Monday, April 13, 2015

የአባ ሳሙኤል ለቤተክርስቲያን አስተዳደር መጨነቅ - “ጅብ በማያውቁት አገር ቁርበት አንጥፉልኝ አለ” የሚለውን ብሂል የሚያስታውስ ነው


ከስምዓ ጽድቅ ኮነ
 ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ አባ ሳሙኤል በቅርቡ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ስለቤተክርስቲያን አስተዳደር አቀረቡት የተባለውና ሐራ “public lecture” የሚል ማጎላመሻ የሠጠው የእርሳቸው ይሁን ከሌላው የተጫኑትና በስማቸው ያቀረቡት የመነሻ ሐሳቡ ዜና ነው፡፡ (እንዲህ የምለው አባ ሳሙኤል በስማቸው ያሳተሟቸው አንዳንድ መጻሕፍት የእርሳቸው ሥራዎች እንዳልሆኑና ሌሎችን አጽፈው በስማቸው እንደሚያሳትሙት የሚናገሩ ስላሉ ነው፡፡ እንዲህ የሚያሰኘው አንዱ ነገርም አንዳንዱ ጽሑፍ የአንድ ሰው ወጥ ሥራ የማይመስልና እንደ ተማሪ የልመና እንጀራ ውጥንቅጥ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ ለምሳሌ “ፈለገ አሚን ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” የተሰኘው “መጽሐፋቸው” ማኅበረ ቅዱሳን ስለ ተሐድሶ ግንዛቤ ማስጨበጫ ብሎ ከዚህ ቀደም ካዘጋጀው ጽሑፍ የተወሰደ ሲሆን እርሳቸው ግን ምንጩን በተገቢው መንገድ አለመጥቀሳቸው ሳያንስ ስለተሐድሶ የተጻፈውን ጉዳይ በትምህርተ ሃይማኖት ውስጥ የነገረ ድኅነት ትምህርት በሚለው ምዕራፍ ውስጥ ነው የደነጎሩት፡፡ ሆኖም ይህ ነገረ መለኮታዊ አቀራረብ አይደለምና የአባ ሳሙኤልን የትምህርት ይዞታ የሚናገር በቂ ማስረጃ ይመስለኛል)፡፡

ዜናው እንደጠቆመው አባ ሳሙኤል ያቀረቡት የመነሻ ሐሳብ ለ/ሲኖዶስ አባላት የተላለፈ ጥሪ መሆኑን ሐራ ዘግቧል፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩን በቀጥታ ለሲኖዶስ ለምን አላቀረቡትም? ለምንስ ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ማኅበረሰብእና ለማቅ ወዳጆቻቸው ማቅረብ ፈለጉ? ለምንስ እስካሁን ዝም ብለው በዚህ ወቅት ማቅረብ ፈለጉ? የሚለው አጠያያቂ ጉዳይ ነው፡፡ የማቅ ብሎግ ሐራ ለሲኖዶስ የቀረበ የመነሻ ሐሣብ መሆኑን የዜናው ርእስ አድርጎ ለምን አወጣው? የሚለውም እንዲሁ ያጠያይቃል፡፡ ለማንኛውም ስለ አባ ሳሙኤል ማንነትና የእስካሁን ተግባር ከብዙ በጥቂቱ ለማቅረብ ፈልጌያለሁ፡፡ ይህን የማደርገው የአባ ሳሙኤል ማንነት አቀረቡ የተባለውን የመነሻ ሐሳብ ለማቅረብ በተለይ ከሞራል አንጻር ብቁ አለመሆናቸውን ለማሳየት ነው፡፡  

 አባ ሳሙኤል ከዚህ ቀደም አባ ተከሥተ በሚለው ስም ይጠሩ የነበረ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ነበሩ፣ በኋላም አባ ሳሙኤል ተብለው የፓትርያርኩ ረዳት በመሆን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው አገልግለዋል፡፡ የሥራ አስኪያጅነታቸው ዘመን ራሳቸውን ለጵጵስና ለማሳጨት ሽርጉድ የሚሉበትና ከፍተኛ ጥረት ያደረጉበት ዘመን ስለነበረ ከሞላ ጎደል መልካም መስለው ለመታየት ሞክረው የተሳካላቸው መስሎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ “ኢትንአዶ ለሰብእ ዘእንበለ ኢትርኣይ ተፍጻሜቶ” “መጨረሻውን ሳታይ ሰውን አታድንቀው” እንደሚባለው በሥራ አስኪያጅነታቸው ያደነቋቸው ሁሉ በዘመነ ጵጵስናቸው እጅግ አፍረው እንደነበርም የሚታወስ ነው፡፡

ሌላውን ሁሉ እንተወውና በእነዚያ ዓመታት አባ ሳሙኤል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ሥራ አስኪያጅና በተለይም ሊቀጳጳስ ሆነው የፈጸሟቸውን አስተዳደራዊ በደሎች፣ ልዩ ልዩ ሙስናዎች፣ በሥልጣን አለአግባብ የባለጉባቸውን ሁኔታዎች፣ በብዙ ሠራተኞችና አገልጋዮች ላይ ይደርስባቸው የነበረውን አስተዳደራዊ እንግልት አስመልክቶ በጊዜው ቤተክህነቱ የሚሰማበት ጆሮ አልነበረውም፡፡ ጉዳዩ እስከ ፓርላማ ደርሶም ሰሚ አልተገኘም፡፡ ስለዚህ በደረሰባቸው እጅግ አሳዛኝ ግፍና በደል ምክንያት መብታቸውን ለማስከበር ወደ ሕግ አቤት እንዳይሉ ጉዳዩ የሃይማኖት ነው፤ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ ሊገባ አይገባም በሚል ሕገ መንግሥቱን በተሳሳተ መንገድ እየጠቀሱ የብዙዎችን መብት ሲጨፈልቁና ብዙዎችን ሲያሰቃዩ እንደነበር፣ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት እንዳይችል ሕግ አውጥተው ይኸው እስከዛሬ በሕገ ወጦች ለሚደርስባቸው የመብት ጥሰት አቤት የሚሉበት ቦታ አጥተው በባርነት እንደሚኖሩ ይታወቃል፡፡ ይህን ያደረጉ አባ ሳሙኤል ናቸው፡፡ በዘመናቸውም 490 ያህል አገልጋዮች መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በሥራ አስኪያጅነታቸው ግማሽ ቀን ብቻ እየገቡ ለዚያውም አንዳንድ ቀን እየገቡ ቀሪ ሰዓታቸውን ከገንዘብ አቀባባዮቻቸው ጋር ሲሞዳሞዱ እንደነበሩት እንደ ቀሲስ በላይ አባ ሳሙኤልም በተለይ ሊቀጳጳስ ሳሉ ብዙ ጊዜያቸውን ያሳልፉ የነበረው ቢሮ ውስጥ ሳይሆን ሥላሴ ኮሌጅ በሚገኘው ቤታቸው ነበር፡፡ በዚያ ወቅት ይቀጠሩ የነበሩት በአብዛኛው በመንግሥት ባለሥልጣናት እና በማኅበረ ቅዱሳን በኩል የተላኩ ሰዎች ነበሩና እነርሱ እንዲቀጠሩ አማላጆቻቸውን ወይም መልእክቱን ይዘው የመጡትን ተቀጣሪዎችን ለማነጋገር በመኖሪያ ቤታቸው ያሳልፉ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡ በዚያ ጊዜ ብዙዎች በዚህ መንገድ ጉዳያቸው እንደተፈጸመላቸውና ቅጥርና ዝውውር እንደተከናወነላቸው ሲናገሩ መስማትም የተለመደ ነበር፡፡

አባ ሳሙኤል ዛሬ ለሕገ ቤተክርስቲያን መከበር ተቆርቋሪ መሆናቸውና ለፋይናንስ ሥርዓቷ መዘመን አሳቢ መስለው የደሰኮሩት ሁሉ ከዚያን ጊዜ ተግባራቸው ጋር ሲነጻጸር የሰማይና የምድር ያህል ይራራቃል፡፡ በዚያ ጊዜ ከየደብሩ “ገንዘብ ተዘረፈ ሙዳየ ምጽዋት ተገለበጠ” የሚሉ መረጃዎች ሲደርሷቸው “ጉዳዩ በአስቸኳይ ይጣራ” በማለት ፈንታ መረጃውን ይዞ የመጣውን ሰው አንገት በሚያስደፋ መልኩ “ምን አገባህ? አርፈህ አትቀምጥም?” በማለት ዘራፊዎችን ሲያበረታቱ፣ ለቤተክርስቲያን የተቆረቆሩትን ደግሞ በማሳፈርና በማዋረድ ዝርፊያን በቤተክርስቲያን ውስጥ ሲያደፋፍሩ እንደነበርና ከእርሳቸው በኋላ እየተስፋፋ ለመጣው ሙስና መሠረቱን የጣሉ መሆናቸው ፈጽሞ አይካድም፡፡

ይህም ብቻ አይደለም ከአንዳንድ አንስት ጋርም በቅድስና ጉዳይ ሲታሙና በቤተክህነት ከዚያ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ በርካታ ሴቶችን መቅጠራቸውና የሚያነጋግሩት ሴቶችን ብቻ ሆኖ በመገኘቱ ሲተቹ ነበር፡፡ እንዲያውም አንድ በዚህ ሁኔታ የመረረው ዲያቆን ወደጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሄዶ የአባ ሳሙኤል ወዳጅ እንደሆነ ወደሚታወቅ አንድ ዶ/ር ዘንድ ቀርቦ “ጾታዬን ለውጡልኝ” ይላል፤ ዶ/ሩም ደንግጦ “ምነው? በምን የተነሣ?” ቢለው ዲያቆኑም “አባ ሳሙኤልን ለማናገር አላስገባ አሉኝ፤ ቢሯቸው እንዲገባ የሚፈቀደው ለሴት ብቻ ሆኗል፤ እኔንም እንዲሰሙኝ ከወንድነት ወደ ሴትነት ጾታዬን መለወጥ አለብኝ ብዬ ስለወሰንኩ ነው” ይላል፡፡ ዶ/ሩም በሁኔታው አዝኖ አባ ሳሙኤልን እንዳናገራቸውና ዲያቆኑም በኋላ ላይ ሥራ እንዳገኘ ብዙዎች ያስታውሳሉ፡፡

እንዲህ ባለ ሁኔታ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ብልሹ አሠራርና ሙስና እንዲስፋፋ የአንበሳውን ድርሻ የተወጡት አባ ሳሙኤል፣ ለ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ቀጣዩ ፓትርያክ እኔ መሆን አለብኝ በሚል በርካታ ገንዘብ መድበውና ሰዎችን ቀጥረው በቤተ ክርስቲያን ባልተመለደ አኳኋን የምርጫ ቅስቀሳ ዓይነት ተግባር ሲፈጽሙ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ በመጨረሻም ሁሉ እንዳልተሳካላቸው አውቀውና አቡነ ማትያስ ፓትርያርከው ሆነው ከተሰየሙ በኋላ ሳይወዱ በግድ ዝምታን መርጠው ቆይተዋል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ግርግሮች ሲፈጠሩ አጋጣሚውን ዘወትር የሚናፍቁትን የፕትርክና ሥልጣን ለማግኘት ሊጠቀሙበት እንደሚፈልጉ እያሳዩ ነው፡፡ ከሰሞኑ በቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ተገኝተው የቅ/ሲኖዶስ አባላት ራሳቸውን በመስጠት ወቅቱን በዋጀ አካሄድ ቤተክርስቲያንን እንዲያድኑ ጥሪ ማቅረባቸውንና ስለ አስተዳደራዊ ችግሮችና የወደፊት ሥጋቶች መናገራቸውን እርሳቸውን ተጠቅሞ የሚፈልገውን መልእክት ማስተላለፍ የፈለገው ሐራ አስነብቦናል፡፡

በአጠቃላይ አባ ሳሙኤል ከስሕተታቸው የማይማሩ ሰው ናቸው፡፡ ሲጀመር ወደ አፋር ክልል አልሄዱ ጋምቤላም አላስተማሩ፣ አላጠመቁ፤ በዕውቀታቸው አልተፈተኑ፡፡ አራት ኪሎ ቁጭ ብለው ያገኙትን ጵጵስና እንደ ቀላል ነገር ነው የቆጠሩት፡፡ መጻሕፍትንና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ባለማወቃቸው በዚህ ዘመን የፖለቲካ ሰዎች እንኳን የተዉትን እርሳቸው ግን ከማኅበረ ቅዱሳን ተልእኮ በመቀበል ሥልጣን በሰጧቸው ፓትርያርክ በአቡነ ጳውለስ ላይ መፈንቅል አድርገው ፓትርያርክ ለመሆን የነበራቸው ቅዠት ከሽፏል፡፡ አሁን ቤተ ክርስቲያን እሳቸው ስለፈጸሙት ስለዚህ ስሕተት ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው እያለች ባለችበት ጊዜ ፍትሐ ነገሥቱንና መጽሀፈ መነኮሳቱን አንብበው አንድ ጳጳስ ለፓትርያርክ ሊሰጠው የሚገባውን ክብር ይቅርና እንዲሁ እንደ ክርስቲያንና በዕድሜ እንደሚበልጧቸው አባት ባለመቁጠር በማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያና በግል ጋዜጦች ስለተሳደቡት ስድብና የስንፍና ንግግር ይቅርታ ሳይጠይቁ አሁን ለሕገ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ በመምሰል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተስፋፋውን ሙስናና ብልሹ አሠራር ለማስተካከል ቅዱስ ፓትርያርኩ ሕግና ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ በሰጡት በሳል አመራር እየታየ ያለውን ጥሩ ጅምር ለማደናቀፍና ወደቀደመው ሙስናዊ መንገድ ለመመለስ በሚመስል መልኩ ሕግ ተጣሰ ቀኖና ፈረሰ ቢሉ ወይም ሐራ እንደዘገበው “እኛ ዘንድ ቀኖና እና ሥርዐት ሲጣስ ‘No’ ማለት የለም፡፡” ቢሉ ማንም አይሰማቸውም፡፡

በቀሲስ በላይ ዘመን በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ ካህናትና ሌሎችም አገልጋዮችና ሠራተኞች ሁሉ የፍትሕ ያለህ ሲሉ፣ አላግባብ ሲባረሩ፣ ሲዛወሩ፣ በአየር ላይ ሲንሳፈፉ የት ነበሩ? ምነው ያኔ ድምፃቸውን አላሰሙ? አሁን ለውጥ ተደርጎ ጥሩ ጅምር እየታየ ባለበት በዚህ ወቅት ብቅ ማለታቸው በራሱ ምን ያሳያል? ስለዚህ ስለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ በመምሰል በዚህ ወቅት ይህን ጉዳይ ይዘው ከመነሳታቸው በፊት በቅድሚያ ራሳቸው ስለጣሱትና የሲኖዶስ ስብሰባ በመጣ ቁጥር ዘወትር ስለሚጥሱትና ለጳጳሳት መጥፎ አርኣያ በመሆን ቀኖና ቤተክርስቲያን እየጣሱ ስላለበት ተግባር ንስሐ ቢገቡ ይሻላል፡፡ ቀድሞውኑ ለስሕተት የዳረጋቸው ማኅበር አሁንም ለሌላ ስሕተትና መፈንቅለ ፓትርያርክ እያጫቸው ነውና “ወተት ላይ የለመደ በማር ላይ ሄዶ ሞተ” እንደሚባለው አቡነ ጳውሎስ ላይ የለመዱት አቡነ ማትያስ ላይ ላይሰራ ይችላልና ሌላ ስሕተት መድገም እንዳይሆንባቸው መጻሕፍትን እየመረመሩና ታሪክን እያገናዘቡ ቢያስተውሉ ይሻላል እላለሁ፡፡

መደረግ ያለበት ሌላው ጉዳይ ሌሎቹ ጳጳሳት ሀገረ ስብከት ይዘው በየጠረፉ በየበረሃውና በየገጠሩ ሲንከራተቱ አባ ሳሙኤል ግን አራት ኪሎን በሊዝ የገዙትና ከማኅበሩ ጋር ያላቸው ቃል ኪዳን ይፈርስ ይመስል ከአራት ኪሎ እንዳይወጡ የተደረገው አሰራር ተሽሮ ወጣ ብለው እንደሌሎቹ ጳጳሳት ቀድሰው አቁርበው አስተምረው ትርፋቸው ቢመዘን ጥሩ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡

27 comments:

 1. ከመጠምጠም መማር ይቅደም!
  የክብር ዲቂና: ቅስናና ጵጵስናም ይቁም።

  ReplyDelete
 2. Bewenet Betam tasazenalathu Balefew kerasathu yehunewen be samedi zemute yewedekewen sew Bewer lememekerena lemegesete ametat fegebathu enaneten yaledegefewen lemakalele abait thekulathu yeneseha edemai yesetene ke enat baitekereseteya ke dougmawa ayeleyen AMEN

  ReplyDelete
 3. aha! ye tehadiso menafiku budin teqorqoari mhonachihu now!

  ReplyDelete
 4. እኔ ምለው ለእያንዳንዱ ጉዳይ ማህበረ ቅዱሳን ካላነካካችሁ መጻፍ አትችሉም እንዴ? እስቲ አሁን ይሄን ምን ይሉታል?

  ReplyDelete
 5. You, Aba Selama groups don't have the moral to judge others

  ReplyDelete
 6. "ኢትንአዶ ለሰብእ ዘእንበለ ኢትርኣይ ተፍጻሜቶ" “መጨረሻውን ሳታይ ሰውን አታድንቀው” የሚለው ቃል መጽሐፈ ሲራክ ላይ እንደሚገኝ መግለጽ ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 7. በክፉ አገልጋዮቿ ክፉ ሥራ መከራ በማየት ላይ ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን የዘመናት ዕድሜ ያላቸው መናፍቃን፣ የስዕለት ገንዘብ በመዝረፍ ላይ ያሉ አስተዳዳሪዎች ጸሐፍትና በአጠቃላይ አማሳኞች ፣ የአባቶችን ቆብ ደፍተው በውስጥ የተሰገሰጉ ፖለቲከኞች፣ በማህበራት ስም እና በግል ጭምር ዝና እያካበቱ በሀገር ውስጥና በውጭ ጉባኤ፣ መዝሙር፣ ስብከት የሚሉ ነጋዴዎችም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት በተቃራኒ የቆመው ማህበረ ቅዱሳንም ጭምር የቤተክርስቲያኒቱ አራሙቻዎች (እንክርዳዶች) ናቸው፡፡
  ከእነዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ የሚብሰው አባ ሳሙኤል የተባለ አስመሳይ ነው ከዚያ ኮሌጅ ምድር ቤት ምሽግ ይዞ ቀን ዕየጠበቀ ፓትር
  ርክ የመሆን ህልሙን ለማሳካት በማህበረ ቅዱሳን ምርኩዝ እየያዘና እየዘለለ ወጣ ይላል፡፡
  በመሆኑም እኔ ጻድቅ ነኝ እያለ ሕዝብን ወደ አመጽና ሁከት የሚነዳ ጳጳስም ቢሆን፣ ባህታዊ፣ ሰባኪም ይሁን ዘማሪ ማህበርም ይሁን አክስዮን የምእመናንን ይሁንታ ማግኘት የለበትም፡፡ ሁሉም የበደለ፣የገደለ፣ የሰረቀ፣ያቀበለ፣አመጸኛ ነው፡፡
  ቤተክርስቲያን ከያዛት መከራ ትላቀቅ ከተባለ እግዚአብሄርን በሚፈሩ/በሚያውቁ አገልጋዮቿ ትመራ/ትገልገል/ትሞላ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ክፉ አስመሳይ!ዝም ብለህ አትዘላብድ። እንደ እንስሳ ከማሰብ እንደ ባለ አዕምሮ አስብና ያንንም ይህንም እንዲህ ከሆነ በሚሉ ባዶ ስሜት አትወራጭ። ትክክለኛ አስተሳሰብ አለኝ ካልክ የሌሎችን ቤተ እምነትና አምልኮ ለባለቤቶቹ ተውት አድርጎ ተደራጅተህ ያመንክበትን መመስረት ነው። ከዛ ውጭ በመምሰል ዝባዝንኬ ተራ ጭፈራ ከንቱነትህን ከማጋላጥ ውጭ ምንም ማድረግ አትችልም። ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ተመስርታላችና የትኛውም የአሉባልና ወሬ ወጀብም ሆነ የስድብ ሞገድ አያናውጣትም።

   Delete
 8. አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል አሉ እሟሆይ።

  ReplyDelete
 9. Tsere tewahedowoch atidkemu,Geta Alelatina Tewahedo benante were atitefam.

  ReplyDelete
 10. ኮሌጁ የምሁራን መድረክ ይመስለኝ ነበር ለካ የደናቁርት መደበሪያ ነው ሳይማሩ የሚያስተምሩበት ሳያውቁ የሚታወቁበት የተራ ሰዎች መድረክ ሆኖ መገኘቱ የኮሌጁ እስታንዳርድ ወይም ደረጃ እጅግ ዝቅ የሰደርገዋል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ፀጥ በለ አንተ አስመሳይ ሰይጣን! ተራ ማህይም። መጀመሪ ስሌሎች እምነትና የማሰልጠኛ ተቋም መዛኝ ከመሆንህ በፊት እራስህን ሁን!ይህን የአረቄ ቤት የቦዘኔ ወሬ ይዘህ አትደንፋ። እዛው በአዳራሽህ ሯሟ ሷ ተረረ እያልክ በርኩሱ መንፈስ ሙሌትህ አጏራ።

   Delete
 11. ይህ ብሎግና ፀሐፊ ተብዮዎች ዋልጌና ተራ ተሳዳቢዎች ጥርሳቸውን በአልኮል ያወለቁ ጥርቅሞች ናቸው። ትናንት በአላማ የሚመስላቸውን በአፈፃፀም የተለያቸውን አቶ አሸናፊን በግብረሰዶማዊነት ሲወርፉት ነበር። ከሱጋ ተስማሙ መሰለኝ ወደ ሚዋጓት የክርስቶስ ቤተክርስቲያንና ወደ አገልጋዮቿ ዘወር አሉ። በእናንተ የየመጠጥ ቤት ወሬና የእብዶች ድንፋታ ቤተክርስቲያንም ሆነች አገልጋዮቿ የሚዳከሙና የሚወድቁ አይምሰላችሁ። እናንት የእውነት አሳዳጆች በአልኮልና በውንብድና የፊት ጥርሳችሁን ያረገፋችሁ ተራ ወሬ አራጋቢዎች ከዚህ ከክስና ስም አጥፊነት ተግባራችሁ የማትታገሱ ከሆነ ፍፃሚያችሁ መድቀቅ ነው። ምክንያቱም እየተጣላችሁ ያላችሁት ከቤተክርስቲያንና ከአገልጋዮቹ ጋር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ነውና። ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ደግሞ ይደቃሉ ተብሏልና። እናንት አስመሳዮች እራሳችሁን መሆን የማትችሉ የናንተ ያልሆነው ስም እየተጠቀማችሁ ዘወትር ስለማትኖሩበትና ስለግለሰቦች የፈጠራ ተውኔትን የምትተውኑ ክርስቶስን እንደማታታልሉት እወቁ።

  ReplyDelete
 12. በጣም ዘቀጣቹ በትንሳኤ ሰሞን ምን አለ ትንሸ ሰለትንሳኤው አውርታቹ ክርሰቲያን ለመምሰል ብትሞክሩ እሱእንኳን ካቃታቹ ዝም በሉ ማፈሪያዎች

  ReplyDelete
 13. ዳሞት የምትጠቀማቸው ቃላት ከክርስቲያን የማይጠበቁ ናቸው ችግሮችን በስድብ ሳይሆን እውነትን በመያዝ ጤናማ ቃላት እየተጠቀህም ምክር በርታ ሰው ሁን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምንም አይነት ችግር የለብኝም ውንድሜ: እኔ እያድረግሁኝ ያለሁት በማስመሰል መናፍቃንና የመናፍቃን ማንፌስቶ አራማጆች ሆነዉ ሳለ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታይ መስለው ለምያራምዱት ክህደት, አሉባልታ, ስድብ, ስም ማጥፋት, አስመሳይነት, ዎንጌልን ማጣመም, በዎንድሞች መካከል ጥልን ምዝራት በአጠቃላይ የሰይጣናዊ ተግዳሮታቸው ነው: ሰው ሁን ላልከው እያመሰኝሁኝ አንተም ከማስመሰልና ንፋስ እንደሚያዎዛውዘው ዛፍ ዎደዛ ዎደዜህ ማለቱን ትተህ ሰው ሁን: እውነትን ጠይቆ ለማውቅ እንጅ በአረቀቤት ውሬ የማትነዳና በእንቅርዳድ የማትታነቅ ሰው ሁን:

   Delete
  2. Berta wodaje damot. This is what saint paulos was doing for anti religions.

   Delete
 14. ግሩም ጽሑፍ

  ReplyDelete
 15. መጽሐፍ አሳተምኩ እያሉ የዘረፉት የምስኪን አገልጋዮች ጻማ ገንዘብና የመሳሰሉት ነጥቦች ቢቀሩም የተቀማውን የሚያስመልስ የተበደለውን የሚያስክስ በአጠቃላይ ንስሀ የሚያስገባ ከሆነ ይበል ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Nissiha, Nissiha,... Yilutal Injji Ayawquttim! Lefi!

   Delete
 16. መሀይሙ ዳሞት እርር ድብን በል

  ReplyDelete
  Replies
  1. እሽ ተራጋሚው ሰይጣን ፤ ወንጌል አጣማሚው፤ የቅዱሳት መጽሐፍት ነቃፊው፤ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ጠላት እሽ እርር ድብን እልልሀለሁ።

   Delete
 17. የተሃድሶ—የአባ ሰላማ—ዲያብሎስ ለቤተክርስቲያን አስተዳደር መጨነቅ - “ጅብ በማያውቁት አገር ቁርበት አንጥፉልኝ አለ” የሚለውን ብሂል የሚያስታውስ ነው

  ReplyDelete
 18. በተጻፈው ጉዳይ ለአባ ሳሙኤል የሚከራከር በገንዘብ የተገዛ ወይም የሙስና በር የተከፈተለት እንጂ ለእውነት የቆመ አይደለም፡፡ ስለዚህ እባካችሁ በጭፍን ከመሳደብ ነገሩን አባ ሳሙኤል ሰርተውታል አልሰሩትም በሚለው ላይ ተቹ

  ReplyDelete
 19. አሁን አባ ሳሙኤል ይህን አሳብ ያቀረቡ ሕይወት ቀጣይ መስሏቸው የቀራቸውን ዘረፋና ጭቆና
  ለማካሄድ አመች ሁኔታ ይፈጠርላቸው ዘንድ እንጂ ዕውነት ሆኖ አይዶለም። እንኳን የዘመናችን ትውልድ
  የድሮ ዘመን ትውልድ ስንኳ ከስንት አንድጂ እንዳማረበት አፍን ሞልቶ መናገር አይቻልም። ከበስተጀርበ ሆኖ የሚጠናወታቸው እንዳለ ባለመግንዘባቸው ነገር ዓለሙን ዘንግተው እስከጊዚያቸው አዝግመዋል።
  እነማን ብትለኝ እነዚያ ናቸዋ! እጸንሖ ለአሞሬዎን እስከ ይትፌጸም ኀጢአቱ ያለውን በጥልቀት ይመለከቷል

  ReplyDelete