Wednesday, May 6, 2015

የማኅበረ ቅዱሳን የአመራር አካላት በሁከት ፈጣሪነት ታሠሩ


REad in PDF 
መሪጌታ ሳለልኝ ከቤተክህነት
በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ ለተሰዉት ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዛዘንና አረመኔያዊ ተግባር የፈጸሙትን ገዳዮች ለማውገዝ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 / በተደረገው ሰልፍ ረብሻ መነሳቱና ብዙዎች እንደተጎዱ፤ ብዙዎችም እንደታሠሩ ይታወሳል። በደረሰን መረጃ በአሁኑ ሰዓት ብዙዎች በተደረገው የማጣራት ሥራ የተፈቱ ሲሆን አንድ መቶ ሃያ ግለሰቦች ደግሞ የረብሻው ቀስቃሽና አስተባባሪዎች ሆነው በመገኘታቸው ጉዳያቸው ወደ ፍርድ ቤት ይተላለፋል እንደተባለ ተሰምቷል። ከእነዚህም ዋናዎቹ ከሃያ እስከ ሰላሣ የሚደርሱ የማኅበረ ቅዱሳን የአመራር አካላት መሆናቸው ታውቋል። ማቅ ውስጥ ለውስጥ ሲያራምድ የቆየው ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ጽንፈኝነት ውጤት አልባ ሲሆን ድንጋይ ይዞ አደባባይ መውጣቱ ለብዙዎች ተግራሞት ሆኗል። በሌላ አንጻር የኢትዮጵያውያንና የመላው ዓለም ክርስቲያኖችን ልብ ያደማ ድርጊት ለማውገዝ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በተመሳሳይ ሁኔታ ለረብሻና ለሁከት ተዘጋጅቶ አደባባይ መውጣት አሳዛኝ ተግባር ነው
ሌላው የማቅ አቀንቃኝ የሆነውና ባለፈው ጊዜ በቤተ ክርስቲያንዋ ትምህርተ ሃይማኖት ላይ ኑፋቄን ዘርቶ በኋላ ጉዳዩ በይቅርታ ታለፈ የተባለለት ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ ከእነዚሁ የማቅ አባላት ጋር ድንጋይ ሲወረውር በመታየቱ ተይዞ እንደታሠረ ታውቋል።
የእነዚህ የማቅ አባላትም ሆኑ የቤተ ክህነት ሠራተኛ የሆነው ኃይለ ጊዮርጊስ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ነን እያሉ ኃዘንተኞችን መከታ አድርገው ድንጋይ መወርወር እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው። እምነታቸውንም ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው። ምክንያቱም ይጠሩበት እንጂ እምነታቸውም ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት እንዳልሆነ የዕለት ዕለት ተግባራቸው ምሥክር ነው።

ቅዱስ ሲኖዶስ  ሚያዝያ 27 ቀን 2007 / የጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ባደረገበት ዕለት ሁከት ለመፍጠር ዕረፍት የሌለው ማቅ እራሱን በአዲስ አበባ የሰንበት /ቤቶች ውስጥ ሰውሮ ቅዱስ ሲኖዶስ ገና ከጅምሩ ዓመታዊ ስብሰባውን በብጥብጥና በሁከት እንዲጀምር ጥረት አድርገዋል። ቅዱስ ፓትርያሪኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት
የመክፈቻ ጸሎት አድርገው ከቤተ ክርስቲያን ሲወጡ መዝሙር ለማቅረብ ተሰበሰብን ያሉት የማቅ አባላት ያዘጋጀነው ደብዳቤ መነበብ አለበት ብለው ሁከት አስነሱ። በአዲስ አበባ የሰንበት /ቤት አንድነት ስም ያዘጋጁት የአድማ ደብዳቤ
የያዘው ዋና ነጥብ የሚከተለው ነው:
1. የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች እየተሸራረፉ ተፈጻሚነት አላገኙም።
2. እርስዎ (ቅዱስነትዎ) በየመድረኩ ስለሙስና የተናገሩት ከንግግር ያለፈ አይደለም።
3. ተሐድሶዎች በሹመትም በእልቅናም ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጠልቀው ገብተዋል።
4. በየአድባራቱ ዘረፋና ሙስና እየተባባሰ ሔዷል።
5. የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ አሥኪያጆች ሹመትን እንቃወማለን።
6. በተልዕኮ ደሞዝ የሚቀበሉ አስተዳዳሪዎች አሉ።
በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህ ከላይ የተቀመጡት ጉዳዮች በአቡነ ሉቃስና በአቡነ ማቴዎስ እንደተዘጋጁ የውስጥ ምንጮቻችን ገልጸውልናል። የማቅ ጳጳሳት ማቅን አሰልፈው ለመረበሽ የፈለጉት በአጀንዳነት ቀርጸው የሲኖዶስ አባላትን ለመበጥበጥና የፈለጉትን አጀንዳ ለማስፈፀም እንደሆነ ይታመናል። ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይና ሐዋርያዊ ተልዕኮዋ ላይ ትኩረት እንዳትሰጥ ለማድረግ እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል። ከሁሉም ለማቅ የራስ ምታት የሆነበት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዋናና የምክትል ሥራአስኪያጆች ሹመት ነው። ምክንያቱም በአባ እስጢፋ በኩል ያቀዱት ዕቅድ ስላልተሳካላቸው መሆኑ
ሲታወቅ በይበልጥ ግን የአሁኑ ሥራአስኪያጆች እነርሱ የሚቃወሙአቸው፤ በቂ ችሎታ ያላቸውና ህሊናቸውን የማይሸጡ በመሆናቸው ነው። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ እንኳ የአስተዳደር ሥራውን እያቃኑ መሆኑንና የተገፉ አባቶችና ወንድሞች ምስጋናን በሚያቀርቡበት ሰዓት ማቅ ለተቃውሞ አደባባይ መውጣት
ትልቅ ትዝብት ላይ ጥሎታል።
……………ይቀጥላል……………

12 comments:

 1. Hahahah Besak....You Better Read the bible and come to the truth rather than disseminating false allegations. Yemedan Ken ahun new ebakih wendime Temeles...

  ReplyDelete
 2. እግዚአብሔር ህሙማንን ይፈውስ…የሉተርን መንፈስ ያስታግስ…ጉባኤ ከለባትን ይገስጽልን፡፡አሜን

  ReplyDelete
 3. አይ መሪጌታ፣ ባይሆን የሊቃውንቱን ስም ለእርስዎ መጠሪያ ባያደርጉት ምናለበት፡፡
  “ደክመ በጸዊረ-ስም ማልኮስ ሐካይ” - የሚለውን መወድስ ሰምተውታል፡፡
  መቸስ መሪጌታ አይደሉ እንዴ ? ያውም ከቤተ- ክህነት ii
  ለነገሩ ፓስተርነቱን የት ጥለው ነው መሪጌታ ነኝ የሚሉት፡፡

  ReplyDelete
 4. Can you pls mention a name and their position in MK? I know you guys are all mindless.

  ReplyDelete
 5. MK leadership is a disciplined and highly responsible team. You are using the wrong weapon to fight them!

  ReplyDelete
 6. ለመርጌታ ሳለልኝ ከሲኦል
  ሐሰተኛ የሐሰት አባት
  ባለሙያ የአሉባለታ ወሬው ቋት
  ሁሉም አውቋል ሰይጣናዊው ቅሰጣህን
  በሰይጣን መንፈስመዋጋትህ
  ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያልሆንህ መሆንሀን
  ሁሉም አውቋል ማንነትህን
  ከሰይጣን ጎራ ለጌዎን መሆንህን
  በሐሰት መንፈስ መሞላትህን
  ታውቋ ከአማናዊቷ ቤተክር ቤተክህነት አለመሆንህ
  ታውቋል ከሲኦል ማህበር ከእውነት ተቃዋሚ መሆንህ
  መርጌታ ሳለልኝ፦ ድንጋይ ወርዋሪ ሁከት ፈጣሪ ማን እንደሆነ እየሳልክ በትንታህ እያነቀህም ቢሆን ታውቀዋለህ። ይኸውም የእውነትን መግደያ የኦርቶዶክስን ማድሚያና ማወኪያ የአገልጋይ የአማኞቿ ደም ማፍሰሻ መግደያ በነቀያፋ መደር መሽገህ በሐሰትና የፈጠራ ወሬ ስም እያጠፋህ ከሲኦል ከአለም ሆነህ ሳለ በሐሰትና በማስመሰል ከቤተክህነት እያልክ ድንጋይ የምትወረውር ሁከትን የምትቀስጥ አንተና አንተን የመሰሉት ሐሰተኞች ሳይሆኑ መስለው ነን እያሉ በክፉ መንፈስ የተሞሉና የታሰሩት ናቸው። በዚህ ድራማህበለበጣ የሚስቅብህ እንጂ የሚታለል ሞኝ እንደሌለ ግልጽ ነው። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች፣ አገልጋዮች በዚህ አሉባልታህ ምንም የሚጎድልባቸውም ሆነ የሚያስጨንቃቸው ነገርየለም። የኦርቶዶክስ አባቶችና አገልጋዮች እለት ኦለት የሚያስጨንቃቸው በአንተና እንዳተ ባሉ ሐሰተኛ አስመሳዮች የክርስቶስ ወንጌልና የመላእክት ስርአት የሆነው የቤተክርስቲያን አገልግሎት በእንክርዳዳችሁ እንዳይበከልና ለክብርና ለህይወት የተፈጠርን የሰውልጆች በእናንተ እርኩሰት እንዳይወድቁና እንዳይሞቱ ነው የሚያስጨንቃቸው። እንጂ ይሔን የአህዛብነታችሁን ተግባር ስድብ አሉባልታ፣ ሐሰተኛ ክስ ውንጀላ፣ እንትና ከብዙ ሴቶች ጋር ታየ ከጋብቻ ውጭ ልጅ ወልዷል፣ ተራ የጠጂ ቤት ወሬ የፈጠራ ታሪካ በማምረት ስም ማጥፋታችሁ፣ እውነቱን ሐሰት ሐሰቱን እውነት ማለታችሁ፣ ነጩን ጥቁር ጥቁሩን ነጭ ማድረጋችሁ፣ ህይወቱን ሞት ሞቱን ህይወት ማድረጋችሁ፣ ዘፈኑን መዝሙር መዝሙሩን ዘፈን ማለታችሁ፣ የአለምን ዳንኪራ ዳንሱን ሽብሸባ ወረብ ወረብ ሽብሸባውን ዳንስ ዳንኪራ መድረጋችሁ፣ የእርኩስ መንፈሱን ጉሪያ ሁካታ መንቀጥቀጥ መዝለፍለፉን የመንፈስ ቅዱስ የመላእክት ምስጋና የሆነውን የመንፈስ ቅዱስን ቅዳሴ ዝማሬውን የእርኩስ መንፈስ ማለታችሁን፣ እንክርዳዱን ወንጌል ወንጌሉን እንክርዳድ ብሎ መፈረጃችሁን፣ ሐጢያቱን ጽድቅ ጽድቁን ሐጢያ እያላችሁ መፈረጂ የእናንተ የህይወት ቃልና መመሪያ ካደረጋችሁት የዛሬ ሳይሆን ከቀደመው አባታችን ጀምሮ ነው። አሳዳሪያችሁና አሰማያችሁ የቀደመው እባብ አባታችን አዳምንና እናታችን ሔዋንን የሞትን መብል ያስበላቸው በፀጋ ተውበው የሚኖሩበትን የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ትእዛዝ የሆነውን አትብሉ የተባሏትን ቅጠል ከበላችሁ አምላክ ትሆናላችሁ ሁሉን የምታውቁ ትሆናላችሁ በማለት ቅጠሏን አምላክና አዋቂ የምታደርግ በማድረግ ነው። ቅጠሏ ግን አምላክም አዋቂም የማታደረግ መራራ ቅጠል ሞትን የምታመጣ ነበረች። እናም የአንተም ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑን ጨለማ ማድረግህና የተዋህዶን ልጆች መዋጋትህ እንዲሁም ሳትሆን እንዲህ ነኝ ብለህ ማስመሰልህ የአባትህ የእባብ ስራ ነውና ካንተ የሚጠበቅ ነው። ነገር ግን የእውነትና የይወት መንገድ የሆነችው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን በአንተና በመሰሎችህ የጥፋት ጦርና ፍላፃ ሳትጠፋ በመከራ ውስጥ እያበራች እስከ ምፅአት ትኖራለች። ለአንተና ለመሰሎችህ ግን የመውጊያውን ቀስት ብትቃወሙ ለእናንተ ይብስባችኋል። ስለሆነም ወደ አይምሮህ ልብ ብትመለስ ይበጂሃል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዴት ብየ እንደምገልፅ አላውቅም፣ ወላዲተ አምላክ ትባርክህ፣

   Delete
  2. ወንድሜ ማሩ ከበደ፦ እኔ በምንም የማልለካ ተራ ሰው ነኝና ለኔ ያለህን እይታ እባክህ እንዳን ምንም እንደማያቅ ትንሽ ግለሰብ አድርገህ ውሰደኝ። ወንድሜ፦ እመ ብርሃን ወላዲተ አምላክ አንተንም በልጇ ፍቅር እንዲሁም በበረከቷ ትባርክህ። ወንድሜ ማሩ፤ ለቤተክርስቲያናችን እምነትና ስርዓት ፀንተን በመቆም ማተባችንን ሊያስበጥሱን፣ ከቅዱሳን በረከትና ምልጃ ሊለዩን፤ ከእውነተኛው የክርስቶስ ወንጌል ነቅለው በነሉተር ፍልስፍና በአለም የስጋ ፍላጎት የተረት እንክርዳዳቸው ወደ ዘባችነት ለመዝፈቅ በዙሪያችን ከሚያገሱት በቤተክርስቲያናችን የማእረግ ስሞች ተደብቀው ከሚዘላብዱት መናፍቃን እራሳችነን እንድንከላከል ሁልጊዜ በቤተክርስቲያናችን የክርስቶስ ወንጌል አስተምሮ፣ ዝማሬና ስርዓት ወገባችን የታጠቅን መሆን ይገባናል።

   Delete
  3. እንዴ ዳሞት ተራነትህን ታውቃለህ እንዴ። ተመስገን ጌታሆይ የታወረ ዐይኑን ስላበራህለት። አሁን የቀረህ የኢየሱስነን ብቸኛ አዳኝነት መረዳት ብቻ ነው።

   Delete
 7. በእጅግ ከሚያስገርሙ ሀሰት መካከል ለነ የማነ እና አሽብር እየሰጣችሁት ያለው ምስክርነት ነው።የማነ የታውቀ ሙሰኛ የመቅደሱን ገንዘብ ትታችሁ የማነ በድሆች ሰም ገንዘብ ሰብስቦ ከተሰወረ የግለሰብ ጋር ለድሆች የትሰበስብን ገንዘብ ከኤልሻዳይ ሚባል በድርጅት ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ጸሐፊ እያለ ከየእጥቢያው በእማካኝ 40ሺ ብር በመስብሰብ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር የበላ ሌባ ነው ። ዛሬ ከተሾመ በውሃላ የማሀይም አባቱን አሰራር የትቃውሙትን ካህናት ጎንደርች ናቸው ብሎ በወረዳ ቤተክህነት በኩል ያገዳቸው ሲሆን ኤልያስ በትባለው ሂሳብ ሹን በኩል ስርቆቱንብተያይዞት እያልለ ስለውንጌል ይገደኛል የሚል ብሎግ እንዳት እንዲህ አይነት ሌባን ይደግፋል። የቦሌ መድሀኔ ዓለም ዘራፍስ ይረሳል እረ ተዉ ከላይ ተመልካች አምላክ አል።ጌታ ይቅር። ይበላችሁ

  ReplyDelete
 8. የማቅ ኑሮ ይለያል ዘንድሮ።

  ReplyDelete
 9. ነጭ ውሸት - ስትዋሹ የሚመስል አድርጉት

  ReplyDelete