Wednesday, April 8, 2015

የዲያቆን አሸናፊ መኮንን አሳዛኝ ፍጻሜና ግብረ ሰዶማዊነቱን የሚያስረዱ መረጃዎች

Read in PDF


የአሸናፊ መኮንን ጉዳይ ለብዙዎች አሳዛኝም አስደንጋጭም ነው። ለማንም ሰው ቢሆን የአሸናፊን ግብረሰዶማዊነት መቀበል ይከብዳል። የሆነው ነገር የሆነ ነው። ከሆነው ነገር ይበልጥ የሚከብደው ለመመለስ እና ንስሀ ለመግባት ፈቃደኛ ያለመሆኑ ነገር ነው። ብሎጋችን ይህን ጉዳይ ለመጻፍ በእጅጉ ተፈትናለች። የአሸናፊን ግብረ ሰዶማዊነት ብናምንበትም ይመለሳል ንስሐ ይገባል በሚል ተስፋ እየጠበቅን ነበር። ግን አልሆነም ይህ ሳይሆን ሲቀር የሚኖረን ምርጫ ሁለት ነው። አንደኛው ከነሀጢአቱ የወደደውን እያደረገ ይቀጥል የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ለእግዚአብሔር ክብር የማይመቹ ነገሮችን ሁሉ በዝምታ ማለፍ ከጉዳዩ ጋር ከመተባበር ስለሚቆጠር የዲያቢሎስን ሥራ መግለጥ አለብን የሚል ነው።
የመጀመሪያው ምርጫ ከእግዚአብሔር ያጣላል። ጌታችን ያወገዘውን ኃጢአት መተባበርም ይሆናል። ይህ የማይሆን ነገር ነው። ሁለተኛው ምርጫ ግን ተገቢ እና ትክክለኛ ነው። ግን በእጅጉ ተስፋ አድርገን በምንጠብቀው ሰው የሆነ ነገር ስለሆነ ፈታኝ ነው። ግን ኃጢአትን ወቃመም አግባብነት አለው። አንዳንድ ሰዎች ለምን ሚስጢር ሆኖ አይቀርም ለምን ይጻፍበታል በሚል እንደሚሞግቱ ይታወቃል። ያ በሁለት ምክንያት አማራጭ ሊሆን አይችልም። የመጀመሪያው ለንስሀ ዝግጁ ያልሆነን ሰው ኃጢአት መሰወር ከኃጢአቱ ጋር እንደ መተባበር ስለሚቆጠርና ሁለተኛው ደግሞ አሸናፊ መኮንን ንስሀ እንዲገባና እንዲመለስ ሊረዱት የሞከሩትን ሰዎች ሁሉ በስም አጥፊነት ፈርጆ እነርሱን የማጥቃት ከፍተኛ ዘመቻ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም እያካሄደ ስለሚገኝ ነው።

ይህን ጉዳይ ጸሀይ እንዲሞቀው የፈለግንበት ተጨማሪ ምክንያትም አሸናፊን ለማሳጣትና ለመወንጀል ከመፈለግ አይደለም። ነገር ግን ጉዳዩ የቤተክርስቲያንን ኅልውና የሚፈታተን በመሆኑ መረጃው የሌላቸው በጭፍን ከመደገፍና ከመቃወም እንዲድኑና ለእግዚአብሔር ክብር እንዲኖሩ፣ እንዲህ ያለው ነገር ወደ ብርሃን እስካልወጣና ድርጊቱን የሚፈጽሙ ሰዎችን ተመለሱ ማለት እስካልተቻለ ድረስ በትውልድ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከባድ በመሆኑ ነው።
በሐዋርያት ዘመንም ቢሆን በተለያየ ኃጢአት ተይዘው ቤተክርስቲያንን የሚያውኩ ሰዎችን ማንነት ምዕመናን እንዲያውቁና እንዲጠነቀቁ ተጽፏል። እኛም ይህንኑ ከግምት በማስገባት ዲያቆኑ በጓዳ የቀረበለትን ተደጋጋሚ የንስሐ ጥሪ አልቀበል በማለቱ ሌላ የንስሐ ጥሪ ለማስተላለፍና ሌሎች ሰዎችም ከዚህ አይነት ኃጢአትና በዚህ ኃጢአት ከተጨማለቀ አገልግሎት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማስገንዘብ ጭምርም ነው፡፡ ይህ ጽኁፍ ባለፈው ሳምንት ወጥቶየነበረው ቀጣይ ነው። ዝርዝር ታሪኩን ከማስቀመጥ ጋር መረጃዎችን ማያያዝ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
የመጀመሪያው መረጃ ቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎትን ከዲያቆን አሸናፊ ጋር የመሰረቱ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት የአሸናፊ መኮንን ግብረ ሰዶማዊነት ካወቁ በኃላ ንስሀ እንዲገባ ያደረጉትን ተደጋጋሚ ጥረትና ያደረጉትም ጥረት አልሳካ በማለቱ ኃላፊነታቸውን ለማውረድና ከአገልግሎቱም ለመሰናበት ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ያስገቡት ደብዳቤ ነው። ይህ ደብዳቤ የጠቅላላው ጉባኤ አባላት የአሸናፊ መኮንን ግብረ ሰዶማዊነትን ካወቁ በኋላ ኃጢአቱ በጽድቅ ንስሐ እንዲገባበት ያደረጉትን ጥረትና ያሳለፉትን ውጣ ውረድ የሚያሳይ ነው።
 መስራች አባላቱ ለፌደራል ጉዳዮች ያስገቡትን መልቀቂያ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ

የመስራች አባላት ደብዳቤ ስለግብረ ሰዶማዊነቱ እንዲህ ሲል አሉኝ የሚላቸውን መረጃዎች ይጠቅሳል

 • ·        በሥራ አስኪያጁ የግብረ ሰዶም በዲያቆን አሸናፊ መኮንን የግብረ ሰዶም ጥቃት ሙከራ የተደረገባቸው ሰዎች በመኖራቸው
  ·        የነዚህን ሰዎች ምስክርነት የሰማን የጠቅላላ ጉባኤውን ሰብሳቢ ጀምሮ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት የሆንን አምስት ሰዎች በመኖራችን
  ·        የጠቅላላ ጉባኤው አባላት ባይሆኑም ሌሎች ተጨማሪ ምስከክርነቱን የሰሙ ስድስት በመኖራቸው
  ·        ዲያቆን አሸናፊ የግብረ ሰዶም ድርጊት መፈጸሙን ያመነላቸው የጠቅላላ ጉባኤውን አንድ አባል ጨምሮ በአካል ያመነላቸው ስድስት ሰዎች እና በስልክ ያመነላቸው ሁለት ሰዎች በመኖራቸው
  ብሎ ያስቀምጣል።

በስተመጨረሻም ለመልቀቅ የወሰኑባቸውን ምክንያቶችም እንዲህ ዘርዝረዋል።

·        የጉባኤው መሪ በግብረ ሰዶም ኃጢአት መውደቁና በምስክር በመረጋገጡ በወንድሞች ህይወት ላይ ችግር በመፍጠሩ

·        ይህ የግብረ ሰዶም ሃጢአት ሙከራው በተፈጸመባቸው ምስክሮች ሲገለጥ ንስሐ እንዲገባ ሲጠየቅ ፈቃደኛ ከሆነ በኋላ ሀሳቡን ቀይሮ በእምቢታ በመጽናቱ

·        በዚህ በተፈጠረው ችግርና በሌሎች በጉባኤው አገልግሎት ውስጥ ባሉ ብልሽቶች ተወያይተን መፍትሔ እናምጣ ብለን ብንጠይቅ ተቀባይነት ባለማግኘታችን
·        ድርጊቱ ወንጀል በመሆኑና በተበዳይ ግለሰቦች ላይ የተፈጸመው ኢሰብአዊ ኢመንፈሳዊ ኢህጋዊ ድርጊት በመሆኑ

ሁለተኛው ደብዳቤ ደግሞ አገር አቀፍ የሆነው የወንጌል አገልግሎት ማኅበራት ኅብረት የአሸናፊ መኮንንን ግብረ ሰዶማዊነት ከሰማ ጀምሮ እውነት መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ያለፈበትን መንገድ እና የጉዳዩን እውነትነት ካጣራም በኋላ ለመፍትሔ የሄደበትን መንገድ የሚጠቁምና ለአባል ማኅበራቱ የበተነው ደብዳቤ ነው። ይህ እንቅስቃሴ ግን በአሸናፊ በኩል ኩርፊያን ከማስከተል ባለፈ ያመጣው ለውጥ አለመኖሩና ከዚህም በመነሳት ያሳለፈውን ውሳኔ የሚያመለክት ነው።

ውሳኔው እንዲህ የሚል ነው

 • ህብረቱም ሆነ አባል ማህበራቱ ለእግዚአብሔር ክብርና ለህብረቱ አገልግሎት ጤናማነት ሲባል፡-
  ·        ለአባሎቻቸው ይህንኑ በየጉባኤያቸው እንዲያሳውቁ
  ·        ከቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎትና ከዲያቆን አሸናፊ መኮንን ጋር ያላቸውን መንፈሳዊ ህብረት እንዳቋርጡ
  ·        የአገልግሎቱንም ሆነ የግለሰቡን አገልግሎትና የጽሁፍ ውጤቶች እንዳይጠቀሙና ሌሎችም በማሰራጨት ተባባሪ እንዳይሆኑ የወንጌል አገልግሎት ማኅበራት ህብረት የወሰነ መሆኑን ያሳውቃል።
በአሸናፊ ግብረሰዶማዊነት በጣም አዝነናል ልባችንም ተሰብሯል። ልንረዳው የምንችለው ግን ንስሐ እንዲገባና እንዲመለስ በመምከር ብቻ ይሆናል። ልቡ ለእውነተኛ ንስሃ እንዲነሳሳና እንዲመለስ በእግዚአብሔር ቃል ጥሪ እናስተላልፍለታለን። 

«......እንዲህም ትላቸዋለሁ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የወደቁ አይነሡምን? የሳተስ አይመለስምን? እንግዲህ ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘወትር ስለ ምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኰልን ይዞአል ሊመለስም እንቢ ብሎአል። አደመጥሁ ሰማሁም ቅንን ነገር አልተናገሩም ማናቸውንም። ምን አድርጌአለሁ? ብሎ ከክፋቱ ንስሐ የገባ የለም ወደ ሰልፍም እንደሚሮጥ ፈረስ እያንዳንዱ በየመንገዱ ይሄዳል። ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች ዋኖስና ጨረባ ዋልያም የመምጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም። እናንተስ። ጥበበኞች ነን የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እንዴት ትላላችሁ? እነሆ፥ የጸሐፊ ብርዕ ሐሰተኛ ነው በሐሰትም አድርጎአል። ጥበበኞች አፍረዋል ደንግጠውማል ተማርከውማል እነሆ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው? ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ። የሕዝቤንም ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ ሰላም ሳይሆን፦ ስለም ሰላም ይላሉ። ስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።» ትን. ኤር 8፡ 4-12 
        ወንድም አሸናፊ ሁለቱም ደብዳቤዎች የሚያስረዱት ይህ ፍርድ በአንተ ላይ ሊፈጸም ወደ ፍጻሜው እየቸኮለ መሆኑን ነው። እባክህ እባክህ ከጌታ ጋር ታረቅ ንስሐም ግባ። 
ስለ አሸናፊ መኮንን የተጻፈውን መጀመሪያ ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ 

88 comments:

 1. pdf readere lelelen sewoche yedebedabewen tikilil hasabe bitaskemitulen

  ReplyDelete
  Replies
  1. ARE GUD HAMUS MATA MATA YEMIHEDU TEHADISO YE THEOLOGY TEMARIWOCHES?

   Delete
 2. የገሀነም ደጆች ተሐድሶ መናፍቃን ገና ተጠፋላችሁ! የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምላክ ገና ብዙ ያሳየናል! ሐይማኖት የለሹ አቶ አሽናፊ እኮ በቁሙ የሞተ ነው፣ ግብረ ሰዶማዊ መሆኑ ምንም አይደንቅም!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አስቀድሞ ነገር ያንተ ፎቶ ከምን የመጣ ነው? ታውቀዋለህ ወይስ ሳታውቅ ነው የተቀበልከው? አንድ ዓይን (The all seeing eye) ሁሉን የሚያይ የኢሉሚናቲ ወይም የሰይጣን አምላኪዎች ዋናው ምልክት ነው፡፡ የዚህ ምልክት መነሻው ዘካርያስ 11 17 እንደሆነ ይነገራል፡፡ የዲያብሎስ አምላኪ፣ ስለክርስትና ምን አገባህ ወይስ ግብረሰዶማዊነት እንዲስፋፋ ሰለምትፈልግ ነው እንዲህ የምትንጨረጨረው፤ ሰይጣን አምላኪው!

   Delete
  2. አስቀድሞ ነገር ያንተ ፎቶ ከምን የመጣ ነው? ታውቀዋለህ ወይስ ሳታውቅ ነው የተቀበልከው? አንድ ዓይን (The all seeing eye) ሁሉን የሚያይ የኢሉሚናቲ ወይም የሰይጣን አምላኪዎች ዋናው ምልክት ነው፡፡ የዚህ ምልክት መነሻው ዘካርያስ 11 17 እንደሆነ ይነገራል፡፡ የዲያብሎስ አምላኪ፣ ስለክርስትና ምን አገባህ ወይስ ግብረሰዶማዊነት እንዲስፋፋ ሰለምትፈልግ ነው እንዲህ የምትንጨረጨረው፤ ሰይጣን አምላኪው!

   Delete
  3. አስቀድሞ ነገር ያንተ ፎቶ ከምን የመጣ ነው? ታውቀዋለህ ወይስ ሳታውቅ ነው የተቀበልከው? አንድ ዓይን (The all seeing eye) ሁሉን የሚያይ የኢሉሚናቲ ወይም የሰይጣን አምላኪዎች ዋናው ምልክት ነው፡፡ የዚህ ምልክት መነሻው ዘካርያስ 11 17 እንደሆነ ይነገራል፡፡ የዲያብሎስ አምላኪ፣ ስለክርስትና ምን አገባህ ወይስ ግብረሰዶማዊነት እንዲስፋፋ ሰለምትፈልግ ነው እንዲህ የምትንጨረጨረው፤ ሰይጣን አምላኪው!

   Delete
 3. ይህ ሰው ዲያቆን አይደለም የናንተ ሃይማኖት የሚከተል (ተሃድሶ/ጴትጤ ነው) ሰው ስለሆነ በማህበረ ቅዱሳን ኣጋላጭነት ቅዱስ ሲኖዶስ ድቁናውን ሽሮ ከ ለሎች መሰሎቻችሁ ጋር ኣውግዞ የለየው ሰው ነው፥ :ይህ ሲፈጸም ምን ያህል ማህበረ ቅዱሳንን አና ሲኖዶሱን ስት ሰድቡና ስታብጠለጥሉ አንደነበር ለናንተ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ነው ፥ኣሁን ሶዶማዊነቱ ሲጋለጥ የኦርቶዶክስ ተከታይ አስመስላችሁህ ዲያቆን እያላችሁ ሰዉን ኣታደናግሩ ሁላችሁም ከሱ ያላነሰ ሃጢያትንናርግማን ተሸክማችሁ የምትዞሩ ናችሁ፥፥፥፥

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተሃድሶም ሆነ ኦርቶዶክስ እናም ወይም ሙስልም .. በመጀመሪያ ይህ ተግባር ለሰው ዘር አይደለም ከላይም እንደተጠቀሰው ለእንስሳ ራሱ በጣም ከባድ ነው የትኛውም እንስሳ እንደዝህ አይነት ነውር አይፈጽምም እናም እኛ ክርስቲያኖች ይህን አይተን ኤጌሌ ነው እንትና ነው ብለን በፌዝ መየት የለብንም ስለ ታየው ነገር በአምላክ ፊት በመውደቅ የትውልድን ህይወት መታደግ እንጂ ።

   Delete
  2. ዲያቆንነቱ ከተሻረ ዓመታት አልፈዋል ። ኦርቶዶክስን በግብረ ሰዶም መውቀስና ማስወቀስ ስለፈለጋችሁ ነው ዲያቆንነቱን የሸለማችሁት ። በበሰበሰ ምሳርም ኦርቶዶክስን ለማጥቃት ብላችሁ ዳግም ሾማችሁት።

   Delete
  3. ይህ ሰው ዲያቆን አይደለም የናንተ ሃይማኖት የሚከተል (ተሃድሶ/ጴትጤ ነው) ሰው ስለሆነ በማህበረ ቅዱሳን ኣጋላጭነት ቅዱስ ሲኖዶስ ድቁናውን ሽሮ ከ ለሎች መሰሎቻችሁ ጋር ኣውግዞ የለየው ሰው ነው፥ :ይህ ሲፈጸም ምን ያህል ማህበረ ቅዱሳንን አና ሲኖዶሱን ስት ሰድቡና ስታብጠለጥሉ አንደነበር ለናንተ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ነው ፥ኣሁን ሶዶማዊነቱ ሲጋለጥ የኦርቶዶክስ ተከታይ አስመስላችሁህ ዲያቆን እያላችሁ ሰዉን ኣታደናግሩ ሁላችሁም ከሱ ያላነሰ ሃጢያትንናርግማን ተሸክማችሁ የምትዞሩ ናችሁ፥፥፥፥

   Delete
 4. ምን ያህል እውነት ነው ግን? እንዴት ነው እሳቸውን የማገኛቸው እውነቱን ደግሞ ከራሳቸው ማረጋገጥ እፈልጋለው ። ዛሬም የማከብራቸው አባት ናቸው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ልክ ነህ ወንድሜ በነዚህ ማንነታቸው በማይታወቅ ሰዎች በጻፉት ተራ ጽሁፍ ብቻ መመራት መጨረሽታው ሞት ነው። እርሱን ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ግን የእርሱን ስልክ ቁጥር አለኝ ልሰጥህ እችላለው። እነዚህ ሰዎች አላማቸው ምን እንደ ሆነ አይታወቅም፡ ትላንት ስለ እሱ መልካምነት የጻፈች እጃጀው ዛሬ እርሱን ለማዋረድ ብትነሳ አይደንቅም። እግዚኣብሄር ልቦና ይስጠን።

   Delete
  2. እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ሁለቱን ደብዳቤዎች ማንበብ የሚረዳ ይመስለኛል። ሁለቱም ደብዳቤዎች ህጋዊና ናቸው። ስህተት ነው ከተባለ አሸናፊ ፊት ለፊት መቃወም ይችላል።

   Delete
  3. መደፈር ካማረህ ሂድና ሞክረው እሱን ብለው የሄዱት በሙሉ ነው የተደፈሩት ወደ እውነተኛ ቤተክርስቲያናችሁ ተመለሱ

   Delete
  4. ይቅር ይበል ወንድሜ በሙሉ ስትል በወሪ ነው የሰማህው ወይስ አይተ አረጋግጥሃል? ደብዳቤ ለምትለው ደግሞ ቅንብር አለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለህ? እውነቱ ያለው ክርስቶስ ጋር ነው እሱ እውነታውን ያውጣ ልቦና ይስተን

   Delete
 5. ወልደ እግዚእ

  የዚህ ንስሃስ ለማን ይነገራል ስሜን ብነግራችሁ ደሞ ታንቄ ሳልሞት አልቀርም

  ወንጌል እማራለው ብዬ በሽታ ሸመትኩ

  ጥቃት ከደረሰብኝ ሰው አንዱ ነኝ

  እየተደበቅሁ እሄድ ነበር አንድ የሚያፈዝ ነገር ነበር

  ብር ይሰጠኝም ነበር

  መጅመርያ ሲስመኝ ወንድማዊ አሳሳም ነው ይለኝ ነበር ሲቆይ ግን ሱስ ያዘኝ ካልሳመኝ ያመኛል እርቃናችንን እንጸልይ እያለ ይነካካኛል ያኔ የተፈወስኩ ያህል ይሰማኝ ነበር ፍቅረኛይን እንድተዋት ወተወተኝ እውነት መስሎኝ ተዉኩዋት ካልዳሰሰኝ ይደብረኝ ነበር ያው አነድ ቀን የሚጸልይ መስሎ ታገለኝ በብረቱ ታገለኝ አልቻልኩም ሁሉም ሄደደው ነበር……ምነው አሼ ስለው እየጸለይን ነው ካላባረከኝ አልለቅህም በል ይለኝ ነበር እኔም እያመመኝ እል ነበር …… እንዲህ አሞኝ አያውቅም እንደደፈረኝ ያወኩትደም ሲፈሰኝ ነው ቢዙ ጊዜ ተገናኘኝ ከአንድ ሰባኪ ነኝ ባይ ጋር በድብቅ እነደሚወጣ ሰማው ያኔ ሁለቱንም ጠላሁዋቸው ክዚሀ ኑሮ ማን ይገላግለኛል አሸናፊ ጋር ባለሄድም ዛሬም ያነገር ልቤን …………..
  ስለነፍስ ከዚህ አውጡኝ አስፈሪ ነው ከዚህ መውጣት ሴት አልቀርብም


  አሁን ሰው አፍራለው ከቤቴ አልወጣም

  ከዚህ ህይወት እንድወጣ ጸልዩልኝ ባካችሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ አሁን የምትናገረው የእብደት ንግግር ነገ በክርስቶስ ፊት ቆመህ መልስ እንደምትሰጥበ አውቀሃል። የምትጸድቀው የምትኮነነው በቃልህ ነውና እባክህ አስተውለህ ተናገር እራስህ ላይ ፍርድ እዳጣመጣ።

   Delete
  2. yesafkew ewnet new. Yihe new benem lay yedereswe.

   Delete
  3. protestantawi astemhrowochn ergif argeh titeh hatyathn lekahn tenazeh nesha gebteh be orthodox abyate kerstianat kalut tsebeloch bemeretkew tsebel tetemek.bet mekemet chigrun ayaswegdim tselotna tsebel new mefthew.mirabawyann behamanot lememselna legenzeb tikim sibal yasadegechahchun kidist betekrstian menakna beastemhrotua lay bemesalek lematfat nufake lay mesemarat sihtet endehone lemekseft endemidarg megenzebna leloch kezih endikotebu memkerm tegebi new. Bizu gizy temekro angetun yadenedene dinget yiseberal fewsm yelewm yemilewn yemetshaf kudus kale astawsna dendana kemehn rashn tebkna kechalk bewendimnet lelochnm miker.

   Delete
 6. እግዚአብሔር ከዚህ ይሰውረን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምኑ ነው እብደት ሰውዬህ ግብረሰዶማዊ መሆኑን ወንድሞችህ አምነዋል። ይህ ሰው የደረሰበትን ነው የጻፈው። ሀጢአት በእናንተ ጊዜ ይመራል አይደል? ከንቱ ሁላ አረ እናንተ መናፍቃም ልብ ይኑራችሁ

   Delete
 7. በጣም ያሣዝናል፡፡፡

  ReplyDelete
 8. geta esuneme yenseha lib yistew. yikerem yibelew. eganem kezhi kunene yiseweren

  ReplyDelete
 9. በጣም ነው ያዘንኩት። አልቅሻለሁም። ውሸት እንዲሆን በጣም ፈለኩ። ግን በቃ ነገሩ እውነት ይመስላል። ዉዉዉዉ በጣም በጣም ያሳዝናል።

  ReplyDelete
 10. የአሸናፊ ነገር ለብዙዎች ግራ የሚያጋባ ሆኗል። ወይ ጉድ እያሰኘንም ነው። እንዴት ለተሀድሶ እንቅስቃሴ ጥሩ ተስፋ ያለው ሰው እንዲዚህ ባለ እርኩሰት ውስጥ ይገኛል? ለምንስ የወንድሞችን ምክር አልሰማ አለ? ለምን ተደብቆ በባልቴቶች ተማምኖ እና ተሽሞንሙኖ ይኖራል? ለምን የቀረበለትን እርዳታ ገፋ? የአደረባት መንፈስ ከግብረ ሰዶማዊነት ያለፈ ምን አድርጎበት ይሆን? ለሚሉ ጥያቆዎች ለብዙ የቀድሞ አድናቂዎቹ ለነበርን ሰዎች ግራ ያጋባን ጉዳይ ነው።
  ራስን ለመከላከል የሚያወጣውን ገንዘብና ጊዜ 0.5 በመቶ እንኳ ንስሀ ለመግባት ፈቃደኛ ቢሆን አያወጣም ነበር፤፤ ባለፈው ሳምንት አባ ሰላማ ላይ ወጥቶ በነበነው ጽሁፍ እንዳነበብነው ይህ ሰው ምን እየሆነ ነው የምንልባቸው ነገሮች በዝተዋል።
  ጌታ ይታረቀው እንጂ ልቡን ይመልስልት አይነ ልቡን ያብራለት ለንስ ሀያንቃው ከማለት ውጭ ምን ለማለት ይቻላል

  ReplyDelete
  Replies
  1. የምንፍቅና መንፈስ ገና ምን የማያሰራው ሃጢያት አለ፡፡ እንደ ፈረንጆቹ የመናፍቃን መጨረሻቸው ገና ብዙ ነው፡፡ ኦርቶዶክስን ያስተወ ገና ብዙ ያሰራል፡፡ ከበለስ ወይንን የሚጠብቅ ማን ነው፡፡

   Delete
 11. አሸናፊ መኮንን የተረት አባት ነው። he is good for nothing የሚባለው አይነት ነው። አንድም አይነት የትምህርተ መለኮት እውቀት እንደሌለው መጽሐፎቹ ያስታውቃሉ። የናንተ ቢጤ ተሃድሶ ስለሆነ ግን ስለሱ ስትጽፉ የሀዘኔታ ቅሬታ አልተለያችሁም። እስኪ ስለ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ የጻፋችሁትን መለስ ብላችሁ እዩት። የእናንተ አባል ስላልሆኑ ለናንተ የድል ዜና ነበር፤፤ አሁን ደግሞ ልንገራችሁ ይህ ለኛ የድል ዜና ነው። ቀዠባራ መናፍቅ ሁላ

  ReplyDelete
 12. Have anybody noticed that when one person is capable of teaching the word of God in truth the others accuse them of something or try to make a story so people could not be hearing the word of God that he speaks. Some people do this on purpose to create doubt on them and they are jealous of them. It is so many other similar stories like that. The devil is doing this to stop people from hearing the gospel. That is what they did to Jesus when he told them to turn back to God they crusty him. So all this accusation doesn't surprise me at all and let the truth come out one day.

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውነት ብለሀል ወንድሜ አቤቱ አድነን ደግ ሰው አልቃልና እ/ር እውነተኛ ዳኛ ነው በፍርድ ይገለጣል. ምን ይሆን የምታገኙት ይህንን በማድረጋችሁ። እኔ ፈራሁ ክርስቲያን መሆን ወንድምን ማጋለጥ ከሆነ አንዱ ሀጥያት ሰራ እንበል በብሎግ ማውጣት ያንጻል? ይቅር ይበላችሁ

   Delete
  2. አንተም ሰዶማዊ ነህ መሰለኝ ሳያውቁ ብዙዎች ተጎዳን እያሉ መውጣቱ ሰዎች እንዳይጎዱ ረዳል የመናፍቅ መጨረሻው ምን እንደሆነ እንድንረዳ ይረዳናል

   Delete
  3. ለእርስዎ
   ለዲያቆን አሸናፊ ያለዎትን አድናቆት ጥሩ ነው። ግን ለስሜትዎ ወይም ደግሞ ለሰውየው ላሎት አክብሮት ከመቆምዎት በፊት ነገሩን በእግዚአብሔር ቃልና በማስተዋል ቢመዝኑት ጥሩ ነበር። ለምን ይመስልዎትዋል ዲያቆኑ ይመራው ከነበረው ሚኒስትሪ ግማሽ ያህሉ ሰው ለቆ የወጣው?
   ለምን ይመስልዎታል እሱ "ካገለገላቸው" ልጆች መካከል የተወሰኑትየግብረ ሰዶም ድርጊት ሰለባ ነን እያሉ ያሉት?
   ለምን ይመስልዎታል ከሚኒስትሪው መስራች አባላት መካከል የተወሰኑት ግብረ ሰዶማዊ ስለሆነ መስራችነቱን ትተናል ብለው ከሚኒሰትሪው ለመንግስት አሳውቀው የለቀቁት?
   ለምን ይመስልዎታል በተሀድሶ አገልግሎት ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሁሉ ሊያገኙት ሲፈልጉ እምቢ ብሎ የተደበቀው?
   ለምን ለምን ለምን?
   አንድ ነገር ልንገርዎት እኔ የዚህ አስተያየት ጸሀፊ ደግሞ አሸናፊ ግብረ ሰዶማዊ ለመሆኑ 100 % እረግጠኛ ነኝ።
   ሰውን ለማሰናከል ሳይሆን ለመታደግ የሱን ድርጊት በዝርዝር መግለጥ የግድ ይላል። ይህ የወንድም ገመና አይደለም። ገመና የሚባለው ሰው ንስሀ ሊገባበት የፈቀደው ኃጢአት ነው። ይህ ግን እርኩሰት ነው። ተቀደሱ ከዞጅ ሽሹማለት የአገልጋይነት ትልቁ ኃላፊነት ነው። አሸናፊ ተሳስቷል። ግን አገልጋይ ቢሳሳት ጌታ አይሳሳትም። የክብሩን ወንጌል ለስጋ ጥቅም የሚሸቅሉትን ሁሉ ጌታ በጊዜው ጊዜ ይገልጠዋል።
   ክርክሩን ትተው ንስሀ እንዲገባ ቢመክሩት ጥሩ ነው።

   Delete
  4. I konw who u are. ጌታ ሲመጣ በፊቱ እንዴት እንደምንቆም አላውቅም፡፡ አብሶ የሰውን ሀጥያት ለመግለጥ የምትተጋው አንተ የአባቶችን የወንድሞችን ገመና በመግለጥ የምትተጋው አንት ይህንን ከየት እንደተማርከው ባለውቅም ግን ሳታውቅ የሰይጣን አገልጋይ ሆነናልና እስቲ ሰውን ንስሀ ግቡ ማለትህ መልካም ቢሆን የጌታ ቃል ራስህን አድን ስለሚል እስቲ አንተም እኔም ንስሀ እንግባ እ/ር አይዘበትበትም በፍርድ ይገለጣል፡፡ ይልቁምን በሰማይ ፍርድ ከሚጠብቅህ በዚች ምድርግ ከፍርድ አምልጥ፡፡
   ኦ ጌታ ያስበን አይ እንኳን ተሀድሶን ልታመጣ ሰውን እያባላህ ኑሮህ ይህ መሆኑ ይገርማል ከእናንተ እናንተ የምታብጠለጥሉት ማቅ ይሻላል፡፡

   Delete
  5. ቆይ የዚህ ጸኃፊ መረዳ ካለህ ለምን አስከተሰውም ይህ እኮ በሰውም በእ/ር ያስጠይቃል፡፡ መንፈሳዊ ናችሁ ተብላችሁ ሰው እንዳይታዘባችሁ ነው፡፡ የሰማዩን ጌታ ሳትፈራ ሰውን የምትፈራ አንተ ማነህ እስቲ ጎበዝ ከሆንክ ክሰሰው ፡፡

   Delete
 13. አሸናፊ መኮንን ይህ የተባለው ነገር እውነት ከሆነ በዚህ ጉዳይ ስለተሰናከልን እግዚአብሔር ይፍረድብህ፤ ይህ የሚባለው ሁሉ ሐሰት ከሆነ እግዚአብሔር ከዚህ ጉድ ያውጣህ፡፡ እንደ ሰው የምለው ይህንኑ ነው፡፡ ለማመን የሚቸግር ግን ደግሞ ሐሰት ነው ብሎ ለመደምደም የሚያዳግት በሁላችንም ላይ የሐዘን ጥላ ያጠላ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ማኅበረ ቅዱሳንም ሆነ ማንም ሊደሰት አይገባም፡፡ ቤተክርስቲያናችንን ከጠላት ዲያብሎስ አፍራሽ ተንኮል ይጠብቅልን፡፡ አባ ሠላማዎች በአሸናፊ ጉዳይ ላይ ያወጣችሁት ዘገባ እውነት ከሆነ ትክክለኛ እርምጃ ወስዳችኋል፡፡ እውነት ካልሆነ ግን ይህ ሁሉ ተከታያችሁ ጥያቄ ውስጥ ያስገባችኋል፡፡ እኔ ግን ለእግዚአብሔር አሳልፌ ሰጥቻለሁ፡፡አሸናፊ መኮንን ይህ የተባለው ነገር እውነት ከሆነ በዚህ ጉዳይ ስለተሰናከልን እግዚአብሔር ይፍረድብህ፤ ይህ የሚባለው ሁሉ ሐሰት ከሆነ እግዚአብሔር ከዚህ ጉድ ያውጣህ፡፡ እንደ ሰው የምለው ይህንኑ ነው፡፡ ለማመን የሚቸግር ግን ደግሞ ሐሰት ነው ብሎ ለመደምደም የሚያዳግት በሁላችንም ላይ የሐዘን ጥላ ያጠላ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ማኅበረ ቅዱሳንም ሆነ ማንም ሊደሰት አይገባም፡፡ ቤተክርስቲያናችንን ከጠላት ዲያብሎስ አፍራሽ ተንኮል ይጠብቅልን፡፡ አባ ሠላማዎች በአሸናፊ ጉዳይ ላይ ያወጣችሁት ዘገባ እውነት ከሆነ ትክክለኛ እርምጃ ወስዳችኋል፡፡ እውነት ካልሆነ ግን ይህ ሁሉ ተከታያችሁ ጥያቄ ውስጥ ያስገባችኋል፡፡ እኔ ግን ለእግዚአብሔር አሳልፌ ሰጥቻለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማንን ነው ቤተክርስቲያናችንን የምትለው እሱ መናፍቅ ነው የነሱን ከሆነ አዳራሾቻችንን በል

   Delete
  2. AnonymousApril 10, 2015 at 2:29 AM

   እውነት ብለሃል።

   Delete
 14. ጣም አሳፋሪ ዘመን ላይ ነን ያለነው

  ወንጌሉን አንብቦ ከሁለት የምበልጡ መጽሔቶችን አሳትሞ ለብዘ ዘመናት በቤተክርስቲያን ቆይተው እንስሳ እንኳ በማይገኝብት ስፍራ መገኘቱ
  በርግጥ አይፈረድም ግን ዘመኑ እንዴት እየነጎደ ነው በእውነት ይህ ምን ይባል ? ግራ የሚያጋባ በሀዘን የምሞላ ነው እና እንድህ ከሆነ ስንቶቹን አምነን ወንጌል እንዲያስተንሩ አምነን እናስተናግድ!!

  አቤቱ! አትታዘበን!!።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሳፋሪው መጀመሪያም በምንፍቅና መንፈስ መያዙ ነው የሱ አይነት ብዙ ጉዋደኞች አሉት

   Delete
 15. lord have mercy !!! thankGod he was suspended from our church no more deakon

  ReplyDelete
 16. አንድ ነገር ግልፅ አልሆንልህ ብሎኛል እናንተም ብትሆኑ ደጀ ብርሃኖች ዲያቆኑ ንስሀ መግባት ያለበት እናንተ ጋ ነው ወይስ ከነሸክማችሁ ኑ ያለው ጌታ ጋር ነው ? እረ ያለምን ሀጢአት ሊያስወግድ የመጣውን ኢየሱስን ፍሩ !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያለጥርጥር ከነሸክማችሁ ኑ ያለው ጌታ ጋር ነው። ንስሀ ግን መጀመሪያ ኃጢአትን ማመን ከዛ መናዘዝ ከዛ የንስሀን ፍሬ ማሳየት ይፈልጋል። አሸናፊ ከነዚህ መሀል የቱን አደረገ? አንዱንም አላደረገም። አባ ሰላማዎችም ሆኑ ደጀ ብርሃኖች እኛ ጋር ንስሀ ግባ አላሉም አይሉምም። ግን ለመመለስ ንስሀ ለመግባት ፈቃደኛ አለመሆኑን ለማወቅ ቀላል ነገር ነው። አሸናፊ ለምን ተው የሚሉትን ሰዎች አያገኝም ለምን ከእነርሱ ጋር የነስሀን ቁም ነገር አይነጋገርም? ይልቅስ ሰዎችን ለመከፋፈል ስም መጥፋት ተደረገብኝ እያለ ነገሩን ከማያውቁ ሰዎች ልብ ለምን ያሳስታል? በደል ደርሶብናል ያሉ ሰዎችን ለምን ያክፋፋል? ችግሩንም ካልፈጸምክ እሺ እንገናኝና እንመካከር መፍትሔ እናፈላልግ ችግሩ አለ ከሚሉ ሰዎችም ጋር አገናኝተንህ እውነቱ ይውጣ ሲባል ለምን ይሸሻል?
   በትክክለኛው የመፍተሔ መንገድ ከመሄድ ይልቅ ታዋቂነቱን ተጠቅሞ የሚያሞኛቸውን ሞኛ ሞኞች ስም ማጥፋት ተደረገብኝ ቅንአት ምቀኝነት ምናምን እያለ ለአመጽ እያነሳሳ ነው የከረመው። እናግኝህ የሚሉትንና እንደ ባለአእምሮ ለችግሩ መንፈሳዊ መፍትሔ እንስጥ የሚሉትን ሁሉ በጠላትነት ፈርጆ የቻለውን ያህል ክፋት ሲፈጽም ነው የኖረው። ይህን የሚያደርግ ሰው በአንተ አይን ንስሀ ገብቷል ይባላል? የአንተን እይታ አላውቅም ግን እንደ ጌታ ቃል አልገባም። እኔ እስከማውቀው ድረስ የክፋት ውድድር ቢደረግ አሸናፊን ቀድሞ አንደኛ ሊወጣ የሚችል ሰው እንኳን ከተሃድሶ ከማቅም የሚገኝ አይመስለኝም። በጣም መጥፎ ሰው ነው። የቻለውን ያህል ክፋትን ፈጽሟል አሁንም አያርፍም። ግን የእግዚአብሔር ጽድቅ ከሱ ስለተለየች ደግሞ የትም አይደርስም። እና ወዳጅ አባ ሰላማም ይሁን ደጀ ብርሃን ኃጢአቱን ለመግለጽ የፈለጉትን አሸናፊ ከጨለማ ሥራ ለመላቀቅ ምንም ፍላጎት የሌለው ሰው መሆኑን በማመናቸው ብቻ እና በዚህ ማንነት ደግሞ የጌታን ሥራ መስራት ስለማይቻል ነው ብለው በማመናቸው ይመስለኛል። እናም እነርሱን እግዚአብሔርን ፍሩ ከማለት አሸናፊን እግዚአብሔርን ፍራ ብትለው ይሻላል።

   Delete
  2. አላማችሁ ምንድን ነው የኢትዩጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ስማ ማጥፋት???? እንዳትሳሳቱ እንደዚህ አይነት ዜናዎች በመለቀቃቸው ብዙዎችን ከክርስቶስ ፍቅር ታርቃላቹ ነገር ግን ቤተክርስቲን በክርስቶስ ደም ነውና የተመሰረተችው መቼም አትጠፋም፡፡
   “ የዲያቆን አሸናፊ መኮንን አሳዛኝ ፍጻሜና ግብረ ሰዶማዊነቱን የሚያስረዱ መረጃዎች“ ሌላም ሌላም ይጻፋል ድኅረ ገጻችሁ ላይ በመጀመሪያ ዲያቆን አሸናፊ መኮንን ማነው?? የየት ቤተክርስቲያን አገልጋይ ነው ስለማን እንደምታወሩ እንኳን በቅጡ አይታወቅም በግለሰቦች የተቀረጸ አንድ ገጸ-ባኅሪ በቃ፡፡ እንበልና አንድ ግለሰብ ቢበድል ምንም አይነት ጥፋት ቢያጠፋ ይህ ግለሰብ ግለሰብ ነውና ቤተክርስቲያንን አይወክልም፡፡ አላማቹ ስል ክርስቶስ መስበክ ነው ወይስ ሰዎች በግለሰቦች ተሰናክለው ከቤተክርስቲያን እንዲወጡ ማድረግ የወንድምህን ሀጢአት በአደባባይ አትናገርም የክርስትና ስነምግባር አይደለም፡፡ ሰዎች በዚህ ግለሰብ እንዳይሰናከሉ ከፈለጋቹ ብዙ መደረግ ያለባቸው ነገርች ይኖራሉ፡፡ እባካቹ ልባችሁ ያስተውል፡፡

   Delete
  3. ወንድሞች ይህ ሰው እግዚአብሔር ምን ያህል ታግሶት አሁን ወደ አደባባይ እንዳወጣው ምን ታውቃለችሁ? ዝም ብላችሁ አጉል ሊቅ አትሁኑ። ኃጢአተኛው ኃጢአት ሲሰራ ኃጢአት ሰርተሃል ማለት እና ንስሀ ግባ ማለት ትክክለኛ ክርስትና ነው እንጂ ፍርድ አይደለም። ጥፋ ያለው ያለው የለም የተባለው ኃጢአት ሠርተሃል ንስሀ ግባ ነው። እንደእናንተ አይነት አጉል ክርስቲያን ተሰብስቦ ነው አገልጋዩ ሁሉ ልቅ የሆነው። ጌታ ይህን መንፈስ ይገስጽ

   Delete
 17. አባ ሰላማዎች!!!
  ውሻ በቀደደው ጅብ እንዳይገባ
  ሰድቦ ለሰዳቢ ላለመስጠትና ዋናው የመንግሥቱ ሥራ እንዳይሰናከል ጥንቃቄ በደረግ

  ለማንኛውም ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ቢሰጥ መልካም ነው እላለሁ፡-

  1) በአስቆረቱ ይሁዳ ሐጢአት ሌሎች ሐዋርያት ተጠይቀው ነበርን?
  2) በንስሐ መመለስ የሚባል ነገር የለም?
  3) አንዳንድ መነኩሲዎች በዝሙት በመውደቃቸው ምክንያት ኦርቶዶክስ መወገዙዋ ትክክል ነውን?
  4) ማን የስህተት አስተማሪ እንደሆነስ ተጠቃሚው ሕዝብ ምንም አያውቅም ማለት ነውን?
  5) እውነተኛ ክርስቲያኖችን ወይም ሰባኪዎችን እንዴት እንወቃቸው?
  6) ክርስትና ፍቅር ሆኖ ሳለ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ግን በተቃራኒው ጥላቻ፣ ክፋትና መነቃቀፍ ከየት መጣ?
  7) በአጠቃላይ በዚች ታሪካዊ ቤት ክርስቲያናችን ላለው መነታረክና መበጣበጥ (በውስጥም በውጪም አገር) መፍትሔው ምንድነው? ብላችሁ ታስባላችሁ? በዚህ ላይስ በርትቶ መስራት አይሻልምን?


  ለበቤተ ክርስቲያናችን ምህረት ከእግዚብሔር ብቻ ይምጣልን!!!!

  መፍትሔ! መፍትሔ!! መፍትሔ!!!

  ሰላም ይብዛላችሁ!!!
  አክባሪ ወንድማችሁ

  ተናገር ነኝ

  ReplyDelete
 18. እኔ የምለው ከጽድቅ ጋር መቆም የምርጫ ጉዳይ ሆነ እንዴ? "እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ደስ እንደምናሰኝ አይደለም።"

  ReplyDelete
 19. የአሸናፊ ግብረሰዶማዊነት በጣም ያሳዘናል ልብንም ይሰብሯል። ግን ንስሐ እንዲገባና እንዲመለስ እግዚአብሔር ይርዳው።

  ReplyDelete
 20. betam yasazenal endih thaye yemokewal beye asebie alawekem neber gen yemishalew yehie new

  ReplyDelete
 21. አሹ መቸም ታነበዋለህና በጎዳ ያጣሁትን እድል አሁን ልንገርህ እባከህ ንስሀ ግባ ወንድሞችህን ማሳደዱ ስም ሞጥፋቱ ደብዳቢ ቀጥሮ መላኩ ያነተን ሀጢያት አያጥብልህም በስጋ ቢጎዱ እንኮን እነዚህ ወገኖች እኮ አድራሻ አላቸው የአንተ አያስጨነቀን ያለው እየተበደለ ያለው የእግዚአብሐር መንግስት ስራ ያጣኸው የዘላለም ህይወት ነው በዙሪያህ ያሉት ያስጨነቃቸው ምድራዊ ስም ነው… ብዙ ጊዜ የምትናገራትን ላስታውስህ ‹ባልሞተ ሰው ተስፋ አይቆረጥበትም እግዚአብሔር እድሜን ለንስሀ ሰጦታልና› እባክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ጊዜ ተጠቀምበት መቼም ንስሀ ግባ ካሉት ወንድሞች መካከል ማንም ጠላትህ እንዳልሆነ ያንተን ጉድለት ባላቸው ሁሉ ሲሞሉ የኖሩ በገንዘባቸው በእውቀታቸው የስጋ እናኮን ሸክምህን የተሸከሙ እነደሆኑ ልቦናህ ያውቀዋል አሹ ወደ ጌታ ዘወር ማለት ይሻላል!! እጅግ የምወድህ መመለስህን የምናፍቅ እህትህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. i 100% share your idea. it is so true

   Delete
  2. He hides himself from you because you are female....Send your brother and he will meet him.

   Delete
 22. ግብረ ሰዶም የማን ተግባር ነው? የማንስ አስተምሮ ነው? በዲሞክራሲ፣ በሰብአዊ መብት በልጽገናል የሚሉ የምዕራባውያን በሽታ አይደለምን? እንደ አገር የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ህጋዊ ከማድረግ አንስቶ በየ ቤተ እምነቶቻቸው ‹‹ ሥርዓት›› ሰርተው እየፈጸሙ አይደለምን? ከዚህ ባለፈስ ለውሾቻቸው ሳይቀር ሥርዓተ ጥምቀትና ሥረዓተ ጋቻ እየፈፀሙ አይደለምን፡፤ ታዲያ የአሸናፊና የግብረ አበሮቹ ግብር ምን ይደንቃል? በፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ የተቃኘ ግብሩን ነውኮ የገለፀው፡፡ እነ አሸናፊ ‹‹ተው ተመለሱ›› ሲባሉ እንኮ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡ አዎ በብዙዎቻችን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ በእኩይ ግብራቸው አሸናፊን የሚበልጡ ና እሱን የመሰሉ ‹‹“ጌታን የማያውቁ የጌታ አገልጋዮች ነን ባዮች ፣ ከሃይማኖት የከራቁ ልበ ቢሶች›› እንዳሉ ይታወቃል፡፡ አሸናፊን ሆነ ሌሎችን በሰውነታቸው የሚጠላ ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ ለአገርና ለሃይማኖት ፀር የሆነ እኩይ ግብራቸው እንጂ፡፡ ሁላችንንም ወደ ልባችን ይመልሰን፡፡ በነዋይ የነፈዘ አዕምሮአችንን ይለውጥልን፡፡

  ReplyDelete
 23. የጠበቀን፣ የመጣብንንም ወራሪ በእጃችን የጣለልን እግዚአብሔር ነው። 1ኛ ሳሙ 30፤23 +++
  ዳዊት ከሳኦል ሸሽቶ ወደ ፍልስጥኤም ሔደ፤ አንኩስንም መጠጊያ ሲለምነው፤ ጺቅላግን ሰጠው። ፍልስጥኤማውያን፣ እስራኤልን ለመውጋት ሲወጡ፣ አንኩስ ስለተማመነበት፣ ዳዊትንም ወደ ጦርነት ይዞት ሔደ። ሆኖም፣ የፍልስጥኤም ገዥዎች፣ ዳዊትን ስላላመኑት፣ ዳዊት፣ ሰዎቹን ይዞ ወደ ፍልስጥኤም ተመለሰ። በሦስተኛው ቀን ጺቅላግ ሲደርሱ ግን፣ እነ ዳዊትን የገጠማቸው አስደንጋጭ ነገር ነበር። አማሌቃውያን፣ ጺቅላግን ወረው፣ ወግተው፣ ከተማይቱ በእሳት ጋይታ፣ ሚስቶቻቸውና ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው፣ ሽማግሌዎችና ወጣቶች ሁሉ ተማርከው፣ ጠበቃቸው።
  በዚህ ጊዜ ዳዊት፣ እግዚአብሔርን ʻይሔንን ወራሪ ሠራዊት ልከተለውን? እደርስባቸዋለሁን?ʼ ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም ʻትደርስባቸዋለህ፣ ምርኮውን ትመልሳለህ፣ ተከተላቸውʼ አለው። ሁለት መቶ ሠዎች ሲቀሩ፣ አራት መቶ ሠዎች ተከትለውት ሔዱ። በምድረበዳም፣ አንድ ግብጻዊ አገኙና፣ ወራሪው ሠራዊት ወዳለበት መርቶ አደረሳቸው። ዳዊትም አማሌቃውያን የወሰዱትን ሁሉ አስጣለ፤ ሁለቱንም ሚስቶቹን አስመለሰ፤ ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንዶችም ሆነ ሴቶች ልጆች፣ ምርኮም ሆነ ሌላ፣ አማሌቃውያን ከወሰዱት ነገር ምንም የጎደለ አልነበረም፤ ዳዊት ሁሉንም አስመለሰ። እንዲሁም፣ የበጉን፣ የላሙን፣ የፍየሉን መንጋ ሁሉ ወሰደ።
  ከዚያም ዳዊት፣ እጅግ በመድከማቸው የተነሣ ሊከተሉት ወዳልቻሉት ወደ ሁለት መቶ ሰዎች መጣ። አብረውት ከተከተሉት መካከል አንዳንዶች፣ ʻአብረውን ስላልዘመቱ ካመጣነው ምርኮ አናካፍላቸውምʼ አሉ። ዳዊት ግን፣ ʻወንድሞቼ ሆይ፣ የጠበቀን፣ የመጣብንንም ወራሪ በእጃችን የጣለልን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በሰጠን ነገር ይህን ማድረግ አይገባችሁም፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉʼ አላቸው፤ አደረገውም።
  ወገኖቼ ሆይ፣ አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን ላይ በሚመጣ መከራ አብረውን የማይቆሙ ሰዎች ይኖራሉ፣ አልፎ ተርፎም ምናልባትም፣ ሊሳለቁብንና ሽንፈታችንን በጉጉት እየጠበቁ ከጎን ቆመው የሚያዩ ሰዎች ይኖራሉ፣ ቢሆንም ግን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከመሆኑ የተነሳ የማይታመኑ፣ ድንቆችንና ሁኔታወችን አመቻችቶልን፣ በመከራችን ላይ ድልን ባገኘን ግዜ፣ ያስቀየሙንን፣ ድል አታገኙም ብለው፣ የሳቁብንን፣ ያዋረዱንን፣ ያሙንን ሁሉ ልንባርካቸው እንጅ፣ የታባታቸው ብለን ልንበቀላቸው አይገባም።
  በድህነታችን፣ በማጣታችን ግዜ፣ ወይም በሕመም እና በችግራችን ግዜ፣ ወይም በሕይወታችን ላይ ሰልፍ በበረታ ግዜ፣ ከዳር ቆመው ስንሞትና ስንዋረድ ለማየት እንዲሁም ለመሳቅ እና እሰይ ለማለት አሰፍስፍው የነበሩትን ሰዎች ሁሉ፣ በጌታ ተዓምራት ሁሉን አልፈን ባዩን ግዜ ልናባርካቸው ይገባል።
  የናቁን፣ ያንቋሸሹንን ሁሉ፣ በልዩ ልዩ፣ የጸጋ አገልግሎቶች በተገለጥን ግዜ፣ እግዚአብሔር ከሰጠን፣ የጸጋ አግልግሎት፣ የትንቢትም ሆነ፣ የፈውስ አግልግሎት በረከት በፍጹም ፍቅር ልናካፍላቸው ይገባል።
  ውርደታችንን በክብር፣ ሐዘናችንን በደስታ እግዚአብሔር በለወጠልን ግዜ፣ ከዳር ቆመው ያሾፉብንን ሁሉ፣ በእኛ ላይ የሆነውን የጌታን ማዳን አይተው በሕይወት መዝገብ ላይ ከእኛ ጋር ስማቸው አብሮ እንዲጻፍ ልንረዳቸው ይገባል፤ ምክያቱም እኛም ሰው የሆንነው፣ በጌታ ጸጋ፣ እርዳታ፣ ምሕረትና፣ እገዛ በመሆኑ!!!!!!!
  አብ አባት ሆይ! ሠልፉ ያንተ ነውና፣ አንተ ተዋግተህ ባሸነፍክልንና ድልን ባቀዳጀህን ቦታዎች እና በሮች ሁሉ፣ እኛም ትህትናን ካንተ ተምረን፤ ለናቁንና ለጠሉን ሁሉ የበረከት እና የፈውስ ምንጭ አድርገን፤ በቀል በኢየሱስ ስም ዛሬ ከእኛ ይራቅ! ሠምተህኛልና ተባረክ።

  ReplyDelete
 24. plz at least put the title Deacon in qoutation or remove it. because he is already avoided from church by Holy Synod.

  ReplyDelete
 25. asu gibre sedomem menafikem aydelem
  degmom behon enkwan yesu ena yegetaw guday new
  yegeta eyesus dem kehatyeyat hulu yanethal
  egziabeher endemitekembet gin ene meseker negn

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dersohal Ende? hahahaha

   Delete
 26. diben yale wushet now yemayihon neger

  ReplyDelete
 27. ጤና ይስጥልኝ፡፡ ይህንን ስው እኔ በቅርበት የማውቀው ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንደ ወንጌል ሰባኪና የበጎ ፈቃድ አገልጋይ እየሆነ ፓስተር ዳንኤልን (የፕሪዝን ፌሎውሽፕ ድርጅት መሪ) ይመጣ ነበር፡፡ እሱና ወዳጁቹ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን እንደ አገር እንዳትኖር ለሚሰሩ ስውር ድርጅቶች የሚተጋ ተላላኪ ነው፡፡ በዚህ ረገድ በነበረኝ የሥራ ኃላፊነት የተነሳ አሸናፊን የማውቀው በርካታ የርኩሰት ተግባራትን በመፈፀሙ ነው፡፡

  ReplyDelete
 28. ጤና ይስጥልኝ፡፡ ይህንን ስው እኔ በቅርበት የማውቀው ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንደ ወንጌል ሰባኪና የበጎ ፈቃድ አገልጋይ እየሆነ ፓስተር ዳንኤልን (የፕሪዝን ፌሎውሽፕ ድርጅት መሪ) ይመጣ ነበር፡፡ እሱና ወዳጁቹ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን እንደ አገር እንዳትኖር ለሚሰሩ ስውር ድርጅቶች የሚተጋ ተላላኪ ነው፡፡ በዚህ ረገድ በነበረኝ የሥራ ኃላፊነት የተነሳ አሸናፊን የማውቀው በርካታ የርኩሰት ተግባራትን በመፈፀሙ ነው፡፡

  ReplyDelete
 29. ተመክሮ ተመክሮ አልመጀለስ ካለ በቃ እንደተጻፈው እንደ አረመኔና ቀራጭ ሆኗል ማል ነው። ጌታ ይገስጸው አቦ

  ReplyDelete
 30. This guy was ex-communicated from EOTC beacuse of his protestant views and His no more a decaon call it Pastor or whathtever you lie! Such type of persons usual say " Holy spirit" lead them to the path of protestant Tehadiso. I agree agree it is a spirit that lead me astray from the apostolic faith of EOTC. As this is spirit s a forged holy spirit or evil spirit controls their mind and body, he gives them feeling that is not natural to them! The cure to repent and casting the devil inside them by the cross and holy water. Homosexuality is possession by demon!

  Yadekone seytan seyasekesse aylekem!

  ReplyDelete
 31. አሸናፊ እኮ አጭበርባሪ ሰው ነው እንደ አሳ የሚሙለጨለጭ ክፉ ነው። በቅርበት አውቄው የናኩት ሰው ነው። ዛሬው ከረዥም ዓመት በኃላ ለሱ የምትረከራከሩ ጅሎችን ሳይ ይገርመኛል

  ReplyDelete
 32. aba selamawoch tebareku

  ReplyDelete
 33. ጨርቆስ አካባቢ ያሉ ግብረ ሰዶማዊያን በሙሉ ከአሸናፊ መኮንን ጋር ቅርርብ የነበራቸው ወይም ያላቸው ናቸው። ይህ ዝም ብሎ አጋጣሚ ሊሆን አይችልም። ተገቢውን ኮርስ ከሱ ወስደው ነው የሚሆነው ይሄ ማፈሪያ ወንድሞቻችንን ጨረሰብን

  ReplyDelete
  Replies
  1. hahahahahha wendemamacocu yihin anbebewewal?

   Delete
 34. Wondimoche....enem kewanaw bayihonim kissing dersognal.

  ReplyDelete
  Replies
  1. me too. he is an expert kisser. he told me that he kiss me because he loves me. he kissed me for an hour or more. he always told me that he i stand against his will i will day in a moment. it was not that much simple to me, i fear him a lot. so even if i am not comfortable at all that i let him kiss me. o God what a shameful person.

   Delete
 35. ወይ ጊዜ ይሄም ጊዜ ደርሶ አሹ ተጋለጠ። ለእንደኔ አይነቱ ሰው ህልም ነበር የሱ ግብረ ሰዶማዊነት መጋለጥ። እንዴት አድርጎ እያግባባ ወደዚህ ነገር እንደሚከታችሁ ልነግራችሁ አልችልም። መጽሀፍ ቅዱስን በሰው ፊት ሲናገረውና ለብቻችሁ አግኝቶ ለሰዶማዊነቱ ተገቢነት ሲጠቅስላችሁ። በጣም ነው ግራ የሚገባችሁ። አሳች የአሳች መጨረሻ ነው። ስንት ቀን አታለለኝ ጌታ ነጻ እስኪያወጣኝ ድረስ

  ReplyDelete
 36. እኛ ግን ከድንቁርና መቼ ነው የምንወጣው? አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በጣም ይገርማሉ፡፡
  በመጀመሪያ ሰውዬውን ሳይሆን ሐጢአቱን ነው መጥላት ያለብን፡፡
  ሌላ ደግሞ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውም የሃይማኖት ድርጅት ግብረሶዶማዊነት አይደግፍም ስለዚህም አስተያየታችን ቀናነት ይኑሮው ባገኘነው አጋጣሚ ሌላ ሃይማኖት ለመዘርጠጥ አኑሯራጥ፡፡
  እንግዲህ ሰዎቹ ባላቸው መረጃ መሰረት ፍርድ ሰጥቷል ሌላ ምንም ማድረግ አይቻልም ፡፡ ገስፀው መመለስ ካልቻሉ ትክክለኛ እርምጃ ነው እላለሁ በኔ አስተያየት ፡፡

  ReplyDelete
 37. የሉቃስ ወንጌል 6 :-41-42
  በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለ ምን ታያለህ፥ በራስህ ዓይን ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም? በዓይንህ ያለውን ምሰሶ ራስህ ሳታይ፥ እንዴት ወንድምህን። ወንድሜ ሆይ፥ በዓይንህ ያለውን ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ ልትል ትችላለህ? አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ ከዚያም በኋላ በወንድምህ ዓይን ያለውን ጉድፍ ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የጠቀስከው ጥቅስ መልዕክት ገብቶሀል ግን? አልመሰለኝም። የግብረ ሰዶም ኃጢአት ምን እንደሆነ እና እግዚአብሔር ምን ያህል እንደሚጸየፈውም የምታውቅ አልመሰለኝም።

   Delete
 38. የአሸናፊ ነገር ለብዙዎች ግራ የሚያጋባ ሆኗል። ወይ ጉድ እያሰኘንም ነው። እንዴት ለተሀድሶ እንቅስቃሴ ጥሩ ተስፋ ያለው ሰው እንዲዚህ ባለ እርኩሰት ውስጥ ይገኛል? ለምንስ የወንድሞችን ምክር አልሰማ አለ? ለምን ተደብቆ በባልቴቶች ተማምኖ እና ተሽሞንሙኖ ይኖራል? ለምን የቀረበለትን እርዳታ ገፋ? የአደረባት መንፈስ ከግብረ ሰዶማዊነት ያለፈ ምን አድርጎበት ይሆን? ለሚሉ ጥያቆዎች ለብዙ የቀድሞ አድናቂዎቹ ለነበርን ሰዎች ግራ ያጋባን ጉዳይ ነው።
  ራስን ለመከላከል የሚያወጣውን ገንዘብና ጊዜ 0.5 በመቶ እንኳ ንስሀ ለመግባት ፈቃደኛ ቢሆን አያወጣም ነበር፤፤ ባለፈው ሳምንት አባ ሰላማ ላይ ወጥቶ በነበነው ጽሁፍ እንዳነበብነው ይህ ሰው ምን እየሆነ ነው የምንልባቸው ነገሮች በዝተዋል።
  ጌታ ይታረቀው እንጂ ልቡን ይመልስልት አይነ ልቡን ያብራለት ለንስ ሀያንቃው ከማለት ውጭ ምን ለማለት ይቻላል

  ReplyDelete
 39. weye ashu yante mecheresha yihe yihun

  ReplyDelete
 40. ashume kentu hone wende afkero gedel geba

  ReplyDelete
 41. weye yeferahut derese

  ReplyDelete
 42. DIRTY JOKE PRESENTED BY PROTESTANT FOLLOWERS ! THEY CALL THEM SELVES ABA SELAM KI KI KI KI

  ReplyDelete
 43. dirty comment by a jerk a believe sedomi is a right. man it will not happen in Ethiopia.

  ReplyDelete
 44. ወይ አሹ!! አሹ ብልሹ

  ReplyDelete
 45. መናፍቃን መጨረሻቸው ይሄ መሆኑን አወሮፓውያን አሳይተዋል፡፡ የርኩስ መንፈስ ልጆቻቸውም በአፍሪካ ይህንን ይከተላሉ፡፡ አሸናፊ ችግር አለበት ብላ ቤተ ክርስቲያን ስታወግዝ እናንተ ጠበቆቹ ነበራችሁ፡፡ አሸናፊም እውነተኛ ክርስቲያን ስለሆ “ማኅበረ ቅዱሳን ዲ/ን አሸናፊን ለመክሰስና ለማስወገዝ የተንቀሳቀሰው በዋናነት የእርሱ መጻሕፍቱ በቤተክርስቲያን ውስጥ በስፋት በመነበባቸውና ለብዙዎች የመንፈስ እረፍትንና እርካታን በማምጣታቸው ቀንቶና ተመቅኝቶ እንደሆነ ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡ ዲ/ን አሸናፊ እስካሁን የጻፋቸውን 16 መጻሕፍት በግንቦት 2003 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ገሪማ ፊርማ ለሊቃውንት ጉባኤ በተጻፈ ደብዳቤ የሊቃውንት ጉባኤው ለሥራ እንዲጠቀምባቸው መመሪያ ተላልፎ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው“ ብላችሁ ቅዱስ ሲኖዶስን ተሳደባችሁ ማኅበረ ቅዱሳንንም የስድብ ናዳ አወረዳችሁበት፡፡
  “በሕገ ወጥ መንገድ ውግዘት ያስተላለፈው ሲኖዶስ ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ ማውገዙና ሕግ ማፍረሱ ሳያንስ፣ በመግለጫው መጨረሻ ላይ የተወገዙት ይቅርታ ከጠየቁ ቤተክርስቲያን በሯ ክፍት ነው ማለቱ የተወገዙትን ወገኖች በእጅጉ እንዳሳዘነ እየተነገረ ነው፡፡” በማለት ለቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ለመስጠትም ፈልጋችሁ ነበር፡፡
  ይሄው ዛሬእዉነቱ ታወቀና አገር ያወቀውን ጸሃይ የሞከውን ዉነታ ለመደበቅ አልቻላችሁም፡፡ ግብረ ሰዶማዊ የጻፋቸውን መጽሃፍ እያሞካሻችሁ አሁንም እንድናነብ ትጋብዙናላችሁ፡፡ እኛ ዕድሜ ሰጥቶን እናያለን፡፡ እንናተ ዛሬ አሸናፊን ለመውቀስ በሌላችሁ መንፈሳዊነት እየተሯሯጣችሁ ነው፡፡ ለመሆኑ ከአሸናፊ በምን ትለያላችሁ፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት የገባው በፕሮቴስታንት ነው፡፡ ሃገራችንን የውርደት ካባ አለበሳችኋት፡፡ ከእናንተ ጋር……. እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ፡፡ ኢትዮጵያን ህይወት አልባ አደረጋችኋ!!!!!
  አሸናፊ አንቀጸ ብርሃን የሚባል ማኅበር አላውቅም ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስን ዋሸ፡፡ እናንተ ደግሞ ሥራ አስኪያጅ እንደሆነ መሠከራችሁበት:: እግዚአብሔርን ሊያውቁት ባለወደዱ ቁጥር እዕምሮን ለማይገባ ነገር አሳልፎ እንደሚሰጥ አያችሁት? እናንተም ካልተመለሳችሁ ነገ በዚህ ግብረሰዶማዊነት የሚያውቃችሁ ሁሉ አደባባይ ወጣዋል፡፡
  ቤተ ክርስቲያን አሁንም አትጠላችሁም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም አትመለሱ አላለም፡፡ ነገር ግን የምትመለሱት ልታስተምሩ ሳይሆን የበደላችኋትን ቤተ ክርስቲያን ይቅርታ ብላችሁ እድሜያችሁን በንስሃ እንድታሳልፉ ነው፡፡ እናንተ እንመለስና እንግባ የምትሉ በልባችሁ ያለውን የአጋንንት መንፈስ ይዛችሁ መድረክ ላይ ለመውጣት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን አይዋጥላትም፡፡ የሰደባችኋው ቅዱሳን ቢያዝኔባችሁም ዛሬም እንድትመለሱ እንደሚጸልዩላችሁ አትርሱ፡፡- ቅዱሳን በዚህ አይበቀሉም! የሚበቀል አምላክ ስላላቸው!
  መናፍቃን ፤ - አትፍሩ ደፍራችሁ ተመለሱ፡፡ ወደ ኑፋቄ ያስገባችሁትን ሰው አትፍሩ፡፡ ከእናንተ አይቶ ነግ ተምሮ ይመለሳል፡፡ የሰውን ሃሜት አትፍሩ፡- ቤተ ክርስቲያን ተመልሳችሁ ቁጭ ብላችሁ እንድትማሩ ትፈልጋለች፡፡
  አምላከ ቅዱሳን ተመልሳችሁ ላጠፋችሁት ጥፋት ደግሞ ይቅርታ ጠይቃችሁ በቀደመ ቤታችሁ ለመኖር ይርዳችሁ፡፡

  ReplyDelete
 46. I have a question?

  I guess practicing Sodomy & homosexuality is punishable by law in our country, Ethiopia. And, my Q is: why don’t you take Daqon Ashenafi to the courts if you believe you have the evidence?

  Thank you!

  ReplyDelete
 47. wegenoche yihe sew auneme altewem sedomawi practisun ketelobetal

  ReplyDelete
 48. ሰወች ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ ፡፡ ሲቀጥል ደግሞ ሁላችንም ቢሆን የራሳችንን ጉድፍ ደብቀን ስለሰው ምናወራው ፡፡ አትፍረድ ይፈረድብሀል ፡፡ ማንም ከሀጥያጥ ንፁህ የሆነ በድንጋይ ይውገረው ፤፤

  ReplyDelete