተውና ውሳኔ እንዲያሳልፍበት ወደ ጉባኤው መርቶታል ተብሏል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ የራሱን ውሳኔም እንዲህ ሲል ገልጿል ነው የሚሉት ምንጮች፡፡ ኃይለጊዮርጊስ የሰራሁት ሥራ ጥፋት ነው ካለ ቤተ ክርስቲያንን በደብዳቤ ይቅርታ እንዲጠይቅና በቤተክርስቲያንዋ ሕጋዊ ልሳን ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ላይ ስህተቱ ተገልፆ የእርምት ጽሑፍ እንዲጻፍ፣ ይቅርታ አልጠይቅም፣ ንስሐ አልገባም ካለ ግን ሥርዓተ ቤተክርስቲያን በሚያዘው መሠረት እርምጃ እንዲወሰድብት አሳስቧል ሲሉ ምንጮቻችን ያክላሉ፡፡
በደረሰን መረጃ መሰረትም ኃይለጊዮርጊስ በነገው ዕለት ሊቃውንት ጉባኤ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እንደ ብዙዎች እምነት ከሆነ ይህ ጉዳይ የሊቃውንት ጉባኤውም የሚፈተንበት ይሆናል ነው እየተባለ ያለው፡፡ በእውነት ላይ ተመሥርቶ ፍትሐዊ ማጣራት ያደርጋል? ወይስ አሁን እያሽቆለቆለ በሚገኝበት ሁኔታ "መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ባይኖርም አዋልድ መጻሕፍት ይደግፉታል" ብሎ እውነትን አሳልፎ ይሰጣል? ሁሉንም የምናየው ይሆናል፡፡
አቡነ ማርቆስን የኒቂያ አባቶች ወዴት አላችሁ? ያሰኛቸው ጉባኤው ይህ ክህደት በትክክል ተሰምቶት ቤተክርቲያንን ከነቀፋ የሚያድናት ውሳኔ ይሰጣል በሚለው ነገር ላይ ጥርጣሬ አድሮባቸውም ሊሆን ይችላል፡፡ ለማንኛውም የጉባኤውን ውሳኔና አካሄድ በቆይታ የምንመለከተው ይሆናል፡፡
የምንመኘው ኃይለ ጊዮርጊስ ጥፋቱን አምኖ እንዲጸጸትና ንስሀ እንዲገባ ነው፡፡ ይህ እድል ለሱም ቢሆን ከጌታው ጋር በእውነተኛ ንስሀ የሚታረቅበት ሊሆንለት ይችላል፡፡ ያድርግለትም፡፡ ስህተቱን ለማመንና ንስሀ ለመግባትም ድፍረት፣ ዝግጁነትና እውነተኛ ጸጸት ግን ያስፈልገዋል፡፡ ካደረገው ያስመሰግነዋል፡፡ ስህተቱን ደባብሶ ማለፍና በቅዱስ አምላክ ላይ የተነገረውን ይህን ኑፋቄ አባብሎና አሽሞንሙኖ አንድም ብሎ ትክክል ለማድረግ መሞከር ግን ጥፋቱን የጎላ ያደርገዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ በጣም የሚገርመው “ኢየሱስ ጌታ ነው” ሲባል መቋቋም እንደማይችለው ሰይጣን የሚጮኸውና ተቃውሞውን ለማሰማት ማንም የማይቀድመው የኃይለ ጊዮርጊስ ሞግዚትና አይዞህ ባይ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህ ያለውን ኑፋቄ ሲሰማ ዝም ማለቱ ነው፡፡ ቀድሞውንም ቢሆን ኃይለጊዮርጊስ እንዲህ ያለውን ኑፋቄ የጻፈው ማቅን ተማምኖ እንደሆነ ግን የታወቀ ስለሆነ ዝምታው የሚጠበቅ ነገር ነው፡፡ ማቅ ከእግዚአብሔር ይልቅ ለወግና ለሥርዓት ግድ የሚለው ስብስብ በመሆኑ ዝምታን መምረጡ ብዙም አይደንቅም፡፡
በመጨረሻም በጉዳዩ ላይ ሊቃውንት ጉባኤው ጉዳዩን እስኪያጣራና አንድ ውሳኔ እስኪተላለፍ ድረስ በብፁዕ አቡነ ማርቆስ ቅኔ ቤተ ክርስቲያንን ዳግም እንጠይቃለን፡፡ እንዲህ በማለት፦
“ለምንት አርመምኪ ኒቅያ ወኢተናገርኪ ምንተ
ዘእምድንግል ይትሌቃሕ ፈጣሪ ንጽሐ ባሕርይ መክሊተ50 comments:

 1. Esti atechuhu,lejeleria tsehafiw yiteteq,ye amargna atereguagom (ersuan betsuh ayidelechim malet esunem netseh aydelem endemalet yiqoteral,sega kersua nestual ena),lilu new weys dahetse lisan?mejemeria sewuyew teteyiqo kezia behuala ye miaschoh kehone bedenb techohalachehu;enante krestosen amalaj sitelut eko kezih kemetaragebut bikefa enji ayishalem

  ReplyDelete
  Replies
  1. እዛና እዚህ መርገጡን ትተህ የ ሊቀ ጳጳሱን ቅኔ እስቲ በማቅ አስተምህሮ እርምት አድርግለት፡፡

   Delete

  2. ምነው ወንድም የአእምሮ ችግር አለብህ እንዴ? ምኑን ከምን ነው የምታዛምደው? እንዲያው ልከራከርስ ብትል ለዚህ አይነቱ ደረጃ የማይገኝለት ምንፍቅና ትከራከራለህ አንዴ? ጌታ ይቅር ይበልህ፡፡ እሱ በክብሩና በልዕልናው አይደራደርም፡፡ ቅድስና አልቆበት ከፈጠረው ፍጥረት ባክህ ባክሽ ብሎ የሚዋስ አለመሆኑን ማወቅ ይኖርብሃል፡፡ ማስተዋሉን ይስጥህ

   Delete
 2. አሳዛኝ ነው!!!!

  ReplyDelete
 3. bhgererachin moge bayafere zemedu yaferal yimil tere neber. ahun seweyem zemedochum moge honew yimiyafer teftowal. yihe eko yekefa minfikina new. yasazenal

  ReplyDelete
 4. እዛና እዚህ መርገጡን ትተህ የ ሊቀ ጳጳሱን ቅኔ እስቲ በማቅ አስተምህሮ እርምት አድርግለት፡፡

  ReplyDelete

 5. “የእውነት ጩህ ጩህ ያሰኛል፡፡ ነገሮች በዚህ ከቀጠሉ እና ይህን የመለሰ ትልቅ ኑፋቄ በዝምታ የሚታለፍ ከሆነ ቤተክርስቲያኒቱን ወደ ባሰ ውድቀት ይከታታል፡፡ ይህንን አባባል እንደ ትምህርቷ የምትቀበል ቤተክርስቲያን ካለች በግልጥ የማርያምን አምልኮ መጀመርዋን ስለሚያመለክት ከቤተክርስቲያን ቁጥር መደመሩም ያበቃላታል፡፡ ጌታችን ንጹህ ባህሪ የኖረው ከማርያም የተነሳ ነው ካልን አለም ከተፈጠረ ጀምሮ የሌለበትን ንጽህና ማርያም ሰጠችው ያሰኛል፡፡ ይህ እስከዛሬ ድረስ ከተሰሙ ምንፍቅናዎች ሁሉ የከፋ ያደርገዋል፡፡”
  100 በ100 ትክክል ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለምን አትተረተርም? ማን ጉሮሮህን ያዘህ? አቶ እንቶ ፈንቶ፦ አሉባልታና የፈጠራ ወሬ በማራገብ ስለ ማትኖርበት ከመምትዘላብድ ሳር ስለሚያስግጠው ትምህርታችሁ ብታወራና ብትጮህ ይሻልሀል። በየትኛውም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ የባህሪው ንጽህና ከድንግል ማርያም ንጽህና ነው የሚል ትምህርትየለምም አገልጋዮቿም እንዲህ ብለው አያስተምሩ። የእናንተ ያልተጻፈ የማንበብና የማጣመም አሉባልታ እንጂ እውነት አይደለም። ለምን እውነት ነው ካላችሁ ሙሉውን ጽሑፍ ሳትቆራርጡ አትለጥፉትም ነበር። ለሁሉም ክርስቶስ የለበሰው ስጋ ከድንግል የነሳው ነውና እሷም የውርስ ሐጢያት ያልነካት ንፅህት ዘር ናትና የለበሰው ስጋ ንጽህና ከድንግል ንጽህና የተነሳነው። ምክንያተቱም ክርስቶስ ንፁሐ ባህሪ የሆነ ነውና ሐጢያት የነካው የአደፈ ሰውነት አይስማማውምና። ለማንኛውም መናፍቆች እናንተና ሳር አስጋጮች መሰሎቻችሁ እንጂ ቤተክርስቲያን አይደለችም። እናንተ በቤተክርስቲያን ላይ ብዙ የጥፋት ፍላጻዎችን ብትወረውሩም ቤተክርስቲያን ከልጆቿ ጋር አለች። ምክንያቱም የገሀነም ደጆች ስለማይችሏት።

   Delete
  2. ዳሞት እንዳንተ ያለ በቁሙ የዛገ ጭንቅላት ያለው ሰው ያለም አይመስለኝ። ማንም ለዘባረቀው ምን ጥብቅና አስቆመህ? እነዳንተ አይነት ሰው ነው የመናፍቃን አውራ የምንፍቅና ጠበቃ። የምትተቸውን እንኳ የማታውቅ ግልብ ነህ። ታሳዝናለህ። ለእንደዚህ አይነት ኑፋቄ ከተከራከርክ ነገ ደግሞ ኢየሱስን የፈጠረችው ማርያም ነች ከተባለም አብረህ ትቆማለህ። ጌታ ይገስጽህ። ወይ ተመለስ ወይ ተገንደስ

   Delete
  3. ለanonymous march 8,2015 at 10:58pm
   ውድ ወዳጄ፦ ብራቮ ብያላሁ! እነዚህን የመሰሉ ውብ ቃላቶች ይዘህ እስካሁን በቅድስና አክሊሎች ተውበህ አለመነጠቅህ ግን በጣም ያሳዝናል ጥያቄም ያስነሳል። አይምሮ ይዝጋል እንዴ? የአይምሮ መዛግ ካለ ደግሞ አንተው የተሸከምከው ጭንቅላት ይሆናል እንጂ አይምሮ አይዝግም። ያንተ ጭንቅላት ግን በተነነው የጉም ቅዠት በሆነው በዲያብሎስ መንፈስና በአሉባልታ እንዲሁም በአስመሳይነት የተሞላና የተበላሸ ነው። እኔ ትችት አይደለም የተናገርኩት። ጩህ ጩህ ያሰኛል ላለው አስተያየት ሰጭ ነው መልስ የሰጠሁት። ሌላው ነገ እንደዚህ ተባለ ለማለት የዶለትኸውን አሉባልታ አምልጦህ ይሁን አውቀህ ተንፍሰኸዋል። ይኸውም "ማርያም ፈጠረችው" የሚል የውሸትና የክህደት አሉባልታህን። ለማንኛው ድንግል ማርያም ክርስቶስን ወለደችው እንጂ እሱ በማንም የተፈጠረ አይደለም ክብር ምስጋና ለሱ ይሁንና። ለሌላው የስድብ ዘባተሎህ ግን ደራርተህ ስፍና ልበሰው ከማለት ውጭ ሌላ ማለት አያስፈልግምና ደህና ሁን፡

   Delete
  4. ዳሞት
   የምትሰጣቸውን ኮሜንቶች ሳነብ በጣም ትገርመኛለህ
   1ኛ ጭፍን ነህ
   2ኛ ለመነፈሳዊው ነገር መሀይም ነህ
   3ኛ እራስህን ሊቅ አርገህ ትቆጥራለሀ
   4ኛ ትልቁ ትኩረትህ እንደመንደር ሴት በስድብ መራቀቅ ነው፤፤
   አንተ ባታፍር የሚያፍሩልህ ዘመዶች የሉህም?

   Delete
  5. የእንትናን ለእንትና መሆኑ ነው? ሴቶችን የመንደር የስድብ ተራቃቂ ማድረግህ እናትና እህትህ እንዲሁም ሴት ዘመዶችህና ሚስትህ አፈሩ አንተ ባታፍር። ምክንያቱም እንዲህ አይነት ከእንስሳ በታች የምታስብ ከንቱና ክፉ ግለሰብ በመሆንህ፡

   Delete
 6. ኸረ ወዴት እየሄድን ነው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኛ ህይወት ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ። አንተና ይህ የውሸት ክስ ማወጃና የአሉባልት መርጫ የሆነው ብሎግ ደግሞ ወደ ክፋትና ጥፋት።

   Delete
  2. ወዴት ወዴት ዳሞት አንተ ወደ ጭለማው አበጋዝ ወደ ዳቢሎስ እኛ ደግሞ ወድ ብርሃን አምላክ ወደ ክርስቶስ

   Delete
  3. ለanonymous march 8,2015 at 10:59pm
   ወንድም፦ በአሉባልታ፣ በውሸት፣ በክህደት፣ በከሳሽነት፣ ወተቱን ጥቁር ጥቁሩን ነጭ በማለት፣ በአስመሳይነት እና በዳቢሎስ መንፈስ እሪታ ነው እንዴ ወደ ብርሃን የሚኬደው? እውነትም መጽሐፍ ቅዱስ አዋቂ አንባቢና የጽድቅ መንገድ ተከታይ ነህ። በል በርታ የጽድቅ ጠላት!

   Delete
  4. ዳሞት
   አሉባልታ አይደለም መጽሔቱን ፈልገህ ማንበብ ትችላለህ

   Delete
  5. ምን ትልመጠመጣለህ ።አሉባልታማ ነው። ከአሉባልታ በላየ ደግሞ እውነትን የመደበቅና የአንዲቷን የክርስቶስ ቤተክርስቲያን እምነትና አገልጋይ በሐሰት የመክሰስና የሥም ማጥፋት ዘመቻ ነው። አሉባልታ አይደለም ብለህ በአዳራሽህ አንቧርቅ እንጂ ሳትሆን እንዲህ ነኝ እያልክና እያላችሁ በማስመሰል የምትሰሩትን ጽርፈትና ክስ ማንም አይሰማም።

   Delete
  6. መጽሔቱን ፈልገህ አንብብ ተባልክ። ለምን ፈልገህ አንብበህ ይሄ ውሸት ነው አትልም? ዝም ብለህ ልቅ ስድብሀን ከመደርደር ለማወቅም ቢሆን ማንበብ ያስፈልጋል። ባልገባህ እና ባለወከው ነገር አትወናቸር። አሳፋሪ ሰው ነህ

   Delete
  7. ለanonymous march 10, 2015 at 8:46 pm
   ለምን ትፈራለህ ወንድም። ተጽፏል የሚትለውን ጽሑፍ የአንተን የውሸት፣ የፈጠራና የተጻፈውን እውነትና ትክክለኛ መልእክት የማጣመም የአሉባልታ ጽሑፍህን በዚህ የሰይጣን አላማ ማራመጃ ብሎግ ተብዬ እንደ ለጠፍከው የመጽሔቱንም ጽሑፍ ለምን አታወጣውም። ማንበብና ማወቅ ከመንፈሳዊነትና ከክርስትና አንጻር በቂ አይደሉም። የአነበቡትን ለማወቅ ትምህርት የመጀመሪያው ነውና መማር ይቀድማል ይጠቅማል ከማንብብ በፊት። ከተማሩ ባያነቡም በተማሩት የሚያደርጉትን ማወቅ ይችላሉ።

   Delete
 7. የአረብ እስላም ሴቶች የሚለብሱትን የአሸባሪነት ጥቁር ልብስ መልበስ ከቤተ ክርስቲያናች ቢወገድ ጥሩ ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሁን አወቅህ መጠቅህ ፀደቅህ ማለት ነው? ባዶ! በቤተክርስቲያን የሚለበሱትን አልባሳት መሠረታቸውንና ትርጉማቸውን ብታውቅ እንዲህ አይነት ባዶ መሆንህን ባላጋለጥኸው ነበር። ለማንኛው አንተ የጠቀስሐቸው እንሿን የሚጠቀሙበትን አልባሳትና የአለባበስ አይነት ከየት እንደወሰዱት ለማወቅ ብትሞክር መልካም ነበር እንዲህ በእውር ድንብር ከምታቃስት። እስቲ አንተ ሱፍ በከረባት የመንፈሳዊያን አልባሳት ነው ብለህ ማስረጃ አቅርብ?

   Delete
 8. who is haileyesus please ? i have never heard such kind of heresy in the past . This is a serious blasphemy emanated from a person with a little knowledge.*little knowledge is dangerious.
  WE memeber of EOTC, glorify St Mary abundantely than any other Saint , for she gave birth to God the Son, Creator of Heaven & Earth.

  But, we don't attribute such kind of power to St Mary., May Her Blessings & prayer bestowed upon us , Amen!
  It is only God who offer chastity , and all other heavenly & earthly graces out of His unconditional love & mercy.But, He don't borrow anything from His creatures.

  May milliard of Thanks extend to HIm

  Aman  ReplyDelete
 9. ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢያት ይመለከታታልን ?
  ድንግል ማርያም የዘር ኃጢያት የለባትም ለዚህም እጅግ በርካታ ማረጋገጫዎችን መዘርዘር ሲቻል በዚህ ጽሁፍ ግን ለጊዜው የሚከተሉትን ሶስት ነጥቦች እንመለከታለን
  ፩.አስቀድመው ነብያት የዘር ኃጢአት [ጥንተ አብሶ ] እንደሌለባት አስረግጠው ተናግረዋል ከነዚህም ጥቂቶቹ ለመመልከት ያህል
  ፩.፩ ነብዩ ኢሳይያስ «እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ስዶም በሆንን እንደ ግሞራም በመሰልነ ነበር» ኢሳ፩፤፱ ዘር የተባለች ዓለም የዳነባት አምላክ ሰው የሆነባት ድንግል ማርያም ናት ቅዱስ ጳውሎስ በእብራዊያን ክታቡ «የአብራሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም » እብ፩፤፲፮ በማለት ጌታ ሰው የሆነባትን ዘር የአብርሃም ዘር እያለ ይጠራታል ነቢዩ ኢሳያስም እግዚአብሔር ያስቀራት ዘር ያላት እመቤትችንን ነው አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሰው ሲሆን ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ለይቶ በንጽሐ ስጋ በንጽሐ ነፍስ ጠብቆ ከስጋዋ ስጋ ከነፍስ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ለማዳን ምክንያት ያደረጋት ዘር ናት
  ፩.፪ ነብዩ ዳዊት « የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግስቲቱ በቀኝህ ትቆማለች ልጄ ሆይ ስሚ እይ ጆሮሽንም አዘንብይ ወገንሽን የአባትሽን በት እርሺ ንጉስ ውበትሽን ወዶአልና» መዝ፵፬፤፱-፲፩ መቼም ማንም ሊከራክር ቢወድ ከእመቤታችን በላይ ለሌላ ይህ ቃል ገላጭ በምንም መልኩ አያስከድም ይልቁንም በምስተዋል ላነበበው ድንግል ማርያምን የሚገልጽ ጥልቅ ትምህርት ማግኘት ይችላልወርቅ የንጽሕና ምሳሌ ሲሆን ደርባ ደራርባ የተባለው ደግሞ ንጽሓ ስጋ ላይ ንጽሓ ነፍስ ንጽሃ ነፍስ ላይ ንጽሓ ልቦና መደራረቧን የሚያስረዳ ነው ወገንሽን የአባትሽን ቤት እርሺ የተባለው ደግሞ ከሰው ዘር በሙሉ መለየቷን የዘር ኃጢአት እንዳላገኛት የሚያስረዳ ነው ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ እመቤታችንን ልጄ እያለ መጥራቱ ከሱ ዘር እንደምትወለድ ያስረዳናል ጌታም ከሷ ስለተወለደ የዳዊት ሊጅ ተብሎ ተጠርቷል ማቴ፩፤፩ ንጉስ የተባለ ልጇ እይሱስ ክርስቶስ ሲሆን ውበትትሽን ወዷልና ማለት ውበት ንጽሕናሽን ሊዋሃደው ወዷልና ማለት ነው
  ፩.፫ ጠቢቡ ሰሎሞን «ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም» መኃ፬፤፯ ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ ትንቢት ተቃኝቶ እመቤታችንን ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየ ንጹህ ነው ብሎ አመስግⶈታል

  ፪. የቅዱስ ገብርኤል ብስራታዊ ሰላምታ እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ (የዘር ኃጢአት ) እንደሌለባት በሚገባ ያስረዳል ይህንንም እንደሚከተለው በሶስት ክፍለን ማየት እንችላለን
  " ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ጌታ ካንቺ ጋር ነው
  አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ" ሉቃ ፩፣ ፳፰
  ግሩም ከሆነው የመልአኩ የምስጋና ቃል ውላዲተ አምላክ ኃጢአት የሚባል ጨርሶ እንደማያውቃት ሶስት ጥልቅ የሆኑ መልእክቶችን እንመልከት

  ፪.፩" ጸጋ የሞላብሽ ሆይ" እናስተውል የሰው ልጆች ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል በተባለበት ዘመን ጸጋ የሞላብሽ የሚል ልዩ ምስጋና የቀረበላት እመቤታችን ብቻ ናት በጥንተ አብሶ ፍዳ ምክንያት ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲህ ነበር የተባለው
  "ሁሉ የእግዚአብሔር ክብር (ጸጋ )ጎሎአቸዋል" ሮሜ፫፤፳፬
  እንግዲህ ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል የተባለው ሁሉ ኃጢአት ስለሰሩ አይደለም ነገርግን አዳማዊ መርገም በሁሉ ስለደረሰ ነው ለዚህም ነው
  "ኃጢአት ባልሰሩት ላይ እንኳን ሞት ነገሰ " ሮሜ፭፤፲፬ ተብሎ የተጻፈው ታድያ ሰው ሁሉ መረገመ አዳም ስለደረሰበት ከጸጋ በታች ከተባለ ድንግል ማርያም እንዴት ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ? ይህ በርግጥም እመቤታችን የዘር ኃጢአት ፍዳ እንደማይመለከታት ያስረዳናል ድንግል ማርያም ይህ የምስጋና ቃል የቀረበላት ጌታን ገና ከመጽነሷ በፊት ነው ይህ ማለት ደግሞ ጌታችን ሰው ሆኖ ጸጋ ለጎደለው አለም ካሳ ቤዛ ሳይሆንለት ድንግል ማርያም ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ማለት ከእናቷ ማህጸን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ጠብቋታል ማለት ነው
  ፪.፪ ከሴቶች መካከል
  ሁለተኛው ነጥብ ድንግል ማርያም ከሴቶች ተለይታ የተባረከች እንድትባል ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ በዘር ኃጢአት ምክንያት በሌሎች የደረሰ መረገም በእርሷ ስላልደረሰ ነው እንዲህ ባይሆን ኖሮ ይህ ምስጋና ባልተገባትም ነበር ስለ ሌሎች የሰው ልጆች መጽሓፍ ቅዱስ ሲገልጽ
  " ልዩነት የለም ሁሉ ከበደል በታች ናቸው" ሮሜ፫፤፳፪ ይላል
  ስለእመቤታችን ሲናገር ግን ከሴቶች መካከል ብሎ መለየቷን በግልጽ ያስቀምጣል እንግዲህ ሰው ሁሉ ያለ ልዩነት ከበደል በታች በተባለበት ዘመን እርሷ የተለየች ከተባለች በእርግጥም ወላዲተ አምላክን የውርስ ኃጢአት ፍዳ አይመለከታትም ማለት ነው ። እመቤታችን ከብር ምስጋና ይግባትና የጥንተ አብሶ ፍዳ ይመለከታታል ከተባለ የእርሷ መለየት የቱ ጋ ሊሆን ነው? ስለዚህም የመልአኩ የሰላምታ ቃል ስህተት ነው እንላለን? አንልም እውነታውን ይዘን ድንግል ማርያም በእውነት ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየች ንጽህይት ቅድስት መሆኗን እንመሰክራለን እንጂ
  ፪.፫ የተባረክሽ ነሽ
  በሶስተኛ ደረጃ ከመልአኩ የምስጋና ቃል ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት እንደሌለባት የሚያስገነዝበን የተባረክሽ ነሽ የሚለው ኃይለ ቃል ነው በጣም የሚገርመው በዚሁ ተመሳሳይ ቃል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስም በተመሳሳይ ስፍራ ምስጋና ቀርቦለታል
  "አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው"ሉቃ፩፤፵፪
  እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለንና እመቤታችንም ይተባረክሽ ነሽ ጌታም የተባረከ ነው የሚል ተምሳሳይ ምስጋና ቀርቦላቸውል ይህ ማለት ሁለቱንም የጥንቱ መርገም እንደማይመለከታቸው ያመልክታል የበረከት ተቃራኒ መርገም ነው ስለዚህም የተባረክሽ ነሽ ማለት መርገም የሌለብሽ ነሽ ማለት ሲሆን ጌታ ደግሞ የተባረከ ነው ሲባል መርገምን የሚያርቅ ማለት ነው። ልዩነቱን ልብ እንበል እምቤታችን የተባረክሽ ስትባል ከእናቷ ማህፀን ጀምሮ ልጇ ከምርገም ጠበቃት ማለት ሲሆን እርሱ ጊን የተባረከ ነው ሲባል ለባህሪው መርገም የማይስማማው ከሌሎች መርገምን የሚያርቅ ማለት ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Tadiya yehan hulu gebste, soriya, hind batekalay "oriental" Abiyate kirstiyanat sayawku kertew new? Zim beleh ye catholic nufaqa atezra

   Delete
 10. በአጠቃላይ ድንግል ማርያም ከላይ በመልአኩ የሰላምታ ንግግር ከብዙ በጥቂቱ እንደተመለከትነው የዘር ኃጢአት በፍጹም እንደማይመለከታት ነው ይህም አምላክ አለምን ለማዳን ከእርሷ ከስጋዋ ስጋ ክነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ለምሆን ያዘጋጃት በመሆኗ የእርሷ ንጽህና በሰው ልጆች መዳን ውስጥ በምክንያትነት

  3.እመቤታችን ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት አለባት ማለት የጌታችንን ንጹሐ ባህሪውን መዳፈር ነው
  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሰው ሲሆን ስጋና ነፍስን ከሰማይይዞ አልወረደም ሰው የሆነው የእኛን ባህሪይ ተዋሕዶ ነው።ይህን በተመለከተ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል"እንግዲህ ልጆቹ በስጋና በደም ስለሚካፈሉ እርሱ ደግሞ በሞት ላይስለጣንያለውንእንዲሽር-እንዲሁ ተካፈለ የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም''ዕብ2፤14-15
  እንግዲህ ጌታ ሰው ሲሆን ስጋንም ነፍስንም ከድንግል ማርያም ከነሳእርሷ ደግሞ መርገም ነክቶአታል ከተባለ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታ ኃጢአትያለበትን ስጋ ተዋሐደ ልንል ነውን?እንዲህማ ካልን ተረፈ አይሁድ ሆነናል ማለትነው ምክንያቱም ደፍረው ጌታን ኃጢአት አለበት ያሉት አይሁድ ናቸውና
  " ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እኛእናውቃለን" ዮሐ 9፤24
  እኛስ ከእመቤታችን ምንም ምን ኃጢአት ያላወቀውን ስጋ እንደነሳ እንመሰክራለን እንደ እውነተኞቹ አባቶቻችን ጌታችን ንጽሕት ቅድስት ከምትሆን ከእመቤታችን ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን እናምናለን እንመሰክራለን " ኦ ድንግል አኮ ዘተአምሪ ርስሐተ ከመ አንስት እለ እምቅድሜኪ ወእምድሬኪ አላ በቅድስና በንጽሕና ስርጉት አንቲ "ትርጉም"ድንግል ሆይ ካንቺ አስቀድመው ካንችም በኋላ እንደ ነበሩ ሴቶች አደፍ ጉድፍን የምታውቂ አይደለሽም በቅድስና በንጽሕና ጸንተሽ ኖርሽ እንጂ"ቅዳሴ ማር5፤42
  መቼም አባቶቻችን እነ ቅዱስ ኤፍሬም እነ አባ ሕርያቆስ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው የደረሱአቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት የማይቀበል ኦርቶዶክሳዊ አለ ማለት እጅግ ይከብዳል ፡፡ እንግዲህ ቅድስት ቤተክርስትያን ስለነገረ ማርያም በጥንቃቄ የምታስተምረው ስለድንግል ማርያም የምናምነው ነገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከጌታችን ማንነት ጋር ተያያዥነት ስላለው ነው እግዚአብሔር ይግለጥልንና ጌታ ከእመቤታችን መርገም ያለበትን ስጋ ተዋሐደ ማለት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰረታዊ ተቃርኖዎችን ያስነሳል። ይቆየን


  ፩. የድንግል ማርያም ሥጋ የውርስ ኃጢአት ወይም የጥንተ አብሶ ፍዳ አለበት ከተባለ ክርስቶስ ከርሷ ሲወለድ ኃጢአት የወረሰውን ሥጋ ወሰደ ሊባል ነው ይህ ማለት ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ትምህርት ነው ምክንያቱም ለኢየሱስ ክርስቶስ ባሕሪይ ኃጢአት ፈጽሞ አይስማማውምና ኃጢአት የነካውን ሥጋ ተዋሐደ ከተባለ መለኮት ኃጢአት ይስማማዋል እንደማለት ነው ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያወግዘው ክህደት ነው ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቦች መመልከት ይቻላል
  «ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞት የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ» ዕብ ፯፤፳፮
  «ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደኛ ተፈተነ…………» ዕብ ፬፤፲፭
  «ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለኛ ኃጢአት …………»፪ቆሮ፭፤፳
  ፪. የድንግል ማርያም ሥጋ የጥንተ አብሶ ፍዳ ወይም የውርስ ኃጢአት አለበት ማለት የክርስቶስን የማዳን ስራ አለመቀበል ነው ። ምክንያቱንም ከዚህ እንደሚከተለው ማብራራት ይቻላል ። ጌታ ከድንግል ማርያም መርገም ያለበትን ሥጋ ከነሳ ክብር ምስጋና ይግባውና መርገም ባለበት ሥጋ መርገምን አራቀ ማለት በጭራሽ አያስኬድም። ይህ ደግሞ አለም እንዲድን የአምላክ መውረድ መወለድ ያስፈለገበትም ምክንያት ከንቱ ሊሆን ነው ። የአምላክ መውረድ መወለድ ያስፈለገበት ምክንያትኮ ሰው ሁሉ የመረገም የእዳ የበደል ተጠያቂ ስለነበር ንጹሕ የሚያድን በመጥፋቱ ነው።ለዚህም ነው በነብዩ ኢሳያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው
  «እግዚአብሔር አየ ፍርድም ስለሌለ ተከፋ ሰውም እንደሌለ አየ ወደ እርሱ የሚማልድም እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም ስለዚህም የገዛ ክንዱ መድኃኒትን አመጣለት ጽድቁምአገዘው» ኢሳ፶፱፡፲፮
  አዎን እግዚአብሔር ያጣው ንጹሕ ሆኖ ስለ ሌላው የሚማልድ ካሳ ቤዛ የሚሆን ሰው ነበር ነገር ግን ሁሉ ከእዳ ከበደል በታች ስለነበሩ ንጹሕ መረገም የሌለበት ጠፋ ስለዚህም በንጹሐ ባህሪው ጌታ ንጹሕ ስጋን ተዋህዶ ወደ እኛ መጣ ።ነብዩ የገዛ ክንዱ መድኃኒትን አመጣለት ማለቱ እርሱ እራሱ ሰው ሆኖ አዳነን ማለቱ ነው ። እርሱ በባህሪው ኃጢአት ስለማይስማማው ኃጢአት የሌለበትን ሥጋ ለመዋሐዱ ምንም ሊያከራክር አይችልም ።መርገም ያለበት መርገም ያለበትን ማዳን ቢችል ኖሮ ከብዙ ነብያት አንዳቸው አለምን ማዳን በተቻላቸው ነበር። የድንግል ማርያምን ንጽህና በጥቃቄ ከተረዳን ነገረ ድኅነትን እንዳናፋልስ ይረዳናል ለዚህም ነው ቅዱስ አትናትዮስ ሐዋርያዊ ስለጌታ ሰው መሆን ሲገልጽ ስለእመቤታችን ንጽሕና አስረግጦ የተናገረው
  «ወለደት ድንግል ዘፀንሰቶ እንዘ ኢተአምር ብእሴ በስጋ ዘፈጠሮ ለእርሱ ወወለደቶ ዘእንበለ ደነስ ወሕማም ወኢረሰስሐት በሐሪስ ሐፀነቶ ዘእንበለ ፃማ ወድካም ወአጥበቶ ዘእንበለ ድካም ወአልሐቀቶ በሕግ ዘሥጋ ዘእንበለ ትካዝ ።» ሃይማኖተ አበው ዘአትናትዮስ ፳፰፡፲፱ትርጉም
  « ለተዋሕዶ የፈጠረውን ሥጋ ያለ ወንድ ዘር ያለ ኃጢአት ያለምጥ ወለደችው የአራስነት ግብርም አላገኛትም ያለድካም ያለመታከት አሳደገችው ያለድካም አጠባችው ለስጋ በሚገባ ሕግ ምን አበላው ምን አለብሰው ሳትል አሳደገችው» ማብራሪያውን በቀጣዩ ጽሁፋችን እንመለከታለን  «ወለደት ድንግል ዘፀንሰቶ እንዘ ኢተአምር ብእሴ በስጋ ዘፈጠሮ ለርእሱ ወወለደቶ ዘእንበለ ደነስ ወሕማም ወኢረሰስሐት በሐሪስ ሐፀነቶ ዘእንበለ ፃማ ወድካም ወአጥበቶ ዘእንበለ ድካም ወአልሐቀቶ በሕግ ዘሥጋ ዘእንበለ ትካዝ ።»
  « ለተዋሕዶ የፈጠረውን ሥጋ ያለ ወንድ ዘር ያለ ኃጢአት ያለምጥ ወለደችው የአራስነት ግብርም አላገኛትም ያለድካም ያለመታከት አሳደገችው ያለድካም አጠባችው ለስጋ በሚገባ ሕግ ምን አበላው ምን አለብሰው ሳትል አሳደገችው» ሃይማኖተ አበው ዘአትናትዮስ ፳፰፡፲፱ትርጉም ማብራሪያውን በቀጣዩ ሐዋርያዊው ቅዱስ አትናትዮስ ካስተማረው ትምህርት እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት በሚገባ ማስተዋል ይቻላል ግልጽ ለማድረግም የሚከተሉትን ነጥቦች መመልከት ይቻላል

  ReplyDelete
  Replies
  1. Tadiya yehan hulu gebste, soriya, hind batekalay "oriental" Abiyate kristiyanat sayawku kertew new? Zim beleh ye catholic nufaqa atezra

   Delete
  2. Shewafawe,

   Tell us what is the difference between Roman Catholic and Orthodox ( in particular the Oriental Orthodox Churches belief)? The argument you are making about the book of Isaiah is completely debunked. Please read the confusing readings that were debunked fully.

   Delete
  3. shewaferahu
   ድንግል ማርያም የዘር ሀጥያት እንደሌለባት ለማስረዳት መፅሐፍ ቅዱስ የማይለውን ለምን በግድ ለማስባል ትሞክራለህ?
   ዘር ተብሎ የተጠቀሰባቸው ክፍሎችን በሞላ የሚናገሩት ስለ ማርያም ስለመሆኑ ምን ማሰጃ አለህ? ሐዋርያው ጳውሎስ ማርያምን የአብርሃም ዘር ብሎ ይጠራታል ስትል ይህን የሚያስረዳልህ በክፍሉ ውስጥ ስለ ማርያም የሚገልፅ ምን አይነት ሃሳብ ስላለ ነው? የአብርሃም ዘር ማለት: የአብርሃም ዘር ማለት ነው (እግዚአብሔር ተስፋን የሰጠው ለአብርሃም መሆኑን ልብ በል)
   ሁሉም ሀጥያትን ሰርተዋል የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል በተባለበት ዘመን መላኩ ገብርኤል ፀጋን የተሞላሽ ነሽ አላት ብለህ ፀጋና ክበር አንድ እንደሆኑ አደናግረህ አለፍክ:: ፀጋን የተሞላሽ ማለት (to whom a special grace have been given) ማለት እንጂ ለማነፃፀር እንደሞከርከው የእግዚአብሔር ክብር (glory) የሞላብሽ ወይም ሀጥያት የሌለብሽ ማለት አይደለም:: ያዳም ልጆች ሁሉ (ድንግል ማርያምን ጨምሮ) የእግዚአብሔር ክብር የጎደላቸው አዳማዊ የዘር ሀጥያት ያለባቸው ቢሆኑም እንኩአ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በሆነው በፀጋው እንዲያው እንደሚድኑ አንተ በጠቀስከው የሮሜ ፫ : ፪፬ ላይ ተገልፆአል:: ከዚህም ፀጋ ማለት አምኖ ለተቀበለ ለማንም ሳይገባው በነፃ የሚሰጥ ስጦታ ( free and unmerited favor of God) መሆኑን እንረዳለን:: ለሌሎቹ በሌላ ጊዜ በስፋት እመጣለሁ

   Delete
  4. ከየት የመጣኸው ወንጌል ሰባኪነህ ባክህ? ምኑን ከምኑ እያመሰቃቀልክ ነው የምትገጣጥመው? ደግሞ የየትኛው ቲዮዎሎጂ ተመራቂ ትሆን? የአማረኛውን በእንግዚዘኛ እየተረጎመህ እንክርዳዱን በሙላት ለቀቅኸው እኮ። ሌሎችን እንክርዳዶችን ደግሞ በስፋት ትመለስባቸዋለህ አይደል? ጎበዝ! በርታ! ነገ ሳጥናኤል በለሷን በደንብ ያበላሀል የአጋንት አለቃ እንድትሆን። " ፀጋ ማለት አምኖ ለተቀበለ ለማንም ሳይገባው በነፃ የሚሰጥ ስጦታ" ነው ነው ያልከው። ከካዱና ከሳቱ ላይቀር እንዲህ ነው እንጂ። እውነትም መጽሐፍ ቅዱሱን ጥት ነው ያደረክኸው። ማንበብና መልእክቱን መረዳት ማለት እንዳንተ ነው። ሮሜ 3፥ 24" በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በፀጋው ይድናሉ " ነው የሚለው። እንዴትና ከየት እያመጣህ ነው ፀጋ ማለት ሳይገባው በነፃ የሚሰጥ ነው ያልከው። ይሄም ብቻ አይደለም "አምኖ ለተቀበለ"የሚል ተጠቅመሀል። ታዲያ ያመነማ ከእምነቱ የተነሳ እግዚአብሔር ላመኑት ልዩ ልዩ ፀጋንእንደሚሰጣቸው ተናገረ እንጂ ሳይገባው ይላልን? ሳይገባው ማለት እኮ እምነትም ሆነ ምንም አይነት የእምነት ምግባር ሳይፈፅሙ ክርስቶስ በፈፀመው የማዳን ቤዛነት ያገኘነው ከቀደመ በደላችን መዳናችንንና ነፃ መውጣታችንን የሚናገር እንጂ የእምነት ፀጋን
   የሚያመለክት አይደለም። በሌላ ጊዜ በስፋት የምትመለስባቸው ደግሞ ምን ይመስሉ ይሆን ውድ ያሬድ?

   Delete
  5. ሀዳስ ኪዳኔኪዳኔ በሮማን ካቶሊክና በኦርቶዶክስ መካከል ያለው ልዩነት፤ ካቶሊክ ከናቱዋ ማህጸን ጀምሮ ስትል ኦርቶዶክስ ደግሞ አዳም ከመበደሉ በፊት የነበረው ንጽህና በአዳም ገላ/ትውልድ ውስጥ ከአዳም ጀምሮ የሰው ልጅ ሲበድል እንዲመለስ የሚያደርገው በትውልድ ውስጥ ያለፈው ንጹህ ህሊና ከድንግል ማርያም የደረሰ ነው፡፡

   Delete
 11. የዘመኑ መነሰፍቃን በቤተ ክህነት

  ReplyDelete
 12. ታዲያ"አንጺሃ ሥጋሁ ቀዲሳ ኪያሁ ሀደረት ላዕሌሁ" ማለትህ ይሂን? ,አላዋቂ ሳሚ እንትን ይለቀልቃል የምትባል ሰው ነህ

  ReplyDelete
 13. Mahibere kidusan is coming down soon. Just wait for 2 months and See. Hailemariam has a delicious dish for this evil mahiber.

  ReplyDelete
 14. Shewaferawe,

  I am amazed how little did you bother to check if the Ethiopian Orthodox Tewahedo church actually shares a common belief with other Orthodox Churches. In fact, Abune Mathias said that "EOTC shares the same doctrine, dogma and discipline." This is in contrary to what Abune Mathias did to Kansas Kidanemihret in 2004. Please visit this website http://medhanialemeotcks.org/

  ReplyDelete
 15. Ene yetelye tiyqe alegne " original sin " ( tinte absso ) mindn new? What is the basic meaning ? Mr Shewaferaw ebakih abraraw thank you

  ReplyDelete
 16. There is a guy who comments with nick name "DAMOT". What ever truth is told here, he is always there to disagree. I doubt devil is working through him. Hasty generalization is nothing than being messenger of devil. So the arrogant and ignorant guy pls donot dump your lousy story here.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Never ever this blog and his soldiers have truth. They are professional liar. There mindid ccontrolled contro and directed by the devil sprit. they born and grow up in devil sprit. I am arguing and responding for there false accusations and messages.

   Delete
 17. የማቅ አስተምህሮ አንቆ ስለያዘው እኮ ነው ነፈዝ መሀይም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous march 10,2015 at 7:33am
   ውድ አራዳው መሃይም፦ ሰዎችን ያልሆኑትን እንዲህ ሆኑ፤ ይሄን ሰሩ፤ ሌላም ብዙ የጥላቻና የማጣጣያ ተቀጽላዎችን መስጠት ልማዳችሁና ባህሪያችሁ መሆኑ ይታወቃል። ለነገሩ ከመናፍቅና ከእውነት ጠላት ምን ይጠበቃል። እናንተም እኛ በእምነታችን ኦርቶዶክስ ነን በሚል ጭንብል ተከልላችሁ አይደል ኦርቶዶክስንና ተከታዮቿን የምትወጉት። ይሄ ደግሞ ክርስቶስን የማያስደስትና ህይወት የማያሰጥ ነገር ግን ለሞት ፍርድ የሚያቀርብ ነው። በመጽሐፍ እንዲህ እንደተባለው "የአብርሀም ልጆች ብትሆኑስ የአብርሃምን ስራ በሰራችሁ ነበር።" ስለዚህ ቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያላችሁ የምታስመስሉ ነገር ግን ምንም አይነት የቤተክርስቲያኗ መገለጫ የሌለባችሁ ክፉ ከሀዲዎች ናችሁ። የካድህና የካዳችሁ፤ የማታምንና የማታምኑ ጠማማዎች መሆንህና መሆናችሁ ባውቅም አሁንም ልንገርህ ልንገራችሁ። እኔ የማህበረ ቅዱሳን አባል አይደለሁም። ማህበረ ቅዱሳን የሚያስተምሩት የአንዲቷን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን አስተምሮ የክርስቶስን ወንጌልና የቅድስናን ህይወት ነውና በተማርሁት የእምነቴ መንፈስ ፀንቸ እቆማለሁ። ቤተክርስቲያንና ማህበራቷ ማንንም አስገድደው አይዙም ፤ አማኝም አያደርጉም ። ምክንያቱም ክርስቶስ ማንንም አስገድዶ ተከታይና አማኝ አላደረጀም። የሚወደኝና የሚያምንብኝ ቢኖር ይከተለኝ ነውና ክርስቶስ ያለው ቤተክርስቲያንም የአምላሿን ቃል ጠብቃ ተግባራዊ ታደርጋለች። ስለዚህ አቶ አራዳው መሃይም፦ "አንቆ" የሚለው ቃል የክፋት አሳዳጊ አባትህ ዲያብሎስና አንተ ባሪያው አላማችሁን የምታስፈጽሙበት ቃል ነው። አቶ አራዳው መሃይም፦ ማህበረ ቅዱሳን ለናንተ አሉባልታ ቦታም ትኩረትም የለውም። ማህበሩ ብዙ የቤተክርስቲያን የማዳንና የጽድቅ ተልኮ አለበት። ቤበክርስቲያን ማህበሩን ብዙ ሊድኑ የሚወዱ የክርስቶስ ነፍሳት በሾኮች መካከል አሉና የክርስቶስን ወንጌልና ስርዓት ይዛችሁ ተፋጠኑ ብላ ስላዘዘቻቸው የሾኮችን ውጊያ ሳይፈሩ ለመዳን የክርስቶስን ወንጌል ለሚጠባበቁት ለመድረስ ይፋጠናሉ። ማህበሩ የእውነትና የክርስቲያኖች ጠላትን እንቅስቃሴ በመከታተል በቤተክርስቲያን ላይ የአቀዱትን የጥፋት ዘመቻና ተሳታፊዎችን በማጋለጥ ቤተክርስቲያንና በክርስቶስ ያላትን የጽድቅ እምነት ለመጠበቅ ተግቶ ይሰራል። ማህበሩ በተለያዩ የማህበራዊ ውጣውረዶች ላሉት የበጎ አድራጎት ስራዎችን ለማከናወን ይፋጠናል። እናንተ ግን በውሸትና በፈጠራ እንትና እንዲህ ተባለ ፤ እንዲህ አደረገ፣ ወዘተ የሚሉ የዲያቢሎስን የእርኩስ መንፈስ ቋንቋዎችንና ቀስቶችን እውነትንና እውነተኞችን ለማስነወርና ለመውጋት ሌት ተቀን ለመወርወር ትፋጠናላችሁ። በሉ መናፍቆችና አራዳው መሃይም ደህና ሁኑ ሁን።

   Delete
 18. @Damot
  kikiki...........you are professional idiot. As you bark to undermine others you are showing how kiddish and raw you are.

  ReplyDelete
  Replies
  1. For anonymous march 10, 2015 at 3:04pm
   You are out of the human being immage. You are a proffssional liar. There is no competitive for your false creativity and accusation to make the milk dark. I know who you are even you use the profile name anonymous. you are aba selam blog.

   Delete
 19. በመንፈሳዊ አስተምህሮ ውስጥ ሆናችሁ ስትሰዳደቡ በጣም ትሰቀጥጣላችሁ። መሰዳደብ ነው ወይስ በተሠማችሁ ነገር ላይ አስተያየት መስጠት ነው የያዛችሁት?
  አባታችን ምን ማለት እንዳለባቸው የሚያውቁ ይመስለኛል። እኔን እንደገባኝ ግን እመቤታችን መጀመሪያ ስትፈጠር ለአምላክ ማደሪያና አላማውን ማስፈጸሚያ ሆና ተፈጥራለች ወይም ፈጥሯታል። መጀመሪያም በአምላክ ህሊና ታስባ ትኖር ነበር ተብሎ ተምረናል። ስለዚህ አምላክ ንጽህናን ከሰው የንጽህና ባህሪ ተዋሰ ሳይሆን እረሱ ንጽህናን ይሰጣል ማለት ነው። መጥቶ ያደረባት ለማደሪያው እንደምታመቸው ንጹህ አድርጎ ስለፈጠራት ነው። በእመቤታችን ለአምላክ ማደሪነት ዙሪያ አባቶቻችን ብዙ ብለውላታል። ሆን ብሎ ለማጣመም ካልሆነ በስተቀር። እግዚአብሄረ በተክርስቲያናችንን ያጽዳል።

  አምላካችን ልቦናችንን ያብራልን።

  ReplyDelete
 20. እረገይ! መሰዳደብ አያሥፈልግም ነውር ነው::ኑማ ወዲ ነገሩን እናብስለው::ሁላችንስ ለምጥደቅማ አይዶል? ስድብና ፌዝ የት ያደርሰናል?

  የተዋሕዶ እምነት ዛሬ በሚወጡ ጽሁፎች አይደለም የሚወሰነው::የተወሰነ፣ የተቆጠረ ፣የታመነ፣የተሰፈረ፣ መሰረታዊ የሃይማኖት ድንጋጌ ያለት፤ በደም የተመሠረተች፤ ለ ዘመናት የምታበራ ናት_ ይች ቤተ ክርስቲያን::

  ሰውዬው እንደዛ ካለ ይህ ከቤተ ክርስቲያን በአፋ ነው::

  ግን ቤተክርስቲያኗ እና አማኞቿ ምን ይላሉ ነው ጉዳዩ?
  እንዲህ:-
  ፩.ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው::
  ፪.ኢየሱስ ፈራጅ እንጅ አማላጅ አይደለም::
  ፫.ድንግል የኢየሱስ እናት እናት፤ድንግል የእግዚአብሔር እናት ናት::
  ፬.ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው!
  ፭.ክርስቶስ ምንም ከማንም አይፈልግም::ነገር ግን በፈቃዱ እና በፈቃዷ ከድንግል ሥጋና ነፍስን ነሣ(ወሰደ ፣ገንዘቡ አደረገ)::
  ፮.ክርስቶስ የለበሰው ሥጋ ና ደም ነፍስም ከድንግል ነሳ! ይህም ሥጋ ደም ነፍስም ከአብሶ ነጻ ነው ፤ምንም እንከን የለበትም::
  ፯.ድንግል ማርያምም እንከን የለባትም::
  ከዚህ ውጭ የሚያስተምር ውጉዝ ይሆናል::
  በቃ!
  አንድ ሰው እንዲያ ፣ሌላ እንደዚህ ቢል መንጫጫት አያስፈልግም::
  ሰው ከስህተት ፣ይህ ብሎግ ከውሸት፣ ብረትም ከዝገት ወጥቶ አያቅምና!

  ውይ እረስቸው!
  ጾም ነው! ክፉ ነገር ከመናገር ከመጻፍ ከማንበብም እንቆጠብ!
  እናሳርገው:-
  በወልድ ያመነ የዘላለም ሕይወት አለው::ሰው ኢየሱስ ክርስቶስን አምላኬ ፈጣሪዬ ብሎ ካላመነ ዛሬ ይፈረድበታል፤ መቼ?- ዛሬ!!!
  (ጌታዬ ሆይ ስምክን አንጠልጥዬ ኢየሱስ ስላልሁ ይቅር በለኝ::ወደ ወረዱት ወርደን እንኖራለንና ወደ እነሱ ሜዳ ወርደን ሥምህን '''ጌታችን ፣መድኃኒታችን፣ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ''' ብንል አያቁህምና ነው!)

  ReplyDelete
 21. ለምን እንደ አህያ ታናፋለህ የአህያ ተፈጥሮ አለህ አንዴ?

  ReplyDelete
 22. Beweld yamene...ena leloch mistratin mefetsem yasfeligal. Lemisale sigawun demun mewsed, metemek, be niseha memelalese.... Yaleziya eyesus geta new eyalk tifenedaleh enji fitun atayim. Ante menafi!!!

  ReplyDelete
 23. Dear Editor,

  Can you please publish the pdf copy of the original publication? If the Orthodox church leadership has been quite after the alleged article has come out, it means the church is dead. In order to believe, i need to see the original copy. It is kind of difficult to imagine this kind of piece "“እመቤታችን ጥንቱን ሰው ሲፈጠር ንጽሕት ዘር ሆና ተወልዳለች፡፡ ጥንተ አብሶ የለባትም የልጇም ንጹሐ ባሕርይነት ከምንጩ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ፍጹም ንጽሕና የተነሣ ነው፡፡” (ገጽ 36)."

  The writer of the above quote is as bad as Arios, if not worse.

  ReplyDelete
 24. ለሁሉም ክርስቶስ የለበሰው ስጋ ከድንግል የነሳው ነውና እሷም የውርስ ሐጢያት ያልነካት ንፅህት ዘር ናትና የለበሰው ስጋ ንጽህና ከድንግል ንጽህና የተነሳነው። ምክንያተቱም ክርስቶስ ንፁሐ ባህሪ የሆነ ነውና ሐጢያት የነካው የአደፈ ሰውነት አይስማማውምና።

  ReplyDelete
 25. ሰዎች ተረጋጉ እንጂ በስድብና በነቀፋ ማንንም ማሳመንና መመለስ አይቻልም። ባይሆን በመረጃና በማስረጃ ለመተራረም ሞክሩ። እንደኔ ድንግል ማርያም ጠንተ አብሶ ወይም የውርስ ሀጢያት የለባትም። ይህም ጌታ ለማደሪያነት ስለመረጣት በልዩ ጥበቡ ከሀጢያት ጠበቃት። ያ ማለት ግን የእረወሷ ንፅህና ለክርስቶስ መሰረት አይደለም ባይሆን በተቃራኒው ነው እንጂ። የእርሱ የባህሪ ንፅህናው ለእረሷ የፀጋ ንፅህናን ሰጥቷታል

  ReplyDelete
 26. ለሀጢያተኛው ሠው ቤዛ ለመሆን ንፁህ የሆነ ከሠው ወገን ስለጠፋ ፍፁም ሠው ፍፁም አምላክ የሆነው ከድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ የነሳው እየሱስ ክርስቶስ ሁሉ ቻይነቱን ተጠቅሞ( በመንፈስ ቅዱስ ልዪ ጥበቃ ) ሰውን አደነ ፡፡ ፡፡ ፡፡

  ReplyDelete