Wednesday, March 18, 2015

ዝማሬዎቻችን በወንጌል ጐዳና እየተጓዙ ነው የዘማሪ ገ/ዮሐንስ፣ የዘማርያት ጽጌረዳና ዘርፌ እውነተኛ ዝማሬዎች በጥቂቱ ሲቃኙዝማሬዎቻችን ከጊዜ ወደጊዜ ከፍተኛ ለውጥ እየታየባቸውና ለሕዝበ ክርስቲያኑ መንፈሳዊ መነቃቃትን እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ የክርስቶስን አዳኝነት የሚሰብኩ፣ መንፈሳዊ ቆራጥነትንና ጀግንነትን በማወጅ ክርስቲያኖች ሁሉ ስለክርስቶስና ስለወንጌል እንዲጀግኑ እንጂ እንዳይፈሩ የሚያደፋፍሩ ዝማሬዎች በስፋት እየፈሰሱ ነው፡፡ የሕዝበ ክርስቲያኑን መንፈሳዊ ረሃብና ጥማት እያስወገዱና እያረኩ እንዳሉም ዝማሬዎቹ ካላቸው ተደማጭነትና ተቀባይነት መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለዛሬው በቅርቡ ተደማጭነት እያተረፉ ካሉ ዝማሬዎች የዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገብረ ጻድቅ፣ የዘማሪት ጽጌረዳንና የዘማሪት ዘርፌ ከበደን ጥቂት ዝማሬዎች ለአብነት እንዳስስ፡፡

“ዘፀአት ነው ለሕዝቡ” የሚል ስያሜ የተሰጠው የዘማሪ ገብረ ዮሐንስ ቍጥር 2 የዝማሬ ሲዲ ውስጥ ከተካተቱት ድንቅ ዝማሬዎች መካከል አንዱ “አብ የተከለው” የሚል ነው፡፡ ርእሱ እንደሚመሰክረው ዝማሬው ጌታችን በተናገረው ሕያው ቃል ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል” (ማቴ. 15፥13) በሚለው ቃል ላይ፡፡ በዚህ ቃል አዝማችነት የተዋቀሩት የመዝሙሩ ስንኞች በሰማዩ አባት የተተከለ ክርስቲያን ሕይወቱ የድል፣ የጽናት፣ የውጤት መሆኑን ያመለክታሉ፡፡ ይህም የሚሆነው የወይን ግንዱን ኢየሱስ ክርስቶስን የተደገፈ ሕይወት ስለሚኖረው ነው፡፡ የዝማሬው አዝማች እነሆ
አብ የተከለው አይነቀልም
ያድጋል በጸጋ ለዘለዓለም
የወይን ግንዱን የተደገፈ
ያልፋል ሁሉንም እያሸነፈ
ሌላው የዘማሪው ድንቅ መዝሙር “ኢየሱስ ልበል ኢየሱስ እርሱ ነው ሕይወቴ
                                   የምኖርበት ተስፋ እርሱ ነው ዕረፍቴ
   ያለጌታ ብኖርማ እንዴት እሆናለሁ
   ስለስሙ ብነቀፍም ነፍሴን እሰጣለሁ
ይህ ዝማሬ ከጥቂት ዓመታት በፊት “ኢየሱስ” ብሎ ስሙን መጥራት እንደሌላ በሚያስቆጥርበት ማኅበረሰብ ውስጥ የተዘመረ መሆኑን ስናስብ፣ ምንም እንኳ ስሙ መጠራቱ የሚያስቈጣቸው ቢኖሩም ነገሮች እየተለወጡ መሄዳቸውን ግን ያሳያል፡፡ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በሊቀ ጳጳስ ደረጃ እንኳ “ኢየሱስ አትበሉ” ሲባል በሰማንባት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ፦

“ኢየሱስ ልበል ኢየሱስ እርሱ ነው ሕይወቴ” ሲባል መስማት እጅግ ደስ ያሰኛል፡፡ እውነት እያሸነፈ ሐሰት ደግሞ እየተሸነፈ መሄዱን ያሳያል፡፡ በዚህ ዝማሬ ስንኞች ውስጥ ዘማሪው የጌታን ስም የሚጠራው ጌታ ሕይወቱ ስለሆነና ያለእርሱ መኖር እንደማይችል ማመን መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ ኢየሱስ በማለቱ ግን ነቀፋ እንደሚገጥመውና ቢነቀፍም ነፍሱን ይሰጣል እንጂ ኢየሱስ ማለቱን እንደማያቆም ያሰረዳል፡፡ ይህም የአይሁድ ሸንጎ ሐዋርያት ዮሐንስና ጴጥሮስን ጠርተው ከዚህ በኋላ ኢየሱስ የሚለውን ስም ጠርተው እንዳያስተምሩ ባዘዟቸው ጊዜ “እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እናንተን እንሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት የሚገባ እንደ ሆነ ቍረጡ፤ እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም” ካሏቸው ጋር ይመሳሰላል፡፡ (የሐዋ. ሥራ 4፥19-20)፡፡ የዝማሬው አብዛኛው ስንኞችም ከዚህ ሐሳብ ጋር የተያያዙ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ለምሳሌ፡-
በአይሁድ መንደር ስሄድ የቤቱ ቅናት በላኝ
ኢየሱስ የሚሉትን ስሙን አትጥራ ቢሉኝ
እምቢ ብያለሁ ያለፍቅሩ አልመላለስም
ያበራልኝ ይታየኛል እኔ አላፍርበትም  
የሚሉትን ስንኞች መጥቀስ ይቻላል፡፡ ዘማሪው ቀድሞ አይሁድ የኢየሱስን ስም ለምን ትጠሩብናላችሁ በሚል በሐዋርያት ላይ ያደርሱት የነበረውን ዓይነት ስደት ዛሬም ለመድገም የሚፈልጉ ወገኖች ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳሉ እየጠቆመ ይመስላል፡፡ “የኢየሱስን ስም ለምን ትጠራላችሁ? ኢየሱስ ማለት የሌሎች ነው የእኛ አይደለም” ወዘተ እያሉ ለሃይማኖታቸው ቀናተኛ የሆኑ ለእግዚአብሔር ጥብቅና የቆሙ የሚመስላቸው ነገር ግን የእግዚአብሔርን ሐሣብ እየተቃወሙ ያሉ ዛሬም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ አሉ፡፡ ስለዚህ እንደ አይሁድ የኢየሱስ ስም ሲጠራ ከሚበሳጩ ይህን ስም በእምነት ቢጠሩ ይድናሉ፡፡ ይህን ምርጫቸው ቢያደርጉ መልካም ይሆንላቸው፡፡

ሌላው የዘማሪ ገ/ዮሐንስ ድንቅ ዝማሬ፦ እውነት ነው አዎን እውነት ነው
                                        ሕይወት ነው በእርግጥ ሕይወት ነው
                        መንገድ ነው አዎን መንገድ ነው
                                        ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው
                                                ወደ እግዚአብሔር አብ የምንደርስበት
                                                አንድያ ልጁም የምናምንበት
                                                የሕይወት መንገድ እርሱ ብቻ ነው
                                                የባሕርይ አሞላክ ብለን የምናምንበት … እያለ የሚቀጥለውና በዮሐንስ ወንጌል 14፥6 ላይ የተመሠረተው ዝማሬ ነው፡፡ ይህም ዝማሬ ወንጌሉን መሠረት በማድረግ የመዳን ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ መሆኑን የመሰከረበት ዝማሬ ነው፡፡ ከዘመሩ አይቀር እንዲህ ነው!!

ዘፀአት ነው የሚለው ሌላው ዝማሬም እንዲሁ ግሩም ድንቅ ምስጢር የተመሰጠረበት ዝማሬ ነው፡፡ የእስራኤል ዘሥጋን ከባርነት ቤት ከግብጽ ነጻ የመውጣት ታሪክ የእስራኤል ዘነፍስ የእኛን ከዘላለም ሞት በክርስቶስ ነጻ ከመውጣት ጋር የተናጸረበት ዝማሬ ነው፡፡

ሌላዋ ድንቅ ዝማሬዎችን ያበረከተችልን ዘማሪት ጽጌረዳ ናት:: ከዘማሪት ጽጌረዳ መዝሙሮች መካከል የአመቱ ምርጥ ዝማሬ ሊባል የሚችለው ዝማሬ “በሬ ነህ” ይሰኛል፡፡
በሬ ነህ መመላለሻ መንገዴ
ሕይወት ነው ሞት አይደለም ባንተ ፍርዴ
በሬ ነህ መመላለሻ መንገዴ
ይህ ዝማሬ በዮሐንስ ወንጌል 10 እና 14፥6 ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ላይ “በሩ እኔ ነኝ” ብሎ ተናግሯል፡፡ ዘማሪዋም ጌታዋን በሬ ወይም የእኔ በር አንተ ነህ፤ የምገባው በአንተ በኩል እንጂ እንደ ሌባ በሌላ በኩል አይደለም ስትል ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ወደ እግዚአብሔር የሚገባበትም በር እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑን መስክራለች፡፡
ህይወትና ሰላም ባንተ ያሉት ሁሉ
ከበው ያፅናኑኛል እየተከተሉ
አልዞርም በጓሮ እኔስ እንደ ሌባ
በሬ ነህ ክርስቶስ ባንተ በኩል ልግባ
ያለው አንድ በር ነው ብዙ በሮች የሉም እያለ ቅዱስ መጽሐፍ እጅግ በርካታ በሮች አሉን በፈለግነው አማርጠን መግባት እንችላለን፤ ከዚህኛው በር ያኛው ይሻላል ወዘተ በሚልና በሮቹን ባበዛው ትውልድ መካከል ያለው በር አንድ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ጽጌረዳ በዝማሬዋ መስክራለች፡፡ እንዲያውም እንደሌባ በጓሮ አልዞርም በበሬ በኢየሱስ በኩል ነው የምገባው እያለች ነው፡፡ የዚህ የዝማሬ ሐሣብ የተወሰደው ከወንጌል ነውና እውነት ነው ምንም ሐሰት የለበትም፡፡ እውን ይህን ዝማሬ ማን ሊቃወመው ይችላል? ይህን ዝማሬ መቃወም ማለት ጌታችን ያስተማረውን ትምህርት መቃወም ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ እባካችሁ የመዝሙር ግጥም የምትገጥሙ ወንድሞችና እኅቶች ቃሉ የሚለውን መሠረት አድርጋችሁ ብቻ ዝማሬዎችን ሥሩ እንጂ ለሰው ደስታ ወይም ስማችሁን ለመጠበቅ ስትሉ ያልሆነ ነገር አታደርጉ፡፡ ለቃሉ ታማኞች ሆናችሁ ዝማሬዎችን ከሠራችሁ ዝማሬዎቻችሁ የሰውን ሕይወት የሚነኩ ይሆናሉ፤ በቃሉ ላይ የተመሠረቱ እስከሆኑ ድረስ ዘመን ይሻገራሉ፤ አይሰለቹም፡፡ 

የጽጌረዳ ሌላው ድንቅ መዝሙር “ዋላ” የሚለው ነው፡፡ ይህ ዝማሬ የዳዊትን መዝሙር የሚያሳስብና(መዝ. 42÷1) የነፍስን ጥማትና የእርካታዋን ምንጭም በግሩም ሁኔታ የሚመሰክር ዝማሬ ነው፡፡
ዋላ ወደ ውሃ ምንጮች እንደሚናፍቅ እንደሚጠማ
ውሃ ናፍቅሀለች ነፍሴ ተትረፍረፍላት ይቆረጥ ጥሟ
በሚል አዝማች የሚጀምረው ሌላው የዘማሪት ጽጌረዳ ዝማሬ ነፍሷ ጌታዋን እንደ ናፈቀችና ጌታ በተትረፈረፈ ሁኔታ በሕይወቷ እንዲገኝና ጌታን መጠማቷ በጌታ እርካታ እንዲተካ ትማጸናለች፡፡ ከዚህ የበለጠ ጌታን የሚያስደስተውና ቶሎ ምላሽ የሚያስገኝ ጥያቄ የለም፡፡ ምክንያቱም “እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።” ተብሏልና (ሰቆ. 3፡25)፡፡ ዋላ የተባለው የዱር እንስሳ ውሃ ወዳለበት እንደሚናፍቅ የነፍስ ትክክለኛ ጥሟና ረኃቧ አምላኳ ብቻ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ለነፍሳችን ከአምላካችን ውጪ ያሉትን ሁሉ በመስጠት ብዪ ጥገቢ ጠጪ እርኪ ብንላትም ነፍሳችን ግን በዚህ ተደልላ ለጊዜው የበላችና የጠገበች የጠጣችና የረካች ቢመስላትም አምላኳን እስክታገኘው ድረስ ግን እንደባዘነች ትኖራለች፡፡ ስለዚህ ዝማሬው ሰው ሁሉ እውነተኛ እርካታውን ጌታን እንዲጠማ ይጋብዛል፡፡ 
  
በበረሀው አልተጎዳንም በውሀ ጥም
ጠላት ሸሸ አንተ ስትወጣ ስትቀድም
አሳረፍከን ነፍሳችን ሀሴት አደረገች
አማኑኤል ባንተ ከወጥመድ አመለጠች

አዎን ነፍሳችን በአዳኛችን በክርስቶስ ኢያሱስ ከኃጢአት እና ከዲያቢሎስ ወጥመድ አምልጣለች። በርሱ አርፋለች፤ ሀሴትን አድርጋለች፤ ተጽናንታለች። ጌታችን ኢያሱስ ክርሰቶስ የዘላለም እርካታችን ነው የሚል ነው የመዝሙሩ መልእክት። ይህን እውነት መረዳት እንዴት ያሳርፋል?
ሳምራዊቷን ጎብኝተሃታል በቃል ወተት
ከእንግዲህማ የያዕቆብ ጉድጓድ ምን ሊረባት
ተሰደደች ወደ ከተማው ወደ ደርቡ
የሕይወት ውሃ ፈልቆላችኋል ተሰብሰቡ
በእነዚህ ስንኞች ውስጥ ከሳምራዊቱ ሴት ሕይወት ጋር በማዛመድ ክርስቶስን ያገኘ ከዚያ በፊት በክርስቶስ ቦታ የተካውን ሁሉ እንደሚተውና ለሌሎችም ይህን እንደሚሰብክ ዝማሬው ያስረዳል፡፡ እውነት ነው፤ ክርስቶስን በቃሉ መሠረት ያወቀና ሕይወቱን ለእርሱ ያስረከበ ሰው ከእርሱ ውጪ ለማንም ራሱን አያስገዛም፡፡ ከእርሱ ውጪ በሕይወቱ ስፍራ የሚሰጠው ሌላ ሰው ወይም መልአክ የለም፡፡ ነገር ግን መች በዚያ ያበቃል? ይህን ትልቅ ሕይወት ለሌሎችም በማካፈል ሰዎች ሁሉ ወደ ክርስቶስ እንዲሰበሰቡ ያደርጋል፡፡
አቤት ውሃ የሕይወት ፈሳሽ ታላቅ እረፍት
ለምለሙ ሳር ባንተ ቸርነት ምኖርበት
አንድ መንጋ አንድ እረኛ ነው ዛሬም ሰልፉ
ያመኑብህ የእሳቱን ባህር ባንተ አለፉ

የተጠራነው ተበታትነን እኛ እና አነርሱ ልንባባል አይደለም፡፡ በሥላሴ ያመኑ በክርስቶስ ያመኑ ሁሉ የዚሁ አንድ መንጋ ክፍሎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ለቤተ ክርስቲያን አንዲት መሆን ልንተጋ እንደሚገባ ዝማሬው ያሳስባል፡፡  

ሌላዋ በቅርቡ የንስሐ የተባሉ ዝማሬዎችን ያበረከተችልን ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ስትሆን ከዝማሬዎቿ መካከል “አላፍርበትም” የተሰኘው ዝማሬ አንዱ ነው፡፡
አላፍርበትም ያመንኩትን አውቀዋለሁ
አላፍርበትም ለታመነው ታምኛለሁ
ማዕረጌ ነው እስራቱ
ሀብሌ ነው ሰንሰለቱ
እመካለሁ በመከራ
አምኛለሁ እንዳልፈራ

ምን ቢደከም ምን ቢመከር
የእግዚአብሔርን ቃል ላይታሰር
ፍቅሩ ሰብሯል ዝምታዬን
ማን ሊቀማኝ እልልታዬን
በእነዚህ ስንኞች ውስጥ የሰይጣንን ሐሳብ በማስተናገድ በክርስቲያኖች ላይ መከራን ለማድረስ የሚጥሩ ሰዎች ቢኖሩም እንኳ መከራ ሊያደርሱ የሚችሉት በክርስቲያኖች ላይ እንጂ የእግዚአብሔርን ቃል ከመሮጥ አይገቱትም (“የጌታ ቃል እንዲሮጥ” ተብሎ ተጽፎ የለምን?)፡፡ በክርስቶስ ፍቅር ያልተነካና ከእርሱ ይልቅ በዚህ ምድር ለጥቂት ጊዜ እንደ ውርደት የሚቆጠረውን ክብር ይዞ ለመኖር የሚፈልገው ከንቱ ሰው ካልሆነ በቀር የክርስቶሰ ፍቅር የነካውና ልቡ በፍቅሩ እሳት የተቀጣጠለበት ሰው ስለክርስቶስ ከመመስከር ስለእርሱም ከመዘመር ወደኋላ አያፈገፍግም፡፡ ለዚህ ነው፦
“ፍቅሩ ሰብሯል ዝምታዬን
ማን ሊቀማኝ እልልታዬን” ያለችው

ከርሱ ጋር ሞት ትንሳኤ አለው
ያልርሱ ግን ህይወት ሞት ነው
ባናምነውም ታምኖ ይኖራል
ራሱን ሊክድ መች ይችላል

ያምናል ልቤ በዚህ ጌታ
አላዜምም ለሰው ደስታ
የታዘዝኩት በቃሉ ነው
በኢየሱስ ስም እንዳደርገው።

በእነዚህ ስንኞች ውስጥ ከጌታ ጋር በሞቱ መተባበር በትንሣኤው ተካፋይ የሚያደርግ መሆኑ በሚገባ ተገልጧል፡፡ ወደ ትንሣኤ የሚደረሰው አስቀድሞ በመሞት ነው፡፡ ከእርሱ ጋር ያልሞተ በትንሣኤው ተባባሪ አይሆንም፡፡ ስለዚህ ከጌታችን ጋር መክበር የሚፈልግ ከእርሱ ጋር መሞት አለበት፡፡ ደግሞም ያለጌታ የምንኖረው ጥሩ የሚባል የዚህ ዓለም ኑሮ በእርሱ ፊት ሲታይ ሞት ነው፡፡ ስለዚህ በማንኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ እንገኝ ዋናው ነገር ከጌታ ጋር እየኖርን ነውይ? የሚል ይሆናል፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን ተጎጂዎቹ እኛ ነን፡፡ ባናምነው ጌታ ታምኖ ይኖራል እንደተጻፈው ራሱን ሊክድ አይችልምና፡፡የመጀመሪያዎቹ አራት ስንኞች መልእክት ይህ ነው፡፡

በቀጣዮቹ ስንኞች ውስጥ ወንጌል ይዞ ተከብሮ መኖር እንደሌለና ስለ ጌታ ስም መከራና ሥቃይ መቀበል እንደሚኖር ተመልክቷል፡፡ ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐቅ ተቀብሎ ክርስቶስን ለመከተል የወሰነ ሰው ደግሞ ስለ ስሙ ቢታሰር ለእርሱ ክብሩና ማዕረጉ ነውና በመከራው በማዘን ፈንታ ይመካል፡፡ “ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤” የሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ አብነት አለውና፡፡ “ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤ (ሮሜ 5፥3-4)፡፡”
ያምናል ልቤ በዚህ ጌታ
አላዜምም ለሰው ደስታ
የታዘዝኩት በቃሉ ነው
በኢየሱስ ስም እንዳደርገው
የሚሉት የዚህ ዝማሬ ስንኞችም እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ ለመከተል መጨከን የታየባቸው ናቸው፡፡ አዎን ለሰው ደስታ ሲባል፣ ለእንጀራ ሲባል፣ ለሲዲው ገበያ ሲባል፣ ዝማሬን መሸቃቀጥ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ለጊዜው ሰው ቢያዝንም እንኳ እግዚአብሔር ደስ ይለዋልና ከሰው ይልቅ እግዚአብሔርን መስማት ለእርሱም መታዘዝ ያስፈልጋል፡፡ ዝማሬን ሁሉ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ብቻ ማድረግ በመድኀኒታችን ኢየሱስ ስምም መዘመር ተገቢ ነው፡፡ እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።” (ቆላ. 3፥17) ተብሎ ታዟልና፡፡

በእምነት እንቢ የሚያሰኘኝ
ከእልፍኝ ስደት ያስመረጠኝ
ውለታው ነው ብድራቱ
መዳፉ ነው እትራቱ
መነቀፌ ብልጥግና
መከራዬ ድል ነውና
በሸንጎ ፊት ቃሌ አንድ ነው
የተቤዠኝ ኢየሱስ ነው    

እነዚህ ስንኞች እንዲሁ ግጥም ለመግጠም ያህል የተገጠሙ አይደሉም፡፡ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ካለው ነባራዊ ሁኔታ፣ በክርስቶስ ስም በአገልጋዮች ላይ እየደረሰ ካለው ስደትና መከራ፣ እንዲሁም በክርስቶስ ፍቅር ልባቸው ከመቀጣጠሉ የተነሣ ለእርሱ በመቅናት የተደረሱ ዝማሬዎች ናቸው፡፡

ሌላውና የዚህ ጽሑፍ መደምደሚያ የምናደርገው ዝማሬ “ባማዬ እልሃለሁ” የተሰኘው ዝማሬ ነው፡፡ ይህ ዝማሬ የሲዲው ስያሜ የሆነው ዝማሬ ነው፡፡ ዝማሬው መልካምና ስንኞቹም ጥሩ መልእክት ያላቸው ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ “ባማ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሕዝ. 20፥29 ላይ የተጻፈ ሲሆን የቃሉ ትርጉም በዕብራይስጥ ከፍ ያለ ቦታ ማለት ሲሆን ጣዖታትን ለማምለክ የሚጠቀሙበትን ቦታ ያሳያል፡፡ መዛግብተ ቃላት እንዲህ ይላሉ ...
Biblehub.com bamah የሚለውን ቃል ሲፈታው “… a name used simply to denote a high place where the Jews worshipped idols” ይለዋል። እስራኤላውያን ጣኦትን የሚያመልኩበት ከፍተኛ ሥፍራ ማለት ነው። ጂውስ ኢንሳይክሎፒዲያም በተመሳሳይ መንገድ ነው ቃሉን የሚፈታው።

ስለዚህ የዚህን የአምልኮተ ጣኦት ቦታ መጠሪያ “ባማ”ን ለጌታ መስጠትና ጌታን “ባማዬ” ማለት ተገቢነት የለውም፡፡ ለወደፊቱም እንዲህ አይነት ስህተት ባይደገም ጥሩ ነው። የዚህ ዝማሬ ግጥም ደራሲ መ/ር ጋሻዬ ደግሞ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ምሩቅ እንደ መሆኑ መጠን ይህን ነገር ማገናዘብ ነበረበት የሚል ግምት አለን፡፡ ነገረ መለኮትን የተማረ ሰው እንዲህ አይነት ስህተት መሳሳት የለበትም። ሚሥጢር ከማዛባት አልፎም ለጌታ የማያስፈልገውን መስዋዕት ማቅረብም ይሆናል። መምህር ጋሻዬ በበቤተክርስቲያኒቱ ላለው የመዝሙር አብዮት እግዚአብሔር ረድቶት ትልቁን ድርሻ የተወጣ ሰው ነው። ቢሆንም ግን ጌታ የሰጠውን ጸጋ በአግባቡ ለመጠቀም፤ ጸጋው የሚጠይቀውን መንፈሳዊ ዝግጅት ማድረግን ግን ቸል ሊል አይገባም። ቃሉን ማጥናት ትርጉሙን ማሰላሰልና አብርሆትን ከመንፈስ ቅዱስ መቀበል የግድ የሚያስፈልግ ነገር ነው። ስለዚህ ለወደፊቱ እንዲህ ያሉ ቃላትን ስንጠቀም ትርጉማቸውን በሚገባ ማጤን፣ ስለምን እንደ ተነገሩ ማስተዋልና መፈተሽ ይኖርብናል፡፡ አሊያ ትልቅ ነገረ መለኮታዊ ስሕተት ውስጥ ልንወድቅ እንችላለን፡፡ ስለዚህ የዝማሬ ግጥም ደራሲዎች ይህንና ሌሎችንም ከመዝሙር ግጥም ጥራትና ይዘት ጋር የተገናኙ ጕዳዮችን በሚገባ ሊያስቡ ይገባል፡፡ 

በአጠቃላይ ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር ብቻ የሰጡት ዝማሬዎች የመወደዳቸው ምስጢር ሌላ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረቱ መሆናቸው ነው፡፡  ይህ መሠረታዊ ነገር ዝማሬዎቹን ዘመን ተሻጋሪ ያደርጋቸዋልና ለወደፊቱም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ ይህን የማይወዱና ዝማሬዎች በሌላ መንገድ እንዲቀርቡ የሚፈልጉ፣ በዚህ መንገድ እየዘመሩ ያሉትን መዘምራንና መዘምራት በተሐድሶነት የሚፈርጁ ክፍሎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ ዘርፌ እንደዘመረችው ለሰው ደስታ ተብሎ የሚዘመር ከሆነ እግዚአብሔር ያዝናል፡፡ የመዘምራኑም ኅሊና ዘወትር ይከሰሳል፡፡ ስለዚህ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ምረጡ!! ከላይ የተጠቀሱ ዝማሬዎችን የደረሱ ደራሲዎችን በዚህ አጋጣሚ በርቱ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ምንም እንኳን ዝማሬዎቹ በመዘምራኑ ቢታወቁም ከእነርሱ ጀርባ ያለችሁት እናንተ ናችሁና ለእናንተም ዕውቅና መስጠት ያስፈልጋል፡፡

18 comments:

 1. ማስተዋሉ ይጠቅማል
  BAMAH:
  This word, which ordinarily designates a "high place" (see High Places), is introduced in Ezek. xx. 29 as a generic name for an idolatrous place of worship for the purpose of playing upon the word, as though "Bamah" were compounded from "ba" (come) and "mah" (whereunto); the term being thus interpreted as a place to which people come—that is, for worship.

  http://www.studylight.org/dictionaries/hbd/view.cgi?n=666

  ReplyDelete
 2. Glory to GOD who created us to worship HIM
  Glory to Marry the MOTHER OF GOD Holy Theotokos
  Glory to the Holy Cross of CHRIST our pride and strength

  ReplyDelete
  Replies
  1. Glory to the father the Pantocrator, and to the Son Lord Jesus Christ, and to the Holy Spirit the life giver.

   We don't give Glory to anyone but God. We honor and venerate his mother and the holy cross.

   Delete
 3. hahhahaha Minew yehen zenegachute kese belachu ende protesetant Kiresetose Amalaje new maletachu yemayeker new 3. እኔምትውልድ ነኝ heart emoticon heart emoticon heart emoticon
  እኔም ትውልድ ነኝ ብፅኢት እልሻለው
  እንደአ ባቶቼ ስምሽን አከብራለው(2)
  አይደለም ከአለም ከስጋናከደም
  በመንፈሥቅዱስ ነው ያወኩት ያንቺን ስም
  ስለዚvማርያም ሆይ ከፍአደርግሻለው
  የፍጥረቱን ጌታ በእቅፍሽ ስላየው
  አዝ……………..
  በዘላለም ኪዳንvእግዚአብሔርbበሰጠሽ
  ከጥፋቱ ውሐ ትውልዱን አስጠለልሽ
  እስከvአድማስ ጥግ ብደርስ ክብርሽን ልገልፅ
  የሚስተካከልሽ የለምከፍጥረት
  አዝ……………..
  በኀጥያትvደክሜ ብኆንም ኮል ታፋ
  ድንግል ሆይ ምልጃሽን አድርጌአለው ተስፋ
  ምስጋናሽ በዝቶልኝ ከጠwaት እስከማታ
  ተፈሥሒል በልበገብርኤል ሠላምታ
  አዝ……………..
  ስለተቀበልኩኝ ስምሽን ከአባቶቼ
  ለአለም እነግራለውክብርሽን አብዝቼ
  ይው እንደሰማው ባይኔም አየሁሽ
  መንገዴን ስትመሪ ከፊቴ ቀድመሽ
  እኔም ትውልድ ነኝ ብፅኢት እልሻለው
  እንደአባቶቼ ስምሽን አገናለው(2)
  ዘማሪ ገብረዩሀን ስገብረፃዲቅ
  ለዘማሪ ገብረዩሀንስ ገብረፃዲቅ
  ዝማሬ መላእክት ያሠማልን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህ ዝማሬ እንዳይታማና ስሙን ለመጠበቅ ሲል የዘመረው እንጂ ትክክለኛ ዝማሬ ነው ብሎ መውሰድ አስቸጋሪ ነው፡፡ ጉዳዩ ይህንንም ያንንም ዘምሯል ሳይሆን በወንጌል መሠረት የተዘመሩትን መዝሙሮች ማድነቅ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ዘምሯል ማለት ዘማሪውን ትክክለኛአያደርገውም እነደውም ቀላቃይና ሸቃጭ ነው፡፡ ምክንያቱም አንዴ ክርስቶስ አንዴ ደግሞ ማርያም እንዴት ይሆናል? አቦ አንዱን ምረጥ? ኤልያስ እንኳን እስከ መቼ በሁለተ ሐሣብ ታነክሳላችሁ በሏል፡፡ ኢያሱም የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤተ እግዚአብሔርን እናመልካለን ነው የሚለው፡፡ ስለዚህ ፍሬንድ ተሳስተሻል፡፡ ይልቅ በገብረ ዮሐንስ እውነተኛ ዝማሬዎች ወደ ወንጌል ና ጌታም እረፍት ይሰጥሃል፡፡

   Delete
  2. ለእንዳይታማና ስሙን ለመጠበቅ ሲል
   ተራ አሉባልተኛና ሐሰተኛ መሆንህ የሚረጋገጠው "እንዳይታማና ስሙን ለመጠበቅ" የሚል አለማዊ የሆነ ንግግርን መጨመርህ ነው። ማንም ቢሆን ላለማታማትና ለስሙ ብሎ ከአመነበት ወደ ኋላ የሚል ካለ እሱ ውሸተኛና ከአህዛብ ፍፁም የባሰ አጥፊ ነው። ይህም ብቻ አይደለም ፦ ማንም በማያምንበት ቦታ ተመሳስሎ የሌላውን ቤት መበጥበጥና ተደብቆ መወንጄል እጂግ የተጠላና የሰይጣን ነው። ዘማሪው አንተ እንዳልከው እንዳይታማና ለስሙ ብሎ ሳይሆን ያመነበትንና እውነተኛውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን መዝሙር ነው የዘመረው። "ዝማሬ ነው ብሎ መውሰድ ያስቸግራል" ላልከው አንተ እንድትዘምረውና እንድትወስደው አትገደድም። ነገር ግን ማወቅ ያለብህ ከመዝሙርም መዝሙር ስጋን ሳይሆን ልብንና ነፍስን የሚገዛ የእውነት መዝሙር ነው። መዝሙርማ ያልሆነውና እግዚአብሔር በማይከብርበትና አለም ስጋውን በሚያስደስትበትና በሚዝናናበት ዳንኪራ የምትደልቁት የእናንተው ረጌ ራጋ ዳንሳችሁ ነው። ሌላው ስህተትህ "በወንጌል መሰረት የተዘመሩትን መዝሙሮች ማድነቅ ነው" የሚለው ነው። እንግዲህ እንዲህ አይነት ማወቅና ማስተዋል ያለህ ግለሰብ ነህ ለነቀፋና ለክስ የተኮፈስከውና የተንጠራራኸው። በመጀመሪያ የተዘመሩትን መዝሙሮች ልንገለገልባቸውና ልናመሰግንባቸው እንዲሁም ልንፈወስባቸው እንጂ ልናደንቃቸው አይደለም የሚዘጋጁት። ሁለተኛው በወንጌል ማድነቅ ሳይሆን እውነትን ማመንና መፈፀም ነው የሚያስፈልገው። ትቀጥልና ደግሞ ቀላቃይና ሸቃጭ በማለት የትችት ማማ ላይ ትንጠለጠላለህ። ምክንያቱም ትልና ደግሞ አንዴ ኢየሱስ አንዴ ደግሞ ማርያም ይሆናል የሚል የማሞ ቂሎ አይነት ማስተዋል የጎደለውና ተራ የክስ ምክንያት ተብየ ምክንያት ትጠቅሳለህ። ለሁሉ ዘማሪው ኢየሱስን አምላክ ብሎ በፀሎት በመዝሙር ያመሰግናል የክርስቶስ የሆኑትን ቅዱሳን እናቱን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምን ጨምሮ ደግሞ ክብርና ፀጋ የበዛላችሁ፣ አምላክ ያከበራችሁና የመሰከረላችሁ፣ የማማለድ የመፍረድ ስልጣን የተሰጣችሁ፣ የማዳን የመፈወስ ስልጣን የተሰጣችሁ፣ በአምላክ ፊት ሞገስን ያገኛችሁና እናንተን የሚጠላ ይፀፀታ የተባለላችሁ እንዲሁም እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል ብሎ ጌታ ኢየሱስ የተናገራላችሁ ክብር ይገባችኋል የእናንተ የአባት የእናቶቸ መንፈስ በኔ ላይ ይደር እያለ ያመሰግናል ይዘምራል። ታዲያ ምኑ ነው ቀላቃይና ሸቃጭ የሚያስብለው ያመነበትን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ከመፈፀሙ ውጭ። የመጽሐፍ ቅዱሱ እውነት አንዴ ተተክቧል። ቀላል አማረኛ እያላችሁ እውነትን በአለም ከንቱ ሃሳብ ለመለወጥ የነጭ ብር ብታፈሱም የክርስቶስን አምላክነትና እውነት እንዲሁም የቅዱሳኑን ክብር ልታጠፉ ቀርቶ ማደብዘዝም አልቻላችሁም። ደግሞ ተራ ድሩየ መሆንህ የሚገርመው" አቦ" የሚል ተራ ቃል መጠቀምህ ነው። ለመሆኑ አቦ ወይስ አቮ ነው ትክክለኛው የአለሙ ያራዳ ቃል? ትወርድና ደግሞ "እስከመቸ በሁለት ሀሳብ ታነክሳላችሁ ብሏል ኤልያስ" የሚል የምንፍቅና ቃላት ውጊያን አራምደሃል። እዛው ትቀጥልና "ኢያሱም የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን" ነው ያለ የሚል ያላዋቂ ክስህንና ውጊያህን ለማካሄድ ደከምህ። ወዳጄ ብዙ ከመሳት ረጋ ብሎ የእግዚአብሔርን ቃል መልእክት ለማወቅና ለመረዳት ለመማር ብትሞክር የተሻለ ነው። አንተ የጠቀስካቸው ኤልያስም ሆነ ኢያሱ የተናገሩት አንድ አይነት የሆነ የተናገሩት ደግሞ እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ውጭ የተቀረፁ ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው እግዚአብሔርም የማይከብርባቸው ብዙ አምላኮች ስለነበሯቸውና ያመልኩ ስለነበር እንጂ እግዚአብሔር ከሚከብርባቸው ከቅዱሳን ክብር ጋር በምንም የሚገናኝና የሚናገር አይደለም። አራዳው ሰይጣን ነህና "ፍሬንድ ተሳስተሻል"የሚል ገልፀሐል። ይህም ከመንፈሳዊነት ይልቅ በአም ዝብርቅርቅ ቃላት መካንህን ነው የሚያረጋግጠው።በመጨረሻም " ይልቅ በገብረ ዩሐንስ እውነተኛ ዝማሬዎች ወደ ወንጌል ና ጌታም እረፍት ይሰጥሃል"በማለት እራስህን ፍፁም ለማድረግ ተቸግረሃል። ወዳጄ ገብረ ዩሐንስ እኮ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዘማሪና የአመነበትን ሳይጠራጠር የሚያመልክና የሚያከብር እንዲሁም ለቅዱሳንንም ክብር የሚሰጥና የሚዘምር እንጂ እንዳንተ አስመሳይ ተንኮለኛ እባብ አይደለም። መዝሙሮቹ ሁሉ እኮ እውነትን የያዙ ትህትናን የሚያስተምሩ እንጂ በጃዝ በካንትሪ የሚያንቧርቁ የእናንተ አዳራሽ ምርት አይደሉም። በእርግጥ አንተ ጌታ የምትለው ሐሰተኛውን ክርስቶስ መሆኑ ግልፅ ቢሆንም ለመሆኑ ጌታ ያሳርፍሃል ማለት ምን ማለት ነው? በመጨረሻ ስለማታውቀውና ስለማታምንበት ከምትዘባርቅ የተካንህበትን የአራዳ ቋንቋ ብታጠናክርና ብትተውን ብዙ ጥርስ ከፋቾች ታገኛለህ። ይህን ያልኩት እውነት ቢነገርህ ስለማትሰማና ልብህን እውነትና ተህትና እንዳይገቡ በትቢትና በውሸት ክርችም አድርገህ ስለዘጋኸው ነው። ደህና ሁን ወዳጄ።

   Delete
  3. Mr. Damot: ወደድክም ጠላህ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ያለሆኑት ዝማሬዎች ከዚህ በኋላ ሥፍራ የማይኖራቸው መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ አይልማ ቃሉ! ከየት አመጣነው? የግድ ጣዖት መመለክ አለበት እንዴ ዛሬም እንደ ብሉይ ኪዳን? የተያያዝነው ባዕድ አምልኮ ነው፡፡ የትኛው አማኝ ነው “አምልኮና አክብሮት” የሚለውን ሀሳብ ተረድቶ እየኖረ ያለ? የት ጋ ነው ሐዋሪያት እነ ጳውሎስ ዛሬ ይህች ቤተክርስቲያን ካሏት ስርዓቶች መካከል ሥፍራ የሰጡት? ግድ የለም አንተም እንደተፍጨረጨርክ አትቀርም እውነት ሲበራልህ እንደ እኛ እጅህን መስጠትህ አይቀርም! እስከዚያው ግን ተፈራገጥ! ሠላም!

   Delete
  4. ለNahom Arayasilassie
   በመጀመሪያ ዛሬ በስምህ መምጣትህ ጥሩ ነው ምንም እንሿን ስም ከመጠሪያነት ባሻገር የአንተን ምግባርና እምነት ባይወክልም።ወደድክም ጠላህም ነው ያልከው? እኔ እንሿን የመውደድና የመጥላት በሚል ምን ለመግለጽ እንደሆነ ባልተረዳኸው ለመመለስ አልፈልግም። ነገር ግን አመንክም አላመንክም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራት ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑ ሰውን ወደ እግዚአብሔርና ንስሐ የሚያቀርቡ ናቸው። ስለሆነም የአንተ የተለሰነው መቃብር የአለምዳንኪራ እግዚአብሔር የማይከብርበት ሰውንም ወደ እግዚአብሔርና ንስሐ የማያደርስ ነገር ግን በአለም ምኞትና ግሳግስ ጠልፎ የሚያስቀር ልብንና መንፈስን ሳይሆን ስጋን የሚያስደስትና የሚገዛ ነውና በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰሚም ስምም የላቸውም። ሌላው "አይልማ ቃሉ" የሚል አስቀምጠሃል። ስለ ምን እንደምትናገር እንሿን የምታቅ አትመስልም። ምክንያቱም የለም አይልም የምትለውን አልገለጽከውምና ነው። ያው አባትህ ሰይጣን ማወናበድና ማታለል ነውና ተግባሩ አንተም ልጁ ያወናበድኩና ያተለልኩ መስሎህ አይልማ ቃሉ የሚል ቃላቶችን አስቀመጥህ። እራስህንና በመዳራት መንፈስ ከሚመስሉህ ውጭ ማንንም ማወናበድና ማታለል አትችልም። ከዛም "ከየት አመጣነው?" ትላለህ። ለዚህም መልስ አይሰጥህም። ምክንያቱም የምትጠይቀውን አንተው አላወቅኸውምና ነው። ትቀጥልና የሰይጣን አስመሳይ ክስህን እንዲህ ትላለህ፦ "የግድ ጣዖት መመለክ አለበት እንዴ ዛሬም እንደ ብሉይ ኪዳን?" በማለት ነው ብሉይ ኪዳን ጣዖት የምታስመልክና የጣዖት አምልኮን የምትፈቅድ አድርገህ ያቀረብኸው። በእውነት እንዲህ የምትል ግለሰብ ነህ መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢና አዋቂ መስለህ ሌላውን በተቀደሰችው የክርስቶስ ቤተክርስቲያ ያሉትን ከእውነት ቦታ በስህተት ትምህርትህ ለማስወጣት መጽሐፍ ቅዱስ ሂድና አንብብ አንብቢ እያልክ በውሸት መንፈስ የምትከሰው። በእውነት እንደ ልድያ ልቦናው የተከፈተ በአንተው የክህደት ወጥመድ የተተበተበ ካለ ይህን የብሉይ ኪዳንን ከጣዖት ያወዳጀኸበትን አይተው በል ሰይጣን ዛሬ ተጋለጥህ እኔ ነፃ ወጣሁ ብለው ከተተበተቡበት መላቀቅ ያለባቸው ዛሬ ነው። በብሉይ ኪዳን ታቦት ነበረና ታቦቱ ጣዖት ነበረ እንዳትለኝና ክህደቱን እንዳታደምቀው። በብሉይ ኪዳን ለቅዱሳን ለመላዕክት ክብር ይሰጥ ነበርና ጣዖታት ናቸው ብለህ ክህደትህን እንዳትለጥጠው። በብሉይ ኪዳን የቤተ መቅደስ ስርዓትና አገልግሎት ነበርና እነዚህም ጣዖት ነበሩ በለንና ክህደትህን እንደባቢሎን ግንብ አስረዝመው። ሌላ የጨመርከው "የተያያዝነው ባዕድ አምልኮ ነው" ብለሃል። በእርግጥ አንተ የተያያዝከው ባዕድ አምልኮ ነው። ምክንያቱም አንተ ክርስቶስን ክደህ ሰይጣንን የምትከተል ነህና ነው። ሰይጣንን የሚያመልክ ደግሞ ለእሱ ለሆኑት ጣዖታት ሁሉ የሚገዛና የሚንበረከክ በመሆኑ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን የምታመልከው እግዚአብሔርን በስም ሶስትነት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ የሚጠራውን ነው። የምታከብረውም የአምላሿ የእግዚአብሔር የሆኑትን እሱ የሚከብርባቸውንና የሚገለጥ የሚጠራባቸውን ነው። ለምሳሌ ታቦትን ታከብራለች ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚከብርበት ስሙና አስርቱ ቃላት የተጻፍበት እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ነው። ነገር ግን ሰይጣንና የእሱ የሆኑትን ሁሉ ተዋህዶ እምነታችን ትጠላ ትጠየፍ ትቃወማለች እስከ ዓለም ፍፃሜ። ከዛም የሚትገርምና ቂል አመፀኛ ከመሆንህ የተነሳ "የትኛው አማኝ ነውአምልኮና አክብሮት የሚለውን ሃሳብ ተረድቶ እየኖረ ያለ?" የሚል የባዶነትህን ክስ ያወጅኸው። እስቲ አንተን መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢውን ልጠይቅህና ክርስቶስ በምድር ላይ በተመላለሰ ጊዜ ይከተሉት ከነበሩት አምስት ሺ ህዝብ ውስጥ ምን ያህሉ ነበር ቃሉን ሰምተው አምነው ይተገብሩ የነበሩት። እዚህ ጋ መታወቅና ማወቅ ያለብህ የቤተክስቲያን እምነትና ትምህርቷ ምን ይመስላል ነው እንጂ ግለሰቦች ምን ይተገብራሉ አይደለም። የግለሰቦች ክፉ ተግባር የራሳቸው እንጂ የክርስቶስን ቤተክርስቲያንን አይወክልም አይመለከትም። ይሁዳ ሌባ ጌታውን አሳልፎም የሰጠ ሆኗልና የክርስቶስ ነው ከክርስቶስ ነው የተማረው ሊባል አይችልም። ሌላው ምንም የማታውቅ መሆንህናለክርስትና ባይታወር ለሰይጣንና ተግባሩ ደግሞ ፈላስፋና የተካንህ ስለመሆንህ ያረጋገጥህበትን እውነት እንዲህ ስትል "የት ጋ ነው ሐዋርያት እነ ጳውሎስ ዛሬ ይች ቤተክርስቲያን ካሏት ስርዓቶች መካከል ስፍራ የሰጡት?" ያላዋቂ ክስና ኢክርስትና አስቀምጠሃል። አይ ወዳጄ!ለምን ከሐዋርያት ሳትሔድ እኮ ክርስቶስ እራሱ እኮ "እኔ ህግንና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ፤ ልፈፅማቸው እንጂ"ብሎ ተናግሯል። ሐዋርያትም "በእናንተ ዘንድ ስንኖር ካለ ስርዓት አልተመላለስንም" ነው ያሉት እኮ። በዘጠኝ ሰዓት ለፀሎት ወደ ቤተ መቅደስ መሄድስ የማን ስርዓት ይመስልሃል? ሐዋርያት የፈፀሙት ዛሬም የሚፈፀም የቤተክርስቲያን ስርዓት ነው። ወዳጄ በክህደትና በሐጢያት የእሳት ክምር እራስህን ከምታቃጥልና ፊደል ቆጥሪያለሁ ብለህ በፊደል ጦር እራስህን ከምትጎዳ በትህትና ወድ ብለህ ብትማር ሁሉንም የቤተክርስቲያን እውነት ትገነዘባለህ ትረዳለህ። በመጨረሻ "ግድ የለም እንተም እንደተፍጨርጨርህ አትቀርም እውነትሲበራልህ እንደ እኛ እጅህን መስጠትህ አይቀርም!እስከዚያው ግን ተፈራገጥ!" የሚል መፈክር ይሁን ዛቻ፣ ህልም ይሁን ቅዠት ወይም ትንቢት አስፍረሃል። ወዳጄ፦ እኔ የሚያጽናና የሚያረጋጋና ወደ እውነት በሚመራ መንፈስ ነው የታተምኩት እንጂ የሚያፍጨረጭር የሚያንፈራግጥ አይደለም። በአመንሁበትም እምነቴ ነው እንዳንተ ሳላምን በማስመሰል ሳይሆን ሆኜ ፀንቸ የቆምኩት ። የምትፍጨረጨረውማ አንተ ነህ በተቢትና በአመፃ መንፈስ አማኝ ሳትሆን መስለህ የክርስቶስን ቤተክርስቲያን ለማፍረስና ለማጥፍት እየተፍጨረጨርክና እየዳከርክ ያለኸው። የምትፈራገጠውማ አንተው ነህ በክፉ መንፈስ እየተናጥህና በክፉው መንፈስ ከመሬት ተዘርረህ እያጓራህና አየጮህ የምትንፈራገጠው። ሌላው ስለ እውነት ብርሃን ተናግረሃል። በብርሃን ሳትመላለስ ስለ እውነት ብርሃን ለመናገር አትችልም። ምክንያቱም አታውቀውምና ነው። የክርስቶስ ብርሃን በርቶ እነሆ ብርሃኑን ባለባት በቤተክርስቲያን እገኛለሁ። ሌላው ደግሞ " እጅ መስጠትህ አይቀርም" ብለሃል። ወዳጄ፦ እጅ መስጠት ማለት ምን ማለት ነው? ከየትስ ነው ያገኘኸው? ይሄ እኮ አንተን አስሮ የያዘህ የሰይጣን ቋንቋ እንጂ የክርስቶስ አይደለም። ልብህን ነው ለእግዚአብሔር መስጠትና ማስገዛት። የልቦናህን በር ነው የክርስቶስ ወንጌል እንዲገባ መክፈትና ማስማረክ ያለብህ። ሁለመናችን ነውለክርስቶስ መስጠትና ማስማረክ ያለብህ እንጂ እጅ እግር የሚባል አነጋገር አይሰራም። ደህና ሁን!

   Delete
 4. ከዚህ ጽሁፍ የተገነዘብኩት ነገር ቢኖር ሥርዓት አልባነትን ነው፡፡ እነዚህ ሠዎች በንስሃ እንኳ እንዳይመለሱ ወደ ገደል የሚወረውር የሰይጣን መሳሪያ!
  እስኪ አሁን ልጆች ሲሳቱ አብሮ መገፋፋት ምን ይሉታል? አንተ ቀበሮ (ሰደበኝ እንዳትል ጌታ ቀበሮ ብሎ ሲገስጽ ስለነበረ ነው) እባክህን ከህይወት መንገድ ዝወር በል፡፡ እነዚህ እምቦቃቅላ የሃይማኖት ህጻናት ምኑንም ሳይውቁት ነው ወደ ኑፋቄው እንዲገቡ ወጥመድ የተጣለባቸው፡፡ አሁንም እንደሚመለሱ ተስፋ አለኝ፡፡ ለዘፈኑት ዘፈንም ይቅርታን ይጠይቃሉ፡፡ እነንተ የሰዶም አለቆች የሰውን ነፍሳት ወደ ሰዶም መንደር መምራት ብታቆሙ ጥሩ ነው፡፡ አውሮፓና አሜሪካን የሰዶም እራት ያደረገ የፕሮቴስታንት መሪ (ሰይጣን) እናንተን እንዳስገባ ሁሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማስገባት ይችላል ብላችሁ አታስቡ፡፡ ዛሬማ ተነቃባችሁ፡፡ ፓስተራችን የምትሉት ዳዊት ሰባ ሽሕ ብር በላ ብላችሁ አማችሁኝ…. ነፍስ የማድን ስለሆኩ እንዲያውም ያንሰኛል ሲል ሰምቻለሁ፡፡ ነገ ደግሞ እናንተ ጌታ አውሮፕላን እንድገዛ ነግሮኛልን ግዙልን እያላችሁ ለመዝረፍ የሚመች ሕዝብ እያፈራችሁ ለመሄድ እንደምትታገሉ ይገባኛል፡፡ ሃብትና ንብረት ፍለጋ ከሆነ ፍላጎታችሁ የንግድ ዘርፎች ስለተበራከቱ ወደዚያ ብትሄዱ መልካም ነው፡፡
  የእናንተ ጉደኛ አውሮፕላን ግዙልኝ ሲል የተሰማው አስቀድሞ የሚመክረው ስላጣ ነው፡፡ እባክህ ጸሐፊ ይህንን አዳምጠው፡፡ http://www.thedailybeast.com/articles/2015/03/14/jesus-wants-me-to-have-this-jet.html?via=desktop&source=facebook

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስማ እንተን ብሎ ደግሞ ተቺ። እዛው ኦርቶ ለኦርቶ ተንጫጫ እንጂ አኛን ለቀቅ አርገን። ዘማዊ የሆኑ መነኮሳትህን ነጻ ለማውጣት ሞክር። አንዱም እዚሁ ብሎግ ጋር ያነሳችሁዋቸው ጳጳስ ናቸው። ግብረ ሰዶም ግብረ ሰዶም ትላለህ ደግሞ ሰሞኑን እንኳ በዚሁ በብሎጋችሁ ከተከስተ ታሪክ ጋር ያነሳችሁት የናንተው ሰባኪ አሸናፊ መኮንን የተባለው ግብረ ሰዶማዊ ነው እያላችሁ በኮሜንት ስትጻጻፉ ነበር። የኛ ተከስተስ ንስሀ ገብቷል። የናንተዎቹ ግን አሁንም ከነ ኃጢአታቸው አሉ። ስለዚህ ወንድም የኛን ፓስተሮች ለቀቅ አድርግና ያንተን ጳጳስና ዲያቆን ጠበቅ አድርግ። ስለ ዝሙትም ስለ ግብረ ሰዶምም ስታወራ ቀድመው እነሱ ትዝ ይበሉህ። የራስህን ስትጨርስ የኛን ቤት ታንኳኳለህ

   Delete
 5. Zemariwochachin OR Zefagnochachin?
  The Mentioned persons are musicians.

  ReplyDelete
 6. በጣም ደስ ይላል። በጎ ነገር መጻፍ ያስደስታል።

  ReplyDelete
 7. ልብ ማድረግ የሚገባን ነገር ለእግዚአብሔር ሥም የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው። የሚሰጠውም ሥም ደግሞ የራሱን የእግዚአብሔር ስም የሆነውን የራሱን ሥም ነው። ለዚህም ነው ከሥም ሁሉ በላይ የሆነው ስም የእግዚአብሔር ሥም የሆነውን " ኢየሱስ" የሚለውን ሥም ይዞ በሰዎች መካከል ክርስቶስ የተመላለሰው። ልብ ማድረግ የሚገባን አብ ማለት ስም አይደለም ነገር ግን አባትነትን ያሳያል። ወልድ ማለት ሥም አይደለም መወለዱን ወይም ልጅነቱን ያሳያል። መንፈስ ቅዱስ ማለት ስም አይደለም ነገር ግን የተቀደሰ መንፈስ መሆኑ ያሳያል። ስለዚህ የአብ ስም የወልድ ስም የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን ነው? እግዚአብሔርም አብ ለልጁ ከስም ሁሉ በላይ ስም ሲሰጠው የራሱን ስም ነው የሰጠው። በዚህም ክርስቶስ እግዚአብሔር ወልድ ይዞት የመጣው ስም የአባቱ ስም "ኢየሱስ የሚለውን ስም ነው። በዚህም እርሱ ራሱ በትምህርቱ ውስጥ " 43 እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ አልተቀበላችሁኝምም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ እርሱን ትቀበሉታላችሁ።" (ዩሐ. ም5) ብሎ የአባቱን ስም "ኢየሱስ" የሚለውን ሥም ይዞ እንደመጣም ተናግሯል። እንዲሁም አሁንም እንዲሁ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አሁን በእኛ መካከል ሲመላለስ ይዞት የመጣው ሥም የእግዚአብሔርን ስም መሆኑንም አሁንም ወንጌሉ ይመሰክራል። በዚህም መሠረት "26 አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።" (ዩሐ. ም14) ብሎ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለወግኖቹ ነግሯቸዋል። ስለዚህ ከዚህ የምንረዳው እኛ ሁሉ ልንድንበት የተሰጠን ስም " ኢየሱስ" የሚለው የእግዚአብሔር ሥም ብቻ ነው። እግዚአብሔርም አስቀድሞ በነቢዩ ኢስያስ ላይ አድሮ እንደገለጸው ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተናገረው፡
  " 1፤ ደሴቶች ሆይ፥ ስሙኝ፥ እናንተም በሩቅ ያላችሁ አሕዛብ፥ አድምጡ፤ እግዚአብሔር ከማኅፀን ጠርቶኛል፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን አንሥቶአል፤" (ኢሳ. ም49) ብሎ ገና ከእናቱ ከድንግል ማርያም ማህፀን እንዳለ " ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።" ብሎ ነግሯታል። ስለዚህ ኢየሱስ የሚለው ስም የእግዚአብሔር ሥም ነው። ለዚህም ነው ቅዱስ ዳዊት " 26 በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤" (መዝ. ም118) ብሎ እግዚአብሔር አስቀድሞ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እንዳለ የተናገረው። በዚህም መሠረት እርሱም በእግዚአብሔር ስም በሆነው " ኢየሱስ" እንደመጣም በዚህም እርሱም ለአባቱ ያዘዘውን ሥራ ፈጽሞ በጨረሰ ጊዜ በጸሎት አድርጎ እንደተናገረው "5 አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።6 ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው፤7 ቃልህንም ጠብቀዋል። የሰጠኸኝ ሁሉ ከአንተ እንደ ሆነ አሁን ያውቃሉ፤8 የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።" (ዩሐ. ም17) ብሎ ለደቀ መዛሙርቶቹ መዳን የሚገኝበትን የአባቱ ስም "ኢየሱስ " የአባቱ ሥም መሆኑን ገልጾላቸዋል። ለዚህም ነው እኔ በአባቴ ሰም መጥቻለሁ አልተቀበላችሁኝም ነገር ግን ሌላው በራሱ ሥም ቢመጣ ትቀበሉታላችሁ ብሎ ወግኖቹን የወቀሳቸው። ስለዚህ ይህም ሥም ደግሞ ባለንበት ዘመን ብዙዎች ይዘውት የሚነሱትና ብዙዎችን የሚሳስቱበትም ሥም ነው። ስለዚህ እኛ የምናመልከውን አምላክ በእውነት እናወቀዋለን??? አንዳንዶች ኢየሱስ ዳግመኛ ሲመጣ ወደ ሰማይ ቤት ይዞን ይሄዳል በዚያም ለዘላለም እንኖራለን ብለው የሚያምኑም አሉ። ሌሎቹ ደግሞ በተቃራኒ ዳግምኛ ሲመጣ ከእርሱ ጋር አብረን በምድር ላይ እንነግሳለን ብለው የሚያስተምሩ አሉ። ስለዚህ እንዲሁም የተለያየ ነግሮችን በማንሳት ኢየሱስ የሚለውን ስም በመጥራት በከንቱ የሚመላለሱ በዓለም ውስጥ በብዛት አሉ። ስለዚህ እውነተኛው " ኢየሱስ" ማን ነው???።
  አባቶቻችን ቅዱስ ሐዋርያት በመጽሀፉ እንደሚመሰክሩት ። " 5 ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?6 በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም።7 መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።8 የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።9 የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።10 በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።11 እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።" (1ኛ ዩሐ. ም5)። ብለው ስለ እውነተኛው ኢየሱስ ክርስቶስ መስክረዋል። በዚህም ይህ የሕያው እግዚአብሔርም ልጅ ኢየሱ ክርስቶስም ፡
  "32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።" (ሉቃ. ም1) ይላል። በዚህም ይህ በዳዊት ዙፋን ወደፊት ዳግመኛ ሲመጣ የሚቀመጠው እውነተኛ ኢየሱስ ነው። ይህንንም የበለጠ እንድረዳ ነቢዩ ኤርምያስም የእግዚአብሔርን ቃል እንደመዘገበው ማን እውነተኛ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ እንድንረዳ፡"5 እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።6 በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም። እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው።" (ኤር. ም23) ብሎ እውነተኛው የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ መጥቶ በአባቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ይቀመጣል።
  በዚህም ወቅት "5 ፀሐይ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ፥ በጨረቃም ፊት ለፊት ለልጅ ልጅ ይኖራል።6 እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ፥ በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይወርዳል።7 በዘመኑም ጽድቅ ያብባል፥ ጨረቃም እስኪያልፍ ድረስ ሰላም ብዙ ነው።8 ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፥ ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይገዛል።9 በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።" (መዝ. ም72) ብሎ ያስተምረናል። በዚህም ጊዜ ምን እንደሚሆን ነቢዩ ዘካርያስ የእግዚአብሔርን ቃል እንደመዘገበው፡"9፤ እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።" (ዘካ. ም9) ብሎ ማን እውነተኛ ኢየሱስ ማን እንደሆነ ያስተምረናል።
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
 8. በመቀጠልም
  ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተበሰራት መሠረት እግዚአብሔር ወደፊት እውነተኛው አሸናፌው ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ በዚህም ወቅት ነቢዩ ዳንኤልም የእግዚአብሔርን ቃል እንደመዘገበው፡ እግዚአብሔር አባቱ አብ ለልጁ ለኢየሱስ ክርስቶስ፡ "14፤ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።" (ዳን. ም7)። ይላል በዚህም ወቅት እኛም እውነተኛውን ኢየሱስ ክርስቶስን በቃሉ አውቀን እርሱም የሕያው እግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምነን እስከ መጨረሻው ጸንተን ከኖርን እርሱም በአባቱ ዙፋን እንደተቀመጠ ለእኛም ለወገኖቹ ፡
  "26-27 ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፥ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤" (ዩሐ. ራዕይ ም2) ብሎ ተስፋ ሰጥቶናል።
  ነገር ግን ይህ የተቀደስ ሥም የሰው ልጆች ሕይወት የሚያገኙበት በዘመናችን ለንግድ የዋለ ለጥቅምና ለገንዘብ የዋለ በመሆኑ ያሳዝናል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል አይሸጥም አይለወጥም። ነገር ግን ሰዎች እያሳበቡ በዘመናችን ትርፍ የሚገኙበት የንግድ ዕቃ ሆኗል። የሕይወት እንጀራ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ሳያውቁ ስሙን በመጥራት የደረቁ አጥንቶች ይዘው የሚመላለሱ ብዙዎች ናቸው። ልብ እናድርግ! እግዚአብሔር ቃሉን መንፈሱን የእግዚአብሔርን ጸጋ የሰጠን እኛ ከሞት ወደ ሕይወት እንድንሻገር እንጂ ሽጠን ትርፍ እንድናገኝ አይደለም። ሁሉም ነገር በነጻ ለአዳም ልጆች የተሰጠን የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ይህንንም ጸጋ በእምነት ሆነን እንድንገኘው በብዛት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል አፈሶልናል። ይህም ጸጋ በደሙ ማስተሰርያ አድርጎ ያቆመው ሁላችንም ልንመገበው የሚገባን የሕይወት ቃል ነው። አሁንም የምናደርገውን ባለማወቃችን የተነሳ ቃሉን ለገንዘብ ለውጠነዋል። ይህንን ማቆም አለብን። ይህንን እግዚአብሔር የሰጠንን ጸጋ ሁሉ በነጻ በምንችለው አቅም ለሰው ልጆች በማዳረስ ማገልገል ይገባናል። አለበለዚያም አሁኑኑ የሥጋ ደመወዝ ካገኘን በኋላ የሚሰጠንን ደመወዝ መንግስቱን አናገኝም ። በዚህም ሁላችንም በእውቀት በጥበብና በማስተዋል ሁነን እግዚአብሔርን ማምለክ ይገባናል።
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር!

  ReplyDelete
 9. የቤተክርስቲያኗን የመዝሙር አገልግሎት ቤተክርስቲያኗ ባላት እምነትና ስርዓት የሚፈፀም መሆኑ የታወቀ ቢሆንም ጠላት ይህን አገልግሎቷን ለማስጣልና የጩኸትና የረጌ ራጋ ዳንስን ለማስገባት ሲያንቋሽሹና ሲያጣጥሉ እንዲሁም ሲዘብቱ ይታያሉ። ዝማሬዎች በሚል የቀረበውና ሶስት ዘማሪዎችንም ከነ ስማቸው በመጥቀስ እንክርዳድን ለመርጨት ቤተክርስቲያንን ለመክሰስ የተለጠፈው ጽሑፍ ይህ ብሎግና ፀሐፊዎቹ ከቤተክርስቲያን ያልሆኑ የሐሰትን ወንጌል የሚበትኑ የስተት አራማጆችና አስተማሪዎች መሆናቸው የተረጋገጠ ነው። የሚገርመው "አንድ ጳጳስ ኢየሱስ አትበሉ ሲሉ"ተሰምተዋል የሚል ሌላ ውሸትና ስም ማጥፍት ተጠቅመዋል። በእርግጥ የአምላክን ስም በማይገባና እንዲያው ወረቀት ኮሽ ባለ ቁጥር መጥራትና በኢየሱስ ስም ማለት ማመስገን ሳይሆን ማፌዝ፤ ክብር መስጠት ሳይሆን ማቃለል ነውና በማይገባ ሁኔታ የአምላክን ስም አትጥሩ ማለትና መምከር ተገቢ ነው። ከዛ ውጭ ጳጳስ እንዲህ አለና እንዲህ አደረገ አሉባልታና ክሳችሁ ከጠላት ከሰይጣንና መልእክተኞቹ የሚጠበቅ ዘመቻ ነውና አዲስ ነገር አይደለም። እናንተማ አልሆነላችሁም እንጂ ኑሮ እንደኔ ያጎሰቆለችውን ደልላችሁ አቡነ ያሬድ ነኝ እንዲል አድርጋችሁ ጳጳስ ሙሉወንጌል አዳራሽ ገባ መናፍቅ ሆነ ብላችሁ ስታስደልቁ ነበር አይደል። ነገር ግን ነገሩም የጠላት ስራ፤ የደለላችሁት የኔቢጤውም ምጽዋትን ፍለጋ በቤተክርስቲያን ደጄ ሆነው ተገኙ እንጂ። ወደ መዝሙሮቹ ልመለስና ከዘማሪ ገብረ ዮሐንስ ልጄምር። ዘማሪውም ሆነ የመዝሙሩ ገጣሚ ለመመስከርና ለማስተላለፍ የፈለጉት በአንዲቷ በክርስቶስ ቤተክርስቲያን እምነትና ስርዓት ለመቆም ያልፈለጉትን ነገር ግን እምነትና ስርዓቷን ለሚተቹትና ለሚያጣጥሉት ነው። ይኸውም አብ ያልተከለውና ያልጠራው በክርስቶስ ቤተክርስቲያን እምነትና ስርዓት ፀንቶ እንደማይቆም፤ የቤተክርስቲያን እምነቷና ስርዓቷ ክርስቶስ መሆኑን አውቆ ያልተቀበለ በዚህ አለም የውሸት ውዠንብር ተሸናፊ እንደሚሆን ነው። ሌላው ለክስለመጠቀም የሞከራችሁበት የወንድማችን መዝሙር "ኢየሱስልበል ኢየሱስ…" የሚለውን ነው። እናንተ የአምላካችን የኢየሱስ ስም በቤተክርስቲያን የሌለ ለማስመሰልና ሊቀጳጳስም ኢየሱስ የሚለውን ስም እንዳይነሳ ከለከሉ ለማለት ነው የሞክራችሁት። ነገር ግን ወንድማችን ገብረ ዮሐንስ ለማጋለጥና ለመመስከር የተነሳውም ይህን ሐሰተኛ ክሳችሁንና የአሉባልታ ውንጀላችሁን ነው። ገብረ ዮሐንስም ገጣሚውም ኢየሱስ በቤተክርስቲያን እንዳለና በክብር እንደሚጠራ፣ ቤተክርስቲያን የአምላካችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ብቻ እንደሆነችና በሱ እንደተመሰረተች፣ የክርስቶስ ኢየሱስ ስም ቤተክርስቲያን በኪዳን በሰዓታት በቅዳሴ እንደሚጠራ እንደሚመሰገን እንደሚመለክና በዚህም ነቀፋ ቢመጣ እስከሞት እንደምትፀና እንደሚፀና የመሰከረበት ነው። እናንተ ያው ከክስ ሌላ ሌላ ተግባር የላችሁምና የዘማሪውን ጥቂት ስንኞችን ነቅሳችሁ ክሳችሁን ለማስወንጨፍ ብትሞክሩም ስንኞቹ መልሰው እናንተ ማን ናችሁ የመዝሙሩ መልእክት ይነው አሏቹህ። ሌላኛዋ ዘማሪት ጽጌረዳ ናት የጠቀሳችኋት። ዘማሪዋ በማወቅም ይሁን የገጣሚውን ማንነት ካለመረዳት የመጣ የዋህነት የተጠቀሱትን ስንኞች ዘምራለች። ነገር ግን ስንኙ ፍፁም ስድብና ክህደት የሞላበት የእግዚአብሔርን ቃል መልእክት ያጣመመና የአምላክን ክብር ያዋረደ ነው። ከዛም ባሻገር ግለሰቦች በሌላቸው መንፈሳዊ ህይወት እንዲታበዩ የሚያደርግና ቅዱሳን በእግዚአብሔር ዘንድ ያላቸውን ክብርና ፀጋ እንዲሁም የጽድቅ አገልግሎትን ለመካድና ለማጥላላት የተደረሰ የስጋ አስተሳሰብ የታጨቀበት በምንፍቅና ውስጥ ያለ የቤተክርስቲያን ጠላት ድርሰት ነው። ዘማሪዋም ትናን ተታላ ወይም በየዋህነት መስሏት ለተንኮለኞች መሳሪያ ብትሆንም ነገ ግን ዘወር በል ሰይጣን አምላኬን አታቃልብኝ እውነትን አታጣምብኝ ሚስጢር አታበላሽብኝ እነደምትለው ተስፋ አለኝ። ሌላ የተጠቀሰችው ዘማሪ ከተባለች ዘማሪት ዘርፌ ናት። እህታችን የነበረችበትን የዘፋኝነት ህይወት ትታ በመንፈሳዊው የህይወት ጎዳና ለመጏዝ መምረጧ ቢያስደስትም አሁን እያደረገቸው ያለው በትቢት መወጠርና እራሷን የማሞገስ መዝሙር ተብዬ ግን አልሸሹም ዘወር አሉ አይነት ነው። በመጀመሪያው መዝሙሯ የነበሩትን ከዜማ ቅላፄ ጀምሮ የግጥሞች ችግር አይ ይች እህታችን የመጣችው ሥራ ብላ ከያዘችው የዘፋኝነት ህይወት ነውና ነገ ትለወጣለች ብየ እከራከር ነበር። ግን ከአንዱ ጥፋት ወደባሰው ጥፋት በዘዋሪዎቹ የግጥም ገጣሚዎች እየተመራች ከመሸጋገር ውጭ መንፈሳዊነትን ልታገኘው አልቻለችም። ዘመርኩ ብላ ስለራሷ ስትናገርና ጠላት የምትላቸውን ደግሞ ስትሳደብና ስትንቅ ከማየት ውጭ የእግዚአብሔርን አምላክነት፣ ክብርና እውነት ስታገለግል አላየኋትም። እሷ ሳታውቅና ለገቢ ማግኛ ስለሆናት ይሆናል ይህን የውድቀት መንገድ እየሄደችበት ያለው። ግጥሙን የሚሰጧትና በመሳሪያነት እየተጠቀሙባት ያሉት ግን ሆነ ብለው በአላማ እንክርዳድ እየዘሩና አለማዊነትን እያራመዱ ናቸው። የሚገጠሙት ግጥሞች ቤት መምታታቸውን እንጂ ስለመልእክቱ የማይጨነቁ፣ አንዱ መሥመር ከሌላው የሚጋጭ ውሃ እንቦጭ እንትና እንዘጭ አይነት ናቸው። ለምሳሌ "ባናምነውም ታምኖ ይኖራል" ይልና "ራሱን መች ሊክድ ይችላል" የሚል ቤት እንዲመታ ተብሎ የተገጠመ አለ ግን በመለኮታዊ ሚስጢር እንዲህ አይነት መልእክት ምን ይሆን የሚባለው። ራሱን መች ሊክድ ይችላል ማለትስ ምን ማለት ነው? በአጠቃላይ በሁለቱ እህቶቻችን በኩል ጠላት በሰራዊቶቹ አማካኝነት ሞትን እያራመደና በክህደትላይ ክህደትን እየጨመሩ ለስጋ ደስታና ስለራስ ማውራት ለዛውም ባልሆኑትና ባላለፉበት እንዲዘባርቁ እየተደረገ ነው። እህታችን ዘርፌን በአካል ያየኋትና እንዴት በክፉዎች ተጠልፋ እንደወደቀች ተመልክቻለሁ። ይኸውም ለጽዮን ማርያም በአለ ንግስ ላይ እንድታገለግል ተጠርታ ታቦት ሲዞርም አልዞርም በዓሉ በተመለከተም አልዘምርም ብላ እንዴት አይነት ስለራስ የሚናገር መዝሙር ተብዬ ስትዘምር እንደነበር አስታውሳለሁኝ። እናም እህቴ እባክሽ በከንቱ አትታበይ፣ በክፋዎች ጎዳና አትሒጂ አትተባበሪያቸው፣ ምድራዊ ሐብቱም ክብሩም ያልፋሉ። በመጨረሻ የእግዚአብሔር የሆነ መንፈሳዊ መዝሙር ጊዜ አይገድበውምና ዘመን ተሻጋሪ እያላችሁ ተራ የአለም ቋንቋን አትለፍፉ።

  ReplyDelete
 10. ayii woregna hula dedeboch nachu eshi

  ReplyDelete
 11. "13፤ ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።"
  (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:13፤)

  ReplyDelete