Tuesday, May 5, 2015

በስደት ላይ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ 41ኛ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቀቀ።

Read in PDF

ከሚያዚያ 21 እስከ 23 2007 ዓ. ም በባልቲሞር የኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ሲካሄድ የሰነበተው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከወትሮው ለየት ያለበት ነገር ብዛት ያላቸው ካህናት መገኘታቸው፣ እንዲሁም ጳጳሳት እና ካህናት የተለያየ ጉባኤ ያካሄዱበት መሆኑ ነው። ድሮ ካህናቱ እና ጳጳሳቱ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ እኩል ይወያዩበት የነበረው ሲኖዶስ ዘንድሮ ግን ካህናቱን ለብቻቸው እንዲሰበሰቡ በማድረግ ከጳጳሳት ጉባኤ አስወጥቷቸዋል። 
 በካህናት ጉባኤ ላይ በርከት ያሉ ጉዳዮች ተነሥተዋል። ውስጥ ለውስጥ አንዷለምና አባ ጽጌ ይመሩት የነበረው የነአቶ ምርጫው ቡድን በነአባ ገብረ ስላሴና በነ አባ ሀብቴ በኩል ቆሟል የተባለው የምዕናን ጉባኤ ዋና መከራከሪያ ነበር ተብሏል በነዚህ ጉባኤያት ላይ የተወሰነውን ግን ለጊዜው እናቆየው።ካህናቱን ለሁለት ክፍሎ ሲያፋልም የቆየበት ርጅም ጊዜ ግን በእርቅ ተደምድሟል። በላስቤጋስ ሚካኤል ለሚገኘው ተሰዳቢ ወጣት የስድብ ዶክሜንት በማቀበል አባ ወልደ ትንሣኤን እና ሌሎች አገልጋዮችን ሲያስረግሙ የነበሩት የነአቶ ምርጫው ቡድን አባ ወልደ ትንሣኤና አባ ገብረ ሥላሴ እየዞሩ ማስተማር እንዲታገዱ ያቀረቡት ሐሳብ መሳቂያ ሆኗል። የላስቤጋሱ ተሳዳቢ ግን እነአባ ወልደ ትንሣኤ ካገልግሎት ታገዱ ሲል ሰበር ዜና አድርጎ አቅርቦታል። ይህ ሰው ሐሰትን ሲናገር ስቅጥጥ የማይለው የደቡብ አፍሪካ የኢምግሬሽን ደላላ እንደነበር ታውቋል። የሰላሙ እጦት ዋና ምክንያቶች ናቸው የተባሉ ካህናት ተወቅሰዋል አንዷለምና አባ ጽጌም ከተወቃሾ ነበሩ። በሁሉም ዘንድ የነበረው ጥርጣሬ ግልጥ ወቀሳ ቀርቦበታል። በመጨረሻም ያለፈውን ነገር በመተው በሁሉም ካህናት መካከል እርቀ ሰላም ተደርጓል።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ያቀረቡት ማብራሪያ ያለምንም ተቃውሞ ተቀባይነት አግኝቶ ታልፏል። ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንንም ማጠናከር እንደሚገባ ታምኖባታል።   
  የሲያትሎቹ አቡነ ሉቃስና አባ ታደሰ (አባ ገ.ሥላሴ) ከመምህር ልዑለ ቃል ጋር አንታረቅም በማለታቸው በክፉ አሳቢነት ተፈርጀዋል። የነአባ ታደሰ እምቢተኝነት ብዙ ሰዎችን በጣም ያሳዘነ ነው። መምህር ልዑለ ቃል ከአትላንታ  ቤተ ሰቦቹ ወደሚገኙበት ወደ ሲያትል ለመሄድ ሲያስብ እነ አባ ታደሰን ወደ ሲያትል ልመጣ ነው ከእናንተ ቤተ ክርስቲያን አብሬያችሁ ላገልግል ብሎ ጠይቋቸው ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በመግለጣቸው እንግዲያስ እናንተ ካልወደዳችሁኝ የራሴን ቤተ ክርስቲያን መሥርቼ አገለግላለሁ እንጂ ያለቤተ ክርስቲያን ልኖር አልችልም ብሎ ለምኗቸዋል። እነርሱም ቤተ ክርስቲያን መክፈት ትችላለህ ወደ እኛ ብትመጣ ግን አንቀበልህም በሚለው ተስማምተው ነበር። ይህን ያሉበት ምክንያት የልዑለ ቃልን ችሎታና ተደማጭነት በመፍራት ነው። ደካማ ካህናት ሁል ጊዜ ድካማቸውን የሚሸፍኑት ከነርሱ በላይ ተደማጭነት ያለውን ሰው ከአካባቢያቸው በማራቅና ሕዝቡን በማፈን ነው። እነ አባ ታደሰ ይህን ይበሉ እንጂ ውስጥ ለውስጥ ግን ልዑለ ቃል በስያትል ቤተ ክርስቲያን እንዳይከፍትባቸው አቡነ መልከ ጼዴቅን ሲማጸኑ ነበር። አቡነ መልከ ጼዴቅም ከናንተ ጋር ላገልግል ሲል እምቢ አላችሁ የራሴን ልክፈት ሲልም እምቢ ካላችሁ እናንተ ቅናት ነው ያለባችሁ ብለው መልስ በመስጠት ሳይሰሟቸው ቀርተዋል። ይህ ጉዳይ ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ እነ አባ ታደሰ አንቀበልም በማለታቸው ልዑለ ቃል ቤተ ክርስቲያን እንዲከፍት ተወስኖለታል። ለዚህም አቡነ ኤልያስና ሊቀ ካህናት ምሳሌ ተገኝተው እንዲባርኩ ትኬት ተቆርጦላቸው ሲያትል ከመጡ በኋላ በነ አባ ታደሰ አስፈራሪነት በመታገዳቸው በአቡነ ያዕቆብ ባራኪነት ቤተ ክርስቲያኑ ተከፈተ። እነ አባ ታደሰ እንደፈሩትም ልዑለ ቃል በሚሰብከው የእግዚአብሔር ቃል ሕዝቡን መሳብ ቻለ አሁን ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት በመፈለግ ላይ ነው። ይህ ስጋት ላይ የጣላቸው የሲያትሉ ጳጳስ አቡነ ሉቃስ ልዑለ ቃልን በሀገረ ስብከቴ እውቅና አልሰጥም አሉ። ሲኖዶሱ እርቅ እንዲፈጽሙ እና በጋራ እንዲያገለግሉ ቢለምናቸውም አሻፈረኝ ብለው እድላቸውን አባላሽተዋል። ምክንያታቸውን ሲጠየቁ ከዚህ በፊት በቤተ ክርሥቲያናቸው እየጋበዙት ያስተምር እንዳልነበረ መናፍቅ ስለሆነ ነው በማለት ነጠላ ዜማቸውን ለቀዋል።  ነገር ግን ከኮልፌ እስከ ሜኖስታ፤ ከሜኖስታ እስከ ኦክላንድ፤ ከኦክላንድ እስከ ዴንቨር ልዩና አስገራሚ የታሪክ ዓይነት ያለውን ሰው ተቀብለው ቅዱስ ቅዱስ እያሉት ይገኛሉ። የሚቀኑበትን ሰው መናፍቅ ሲሉ በብዙ ነውር የተጨማለቀውን ሰው ግን ተቀብለው ቅዱስ ይሉታል።  ስለዚህ ሰው በእውነተኛ መረጃዎች የተደገፉ ታሪኮች ደርሰውናል፤ ንስሐ የማይገባና የማይለወጥ ከሆነ ለሌሎች ደህንነት ስንል ወደ አደባባይ እናወጣዋለን።     
 የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ 25ኛ በዐለ ሲመትን ለማክበር ዝግጅት ሲደረግ ቢቆይም ቅዱስነታቸው ግን ልጆቼ እንደበግ በታረዱበት ወቅት በዓል አላደርግም በማለታቸው በዓሉ የሰማዕታቱ ሆኗል። በዚያውም ሰማዕታተ ኢትዮጵያ በሀገረ ሊቢያ ተብለው በየዓመቱ እንዲታሰቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወስኗል። ደግ ነገር ነው።
 ቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስን እንደራሴ አድርገው ሹመው የነበረ ሲሆን ሌሎች ጳጳሳት በከባድ ሁኔታ ተቃውመውታል። በኦሐዮው ሲኖዶስ እንደራሴ እንዲሾም ሁሉም ጳጳሳት ተስማምተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፤ እንደራሲነቱን ሲያደቡ የነበሩት ሁሉ አልተቀበሉትም። አቡነ ዮሐንስ በተወሰኑ ካህናትና በፓትርያርኩ ተመራጭ ሆነው ሲሾሙ የሚያስቅና የማይረሳ ታሪክ ተከስቷል። ጥቂት መንፈሳዊ ጳጳሳትና ካህናት ድጋፍ አድርገው አልተሳካላቸውም፤ እንደራሴ ይሾም የሚለውን ሐሳብ ያመጡት ጳጳሳት ዋና ተቃዋሚ ሆነው ታይተዋል። ስለዚህ እንደራሲ ለጊዜው አያስፈለግም በሚለው ተደምድሟል።  የሥልጣን ነገር ሲመጣ የማያዳልጠው መንፈሳዊ ጳጳስ ማግኘት አልተቻለም። ሊቀ ካህናት ምሳሌ አቡነ ዮሐንስን ለምን እንደሚቃወሙ ግን ለብዙዎች ግራ የሚያጋባ ሆኗል።
 በርካታ ካህናት ፀረ ወንጌል እንቅስቃሴዎችን የሚካሂዱ የማቅ ሰዎች ገብተውብናል የሚለውን ሥጋታቸውን ከፍ አድርገው ተናግረዋል። የዚህ እንቅሥቃሴ ተዋናይ የዳላሱ ነው የሚለው የሁሉም ጥርጣሬ ነው። በሕዝቡም ሆነ በአገልጋዩ ዘንድ ግን ምንም ተቀባይነት ባማጣቱ፤ ያሬዳዊ ዜማን ለዓለም አስተዋውቃለሁ በሚል ሌላ መንገድ በማፈላለግ ላይ ነው መጨረሻውን ግን አብረን የምናየው ይሆናል።
 በመጨረሻም ኢትዮጵያን የሚገዛው መንግሥት የወጣቱ ስደት ምክንያት መሆኑን በማመን በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍ በማውገዝና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድነት ጥሪ የሚያቀርብ መግለጫ በማቅረብ ጉባኤው ተፈጽሟል።   

3 comments:

 1. ያቀረባችሁት ሪፖርት እጥር ምጥን ያለ መሆኑ ጥሩ ነው። ነገር ግን ለኮፍ ለኮፍ ያደረጋችኋቸውን ነጥቦች መጻፋችሁ ካልቀረ ለሰዉ ግልጽ እንዲሆን ትንሽ ሰፋ አድርጋችሁ፤ የጠቀሳችኋቸውን ቢጽ ሃሳውያን በመስታወት እራሳቸውን ያዩ ዘንድ ብትታደጓቸው ጥሩ ነበር። ታዲያ አንባቢው ብቻ ሳይሆን እነሱም ቢሆኑ ከተዘፈቁበት ማጥ ሊወጡ ስለሚችሉ ባያመሰግኗችሁ እንኳ ሰይጣናዊ ተግባራቸው መታወቁ ሲገባቸው ምናልባት ከስም መለጠፍ (መናፍቅ፤ ተሃድሶ፤ ጴንጤ፤ ፕሮቴስታንት፤ ወዘተ....) በሽታቸው ይሽሩ ይሆናል። ልዑለቃል የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ስላስተማረ መናፍቅ ከተባለ መናፍቅ ባዮች ወንድማቸውን ይቅር አንልም አሻፈረን ያሉት ምን ሊባሉ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነው የሚለው። ታዲያ የበደልከውን ሳይሆን የበደለህን ይቅርታ ጠይቀው የሚለው የወንጌል ቃል የተጻፈው ለማን ነው? ካህናቱ ይቅር ካልተባባሉ? ምእመናኑ ምን ይጠበቅባቸዋል? በጽሁፋችሁ የተጠቀሱት የተዝጎረጎረ ታሪክ ያላቸው እነግማዊና ምርጫው ከነግብረአበሮቻቸው ቤተክርስቲያናትን ሲበጠብጡ መኖራቸው አንሶ አሁን ደግሞ ሲኖዶስን ለማፍረስ በከንቱ ሲደክሙ ይታያሉ። ይኸ ሁሉ የሆነው ማንነታቸውን በማያውቅ ህብረተሰብ መካከል ገብተው እኛ እናውቅልሃለን ዝም ብለህ ተከተለን እያሉ አይኑን ሸብበው በሃሰት እየሞሉ ወደ ጥፋት እየነዱት ስለሆነ ነው። ስለዚህ አለን የምትሉትን ማስረጃ ሁሉ ብትዘግቡና እነሱም ለንስኃ ቢበቁ፤ ምእመናኑም ከስህተት ተመልሶ ይቅር ቢባባል ለናንተም እግዚአብሔር ዋጋችሁን አያሳጣችሁም። ከዚህ በፊት የግማዊን ታሪክ እናወጣለን ብላችሁ ባለማውጣታችሁ ዛሬ ጳጳሳትን ሽቅብ እንዲሳደብ፤ ቤተክርስቲያናትን እንዲያበጣብጥና፤ የልብ ልብ እንዲበቃው አድርጋችኋል። ቀጥሎ ምን ይሰራ ይሆን፧ እግዚአብሔር የተጫነውን ያቅልለት!

  ReplyDelete
 2. ስደተኛ ሁላ በሰው አገር ምን አንጨረጨረው የፈረኝጅ ባሪያ

  ReplyDelete
 3. ውድ አባቶቻችን ወንድሞቻችን!
  የቀረበው ሪፖርት ጥሩ ሆነ መጥፎ ሆን ይህ ለእኛ ለሁላችን አይጠቅምም። ለእኛ የሚጠቅመን ሁላችንም እግዚአብሔርን አውቀን ስንኖር ነው። በመካከላችን ሰላም ሲኖር ነው።
  ይህ ዛሬ የምንሰማው ነገር ሁሉ በጥበብ የተሞላ ሳይሆን በችግርና በጥል የተሞላ ከተማ (ቤተ-ክርስትያን) ውስጥ ያለን መሆኑን ያስተምረናል። ሁላችንም ጊዚያችንን የምናጠፋው እርስ በርሳችን በመካሰስ ስለሆነ ይህ ለሁላችንም ያሳዝናልም አይጠቅምም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይሰጥምም። ስለዚህ ጥበበኛው የት አለ? አስተዋዩስ የት አለ? ይህ ሁሉ እሳት በቤተ ክርስትያናችን ሲነድ አንድ ጥበብኛ ከመካከላችን ቢኖር ከመንደድ እንድናለን። ቅዱስ ሰለሞንም በመጽሀፉ ውስጥ እንደሚመክረን አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች ይላል። ይህችንም ከተማ አጥፊ መጣባትና ከበባትም ነገር ግን አንድ የተናቀ ጥበበኛ ነበረና ከጥፈት ከውድመት ከእሳት ይህችን ከተማ አዳናት ይላል። በዚህም መሠረት እኛስ እንዲሁ በድንቁርና ስንካሰሰ ከመካከላችን አንድ ጥበበኛ የለም? በዚህም ቅዱስ ሰለሞን እንደሚመክረን፡
  " 14፤ ታናሽ ከተማ ነበረች፥ ጥቂቶች ሰዎችም ነበሩባት፤ ታላቅ ንጉሥም መጣባት ከበባትም፥ ታላቅ ግንብም ሠራባት።15፤ ጠቢብ ድሀ ሰውም ተገኘባት፥ ያችንም ከተማ በጥበቡ አዳናት፤ ያን ድሀ ሰው ግን ማንም አላሰበውም።16፤ እኔም። ከኃይል ይልቅ ጥበብ ትበልጣለች፤ የድሀው ጥበብ ግን ተናቀች ቃሉም አልተሰማችም አልሁ።17፤ በሰነፎች መካከል ከሚጮኽ ከገዢው ጩኸት ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች።18፤ ከጦር መሣሪያዎች ይልቅ ጥበብ ትሻላለች፤ አንድ ኃጢአተኛ ግን ብዙ መልካምን ያጠፋል።" (መክ. ም9)። ይላል።
  ሁላችንም እግዚአብሔርን ማስደሰት የሚመስለን ከላይ በለበስነው ልብስ ድምቀት የሚመስለን ብዙዎች ነን። ነገር ግን በሁላችን ላይ ጥበብ የሚሰጠውን ቃሉን ተገንዝበን ብንራመድ ይህ ሁሉ ብጥብጥ መከፋፈል አይኖርም። ስለዚህ እባካችሁ እኛንም ይዛችሁ ወደ ሲኦል አትውረዱ! እናንተን ተከትለን ስንሮጥ ሁላችንም ማረፊያችን እሳት እንዳይሆን ጥበብን ማስተዋልን እውቀትን የሚሰጠውን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ቃል አስተምሩን። በቃሉም እንቀደሳለን በቃሉም እንባረካለን በቃሉም ሕይወትን እናገኛለን። እኛ ዛሬ ለራስችሁ ጥቅም በምታደርጉት ትግል ምክንያት እኛም ክርስትያኖች በእናንተ ብጥብጥ ስለተሞላን ይህ ሁሉ ለእኛ አይረባንም አይጠቅመንም። እባካችሁ አስተውሉ፡! ይቅርታን አብዙ! አንድ ሁኑ ! ስም በመጥራት ሰውን አትበድሉ! እራሳችሁን ጻድቅ አታድርጉ! ልብ አድርጉ ያ የተናቀው ድኃ ጥበበኛ ክፉን ነገር ያሸነፈው እግዚአብሔርን መፍራትን ስላወቀ ነው። ነገር ግን እናንተ ባላችሁ ሥልጣን ታዋቂነት በአለባበሳችሁ በመልካችሁ በተናጋሪነታችሁ እራሳችሁንም አያሳስታችሁ እኛንም ሁሉ ታሳስታላችሁ። ለሥጋችሁ ጥቅም ስለምትሮጡ በልባችሁ ያለው መዝገባችሁ ሁሉ ሕይወት የሚሰጠው የክርስቶስ መንፈስ የራቀው ይመስላል። ለዚህም ነው ስትወጋገዙ ሁልጊዘ የምትኖሩት። ስለዚህ እግዚአብሔር ይህንን አይፈልግም። እርሱ የሚፈልገው የእርሱን በጎች በጥበብ የሚመሩትን ጥሩ ሠራተኞችን ነው። ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃሉ እንደሚአስተምረን፡
  " 43 ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር።44 ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።45 እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?46 ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤47 እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል።48 ያ ክፉ ባሪያ ግን። ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ፥49 ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥50 የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፥51 ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፥ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።" (ማቴ. ም24) ይላል።
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር!

  ReplyDelete