Wednesday, March 25, 2015

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ እና ለመጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር ደማቅ አቀባበል ተደረገ

Read in PDF

ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለግል ጥቅማቸውና መንደረተኛ ፖለቲካ በቤተክህነት በኩል አድርጎ ወደ ቤተመንግሥት የሚያደርገውን ግስጋሴ ለማሳለጥ ውስጥ ውስጡን በመናበብ ሲሠሩ የቆዩት አባ ማቴዎስና ማቅ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚችሉትን ያህል የወንዞቻቸውን ሰዎች በቅጥርም በሰበካ ጉባኤ አባልነትም ቦታ ቦታ ሲያሲዙ ከቆዩ በኋላ በሙስና የተጨማለቁትና ብዙዎችን በጉቦ ሲያስለቅሱ የነበሩት የወንዛቸው ልጅ ቀሲስ በላይ መኮንን በፓትርያርኩ ትእዛዝ ከቦታቸው መነሣታቸውንና በቦታቸው ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ መሾማቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ዘመቻ ከፍተው መሰንበታቸው ይታወሳል፡፡ 

ዘመቻቸው የማኅበረ ቅዱሳን ንብረት በሆነው በሐራ ተዋህዶ ላይ ከፍተው የሰነበቱ ሲሆን፣ አባ ማቴዎስ አለኝ በሚሉት የሥራ አስኪያጅነት ሥልጣን ሹመቱን አልቀበልም በሚልና ወደ ቋሚ ሲኖዶስ እወስደዋለሁ በማለት ለማደናቀፍ ሲጥሩና ሲያንገራግሩ፣ ማቅም ሕግ ተጥሷል በሚልና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሆነው አዲስ በተሾሙት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻውን ከፍቶባቸው መሰንበቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከቆራጥ ውሳኔያቸው ማንም ዝንፍ ያላደረጋቸው ቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ በውሳኔያቸው ጸንተው ለሥራው ይመጥናሉ ለውጥም ያመጣሉ ብለው ያሰቧቸውን ሊቀማእምራን የማነንና መጋቤ ብሉይ አእመረን ሾመዋል፡፡ የቅዱስ ፓትርያርኩን ሥልጣንና ትእዛዝ ለመጋፋት መሞከር ዛሬ ያበቃለት ይመስላል፡፡
ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ተጀምሮ አባ ማቴዎስ እንደ ኮሶ ከተጣባቸው ዘረኛነትና የአንኮበር ፖለቲካ የተነሣ በእንቢተኛነታቸው ሲታሽ የሰነበተው የሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራአስኪያጅ ሹመት በቅዱስ ፓትርያርኩ ቆራጥ አመራርና ቀጥተኛ ትእዛዝ ተፈጻሚ ሆኖ በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለተሾሙት ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ ለአቀባበሉ አዳራሹ ከአፍ እስከ ገደፉ የሞላ ሲሆን ወንበር መቀመጫ ጠፍቶ የቆሙ ሰዎች ይታዩ እንደነበር በስፍራው የነበሩ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በፓትርያርኩ ቀጥተኛ ትእዛዝ ለተሾሙት ሰዎች የተጻፈላቸው ደብዳቤ በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ መነበቡን የገለጹት ምንጮች፣ በሹመቱ የተከፉትና ሁል ጊዜ ድብቅ ዓላማቸውን ለማሳከትና የመንደር ፖለቲካ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ተንጠላጥለው ለማራመድ የሚፈለጉት አባ ማቴዎስና ብጤያቸው አባ ቀሌምንጦስ በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ብዙዎችን አነጋግሯል፡፡ በዚህም ትልቅ ትዝብት ላይ የወደቁ ሲሆን ማንነታቸውን አጋልጠዋል፡፡ በመሆኑም አዲስ የተሾሙት ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች በፓትርያርኩ ቀጥተኛ ትእዛዝ የተሾሙ ሥራ አስኪያጆች ሆነዋል፡:

በአቀባበል ሥነሥርዓቱ ላይ በርካታ ሐሳቦችና አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሰው በሥነሥርዓቱ ላይ የተገኘው ያለማንም ቀስቃሽ መሆኑ አብዛኛው ሰው ለውጥ ፈላጊ መሆኑን እንደሚያሳይ የተመለከተ ሲሆን፣ ሀገረ ስብከቱ አገልጋዩን ክፍል በገዛ አገሩ ላይ የዜግነት መብቱን እንኳ ሳይቀር የገፈፈ ሀገረ ስብከት ሆኖ መቆየቱ ተገልጿል፡፡ እንደ ሰባ ሰባት ድርቅ በሀገረ ስብከቱ በር ላይ ነጋ ጠባ የሚኮለኮሉትን መታደግ የሚያስፈልግበትና እንባቸው የሚታበስበት ጊዜ አሁን ነውም ተብሏል፡፡ በተለይም ከጉቦ አሰራር ጋር በተያያዘ 40 እና 50 ሺህ ብር ከየት ይመጣል? በሚል የጉቦ አሠራር ምዕራፉ ጨርሶ ሊዘጋ ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ ታዳሚዎች አሉ፡፡ 
በሌላም በኩል በየአጥቢያው ያሉ የማይመለከታቸውና በየዐውደ ምሕረቱ እንዘዝበት የሚሉ በቡድን የተደራጁ ማለትም ማኅበረ ቅዱሳን ያደራጃቸውን አንድ ማለት የሚጠበቅ መሆኑንና አሁን የተሾሙት ይህን የማስተካከል ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ታዳሚዎች ጠቁመዋል፡፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አንዳንድ ሠራተኞች የማኅበሩ አሽከሮች መሆን እንደሌለባቸው የጠቆሙት ታዳሚዎች፣ በማኅበሩ ሳንባ የሚተነፍሱ አለቃዎች፣ ጸሐፊዎች፣ ሰንበት ት/ቤቶች፣ ሰባክያንም የቤተክርስቲያን ጠላት ለሆነ ማኅበር ሳይሆን ለቤተክርስቲያን እንዲወግኑ አሳስበዋል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ሠልጥኖ የቆየውን የግፍ አገዛዝ በተለይ ዘረኝነቱንና ጉቦኝነቱን አዲሶቹ ተሿሚዎች እንደሚቀርፉ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ዛሬ የተገኙትም የፓትርያርኩን መመሪያና ትእዛዝ በማክበር እንደሆነና በሐራ የተቦካውን አሉባልታ ለመቃወም ጭምር መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ ሐራ የተባለው የማኅበረ ቅዱሳን አሉባልታ መንዣ፣ የእነ አባ ማቴዎስ ሉቃስና ቀሌምንጦስ ፖለቲካ ማካሄጃ የሲኖዶስ ምስጢር ማውጫ (በእነ አሉላ ብርሃኑ አድማስ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም ጦማሪነት) የሆነው ብሎግ አንድ መባል አለበት ብለዋል፡፡
እንዳይሾሙ ለማድረግ ማኅበሩ በተለመደ ስልቱ የሥም ማጥፋት ዘመቻ የከፈተባቸው ሊቀ ማእምራን የማነና መጋቤ ብሉይ አእመረ ማኅበሩ እንዳለው ሳይሆኑ የተሻለ ሥራ ሊሠሩ የሚችሉ መሆናቸውን ብዙዎች ገልጸዋል፡፡ ሃይማኖተ ወልጋዳው ሐራ ታላቁን ሊቅ አእመረ አሸብርን “በሃይማኖታቸው ርቱዕነት ነቀፌታ አለባቸው” ማለቱን ከመድረክ መሪው አንስቶ አለቆችና ጸሐፊዎች ጭምር በመቃወም እውነተኛ ምሰክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ እርሳቸው በዘመድ ወይም በጉቦ ተመድበው ሳይሆን ተወዳድረው አንደኛ በመውጣት የሊቃውንት ጉባኤ አባል መሆናቸው፣ እዚህ ደረጃ ላይ ለመድረሳቸውም የያዙት ዕውቀት አስተዋፅኦ እንዳበረከተ፣ በሌላም በኩል ማኅበሩ በሐራ ያቀረበውን ሃይማኖታዊ ክስ ለመመርመር ብቃቱ የሌለው መሆኑን ያብራሩ ሲሆን ትናንት ዛሬ፣ ነገም ለቤተክርስቲያናቸው ወግነው እንደሚሠሩና ለአሉባልታ ቦታ እንደማይሰጡ ተናግረዋል፡፡
በሊቀ ማእምራን የማነ እንደተገለጸውም በየቦታው መሽጎ አባቶችን ተገን በማድረግ እያበጣበጠ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ ተመልክቷል፡፡ እየተፈጸመ ያለውን ብልሹ አሠራር በተመለከተም ወደመኪና ሲገባ በር የከፈተ፣ ወደቤተክርስቲያን ሲገባ ጫማ የያዘ ሁሉ እየተሾመ ቤተክርስቲያን ውስጥ መግባባት እስከማይቻል ድረስ ትልቅ ችግር እየተፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም አንዱ ተባርሬያለሁ ብሎ አቤት ሊል ሲመጣ ሌላው ለማባረር ይመጣል ሲሉ ቤተክርስቲያን በተበላሸ አሠራር ውስጥ መውደቋን አመልክተው ቤተክርስቲያን የጣለችባቸውን ኃላፊነት ለመወጣትና ላለማሳፈር እሠራለሁ ብለዋል፡፡   
በዚህ ታሪካዊ ሊባል በሚችል፣ ማኅበረ ቅዱሳንና ተላላኪ ጳጳሳቱ አንገት በደፉበት፣ ለሰበር ዜና ማንም አይቀድመኝም ባዩ ሐራም ምንም እንዳልተፈጠረና ምንም እንዳልሰማ ሆኖ ባንቀላፋበት በዚህ ክሥተት ፓትርያርኩ የወሰዱት ቆራጥና ፈጣን እርምጃ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው፡፡ መሪ ሊኖሩት ከሚገቡ አቋሞች አንዱ ወሳኝ በሆነ ጕዳይ ማንንም ሳይፈራና ኀላፊነቱን በመውሰድ ፈጣን ምላሽ መስጠቱ ነው፡፡ ፓትርያርኩም በዚህ ውሳኔ ላይ የወሰዱት እርምጃ መሪነታቸውን ያሳየ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እንደ አቡነ ጳውሎስ ማኅበረ ቅዱሳንን እሹሩሩ ሳይሉና ሳይፈሩ፣ ለተላላኪ ጳጳሳቱም አድማና ሴራ ሳይንበረከኩ በአቋማቸው መጽናታቸው ትልቅ ሰብእናቸውን ያሳያል፡፡ እንዲህ ባያደርጉ ኖሮ ምን ይከሠት ነበር? ማኅበረ ቅዱሳን ከዚህ የበለጠ ይፈነጭ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን የተሾሙት ሥራ አስኪያጅና ምክትላቸው በተለይ ለማኅበሩ ሥጋቶች መሆናቸው አይቀርም፡፡ ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ ከዚህ ቀደም የማኅበሩን እኩይ ሥራ በአደባባይ በመቃወም አቋማቸው ታይቷል፡፡ መጋቤ ብሉይ አእመረም በሊቅነታቸውና አብነታዊውን ትምህርት ከዘመናዊው ትምህርት ያስተባበሩ በመሆናቸውና ማኅበሩ ባልዋለበትና እያወላገደ ኦርቶዶክሳዊ የሚለውን ኢርቱዕ ትምህርቱን ስለማይታገሡ ከፍተኛ ጥላቻ አለው፡፡ 
በሰሞኑ አድማና ሤራ ማቅና ተላላኪ ጳጳሳቱ አባ ማቴዎስ፣ አባ ሉቃስና አባ ቀሌምንጦስ ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆቹ እንዳይሾሙ ለማድረግ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡ ግን አልተሳካም፡፡ ከዚህ ሴራ በስተጀርባ የማቅ እጅ እንደነበረ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ማኅበሩ ለአባ ማቴዎስና ለአባ ቀሌምንጦስ የቤት ሥራ ሰጥቶ የፓትርያርኩ ትእዛዝ ተፈጻሚ እንዳይሆን ሲታገል ቆይቷል፡፡ በዚህም ማቅ የቆመው ለተራና ምድራዊ ጥቅሙ እንጂ ለቤተ ክርስቲያን እንዳልሆነ በብዙ መንገድ አሳይቷል፡፡ አለአግባብ የታገዱ፣ ዘወትር ሮሮ የሚያሰሙ፣ የሚያለቅሱ በጉቦ ምክንያት የሚሠቃዩና የተባረሩ ሠራተኞችን እንባና ብሶት ከምንም አልቆጠሩም፤ ከምንም በላይ የቀሲስ በላይን ሙስና አላጋለጡም፡፡ በዚህም ለግል ጥቅማቸው እንጂ ለቤተክርስቲያን እንዳልቆሙ አስመስክረዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን የተሾሙትን ሰዎች ከሌላ ፕላኔት የመጡ በማስመሰል ሌላ ምስል ለመፍጠር ያደረጉት ጥረት ዓላማው ዘረኝነትና ፖለቲካ እንጂ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ቀሲስ በላይ ሲሾሙ፣ በኋላም ሲዘርፉና ሲመዘብሩ ብዙዎችንም ሲያስለቅሱ ምንም እንዳልተፈጠረ ሆነው ነውና የኖሩት፡፡
ለአቡነ ጳውሎስ የሥራ እንቅፋት እየሆኑ ያስቸግሩ የነበሩትና ትግሬዎችን በፖለቲካ ጎጃሜዎችን ደግሞ በመናፍቅነት የሚከሱ ሰዎች አሁንም ይህን ጉዳይ ማራገባቸው አልቀረም፡፡ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲህ ያለው ዘረኛ አስተሳሰብ የሚራመደው ግን እስከ መቼ ይሆን? ምናለበት ሰውን በዘሩ ሳይሆን በሰውነቱ መመልከት ቢቻል? ሁሉም ወገን ዕውቀቱና ችሎታው እስካለው ድረስ ዘሩና ወንዙ መመዘኛ ሳይሆኑ እንዲሠራ ቢደረግ ምናለበት? ሌላውን በማስተማር ምሳሌ መሆን የሚገባት ቤተክርስቲያን የችግሩ ምንጭ ከሆነች በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ይህ ዘረኛ አስተሳሰብ ከቤተክርስቲያን መወገድ ካልቻለና ሰውን በሰውነቱ መቀበል ካልቻልን የቤተክርስቲያን ችግር እየባሰበት እንጂ እየተሻለው አይሄድም፡፡ ሁሉም ጳጳስና ሥራ አስኪያጅ ሲሾም የወንዙን ልጅ መሰብሰቡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ዘረኛነትን እያስፋፋው ይገኛል፡፡ ቤተክህነት ውስጥ ሰው መመደብ ያለበት በችሎታውና ለቦታው የሚመጥን ሙያ ያለው እንደሆነ ብቻ መሆን አለበት፡፡ ብዙዎቹ ጳጳሳት ግን እንዲህ ሲያደርጉ አልታየም፡፡ በተለይ የአቡነ ማቴዎስ ዘረኛ አሠራር ቅጥ ያጣ ሆኗል፡፡
እኚህ ዘረኛ ጳጳስ በሙስና ምክንያት ዝውውርም ሆነ የደረጃ እድገት ለጊዜው እንዲቆም በታዘዘበት ወቅት በርካታ የወንዞቻቸውን ልጆች፣ ለተመደቡበት ቦታ እንኳ እንደማይመጥኑ እየታወቀ ሥልጣናቸውን አለአግባብ በመጠቀም ሲቀጥሩና ሲያዘዋውሩ ነበር፡፡ ለአብነት ያህል ጥቂቱን ቀጥሎ እንዘረዝራለን፦
·        መጋቤ ምስጢር ሳሙኤልን ከቁልቢ ንዋየ ቅድሳት መሸጫ ወደ ትንሣኤ ዘጉባኤ ምክትል ሥራ አስኪያጅነት
·        ቄስ ይኄይስን ከአስተዳደር ጸሐፊነት (አርቃቂነት) ወደ ሥራ አስኪያጅ ዋና ጸሐፊነት (የእርሳቸው ጸሐፊ)
·        ወ/ሮ ሸዋዬ ከመዝገብ ቤት ሠራተኛነት ወደ ቁልቢ ንዋየ ቅድሳት መሸጫ
·        ቄስ ቃለ ጽድቅ ከጉራጌ ሀገረ ስብከት (ከሆሳዕና) ለሌላ ዝውውር እየተባለ ከነበጀቱ የትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ቁጥጥር ሃላፊ፣ አሁን ደግሞ ለሥራው የሚያበቃ ሙያ ሳይኖረው ኦዲተር ተደርጓል፡፡
·        ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ ወንጀል ፈጽሞ ከታሰረ በኋላ ሲፈታ ለማንም ያልተደረገና የማይደረግ የታሰረበት ጊዜ ያልተከፈለው ደሞዝ በሞራል ካሳ ስም እንዲከፈለው ተደርጎ የትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ምክትል ኃላፊ ተደረገ፡፡ እዚያም ወንጀል ፈጽሞ ወደ ስብከተ ወንጌል መምሪያ ተዛወረ፣ እዚያም ሃይማኖታዊ ወንጀል ፈጽሞ መናፍቅነቱን ያመነ ሲሆን ጉዳዩ በእንጥልጥል ላይ ነው፡፡
·        የአልባሳት መምሪያ ጸሐፊ የነበረን ሰው አሁን የጳውሎስ ኮሌጅ የሠራተኛ አስተዳደር ዋና ኃላፊ አድርገውታል፡፡
·        ቄስ ምትኩ ከንቲባ ጡረታ ክፍል ኃላፊ የነበረ ሰው በ6 ወር ውስጥ የአልባሳት ምክትል መምሪያ፣ የሙዚየም ምክትል መምሪያ፣ የዕቅድና ልማት ምክትል መምሪያ
·        አቶ ያለው ምንም የትምህርት ማስረጃ የሌለው ሲሆን የአስተዳደር ክፍል ሆኖ ይሠራ የነበረ አሁን ገንዘብ ወደሚገኝበት የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የደንበኞች አገልግሎት ዋና ኃላፊ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ደግሞ፦
·        ሳህለ ማርያም ካህናት አስተዳደር ሲሆን ለሕግ መምሪያው ተወዳድሮ ሳያልፍ ቀርቶ አባ ማቴዎስ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ልከውት በካህናት ላይ ሙስና እየፈጸመ ይገኛል፡፡
·        የሳህለ ማርያም ወንድም የትምህርት ክፍል ም/ኃላፊ
·        ማሙዬ ጠቅላላ አገልግሎት
·        በእደ ማርያም ከቦሌ ክፍለ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት
·        የቻለው ለማ ከጠቅላይ ቤተክህነት ወደ አዲስ በባ ሀገረ ስብከት የተዛወረ እና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡
ይህን ያነሳነው ለማሳያ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች የሸዋ ሰዎች ቢሆኑም ዕወቀቱና ሙያው ኖሯቸው በተገቢው መንገድ ተመድበው ቢሆን ኖሮ ትክክል ነው፡፡ የሆነው ግን የሸዋ ሰዎች ስለሆኑ ብቻ በወንዝ ልጅነት ነው ዝውውርና ቅጥር የተደረገላቸው፡፡ አሁን የተሾሙት ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራአስኪያጅ እንዲህ ያለውን የዘመድ አዝማድ ሥራ ለማስወገድ የሚፈለግባቸውን ሁሉ ማድረግ አለባቸው፡፡ በቅድሚያ ያለውን የሙስናና የዘረኛነት ችግሮች በጥልቀት ማጥናትና የተዘረጋውን የሙስና ሰንሰለት ለመበጣጠስ የሚያስችል አሠራር መዘርጋት አለባቸው፡፡ በሙዳየ ምጻት ቆጠራ፣ በሠራተኛ ዝውውርና ቅጥር ላይ ግልጽነት የሠፈነበትን አሠራር መቀየሥ፣ ሥራና ሠሪውን ማገናኘት አለባቸው፡፡ በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደተንጸባረቀው ለውጡ መጀመር ያለበት ከዚያው ከሀገረ ስብከቱ መሆን አለበት፡፡ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ መሽገው የቤተክርስቲያኗን ሳይሆን የማኅበሩን ተልእኮ የሚፈጽሙትንና ዘረኛ ፖለቲካ የሚያራምዱትን ማጥራት ያስፈልጋል፡፡ ማኅበሩ እንደ አስተኳሽ የሚጠቀምባቸውን የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶችን ኅብረት ነን ባዮችን ማጥራት ያስፈልጋል፡፡
በመጨረሻም ቀሲስ በላይ ከሥራ አስኪያጅነት የተነሡት ለምንድነው? ጩኸት ስለበዛ ነው፡፡ የጩኸቱ ምክንያት ደግሞ በዋናነት ሙስና ነው፡፡ ይህ ከታወቀ ደግሞ ቀሲስ በላይ መኮንን በሙስና ወንጀል መጠየቅ አለባቸው፡፡ ካልተጠየቁ ግን የተደረገው የአመራር ለውጥ ትርጉም የለውም፡፡ አሁን ለተሾሙት የሚያስተላልፈው መልእክትም ጥሩ አይደለም፡፡ ስለዚህ ቀሲስ በላይ ተጠያቂ የሚሆኑበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት፡፡

37 comments:

 1. እግዚአብሔር ይባርካችሁ አንጀት አርስ ዘገባ ነው።

  ReplyDelete
 2. ጉድ ነው አድነኝ ጌታዬ

  ReplyDelete
 3. ጉድ ነው አድነኝ ጌታዬ

  ReplyDelete
 4. I have seen everything! It was very colorful! It shows the griefs of the workers. I have been surprised by the decision of the Patriarch. He is commuted to go further. It is also great responsibility for those newly assigned officials. May God save the Church!

  ReplyDelete
  Replies
  1. What are the colors you seen? what are the griefs of the workers? You said, you have been surprised by the decision of the patriarch. So how much you are surprised surpr, how many time you are surprised such kind of faithless decision decis? you are talking just like people who are missed there humanity.

   Delete
 5. + ለአብነት መምህራን እና ደቀ መዛሙርት ድጋፍ ተደረገ ::
  በማኀበረ ቅዱሳን ጎንደር ማእከል የቅዱሳት መካናት እና ማኀበራዊ አገልግሎት ክፍል መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ.ም በማክሰኝት ከተማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ከ600 በላይ ለሚሆኑ የአብነት መምህራን እና ደቀ መዛሙርት የመጻሕፍት፣ የሕክምና፤ የአልባሳት እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ፡፡
  + የመምህር አካለ ወልድ የሐዲስ ኪዳን የመጻሕፍት ትርጓሜ ት/ቤት የበግ ማድለብ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ ነው
  + የደሴ ማእከል ሙያ አገልግሎት እና አቅም ማጎልበቻ ክፍል ከመቅደላ ወረዳ ማእከል ጋር በመተባበር በመቅደላ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና ከወረዳ ቤተ ክህነቱ ለተውጣጡ 116 ካህናት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለሚገኙ ቅርሶች አያያዝና የይዞታ አከባበር የካቲት 14 ቀን 2007 ዓ.ም ሥልጠና ሰጠ፡፡
  + በሲዳማ፣ጌዲኦ.አማሮና ቡርጂ ሀገረ ሰብከት በሐዋሳ ወረዳ ቤተ ክህነት የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አዲስ ያሰገነባውን ባለ 4 ፎቅ ሁለ ገብ ህንጻ እና ት/ቤት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ፣የክልሉ ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት እና ምዕመናን በተገኙበት የካቲት 7 ቀን 2007 ዓ.ም በድምቀት አስመረቀ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሌቦችና የሌቦች ጥርቅሞች መሆናችሁ ይፋ ይወጣል፡፡ በማንኛው የቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ የገቢ ደረሰኝና በማንኛው አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ አመራር እንደ ድሪቶ በቤተ ክርስቲያን የክብር ካባ ሥር ተጠልሎ ቤተ ክርስቲያንንበየምክንያቱ መዝረፍ፣ ለእነዚህ እኮ ሕጋዊ መምሪያወች አሉ እናንተ ምንድን ናችሁ የማደጎ ቤተ ክህነት ናችሁ፣ ዋናውን በማዳከም ለራሳችሁ ዝና እና ዝርፊያ፣ በጎ አድራጎ ከሆነ ደግሞ ጡሩምባ አያስፈልግም፣ ማቅ የሌቦች ጥርቅም መሆኑን ጠብቁ እናጋልጠዋለን አትጠራጠሩ !!!!!!!!!

   Delete
  2. ለanonymous march 28,2015 at 2:45
   ውድ እናጋልጠዋለን አትጠራ፦ ዛቻህ ሒትለርን ፤ ድንፋታህ ጎልያድን ይመስላል። በጣም የተበሰጨህና የእግዚአብሔር ባሪያዎች የሆኑት የቤተክርስቲያን ልጆች ለቤተክርስቲን ሁለንበናዊ አገልግሎት በተጠናገረና በተደራጀ ሁኔታ እንዲፋጠን በሰሩት ስራ ስትረበሽ ትታያለህ። ምክንያቱም ደግሞ የናንተ የስህተት ትምህርት ምንፍቅናና የዘረፋ መንገድ ተዘጋብኝ የነቁ ለእምነታቸው የፀኑ የማይወላውሉ የክርስቶስ ወንጌል ለቅዱሳን ክብር የቆሞ እኔንና መሰሎቸን በወንጌል መዶሻ የሚያንበረክኩ ሆኑብኝ በማለት ነው። አቶ እናጋልጠዋለን አትጠራጠሩ፦ አንተ የበግ ለምድ የለበስ ተኩላ የሰይጣን ቅጥረኛ ሆነህ ሳለህ ሳትሆን መስለህ ቤተክርስቲያኗ ቡራኬና መመሪያ ሰጥታ በቤተክርስቲያን የተለያዩ አገልግሎቶች በገንዘብ በእውቀታቸው እየሰሩ ያሉትን ለማንጏጠጥ ተነሳህ። አቶ እናጋልጣቸዋለን አትጠራጠሩ ፦ ለራሳቸው ዝናና ዝርፊያ ነው ያልከው። አይ ጥንተ ጠላት ሰይጣን ሰውን በአርነት መልሰህ የሐጢያት ባሪያ ሐሰተኛ ከሳሽ ታደረገው። ወንድም በውሸት ክስና አሉባልታ በመዘብዘብ ምድራዊ አጨብጫቢ ካልሆነ ሰማያዊ ጽድቅ አያሰጥም። እነሱ በገንዘባቸው በእውቀታቸው ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ ከቤተክርስተያን በረከትንና ጽድቅን ከማግኘት ሌላ አለማዊ ስጋዊ ትርፍ የላቸውም። ዝናቸው እግዚአብሔርን ማምለክ ወንጌልን መስበክ የቅዱሳንን ክብርና አሰረ ፍኖት ማብሰርና መከተል ነው። አቶ እናጋልጠዋለን አትጠራጠሩ ፦ የእግዚአብሔር ህዝብና አገልጋዮች ስራ የተገለጠ የሚታይ ምስክር ማረጋገጫ ያለው በማስመሰል ያልተሞላ ተንኮል መሰሪ አላማና እሳቤ የሌለበት ነው። አቶ እናጋልጠዋለን አትጠራጠሩ፦ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ይህ ተሰራ መባሉ ደምህን አፍልቶ አይንህን አጉረጥርጦ የአሉባልታና የውሸት ነጋሪት ለምን ያስጎስማል? መልሱ አንድና አንድ ነው ። ይኸውም የክርስቶስና የቤተክርስቲያን ጠላት ስለሆንክ፤ ከቤተክርስቲያን ገብተህ ለመዝረፍ መቋመጥህ ስላልሆነልህ፤ ምንፍቅና የሐሰት ትምህርት እንክርዳድ መዝራት ስላልቻልክ ነው። አቶ እናጋልጠዋለን አትጠራጠሩ፦ እዛው ካዳራሽህ በውሸት የመንፈስ ወረደ ጫጫታህ እያጓራህ መፎከር ማጋሳትህን ብታቀላጥፈው ይሻልሃል የምታውቀው እሱኑ ነውና።

   Delete
  3. ዛቻው ቀኖናን የማስከበር ድንፋታውም ሥርዓትን የማስጠበቅ ነው፡፡ አንተ ዛቻና ድንፋታ ካልካቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታክ ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳንን የመሰለ እጅግ አስከፊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጠላት ተፈጠሮ አያውቅም፡፡ ለመሆኑ እነማን የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ናቸው የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች አንድ ስም ጥራ እኔ ማንነታቸውን እነግርሃለሁ፡፡ ለማያውቅሽ ታጠኝ አሉ፡፡ በመሠረቱ እነ አቶ እናጋልጣለን ማኅበረ ቅዱሻን ናቸው እስኪ እናንተ የምትጠቀሙበትን ማስፈራሪያ ስትሰሙት ምን ይመስላችኋል ብየ ስሞክራችው እውነትም እንደጠበቁት አገኘሁት፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ጠላትነት ልዩ የሚያደርገው በሃይማኖት አስመስሎ የገንዘብ ዘራፊ፣ አገልጋይ አሳዳጅ፣ የርካሽ ዛና ፍርፋሬ ለቃቃሚ፡፡ አቶ የእናጋልጠዋለን ባለቤት የማቅ አንጃ ተከታይ አዎ ልክ ነህ የማኅበረ ቅዱሳን አስመሳይነት፣ ሙሰኛና ዘራፊነት፣ የጥላቻ ምንጭ፣ ከፋፋይ፣ አድመኛና ቡድነኛነት እንደ መዥገር ከቤተ ክርስቲያን ጉያ ተደብቆ ደሟን የሚመጥ፣ ሲሏን የሚያዳክም፣ አስተዳደሯን የሚያጣምም፣ ቀኖናዋን የሚሽር፣ እንደ ድሪቶ በክብር ካባዋ ላይ ተጭኖ ስሟን የሚያክፋፋ፣ በፖለቲካ ምሕዋር ነብዞ መዋቅሯን እያጠፋ ልጆቿን እያሳደደ ያለ እፍኝ መንጋ ሲኖር ለምን አያናድድ፣ በቅንነት ከሰማህ ልንገርህ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ያሉት ከአውደ ምህረቱ፣ ከቤተ መቅደሱ፣ ከቤተ ልሔሙ ነው፣ ከቤተ/ክ አጸድ ከሰንበት ትምህርት ነው እንጅ፣ በቡድን ስሙ ካሠራው አንተ አዳራሽ ካልከው ሕንፃ ውሽጥ አይደለም፣ ባታውቀው ነውእንጅ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ታሪክ ከቤ/ክ አጸድ ውጭ ጉባኤና የአዳራሽ ስብሰባ የጀመረው ማቅ ነው፡፡ እና ማገልገል ከፈለግህ የቤተ ክርስቲያን ደጅ ክፍት ነው፣ ሰበካ ጉባኤ መድረክ ይጣራል በቡድን ጉያ ተደብቀህ በቤ/ክ ስም አትነግድ፣ መናፍቅ ማለት የሚጀምረው ከቀኖና ማፋረስ ሲሆን ከሀዲ ደግሞ ከይሁዳ ነው፣ ማቅ አሁን እንደይሁዳ የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ገና ሙዳይ ምጽዋት ሳይገባ እየዘረፈ ነው፡፡ እና ንቃ ለመዝለፍ ለመሳደብ አትቸኩል አሁንም ከፈለግህ ወቅቱ ይድረስ አንጅ የአንተን ዝነኞች ማንነት በአይንህ ታየዋለህ፡፡

   Delete
  4. ለanonymous April 8,2015 at 7:25 am
   ምንድን ነው ይህ ሁሉ ግሳትና አስመሳይነት። ከመቸ ወዲህ ነው ህንፃና አዳራሽ አንድ የሆኑት? ምነው ፊደል ስለተጠራቀመና ምላስህ ስለተውለበለበ የተኩላ ጩኸትህን አጮኸው? ማህበሩ እኮ ጉባኤ የሚያካሒደው ቤተክርስቲያን ለመንፈሳዊ አገልግሎቶች ባሰራችው የቤተክርስቲያኗ ቅጥር እንጂ አዲስ አበባ ስታዲየም ወይም መብራት ሐይል አዳራሽ አይደለም። ስለሌላው ክፉ ክስህና ቀረርቶህ ሰሚ ባታገኝም ስለማህበሩ ቤተክርስቲያንና ተግባሩ ምስክር ናቸውና ያ በራሱ በቂ ነው። አንተ የክርስቶስን አምላክነትና የቅዱሳንን ክብርና አማላጅነት የማታምንና የማትቀበል የወንጌል አጣማሚ የሰይጣን መልክተኛ ሳለህ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ለመምሰል መንከራተትህ ምን ያክል በራስህ የማትተማመንና ሐሰተኛ መሆንህን ነው የሚያረጋግጠው። ስለዚህ ውድ ከሳሽ በራስህ ለመታመንና ከአስመሳይነት እራስህን ነፃ አውጣ ስለሌሎች ከማውራት። የለበስኸው ጭንብል ያንተው አይደለምና ነገ በወንጀል የሚያስጠይቅ በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት ደግሞ አንተ ክፉና አስመሳይ ከሳሽ ለብሰኸው የነበረው የአስመሳይነት ጭንብል የኔ የሆነውን ለማጣመምና ለማስካድ ነውና ሒድ ወደ ተዘጋጀልህ የዘላለም ሞት ወደ ገሃነም የሚያስብል ነው። ደህና ሁን ቀረርቶ

   Delete
 6. እናንተም ምንም አይነት የአምልኮ መልክ የሌላችሁ በአመፃ ተወልዳችሁ በፈጠራ የክስና የሥም ማጥፋት ፕሮፌሽን ተጠብባች አሉባልታና የክርስቶስን ህዝብና ቤት ለማጥፋት የጎልያድን ጦር በስምነና ማንነትን በመለዋወጥና ተገን በማድረግ ትረውራላችሁ የክርስቶስ የሆኑትም መዳን ስላለባቸው ነፍሳትና የክርስቶስ ወንጌልን እውነት ለተጠሙና ለሚሹት ለመድረስ በትጋትና በፅናት ይሠራሉ። እናንተም የሰይጣንን የማስመሰያ ሙያ ለብሳችሁ ሐሰትንና ሐሰትን እየነዛችሁ በወንድማማቾች መካከል ፀብንና መለያየትን ለማድረግ አጥብቃችሁ ትተገብራላችሁ እውነተኛው ጌታ ደግሞ ነፍሱ አጥብቃ እናንተን ትፀየፋለች። እናንተ ሰይጣን ባስታጠቃችሁ ጦር እውነተኞችንና እውነትን ትዋጋላችሁ እውነትና እውነተኞች ደግሞ የእምነት ጋሻ ጥሩራቸውን ለብሰው ዘወትር በትጋት ከእውነትና ከእምነታቸው ጋር ይቆማሉ። እናንተ የክርስቶስን ቤተክርስቲያንና ተከታዮቿን በአባታችሁ ከዳቢሎስጋር አብራችሁ ትዋጋላችሁ እግዚአብሔር ደግሞ ስለ ቤተክርስቲያንና አማኞቿ ይዋጋል። እናን በስም የተደገፋችሁ በራሳችሁ የማትቆሙ አባ ሰላማ ተብየዎችና አሉባልታና ውሸት የፈጠራ ታሪክ የምትጽፋ የትኛውም ለእምነቱና ለቤተክርስቲያን የቆመ በህጋዊም ይሁን በሌላ ተሻሚ ሒድ አንተ ሰይጣን በራስህ የማትኖሮ በማስመሰል የምትመላለስ የጥፋት አገልጋይ አልሰማህም እንደሚሉህ የታመነ ነው። ዛሬ የጳጳሱን ተሻሚዎች እንዳሞጋገስካቸው ነገ እንደምታብጠለጥላቸው እርግጠኛ ነኝ። አሁን ምናልባት እንዲህ አይነት ተንኮልን የነሱ ያደላህ መስለህ አሉባልታና ውሸት የምትነዛው ቀዳዳ ነህና ለሰይጣን ተግባሬ መግቢያ ቀዳዳ አገኛለሁ በማለት እንደሆነ የታወቀ ነው። ይህ ደግሞ ጊዚያችሁ አይደለምና አይሆንላችሁም። አንተ የእውነትና የህይወት ጠላት አባ ሰላማ ነኝ ባይ ብሎግና አራማጆቹ እናንተም በእውነትና በፅናት የቆሙት ለመዋጥ አንቧርቁ እውነተኞችም የእምነት ጋሻቸውን ለብሰው ይዋጏችኋል

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ግን ተፈጥሮህ ከምንድን ነው? ዝም ብለህ ብቻ መንጫጫት ለኡኡታ ሰይጣን የሚያተጋህ ሰው ነህ

   Delete
  2. ለanonymous march 27,2015 at 8:42am
   ውድ የእውነት ጠላት፦ ስለ ተፈጥሮዬ ከሆ ለመጠየቅ የፈለግኸው እኔ የማመልከው አምላኬ እግዚአብሔር ነው ድንቅና ውብ አድርጎ በአምሳሉ የፈጠረኝ። በአጭሩ የእግዚአብሔር የእጁ ፍጥረት ነኝ ማለት ነው። ይህን ሰው በእግዚአብሔር መፈጠሩን አላምን ካልክ አለማመንህ እንደተከበረልህ ነውና አለማመን ትችላለህ። እናም ወደ እራስህ ተመልሰህ በአምኛው አስተሳሰብህና አተገባበርህ የስነ ፍጥረት ተመራማሪዎችህን ጠይቀህ ድምዳቤህን ስለኔ ተፈጥሮ መግለጽ ነው። ሌላው እያስመሰልህ ነገር ግን ሳትሆን እኔን ለመክሰስ የተጓዝህበት መስመር ነው። እንዲህም ትላለህ "ዝም ብለህ ብቻ መንጫጫት ለኡኡታ ሰይጣን የሚያተጋህ ሰው ነህ።" አይ የእውነትና የቤተክርስቲያን ጠላት!አይ የክርስቶስ የእርሱ የሆኑት ተቃዋሚ! አይ አስመሳዩ ከጥንት ጀምሮ በተንኮል የተወለድህ እባብ! አይ አስመሳዩ የእውነትና የክርስቶስ ወንጌል ጠላትና አጣማሚ! አይ አስመሳዩቅዱሳንን የምትጠላና የምታሳድድ እንዲሁም የምታክፋፋ!አይ አስመሳዩ የእግዚአብሔርን ሃይል የማታምን! አይ አስመሳዩ በክፋትና በተንኮል ተሞልተህ ሳለ እራስህን የብርሃን መላክ የምታስመስል! አይ አስመሳዩ በሐጢያትና በሰዶማዊ ምግባር ተሰማርተህ ሳለ እራስህን ፍፁም የምታስመስል! አይ አስመሳዩ በሰይጣን መንፈስ ተሞልተህና እየታዘዝህ በተግባር ሰይጣንን እያገለገልህ ሆነህ ሳለ ሌላውን ሰይጣን የሚያተገህ የምትል! በአሉባልታና በፀያፍ የሰይጣን ቅሰጣ የፈጠራ ታሪክ እውነትና ቤተክርስቲያን፣ ቤተክርስቲያንና እውነተኞቹ የሚጠፉ መሰለህን? እረ በፍፁም አይሆንም ወዳጄ አስመሳዩ። አቶ ወዳጄ አስመሳዩ፦ እኔ መንጫጫት ኡኡታ ሳይሆን ለእናንተ ባዶ አሉባልታና የፈጠራ የክህደት ወሬዎቻችሁ ነው መልስ እየሰጠሁ ያለሁት። ጫጫታና ኡኡታ ያለውማ ከእናንተው የሁከት መንፈስ አዳራሾቻችሁ ከመናፍቆቹ ከለጌዎኖች መንደር ነው። ሌላው አቶ ወዳጄ አስመሳዩ የተናገርከው "ሰይጣን የሚያተጋህ ሰው ነህ" የሚል ነው። ነገር ግን ያላዋቂ ትችትህንና ክስህን ስትጀምር ተፈጥሮየን ጠይቀኸኝ ነበር። በዚህ ተረትህ ግን ሰው መሆኔን ገልፀሃል። ይህ ደግሞ ነገሮችን የምትገዛለት ክፉ መንፈስ እንዳታስተውልና ወደ እውነት እንዳትቀርብ እንደተቀላቀለብህ ነው። ለማንኛውም እኔ ለማንኛውም ሰይጣንንና ክፉ ተግባሩን የምሸሽና የምቃወም በቅዱሱ የእግዚአብሔር መንፈስ የታተምኩኝ ነኝ። የቆምኩት ደግሞ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ስለተሰጠችው ስለ አንዲቷ ሃይማኖቴ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነቴ ነው። አቶ ወዳጄ አስመሳዩ፦ አንድ ነገር ማወቅ ያለብህ በማይኖሩበት በማስመሰል መዳንና ክርስቶስን ማስደሰት አይቻልም። እናም እውነትንና የክርስቶስ የሆኑትን ባትቃወም መልካምነው። እምቢ ካልክ ግን የመውጊያውን ቀስት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል። ደህና ሁን!

   Delete
 7. Papasaten yemetenagerubet Afe yegeremale manew tamagn agelegaye enanete weyes ? Bezuwethen bemekeses tethegerathuhale yerasathehune gudef yasayathu lebuna yesetathu

  ReplyDelete
 8. Yeteft meleketegnuthe

  ReplyDelete
 9. አባ ሰላማዎች እንዴት ናችሁ እውነቱን እውነት ውሸቱን ውሸት ማለታችሁን ቀጥሉበት

  ReplyDelete
 10. ማህበረ ቅዱሳን የተመሠረተው ቅዱሳንን
  ለማሰብ ነው ተብሏል። አሁን እያሰበ ያለው
  ግን በእምነት የተጋደሉትን የክርስቶስ ቅዱሳን
  ሳይሆን ለመንግሥት ሥልጣን የተጋደሉትን
  የይኩኖ አምላክ ቅዱሳንን ነው። የይኩኖ
  አምላክ ቅዱሳን ደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ እያሉ
  ይሰብኩናል። የክርስቶስ ቅዱሳን ግን ንስሐ
  ግቡ በሃይማኖት ጽኑ እያሉ ይሰብኩናል። አሁን
  ማህበረ ቅዱሳን የሚሞትበት ጊዜ ደርሷል፤
  ቁርባኑንም በተክለ ሃይማኖት አጥንት
  ተቀበሎታል። ግን የት ይቀበር ይሆን ? ሲሰብክ
  እንደኖረው ደብረ ሊባኖስ ይቀበር ይሆን ?
  እንደዚያ ከሆነ ሲኦልን አያይም። ወይስ አራት
  ኪሎ ቤተ መንግሥት ይቀበር ይሆን እንደዚህ
  ከሆነ ግን ኢትዮጵያን ይቀብራታል። ቀባሪዎች
  ሆይ ! እባካችሁ መጥፎ ሽታ ሳይመጣ ቶሎ
  ቅበሩልን!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous march 27,2015 at 4:42am
   ውድ የቀባሪዎችን እርዳታ ናፋቂ፦ እውነትንና እውነተኞችን መግደል ማስገደል ነውና አላማ ትምህርትህ ቀባሪዎች ሆይ እያልክ ትጣራለህ። ይህ ደግሞ የሚያመላክተው ክርስትና ምንና ምን ማለት እንደሆን የማታውቅ ለክርስቶስ ወንጌልና መንግስ ባይታወር ለሰይጣን ተግባርና መንግስት ደግሞ ብርቱ ቤተኛ መሆንህን ነው። የፈጠራ ክስና ውሸት ለመናገር የቆምህለት አላማ ሊቅ አድርጎሃልና ቅዱሱን ስትጠላና ስታንቋሽሽ፣ ስለቅዱሱ ቅድስናና በእግዚአብሔር የነበረውን አገልግሎቱን የተናገሩትን ደግሞ የጎዳሁ ያሳፈርኩ፣ ገዠና አሳዳሪህን ሰይጣንንና ጭፍሮቹን ያስደሰትህ መስሎህ በዘረኝነት መንፈስ ለመዘብዘብ ሞክረሃል። አቶ ከሳሽና ሐሰተኛ፦ በተዘዋዋሪ ደግሞ ከሙታን አንዱ መሆንህን ቀባሪዎችን ትጣራለህ። ቀባሪዎች ደግሞ ሙታን ናቸው። ምክንያቱም ሙታንን ሙታን ይቅበሯቸው ተብሏልና ነው። አቶ የቅዱሳን ጠላትሰይጣን፦ አመንክም አላመንክም ተክለሐይማኖ ቅዱስ ናቸው። እግዚአብሔር ፀጋን ያበዛላቸው አጋንትን ያስጨነቁና ከክርስቶስ ህዝብ የአስወጡ ናቸው። ከቅዱስም ቅዱስ በወንጌል ትምህርት አህዛብን ወደክርስትና የመለሱ የክርስቶስ ወንጌል ታታሪ ገበሬ ናቸው። ቅዱስ ተክለሐይማኖት በክርስትና የመንፈስ አባት ፃድቅ እንጂ አምላክ አይደሉም። አን ሰይጣኑ ግን ውሸታምና ሌባ ነህና የፈለግኸውን ማለትና መፃፍ ትችላለህ። ደህና ሁን ሙታን ቀባሪ ጠሪው።

   Delete
 11. እንግዲህ የቤተ ክርስቲያችንም ሆነ የሀገራችን
  የሁከት ምንጮች ገድለ ተክለ ሃይማኖትና
  የተክለ ሃይማኖትን ገድል በዘመናችን
  ለመድገም የሚራወጡ አድመኛና አክራሪ
  ብዱኖች ናቸው። እነዚህ አድመኞች የኢትዮጵያ
  ሕዝብ ቅዱሱን እና ንጹሑን የእግዚአብሔር
  ወንጌል አምኖ ወደ ሕይወት እንዳይሻገር፣
  ወንጌሉን አፍነው የሚሰብኩትንም አሳደው
  ይህን በዘር ፖለቲካ የተቀመረውን ገድል
  ይሰብካሉ። ይህን የሚቃወሙትን እውነተኛ
  ኦርቶዶክሳውያንን ተሐድሶ ፣ መናፍቅ እያሉ
  ይገድላሉ ያሳድዳሉ ይደበድባሉ። በወንጌል
  አምኖ ንስሐ የገባ የዘላለም ሕይወት አለው
  የሚለውን የሐዋርያት እምነት ገልብጦ
  « በተክለ ሃይማኖት አጥንት ላይ ቁርባን
  የተቀበለ ሲዖልን አያይም» የሚለውን ባዕድ
  ወንጌል ይሰብካሉ። ወዴት ጠጋ ጠጋ ? አንድን
  አማኝ ሲዖልን እንዳያይ የሚያደርገው ሥጋውና
  ደሙን መቀበሉ ወይስ በተክለ ሃይማኖት
  አጥንት ላይ መቀበሉ? የትኛው ነው እውነቱ ?
  ደብረ ሊባኖስን የማያውቁና መሄድ የማይችሉ
  የጎጃም የጎንደር የወሎ የትግራይ የደቡብና
  የምራብ ክርስትያኖች እንዴት ሊሆኑ ነው ?
  እነርሱ በዚያው ባካባቢያቸው ባሉ አብያተ
  ክርስቲያናት ቢቆርቡ ከሲኦል አይድኑምን ?
  ገድለ ተክለ ሃይማኖት « በተክለ ሃይማኖት
  አጥንት ላይ የቆረበ ሲዖልን አያይም» ሲል ምን
  ለማለት ፈልጎ ነው። ነጹሑን ኦርቶዶክሳዊ
  እምነት ካጥንትና ከመቃብር ጋር ለምን
  ያያይዙታል ? በኢትዮጵያ ከሞቱ ቅዱሳን ሁሉ
  የተክለ ሃይማኖት አጥንት ለመቁረቢያነት ለምን
  ተመረጠ ? ምሥጢሩ ግን በማህበረ ቅዱሳን
  ለፈዘዙ ሰዎች እንጂ እግዚአብሔር እውነቱን
  ለገለጠልን ለኛ ግልጥ ነው። ያው የተክለ
  ሃይማኖትን ሥልጣነ ክህነት ለመከላከል ሲባል
  የተገነባ የጭንቀትና የፍርሐት አጥር ነው።
  ክህነት ከተክለ ሃይማኖት ወገን የሚለው
  ስብከት የጸና እንዲሆን የተጨማመረ ማታለያ
  ነው። እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲታረም ነው
  የዘወትር ጩኸታችን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous march 27,2015 at 5:14 am
   መዘላበድና እውነትን በመካድና ያልተባለን በማለት የት ለመድረስ?
   መዘላበድም፣ እውነትን መካድና ያልተባለ ያልታሰበ መናገርም በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ፤ ወደ ጽድቅም የማይደርሱ መሆናቸው እሙን ነው። ታዲያ ወዳጄ ምነው ይህ ለመዳንና ለህይወት የማይሆን የዘር ጥላቻና በእግዚአብሔር መንፈስ የተደረገንና የተፈፀመን የእምነት ገድል በአለም የፍልስፍና አታካሮ ፓለቲካ መግለጽና ማወዳጄት ምን ለመሆን የት ለመድረስ ነው? ቅዱሱና ንፁሑ የእግዚአብሔር ወንጌል ነው ያልከው? ስታስመስል መጽሐፍ ቅዱሱን አንባቢና ቅዱሱን ወንጌልም አዋቂ ፍፁምና እንከን የለሽ ሆነህ ነው። ለመሆኑ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ቃል ጻድቃን የሚጠላ ቅዱሳንን የማይቀበል ዘረኛነትንና ጥላቻን ሐሰትንና አሉባልታን ከአምሮው አፍልቆ መንዛትንና አስመሳይ መሆኑ የተባረከ የተወደደ ነው የሚለውን? ደግሞስ የእግዚአብሔር ለቅዱሳኑ የሰጣቸው የተጋድሎና የመፈወስ ብሎም ታምር የማድረግ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ የተወሰነና የተገደበ ነውን? እግዚአብሔር በወደዳቸው በስጋም በነፍስም በታመኑት በቅዱሳኑ በኩል በመረጠውና በፈቀደው መንገድ ስራውን ይሰራል። እስራኤል ዘስጋን በነሐስ እባብ ከመቅሰፍት አድኗቸዋል። የጳውሎስ ቀሚስ አጋንትና ያስወጣ ህሙማንን ይፈውስ ነበር። እና ይህንም በመጽሐፍ ቅዱስ ባይኖር ኖሮ ውሸት ትለው ነበር። ደግሞስ የእግዚአብሔር እጅ ማዳን በመረጣቸው በኩል አቁማለችን? እረ በፍፁም!እግዚአብሔር ዛሬም ነገም ይሰራል በመረጣቸውም በኩል ድንቅን ያደርጋል እነሱንም አክብሮ አክብሯቸው ይለናል። አንተ እኮ ዛሬ እግዚአብሔር ፍጥረቱን ከማዳን ያቆመ፤ በመጽሐፍ ከተጠቀሱት ውጭ ሐዋርያት እንደፈፀሟቸው ተጋድሎ፣ የመፈወስና ታምር የማድረግ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋና ሐይል ሌሎች ለታመኑለት የማይሰጥ ነው ያደረግኸው። ይሄ ደግሞ ስህተትና በእግዚአብሔር አሰራር አለማመን ነው። ሌላው አስገራሚ ቂልና መናፍቅ መሆንህን ያሳበቀብህ የቅዱስ ተክለሐይማኖት ገድል፣ ቅድስናና ክብር እንዲነገርለትና እንዲከበር ያደረገው የታመነለት በነፍስም በስጋም በእምነት ጽናት ያገለገለው እግዚአብሔር እንጂ ማህበረ ቅዱሳን አይደለም። እናንተ ማህበሩን የምታክፋፉትና በውሸት የምትወነጅሉት ለእግዚአብሔር የእውነት ወንጌልና ለቤተክርስቲያን ሰማያዊ አገልግሎት ማንም ሳይሆን እግዚአብሔር ባወቀና በወደደው መንገድ ተመስርቶ ቤተክርስቲያንን ስለሚያገለግልና ከመናፍቃን ወረራና እንክርዳድ ስለሚከላከል ነው። አንተና መሰሎችህም እዚህ ብሎግ ላይ ከቤተክርስቲያን ነን እያላችሁ የምታስመስሉ ቢሆንም እውነተኛው ማንነታችሁ ግን መናፍቃንና የክርስቶስን ቤተክርስቲያንና ትክክለኛውን የክርስቶስን ወንጌል ትምህርት ለማጥፋትና ለመበከል ቅጥረኛ ሌቦችና የሰይጣን በላላኪዎች ናችሁ። ስለሆነም ማህበረ ቅዱሳን እውነተኛ ማንነታችሁን ስላወቀ ስለሚያጋልጣችሁና በወንጌል ቃል ስለሚዋጋችሁ፤ ለክርስቶስ ጠላትና ተቃዋሚ እንደመሆናችሁ ሁሉ የእሱ የሆኑትንና በእውነት የቆሙትን እንደ ማህበረ ቅዱሳን ያሉትን ማህበራት ሁሉ ትከሱ ትቃወማላችሁ። ወዳጄ ሰባት ጊዜ ሰባ አሉባልታ ብትነዛና ተንኮል ብትጠነስስ ማህበረ ቅዱሳን እንደሆነ በእግዚአብሔር ሐይልና በአባቶች ፀሎት ቆሟልና ምንም የምትለውጠው ነገር የለም። የአንተም ማንነት በእጅህ ጽሑፍና በተግዳሮትህ በጋልጧልና ሰይጣን ዞር በል ከመባል ውጭ ሰሚ የለህም። ደህና ሁን!

   Delete
 12. Zere tezera alu bebiet kehente
  Yeneliyon lejoch deberuwan wersuwat
  Ametsegnawu hulu gebeto mezeberat
  Liebana wenbediew alehuleshe alat
  Bezer temeketo wenebediew zerefat
  Edeme zelalemun keto layenorebat
  Yalefewun reseto kelayem ketachim denaqurtmolabat

  ReplyDelete
 13. ጥሩ ዜና ነው። አዲስ አበባ ቢያንስ ከሙስና ትጸዳለች

  ReplyDelete
 14. እውነቱን ለማገር መጋቢ ብሉይ አእመረ አሸብርን የመሰለ ሊቅ ቤተ ክርስቲያን የላትም እግዚአብሔር ያሳድግህ ከክፉዎች ያውጣህ አንተንና መሰሎችህን ለማጥፋት የሞዶሉቱ ብዙ ናችሁ፣ በአጠቃላይ ሰበካ ጉባኤ ባቀረብከው ቃለ ጉባኤ አእመረ ማቅ ሆነ እንዴ ተብሎ ተወርቶ ነበር አንተ ግን ለጥፋት ቡድነኞች እና ከሰሜን ሸዋ በስተቀር ጎጃሜ፣ ትግሬ፣ ወሎና ጎንደሬ ሰው የማይመስላቸው ማቆችን እንደማትመስል እስከ ሞት እንመሰክርልሃለን

  ReplyDelete
 15. ምን አልክ ወዳጄ " አዲስ አበባ ቢያንስ ከሙስና ትጸዳለች" የማታውቀውን ባትናገር ጥሩ ነው! የማነ ዘመንፈስ ሌላው ቀርቶ ቦሌ መድኃኔ ዓለም በፀሐፊነት ለመመለስ ያወጣውን የጉቦ መጠን እስከሚመልስ በሙስና መዘፈቅ አይደለም ሊዋኝ ሁሉ እንደሚችል እየተነገረ መሆኑን አልሰማህም!!!

  ReplyDelete
 16. እኔን የገረመኝና የደነቀኝ ነገር በዘረኞች አስተሳሰብና እይታ ውስጥ አቡነ ተክለሀይማኖት በሸዋ ተወላጅነታቸው ተካትተው መዘለፋቸው። አረ እናንተ እፈሩ። እሳቸው አኮ በሸዋ(በጽላሊሽ) ተወስነው የቀሩ ሳይሆኑ አለማቀፋዊ እና ሰማያዊ ጻድቅ ናቸው። ልክ ከክብራቸው ያወረዳችኋቸው መስሎአችሁ እግዚአብሔር ያከበራቸውን(ካከበራቸው ስንት መቶ አመታት ያስቆጠሩትን) ጻድቅ ከክብር ለማሳነስ እየጣራችሁ ነው። ግን ምንም እንደማታመጡ ይታወቃል። ደብረሊባኖስንም እንዲሁ ታነሳላችሁ። አንኮበሮችና አንኮበርም እንዲሁ በተደጋጋሚ ይሰደባሉ። እናንተ ኢትዮጵያውያን ከሆናችሁና በቅን አስተሳሰብ እምታስቡ ከሆነ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ከሆናችሁ። ወይም የታሪክ፣ የሀይማኖትና የዘር ጥላቻ አራማጆች ባትሆኑ ኖሮ እንኳን እነዚህን ቦታዎችንና ባለታሪኮችን ልትዘልፉና ልታንቋሽሹ ቀርቶ ከታሪካቸው ብዙ ነገር ለመማር በጣራችሁ ነበር። ግን አቡነ ተክለሀይማኖት በተሠጣቸው ቃልኪዳን ትውልድን ሁሉ(የተሠጣቸውን ቃል ኪዳን የተቀበለ) ሲያማልዱ ይኖራሉ። ሸዋዎች(አንኮበሮች)ያሉፉት ታሪካቸው ሲወሳ ለእድገትና በራስ ለመተማመን መሰረት ሲሆን የኖራል። ምክንያቱም ጀግንነታቸውን ማንም በማይክደው ሁኔታ አስመስክረዋልና። እናንተ መካድ ትችላላችሁለ። ታሪክንና የቅዱንን ቃልኪዳን አንቀበልም ያለ ትውልድ፣ ምንም ቢነግሩት አጣሞ ከመረዳት በቀር ስለማይቀበል ምን ይደረጋል። ሸዋዎች እና ሸዋ እንደሆነ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦረቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት የቁርጥ ቀን ልጆችና አገር ናቸው። እንዴት? ታሪክን መመርመር!!!! መህበረ ቅዱሳንም በውስጡ ያሉ ችግሮችን በመፍታት ተስተካክሎ የአንዲቷ ቅድስት ተዋህዶ ሀይማኖት አውነተኛ መሣሪያ እንደሚሆንና አቡነ ተክለሀይማኖትን፣ የሸዋ ቅዱሳንን፣ ሸዋን(አንኮበርን) እና ባለታሪኮቿን ከማሰደብ እንደሚታረም ምንም ጥርጥር የለንም። የበጠበጠው አንድ አስቸጋሪና ከቤተክርስቲያኗ አካሄድ ጋር የማየሄድ ነገር አለ። እሱን ደግሞ አንደኛ አምላካችን፣ ሁለተኛ አቡነ ማትያስም በእግዚአብሔር እርዳታ እንደሚያስተካክሉት እምነታችን ነው። ይህ ማህበርም የሸዋ ቅዱሳንና ሸዋን እስከመቼ ሲያሰድብ ይኖራል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous march 30,2015 at 1:30am
   ወጣ ወጠና… ነው የተባለው። ወንድሜ ማስመሰሉንና ሳይሆኑ ነኝ ማለቱንማ እነሱም ለጥፋት ተግበራቸው እየተጠቀለሙበት አይደል። አንተስ ከነሱ በምን ተሽለህ ተለይተህ ተገኘህ። እነሱ እኮ ቤተክርስቲያንን የመናፍቃን አዳራሽና የሸቃጮች መራኮቻ ለማድረግ ሲነሱ ቤበክርስቲያኔ እምነቴን አላስነካ ብሎ የእግር እሳት የሆነባቸውን ማህበረ ቅዱሳን፣ እውነተኛ አባቶችን፣ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆነውን የክርስቶስ ወንጌልን የሚያስተምሩት ና አገልግሎት የሚሰጡትን በልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን ማእረጋት ያሉትን አገልጋዮችን፣ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ ዘማርያንና የቤበክርስቲያን እምነትና ስርዓት ይህ እንጂ ፕሮታንቲዝም አይደለም ያሉትን ነው ዕለት ተለት የሚዋጉት፣ በሐሰት የሚወነጅሉት፣ በውሸት የሚከሱ የሚያሙት፣ ካለስም ምግባራቸው ልዩ ልዩ ልቦለድ ፈጠራዎችን እየፈበረኩ ስም ምግባራቸውን የሚያጠለሹትና ትንሽ ትልቅ ሳይሉ በስድብ ናዳ የሚያበሻቅጡትና የሚዘልፉት። ታዲያ አንተስ እውነተኛው የክርስቶስ ትምህርትና የቤተክርስቲያን ስርዓት ይህ ነው ብሎ ጠብቆና አስተምሮ በአባቶች ምክርና መመሪያ እየሰራ፣ የሊቃውንት ምንጭ የቆሎ ትምህርት ቤት እንዳይዘጋና ሊቃውንት ከቤተክርስቲያን አውደምህረት እንዳይታጡ የአብነት ትምህርት ቤት እንዲጠናከርና እንዲስፋፋ የሚሰራ፣ የተጎዱና ያረጁ አድባረታ እንዲጠገኑና እንዲሰሩ ሙያዊና ልዩ ልዩ ድጋፎችንና እርዳታዎችን የሚያደርግ፣ የገጠር አድባራትና አቢያተ ቤተክርስቲያናት በአገልጋይና በንዋየ ቅዱሳት እጦትና ችግሮች እንዳይዘጉና አገልግሎታቸው እንዳይቋረጥ በዚህም የተነሳ ጠላት ሰይጣን የክርስቶስን ህዝብ እንዳይውጥ ለአገልገዮች ደሞዝ ከመክፈል ጀምሮና ንዋየ ቅዱሳት ከማቅረብ አንስቶ ለራሳቸው ገቢ የሚያገኙበትን ስልት እስከመሸየስ በትጋት እየሰራ፣ ወንጌል ላልደረሳቸው ለመድረስ እየተፋጠነና ለቤተክርስቲያን አገልግሎቶች በቅንነት አጋር በመሆንና ለዘርፈ ብዙ ፈተናዎቿ ደራሽ እየሆነ ያለን የቤተክርስቲያን ማህበር የምትተች ከሆነና የምትቃወም ከሆነ ምኑን ከመናፍቆች ተለየኸው። ጭራሽ ደግሞ "ይህ ማህበረ የሚያሰድበው እስከመቼ ነው" የሚል ቂል የሆነ ፍረጃና ከነሱው ከተሳዳቢዎች ጎራ መሆንህን የሚያሳብቅ ድምዳሜ አይሉት ማጠቃለያ ሐሳብ ተብየ ገልፀሃል። ወዳጄ አንተ የማህበሩን ማንነት በሚታየው ማንነቱ ሳይሆን በስሙ የምታውቀ ነው የምትመስለው። አሊያም ደግሞ አንተም ለቤተክርስቲያን መዳከምና ለእምነት ስርዓቷ መጣስ መፍለስ ተግተው ከሚሰሩት ተባባሪዎች በመሆንህ በማህበሩ ላያ የሞኝ ፍረጃ ፈረጅህ። ነገር ግን ያንተ ብያኔ ተቀባይነት ባይኖረውም ክፉ ለመሳደብ በአንድ ወይም በሁለት ነገሮች ብቻ አይወሰንም። ምንም ጽድቅ፤ ምንም እውነት፤ ምንም መልካም ነገር ፤ ምንም ትህትና ክፉውን ለመሳደብ ከመነሳት አያግደውም። ሁሉንም ከማጥላላት፤ አንዱን ካንዱ ለማጋጨት፤ የከበረውን ለማወረድ፤ ነጩን ለማጥቆር ሰይጣን ተንኮል ከማሴርና ከመሳደብ አይቆጠብም። ሐሰተኛ በመሆናቸው እንጂ ይህ ብሎግና ፀሐፊ ተብየዎች እውነት ቢኖራቸው ለስድብና ለትችት ባልበረቱ ነበር። ተሳዳቢነት የጠላት ሰይጣንና ግብር አበሮቹ ነውና እነሱም ከግብር አበሮቹ አንደኛዎቹ በመሆናቸው ይሳደባሉ። ስለሆነም ወንድም እባክህ ማህበሩን በከንቱ ነገር አትፈርጀው። ደህና ሁን።

   Delete
  2. ንኮበር ከመቸ ወዲህ ነው ጀግና የሆነው ማነውስ አንኮበር ጀግና እስኪንገረኝ ለመሆኑ የአንኮ በርን ታሪክ ታውቀዋለህ፡፡ እስኪ ገዚ ውሰድና ትንሽ አንብብ አታጣም፡፡ ከአርጎቦች እና የይፋት፣ ሙስሊሞች ታሪክ በኋላ አሁኑ ታሪኳ የሚጀምረው ከሣህለ ሥላሴ ነው፡፡ ሣህለ ሥላሴ በሴሰኝነቱና በባንዳነቱ ይታወቃል፣ ልጁ ኃይለ መለኮት ያው እንደምታውቀ አኒህ አጼ ቴዎድሮስ እንዴት ተወደዱ የሸዋን ሰው ሁሉ እጅ ነሥተው ሄዱ ተባለው በኃይለ መለኮት ነው ትርጉሙን ትቸዋለሁ ለማንኛውም በቴዎድሮስ ተሸንፈው በድንጋጤ ነው የሞቱት፣ ተተኪው ምኒልክም ያው ወደብ የሌላት፣ አንገቷ የተቆረጠ ሀገር ያስረከበን የአንኮበሩ ምኒልክ ነው፣ በፈሪነቱና በከዳተኛነቱ ይታወቃል፣ የሚገርመው በማያውቀው ሀገር በአድዋ እነ ራስ መንገሻ፣ ራስ ወሌ፣ ራስ አሉላ፣ ራስ ማርዬ፣ እቴጌ ጣይቱ ... በተዋሁ ምኒልክ አድዋ ላይ ጣሊያንን አሸነፈ መባሉ ነው፡፡ እሱም ታሪክ እስኪ ነጋ ዋሽ፣ አጼ ቴዎድሮስ የሌባ እጃችሁን ቆረጡ፣ አጼ ዮሐንስ የሕሊና ጥመታችሁን ቆረጡ፣ አሁን የጠፋው የውሽት ምላሳችሁን የሚቆርጥ ነው፡፡ ከዚያ ጀግናውን ልጅ ኢያሱን በመፈንቅለ መንግሥታ አስወግዳ ዙፋን ላይ ቁብ ያለችው ሌላዋ አንኮበር አቅንቃኝ ተፈሪ ጣሊያን መጣ ሲሏት ሸሽታ እንግሊዝ ሔደች ከዚይ አፍሪካወውያንን ሁሉ ክዳ ከቅኝ ገዥዎች ጋር ተባብራ በጀግባው እንግሊዝ ጦር ድጋፍ አገሯ ገብታ ስንት አርበኛ ፈጀች እሷንም የራሷ አሥር አለቃ ዱብ አደረጋት እውሩ ደርግም ከአንኮበር አይወጣም ያው ሸሽቶ ዚምባቡየየ ነው ያለው እስኪ አንኮበር ጀግና ጀግኖችህን ንገረኝ ለኢትዮጵያ ያመጣችሁትን ዝና አውራኝ፡፡ ታሪክ እስኪነጋ አይታወቅም ብላችሁ ለፍልፉ አንድ ቀን ከንቱ ይሆናል፡፡ አሁንም ሆኗል፡፡
   እስኪ የአንኮበርን ሃይማኖት ንገረኝ የሦስት ልደት አማኝ የተጣመመ እና በኋላ ቦሩ ሜዳ ድራሹ የጠፋ ሃይማኖት እኮ ነው፡
   ምናልባት ስለ አንኮ በር ያወራሀው አንኮ በር የተወላጅ አርጎባዎች በነበረች ጊዜ ከሆነ እነሱ በእስልምና ሃይማኖታቸው፣ እና በንግድ ጽናታቸው ይታወቃሉ ከሣህለ ሥላሴ በፊት፡፡

   Delete
 17. Aba Merkebu Haiku from Atlanta will travel Ethiopia to transfer money for opposition that distablize coming Ethiopian election.

  ReplyDelete
 18. Aba Merkebu is spy agent for mk.

  ReplyDelete
 19. ድንቄም የአንኮበር ጀግና! አንኮበር ዝንጆሮ እንጂ ጀግና የለውም!

  ReplyDelete
 20. Who is Aba Tebate Merkebu

  ReplyDelete
 21. ያ ሁሉ ውሸታም ተጠቅልሎ ለውሸት ይቆማል እንዴ እናንተ ሁላችሁ ተሃድሶን ግብር አበሮቻቸው ናችሁ

  ReplyDelete
 22. ዛቻው ቀኖናን የማስከበር ድንፋታውም ሥርዓትን የማስጠበቅ ነው፡፡ አንተ ዛቻና ድንፋታ ካልካቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታክ ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳንን የመሰለ እጅግ አስከፊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጠላት ተፈጠሮ አያውቅም፡፡ ለመሆኑ እነማን የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ናቸው የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች አንድ ስም ጥራ እኔ ማንነታቸውን እነግርሃለሁ፡፡ ለማያውቅሽ ታጠኝ አሉ፡፡ በመሠረቱ እነ አቶ እናጋልጣለን ማኅበረ ቅዱሻን ናቸው እስኪ እናንተ የምትጠቀሙበትን ማስፈራሪያ ስትሰሙት ምን ይመስላችኋል ብየ ስሞክራችው እውነትም እንደጠበቁት አገኘሁት፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ጠላትነት ልዩ የሚያደርገው በሃይማኖት አስመስሎ የገንዘብ ዘራፊ፣ አገልጋይ አሳዳጅ፣ የርካሽ ዛና ፍርፋሬ ለቃቃሚ፡፡ አቶ የእናጋልጠዋለን ባለቤት የማቅ አንጃ ተከታይ አዎ ልክ ነህ የማኅበረ ቅዱሳን አስመሳይነት፣ ሙሰኛና ዘራፊነት፣ የጥላቻ ምንጭ፣ ከፋፋይ፣ አድመኛና ቡድነኛነት እንደ መዥገር ከቤተ ክርስቲያን ጉያ ተደብቆ ደሟን የሚመጥ፣ ሲሏን የሚያዳክም፣ አስተዳደሯን የሚያጣምም፣ ቀኖናዋን የሚሽር፣ እንደ ድሪቶ በክብር ካባዋ ላይ ተጭኖ ስሟን የሚያክፋፋ፣ በፖለቲካ ምሕዋር ነብዞ መዋቅሯን እያጠፋ ልጆቿን እያሳደደ ያለ እፍኝ መንጋ ሲኖር ለምን አያናድድ፣ በቅንነት ከሰማህ ልንገርህ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ያሉት ከአውደ ምህረቱ፣ ከቤተ መቅደሱ፣ ከቤተ ልሔሙ ነው፣ ከቤተ/ክ አጸድ ከሰንበት ትምህርት ነው እንጅ፣ በቡድን ስሙ ካሠራው አንተ አዳራሽ ካልከው ሕንፃ ውሽጥ አይደለም፣ ባታውቀው ነውእንጅ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ታሪክ ከቤ/ክ አጸድ ውጭ ጉባኤና የአዳራሽ ስብሰባ የጀመረው ማቅ ነው፡፡ እና ማገልገል ከፈለግህ የቤተ ክርስቲያን ደጅ ክፍት ነው፣ ሰበካ ጉባኤ መድረክ ይጣራል በቡድን ጉያ ተደብቀህ በቤ/ክ ስም አትነግድ፣ መናፍቅ ማለት የሚጀምረው ከቀኖና ማፋረስ ሲሆን ከሀዲ ደግሞ ከይሁዳ ነው፣ ማቅ አሁን እንደይሁዳ የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ገና ሙዳይ ምጽዋት ሳይገባ እየዘረፈ ነው፡፡ እና ንቃ ለመዝለፍ ለመሳደብ አትቸኩል አሁንም ከፈለግህ ወቅቱ ይድረስ አንጅ የአንተን ዝነኞች ማንነት በአይንህ ታየዋለህ፡፡

  ReplyDelete
 23. ንኮበር ከመቸ ወዲህ ነው ጀግና የሆነው ማነውስ አንኮበር ጀግና እስኪንገረኝ ለመሆኑ የአንኮ በርን ታሪክ ታውቀዋለህ፡፡ እስኪ ገዚ ውሰድና ትንሽ አንብብ አታጣም፡፡ ከአርጎቦች እና የይፋት፣ ሙስሊሞች ታሪክ በኋላ አሁኑ ታሪኳ የሚጀምረው ከሣህለ ሥላሴ ነው፡፡ ሣህለ ሥላሴ በሴሰኝነቱና በባንዳነቱ ይታወቃል፣ ልጁ ኃይለ መለኮት ያው እንደምታውቀ አኒህ አጼ ቴዎድሮስ እንዴት ተወደዱ የሸዋን ሰው ሁሉ እጅ ነሥተው ሄዱ ተባለው በኃይለ መለኮት ነው ትርጉሙን ትቸዋለሁ ለማንኛውም በቴዎድሮስ ተሸንፈው በድንጋጤ ነው የሞቱት፣ ተተኪው ምኒልክም ያው ወደብ የሌላት፣ አንገቷ የተቆረጠ ሀገር ያስረከበን የአንኮበሩ ምኒልክ ነው፣ በፈሪነቱና በከዳተኛነቱ ይታወቃል፣ የሚገርመው በማያውቀው ሀገር በአድዋ እነ ራስ መንገሻ፣ ራስ ወሌ፣ ራስ አሉላ፣ ራስ ማርዬ፣ እቴጌ ጣይቱ ... በተዋሁ ምኒልክ አድዋ ላይ ጣሊያንን አሸነፈ መባሉ ነው፡፡ እሱም ታሪክ እስኪ ነጋ ዋሽ፣ አጼ ቴዎድሮስ የሌባ እጃችሁን ቆረጡ፣ አጼ ዮሐንስ የሕሊና ጥመታችሁን ቆረጡ፣ አሁን የጠፋው የውሽት ምላሳችሁን የሚቆርጥ ነው፡፡ ከዚያ ጀግናውን ልጅ ኢያሱን በመፈንቅለ መንግሥታ አስወግዳ ዙፋን ላይ ቁብ ያለችው ሌላዋ አንኮበር አቅንቃኝ ተፈሪ ጣሊያን መጣ ሲሏት ሸሽታ እንግሊዝ ሔደች ከዚይ አፍሪካወውያንን ሁሉ ክዳ ከቅኝ ገዥዎች ጋር ተባብራ በጀግባው እንግሊዝ ጦር ድጋፍ አገሯ ገብታ ስንት አርበኛ ፈጀች እሷንም የራሷ አሥር አለቃ ዱብ አደረጋት እውሩ ደርግም ከአንኮበር አይወጣም ያው ሸሽቶ ዚምባቡየየ ነው ያለው እስኪ አንኮበር ጀግና ጀግኖችህን ንገረኝ ለኢትዮጵያ ያመጣችሁትን ዝና አውራኝ፡፡ ታሪክ እስኪነጋ አይታወቅም ብላችሁ ለፍልፉ አንድ ቀን ከንቱ ይሆናል፡፡ አሁንም ሆኗል፡፡
  እስኪ የአንኮበርን ሃይማኖት ንገረኝ የሦስት ልደት አማኝ የተጣመመ እና በኋላ ቦሩ ሜዳ ድራሹ የጠፋ ሃይማኖት እኮ ነው፡
  ምናልባት ስለ አንኮ በር ያወራሀው አንኮ በር የተወላጅ አርጎባዎች በነበረች ጊዜ ከሆነ እነሱ በእስልምና ሃይማኖታቸው፣ እና በንግድ ጽናታቸው ይታወቃሉ ከሣህለ ሥላሴ በፊት፡፡

  ReplyDelete