Saturday, March 14, 2015

ሰበር ዜና፦ ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ በሊቃውንተ ጉባኤ ፊት ተጠይቆ ኑፋቄውንና ክሕደቱን አመነከዚህ ቀደም እንደ ዘገብነው ለዘንድሮው የጥምቀት በዓል በተዘጋጀ መጽሔት ላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ የሆነና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም ታይተውም ተሰምተውም የማይታወቁ ኑፋቄዎችን በመዝራት ቤተክህነት ውስጥ ትልቅ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ የሰነበተው፣ በቅዱስ ፓትርያርኩ ስለኑፋቄው የተገሠጸውና ቋሚ ሲኖዶስም ስብሰባ አድርጎ ኑፋቄው በአስቸኳይ ተጣርቶ እንዲቀርብና ምላሽ እንዲሰጥበት ውሳኔ ያሳለፈበት፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስም በፓትርያርኩ በዓለ ሢመት ላይ ከኑፋቄዎቹ አንዱን ነቅሰው “ይበል” በሚያሰኝ ግሩም ቅኔያቸው ለኑፋቄው የቤተ ክርስቲያን ዝምታ እንዲሰበር የቀሰቀሱበት ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ ከብዙ ማንገራገር በኋላ አርብ መጋቢት 4/2007 ዓ.ም. በሊቃወንት ጉባኤ ፊት ቀርቦ የእምነት ክሕደት ቃሉን በመስጠት በጽሑፍ ያስተላለፈወ ትምህርት ኑፋቄ መሆኑንና መሳሳቱን እንዳመነ ምንጮቻችን ገለጹ፡፡

እንደ ምንጮቻችን ከሆነ በዕለቱ የመጽሔት ዝግጅት ክፍሉ አባላት በተገኙበት በሊቃውንት ጉባኤ ተጠይቆ የፈጸመውን ትልቅ ስሕተት በመጽሔት ዝግጅት ክፍሉ ላይ በማላከክና ታይቶ የታተመ ጽሑፍ አስመስሎ በማቅረብ ለማምለጥ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም፣ የመጽሔቱ ዝግጅት ክፍል አባላት በበኩላቸው ቅድመ ኅትመት ሁሉም ጽሑፎች በኮሚቴው አባላት የተገመገሙ መሆኑን በአንድ ድምፅ ገልጸው፣ በግምገማቸው ላይ ኃይለ ጊዮርጊስ ጽሑፉን እንዲያርም የነገሩት መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በምን መንገድ እንደሆነ ለጊዜው ባይታወቅም በበሩ ሳይሆን በሌላ በር ገብቶ ጽሑፉ መታተሙን ኮሚቴው አስረድቷል፡፡ ኮሚቴው በመጽሔቱ ላይ ለወጡት ጽሑፎች እያንዳንዱ ጸሐፊ ለጻፈው ጽሑፍ ኃላፊነቱን የመውሰድ አሠራር እንዳላቸው ታውቋል፡፡ የሊቃውንት ጉባኤው በኃይለ ጊዮርጊስ ጽሑፍ ላይ ከሰባት በላይ ኑፋቄዎችን ነቅሶ ቢያወጣም ወደ ክርክሩ ከመግባቱ በፊት ኃይለ ጊዮርጊስ መሳሳቱን በሊቃውንት ጉባኤው እርምት እንደሚያምን አረጋግጧል፡፡

የሊቃውንት ጉባኤው ለኃይለ ጊዮርጊስ ግለሰቡ አመንም አላመነም፤ ተቀበለውም አልተቀበለውም የጻፈው ከባድ ክሕደት መሆኑን ቋሚው ሲኖዶስ ጭምር ጽፎ ስለላከለት እርምት የሚሰጥ መሆኑንና በቤተ ክርስቲያናቱ ልሳናት ስሕተቱ ታርሞ እንደሚወጣ በግልጽ ነግሮታል ብለዋል ምንጮቻችን፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኀይለ ጊዮርጊስ አስቀድሞ የጻፈው ክሕደት ሳያንስ ምንም አልተሳሳትኩም በማለት ክሕደቱን የሚያጠናክር 2 ገጽ ጽሑፍ ከሳምንት በፊት በስሙ ጽፎ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ በትኖ የነበረ ሲሆን ይህም ጽሑፍ ስሕተት መሆኑን በመቀበል ሐሳቡን ማንሣቱን እንዳመነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

እንደዚህ ዓይነቱ ውሳኔ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ውሳኔ በመሆኑ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲጣራ ያደረገው ቋሚ ሲኖዶስና የሊቃውንት ጉባኤው ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፡፡ ብዙዎች እንዲያውም እንዲህ ዓይነቱ ስሕተት ዛሬ የተጀመረ እንዳልሆነና ብዙ ኑፋቄዎችና ክሕደቶች እንዲህ ተከታትሎ እንዲጣሩና ተገቢው ውሳኔ እንዲሰጣቸው ባለመደረጉ ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ እውነተኛ ትምህርት መስለው በነጻነት እንደተቀመጡና የእውነትን ያህል ቦታ ተሰጥቷቸው እንደሚሠራባቸው በሐዘን ይናገራሉ፡፡

የኃይለ ጊዮርጊስ ክሕደት ለጥምቀት በዓል በተዘጋጀው መጽሔት ውስጥ ሲበተን ከሁሉ ቀድሜ ለቤተክርስቲያን ደራሽ ነኝ የሚለው የኃይለ ጊዮርጊስ ወዳጅ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን እስካሁን አንድም ነገር ትንፍሽ አላለምና ብዙዎች ለምን? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ሌሎች የማኅበሩን የተሳሳተ አስተምህሮና አቋም የማይግፉ የቤተ ክህነት ሰዎች በጽሑፍ ወይም በንግግር መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነትን ገልጠው ቢሆን ኖሮ ለክስ ማንም የማይቀደመው ማኅበረ ቅዱሳን በኃይለ ጊዮርጊስ ጉዳይ የዝኆን ጆር ይስጠኝ ብሎ ዝምታን መምረጡ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ለቤተክርስቲያን ትምህርት ከእኔ በላይ ተጠያቂ የለም ባዩ ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህ ያደረገው ነገሩን ስላልሰማ ሳይሆን ኃይለ ጊዮርጊስ ያሠራጨው ኑፋቄ የእርሱም አስተምህሮ ስለሆነ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ እንዲያ ባይሆን ኖሮ ቤተክህነቱ የክሕደት ትምህርት ነው ሲል ማኅበረ ቅዱሳን ዝምታን መምረጥ አልነበረበትም፡፡ እንዲያውም የብዙዎች ጥርጣሬ ጽሑፉን የጻፈው ኃይለ ጊዮርጊስ ሳይሆን ማኅበረ ቅዱሳን ነው የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም ጽሑፉ የእምነት መግለጫ ዓይነት ይዘት ያለውና ስለእመቤታችን በተሳሳተ መንገድ እየተራመደ ያለውን አንዳንድ የስሕተትና የክሕደት ትምህርት ሕጋዊ እንዲሆንለት በማሰብ በነጥብ በነጥብ የተቀመጠ በመሆኑ የአንድ ግለሰብ አቋም ብቻ አድርጎ ለመውሰድ ያስቸግራል ይላሉ፡፡ ስለዚህ የማኅበሩ ዝምታ ከዚህ ጋርም የሚያያዝ ይሆናል የሚል ሰፊ ግምት አለ፡፡

ኃይለ ጊዮርጊስም ክሕደቱን በዚያ መልክ ያሰፈረው ከማንም በላይ ማኅበረ ቅዱሳንን ተማምኖ ነው የሚሉ ወገኖች ይበዛሉ፡፡ ምክንያቱም ማኅበሩ ባለፉት 20 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ቤተ ክርስቲያኗን ከተሐድሶኣዊ ጉዞዋ የኋሊት የጎተታት በልዩ ልዩ መንገድ ሲሆን በዋናነት ኑፋቄና ክሕደት እንደልብ እንዲነገርና ማንም በማኅበሩ በኩል እየተስፋፋ ባለው ክሕደትና ኑፋቄ ላይ ቃል እተነፍሳለሁ የሚል ቢኖር ተሐድሶ መናፍቅ እናሰኘዋለን የሚለውን የማጥቂያ ስልት በመጠቀም እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዛሬ የብዙ ሊቃውንት አፍ ተሸብቦ ያለው በዚህ የማጥቂያ ስልት ሥነ ልቡናቸው ስለተሰለበ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ቋሚ ሲኖዶሱ እንደ ኃይለ ጊዮርጊስ ሁሉ በማኅበረ ቅዱሳን መጽሔትና ጋዜጣ ላይ የሚወጡት ጽሑፎች እንዲጣሩ ቢያደርግ ብዙ ኑፋቄዎችና ክሕደቶች እንዲሁም የቤተክርስቲያን ያልሆኑ ትምህርቶችን እንደሚያሠራጭ ይደርስበት ነበር፡፡ ለነገሩ ከዚህ ቀደም በአባ ሠረቀ በኩል የአጽዋማት ቀኖናን ያፋለሰበትን ጽሁፍ ጠቅላይ ቤተክህነቱ እርምት እንዲሰጥበት ትእዛዝ ቢያስተላልፍም፣ ማን አለብኝ ባዩ ማኅበረ ቅዱሳን እስካሁን ድረስ ምንም ምላሽ አልሰጠም፡፡ ቤተክህነቱም ያ ባለመፈጸሙ በማኅበሩ ላይ የወሰደው እርምጃ የለም፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ብዙዎቹን ጳጳሳት በጥቅምና በማስፈራራት ስለያዛቸው ነገሩ ታፍኖ እንዲቀር በመደረጉ ነው፡፡ ስለዚህ ሲኖዶሱም ሆነ የሊቃውንት ጉባኤው በኃይለ ጊዮርጊስ ኑፋቄና ክህደት ላይ የወሰደውን እርምጃ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ባሉ የኑፋቄና የክሕደት ፋብሪካዎች ላይም ሊወስድ ይገባል፡፡

ለኃይለ ጊዮርጊስ እንዲህ የልብ ልብ የሰጡትና ሌላው መተማማኛው ዘረኛውና በአሁኑ ጊዜ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት የወንዙ ልጅ አቡነ ማቴዎስ ናቸው፡፡ እርሳቸው ከዚህ ቀደም ኃይለ ጊዮርጊስ ከተገኙበትና በዝዋይ ማረሚያ ቤት 8 ወራት ከታሰረበት ሴት የመድፈርና የግብረ ሰዶም ወንጀል መታረም አለመታረሙ በቅጡ ሳይረጋገጥ ለእርሱ ማንነት በማይመጥነው የስብከተ ወንጌል መምሪያ ምክትል ኃላፊ አድርገው መደቡት፡፡ በቅርቡም በትንሣኤ ዘጉባኤ በማሽን ግዢ አጭበርብሮ ጉዳዩ በማስረጃ በመረጋጋጡ በአባ ማቴዎስ አካማይነት ከደመወዙ እየተቆረጠ እንዲከፍል በማስድረግ ብቻ እንዲታለፍ ትልቅ ውለታ ውለውለታል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን አባ ማቴዎስ ለዘብተኛ አቋም እያራመዱ ያለው ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ባላቸው ግንኙነትና ለአንኮበሩ ፖለቲካ ኃይለ ጊዮርጊስ ትልቁ ካድሬያቸው ስለሆነ ነው፡፡

አሁን ያለው ትልቁ ስጋት ማኅበረ ቅዱሳንና አባ ማቴዎስ በቋሚ ሲኖዶስ የተወሰነውንና በሊቃውንት ጉባኤ የተጣራውን የኃይለ ጊዮርጊስን ኑፋቄና ክሕደት በተያዘው መንገድ በቤተክርስቲያን ልሳናት እርምት እንዲሰጥበት ሲደረግ ዝም ብለው ይመለከታሉ ወይስ ታፍኖ እንዲቀር ያደርጋሉ የሚለው ነው፡፡ ለሁሉም ሁሉንም እየተከታተልን ለመዘገብ እንሞክራለን፡፡ ይህን ክሕደትና ኑፋቄ በአስቸኳይ እንዲጣራ ላዘዘው ለቋሚ ሲኖዶስና ላጣራው ለሊቃውንት ጉባኤ ግን በድጋሚ ከፍ ያለ ምስጋናችንን ማቅረብ እንወዳለን፡፡

15 comments:

 1. ካፈርኩ አይመልሰኝ! ለአባ ሰላማ ባይ የሰይጣን ብሎግ
  ብዙ ዳከራችሁ፣ ብዙ ስሞች እየቀያየራችሁ ብዙ የጥፋት ቅሰጣዎችን ተገበራችሁ፣ ምንም አይነት ለተንኮላችሁ የሚያፍር ህሊና ሳይኖራችሁ የጊዜውን የፓለቲካ ውጥቅንጥና ከስርዓቱ ጋር ያላችሁን ቁርኝት እንደጋሻ በመጠቀም በማን አለብኝነት ለግለሰቦች የተለያዩ ተቀጥላዎችን በመስጥተና ያልዋሉበትን ዋሉበት፤ ያልሰሩትን ይህን ሰሩ፤ ያልተናገሩትንና ያልጻፉትን ይህን ጻፉና ተናገሩ፤ ቤተክርስቲያን ያመነችበትን እምነትና ስርዓት በማምለሿና በመፈፀሟ ብቻ ስታብጠመጥሏትና ስታቃልሏት ሰው የሚባለው የተሸከመው እንዲህ አይነት ስነምግባር ነው ወይ እውነት ሰው የእግዚአብሔር ፍጡር ነውን በሚያሰኝ ሁኔታ ምድራዊ ፍላጎታችሁንና ሰይጣናዊ ተልሿችሁን ስትከውኑ እረ ታቀቡ የሚላችሁ አልታየም። ይኼን የአሉባልታና የስም አጥፊ ቧልታችሁን ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር የቦለታችሁት። እንዲህም ብላችሁ ነበር በሊቀ ጳጳሱ በዓለ ሲመት ማግስት በአባቶች ፊት ቀርቦ ሊመረመር ነው የሚል ውሸታችሁንና አስመሳ መሰሪነታችሁን እውነት ለማስመሰል። ነገር ግን ነገራችሁ ሁሉ የውሸትና የጠላት ቅሰጣ መሆኑ ሲነቃባችሁ ከአፈርኩ አይመልሰኝ በማለት አመነ በሚል ሌላ የውሸት ቧልት ብቅ አላችሁ። ምንጮቻችን ነው ያላችሁት። የምን ማስክ ማጥለቅ ነው። እነማን ይሆኑ ምንጮቻችሁ። እነ ስሜ እገሌ ወይስ መምህር ነኝ ባዩ አዲስ፣ ነው ከብዙዎች እየለዋወጣችሁ ከምትጠቀሙባቸው ስሞቻችሁ ። መቸም ስም አይገዛም ካለከልካይ ብዙ ስም ትለዋውጣላችሁ። አንድ ነገር እወቁ ይህ የለቀቃችሁት ጽሑፍ እውሸት መሆኑን በእያንዳንዷ የተጠቀማችሁባቸው ማረጋገጥ ይቻላልና ከራሳችሁና ከላኪያችሁ ከሰይጣን ውጭ ማንም አይቀበለውም። እናንተ ብዙ ፀያፍና ነውረኛ ንግግሮችን እየተጠቀማችሁ በቤተክርስቲያንና በእውነተኞቹ አገልጋዮች ላይ ብትዘምቱም ከንቱ ትደክማላችሁ እንጂ ሄኖክና ኤልያስ መጥተው እውነትን እስኪመሰክሩላችሁና አንቀበልም ብላችሁ እነሱን በሰይፋችሁ ቀልታችሁ በአደባባይ እስክትጥሏቸው ቤተክርስቲያንም ትኖራለች እውነተኛ አገልጋዮችም በአገልግሎታቸው ፀንተው ያገለግላሉ።

  ReplyDelete
 2. yenanten tsuhif sanib pente lay yalegn tilacha eyechemerebing newu, min yishalegnal??? bewunu methihaf kidus washtachihu silegeta sibeku yilal?
  eske mawkachewu abune matewos kidus sewu nachewu, haile geyorgisim gibre sedomawi aydelem. yih hulu wushet yemiasayewu enante sewoch/pente/ yeseytan maderia mehonachihun newu. ke tifat serawit amlak yitebiken.

  ReplyDelete
 3. It would be great if you provide documentation or evidence (letter from the synod, minutes, his response,....) to substantiate your writings. Also, we would like to know all of his heresies (7 in total?) in addition to the one related to St. Mary and Jesus Christ.

  ReplyDelete
 4. Ymndr wregna!! LMHONU THADSOAWE guzu mn lmalt nw? Chrash bgiltis? ??

  ReplyDelete
 5. ወኖላዊነ ካልእ ኢይሰየም ውስተ ኩሉ አጽናፍ
  በሐውርተ ሽዋ ወዳሞት ዘኢኮነ እምቤተ ተክለ
  ሃይማኖት ወኮነ ሥሩዓ በግዘት በመዋእለ አቡነ
  ፊልጶስ ሊቀ ኖሎት » ( ከሽዋና ከዳሞት አውራጃ
  ጀምሮ በሁሉም ሀገር ከተክለ ሃይማኖት ወገን
  ያልሆነ አለቅነት አይሾም፤ ይህም በአባታችን
  በፊልጶስ ዘመን በግዝት ተወስኗል) ገድ /ተ / ሃይ/
  ም 59 ቁ 11 ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous march 15,2015 at 6:59pm
   ለመሆኑ ከተክለሃይማኖት ወገን ካልሆነ ሲል ምን ማለት እንደሆነ ገብቶሃል? አንተ የተመለከትክበት በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱሳ በመንፈሳዊ አይን ሳይሆን በሰይጣን መንፈስ በስጋ አይን ነው። ለማለትም የፈለግኸው ለክስና መልካሙን መልእክት ከፉ ለማድረግ በተለመደው የዘረኝነት ግሳንግስህ ለማዳበል ነው። አስተያየት ብለህ የጻፍከው በራሱ እንሿን የውሳኔውን ትክክለኛ ትርጉም ይነግርሃል። ይኸውም በስም የጠቀስካቸውን ጨምሮ በሁሉም አገር ሲል የተክለሃይማኖትንም የትውልድ አገር ይጨምራልና ነው። ለሁሉም ግን ከተክለሃይማኖት ዐገን ሲል በሃይማኖት፣በአገልግሎት፣ በምግባር፣ በኑሮ፣ በአጠቃላይ በክርስትና የመንፈሳዊ ህይወት የሚመስልና አንድ የሆነ ማለት ነው እንጂ የዘር ምርጫና ጥላቻ አይደለም። ወገን የሚለው ቃል በህይወት መጽሐፍ ውስጥም ይገኛል፤ እንዲሁም ተብሉ "ከኛ ወገን ነበሩ…።" እዚህ ጋ ከኛ ወገን ሲል በዘር መመሳሰል ወይም በአር ልጅነት ሳይሆን በእምነት ወገንተኝነትን ወይም አንድ መሆንን ነው የሚገልጠው። ወዳጄ በቤተክርስቲያ ባሪያ ጭዋ አይሁዳዊ ግሪካዊ የሚባል ቋንቋ የለም። ሌሎች የገድላት መጽሐፍትን መልእክታትም እንዲህ በአለማዊ አይን እየተመለከታችሁና እየሳታችሁ ትክክለኛውን ትርጉም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከተሰማራችሁበት አላማ በመነሳት እያጣመማችሁ እውነትንና የእግዚአብሔርን ሐይል እንዲሁም የቅዱሳንን ክብርና ፀጋ ለማራከስና ለመወንጀል ስትዳክሩ ትገኛላችሁ ትታየላችሁም። ይህም የስተት ጉዟችሁ ለመዳን ሳይሆን ለመጥፋትና ለጊዜውም ቢሆን በሚጠፋና በሚዝግ ምድራዊ ጥቅም መደሰት ነውና ማንኛውም እውነትን የማጣመም እንቅስቃሴያችሁ የሚጠበቅ ነው። የእውነት በትር ትቀጥናለች እንጂ አትሰበርምና ቤተክርስቲያንና እምነቷ ብዙ ፈበናና መከራ ቢፈራረቁባትም ሳትሰበር ትኖራለች።

   Delete
 6. @Damot
  You are anti gospel. May lord Jesus open your eyes.

  ReplyDelete
  Replies
  1. No, No, ny dear. I am anti devil. I am try to show your bad act and behaviour. I am answering and responding for what you are saying and said. If you not stop attacking the truth and our church which is Orthodox tewahedo, I will tell you your mistake and false accusation.

   Delete
 7. thank you guys, truth never never never die.........................

  ReplyDelete
 8. Why don't You join ISIS? Maferiawoch.

  ReplyDelete
 9. thank you very much aba selama. this is good news for our church

  ReplyDelete
 10. አቤት ውሸት፣ አቤት ተረት፣ አቤት ስም ማጥፋት። ለነገሩ ከናንተ ሌላ ምን ይጠበቃል? ከዝንብ ማር? እንዴት ተደርጐ።

  ReplyDelete