Wednesday, April 1, 2015

ጆሮ ጭው የሚያደርግ ክፉ ወሬ: የአሸናፊ መኮንን ጉዳይ(ዘንድሮ በተለየ ሁኔታ ስለግብረ ሰዶማዊነት ዘግበናል፡፡ የችግሩ አሳሳቢነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በዛሬው ዕለት እንኳ ሪፖርተር ጋዜጣ ሻሸመኔ ላይ በግብረ ሰዶማዊነት ተከሶ ስለታሰረ አንድ የጣሊያን ዜግነት ስላለው ነጭ አስነብቦናል፡፡ በየሚዲያው ይህ ጉዳይ የእለት ከዕለት መነጋገሪያ እየሆነ ነው። ምን እንደምንል ግራ እስኪገባን ድረስ በቤተክርስቲያን ጭምር ግብረ ሰዶማዊነትን የሚመለከቱ ወሬዎችንና ግብረሰዶማዊ ስለሆኑ ሾልኮ ገብ አገልጋዮች መስማት እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ዓለሙም ወደ ጥፋት እየተጓዘ ከሄደ ሰነበተ፡፡ በአሜሪካና በአውሮፓ ያሉ “አብያተ ክርስቲያናት” ግብረ ሰዶማዊያንን ማጋባት ጀምረዋል፡፡ ያሳዝናል። ነገሩን በዝምታ ማለፍ ችግሩ እንዲባባስ በር ከመክፈት ተለይቶ አይታይም። በወንጌል አገልግሎት ዙሪያ የግብረ ሰዶማዊያን አገልጋዮች ጉዳይ መነጋገሪያ ከሆነ ሰነበተ፡፡ ይባስ ብሎ የሌባ አይነ ደረቅ አይነቶቹ ደግሞ እንደ መብት ኢየሱስንም ግብረ ሰዶማዊነትንም አጥብቀን እንይዛለን እያሉን ነው። የማይሆን ነገር የማይሆን ነው። የማንቀበለውም ነገር የማንቀበለው ነው። ስለዚህ የግብረሰዶምን ኃጢአት ከማውገዝ አንቦዝንም፡፡
ይህ ጽሁፍ የደረሰን በኢሜይል አድራሻችን ነው። ዜናውን አስቀድመን ስለምናውቀው ከአንዳንድ ማስተካከያዎች ጋር ልናወጣው ወድደናል፡፡ አባ ሰላማ በዚህ ጉዳይ ላይ ጽሁፉን ከጻፈው ሰው የተለየ አቋም የላትም፡፡ መልካም ንባብ፡፡)
ግብረ ሰዶማዊነት ዛሬ ሳይሆን ጥንቱኑ የተወገዘ ነው፡፡ ለሰዶምና ገሞራ ህዝብ መጥፊያ የሆነዉም ሀጢአት በስማቸው መጠሪያ ሆኖ የቀረና በተፈጥሮ የሌለ የረከሰ ተግባር ነው፡፡ በዘመናችንም እንደ መልካም ነገር ተቆጥሮ በአደባባይ በምዕራቡ ዓለምና በሌሎች ሥልጡን ነን ባዮች አገራት እንደ ሁነኛ ተግባር ባልተለመደ ሁኔታ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ በአገራችን እንኳ በዚህ የቆሸሸ ተግባር ውስጥ የተሰማሩ መርገምቶች በስውርና በግልጽ አንዳንድ ተግባራት እየፈጸሙ እንደ ሆነ ይታወቃል፡፡ ይባስ ብሎ ቤተ ክርስቲያን ደጅ እንኳን እንደደረሰ በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡ በጽድቅ ቃል ልንዋጋው የሚገባ ዘመነኛ የእውነት ጠላት ነው፡፡
ውድ አንባቢዎቻችን ይህን ዜና ስናስነብብ ከታላቅ ሐዘንና ቁጭት ጋር እንደሆነ ልናሳስብ እንወዳለን፡፡  ኀጢሃትን መቃወም ተገቢ ስለ ሆነና ከክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ነቀፌታን ማስወገድ ብሎም መታደስ ለሁሉም ስለሆነ ይህ ግድ ብሎን ከወትሮው በተለየ አሳዛኝ ዜና ልናስነብባችው ወደድን፡፡ ይልቁን ደግሞ በትእቢትና በኩራት መንፈስ ንስሓ ከመግባት ይልቅ መሰናከያ ሆኖ በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ላይ መርገምን የሚጨምር ተግባር ውስጥ መገኘት በግድ ሊወገዝ የሚገባው ተግባር ነው፡፡ ሌሎችን ለመታደግና ለእግዚአብሔር ጽድቅ ሲባል የጨለማ ሥራን ግለጡት እንዲል መጽሃፍ /ኤፌ. 511/ በውስጥ ያለዉን ማድፈንፈን ይልቅ ከብዙ ተጨባጭ መረጃዎች ጋር እውነቱን በማገናዘብ ለብዙሃን ጠያቂዎችና ግራ ለተጋቡ እውነታውን ወደ ብርሃን ብለናል፡፡ ከዚህ አንጻር የብርሃን ልጆችን ተቀላቅለው በጨለማ ከሚጓዙ የአመጻ ልጆች መካከል የአንዱን ግብረ ሰዶማዊ ማንነት በዝርዝር እናቀርባለን፡፡ ይህ ሰው አሸናፊ መኮንን ይባላል፡፡
አሸናፊ መኮንን በብዙሓኑ ዘንድ የሚታወቀው በብዙ ስነ ምግባርና ሕይወት ነክ በሆኑ ጽሑፎቹ ነው፡፡ በብዙዎቻችን ልብ ውስጥ ትልቅ ሥፍራይዞ የነበረና እደግ ተመንደግ ያልነው፤ በተለያየ ጊዜ በልዩ ልዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ በተለይ የእግዚአብሄር ትእግስት፣ የሚለውጥ ፍቅር፣ ምክር ለወዳጅ የሚባሉ እና ሌሎች መጻሕፍትን የጻፈ ሰው ነው፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት በርሱ ዙሪያ ለሰሚ ጆሮ ጭው የሚያደርግ ወሬ ይሰማ ጀመር፤ ይህም አሸናፊ ግብረ ሰዶማዊ ነው፣ ይህን ተግባር የሚያበረታታ ሁኔታ ይታይበታል የሚል ነበር፡፡ ከዛም ጥቃት ደርሶብናል የሚሉ ሌሎች አካላትን እናውቃለን የሚሉ ሰዎች ብቅ ብቅ ማለትን ጨምሮ በትምህርቱ ምንኩስናን በማበረታታት ውስጥ ጋብቻን ይነቅፋል፣ ላገባ ነው ብሎ ለምክር አገልግሎት ወደ እሱ ጋር የሚሄዱ አገልጋዮችን ከማበረታታት ይልቅ ትዳር ምንያደርግልሃል፡፡ ምን ያደርግልሃል? እያለ ያጣጥላል። “ሰዎች እኮ የሚጋቡት የት ነህ? የት ነሽ? ለመባባል ነው አሁን ይሄ ምን ያደርጋል? በራስ ላይ እስራት ማወጅ አይደለም?...” እያለ በስብከት ጭምር ጋብቻን ያንቋሽሻል፡፡ ተጣልተው አስታርቀን በማለት ወደ እርሱ ጋር የሚሄዱ ባለትዳሮችንና እጮኛሞችን ከማስታረቅ ይልቅ ምክንያት እየፈለገ መንፈሳዊ የሚመስል ቋንቋ ተጠቅሞ ያለያያል። በየምክንያቱ እጮኛሞችን ያለያያል። እጮኛ የያዙ የጉባኤው አባሎችን እንዲለያዩ ያበረታታል። ለሴት ልጅ ያለው ጥላቻ እንኳን ከአንድ የወንጌል አገልጋይ ከአንድ ትልቅ የስነ ምግባር ችግር ካለበት ሰው እንኳ የከፋ ነው፤ ከአንዳንድ በግብረ ሰዶማዊነት ከሚታሙ መነኮሳት ጋር ያዘወትራል እና በዚህ ልክፍት የተጠቁ ሰዎች የሚታይባቸው ጠባይ ሁሉ በግልጽ ይታይበታል ከሚሉ እውነታዎች በመነሳት የግብረ ሰዶማዊነቱ ወሬ ተጠናክሮ ቀጠለ። ከዛ በኋላ ግን አረ ይሄ ሰው ግብረ ሰዶማዊ ነው እኔ ላይም እኮ ሙከራ አድርጎብኛል የሚሉ ሰዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። 
ይህ ወሬ ወሬ ከመሆን አልፎ በተጨባጭ መነጋገሪያ መሆኑን ያወቀው አሸናፊ መኮንንም አስቀድሞ የመከላከል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ጀመረ። እንቅስቃሴውም “…ጉባኤው መንፈሳዊነት ይጎድለዋል አንተም ጌታን ረስተሃል። መንፈሳዊነት ርቆሀል ከክርስቶስ ይልቅ ራስህን መስበክ ጀምረሃል። ስለዚህ ተመለስ ተስተካከልም..አብረንህ የቆምነው ለእግዚአብሔር መንግስት ሥራ ነው አንጂ ለግለሰብ አምልኮ አይደለም።…” ብለው በጉባኤው አስተዳደራዊና መንፈሳዊ ችግሮች ዙሪያ ጥያቄ ያነሱበትን ሰዎች በተመለከተገንዘብ ካለመጣህ ብለው ስሜን እያጠፉ ነው”  ብሎ ማውራትና ማስወራት ላይ እና ወደነዚህ ሰዎች ደግሞ “ገንዘብ እንስጣችሁና እሱን መቃመም አቁሙ፡፡” በማለት የሚያባብሉ ሰዎችን መላክ ላይ ያተኮረ ነበር። የዚህን ልክፍት የሆነ ሃጢአት ወሬ የሰሙ አንዳንዶች ነገሩን በስውር በመያዝ ችግሩ ካለ እርሱን ከዚህ ለማውጣት ወይም ደግሞ በሐሰት ስሙን ለማጥፋት የተደረገ ሙከራ ሊሆን ይችላል በማለት ልዩ ልዩ የማጣራት ሥራዎችን እየሰሩ ብዙ ጥረትና መንፈሳዊ ተጋድሎዎች ሲያደርጉ ቆዩ፡፡
ቀናት እያስቆጠረም ሲሄድ ወሬው እውነት ነው? አይደለም? በሚል ሙግት ላይ እየተሽከረከረ ባለበት ሁኔታ አሸናፊ ለዓመታት የቆየ የግብረ ሰዶማዊነት ልምምድ አለው ለዚህም እኛ ምስክሮች ነን ተጠቅተናልም።የሚሉ ሰዎች ብቅ አሉ።
ይህ ነገርም የወሬውን አቅጣጫ ለውጦ በተለይም ረዥም ጊዜ እሱን የሚያውቁ ሰዎች ቀጥታ እሱን ለማነጋገር እና ለተከሰተው ኃጢአት መንፈሳዊ መፍትሔ ለማበጀት እንቅስቃሴ ማድረግ ይጀምራሉ። ይህ እንቅስቃሴም ጥቃት ደረሰብን የሚሉ ሰዎችን ጨምሮ መካሄድ ጀመረ። ከዛ በኃላም እርሱን በግልጽ በማግኘት በችግሩ ዙሪያ መነጋገር ይጀመራል። ምንም እንኳ የተለያየ እንቅፋቶችን በሂደቱ ላይ ለመፍጠር ቢሞክርም በስተመጨረሻ ግንማሩኝማለት በመጀመሩና ነገሩ በዚህ ደረጃ ተገልጾ መውጣቱ አስደንግጦት እውነተኛ የንስሐ በሚመስል ስሜት ከእንባ ጋር ለመመለስና ንስሃ ለመግባት እና የንስሀን ፍሬን ለማፍራት ቃል በመግባቱ ጥቃቱ የደረሰባቸውን ሰዎች ጨምሮ እሱን ያነጋገሩ ሰዎችና ጉዳዩን የሰሙ ጥቂት ሰዎች ዘንድ የመመለሱና ንስሀ የመጋቱ ሀሳብ ደስታን ፈጠረ።
እነዚህ ሰዎች ቀጥሎ ያደረጉት ነገር ወሬውን አስቀድሞ ከሰሙ ሰዎች ውጭ ለሌሎች ሰዎች እንዳይደርስ መስማማትና የግድ ጉዳዩን ማወቅ ከሚገባቸው ሶስት የአገልግሎቱ የቦርድ አባላት ውጭ ማንም እንዳይሰማ ማድረግ ነበር። የቦርድ አባላቱም እንዲሰሙ ያስፈለገበት ምክንያት አሸናፊ ለችግሩ ለሚሰጠው መንፈሳዊ መፍትሔ ፍጹም ትብብርን ማሳየት ስለጀመረ እና መፍትሔውም ፍጹም ንስሀን ጾም ጸሎትን እና የስነ ልቦና እርዳታን የጨመረ ስለነበር ነው። በዚህም አግባብ ከተኬደ ከችግሩ ነጻ ለመውጣት እስከ አንድ ዓመት ጊዜ ሊፈጅ ስለሚችል፤ በዛ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከአገልግሎት ርቆ በፍጹም ንስሐ ለመቆየት ስለተስማማ የአገልግሎቱ ሥራ አስኪያጅነቱን ቦታ በጊዜያዊነት ሌላ ሰው ሊተካው ስለሚገባ ነበር።
ነገሩ ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ በንስሀ መንፈስ መጓዝ ከጀመረ በኋላ ግን አሸናፊ አገልግሎት ለተወሰነ ጊዜ ማቆም የሚለው ነገር አልዋጥልህ እያለው መቸገር ጀመረ። እንዲያውም የንስሓ ፍሬን እስክታሳይ ድረስ አገልግሎት ማቆምህ አግባብ ያለው መንፈሳዊ መንገድ ነው ብለው የንስሓውን ሂደት ከጠቆሙት ሰዎች መካከል አንዳንዶቹን “ንስሓዬ አገልግሎቴን ሳላቋርጥ ቢሆንስ?” የሚል ጥያቄን እንዲጠይቅ አስገደደው፡፡ የተሰጠው መልስ ግን ለእሱም እውነተኛ ንስሓ ለአገልግሎቱም ጤናማነት የሚሻለው አገልግሎቱን አቁሞ ንስሓ መግባቱ እና በሌሎች ወንድሞችና እህቶች ዘንድ የጽሞና ጊዜ ላይ ነው ብሎ ማስወራት እንደሚቻል የተጠቆመበት ነበር፡፡ እሱ ግን ከጽድቅ ይልቅ ክብሩን ስለሚወድና ይህም ልቡን ለሁለት ከፍሎበት በችግሩ ዙሪያ የሰዎችን ስነ ልቦና መፈተን ጀመረ።በፊት እኔ አገልግያችኋለሁ አሁን ደግሞ እናንተ እኔን አገልግሉኝ።በማለት እያለቀሰማሩኝስላለቸው ንስሓ የመግባት ተነሳሽነቱን በቅን ልብ የተቀበሉትን ጥቃት ያደረሰባቸው ሰዎችንና ነገሩን  ያወቁ ሌሎች ሰዎችን ለመከፋፈልና እርስ በእርስ ለማጣላት በመካከላቸው ክፉ ወሬን ለመዝራትም ተነሳሳ። ግን አልያዘለትም። ጎን ለጎንም ለኔ ታማኝ ናቸው የሚላቸውን ሰዎች ሥነ ልቦና የመስረቅ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመረ። ይህም በአንድ ቀን ኃጢአቱን  ከሚያውቁ ሰዎች ጋር በስልክ ስለንስሐው አፈጻጸም እያወራ ለሌሎች ደግሞ እነ እከሌ ስሜን እያጠፉት ነው  በሚል ኃጢአቱን የመሸፈን  እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመረ። ይህን መቼም ህሊናው በኃጢአት ከደነዘዘበትና ከሞተበት ሰው በቀር ሌላ ሰው በቀላሉ ሊያደርገው አይችልም። እንዲህ ያደረገው የሰዎችን ንስሀ መግባት እና መመለስ የማይወድን የዲያቢሎስን ምክር ለመስማት ልቡን ስለከፈተ ነበር።
የእግዚአብሔር ቃል በሰዶማዊነት ውስጥ ያሉ ሰዎችን ለማይረባ አእምሮ ተላልፈው የተሰጡ ስለሚላቸው ተላልፎ የመሰጠትን ትርጉም ያሳየ ድርጊትና እንቅስቃሴ ነበር። እንቅስቃሴው ነገሩ ከጥቂቶች እጅ ወጥቶ በቅርብ ርቀት ወደሚያውቁት ወገኖች እንዲደርስ አደረገው። ለዚህ ደግሞ የመጀመሪያ ተጠያቂዎቹ ራሱ አሸናፊ እና በዙሪያው ያሉ “ብታደርግስ ምናለበት…አይዞህ” ባዮቹ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ቀድመን እኛ ብናወራው ነገሩ ወደሌሎች ይዞራል ስም ማጥፋትም ሆኖ ይቀራል በሚል የተሳሳተ ስሌት በአሸናፊ ጉባኤ ላይ ለሚመጡ ሰዎች በቡድን በቡድን እየጠሩ “የእርሱ ስም እንዲህ እየተባለ እየጠፋ ነውና እንዲህ ያለ ወሬ ብትሰሙ ስም ማጥፋት መሆኑን እወቁ እንዲህ የሚያደርጉት ደግሞ በአሹ የቀኑ እነእንትና ናቸው” ብለው ለማስተባበል በመሞከራቸው ወሬውን ባርከው አደባባይ ላይ አሰጡት፡፡ ይህ በወቅቱ ንስሐ ለመግባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ለሚያውቁና ለተግባራዊነቱም እየረዱት ለነበሩ ሰዎች ትልቅ ሀዘን ነበር። ከጉባኤው አባላትም እነ እገሌ አወሩት ከሚል ወሬ በቀር አንድም እንኳ እነ እገሌ ነገሩኝ የሚል አይገኝም፡፡ “ሰይጣን ጥሎ ጣሉት ይላል” የሚባለው በእንዲህ ያለ ጊዜ ነው፡፡
ወሬው የአዳባባይ ምሥጢር ከመሆኑ በፊት ለእርሱ ቅርብ የሆኑ ወንድሞችና እህቶች በንስሓ እርሱን ለማቅናት ጥረት በማድረግ እርሱም ራሱ በዚህ ክፉ ወሬ ላይ የማያዳግም ማስተካከያ ሰጥቶ ከዚህ ዐይነት ነቀርሳ ሓጢአት በታላቅ ንስሓ ራሱን በእግዚአብሔር ፊት እንዲያዋርድ ብዙ ምክክሮች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ ወሬው የአደባባይ ሚሥጢር ከሆነም በኋላ ይህ ጥረት አልተቋረጠም ነበር። እሱ ግን የንስሀውን እና የመመለሱን መንገድ አብሮዋቸው የጀመረ ሰዎችን ስልክ ማንሳት አቆመ።ደጋፊ ካገኘሁ እማ የምን ንስሐ ነው?” በሚል ስጋዊ ስሌት “…ስሜን እያጠፉ…” የሚለውን ወሬ ከአዲስ አበባ እስከ አሜሪካ እና ሌሎችም ሀገራት ተግቶ ማዳረሱን ተያያዘው። ለዚህ ተግባር ባደራጃቸው በአንዳንድ በገንዘብ የተገዙ ሸቃዮች አማካኝነት በአራት ኪሎ አካባቢ በስፋት የመከላከል ወሬውን ማስወራት ጀመረ። ነገሩን ምንም ቢሆን አይተዉትም ለጠየቃቸውም ሰው እውነቱን ከመናገር አይመለሱም የሚላቸው ሰዎች ላይም በስፋት ስም የማጥፋት ወሬ ከማስወራት አልፎ በቴክስት የማሰደብና ዱሪዬ ገዝቶ የማስፈራራትና የማስደብደብ ሙከራንም ማድረግ ጀመረ። ይህ ለችግሩ በአሸናፊ በኩል የተሄደበት ሥጋዊ መፍትሔ እንጂ መንፈሳዊ መፍትሔ አልነበረም። ስለዚህ የእግዚአብሔር መንፈስ ሊያግዘውና ሊደግፈው አልቻለም። ይልቁንም ይህንን ጉዳይ በተረዱ የወንጌል አገልጋዮች ዘንድ ግርምትን የፈጠረ እናለካ ጌታን የማያውቁ የጌታ አገልጋዮች ነን ባዮችን ነውና ይዘን እየተንቀሳቀስን የነበርነውያሰኘ ነበር።
ይህም ሆኖ ግን ብዙ ወገኖች ይመለሳል ከጌታ ጋር ይታረቃል በሚል ተስፋ ቀን ከሌሊት ከዚህ ውርደት እንዲላቀቅ በእርሱ ፈንታ ንስሓ ሲገቡ፣ ሲያለቅሱ፣ ሲጾሙ፣ ሲጸልዩ ቢቆዩም በርሱ በኩል ይህን ተግባር ከቁም ነገር ሊቆጥረው አልቻለም፡፡ ይህም በጣም አሳዛኝ ክስተት ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ነገሩ በስውር ተይዞ እርሱን ወደ ንስሓ ለማቅረብ ጥረት መደረጉ አልቆመም ነበር። ሁኔታዎች ተስፋ የሚያስቆርጡ ሲመስሉም በልዩ ልዩ ብሎጎች ላይ  ማንነታቸው በማይታወቁ ሰዎች አስተያየቶች መውጣት ጀመሩ፤ እርሱን ለማግባባትና ይህን የጋራ ውርደት፣ አሳፋሪና በሰውም በእግዚአብሔር ፊት የተጣለ ተግባር አሽቀንጥሮ እንዲጥል ጥረት ቢደረግም በአሸናፊ በኩል ግን ብልጠት በተሞላበት መልኩ አንዱ ጋር ንስሓ የገባ ማስመሰል አንዱ ጋር ይቅርታ መጠየቅ፣ ሲያመች እነ እገሌ ስሜን አጠፉ እና መሰል ክፉ የሆኑ አጋንንታዊ መደንደን ውስጥ ገብቶ ክፋቱን ከእለት ወደ እለት እየገፋበት ሄደ፡፡ ይባስ ብሎ በጥቂት ወንድሞች መካከል ሊቋጭ የሚችለውን ችግር ከሌሎች ለርሱ የዘላለም ሞትና ጨለማ ከሚያዘጋጁለት ባልቴቶችና ከሃይማኖት ከራቁ ልበ ቢሶች ጋር ሳይቀድሙኝ ልቅደማቸው በሚመስል አልባሌ ምክር ተነድቶ ራሱን ለከንቱነት አጨ። አንዳንድ ግራና ቀኛቸውን መለየት የማይችሉ ሰዎች የውሸት ስለባ ሆነው እስከዛሬ የዚህ እንቆቅልሽ አጃቢና የወሬው ተከላካይ አጋፋሪ ሆነዋል፤ ይህኔ ያለምንም መሸማቀቅ ከአሸናፊ ክብር የእግዚአብሔር ጽድቅ ይበልጣል ስለ ኃጢአቱ ንስሓ ሊገባ ይገባል ያሉ ወንድሞችና እህቶች በአንዳንዶች ግብዝነት በተመላበት ሁኔታ በተቀናቃኝነት ተፈርጀዋል፡፡ እውነታው ግን ይህ አይደለም።
እውነቱ ግን  አሸናፊ አሁን ባላንጣ አድርጎ ስማቸውን ከሚያጠፋው ወንድሞች መካከል ባላንጣ ሊሆነው የሚችል ሰው ከዚህ በፊት ለመኖሩ ምንም ማመሳከሪያ ማግኘት ያስቸግራል፡፡ ከዚያ ይልቅ በወንድሞች መካከል በቀላሉ ተቀባይነት ያገኘ ብዙዎችም የርሱን ስራ ባክብሮት የሚመለከቱና በበጎ ዐይን የሚታይ ግለሰብ ነበር፡፡ ግብረ ሰዶማዊነትን እንጂ አሸናፊን እንደ ግለሰብ በጥላቻ አይን በሚመለከት ሁኔታ የተንቀሳቀሰ ሰው የለም።
ግብረ ሰዶማዊነት ክፉ አጋንንታዊ ሕይወት መሆኑን ካለመረዳት ነገሩን እንደ ዋዛ እንዲታይ የሚፈልጉ ግለሰቦች አልታጡም፡፡ ይህ ለርሱ እምነቱ ሊሆን ይችል ይሆናል ማን አውቆ፤ እምነት አድርጎ እንደ አንዳንድ የምዕራብ አገራት ሃይማኖት መሪ ነኝ ባዮች  ለመደገፍ  ከልቡ ካለ እንደ ዋዛ ሊታይ አይችልም፤ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሲታዩም አሁንም ደግ አደረኩ የሚል ይመስላል፡፡ ነገር ግን በክርስትና አስተሳሰብ ፈጽሞ የተወገዘ የተጠላ አጋንታዊ ትምህርትና ሕይወት ነው፡፡
ከላይ ሂደቱን ለመግለጽ እንደተሞከረው አንዳንዶች በርሱ ጎራ በመሰለፍ ይህን አጸያፊ ነገር በንስሓ እንዲያርም ከማገዝ ይልቅ የልብ ልብ ተሰምቶት እንዲቀጥል አስተዋጽዖ አድርገዋል። በአንጻሩ ደግሞ በርሱ ፈንታ ሌሎች ለዚ አሳፋሪ ተግባርና ሕይወት በንስሓ በአምላክ ፊት ሲማልሉ ቆይተዋል፡፡ በቀዳሚነት ከእርሱ ጋር ቆሞ በመንፈሳዊ እገዛ እርሱን ለማቅናት የተወሰዱት ርምጃዎች ሁሉ ከሽፈዋል፤ ግብረ ሰዶማዊያንን ከዚህ ሕይወት በመታደግ ይበል የሚያሰኝ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉት ዶክተር ስዩም አንቶኒዎስ ጋር ተይዞለት የነበረው ቀጠሮ በሱ አቋም መቀየርና በቀጠሮው ቀን ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያት ተሰርዟል። አሸናፊ አሁን የሚገኝበት ሚኒስትሪም በጠቅላላ ጉባኤና በቦርድ ሊወስዱ የሚገባቸው ማስተካከያ ርምጃዎች ለመውሰድ ሳይታደል ቀርቷል፡፡  ተገቢ ምክክር አድርጎ መፍትሔ የማዘጋጀት ሙከራው በአንዳንድ አውቆ አጥፊዎች ተሰነካክሎ  ያለውጤት ቀርቷል፡፡ የማህበሩ አባላት የሆኑ ወገኖች ለችግሩ መንፈሳዊ መፍትሔ ለመስጠት ያደረጉት ጥረት ሁሉ ስላልተሳካ ለሚኒስትሪያቸው ፈቃድ ለሰጠው አካል ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በጻፉት ሕጋዊ ደብዳቤ ራሳቸውን አግለዋል፡፡ ሌሎችም ራሳቸውን ከዚህ ማህበር አቅበዋል፤ ይህ ሁሉ ሲደረግ በአሸናፊ በኩል የተወሰደ ርምጃ የለም፤ ይልቁን ከነግብረ ሰዶማዊነቱ እስካሁን ቀጥሏል፡፡ የቀድሞዎቹ አባላት በዚህ መንገድ ራሳቸውን ቢያገሉም የእርሱ ተባባሪ የሆኑትን አንዳንድ የቀድሞ አባላቱንና አዳዲሶችን ይዞ በዚህ አስነዋሪ ኃጢአት ውስጥ የተነከረውንአገልግሎትቀጥሏል፡፡
የሚገርመው ነገር ግብረ ሰዶማዊነቱ ሳይታወቅ ከጓደኞቻቸው ጋር ያለያያቸውን ሰዎች አሁን እየጠራ በአስቸኳይ ተጋቡ ማለት ጀምሯል። ከወንዶች ይልቅ ሴቶችን ለማቅረብ ሙከራ እያደረገ ነው። ንስሀ ይገባ ዘንድ ጥረት ካደረጉ ሰዎች ሁሉ ጋር ተቆራርጦ ቀርቷል። ተው ያለውን ሰው ሁሉ ስልክ አያነሳም ማግኘትም አይፈልግም።
ይህን ጽሁፍ በዚህ ብሎግ ላይ ለማውጣት ስንወስን ለሰው ቸር ወሬ እንደሚያወራ ሰው ሆነን አይደለም። ነገር ግን ከወንጌል አገልግሎት አላማዎች አንዱ በራስም ያለውን ስህተት ማጥራት መሆኑን ስለምናምን ነው። በዚህ አገልግሎት ተስፋ ከተጣለባቸው ወንድሞች መካከል አንዱ አሸናፊ መኮንን ነበር።  በርካታ የወንጌልን አላማ የሚደግፉ ሰዎችም ለእሱ ያላቸው ክብር የተለየ ነበር። ግን ከጽድቅ መንገድ ከወጣ ደግሞ ማንም  ቢሆን ሊቆረጥ እንደሚችል ከአሸናፊ የተሻለ ማስረጃ ልናቀርብ አንችልም። የተጀመረው የመንፈሳዊ ለውጥ  አገልግሎት የማመቻመች አገልግሎት አይደለም። ከኃጢአት ጋር ተስማምተን የምንኖርበትም ነገር አይደለም። ኃጢአትን ኃጢአት ብለን ጽድቅን ተሸክመን ልንጓዝ ግድ ነው። ለተመቻመቸ ጉዞ ከግለሰብ ይልቅ ከማኅበራት ጋር ማመቻመች ይቀል ነበር። ለክርስቶስ ጽድቅ ከጨከንን ጽድቁ የሚጠይቀንን ግዴታም ማሟላት ይገባናል።
አሸናፊን ለማዳን ለአንድ ዓመት ያህል ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል። በችግሩ ውስጥ ስለመውደቁ ከበቂ በላይ የሆኑ በርካታ ማስረጃዎች ቢኖሩም እንኳ የሚቀድመው ወንድምን መታደግ ስለሆነ እርሱን ለመርዳት እና ከዚህ ችግር ለማላቀቅ ከፍተኛ ጥረቶች ተደርገዋል። ከመንፈስ ቅዱስ ምክርና ወቀሳ የተለየው ይህ ወንድም ግን የራሱን አጥር አጥሮ ከመቀመጥ ባለፈ የእግዚአብሔርን ሀሳብ እሺ በማለት ለመታዘዝ አልፈቀደም። ስህተት ነው ካልክ ምን ያስፈራሃል በግልጽ ተናገር ሲባልም እኔ የምላችሁን ተቀበሉ እንጂ ከማንም ሰው ጋር አትገናኙ አታገናኙኝም ሲል ሽሽትን መርጧል። በአንጻሩ ሰዶማዊ ነው የሚሉ ሰዎችበማንኛውም ቦታ በየትኛውም ሁኔታ የተባልኩት ነገር ስህተት ነው ለማለት ከፈለገ ልናዳምጠው ዝግጁ ነን። እኛ እውነት ለመሆኑ ከራሱ እምነት ጀምሮ በቂ ማስረጃ ስላለን ነው እንጂ እሱን ለማጥፋት ፈልገን አይደለም የሚሉናቸው። ማንም ባለ አእምሮ እንደሚገነዘበው ውሸት ነው ካለ ሰዎችን ለማግኘት ምን ያስፈራዋል? ከዛ አልፎም ተከታዮቹን ሁሉ ነገሩን የሚያምኑበትን ሰዎች እንዳያገኙና ሰላም እንዳይሉም ከልክሏል። የሌባ አይነ ደረቅ.. እንደሚባለው ነው።
በዚህ ሰዓት ይህን ጹሁፍ ለማስነበብ የተገደድነው ትክከለኛ መረጃ ከማጣት አንዳንዶች የተዛባ መልእክት ሲተላለፍላቸው ማየታችን፣ በአሸናፊ በኩል አሁንም ምንም ማስተካከያ አለመደረጉ፣ ውሸትና የተዛባ ስራ አሁንም እየሰራ በመገኘቱና በግብረ ሰዶማዊነት ላይ የጸና ተቃውሞ እንዲደረግ በማሰብ ይልቁንም ደግሞ ኃጢሃትን አንደጽድቅ በመቁጠር የረከሰ ነገር በተቀደሰ አገልግሎት ውስጥ መደበቅና መሸፈን ስለማይቻል ነው፡፡ ለሰው የሚበልጠው ነገር ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት ነው። የተጠራነው ሰውን ደስ ለሚያሰኝ አገልግሎት ራስን ልናጭ አይደለም። ለክርስቶስ መንግስት ጽድቅን ትቶ ሊሰራ የሚችል ሥራ የለም። ጳውሎስ ዴማስ የአለሙን ነገር ወዶ ትቶኛል ሲል ዴማስን ለማጋለጥ ፈልጎ አይደለም። ለጽድቅ ያልተበጀን ሰው ለጽድቅ ሥራ መናፈቅ ከንቱ መሆኑን ለማሳየት ነው። ለዚህ ወንድምም እግዚአብሔር ለንስሓ የሚያተጋውን ወቃሽ መንፈስ እንዲሰጠው እንጸልያለን። የጌታ የሆኑ ሁሉም በጸሎታቸው እንዲያስቡትና ከአመጻ ሥራው ተከፋይ እንዳይሆኑ ለማስገንዘብ እንወዳለን።

44 comments:

 1. betam asdengtogal!!!ejig ymakebrew sew neber .lemenfawi meshafochu yalegim endihu........wedet lihid manin limen ?ke man gar hibret ladirg?kiburu ye sew lig endet yihn yimertal?tefetro enkuwan zer lemasketel tekarani sotan sitimert ,sew gin endet?tilant yesew lig erasun yemiyastegabet bota yelwm nege degmo yesew lig erasu aynorim!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ድሮም ከመናፍቅ ጋር መሆን ሲዖል መግባት ነውና የተለየ ነገር አልመጣብህም.... የተሐድሶ መናፍቃን የመጨረሻ ግብ እኮ ይህ ነው አታውቅም ኖሯልን ...ሞኝ አትሁን ንቃ የሚከተለውን አንብብ...
   http://eotcmk.org/site/-mainmenu-24/--mainmenu-26/2059-2016-01-06-tehadeso-amelekote-seyetane

   Delete
 2. አሸናፊ መኮንን የምትሉት ወንድማችሁ ጸባዩ እንደጻፋችሁት አይነት ከሆነ ስምኦን መሰሪይን ነው ማለት ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. hahahahahahahahahahahahahhahahahhahahaha

   Delete
 3. Yegermal get yerdaw

  ReplyDelete
 4. If indeed true, totally flabbergasted!

  ReplyDelete
 5. Who is Ashenafi ???

  ReplyDelete
 6. It is very hard to trust the above accusation because the writer didn't support his accusation with evidences. Probably, false accusations. ' I said probably.' only Lord Jesus knows about him! I hope he is not gay , he is straight.

  ReplyDelete
 7. ከዝንብ ማር ይጠበቃል እንዴ ድሩሰ ከተሃድሶ መናፍቅ እችን ፈልጎ አይደል እናንተጋ የመጣው ትውልዶን ለማጥፋት የተነሳቹህ ሰለሆነ አባ ሰላማዎች እግዚአብሔር የገሰፃቹ

  ReplyDelete
 8. ኦላ ኦላ ኦላ ይላሉ እስፓኒሾች

  ReplyDelete
 9. the one who stand and far from church the result is ...

  ReplyDelete
 10. መናፍቃን መጨረሻቸው ይሄ መሆኑን አወሮፓውያን አሳይተዋል፡፡ የርኩስ መንፈስ ልጆቻቸውም በአፍሪካ ይህንን ይከተላሉ፡፡ አሸናፊ ችግር አለበት ብላ ቤተ ክርስቲያን ስታወግዝ እናንተ ጠበቆቹ ነበራችሁ፡፡ አሸናፊም እውነተኛ ክርስቲያን ስለሆ “ማኅበረ ቅዱሳን ዲ/ን አሸናፊን ለመክሰስና ለማስወገዝ የተንቀሳቀሰው በዋናነት የእርሱ መጻሕፍቱ በቤተክርስቲያን ውስጥ በስፋት በመነበባቸውና ለብዙዎች የመንፈስ እረፍትንና እርካታን በማምጣታቸው ቀንቶና ተመቅኝቶ እንደሆነ ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡ ዲ/ን አሸናፊ እስካሁን የጻፋቸውን 16 መጻሕፍት በግንቦት 2003 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ገሪማ ፊርማ ለሊቃውንት ጉባኤ በተጻፈ ደብዳቤ የሊቃውንት ጉባኤው ለሥራ እንዲጠቀምባቸው መመሪያ ተላልፎ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው“ ብላችሁ ቅዱስ ሲኖዶስን ተሳደባችሁ ማኅበረ ቅዱሳንንም የስድብ ናዳ አወረዳችሁበት፡፡
  “በሕገ ወጥ መንገድ ውግዘት ያስተላለፈው ሲኖዶስ ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ ማውገዙና ሕግ ማፍረሱ ሳያንስ፣ በመግለጫው መጨረሻ ላይ የተወገዙት ይቅርታ ከጠየቁ ቤተክርስቲያን በሯ ክፍት ነው ማለቱ የተወገዙትን ወገኖች በእጅጉ እንዳሳዘነ እየተነገረ ነው፡፡” በማለት ለቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ለመስጠትም ፈልጋችሁ ነበር፡፡
  ይሄው ዛሬእዉነቱ ታወቀና አገር ያወቀውን ጸሃይ የሞከውን ዉነታ ለመደበቅ አልቻላችሁም፡፡ ግብረ ሰዶማዊ የጻፋቸውን መጽሃፍ እያሞካሻችሁ አሁንም እንድናነብ ትጋብዙናላችሁ፡፡ እኛ ዕድሜ ሰጥቶን እናያለን፡፡ እንናተ ዛሬ አሸናፊን ለመውቀስ በሌላችሁ መንፈሳዊነት እየተሯሯጣችሁ ነው፡፡ ለመሆኑ ከአሸናፊ በምን ትለያላችሁ፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት የገባው በፕሮቴስታንት ነው፡፡ ሃገራችንን የውርደት ካባ አለበሳችኋት፡፡ ከእናንተ ጋር……. እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ፡፡ ኢትዮጵያን ህይወት አልባ አደረጋችኋ!!!!!
  አሸናፊ አንቀጸ ብርሃን የሚባል ማኅበር አላውቅም ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስን ዋሸ፡፡ እናንተ ደግሞ ሥራ አስኪያጅ እንደሆነ መሠከራችሁበት:: እግዚአብሔርን ሊያውቁት ባለወደዱ ቁጥር እዕምሮን ለማይገባ ነገር አሳልፎ እንደሚሰጥ አያችሁት? እናንተም ካልተመለሳችሁ ነገ በዚህ ግብረሰዶማዊነት የሚያውቃችሁ ሁሉ አደባባይ ወጣዋል፡፡
  ቤተ ክርስቲያን አሁንም አትጠላችሁም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም አትመለሱ አላለም፡፡ ነገር ግን የምትመለሱት ልታስተምሩ ሳይሆን የበደላችኋትን ቤተ ክርስቲያን ይቅርታ ብላችሁ እድሜያችሁን በንስሃ እንድታሳልፉ ነው፡፡ እናንተ እንመለስና እንግባ የምትሉ በልባችሁ ያለውን የአጋንንት መንፈስ ይዛችሁ መድረክ ላይ ለመውጣት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን አይዋጥላትም፡፡ የሰደባችኋው ቅዱሳን ቢያዝኔባችሁም ዛሬም እንድትመለሱ እንደሚጸልዩላችሁ አትርሱ፡፡- ቅዱሳን በዚህ አይበቀሉም! የሚበቀል አምላክ ስላላቸው!
  መናፍቃን ፤ - አትፍሩ ደፍራችሁ ተመለሱ፡፡ ወደ ኑፋቄ ያስገባችሁትን ሰው አትፍሩ፡፡ ከእናንተ አይቶ ነግ ተምሮ ይመለሳል፡፡ የሰውን ሃሜት አትፍሩ፡- ቤተ ክርስቲያን ተመልሳችሁ ቁጭ ብላችሁ እንድትማሩ ትፈልጋለች፡፡
  አምላከ ቅዱሳን ተመልሳችሁ ላጠፋችሁት ጥፋት ደግሞ ይቅርታ ጠይቃችሁ በቀደመ ቤታችሁ ለመኖር ይርዳችሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. It is really an interesting comment. Reformists and protestants please return back home and repent in front of GOD.

   Delete
  2. This article is related to his sinful lifestyle. Your accusation is irrelevant in regards to his professions in his books & sermons. Even evil spirits confess Jesus as the Son of God (Mark 3: 11). So are you going to deny the Son just because these are evil spirits that uttered it? That's delusional!

   Delete
  3. Silemengiste semay bilew erasachewun mawared betam tinish neger silehone yenisiha fire yafiru!

   Delete
 11. ወንድሜ እውነቱን በሚገባ ገልጸኸዋል፤ መነናፈፍቃኑ መጨረሻቸው ይኸው ነው፤ እድሜ ከሰጠን ገና ብዙ እናያለን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ እውነቱን በሚገባ ገልጸኸዋል፤ መነናፈፍቃኑ መጨረሻቸው ይኸው ነው፤ እድሜ ከሰጠን ገና ብዙ እናያለን፡፡

   Delete
 12. ይኽ ሰው ምንያህል ቢበድላችሁ ነው እንደዚህ የምትንጫጩት! ይገርማል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጽሁፉን በደንብ ካነበቡት በደል ሳይሆን ይሄ እርዳታ ነው። ብዙ እኮ ደክመውለታል አልሰማ አለ እኮ። ልክ እንደ ተከስተ ይህ መንገድ ለንስሀ ይጠቅመው ይሆናል ማን ያውቃል

   Delete
  2. ፓስተር ተከስተ ንስሐ ገብቷል። የበደላትን ሴት ባለቤትዋን ሚስቱንና ቤተክርስቲያንን ይቅርታ ጠይቋል አሁንም የንስሀን ፍሬ እስኪያሳይ አገልግሎት አቁሟል ምኑን ከምን ነው የምታወዳድሩት

   Delete
 13. የሚገርመው ነገር ይህ ሰውዬ ትምህርቱንና ስብከቱን የሚያደምጡት ሰዎች እግዚአብሄርን ሳይሆን እርሱን ወደ ማምለክ ሲሄዱ በብዙ ተምልክቻለሁ ፡ ይህ ደግሞ ከምን አሰራር መሆኑ ግልጽ ነው፡ ግን ጣፋጭ መስሎ መራራ ፤ ጽድቅ መስሎ ሃጢያትን ፤ በረከት መስሎ መርገምን ፤ ዕውነት መስሎ ሃሰትን ፤ ሃሰተኞች ድንቆችን ይዞ የ እግዚአብሄርን መንግስት የሚያግለግል መስሎ የሚያፈርስ ፡ ከየትኛውም የበለጠ አደገኛ የሆነ ፡ ነፍሳትን ለዲያብሎስ መንግስት እየመለመለ ፡ ብዙዎችን በ ሰንሰለቱ ውስጥ የከተተ ረቂቅ በሆነ መልክ ሰውን ያሳተ ፡ ገደል የከተተ እየከተተም ያለ ሊታለፍ የማይገባው ነውና ፡ አለን የምትሉት ነገር ካለ በአስቸኳይ ለሚመለከተው ክፍል ታውቆ አገልግሎቱ መቆም አለበት። በ እግዚአብሄር አውደ ምህረት ላይ ቆሞ የ ሰይጣንን መንግስት ለማስፋፋት ሁላችንም ልንፈቅድለት አንችልም ። አምናለሁ እግዚአብሄር ይቅር ባይ ነው ፡ የ ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ያማያነጻው ሃጢያት የለም ፡ ይህ ግለሰብ በ ንስሃ ቢመለስ ተመልሶ የ እግዚአብሄር ልጅ የማይሆንበት ምክንያት የለም እግዚአብሄር በጠራውና በሰጠው ጸጋም የማያገለግልበት ምክንያት የለም ፡ ሁላችንም እንደምንስተው እና ምህረትን ደግሞ እንደምንቀበል ሁሉ ፡ ጌታ የአንዱን ሃጢያት መዝኖ ይህን ያህል ነው የሌላውን ደግሞ ያን ያህል ነው አይልም ፡ አምናለሁ ሆኖም ግን የበደለውን አምላኩንና ፡ ህዝብን ይቅርታ ሊጠይቅ ግድ ነውና ለሌላውም ወድቀት ምክንያት ሆኗል እየሆነም ነውና ፡ በ ኢንተርኔት ማወጁና ኢንፎርሜሽን ማቀበሉ ብቻ በቂ አይደለም WE NEED TO TAKE ACTION RIGHT NOW

  ReplyDelete
 14. ተሀድሶነታችሁን በግልጽ አሳይታችሆል ወደ ውስጥ ማየት የትልቅነት ምልክት ነው። አስተያየት የምትሰጡ ወገኖቼ ለምን በውስጣችሁ ያለውን ሀጥያት አጋለጣችሁ ከምትሉ ግብረሰዶማዊነት ከቤተ ክርስቲያናችን እንዲጠፋ እንተባበር ተሀድሶዎችና ፕሮቴስታንቶች ከምንል መጀመሪያ በዚህ ሀጥያት የረከሱትን ጳጳሳቶቻችንን እና መነኮሳተቶቻችንን እንቃወም ገዳሞቻችንን እናጥራ። እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጠን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous April 2,2015 at 12:45pm
   ወንዳጄ፦ ለምን ወደ ሌላ መዘባረቅ ትገባለህ? ለምንስ ንፁሐንና የማትኖርባትን የክርስቶስን ቤተክርስቲያንና ገዳማትን ለማፀየፍና ለማራከስ በውሸት አሉባልታና የፈጠራ ዝባዝንኬህ ትገዳደራለህ?አንተ ጳጳሳት ከሚገኙበት የእውነት ቦታ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ውጭ የሆንክ ሆነህ ጳጳሳትን በአንተው የመዳራት ምግባር በሐሰት ለመደባለቅና ስም ንጽህናቸውን ለማራከስ ለምን ፈለግህ? መናፍቃንና እራሳቸውን ተሐድሶ ብለው የሰየሙ የመናፍቃን ቅጠረኛ የጥፋት ተላላኪዎች የሰይጣን ሰራዊት ሌጌወኖች ናቸውና ሁልጊዜ ሐሰትን ከልባቸው እያፈለቁ እውነተኞችንና የእውነት አገልጋይ በጎቸን ጠብቁ የተባሉትን በስድብ ማበሻቀጥና ምግባራቸውን ማክፋፋት ማራከስ ብሎም በውሸት መወንጄል መክሰስ ዋነኛ መገለጫቸውና ተግባራቸው ነው። ስለሆነም የተፃፈው የራስህና መሰልህ ጉዳይ እያለ በጥላቻ የእውነትን ቤትና አገልጋዮችን ስለምትጠላ ብቻ ጳጳሳትን፤ ገዳማትንና ቤተክርስቲያንን ለመዝለፍ፤ ለማንጓጠጥና በሐሰት የፈጠራ ቱሪ ናፋ ለማንቧረቅ አንተም ከመናፍቃን አንዱ ነህና ላንቃህን ከፈትህ። ለሁሉም ምንም ብታንቧርቅ ይህን የተረት ክስህን ከቢጤህ ውጭ ሰሚም የለም ለአንተም ህይወት ሳይሆን ሞት ነው።

   Delete
  2. ዳሞት
   አንተን ንቆ ከመተዉ የተሻለ አማራጭ የለም፡፡ ገና ጨቅላ ስለሆንክ(በአስተሳሰብ) ካንተ ጋር ምክንታዊ ሆኖ መነጋገርና መተማመን አይቻልም፡፡ ጡጦዉን እንደነጠቁት ህጻን ከማልቀስና ምክንያት ፈልጎ ከማልቀስ የዘለለ ፍሬ ነገር ጽፈህ አይቼ አላዉቅምና እንደ ማቱሳላ እድሜ የረዘመና በአንተ የኮሜንት ስም የሚጀምር ዘባተሎ ጽሑፍ ካለ አላነበዉም፡፡

   Delete
  3. ዳሞት ምነው ከማን እንደሆንክ እስከሚያስታውቅብህ ድረስ እንደስድብ አባት ዲያቢሎስ የስድብ ናዳህን አወረድከው? ለነገሩ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ አይደል የሚለው ቃሉ? አባቶችን ለማዋረድ ከማሰብ ተነስቼ ምንም አላልኩም ግን ማንም ቢሆን በሀጥያት ከተገኘ መታረም ይገባዋል። አንተ ጻድቅ ያረካቸው ጳጳሳቶቻችን በታሪክ ተሰምቶብን የማይታወቅ ውድቀትን አሳይተውናል ምነው ጵጵስናቸውን አፍርሰው ያገቡትን ጳጳስ ስም ጠቅሼ መናገር የሚያስፈልግ አይመስለኝም የቅርብ ቀን ትዝታችን ናቸውና። የሥላሴ ጊቢው የሴቶች ድብድብ ጊቢ ሆኜ ያየሁት ስለሆነ ያንተ ማረጋገጫ አያስፈልገኝም። የግብረ ሰዶማውያኑን መዘርዘር የሚያስፈልግ ከሆነ ጠይቀኝ በዝርዝር እነግርሀለሁ። ለማንኛውም ወንድሜ ቁም ነገሩ እንዴት አርገን ቤተክርስቲያናችንን ከሚመጣው የሀጥያት ጥፋት እንታደግ በሚለው ጉዳይ ብናወራ ይሻላል በግልጽ ያለ አንዳች ሀፍረት ተሀድሶ ነን ብለው የራሳቸውን ገበና አውጥተው ስለ ንስሀ ሲነጋገሩ የኛ መሸፋፈን ዋጋ የለውም። ዲ አሸናፊ እጅግ አሳፋሪ ህይወት ውስጥ እየዳከሩ መፍጨርጨር አያዋጣህም ንስሀ ግባ ተመለስ በዙሪያህ የሰበሰብካቸው ጀሌዎችህ አያዋጣህም።

   Delete
 15. አሸናፊ እግዚአብሔር ያስብህ ንስሀ ይሻልሀል ሀጥያት ሌላ ስም የለውም ሀጥያት ነው። እዚ ትደርሳለህ ብዬ አላሰብኩም ነበር። ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ በጾም በጸሎት በእግዚአብሔር ፊት ለምኜልሀለሁ አሁንም እርሱ ይርዳህ አሜን።

  ReplyDelete
 16. አሸናፊ እግዚአብሔር ያስብህ ንስሀ ይሻልሀል ሀጥያት ሌላ ስም የለውም ሀጥያት ነው። እዚ ትደርሳለህ ብዬ አላሰብኩም ነበር። ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ በጾም በጸሎት በእግዚአብሔር ፊት ለምኜልሀለሁ አሁንም እርሱ ይርዳህ አሜን።

  ReplyDelete
 17. ጻድቅ ሰባት ጊዜ ወድቆ ሰባት ጊዜ ይነሳል፡፡ አሸናፊም ቢሆን ሰዉ ነዉና በሐጢያት ተፈተነ፡፡ ይህ ሊደንቀን አይገባም፡፡ ወንድማችን ከልቡ ንስሐ እንዲገባና ከማንም በላይ ከበደለዉ ጌታ ጋር እንዲታረቅ እንጸልይለት፡፡ ከዚያ ዉጭ የሚደረግ ጉንጭ አልፋ ክርክር ለማንም አይበጅም፡፡ ማንም የቆመ ቢመስለዉ እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ፡፡

  ReplyDelete
 18. አሽናፊ መናፍቅ ነው፣ የቤተ ክርስቲያን ቀንደኛ ጠላት ነው፣! እግዚአብሄር ገና ይፈርድበታል!!!

  ReplyDelete
 19. I can't blive this arthicl

  ReplyDelete
 20. What is special? this is their doctrine and belief which expected from Tehadiso/Protestant.

  ReplyDelete
 21. this article is the message of Devil, Ashenafi is a real Christian. never mind our Enemy is always against us. Deacon Ashenafi please be strong God is with you always.

  ReplyDelete
  Replies
  1. u r devil that is why u oppose this well organize article.

   Delete
  2. THANX MAN !!! GODBLESS U !!!

   Delete
 22. እግዚአብሔር ልቦና ይመልስ!!እግዚአብሔር ልቦና ይመልስ!!

  ReplyDelete
 23. እግዚአብሔር ልቦና ይመልስ!!እግዚአብሔር ልቦና ይመልስ!!

  ReplyDelete
 24. አጃኢብ ነው

  ReplyDelete
 25. የአሹን ባህሪ ለማያውቁ ሰዎች የእሱ እንደዚህ መሆን ለመቀበል ይከድዳቸው ይሆናል። ባህሪውን በደንብ ቀርበን ያወቅነው ሰዎች ግን ይህን ማድረግ ለአሹ ትንሽ ነገር እንደሆነ እናውቃለን። እጅ እጅ ብሎኝ ክርስትናን በወሬ እንጂ በተግባር እንደማያውቃት ጠንቅቄ ተረድቼ የተለየሁት ሰው ነው። ብዙ ጊዜ ከገርል ፍሬንዴ እንደለያይ መከረኝ። አላማው አልገባኝም ነበረ ለካ........................

  ReplyDelete
 26. ABA SELAMAS! WHY DONT YOU CHANGE YOUR PROFILE NAME BY LUTER YOUR PROTESTANT FATHER. EVERY TIME YOU WRIGHT ON YOUR BLOG UNINTERESTING STORIES . SPECIALLY ON ORTHODOX RELIGION . I AM REALLY SORRY FOR YOU & YOUR FOLLOWERS TOO.PLZ IF YOU HAVE TIME TRY TO PREACH GOSPELS , THAT IS BETTER , DONT SUE EVERY ONE WITH OUT EVIDENCE .

  ReplyDelete
  Replies
  1. don't u read the second? article this article has plenty of evidence. and the person also purely gay. for your information man he is not an orthodox tewahedo christian. he is out from z church. he use the name diacon to mislead our Christians.

   Delete
 27. Yidfahe abo anten blo diyakon. set tefto new wende lewende yemetleksesekse

  ReplyDelete
 28. መናፍቃን መጨረሻቸው ይሄ መሆኑን አወሮፓውያን አሳይተዋል፡፡ የርኩስ መንፈስ ልጆቻቸውም በአፍሪካ ይህንን ይከተላሉ፡፡ አሸናፊ ችግር አለበት ብላ ቤተ ክርስቲያን ስታወግዝ እናንተ ጠበቆቹ ነበራችሁ፡፡ አሸናፊም እውነተኛ ክርስቲያን ስለሆ “ማኅበረ ቅዱሳን ዲ/ን አሸናፊን ለመክሰስና ለማስወገዝ የተንቀሳቀሰው በዋናነት የእርሱ መጻሕፍቱ በቤተክርስቲያን ውስጥ በስፋት በመነበባቸውና ለብዙዎች የመንፈስ እረፍትንና እርካታን በማምጣታቸው ቀንቶና ተመቅኝቶ እንደሆነ ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡ ዲ/ን አሸናፊ እስካሁን የጻፋቸውን 16 መጻሕፍት በግንቦት 2003 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ገሪማ ፊርማ ለሊቃውንት ጉባኤ በተጻፈ ደብዳቤ የሊቃውንት ጉባኤው ለሥራ እንዲጠቀምባቸው መመሪያ ተላልፎ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው“ ብላችሁ ቅዱስ ሲኖዶስን ተሳደባችሁ ማኅበረ ቅዱሳንንም የስድብ ናዳ አወረዳችሁበት፡፡
  “በሕገ ወጥ መንገድ ውግዘት ያስተላለፈው ሲኖዶስ ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ ማውገዙና ሕግ ማፍረሱ ሳያንስ፣ በመግለጫው መጨረሻ ላይ የተወገዙት ይቅርታ ከጠየቁ ቤተክርስቲያን በሯ ክፍት ነው ማለቱ የተወገዙትን ወገኖች በእጅጉ እንዳሳዘነ እየተነገረ ነው፡፡” በማለት ለቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ለመስጠትም ፈልጋችሁ ነበር፡፡
  ይሄው ዛሬእዉነቱ ታወቀና አገር ያወቀውን ጸሃይ የሞከውን ዉነታ ለመደበቅ አልቻላችሁም፡፡ ግብረ ሰዶማዊ የጻፋቸውን መጽሃፍ እያሞካሻችሁ አሁንም እንድናነብ ትጋብዙናላችሁ፡፡ እኛ ዕድሜ ሰጥቶን እናያለን፡፡ እንናተ ዛሬ አሸናፊን ለመውቀስ በሌላችሁ መንፈሳዊነት እየተሯሯጣችሁ ነው፡፡ ለመሆኑ ከአሸናፊ በምን ትለያላችሁ፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት የገባው በፕሮቴስታንት ነው፡፡ ሃገራችንን የውርደት ካባ አለበሳችኋት፡፡ ከእናንተ ጋር……. እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ፡፡ ኢትዮጵያን ህይወት አልባ አደረጋችኋ!!!!!
  አሸናፊ አንቀጸ ብርሃን የሚባል ማኅበር አላውቅም ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስን ዋሸ፡፡ እናንተ ደግሞ ሥራ አስኪያጅ እንደሆነ መሠከራችሁበት:: እግዚአብሔርን ሊያውቁት ባለወደዱ ቁጥር እዕምሮን ለማይገባ ነገር አሳልፎ እንደሚሰጥ አያችሁት? እናንተም ካልተመለሳችሁ ነገ በዚህ ግብረሰዶማዊነት የሚያውቃችሁ ሁሉ አደባባይ ወጣዋል፡፡
  ቤተ ክርስቲያን አሁንም አትጠላችሁም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም አትመለሱ አላለም፡፡ ነገር ግን የምትመለሱት ልታስተምሩ ሳይሆን የበደላችኋትን ቤተ ክርስቲያን ይቅርታ ብላችሁ እድሜያችሁን በንስሃ እንድታሳልፉ ነው፡፡ እናንተ እንመለስና እንግባ የምትሉ በልባችሁ ያለውን የአጋንንት መንፈስ ይዛችሁ መድረክ ላይ ለመውጣት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን አይዋጥላትም፡፡ የሰደባችኋው ቅዱሳን ቢያዝኔባችሁም ዛሬም እንድትመለሱ እንደሚጸልዩላችሁ አትርሱ፡፡- ቅዱሳን በዚህ አይበቀሉም! የሚበቀል አምላክ ስላላቸው!
  መናፍቃን ፤ - አትፍሩ ደፍራችሁ ተመለሱ፡፡ ወደ ኑፋቄ ያስገባችሁትን ሰው አትፍሩ፡፡ ከእናንተ አይቶ ነግ ተምሮ ይመለሳል፡፡ የሰውን ሃሜት አትፍሩ፡- ቤተ ክርስቲያን ተመልሳችሁ ቁጭ ብላችሁ እንድትማሩ ትፈልጋለች፡፡
  አምላከ ቅዱሳን ተመልሳችሁ ላጠፋችሁት ጥፋት ደግሞ ይቅርታ ጠይቃችሁ በቀደመ ቤታችሁ ለመኖር ይርዳችሁ፡፡

  ReplyDelete