Tuesday, March 24, 2015

የአባ ቀለምንጦስ የአካሄድ ስህተትና የማቅ መሸበር ምክንያቱ

Read in PDF


ያበራል እውነቱ ከቤተክህነት
የቀሲስ በላይ መኮንን ከሥልጣን መነሳትና የእነ ሊቀ አእምራን የማነ ዘመንፈስ እንዲተኩ መመረጥ አስመልክቶ የሁኔታዎች ሂደትና አፈጻጸም እንደሚከተለው ተዳሷል። ውኃ ከጥሩ ነገር ከሥሩ. እንዲሉ። የቀሲስ በላይ ዓይን ያወጣ ሙስና የፈጠረው ጩኸት ያስተጋባው አባ ቀሌምንጦስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከመሾማቸው በፊት ነበረ። ከሹመታቸው በኋላ የቀሲስን ዓይን ያወጣ ሙስና በተመለከተ ከቅዱስ ፓትርያሪኩ ጋር ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ አባ ቀሌምንጦስ ትንሽ ጊዜ ይሰጠኝ በማለታቸው ለጊዜው ባለበት ቆመ።
ይሁን እንጂ ከተወሰኑ ወራት በኋላ ራሳቸው አባ ቀሌምንጦስ ወደ ቅዱስነታቸው መጥተው ይህ ሰው  (ቀሲስ በላይ)መውረድ አለበት፤ ጩኸት በዛ። በቅዱስነትዎ በኩል  የሚጠቁሙት ሰው አለ ወይ? ብለው ይጠይቃሉ። ቅዱስነታቸው ለጊዜው ላስብበት ብለው ይለያያሉ። በቀጣዩ ጊዜ አባ ቀሌምንጦስ የራሳቸው ሦስት ሰዎችን መርጠው ያቀርባሉ። ሦስቱም ሰዎች የማቅ አባላት ነበሩ። እነዚህ ሦስት ሰዎች ታሪካቸው ሲጠና ሁለቱ ክህነት የሌላቸው፤ ከሦስቱ አንዱ ደግሞ ክህነት ያለውና በዘመናዊ በኩል ግን አራተኛ ክፍል እንኳን ያልደረሰ መሆኑ ይረጋገጣል። በመሆኑም ሦስቱም ለዋና እና ለምክትል ሥራ አስኪያጅነት የሚያበቃ መሥፈርት ሳያሟሉ ይቀራሉ። ስለሆነም በቅዱስነታቸው በኩል በቤተ ክርስቲያንዋ መንፈሳዊ ትምህርትም
ሆነ በዘመናዊ (አካዳሚ) ትምህርት መሥፈርት ያማሉት ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስና መጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር ይቀርባሉ። ይኽንኑ ተከትሎ ባለው ህጋዊ አሠራር መሠረት የሹመት ደብዳቤያቸው በዋና ሥራ አስኪያጅ በኩል ተፈጻሚነት እንዲኖረው ቅዱስነታቸው ለዋና ሥራ አስኪያጁ መመሪያ ይሰጣሉ።

በዚህ ጊዜ ማቅ የሰጣቸው መመሪያ ስላልተሳካላቸው አባ ቀሌምንጦስ ተበሳጩ። እንዲህ ከሆነ እኔ ሥራውን እተዋለሁ በማለት ሥሜታቸውን ሳይደብቁ ተስፋ መቁረጣቸውን ገለጹ። የቅዱስ ፓትርያሪኩንም መመሪያ ላለመቀበል ከስውር ቡድናቸው ከአባ ማቴዎስና ከአባ ሉቃስ ጋር ማደም ይጀምራሉ። ማቅም ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ያለማቸው ድንግል-በክልኤ የሆኑ (የዓለማዊውም ሆነ የቤተ ክህነት ትምህርት የሌላቸው) አባላቶቹ ስላልተመረጡ በሁለት መንገድ የአሸባሪነት ወሬውን ማናፈስ ቀጠለ።
1ኛ በለመደው መንገድ እውነተኛ ታሪኮችን እያዛባ የሰዎችን ሕይወት ጥላሼት መቀባባቱን ተያያዘው። በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ ያነጣጠረው ህልሙ ስላልተፈታ የቤተ ክርስቲያንዋን ንጹሐን ልጆች አንዱን ዘራፊ ሌላውን መናፍቅ በማለት የማጥላላት ሥራውን በሐሰት ብሎጉ በሐራ አናፈሰው። እንዲህ ዓይነቱ የስም ማጥፋት ዘመቻ ጎጅነቱ ለግለሰቦች ብቻ ሳይሆን ታላቋን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ማዋረድም እንደሆነ ሁሉም ማስተዋል የሚገባው ነው። ምክንያቱም በጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያና በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ የሚገኙትንና ቤተ ክርስቲያንዋ አገልጋዮቼ የምትላቸውን ባልተጨበጠና ባልታወቀ ምክንያት መናፍቅ ወይም ዘራፊ ማለት ቤተ ክርስቲያንዋን መወንጀልና መሳደብ ነውና።
2ኛ በውስጥ ተላላኪ ጳጳሳቱ (አባ ማቴዎስና አባ ሉቃስ) በኩል የቅዱስ ፓትርያሪኩ መመሪያ ተፈጻሚነት ለማደናቀፍ የሙከራ ሥራ አድርጓል። አስገራሚው ነገር ደግሞ የአባ ማቴዎስ ቅሌት ነው። አባ ማቴዎስ ከአባ ቀሌምንጦስ፤ ከአባ ሉቃስ፤ ከማቅ አማካሪዎች ጋር ስውር አድማን ከአካሔዱ በኋላ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ያስተላለፉትን መመሪያ ወደ ቋሚ ሲኖዶስ ጉባኤ አምጥተው እንነጋገርበት ማለታቸው ነው። አካሔዱ ማቅ ቋሚ ሲኖዶስ ውስጥ በአሁኑ ዙር ያሉትና የእኔ ናቸው የሚላቸው ጳጳሳት በድምፅ ብልጫ የፓትሪያርኩን መመሪያ ውድቅ አድርገው እኔ የመረጥኩአቸውን ያጸድቁልኛል በማለት የተዘየደ አካሔድ ነበረ። ሆኖም የማያወላውል አቋም ያላቸው ቅዱስ ፓትሪያርኩ ግን ይኽ የተሰጠዎት መመሪያ ሥራ እንዲያስፈጽሙ እንጂ ወደ ቋሚ ሲኖዶስ የሚያመጡት አልነበረም። ቋሚ ሲኖዶስን አይመለከትምና። የብፁዕነትዎም መብት አይደለም። የሀገረ ስብከቱን አቤቶታ የመስማት፤ ችግሮችን የመቅረፍ ኃላፊነት አለብኝ። ይኽንን አስቀድመን ከብፁዕነትዎም ሆነ ከአባ ቀሌምንጦስ ጋር ተወያይተናል። በመሆኑም የአስተዳደርን አሠራር ተከትለን መሔድ፤ የሰዎችንም ጩኸት መስማት ግድ ይለናል በማለት መልሰዋል። የማቅ ተላላኪዎቹና ተስፋዎቹ የሆኑ ጳጳሳት ምንም ትንፍሽ ሳይሉ ጉዳዩ በቅዱስነታቸው መልስ ተዘግቶ ወደ ሌላ አጀንዳ ተገብቷል። ይኽ በእንዲህ እንዳለ በማቅ ብሎግ በሐራ የሚናፈሰው ወፍ ዘራሽ ወሬ ግን በግልባጩ ነው። መቼም እስከ ዛሬ በሐሰት ወሬ የተካነው የማቅ ብሎግ የሆነው ሐራ ከእውነት ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነት እንደሌለው ስለምናውቅ አሁን በሚያስወነጭፈው የሐሰት ወሬ ብዙም አንደነቅም።
በሌላ መልኩ የቅዱስነታቸው ቆራጥ አቋም ይበል የሚያሰኝ ነው። ገና ወደ ፕትርክናው መንበር ሲመጡ ያወጁትን ሙስናንና ብልሹ አስተዳደርን የመቃወም ዓላማቸውን እየተወጡ ነው። ብዙዎች እንደሚስማሙበት ቅዱስነታቸው አጀብ የሚፈልጉ፤ ልከበር የሚሉ አባት አይደሉም። በቅድስናቸውና በጽኑዕ አቋማቸው የታወቁ አባት ናቸው። ከምን ጊዜውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁነኛ አባት ያገኘች አሁን ገና መሆኑን ብዙዎች የሚናገሩት እውነት ነው። ለቤተ ክርስቲያን ክብር ብቻ የቆመ ፓትሪያርክ በተገኘበት በአሁኑ ሰዓት በዙሪያቸው ያሉት ሁሉ የአቋማቸውና የዓላማቸው ተጋሪ ቢሆኑ እንዴት መልካም ነበር! በመቶዎች በሚቆጠሩ ዓመታት በሙስናና በተንኮል የተዘፈቀ ቤትን ማጽዳት በጣም ከባድ ነው። ፓትሪያርክ ማትያስ ግን ጀምረውታል። በእግዚአብሔር አጋዥነትም ይፈጽሙታል ብለን እናምናለን። ማቅ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ቢሆንና ለቤተ ክርስቲያን የሚሠራ ማኅበር ቢሆን ፓትሪያርክ ማትያስ ከሰማይ የወረዱለት መና ነበሩ። ግና ምን ይሁን! ዓላማቸው አልተገናኘም። ፓትሪያርክ ማትያስ ሙስናን ሲቃወሙ የመጀመሪያው ሙሰኛ ሆኖ የተገኘው ደግሞ ማቅ በመሆኑ እንደ ሰማይና እንደ ምድር ተራራቁ። ስለዚህም ቅዱሱን አባት ያለምክንያት በየብሎጎቹ ማጠልሸት ሥራው ሆነ። የቤተ ክርስቲያን ልጅነት የማይነካካው ፓለቲከኛና ነጋዴ ማኅበር መሆኑን በግልጽ አስመሰከረ።
ይኽን ተከትሎ ብዙዎች በጉጉት የሚጠባበቁት የቀሲስ በላይ ከኃላፊነት መነሳት ዋና ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ነው። ጉዳዩ ዓለም ያወቀው፤ ፀሐይ የሞቀው ,ሙስና. መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። የተጨበጠና በቂ የሆነ መረጃ እንዳለም ለማወቅ ተችሏል። ይኽ ተለባብሶ ከታለፈ ግን የቅዱስ ፓትሪያርኩን እርምጃ ውጤታማ አያደርግም። ተተኪውም ሥራ አስኪያጅ ሊማርበት አይችልም። ይኽ መረጃ ግን ይፋ ቢሆንና የቅጣት እልባት ቢሰጠው በተመሳሳይ መንገድ በሙስና ተዘፍቀው ላሉት ሰዎች መማሪያ ይሆናል ብለን እናምናለን።

17 comments:

 1. "በቤተ ክርስቲያንዋ መንፈሳዊ ትምህርትም
  ሆነ በዘመናዊ (አካዳሚ) ትምህርት መሥፈርት ያማሉት ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስና መጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር ይቀርባሉ"
  ወዳጄ ለመኾኑ የማነ የተማረው የቤተ ክርስቲያኗ ትምህርት የትኛው ነው?

  ReplyDelete
 2. አነጋገራችሁን ፍጹም ኦርቶዶካሳዊ አድርጋችሁ ለማስመሰል የምታደርጉትን ጥረት በጣም እናደንቃለን፡፡ ግን ማንም በእናንተ ቅሰጣ የሚታለል የለም አባ ሰላማ ብሎክ የወጣለት መናፍቅ ዉሸታምና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የተመሰረተ ማኅበር ወይም ብሎግ መሆኑን ካወቅን ሰነበትን ስለዚህ አትሞኙ እያንዳንድሽ ተነቃብሽ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰላማዎች / ወያወጽዑ ለክሙ ስመ እኩዬ / የነ አባ ማቴዎስ የህልም ፓትርያርክ እና /የዘመኑ ፖለቲካ ተካታይ በመምሰል ለማታለል ቀን ተሌሊት ከተራ ካድሬዎች ወሬ የሚለቃቅሙት አባ ቀሌሚንጦስ ድብቅ የፖለቲካ ማህበር / ማቅ / ስማችሁ ብያጠፋም ደስ ይበላችሁ ለእውነት መቆማችሁ ማንነታችሁ እያስመሰከረ ነው የእየሱስ ክርስቶስ የንጽህና ባህርይ ከእናቱ የተገኘ ነው ያለው መናፍቁ ኃይለጊዮርጊስ ምንም ያላለው ማህበር ማንንም መናፍቅ ብሎ የመጥራት ሞራል የለውም እርግጥ የ ነአባ ማቴዎስ ሰዎች ሆድ እንጂ ጭንቅላት ሞራል ሕግ መቸም የላቸውም / ከቢታንያ ደንጋይ በእጅጉ የባሱ ጠንካራች ናቸው የቢታንያ ድንጋይስ በሆሳእና ዕለት ስብሀት ለእግዚአብሄር ብሎ አመስግኖአል ወደ ቁም ነገሩ ልግባ
   ጉበኛው ዘረኛው አስመሳዩ ውሸታሙ ቀሲስ በላይ በመነሳቱ ተመስገን በማለት ፈንታ የተናደዱት እንደ ዕብድ ልብሳቸው ለመቅደድ የወሰኑት ብጹዕ አቡነ ቀሌሚንጦስ ለምንድነው ከተባለ ከሱ ጋር አንድ የሚደርግ የሙስና ባህርይ ስላላቸው ነው እሳቸው ከመጡ ጀምሮ በስርቆት በማጭበርበር የተያዙት ወገኖቻቸው ነጻ በማውጣት ካጠፉበት ደብር ወደተሸለ ደብር እንዲዛወሩ በማድረግ ላይ ናቸው የዚህ አይነቱ የሀቲአት ሥራ አዝዞ ለማሰራት ደግሞ ከሀይማኖተ አልባው ሊቀአእላፍ በላይ መኮነን ውጭ በምድር ላይ ሰው አይገኝም እሱ ገንዘብ ካገኛ ሌባን ጻድቅ ጻድቅን ሐትእ ለማለት ወደር የለውም ስለሆነም ሊያለቅሱ ይገባቸዋል ቀን በቀን ከፊታቸው ቆመው የሚያለቅሱት ሊቃውንትን ሳይሆን መረቴት በማረስ ተረጋግተው የሚኖሩት ዘመዶቻቸው ከባለ አገር በደላላዎች እያፈናቀሉ በማምጣት በማስጠራት በሌላቸው እውቀት መምህራን መዘምራን በማለት በየአድባራቱ በግዳጅ መቅጠር በጀመሩበት ሰዓት ይህ ጉድ ሲወርድባቸው እሳቸውን ከጀመሩት ዘረኝነት በላይ ከጎረሰው ጉባ ከሰማይ የወረደ ዕዳ ነውና ሊልቅሱ ይገባቸዋል ለእሳቸውም ሆነ ከስልጣናቸው በላይ ለሚያስቡ አባ ማቴዎስም መከራ መሆኑ ግልጽ ነው ቅዱስ ሲኖዶስ በማሰልጠኛዎች አሰልጥኖ በየአህጉረ ስብከቱ የመደባቸው ዘመዶቻቸውን ኢየሰበሰቡ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በማስመታት ገጠሪትዋ ቤተክርስቲያን ያሰባኪዎች በማስቀረት በአንድ ስራ ላይ 3 ሰራተኛ እንዲደራረብ እያደረጉ ይገኛሉ ይህን የመሰለ የዘረኝነት ተግባር የሚፈጽምላቸው ሰው ስለማያገኙ ቢያለቅሱ ይግድነው በአጠቃላይ ኣባ ማቴዎስ ለቤተክርስቲያን የሚያስቡ ቢሆኑ ኖሮ የሊቀ አዕላፍ በላይ ውሸታምነትና የዘረፋ ቅሌት ተግባር መቃወም ነበረባቸው ግን እሳቸው ማናቸው የዘረኝነትና የክፋት ይጥላቻ አባት እኮ እሳቸው ናቸው ግብራቸው ከመልካቸው የከፋ ነውና ከእሳቸው አከባቢ ያልሆነን ኢትዮጵያዊ ሰራተኛ ጥርሳቸው ዕየነከሱና ጎራዳ ጢማቸው እያሹ ከማሰብ ውጭ የት ያለ ክርስትና ከእሳው አከባቢ ውጭ ላለው ሰራተና ያላቸው አጤአዊ ጥላቻ ከሚያስወግዱ ቆባቸው ቢወገድ ይቀላቸዋል ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አባ ማቴዎስ ለጉበኛው በላይ መኮነን ክፍት አድርገው ያስቀመጡት የህግ መምሪያ ኃላፋነት ሊሰጡት ነው የህግ ሙያ ይቅርና ህገ ልቡና የሌለው ሰው ሲዘርፍ ሲቀማ ሰዎችን በብሄራቸው ሲያስለቅስ የነበረ ሰው የሕግ መምሪያ ኃላፊ ሊሆን አይገባውም ቅዱስ ፓትርያርኩ እዚህ ላይ ልብ ሊሉ ይገባል ቋሚ ሲኖዶስም ይህን ዘራፊ ለህግ በማቅረብ ለመጪዎችም ትምህርት የሚሆን እርማት እንዲሰጥ ማድረግ አለበት ከወንበር ከተነሳ በኃላ ከብር 25000 እስከ 80000.00 በመቀበል የፈጸማቸው ሕገ ውጥ ቅጥሮችና ዝውውሮች መሻር እንዳለባቸውም መዘንጋት የለበትም ደላላዎችም እንዲሁ የሚተዉ መሆን የለባቸውም ሊቀጳጳሱ በቅርቡ ያመጡት ና የሰው ሀይል አስተዳደር በማለት ከፓትርያርኩ እውናና ፈቃድ ውጭ ያስቀመጡት ሰው በ3 ወራት መኪና በ6 ወራት ቤተ በሚል መፎክር ሰወፖችን ለሃጢአታቸው ከቦታ ወደቦታ በማቀያር ከብር 15000 እስከ 25000 በቀን ቢያንስ በቁጥር 20 ከሚሆኑ ሰዎች ይቀበላል ይፈጽማል ያስፈጽማል በላይኑፓሱ የአንድ ሳንቲም አንድ ገጽታ ሲሆኑ እሱ ደግሙ የሳንቲሙ ጠርዝ ነውና ትኩረት ሊደረግበት ነው እናንተ ግን እውነትን ለመጻፍ ስለፈቀዳችሁ እግዚአብሄር ይቀበላችሁ ኮንትሮባንድ ነጋዴው ማህበር ግን ሌብነቱን እስካላጋለጥክ ሌባ ብትሆንም ምንም አይልህም መናፍቅ ብትሆንም ምንም አይልም አልማ የሌለው የገንዘብ መሰብሰቢያ የነአባ ማቴዎስ የነገይቱ ተስፋ ነውና ተስፋው ግን አይፈጸመም

   Delete
  2. የእብድ አይምውን የሳተ የሚጽፈውንና የሚሰጠውን አስተያየት ከየት ጀምሮ የት እንደሚጨርስ የማያቅ እዛም እዚህም የሚናከስ የሰካራም አካሔድን የሚራመድ የሰይጣን ፈረስ አይነት ግለሰብ ነህ። መጀመሪያ እራስህን ሆነህ ተገኝ ሌላውን ለመተቸት በማታውቀው ከምትደናበር!

   Delete
 3. በቃ ማህበረ ቅዱሳን እሱ ያልፈለገው ሰው ከሆነ መበጥበጡን አይተውም ማለት ነው? ድራሹ ይጥፋ ይሄ የሰይጣን ማሕበር

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቸሩ ጌታ ልቦና ይስታቹህ
   ወተቱን አጥቁሮ ማሩን አምርሮ ሆነባቹ
   ግን ለምን ለጠፊ ገንዘብ ሞት አለና ንስሀ እንግባ
   እዉነተኛዉ እምነት መችም አይጠፋም፡፡

   Delete
 4. ቸሩ ጌታ ልቦና ይስታቹህ
  ወተቱን አጥቁሮ ማሩን አምርሮ ሆነባቹ
  ግን ለምን ለጠፊ ገንዘብ ሞት አለና ንስሀ እንግባ
  እዉነተኛዉ እምነት መችም አይጠፋም፡፡

  ReplyDelete
 5. አባ ሰላማዎች እናንተ መናፍቅ ናቹ ክርሰቲያንመሰላቹኽና ለቤተክርሰቲያን ያሰባቹ በመምሰል ሽብር ለመንዛት ባትሞክሩ ምክንያቱም ከንቱ ድካም ሰለሚሆንባቹ ሁል ጊዜ ማህበረ ቅዱሳን እንዳላቹ እሱ የሚሰራውን ትንሸ እንኳን ለመሰራትሙከራ እንኳን ሳታረጉ መውቀሱ ማንነታቹሁን ነው ሚያሳብቅባቹ ሰለዚኸ እድሚ ለፀሀዩ መንግሰታችን የምትፈልጉትን እምንት መከተል ምድራዊ መብታቹ ሰለሁን እራሳችሁን ቻሉ የቤተክርሰቲያኒቱን ጉዳይ ለክርሰቲያኖች ተዉላቸው

  ReplyDelete
 6. ስማችሁ ከላይ የተገለፀው የማቅ ወዳጆች የተባላችሁ ሊቃነ ጳጳሳት ግን ምን ነካችሁ? እውነት ከሆነ እውነት፣ ሀሰት ከሆነ ሀሰት ለምን አትሉም? ጥፋት ካለ ማረም ምን ይጎዳል? ለነገሩ ሆን ተብሎ ችላ የተባለ ነገር ካልሆነ በቀር ከናንተ የሚያልፍ አልነበረም። ግን እኮ እግዚዚአብሔር ከኋላ ተነስቶ ይቀድማል። እኛ እናንተ ካልፈረዳችሁ ብለን አናስገድድም። ግን አቡነ ማትያስ ስራቸውን ይስሩበት። የፍትህ ያለህ ለሚለው ወገን የራሳቸውን ኃላፊነት ይወጡ። በሌብነት ሱስ ተጠምዶ ራሱን የዘነጋ ምን እንደሚደርስበት ማንም ያውቃል። ከማንም ምክርና ዕውቀት ሳይበደር በትክክል የሚፈርድ አምላክ ስላለን ደስ ይለናል ተስፋም እናደርጋለን።

  ReplyDelete
 7. 1ኛ ወዳጄ ማሕበረ ቅዱሳን በላይ መኮነን የተማረውን የቤተክርስቲያን ትምሀርት ብትነግረኝ
  ለነገሩ አንተም የእነ አባ ማቴዎስ የክብር ዲያቆን / የክብር ቄስ ነህ ምኑ ትነግረኝ
  ባይሆን የቤተክህነት ሰራተኞች የሊቀአእላፍ በትክክል ለመጻፍ ሊቀ አእዋፍ በላይ
  መንፈሳዊ ትምህርት ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል
  2ኛ ጥያቄ አቡሀ ለሐሰት የተባለው ማነው መልስ እኔ ሊቀአእዋፍ በላይ መኮነን ነው ብል ሰይጣን በስም ማሳጣት አይጣላኝም እውነት ውሸት

  ReplyDelete
 8. ያበራል ያብረቀርቃል ውሸቱ የመናፍቁ
  ወዳጄ ያበራል ውሸትህ፦ እንሿን ስምህን ቀይረህ ከሰይጣን ማዘዣ ከመናፍቁ ስፍራ ብቅ አልክ። ስታወራ አይደለም ቀን ማታና ሌሊት ከጳጳሱ ጋር የምትውል የምታድር ሆነህ ነው በውሸት ቀዳዳ ላይ ሌላ ቀዳዳ እየጨመርህ የምትለጣጥፈው። ቀዳዳ በቀዳዳ ላይ ቢከመርና የባቢሎን ግንብ ቢያክል ቀዳዳውን አይደፍነውምና አንተም የውሸት ክምርህን አሉ ይላሉ እያልክ ብትቀደድ ውሸት ከውሸትነቱ ሌላ ምንም አይነት እውነት አይገኝበትም። የራስህን ማንነት ለመሸፈን የጣርህ ያጣጣርህበት እንሿን ምን ያክል እምነት የለሽ በራስህ የማትተማመን ተራ የሰይጣን ጭፍራ መሆንህን ነው። አቶ ያብረቀርቅ ያበራል ውሸቱ ከመናፍቅ አዳራሽ፦ እውነተኛ የቤተክርስቲያኗ አባቶችም ሆኑ መንፈሳዊ ማህበራትና ምእመናን የሚያስጨንቃቸው የክርስቶስ ወንጌልና የቤተክርስቲያን ነገር እንጂ ሌላ አይደለም። የተሸበርከው አንተውና አዛዥ ደሞዝ ከፋይህ ሰይጣን ናችሁ። ምክንያቱም መዳን የሚገባቸውን ነፍሳት እንዳይድኑ የምታደርጉበት የስህተት ትምህርታችሁ ስለሚጋለጥ፣ አለማዊና የእግዚአብሔርን ስም ለሰይጣን አላማ ማስፈፀሚያ የምታደርጉበት የዳንኪራ መዝሙር ተብየ ዘፈናችሁ በእውነት ቤት ውስጥ ስፍራ ስለማይኖራቸው፣ የቤተክርስቲያኗን ሐብትና ንብረት በመዝረፍ ምድራዊ ሀብት የምናካብትበት መንገድ ታጥሮብና ብላችሁ፣ የቤተክርስቲያኗን እምነትና ስርዓት አውቀው በመኖር ጠብቀው በማስጠበቅ የተጉ አባቶችና አገልጋዮች የጽናት ተጋድሎ ለመናፍቆች ቦታ ስለማይኖራቸውና በልዩ ልዩ ምድራዊ አለማዊ ምኞት ቅዠቶቻችሁ የሚሆን በማጣትና በማግኘት አየር ላይ በመንጠልጠላችሁ ነው። አቶ የብረቀርቅ ያበራል ውሸቱ የመናፍቁ፦ መቶ አመት የቆየ ሙስና ነው ያልከው!ለመን በመቶ አመት የተደረጉትን ሙስናዎች አንድ ሁለት ብለህ አልጠቀስሐቸውም? የውሸት ቀዳዳ ግንብ ማለት ይሄ ነው። ምንም እንከን ሙስና በአለም ላይ በየትኛውም ተቋም ያለ ቢሆንም እንዲህ በመላምት ለዚህን ያክል አመት የቆየ ሙስና ማለት ግን ከሐሰተኛና ከሙሰኛ የሚወጣ መላምት መረጃ አልባ ውሸት እንጂ ከእውነተኛና የሙስና ጠላት ከሆና የሚወጣ መዘላበድ አይደለም። አቶ ያብረቀርቅ ያበራል ውሸቱ የመናፍቁ፦ በላይ ሙሰኛና ዘራፊ ለመሆኑ በቂና አስተማማኝ መረጃ አለ ነው ያልከው። ለምን አንዱን እንሿን ማስረጃ አላቀረብከውም? በአሉባልታና በውሸት ክምር የሰውን ማንነትና ንፅህና ማጥቆር ለጊዜው የሚሆን ቢመስልህም እውነት እውነት ነውና ነገ ደምቆ ይወጣል። ደግሞ ከአንተ በአለም አስተሳሰብ ከምትመላለሰው የሚጠበቅ ነው። ምክንያቱም አለም አይደለም ለእውነተኞቹ ለክርስቶስ ተከታዮች ለራሱም ለክርስቶስ ያልተመቸች በውሸት ክስ የወነጀለችና ያክፋፋች ናትና ነው። አቶ ያብረቀርቅ ያበራል ውሸቱ የመናፍቁ፦ ብዙ መዘባረቅና ተረታ ተረቶችን የቀባጠርህ ቢሆንም ውሸትህን ካስዋብክባቸው ትርኪምርኪ ትረካዎችህ አንዱ ማህበረ ቅዱሳን አቀረባቸው ያልከውና አንዱ የክህነት ትምህርት ቢኖረውም በዘመናዊ ትምህርቱ ግን ከአራተኛ ክፍል ያልዘለለ ነው ያልከው ተውኔትህ ነው። ለምን ከኬጂ ያላለፈ የትምህር ደረጃ ነው ያለው ብለህ ድራማህን ሰርተህ የአለምን ፈገግታ አታስከፍተውም ነበር።

  ReplyDelete
 9. selam aba selam

  ReplyDelete
 10. ተሃዲሶዎች ብዙ ጊዜ የምትደግፉት ማህበረ ቅዱሳንን ይደግፋሉ የምቱዋቸውን እንጂ እውነትን አይደለምና እባካችሁ አካሄዳችሁን እሰተካክሉ፡፡

  ReplyDelete
 11. ተሃዲሶዎች ብዙ ጊዜ የምትቃወሙት ማህበረ ቅዱሳንን ይደግፋሉ የምቱዋቸውን እንጂ እውነትን አይደለምና እባካችሁ አካሄዳችሁን እሰተካክሉ፡፡

  ReplyDelete
 12. ere bakachhu lemsale ene le keyari enkuan 15 000 birr kefyalew lebelay belachhu tamnalachhu? adisabeba medical college heje askemechalew

  ReplyDelete