Tuesday, May 19, 2015

መንግሥት አሸባሪነትን ለመዋጋት ከራሱ ሹመኞች ይጀምርአሸባሪነት ዓለም አቀፍ ሥጋት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ ትኩረት ባይሰጠውም ስጋቱ በአገራችን መኖሩ መታየት ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በጅማ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ አንዱ ምልክት ነበር፡፡ ለጥቃቱ ሽፋን ሰጪና ተባባሪ የነበሩት የአካባቢው የመንግስት ሹመኞች መሆናቸው ደግሞ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎት ነበር፡፡ በወቅቱ ዘግይቶ ጥቃቱ ከደረሰና በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ከተከሠተ በኋላ ቢሆንም መንግሥት እርምጃ በመውሰዱ በአካባቢው የተሻለ ሰላም ሰፍኖ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ እዚህም እዚያም በእስልምና እምነት ውስጥ የተሸሸጉ አክራሪዎች በሚበዙበትና ሹመኞችም ሙስሊሞች በሆኑባቸው እንደ ስልጤ ዞን ባሉት የአገራችን ክፍሎች በተለይ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ላይ እየደረሰ ያለው ተጽዕኖና እየተፈጸመ ያለው ጥቃት የሽብር ዋዜማ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ 

ከፍተኛ የሆነ ሃይማኖታዊ ተጽእኖ እየደረሰባቸው የሚገኙ የስልጤ ዞን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች የድረሱልን ጥሪ አሰምተዋል፡፡ በአገራቸው ውስጥ እየኖሩና አይ ኤስ በቅርቡ ወገኖቻችንን ማረዱና መግደሉ በተሰማበት ማግሥትና የሐዘኑ ቁስል ሳይሽር እንዲህ ያለው የድረሱልን ጥሪ መሰማቱ የት እንዳለን በግልጽ የሚያሳይና ፈጽሞ ሊናቅና ትኩረት ሊነፈገው የማይገባ ጉዳይ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ጉዳይ በቶሎ እልባት ካልተሰጠው ውሎ አድሮ መዘዙ ቀላል አይሆንም፡፡ ስለዚህ መንግሥት በአካባቢው ሹሞች ላይ ተገቢውን እርምጃ ሊወስድ ይገባል፡፡ የሽብር ጥቃት እየፈጸሙ ያሉትንም ጽንፈኞች ይዞ ለፍርድ ማቅረብ አለበት፡፡ በዘላቂነትም በስልጤና በአንዳንድ ተመሳሳይ ምልክቶች እየታዩባቸው በሚገኙ የአገራችን ክፍሎች ተገቢው ትኩረት ሊሰጣቸውና የሽብርተኝነትን አደጋ በእንጭጩ መቅጨት ያስፈልጋል፡፡

ቤተክህነትም የአክራሪ እስልምናን እንቅስቃሴ የሚያጠናና የችግሩን ጥልቀት ለመንግስትና ለህብረተሰቡ የሚያሳውቅ አንድ መምሪያ ልታቋቁም ይገባታል። ለጸሎትም ቢሆን መረጃ አስፈላጊ ነገር ነው። ክርስቲያኖች ባሉበት አካባቢ ሁሉ ከለላ ያስፈልጋቸዋል። ማንም እየተነሳ እንደፈለገ የሚጫወትባቸው አሻንጉሊቶች አይደሉም። በተለይም ለአክራሪ ኃይል የሚታጠፍ ግንባር ሊኖረን አይገባም። ድምጻችንን በአንድነት ልናሰማ ያስፈልገናል።
ሽብርተኝነትን ለመዋጋት መንግስት ያለውን ቁርጠኝነት እናውቃለን። ነገር ግን በውስጡ የተሰገሰጉ አክራሪ ኃይሎችን ሥርዓት ለማስያዝ ቸልተኝነት ያበዛል። የትም አይደርሱም የሚል አጉል ትምክህትም አለበት። በእንጭጩ ሊቀጭ የሚገባው እንጂ ቸል ሊባል የሚገባው አክራሪ ኃይል መኖር የለበትም። አክራሪን በጊዜ ሥርዓት ማስያዝ ያቃታቸው እንደ እነ ናይጄሪያ ያሉ ሀገራት እየከፈሉ ያሉትን ዋጋ እያየን ነው። ቦካ ሀራም የተወለደው የናይጄሪያ መንግስት እሹሩሩ ይለው የነበረው የሰሜን ናይጄሪያ አክራሪ የመንግስት ባለሥልጣናት እንቅስቃሴ ውስጥ መሆኑ ግልጽ ነው። የመንግስት ሹመኛ ሀይማኖትና ዘር ሳይለይ ህብረተሰቡን ማገልገል ይገባዋል። ለአክራሪ የሃይማኖት ወገኖቹ ከለላ እየሰጠ ተጠቂውን ኃይል መልሶ የሚያጠቃ ከሆነ አንድ ሊባል ይገባል።  ለመፍትሔው መንግሥት መጀመር ያለበት ከራሱ ነው፡፡ በመዋቅሩ ውስጥ የተሰገሰጉትንና ችግሩ በተፈጠረባቸው አካባቢዎች የሚገኙና ጽንፈኝነትንና ሽብርተኝነትን በጉያቸው ታቅፈው እየተንከባከቡና እያሳደጉ የሚገኙትን ሹመኞቹን ሊፈትሽ በጉዳዩ እጃቸውን ያስገቡትንና ለጽንፈኞች በልዩ ልዩ መንገድ ሽፋንና ትብብር እያደረጉ ያሉትን ደግሞ ተገቢውን እርምጃ ሊወስድባቸው ይገባል፡፡ ለኦርቶዶክሳውያን ዜጎችም ተገቢውን ጥበቃ የማድረግና መብታቸውን በተለይም የማምለክ ነጻነታቸውን ማረጋገጥና ዋስትና መስጠት አለበት፡፡

3 comments:

 1. this is actually what Redwan hussen and Muktar are doing....and was previousely done by Ali Abdo...
  was seen in Ziquala with the Erecha staff.....

  ReplyDelete
 2. አባ ሰላማዎች ጥሩ ነው። በርቱ ብለናል

  ReplyDelete
 3. ምን እሱ ብቻ በደቡብ ወሎ ዞን በአርጎባ ወረዳ ከ 150 በላይ የሚሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች የአምልኮ ቦታ እንዳይኖራቸው ተከልክለው የሰሚ ያለህ እየተባለ ከዓመት በላይ ሆነው አይደለም ወይ?እንደውም እኮ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ የአምልኮ ሕንጻ ለመሥራት ፈቃድ ከመንግሥት ታውጣ እያሉ ማሾፍ ጀምረዋል።እንዲህ ነው እንግዲህይሏችኋል።እየተባሉ ሲጠሩ የነበሩት መጠጊያ ካገኙ በኋላ መጠጊያ የሰጣቸውን ክፍል አሁን ለዚህ ምላሽ የሰጡት እንዲህ በማለት ነው።ይሉታልም ይሄ ነውና! ኧረ የመንግሥት ያለህ! ይህች ጥሬ ካደረች አትቆረጠምም!!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete