Tuesday, May 26, 2015

ስብከተ ወንጌልና ተግዳሮቶቹ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

በምድር ላይ ላለችው ተዋጊዋ ቤተክርሰቲያን ስብከተ ወንጌል ዋና ተልእኮዋ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን የምትሰብከው ወንጌልን ነው፡፡ ወንጌልን የምትሰብከውም ሰዎች በሃይማኖት ውስጥ ሲኖሩ በታሪክ የሚያውቁትን ነገር ግን በሕይወታቸው የራሳቸው ያላደረጉትን የክርስቶስን አዳኝነት ገንዘብ እንዲያደርጉትና በበጎ ምግባር ጸንተው መዳናቸውን እየፈጸሙ እንዲኖሩና የዘላለማዊ ሕይወት ባለቤቶች እንዲሆኑ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን እንደ ቤተክርስቲያን መቀጠል የምትችለውም ወንጌል ሲሰበክባትና ሰዎች በክርስቶስ አዳኝነት አምነው የዘለላለም ሕይወት ባለቤቶች ሲሆኑ ነው፡፡
ስብከተ ወንጌል ዋና ስለመሆኑ ከፓትርያርኩ አንስቶ ብዙዎች ይናገራሉ፤ ይጽፋሉ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ከዜና ቤተ ክርስቲያን መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ አንዱ የተነሣው የስብከተ ወንጌል ጉዳይ ነው፡፡
ዜና ቤተክርስቲያን “ከቤተክርስቲያናችን ቁልፍ ሥራዎች አንዱ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁንና አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴው የሚፈለገውን ያህል አይደለም፡፡ ይህን የቤተክርስቲያንዋ ቀዳሚ  ሥራ የሆነውን ተልእኮ ለማጠናከር ቤተ ክርስታየኒቱ ምን ማድረግ አለባት?” ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ ፓትርያርኩ ሲመልሱ እንዲህ ብለዋል፡፡
ቅዱስ ፓትርያርክ፡-“እንደኔ እምነት ቤተክርስቲያን ትልቁን በጀት መመደብ ያለባት ለስብከተ ወንጌል ሥራ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን ቤተ ክርስቲያናችን ከሁሉ አኀት አብያተ ክርስቲያናት የበለጠ ተከታይ ምእመን አሏት፡፡ በቅድሚያ ያሉንን ምእመናን በእምነታቸው፣ በዕውቀታቸው እንዲጠነክሩ ማስተማር ያስፈልጋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ያላመኑትን ለማስተማር፣ ወጣቱን ትውልድ  በሚገባ ለመያዝ የተጠናከረ የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ወደ ተግባር ለመለወጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ትልቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ በአጠቃላይ መምሪያው በሠለጠነ የሰው ኃይልና በበጀት ሊጠናከር ይገበዋል፡፡”(ዜና ቤተክርስቲያን መጽሔት ሚያዝያ 2005 ገጽ 9)፡፡

እንዲህ ቢባልም ስብከተ ወንጌል አሁንም ድረስ የዋናነቱን ያህል ትኩረት አልተሰጠው፡፡ በቂ በጀት አልተመደበለትም፣ መከሩ ብዙ የመሆኑን ያህል በቂ ሰራተኞችም አልተሰማሩበትም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚደረጉ ስብሰባዎች ስብከተ ወንጌል ዋና የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ብዙ አያውቅም፡፡ከዚህ አንጻር ብዙዎች እናት ቤተክርስቲያንን እየተዉ ወደሌሎች የእምነት ተቋማት እየፈለሱ ይገኛሉ፡፡ ጥናት የሚጠይቅ ቢሆንም ቤተክርስቲያናችን ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚደርሱ አማኞቿ ከቁጥር የጎደሉት በዋናነት ወንጌል ባለመሰበኩ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኗ በስብከተ ወንጌል በኩል ደካማ ብትሆንም አንዳንዶች በራሳቸው ጥረት ተነሳስተው ለስብከተ ወንጌል ሲፋጠኑ፣ አንዳንዶችም ብዙዎችን ማስከተል ሲችሉ ተመልክተናል፡፡ በዚህ ጊዜ ወንጌል የማይሰብኩ ወግ ጠራቂዎችና ተረት ተራቾች ስማቸውን ሲያጠፉና እነርሱን ከሚከተላቸው ሕዝብ ለመነጠል ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲከፍቱባቸውና በጀት መድበው ሲንቀሳቀሱባቸውም ታዝበናል፡፡
ሲኖዶሱም በአንድ በኩል እየተመራ ያለው ከጀርባው ባለው የማቅ ረጅም እጅ በመሆኑ ከስብከተ ወንጌል ይልቅ ለፀረ ስብከተ ወንጌል ጉዳዮች ነው ትኩረት የሚሰጠው፡፡ ዙሪያችንን በፀረ ክርስትና ኃይሎች ተከብን ሳለ በዚያ ላይ ከመነጋገርና ስብከተ ወንጌልን ከማጠናከር ይልቅ ወንጌል የሚሰብኩ ሰዎች እንዴት እንደሚወገዙና እየሰጡ ያለው አገልግሎት እንዴት እንደሚጨናገፍ ነው የሚያስበው፡፡ ስብከተ ወንጌልን ስለማጠናከር ኮሚቴ ከሚሰይም ይልቅ በማኅበረ ቅዱሳን “ተሐድሶ” እየተባሉ የተፈረጁትን የቤተክርስቲያን ልጆች ስለማውገዝና ስለማባረር የሚያጠና ኮሚቴ ቢሰይም ነው የሚቀለው፡፡
ወንጌል ስለተሰቀለው ስለሞተውና ስለተነሣው ስለ አዳኙ ኢየሱስ የሚነገርበት የምስራች ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ያረጋግጣል “ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።” (ሮሜ 1፥3-4)፡፡
እንዲሁም “ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤ በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ። እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥(1ቆሮ. 15፥1-4)፡፡
በ1957 ዓ.ም በአዲስ አበባ አፍሪካ አዳራሽ የተካሄደው የአምስቱ ኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ከወሰናቸው ውሳኔዎች መካከል አንዱ ሐዋርያዊ አገልግሎትን የተመለከተ ነው፡፡ በውስጡም “የሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ዓላማ ክርስቶስን ጉልሕ አድርጎ ማሳየት ነው” የሚል ሐሣብ ይገኛል፡፡ ወንጌል ይኸው ነው፡፡ ከዚህ ውጪ በወንጌል እንሰብካለን ስም የሚሰበክ ነገር ሁሉ ወንጌል ሊሆን ሊባልም እንደማይችል ሊቀ ሥልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህ እንዲህ ሲሉ ያስረዳሉ የእግዚአብሔር ቅዱስ ዐላማ ሰው ሁሉ እንዲድን፣ ሰው ሁሉ የመንግሥቱ ወራሽ እንዲሆን የታለመ ነው፡፡ ለዚህም ሁሉ መምህር ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ መጣ የስብከቱ ጠባይ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥራ የሚከተል፣ ራሱን ኢየሱስ ክርስቶስን ማእከል አድርጎ የሚሄድ ይሆናል፡፡ ስለ ሰው ደኅንነት ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ሞቷል፡፡ እንግዲያውስ የስብከቱ ይዘት የስብከቱም ጠባይ የተሰቀለውን ኢየሱስን የሚመለከት መሆን አለበት፡፡ ሰባኪው በፈቀደው ርእስ ሊናገር ይችላል፤ ሆኖም ዋናው ዓላማ የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት ለመናገር መሆን አለበት፡፡
ምንም የስብከት ምንጩ ቅዱስ መጽሐፍ ቢሆንም ጥቅሱም ከእርሱው ቢወጣም ሐተታውና አገላለጡ ስለ አዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆን አለበት፡፡ ኢየሱስን ማእከል ያላደረገ፣ የእርሱንም አዳኝነት የማይገልጥ ስብከት ሊሆን ሊባልም አይችልም፡፡” (የስብከት ዘዴ ገጽ 64፡67)፡፡
ይሁን እንጂ ይህን መርሕ የማያውቁና የማይከተሉ፣ ቢያውቁም ስደትን በመፍራትና ለጥቅም በማደር የማይተገብሩት ብዙዎች ናቸው፣ በወንጌል እንሰብካለን ስም አውደ ምህረት ላይ ቆመው ወንጌልን ሳይሆን ሌሎች ነገሮችን ነው የሚሰብኩት፡፡ ይህ መርሕ የገባቸውና ለጌታቸው ለኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ የሆኑት አገልጋዮች ግን እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፥ስለዚህ ምክንያት ምሕረት እንደ ተሰጠን መጠን ይህ አገልግሎት ስላለን አንታክትም። ነገር ግን የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናልና በተንኮል አንመላለስም የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናመሰግናለን። ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው።ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ። ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።”(2ቆሮ. 4፥1-5)እያሉ ወንጌልን በመስበክ ጸንተዋል፡፡

በዚህ ዘመን ከስብከተ ወንጌል ጋር በተያያዘ በርካታ ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡ ከላይ እንደጠቃቀሰንው አንዱና ዋናው ችግር ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት ትኩረት መነፈጉ ነው፡፡ ይህም በብዙ መልክ የሚታይ ሲሆን፣ ከላይም ለመግለጽ እንደተሞከረው የስብከተ ወንጌል መምሪያው ስለስብከተ ወንጌል አብዝቶ የሚያስብና እርሱ ላይ ሰፊና ጠንካራ ስራ የሚሠራ አለመሆኑ ነው፡፡ በየደብሩና በየገዳሙ በርካታ የማህሌትና የቤተመቅደስ አገልጋዮች አሉ፣ በቂ ሰባክያነ ወንጌል ግን የሉም፡፡ ለሌላው አገልግሎት ሰፊ ጊዜ ሲኖር ለስብከተ ወንጌል የሚሰጠው ጊዜ ግን እጅግ አናሳ ነው፡፡ በቅርቡ የወጣ ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ላይ እንደ ተጠቆመው ለስብከተ ወንጌል የሚሰጠው ጊዜ 20 ደቂቃ ለአሰልቺ ልመና የሚሰጠው ደግሞ ብዙ ሰዓት ነው፡፡ የደብር አስተዳዳሪዎች ትኩረት ከሕዝቡ በሚገኘው የልመና ገንዘብ ላይ እንጂ ለሕዝቡ ወንጌል ስለመሰበኩ አይደለም፡፡
ሌላው ችግር ሰባክያን ያልሆኑ ሰዎችን በሰባኬ ወንጌልነት መመደብ ነው፡፡ አንዳንድ መሪጌቶችና ሌሎችም በመሪጌትነት ከማገልገል ይልቅ በስብከተ ወንጌል ተመድበው መሥራት ነው የሚፈልጉት፡፡ የሚፈልጉትም ስብከተ ወንጌል ቁጭ ብለው የሚበሉበት የሥራ መደብ ስለሆነ ነው፡፡ እንደዚያም ሆኖ ብዙዎች ሙያቸውን እንኳ ለማሻሻል አይሞክሩም፡፡ በዚህ ረገድ አለሙያቸውና አለ ጸጋቸው በስብከተ ወንጌል ላይ የተመደቡ ሰዎች ወንጌልን ሳይሆን በወንጌል ስም ሌሎች ጉዳዮችን ነው የሚሰብኩት፡፡ ለስብከተ ወንጌል የሚሰበሰበው በአብዛኛው አልፎ ሂያጅ ስለሆነ በቤተክርስቲያን አውደ ምሕረት ላይ ወንጌል ሊሰበክ ሲገባው በሰንበት ት/ቤትና በሌሎችም መድረኮች ሊሰጡ የሚገባቸው ትምህርቶች ወንጌልን ተክተው የሚሰጡበት ሁኔታ አለ፡፡ ወንጌልን በሕዝብ ቋንቋ በቀላሉና ሰው ሊረዳው በሚችል መንገድ ከማስተማር ይልቅ ዐውደ ምሕረት በአንድምታ መንገድ በቃል ያጠኑትንና የሸመደዱትን ትምህርት እንዳለ ምእመናኑ ላይ አራግፈው የሚወርዱ የመጻሕፍት መምህራንም አሉ፡፡ ይህ ለአንድምታ ተማሪዎች እንጂ ለምእመናን ምን ይጠቅማቸዋል? ባይሆን በአንድምታ ውስጥ የወንጌል እውነት ካለ እርሱን ለሰው በሚገባው መንገድ ማቅረቡ ነው የተሻለ የሚሆነው፡፡ 

በስብከተ ወንጌል ላይ የሚስተዋለው ሌላው ችግር ወንጌል የሚሰብኩትን በልዩ ልዩ መንገድ የማሸማቀቅ ሥራ መሥራት ነው፡፡ አንዳንድ ቦታ ላይ በዚህ ርእስ አስተምር ብሎ ወንጌል ያልሆነን ነገር አውደ ምሕረት ላይ እንዲያስተምር ግድ የሚሉ አስተዳዳሪዎች እና የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች አሉ፡፡ ይህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተግባራዊ እየሆነ የመጣ የማሸማቀቂያ ስልት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የነበረው ልምድ “በከመ አለበወከ መንፈስ ቅዱስ፣ መንፈስ ቅዱስ እንዳሳሰበህ” አስተምር የሚል ነበር፡፡ አሁን ግን የመንፈስ ቅዱስን  ስፍራ ሰዎች እየወሰዱ ሰባክያንን እንምራ ይላሉ፡፡ ይህም ማኅበረ ቅዱሳንን ለማስደሰት ወይም በመፍራት የሚደረግ ነው፡፡ እውነቱን እንነጋገር ካልን ምእመናኑ በሚገባ ያልተማሩት ስለማነው? ስለአዳኙ ኢየሱስ ክርሰቶስ ነው ወይስ ስለሌሎች? መሰበክ ያለበትስ ክርስቶስ አይደለምን? ታዲያ ሊሰበክ የሚገባው ወንጌሉ እያለ ስለታቦት አስተምር፣ ስለጠበል አስተምር፣ ስለአማላጅነት አስተምር ወዘተ መባሉ ለምን አስፈለገ? በዚህ መንገድስ በየጊዜው እየሄደ ያለውን ሕዝብ ማቆም ይቻላል ወይ? አይቻልም፡፡ ስለዚህ መፍትሄው የተሰቀለውን ክርስቶስን መስበክ ብቻ ነው፡፡

ስለእገሌ አስተምር ወይም ከክርስቶስ ውጪ በዚህ ላይ ስበክ፣ አስተምር ሲባሉ መንፈስ ቅዱስ እንደመራኝ ነው የማስተምረው ብለው ወንጌል በሚሰብኩት ላይ ልዩ ልዩ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸው፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ለሰው ሐሳብ ታዛዥ ለሆኑት ከሚከፈላቸው በታች ውሎአበል ተቀናንሶ እንደሚሰጣቸው፣ ተሐድሶ መናፍቅ የሚል ታፔላ እንደሚለጠፍባቸው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት ችግሮች በተጨማሪ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የዌዘር (weather) ሰባክያን ጉዳይ ነው፡፡ እንደእነዚህ ላሉት “ሰባክያን” ዌዘር የሚል ስም የወጣላቸው ልክ እንደ አየር ንብረት ሁኔታውን እያዩ ስለሚለዋወጡ ነው፡፡ እነዚህ ሰባክያንና ዘማርያን ከሚያከናውኗቸውና ከሚታወቁባቸው ነገሮች መካከል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፤
·        የማቅ ክልል ነው ተብሎ በሚታወቅ ደብር በስብከታቸውም ሆነ በመዝሙራቸው በስፋት የሚሰብኩትና የሚዘምሩት ስለማርያምና ስለ ቅዱሳን ነው፡፡
·        ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ ሀገር ርእስ ተሰጥቷቸውይሄዳሉ፡፡
·        ተከፍሏቸው ስለማርያም ይሰብካሉ ይዘምራሉ፡፡
·        አዲስ አበባ ላይ በስብከተ ወንጌል ከእነርሱ የተሻለውን አገልጋይ ለማሳጣት ሕዝቡ አእምሮ ላይ አረም የሆነ ትምህርት ይዘራሉ፡፡
·        ስለክርስቶስ ዘምሮ የወረደ በሌላ ቀን ተልኮ  ስለ ቅዱሳን ይዘምራል፡፡ ወዘተ
እንዲህ እንደ አየር ንብረት የሚለዋወጥ ስብከትና ዝማሬ ቤተክርስቲያኗን የት ያደርሳታል፡፡ አንዳንዶቹ ዌዘር ሰባክያን ቢዝነስ ተኮር ጉባኤዎችን ያዘጋጃሉ፡፡ ለገበያ የሚቀርብና ወቅታዊ የሆነ ርእሰ ጉዳይ ፈልገው ብቅ ይላሉ፡፡ ለዚህ ዘበነ፣ ምህረተ አብ፣ ዘመድኩን ተጠቃሾች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ገበያ ተኮር ርእስ ሲገኝ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሱት፡፡ ካልሆነ ግን የት እንዳሉ እስከማይታወቅ ድረስ በዝምታ ይዋጣሉ፡፡ ለምሳሌ ዘመድኩን በስም አጥፊነት ታስሮ ከተፈታ በኋላ ድምፁ ተሰምቶም አያውቅም ነበር፡፡ ባለፈው ሰሞን ግን ተመልካች ባያገኝም እዩኝ ለማለት ዳድቶት ነበር፡፡ ስብከተ ወንጌል ማለት ለገበያ የሚቀርብ ሸቀጥ ነው እንዴ? 

ስለዚህ ሁኔታውን እያያችሁ ወንጌልን የምትሸቃቅጡ ሰባክያን ሆይ ለሰው ሳይሆን ወንጌል ሰባኪነትን በአደራ ለሰጣችሁ ጌታ የታመናችሁ ሁኑ፡፡ ስብከተ ወንጌልን አትነግዱበት፡፡ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል ብሎ የደነገገው ጌታ እናንተን አይጥላችሁም፡፡ ብቻ ታማኝ ሆናችሁ ስለተሰቀለው ክርስቶስ ለኀጢአተኞች ሰዎች የምስራቹን ስበኩላቸው፡፡ ወቅት እያያችሁና ለገበያ የሚሆን ርእስ እየፈለጋችሁ ሳይሆን በጊዜውም አለጊዜውም ቃሉን ስበክ የሚለውን ሐዋርያዊ መመሪያ ተከትላችሁ ዘወትር ለስብከተ ወንጌል የተፋጠናችሁ ሁኑ፡፡

ቤተ ክርስቲያንም ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት ከፍተኛ ትኩረት ልትሰጥ ይገባታል፡፡ አባላቷን ከፍልሰት ማዳን የምትችለው በሃይማኖታቸው ጸንተው እንዲኖሩ ማድረግም የምትችለው ንጹህ ወንጌልን ስትሰብክ ነው፡፡ ስለ ተሐድሶ የሚያጠና ኮሚቴ ከምትሰይም ይልቅ ስብከተ ወንጌልን ስለማጠናከር የሚያጠና ኮሚቴ ብትሰይም የተሻለ ነው የሚሆነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለስብከተ ወንጌል የሠጠችው ትኩረት እጅግ አናሳ ነው፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ ምእመናንና አገልጋዮቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እየኖሩ ባሉበት ሁኔታ ስብከተ ወንጌልን አለማጠናከር ውጤቱን የከፋ ነው የሚያደርገው፡፡ ስለዚህ ከምንም በላይ ጊዜውን ልትዋጅና ለስብከተ ወንጌል ትኩረት ልትሰጥ ይገባል፡፡

12 comments:

 1. Atlanta fake priest who have been violated church and USA laws several times that called himself as Melakselam Mr. Efrem kebede exchange illegal drug with his criminal business partner Daniel balcha. Daniel balcha and Mr . Efrem arrested five times.

  ReplyDelete
  Replies
  1. how you guys with out evidence same body doummege a person name and put your blog.?
   he said Atlanta fake priest arrest fife times
   do you have a enough evidence.
   we need this person name and His e mail and also address.
   he try it to dameg our church

   Delete
 2. tinish kolo yizeh keasharo tetega malet yih newu.beortodoks sim proteatantism mognhin felig

  ReplyDelete
 3. ya, but in the name of wengel, we do not need 'wenjel'. this 'wenjel' is an attempt by tehadiso to replace the orthodox doctrine with non-biblical protestant NUFAKE.. we need only the TRUE ORTHODOX WENGEL. DO NOT DECEIVE US YOU WOLF.

  ReplyDelete
 4. የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! እንደሚታወቀው የወንጌል ዋና ዓላማዋ ሁላችንም በእምነት ሆነን በጥምቀት ወደ እግዚአብሔር የቀርብን ልጆቹ ሁሉ የእርሱን የእግዚአብሔርን መንግሥት እንድንወርስ የምትመክረን የምትገጽሰን የምትዘልፈን እውቀት ጥበብና ማስተዋልን ሰጥታ የሞተውን የሥጋ መንፈሳችንን በማስወገድ ሕይወትን እንድናገኝ የምትሰበክ የምትወራ የምትበላ የምትሰማ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ይህም የእግዚአብሔር ቃል በወንጌል የተመዘገበው ኢየሱስ ክርስቶስን ተመግበበን የሞተውን ሰውነታችን ሕይወት እንድናገኝ ይረዳናል። ለዚህም ነው ቅዱስ ዩሐንስ በወንጊሉ ቃል የሆነው እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ፡ "4 በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።5 ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።" (ዩሐ. ም1)፡ ይላል። በዚህም የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሀፍ ውስጥ የተመዘገበው ቃል እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በዚህም በቃሉ ብርሃን የሆነውን ህይወት የሚሰተውን ለንፍሳችን ምግብ እናገኛለን። እንዲሁም ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ እንደመከረው፡" 14 አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤15 ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።" (2ኛ ጢሞ. ም3)። ብሎ መክሮታል። በተመሳሳይ መልኩ አሁንም ሁላችንም ትኩረት ማድረግ የሚገባን የእኛን ሁሉ ልብ ለማቅናት የምንችልበትን በጽድቅ ሥር የሚመራንን በጥበብ ሆነን እግዚአብሔርን እንድንፈራ የሚያስተምረንን እንዲሁም በማስተዋል ሆነን ከኃጢያት የምንርቅበትን እውቀት የሚሰጠንን ቃል የሚሰጠን ወንጌል ስንመገበው ብቻ ነው። ለዚህም ደግሞ ሃላፊነቱ የተሰጣቸው እረኞች ስለሆኑ ይህንን ሁሉ ማስተዋል ይገባቸዋል። ነገር ግን ሁላችንም በስንፍና እውቀትን ከጠላን ሕይወት የሚሰጠውን ክርስቶስን ማግኘት ችግር ይሆንብናል። .......ይቀጥላል።

  ReplyDelete
 5. በመቀጠልም አባቶቻችን በወንጌል እንደሚመስክሩት። " 1 ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤2 ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤3 እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።" (1ኛ ዩሐ. ም1)። ይላል። በመቀጠልም እንዲሁ ቅዱስ ዩሐንስ በምስክርነቱ ውስጥ እንደሚያስተምረን ፡" 9 የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።10 በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።11 እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።" (1ኛ ዩሐ. ም5)። ይላል። ስለዚህ ልጁ ያለው ሕይወት አለው ስላለ ወንጌልም ሁላችንም የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ማደሪያዎች እንድንሆን ሕይወት የሆነውን ክርስቶስን ቃልን ትመግበናለች። እርሱም ሕይወታችን ናው። ምክንያቱም በዩሐንስ ወንጌል ተመዝግቦ እንደሚገኘው፡"63 ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።" (ዩሐ. ም6)። ይላል። ስለዚህ የግዴታ ሕይወትና መንፈስ የሆነውን ቃል የምናገኘው ከወንጊል እስከሆነ ድርስ ለምን ዝም ብለን ተረት ተረት እንወራለን????? አንድ ክርስትያን የወንጌል እውቀት ከሌለው የሚያመልከውን አምላኩን ማወቅ ያስቸግረዋል። ምክንያቱም ቃሉ በርሱ የልምና። በዚህም እንዲሁ ደግሞ የክርስቶስ ወንገን የሚያደርገውን መንፈስም ከርሱ ጋር ባለመኖሩ ብቻ የደረቁ አጥንቶቹን ይዞ ይመላለሳል። በዚህም ከዚህ ከወንጌል ድርቅ ለመውጣት ቤተ ክርስትያናችን ቅድሚያ መስጠት የሚገባት ወንጌልን ማስትማር ነው። ምናልባት አንድንዶች ወንጌል ይሰበካል ብለው ይናገሩ ይሆናል ነገር ግን ብዙዎች የእግዚአብሔርን ቃል በመራባቸው ምክንያት የተበተኑ የእግዚአብሔር በጎች ብዙ ናቸው። በዚህ ምክንያት በጉድጓድ ገብተው ተስብረው የወደቁና የሞቱም ብዙ ናቸው። ስለዚህ ሕይወት የሚሰጠውን ቅዱስ መጽሀፉን ተክትሎ ማስተማር ግዴታ ነው። በዚህም ቅዱስ ሰለሞን በመጽሐፉ እንድሚመክረን ወንጌል ማለት ጥበብ ማለት ነው። ጥበብ ማለት ደግሞ ሕይወት የሚሰጠው ቃል ከድንግል ማርያም ሥጋዋን በመንሳት እኛን በደሙ የዋጀን ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። በዚህም እርሱን በልቦናችን ወይም ቃሉን በልቦናችን ካለ ደግሞ ሁላችንም ሕይወት እንገኘለን። በዚህም እንድሚመክረን " 1 ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ብትቀበል፥ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፥2 ጆሮህ ጥበብን እንዲያደምጥ ታደርጋለህ፥ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ።3 ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት፥ ለማስተዋልም ድምፅህን ብታነሣ፥4 እርስዋንም እንደ ብር ብትፈላልጋት፥ እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት፤5 የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ።6 እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤7 እርሱ ለቅኖች ደኅንነትን ያከማቻል፤ ያለ ነውር ለሚሄዱትም ጋሻ ነው፤8 የፍርድን ጎዳና ይጠብቃል፤ የቅዱሳኑንም መንገድ ያጸናል።9 የዚያን ጊዜ ጽድቅንና ፍርድን ቅንነትንና መልካም መንገድን ሁሉ ታስተውላለህ።10 ጥበብ ወደ ልብህ ትገባለችና፥ እውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለችና፤11 ጥንቃቄ ይጠብቅሃል፥ ማስተዋልም ይጋርድሃል፥" (ምሳ. ም2)። ይላል።
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር!

  ReplyDelete
 6. የዚህ አለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ። 2ኛ ቆሮ 4÷4-5
  ከመጀመሪያ አስተያየቴ በመቀጠል የመናፍቃኑንና የዚህን ብሎግ በእውነት ላይ ያላቸውን ተግዳሮት የግሌን እናገራለሁ።
  ለመሆኑ ወንጌል ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ጨለምተኛ የአሉባልታ ወግ ጠራቂ ሐሰተኛ ጽሑፍ " ወንጌል ስለበሰቀለው ስለሞተውና ስለተነሳው ስለአዳኙ ኢየሱስ የሚነገርበት ነው " ይላል። ሆኖም ግን አስመሳይነትን የተላበሰ ነገር ግን የተሳሳታ ጎዶሎ አስተሳሰብ ነው። ወንጌል ምንም እንሿን የምስራች የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ቢሆንም ኢየሱስ ኢየሱስ፣ ሞቷል ተነስቷል የሚል ብቻ ነው ማለት ግን የዚህ አለም አምላክ አሳባቸውን ያሳወረባቸው የመናፍቃኑ የበከንቱ ተመፃዳቂዎችና አስመሳዮች አስተሳሰብ ነው። ወንጌል ግን የእግዚአብሔር ቃል ነው። ወንጌል እግዚአብሔር እንድናውቅና እንድናምን የሚናገር ነው። ወንጌል በእግዚአብሔር አምነንና በሱ ታምነን እንድንኖር የሚናገር ነው። ወንጌል ስለ እግዚአብሔር ህግና ስርዓት የሚናገር ነው። ወንጌል ስለክርስቶስ እራሳቸውን ጃንደረባ ስላደረጉ የሚናገር ነው። ወንጌል ስለክርስቶስ መወለድ፣ በምድር ላይ መመላለስ፣ ህሙማንን መፈወሱ፣ ስለማስተማሩ፣ ታምራት ስለማድረጉ፣ በአይሁድስለተፈፀመበት፣ ስለ መከራ መስቀሉ፣ስለሞቱና ትንሳኤው፣ ሰለ እርገቱ፣ ስለዳግም ምፃቱ፣ ለእኛ ምሳሌ ይነን ዘንድ ስለፈፀማቸውና ወዘተ የሚናገር ነው። ወንጌለ ስለታቦት፣ ስለቅዱሳን፣ ስለ መላእክት፣ ስለ ድንግል ማርያም፣ ስለ ስግደት፣ ስለ ፃም፣ ስለ ጠበል፣ ስለ ቤተመቅደስ ስርዓት፣ ስለ አማላጂነት፣ ቅዱሳኑ በእግዚአብሔር ፀጋ ስለ አደረጉት ታምራት፣ ቅዱሳን እንደሚፈርዱ፣ ወዘተ ይናገራል። ታዲያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ በእግዚአብሔር ስለሆነ እምነቷ ስታስተምር የሚቃወሙት ለምንድን ነው? ታዲያ ይህ ሐሰተኛ ወግ ጠራቂ አሉባልተኛ ፀሐፊ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስያን ስለ ታቦት፣ ስለ ቅዱሳን፣ ስለ ጠበል፣ ስለ መላእክት፣ ስለድንግል ማርያም፣ ስለ በአላት፣ ስለ ሐይማኖት፣ ወዘተ ስታስተምርና ስትመሰክር ለምን ይቃወማሉ? መልሱ አንድና አንድ ነው። ይኸውም ክርስቶስንም ወንጌሉንም ስለማያውቁት ነው። ወንጌል የክርስቶስ የህይወት ቃል ነው። ቃሉ ደግሞ መዳን ስለሚገኝበት ስብዙ የእምነት ፍሬወችና ተገባሮች የሚናገር እንጂ ኢየሱስ ሞተ ተሰቀለ ተነሳ ብሉ የሚናገር ብቻ አይደለም።
  ወደ ሌላኛው እንክርዳድ የሆነ የተሳሳተ አስተሳሰብ አራሙቻ ወሬ ጥረቃው ልመለስ። እንዲህ ይላል "ቤተክርስቲያን እንደ ቤተክርስቲያን መቀጠል የምትችለው ወንጌል ሲሰበክባትና ሰዎች በክርስቶስ አዳኝነት አምነው የዘላለም ህይወት ባለቤቶች ሲሆኑ ነው" ይላል። ይህ ፀሐፊ ምድራዊ እንጅ ሰማያዊ የሆነ ምንም አይነት እይታ የሌለው የክርስቶስ ብርሃን የሌለው ነው። ቤተክርስቲያን ወንጌልን( የእግዚአብሔርን ቃል) ታስተምራለች እምነቷን ትፈፅማለች። እምነቷንና ትምህርቷን ሰምቶ ተምሮ መኖርና አለመኖር የሰሚው እንጅ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአፍ የአርቶዶክስ ተዋህዶ ችግር አይደለም። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክርስቶስ የሰጣት ንፁህ የሆነ እምነትና ወንጌል አላት። ያን እምነቷንና ወንጌል ታስተምራለች። ከዛ ውጭ ክርስቶስ ያልተከለውና ያልጠራው አይበቅል አይመጣምና ይህን ያክል ምዕመናን ጠፍተዋል እየተባለ የሚቧለተው ቧልትና ምክንያቱም የወንጌል ችግር ነው የሚባለው ወሬ ጥረቃ የእግዚአብሔርን ጥሪ ያለማወቅና የጠላት ክስ ነው። ይሁዳና የእጁን ታምራት ያዩ እንጀራውን የበሉ ክርስቶስን ትተው ወጥተዋልና የክርስቶስ ችግር ነው ማለት ፍፁም ድንቁርና ምንፍቅና ነው። አስር ምዕመናን ጠፍተዋል የሚባለውም ጠላት የእምነት ችግር ቢያስመስለውም እውነታው ግን አገር ቤት ባለው ዘረኛ መንግስት ምክንያት ቤተክርስቲያኗን ከላይ እስከታች በሚባል ሁኔታ በመያዝና በውስጧ በሚካሄደው ከእምነት ውጭ የሆነ እንቅስቃሴ አዝነው ቤታቸው የተቀመጡና የሸሹ ናቸው ባይ ነኝ። ወደ ሌላ እምነት ሄደው ከሆነም ክርስቶስ የሰጣቸው ነፃ ፈቃዳቸው ስለሆነ ቤተክርስቲያን አርነት ወጥተው ዳግም ክርስቶስን ክደው የክህደት ባሪያ በመሆናቸው ብታዝንም ምርጫቸውን አትከለክልም።
  ሌላው ክፉው የከሰሰበት ክስ ዌይዘር(weather) የሚል ቋንቋን በመጠቀም ነው። በመጀመሪያ ፀሐፊ ተብየው ወሮበላ ከመሆኑ የተነሳ እንዲህ አይነት ተራ ቃልን ተጠቅሟል። ሆኖም ግን የተጠቀመበት ቃልን እኔ ጊዜውን በመዋጀት የሚከናወን የሚቀርብ የእምነት እንቅስቃሴን አመላካች ማለት ነው ብየ ለስድብ ያደረገውን ወቅታዊ ስለሆነ አገልግሎት የሚያመለክት አድርጌዋለሁ። እንደ መናፍቃኑ የጊዜው እንቅስቃሴያቸው የተዋህዶ አገልጋዮችም ወቅቱ የዋጀ አገልግሎትን ትምህርትን ይሰጣሉና ከጊዜው ጋር መሔዳቸው ከክርስቶስ የተማሩ እውነተኞች መሆናቸውን ነው የሚያሳየው።
  ሌላኛው ሰይጣን የሚቃወመው የወንጌል አንድምታን ነው። ይህን የሚቃወምበት ምክንያቱ የክርስቶስን ቃል በማጣመም የሚዘራውን እንክርዳድ በትርጓሜው ስለ ሚነቅልበትና ስለሚያደርቅበት ነው። አንድምታ ማለት የወንጌ( የክርስቶስ ቃል) ትርጉም ማለት ነው። ፊደል ይገላል ትርጉም ግን ያድናልና ነው።
  ሌላኛው የጠላት ሙከራ ወንጌል( የእግዚአብሔር ቃል) በሰንበት ትምህርት ቤት ለምን ይሰጣል በአውደምህረት ብቻ ነው የሚል ክፉ ውጊያን ለማድረግ ሞክሯል። ወንጌልን የትና እንዴት እንደምታስተምር ቤተክርስቲያን ታውቃለች። ጠላት ለሰንበት ትምህርት ቤት የእግዚአብሔር ቃል መሰጠቱ ያስጨነሸው አንዳንድ የተዘናጉ ባገኝ ብሎ መቅረብ ባመቻሉና በእግዚአብሔር ቃል እራስ እራሱን ቀጥቅጠው ስለሚያባርሩት ነው።
  ሌላኛው መርጌታ ለምን ያስተምራል ይላል። አንተም አለህ ጨለምተኛው ሐሰተኛ የክርስቶስ ያልሆነ ትምህርት ለማሰራጨት የምትዳክረው። አንተ አዳራሽ አልመጡ ምን አንቦቀቦቀህ።
  በአጠቃላይ ይህ የማያምን አሳቡ የታወረበት ፀሐፊና ፅሑፍ የሰይጣን የሐሳዊው መሲህ ደቀ መዝሙር እና መርዝ እንጂ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አይደለም።
  ዛሬም ነገም እንክርዳድ አራሙቻ ዘሪዎች፤ የክርስቶስ ወንጌል አጣማሚዎች፤ ወሬ ጠራቂ ቧልት ቦላቾች መናፍቃን ተሐድሶ ነን ባዮች ሁሉ ከቤተክርስቲያን አፀድ ይነቀላሉ። ልዩ ትምህርትና እምነት አለኝ የሚል ሁሉ ያመነውን መከተል መተግበር የሚችለው በራሱ ግዛት እንጂ በክርስቶስ ቤተክርስቲያን አይደለምና መናፍቃንና ተሐድሶዎች ይባራሉ። ክርስቶስ ቤቱን ያፀዳል።

  ReplyDelete
 7. Tenektobishal Tehadiso protestant...

  ReplyDelete
 8. Anteneh from mk informed to law enforcement mr. EFREM used his fake church using as stock storage of his illegal substance. The deacon actively serving his fake church was arrested in connection with drug and other criminal count. That was in shame for all Eotc in Atlanta. To find concreEvidence go to Dekalb county jail Web then look at Daniel Balcha and Efrem kebede a rested same time.

  ReplyDelete
 9. የዚህ አለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ 2ኛ ቆሮ 4÷4-5
  ዛሬ የክርስቶስ ጠላቶች፤ የቤተክርስቲያን ተገዳዳሪዎች፤ የጽድቅ ነቃፊዎች ነጋ ጠባ በክፍትና በውሸት ተግተውና ሰክረው እንደበታቸውን እያላቁና እግራቸውን ደም ለማፍሰስ እያንቀሳቀሱ ያሉት እየገዛቸውና እያመለኩት ያለው የዚህ አለም አምላክ የተባለው ዲያቢሎስ አሳባቸውን ስላሰወረው። እነዚህ ወንጌል ማለት ምን ማለት እነደሆነ ያልገባቸው ነገር ግን ወንጌል አንድ ወይም ሁለት ጥቅስ ነው ብለው የዚህ አለም አምላክ በሚያስደልቃቸው ነጋሪት በፊደል ብቻ ወንጌል ወነንጌል እያሉ በከንቱ የሚጎስሙ እንዲቷን እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ለማፍረስ መርዝን በየእለቱ ይረጫሉ። እነዚህ ሐሰተኞች መዳን መጽደቅ ማለት ኢየሱስ ኢየሱስ ማለት ብቻ የሚመስላቸው በአምላካችን ስም የሚያላግጡ በአምላክነቱና በአዳኝነቱ የሚዘባበቱ እጂግ ለጥፋትና የእውነትን መንገድ አይሳካላቸውም እንጂ ለመዝጋትና በእንክርዳድ ለመተካት የአሸዋ ላይ ቤት ለማድረግ ይራወጣሉ።
  ይህ በውሸት ትረካ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እውነት ጥላሸት ለመቀባት ታስቦ በዚህ እንክርዳድና የአሉባልታ ወግ በሚጠረቅበት ብሎግ አዘጋጅነት ወይም ደግሞ ስሙ የማይታወቀው ክርስቶስም የማያውቀው እሱም ክርስቶስንም ወንጌልንም የማያውቅ ሁሌም እንዳባቱ ተደብቆ የፅድቅን አንገት መቅያ ሰይፍን የሚመዝ ግለሰብ የተደረተ እውነትን የመቃወምና ወንጌል ማለት ምን እንደሆነ የማያውቅ ፅሑፍ ተብዬ የሚያሳየው የዚህ አለም አምላክ ሐሳባቸውን ያሳወረባቸው መሆኑን ነው። የማያምኑትን አሳብ አሳወረ ማለት እውነቱን እንዳይረዱት፤ ፅድቅን እንዳያውቁት በማይረባ ተመፃዳቂና መናፍቅነት አስተሳሰብ ሰጣቸው ማለት ነው። ይህን ያልኩበት ምክንያት ይህ የተረት ተረት ወግ ጠራቂ ፅሑፍ ተብዬ የወንጌል ትርጉም ያልገባውና ወንጌል ማለት በቃላት መዋጋት ኢየሱስ ኢየሱስ ብቻ ብሎ ማንቧረቅ ወይም አንድ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የሚመስላቸው ኢየሱስ ግን የማያውቃቸው መናፍቅ ናቸው። በተጨማሪም እራሳቸውን በቃላት በመዋጋት የሚኮፈሱ ስለማይኖሩበትና ባላላገኙት ወንጌል በማስመሰል የሚመፃደቁ ማየት የተሳናቸው አባታቸው ዲያቢሎስ አሳባቸውን የአሳወረባቸው ናቸው።
  በዚህ ጨለማ ጽሑፍ ተብየ የተዘረዘሩት አረፍተ ነገሮችና ቃላቶች እንሿን ማስተዋል በሌለው አስተሳሰብ የተከተበ ነው። ለምሳሌ "በሐይማኖት ውስጥ ሲኖሩ በታሪክ የሚያውቁትን ነገር ግን በህይወታቸው ለራሳቸው ያላደረጉትን የክርስቶስን አዳኝነት ገንዘብ እንዲያደርጉትና በበጎ ምግባር ፀንተው መዳናቸውን እየፈፀሙ እንዲኖሩና የዘላለም ህይወት ባለቤት እንዲሆኑ ነው" የሚል የቃላት ድንግርግሮሽና የአረፍተነገር አራሙቻ ይታያል። በዚህ የአረፍተነገር ላይ ይህአባ ሰላማ ተብዬ ብሎግ ወይም የተደበቀው ፀሐፊ እራሳቸውን ፍፁም አዋቂና ፃድቅ በማድረግ ሌላውን በታሪክ የሚያውቁት እያለ ይከሳል፤ ይፈርዳል። በተጨማሪም የተለያዩ ቃላቶችን በመደራረት በውሸት እራሱን ፃድቅ በማድረግ ሌላውን ደግሞ ይኮንናል። ፀሐፊው አይነ ልቦናው በመታወሩ ትርጉማቸውን ባለማወቁ የክርቶስን አዳኝነት ገንዘብ እንዲያደርጉ፣ በበጎ ምግባር እንዲፀኑ፣ መዳናቸውን እየፈፀሙ እንዲኖሩ እና የዘላለም ህይወት ባለቤት እንዲሆኑ እያለ እውነትን መቃወምና ምንፍቅናን ያራምዳል። ለመሆኑ በሐይማኖት ውስጥ ሲኖሩ በታሪክ ያወቁትን እያለ በታወረው አሳቡ የሚናገረውና የሚከሰው ታሪክ ማለት ምንድን ነው? በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ታሪክ ቦታ አለው። እውነተኛ ታሪክ አለ፤እውሸተኛ ታሪክም አለ። በሐይማኖት የሚገለጽ ታሪክ እውነተኛ ታሪክ ለህይወትና ለምግባር የሚሆን ታሪክ ነው። ደግሞስ ሰው በሐይማኖት ውስጥ እንዲሆንና የተማሩትን አውቁ መኖርና ህይወትን ማግኘት አይደለምን የሚጠበቅባቸው። ታዲያ በሐይማኖት መኖራቸውና የእምነታቸውን ታሪክ ማወቃቸው ለምን ጠላትን አንጨረጨረው? የክርስቶስ አዳኝነት፣ በጎ ምግባርና የዘላለም ህይወት ያለው እኮ በሐይማኖት ውስጥ ሲሆኑ እና የእምናታቸውን ታሪክ ሲያውቁ ነው። ለምን ጠላት አዳኝነት፣ ምግባር እንዲሁም የዘላለም ህይወት በሚል ሽፋን አረም የሆነውን እንክርዳዳቸውን እውነተኛ ለማስመሰል ደረቅ ቃላቶችን መረጠ? ለኔ መልሱ ሐሰተኛ የሐሰት አስተማሪ መሆኑ እንዳይገለጥበት ነው። ለመሆኑ የክርስቶስ አዳኝነት ሲባል ምን ማለት ነው? እንዴትስ ነው የተከናወነው የሚከናወነው? ክርስቶስ በነፍስም በስጋም አዳኝ ነው። አዳኝነቱም በተለያ መንገድ ይከናወናል። ከነዚህም አንዱ ማዳኑን በቅዱሳኑ በኩል ያደርጋል። ነገር ግን ይህን አዳኝነት ለማግኘት ማመንና በእምነት አዎ በቅዱሳኑም በኩል ያድናል ብሎ መቀበል ይገባል። ለምሳሌ በሐዋርያው በቅዱስ ጴጥሮስ እጂ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከስጋ ሞትና በሽታ ማዳንን አድርጓል። ምግባርም በእምነት የሚከናወን ነው። የዘላለም ህይወት ለማግኘት ደግሞ እግዚአብሔር አምላክ ነው ብሎ በማመንና የእግዚአብሔርን ቃል በመፈፀምና ትእዛዙን በመፈፀም ምግባር በማድረግ የሚከናወን የሚገኝ ነው። እምነትን በሥራ እየተገበሩ ሲኖሩት ነው የዘላለም ህይወት የሚገኘው::

  ReplyDelete
 10. Ahun ante lemenfeskidus azneh newu?Kazenk lemin ante lebicha atakebrim medan begara ale inde? begil newu.

  ReplyDelete
 11. የዚህ አለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ 2ኛ ቆሮ 4÷4-5
  ዛሬ የክርስቶስ ጠላቶች፤ የቤተክርስቲያን ተገዳዳሪዎች፤ የጽድቅ ነቃፊዎች ነጋ ጠባ በክፍትና በውሸት ተግተውና ሰክረው እንደበታቸውን እያላቁና እግራቸውን ደም ለማፍሰስ እያንቀሳቀሱ ያሉት እየገዛቸውና እያመለኩት ያለው የዚህ አለም አምላክ የተባለው ዲያቢሎስ አሳባቸውን ስላሰወረው። እነዚህ ወንጌል ማለት ምን ማለት እነደሆነ ያልገባቸው ነገር ግን ወንጌል አንድ ወይም ሁለት ጥቅስ ነው ብለው የዚህ አለም አምላክ በሚያስደልቃቸው ነጋሪት በፊደል ብቻ ወንጌል ወነንጌል እያሉ በከንቱ የሚጎስሙ እንዲቷን እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ለማፍረስ መርዝን በየእለቱ ይረጫሉ። እነዚህ ሐሰተኞች መዳን መጽደቅ ማለት ኢየሱስ ኢየሱስ ማለት ብቻ የሚመስላቸው በአምላካችን ስም የሚያላግጡ በአምላክነቱና በአዳኝነቱ የሚዘባበቱ እጂግ ለጥፋትና የእውነትን መንገድ አይሳካላቸውም እንጂ ለመዝጋትና በእንክርዳድ ለመተካት የአሸዋ ላይ ቤት ለማድረግ ይራወጣሉ።
  ይህ በውሸት ትረካ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እውነት ጥላሸት ለመቀባት ታስቦ በዚህ እንክርዳድና የአሉባልታ ወግ በሚጠረቅበት ብሎግ አዘጋጅነት ወይም ደግሞ ስሙ የማይታወቀው ክርስቶስም የማያውቀው እሱም ክርስቶስንም ወንጌልንም የማያውቅ ሁሌም እንዳባቱ ተደብቆ የፅድቅን አንገት መቅያ ሰይፍን የሚመዝ ግለሰብ የተደረተ እውነትን የመቃወምና ወንጌል ማለት ምን እንደሆነ የማያውቅ ፅሑፍ ተብዬ የሚያሳየው የዚህ አለም አምላክ ሐሳባቸውን ያሳወረባቸው መሆኑን ነው። የማያምኑትን አሳብ አሳወረ ማለት እውነቱን እንዳይረዱት፤ ፅድቅን እንዳያውቁት በማይረባ ተመፃዳቂና መናፍቅነት አስተሳሰብ ሰጣቸው ማለት ነው። ይህን ያልኩበት ምክንያት ይህ የተረት ተረት ወግ ጠራቂ ፅሑፍ ተብዬ የወንጌል ትርጉም ያልገባውና ወንጌል ማለት በቃላት መዋጋት ኢየሱስ ኢየሱስ ብቻ ብሎ ማንቧረቅ ወይም አንድ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የሚመስላቸው ኢየሱስ ግን የማያውቃቸው መናፍቅ ናቸው። በተጨማሪም እራሳቸውን በቃላት በመዋጋት የሚኮፈሱ ስለማይኖሩበትና ባላላገኙት ወንጌል በማስመሰል የሚመፃደቁ ማየት የተሳናቸው አባታቸው ዲያቢሎስ አሳባቸውን የአሳወረባቸው ናቸው።
  በዚህ ጨለማ ጽሑፍ ተብየ የተዘረዘሩት አረፍተ ነገሮችና ቃላቶች እንሿን ማስተዋል በሌለው አስተሳሰብ የተከተበ ነው። ለምሳሌ "በሐይማኖት ውስጥ ሲኖሩ በታሪክ የሚያውቁትን ነገር ግን በህይወታቸው ለራሳቸው ያላደረጉትን የክርስቶስን አዳኝነት ገንዘብ እንዲያደርጉትና በበጎ ምግባር ፀንተው መዳናቸውን እየፈፀሙ እንዲኖሩና የዘላለም ህይወት ባለቤት እንዲሆኑ ነው" የሚል የቃላት ድንግርግሮሽና የአረፍተነገር አራሙቻ ይታያል። በዚህ የአረፍተነገር ላይ ይህአባ ሰላማ ተብዬ ብሎግ ወይም የተደበቀው ፀሐፊ እራሳቸውን ፍፁም አዋቂና ፃድቅ በማድረግ ሌላውን በታሪክ የሚያውቁት እያለ ይከሳል፤ ይፈርዳል። በተጨማሪም የተለያዩ ቃላቶችን በመደራረት በውሸት እራሱን ፃድቅ በማድረግ ሌላውን ደግሞ ይኮንናል። ፀሐፊው አይነ ልቦናው በመታወሩ ትርጉማቸውን ባለማወቁ የክርቶስን አዳኝነት ገንዘብ እንዲያደርጉ፣ በበጎ ምግባር እንዲፀኑ፣ መዳናቸውን እየፈፀሙ እንዲኖሩ እና የዘላለም ህይወት ባለቤት እንዲሆኑ እያለ እውነትን መቃወምና ምንፍቅናን ያራምዳል። ለመሆኑ በሐይማኖት ውስጥ ሲኖሩ በታሪክ ያወቁትን እያለ በታወረው አሳቡ የሚናገረውና የሚከሰው ታሪክ ማለት ምንድን ነው? በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ታሪክ ቦታ አለው። እውነተኛ ታሪክ አለ፤እውሸተኛ ታሪክም አለ። በሐይማኖት የሚገለጽ ታሪክ እውነተኛ ታሪክ ለህይወትና ለምግባር የሚሆን ታሪክ ነው። ደግሞስ ሰው በሐይማኖት ውስጥ እንዲሆንና የተማሩትን አውቁ መኖርና ህይወትን ማግኘት አይደለምን የሚጠበቅባቸው። ታዲያ በሐይማኖት መኖራቸውና የእምነታቸውን ታሪክ ማወቃቸው ለምን ጠላትን አንጨረጨረው? የክርስቶስ አዳኝነት፣ በጎ ምግባርና የዘላለም ህይወት ያለው እኮ በሐይማኖት ውስጥ ሲሆኑ እና የእምናታቸውን ታሪክ ሲያውቁ ነው። ለምን ጠላት አዳኝነት፣ ምግባር እንዲሁም የዘላለም ህይወት በሚል ሽፋን አረም የሆነውን እንክርዳዳቸውን እውነተኛ ለማስመሰል ደረቅ ቃላቶችን መረጠ? ለኔ መልሱ ሐሰተኛ የሐሰት አስተማሪ መሆኑ እንዳይገለጥበት ነው። ለመሆኑ የክርስቶስ አዳኝነት ሲባል ምን ማለት ነው? እንዴትስ ነው የተከናወነው የሚከናወነው? ክርስቶስ በነፍስም በስጋም አዳኝ ነው። አዳኝነቱም በተለያ መንገድ ይከናወናል። ከነዚህም አንዱ ማዳኑን በቅዱሳኑ በኩል ያደርጋል። ነገር ግን ይህን አዳኝነት ለማግኘት ማመንና በእምነት አዎ በቅዱሳኑም በኩል ያድናል ብሎ መቀበል ይገባል። ለምሳሌ በሐዋርያው በቅዱስ ጴጥሮስ እጂ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከስጋ ሞትና በሽታ ማዳንን አድርጓል። ምግባርም በእምነት የሚከናወን ነው። የዘላለም ህይወት ለማግኘት ደግሞ እግዚአብሔር አምላክ ነው ብሎ በማመንና የእግዚአብሔርን ቃል በመፈፀምና ትእዛዙን በመፈፀም ምግባር በማድረግ የሚከናወን የሚገኝ ነው። እምነትን በሥራ እየተገበሩ ሲኖሩት ነው የዘላለም ህይወት የሚገኘው

  ReplyDelete