Saturday, April 18, 2015

አዲሱ ገበያ የሚገኘው ደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን በአለቃው እየታመሰ ነውበአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙ የደብር አለቆች አብያተ ክርስቲያናትን የሚመሩ እንደመሆናቸው መጠን ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ይህን ኃላፊነታቸውን የሚወጡ አለቆች መኖራቸው ባይካድም ሥልጣናቸውን ለተለያየ የግል ጥቅም በማዋል ብልሹ አስተዳደርን ያሰፈኑ፣ የቤተክርስቲያንን ሀብትና ንብረት የሚዘርፉ፣ ለዚህም እንዲረዳቸው ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ማበርና የማኅበሩ ወዳጅ በመሆን ከተጠያቂነት ውጪ የሚሆኑ፣ ማቅም ታማኝ ወዳጆቹ አድርጎ የሚቆጥራቸው አለቆች አሉ፡፡ እንደእነዚህ ያሉትን አለቆች ማቅ ማሳኝ-አማሳኝ መሆናቸውን ቢያውቅም ስለእነርሱ “በጎነት” እንጂ ማሳኝ-አማሳኝነት ከቶም ቢሆን ማውራት አይፈልግም፡፡ እነርሱም በቤተክርስቲያን ያሻቸውን እያደረጉ ስለሚገኙና ጥፋታቸውን ማቅ በዝምታም ቢሆን ስለሚሸፍንላቸው እነርሱም በበኩላቸው ለማቅ ውለታ ብድራት ይሆን ዘንድ በየደብሩ ያሉ የማቅ ወኪሎች “እገሌ ተሐድሶ ነውና እርምጃ ይወሰድበት” ብለው “ብላክሊስታቸው” ላይ የከሰሱትን አገልጋይ ሲጠቁሟቸው በዚያ አገልጋይ ላይ ሥልጣናቸውን መከታ በማድረግ ልዩ ልዩ ሕገወጥ ድርጊት እየፈጸሙባቸው እንደሚገኙ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ እንዲህ እያደረጉ ከሚገኙ አለቆች መካከል አንዱ የደብረሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስታየን አስተዳዳሪ አንዱ ናቸው፡፡
እኚህ ሰው አስቀድሞ የገነተ ጽጌ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሙዳየ ምጻት አዟሪ ባለትዳርና የልጆች አባት የነበሩ ሲሆን፣ በምን ምክንያትና የት እንደ መነኮሱ ሳይታወቅ መንኩሰው አለቃ ሆነው ተመለሱ፡፡ አለቃ ሆነው በሰሩበት በጃቲ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን በፈጸሙት ውንብድና ተባረው ለ4 ወር ያህል ያለ ሥራ ቆይተዋል፡፡ አሁንም ጳጳሱን አባ ሳሙኤልን ተገን በማድረግ በደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ውስጥ ልዩ ልዩ የውንብድና ሥራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ከሚጠቀሱት መካከል
·        ከኃላፊነታቸው ከተነሡት ከሊቀ አእላፍ በላይ ጋር በመመሳጠር ከሰራተኞች ገንዘብ እየተቀበሉ ሕገወጥ ቅጥርና ዕድገት መፈጸም፣ ለዚህም ገንዘብ ተቀብለውናል ሲሉ አባ ቤዛ የሺዓለም ከአሳራጊነት ወደ ሰባኪነት፣ እንዲሁም አባ ተክሌም በተመሳሳይ ሰባኪ ሆኛለሁ በማለት “ጉዳ” ለተባለ በቤተክርስቲያን ገንዘብ ቤቱን እየገነባ ላለ የልማት ኮሚቴ አባል መናገራቸው ታውቋል፡፡ “ጉዳ” የሚባለው የህንፃው እቃ ግዢ ያለምንም የደብሩ ፈቃድ እቃ ይገዛል፤ አጂፕ አካባቢ ትልቅ ህንፃ የገነባ ሲሆን፣ የእህቱ ባል ዲ/ን ይድነቃቸው ደግሞ የህንፃ ኮሚቴ ተከፋይ ነው፡፡ 

·        በዚሁ ዓመት ለገና በዓል እንደዔሊ እየተጓዘ ካለውና ከፍተኛ ሙስና ከሚፈጽሙበት የሕንጻ ሥራ ገቢ ላይ ለካህናት ቦነስ ልክፈል ብለው የወሰዱትን ብር የት እንዳደረሱት እስካሁን ድረስ አልታወቀም፡፡
·        በተመሳሳይ ሁኔታም ለሀገረ ስብከቱ ፐርሰንት ልክፈል ብለው ከሕንጻ አሰሪው ኮሚቴ የወሰዱትን ብር ለሀገረ ስብከቱ ገቢ ያላደረጉ መሆኑ ግልጽ ሲሆን ገንዘቡን እምጥ ያግቡት እስምጥ አልታወቀም (አዲሱ ሥራ አስኪያጅና ምክትላቸው ትኩረት ሊሰጡት ይገባል)፡፡        
·        ማኅበረ ቅዱሳን ከአባ እስጢፋ ጋር በመተባበር ያለካህናቱ ፈቃድ፣ ዕውቅናና ተሳትፎ በካህናቱ ላይ የለውጥ መዋቅር የተባለውን ረቂቅ ሕግ በኃይል ለመጫን እንቅስቃሴ ያደርጉ በነበረ ጊዜ “የለውጥ መዋቅር” የተሰኘውን የማቅ ረቂቅ ሕግ “በመንግሥት ተፈቅዷል” ብለው በዐውደ ምሕረት ላይ ያነበቡ ብቸኛ አስተዳዳሪ ናቸው፡፡
·        አባ ገ/ሚካኤል ለውንብድናቸው ተባባሪ የሚሆኗቸውንና በጥቅም የተሳሰሯቸውን ግለሰቦች በመመልመልና በሰበካ ጉባኤ ውስጥ በመሰግሰግ ይታወቃሉ፡፡ ለምሳሌ አቶ ዮናስ ሽፈራው የተባለውንና ሚስቱን ፈትቶ ሌላ ሚስት በማግባት ከቤተክርስቲያን ህግ ውጪ የተሾመውን ሰው ከግሮሰሪ ጠርተው የሰበካ ጉባኤ ሊቀ መንበር አድርገዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በደብሩ ውስጥ እንዲፋንን በአንጻሩ ደግሞ ለተሠራለት ውለታ የእርሳቸውን ውንብድና እንዲሸፈንና ጥበቃና ከለላ እንዲሰጣቸው ለማድረግ በሚል ከቃለ አዋዲው ውጪ የአጥቢያው ምእመን ያልሆነና ቅጽ ውስጥ ያልነበረ ዶ/ር ኃይሉ የተባለ ግለሰብ የሰበካ ጉባኤ አባል አድርገዋል፡፡
·        በየጊዜው ለአገልጋዮች ደሞዝ አለመክፈል፣ ቦነስ መከልከል፣ ካህናቱ እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ረገጣ እንዳይጠይቁ መድረኩን በመቆጣጠርና እንደሰካራም ቀንድና ጭራ የሌለው ነገር በመቀባጠር በተለይም “መሬት አሰጣችኋለሁ” በማለት ትኩረት በማስለወጥ በካህናቱ እየተጫወቱ ነው፡፡
·        የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴዎች በግልጽ እንዲህ ዓይነት ወንበዴ አለቃ እንዳልገጠማቸው ለምእመናን እየተናገሩ መሆናቸው የአባ ገ/ሚካኤልን ማንነት የሚገልጽ ትልቅ ምስክር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አለቃውን እየተባበሩና ከሕንጻው ገቢ እያገኙ ያሉት ዲ/ን ይድነቃቸው መኮንን እና ወጣት የትናዬት ኃይሉ የተባሉ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሆነው ገንዘብ የሚመድቡና ለአባ ገ/ሚካኤል እየተከላከሉና ሽፋን እየሠጡ መሆናቸው የሕንጻ አሠሪውን ኮሚቴ እያነጋገረና ዓላማቸው ግራ እንዳጋባው ይገኛል፡፡
·        ፎርማን ባይሳ የማቅ አባል ሲሆን የወር ደሞዙ 8 ሺህ ብር ነው እዚህ ቦታ ላይ ከገባ ወዲህ አንድ ዲኤክስ መኪና ገዝቷል፣ ሌላው ካህን ከሚያገኘው እጅግ ከፍ ያለ ክፍያ ነው የሚከፈለው፡፡
·        የአቶ ሀይሉ መላኩ ልጆች እስጢፋኖስ እና የትናዬት የማቅ አባል ሲሆኑ፣ አንዱ የህንፃው ሌላው የሰበካ ጉባኤ አባል ሆነው መንግሥትንም አሁን ያሉትን ፓትርያርክም በግልፅ ይቃወማሉ (አባታቸው ለደብሩ የመርቆሬዎስን ፅላት ቀርፀው ያስገቡ ሲሆን፣ በዚህ ፅላት አማካይነት በሟርት ነው ሀብት ያካበቱት ተብሎ በሰፊው ይወራል) ካወሩት አንዱ ገ/ሚካኤል ናቸው፡፡
·        አሁን በቅርቡ ህንፃ በውርስ ያገኘውን ቤት ያለምንም የደብሩ ፈቃድ ጨረታ 2 ሚሊዮን 5ዐዐ ሺሕ ተሸጦ የት እንደደረሰ አይታወቅም፡፡
·        አለቃው ቤተ ክርስቲያኑን የፖለቲካ ማራመጃ ከማድረጋቸው የተነሣ በወንጌል ስብከት ሊያሳርፍ የሚመጣውን ሕዝብ በመንግሥት ላይ የሚያነሳሳ ትምህርት ሲሰጡ የነበረ ሲሆን ሕዝቡም መንግሥት የለም ወይ እያለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህም ግለሰቡ የማቅ የፖለቲካ ሙሌት መሆናቸውን እያስመሰከሩ ነው፡፡
·        በቅርቡ የሆሣዕና ዕለት ለሕንጻው ማጠናቀቂያ እስከ ትንሣኤ 3 ሚሊዮን ብር ማግኘት አለብን ብለው የመስተንግዶ ኮሚቴ ሰይመዋል፡፡
·        በደብሩ ጥበቃዎች እንደተገለፀው አባ ገ/ሚካኤል በኮንትራት ታክሲ ሴት እያስገቡ አድራ ሌሊት እንደምትወጣ ጉዳዩን ለህንፃ አሰሪ ኮሚቴዎች አሳይተው የህንፃ አሠሪ ኮሚቴው በስብሰባው ላይ አንስቶት ነበር፡፡
·        ላዛሪስት አካባቢ ሠብለ የተባች ሴት ግልፅ በሆነ ሁኔታ በቅምጥነት ያስቀመጡ ሲሆን ብዙ ጊዜ ውሏቸውና አዳራቸው እዚያው ሆኖአል፡፡ እጅግ በጣም ሕዝቡን ከመናቃቸው የተነሣ ባለፈው ሳምንት የስቅለት ዕለት ስለታረደው የእግዚአብሔር በግ ስለ ክርስቶስ ሕማምና መከራ ከማስተማር ይልቅ በማይክራፎን በግ ለጨረታ በማስተዋወቃቸው ምእመናን እጅግ  ተማረው እንደነበር ይገልጻሉ፡፡ በትንሣኤ ሌሊት ላይ በጉ ለማን እንደወጣ ሳይታወቅ ወጥቶአል ብለው መናገራቸውንና በጉን ግን ላዛሪስት ላለችው ቅምጣቸው ለሰብለ መውሰዳቸውን የተመለከቱ የሰንበት ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡
·        የቤተ ክርስቲያኑ ዋና ፀሐፊ ሊቀ ስዩማን ሳለ አምላክ ለሰውየው የሚመጡ ግልፅ ክሶችን ደብቆ በመያዝ፣ ሰውየው ለሚያደርገው ህገወጥ ሥራ ሽፋን በመስጠት ብሎም  በመተባበር የማህበረ ቅዱሳን አባላት ፅፈው በሚሰጡት ደብዳቤ ላይ ማህተም እንደሚያደርግ ምንጮች ያስረዳሉ፡፡ ባለው ሥልጣን መጠቀም አልቻለም ይላሉ፡፡ እሱ ደግሞ “ሰውየው እብድ ነው ምን ላድርግ?” ይላል ይላሉ፡፡
·        የሰንበት ት/ቤት አባል ዲ/ን ዮናስ መኮንን፣ አስፋው እና ሃይማኖት የተባሉ ግለሰቦች በሕሙማን ስም ከህዝብ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መድኃኒት እንረዳለን ብለው ቢወስዱ ሆስፒታሉ ከአምናው ልምድ በመነሣት ህገወጥ ስጦታ ነው ብሎ በዘንድሮ ፋሲካ ሳይቀበላቸው መልሶአቸዋል፡፡ አምናም ተመሳሳይ ችግር የተፈጠረ መሆኑን ዘግበን እንደነበር ይታወሳል፡፡ ገንዘቡም የት እንደ ደረሰ አልታወቀም፡፡
·        የህንፃው አሰሪ ግዢ ክፍል የሆነው ጉዳ ለንስሐ አባቱ እንደተናገረው አንተም ከምትዘርፈው ገንዘብ አካፍለኝ ያለበለዚያ ታቦቱን አሁን ባለበት አስገብተን አስመርቀን በኋላ አንተና የእህትህ ባል ገንዘብ ታጣላችሁ እያለ አባ ተክለጊዮርጊስን እንደጠየቀ ራሳቸው መስክረዋል፡፡
እነዚህን ለአብነት ያህል አነሣን እንጂ አለቃው እየፈጸሟቸው ያሉ እጅግ በርካታ ችግሮች አሉ የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ከዚህ ቀደም በጃቲ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን ዓይነት ብጥብጥ የሚያስነሣ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ ስለዚህ እንደነዚህ ዓይነቶቹን ተጠሪነታቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን አድርገው ቤተክርስቲያንን እየበደሉ ለግል ጥቅማቸው እየሰሩ ያሉ አለቆችን መስመር ማስያዝ አስፈላጊ በመሆኑ አዲሱ የሀገረ ስብከቱ አመራር ሊመለከታቸውና ተገቢውን እርምጃ ሊወስድ ይገባል እንላለን፡፡         

2 comments:

  1. abat wesha yemetgaga weshat betaweru men alabet

    ReplyDelete
  2. ህግይህርህ

    ReplyDelete