Friday, March 20, 2015

በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት፤ የቀሲስ በላይ መሻርና የሊቀ ማእምራን የማነ መሾም በማቅ መንደር ሽብር ፈጠረበሙስና የተዘፈቀውና እጅግ የተጨማለቀው የቀሲስ በላይ አስተዳደር ለሙሰኞች ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጥሮ በርካታ ድኾች አገልጋዮችን፣ ጉቦ እየበላ በአየር ላይ በማንሳፈፍ፣ ሕገ ወጥ ዝውውር በማድረግ ከደረጃ በማውረድ ከሥራ በማገድና በመሳሰለው የዝርፊያ ስልቶቹ ሲያስጨንቅና ሲያውክ ለበርካታ ወራት ከቆየ በኋላ ከሥልጣን እንዲነሣ መደረጉን የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ ሐራ ዘገበ፡፡ ሐራ ሙሰኛው ሥራ አስኪያጅ ሲሾሙ ተበሳጭቶ “የፓርላማ ተመራጩ ሊቀ አእላፍ በላይ መኰንን የአዲስ አበባ /ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ” በማለት ዘግቦ የነበረ ሲሆን፣ የመሻራቸው ዜና በአባ ማቴዎስ በኩል ሲደርሰው ግን በሐዘን ስሜት “የፓርላማ ተመራጭ” የሚለውንና ሲሾሙ የቀጸለላቸውን “ማዕርግ” አንሥቶላቸው “የአ/አበባ /ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን ከሓላፊነታቸው ተነሡ፤” ሲል ነው የዘገበው፡፡ ይህም በግልጽ የሚያሳየው ቀሲስ በላይ ማቅ በመጀመሪያ ያሳያቸውን ጥላቻ ለማስወገድ ማቅ እንደሚፈልገው ሆነው የሥልጣን ዘመናቸውን መጨረሻቸውን ነው፡፡ ለዚያ ነው ሊቃውንቱና ካህናቱ የፍትሕ ያለህ እያሉ ጩኸት ሲያሰሙ የማቅ ብሎግ ሐራ አንድም ቀን ምንም ትንፍሽ ያላለው፡፡
በቀሰስ በላይ የአስተዳደር ዘመን ለግል ጥቅሙና ለሥልጣኑ እንጂ ለቤተክርስቲያንና ለአገልጋዮቿ ደኅንነት ግድ እንደሌለው ያሳየው ማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት በሙስና በጉቦ በዘረኛነት ሕገ ወጥ አሰራሮችና የአስተዳደር ብልሹነቶች ማለቃችን ነው እያሉ ድምፃቸውን ሲያሰሙ “አይሰማም” በሚል ዝምታን መርጦ መቆየቱ የማኅበሩን ትክክለኛ ማንነት ገሃድ ያወጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ስለአንዳንድ ደብሮች ሙስና ሲዘግብም የዘገባው ዋና ነጥብ ሙስናው ሳይሆን ለማቅ ያልተመቸው የዚያ ደብር አለቃ ወይም ጸሐፊ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል፡፡ 

በተደረገው  ሹም ሽር የተበሳጨው ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ሳይሆን ከቤተክህነቱ እየጎረሱ ወደማኅበረ ቅዱሳን በመዋጥ የሚታወቁት የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ አባ ማቴዎስና ጸሐፊው አባ ሉቃስ ናቸው፡፡ እነዚህ የማቅ ተላላኪ ጳጳሳት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሹማምንት በሀገረ ስብከቱ ካህናት ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና በደል ፈጽሞ ተሰምቷቸው አያውቅም፡፡ ከዚያ ይልቅ ለማቅ የተመቹትና በሙስና የተዘፈቁት ሥራ አስኪያጅ መሻራቸው ነው ያንገበገባቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ የማቅ ብሎግ ሐራ ሙሰኛ ስለነበሩት  ምክትል ሥራ አስኪያጅ ባለድጓው መምህር ኃ/ማርያም ምንም አላለም፡፡ ዘረኛ አመለካከቱ ይህን እንዲል አይፈቅድለትምና፡፡
ሐራ ዘማኅበረ ቅዱሳን የቀሲስ በላይን መውረድ ብቻ ሳይሆን በዘረኛ አመለካከት ስለተለከፈ የአዲሶቹን ተሿሚዎች ስም በማጠልሸት ጭምር ነው ዘገባውን ያቀረበው፡፡ ይህም የሚያሳየው የሥልጣን ዝውውሩ ለማቅ ፈጽሞ የማይመች ሁኔታን የፈጠረ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ለማቅ ሐዘን ቢሆንም በቀሲስ በላይ ሙሰኛ አስተዳደር ለተንገላቱ ብዙዎች ግን ትልቅ የምሥራች ነው፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ የሊቃውንቱንና የካህናቱን ሮሮና እንግልት ሰምተው ለውጥ ማድረጋቸው በራሱ ትልቅ እርምጃ ነው፡፡ ሊቀ ማእምራን የማነ እና መጋቤ ብሉይ አእመረ ዕውቀትም ሆነ ችሎታ ያላቸው መሆናቸው ብቻ ሳይሆን እንደ ቀሲስ በላይ ቤተክርስቲያንን እንደ ማቅ ላለ ጠላት አሳልፈው የማይሰጡ ናቸው፡፡ ቀሲስ በላይ ግን ክርስቶስን ክጃለሁ ማኅበሩን አምኛለሁ በክፉ ሥራውም ተጠቅሜያለሁ በማለት ሙስናንና ነውርን ለመሥራት ያለከሳሽ በማንአለብኝነት ለመኖር ሲሉ በማኅበሩ አሠራርና ቀኖና መጠመቃቸውን አስመስክረዋል፡፡ ለማቅ በገቡት አዲስ ቃል ኪዳን የማቅ አጀንዳ አስፈጻሚ ሆኖው በብዙ ሊቃውንት ላይ ግፍና በደልን ሙስናና ዘረኛነትን ጣራ ላይ በማድረስ ታሪካዊ ስሕተት ፈጽመዋል፡፡ማቅም በሰሩት ግፍና ዐመፅ ተባባሪ ነውና ያን እንደውለታ ቆጥሮላቸው ሲሾሙ ወያኔ መናፍቅ እንዳላላቸው ከዚያ በኋላ ግን ያ በደላቸው ስለተሰረየላቸውና “የማቅ ጽድቅ” ስለተቆጠረላቸው አንድም ቀን በማቅ በኩል በሙስናና በጉቦ አልተከሰሱም፡፡ ሲወርዱም በጳጳሶቹ አባ ማቴዎስና ሉቃስ በኩል እየተሟገተ መሆኑን በተዘዋዋሪ በሐራ በኩል ግልጽ አድርጓል፡፡
አዲስ የተሾሙት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዕውቀቱ ያላቸው መሆናቸው፣ የማቅን ስውር ሴራ በአደባባይ ያጋለጡ መሆናቸው፣ ቤተክርስቲያንን እንደማቅ ላሉ እኩያን አሳልፈው የማይሰጡ መሆናቸው በተግባር የታየ ነው፡፡ ማቅም የነካውንና እውነቱን የገለጠበትን መርዞ መያዝ ሥራው ነውና ከወዲሁ ዘመቻ ከፍቶባቸዋል፡፡
ሊቀ ማእምራን የማነ ከደብር ወደዚህ ሥልጣነ የመጡ በመሆናቸው በድኾች ሠራተኞች ላይ ግፍና በደል ላይፈጽሙ ይችላሉ የሚል ግምት አለ፤ ሆኖም ሌሎች የግል ሥራዎችንም ስለሚሠሩ የሥራአስኪያጅነቱ ሥራ ሊበደል ይችላልና ይህን አስበው ሊገቡበት ይገባል፡፡ ከደብር የመጡ እንደመሆናቸው የሙዳየ ምጽዋትን ገንዘብ ከዝርፊያ ለመጠበቅ ከንግግር ባለፈ ቁርጠኝነታቸውን ማሳየት አለማሳየታቸው የሚፈተንበት ሹመት እንደሚሆን የቅርብ ጓደኞቻቸው ይመስክራሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ጠንካራ በመሆን የተሻለ አሰራርን ሊዘረጉ ኦደሚችሉ ማሳየት ይኖርባቸዋል። እውቀት የሚፈተነው በተግባራዊ አሰራር ነውና ሥራውን በተሻለ ሁኔታ መስራታቸውን ሊያሳዩ ይገባል።
በመጨረሻም ለማለት የምንፈልገው ቀሲስ በላይ ከሥልጣን የወረዱበት ምክንያት ሊገለጽ ይገባል የሚል እምነት አለን፡፡ ከሥልጣን የወረዱት በሙስና ቅሌት መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ነገር ግን ምንም ተጠያቂነት ሳይኖርባቸው ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት ሥልጣን አውርዶ ወደሌላው የቤተክህነት ክፍል ማዛወር ማለት ለቀጣዩ ሥራ አስኪያጅ የሚሰጠው መልካም ትምህርት የለም፡፡ ቀሲስ በላይ ምንም ካልተደረጉ ሊቀ ማእምራን የማነ ምን ሊማሩ ይችላሉ? ስለዚህ ቀሲስ በላይ በሕግ ሊጠየቁ ይገባል፡፡ ቀሲስ በላይና ምክትላቸው ብቻም ሳይሆኑ በሙስናው መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉት ዳዊት፣ ማሙዬና ታዴዎስ መነሣትና በሕግ መጠየቅም አለባቸው፡፡ በእውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች መተካት አለባቸው፡፡ አሊያ በአሮጌው አቁማዳ አዲሱን ወይን እንደማኖር ነው የሚቆጠረው፡፡ አዲሱ ሥራ አስኪያጅና ምክትላቸው ከሁሉ አስቀድሞ በሀገረ ስብከቱ አሠራር ላይ መሠረታዊ ለውጥ ሊያመጣና መልካም አስተዳደርን ሊያሰፍን፣ ሙስናንና ዘረኛነትን ሊያስወግድ የሚችል ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበትን አሠራር መዘርጋት አለባቸው እንላለን፡፡        

10 comments:

 1. ለጌዎኖችና የአበዱት ተናካሽ ውሾች ለምን ይቦርቃሉ?
  ክርስቶስ ሲሰቀል፣ እውነት ሲፈተን፣ ቤተክርስቲያን ስትታወክ፣ በእውነትና በቅንነት የሚያገለግሉ ካለ ወንጀላቸው ሲከሰሱ ካለ ስማቸው ስም ሲሰጣቸው፣ በአጠቃላይ የጽድቅ አገለግሎትና የህይወት መንገድ በሾህ ስትከበብ ለመን ለጊዎኖችና ተናካሽ እብድ ውሾች በደስታ ይፈነጥዙ ይደልቃሉ?
  1ኛ፦ ለእርኩሰት ሐጢያታቸው፤ ለጥርጥር እንክርዳዳቸው ፤ ለምንፍቅና ክህደታቸው፤ ለዳንኪራ አለማዊ ዳንኪራቸው መተላለፊያ ቀዳዳና መፈፀሚያ ያገኙ ስለሚመስላቸው።
  2ኛ፦ ያልፀና ለክፍውና ለአለማዊነት የተሸነፈ ልብ ልናገኝ ነው በማለት።
  3ኛ፦ የቤበክርስቲያኗን ትምህርት፣ ስርዓትና የምትመራበትን ህግጋቶቿን የማያከብሩና የማያስከብሩ አገልጋይ ተብዮዎችና ተገልጋይ ተብዮዎች እንዲሁም ቅዱስነትዎ ተብለው የቅዱስነትን ተግባር የማይተገብሩና የማይተገብሩ እንዲያውም አባት ተብለው ለመንጋውና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ የተባለውን ትእዛዛዊ ማሳሰቢያ የዘነጉ አንዳንድ አካለትን አገኘን የሺ የህም ለኛ የጥፋት ኤንቅስቃሴ ጥሩና የምንፈልገው ነው በማለት።
  4ኛ፦ ቤተክርስቲያኗ ከልጆቿ ከአስራት፣ ከምጽዋትና ለእምነታቸው ቀናኢ ከሆኑት የምታገኘውን ገንዘብ ለመዝረፍ የተመቻቸ ነው በማለት።
  እንዲሁም ለመዳን ሳይሆን መመጥፋት፤ ለመስራት ሳይሆን ለማፍረስ እንደሁም ለመቆም ሳይሆን ለመውደቅ የተከፈተ ልብ አግኝተናልና ገብተን ተሰግስገን ካለከልካይ የፈለግነውን ሰይጣናዊ ተልኮ የምንፈፅምበት አገኘን በማለት ነው። ሆኖም ምናልባት ከነዚህ የጥፋት ሰራዊት መካከል የምትድን ነፍ ስ ካለች ማወቅ ያለባቸው የቤተክርስቲያን ፈተናወቿ ሁሉ የምጻት ቀን የመቃረቡ ምልክቶች መሆናቸውን ማስተዋልና ከክፉ ምኞት መሻታቸው ለመለየት ቀና ብለው ቢመለከቱ የተሻለ ይሆንላቸዋል። እናንት መናፍቃን አስመሳዮች በራሳችሁ የማትተማመኑ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ጠላቶች ፣ ከጽድቅ ይልቅ ሐጢያት ፣ ከእውነት ይልቅ ሐሰት ከበጎነት ይልቅ ክፋት ከእምነት ይልቅ ክህደት ከሰላም ይልቅ ብጥብጥ
  የምታራምዱ መልካሙን የምታቆሽሹ ጥሩውን የምታፀይፉበስም የተደገፋችሁ አባሰላማ ነን ባዬችና ከጥላቻ ከክስ ስም ከማጥፋት ከስድብ ውጭ ሌላ በልባችሁ ድሪቶ
  አሉባልታ ደርታችሁ ፀሐፊ ነንም ብላችሁ በዚህ የመናፍቃን ብሎግ የምትለጣጥፋ በከንቱ ከመድከም ውጭ ምንም አታተርፉምና እንተና ተመረጠ እንትና ተሻረ ብትሉ የትኛውም የተመረጠ ሂድ መናፍቅ ከማለት ውጭ የትኛውም አይቀበላችሁም።

  ReplyDelete
 2. እረ አልበዛም እንዴ? ለበላይ ለአንድ ሙሰኛ የኽል ጩኸት ማህበረ ቅዱሳኖች ትዝብት ውስጥ አልወደቃቹ ምን ማለት ፈልጋችሁ ነው?

  ReplyDelete
 3. ሠላም ይሁን

  ReplyDelete
 4. አረ ተዉ ማቆች ሙሥና አትደግፉ

  ReplyDelete
 5. Menafk malet min malet new????????? Ene endemeselegne..kirstosn yemisebk , eyesus eysus yimel,...new meselegne menafik.tiret yale orthodoxawi eyesus eyesus ayelem.yihinen sim abzito yetera hulu menafik, tehaddso new.wey eyesus!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 6. Enes ende mk yeleyelet menafik alayhum::mechem amlak cher hono enjji zime bilo yemitagesachu.memchwom selederese fiyelochu bemikomubet endatkomu hahunu simun mekawemachun akumu.wede esatem wede zelalem histone yemiyasgaban ersu bicha new.lemtafrubet yafrbachwal.

  ReplyDelete
 7. Mak yene abune Mathews dibk wetader ene Belay yemesaselut Yeken leboch yemidegf yeleboch tiki mehonu bedigami asmeseker Mak lebetekirsitiyan yalkom yekontroband negadewoch tiki new MAK TETEYEK BELAY GUBEGNA NEW AYDELEM? YELEBOCH MAHBEREEK

  ReplyDelete
 8. ይገርማል!! ስለ አንድ ወጣት ሰባኪ ልጅ በመንገድ እየተጓዝኩ ሳዝን ነበር። በጣም አዝኛለሁ። በእንዲህ ሁኔታ ላይ እያለሁ እንዳጋጣሚ ብሎጉን ከፍቼ ሳነብ ይህን ተመለከትኩ። በተፈፀመው ሁሉ ተስፋ በመቁረጥ ተዝለፍልፌ እያለ ይህን በማዬቴ ትንሽ ተስፋ በማድረግ ትንፋሼን ለመሰብሰብ ሞከርኩ። ምን አልባት ይስተካከል ይሆን? ብዬ። በሙስና ምክንያት ከስራ በመፈናቀል ቤተሰባቸውን ማስተዳደር ያልቻሉ፣ በስውር ደባ ህይወታቸውን ያጡ(ታመነም አልታመነም) በሀሰት የታሰሩ(የተወነጀሉ) አረ ስንቱ ብቻ መድሀኒአለም ይመልከተው። ስሜቴን መግለጽ አልችልም።

  ReplyDelete
 9. እነዚህ ሰዎች እስከ መቼ ነው ቤተ ክርስቲያኒቱንና አገሪቱን እየበጠበጡ የሚኖሩት? ይገርማል

  ReplyDelete