Tuesday, April 28, 2015

ቤተ ክርስቲያን በአደጋ ክበብ ውስጥ (ክፍል አምስት)

Read in PDF

የመጨረሻ ክፍል
                                          ከዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ
በአለፉት አራት ተከታታይ ጽሁፎች ቤተክርሰቲያንን አስመልከቶ የታዩኝን ችግሮች ከነመፍትሔዎቻቸው የሚጠቁም ጽሁፍ አቅርቤያለሁ። ይህ የመጨረሻው ክፍል ነው። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ። ጊዜው ሳይመሽ እና ዕድል ሳያመልጠን ቤተክርሰቲያናችንን ከከበቧት አደጋዎች እንታደግ።
1.9.      ትላንት በግልጽ ዛሬ ደግሞ “በመንፈስ የግብጻውያን” ተጽዕኖ አለመቅረቱ

     ከአንድ ሺህ አምስት መቶ አመት በላይ ከአንድ መቶ አስራ አንድ አባቶች የማያንሱ ጳጳሳት የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከግብጽ እልፍ አዕላፍ ወርቅ ፣ ዕንቁ ፣ የዝሆን ጥርስ ፣ አልማዝ ፣ የከበረ ድንጋይ ፣ ብር ፣ የተለያዩ ውድ አልባሳትና ሌሎች ብዙ እጅ መንሻዎችንና ገጸ በረከቶችን በማቅረብ (ልዋጭ በመስጠት) ታስመጣ ነበር፡፡ የማስመጣቷ ምክንያት ደግሞ እስከዛሬ ከፍትሐ ነገስታችን ላይ ጉብ ብሎ እስካልተነሳው ስርዋጽ አንቀጽ የተነሳ ነው፤
                     “የኢትዮጲያ ሰዎች ከዐዋቂዎቻቸው ወገን በራሳቸውም ፈቃድ ሊቀ ጳጳሳትን
                        ለራሳቸው አይሹሙ፡፡ ጳጳሳቸው ከእስክንድርያው በዓለ መንበር ሥልጣን በታች
                   ነውና፡፡” ፍትሐ ነገስት.አን.፬ ቁ.፶ (ገጽ.30)
      ይህ አንቀጽ ለምን ይሆን ዛሬስ ከፍትሐ ነገሥቱ ላይ ያልተነሳውና ወደሙዝየም ያልገባው? ነው ወይስ ለዳግመኛ ባርነት ሌላ የሚጠብቀው ትውልድ አለ? በጣም የሚያሳዝነው ሌላው ታሪክ ደግሞ በአንድ ወቅት ኢትዮጲያውያን ጳጳስ ይሾምልን ብለው ግብጻዊውን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤልን እነአጼ ሐርቤ ስለጠየቁ “ንጉሡ ኢትዮጲያውያን ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ በመጠየቁ እግዚአብሔር ተቆጥቶ በአገሩ በኢትዮጲያ ላይ መቅሰፍት አወረደ” ይላል በሚያዝያ ፲ ቀን የሚነበበው “ስንክሳራችን”፡፡ እንዴት በገዛ እጃችን በራሳችን ላይ ተሳልቀናል?! እንዴት ባለ ትብታብና ድንዛዜ ነው የተያዝነው?  
    ከግብጽ ከሚመጡት ጳጳሳት ከእጅግ በጣም በጣም ጥቂቶቹ በቀር አብዛኛዎቹ  እንደ“አቡነ” ዳንኤል ያሉት ገንዘብ አፍቃሪዎች ፣ እንደ“አቡነ” ሳዊሮስ ያሉት መስጊድ የሚያሠሩ የሙስሊም ኢማሞች … ሌሎቹ ደግሞ አመንዝሮችና ቅጥ ያጡ ጥቅመኞች ነበሩ፡፡ ሌሎቹ  እንደአቡነ ሚካኤል ያሉት ደግሞ ከእርጅና የተነሳ ምንም መሥራት የማይቻላቸው ነበሩ፡፡ (የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ፤ አባ ጎርጎርዮስ (M.A) ፤ 1991 3ኛ ዕትም ፤ አዲስ አበባ ፤ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ ገጽ.34-35)
   የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ትላንት “ከጠቀመችን ጥቅም” ይልቅ በጉዳት ያጠቃችን ጥቃት እጅግ ይበልጣል፡፡ በታሪካችንና በአምልኮአችን ውስጥ ረጅም እጇን ሰድዳ ወደአሻት አቅጣጫ ስትመራን ኖራለች ማለት ይቻላል፡፡ የኢትዮጲያ ቤተ ክርስቲያን በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የደረሰባትን በደል አባ ጎርጎርዮስ ሲያስረዱ፦
       
“ … በነዚህ አያሌ አመታት ውስጥ ውስጥ ለመላው ኢትዮጲያ ሚላከው አንድ ጳጳስ ብቻ ነበር ፤ እሱውም የሕዝቡን ቋንቋ ስለማያውቅ ለማስተማርም ሆነ ለማስተዳደር በስማ በለው ነበር፡፡ የሚቀመጠውም ንጉሡ ባለበት ቦታ በከተማ ብቻ ስለነበር ፤ በገጠሩ የሚኖረው ሕዝብ ቤተ  ክርስቲያኑ እንዳይዘጋበት ሕጻናቱን በጀርባው አዝሎ በትከሻው ተሸክሞ ጳጳሱ ወዳለበት የወር የሁለት ወር ጐዳና ተጉዞ ይመጣል፡፡ ከዚያም ገንዘቡን ከፍሎ ካኑልኝ ሲል ጳጳሱ ገንዘቡን ተቀብሎ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ ዕድሜው ለክህነት ሳይደርስ ፤ ለክህነት የሚያበቃ ሙያ ሳይኖረው እየካነ ይልከዋል፡፡ ልጁም ተክኖ በቂ ትምህርት ሳያገኝ በቤተ ክርስቲያን በድምጫ የሰማውን ብቻ ይዞ … ያገልግላል፡፡” (ገጽ.75)

Friday, April 24, 2015

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር የሥራ አስኪያጅ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ለውጥ ከተደረገ በኋላ ተስፋ ሰጪ ጅምሮች እየታዩ ነው


በሙስና የተዘፈቀውና በርካታ አገልጋዮችን በግፍ ሲጨቁንና ሲበዘብዝ የነበረው አማሳኙ የነቀሲስ በላይ አስተዳደር ከተሻረና ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ እና መጋቤ ብሉይ አአመረ አሸብር ከተሾሙ ወዲህ ጥሩ ጅምሮች እየታዩ መሆኑን እያስተዋልን ነው፡፡ ኃላፊዎቹ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በመልካም ጀማሮ የጀመሩት መሆኑ በርካታ ግፉዓንን አስደስቷል፡፡ የሥራቸው መጀመሪያ ያደረጉትም የተበላሸውን የማስተካከል እና ፍትሕ ያጣውንና የተበደለውን በተገቢው መንገድ መካስ መሆኑ ቀደም ብሎ የነበረውን ልቅሶና ጩኸት በተወሰነ መልኩ ወደ ደስታ ለውጦታል፡፡ በቀሲስ በላይ ሥራአስኪያጅነት ዘመን 80 የሚደርሱ የታገዱ፣ ሕገወጥ ዝውውር የተካሄደባቸውጉዳያቸው በእንጥልጥል ላይ የነበረ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ መካከል አብዛኛው ጉዳያቸው መፍትሔ አግኝቷል፡፡ ይህን በጎ ጅምርና ሥራ አስኪያና ምክትላቸው እየወሰዱት ያለውን አዎንታዊ እርምጃ የተገፉ ብዙዎች በአድናቆት እየተመለከቱት መሆኑን መናገር እንችላለን፡፡ በአንጻሩ ለማድነቅ መቸኮል አያስፈልግም ጊዜው ገና ነውና ፍጻሜያቸውን አይቶ ነው ማመስገን የሚሉም አልጠፉም፡፡ ይሁን እንጂሰዎች መልካም ሲሰሩ ማመስገን ሲያጠፉ ደግሞ መውቀስና እንዲስተካከሉ ማድረግ ነው እንጂ፣ ምስጋናውንም ሆነ ወቀሳውን በጊዜ መገደብ ተገቢ አለመሆኑን ለአዳዲሶቹ ኃላፊዎች አድናቆት እየቸርን ያለን እናምንበታለን፡፡
በእነዚያ ወገኖች መከራከሪያ መሠረት አድናቆታችንም ሆነ ወቀሳችን በምክንያት ላይ የተደገፈ ካልሆነ ግን የክፉዎች ስብስብ ከሆነው ከማኅበረ ቅዱሳን የአድናቆትና የወቀሳ መንገድ አልወጣንም ማለት ነው፤ ምክንያቱም ማኅበረ ቅዱሳን ዘርና ጐሣ እየመረጠ የሚያደንቅና ዘር እየለየ ስም የሚያጠፋ ነውና፡፡ ለምሳሌ ያህል አባ ወልደ ገብርኤል የተባሉ የትግራይ ተወላጅ መነኩሴ በ1998 ዓ.ም. ቆባቸውን ጣሉ፤ ትግራይ አባ ወ/ገብርኤልን ብቻ የወለደች ይመስል በየጋዜጣውና በአራት ኪሎ በሚገኙት ምግብ ቤቶች በሙሉ ፖስተር ሲለጥፍ፣ በየጋዜጣው ሲፅፍና ሲሳደብ መኖሩ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ የሚኖሩት ጳጳስ አባ ኤዎስጣቴዎስ ግን ጳጳስ ሆነው በዓለም የሚኖር ሰው እንኳን የማያደርገውን ከሁለት እህትማማች ጋር ግንኙነት እንደነበራቸውና በአሁኑ ጊዜ ቆባቸውን ጥለው ትዳር መስርተው የሚገኙ ሰው መሆናቸውን በተመለከተ አንድም ቀን ትንፍሽ አለማለቱ ከፈጸማቸው ታሪካዊ ስህተቶች አንድ ትልቅ ትዝብትና ማሳያ ሆኗል፡፡ ስለዚህ እኛን ከዚህ እኩይ ማህበር የሚለየን አንዱ ነጥብ ሰው መመስገን ያለበት በመልካም ሥራው ነው፤ መወቀስ ያለበትም በክፉ ሥራው ነው እንጂ በሌላ መስፈርት ሊሆን አይገባም ማለታችን ነው፡፡ አበው እንደሚሉት መልካሙን መልካም ማለት ትክክለኛ አስተሳሰብ ነው፤ ክፉውን መልካም ማለት ደግሞ አጋንንታዊ ነው፡፡ ስለሆነም ገና ያለጉቦ በተገቢው መንገድ ለድኾችና ለግፉዓን በተሰጠው ፍትሕ ከጅምሩ ስለተሠራው መልካም ነገር አድናቆታችንን መግለጽና በርቱ ከጎናችሁ ነን ማለት እንወዳለን፡፡

Wednesday, April 22, 2015

“ጌታ ሆይ፥ በISIS ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው”


 Read in PDF
ምንጭ፡-የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
በድጋሚ በግፈኛው ISIS ለተሰው ክርስቲያን ኤርትራውያን ፣ ኢራቃውያን ቤተሰቦች ጌታ መንፈስ ቅዱስ መጽናናትን እንዲያድላቸው ብርቱ ጸሎታችን ነው!!!
    የአንዲት ሕያው ቤተ ክርስቲያን ልዩና የሁል ጊዜ መገለጫ፥ “የእግዚአብሔርን ቃል ለሁሉ በማዳረስ ማስፋትዋና የደቀ መዛሙርትን ቁጥርና እጅግ የሚታዘዙትንም ማብዛቷ ነው፡፡” (ሐዋ.6፥7) የባለበት ሂድ ወይም የእየቀጨጩ ዕድገት ጤናማነቱ ተፈጥሮዐዊም ፤ መንፈሳዊም አይደለም፡፡ በብዛትም በጥራትም ማደግ የጤናማ ተፈጥሮዐዊና መንፈሳዊ ዕድገት መገለጫ ነው፡፡ ወንጌሉ ሕያው ነውና ተበትኖ ፤ ተሰብኮ እንደዋዛ አይቀርም ፤ ሕያው ፍሬንም ያፈራል እንጂ፡፡

     ክርስትና ገና ጉዞውን በጀመረበት ቀደምት ጊዜያት፥ በአንድ የስብከት ርዕስና በአንድ ብርቱ ተአምራት ስምንት ሺህ የሚጠጉ አማኞች ወደአንድ መቶ ሐያው የጌታ ቤተሰብ ተጨመሩ፡፡ ሥራውን ሠሪው መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ የቁጥሩ አጨማመር ከመደመርም ከብዜትም ይልቃል፡፡ እኛ የቀደምንበት አገልግሎት ጠላትን አለጊዜው ያጎለምሳል ፤ ጌታ የቀደመበት አገልግሎት ግን ጠላት ተኩላ እያለ ሥራውን ያሠራል፡፡(ማቴ.10፥16)

     ክርስትና ገና ከኢየሩሳሌም ሳይወጣ ፤ ያመኑት የመጀመርያው ወደስምንት ሺህ የሚጠጉ ክርስቲያኖች በአንድነት ተቀምጠው ሳሉ እስጢፋኖስ በስምንት ሺህ አማኞች ላይ አሳላፊ ሆኖ እያገለገለ ባለበት ወራት፥ “የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤” (ሐዋ.6፥9)
      ጌታን በአድመኝነት አሳልፈው የሰጡት እኒያው ሰዎችና መሪዎች ዛሬም በእስጢፋኖስ ላይ ተነሳሱበት፡፡ ተኩላው ይጮኻል ፤ ያደባል ፤ በጎቹም ተኩላዎቹ ባሉበት ዓለም ይሠማራሉ፡፡ ለጌታ ያልራሩ ገዳዮች እንዲሁ ለእስጢፋኖስ ስስ አንጀት የላቸውም፡፡ “እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር። … ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም።” (ሐዋ.6፥8 ፤ 10) 

Tuesday, April 21, 2015

የልቅሶና የዋይታ ድምፅ በደቡብ አፍሪካ፣ በየመን፣ በሊቢያ ምድር ተሰማ፡- እናት ኢትዮጵያም ስለ ልጆቿ አለቀሰች የሉምና!!በዲ/ን ተረፈ ወርቁ  nikodimos.wise7@gmail.com

‹‹. . . ዓይኔ በእንባ ደከመ፣ አንጀቴም ታወከ፡፡ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ አንጀቴ በምድር ላይ ተዘረገፈ፡፡ አቤቱ የሆነብንን አስብ፣ ተመልከት ስድባችንንም እይ . . .፡፡››  ሰቆ. ፪፣፲፩ ፤ ፭፣፩ ፡፡

ይህን ቃል የተናገረው በመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ዘንድ ‹‹አልቃሻው፣ ባለ ሙሾው ነቢይ›› በመባል የሚታወቀው አይሁዳዊው ነቢዩ ኤርምያስ ነው፡፡ ይህንን ነቢይ እንዲህ እንደ ርኁሩኋ እናት አንጀቱን ያላወሰው፣ እንባው እንደ ክረምት ጎርፍ እንዲፈስ ያደረገውና ነፍሱ ድረስ ዘልቆ ብርቱ ኀዘንና ቅጥቃጤን የፈጠረበት ምክንያቱም፡- ኢየሩሳሌም በጠላቶቿ ተማርካ፣ ሕዝቦቿም ተዋርደው፣ ከአገራቸውና ከምድረ ርስታቸው ተነቅለው፣ ያ እጅጉን ያከብሩትና ይፈሩት የነበረው መቅደሳቸው ፈርሶ፣ በግዞት ውስጥ የነበሩትን የሕዝቡን ሰቆቃና መከራ በዓይኑ በማየትና የመከራቸውም ተካፋይ መሆኑ ነበር፡፡፡
ጸሎተኛውና ኀዘንተኛው ኤርምያስ ስለ ኢየሩሳሌም ኃጢአትና በደል በዚህም ስለደረሰባት ከባድ ውርደትና መከራ ዓይኔ ምነው የእንባ ምንጮች ፈሳሽ በሆኑልኝ በማለት የተመኘ፣ በብርቱ የጸለየ፣ የተማጸነና የማለደ የሀገሩ፣ የሕዝቡ ውርደትና ጭንቀት፣ መከራና አበሳ፣ ሰቆቃና ዋይታ እንቅልፍ፣ እረፍት የነሳው ብርቱ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር፡፡

ከራብ የተነሳ እናቶች የአብራካቸውን ክፋይ ልጆቻቸውን የበሉበትን፣ በቅምጥልነት የኖሩ የኢየሩሳሌም ቆነጃጅትና ደናግል በጠላቶቻቸው ብርቱና ጨካኝ ክንድ ከሰውነት ክብር ተዋርደው፣ ከመፈራትና ከመወደድ የክብር ሰገነት ላይ ተሸቀንጥረው፣ ተንቀውና ተጥለው በጎዳና ያለ ምንም ተሰፋ ሲንከራተቱና የሁሉም መጫወቻና ማላገጫ ሲሆኑ፣ ሕፃናት በእናቶቻቸው ደረቅ ጡት ላይ አፋቸው ተጣብቆ በጣእረ ሞት ተይዘው ሲጨነቁ፣ አባቶችና እናቶች የጥንቱን የበረከትና የድሎት ኑሮአቸውን እያሰቡ እንባ ሲቀድማቸው፣ ከክፉ ጠኔ የተነሳ ወላዶች የማኅፀናቸውን ፍሬ እንኳን ለመብላት ያስጨከናቸውን ያን ክፉ ቀናት የታዘበ ነቢዩ ስለ ቅድስት ምድሩና ሕዝቡ ሰቆቃና መከራ እንዲህ ጸለየ፡፡
 ‹‹እግዚአብሔር ከሰማይ እስኪጎበኝና እስኪመለከት ድረስ ዓይኔ ሳታቋርጥ ዝም ሳትል እንባን ታፈሳለች፡፡›› ሰቆ ፫፣፵፱፣፶፡፡ በማለት በመጮኽና በመቃተት ሰለ አገሩ ውርደት ስለ ሕዝቡ መከራ ሌት ተቀን በእንባ ባሕር እንደዋኘ ውሎ የሚያድር ኀዘንተኛና ሙሾ የሚደረድር ነቢይ ነበር አይሁዳዊው የእግዚአብሔር ሰው ኤርምያስ፡፡

Monday, April 20, 2015

አዝነናል

Read in PDF

አይሲስ የተባለ የሰይጣን ደቀ መዝሙር ክርስቲያን ወንድሞቻችንን ክርስቲያን መሆናቸውን ብቻ እንደ ትልቅ ወንጀል ቆጥሮ ዘግናኝ በሆነ መልኩ ገድሏል። እንኳን  በወገን ላይ እንኳን በወንድም ላይ በእንስሳ ላይ እንኳን ሲፈጸም ማየቱ የሚዘገንንን ደርጊት በወንድሞቻችን ላይ ፈጽሟል። ይህ የክፉ መንፈስ አንጋሽና የሀሰተኛው ክርስቶስ እንደራሴ የሆነው ጽንፈኛ ድርጅት ለልባችን ስብራትን ትቶ አልፏል። የማኅበራዊ ሚዲያዎች በዚህ ጉዳይ በሰፊው ዘግበዋል። በርካታ ኢትዮጵያዊያንም የልባቸውን ስብራት በተለያየ መንገድ ገልጸዋል። ነገሩ ልብ የሚያደማ እንቅልፍም የሚነሳ ነው። ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ ሳያባራ የዚህኛው መከሰት ሀዘኑን ከባድ አድርጎታል።

 ለኢትዮጵያውያን ሳምንቱ ጥቁር ሳምንት ነው። ሀዘኑ ጥልቅ ቢሆንም በአይሲስ ታጣቂዎች እጅ ሰማዕት የሆኑት ወገኖቻችን እምነታቸውን አንክድም ብለው መሞታቸውን ማወቅ ደግሞ ደስ ያሰኛል። በዚህም ዘመን ለእውነት አንገት መስጠት መቻል መታደል ነው። በኢየሱስ ስም የምንቀበለው መከራ ለክብር ነው። ሞታችንም የድል አክሊል ነው። 

Saturday, April 18, 2015

አዲሱ ገበያ የሚገኘው ደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን በአለቃው እየታመሰ ነውበአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙ የደብር አለቆች አብያተ ክርስቲያናትን የሚመሩ እንደመሆናቸው መጠን ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ይህን ኃላፊነታቸውን የሚወጡ አለቆች መኖራቸው ባይካድም ሥልጣናቸውን ለተለያየ የግል ጥቅም በማዋል ብልሹ አስተዳደርን ያሰፈኑ፣ የቤተክርስቲያንን ሀብትና ንብረት የሚዘርፉ፣ ለዚህም እንዲረዳቸው ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ማበርና የማኅበሩ ወዳጅ በመሆን ከተጠያቂነት ውጪ የሚሆኑ፣ ማቅም ታማኝ ወዳጆቹ አድርጎ የሚቆጥራቸው አለቆች አሉ፡፡ እንደእነዚህ ያሉትን አለቆች ማቅ ማሳኝ-አማሳኝ መሆናቸውን ቢያውቅም ስለእነርሱ “በጎነት” እንጂ ማሳኝ-አማሳኝነት ከቶም ቢሆን ማውራት አይፈልግም፡፡ እነርሱም በቤተክርስቲያን ያሻቸውን እያደረጉ ስለሚገኙና ጥፋታቸውን ማቅ በዝምታም ቢሆን ስለሚሸፍንላቸው እነርሱም በበኩላቸው ለማቅ ውለታ ብድራት ይሆን ዘንድ በየደብሩ ያሉ የማቅ ወኪሎች “እገሌ ተሐድሶ ነውና እርምጃ ይወሰድበት” ብለው “ብላክሊስታቸው” ላይ የከሰሱትን አገልጋይ ሲጠቁሟቸው በዚያ አገልጋይ ላይ ሥልጣናቸውን መከታ በማድረግ ልዩ ልዩ ሕገወጥ ድርጊት እየፈጸሙባቸው እንደሚገኙ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ እንዲህ እያደረጉ ከሚገኙ አለቆች መካከል አንዱ የደብረሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስታየን አስተዳዳሪ አንዱ ናቸው፡፡
እኚህ ሰው አስቀድሞ የገነተ ጽጌ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሙዳየ ምጻት አዟሪ ባለትዳርና የልጆች አባት የነበሩ ሲሆን፣ በምን ምክንያትና የት እንደ መነኮሱ ሳይታወቅ መንኩሰው አለቃ ሆነው ተመለሱ፡፡ አለቃ ሆነው በሰሩበት በጃቲ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን በፈጸሙት ውንብድና ተባረው ለ4 ወር ያህል ያለ ሥራ ቆይተዋል፡፡ አሁንም ጳጳሱን አባ ሳሙኤልን ተገን በማድረግ በደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ውስጥ ልዩ ልዩ የውንብድና ሥራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ከሚጠቀሱት መካከል
·        ከኃላፊነታቸው ከተነሡት ከሊቀ አእላፍ በላይ ጋር በመመሳጠር ከሰራተኞች ገንዘብ እየተቀበሉ ሕገወጥ ቅጥርና ዕድገት መፈጸም፣ ለዚህም ገንዘብ ተቀብለውናል ሲሉ አባ ቤዛ የሺዓለም ከአሳራጊነት ወደ ሰባኪነት፣ እንዲሁም አባ ተክሌም በተመሳሳይ ሰባኪ ሆኛለሁ በማለት “ጉዳ” ለተባለ በቤተክርስቲያን ገንዘብ ቤቱን እየገነባ ላለ የልማት ኮሚቴ አባል መናገራቸው ታውቋል፡፡ “ጉዳ” የሚባለው የህንፃው እቃ ግዢ ያለምንም የደብሩ ፈቃድ እቃ ይገዛል፤ አጂፕ አካባቢ ትልቅ ህንፃ የገነባ ሲሆን፣ የእህቱ ባል ዲ/ን ይድነቃቸው ደግሞ የህንፃ ኮሚቴ ተከፋይ ነው፡፡ 

Monday, April 13, 2015

የአባ ሳሙኤል ለቤተክርስቲያን አስተዳደር መጨነቅ - “ጅብ በማያውቁት አገር ቁርበት አንጥፉልኝ አለ” የሚለውን ብሂል የሚያስታውስ ነው


ከስምዓ ጽድቅ ኮነ
 ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ አባ ሳሙኤል በቅርቡ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ስለቤተክርስቲያን አስተዳደር አቀረቡት የተባለውና ሐራ “public lecture” የሚል ማጎላመሻ የሠጠው የእርሳቸው ይሁን ከሌላው የተጫኑትና በስማቸው ያቀረቡት የመነሻ ሐሳቡ ዜና ነው፡፡ (እንዲህ የምለው አባ ሳሙኤል በስማቸው ያሳተሟቸው አንዳንድ መጻሕፍት የእርሳቸው ሥራዎች እንዳልሆኑና ሌሎችን አጽፈው በስማቸው እንደሚያሳትሙት የሚናገሩ ስላሉ ነው፡፡ እንዲህ የሚያሰኘው አንዱ ነገርም አንዳንዱ ጽሑፍ የአንድ ሰው ወጥ ሥራ የማይመስልና እንደ ተማሪ የልመና እንጀራ ውጥንቅጥ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ ለምሳሌ “ፈለገ አሚን ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” የተሰኘው “መጽሐፋቸው” ማኅበረ ቅዱሳን ስለ ተሐድሶ ግንዛቤ ማስጨበጫ ብሎ ከዚህ ቀደም ካዘጋጀው ጽሑፍ የተወሰደ ሲሆን እርሳቸው ግን ምንጩን በተገቢው መንገድ አለመጥቀሳቸው ሳያንስ ስለተሐድሶ የተጻፈውን ጉዳይ በትምህርተ ሃይማኖት ውስጥ የነገረ ድኅነት ትምህርት በሚለው ምዕራፍ ውስጥ ነው የደነጎሩት፡፡ ሆኖም ይህ ነገረ መለኮታዊ አቀራረብ አይደለምና የአባ ሳሙኤልን የትምህርት ይዞታ የሚናገር በቂ ማስረጃ ይመስለኛል)፡፡

ዜናው እንደጠቆመው አባ ሳሙኤል ያቀረቡት የመነሻ ሐሳብ ለ/ሲኖዶስ አባላት የተላለፈ ጥሪ መሆኑን ሐራ ዘግቧል፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩን በቀጥታ ለሲኖዶስ ለምን አላቀረቡትም? ለምንስ ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ማኅበረሰብእና ለማቅ ወዳጆቻቸው ማቅረብ ፈለጉ? ለምንስ እስካሁን ዝም ብለው በዚህ ወቅት ማቅረብ ፈለጉ? የሚለው አጠያያቂ ጉዳይ ነው፡፡ የማቅ ብሎግ ሐራ ለሲኖዶስ የቀረበ የመነሻ ሐሣብ መሆኑን የዜናው ርእስ አድርጎ ለምን አወጣው? የሚለውም እንዲሁ ያጠያይቃል፡፡ ለማንኛውም ስለ አባ ሳሙኤል ማንነትና የእስካሁን ተግባር ከብዙ በጥቂቱ ለማቅረብ ፈልጌያለሁ፡፡ ይህን የማደርገው የአባ ሳሙኤል ማንነት አቀረቡ የተባለውን የመነሻ ሐሳብ ለማቅረብ በተለይ ከሞራል አንጻር ብቁ አለመሆናቸውን ለማሳየት ነው፡፡  

Saturday, April 11, 2015

የጻፍሁትን ጽፌአለሁ !           Read in PDF      
   ‘‘የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ’’    ዮሐ 19፡22
                                                                                ቀሲስ ጋይዮስ
   ጲላጦስ የይሁዳ አውራጃን ያስተዳድር የነበረ ሮማዊ ገዥ  ሲሆን   በስልጣን ዘመኑ ከተመለከታቸው ጉዳዮች እና ከአስቻላቸው ችሎቶች የኢየሱስ ጉዳይ የሚመስል እና ለመወሰን  የተቸገረበት ዘመን የለም። የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ   በመስቀል ላይ መሞት በዓለም   ከታዩት የፍርድ መጉደል ሁሉ የበለጠ ነው። አንድ ሰው በመስቀል ተስቅሎ  ከመሞቱ በፊት መገረፍ እንዳለበት የሮማውያን ህግ ይናገራል። ግርፉቱ በጣም አደገኛ በመሆኑ  በግርፉቱ ብቻ  ብዙ ሰው ሞቷልምክንያቱም መግረፊያው የሚሰራው ከቆዳ ሲሆን በጫፉ ላይ ብረታ ብረት፡አጥንት ወይም ሹል ነገር ይቋጠርበታል። ወንጅለኛ የተባለው ሰው ሲገርፍ እነዚያ ሁሉ ነገሮች በጀርባው ላይ ያርፉሉ፡ ከዚህ በኋላ ጉዳቱ የባሰ ሰለሆነ ሥጋው በማለቅ  አጥንቱ ከዚያም አልፎ ውሳጣዊ የሰውነት ክፍሎች  ይታያሉ።ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ  ሲገረፍ   ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ ደርሰውበታል። ጲላጦስ ብዙ ይተገረፈውን   ስጋው አልቆ አጥንቱ የታየውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚገባውን  ቅጣት ስለተቀበለ በነፃ ለማሰናበት በማለት በህዝቡ ፊት አቀረበው(ሉቃ 2316_22) አይሁድ ግን በደም የተሸፈነውን የኢየሱስን አካል በማየት ቅንጣት ያህል አላዘኑለትም፡ይልቁንም ምራቅ እየተፉ  በጥፊ ይመቱት ነበር(ማቴ 2727_31)።ኢየሱስ  እኛን ሰለሚወደን ይህን ሁሉ ታግሷል።

ጲላጦስ ጌታ ኢየሱስን  ነፃ ለማድረግ  ብዙ መንገዶችን ሞክሯል እንዲለቁት ብሎ አስገርፎታል፡እናንተ አልፈለጋችሁት  ግሪክ ሂዶ ያስተምር ብሎቸዋል፡ በየአመቱ የፉሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ  ኢየሱስን ከአደገኛው ወንበዴ ከበርባን ጋር ለምርጫ አቅርቧል። አይሁድ ግን ልባቸው በክፋት ስለ ተያዘ ኢየሱስ እንዳይፈታ በኃይል ይጮሁ ነበር፡የምትፈታው በርባንን ነው አሉ(ዮሐ18: 40) ኸቱ ሁሉ  ወንበዴን ፈቶ ንጹሑን   ለመግደል ነው ጲላጦስ ሮምን  ሕግ ማስፈጸም ተሳነው ህጕ ወንጅል የሌለበትን አይቀጣምና። ጲላጦስ አንድ ንጹሕ መግደል ነው ያለበት? ወይስ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ውሸተኞችን መስማት?  በነገሩ ግራ ተግብቶ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ምን  ላድረገው (ማቴ 2722)  ሲላቸው  አይሁድም በአንድነት ስቀለው ስቀለው አሉ።  ጲላጦስ ግን አንዳች በደል አላገኘሁበትም   እናንተ ስቀሉት ሲላቸው እኛ ህግ አለን  እንደ ህጋችን ሊሞት ይገባዋል ብለው  ወዲያዉኑ ኢየሱሰን ለመስቀል ወንጅል ያሉትንእራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝብሏል በማለት ነገሩን ከሮም ህግ  ወደ እግዚአብሔር ህግ ቀየሩት( ዮሐ198_11)    ጲላጦስ  ውሳኔ ግን ጌታን መልቀቅ ነበር