Saturday, April 11, 2015

የጻፍሁትን ጽፌአለሁ !           Read in PDF      
   ‘‘የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ’’    ዮሐ 19፡22
                                                                                ቀሲስ ጋይዮስ
   ጲላጦስ የይሁዳ አውራጃን ያስተዳድር የነበረ ሮማዊ ገዥ  ሲሆን   በስልጣን ዘመኑ ከተመለከታቸው ጉዳዮች እና ከአስቻላቸው ችሎቶች የኢየሱስ ጉዳይ የሚመስል እና ለመወሰን  የተቸገረበት ዘመን የለም። የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ   በመስቀል ላይ መሞት በዓለም   ከታዩት የፍርድ መጉደል ሁሉ የበለጠ ነው። አንድ ሰው በመስቀል ተስቅሎ  ከመሞቱ በፊት መገረፍ እንዳለበት የሮማውያን ህግ ይናገራል። ግርፉቱ በጣም አደገኛ በመሆኑ  በግርፉቱ ብቻ  ብዙ ሰው ሞቷልምክንያቱም መግረፊያው የሚሰራው ከቆዳ ሲሆን በጫፉ ላይ ብረታ ብረት፡አጥንት ወይም ሹል ነገር ይቋጠርበታል። ወንጅለኛ የተባለው ሰው ሲገርፍ እነዚያ ሁሉ ነገሮች በጀርባው ላይ ያርፉሉ፡ ከዚህ በኋላ ጉዳቱ የባሰ ሰለሆነ ሥጋው በማለቅ  አጥንቱ ከዚያም አልፎ ውሳጣዊ የሰውነት ክፍሎች  ይታያሉ።ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ  ሲገረፍ   ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ ደርሰውበታል። ጲላጦስ ብዙ ይተገረፈውን   ስጋው አልቆ አጥንቱ የታየውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚገባውን  ቅጣት ስለተቀበለ በነፃ ለማሰናበት በማለት በህዝቡ ፊት አቀረበው(ሉቃ 2316_22) አይሁድ ግን በደም የተሸፈነውን የኢየሱስን አካል በማየት ቅንጣት ያህል አላዘኑለትም፡ይልቁንም ምራቅ እየተፉ  በጥፊ ይመቱት ነበር(ማቴ 2727_31)።ኢየሱስ  እኛን ሰለሚወደን ይህን ሁሉ ታግሷል።

ጲላጦስ ጌታ ኢየሱስን  ነፃ ለማድረግ  ብዙ መንገዶችን ሞክሯል እንዲለቁት ብሎ አስገርፎታል፡እናንተ አልፈለጋችሁት  ግሪክ ሂዶ ያስተምር ብሎቸዋል፡ በየአመቱ የፉሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ  ኢየሱስን ከአደገኛው ወንበዴ ከበርባን ጋር ለምርጫ አቅርቧል። አይሁድ ግን ልባቸው በክፋት ስለ ተያዘ ኢየሱስ እንዳይፈታ በኃይል ይጮሁ ነበር፡የምትፈታው በርባንን ነው አሉ(ዮሐ18: 40) ኸቱ ሁሉ  ወንበዴን ፈቶ ንጹሑን   ለመግደል ነው ጲላጦስ ሮምን  ሕግ ማስፈጸም ተሳነው ህጕ ወንጅል የሌለበትን አይቀጣምና። ጲላጦስ አንድ ንጹሕ መግደል ነው ያለበት? ወይስ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ውሸተኞችን መስማት?  በነገሩ ግራ ተግብቶ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ምን  ላድረገው (ማቴ 2722)  ሲላቸው  አይሁድም በአንድነት ስቀለው ስቀለው አሉ።  ጲላጦስ ግን አንዳች በደል አላገኘሁበትም   እናንተ ስቀሉት ሲላቸው እኛ ህግ አለን  እንደ ህጋችን ሊሞት ይገባዋል ብለው  ወዲያዉኑ ኢየሱሰን ለመስቀል ወንጅል ያሉትንእራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝብሏል በማለት ነገሩን ከሮም ህግ  ወደ እግዚአብሔር ህግ ቀየሩት( ዮሐ198_11)    ጲላጦስ  ውሳኔ ግን ጌታን መልቀቅ ነበር  

 የአይሁድ ካህናት ግን  እየሱስ  እንዳይለቀቅ ጲላጦስን በማስጠንቀቂያ   ብትፈታው የቄሳር  ወዳጅ  አይደለህም በማለት  ጉዳዩን  ከሃይማኖታዊ ወደ ፖለቲካዊ ይዘት ለወጡት። ይህ ለጲላጦስ ፈታኝ ነበር ወይ ከኢየሱስ ጋር መሆን አልያም ለራሱ ክብር ሲል የቂሣር ወዳጅ ሆኖ መቀጠል።ጲላጦስ ግን እንድገና የኢየሱስን ጉዳይ መየት ጀመረ ለስቅላት የሚዳርገውን ወንጅሉን በመርመር ኢየሱስን  ሲጠይቀው ምንም አላገኘበትም። ጲላጦስ ግን የቂሣር ወዳጅ አይደለህም ተብሎ ስለ ተነገረው ፍርድን  በማንጋደድ  ኢየሱስ እንዲሰቀል  ፈረደ። ስለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ   በመስቀል ላይ መሞት በዓለም   ከታዩት የፍርድ መጉደል ሁሉ የበለጠ ነው ያልነው።ጲላጦስ  ኢየሱስን  የሰቀለበት ምክንያት ከአይሁዳውያን የተለየ  ነበር፡ አይሁድ  በቅንዐት ገድለውታል፡ ጲላጦስ ግን የሰቀለበት ምክንያት ክብሩ እንዳይነካበትና ሌሎችንም በመፍራት ነው።ለጥቅም ለራስ ክብር እና ሌሎችን በመፍራት ፍርድ ይዛባልና። ጲላጦስ የኢየሱስ ወዳጅ ሆኖ ሌላው ቢጠላው ይሻለው ነበር።ያሳሰበው ሌሎች ምን ይሉኛል የሚለውን እንጅ ስለ እውነት  መቋም አይደለም። ፍትህን ከማስከበር ይልቅ ለራሱ ክብር በመቆም እና ለይሉኝታም ተገዢ ሆነ።ጲላጦስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሰቅሉትለወታደሮች አሳልፎ ሰጠው። ኢየሱስም የሚሰቀልበትን መስቀል ተሸክሞ በአራማይክጎልጎታተብሎ ወደ ሚጠራው  የራስ ቅል ወደተባለው  ቦታ ወጣ(ዮሐ 1917)  በዚያም ተሰቀለ :  አይሁድም በታሪካቸው ትልቅ ስህተት ሠሩ። 
 ምንም በደል የሌለበትን ንፁህ በግ ኢየሱሰን  ገድለዋልና። ጲላጦስ ግንከመስቀሉ ራስጌየአይሁድ ንጕሥ የናዛሬቱ ኢየሱስየሚል ጽህፈት ሰው ሁሉ እንዲያወቀው  ፃፈ። ይህ ጽህፈት በጌታ ልደት ጊዜ ኢየሱስን ፍለጋ የመጡትን ሰብአ ሰገል የጠየቁትን ጥያቄ ያስታውሳል የተወለደው የአይሁድ ንጕሥ ወዴት ነው? የሚለውን (ማቴ 22) አሕዛብ  የኢየሱስን ንግሥና  ሲያምኑ አይሁድ ግን በአለማመን ጠንቅ ኢየሱስን ገፉ።የአይሁድ ንጕሥ የናዛሬቱ ኢየሱስ  የሚለው ጽህፈት የተፃፈውም  በላቲን፡ በፅርዕ(ግሪክ) እና በአራማይክ ነበር(ዮሐ 19: 20)።ላቲን የሮማውያን መንግስታዊ ቋንቋ፡ግሪክ ደግሞ በሮም ግዛት የነበረው ህዝብ የሚግባባት ሲሆን አራማይክ ቋንቋ ደግሞ የጳለስጠናውያን ቋንቋ ነበር። በእነዚህም ቋንቋዎች መጻፉ ኢየሱስ የሞተው ለአይሁዳውያን
ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም መሆኑን  ያመለክታል። ነገር ግን  የአይሁድ ንጕሥ የናዛሬቱ ኢየሱስ  የሚለውን ጽህፈት የአይሁድ የካህናት አለቆች አላወደዱትም፡ ጲላጦስንም በመቃወም እርሱ  የአይሁድ ንጕሥ ነኝ እንደለ ጻፍ እንጅ የአይሁድ ንጕሥ ብለህ አትጻፍ(ዮሐ 1921) አሉት ጲላጦስ ግን    የጻፍሁትን ጽፌአለሁየአይሁድ ንጕሥ የናዛሬቱ ኢየሱስ   (ዮሐ 1922)ነው። በማለት በአፅንዖት በቃየአይሁድ ንጕሥ የናዛሬቱ ኢየሱስነው አለ።     ጲላጦስ  የአይሁድ ንጕሥ የናዛሬቱ ኢየሱስ የሚለውን ጽህፈት አልቀየረውም፡ ምክንያቱም የኢየሱስ ንግሥና አይሻርም ከቶም አይቀየርም
 ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ  ግን  በመስቀል ላይ  ስቃይ ሳለ ቅድሚያ ይሰጥ የነበረው ለራሱ አልነበረም። የሰው ማንነቱ የሚለካው  በመከራ ውስጥ ሆኖ  ለሌላው ማሰቡ ነውና ስለ  ድካሙ፡ ስለ ህማሙ እና ስለ ቁስሎቹ እንኳ  አላሰበም።ይልቁንም በእጆቹ እና በእግሮቹ ላይ በትልቅ መዶሻ ተቸንክረው የነበሩትን ችንካሮችን ትኩረት አልሰጠም።ከዚህም በበለጠ ከራሱ ላይ ደም እየፈሰሰ አናቱን እየወጋ ስቃዩን እያበረታበት ላለው የእሾህ አክሊልም ቅንጣት ያህል አላስታወሰም።የተቀበለውን ግርፋት፡ ስቃይ  ሁሉ ወደ ጐን በመተው ለሌላው ሕይወት ያስብ ነበር።የሰው ልጅ ይቀር እንዲባል እንዳይጠፋ ይፀልይ ነበር። እውነተኛው  እረኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሰቀሉ በፊትም፡ በመስቀል ላይም እያለ በጐቹ እንዳይጠፋ ያስባል ከስቅለቱ በኋላ በጐቹን  በግርማው ዙፋን ተቀምጦ ይጠብቃል።
      ያለ  እና ነበረው  ወደ ፊትም የሚኖር ኢየሱስ ክርስቶስ በትምህርቱ በታአምራቱ በህይወቱ
የዓለምን ታሪክ ጅጉ ነካ ሲሆን  ሁልጊዜ ሥራው ህያው ነው።የተወለደበትም ቦታ  በጣም ዝቅተኛ መንደር፡ ልደቱ አስገራሚ ያስተማረው ትምህርት  ሀዘንን የሚያስረሳ ህያው ቃል  ስከ ዛሬም  የተጠና እና የተበላም  የሚገኝ።የዘለዓለም አምላክ  ሲሆን  ሥጋው ወራት  ወንድሞቼ ብሎለመጥራት ያላፈረብን፡  የተጨነቀናየተከዘ ልብን  መፈወስ የሚችል ልብ ያለው።ከ ድሆች    ኃጢአተኞች ጋር በርጋታ በርህራሄ ልብ  የቀረበ ለሃይማኖት መሪዎች ለባለጠጐችም  በኃይል በስልጣን ያነጋግረ። ማንም ቢሆን የማይቀበላቸውን  ቀራጮችን  ወደ ቤታቸው  የሄደላቸው። ሰው የረሳቸውን የብዙ ዘመናት  ህመምተኞችን  ጤናቸውን የሰጠ። ለዘመናት ተጠቅተው  የወደቁትን የእርዳታ ጩኃታቸውን  ሰምቶ  የመለሰ። በሀዘንተኞች ቤት ተገኝቶ ሙት ያነሳ በሰርግ ቤት  ተግኝቶ የደጋሹን ጭንቀት ያስወገደ።ኑሮው ራሱን ክዶ ለሌሎች በማሰብ ላይ  ሲሆን  ነፍስ ሁሉ በፊቱ የከበረች   ልቡ በርህራሄ  የተሞላ የተናቁትን  ያከበረ   እንባን  ሁሉ ያበሰ የተረሱትን ያስታወሰ የተጨነቁትን ያረጋጋ  

 ኃጢአተኛውን ዓለም    ለማዳን  የተሰቀለ፡ የእግዚአብሔርም  ፍርድ በኃጢአት  ላይ የጸና በመሆኑ   የኃጢአትን ዋጋ ለመክፈል እንደ ወንበዴ ተይዞ በፊቱ የተደቀነውን የመከራ ዳገት  ለሰው ልጀች ሲል በመጋፈጥ ወደ ውስጥም ዘልቆ በመግባት በውርደቱ ክብርን በጭንቀቱ  ሰላምን፡ በሞቱ ለዘለዓለም  ህይወትን ሰጠ በዚህም በእርሱ ከተደረገው መሥዋዕትነት በቀር መዳን የለለ(የሐዋ4:12)የአብንም ፍቅር ከኢየሱስ ክርስቶስ  የመስቀል ሞት በቀር ሊገልጥ የሚችል ከቶ ያልተገኘ(ዮሐ 316)  ።በመስቀል ላይ በመሞት  ታላቁ  ዙፉን  ፍቅር ፍርድ ተከናውነው ሰው
ታሪኩ ተለወጠ።የእግዚአብሔር  ፍርድ በኢየሱስ ላይ፡ ፍቅሩ እኛን  በማዳን  ተገለጠ። በዚህም ፍቅር የልዩነትን ግንብ  ፈረሰ፡  አንድ ቤተሰብ (መንጋ) ሆነ በፍቅር ጀምሮ  በፍቅርም  ፈፀመ፡  ስለዚህም የሰውን ልብ በፍቅር ማርኮ በግርማው ቀኝ ተቀምጦ ሲመለክ  ይኖራል። እኛም ዛሬ ራስ  ቅልአችን(አእምሮ)  የተሰቀለውን   እያሰብን     ንጉሥአችንን እያመልክን   እንደ አይሁድ ሳይሆን እንደ ዳዊት  እኔ ግን በላየ ላይ ንጉሤን ሹሚያለሁ (መዝ 26) ልንል ይገባል።
   ዛሬም ቤተክርስቲያን    ፍቅር እር  የሰላምን አዋጅ   ለዓለም የምታበስር ወንጌልን  ለሰው ልጀች  ማለትም የኢየሱስ  ክርስቶስን  ልደቱን ጥምቀቱን፡ህማሙን፡ ስቅለቱን፡ ሞቱንና ትንሳኤውን ፡ ዕርገቱንና ዳግም ምፅአቱን  ከማስተማር ሌላ ስራ  ሊኖራት አይገባም ( ማር 1616)።የ ቤተ ክርስቲያን የወንጌል ስብከት  የተመሰረተው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ላይ ነውና።
    ይህም  የወንጌል   ተል  ጉዞው ረጅም በብዙ መልኩ  ፈተና  ያለበት በጥብቅ የሚሰለፉበት 
ንደ በጐች አራዊት መካካል የሚላኩበት  ከባድ ተልእኮ  ነው ።በዚህ ተል ውስጥ የሚገጥመንን
ችግር ፈተና  ሁሉ   በምስጋና  በመቀበል  ጨከኖም መስቀሉን  ተሸክሞ መከተል የተልእኮውንም መሰረት   ለማጣበቅም  ጸሎት፡ ሐቀኝነት   ሕሌና ውሳኔ   ያስፈልጋል።  በተለይ በአሁን  ጊዜ ለክርስቶስ ወንጌል  የተለዩ ቆራጥ አማኝ   አገልጋዮች ያስፈልጉናል። የጥንቷ ቤተክርስቲያን  ወንጌል ለመስበክ ብዙ መስዋትን  ከፍላለች።   ዓለማዋም ብዙዎችን  የክርስቶስ ተከታዩች  ማድረግ   ለተገፉት ና ለተጐዱትም  መሟገት ነበር።  ዛሬም ቢሆን ቤተክርስቲያን ህይወት ወንጌልን በመሰብክ፡ ለፍትህ በመቋም እና ለእውነትም  ታጥቃ በመነሳት በተጨማሪም በራዕየ ዬሐንስ  እንደተጠቀሱት ሁለቱ የጴርጋሞን   የትያጥሮን  አብያተ ክርስቲያናት  የተነቀፉበትን ወደቀው ንስሐ እንዲገቡበት የታዘዙትን  አጋንንታዊ ከሆነ አምልኮተ ጠዖት የጥንቋላ ትምህርት እና ዝሙት መንፈስ  የተሳሰሩ በውስጧ ያሉ የሀሰት አገልጋዮቿንና ምዕመናን ልታጠራ ይገባል( ራዕይ 213_15,  218-20) በእነዚህም  በማይታዘዙ  አገልጋዮች  ምክንያት  የቤተክርስቲያን  እድገ አሽቈልቈሏል እና ተልዕኮዋም  ተዛብቷል።
ቤተ ክርስቲያን  ሆይ !   አጥርተሽ እንድታይ  ኵልን  ክርስቶስ  ግዢ፡  ወደቀሸም ንስሐ ግቢ(ራዕይ 3 ፡18_19)ሰባት የወርቅ መቅረዞች በፊቱ ለሚቀጣጠሉት፡ለሚያባራው የንጋት ኮከብ ፡ለታረደው በግ ኢየሱስ ክርስቶስ   ክብር፡ምስጋና ፡ውዳሴ፡ዝማሬ፡እልልታ፡ሰግደት እና አምልኮ  ይሁን ! አሜን ወአሜን ለይኩን ለይኩን………………………………………

18 comments:

 1. ጥሩ ጽሁፍ ነው። ግልጽና ተቀባይነት ያለው ሀሳብ

  ReplyDelete
 2. thank you lord for this blog.

  ReplyDelete
 3. ሽ ምዕራፍና ቁጥር ቢደረደር ቃላቶች በቃላት ብዛት ቢቆለሉ በእውነተኛው የወንጌል አተረጓጐምና መልእክት ካልተገለጠ እንክርዳድ እንጂ ስንዴ አልተዘራምና ያው እንክርዳድ ነው የዘራኸው። ደግሞ ቤተክርስቲያን ትላለህ። ለመሆኑ ስለየትኛዋ ቤተክርስቲያንና በየት ስለምትገኘው ቤተክርስቲያን ነው የምትቀባጥረው። ደግሞስ ቤተክርስቲያንን የሰራት ክርስቶስ ነው ። የክርስቶስን ቤተክርስቲያን አሮጌ አዲስ ለማለትስ አንተ ማን ነህ? ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በአዲስ ኪዳን ነው ። ታዲያ የክርስቶስን ቤተክርስቲያን የጥንት የዛሬ ብሎ መካድና መከፋፈል የሰይጣን እንጂ የክርስቶስ አይደለምና አንተ ከየት አመጣኸው። ሌላው መያዣ መቋጫ ለሌለው ጽሑፍ ተብየ አተካራህ ሰይጣንና የሱ ከሆኑት ውጭ የሚሰማም የለምና በከንቱ አትዳክር።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ato or w/o Damot : Ante sew neseha geba! I don't understand why you always opposing spiritual articles?

   Delete
  2. For the commentator April 12,2015 at 10:48pm
   Dear commentator, you need to know, understand and believe Jesus is not only Lord. He is also God. He is the lord of lords. Everything is happened happenand done by him. He is completely a judge, but he is never ever an advocate. finally Fina you said, "I don't understand why you always opposing spiritual articles?" of cour you can't can undestand; because your eyes covered by the witches. Also you and me are moving in different Way. So you can't uderstand my comment. I don't think you also understand the meaning of spritual articles. I am arguing the bad and wrog thoughts and false gospels and messagers.

   Delete
 4. KALEHIEWET YASAMALEN!

  ReplyDelete
 5. ዳሞትዬ የ ጥንቷ ቤተክርስቲያን ማለት በሐዋርያት ዘመን የነበረችዋ ናት
  አበውን ጠጋ ብለህ ጠይቅ ለመክሰስ አትቸኩል ፡
  በየተኛውም ሚዛን ካሳሽ ና አሳዳጅ እግዚአብሔር አይቀበለውም ፡ በክርስትና ህይውት ውስጥ ወንድሙን የሚከስ ሰው ክርስቲያን አይደለም : አስብበት መጽሐፍ ቅዱስን ሁል ጊዜ አንብብ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous April 12, 2015 at 10:57pm
   ውድ አበውን ብለህ አበውን የምትወርፍ፤ አበው ብለህ ከነ ቀያፋ ጋር መድበህ በሐሰት የምትከስ ማስመሰል የተመረጥህበትና ሰልጥነህ የተካንህ ሙያህ ነውና "አበውን ጠጋ ብለህ ጠይቅ ለመክሰስ አትቸኩል" ትላለህ። ለመሆኑ ክርስቶስ አስመስሉ ብሏልን? እረ እሱስ አላለም ሰይጣን እንጂ። ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ ሁሉን ያውቅህ በማስተዋል የተሽሞነሞንህ የሆንህ መስለህ እኔን "አስብበት መጽሐፍ ቅዱስ ሁልጊዜ አንብብ" ትላለህ። ስለምክሩ አመሰግናለሁ። ግን ቃሉን ያነበበ ነው ወይስ ቃሌን የሚሰማና የሚያደርገው ነው ይድናል የተባለው? ወዳጄ ቃሉን መስማትና ማድረግ እኮ በማንበብ ባለፈ ከተማሩት መማርና የተማሩትን በእምነት መተግበር እንጂ የእግዚአብሔር ቃል እንደልብ ወለድ ዝም ብሎ በማንበብ የሚተረክ ተራ ታሪክ አይደለም። ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ በሰረገላ ይጓዝ ወደ ነበረው ሰው እንዲሔድ ሲልከው እንዲሁ በዘልማድ እንዲተዋወቀውና ስለሚያነበው እንዲያስተምረው እንጂ። በሰረገላ የነበረው ጃንደረባም ስለሚያነብ ብቻ የምታነበውን ታውቀዋለህ ብሎ ሐዋርያው ሲጠይቀው አንብቢያለሁና አውቂያለሁ ብሎ አዎ አላለም። ይልቁንም ማን አስተምሮኝ ብሎ በሚያስደስት ትህትና መለሰ። ሐዋርያውም የህንደኬው ጃንደረባ ያነበው የነበረውን ክፍል ስለማን እንደሚናገር አስተምሮታል። እና ወዳጄ ምናለ በከንቱ ባትኮፈስና ባትታበይ። ለመሆኑ ለሐዋርያት የተሰጠችው ቤተክርስቲያን የአምልኮ ስርዓት እንዳላት ታውቃለህን?ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቤተክርስቲያን ስርዓት እንዳልናገር ጊዜ ያጥረኛል የሚለውን አንብበኸዋልን? መቸም ቅዱስ ጳውሎስ ጊዜ ያጥረኛል ሲል የቤተክርስቲያን የአምልኮ አፈፃፀም ሥርዓትን ስለሚቃወም እንዳልሆነ ግልፅ ነው። ነገር ግን በጊዜው የቤተክርስቲያን ስርዓትን ያለመቀበልና ያለማወቅ ሳይሆን ችግሩ የተወለደው ክርስቶስ ትንቢት የተነገረለት በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ቃል ያም ቃል እግዚአብሔር መሆኑን ያለመቀበልና ያለማወቅ ስለነበረ ይፍጥ የበረው ትውልድ ሁሉ የተወለደውን የአይሁድ ንጉስን ማን እንደሆነ እንዲያውቅና እንዲያምን ስለነበረ ነው። የጥንቷ ቤተክርስቲያን ለሐዋሪያት የተሰጠችው ከሆነች አዲስቷስ የትኛው ናት? የናንተዋ የአስመሳዮች ለሐሰተኛው ክርስቶስ መንገድን የምትጠርጉለት አዳራሽ መደለቂያ ነውን? ሌላ ከሳሽ አሳዳጂ እያልክ በአስመሳይ ምላስህ ትቀባጥራለህ። ለመሆኑ ማሳደድና መክሰስ ምን እንደሆን ገብቶሐልን? የምትከስና የምታሳድድማ አንተው አስመሳዩ እባብ ለመሆንህ ግልጽ ነው ። አሮጌ አዲስ እያልክ ያንተ ስላልሆነው የምትቀባጥርና የፈጠራ ክስ እያስወነጨፍህ የክርስቶስ የሆኑትን ደም ለማፍሰስና ለማፈናቀል የጎልያድን ጦር የምትወረው አንተ አይደለህምን? የምታወሩት እኮ ስለማትኖሩበት የእምነት ተቋምና ስለግለሰቦች ነው። ግለሰቦች ያድርጉትም አያድርጉትም እንትና እንዲህ ሆነ ያን ሰራ የሚል የአህዛብን ስራ ሐሜትን አይደለም እንዴ የምታካሒዱትን። እና ይህን ሐሜትንና ስለማትኖሩበት ቤተክርስቲያን ማውራትንና መሳደብን የምታከናውኑ እናንተ ናችሁ ከሳሽና አሳዳጅ። እኔ ስለፃፋችሁት ሐሰተኛና አስመሳይ ጽሑፍ ነው ምላሽ የሰጠሁት። የእኛ ቤተክርስቲያን ክርስቶስ የመሰረታት ለሐዋርያትም የሰጣት ዛሬም ያለችሁ እስከ አለም ፍፃሜም እያበራች የምትኖረው ትናንትናም አዲስናት ዛሬም አዲስ ናት።

   Delete
 6. damot kal hewet yasemahe izoge berta

  ReplyDelete
 7. ዳሞትዬ ይህን ንጹህ ትምህርት የክርስቶስ ህይወትነት መመገብ አቅቶሃል መቸም ለ አህያ ማር አይጣፍጣትም እንዲሉ
  ስለ እንቁርቁሪት ጠበል ና ስለ ደብረ ሊባኖስ ቆሪት ቢጽፍ ልብህ ይወዳል ፡ የመስቀሉ ነገር ለአንተ ሞኝነት ነው ፡ እግዚአብሄር ይርዳህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ ወዳጄ! ለካም እንዲህ ያለ ተረት ተራች ነህ። ለመሆኑ ለአህያዋ ማር ለመመገብ ሞክረህ ነበርን? ወዳጄ አህያ ካንተ ትሻላለች በማስተዋል። እንዴት ካልክ በለአም ተጭኖባት የነበረችውን አህያ ሒድና ጠይቃት። እንዴት ካንተ እንደምትሻል ትነግርሃለች። ወረድ ትልና ደግሞ ስለ ጠበልና ደብረሊባኖስ ያለህን አላዋቂና መሰሪ የሆነውን ማንጓጠጥህን አስቀምጠሃል። ምነው አረክስ አፈርስ ብለህ ሔደህ በክርስቶስ ሐይል ጉድህ ወጥቶ እያጏራህ ወደሪያዎች ተጣልህ እንዴ። ለመውደቅና ለመጥፋት ከመታበይህ በፊት ሒድና የውሃውን መናወጥ ጠብቀው ከደዊያቸው ለመፈወስ የመሽቀዳደሙትን ጠይቅ። ወዳጄ በጠበል ቦታና ገዳማት ስለሚደረጉት የእግዚአብሔር ማዳን ሲነገር የማያስደስተው ሰይጣን ብቻ ነው። ወገኛው የመስቀሉ ነገርም ትላለህ። ለመሆኑ አንተ የመስቀል ጠላትና ነቃፊ ተቃዋሚ አይደለህምን? መስቀሉን እንጨት እያልክ የክርስቶስ ሃይል የተገለፀበትን የምታንቋሽሽ አንተ አይደለህምን? ምነው ለአህያ ማር መጋቢው እንደ ተጣለው እባብ ሔዋንን እፀበለስን ለማብላት ከገነት ዛፍ ሁሉ ብሎ እንደሸነገላት በመስቀል ተከልለህ በአስመሳይነት እንክርደድህን እውነት ለማስመሰል ተንቀሳቀስ? ደግሞ ንፁህ ትምህርት ተባለልኝ። ወጉ አየቅረኝ። ሲሉስ ሰምተሃል ንፁህ ትምህርት ምን እንደሆነና ምን ማለት እንደሆነ አልገባህም እንጂ። ንፁህ ትምህርት ማለት እኮ ሰይጣን ቃላት እየጠቀሰ ክርስቶስን እንደፈተነው በምዕራፍና ቁጥር ድርደራ በቃላት ክምር እውነትን መዋጋትና መፈተን አይደለም? ደግሞ April 12, 10:57pm ለለጥፈኸው አስተያየትህ የመለስኩልህ ቢሆንም ማንነትህ እንዳይገለጥብህና ሰዎች አይተው እውነትን ከውሸት ለይተው እንዳይወስኑ ስለፈለግህ ለማውጣት አልፈለግህም። አንተ ግን ውሸትን እውነት ለማስመሰል ደግመህ ይህንን የማደናገሪያና የክስ ቧልትህን ለጠፍኸው። ይህም ወጣም አልወጣም አንተ ማየትህ ስለማይቀር መልሴን ልኬልሃሉ። ደህና ሁን አህያን ማር መጋቢው።

   Delete
 8. የበሰለ ጽሁፍ ነው

  ReplyDelete
 9. አሜን ብያለሁ በዚህም በእርሱ ከተደረገው መሥዋዕትነት በቀር መዳን የለለ(የሐዋ4:12)የአብንም ፍቅር ከኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ሞት በቀር ሊገልጥ የሚችል ከቶ ያልተገኘ(ዮሐ 3፡16)

  ReplyDelete
 10. ሁሉም ሊያነበው የሚገባ ነው ::
  ያስለነፈው ሳምንት ብዙዎቹ የሳምንት ክርስቲያን የሆኑበት ሳምንት ነው : የከርስቶስ ነገር አልገባቸውም አመቱን በሙሉ ሌሎችን በመከተል ና በማገለገል ቆይተዋል ኢየሱስ ክርስቶሰን ካልያዙ በቀር መዳን የለም(የሐዋ4:12)የአብንም ፍቅር ከኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ሞት በቀር ሊገልጥ የሚችል ከቶ አልተገኘ(ዮሐ 3፡16)

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous April 13, 201at 8:33pm
   ለምን የእግዚያብሔር ቃል የሚያጣምም ጽሑፍ ተለጥፏል እያልክ ነጋሪት አትጎስምም? ለምን አደባባይ ወጥተህ ሁሉ ሊያነበው የሚገባ እንክርዳድ በስንዴው መካከል ተዘርቷል እያልክ አትለፍፍም? ለመሆኖ አንተን ዳኛና ፈራጅ አድርጎ የሳምንት ክርስቲያኖች ብለህ እንድትፈርጅ ማን ሾመህ? ክርስትና ምን ማለት እንደሆን እንሿን የማታውቅ አስመሳይ ሰይጣን ነህ። ክርስትና ስለሌላው ማውራት ሳይሆን ልትኖረውና በሌላው ላይ ጣትን ከመቀሰር ነፃ እንድትሆን ነው የምትናገረው። ለምን የራስህን የአዳራሽ አምልኮና ተግባሮች አታናገር አታወሩም? በማስመሰል ክርስትናና ህይወት አይገኝምና ስለማታውቃት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ስለሆነችው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና እምነት በከንቱ ባትደክምና የእዳ ሸክምን በክፉ ተግዳሮትህ ባትከምር መልካም ነው። ያለበለዚያ "ከእግዚአብሔር ጋ የሚጣሉ ይደቃሉ" ተብሏልና በቤተክርስቲያን ላይ የጎልያድን ጦር ደጋግመህ ብትወረውር ተመልሶ አንተን ይወጋሀል እንጂ ቤተክርስቲያን ምንም አትሆንም። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አምላሿ እግዚአብሔርተዋጊ ነው።እስቲ አስመሳዮና አሉባልተኛው መናፍቅ ልጠይቅህ ባትመልሰውም፦ ለመሆኑ የእግዚአብሔር የሆነውን መከተልና ማገልገል በመጽሐፍ ቅዱስ ያለ ነው ወይስ የሌለ ነው? ለመሆኑ እየሱስ ክርስቶስን ካልያዙ ማለት ምን ማለት ነው? ለምን ክርስቶስን እንደ እቃና እንስሳ በማይገባ ቋንቋ እየገለጽህ ታቃልልና የእርሱ የሆኑትን ትዋጋለህ? ክብር ለሚገባቸው ክብር መስጠትን፤ መገልገል የሚገባቸውን ማገልገልና ስለክርስቶስ ሲሉ መልካም ስላደረጉት መልካም ስራቸው እንዲነገረ የተናገረውና ያስተማሩ የቃሉ ባለቤት ክርስቶስ እንጂ አንተ እያገለገልኸው ያለኸው የተጣለው የሰው ልጆች ጠላት ሰይጣን አይደለም። ወደድክም ጠላህም አንተና ይህ ብሎግ ከነ ሚለጣጥፏቸው መርዘኛ ጽሑፎች ጋር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ያልሆናችሁ ጠላቶቿና መናፍቃኖች ናችሁ። መቸም ቢሆን ምኞታችሁና አላማችሁ አይሆንላችሁምና ማስመሰሉንና ስለሌሎች ማውራቱን አቁማችሁ የኔ የምትሉት ካላችሁና የማታፍሩበት ከሆነ አዳራሽ ሰርታችሁ ብታራምዱ ይሻላችኋል። ስለሌላው ከማውራትና ከማስመሰል ራስን ሆኖ መታየት በትንሹም ቢሆን እዳን ያቀላልና ራስህን ሁን!

   Delete
 11. አሜን geta abezeto yebarekehe

  ReplyDelete