Friday, May 15, 2015

ይድረስ ለኢህአዴግና ለተቃዋሚዎች።እኔ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብሎም በሀገሪቱ የሕይወት ለውጥ እንዲመጣ የድርሻዬን እየተወጣሁ የምገኝ የወንጌል ሰባኪ ነኝ። ዛሬ ይህን መልእክት ስጽፍላችሁ በማያገባኝ ገብቼ ፖለቲካን መነካካት ፈልጌ አይደለም። እኔ በወንጌል አገልግሎት የኢትዮጵያ ነጻነት እንደሚመጣ አምናለሁ፤ ወንጌል መግሥትንም ሆነ ለመንግሥትነት ያልበቁ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶችን ነጻ ያወጣል የሚል ትልቅ ተስፋ አለኝ። ይህ ብቻ አይደለም ወንጌል እርስ በርሳችን እንድንዋደድ፣ ያለፈውን በደላችንን ሳንቆጥር ይቅር እንድንባባል  አቅምን የሚሰጠን የእግዚአብሔር መለኮታዊ ኃይል ነው። ወንጌል በውስጡ ሌላም በረከት አለው፣ የሀገሪቱን ነውር ከትውልዱ ላይ በማንከባለል የእንጀራን በረከት የሚያወርስ መንፈሳዊ የግዝረት ሥርዓት ነው። የእግዚአብሔር የዙፋኑ መሠረት የሆኑት ፍትሕና ጽድቅ በሀገሪቱ እንዲሰፍኑ ወንጌል መሰበክ አለበት ብዬ አምናለሁ። ስለዚህም እኔና እኔን የሚመስሉ ጓደኞቼ የናንተን መንገድ ትተን የጌታን መንገድ ተከትለን ወንጌልን እንሰብካለንና ፖለቲከኞች መሆን አንፈልግም፣ ደግሞም የሚበጀንን አይተን መምረጥ እንጂ የሄትኛውም ፓርቲ ደጋፊ ሆነን አቀንቃኝ፣ ወይም ተቃዋሚ ሆነን የምናጥላላ አይደለንም።
  ታዲያ ምን ለማለት ፈልገህ ነው "ይድረስ ለኢህአዴግና ለተቃዋሚዎች” የሚል ርእስ ያለው መልእክት የምታስነብበን ? ማለታችሁ አይቀርም። መልሴ ምንም ፖለቲካ ባይመለከተኝም የሀገሬ ጉዳይ ግን ያሳስበኛልና አመለካከቴን ላካፍል የሚል ነው። እግዚአብሔር ለመኖሪያ የሚሆን አገር ሰጥቶናል እርሱን መንከባከብና መጠበቅ፣ ማልማትና ማሳመር ግዴታችን ነው። ኢትዮጵያዊ ስለሆንን የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተናል አገራችን በሰማይ ቢሆንም ወደዚያ የምንሄደው ምድር ላይ ቆይተን ነው ማንኛውም ሰው ወደ ሰማይ የሚያየው እኮ ምድር ላይ ሆኖ ነው እኔም ባየር ላይ አይደለሁምና ስለቆምሁበት ምድር የመናገር መብት አለኝ መንፈሳዊነት ምድርን ለቆ በሰማይ ላይ ብቻ መንሳፈፍ አይመስለኝም። እንግዲህ በዚህ ከተስማማን የሚከተለውን ምክር ለመለገስ እወዳለሁ።
ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለኝ መልእክት
. ብልህ እንሁን!
  በእኔ አመለካከት ብልህ መሆን ማለት ቅድሚያ ለሀገር ማሰብ ማለት ነው። በአሁኑ ሰዓት የዓለምን ሁኔታ መመልከት ብንችል ለሀገራችን የሚበጃትን ትልቅ ትምህርት እናገኛለን። በሶሪያ የተለያየ ጥቅም ያላቸው ኃይሎች በፈጠሩት ሽኩቻ ሕዝቡ ሰላሙን አጥቷል፣ አገሩን ትቶ ተሰዷል፣ ልጆቹንና ዘመዶቹን በሞት ተነጥቋል፣ ኑሮው ተመሰቃቅሎ የሌሎችን እርዳታ በመጠበቅ መኖር ጀምሯል። ይህም ሆኖ ለውጥ እናመጣለን ያሉት ቡድኖች መከራን ነው ያመጡት፣ መንግሥታቸው መለወጥ የማይችል ወይም ሀገሩን መከላከል የማይችል ሽባ ስለሆነ ሶሪያ ወደ ፈተና የገባች ሀገር ሆናለች። ዛሬ ሶርያ አይሲስ የሚባል ዓለም አቀፍ አውሬ የተሰማራባት አሳዛኝ አገር ሆናለች። ይህ የተለያየ ምኞት ያላቸው ጥቂት ቡድኖች የፈጠሩት ነገር ነው።

 የመን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው በዚያ ድህነቷ ላይ ያላትን እንኳ የሚያሳጣትን ሁከት ማቆም አልቻለችም። የመን ውስጥ ሰርቶ መብላት አይቻልም፣ ወጥቶ መግባት አይታሰብም፣ ምግብና ውሃ መጠላያም እየጠፋ ነው። ይህችን አገር እንደገና ለመገንባት ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ እግዜር ይወቀው። እንግዲህ የሊቢያን የኢራቅን የሶማሊያን የደቡብ ሱዳንን ችግር በዚህ አንጻር እንመልከተው።
 ምን ማድረግ አለብን?
የልዩ ልዩ ቡድኖችን ቅስቀሳ በጥንቃቄ ነቅተን እንጠብቅ። የተሳሳተ ዓላማቸውን በኛ ላይ እንዳያራግፉ እሳት ለኩሰው እርስ በእርሳችን እንዳያነዱን እንጠንቀቅ። በኢትዮጵያ ጉዳይ ከመቶ በላይ የሆኑ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ቡድኖች አሉ። ከመቶ በላይ የሆኑ የተለያዩ ቡድኖች፣ የተለያየ አቋም ያላቸው ናቸው እነዚህን ሁሉ ብንከተልና መቶ ቦታ ላይ ሆነን ብንጣላ ምን የምንሆን ይመስላችኋል? ማንስ መጥቶ ሊያስታርቀን ይችላል? እሺ ከመቶው ቡድን ውስጥ የትኛው ነው አገሪቱን ለመረከብ ብቃት ያለው?
  ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል እንደተባለው ወደ ኢትዮጵያ ለመግባትና ያለንን ለመንጠቅ የሚፈልጉ በርካታ ጅቦች መኖራቸውን ልንዘነጋው አይገባም። ለምሳሌ ግብፅ ለኢትዮጵያ ትተኛለች ብሎ ማሰብ ትልቅ ሞኝነት ነው። አባይን ገድበን ለመጠቀም ስንንቀሳቀስ ዓይኗ የቀላው ግብፅ ምን ልታደርግ እንደምትችል ከመገመት መቦዘን የለብንም። ግብፅ ከጥንት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን በኩል ቅኝ ስትገዛን እና ስትቆጣጠረን ነው የኖረችው። ዓመቱን ሙሉ ቀኑን ሁሉ በዓል ነው ብላ እንዳንሠራና እንዳንለወጥ ያደረገችውን ሥውር ሴራ እስካሁን የነቃንበት ጥቂቶች ነን። የተለያዩ ታጣቂ ኃይሎችን በማስታጠቅ ኢትዮጵያ ወደ ልማት እንዳትዞር ያደረገችውን የእጅ አዙር ጦርነት ለማንም የሚሰወር አይመስለንም። ይልቁንም አሁን በዚህ ትውልድ የሚታየውን መነቃቃት የታላላቅ ግድቦች ፕሮጀክቶችን፣ መንገዶችንና ኢንዱስትሪዎችን ስታይ ጭንቀት ውስጥ መግባቷ የማይካድ ነው። ከላይ የጠቀስናቸው ከመቶ በላይ የሆኑ ቡድኖች ፈጽሞ ሊቀራረብ በማይችለው አመለካከታቸው እርስ በእርሱ ቢለያዩ ለግብፅ በገና እንደመደርደር ነው።
 ዓለም አቀፉ አሸባሪ አይሲስ በካርታው ውስጥ ከጠቀለላቸው ሀገሮች ውስጥ አንዷ የእኛይቱ ኢትዮጵያ መሆኗ እንደ ቀልድ የምናየው አይደለም። ውስጥ ለውስጥ የሚሄድበት መንገድ በኢትዮጵያ ውስጥ መገንባቱንም እናውቃለን። በሊቢያ ያረዳቸው ወገኖቻችን በአይሲስ ዘንድ፤ ኢትዮጵያ ለግልሙትናው ሊደፍራት ያጫት ልጃ ገረድ መሆኗን የሚያስረዳ ነው። ከላይ የጠቀስናቸው ከመቶ በላይ ቡድኖች እርስ በእርስ ተለያይተው ቢያለያዩን አገራችን ለዚህ ክፉ አውሬ ትጋለጣለች።
  የኤርትራ ሕዝብ የምንወደው ወገናችን ቢሆንም ሻዕቢያን ግን ልናምነው አይገባም። ይህን የምለው ኢሓዴግ ስለሚጠላው እኛም ተደራቢ ለመሆን ፈልገን አይደለም። ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ላይ ያለውን አቋም ከታሪክ ስለተረዳናን አሁንም ያን አቋሙን ለመቀየሩ ማስረጃ ስለሌን ነው። ኢህአዴግን ስለምንጠላው ሻቢያን ልንወደው አንችልም። የሀገሩን ወጣት ትውልድ እያሳደደ ነው፤ በኤርትራ የመንፈሳዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴዎችን አይፈቅድም፣ የዚህ እንቅሥቃሴ አባላትንም የት እንዳሰራቸው እንኳ አይታወቅም። በሀገሩ በርካታ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች አሉት ይባላል እውነት መሆኑን ባላረጋግጥም የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባርን ያስታጥቃል፣ ኦነግን ያስታጥቃል፣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን ያስታጥቃል፣ የአማራን ድርጅት ያስታጥቃል፣ የሲዳማ አርነት ንቅናቄን ያስታጥቃል፣ የጋምቤላ ነጻነት ንቅናቄን ያስታጥቃል፣ የጉሙዝ ነጻነት ንቅናቄን ያስታጥቃል፤ የአፋር ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን ያስታጥቃል፣ ግንቦት ሰባትን ያስታጥቃል፤ ሻቢያ በኢትዮጵያ ላይ ያላስታጠቀው ማን ነው? ድሮም ሕውሐትን ያስታጠቀው እርሱ ነው። በጠቅላላው ብሔር ብሔረ ሰቦችን አስታጥቋቸዋል። ይህ ምን ትርጉም ይሰጣል? ለኢትዮጵያ አስቦ ይሆን? ለኢትዮጵያ ካሰበ ሁሉም አንድ ሆነው እንዲታጠቁ ለምን አላደረገም? አንድ ኃይል እንዳይሆኑ ለምን ከፋፍሎ ያስታጥቃል? እኛ ግን መልሱን እናውቃለንና ሞኝህን ፈልግ እንበለው።
  ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ አትታለል፤ እራሳችንን በአንድነት እንጠብቅ፤ የተበታተነ ኃይል በየራሱ ታጥቆ ነጻ ሊያወጣን አይችልም አገራችንን ሲኦል ከማድረግ በስተቀር ከነዚህ ቡድኖች መንግሥተ ሰማያትን አንጠብቅ። ስለዚህ ከፖለቲካዊ ፍላጎታችን በፊት ሀገራችንን አስቀድመን ጥንቃቄ እናድርግ ይህ ብልህነት ነው። ይህ ሁሉ አንድ ሆኖ ከኢሕዴግ የተሻለ ኃይል ካልሆነ አገራችንን ላውሬ መሰማሪያ ማድረግ ነው የሚሆነው። ሌባ ሲሰርቅ እንጂ ሲካፈል አይስማማም የሚለውን ነበር ድሮ የምናውቀው። እነዚህ ሁሉ ታጣቂዎች ግን እንኳን ሲካፈሉ ሲሰርቁም አልተስማሙም፣ በመሆኑም ከብልህ ሌባ እንኳ አይሻሉም፤ ሲሰርቁ ካልተስማሙ ሲካፈሉ ምን ይሆኑ ይሆን?
ለሰላማዊ ተቃዋሚዎች ያለኝ መልእክት
 ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መስፈን የምታደርጉትን ትግልና እየከፈላችሁ ያለውን ትልቅ ዋጋ የምንረሳው አይደለም። በየእሥር ቤቱ የወደቃችሁ ታጋዮችን ሁሉ በጸሎታችን እናስባችኋለን። "ወዘአዝለፈ ትእግሥቶ ውእቱ ይድኅን‚ ትርጉም እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል እንዳለ መጽሐፍ አንድ ቀን እግዚአብሔር የትእግሥታችሁን ዋጋ እንደሚከፍላችሁና ሐሳባችሁን እንደሚፈጽመው እናምናለን። ነገር ግን የእናንተም እርስ በእርስ አለመስማማት እጅግ ያሳስበናል። በአንድ ሐሳብ የመሸነፍ፣ የራስን ትቶ ወደ አንዱ የሚያቀራርብ ጉልበት ለምን አጣችሁ? አንድነት ኃይል ነው የሚለውን እያወቃችሁ እናንተ ግን አንድነትን ስትመሠርቱ አናያችሁም። ስለዚህ ባጭሩ እንፈራችኋለን። የኢትዮጵያ ሕዝብ በይቅርታ የሚያገናኘውን፣ ይቅር ለእግዚአብሔር ተባብሎ የሚያሳርፈውን እየፈለገ ነው። ጥቅምን፣ ሥልጣንን፣ ርእዮተ ዓለምንም እንኳ ቢሆን ለጊዜው ብትተውት ምን አለበት? የፖለቲካውን ጉዳይ ለጊዜው አስቀምጡና የሀገርን ጉዳይ እንድታስቀድሙ እንማጸናለን። ከሁሉም በላይ የጥላቻ ፖለቲካችሁ ተቀበይነት የለውም። ምክንያቱም ሁሉም ወደየጉድጓዱ ገብቶ እራሱን እንዲከላከል የሚያደርግ እንጂ ከበቀል ፍርሐት ነጻ የሚያደርግና የሚያጠጋጋ አይደለምና እራሳችሁ ለውጥ ያስፈልጋችኋል። አንዳድ ሰዎችን ጨካኝ የሚያደርጋቸው ፍርሐት መሆኑ ይታወቃል። ኢሕአዴግን ከፍርሐቱ ነጻ የሚያደርገው የሀገር መሪ አስፈላጊ ነው።
ለኢህአዴግ ያለኝ መልእክት
ማንኛውም ነገር ሲከር ይበጠሳል። ኢሐዴግም እስከ መቼ እንደሚያከር ማወቅ አልተቻለም? እስኪበጠስ? እርሱም ሆነ እኛ እውነቱን እንደምናውቀው የብዙ ታጣቂዎች ወደ በርሃ መውረድ ምክንያቱ ጦርነት ስለሚወዱ አይመስለንም። ፍትሕ ያጡ፣ በልዩ ልዩ ምክንያት የተፈናቀሉ፣ ሙስና ያስመረራቸው ናቸው። እነዚህ ኃይሎች አገራቸውን እንደሚጠሉ ተደርጎ የሚወራውም ከእውነት የራቀ ነው። ስለዚህ ኢህአዴግም ከማንኛውም ጥቅሙ በፊት ሀገራችንን እንዲያስቀድም ስንል እንማጸናለን። በዘመኑ የተሠሩ የልማት አውታሮች፣ መንገዶች፣ ግድቦች፣ ፋብሪካዎች፣ የመኖሪያ ሕንጻዎች፣ የግብርና ሥራዎች የሚያበረታቱ ናቸው። ነገር ግን በሕዝብ ላይ የሚፈጸሙ በደሎች ኣመጻዎችን ሊወልዱ ይችላሉ፣ ኢሕአዴግን የወለዱት የጥንት በደሎች ናቸው፤ የዛሬ በደሎችስ መካን ናቸው ያለው ማን ነው? እንዲያውም መንታ መንታውን ሊወልዱ የሚችሉ በደሎች አርግዘው ነው የምናያቸው። አመጻዎች ደግሞ ልማቶችን ሲያፈርሱ፣ የውጭ ጣልቃ ገቦችን ሲጋብዙ ነው የምናውቀው። ኢህአዴግ ከውጭ የሚላኩ ኃይሎች የሚላቸው ከውስጥ የሚገፉ አይደሉምን? ኢህአዴግ ቆም ብለህ አስብ! ኢሕአዴግ የተባረከ ይሁን እንድል ከፈለገ የፖለቲካ ሜዳውን ለዳኛው ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲተውና አገር የመምራት አቅም ያለው፣ የተጀመረውን ልማት ወደ ፍጻሜው የሚያደርስ፣ ባለፈው የማይበቀል ድርጅት እንዲፈጠር ማድረግ ይችላል። ይህ መልካም ሥራ ነው፤ ለሁሉም የሚጠቅም የሰላም ሐሳብ ያለው ነው። ከዚህ ውጭ ሁሉን በጠላትነት በመፈረጅ እየተሄደበት ያለው መንገድ ግን ለማንም አይጠቅምም።
  ሁሉን አዋቂ እግዚአብሔር ቢሆንም የኢሕዴግ አክራራሪነት ግን አንጀቴን ሊበጥሰው ይችላል እያልሁ ፈራለሁ። ስለዚህ እግዚአብሔር እውነቱን እንዲገልጥለት የሽበት ዘመኑም በክብር እንዲፈጸም ምኞቴ ነው።
                     
 ጠፍቼ የኖርሁት ተስፋ ነኝ   
   
  

24 comments:

 1. አባ ሰለማዎች ይህን እውነት ለመግለጥ ድፍረት የሰጣችሁ ጌታ ይመስገን። እውነትን ስትገልጡ ነፍሴ ትረካለች በርቱ!!!!

  ReplyDelete
 2. Wow!!!, Tesfa, first of all welcome back !!! I missed ur Positive and intellectual Idea and truth. This message is very, very, very, and very good. I hope everybody understand this truth. Getta ahunem abzeto yibarkeh!!!! Please keep in touch. We have Hope......

  ReplyDelete
 3. ጠፍቶ ለነበረው ለተስፋ
  ለራሷ ክርስትና አልተነሳች ልታቋቁም ወጣች ነው የተባለው። አቶ ተስፋ ምንም አልተሳሳትክ ጠፍተሃል አሁንም እንደጠፋህ አለህ። ተመፃዳቂው ተስፋ፦ እኔ ወንጌል ሰባኪ ነኝ ነው ያልከው? ድንጌም ወንጌል ሰባኪ። ወጉ አልቀረህም። መጀመሪያ አንተ ተሰበክ፤ እውነትን እወቅ፤ ከገባህበት ጨለማና ሐሰተኛ የጨለማ አስተምሮ ውጣ፤ ከስድብና ከቂል ፈራጂነት ተላቀቅ፤ የክርስቶስ የሆኑትን ከማጥላላትና ከማቃለል ወጥተህ ለማክበር ተነሳ፤ ስለማታውቃት ቤተክርስቲያን ለማውራትና ለመተቸት ከመሯሯጥህ በፊት ከቤተክርስቲያኗ እውነተኛ ልጆች ለማወቅ ሞክር፤ ስለህይወት ለመናገር በመጀመሪያ ህይወት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እንዳለና እሱም ክርስቶስ መሆኑን ማመን ያስፈልግሃል። ዘላባጁ የሐሰተኛው ተላላኪ ተስፋ፦ አንተነህ ወደ ህይወት መለወጥ ያለብህ በሞት ውስጥ ስላለህ። አንተነህ ወደ ብርሃን ወደ ምታስገባው በንስሃ መመለስ ያለብህ። ምነው ለመውደቅ ዲያቢሎስ ክርስቶስን እንደተገዳደረው አንተም የሰይጣን መልክተኛ ሆነህ የክርስቶስ አካል ቤተክርስቲያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለመገዳደር ተንጠራራህ። በአንተ አሉባልታ የኦርቶዶክህ ተዋህዶ እምነትና ስርዓት አይፈታም። ሌላው ዘባተሎ አሉባልታህ ወሬ ብቻ ነው። አቶ ተስፋ፦ ወንጌል ሰባኪነኝ ያልክበት አፍህ ወንጌሉን ትቃወማለህ እንዲህ በማለት በአላትን ማክበር አገሪቱን ድሃ አደረጋት የሚል የስንፍናህ መከላከያ ይሆነኛል ያልከውን ከንቱ ክህደትህን። በወንጌል እኮ በአልን የሚያከብር ስለ እግዚአብሔር ብሎ ያክብር ተብሎ ተጽፏል። ሌላው ነገሮች ሁሉ የተምታቱብህ በመደናበር የምትንቀዋለል መሆንህን ያረጋገጠብህ ፖለቲከኛ አይደለሁም ትልና የአገሬ ጉዳይ ግን ያገባኛል በሚል የዘባረቅኸው ዝብርቅርቅና በኢትዮጽያ ያለው ዘረኛና ዘራፊ ሐይማኖት የለሽ መንግስት እንዲቀጠል የምትፈልግ አደናጋሪ ዘረኛ ፓለቲከኛ መሆንህን ነው። ለሁሉም ጠፍቸ የነበርኩት ተስፋ ነኝ ከምትል የጠፋሀት ተስፋቢስ ነኝ ብትል ማንነትህን ይገልጠዋል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. መቼም የማቅ ደጋፊ ዞሮ ዞሮ ከዚህ አይወጣም። ማፈሪያ

   Delete

  2. ዳሞት
   ተዉ ተመከር ዝም ብለህ ሰዉ ለመተቸት ብቻ አፍክን አትክፈት፡፡ በኢትዮጽያ ያለው ዘረኛና ዘራፊ ሐይማኖት የለሽ መንግስት እንዲቀጠል የምትፈልግ…… ነዉ ያልከዉ? ለመሆኑ መንግስት ሃይማኖት እንዲኖረዉ ይጠበቃል? በህገ መንግስቱ መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ እንደሆኑና መንግስታዊ ሃይማኖት እንደሌለኮ ተደንግጓል፡፡ ይሔን ጡት ከሚጠባ ህጻን በላይ የማይጠበቅ አርቲ ቡርቲ ሃሳብህን ሳታፍር ወደ አደባባይ ስታወጣ እንዴት ትንሽ እንኳን እንዳልሰቀጠጠህ ይገርማል፡፡ አለማወቅህን የማታዉቅ ግብዝና ተመጻዳቂ ስለሆንክ ካልሆነ በስተቀር የትምህርት ቤት በር ከረገጠ ሰዉ ይሔን አይነት የወረደ አስተሳሰብ አይጠበቅም፡፡

   Delete
  3. ለወዳጀ anonymous May 18,2015 at3:54 am
   በመጀመሪያ ሰላም! ከዛም እኔ የት/ቤት አልረገጥሁም። ስለስድቡ እያመሰገንሁኝ በእኔ እምነት ግብዝም ተመፃዳቂም ነኝ ብየ አላምንም። ደግሞ እባክህ ከየትኛውም አካልም ይሁን ማህበር ጋር አታቆራኘኝ። ፈርቸ ሳይሆ አንተ በበደል ላይ ሌላ ክፋት በራስህ ላይ እንዳትጨምር ብዬ ነው። ህገ መንግስት ለምትለው ወረቀት እንጂ በተግባር የማገለፅ አይደለም። መንግስት የአንድ እምነት አካል ይሁን የሚል አስተሳሰብም አላንፀባረቅሁም አላልኩም። ሐይማኖት የለሽ ያልኩት ከሚፈፅማቸው ኢሰባዊ ድርጊቶች በመነሳት መሆኑ መታወቅ አለበት። ሐይማኖት የለሽ ያልኩትም ከየትኛውም የእምነት ስነምግባርና ርህራሔ የወጣ ጨካኝ መንግስት በመሆኑና ፍፁም ዘረኛ ስለሆነ ነው። ዘራፊ መንግስ ያልኩ እጅግ ያቃጠለህም ትመስላለህ። ማንነትህም ከዛው ወይም አገልጋይ የዘራፊዎች ባሪያ ትርፍራፊ ቀማሽ ትመስላለህ። እያቃረህም ቢሆን የወጣለት ዘራፊ መንግስት ነው። ከአገርቤት ጀምሮ እስከ ውጫገር ሐብት ያካበቱ ሌቦች ናቸው። አገር ቤት የሚያማምሩት ውድ ህንፃዎች እኮ የባለጊዜዎች ነው እየተባለ ከተነገረ ቆየ። እኔ እንሿን የማውቀው የ300(ሶስት መቶ) ብር ታክሲ ሾፌር የነበረ ከዛሬ ሁለት አመት በፊት ባገኘሁት መረጃ ቦሌ አካባቢ ባለሁለት ውድ አፓርታማዎች ባለቤት ሆኗል። የስርዓቱ ሰው በመሆኑ ብቻ። ይህ በጣም ትንሹን ዘረፋ ነው እንደምሳሌ ያቀረብሁልህ። ጡት የሚጠባ ብለህ የዘላበድኸውን የአሮጊቶች ተረትህን በኔ ላይ አንዳች ስፍራ የለውም። ጡት የሚጠቡ ህፃናትን ያክል ግንዛቤ ቢኖርህ እንዲህ በረከሰየዘረኝነት ገመድ ተተብትበህ እንዲህ አይነት እብሪተኝነት ባለተጠናወተህ ነበር። ነገር ግን ከበለአም አህያ አንሰህ ሰባዊነትን የምታይበት ማስተዋል አጥተህ መውደቅህ ያሳዝናል። ለእኔ አይደለም የሚያሳዝነው ለአንተውና ለቤተሰብህ እንጂ። እኔማ አንተን ከመሰለ የክፉውና የክፋት አቀንቃኝ እንዲህ አይነት ዘረኝነትና ውሸት እንደሚሆን እጠብቃለሁኝና አይደንቀኝም።ህይወት የሚሆነው የክርስቶስ ቃል ነው። ክርስቶስ ደግሞ ዘረኝነትን ይጠላል።ሐሰተኝነት፣ ሌብነትን፣ አሳዳጅ አሳሪነትን፣ ገዳይነትን፣ በጥባጭነትን፣ መለያየት ይጠላል። እናም ምረጥ። ወይ ወደ ክርስቶስ ሃሳብ ወይ ወደ ዘረኞች ሐሳብና ተግባር።

   Delete
 4. አባ ሰላማዎች የምትገርሙ ናችሁ ፖለቲካ አይመለከተኝም እያልክ አሁን ምን እያወራህ ነው? ከዚህ በፊት ማኅበረ ቅዱሳን ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ ብዙ አስተማሪ የሚሆኑ መጣጣጥፎችን ጽፎ ሳለ ፖለቲካ ነው ሃይማኖትንና ሃይማኖተኞችን አይወክልም እኛ ሀገራችን በሰማይ ነው ብላችሁ ነበር አሁን ኢትዮጵያ የተቀመጠችው በምድር ላይ መሆኗን ማን ነገራችው ይበል ነው ነገ ደግሞ ተገልብጣችሁ ምን ትፅፉ ይሆን

  ReplyDelete
 5. ጠፍቶ ለኖርህ ተስፋ ነኝ ላልከው ወንድም ወይም እህት!
  የወንጌል ታልቅ መልዕክቷ ወይም ኃይለ ቃሏ " የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" ነው። ስለዚህ ሁላችንም ዛሬ ወንጌል የሚያስተምረን በቅርቡ የሚመጣውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመግባት እንድንችል ወንጌሉን ተረድተን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማድረግ እንድንጠብቀው ይመክረናል።
  ወንድማችን አንድ ነገር መረዳት የሚገባህ ነገር ከመጀመርያው ጀምሮ መንግሥታትን በምድር ላይ የሚጥልና የሚያነሳ እግዚአብሔር ነው። በዚህም መሠረት አንድ መንግሥት መጥፎም ሆነ ጥሩ ሁሉም በእግዚአብሔር ቃል የሚከናወን መሆኑን ወንጌል አስተማሪዎቻችን አልተረዱትም። ለምሳሌ ያህል ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በሚመላለስበት ወቅት ይህ ጥሩ መንግስት ነው ውደዱት ወይም ይህ ነ ክፉ መንግሥት ነው ጥሉት ብሎ አልተናገረም ። ነገር ግን ሁላችንም ወደ እርሱ የዘላለም ወደሆነችው መንግስቱ እንድንገባ ምሥራች ብቻ ነው ያስተማረው። ምክንያቱም ሁሉም የራሱ የሆነ ጊዜ ስለተሰጠው በጊዜው ይከናወናል። ልናቆመው አንችልም። በተጨማሪም ደግሞ የመጽሀፉን ነገር ባለመረዳታችን ምክንያት ወደ ሰማይ ለመሄድ እንችኩላለን። ነገር ግን እስኪ የእግዚአብሔር መንግሥት የት ቦታ ለዘላለም ትቆማለች? መጽሀፉ ምን ያስተምረናል? ብለን እርሳችንን እንጠይቀው። የፊተኛው ትንሳኤ ምንድን ነው? ይህን ከተረዳን የምናመልከውን አምላክ የድንግል ማርያምን ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን እናውቃለን። ለዚህም እንዲረዳን ለምሳሌ ያህል የነቢዩ ዳንኤልን መጽሀፍ በጥሞና እንድናስተውለው ይገባል።
  በዚህም መሠረት እግዚአብሔር የእርሱ መንግሥት እስኪመጣ ድረስ አስቀድሞ እንደተናገረው ማን መቼ እንድሚነሳ መቼስ እንድሚወድቅ በግልጽ በወንጌሉ ወይም በመጽሀፍ ቅዱሱ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል። ለምሳሌ ያህል፡ ንጉሱ ናቡከደነፆር ያየውን ሕልምና ፍቺ ነቢዩ ዳንኤል ምሥጢሩን በሚነግርበት ወቅት እንደተናገረው፡
  " 27፤ ዳንኤልም በንጉሡ ፊት መልሶ እንዲህ አለ። ንጉሡ የጠየቀውን ምሥጢር ጠቢባንና አስማተኞች የሕልም ተርጓሚዎችና ቃላተኞች ለንጉሡ ያሳዩ ዘንድ አይችሉም፤28፤ ነገር ግን ምሥጢር የሚገልጥ አምላክ በሰማይ ውስጥ አለ፥ እርሱም በኋለኛው ዘመን የሚሆነውን ለንጉሡ ለናቡከደነፆር አስታውቆታል። በአልጋህ ላይ የሆነው ሕልምና የራስህ ራእይ ይህ ነው።" (ዳን. ም2)። ይላል። በዚህም መሠረት በኋለኛው ዘመን የእግዚአብሔር መንግሥት እስኪመጣ ድረስ ተራ በተራ ማን ይህችን ምድር በኃያልነት እንድሚገዛ ነግሮታል። በዚህም መሠረት በመቀጠልም፡" 36፤ ሕልሙ ይህ ነው፤ አሁንም ፍቺውን በንጉሡ ፊት እንናገራለን።37፤ አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ የሰማይ አምላክ መንግሥትንና ኃይልን፥ ብርታትንና ክብርን የሰጠህ የነገሥታት ንጉሥ አንተ ነህ።38፤ በሚቀመጡበትም ስፍራ ሁሉ የሰው ልጆችንና የምድር አራዊትን የሰማይ ወፎችንም በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶሃል፥ ለሁሉም ገዥ አድርጎሃል፤ አንተ የወርቁ ራስ ነህ።39፤ ከአንተም በኋላ ከአንተ የሚያንስ ሌላ መንግሥት ይነሣል፤ ከዚያም በኋላ በምድር ሁሉ ላይ የሚገዛ ሌላ ሦስተኛ የናስ መንግሥት ይነሣል።40፤ አራተኛውም መንግሥት ሁሉን እንደሚቀጠቅጥና እንደሚያደቅቅ ብረት ይበረታል፤ እነዚህንም ሁሉ እንደሚፈጭ ብረት ይቀጠቅጣል ይፈጭማል።" (ዳን. ም2)። ይላል። በዚህም መሠረት በወርቅ በብር በነሀስና በብረትና በሽክላ የተመሰሉ መንግሥታት እንደሚነሱና እንደሚወድቁ ነግሮታል። እነዚህም አራት መንግሥታት ጽዋቸው ሲሞላ በኋለኛው ዘመን የእግዚአብሔር መንግሥት ትገለጣለች። በዚህም ከዚያም አራተኛው መንግሥትም ጽዋው ወደፊት ሲሞላ ደግሞ የሚሆነውን እንዲህ ሲል ገልጾለታል።
  " 44፤ በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል፤ ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል፤ እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፥ ለዘላለምም ትቆማለች።" (ዳን. ም2)። ይላል።
  ስለዚህ ይህ የማይፈርስ መንግሥት ዛሬ ወንጌል የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡና ጠብቁት ብላ የምታስተምረን የእግዚአብሔር መንግሥት ነው። በተጨማሪም ይህ መንግሥት የት እንድሚቆምም አሁንም ለነቢዩ ዳንኤልን እግዚአብሔር እንደነገረው ፡
  " 35፤ የዚያን ጊዜም ብረቱና ሸክላው፥ ናሱና ብሩ ወርቁም በአንድነት ተፈጨ፥ በመከርም ጊዜ በአውድማ ላይ እንዳለ እብቅ ሆነ፤ ነፋስም ወሰደው፥ ቦታውም አልታወቀም፤ ምስሉንም የመታ ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ ምድርንም ፈጽሞ ሞላ። " (ዳን. ም2)። ይላል። አህንም ይህ መንግሥት የዓለምን መንግሥት በማሸነፍ አስቀድሞ አሕዛብ ወይም ሰዎች የሚያስተዳድሩትን ወደፊት አባቱ ጠላቶቹን ድል ካደረገለት በኋላ በምድር ላይ ለወዳጆቹ ያስረክባቸዋል። በዚህም መሠረት
  "44፤ በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል፤ ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል፤ እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፥ ለዘላለምም ትቆማለች።" (ዳን፡ ም2)። ይላል። ይህች መንግሥት የእግዚአብሔር መንግሥት ናት። እኛ ዛሬ ሁላችንም የምንጠብቃት ወይም ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ኪዳን ባደረገው መሠረት፡ " 1 ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።2 በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤3 ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።" (ዩሐ. ም14)። ብሎ እርሱን እንድንጠብቀው ነግሮናል። ይህ ማለት ሰማይ ቤት ይወስደናል ማለት አይደለም። ምክንያቱም " 26-27 ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፥ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤" (ዩሐ. ራአይ ም2) ይላል። ስለዚህ አሕዛብ የሚገኙት የት ነው? ሰማይ ወይስ ምድር? መጀመሪያ የፊተኛው ትንሳኤ ምን እንደሆነ ካልተረዳነው እውነተኛው ክርስቶስን ልንረዳው አንችልም።.........ይቀጥላል

  ReplyDelete
 6. በመቀጠልም......
  አሁንም የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያስተምረን፡" 12፤ ከቀሩትም አራዊት ግዛታቸው ተወሰደ፤ የሕይወታቸው ዕድሜ ግን እስከ ዘመንና እስከ ጊዜ ድረስ ረዘመ።13፤ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት።14፤ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።" (ዳን. ም7)፡ ይላል።
  በዚህም በአራዊት የሚመስላቸው (አንበሳ (ባቢሎን) ድብ(ፋርስ ሜዶን) ነብር (ግሪክ) የምታስፈራና የምታስደነግጥ አውሬ አሥር ቀንዶች ያልት (የሮም ኢምፓየርና እርሱ ከደከመ በኋላ የተነሱትን አሥር መንግሥታትን ያመለክታል)። በዚህም እነዚህ አሁን ያለንበት ዘመን መንግሥታት ጽዋቸው ሲሞላ ወደፊት ደግሞ ምን እንደሚሆን እንዲህ ሲል ያስተምረናል።
  " 23፤ እንዲህም አለ። አራተኛይቱ አውሬ በምድር ላይ አራተኛ መንግሥት ትሆናለች፤ እርሱም ከመንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፥ ምድሪቱንም ሁሉ ይበላል፥ ይረግጣታል ያደቅቃትማል።24፤ አሥሩም ቀንዶች ከዚያ መንግሥት የሚነሡ አሥር ነገሥታት ናቸው፤ ከእነርሱም በኋላ ሌላ ይነሣል፥ እርሱም ከፊተኞች የተለየ ይሆናል፥ ሦስቱንም ነገሥታት ያዋርዳል።25፤ በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።26፤ ነገር ግን ፍርድ ይሆናል፥ እስከ ፍጻሜም ድረስ ያፈርሱትና ያጠፉት ዘንድ ግዛቱን ያስወግዱታል።27፤ መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል።28፤ የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው። እኔም ዳንኤል በአሳቤ እጅግ ተቸገርሁ፥ ፊቴም ተለወጠብኝ፤ ዳሩ ግን ነገሩን በልቤ ጠብቄአለሁ።" (ዳን. ም7)። ይላል። ስለዚህ ከዚህ ቃል የምንረዳው የእግዚአብሔር መንግሥት በምድር ላይ እንደምትሆን ይነግረናል። ምክንያቱም ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል። ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት (በምድር ላይ ያሉት) ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል ይላል። በዚህም ጊዜ የሚሆነውንም ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ሲል የእግዚአብሔርን ቃል መዝግቦታል።
  " 9፤ እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።" (ዘካ. ም14)። ይላል። በተጨማሪም ቅዱስ ዩሐንስ በራዕዩ እንደሚመሰክረው፡
  "9-10 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።" (ዩሐ. ራእይ ም5)። ይላል። ብምድር ላይ ከወገኖቹ ጋር በሚነግስበት ወቅት ደግሞ የሚሆነውንም እንዲህ ሲል ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አብስሮታል።
  "32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።" (ሉቃ. ም1)። ይላል። የዳዊት ዙፋን በምድር ወይስ በሰማይ ያለችው???? መልሱን ለወንጌላውያን ይሁን።
  ስለዚህ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል። ነገር ግን የሰማይ መንግሥት ሲባል ብዙዎቻችን ወደ ሰማይ የምንሄድ ይመስለናል። ነገር ግን ወደ ሰማይ ቤት ሄዶ ለመኖር የሚቸኩል አንድ ነገር ብቻ ነው እርሱም ። ሳጥናኤል ነው። በዚህም "12፤ አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ!13፤ አንተን በልብህ። ወደ ሰምይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤14፤ ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ።15፤ ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።"(ኢሳ. ም14)። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ወንጌል ስናስተምር መጠንቀቅ ይገባናል።
  በተጨማሪም የእግዚአብሔር መጽሀፍ እውነተኛው ክርስቶስ በምድር መጥቶ ይነግሳል ብሎ የእግዚአብሔር ቃል ያስተምረናል። ይህችም መንግሥት በሰማይ ሆና ተዘግጅታ ጊዜዋ ሲደርስ ወደ እኛ መካከል ትመጣለች። ለዚህም ነው "መንግሥትህ ትምጣ" ብለን የምንጠይቀው። ከዚያም በቃሉ መሠረት በአባቱም በዳዊት ዙፋን ላይ ይቀመጣል። በዚህም እግዚአብሔር እንድሚይስተምረን፡ " 5 እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።" (ኤር ም23)። ይላል። እንዲሁም " 14 እነሆ፥ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።15 በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ፤ እርሱም ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል።" (ኤር. ም33)። ይላል። በመጨረሻም " 1 ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።2 ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።3 ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤4 ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቍጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና።5 ስለዚህ ስለ ቍጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው።6 ስለዚህ ደግሞ ትገብራላችሁና፤ በዚህ ነገር የሚተጉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።7 ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።8 እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና።" (ሮሜ ም13)። ይላል።
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር!
  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህ ሁሉ በክርስቶስ ቃል መዘባበትና መዘባረቅ እውነት ህይወት ነውን? ወንድም ወይም እህት anonymous May 16,2015 7:34 and 7:35 pm፦ ሌላው በህይወት ቃል እያላገጥህ ትርጉሙና መልእክቱም ሳይገባህ የዘባረቅኸው ፍፁም ክህደትና ለጥፋት እጅግ የተጋህ መሆንህን ነው። ከብዙ አላጋጭ መልክቶችህ እንደተገነዘብኩት ፍፁም መናፍቅና የጆቫ እምነት አቀንቃኝ መሆንህን ነው። በዚህ በግብ ከሚመስልህ ብሎግ ላይ በመጀመር ቀጥለህ ባስቀመጥኸው አስተያየት ተብዬ እንደ ስጋ ፈቃድህና ሰይጣን እንደመራህ የጫጫርሃቸው ቃሉ ምንም እንሿን የእግዚአብሔር ቃል ቢሆንም የገለጽክበት አገላለፅ ግን የተሳሳተ ነው። ለዚህም ነው የእግዚአብሔር ቃል "መንገዴ ከመንገዳችሁ፤ ሐሳቤ ከሐሳባችሁ የተለየ ነው" የሚለው። አንተም የህይወት ቃሉ ትርጉምና የተፃፈበት ምክንያት ሳይገባህና ሳትማር እንደልቦለድ በማንበብ ስተህ የምታስተው። ሌሎች ስተቶችህ ይቆዩና፤ ለመሆኑ የሰይጣን ስፍራው በሰማይ ነው ለማለትና እንዲህ በታወረ ልቦናና አይምሮ እንድትመፃደቅ ያደረገህ ከየት ተምረኸው ነው? መቸም ከሰይጣን እንጂ ከክርስቶስ ወንጌል አይደለም። አንተ የጠቀስከውና ያልገባህ የእግዚአብሔር ቃል እንሿን የአንተን ሐሰተኛ አስተማሪነትና የቃሉ አጣማሚ መሆንህን ነው የሚመሰክርብህ። የጠቀስከው ቃለ ይህ ነው፦ " አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ አህዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ እንዴት እስከምድር ድረስ ተቆረጥህ፣ አንተም በልብህ ወደ ሰማይ አርጋለሁ …… በልዑልም እመሰላለሁ አልህ።" " ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጏድም ጥልቅ ትወርዳለህ" የሚለው እንሿን የሚያመለክተው ሰይጠን ቦታው በሰማይ አለመሆኑን ነው። ዲያቢሎስ እራሱን አምላክ አድርጎ በልዑልም ተመስሎ በሰማይ ለመቀመጥ በመሻቱና የፈጠረውን አምላኩን እግዚአብሔር በመካዱ ወደ ጥልቁ የተጣለና የተዋረደ በሰማይም ስፍራ የሌለው ነው። ታዲያ አንተ ከየት አምጥተኸው ነው የሰይጣን ስፍራ በሰማይ የሆነው። እንግዲህ እንዳንተ አይነቱ መናፍቅ ነው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆነ መንፈስና ምግባር እንዲሁም አምልኮ ሳይኖራችሁ የቤተክርስቲያኗ የሆኑትን አንዳድ ቃላቶችንና መጠሪያ ስሞችን በመውሰድ በማሥመሰል ቤተክርስቲያንን የምትፈታተኗት። ለሁሉ ዐጨለማ ነውና ያለኸው ሳይገባህ በድንግዝግዝና በስጋ ስሜት ቃሉን ከማጣመም ወጥተህ ወደ ብርሃን ብትመለስ ይሻልሃል።

   Delete
 7. Ayi tesefa yet tefeteh new mercha siders bik yalikew

  ReplyDelete
 8. Good Point tesfa

  ReplyDelete
 9. አንት ዘላባጅ ዝም ብለህ አትቀባጥር

  ReplyDelete
 10. hi YETEFAHEW Tesfa(u).....Enquan ke Bercha wode mircha Ashegagereh...

  ReplyDelete
 11. ድንባዣም

  ReplyDelete
 12. እናመሰግናለን ተስፋ. ዛሬ ያለው የፓለትካ ሁኔታ ስንመለከተው ትላትና 30 ዓመታት ደማችን በከንቱ ያፈሰሰውን የሻብያ መንግስት ተባብረው ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚበጅ መንግስት እናመጣለን እያሉ አሁንም የኢትዮጵያን ወጣት ለሞት ለመዳረግ እየተሯሯጡ ናቸው ያሉትን የእሳት ተለቭዠን የሐሰት ወረ በትውልድ የጎንደር ተወላጅ ነን እያሉ ነገር ግን የሻብያ ዝርያ ያለቸው ለኢትዮጵያ ማደግ የማወዱ ናቸው። የኢትዮጵያን ህዝብ ወድቀት ዛሬም በእኛ ቋንቋን እየተናገሩ ልያጠፉን እንቅልፍ አጥተዋል።የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አማረኛ ቀልጠፍ አድርጎ የተናገረ ሁሉ ኢትዮጵያው የተሻለ ለዉጥ ያመጣል ማለት የዋህነት ነው። ብያንስ ወያኔ ከሻብያ ወይንም ከኢሳያስ አፈወቅ መንግስት ለሀገራችን ይበጃል። ሁላችንም ቆም ብለን እናስብ ወገኖቼ። ለዉጥ ለማምጣት መታገል መልካም ነው። ያሁኑ አካሄድ ግን ለኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅ ነው። ሰሞኑን እንኳን የእሳት ተሌቭዠን ጣብያ ሀይማኖት በሐይማኖት ላይ ስያነሳሰ አይተናል። ይሄ የሙስልሙን መስግድ እየፈረሰ ነው እያለ በተዘዋዋር ክርስትያኑን ለማሰጠቃት ቅስቀሳ ስያደርግ አዳምጠናል። ክርስትያኑና ሙስሊሙ ተከባበሮ ተቻችሎ የሚኖርባት ሀገራችን ብቻ ነው።የሻብያ አማርኛ ተናጋርዎች ይሄን አይነቱ አኗኗር አይዋጥላቸውም። መልካም አስተዳደር መፈለግ መልካም ነው። የኢትዮጵያ ህዝቦችና ልጆቿን ለ30 ዓመታት በከቱ ያፈሰሰውን ሻብያ ተባብረው ኢትዮጵያን ከወያኔ መንግስት ነጻ እናወጣታለን ብሎ ማሰብ በራሱ በህዝባችን ደም መቀለድ ነው። በቃን በቃን በቃን የሻብያ ተንኮል አይጠቅመንም አይበጀንም ።

  ReplyDelete
 13. lemircha lemin altewedaderkim Ato Tesfa!!!!

  ReplyDelete
 14. ወዳጆቼ! ኢህአዴግን ምን እንዲህ አስፈራዉ? የተስፋ መልዕክት ዝም ብሎ አይደለም። መንፈሳዊም አይደለም። የኢህአዴግ የምረጡኝ ቅስቀሳ ነዉ።በየግድግዳዉ፣ በየሜዳዉ፣ በየአጥራችን፣ አሉ የተባሉትን ሚዲያዎች ተጠቅሞ የቀረዉ መንፈሳዊ ብሎጎች ብቻ ነበሩ። ከነዚሀ ደግሞ ደስ ብሎት የሚያስተናግደዉ አባ ሰላማ ስለሆነ ቅሰቀሳዉን የወንጌልካባ አልብሶ ተስፋ በተባለ ቅጥረኛዉ ለጠፈልን። ተስፋ፣ንቢቱን የት አደረግሃት?ኢህአዴግ ምርጫ ሲያጭበረብር በሚነሳዉ ተቃዉሞ የሚገድለዉ ሰዉ ቁጥር እንዲያንስለት ነዉ እንጂ እንደመንግሥት መቀጠሉን ተጠራጥሮ አይደለም፣ ሕዝቡ ያንተን ጉዳይ ለእግዚአብሔር ሰጥቶ ዝም ብአልና አትርበትበት በለዉ። ተስፋ ሆይ አን ደገሞ እኛ ጣታችንን የምንጠባ ሰላልሆነ ሌላ ወሬ አምጣ።

  ReplyDelete
 15. ለዳሞትMay 18, 2015 at 8:17 AM
  ለተከበርከው ዳሞት መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋን ሰላም ይሁንልህ! መጀመሪያ ስይጣን አኗኗሩ ምን ይመስል ነበር????
  " 14፤ አንተ ልትጋርድ የተቀባህ ኪሩብ ነበርህ በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አኖርሁህ፤ በእሳት ድንጋዮች መካከል ተመላለስህ።" (ሕዝ. ም28)። ይላል። ነገር ግን ስይጣን ከእግዚአብሔር ፈቃድ በመውጣቱ ምክንያት፡ ምን ሆነ????
  " 15፤ ከተፈጠርህበት ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ ድረስ በመንገድህ ፍጹም ነበርህ።16፤ በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።" (ሕዝ. ም28)። ይላል። በዚህ የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ስይጣን ወደ መሬት ተጣለ። ስለዚህ አሁንም ይህ የተጣለው ስይጣን ዛሬም የሚያስበው ምንድን ነው???? የሚያስበውም ከሰማይ ስለተጣለ ነገር ግን ዛሬ ወደ ሰማይ ለማረግ ይፈልጋል። ለዚህም ነው እግዚአብሔር በቃሉ
  " 13፤ አንተን በልብህ። ወደ ሰምይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤" (ኢሳ. ም14)ብሎ የተናገረው። ስለዚህ ማረግ ማለት ከምድር ወደ ሰማይ መነጠቅ ማለት ነው። ስለዚህ ስይጣን ይህን ያሰበው መጀመሪያ በሰማይ ሥፍራው በነበረበት ነው? ወይስ አሁን ባለበት በተጣለበት ምድር ነው??? መልሱ ግልጽ ነው። በዚህም ይህንን ሰማይ ማረግን የሚመኝ ስይጣን ብቻ ነው። ወንድማችን የእግዚአብሔርን ቃል ባለመረዳታችን ምክንያት እራሳችንን ወንጌላዊ በማድረጋችን ብቻ እውቀት ስሌለለን አስቀድመን ስድብ ይቀድመናል። ጥብብ ያለው ሰው በጥብብ ያስተምራል እንጂ አንት ጴንጤ አንት ጆሆባ ራስን ጻድቅ አድርጎ እኔ ብቻ እግዚአብሔርን አውቅለሁ ማለት ትዕቢት ስለሆነ የእግዚአብሔርን መንግሥት አያወርስም። ነገር ግን ለተሳሳተ ሰው መጽህፉን በመጥቀስ ይህ ትክክል አይደለም ብሎ ማስተማር የእግዚአብሔር ሰው ፋንታ ነው። ምን አልባት ለጆሮህ አዲስ የሆነብህ ያልተገለጠልህ ነገር ስላለ ዝም ብለህ ሰውን አትዝለፍ። የእግዚአብሔር ቃል ነው ብትፈልግ ተቀበለው ብትፈልግ ተወው። እውቀትን ማስተውልና ጥበቡን እግዚአብሔር ይስጥህ!
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous May 19,2015 at 7:48 am
   ወንድም ወይም እህት፦ በመጀመሪያ እኔ ወንጌላዊ ወይም መምህር አይደለሁም እኔ ተራ ግለሰብ ነኝ። ትክክል አይደለም ብዬ የተናገርኩት ደግሞ እምነቴ ከምታስተምረው ያወቁሁትንና አንብቤ ያረጋገጥሁትን መሠረት በማድረግ ነው። ለማስተማር ሳይሆን ከጠቀሥካቸው(ሻቸው) የመጽሐፍ ቅዱስ የትንቢት ቃል በመነሳት የተናገርሃቸው(ሻቸው) ትክክል አይደለም ፤ ትክክለኛው ትርጉም ጥንተ ጥላት ዲያቢሎስ ወደምድር ተጥሏል፤ ስፍራውም ሲኦል ነው ፤ የዚህ አለም የክፋት ገዠም እሱ ሰይጣን ነው፤ በሰማይ ስፍራ የለውም ምክንያቱም የማይገባውን ተመኝቶ እንዳይነሳ ሆኖ ወድቋልና ነው። በምናባዊ እሳቤ አንተ(ች) ቦታየ በሰማይ ነው ብሎ ይላል ብለህ(ሽ) ብት ደመድም(ሚ) እንሿን ምናባዊው እሳቤ የጉም ሐሳብ የሰይጣን ፍላጎትም የእንቅልፍ ቅዠት ነው። እየተነጋገር ያለነው ዲያቢሎስ የተባለው አምላክነትን በመፈለግና ከሰማየ ሰማያት በላይ ሆኖ መታየትን በመመኘቱ ወደ ጥልቅ ከተጣለ በኋላ ስላለው መሆኑ መታወቅና ግልጽ መሆን ይገባዋል ። ሌላው ጥበብ ያለው በጥብ ያስምራል ካልሽ(ህ) በኋላ አንተ ቤንጤ አንተ ጆሆቫ ራስን ጻድቅ አድርጎ እኔ ብቻ እግዚአብሔርን አውቃለሁ ማለትትዕቢት ስለሆነ የእግዚአብሔርን መንግስት አያወርስም ትላለህ። በመጀመሪያ እኔ ጴንጤ አላልኩም። ቃሉ የተቆነፀለ ቢሆንም ጴንጤቆስጤ ማለት መንፈስ ቅዱስ የወረደበትበዓለ ዕለት ነውና ለናንተ አይመጥንም። የጆሆቫ አስተሳሰብ አራማጅ መናፍቅ ነህ ነው ያልኩት። ምክንያቱም በመጨረሻ "ወስብሃት ለእግዚአብሔር" የሚለው የአንዲቷ በክርስቶስ የተመሰረተችው ቤተክርስቲያን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቋንቋ እንጂ የሌላ የእምነት ድርጅትም ሆነ መናፍቅ ስላልሆነ ነው። እንዲህ እንዳንተ(ች) አይነት የእግዚአብሔርን ቃል ማጣመምና ሐሰተኛ አስተሳሰብ የመናፍቃን እንጂ ወስብሃት የሚለው ቋንቋ ባለቤት የሆነች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አይደለምና ያልኩትን ብያለሁኝ። ቋንቋውን ለምን አወቅህ ለምን ተናገርህ የሚል ተቃውሞ የለኝም። ነገር ግን ለሐሰተኛ አስተሳሰብህ መሸፈኛና ማታለያ መጠቀምህን ግን እቃወማለሁኝ። ከዛ ባሻገር ግን እኔ እራሴን ብቸኛ እግዚአብሔርን አዋቂ አላደረግሁም አላልኩምም። ስህተትን መቃወም ደግሞ በዚህ መልኩ ሰውን አያስፈርጅም። ከዛም በመቀጠል ለተሳሳተ ሰው መጽሐፍ በመጥቀስ ይህ ትክክል አይደለም ብሎ ማስተማር ነው ብለሻል(ሃል)። አሁንም ደግሜ ማረጋገጥ የምፈልገው አስተማሪ አለመሆኔንና ተራ ግለሰብ መሆኔን ነው። ትክክል ያልሆነን አስተሳሰብ ለመቃወምና ተሳስተሃል ለማለት የግድ አስተማሪ መሆን አይጠበቅም። አንተ(ች) ስህተትን መቀበል አልፈለጋችሁም እንጂ በራሳችሁ የተጠቀሰው ቃል በራሱ እውነቱን በግልፅ ይናገራችኋል። በመቀጠልም ለጀሮህ አዲስ የሆነብህ ያልተገለጠልህ ነገር ስላለ ዝም ብለህ ሰውን አትዝለፍ ትላላችሁ። በመጀመሪያ ሁሌም ለጀሮ አዲስ፤ ቢሰሙት፣ ቢናገሩት፣ ቢማሩት የማይጠገብ የማይሰለች የእግዚአብሔር ቃል ቅዱስ ወንጌል ነው። ከዛውጭ ግን ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም ተብሏልና ሌላ አዲስ ነገር አያስፈልግም። ወንጌል ከሚናገረው ሐዋርያት ከሰበኩት ክርስቶስ ውጭ ሌላ ክርስቶስንና እንግዳ ሐሰተኛ ወንጌልን አልሰማም። ለአንተ(ች) ሐዋርያት ከሰበኩት ውጭ የሆነ ልዩ ወንጌልና ክርስቶስን ከሆነ የምትፈልጉት ምርጫው የናንተው ነው። ውሃና እሳት ተምጧል ወደ ወደድኸው እጅህላክ ተብሏልና ነፃ ፈቃድ አላችሁ የፈለጋችሁትን ለማለትና ለመከተል። ሌላኛው ማደናገሪያ የእግዚአብሔር ቃል ነው ከተቀበልህ ተቀበል የሚል እንደ ገበያ እቃ በእግዚአብሔር ቃል የተዘበተው ዝበታ ነው። እዚህ ጋ ያለው ቃሉን የመቀበልና ያለመቀበል አይደለም። የቃሉን መልእክት በትክክል ተረድቶ አምኖ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው። እስቲ ወደሌላው ስህተትህ ልሒድ፦ በትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 28 ከቁጥር 13 እስከ 16 የተመዘገበው ቃል በመምዘዝ ለማንና ለምን እንደተነገረ ሳይገባህ እንዲህ ብለህ ትጠይቃለህ፦ የተጣለው ሰይጣን ዛሬ የሚያስበው ምንድን ነው የሚል። ሰይጣን ምንም ያስብ ይበል ፣ ምንም ይመኝ ያውራ ሰይጣን ምንም አይነት እድል ፈንታ በሰማይ የለውም። እድል ፈንታ ግዛቱ ሲኦል ብቻ ነው። ይህን ካልኩኝ በኋላ ገንጥለህ ያውጣኸው እግዚአብሔር ለነብዩ ሕዝቅኤል የነገረው የትንቢት ቃል የተነገረው በጢሮስ ስለነበረ ገዠ( ንጉስ) ነው። ሙሉውን ከፈለግህ ት•ሕዝ ምዕራፍ 28:ከ ቁጥር 1 እስከ19 ካልሆነም ከቁጥር 11 እስከ 19 ተመልሰህ(ሸ) አንብቢው(በው) ። አንተን ያልገባህ የተለፀበትን አገላለፅ ባለማወቅህ ነው ለተሳሳተ አስተሳሰብ የከተታችሁ። ወደ እውነተኞቹ አስተማሪዎች ጠጋብላችሁ ይህ የትንቢት ቃል ለማን ተፃፈ ፤ ለምን በእንዲህ አይነት አገላለፅ ተነገረ ብላችሁ ጠይቁ። ከዛም እውነቱን ተገኙታላችሁ። ትንቢትን እንደራስ ፍላጎት መተርጎም ሐጢያት ነው። እስቲ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፤ ወደ ሰማይ የወጣ፤ በሰማይ የሚኖር ማን ነው? በሰማይስ ስፍራ አዘጋጅላችኋለሁ የተባለውስ ለማን ነው? ሰመይም ተከፍቶ አያለሁ ያለውስ ማን ነው? ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልሆን አሻለሁ ያወስ ማን ነው?ክርስቶስ ያለውስ በሰማይ አይደለምን? በሰማይ የክብር አክሊል ተዘጋጂቶልኛል ያለውስ ማን ይሆን?ሐዋርያውቅዱስ ጳውሎስ አይደለምን? በሰማይ ከእግዚአብሔር ጋርለመሆን መፈለግና መንግስተ ሰመይን መሻት በክርስቶስ ላመኑ ለሰው ልጆች እንጂ የሰይጣን አይደለም። ሰይጣን ምንም አሰበ ተመኘም በሰማያት እድል ፈንታ እንዳይኖረው ሆኖ ወደ ሲኦል ተጥሏልና ነገሩ ሁሉ ከንቱ ነው። የቀደመው እባብ ተጥሏል ተብሏልና ነው። በንባብ ከመጥፋት እባክህ(ሸ) በመጀመሪያ ተማሩ። ማስመሰሉ አያድንም አምኖ መኖር ነው የሚያድነው። ደህና ሁን።

   Delete
 16. ይድረስ ለወንድሜ ዳሞት! እኔ አሁን ሰውን ለመንቀፍ ወይም ለመሳደብ ሳይሆን ይህንን የምጽፈው የእግዚአብሔርን ቃል በደንብ እንድረዳና እርስ በእርሳችን እንድንማማር ነው። በዚህም መሠረት የነቢዩ ሕዝቀኤልን መጽሀፍ በም. 28 ተመዝግቦ እንድሚገኘው ይህ ቃል የተነገረው ለጢሮስ ንጉሥ (በሥጋ በዙፋን ለተቀመጠው) ነው ያልከው ትክክል አለመሆኑን እንድትረዳልኝ ከዚህ ቀጥየ በመጽሀፉ የተመዘገበውን ቃሉን አስረዳለሁ። በዚህም መሠረት ፡"1፤ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። ብሎ ሕዝቀኤል በመጽሀፉ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲህ ሲል ይመስክራል። " 2፤ የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ልብህ ኰርቶአል አንተም። እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር መካከል ተቀምጫለሁ ብለሃል፤ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።" (ሕዝ. ም28) ይላል። በመቀጠልም ................... 9፤ በውኑ በገዳይህ ፊት። እኔ አምላክ ነኝ ትላለህን? ነገር ግን በገዳይህ እጅ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።(ሕዝ. ም28) ። በዚህ መሠረት በሥጋ ያለው የጢሮስ ንጉሥ እንደ እግዚአብሔር አምላክ ነኝ ብሎ ተናግሯል። ነገር ግን ይህንን የሚናገረው የዓለም ንጉሥ (የአሕዛብ መንግሥትን የሚመራ) የእግዚአብሔር መንግሥት እስኪመጣ ዓለምን የሚያስተዳድረው ስይጣን ነው። በመቀጠልም የበለጠ ምሥጢሩ እንዲገባን እግዚአብሔር እንደተናገረው፡
  "12፤ የሰው ልጅ ሆይ፥ በጢሮስ ንጉሥ ላይ ሙሾ አሞሽተህ እንዲህ በለው። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ጥበብን የተሞላህ ውበትህም የተፈጸመ መደምደሚያ አንተ ነህ።13፤ በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ፤ የከበረ ዕንቍስ ሁሉ፥ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ወርቅ፥ ልብስህ ነበረ፤ የከበሮህና የእንቢልታህ ሥራ በአንተ ዘንድ ነበረ፤ በተፈጠርህበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር።" (ሕዝ. ም28) ይላል። በዚህም መሠረት በሥጋ ያለው የጢሮስ ንጉሥ በእግዚአብሔር ገነት ነበር?????? አልነበረም። በእግዚአብሔር ገነት የነበሩት አዳምና ሔዋን በመልካም ዛፍ የተመሰለው ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስና በክፉና በመልካም ዛፍ የተመሰለው ስይጣን ብቻ ነብሩ። ነገር ግን በሥጋ ያለው የጢሮስ ንጉሥ በእግዚአብሔር ገነት በዔድን አልነበረም። ስለዚህ ይህ ሁሉ በሥጋ ለተቀመጠው ለጢሮስ ንጉሥ የተነገረ አይደለም። በመቀጠልም እንደተናገረው
  «የከበረ ዕንቍስ ሁሉ፥ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ወርቅ፥ ልብስህ ነበረ፤ የከበሮህና የእንቢልታህ ሥራ በአንተ ዘንድ ነበረ፤ በተፈጠርህበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር።"» ይህ ሁሉ ልብስ ከተለያዩ ድንጋይ የተሰሩ በሥጋ ያለው የጢሮስ ንጉሥ ለብሶታል???? አይደለም። ነገር ግን አሁንም በጢሮስ ንጉሥ ለተመሰለው ለስይጣን የተነገረ ቃል ነው። አሁንም በመቀጠልም፡ ለዚሁ ለጢሮስ ንጉሥ እግዚአብሔር እንደተናገረው፡ "14፤ አንተ ልትጋርድ የተቀባህ ኪሩብ ነበርህ በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አኖርሁህ፤ በእሳት ድንጋዮች መካከል ተመላለስህ።" (ሕዝ. ም28) ይላል። በዚህ ቃል መሠረት በሥጋ ያለው የጢሮስ ንጉሥ በእግዚአብሔር ተራራ (ሶስተኛው ሰማይ) ተቀብቶ ኪሩብ ነበረ?????? አይደለም። ነገር ግን ሳጥናኤል በደል ከማድረጉ በፊት የተቀባ ኪሩብ እርሱ ብቻ ነበር። አሁንም በመቀጠል እግዚአብሔር ለጢሮስ ንጉሥ እንደነገረው። " 15፤ ከተፈጠርህበት ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ ድረስ በመንገድህ ፍጹም ነበርህ።16፤ በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።" (ሕዝ. ም28) ይላል። ስለዚህ እንደ እርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ የተጣለው በሥጋ ያለው የጢሮስ ንጉሥ ነው????? መጀምሪያ በሥጋ ያለ ሰው በሰማይ መኖር አይችልም እንዲሁም በእግዚአብሔር ተራራ ኪሩብ ሆኖ አገለግሎ የሚያውቅ ሰው በሥጋ የለም። ስለዚህ ይህ ሁሉ ቃል የተነገረው ለስይጣን ነው። ይቀጥላል............

  ReplyDelete
 17. በመቀጠልም የበለጠ ነገሮችን ለመረዳት እንድንችል ። ቅዱስ ገብርኤል የተናገረውን ቃል ነቢዩ ዳንኤል በመጽሀፉ እንደመዘገበው እንዲህ ይላል። ይህንንም የተናገረው እግዚአብሔር የነቢዩ ዳንኤልን ጸሎት ስለሰማ ለጸሎቱም መልስ እንዲሆን ቃሉን በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት በሚልክበት ወቅት እንዲህ ሲል ተናግሯል።" 12፤ እርሱም እንዲህ አለኝ። ዳንኤል ሆይ፥ አትፍራ፤ ልብህ ያስተውል ዘንድ፥ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቃልህ ተሰምቶአል፤ እኔም ስለ ቃልህ መጥቻለሁ።13፤ የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት።" (ዳን. ም10)። ይላል። በዚህም ቃል መሠረት ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ዳነኤል መልእክቱን መጥቶ እንዳይነግረው 21 ቀን የተቋቋመው የፋርስ መንግሥት አለቃ ወይም እንደ ጢሮስ ንጉሥ የሆነ ማለት ነው። ስለዚህ ይህ በምሳሌ በንጉሦች የተመሰለው የፋርስ መንግሥት አለቃ በሥጋ ያለው በመንፈስ ያለውን ቅዱስ መልአክ 21 ቀን መቋቋም ይችላል???? በመጀመሪያ በሥጋ ያለ ሰው በመንፈስ ያለውን ቅዱስ መላዕክ ማየትና መዋጋት አይችልም። ነገር ግን በፋርስ መንግሥት አለቃ የተመሰለው ስይጣን ቅዱስ ገብርኤልን ተቁቁሞታል። ምክንያቱም ቅዱስ ገብርኤል ተዋጊ መላዕክ ስላልሆነ የግዴታ እርሱን የሚረዳው ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ መንገዱን ከፍቶለታል። በዚህም የመላዕክት ሥራቸው የተለያየ ስለሆነ ቅዱስ ሚከኤል ሁልጊዜ ተዋጊ አርበኛ መላዕክ ነው። በዚህም እግዚአብሔር አስቀድሞ የጢሮስ ንጉሥ ብሎ በምሳሌ ተናገረ እንጂ በሥጋ ላለው ንጉሥ አይደለም። ምክንያቱም የዓለም መንግሥት የምትገዛው በስይጣን መሆኑን ለመረዳት እንድትችል ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ የመሰከረውን ነግር እንዲህ ይላል።
  " 5 ዲያብሎስም ረጅም ወደ ሆነ ተራራ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው።6 ዲያብሎስም። ይህ ሥልጣን ሁሉ ክብራቸውም ለእኔ ተሰጥቶአል ለምወደውም ለማንም እሰጠዋለሁና ለአንተ እሰጥሃለሁ፤7 ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናል አለው።8 ኢየሱስም መልሶ። ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው።" (ሉቃ. ም4)። ይላል። በዚህም ቃል መሠረት የዓለም ክብር የጢሮስ ንጉሥ ክብር የፋርስ አለቃ ክብር ሁሉ በስተጀርባ ሆኖ የሚመራቸው ይህ ጌታችንን መድሀኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የተፈታተነው በኋላም በእግዚአብሔር ቃል ድል የተነሳው ሳጥናኤል ነው። እንዲሁም አስቀድሞ በሕዝቀኤል ላይ አድሮ እግዚአብሔር አንተ የጢሮስ ንጉሥ « አንተ ልትጋርድ የተቀባህ ኪሩብ ነበርህ በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አኖርሁህ፤ በእሳት ድንጋዮች መካከል ተመላለስህ» ነገር ግን በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።" ያለው ኪሩብ የነበረው ሳጥናኤል ነው።
  በመጨረሻም ከዚህ የምንረዳው ሁላችንም እግዚአብሔር አስቀድሞ በዳዊት መዝሙር ላይ እንደተናገረው። "1 ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድምጡ፤ ጆሮአችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ።2 አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ፥ ያለውንም ተምሳሊት እናገራለሁ።" ባለው መሠረት ነግሮችን በምሳሌ ይናገራል። በዚህም መሠረ የጢሮስ ንጉሥ የፋርስ መንግሥት አለቃ እያለ ስይጣንን ይነግረዋል። በዚህም ነግሮችን እንረዳለን። ይህንንም ላስተማረን ለመክረን ለእግዚአብሔር ምሥጋና ይገባዋል። አሜን!
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር!
  ReplyDelete
  Replies
  1. ለanonymous 21,2015 at 9:56am
   የማያምኑ ስለሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታል፤ ለዚህም ደግሞ የተመደቡ ናቸው። 1ኛ ጴጥ 2÷ 8
   አሁን አን ልበልህ። መቸም ማንበብ እንጅ የምታነበው ምን እንደሚያስተላልፍ አታውቀው። እኔ አንተን ስገመግምህ ከተፃፈው ውጭ የሆነ የምታወራ ድልድይን ሐውልት የምትል ግለሰብ ነህ። ለአንተ የእግዚአብሔርን ቃል ጠቅሶ መናገር በድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው። እንዲሁም ማፌዝም ይሆናል። ከፃፍካቸው ሐሰተኛና ፍፁ ውሸቶችህ ስለ አንድ ሶስቱን ክህደቶችህ ልናገር። አንደኛ፦ አንተ ሳጥናኤል ሰው እንደሆነ ትናገራለህ። ሳጥናኤል ግን መናፍስት የሆነ እርኩስ መንፈስ ሰዎችን የሚያስትና ክፉ የሚያሰራ ነው። ሳጥናኤል የተቀባ ኪሩብም ነው ትላለህ። ይገርማል ማረጋገጫህ ምን እንደሆነ በራሱ ለማወቅ ያጓጓል። ለመሆኑ የተቀባህ ኪሩብ ነህ ማለት ምን ማለት ነው? እኔ መልስ አልሰጥህም። ነገር ግን መምህራንን ጠይቀህ እንድትረዳ እጋብዝሃለሁ። ሳጥናኤል ከእግዚአብሔር መላእክት አንዱ የነበረ በእግዚአብሔር እጅ የተፈጠረ በኋላም አምላክነትን ሽቶና በማይገባው ቦታ መሆንን በመፈለጉ ከነ ግብራበሮቹ የተጣለ ነው። ሳጥናኤል ሱቅ ከፍቶ የሚነግድ ነጋዴም አይደለም። እሱ አሳሳች ተግባሩም የክርስቶስን ህዝብ ማሳሳትና በሐጢያት አስሮ መግደል ነው። ለመሆኑ ይነግድ የነበረው ምን ነበር? ብቻ ብዙ ምንፍቅና ቃሉ ሳይገባህ ለማስረፅ ተግተሃል። እውነታው ግን ሳጥናኤል ሰው ሳይሆን ክፉ መንፈስ የተፈጠረና የተቀባምኪሩብም ሆነ ነጋዴ አይደለም። 2ኛ፦ ተራራውን ሶስተኛ ሰማይ ነው አልክ። ከየት አመጣኸው?ለምን ሁለተኛ አምስተኛ ወይም ሰባተኛ አላደረግኸውም? የምታሳዝን ለጥፋት የታዘዝህ የምታስተውልበት አይን የሌለህ ግለሰብ ነህ። ከዛም በመቀጠል ክርስቶስን ወደ ተራራ ወሰደው ከተማም አሳየው … ትልና ተራራ የሚል ስላገኘህ ብቻ ነገሮችን ለማመሳሰል ዳክረሃል። ማስተዋል ይስጥህ ከማለት ውጭ ምን የሺ የባላል። 3ኛ፦ ገብርኤል ለዳንኤለ መልእክት ነገረው የሚል የሌለ ታሪክ በመፍጠር ታወራለህ። ይህ ብቻም አይደለም ዳንኤልን የፋርስ ንጉስ ለ21 ቀናት ተቋቋመኝ ያለውን ቅዱስ ገብርኤልን ተቋቋመው የሚል ክህደትን ተናግረሃል። አንተ እንዲህ ወርደህና ታውረህ ለዛውም የሌለና ያልተፃፈን ብታወራም የእግዚአብሔርን መላእክት ሰይጣን አይቋቋማቸውም። መጽሐፍ ላይ ዳንኤልን ሊረዳው የመጣው ሚካኤል መሆኑ በግልጽ ነው የተቀመጠው። አንተ ታዲያ ገብርኤልን ለዛውም አቅም አሳጥበህ የተናገርኸውን ንግግር ከየት አመጣኸው። በመጨረሻም "ላስተማረን ለመከረን እግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል"በማለት እጅግ በዘባች ስላቅህ ተናግረሐል። እግዚአብሔር እንዲህ አይነት የእውርና የአልተፃፈ ማንበብ ትምህርት አላስተማረም። ስለምሳሌ የተናገርኸውም አንተ በሔድክበት መንገድ የፍርስን ንጉስ የሳጥናኤል የማድረግ አይነት ግን ፍፁም ትክክል አይደለም። የምታነበውን አታውቀውምና ከመካድ ተማር።

   Delete